YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሰላም ሚኒስቴር 12 የእርሻ ትራክረተሮችን ገዝቶ ለክልሎች አስረከበ። የሰላም ሚኒስቴር ዛሬ ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም በ28 ሚሊየን ብር የገዛቸውን የእርሻ ትራክተሮች ለጋምቤላና ለቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አስረክቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የውሃ መሰረተ ልማት ላይ ባእድ ነገር የጨመሩ ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንች ተያዙ!

ባለቤትነቱ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን የሆነ የፍሳሽ መሰረተ ልማት ላይ ባእድ ነገር ሲጨምሩ የተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለስልጣኑ አስታወቀ፡፡ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የፋብሪካ ተረፈ ምርት በቦቴ ተሸከርካሪ በማጓጓዝ በባለስልጣኑ የፍሳሽ መስመር ውስጥ ሲደፉ በመገኘታቸው ነው፡፡ጥር 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት በተለምዶ ጠማማው ፎቅ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ባእድ ፍሳሹን ወደ መስመር ሲጨምሩ የተገኙ ሁለት ግለሰቦች ከነተሸከርካሪው በጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው ተናግረዋል

ምንጭ:ኢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

ትናንት በቦሌ ክ/ከተማ 24 ቀበሌ አካባቢ ከተከሰተው ክስተት ጋር ተያይዞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ለኢትዮ ኤፍ.ኤም መግለጫ ሰጥተዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ መረጃዎች የሀሰት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገግጿል፡፡ፖሊስ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተገናኘ በቀጣይ በምርመራ የሚያገኘውን ውጤት ለህዝብ የሚገልፅ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለኮሮና ቫይረስ መድሃኒት ለማግኘት ለሚደረገው ጥረት የሚውል የ100 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አድርገዋል።

ምንጭ: ፎርብስ
@YeneTube @FikerAssefa
አንድነት ፓርክ ከቅዳሜ ጥር 30 እስከ ረቡዕ የካቲት 4 ድረስ ለጎብኚዎች ዝግ እንደሚሆን እየገለፅን በእነዚህ ቀናትም ፓርኩን ለመጎብኘት ትኬት አስቀድማችሁ የቆረጣችሁ ጎብኚዎች ከሀሙስ የካቲት 5 ጀምሮ ጉብኝታችሁን ማከናወን የምትችሉ መሆኑን ከፓርኩ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ያለፈው 24 ሰዓት ከእስካሁኑ ከፍተኛ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች የተመዘገቡበት መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት WHO አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ ከ24,500 በላይ ሰዎች የተጠቁ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም 492 ደርሷል።

Photo:Worldwide የቫይረሱ ስርጭት
ምንጭ:CNN
@YeneTube @FikerAssefa
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቀረቡባቸው ክሶች ነጻ ሆኑ።

አሜሪካንን በከፍተኛ ሁኔታ ከፍሎ የነበረውና በአገሪቱ ምክር ቤት ፕሬዝዳንቱን ከስልጣን ለማስነሳት የቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ፤ ትራምፕም ነጻ ሆኑ።በፕሬዝዳንቱ ፓርቲ አባላት በበላይነት በተያዘው የአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ውስጥ በተሰጠ ድምጽ፤ ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም የቀረበባቸው ክስ 52 ለ 48 በሆነ ድምጽ እንዲሁም የአገሪቱን ምክር ቤት ሥራ በማደናቀፍ ለሚለው ክስ ደግሞ 53 ለ47 በሆነ ድምጽ ብልጫ ክሶቹ ውድቅ ተደርገዋል።

የፕሬዝዳንቱ ተቀናቃኞች የሆኑት ዴሞክራቶች ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀጣዩ ምርጫ ዋነኛ ተቀናቃኛቸው ይሆናሉ በተባሉት ጆ ባይደን ላይ ዩክሬን አጥፍተዋል ብላ ምርምራ እንድታደርግ ግፊት አድርገዋል ሲሉ ከሰዋቸው ነበር። ትራምፕ ባለንበት የፈረንጆች ዓመት ማብቂያ ላይ በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ በመሳተፍ ክስ ተመስርቶበት ምርጫ የተወዳደረ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት ይሆናሉ ተብሏል።

የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ትናንት በሰጠው ታሪካዊ ድምጽ የአሜሪካ 45ኛው ፕሬዝዳንት ከዩክሬን ጋር ባደረጉት ያልተገባ ግንኙነት ሳቢያ ከስልጣናቸው ከመባረር አትርፏቸዋል።. ትራምፕ ቀርቦባቸው ከነበሩት ክሶች በአንዱ እንኳን ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተው ቢሆን ኖሮ ስልጣናቸውን ለምክትላቸው አስረክበው ዋይት ሐውስን ጥለው መውጣት ይጠበቅባቸው ነበር።ትራምፕ ላይ የቀረበው ክስ በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት እንዲታይ ያጸደቀው በተቀናቃኞቻቸው ዴሞክራቶች የሚመራው የተወካዮች ምክር ቤት ነበር።

በቀጣዩ ምርጫ ለሁለተኛ ዙር ለመወዳደር እየተዘጋጁ ያሉት ትራምፕ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ክሱን ውድቅ እስኪያደርገው ድረስ "ምንም አይነት ጥፋት አልፈጸምኩም" በማለት ሲከራከሩ ቆይተዋል።የፕሬዝዳንቱን የምርጫ ዘመቻ ከሚመራው ቡድን የምክር ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ የተሰጠ መግለጫ እንዳለው "ትራምፕ ከቀረቡባቸው ክሶች ሙሉ ለሙሉ ነጻ ሆነዋል። እናም አሁን የአሜሪካን ሕዝብን ለማገልገል ወደ መደበኛው ሥራ የመመለሻ ጊዜ ነው" ብሏል።"ምንም ማድረግ የማይችሉት ዴምክራቶች ትራምፕን እንደማያሸንፉ ቢያውቁም፤ ይህንን ክስ አቅርበዋል" ሲል ይህ አስቀያሚና እርባና የሌለው ውጣ ውረድ የዴሞክራቶች የምርጫ ዘመቻ ታክቲክ ነው ሲል ከሷል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
በቻይና በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 563 ደረሰ!

በቻይና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ500 በላይ መድረሱ ተነገረ።በትናንትናው እለት ብቻ በሁቤይ ግዛት 70 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።ከዚህ በተጨማሪም 3 ሺህ አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች ተገኝተዋልም ተብሏል።ከዚህ ባለፈም በሆንግ ኮንግ እና ፊሊፒንስ ሁለት ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋልም ነው የተባለው።በጃፓኗ የወደብ ከተማ ዮኮሃማ ደግሞ 10 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።ከዚህ ባለፈም 3 ሺህ 700 ሰዎች ለሁለት ሳምንታ በልዩ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ ተደርገዋልም ነው የተባለው። የቫይረሱ ስርጭት አድማሱን እያሰፋ ሲሆን፥ አሁን ላይ ከቻይና ውጭ ከ260 በላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸው እየተነገረ ነው።

ምንጭ፦ ሬውተርስ/FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት ከ104 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሬያለሁ አለ፡፡

ለመፍጠር ታቅዶ ከነበረው አንፃር ማሳካት የተቻለው 93 በመቶውን እንደሆነ ከስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡የስራ እድሉን ካገኙት መካከል 83 በመቶዎቹ ወጣቶች ናቸው፡፡
ሴቶች የ45.99 በመቶ ድርሻ ሲኖራቸው የዩኒቨርስቲና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተመራቂዎች ይገኙበታል፡፡በጊዜ ማዕቀፉ ለ317 አካል ጉዳተኞች የስራ እድል ማመቻቸቱን ቢሮው በሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡ማኑፋክቸሪንግ፣ ኮንስትራክሽን፣ የከተማ ግብርና፣ ንግድ እንዲሁም አገልግሎት ዘርፉ፣ በግልና የመንግስት ተቋማት የስራ እድሉ የተገኘባቸው መስኮች ናቸው ተብሏል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የታዋቂው ስፓርታከስ ፊልም መሪ ተዋናይ ኪርክ ዳግላስ በ103 አመቱ አረፈ። ልጁ ሚካኤል ዳግላስ በኢንስታግራም ገፁ እሱና ወንድሞቹ አባታቸውን በማጣታቸው እንዳዘኑ አስፍሯል። ዳግላስ በ1960ዎቹ የሆሊዉድ ወርቃማ ዘመን ስማቸው ከሚነሳላቸው ተዋንያን አንዱ የነበረ ሲሆን 3 ጊዜ ለኦስካር ሽልማት መታጨትም ችሎ ነበር። በ1996 የህይወት ዘመን የኦስካር ሽልማትም ተበርክቶለታል።

ምንጭ:Variety
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ 120 አውቶቡሶችን ማሰማራቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ የሚታየውን የትራንስፖርት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ካስገባቸው አዲስ የአንበሳ ከተማ አውቶቡሶች 20ዎቹ በልዩ ሁኔታ የሚሰማሩ ናቸው፡፡በተለይም በከተማዋ ችግሩ ባስ ባባቸው አካባቢዎችን በመምረጥ ተሸከርካሪዎች ችግር በሚታይባቸው ስፍራዎች በተወርዋሪነት አገልግሎት እንደሚሰጡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ መልካሙ ሌሊሳ ለኢቲቪ ገልጸዋል።

በልዩ ሁኔታ አገልግሎት የሚሰጡት 20 አውቶቡሶች የትራንስፖርት ችግሩ በሚባባስበት ጠዋት ስራ መግቢያና ማታ ስራ መውጫ ሰዓት ላይ በተሻለ ሁኔታ ፈጥነው በመድረስ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡አውቶቡሶቹ ከተለመደው አሰራር ወጣ በማለትም 35 ሰዎችን በወንበር ብቻ በመጫን ሰው በሚበዛበት መገናኛ፣ ፒያሳና ሜክሲኮ መስመር ወደ ስራ መግባታቸውን አቶ መልካሙ ተናግረዋል።እንደ ቢሮው ገለጻ ተሸከርካራቹ በየመንገዱ ቆመው ሰው የሚጭኑ ሳይሆኑ በልዩ ሁኔታ ከመነሻ እስከ መድረሻቸው ቀጥታ በፍጥነት እንደሚጓዙ ባለስልጣኑ ገልጻል።

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
የኬኒያው ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ ተቃወሙ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮሮና ቫይረስ በተስፋፋበት ወቅት ወደ ቻይና ጉዞ ማድረጉ ተገቢ እንዳልሆነ የኬኒያው ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬኒያታ ተናገሩ፡፡አየር መንገዱ በዚህ ወቅት ወደ ቻይና መብረሩ ቫይረሱ አፍሪካን ወደ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡ኬኒያታ‹‹ ጭንቀታችን ቻይና ቫይረሱን ትቆጣጠረዋለች የሚለው ሳይሆን የሚያሳስበን ደካማ የጤና ሥርዓት ባለን አገራት ውስጥ እንዳይገባ ነው›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና በሚያደርገው የቀጥታ በረራ አምስት መዳረሻዎች ሲኖሩት ፤ ወደ ቤጂንግ፣ ሻንጋይ፣ ጉዋንዙ፣ ቼንጉዱ እና ሆንግ ኮንግ በረራዎቹን ማድረጉ ቫይረሱ ወደ አህጉሪቱ እንዳይገባ ስጋት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡አየር መንገዱ አሁንም ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ አላቋረጠም፡፡ትላንት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ተወልደ ገብረ ማርያም ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ወደ ቻይና በረራ ማቆም ዋስትና አይሰጥም ብለዋል፡፡ባሳለፍነው ሳምንት ኬኒያን ጨምሮ አምስት የአፍሪካ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ማቋረጣቸውም የሚታወስ ነው፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የኦነግ ሸኔ የታጠቀ ቡድን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልክ ንብረት አቃጥለው የጦር መሳሪያዎችን መዝረፋቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በክልሉ 7 ሰዎች ታግተው ተወስደዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሃሰት መሆኑንም የክልሉ ፖሊስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጧል። በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ም/ል ኮሚሽነር ነጋ ጃራ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የኦነግ ሸኔ የታጠቁ አካላት ወደ ክልሉ ገብተው ንብረት አቃጥለው እና ዘርፈው ሸሽተዋል ብለዋል።እንደ ምክትል ኮሚሽነሩ ገለጻ ድርጊቱ የተፈጠረው ጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም በአሶሳ ዞን ውስጥ ባባሲ ወረዳ ውሽማ ጥርጊጊ የሚባል ቀበሌ ላይ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 የሚባሉ ቦታዎች ነው፡፡

ከዚህ በፊት በዚህ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ 4 ሰዎች አካባቢውን ለቀው የሄዱና በኋላም የኦነግ ሸኔ ቡድን የተቀላቀሉ ነበሩ፡፡የኋላ ኋላ እነርሱን ጨምሮ ወደ 28 የሚደርሱ የታጠቁ ሀይሎች በ25/5/2012 ወደ ቀበሌው መጥተው የቀድሞውን የቀበሌ ሊቀ መንበር አቶ አደም ጉምዛ የተባለውን ግለሰብ ያገኙታል፡፡እኚህን የቀድሞ ሊቀመንበር ባገኙ ሰዓት በወቅቱ የነበራቸው ፍላጎት የጦር መሳሪያና ከዚህ በፊት የተሰበሰበ ግብር አለ እርሱን ማምጣት አለብህ ብለው በጠየቋቸው ሰዓት ምንም እንደሌለ በመንገር ይመልሷቸዋል፡፡

በኋላም የዚህን ሰውዬ 6 ቤቶች አቃጥለው 3 ኩንታል ቦሎቄ ፤ ሁለት ኩንታል ጤፍ 1 ኩንታል ጥቁር አዝሙድ ግማሽ ኩንታል ተልባና ሁለት ኩንታል ኑግ በሳት ማቃጠላቸው ተገልጿል።በዛው ቀበሌ ውስጥ ያገኙትን የኢትዮጵያና የክልሉን ሰንደቅ አላማ በማቃጠል ከሚኒሻዎችና ከግለሰቦች ላይ 3 ክላሽና 6 ኋላ ቀር መሳሪያዎችን ነጥቀው መሸሻቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡የክልሉ የፀጥታ ሀይል ወዲያው ወደ አካባቢው ያሰማራን ቢሆንም ሰዎቹን በወቅቱ ማግኘት አልቻልንም በማለት ነግረውናል፡፡

ፀረ-ሰላም ሀይሎች በባህሪያቸው አንድ ቦታ ተረጋግተው የሚቀመጡ ባለመሆናቸው የፀጥታ አካሉ ወደ አካባቢው አምርቶ አሰሳ ቢያደርግም ሊያገኛቸው ግን አልቻለም፡፡በአሁኑ ሰዓት አካባቢው ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ያሉት ኮሚሽነሩ በእኛ ግምገማ እስካሁን በማህበራዊ ሚዲያ የሚራገበው ወሬ አሉባልታ ነው ብለዋል፡፡በክልሉ የታገቱ 7 ሰዎች አሉ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ግን ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል ምክትል ኮሚሽነሩ።

በእርግጥ ንብረት ላይ ጉዳቶች አድርሰው ሸሽቷል፡፡ ከዛ ውጪ ወደ አካባቢው ያሰማራናቸው የፀጥታ ሀይሎች በቦታው ደርሰው ህዝቡን አረጋግተው ይህንን መረጃ አድርሰውናል ብለዋል፡፡ይህ ከሆነበት እለት አንስቶ የኦነግ ሸኔ አባላት ለጥቃት ወደ ክልሉ መግባታቸውን ምልክቶች ታይተዋል በመሆኑም በዚህ ፀረ-ሰላም ሀይል ላይ እርምጃ ለመውሰድና ለመቆጣጠር የክልሉ ፀረ-ሽምቅ ሀይል ፤ የክልሉ ፖሊስ ፤የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በጋራ በመሆን በአካባቢው እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ነግረውናል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፒዮ ከየካቲት 9-11 ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ፡፡ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እና ከፕሬዝዳንት ሳሕለ ወርቅ ጋር በሀገሪቱ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ፡፡ ፖምፒዮ ከአፍሪካ ሴኔጋል እና አንጎላንም ይጎበኛሉ፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የአትሌት አባዲ ሃዲስ የቀብር ስነስርዓት ተፈፀመ!

የወጣቱ አትሌት አባዲ ሀዲስ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬ እለት የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የትግራይ ክልል አትሌቲክሰ ፌዴሬሽንና ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ የክለብ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ አትሌቶች፣ የዞን አመራሮች፣ ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ በተገኙበት ከቀኑ 7፡00 ላይ በትውልድ ስፍራው ማይጨው ከተማ ልዩ ስሙ እንዳመሆኒ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡

Via EAF
@YeneTube @FikerAssefa
ሳዑዲ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የ5 አፍሪካ ሀገራት ዜጎች በ3 ወራት ውስጥ ከወጡ ቅጣታቸውን አነሳላቸዋለሁ ማለቷን ሳዑዲ ጋዜት ዘግቧል፡፡ ስደተኞቹ የፓስፖርት፣ ትራፊክ እና ሌሎች የተከማቹ ቅጣቶችና ክፍያዎች ያሉባቸው ናቸው፡፡ ሌላ ጊዜ ከተመለሱ ግን ቅጣቱ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮናን ቫይረስ ምልክት ማየቱን ቀድሞ ይፋ ያረገው (Whistleblower) ዶክተር ህይወቱ አለፈ!

ሊ ዌንሊያንግ የተባለውና ባለፈው ታህሳስ አጋማሽ ላይ የኮሮና ቫይረስን ምልክት በ7 ታካሚዎች ላይ ማየቱን ቀድሞ በዊቻት ግሩፕ ለሆስፒታሉ ማህበረሰብ በማሳወቁ በፖሊስ ክትትልና ማስፈራሪያ ደርሶበት የነበርው ዶክተር በቫይረሱ ተጠቅቶ ህይወቱ ማለፉን CNN ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የደህንነት ካሜራዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አገልግሎት እየሰጡ ነው ተባለ!

የተማሪዎችንና የግቢውን ደህንነት ለመጠበቅ በደህንነት ካሜራ የታገዘ የቁጥጥር አገልግሎት እየሰጠ እንደሆነ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመለከተ፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአገሪቱ ካሉ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ መርሀግብሮች የሚያስተምራቸው 50 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች አሉት፡፡በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተማሪዎች ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት እንደሌሎቹ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲም አለመረጋጋቶች ተፈጥረው የተወሰኑ የትምህርት ክፍሎች ስራ አቁመው የነበረ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በአደረገው ከፍተኛ ጥረት ትምህርት እንደገና መጀመሩንና ተማሪዎች ለፈተና መዘጋጀታቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ገልፀዋል፡፡

የተማሪዎችንና አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ በደህንነት ካሜራ የታገዘ የቁጥጥር አገልግሎት እየተሰጠ አንደሆነ ፕረዚደንቱ ዶ/ር አስራት ለDW በስልክ ተናግረዋል፡፡ ካሜራዎቹ በዋናነት በምግብ አዳራሾች፣ በመግቢያ በሮች፣ በተማሪዎች መማሪያና ማደሪያ ህንፃዎች፣ በቤተ መጽሐት ተገጥመው የ24 ሰዓት የቁጥጥር ስራዎችን ያከናውናሉ፣ መረጃዎችን ይሰጣሉ ብለዋል፡፡

እስካሁንም በማራኪ፣ በአፄ ፋሲልና በአፄ ቴዎድሮስ ካምፓሶች፣ አንዲሁም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 158 የደህንነት ካሜራዎች ተገጥመው አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ 100 የደህንነት ካሜራዎችን በፀዳ ግቢና በየግቢው ኮሪደሮችና በሌሎች የደህንነት ስጋት ባላባቸው ቦታዎች ለመግጠም የቅደመ ሁኔታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናችን ዶ/ር አስራት አብራርተዋል፡፡

ምንጭ: ዶይቸ ቨለ
@YeneTube @FikerAssefa
በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በዓመት ከአንድ ቢሊየን በላይ እንክብሎችና ሽሮፖችን ማምረት የሚያስችል የመድኃኒት ፋብሪካ ሊገነባ መሆኑ ተነገረ።

ዛሬ ጥር 28/2012 የመሰረት ድንጋይ የተጣለለት ይህ ፋብሪካ በ10 ሚሊዮን ዶላር መነሻ ካፒታል በአገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ባለሃብቶች በጋራ ይገነባል። አፍሪክዩር የተሰኘው ይህ የመድኃኒት ፋብሪካ ግንባታ ከ18 እስከ 24 ወራት ባለው ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሏል። ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር አንድ ቢሊዮን እንክብሎችንና ሽሮፖችን በዓመት በአንድ ፈረቃ የሚያመርት እንደሚሆን ተገልጿል። ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባም ለ109 ሰዎች የስራ ዕድል ይፈጥራልተብሎም ይጠበቃል።

ምንጭ:ፋና
@YeneTube @FikerAssefa