YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገራችን እንዳይገባ ዝግጅቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን በተመለከተ የተዘጋጀ መግለጫ

@YeneTube @Fikerassefa
የጤና ሚንስትሯ ሊያ ታደሰ በትዊተር ገፃቸው

" ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የተሳሳተ ዘገባ መዘገቡን አስታውቋለች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ የተገኘ በሰው እንደሌላ አክለው በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል" ።

@Yenetube @Fikerassefa
በደንቢዶሎ ለታገቱ ወንድም እና እህቶቻችንን ድምፅ ለመሆን የተጠራ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ አሁን እየተካሄደ ይገኛል፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለቦች የስታዲየም መገንቢያ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አስረክቧል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ከወራት በፊት ለክለቦቹ ቃል በገባው መሰረት የስታዲየም እና የስፖርት ማዕከል መገንቢያ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አስረክበዋል፡፡የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ርክክብ ወቅት ኢ/ር ታከለ ኡማ እንደገለጹት ሁለቱ ክለቦች የከተማዋ አምባሳደር ከመሆናቸውም ባለፈ በስፖርታዊ ጨዋነት እና በከተማዋ ሁለንተናዊ ሰላምን በማረጋገጥ ወንድማማችነትን በመስበክ የበኩላቸው ሚና እየተወጡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የህዳሴው ግድብ ውርስ አገኘ!

ግለሰቡ ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ካላቸው ላይ ሃብት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እንዲሰጥ ተናዘው ማረፋቸውን ተከትሎ ግድቡ ውርስ አገኘ።

ውርሱ የሀብታቸውን 10 % ሲሆን 124 ሺ ለህዳሴ ግድብ ገቢ ተደርጓል።

@Yenetube @Fikerassefa
ከአባሳደር ፍፁም አረጋ ትዋተር ገፅ የተወሰደ⬇️

ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኙ ሰልፈኞች በተወካዮቻቸው አማካኝነት የታገቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አስመልክቶ ተወያይተናል::በጽሁፍ ያቀረቡትን ጥያቄም ተቀብለናል ጥያቄውን ለመንግስት አቅርበን ምላሹን ተከታትለን እናሳውቃለን::

(Fistum Arega)
@YeneTube @Fikerassefa
Fact!!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሰሞኑን ትዊት ካደረጋቸው 10 ትዊቶች ሰባቱን ለትዊተር $ ከፍሎ ፕሮሞት ያስደርጋል።

እንዲሁም...

ሰሞኑን የተለያዩ ባለስልጣናት Facebook ላይ Verified የሆነው account ለፌስቡክ $ ከፍለው ሲያስተዋውቁ ተመልክተናል።

👉ለምርጫ ዝግጅት ይሆን?

@Yenetube @Fikerassefa
7.3 ሬ. ስ የመሬት መንቀጥቀጥ በኩባ እና በጃማይካ መካከል ከደቂቃዎች በፊት ተከስቷል።

አሁን ላይ ከ7.3 ወደ 7.7 ማደጉን ተመልክተናል።
.
.

የተሟላ መረጃ ይዘን እንመለሳለን....
@Yenetube @Fikerassefa
የመድኃኒት አምራች ኩባንያ #ጆንሰን እና #ጆንሰን ገዳይ የሆነውን የኮሮኖ ቫይረስ በሽታ ለመከላከል የሚሆን #ክትባት (መድሓኒት) እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በቅርቡ በተደረገው ቃለ ምልልስ የጆንሰን እና ጆንሰን ዋና ሳይንቲስት #ዶክተር ፖል ስቶልፍልስ በወራት ጊዜ ውስጥ ክትባቱን እንደሚፈጥሩ በሙሉ እምነት ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ፣ ለህዝቡ እስኪቀርብ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ሊወስድ ይችላል ብለዋል።

Via:- one america news
@YeneTube @Fikerassefa
ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ ላለው የፋብሪካው ማስፋፊያ 50 ሚሊዮን ዶላር ብድር አገኘ

ኮካ ኮላ የለስላሳ መጠጦች በኢትዮጵያ ለሚያደርገው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከስታንዳርድ ባንክ የ50 ሚሊዮን ዶላር ወይም አንድ ነጥብ ሰድስት ቢሊዮን ብር ብድር ማግኘጡን አስታወቀ።

ብድሩ የተሰጠው ለድርጅቱ የአፍሪካ ቅርጫፍ ኮካ ኮላ ቤቬሬጅ አፍሪካ ሲሆን ገንዘቡም የሚውለው በኢትዮጵያ የኮካ ኮላ አምራች የሆነው ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ለሚያደርገው ማስፋፊያ ነው። ድርጅቱ ብድሩ መሰጠቱን የስታንዳርድ ባንክ የግንኙነት ሃላፊ ሲሞን ሪቭስ ቢዝነስ ሪፖርት ለተባለው የደቡብ አፍሪካ ሚዲያ አረጋግጠዋል።

ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ እያስገነባ ባለው አዲሱ ፋብሪካው ላይ እስካሁን ሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር (70 ሚሊዮን ዶላር) ወጪ ያወጣ ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅ የማምረት አቅሙን 70 ሺህ ካሳ(ሳጥን) ያሳድጋል።

Via:- Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንበራ ወረዳ ሰሞኑን በነበረ ግጭት አንድ ሕጻንና 4 ሴቶችን ጨምሮ 8 ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ ገለጸ። አንድ ሰው የደረሰበት አልታወቀም የግጭቱ መነሾ ባይገለጽም 20 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ምንጭ:- እሸት በቀለ
@Yenetube @FikerAssefa
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽኅፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ጥር 20/2012 ከሰዓት በኋላ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታወቀ::

via:- Addis Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
«ጠቅላይ ሚንሥትሩ ስለልጆቻችሁ እንጠይቃችኋለን ብለውን ወደ አዲስ አበባ እየሄድን ነው።»

የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ልጆቻቸው ከታገቱባቸው ወላጆች መካከል ሦስቱ ወደ አዲስ አበባ ተጠርተው በአውቶቡስ በመጓዛ ላይ መኾናቸውን ለዶይቸቬለ (DW) ተናገሩ። ከሦስቱ ወላጆች ሁለቱ ከሰሜን ጎንደር አንደኛው ደግሞ ከደቡብ ጎንደር የተነሱ ሲኾን፤ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ከሚኖሩበት ዞኖች ጽ/ ቤቶች ተደውሎ የተነገራቸው ሰኞ ዕለት መኾኑንም ገልጠዋል። ከወረዳ፦ ዞን፤ ከዞን ወደ አዲስ አበባ ትሄዳላችሁ ተብለው እንደተጠሩ እንጂ ዝርዝር ነገር እንዳልተነገራቸውም ተናግረዋል።

«ሂድ አሉኝ፤ ምነው ምን ላደርግ ነው የምሄደው? እንዴት ነው፤ ልጆቹን ልናገኝ ነው ወይንስ ምንድን ነው? ገንዘብ የለ፤ እኛ ገበሬዎች ገንዘብ ከየት እናገኛለን ያን ያኽል ሀገር በማናውቀው ሀገር የምንሄድ ብዬ በምልበት ሰአት» ሲሉ በአስቸጋሪ ኹኔታ እየተጓዙ መኾኑን መሪ ጌታ የኔነህ አዱኛተናግረዋል። የተሰጣቸው መልስም፦ «አያይ ለአኹኑ ከዚህ አካባቢ ቤተሰብ ካለ ከጎንደር ያለ ገንዘብ ትንሽ ያዝ እና መድረሻ ያዝና ከዚያ ወዲያ እነሱ ነው የሚከፍሉት፤ የመጣችሁበትን አበል ይቆርጣሉ እና ሒድ ዝም ብለህ» እንደተባሉም አክለዋል። «ምናልባት ልታገኝ ትችላለህ የሚሉት ዐይታወቅም ሲሉኝ፤ መቼም እንግዲህ የጠፋው ችግር ነው፤ እማገኝ እና እናቲቱ ደግሞ የማረጋጋ መስሎኝ ላመጣልሽ በሚል ደረጃ ወጥቼ ወደዚያው እየኼድኩ ነኝ» በሚል ተስፋ ሰንቀው እየተጓዙ መኾናቸውን ገልጠዋል።

ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አዲስ አበባ ሲደርሱ ተቀባይ እናዳላቸው እና በተስፋ ልጆቻችንን እናገኛለን ብለው ረዥሙን እና አስቸጋሪውን ጉዞ በአውቶብስ መያያዛቸውን ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል።

ምንጭ:- Dw
@YeneTube @Fikerassefa
የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ተጣርቶ ቢገለጽ ጥሩ ነው ሲል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፓርላማ ምላሽ ሰጠ!

በርካታ ኢትዮጵያውያንን እያነጋገረና እያስጨነቀ የሚገኘውን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መታገት አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጥ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተጠየቀው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣ የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ‹‹ተጣርቶ ቢገለጽ ጥሩ ነው፤›› የሚል ምላሽ ሰጠ።

ተጨማሪ👇👇👇👇
https://telegra.ph/attorney-01-29
በመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ የተመራ ልዑክ በፈረንሳይ ጉብኝት እያደረገ ነው!

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ልዑክ በፈረንሳይ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።በአየርና በባህር ሃይል ዘርፎች ስልጠና እንዲሁም የወታደራዊ ቁሳቁስ አቅርቦትን አስመልክቶ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የጉብኝቱ አላማ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የደምቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን አስመልክቶ ስለ አጋቾቹ ማንነትና በመንግስት ስለተወሰደው እርምጃ፣ ለህዝብ የተሰጠው መረጃ ምልዑነት የጎደለውና እጅግ የዘገየ ነበር

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም

@YeneTube @Fikerassefa