ፖሊስ የጥቅምት ሁለቱን ሰልፍ ስለመከልከሉ
የአዲስ አበባ ምክር ቤት ጥቅምት 2 2012 ዓ.ም የጠራውን ሰልፍ የአዲስ አበባ መስተዳድር በህጉ መሠረት በዝምታ ፍቃድ ከሰጠ በኃላ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥቅምት 1 2012 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ክልከላ አድርጎበታል።
ይህን አስመልክቶ ምክር ቤቱ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፣ ምክር ቤቱ ቀደም ብሎ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣ለሀገሪቱ ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሰልፉን ሰርዟል።
የመንግስት ህገ ወጥ ክልከላ የዴሞክራሲ እና ፍትህ ቅልበሳውን አረጋግጧል። ስለዚህም፣ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደገለፀው፣ ሰላማዊ ትግሉን በሂደት ወደ ቀጣይ ምእራፍ ለማሸጋገር እንደሚገደድ በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማሳካት ሲንቀሳቀሱ የታሰሩ በርካታ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።
በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ፣ እንዲሁም፣ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቀን ከሌሊት ያደረጋችሁት ልፋት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ መምጣት የምትከፍሉት ዋጋ ቢሆንም፣ ባለ አደራ ምክር ቤቱ የላቀ ምስጋናውን እና አክብሮቱን ይገልፃል።
ፈጣሪ ህዝቧንና ኢትዮጵያን ይባርክ!
የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት
አዲስ አበባ
@YeneTube @Fikerassefa

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በነገው ዕለት በከተማይቱ በሚገኘው የመስቀል አደባባይ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ እንደሌለ አስታወቀ።
ለነገ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ የነበረው የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በበኩሉ በርካታ አባላቱ እና የሰልፉ አስተባባሪዎች ዛሬ መታሰራቸውን ገልጿል።
ለነገ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ የነበረው የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በርካታ አባላቱ እና የሰልፉ አስተባባሪዎች ዛሬ መታሰራቸውን ገለፀ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ደግሞ በነገው ዕለት በከተማይቱ በሚገኘው የመስቀል አደባባይ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ የለም ብሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው በነገው ዕለት በሚኖረው ሰልፍ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች እንደሚኖሩ ፖሊስ ኮሚሽኑ እንደገለጸ ተደርጎ የተላለፈው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል። የከተማይቱ ነዋሪ በነገው ዕለት በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ የሌለ እና ምንም የሚዘጋ መንገድ አለመኖሩን ተገንዝቦ መደበኛ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚችል ፖሊስ ኮሚሽኑ አሳስቧል።
የነገውን ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው በጋዜጠኛ እና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) በዛሬው ዕለት በበርካታ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ ላይ የእስር ዘመቻ መደረጉን አስታውቋል። እስካሁን ምን ያህል ሰዎች በትክክል እንደታሰሩ እንደማይታወቅም አቶ እስክንድር ለ DW ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት ጥቅምት 2, 2012 ዓ.ም የጠራውን ሰልፍ የአዲስ አበባ መስተዳድር በህጉ መሠረት በዝምታ ፍቃድ ከሰጠ ቦኃላ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥቅምት 1 2012 ባወጣው መግለጫ ክልከላ አድርጎበታል።
ይህን አስመልክቶ ምክር ቤቱ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፣ ምክር ቤቱ ቀደም ብሎ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣ለሀገሪቱ ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሰልፉን ሰርዟል።
የመንግስት ህገ ወጥ ክልከላ የዴሞክራሲ እና ፍትህ ቅልበሳውን አረጋግጧል። ስለዚህም፣ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደገለፀው፣ ሰላማዊ ትግሉን በሂደት ወደ ቀጣይ ምእራፍ ለማሸጋገር እንደሚገደድ በዚህ አጋጣሚ ይገልፃል።
የአዲስ አበባ ባላደራ ምክርቤት የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማሳካት ሲንቀሳቀሱ የታሰሩ በርካታ ወጣቶች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።
በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ፣ እንዲሁም፣ በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቀን ከሌሊት ያደረጋችሁት ልፋት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ መምጣት የምትከፍሉት ዋጋ ቢሆንም፣ ባለ አደራ ምክር ቤቱ የላቀ ምስጋናውን እና አክብሮቱን ይገልፃል።
እስክንድር ነጋ --- ዳዊት እንደሻው እንደፃፈው

#FakeNewsAlert
የአዲስ አበባ ባለአደራ ም/ቤት ሰልፍ እንዳያረግ እንደተከለከለ ገልፆ ለዛሬ ታስቦ የነበረው ሰልፍ እንደተሰረዘ ትናንት ገልፆ ነበር። ነገር ግን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ስም የተከፈተ አንድ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ ሰልፉ እንደሚካሄድ ፅፎ ህዝቡን እያደናገረ ነው።
ይህ አደገኛ ፌክ ኒውስ ነው! እውነት መስሎት ሰልፍ የወጣ ሰው ከፖሊስ ጋር አላስፈላጊ ፍጥጫ ውስጥ ሊገባ ይችላል።
ጥቆማ: የፌደራል ፖሊስ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ይህ ነው:
https://www.facebook.com/Addisababapolice/

በአዲስ አበባ ባልደራስ ምክር ቤት ለዛሬ ተጠርቶ የነበረው ሕዝባዊ ሰልፍ ፖሊስ ባደረገው ክልከላ መሰረዙን አስተባባሪው እስክንድር ነጋ በቲዊተር ገፁ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ አስቀድሞ በሰጠው መግለጫ ለሰልፉ ዕውቅና በመንፈግ ምንም አይነት ስልፍም ሆነ የመንገድ መዘጋት እንደማይኖር ህዝቡ ይወቅልኝ ሲል አሳስቦ ነበር። እስክንድር ነጋ በበኩሉ ለሀገር ሰላምና ለህዝብ ደህንነት ሲባል ስልፉን ለመሰረዝ እንደተገደዱ አስታውቋል። የኖቤል የሰላም ሽልማት ለሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር እንዲሰጥ በተበሰረበት ማግስት የተደረገው የሰልፍ ክልከላ የሀገሪቱን ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር የማድረግ ተስፋ መና እንዳያስቀረው ስጋታቸውን የሚገልፁ ዜጎች ቁጥርም ቀላል አይደለም።
Via Wazema
@YeneTube @FikerAsseda
Via Wazema
@YeneTube @FikerAsseda
አዳማ ⬆️
ጠቅላይ ዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም ኖቤል አሸናፊ መሆናቸው አስመልክቶ ህብረተሰቡ አደባባይ ወጥቶ ደስታውን ገልጿል ።
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ዶ/ር አብይ አህመድ የሰላም ኖቤል አሸናፊ መሆናቸው አስመልክቶ ህብረተሰቡ አደባባይ ወጥቶ ደስታውን ገልጿል ።
@YeneTube @Fikerassefa
የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 204ኛ መደበኛ ስብሰባው በሁለት አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 204ኛ መደበኛ ስብሰባው በ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና በ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በመምከር በሁለቱ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡መስተዳድር ምክር ቤቱ የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን የገመገመ ሲሆን በክልሉ በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት በአፈፃፀም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ተመልክቷል፡፡በመሆኑም የ2011 በጀት ዓመት አፈፃፀም እንዲሁም የ2012 በጀት አመት ዕቅድን መስተዳድር ምክር ቤቱ በጥልቀት በመገምገም ለክልሉ ምክር ቤት እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡በመሆኑም ባለፈው አመት ያልተፈፀሙ ተግባራትን ከላይ እስከ ታች ባለው መዋቅር ርብርብ በማድረግ ማካካስ እንደሚገባም አጽኖት ሰጥቶ ተወያይቷል፡፡
የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ማጠቃለያ ዓመት ላይ እንደመሆናችን ከዚህ በፊት ያጋጠሙ የአፈፃፀም ውስንነቶችን ፈጥኖ በማረም በ2012 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በማካተት ለላቀ ክልላዊና ሀገራዊ ስኬት መስራት እንደሚገባም ገልጿል፡፡ መስተዳድር ምክር ቤቱ የክልሉን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በአግባቡ ምላሽ ለመስጠት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም ወስኗል፡፡ መስተዳድር ምክር ቤቱ በቀጣዩ አመት በሚከናወኑ ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎች የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ሊያረጋግጡ በሚችሉ ተግባራት ላይ በማተኮር ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ምንጭ፡ የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ፕሬስ ሴክሬታሪያት
@YeneTube @FikerAssefa

ትናንት ምሽት በፍልውሃ አካባቢ የተፈጠረው ምንድን ነው?
ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ ፍልውሃ አካባቢ 2 የፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወታቸው ማለፉን የፌደራል ፖሊስ ኮምንኬሽን ለሸገር ነግሯል።4 አባላት መቁሰላቸውንም ተሰምቷል።ምክንያቱም ምን እንደሆነ የጠየቅናቸው የስራ ሀላፊ የአንድ አባል ቀልድ መሳይ ብሽሽቅ እንደሆነ ተናግረዋል። በተጀመረውም ብሽሽቅ አንደኛው አባል 2 ጓደኞቹን በእጁ በያዘው መሳሪያ ተኩሶ መግደሉን የፌደራል ፖሊስ ለሸገር ነግሯል።ህይወት ያጠፋው አባልም እንደቆሰለ እና ጉዳዩ በምርመራ እንደሆነ ታውቋል።ሸገር የፌደራል ፖሊስ አባላቱ ፍልውሀ አካባቢ ምን ያደርጉ እንደነበር ጠይቋል። የኮሚንኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ጄላን አባሎቹ በአካባቢው የሚኖሩበት ቦታ አለ በጥበቃም የተሰየሙ ነበሩ የሚል መልስ ሰጥተዋል።
Via Sheger FM

ዛሬ ማለዳ የካቢኔ አባላት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል። ለአመራሩ እንዲሁም ለተገኘው ስኬት ያላቸውን አድናቆት ለመግለጽ የወርቅ ሀብል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያበረከቱ ሲሆን "እውነት ፍቅር ያሸንፋል" የሚል ጽሑፍ ተቀርጾበታል።
#PMOEthiopia
@FikerAssefa @FikerAssefa
#PMOEthiopia
@FikerAssefa @FikerAssefa
የግብፁ መሪ ፕሬዝደንት ሲሲ ከጠ/ሚር አብይ ጋር በቅርቡ ሩስያ ውስጥ በግድቡ ዙርያ ሊመክሩ እንደተስማሙ ተናግረዋል። መቼ እና የት ከተማ የሚለው በግልፅ ባይታወቅም በቅርቡ በሶቺ፣ ሩስያ በሚካሄደው የሩስያ- አፍሪካ ስብሰባ ወቅት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።የጠ/ሚሩ ፅ/ቤት በዚህ ላይ መረጃ እንደሌለው አሳውቆኛል።በቅርቡ ግብፅ የ "አሜሪካ ታደራድረን" ጥያቄ አንስታ ይህም በኢትዮጵያ ውድቅ እንደተደረገ ይታወሳል።
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
በኮንታ ልዩ ወረዳ እየጣለ ያለው ከፍተኛ ዝናብ ለንብረት ውድመትና ለመፈናቀል ምክንያት መሆኑ ተገለጸ።
በኮንታ ልዩ ወረዳ እየጣለ ያለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ ናዳና ጎርፍ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ለወድመት ከ1 መቶ 30 በላይ አባዎራዎች ከቤት ንብረት ለመፈናቀል ምክንያት መሆኑ ተገለጸ፡፡
ከወረዳው መሬት አብዛኛው ተዳፋትና ተራራማ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ በልዩ ወረዳው በተለያዩ ጊዜያት መሬት መንሸራተትና ናዳ በመከሰት ለንብረት ውድመትና ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል ብለዋል የልዩ ወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ፡፡
ከመስከረም 24 እስከ 28/2012 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ ብቻ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡ ከ130 በላይ አባዎራችም በዚሁ አደጋ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡አደጋዎቹ በልዩ ወረዳው ካሉ 50 ቀበሌያት በ15ቱ መከሰቱን የተናገሩት የልዩ ወረዳው አደጋና ስጋት መከላከል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ጎበዜ መንግስት ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲደግፋቸው ጠይቀዋል ሲል የልዩ ወረዳው አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤትን ጠቅሶ የዘገበው የደቡብ መገናኛ ብዙሃን ነው፡፡

በቡርኪናፋሶ በአንድ መስጊድ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በሰሜናዊ ቡርኪናፋሶ በአንድ መስጊድ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡ጥቃቱ የተሰነዘረው ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እንደሆነም የአገሪቱ የፀጥታ ሀይል አስታውቋል፡፡ከአውሮፓውያኑ 2015 ጀምሮ በቡርኪናፋሶ በርካታ የሽብር ጥቃቶች መድረሳቸው ተነግሯል፡፡በዚህ የሽብር ድርጊት ከ500 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ280 ሺህ የሚልቁ ደግሞ ተፈናቅለዋል ተብሏል፡፡
ባለፉት ጥቂት ቀናትም የሽብር ጥቃቱ ተፋፍሞ በመቀጠሉ ሳቢያ በሁኔታው የተረበሹ የአገሪቱ ዜጎች ቀያቸውን ጥለው ሰላም አለበት ወዳሉት ስፍራ እየተሰደዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡መንግስት የሽብር ጥቃቱን ለመከላከል በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የደነገገ ሲሆን የአገሪቱ ጦር ሰራዊትም አገር አቀፍ ፀረ-ሽብር እርምጃዎችን ማጠናከሩ ተገልጿል፡፡
ምንጭ፦ ሽንዋ/ኢቲቪ

የሴቶች የማራቶን የአለም ሪከርድ ተሰብሯል!!
ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የቺካጎ ማራቶን ኬንያዊቷ ብሪጂድ ኮስጊ ለ16 አመት ያክል ተይዞ የቆየውን ሪከርድ በማሻሻል 2:14:04 በሆነ ሰዐት በመግባት ታሪክ ሰርታለች። በትናንትናው እለት የሀገሯ ልጅ ኢሉይድ ኪፕቾጌ ከሁለት ሰዐት በታች ያጠናቀቀ የመጀመሪያው ሰው መሆኑ ይታወሳል።

የጤና ሚኒስቴር ፣ የተጠሪ ተቋማት እና የክልል ጤና ቢሮ ሃላፊዎች ያደረጉት መደበኛ ስብሰባ በዛሬው እለት ተጠናቋል:: በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የታደሱ የህመምተኛ ክፍሎችን እና የጤና ሚኒስቴር ቢሮ እድሳትን የተጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱም ይህንን የሆስፒታልና የቢሮዎች እድሳት በክልሎች ለማስቀጠል የሚረዳ የልምድ ልውውጥ እንዲሆን የሚያስችል ነው ::
Via Dr Amir Aman
@YeneTube @FikerAssefa
Via Dr Amir Aman
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ ዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ያደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ 1ለ 0 ተሸንፏል::በወዳጅነት ጨዋታው ለዩጋንዳ ኢማኑኤል ኦክዊ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።የዮጋንዳ አዲሱ አሰልጣኝ ጆናታን ማካርት የዮጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ስራቸውን በድል ጀምረዋል።
ምንጭ:Ethio Kickoff
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:Ethio Kickoff
@YeneTube @FikerAssefa
#ኢትዮጵያ_እና_ግብፅ
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ላይ የሚደረገውን ድርድር እንደገና ለማስጀመር ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በቅርቡ እንደሚገናኙ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለት በአገራቸው ቴሌቭዥን ባደረጉት ንግግር ከጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ ጋር በሩሲያ እንደሚገናኙ አስታውቀዋል።
አል-ሲሲ ከጠቅላይ ምኒስትሩ ጋር የሚገናኙበትን ትክክለኛ ቀን ባይገልጹም ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ ጥቅምት 12 ቀን በሶቺ ከተማ የሚካሔደውን የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በተባባሪ ሊቀ-መንበርነት ይመራሉ።
ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ የኅዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አስተዳደር ላይ ያደረጓቸው ድርድሮች ያለ ውጤት ተበትነዋል።
ባለፈው መስከረም በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የድርድሩ ፈቅ አለማለት ለቀጣናው መረጋጋት ሥጋት ሆኗል ያሉት ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ከፍትኃዊ እና ሚዛናዊ ስምምነት ለመድረስ ዓለም አቀፍ አሸማጋዮች ጣልቃ እንዲገቡ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በበኩሏ «የሶስተኛ ወገን ጣልቃ-ገብነት ኢትዮጵያ እና ሱዳን የማይቀበሉት እና ተገቢ ያልሆነ» በማለት ውድቅ አድርጋለች።
Via:- Dw
@YeneTube @Fikeraseeda