YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በዛሬው እለት ጠ/ሚ አብይ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ "ብልፅግና ለሀገራችን- ነፃነት ለህዝባችን" ከሚል መልዕክት ጋር የለጠፉት ካርታ ጀዋር መሃመድን ጨምሮ ከተለያዩ ፖለቲከኞች ትችትን አስተናግዷል። "ካርታው ኢትዮጵያን አሃዳዊ የሆነች ሀገር አድርጎ ነው ሚያሳየው፣ የብሄር ብሄረሰቦች ስብስብ ፣ፌዴሬሽን መሆኗን የዘነጋ ነው፣ ይህም ከዚህ በፊት በነበሩ መንግስታት(አገዛዞች) ተሞክሮ የከሸፈና አደገኛ አካሄድ ነው" ብለዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ማይክ ፖምፒዮ ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓም ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ማይክ ፖምፒዮ በነገው እለት ከክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር የሁለቱን አገሮች የሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ።በተጨማሪም ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

Via Spokesperson Office
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጁነዲን ሳዶ ‹ሸገር› የተሰኘ አዲስ ባንክ ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በማቋቋም ላይ መሆናቸውን አስታወቁ።

የባንኩ መሥራች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ጁነዲን ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ ድርሻ የመሸጥ ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝተው ከየካቲት ሰባት ጀምሮ በይፋ አክስዮን መሸጥ ይጀምራሉ። የባንኩ የምሥረታ አስተባባሪ ኮሚቴ በአጠቃላይ 150 ግለሰቦች ያሉበት ሲሆን፣ ከአገር ውስጥ እንዲሁም ከዳያስፖራው ሀብት በማሰባሰብ ካፒታሉን እንደሚያሟላም ጁነዲን ተናግረዋል።

https://telegra.ph/YeneTube-02-18-2
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን ሹም ሽሮች እንደሚኖሩም ይጠበቃል፡፡
@YeneTube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የስነ-ምግባር ጉድለት በተገኘባቸው 29 ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ የስነ-ምግባር ጉድለት በተገኘባቸው 29 ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

ከግብር ከፋዩ የሚመጡ ጥቆማዎችን እና መረጃዎችን ትክክለኛነት በማጥራት የስነ-ምግባር ጉድለት የተገኘባቸው ባለሙዎች እና አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

በዚህም፣ በዘንድሮው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የስነ-ምግባር ጉድለት በተገኘባቸው 29 ባለሙያዎች ላይ ከከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ቅጣት ከስራ እስከማሰናበት የደረሰ እርምጃ መወሰዱን የቢሮው ኃላፊ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ ተናግረዋል።

የቢሮው የስድስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም 94 ነጥብ 46 በመቶ ሲሆን በበጀት አጠቃቀም ደግሞ 93 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል።
ቢሮው፣ የመጀመሪያ ስድስት ወር ዕቅድ አፈፃፀሙን አስመልክቶ ከክፍለ ከተማ የገቢዎች ጽህፈት ቤቶች ከተውጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር ተወያይቷል።

ምንጭ:- ኢዜአ
@YeneTube @Fikerassefa
ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው እለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዛሬው እለት መካሄድ በተጀመረው ጉባዔ ላይ የክልሉ መንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እና ሹመቶችም ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንዲሁም ጨፌው በመደበኛ ጉባዔው በህግ የበላይነትና የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በትኩረት እንደሚመክርም ተገልጿል።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
በጥር ወር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል!

የአስራ አምስት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ንብረት የሆኑ 30 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በማስወገድ ከስምንት ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን የመንግሥት ንብረት፣ ግዢ እና ማስወገድ አገልግሎት አስታወቀ።ለሽያጭ ከቀረቡት 30 ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የ10 ፌዴራል ተቋማት የሆኑ 21 ተሸከርካሪዎች፣ ከመነሻ ዋጋ በላይ ላቀረቡባቸው 13 ተጫራቾች እንዲሁም ተወዳዳሪዎች ከፍተኛውን ዋጋ የሰጡባቸው 9 ተሽከርካሪዎችን ሽያጭ ጨምሮ በድምሩ 8 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በምክትል ርእሰ መስተዳድርነት በእጩነት ቀርበዋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤ በምክር ቤቱ አዳራሽ ተጀምሯል፡፡የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የዕጩ ተሿማዎች ዝርዝር ግለ ታሪክና የሹመቱን አስፈላጊነት ለምክር ቤቱ አባላት አስረድተዋል፡፡ ወቅቱን የዋጀ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ አመራር ለመስጠትና ኃላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት የሚጠይቅ ወቅት ላይ በመሆናቸው ሹመቱ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ላቀ አያሌው፣ የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ በርእሰ መስተዳድር ደረጃ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ መላኩ አለበል እና የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታ ደጀን በፌዴራል መንግሥት ደረጃ ኃላፊነት ስለተሰጣቸው በምትካቸው አዳዲስ ሹመት መስጠት እንዳስፈለገ ነው ርእሰ መስተዳድር የተናገሩት፡፡በመሆኑም ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በምክትል ርእሰ መስተዳድርነት በእጩነት ቀርበዋል፡፡ የምክር ቤት አባላትም በእጩ ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ዙሪያ ሐሳብ እየሰጡ ነው፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በዛሬው የአማራ ክልል ም/ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ወደ ፌደራል የተዛወሩ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ማንነት ይፋ ሆኗል።የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ላቀ አያሌውና የብልፅግና የአማራ ክልል ቢሮ ኃላፊ ዮሃንስ ቧያሌው ከክልል ስልጣናቸው ተነስተዋል።

Via:- ተስፋዬ ወልደየሱስ
@YeneTube @Fikerassefa
በቡራዩ ድምፃዊያን በፀጥታ አስከባሪዎች ተደብድበዋል ሲሉ ድምፃውያኑ ከስሱ!

በቡራዩ ከተማ ገፈርሳ ቀበሌ በተለምዶ ፀርሃ ፅዮን ተብሎ የሚጠራ አካባቢ ቅዳሜ የካቲት 7/2012 ዓ.ም. “ግጭት ተነስቶ የኖርዌይ ዜግነት ያላትን ሀዊ ቀነኒን ጨምሮ ሌሎችም ድምፃዊያን በፀጥታ አስከባሪዎች ተደብድበዋል” ሲሉ ድምፃውያኑ ከስሰዋል።

ይህ ግጭት የተከሰተው በአንድ ሆቴል ምረቃ ሥነ-ስርዓት ላይ መሆኑ ነው የተገለፀው።

Via:- VOA
@YeneTube @Fikerassefa
የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው ፣ የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደረጃ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ መላኩ አለበል እና የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትክሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ፋንታ ደጀን በፌዴራል መንግሥት ደረጃ ኃላፊነት የተሰጣቸው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎ ርዕሰ መስተዳድሩ ወደ ፌዴራል መንግስት በተዛወሩ ሃላፊዎች ቦታ አዳዲስ ሹመቶችን ለመስጠት የእጩ ሹመቶችን ስም ዝርዝር እያቀረቡ ይገኛሉ።

በዚህ መሰረትም ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ለአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት በዕጩነት ቀርበዋል።

አሁን ላይ የምክር ቤቱ አባላት በዕጩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ዙሪያ ሀሳብ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሾሙ፡፡

የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው አስቸኳይ ጉባኤ የክልሉን ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሰይሟል፡፡ በዚህም መሠረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪው ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አድርጎ ሰይሟል፡፡
ለመሆኑ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ሆነው የተሾሙት ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ ማን ናቸው?
👇👇👇
https://telegra.ph/FantaM-02-18
የኮቪድ-19 (የኮሮና ቫይረስ በሽታ) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ
የካቲት 10/2012

➡️ ከጥር 15/2012 ጀምሮ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በ7ቱ መግቢያዎች 146,357 በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3,901 በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ በሁሉም ወደ ሀገር መግቢያ ጣቢያዎች 248,734 በሙቀት መለያው አልፈዋል፡፡ እንዲሁም 697 የሚሆኑት ደግሞ ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ሲሆኑ እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ያለበት ሰው የለም፡፡

➡️ ከጥር 15/2012 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 60 ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡

➡️ ከነዚህም ጥቆማዎች 17ቱ የበሽታውን ምልክቶችን በማሳየታቸው እና የቻይና ጉዞ ታሪክ ስላላቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም 17ቱንም የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡

➡️ ይህ መረጃ እስከ ተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ አንድ የበሽታውን ምልክት ያሳየ ሰው በሽታው እንደሌለበት እስኪረጋገጥ ድረስ በለይቶ ማቆያ ማዕከል ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ቆይቶ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ በመረጋገጡ ከማዕከሉ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

Via Public Health Institute
@YeneTube @FikerAssefa
የአፍሪካ የምድር ጦር ኃይሎች ስብሰባ አዲስ አበባ ውስጥ ተጀመሯል።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የዮሐንስ ቧያለው እና የላቀው አያሌው ከስልጣን መነሳት ተቃውሞ አስነሳ!

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 10/2012 ባደረገው አስቸኳይ ጉዳዔ ላይ የክልሉን ምክትል ርእሰ መስተዳድር ላቀ አያሌው እና የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዮሐንስ ቧያለው ከስልጣናቸው መነሳታቸው ተቃውሞ አስነሳ ፡፡
ለምክትል ርእሰ መስተዳድር በእጩነት በቀረቡት ፈንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) ላይ የተቃውሞ ሐሳብ ባይቀርብም ክልሉን በለቀቁ መሪዎች ላይ ግን የምክር ቤት አባላቱ ‹‹ክልሉን ለቅቀው ወደ ፌዴራል የሄዱት አራቱም መሪዎች ለክልሉ በሚያስፈልጉበት ወቅት ላይ እንዲነሱ መደረጉ አግባብ አይደለም፡፡ በዚህ ሰዓት ክልሉን ማደራጀት እና እንዲጠናከር በማድረግ ፋንታ ወደ ፌደራል መላክ ክልሉን የአመራርነት መለማመጃ ከማድረግ የዘለለ ትርጉም የለውም›› ብለዋል፡፡

መላኩ አለበል የፌዴራል ሹመታቸው ቀድሞ በፓርላማ የፀደቀ በመሆኑ እና ዮሐንስ ቧያለውም የፓርቲ ተልዕኮ እንጂ ጉዳዩ በምክር ቤቱ የማይታይ ባለመሆኑ እንዲሁም በላቀ አያሌው እና ፈንታ ደጀን ክልሉን መልቀቅ ላይ ምክር ቤቱ የተወያየበት ሲሆን የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ የሰው ኃይል ስምሪቱ የፓርቲያቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ሹመቱን የማጽደቅና አለማፅደቅ ስልጣን የምክር ቤቱ ነው፤ የምክር ቤቱን ውሳኔ አከብራለሁ ነገር ግን የሌሎች አካላት ተፅዕኖ እንዳለበት ተደርጎ መወሰድ የለበትም ሲሉም ማላሽ መስጠታቸውን አብመድን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የድንጋይ ከሰል ከውጪ ማስገባት ሊቆም ነው!

በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት ለመጠቀም እና ከወጪ አገራት የሚገባውን የድንጋይ ከሰል በአገር ውስጥ ለመተካት በመታሰቡ የድንጋይ ከሰል ከውጪ አገራት እንዳይገባ ሊደረግ ነው።ከውጪ አገራት የሚመጣውን የድንጋይ ከሰል ምርት ማስቆም ያስፈለገው፣ ኢንዱስትሪዎች በአገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ሀብት መጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ክልል የሠላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አገኘው ተሻገር ከኃላፊነታቸው ተነሱ!

የክልሉ የሠላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አገኛው ተሻገር ከኃላፊነታቸው ተነስተው በምትካቸውም ሲሣይ ዳምጤ የቢሮው ኃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 10/2012 ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ሲሳይ ዳምጤ የቢሮው ኃላፊ እንዲሆኑ በአብለጫ ድምጽ፣ በአንድ ታቀውሞ እና በሦስት ድምጸ ተዓቅቦ ሹመቱን አፅድቋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዩናይትድ ስቴትስ ስቴት ሴክሬታሪ የሆኑትን ማይክ ፖምፔዮን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የኢትዮጵያ እና የዩናይትድ ስቴትን ግንኙነት ስለ ማጠናከር፣ ስለ ቀጣይ የትብብር አቅጣጫዎች፣ ስለ ቀጣናዊ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ለውጥ ተወያይተዋል።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa