This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መንግስት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ የኢትዮያ ሶሻል ደሞክራቲክ ፓርቲ ኢሶዴፓ አሳሰበ፡፡
Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
በአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ ክ/ከተማ የሚገኘው ሶሎ የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ባለፈው ቅዳሜ ከ25 በላይ የተደራጁ ወጣቶች ወደ ት/ቤቱ በመዝለቅ ርዕስ መምህሩን ጨምሮ ስምንት መምህራን በድብደባ ጉዳት በማድረሳቸው ከ1,000 በላይ ተማሪዎች ያሉት ት/ ቤት ዛሬ ድረስ ዝግ መሆኑን ከአስተማሪዎቹ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል።
መምህራኑ ህክምና አግኝተው በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ተነግሮኛል። መምህራኑ ወንጀለኞቹ ተያዘው ለህግ ይቅረቡ ብለው ለፓሊስ አመልክተዋል።
Via:- ተስፋዬ ጌትነት
@YeneTube @Fikerassefa
መምህራኑ ህክምና አግኝተው በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ተነግሮኛል። መምህራኑ ወንጀለኞቹ ተያዘው ለህግ ይቅረቡ ብለው ለፓሊስ አመልክተዋል።
Via:- ተስፋዬ ጌትነት
@YeneTube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጀዋር መሐመድ ዛሬ ከሰዓት በመኖሪያ ቤቱ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ትናንት እኩለ ለሊት ላይ በመኖሪያ ቤቱ ተፈጽሟል ስላለው ጉዳይ እና ምልከታውን ለቢቢሲ አጋርቷል::
BBC አማርኛ
@YeneTube @Fikerassefa
BBC አማርኛ
@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት ምክኒያት የሆነው አቶ ጀዋር መሀመድ በፌስቡክና በቴሌቪዥን ያስተላለፈው እጅግ ኃላፊነት የጎደለው ቅስቀሳ ስለሆነ በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ህዝብ #ይቅርታ እንዲጠይቅና በወንጀል ሊጠየቅ ይገባል ብሏል እስክንድር ነጋ።
እስክንድር ነጋ ለኢሳት ቴሌቪዥን ከትናገረው የተወሰደ
@YeneTube @Fikerassefa
እስክንድር ነጋ ለኢሳት ቴሌቪዥን ከትናገረው የተወሰደ
@YeneTube @Fikerassefa
የኦሮሞ ህዝብ የለውጡ ተጠቃሚ እንዲሆን የኦሮሚያ ፖሊስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ይከፍላል- የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
የኦሮሞ ህዝብ የለውጡ ተጠቃሚ እንዲሆን የኦሮሚያ ፖሊስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ እንደሚከፍል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚነሽነር ከፍያለው ተፈራ ገልጸዋል፡፡ኮሚሽነሩ ትናንት ምሽት በአክቲቪስት ጀዋር መሐመድ ላይ የተከሰተው ጉዳይ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ የኦሮሚያ ፖሊስ እንደ ጀዋር መሐመድ ላሉና የኦሮሞ ህዝብ ዓይን ለሆኑ ግለሰቦች ጥበቃ በማድረግ ኦሮሚያ የተረጋጋች እንዲትሆን ይሰራል ብለዋል፡፡ ኮሚሽነሩ የተከሰተው ችግር ካለመናበብ የተነሳ መሆኑን ጠቅሰው፣ ችግሩ እንዲባባስ ያደረጉ አካላት እንዳሉም ተናግረዋል፡፡የኦሮሚያ ፖሊስ የኦሮሞ ህዝብ ጋሻ ነው ያሉት ኮሚሽነር ከፍያለው፣ የኦሮሞ ህዝብ የለውጡ ተጠቃሚ እንዲሆን የኦሮሚያ ፖሊስ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ሁሉ እንደሚከፍል ገልጸዋል፡፡
የኦሮሚያ ፖሊስ የኦሮሞ ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት እንዳይጠበቅ እንቅፋት ለመሆን የሚሞክሩ አካላትን ለፍርድ ለማቅረብ እንደሚሰራ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡በአሁኑ ሰዓት በሁሉም አከባቢዎች መረጋጋት መፈጠሩን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡የተፈጠረውን ጉዳይ ለማረጋጋት እየሰሩ የዋሉ የኦሮሞ ህዝብ፣ ቄሮዎችና ቀሬዎችን አመስግነዋል ኮሚሽነሩ፡፡ኮሚሽነሩ የተፈጠረው ችግርን ተከትሎ ለጠፋው የሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡ህዝቡ ከጸጥታ አካላት ጎን በመሰለፍ ሰላሙን መጠበቅ እንዳለበት ኮሚሽነር ከፍያለው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa

በማህበራዊ መገናኛ በቲውተር እና በፌስቡብ ላይ #IStandwithabiy (እኔ አብይን ጎን ቆማለው) እና #IStandwithJawar (እኔ ከጅዋር ጎን ቆማለው) የሚሉ ሀሽ ታግ ሰው ሀሳቡን እየገለፀ ይገኛል።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
ግብጽ እና ኢትዮጲያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ የጀመሩት ድርድር ካልተሳካ ወታደራዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ግፊት ማድረጋቸወን ቀጥለዋል።
አምስት ቢሊየን ዶላር እንደሚፈጅ በተነገረለት እና ሰባ በመቶም ግንባታው በተጠናቀቀው ግድብ ዙሪያ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተደረገው ውይይት ያለስኬት ተጠናቋል፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ ለአንድ መቶ ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልገውን የኤሌክትሪክ ሃይል ፍላጎት እንደሚያሟላ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ከኢትዮጲያ ተቃራራቢ የሕዝብ ብዛት ያላት ግብፅ የግድቡን የውሃ ማጠራቀሚ የመሙላት ሂደት የግብጽን የውሃ ድርሻ ይቀንሰዋል የሚል ስጋት አላት፡፡
የእስራኤሉ ዘ ታየምስ ኦፍ አስራኤል የተሰኘው የህትመትና የድረገጽ ሚዲያ ሰፋ አደርጎ ባወጣው ሀተታ ለመንግስት ቅርበት እንዳለው የሚነገርላቸው የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ግድቡ ለግብጽ ብሔራዊ ደህንነት ስጋት ስለሆነ መንግስት ወታደራዊ እርምጃ ሊወስድ ይገባል በማለት ግፊት እያደረጉ ይገኛል፡፡የግብፅ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ ባለፈው ወር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባደረጉት ንግግር ኢትዩጵያ ግድቡን ያለስምምነት እንድትሞላ ፈጽሙ አንፈቅድም” ማለታቸው ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያን የመልማት መብት አምነን የምንቀበል ቢሆንም የአባይ ወንዝ ውሃ ለግብፅ የህልውና ጥያቄ ነውም ብለዋል፡፡የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተመሳሳይ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር “የአባይ ወንዝ አጠቃቀም መወሰን ያለበት በዓለም አቀፍ ሕግ እና የተፈጥሮ ሀብቶችን በፍትሃዊ መንገድ በመጠቀም መርህ ነው” ብለዋል ፡፡
ግብፅ የዓባይ ወንዝ ከፍ ያለውን ድርሻ እየተጠቀመች ነው በሚል የላይኛው ተፋሰስ ሃገራት ኢትዮጲያ እና ሱዳን ለዓመታት ሲያቀርቡ የነበረውን ቅሬታ የምትሞግተው በብሪታኒያ የቅኝ ግዛት ዘመን የተፈጸሙ ስምምነቶችን በማጣቀስ ነበር ፡፡በዚህ ወር መጀመሪያ ያለስኬት የተጠናቀቀው ውይይት እ.ኤ.አ. ከ 2014 በኋላ ለሶስተኛ ጊዜ የተከናወነ ነበር ፡፡
አንድ የግብጽ ባለስልጣን ከአሶሺየትድ ፕሬስ ጋር ባደረጉት ቆይታ “ጊዜያችንን ትርጎም በሌላቸው ውይይቶች አናጠፋም ፡፡ ሁሉም አማራጮች ጠረጴዛው ላይ አሉ፡፡ምርጫችን ግን ድርድር እና ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው” ማለታቸውም ተነግሯል ፡፡ግብፅ በዓለም አቀፍ አሸማጋዮች ከተሻለ ስምምነት እደርሳለሁ በሚል ጉዳዩን ወደ አሜሪካ ሩሲያ ፣ ቻይና እና አውሮፓ ህብረት ወስዳዋዋለች፡፡
ዋይት ሀውስ “አንዳቸው የሌላውን የናይል የውሃ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት መብት በማክበር ከዘላቂ ስምምነት ለመድረስ የሚያደርጉትን ውይይት እንደሚደግፍ” በዚህ ወር መጀመሪያ አስታወቁል፡፡የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን መሃመድ ኢል ሞላ ኢትዮጵያውያን ዓለም አቀፍ ሽምግልናን ካልተቀበሉ ጉዳዩን ለተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እንደሚወስዱ ተናግረዋል ፡፡በብራስልስ መሰረቱን ያደረገ አንድ የዓለም አቀፍ ቀውስ ላይ አሰላሳይ ቡድን ፣ “የሁለቱ አካላት የመዳረሻ ወንዝ አስተዳደር ላይ ካልተስማሙ ለወደፊቱ ግጭት የመጋለጥ እድላቸው ሰፊና ከባድ ሊሆን ይችላል” ሲል በዚህ ዓመት መጀመሪያ ቀደም ብሎ አስጠንቅቆ ነበር፡፡
ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በግብፅ ተቃዋሚ መንግስት ሚዲያዎች እና አንዳንድ ተንታኞች መንግስት በጉዳዩ ላይ በኃይል እንዲቀሳቀስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ለዕለታዊ ጋዜጣ ኤል-ሾሮክ ታዋቂው አምድ አዘጋጅ የሆኑት አብደላ ኤል-ሴናው እንደተናገሩት ብቸኛው አማራጭ አለመግባባቱን ዓለም አቀፍነት በማረጋገጥ ወይም ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ላይ ነው ብለዋል ፡፡በእሁዱ እትም ላይ “ግብፅ አነስተኛ ግዛት አይደለችም” ሲል ጽፏል ፡፡ ሁሉም ዲፕሎማሲያዊ እና ህጋዊ አማራጮች ከከሸፉ ወታደራዊ ጣልቃገብነት አስገዳጅ ሊሆን ይችላል ሲልም አስፍሯል ፡፡
የአል-ማሳሪ አል-ዮየም ጋዜጣ የቀድሞው አምደኛ አንዋር ኤል ሃውሪር ግብፅ በሲና ባሕረ ገብ መሬት ድንገተኛ ጥቃት ከፈፀመችበት የ 1973 ዮም ኪፑር ጦርነት ጋር በማነፃፀር ፡፡በፌስቡክ ገጹ ላይ “ሲናን ለመልቀቅ ከታገልን ውሃውን ነፃ ለማውጣት መዋጋት ምክንያታዊ ነው” ሲል ጽፏል ፡፡ በሁለቱ ጉዳዮች ላይ “አደጋው ተመሳሳይ ነው ፡፡ የመጨረሻው ምላሽ ደግሞ ጦርነት ነው ይላል፡፡ግብጽ በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡ ዙሪያ መውሰድ ስላለባት እርምጃ ለማማከር የተቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ዛሬ የመጀመሪያውን ስብሰባ እንደሚያደረግ ይጠበቃል።
ፕሬዘዳነት አልሲሲ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ መውሰድ ስለሚገባቸው እርምጃዎች የሚያማክረው ቡደን ባሳለፍነው እሁድ አመሻሽ የመጀመሪያውን ስብሰባ ማድረጉ ይታወሳል።ይህ ቡድን የግብጽን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ ይጋፋል በሚል ከአንድ ሳምንት በፊት ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ ብሄራዊ አማካሪ ምክር ቤት ነው።የዚህ ቡድን ዋና አላማ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ የግብጽን ታሪካዊ የውሃ ድርሻ የሚጎዳ በመሆኑ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ የግብጽን ጥቅም ለማስበር መውሰድ ስለሚኖርባቸው እርምጃዎች ማማከር መሆኑ ተገልጿል።ነገ በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ ለሚካሄደው የአፍሪካ ሩሲያ ጉባኤ ላይ ለመታደም ወደ ስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር ከጉባኤው ጎን ለጎን በህዳሴው ግድብ ቀጣይ ድርድር ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
Via Ethio FM

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቱርክ ላይ ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ አነሱ!
አሜሪካ ከዘጠኝ ቀን በፊት ቱርክ ሰሜን ሶሪያ ላይ ጥቃት በመክፈቷ ምክንያት ጥላው የነበረውን ማዕቀብ ማንሳቷን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ። "እኛን የማያስደስተን ነገር እስካልተፈጠረ ድረስ ማዕቀቡ ይነሳል" ነበር ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በንግግራቸው።
-BBC
@YeneTube @FikerAssefa
አሜሪካ ከዘጠኝ ቀን በፊት ቱርክ ሰሜን ሶሪያ ላይ ጥቃት በመክፈቷ ምክንያት ጥላው የነበረውን ማዕቀብ ማንሳቷን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ። "እኛን የማያስደስተን ነገር እስካልተፈጠረ ድረስ ማዕቀቡ ይነሳል" ነበር ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በንግግራቸው።
-BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የቤጉህዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የአመራር ሹመትና ሽግሽግ አካሂዷል።
የቤጉህዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በየደረጃው ባሉ ክፍት ቦታዎች ላይ የአመራር ሹመትና ሽግሽግ አካሂዷል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
1. አቶ አካሻ እስማኤል ማዕድን ሀብት ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
2. አቶ ዩሱፍ አልበሽር የብዙሃን መገናኛ ዋና ዳይሬክተር
3. አቶ አድማሱ ሞርካ የአካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ አጥናፉ ባቡር የንግድና ኢንዱስትሪ ም/ል ቢሮ ኃላፊ
5. አቶ ሀሩን ኡመር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
6. አቶ አብዱልፈታ አብዱራሂም የጤና ጥበቃ ምክትል ቢሮ ኃላፊ
7. አቶ ሀሰበላ አዜን የሲቭል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
8. አቶ አትንኩት ሽቱ የባህልና ቱሪዝም ምክትል ኃላፊ
9. ወ/ሪት አስካለች ተሰማ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ምክትል ኃላፊ
10. አቶ ቱጃኒ አደም የግብርና ኮሌጅ ምክትል ዲን አድርጎ በማደራጀት ስብሰባውን ያጠናቀቀ ሲሆን የዞንንና የወረዳን በቀጣይ የምንገልፅ ይሆናል፡፡
ምንጭ፡- BGPDP CC office

አቶ ኃይለማርያም በስልጣን ዘመናቸው የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናገሩ!
የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዶይቼ ቬለ (DW) ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሚተላለፈው “ኮንፍሊክት ዞን” ከተባለ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “አምባገነን ተብዬ ልጠራ አይገባኝም” አሉ።የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ስለተፈጸሙ ግድያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የሙስና ወንጀሎች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በወቅቱ በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ አሁን ያለው ለውጥ እንዲመጣ የራሴን ድርሻ ተወጥቻለሁ” ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር፤ “እኔን አምባገነን አድርጎ መሳል ትክክል አይደለም” ብለዋል።
Via EPA

ሁለት የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪዎችን ለማስገባት ዓለም አቀፍ ጨረታ ሊወጣ ነው።ከሚያዝያ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ ሦስት የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች እንደሚኖሩ የኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ባልቻ ሬባ (ኢንጂነር) ገልጸዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ
👇👇👇👇👇
https://telegra.ph/telecom-10-24
ዝርዝር ዘገባውን ያንብቡ
👇👇👇👇👇
https://telegra.ph/telecom-10-24
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በህዳሴዉ ግድብ ዙሪያ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ጋር ተወያዩ።
በሩሲያ አፍሪካ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ሁለቱ መሪዎች ከጉባዔዉ ጎን ለጎን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ እንደሚገኙ ታዉቋል፡፡የሁለቱ መሪዎች ዋነኛ የዉይይት አጀንዳ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደሆነም ተነግሯል፡፤ግብፅ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዉሃ አሞላል እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በሚመለከት አዲስ ሃሳብ ይዛ መምጣቷ የሚታወስ ሲሆን ኢትዮጵያ ግን ይህን እንዳማትቀበል ነዉ ያስታወቀችዉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት እንዳስታወቁት ግብፅ በህዳሴው ግድብ በያዘችው አቋም ዙሪያ ከፕሬዝዳንት አልሲሲ ጋር እንደሚወያዩ መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ለድርድር እንደማታቀርብ ነዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሰመሩበት፡፡ሁለቱ መሪዎች በግድቡ ዙሪያ መስማማት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል፡፡
ምንጭ:የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በማህበራዊ ሚዲያ ብዙዎች እየተቀባበሉት የሚገኙትና አሁን ያለው ሁኔታ በቀጣዩ የሀገር ተረካቢ ላይ እያሳደረ ያለውን/ሊያሳድር የሚችለውን ተጽዕኖ የሚያሳይ ፎቶ።
Photo Credit: Aklile T Tesfaye(BCAA)
@YeneTube @FikerAssefa
Photo Credit: Aklile T Tesfaye(BCAA)
@YeneTube @FikerAssefa
በአዳማ ከተማ የገበያ ማዕከል የተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ።
በከተማዋ በተለምዶ ፍራንኮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የገበያ ማዕከል ላይ ዛሬ ንጋት ላይ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ 30 በላይ አነስተኛ ሱቆች ላይ ጉዳት አደረሰ።የከተማ አስተዳደሩ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ኃላፊ አቶ ጉታ ኃይሌ እንደገለጹት ዛሬ ንጋት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ 24 አነስተኛ ሱቆች ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን 10 የሚሆኑት ደግሞ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የአደጋውን መከሰት ተከትሎ ሁለት የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች ተሰማርተው በአካባቢው ከሚገኙ የጸጥታ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስረድተዋል።አደጋው በሰዎች ላይ ምንም ጉዳት እንዳላስከተለ የገለጹት ኃላፊው በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠንና የቃጠሎው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምንጭ: ኢዜአ/ኢፕድ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ በሰኔ 15 በባለስልጣኖች ግድያ ተጠርጥረው አዲስ አበባ በአደራ ቁጥጥር ስር የሚገኙት ተጠርጣሪዎች በዋስ ወይንም ያለዋስ መለቀቅ እንዳለባቸው አሳስቧዋል!
‹‹ታሳሪዎቹ ከ 3 - 4 ወር ያህል የፖሊስ ምርመራን ለማጠናቀቅ በሚል በእስር የቆዩና በአሁኑ ወቅት በሕግ የሚፈቀደው የተጨማሪ ምርመራ ጊዜ በአብዛኛው የተጠናቀቀ እና ቀሪውም በመጠናቀቅ ላይ ያለ በመሆኑ ከዚህ በላይ ታሳሪዎቹ በእስር ሊቆዩ ስለማይገባ እንደየአግባቡ #በዋስ ወይም ያለዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ወይም ተዓማኒ የሆነ ክስ በመደበኛው የወንጀል ሕግ መሰርት ሊቀርብ ይገባል›› በማለት ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡
ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ👇👇👇
https://telegra.ph/Sene15-10-24

ዛሬ ዶዶላ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለፀ!
በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ዛሬ በነበረ ግጭት አራት ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ለቢቢሲ ተናገሩ።ትናንት በአካባቢው ከጠዋት ጀምሮ ሠልፍ እንደነበር የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከሰዓት በኋላ ግን ይህ ሠልፍ መልኩን መቀየሩን ይናገራሉ። ሜዲካል ዳይሬክተሩ ትናንት ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መምጣታቸውንና ሕይወታቸው ማለፉን ገልፀው፤ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ሦስት ሰዎች ደግሞ ምሽቱን ወደ ሻሸመኔና ሀዋሳ ለህክምና መላካቸውን ገልጸዋል።
በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ ለቢቢሲ እንደገለፁት የዛሬው ግጭት ሊቀሰቀስ የቻለው "ከሁለት ወር በፊት አንድ ወጣት መሳሪያ በመተኮሱ ለእርሱ በቀል ነው" ሲሉ ይናገራሉ።በወቅቱ ምንም አይነት ጉዳት ባይደርስም ትናንት ሰልፉን ተከትሎ ግን ግጭት ተከስቶ ሰዎች መጎዳታቸውን፣ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ ሱቆች መዘረፋቸውን ማየቱን ይናገራል።ዛሬ ማለዳ በአካባቢው ግጭት መቀስቀሱንም አረጋግጠው አራት ሰዎች በዱላ ተመትተው ወደ ሆስፒታል እንደመጡና ሕይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል። በዶዶላ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ እንደሚናገሩት ግጭቱ የተከሰተው 02 ቀጠና አምስት በመባል በሚታወቀው ስፍራ ሲሆን ስድስት ቤቶች መቃጠላቸውንና ከብቶች መዘረፋቸውን እንዲሁም የንግድ ሱቆች መቃጠላቸውንና መዘረፋቸውን ይናገራሉ።
ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የሚናገሩት ነዋሪው የዛሬው ግጭት ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ሳይሆን እርስ በእርስ የደረሰ መሆኑን ይናገራሉ። በአካባቢው ያለው ችግር ከፖሊስ ቁጥጥር በላይ ነው የሚሉት ግለሰቡ መከላከያ ገብቶ ሁኔታዎችን ማረጋጋቱን ይናገራሉ።ሁኔታው አስፈሪ ስለነበር ለሕይወታቸው የሰጉ ሰዎች በአካባቢው በምትገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው አንደሚገኙ ተናግረዋል።"እነዚህ ወደ ሆስፒታላችን የመጡ ናቸው" የሚሉት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ሌሎች የሞቱ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል ወሬ ከአካባቢው ማህበረሰብ መስማታቸውን ይገልጻሉ።
ዛሬም ተጎድተው ወደ ሆስፒታላቸው ከመጡ መካከል አንድ ግለሰብ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሀዋሳ መላኩን ዶ/ር ቶላ ገልፀው በአሁኑ ሰዓት ወደ ከተማዋ የመከላከያ ሠራዊት መግባቱን ተናግረዋል።ቢቢሲ ያነጋገራቸው የአካባቢው የአካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊት ወደ በስፍራው መግባቱንና የተፈጠረውን ግጭት ለመቆጣጠርና ህብረተሰቡን እያረጋጋ መሆኑን አረጋግጠውልናል። ከጃዋር መሐመድ ጥበቃዎች መነሳት ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ትናንት በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተካሄዱ ሰልፎችን ተከትሎ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ይታወሳል።
Via BBC

ኦነግ መግለጫ አውጥቷል!
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና ዳይሬክተር በሆነው ጀዋር መሐመድ ላይ ከትናንት በስቲያ ለሊት "የጥቃት ዛቻ እና ማስፈራሪያ" የፈጸሙት የፌደራል መንግሥት አካላት ናቸው ሲል ከሰሰ። ግንባሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ለመጣው የፖለቲካ ለውጥ ጉልህ ሚና የተጫወቱ የሕብረተሰብ ክፍሎች «ተገቢዉን መብት፣ ክብርም ሆነ እዉቅና ተነፍጓቸዋል» ብሏል።ኦነግ መግለጫውን ያወጣው የማክሰኞ ለሊቱን ክስተት ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ከተሞች ተቃውሞ ከተቀሰቀሰ በኋላ ነው። ተቃውሞው ጅማ፣ ቢሾፍቱ እና አምቦ ከተሞችን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎችም ዛሬም ቀጥሏል።
ትናንት በሐረር እና በአዳማ ከተሞች በነበሩ የተቃውሞ ሰልፎች አምስት ሰዎች መገደላቸውን ዶይቼ ቬለ (DW) ከባለሥልጣናት እና የዐይን እማኞች አረጋግጧል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ «የጀዋር መሐመድን ጠባቂዎች ለማንሳት የተፈጸመው ተግባር በማንኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው፤ ድርጊቱ በመንግሥት የማይታወቅ ነው» ብለዋል።ኦነግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ «ሕዝባችን የብዙ ሺህዎች ዉድ ልጆቹን ህይወት፣ ደምና አጥንት ገብሮ ያስገኘዉ ለዉጥ በአግባቡ እየተስተናገደ አይደለም» ሲል ከሷል። «እንደ ግለሰብም ሆነ በቡድን ወይም በድርጅት ታግለው በከፈሉት መስዋዕትነት ይህንን ዛሬ የምናየዉን ለዉጥ እንዲመጣ ያስቻሉት የሕብረተሰቡ ክፍሎች ተገቢዉን መብት፣ ክብርም ሆነ እዉቅና ተነፍጎ ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ» ሆነዋል ብሏል ኦነግ።
ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ምኒስትር ከሆኑ በኋላ «በሕዝባችን ላይ የሚደርስ እሮሮ በይበልጥ እየከፋ፣ ፍትሃዊ ጥያቄዉ እና ድምጹም ከምንጊዜዉም በላይ እየተናቀ እና ወደጎን እየተተወ መጥቷል» ሲል ኦነግ በመግለጫው አትቷል። «ሕዝባችን የዘመናት ትግሉን ውጤት በዜሮ አባዝቶ፣ ትግሉንም ወደኋላ ለመመለስ የሚኬደዉን ይህንን አስጸያፊ ሁኔታ እና አካሄድ በምንም ተዓምር ዕድል» አይሰጥም ሲልም አስጠንቅቋል። ኦነግ «ይህ ሁኔታ በጊዜ ካልታረመና ከቀጠለ እስካሁን ካደረሰዉ ጉዳት እና የሰላም መደፍረስ ይልቅ የወደፊት አቅጣጫዉ እና የሰነቀዉ ጥፋት የሚያሰጋ ሆኖ ይታየናል» ሲል የሁኔታውን አሳሳቢነት ጠቁሟል።
Via DW