በአፋር ክልል ጅቡቲና ኢትዮጵያን በሚያዋስነው አፋምቦ ወረዳ ከፍተኛ ግጭት እንዳለ ተሰማ።
በድንበር አካባቢ በሚኖሩ የአፋር አርብቶ አደሮች ላይ እስካሁን ማንነታቸው በውል ያልታወቁ ታጣቂዎች በተሽከርካሪዎች እየታገዙ ጥቃት አድርሰዋል። በዚህም ሳቢያ በርካቶች መቁሰላቸውንና የሞቱም እንዳልቀሩ ምንጮችን ጠቅሶ ድሬቲዩብ ፅፏል።በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ ምንም አይነት መግለጫ የለም።
@YeneTube @FikerAssefa

12ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ዛሬ ይከበራል።
አስራ ሁለተኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ አላማችን የብዝኃነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ እንደሚከበር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ።ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 3 የተቀመጠውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ትርጓሜ መሰረት በማድረግ የወጣ የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 እንዲሁም በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር ተደንግጓል።ባለፉት ረዥም ዓመታት ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እና ለሀገሪቱ ነፃነት የተደረጉ ትግሎች የሪፐብሊኩን ሰንደቅ ዓላማ የሉዓላዊነት መገለጫና ለህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት ምልክት መሆኑ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ሥራ መሰራቱን ምክር ቤቱ በመግለጫው ጠቅሷል።
ምንጭ: ኢፕድ

ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑ ተጠቆመ!
የዜጎችን በተለይም የአገር የወደፊት አለኝታ የሆኑ ወጣቶችን ህይወት በመቅጠፍ የሚታወቀው ኤች.አይ.ቪ./ኤድስ እንደገና በማገርሸት ሥርጭቱ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።ሰሞኑን በአገራችን ለ32ኛ፣ በዓለም አቀፍ ደግሞ ለ40ኛ ጊዜ በደብረ ብርሃን ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የመምህራን ቀን ላይ የቫይረሱን ሥርጭት፣ ያገጠሙ ችግሮች፣ የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች አስመልክቶ በቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ እንደተገለፀው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በአገራችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎችን ህይወት የቀማበት ወቅት እንደነበር አመላክቶ ነገር ግን በተቀናጀና በተጠናከረ ርብርብ ልንቆጣጠረው ችለን እንደነበር አስታውሷል።ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ቫይረሱ ዳግም በማገርሸት ከሚገባው በላይ መስፋፋቱንና ዜጎችን በተለይም ለጋ ወጣቶችን እያጠቃ እንደሚገኝ ጥናቱ አመላክቷል። የጥናቱ አቅራቢ ወይዘሮ ዓለምፀሐይ እንየው እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት የቫይረሱ ሥርዓት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ወደ ወረርሽኝ ደረጃ እየደረሰ ይገኛል።
Via EPA

ትናንት ምሽት በደቡብ ክልል በኮንታ ልዩ ወረዳ የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከተሎ በናዳ መደርመስ ከፍተኛ አደጋ ደርሷል!
በስፍራው የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ ትናንት ማታ በተከሰተው ናዳና የመሬት መደርመስ ወደ 5 የሚሆኑ ቤቶች ተውጠዋል። በውስጡ የነበሩት ቁጥራቸው ለጊዜው የማይታወቅ በርካታ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡
የአካባቢው ህዝብ ከፖሊስ ጋር በመተባበር የመለየት ሥራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
Via:- ኮንታ የልዩ ወረዳው አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ነው፡፡
@YeneTube @Fikerassefa

ያረጁ የመብራት መስመሮች ነዋሪዎችን ለአደጋ እያጋለጡ በመሆኑ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች አቤቱታ አሰሙ
የእድሜዋን ያክል ማደግ የተሳናት የጉራጌ ዞን መቀመጫ የሆነችው የወልቂጤ ከተማ የመብራት መስመር ዝርጋታ ለውበቷ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባታል፡፡
መኖሪያ ቤቶችን የተደገፉ የንግድ ተቋማት መሃል የተሰገሰጉ ያረጁ የመብራት ፖሎችን ሀይል የተሸከሙ የመብራት መስመሮች እንደሸረሪት ድር ተወሳስበው አስፈሪ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡
የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ማዕከሉ ከማዘጋጃ ቤቱ አገልግሎት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ለአደጋ የተመቹ ተክሎችና ግንባታዎች ስርዓት ማስያዝ ይገባዋል ያሉት ነዋሪዎቹ ማህበረሰቡ ህገወጥ ተግባርን የሚቆጣጠር ህግ አስከባሪ ከሌለ ለአደጋ ተጋላጭ መሆኑንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የወልቂጤ ማዕከል በበኩሉ በቅርቡ ከቻይና ካምፓኒ ጋር ስምምነት ላይ በመድረሱ ያረጁ መስመሮች በኮንክሪት ፖል ለመቀየር ታቅዶ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡
ህብረተሰቡ ንብረቱ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ከማዕከሉ ጋር ተቀራርቦ ቢሰራ አደጋን መቀነስ ይችላል ሲሉ ኃላፊው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
Via:-SRTV

“የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የኖቤል የሰላም ሽልማት የአፍሪካውያን ሽልማት ነው” አፍሪካውያን አምባሳደሮች
ተቀማጭነታቸውን ኬንያ ናይሮቢ ያደረጉ የአፍሪካ አምባሳደሮች ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል ሽልማት ማሸነፋቸው ለኢትዮጵያ ለውጥ እና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራር የተሰጠ እውቅናና የአፍሪካውያን ሽልማት ነው ብለዋል።
አምባሳደሮቹ ትናንት በኢትዮጵያ ኤምባሲ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይን መሸለም በማስመልከት ባደረጉት ዝግጅት የኖቤል ሽልማቱ ለኢትዮጵያ የሚመጥን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚገባ መሆኑን ገልጸዋል።
ሽልማቱ ሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት ያኮራ እና አፍሪካውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው መፍታት መቻላቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር እና የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን አምባሳደር በየነ ርእሶም በበኩላቸው ዶ/ር አብይ የሁላችንም ኩራት ናቸው ብለዋል።
አምባሳደር መለሰ አለም ሽልማቱ ለአፍሪካውያን የተሰጠ እንደሆነ ገልጸው አፍሪካውያን ላሳዩት ድጋፍና ወገንተኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በመጨረሻም አምባሳደሮቹ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትን እንኳን ደስ አላቹ ብለዋል።
Via:- #ENA

የህዳሴው ግድብ የማመንጨት አቅሙ በ1ሺህ300 ሜጋዋ ዋት ቀነሰ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሐሰት ነው ተባለ።
የግብጽና የተለያዩ የአገር ወስጥ መገናኛ ብዙሃን ስለ ህዳሴው ግድብ ያወጡት መረጃ ከእውነት የራቀ እንሆነ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል።የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የግድቡ የማመንጨት አቅም እንዲቀንስ ተደርጓል የሚባለው መረጃ ትክክል አይደለም ብለዋል።የግድቡ የማመንጨት አቅም የሚወሰነው ግድቡ በሚይዘው የውሀ መጠን እና ውሀ ከተርባይን ማእከል በሚኖረው ከፍታ ነው ብለዋል አቶ ሞገስ፡፡
የግድቡ ውሀ ከፍታ በጨመረ ቁጥር የተርባኖች የማመንጨት አቅም ከፍ ያደርገዋል እንጂ ተርባይኖች ብዛት የማመንጨት አቅም እንደማይጨምረው ነው ዳይሬክተሩ የነገሩን።አሁን ባለው ሁኔታ የግድቡን የውሀ መጠን የሚቀንስ ስራ ወይም የግድቡን ከፍታ የሚቀንስ ስራ እየተሰራ አይደለም እየተደረገ ያለው የተርባኖች ቁጥር የመቀነስ ስራ ነው ብለዋል፡፡የተርባይኖች ቁጥር እንዲቀንስ ቢደረግም በማመንጨት አቅሙ ላይ ምንም ተጽእኖ አይኖረውም ምክንያቱም የግድቦች የማመንጨት አቅም የሚወሰነው በተርባይኖች ብዛት ሳይሆን ግድቡ በሚይዘው የውሀ መጠን ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡
ከግብጾች አንጻር አሁን የተነሳው ጥያቄ ግድቡ የሚይዘው የውሀ መጠን የግድቡ ከፍታ እንደማይቀንስ ካሁን በፊት የግብጽ ባለሙያዎች እርግጠኛ ነበሩ ስለሆነም ያንን ተከትሎ የተነሳ እንደሆነም ነው አቶ ሞገስ የተናገሩት፡፡በመሆኑም የህዳሴው ገድብ 6400 ሜጋዋ ዋት እንዲያመነጭ ከዚህ በፊት በታቀደው መሰረት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል። የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ ከ68 ነጥብ 6 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በ2013 ዓ.ም የተወሰኑ ተርባይኖች ሃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ተብሏል።
Via Ethio FM

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የሱዳን የሽግግር መንግስትን ከታጣቂ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ለማስታረቅ በሚደረግ የኢጋድ አባል አገራት የመሪዎች የምክክር ስብሰባን ለመሳተፍ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድንን በመምራት ጁባ ገብተዋል።
ምንጭ: በጁባ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: በጁባ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች እየተከበረ ነው!
የኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኦሮሚያና በትግራይ ክልሎች እየተከበረ ነው፡፡የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ የሰንደቅ ዓላማ ቀን እያከበረ ሲሆን፣ በበዓሉ ላይ የተገኙት የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ ምሰሶ የሆነውና የአንድነታችን መገለጫ የሆነው ሰንደቅ ዓላማ ስር በመሰለፍ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በእኩልነትና በፍቅር አብሮ መስራት እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የትግራይ ክልልም "ሰንደቅ ዓላማችን ለህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርአታችንና ለህገ መንግስታችን ሉኣላዊነት " በሚል መሪ ቃል የሰንደቅ አላማ ቀንን በመቐለ ከተማ፣ በመቐለ ዩኒቨርስቲ በሚገኘው ስፖርት አካዳሚ ስታዲየም በተለያዩ ዝግጅቶች እየከበረ ይገኛል።
ምንጭ:ETV

#Fake_News_Alert
የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት ነው- የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር
“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ወደ አፋር ክልል በመግባት ጉዳት አደረሰ በሚል የሚሰራጨው ወሬ ሐሰት ነው” ሲል የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።
“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዥር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።
በተለያዩ የማሕበራዊ ሚዲዎችና አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን “በአፋር ድንበር በኩል የጅቡቲ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ጉዳት አደረሰ” በሚል የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑም ተገልጿል።
ጅቡቲም ኢትዮጵያን የመውረር ሐሳብ እንደማታራምድና የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጥብቅ መሆኑንም ተናግረዋል።
በሁለቱ አገሮች መካከል ለግጭት የሚዳርግ ምንም አይነት ተጨባጭ ምክንያት አለመኖሩን የገለጹት ኮሎኔል ተስፋዬ እየተሰራጨ ያለው መረጃም ትክክል አለመሆኑን አብራርተዋል።
ይሁን እንጂ በአካባቢው አልፎ አልፎ በግጦሽ፣ ውሃና በሌሎች ምክንያቶች የሚከሰቱ ግጭቶች መኖራቸውን አስታውሰው፤ በክልሉ በዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የመከላከያ ሰራዊት በስፍራው ተገኝቶ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ተናግረዋል።
Via:- ENA

38 ክላሽኒኮቭ ህገ ወጥ መሣሪያ በቁጥጥር ስር ውሏል
በተለያዩ የጉምሩክ የፍተሻ ኬላዎች በየዕለቱ በሚደረጉ ፍታሻዎች የህብረሰተቡን ማህበራዊ ህይወት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ የኮንትሮባንድ እቃዎች ይያዛሉ፡፡
በዚሁ መሰረት በዛሬው ቀን ከሕዝብ በተገኘ ጥቆማ በጋምቤላ ከተማ ኮድ 3 AA 55966 የሆነ FSR መኪና 38 ክላሽኒኮቭ ህገ ወጥ መሣሪያ ሻግ አርጎ በግለሰብ ግቢ ተደብቆ ባለበት በመከላከያ ሰራዊታችን ፌደራል ፖሊስ እና ጉምሩክ ሰራተኞች በጋራ በተሰራ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ውሏል።
ህገ ወጥነት ከህዝቡ አይንና ጆሮ ሊሰወር ስለማይችልና ይህንን የሚሰሩ አካላትም ከህግ ሊያመልጡ ስለማይችሉ ህገ ወጦች ከዚህ ስራቸዉ እዲታቀቡ እናሳስባለን።
ምንጭ፡ የገቢዎች ሚኒስቴር

በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ!
በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ሜጉ ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች በፈፀሙት ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ መሆኑን የአፋር ክልል የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አህመድ ኡመድ ለኢቢሲ ተናግረዋል።
በጥቃቱ እስካሁን 16 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከእነዚህም መካከል 3ቱ ህፃናት እና 4ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው ብለዋል። ጥቃቱ በተሸከርካሪ የታገዘ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የሰነድ ማስረጃዎችን ማግኘት እንደተቻለም ነው ም/ል ኮሚሽነሩ የተናገሩት፡፡
በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ህፃናት በዱቡቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል። የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑን አስታውቋል፡፡
“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዦር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።
Via:- EBC

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምገባ መርሀ ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ምከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የምገባ መርሀ ግብሩን ኣስጀምረውታል፡፡
ምንጭ፦ ኢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
የከተማ አስተዳደሩ ምከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የምገባ መርሀ ግብሩን ኣስጀምረውታል፡፡
ምንጭ፦ ኢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
የፋሲል ግቢ አብያተ መንግስታት እድሳት ተጀምሯል!
እድሳቱ ሲጠናቀቅ የሚታየውን ውብ ገፅታ ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል። ከጎብኝዎች ከሚገኘው ገቢ የተወሰነው ለእድሳት እንዲሆን የተመደበ ሲሆን ብዙውን ግን አለም አቀፍ የቅርስ ተቆርቋሪ ድርጅት እደሚሸፍነው ተነግሯል።