YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.84K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የክልል ልዩ ሃይል ፈርሶ በሃገር መከላከያ ሰራዊት እንዲጠቃለል ተጠየቀ፡፡

ይህ የተባለው ጽናት ለኢትዮጵያ፣የኢትዮጲያ አሜሪካዊያን ዜጎች ምክክር፣የዘር ፖለቲካ በህግ ይታገድ ዘንድ ግፊት የማድረግ ንቅናቄ እና የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትወርክ የተሰኙ የሰብዓዊ ድርጅቶች በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ ትንታኔ የሰጡት የዲላ ዩንቨርሲቲ መምህር መስከረም አበራ በሃገራችን እየተካረረ የመጣው አክራሪ ብሄርተኝነት በመገናኛ ብዙሃንና በክልል ልዩ ሃይሎች እየተደገፈ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
እነዚህ ልዩ ሃይሎች በብዛትና በታጠቋቸው መሳሪያዎች ማእከላዊ መንግስቱን እስከመገዳደር መድረሳቸውን የሚናገሩት ተንታኟ፤ አደረጃጀታቸው ህጋዊ ባለመሆኑ ለሚያደርሱት ጥፋት ተጠያቂ የሚሆኑበት የህግ አግባብ የለም ብለዋል፡፡

ከዚህም ባለፈ ወገንተኝነታቸው ላሰለጠናቸውና ላስታጠቃቸው ክልል ብቻ በመሆኑ በክልሉ ውስጥ ለሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች ከለላ ከመስጠት ይልቅ ራሳቸው በዳይ ሆነው የሚገኙበት ጊዜ በርካታ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ልዩ ሃይሎች በወታደራዊ ስነ ምግባር ያልታነጹ መሆናቸውንም መምህር መስከረም ጠቁመዋል፡፡
በተለይም ቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ ውጤት ላይ የልዩ ሃይሎች መኖር አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚፈጥርና ሃገሪቷን ወደ እልቂት እንዳይወስዳት ስጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

የአስተዳድርና አመራር ባለሙያው ዶክተር ኤርሲዶ ሌንዴቦ በበኩላቸው ህዝባችን በዚህ ሰዓት ከምንም በላይ የሚያስፈልገው ሰላም፣የተረጋገጠ የምግብ ዋስትና፣ጤና እና መሰረተ ልማት እንጂ እርስ በእርሱ የሚፎካከርበት ታጣቂ አይደለም ብለዋል፡፡

በመሆኑም የክልል መንግስታት ለልዩ ሃይሎቻቸው የሚያባክኑትን በጀት ለዜጎቻቸው መሰረታዊ ፍላጎቶች ቢያውሉት መልካም ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

የቀድሞ ወታደራዊ መኮንኖችም እኛ የምናውቀው ልዩ ሃይል ወይም ፈጥኖ ደራሽ ማለት ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ ሆነው ለባህር ሃይልና አውሮፕላን እንዳይጠለፍ እንዲሁም አንዳንድ ብሄራዊ ስጋት ለሆኑ አደጋዎች ፈጥነው የሚደርሱ እንጂ ለክልሎች የሚታዘዙ በርካታ ታጣቂዎችን ማሰለፍ ማለት አይደለም ሲሉ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
እናም መንግስት ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ልዩ ሃይሎችን አፍርሶ በሃገር መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እንዲያጠቃልል በምክክር መድረኩ ላይ ጥያቄ ቀርቧል፡፡

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እየተፈጠሩ ላሉ የሰብአዊ መብት ጥሰት ልዩ ሃይሎች ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሶ መንግስት ልዩ ሃይሎችን እንዲያፈርስ መጠየቁ ይታወሳል።

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድሮች አካሄድ እና አቅጣጫ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውይይት እየተደረገ ነው።

በውይይቱ ላይ ሚንስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
በመድረኩ ግድቡን አስመልክቶ በመደረግ ላይ ስላሉት ድርድሮች አካሄድ እና አቅጣጫ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

በውይይቱም ላይ ሚንስትሮች፣ የተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት፣ ምሁራን፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፏቸውን እያደረጉ ነው። በመድረኩም ግድቡን አስመልክቶ በመደረግ ላይ ስላሉት ድርድሮች አካሄድ እና አቅጣጫ ውይይት በመደረግ ላይ መሆንኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Via:- Addis Ababa city administration
@YeneTube @Fikerassefa
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ወደ ሳኡዲ አረቢያ አቅንተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ወደ ሪያድ ያቀኑት የሳውዲው ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱልአዚዝ ባደረጉላቸው ግብዣ መሰረት ነው ተብሏል፡፡መሪዎቹ በሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እና ሌሎች የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
'ኮሮናቫይረስን ወደ አፍሪካ መውሰድ አልፈልግም''

የ 21 ዓመቱ ካሜሮናዊ ኬም ሴኑ ፓቬል በቻይናዋ ጂንግዙ ግዛት ተማሪ ሲሆን በኮሮናቫይረስ መያዙን ካወቀ በኋላ "ተሽሎሃል ወደ አገርህ ተመለስ እንኳን ቢሉኝ አልመለስም" ብሏል። ምክንያቱ ደግሞ ቫይረሱን ወደ አፍሪካ ይዞ ላለመግባት ነው።

ኬም ሴኑ ፓቬል ከሁለት ሳምንታት ተከታታይ ህክምና በኋላ እየተሻለው መጥቷል። በሲቲ ስካን በተደረገለት ምርመራም ቫይረሱ ከሰውነቱ እንደጠፋ ምልክቶች ታይተዋል።

ፓቬል በገዳዩ ኮሮናቫይረስ የተያዘ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሲሆን ሙሉ የህክምናው ሙሉ ወጪ በቻይናዋ ግዛት ተሸፍኗል።

'' ትምህርቴን ሳልጨርስ ወደ አገር ቤት መመለስ አልፈልግም። ወደ ካሜሩን የምምለስበት ምንም ምክንያት የለኝም፤ ሙሉ የሆስፒታል ወጪዬ በቻይና መንግስት ተሸፍኖልኛል''ብሏል።

Via:- Arts TV

@YeneTube @Fikerassefa
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 79ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የ2012 የፌዴራል መንግስት የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ለተጨማሪ በጀቱ መሰረታዊ መነሻ የሆነው በቅርቡ በመንግስት የተዘጋጀው የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሲሆን ዋናው አላማው ኢኮኖሚው አሁን ከገጠመው ተግዳሮቶች የሚላቀቅበትን የፖሊሲ እርምጃዎች ተግባራዊ ለማድረግ ብር 18 ቢሊየን፤ ለልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ትግበራ ብር 2 ቢሊየን እንደዚሁም ለእኩል ስራ እኩል ደመወዝ አገራዊ ትግበራ ብር 7.9 ቢሊየን በድምሩ ብር 27.89 ቢሊየን ተጨማሪ በጀት እንዲጸድቅ የገንዘብ ሚኒስቴር ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የተጨማሪ በጀት ረቂቅ እዋጅ ላይ በስፋት ተወያይቶ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

በመቀጠልም ምክር ቤቱ የተወያየው በገንዘብ ሚኒስቴር የቀረቡትን ለደብረ ማርቆስ-ሞጣ የመንገድ ሥራ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣ ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የልዕቀት ማዕከል መመስረቻ ፕሮጀክት እና ለሁለተኛው አገር አቀፍ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት ሳንቴሽንና ሐይጅን ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውሉ የብድር ስምምነቶች እና ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ሲሆን ብድሮቹ ከሀገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ፣ የ10 ዓመት እፎይታ ያላቸው፣ በረጅም ጊዜ የሚከፈሉ እንደዚሁም ወለድ የማይታሰብባቸው በመሆናቸው አዋጆቹ ይጸድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡

ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ ዓላማ መዝሙርና የአፍሪካ ቀን ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ አገራችን ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን አጋርነት ለማሳደግ፣ ለፓን አፍሪካኒዝምና ለአፍሪካ የውህደት አጀንዳ ተግባራዊነት ያላትን ቁርጠኝነት ለማስቀጠል እንዲሁም የህብረቱ ኮሚሽን አስተናጋጅ አገርነት ሚናዋን ለመወጣት ከምታከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅ አላማን ማውለብለብ፣ የአፍሪካ ህብረት መዝሙርን ማዘመር እና አፍሪካ ቀን ታስቦ እንዲውል ማድረጉ አገራችን ለህብረቱ አላማዎች ስኬት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ በመሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ይጸድቅ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ ወስኗል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የግብርና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችን ለማቋቋም በተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ኮሌጆቹ ተጠሪነታቸው ለግብርና ሚኒስቴር ሆኖ እራሳቸውን የቻሉ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ተቋማት እንዲሆኑና በግብርናው ዘርፍ በአገሪቱ ልዩ ፍላጎቶች ላይ አትኩረው እንዲሰሩ ማድረግ እንዲቻል የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ም/ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ እንዲወጣና በስራ ላይ እንዲውል መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ከላከልን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
የፀረ ወባ መድኃኒት የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለማከም ውጤታማ መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት የዓለም ስጋት ለሆነው የኮሮና ቫይረስ በሽታ መድኃኒት ለማግኘት የበርካታ ሀገራት ተመራማሪዎች ምርምር በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል። በዚህ መሰረትም በቻይና ብቻ በበሽታው መድኃኒት ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉ ከ80 በላይ የቤተ ሙከራ ማዕከላት ተቋቁመው ስራ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።እነዚህ የቻይና ተመራማሪዎች ለወባ በሽታ መድኃኒትነት የሚያገለግለው “ክሎሮኪን ፎስፌት” የተሰኘው መድኃኒት የኮሮና በሽታን ለማከም ውጤታማ መሆኑን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል።

መድኃኒቱ ተጨማሪ የላቦራቶሪ ሙከራ ከተደረገበት በኋላ በስፋት አገልግሎት ላይ የሚውል መሆኑ ተመላክቷል። በቅርቡ በቻይና ሁቤይ ግዛት ውኃን ከተማ የተከሰተው የኮሮና በሽታ አድማሱን በማስፋት በተለየዩ የዓለም ሀገራት ውስጥ እየተዛመተ ይገኛል።አሁን ላይ በቻይና ብቻ ከ1 ሺህ 770 በላይ ዜጎች በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል።በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ወደ 70 ሺህ 548 ማሻቀቡን የቻይና ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ሺንዋ/FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ተሰርቆ ኔዘርላንድ የተወሰደውን ዘውድ የቅርስ እና ጥበቃ ባለስልጣን በነገው ዕለት ልረከበው ነው አለ፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
84,587 የተለያዩ የውጭ አገራት ገንዘብ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል ታያዘ!

በደወሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ 17,965 የአሜሪካ ዶላር፣ 2,520 ፖውንድ እና 64,102 የየመን ሪያል በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ ሲል በሁለት የመቆጣጠሪያ ጣቢያው ሰራተኞች በተደረገ ፍተሻ የካቲት 08 ቀን 2012 ዓ.ም ተይዟል፡፡ሕገ ወጥ ገንዘቡም ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ የተደdረገ ሲሆን ከዚህ ወንጀል ጋር ተያይዞ አራት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በፌደራል ፖሊስ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው፡፡

Via Ministry of Revenue
@YeneTube @FikerAssefa
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 780 ሚሊዮን የሚጠጉ ቻይናዊያን ዜጎች በጉዞ እግድ ውስጥ በወደቁ አካባቢዎች የሚኖሩ እንደሆኑ CNN ሰበሰብኩት ባለው መረጃ አሳውቋል። ይህም ማለት የሀገሪቱ ግማሹ ህዝብ ወይም የአለም 10% የአለም ህዝብ እንደማለት ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
የሶሪያ ሠራዊት 70 አስከሬኖችን የያዘ የጅምላ መቃብር በደማስቆ አቅራቢያ በሚገኝ ቀደም ሲል በአማፅያኑ ተይዞ በነበረ አካባቢ ማግኘቱን የሀገሪቱን የዜና ወኪል ጠቅሶ የዘገበው አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
ከ123 ሄክታር መሬት በላይ የማልማት አቅም ያለው የመስኖ ፕሮጀክት ተመርቆ ሥራ ጀመረ፡፡በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በግብርና ዕድገት ፕሮግራም በ2010 ዓ.ም የግንባታ ሥራው የተጀመረው የመስኖ ፕሮጀክት ዛሬ ተመርቋል፡፡

ምንጭ:አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የፊታችን እሁድ ሊካሄድ የነበረው ፍቅር ያሸንፋል የኢትዮጲያ ሩጫ እና ፌስቲቫል ተራዘመ፡፡

ለፍቅር እንሩጥ ጥላቻን እናምልጥ በሚል መሪ ሀሳብ የፊታች እሁድ የካቲት 15 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ የተያዘለት ፍቅር ያሸንፋል የኢትዮጲያ ሩጫ እና ፌስቲቫል መራዘሙን ሰምተናል፡፡

የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና የመንግስት ሀላፊዎች ያስጀምሩታል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው ፌስቲቫል እና ሩጫው ወደ ሌላ ጊዜ የተላለፈበት ምክንያት የካቲት 14 ምሽት ላይ ከሚካሄደው #የድምፃዊ_ቴድሮስ_ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ኮንሰርት ጋር የመርሀግብር መቀራረብ በመከሰቱ መሆኑን አዘጋጆቹ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ውድድሩ መራዘሙን እንጂ ትክክለኛ የሚካሄድበትን የውድድር ቀን ገና አልወሰንም ምክንያቱም የአትሌቲክስ ፌዴሪሽን ፕሮግራሞችን ማጣራት ስለሚኖርብንም ብለዋል አዘጋጆቹ፡፡

ከከንቲባ ጽህፈት ቤት እና ከፀጥታ ሀይሎች ጋርም ተነጋግረነን የፕሮግራም ሂደቱን ማመቻት ስለሚያፈልግ ቲሸርቶች የገዙ ተሳታፊዎች ትክክለኛውን ቀን ይፋ እስከምናደርግ በትዕግስት ጠብቁን ብለዋል፡፡በተቀያሪው የጊዜ ሰሌዳ አይመቸንም የምትሉ ታሳታፉዎች ካላችሁ ቲሸርቶቹን በመመለስ ገንዘባቹን ማግኘት ትችላላቹ ተብላቹሀል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የዱባይ ዐለም ዐቀፍ ወደቦች ኩባንያ የኤርትራ ወደቦችን ለማስፋፋት እንደተስማማ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ኩባንያው ለወደቦቹ አዳዲስ የሎጅስቲክ መሳሪያዎችን ይገጥማል፤ የወደቦቹን አገልግሎት አቅም ያሳድጋል፡፡ ኤርትራ ስለ ስምምነቱ ያለችው ነገር የለም፡፡ በሌላ ዜና፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለ3 ቀናት የሥራ ጉብኝት ዛሬ ሪያድ እንደገቡ ቃል አቀባያቸው የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

Via:- ዋዜማ ራዲዮ
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ፎርማጆ ጋር በሐርጌሳ ጉብኝት ለማድረግ ያቀረቡትን ጥያቄ የሱማሌላንድ ራስ ገዝ ውድቅ እንዳደረገው ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል፡፡ የጋራ ጉብኝቱን ሃሳብ ለሐርጌሳ ያቀረቡት ዐቢይ ናቸው፡፡

Via:- Horn Diplomat / Wazema
@Yenetube @Fikerassefa
ለመንግስት ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው

ከመጭው ሚያዝያ ወር ጀምሮ በመንግስታዊ መዋቅር ውስጥ ለሚገኙ ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንደሚሰጥ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የሲቪል ሰርቪስ ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ፕሮጀክት መጀመርን አስመልክቶ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ ፈይሳ እንደገለጹት÷ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናው የሚሰጠው ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የተቃኘ የመንግስት ሰራተኛ እንዲኖርና የወቅቱን የህዝብ ጥያቄ የሚመልስ ኃይል ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ ነው።

https://telegra.ph/yenetube-02-17
መካሄድ የሚጀምረው የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ በህግ የበላይነትና የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በትኩረት እንደሚመክር ተገለጸ።

የጨፌው አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ጨፌው ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ለጸጥታ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደነበር በማስታወስ፥ ይህንንም ተከትሎ በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች ሰላማዊ ሁኔታ እንዳለ ተናግረዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የጉምሩክ ኮሚሽን በጥር ወር ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃ እና ሕገ ወጥ ገንዘብ መያዙን አሰታወቀ።

ይህም ከገቢ 121 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ከወጪ ደግሞ 31 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 152 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተገልጿል።

በቁጥጥር ስር የዋለው የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴው በመጠን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 75 በመቶ ብልጫ እንዳለው ታውቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
የኮሮና ተህዋሲን ለመቆጣጠር የሚደረግ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋሲን አስቀድሞ ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ጊዜያዊ የማቆያ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን የአገሪቱ የማኅበረሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ። ሰሞኑን ከውጭ የገቡ 14 ቻይናውያን በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ በተቋቋመው ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጎአል።

በኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋስን አስቀድሞ ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ጊዜያዊ የማቆያ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን የአገሪቱ የማሕበረሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ። 

ተቋሙ እንዳስታወቀው የኮሮና ተህዋስን አስቀድሞ ለመከላከል ከውጪ ሀገር የሚመጡ የተለያዩ አገራት ዜጎች ከበሽታው ነጻ መሆናቸው እስኪታወቅ ድረስ ክትትል ለማድረግ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ታሳቢ ያደረጉ ጊዜያዊ የማቆያ ስፍራዎች ተቋቁመው ወደ ስራ ተገብቷል። 

በጊዜያዊ የማቆያ ስፍራዎቹ የክትትል ሥራው እየተከናወነ የሚገኘው ከየክልሎቹ የጤና ቢሮዎችና ከከተማ አስተዳደር የጤና ጽሕፈት ቤቶች ጋር በመተባበር መሆኑን በተቋሙ የዓለም አቀፍ የጤና ደንብ የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ፈይሳ ረጋሳ ለዶቼ ቨለ ( DW )ገልጸዋል። 

በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው ሰሞኑን ከውጭ የገቡ አስራ አራት ቻይናውያን በአሁኑወቅት በሀዋሳ በተቋቋመው ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩ መደረጉን ገልፀዋል።

አቶ እንዳሻው አያይዘውም «ከውጭ የገቡ ቻይናውያን በጊዜያዊ ማቆያ ውስጥ ከገቡ ዛሬ ስምንተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል። እስከአሁንም ምንም አይነት ምልክት አልታየባቸውም ።  በአስራ አራት ቀናት ውስጥ የተለየ ምልክት ካልታየ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲቀላቀሉ ይደረጋል» ብለዋል። 

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ ፓርኩ ቻይናውያንና ሌሎች የውጭ ሀገራት ዜጎችን ጨምሮ ከሰላሳ አራት ሺህ በላይ የሰው ሀይል ያለበት በመሆኑ የኮሮና ተህዋስን አስቀድሞ ለመከላከል አስፈላጊው የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የፓርኩ ማህበረሰብ በተህዋሱ ባህሪና በሚያስከተለው በሽታ ምልክቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
YeneTube
የኮሮና ተህዋሲን ለመቆጣጠር የሚደረግ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋሲን አስቀድሞ ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ጊዜያዊ የማቆያ ጣቢያዎች መቋቋማቸውን የአገሪቱ የማኅበረሰብ ጤና ተቋም አስታወቀ። ሰሞኑን ከውጭ የገቡ 14 ቻይናውያን በአሁኑ ወቅት በሀዋሳ በተቋቋመው ጊዜያዊ ማቆያ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጎአል። በኢትዮጵያ የኮሮና ተህዋስን አስቀድሞ ለመከላከል…
ደቡብ ክልል በጊዜያዊነት ማቆያ አዘጋጅተናል ያሉት ከእውነት የራቀ ነው።

ከ14 ቻይናዊ 13 ቻይናዊያን እኔ የምሰራበት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ናቸው። ቤቱን ተከራይተው ያስቀመጠው ድርጅቱ ነው። #ክልሉም ሆነ #ፓርኩ ያደረገው ነገር የለም መረጃውን ያደረሰን ለጉዳዩ መረጃ ያለው ወዳጃችን ነው።

እንዲሁም በፓርኩ ውስጥ ካሉ አንዱ ፋብሪካ ነው ለይቶ ማቆያ ቦታውን ያዘጋጀ ነው።
ከተማ ውስጥ ሌላ ቦታም አለ። ፓርኩ ውስጥ በልየታ የተቀመጡ ሌሎችም አሉ።

@YeneTube @Fikerassefa
#COVID-2019_update

የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከሰባ ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1776 ደርሷል።

Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa