YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ በሽታ) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ
የካቲት 6/2012

➡️ በሁሉም የአገሪቷ መግቢያዎች ከጥር 15/2012 ጀምሮ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ 118 882 መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3 380 በሽታውን ሪፖረት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ እንዲሁም ከ455 በላይ የሚሆኑት ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

➡️ ከጥር 16/2012 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 47 ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡

➡️ ከነዚህም ጥቆማዎች 16ቱ የበሽታውን ምልክቶችን በማሳየታቸው እና የቻይና ጉዞ ታሪክ ስላላቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ ከነዚህም ውስጥ 15ቱ በላቦራቶሪ ምርመራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡በትላንትናው እለት ወደ ለይቶ ማቆያ የገባው የጭምጭምታ ግለሰብ የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በማዕከሉ እንዲቆይ ተደርጎ የምርመራ ውጤቱ በዛሬው ዕለት የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡

➡️ የበሽታውን ምልክት ላሳዩ ሰዎች ለይቶ ማቆየት እና መከታተል ይቻል ዘንድ ለየካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ከክልል እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለተውጣጡ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድኖች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ እንዲሁም ለሆቴል ባለቤቶች እና ስራ አስኪያጆች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

➡️ ለክልሎች የበሽታውን መከላከል ቅድመ ዝግጁነት ለማጠናከር እንዲረዳ የሕክምና መገልገያዎች በመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በኩል እንዲደርሳቸው የስርጭት ዕቅድ ለኤጀንሲው ተሰጥቷል፡፡

📌ጥንቃቄ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች
➡️ የኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከታየባቸው ሀገራት የመጡ መንገደኞች ወይም በዚህ ቫይረስ ከተያዙ ግለሰቦች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ላይ የበሽታው ምልክቶች (ትኩሳት፤ ሳል፤ የትንፋሽ መቆራረጥ፣ የመተንፈስ ችግር) ከታዩ፣ ማንኛውም የህብረተሰቡ አካል በአስቸኳይ በ8335 ነጻ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ሪፖርት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡

➡️ የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሰዎች በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫቸውን በሶፍት ወይም በክንድእንዲሸፍኑ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍት መክደኛ በለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ወስጥ በመጣል የበሽታውን ስርጭት በጋራ እንከላከል፡፡

➡️ እጃቸውን በሳሙናና በንጹህ ውሃ በመታጠብ የኮሮና /COVID የቫይረስ እና ሌሎችንም መሰል በሽታዎች ስርጭት እንዲከላከሉ እንመክራለን፡፡

➡️ በተጨማሪም ህብረተሰቡ በሀገራችን እስካአሁን በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው አለመኖሩን አውቆ ሳይዘናጋ የበለጠ ጥንቃቄ ኢንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ያሳስባል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን phemdatacenter@gmail.com ወይም ephieoc@gmail.com በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡

Via Ministry of Health
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ በሽታ) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ የካቲት 6/2012 ➡️ በሁሉም የአገሪቷ መግቢያዎች ከጥር 15/2012 ጀምሮ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ 118 882 መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3 380 በሽታውን ሪፖረት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ እንዲሁም ከ455 በላይ የሚሆኑት ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ➡️
ከላይ በመግለጫው እንደተቀመጠው የኮቪድ19(ኖቬል ኮሮና ቫይረስ) በሽታ ምልክቶችን ያሳየ ሰው በለይቶ ማቆያ ማዕከል ውስጥ እንደሚገኝና ናሙናው ለላብራቶሪ ምርመራ መላኩ መገለጹ ይታወሳል። አሁን የምርመራው ውጤት የደረሰ ሲሆን ከበሽታው ነጻ መሆኑ ተረጋግጧል።

ምንጭ: ጤና ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ዛሬ አዲስ አበባ በሚገኘው ፅህፈት ቤቱ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለብዙሃን መገናኛ መግለጫ ሰጥቷል።

በተለያዩ የኦሮምያ ክልል ከተሞችና ዞኖች በተለይም በኦሮምያ ልዩ ዞን በሰበታ አዋስ፣ለጋጣፎ፣ቡራዩ እና በአጠቃላይ በ26 ከተሞችና በ7 ዞኖች ድርጅቱ ያሰለጠናቸው እና በትክክል የድርጅቱ አባል የሆኑ 350 ሰዎች ታስረውብኛል ሲል ፓርቲው አስታውቋል።

የኦሮምያ መንግሥት በበኩሉ ኦነግ ባነሳቸው ቅሬታ ላይ መልስ ስጥቷል።

Via:- VOA
@YeneTube @Fikerassefa
ኢጄቶ የሲዳማ ክልል ርክክብ እስከ የካቲት 15 እንዲካሄድ ጠየቀ!

እስከ የካቲት 15 ድረስ የስልጣን ርክክብ ተደርጎ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የማይመሰረት ከሆነ ተቃውሞ እንደሚያስነሳ የሲዳማ ወጣቶች ቡድን የሆነው ኢጄቶ አስጠንቅቋል። ሲዳማ ዞን ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን የቻለ ክልል መሆኑን በድምፁ ካረጋገጠ 3 ወራቶች የተቆጠሩ ቢሆንም ገዥው ፓርቲ የሲዳማን ክልል ለመመስረት እያቅማማ እንደሆነ ስማቸው ያልተጠቀሰ የኢጄቶ አመራር ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። መንግሥት ከህዝቡ የሚተላለፉ ጥሪዎችን በቸልታ የሚያልፍበት መንገድ የሚመጡትን ችግሮች ከማባባስ በቀር መፍትሄ የሚያመጡ አለመሆናቸውን ጠቅሰው መንግሥት የህዝቡን ውሳኔ ላለማስፈፀም አማራጭ እየፈለገ እንዳለ እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በልዩ ልዩ ምክንያት በችግር ውስጥ ከሚገኙ፣ ጥቃት ከደረሰባቸው እና በመጠለያ ውስጥ ከሚገኙ ሴት ኢትዮጵያውያን ጋር በችግሮቻቸው እና በመፍትሄዎች ላይ ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው። በውይይቱ ችግር ከገጠማቸው ሴቶች በተጨማሪ በልዩ ልዩ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ስኬትን ያስመዘገቡ ሴቶችም ተገኝተው ልምዳችውን ያጋራሉ።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በ2012ቱ ሀገር አቀፍ ምርጫ ከዚህ በፊት የነበሩ አስፈፃሚዎች እንደማይሳተፉ ተገለጸ

ቀድሞ በተደረጉ ምርጫዎች የተሳተፉ የምርጫ አስፈፃሚዎች በነሐሴ ወር በሚደረገው በስድተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ እንደማይሳተፉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። እስካሁን የፓርቲዎች የሴቶች ተሳትፎ 10 በመቶ ብቻ መሆኑን አመለከተ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት እንደተገለጸው፤ ከዚህ በፊት አስፈፃሚ የነበሩ ሰዎች ላይ አመኔታ ስለሌለ በምርጫ 2012 እንዳይሳተፉ ተወስኗል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በመድረኩ እንደገለጹት፤ ከዚህ በፊት አስፈፃሚ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ጥፋተኛ ናቸው ማለት አይደለም፤ እንዳይሳተፉ የተደረገው ግን ጥርጣሬን ለማስወገድ ነው።

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa
ባልደራስ በባሕር ዳር ከሕዝብ ጋር እየተወያየ ነው

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ትናንት አመሻሽ ባሕር ዳር ገብተዋል።

ሕዝብ ለፓርቲው ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ የባልደራስ ሊቀ መንበር ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ባሕር ዳር በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ የአማራ ወጣቶች ማሕበር በባሕር ዳር ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
በጣና ግዮን ወጣቶች የበጎ አድራጎት ማህበር አስተባባሪነት የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች በባሕር ዳር ጣና ዳር የፅዳት ሥራ ዛሬ ጧት አከናውኗል።

ሕዝባዊ ውይይቱም በቴዎድሮስ ስታዲዮም ሊጀመር ዝግጅቱ ተጠናቋል። በመድረኩ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ሊቀመንበር ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በፓርቲው እንቅስቃሴ ዙሪያ ንግግር እንደሚያደርጉ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ለኢትዮጲስ ገልፀዋል።

ባልደራስ ነገ እሁድ የካቲት 8 ቀን በጎንደር ከተማ ተመሳሳይ ሕዝባዊ ውይይት እንደሚያደርግም አቶ ስንታየሁ ገልፀዋል።

Via:- ኢትዮጲስ ጋዜጣ
@Yenetube @Fikerassefa
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባዔ ሊያካሂድ ነው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 10/2012 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባዔ እንደሚያካሂድ ይጠበቃል፡፡በዕለቱም ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ እና ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
በአፍሪካ ውስጥ የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ ህመምተኛ ግብጽ ውስጥ መገኘቱ ተነገረ።

ይህም ለግብጽ የመጀመሪያው በበሽታው የተጠረጠረና በሽታው የተገኘበት ሰው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ግለሰቡም በአህጉሪቱ የተገኘ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሆኗል።
የግብጽ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሽታው የተገኘበት ግለሰብ የውጪ አገር ዜግነት ያለው መሆኑን ቢገልጽም ከየት አገር እንደመጣ ግን አላመለከተም።


ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አክሎም ስለበሽታው ክስተት ለዓለም የጤና ድርጅት ማሳወቁንና በበሽታው የተያዘው ግለሰብም በአንድ ሆስፒታል ውስጥ ተለይቶ ክትትል እየተደረገለት መሆኑን ገልጿል።

የአፍሪካ አገራት ከቻይና ጋር ባላቸው የጠበቀ ግንኙነት ምክንያት በሽታው በአጭር ጊዜ አፍሪካ ውስጥ ሊታይ እንደሚችል የጤና ባለሙያዎች ቀደም ሲል ሲያስጠነቅቁ ነበር።

በሽታው በወረርሽኝ መልክ መከሰቱና በተለያዩ አገራት ውስጥ መታየቱ ከተነገረ በኋላ ጥቂት የማይባሉ የአፍሪካ አገራት፣ የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሰዎችን እንዳገኙ ቢገልጹም በኋላ ላይ በተደረጉ ምርመራዎች ግለሰቦቹ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ከቻይናዋ የዉሃን ከተማ ተነስቶ ወደ ተለያዩ አገራት የተዛመተው ይህ በሽታ እስካሁን ድረስ ከ1ሺህ 500 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የሚበዙት ቻይናውያን ናቸው።

Via:- BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከጂንጆ ከተማ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ተጠሪ

በጂንጆ ሁበይ ከተማ የምንኖር ኢትዮጵያውን ቁጥራችን ትንሽ ቢሆንም ሰው እያወራ እየተጨነቀ ያለው ስለ ዉሀን ብቻ ነው ጂንጆ የምንገኝ ተማሪዎች እኛም ተመሳሳይ ጭንቀት ላይ ስላለን መንግስት ትኩረቱን ለኛም እንዲሰጠን እንጠይቃለን ።


@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ በትላንትናው እለት በኮርኖ ቫይረስ ተጠርጥሮ በለይቶ ማከምያ ክፍል የገባው ተጠርጣሪ ከቫይረሱ ነጻ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶችን ያሳየ አንድ ሰው በለይቶ ማቆያ ማዕከሉ ውስጥ ከገባ በኋላ የምርመራ ናሙናው ለምርመራ ተልኮ ነበር።

ተጠርጣሪው አሁን የምርመራው ውጤት የደረሰ ሲሆን ከበሽታው ነጻ መሆኑ እንደተረጋገጠ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እና 27 የተለያዩ የድምበር መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች ላይ የሚደረገው የማጣራት ምርመራ በተጠናከረ ሁኔታ እየቀጠለ ይገኛል፡፡

እስከ ትላንት ድረስ ለ118 ሺህ 882 ተጓዦች የሙቀት መለያ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 3 ሺህ 380ዎቹ የመጡት ቫይረሱ ሪፖርት ከተደረገባቸው ሀገራት ነው፡፡

እንዲሁም ከ455 በላይ የሚሆኑት ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

በኮሮና ቫይረስ እስካሁን 48 ሺህ ታካሚዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት የተደረገ ሲሆን 1ሺህ 500 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን የአለም ጤና ድርጅት አስታውቃል፡፡

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
ጁነዲን ሳዶ ሸገር የተሰኘ አዲስ ባንክ ሊመርቱ ነው!

የቀድሞው የኦሮምያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጁነዲን ሳዶ #ሸገር የተሰኘ አዲስ ባንክ ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በማቋቋም ላይ መሆናቸውን አስታወቁ።

የባንኩ መስራች ቦርድ የሆኑት ጁነዲን እንደተናገሩት ድርሻ የመሸጥ ፍቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝተው ከየካቲት 7 ጀምሮ በይፋ አክሲሆን መሸጥ ይጀምራል ብሏል ።

Via:- አዲስ ማለዳ ጋዜጣ 🖊 YeneTube
@YeneTube @Fikerassefa
አውሮፓ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሞት ተመዝግቧል። የ80 አመት ቻይናዊ አዛውንት ወደ ፓሪስ ለጉብኝት በመጡበት እንደሞቱ VoA ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የክልል ልዩ ሃይል እና ሚሊሻ በፌደራል ስር እንዲጠቃለሉ የሚመክር ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

ውይይቱን ጽናት ኢትዮጵያ የተሰኘው የበጎ አድራጎት ማህበር ያዘጋጀው ሲሆን የክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሻዎች ለአገራችን ሰላም ያላቸው ሚና በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይግኛል። በኢትዮጵያ የዜጎች መፈናቀል፣ የማምለኪያ ቦታዎች መቃጠል እና ሌሎች እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች እንዲቆሙ እና የህግ የበከላይነት እንዲረጋገጥ መፍትሔዎቹ ምን ምን ናቸው በሚል ላይ እንደሚያተኩር የውይይቱ አዘጋጆች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ የህግ ምሁራን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሃይማኖት አባቶች፣የአገር ሽማግሌዎች፣ የጸጥታ እና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።የክልል ልዩ ሃይሎች እና ሚሊሻዎች አሁን ካሉበት ፉክክር ወጥተው እንዴት ለአገር ግንባታ እናውለው በሚልም የመፍትሔ ሃሳቦች እንደሚነሱበትም ይጠበቃል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ያለዕድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም የተዘጋጀዉን ፍኖተ ካርታ በኦሮሚያ ክልል ማስተዋወቅ ጀመረ!

ያለዕድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም የተዘጋጀዉን ፍኖተ ካርታ በኦሮሚያ ክልል ማስተዋወቅ በዛሬዉ ዕለት በጅማ ዞን ተጀምሯል፡፡ይህንንኑ ፍኖተ ካርታ አጠር ባለ መልኩ ያስተወወቁት አቶ ሰሎሞን አሰፋ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚኒስቴር ጽ/ቤት ሀላፊ ሲሆኑ በገለጻቸዉም ፍኖተ ካርታዉ ከሌሎች መሰል አስትራተጂዎች በተለየ መልኩ ለስራዉ አስፈላጊ የሆነ በጀት በዉስጡ እንዳካተተና ያለዕድሜ ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም በከፍተኛ ፍጥነት መሰራት እንዳለበት አጽንኦት የሰጠ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በማስተዋወቂያ መድረኩ ላይ ከጅማ ዞን የተዉጣጡ በሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ላይ የሚሰሩ ሴክተር መ/ቤት ተወካዮች፣ የሀይማኖት ተቋማት ተወካዮችና ሌሎች ጉዳዮ ከሚመለከታቸዉ አካላት የተዉጣጡ ከ 250 በላይ የሚገመቱ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ: የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
#COVID-2019_update

የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከስድሳ ስድስት ሺህ ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ደግሞ 1526 ደርሷል።

Via AFP
@YeneTube @FikerAssefa
"ከ350 በላይ የሚሆኑ አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን ለእስር ተዳርገውብናል" ኦ.ነ.ግ

“27 አባላት እና ደጋፊዎቻችን ለእስር ተዳርገዋል” ኦ.ፌ.ኮ

"በክልላችን የፖለቲካ ፓርቲ አባል ስለሆነ ብቻ ማንም ሰው አይታሰርም መታሰርም የለበትም።” ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት

Via Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
በጅግጅጋ ከተማ ነገ የድጋፍ ሰልፍ ይደረጋል።

በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ በነገው እለት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ እንደሚደረግ ከአዘጋጆቹ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።በነገው እለት ከማለዳው አንስቶ በሚካሄደው ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በጅግጅጋ እና በአከባቢው የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን "በህብር ወደ ብልፅግና!" እንዲሁም " ብልፅግና ለሁሉም ሁሉም ወደ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃልም እንደሚካሄድ ታውቋል።

Via Sheger Times
@YeneTube @FikerAssefa
በተቀማጭ ገንዘብ ማነስ ምክንያት ከባንኮች የሚገኘው ብድር እጅግ ቀንሷል!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ በሀገሪቱ ያሉ የግል ባንኮች በተቀማጭነት ያስቀመጡት ገንዘብ ከሰጡት ብድር ጋር ስላልተጣጣመ ለደንበኞቻቸው የሚሰጠው ብድር ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ እጅግ መቀነሱን የባንክ ሰራተኞች ለፊደል ፓስት ተናግረዋል።አብዛኞቹ ባንኮችም ካላቸው ተቀማጭ ገንዘብ ከ70 እሰከ 90 ከመቶ ብድር ላይ በማዋላቸው የገንዘብ እጥረት ገጥሟቸዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለላኪዎች፣ መድሀኒትና ዘይት አቅራቢዎችእንዲሁም ሌሎች ለሀገሪቱ የግድ አስፈላጊ ከሆኑ ምርቶች በስተቀር ለሀገር ውስጥ እቃዎች ግዢም ይሁን ለሌሎች እቃዎች የሚሰጠውን ብድር እንዳቆመ ስማቸው እንዳይገለፅ ያልፈለጉ የባንኩ ሰራተኞች ለፊደል ፓስት ተናግረዋል። ንግድ ባንክ ለሰራተኞቹ የሚሰጠውን ብድር በተቀማጭ ገንዘብ ማነሱ ምክንያት እንዳቆመ ተናግረዋል።

በዳሽን ባንክ የምትሰራ አንዲት ሰራተኛም ብድሮች እንደድሮ እየተለቀቁ እንዳልሆ ተናግራለች ።እንደሰራተኞቹ ገለፃ ባንኮች የብድር አለቃቀቃቸውን ካላቸው ተቀማጭ ገንዘብ ጋር አመጣጥኖ አለመሄድ፣ የኢኮኖሚው መቀዝቀዝ ፣የዋጋ ንረት ባንኮችን ተቀማጭ ገንዘባቸው እንዲቀንስ አድርጎ የብድር አገልግሎታቸው እንዲቀነስ አድርጎታል።ይሄም ችግርን ለመፍታት ኢኮኖሚውን ማቅናትና የሰጡትን ብድር የመመለስ ረጅም ስራ ይጠብቃል በማለት የባንክ ሰራተኞቹ አስተያየታቸውን ገልፀዋል።

Via Fidelpost
@YeneTube @FikerAssefa