YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አክቲቪስት ጅዋር መሀመድ ከአልጀዚራ ጋር ቃለ ምልልስ እያደረገ ይገኛል መረጃዎች እንደደረሱን ወደ እናንተ እናጋራለን።

ጅዋር መሀመድ #Oromo_First የሚለሁን ስሎጋን ለመጀመርያ ጊዜ በዚህ ጣቢያ ማሰማቱን ይታወሳል።

--ከስፍራው የምትልኩልን አለም አቀፍ ጋዜጠኞች እናመሰግናለን🙏🙏
@YeneTube @Fikerassefa
YeneTube
#ሐረር አራተኛ የተባለ ቦታ ጎማዎች እየተቃጠሉ መንገድዶች ተዘግተዋል ነዋሪዎች ሰልፍ እያደረጉ ይገኛል። @YeneTube @Fikerassefa
ሀረር ከተማ ከጠዋት አንፃር አሁን ላይ ወደ ቀድሞ ሰላሟ ተመልሳለች ነገር ግን እንቅስቃሴ ምንም የለም ማለት ይቻላል።

@YeneTube @Fikerassefa
በሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እንዳይሸከረከር በሞተር ሳይክል ላይ የተጣለው የሰዓት ገደብ ተነሳ!

በሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እንዳይሸከረከር በሞተር ሳይክል ላይ የተጣለው የሰዓት ገደብ መነሳቱን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ኢዮብ አቢቶ በሰጡት መረጃ መሰረት ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ እንዳይሽከረከር የተጣለው የሰዓት ገደብ ተነስቶ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት መፈቀዱ ተገልፃል፡፡ የሞተር ሳይክል ተጠቃሚ ህብረተሰብ በተለያየ መድረክ የተጣለው የሰዓት ገደብ እንዲነሳ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ እንደነበረ ኮማንደሩ ገልፀው የሀዋሳ ከተማ በዚህ ወቅት የተሻለ ሰላም መሰፈኑን ተከትሎ ከኮማንድ ፖስት ጋር በመናበብ መፈቀዱን ተናግረዋል፡፡ከምሽቱ አራት ሰዓት በኋላ የሶስት እግር ተሸከርካሪን ጨምሮ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር እንደማይቻል ገልጸው መንጃ ፍቃድ ፣ሰሌዳና ሶስተኛ ወገን ባለጠፉ ተሸከርካሪዎች ላይ ሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናከሮ እንሚቀጥል ኮማንደር ኢዮብ አቢቶ ተናገረዋል፡፡

Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
#BreakingNews

"ጃዋር መሀመድ በሚቀጥለው ምርጫ እንደሚሳተፍ/እንደሚወዳደር ከደቂቃዎች በፊት ሰምቻለሁ!"

-የAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት

@YeneTube @FikerAssefa
አሰላ⬆️

ትኩረት ለአሰላ አካባቢ ሊሰጥ ይገባል የተፈጠረዉ ዉዝግብ ወደ #ሌላ ( የሀይማኖት) መልክ እየያዘ ነው። የሚመለከተው አካል ይድረስላቸው ለአሰላዎች።

@Yenetube @Fikerassefa
በሕገወጥ መንገድ የእንስሳት የጠረፍ ንግድ ላይ ያላግባብ የሚጓጓዙትን እንሰሳትን ለማስቀረትና ጠረፍ ላይ የሚገኘውን ኳራንቲ በማጠናከር ከጎረቤት አገር ሱዳን ጋር በጋራ መስራት የሚቻልበትን አሰራር ለመዘርጋት የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ኡመር ሁሴን ከሱዳኑ አቻቸው ጋር ተወያይተዋል።ከጎረቤት አገር ጋር በጋራ የሚሰሩ ስራዎች የጋራ እደገትንና ተጠቃሚነትን ስለሚያመጣ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ሚኒስቴሩ ገልጸዋል።

Via:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክለር ኃይልን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል የሚያስችላቸውን የኹለትዮሽ ስምምነት ዛሬ ጥቅምት 12/2012 በሩሲያ ሶቺ ተፈራረሙ።የኹለትዮሽ ስምምነቱ በሩሲያ ሶቺ እየተካሄደው ካለው የአፍሪካ ሩሲያ የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ሲሆን የስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጌታሁን መኩሪያ(ዶ/ር) ፈርመዉታል።

Via:-ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ትብብር ገምጋሚ ቡድን “ከደካማ የድንበር ዘለል የፋይናንስ ቁጥጥርና ክትትል ዝርዝር” (ICRG) ክትትል ሒደት መውጣቷን የሰላም ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።ኢትዮጵያ ከዝርዝሩ መዉጣት የቻለችዉ የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት በመዘርጋቷ እንደሆነ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተናግሯል።

Via:- ዋልታ
@Yenetube @Fikerassefa
ጀርመን ለኢትዮጵያ የ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የእርዳታ ለመስጠት ስምምነት ተፈራረመች።

ገንዘቡ በኢትዮጵያ ያለውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ለማሳደግ፣ የስራ ፈጠራን ለማስፋት እንዲሁም ከስደት የተመለሱ ዜጎችን ለማቋቋም እንደሚዉል ተገልጿል።በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ሪታ ዋግነር በበኩላቸው የጀርመን መንግስት በቀጣይ ከኢትዮጵያ መንግስትና ሕዝብ ጋር በቅርበት ይሰራል ብለዋል።ጀርመን በቀጣይም አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ለመደገፍ ቃል መግባቷንም ተናግረዋል።

Via:- ኢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
ጥቅምት 11/2012 ሌሊት በአክቲቪስት ጀዋር መሃመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በአምቦ በተቀሰቀሰዉ ግጭት ምክንያት አምስት ሰዎች በጥይት እንደተመቱ የአከባቢዉ ነዋሪዎች የተናገሩ ሲሆን ሕክምና ለማግኘት ወደ አምቦ ሆስፒታል የተወሰዱት ግን ሶስት ሰዎች ብቻ መሆናቸዉን የአምቦ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ደበበ ፈጠነ ተናግረዋል።ለተቃውሞ የወጡትን ሰዎች ለመበተን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ መጠቀማቸዉ የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግሯል።

Via:- ቢቢሲ
@Yenetube @Fikerassefa
ራሳቸውን “ቄሮ” ብለው የሚጠሩ ወጣቶች በአዲስ አበባ፣ አዳማና ሌሎች ከተሞች እና የአዲስ አበባ-ሀዋሳ መንገድን በድንጋይ መዝጋታቸውን የተለያዩ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ ክልሉን ከአዲስ አበባ የሚገናኑ አብዛኛዎቹ መንገዶች ዝግ ናቸው፡፡ በአዳማ 2 ዐቢይን ለመቃወም የወጡ ወጣቶች በፖሊስ ተገድለዋል፤ በሐረር 1 ሰው ሞቷል፡፡ በአምቦ 3 ወጣቶች ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ ባንዳንድ ከተሞች ቄሮዎች የዐቢይን “መደመር” መጽሃፍ አቃጥለዋል- ብሏል የቢቢሲ ዘገባ፡፡ በካራ ቆሬ ጃዋርን የሚቃወሙ ወጣቶች በጎዳናዎች መውጣታቸውን የዘገበው ደሞ አዲስ ስታንዳርድ ነው፡፡ ጃዋር በቀጣዩ ምርጫ ለመወዳደር ስለመወሰኑ መረጃ እንዳለው ስታንዳርድ ጠቅሷል።

Via:- wazema
@YeneTube @Fikerassefa
በታላቁ ሕዳሴ ግድብ የተፈጸመ ገንዘብ ምዝበራን የኢትዮጵያ መንግሥት እያጣራ መሆኑን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ለግድቡ ካወጣው 16 ቢሊየን ብር ውስጥ ማወራረድ የሚችለው 9 ቢሊዮኑን ብቻ ነው፡፡ ሜቴክ የግድቡን ሜካኒካል ሥራዎች እንዲሠራ ገንዘቡን የከፈለው መንግሥት ነው፡፡ በሜቴክ ሳቢያ የግድቡ መጠናቀቂያ ጊዜ በ5 ዐመት ዘግይቷል፡፡

Via:- wazema
@Yenetube @Fikerassefa
#ሰበር_ዜና የዎላይታ ሕዝብ በክልል ጥያቄው ላይ ተሰብስቦ እንዳይመክር ደኢህዴን አገደ!

ንቅናቄያችን የዎላይታ ሕዝብ የክልል ጥያቄ የደረሰበትን ደረጃ እና ተያያዥ ወቅታዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ውይይት ለማድረግ እሁድ ጥቅምት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በዎላይታ ጉታራ አዳራሽ ሕዝባዊ የምክክር መድረክ ከዎህዴግ በጋራ መድረክ ማዘጋጀታችን ይታወሳል::

በዚሁ መሠረት የጉታራ አዳራሽ ነጻ መሆኑን ካረጋገጥን በኋላ ለዞኑ አስተዳደር በቁጥር ዎብን/057/2019 ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ከመጠየቃችን በተጨማሪ ከዞኑ ጋር ውይይት ያደረግን ሲሆን አዳራሹ እንደሚፈቀድ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ፈቃድ እንደሚሰጥ ተግባብተን ነበር የተለያየነው::

የዞኑ ጽ/ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ውይይት መድረኩን ማካሄድ እንደማንችል በስልክ ተገልጾልናል:: የሚመለከታቸው አካላት ማለት የደኢህዴን ጽ/ቤት ኃላፊ እና አስተዳዳሪው እንደሆነ መረጃው ደርሶናል::

ደኢህዴን ዛሬ የዎላይታ ሕዝብ በክልል ጥያቄው ዙሪያ ተሰብስቦ እንዳይመክር እገዳ ጥሏል:: የዎላይታ ሕዝብ ሕገ-መንግስታዊ መብት ለማስከበር የሚደረገው ሰላማዊ ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል::

የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን)
ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም
ዎላይታ ሶዶ
@YeneTube @Fikerassefa
"ክስተት 'የግድያ ሙከራ' እንደሆነ ነው የምረዳው" ጀዋር መሐመድ

ጀዋር "የእኔ ጽሁፍ እና ትችት ትናንት ለተሞከረው ግድያ የሚጋብዝ አይደለም" በማለት እርሱ ባለው መረጃ ትናንት በመኖሪያ ቤቱ ተፈጸመ ያለው ክስተት ‘የግድያ ሙከራ’ ስለመሆኑ መደምደሚያ ላይ መድረሱን ተናግሯል።

ሙሉ ቃለምልልሱን ያንብቡት!
👇👇👇👇👇

https://telegra.ph/Jawar-10-23
የአልጀዚራዋ ጋዜጠኛ (Robyn) ጀዋር መሀመድ ከደቂቃዎች በፊት ቃለ መጠይቅ አድርጋዋለች "ጅዋር መሀመድ በቀጣዩ ምርጫ እንደሚሳተፈ ለጋዜጠኛዋ መናገሩን በትዊተር ገጿ አስፍራለች።

ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሰን እናሳውቃለን።
@Yenetube @Fikerassefa
⬆️⬆️የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ፕሬዝዳንት #አቶ_ሽመልስ_አብዲሳ_በአክቲቪስት ጀዋር መሐመድ ላይ የተከሰተውን ጉዳይ አስመልክቶ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• ትናንት ማታ የተፈጸመው ድርጊት ስህተት ነው፤ ስህተቱን ማን እንደፈጸመው፣ ለምን ጉዳዩን ምሽት ላይ ማድረግ እንደተፈለገ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡
• ዛሬ ለሞቱት ወገኖች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስም የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
• ዛሬ በተደረገው ሰልፍ ላይ ኦሮሚያን የግጭት አውድማ ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ሰልፉ ላይ አስነዋሪ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡
• እነዚህ ኃይሎች ጉዳዩ የሃይማኖትና የብሔር መልክ እንዲይዝ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

• የተለያዩ አካላት ለውጡ ዘላቂነት እንዳይኖረው የተለያዩ ሙከራዎች ሲያደርጉ ነበር፡፡

• ዛሬ የተፈጸመው መሆን የሌለበት ነገር ነው፡፡

• መንግስት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል ነው ለወንድማችን ጀዋርና ለሌሎች ከውጭ ለገቡ ሰዎች ጥበቃ የሚያደርገው፡፡

• አሳዛኝ ክስተቶች ዛሬ ተፈጽመዋል፣ የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ድርጊቶቹን የፈጸሙ አካላት ላይ መንግስት እርምጃ ይወስዳል፡፡

• በኦሮሞ ህዝብ መካከል ልዩነቶች እንዲፈጠሩ ገንዘብ መድበው እየሰሩ ያሉ አካላት ስላሉ ህዝባችን ነቅቶ መንቀሳቀስ አለበት፡፡

• የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጉዳዩን ለማረጋጋት ላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ልትመሰገኑ ይገባል፡፡

• ህዝባችንን ተጠቃሚ የማያደርግ ማንኛውንም ተግባር አንፈጽምም፡፡

• ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር እኩልነት ላይ የተመሰረተ እና ለሁላችንም የምትሆን የጋራ አገር በጋራ ለመገንባት መስራት አለብን፡፡

• በኦሮሚያ ውስጥ ያሉት ብሔር ብሔረሰቦችን ለማቀፍና ምንም ዓይነት ችግር እንዳይገጥማቸው ለማድረግ የኦሮሚያ ቄሮዎችና ቀሬዎች መስራት አለባቸው፡፡

• አሁን ወንድማችን ጀዋር በሰላም ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፤ መንግስት የሚያደርግለት ጥበቃም ይቀጥላል፡፡

Via:- OBN
@YeneTube @Fikerassefa
"የትግራይ መንግስት የኤርትራ መንግስትን ለመቀበል ዝግጁ ነን። የተዘጉ መንገዶች ግን ይከፈቱ። ተቋማዊ አሰራርም መተግበር አለበት።"

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ዛሬ የተናገሩት
@YeneTube @Fikerassefa
Youth gather at Jawar Mohammed's house to show support

Hundreds of supporters of Oromia Media Network's founder join protest amid reports of police surrounding his residence.

For more⬇️
https://aje.io/dqx7g
Gaaffii Ummataa Deebisuu Qofatu Nagaa Buusa

Bulchiinsa afaan qawwee fi sirna cunqursaa fi saaminsaa Itoophiyaan ittiin beekamtu jijjiiruudhaan bilisummaa Ummatootaa fi sirna dimokiraasii dhugaa fi nageenya waaraa mirkaneessuuf qabsoo barootaaf gaggeeffame keessatti qoodni Ummata Oromoo guddaa dha. Keessattuu ammoo, sirni EPRDF waggoota 27 dabraniif kan akka Sabaatti irratti qiyyaafatee itti roorrise Ummata Oromoo waan taheef qabsoo sirna cunqursaa EPRDF jijjiiruuf taasifame keessatti kan akka Saba Oromootti wareegama ulfaataa baase hin jiru jechuu dandeenya.

https://telegra.ph/ABO-YeneTube-10-23