YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አምባሳደር ሀሰን ታጁ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሴኔጋል ፕሬዝዳንት አቀረቡ።
@YeneTube @Fikerassefa
#ሼር በ2003 ነበር ከጉራጌ ወደ ሰበታ ገልበት ስራ እንድትሰራ ይዘዋት የመጡት ነገርግን ጠፍታ በፋሚሊ ህጻናት ማሳደጊያ ለተወሰነ ጊዜ በመቆየት በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ ሄዳለች፡፡ አሁን ላይ ቤተሰቦቿን እየፈለገች ሲሆን የአባቷ ስም አቶ ገረመው የእኗቷ ስም ወ/ሮ አለም እንደሚባሉ ታስታውሳለች ያሉበትን፡የሚያቅ በስልክ ቁጥር 0929174211 / 0937999608 ላይ ያሳውቀን ብለዋል፡፡
የምርጫ ቦርዱ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉ የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ!

የኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅርቡ በፀደቀው የምርጫ አዋጅ ላይ ሊያደርገው የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተገለፀ፡፡

ውይይቱ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና በስነ-ምግባር አዋጁ እንዲሁም በቦርዱ የአደረጃጀት ለውጥ ላይ ሊካሄድ የታሰበ ነበር። ሆኖም አዋጁ ከአሁን ቀደም ባደረግናቸው ውይይቶች የተነሱ የማሻሻያ ሃሳቦች ሳይካተቱ የፀደቀ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ የውይይቱ መካሄድ ተገቢነት የለውም በሚል ተቃውመውታል።

ቦርዱ ስምምነት ላይ ሳይደረስ መፅደቁን አለመከላከሉ ተዓማኒነቱን ጥያቄ ውስጥ ሊከተው እንደሚችልም ነው ፓርቲዎቹ ያስታወቁት። በጉዳዩ ላይ ሲከራከሩ የቆዩት ፓርቲዎቹ ውይይቱን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝመው ተለያይተዋል። ፓርቲዎቹ በጋራ ምክር ቤታቸው በኩል መወያየት ጀምረዋል።

Via :- ኢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ከችጉንጉኒያ ወረርሽ ስጋት ለመታደግ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በከተማው ለወራት በዘለቀውና ከ35 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ያጠቃው ወረርሽኙ ከእረፍት እየተመለሱ ባሉ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ላይም ስጋት መፍጠሩ ተገልጿል፡፡የቺኩንጉኒያን ወረርሽኝን ለመከላከል በተማሪዎች አገልግሎት መስጫ ስፍራዎች መድሃኒት መረጨቱን የድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ለአሐዱ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡በድሬዳዋ ከአንድ ቤት ከ2-4 ሰዎች በወረርሽኙ እንደተያዘ የተገለጸ ሲሆን መንግስት ጉዳዩን በአጽኖት እንዲመለከተው የህክምና ባለሞያዎች እየጠየቁ ነው፡፡ከድሬዳዋ የጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የድሬ የበጎ ፍቃድ የህክምና ባለሞያዎች ማህበር ወረርሽኙን ለመግታት የህክምና ዘመቻ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

Via Ahadu Radio
@YeneTube @FikerAssefa
የጤና ሚኒስቴር የተቋሙን አዲሱን መለያ አርማና መሪ ቃል አስተዋወቀ:: የጤና ሚኒስቴር የተቋቋመበትን ዓላማናግብ ለህብረተሰቡ በቀላሉ ለማድረስ ይቻለው ዘንድ አዲስ መለያ ዓርማና መሪ ቃል በማዘጋጀት በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ይፋ አድርጓል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የጠ/ሚ ፅ/ቤት እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ...

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ምኒስትር ዐብይ አህመድ እስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደሃገራቸው መመለስን ጉዳይ አስመልክቶ ከቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር ያደረጉት ውይይት የለም ሲሉ የጠ/ሚ ፅህፈት ቤት ምንጮች ገልፁልኝ ሲል የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል።

የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር በዋቢነት የጠቀሰው 'The Times Of Israel' /ዘ ታይምስ ኦፍ ኢስራኤል/ “የኢትዮጵያው መሪ ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደሃገራቸው በመመለሱ ሂደት ዕገዛ ለማድረግ ተስማምተዋል” ሲል ነው ሰሞኑን የዘገበው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ፅህፈት ቤት ምንጮች እንዳሉት ግን የስደተኞችን ወደሃገራቸው የመመለስ ጉዳይ እንዲያውም በሁለቱ መሪዎች ውይይት አልተነሳም ።

#VOAAmharic
@YeneTube @Fikerassefa
⬆️
ሰኔ 15 ጀነራል ሰአረ መኮንን ላይ ግድያ እንደፈፀመ የተጠረጠረው ጠባቂ መንቀሳቀስ እና መናገር እንደጀመረ መረጃ ደርሶኛል!

መረጃው እንደሚጠቁመው ግለሰቡ በአሁን ሰአት በአራት የፌደራል እና አራት መከላከያ አባላት ጥበቃ ተደርጎለት ህክምና እየተከታተለ ነው። ከዚህ በተጨማሪም ንግግር ማድረግ እና እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል ተብሏል። ሌላው ከዚህ ጋር አብሮ የደረሰኝ መረጃ ግለሰቡ በግድያው ቀን በነበረው ተኩስ አንድ አይኑን አጥቷል። አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ የተባለው ይህ የጀነራሉ ጠባቂ ሰኔ 15 ግድያውን እንደፈፀመ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዳለ ይታወቃል። የመንግስት አካላትም በወቅቱ ይህ ግለሰብ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ሰንዝሮ ነገር ግን ቆስሎ በህይወት እንደተረፈ በወቅቱ ገልፀው ነበር። ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ የፌደራል ፖሊስ ደውዬ ነበር። ነገር አሁን ላይ ምንም ተጨማሪ መረጃ የለም፣ ሲኖር ለህዝብ ይፋ ይደረጋል የሚል መልስ ብቻ አግኝቻለሁ።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
ሻለቃ አስቻለው ለከፈተው ተኩስ በተወሰደ አጸፋ ህይወቱ ማለፉን ፖሊስ ለአብመድ ተናገረ።ግለሰቡ ሰኔ 15 ላይ በተፈፀመው የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የፖሊስ አባላት ግድያ ተጠርጥሮ በህግ ሲፈለግ መቆቱንም ፖሊስ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በቴክኒክ ችግር ወደተነሳበት አየር ማረፊያ ተመልሶ ለማረፍ ተገደደ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET908 የበረራ መስመር ዲአስ ሴኔጋል - ማሊ ባማኮ - አዲስ አበባ የሆነው ቦይንግ 767-300 አውሮፕላን ከሴኔጋል ዲአስ ከተነሳ በኋላ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ወደተነሳበት አየር ማረፊያ ለማረፍ መገደዱን አየር መንገዱ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።አየር መንገዱ አውሮፕላኑ ምን አይት የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው ግልጽ ባያደርግም አጀንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ከሆነ፤ ከአውሮፕላኑ ሞተሮች አንዱ እሳት በመያዙ 90 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረው አውሮፕላን በፍጥነት ተመልሶ እንዲያርፍ ተደርጓል።

የሴኔጋል ኤርፖርቶች ቃል አቀባይን ጠቅሶ ኤኤፍፒ እንደዘገበው የአውሮፕላኑ አብራሪ ተመልሶ ለማረፍ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው አውሮፕላኑ እንዲያረፍ የተደረገው።የሴኔጋል መገናኛ ብዙሃን አውሮፕላኑ አየር ላይ የቆየው ለ10 ደቂቃዎች ብቻ መሆኑን ጨምረው እየዘገቡ ነው።አየር መንገዱ መንገደኞቹ በመጉላላታቸው ይቅርታ በመጠየቅ ሁሉም ተሳፋሪዎች በተለዋጭ በረራዎች ጉዟቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው መርሐ ግብር አዲስ ለተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ

እንኳን ለ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን አዲስ አንደኛ ዓመት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያና የመመዝገቢያ ቀን ጥቅምት 04 እና 05 ቀን 2012 ነው፤

- በተጠቀሱ ቀናት ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ስርተፊኬት፣ የስፖርት ትጥቅ፣ ትራንስክሪፕት ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም አራት ጉርድ ፎቶግራፍ በመያዝ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናስታውቃለን፡፡ከዚህ በፊት Withdrawal ሞልታችሁ የወጣችሁና በRe-admission የምትገቡ ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሱት ቀናት እንድታመለክቱ እናስታውቃለን።

ማሳሰቢያ
- ከተገለጸው ጊዜ ቀድመውም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

-ዲላ ዩኒቨርሲቲ
@YeneTube @FikerAssefa
በአጣዬው ግጭት፣የሰሜን ሸዋ ዞንና የኦሮሞ ብሔር አስተዳደር ውዝግብ

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር«አጣየን ለማጥቃት የተዘጋጀ እና የተደራጀ ኃይል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ አለ» ይላል።በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ በዞኑ የተደራጀና የታጠቀ ኃይል ፈፅሞ የለም ባይ ነው።ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት 8 ሰዎች መገደላቸውና 13 መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡ሰሞኑን በአማራ ክልል አጣዬ አካባቢ የተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት፣« የአማራ ክልል በተለይም የሰሜን ሸዋ ዞን እንዳይረጋጋ የሚፈልጉ ኃይሎች ናቸው» ሲል የሰሜን ሸዋ ዞን የፀጥታ መምሪያ አስታውቋል። የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር፣« አጣየን ለማጥቃት የተዘጋጀ እና የተደራጀ ኃይል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ አለ»ይላል።በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደግሞ በዞኑ የተደራጀና የታጠቀ ኃይል ፈፅሞ የለም ባይ ነው።ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት 8 ሰዎች መሞታቸውና 13 መቁሰላቸውን አመራሮቹ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

-DW
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የታክሲ አገልግሎት (ኤታስ) ከሚሰጡ 13 ተቋማት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በዋነኛነት የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከተሉት ባወጣው መመሪያ ዙሪያ እና የትራንስፖርት ሴክተሩን በዘላቂነት ዘመናዊ ለማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከኤታስ እና ሶፍትዌር ማበልፀጊያ ተቋማት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ በከተማ አስተዳደሩ ረቅቆ በቅርቡ ይፋ የሆነው መመሪያ ቴክኖሎጂው ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

ተቋማቱ ህጉን እንደማይቃወሙ እና ለተፈፃሚነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትራንስፖርት አሰጣጥ በከተማዋ ውስጥ እንዲስፋፋ ፍላጎቱ ነው ብለዋል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የሚረዱ ሌሎች ተጨማሪ ቴክኖሎጂዎችን ለሚያመጡ በራቸው ክፍት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ የተቀላጠፈ እና ህዝቡን የሚጠቅም መመሪያ ቀርጾ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም የኤታስ ተቋሞቹ በከተማዋ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ተሽከርካሪዎች ያረጁ በመሆናቸው የከተማ አስተዳደሩ ተሽከርካሪዎቹን በአዲስ በመተካቱ ሂደት ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ መንግሥት አውሮፕላን ቅዳሜለት የሱማሊያን እገዳ ጥሶ በቀጥታ በሱማሊያዋ ኪሲማዩ ወደብ በማረፉ፣ የሁለቱ ሀገሮች ፍጥጫ እንደገና ተካሯል፡፡ የሱማሊያ ዜና ምንጭ ሒራን ድረ ገጽ እንደዘገበው፣ ሞቃዲሾ ለተመድ ዐለም ዐቀፍ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን ክስ አቅርባለች፡፡ ወደ ኪሲማዩ የሚደረግ የውጭ በረራ ሁሉ በሞቃዲሾ በኩል እንዲሆን ሱማሊያ ባለፈው ወር ነበር ያዘዘችው፡፡ መንግሥት ከጁባላንድ ራስ ገዝ ጋር ውዝግብ ውስጥ ከገባ ቆይቷል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️
#FakeNewsAlert

ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ” በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ብርድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ፌስቡክ ገጽ የተዘገበው ዜና የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬ እለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደረገው ምንም አይነት ውይይትም ሆነ ድርድር ያላደረገ ሲሆን የኢቢሲም ሆነ የኢቢሲን ዜና መሰረት በማድረግ የዘገቡ ሌሎች ሚዲያዎች ዜናዎችን ከማሰራጨታቸው በፊት ማጣራት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳስባል፡፡ ቦርዱ ማንኛውንም የመረጃ ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

Souce: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @FikerAssefa
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በእስካሁኑ የግንባታ ስራው 99 ቢሊየን ብር ወጥቶበታል ተባለ

ቀሪው የግድቡ ስራ 40 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪእንደሚጠይቅ ተነግሯል፡፡ ከሕዝብ የተሰበሰበው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን 12 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መድረሱንም ሰምተናል፡፡

የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የግድቡን አጠቃላይ ሁኔታ አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ሲያደርግ እንደሰማነው ባለፈው አመት ብቻ 970 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማሰባሰብ ተችሏል ተብሏል፡፡

ባለፈው አመት ሀገሪቱ የነበረችበት አጠቃላይ ሁኔታ ህዝባዊ ተሳትፎውን ያቀዘቀዘ ቢሆንም የተሰበሰበው ገንዘብ ግን ከፍተኛ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ስራው 68.5 በመቶ ደርሷል የተነሳ ሲሆን የሲቪል ስራዎች 84.5 በመቶ፣ የኤሌክትሮሜካኒካል ስራዎች 25 በመቶ፣ የብረታ ብረት ስራዎች ደግሞ 15 በመቶ አፈፃፀም ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

Via:- shegerFm
@YeneTube @FikerAssefa
ከሴኔጋል አዲስ አበባ ይበር የነበረው ንብረትነቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የበረራ ቁጥር ET-908 አውሮፕላን ባጋጠመው የቴክኒክ እክል ምክንያት እዛው ሴኔጋል ለማረፍ መገደዱ ተሰማ።

B767-300 አውሮፕላን በመደበኛ በረራ ከሴኔጋል ዲአስ በማሊ ባማኮ አድርጎ አዲስ አበባ ለመብረር ጉዞ ጀምሮ ነበር ተብሏል።
የበረራ ቁጥር ET-908 ባጋጠመው የቴክኒክ እክል ምክንያት ወደተነሳበት ኤርፖርት ተመልሶ ለማረፍ መገደዱንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮምንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አስራት በጋሻው ለሸገር ነግረዋል።

በአውሮፕላኑ የነበሩ መንገደኞችም በሌላ አውሮፕላን ተሳፍረው ጉዞዋቸውን ቀጥለዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።
አውሮፕላኑ ስላጋጠመው የቴክኒክ እክልም እንዲህም ነው እንዲያም ነው የተባለ ነገር የለም።

Via:- Shager FM
@YeneTube @Fikerassefa
“ከመጣንበት መንገድ በላይ ወደፊት አብረን የምንጓዘው ጉዞ ረጅም ነው”:- የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) የአገሪቱን ህዝቦች የእኩልነት፣ የፍትሕና እና የነጻነት ጥያቄዎችን ለመመለስ፣ ብሎም የሕዝቦችን የመልማትና የመበልጸግ ፍላጎት ከግብ ለማድረስ ከእህት ድርጅቶች እና ከአጋሮቹ ጋር ኅብረት ፈጥሮ ሲታገል፣ በጋራ መሥዋዕትነት ሲከፍል መቆየቱንና አሁንም በመታገል ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

https://telegra.ph/ODP-10-09
በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተካፈለው ልኡካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት::

ለ17ኛ ጊዜ በኳታር ዶሃ ከመስከረም 16-25/2012ዓ.ም. በተካሄደው የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና ላይ ተካፍሎ በሁለት ወርቅ፣ አምስት ብር እና አንድ ነሀስ በድምሩ በስምንት ሜዳልያ ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው የአትሌቲክሰ ቡድናችን ዛሬ ከማለዳው 1፡30 ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርስ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አትሌት ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም እንዲሁም የአትሌቲክስ የሙያ ማህበራትና ክለብ አመራሮች ተገኝተው የአበባ አሰጣጥና እንኳን በድል ተመለሳችሁ ያሉ ሲሆን በቀጣይ በሚዘጋጅ መርሃ ግብር ለቡድኑ አቀባበልና ሽልማት የሚደረግለት ይሆናል፡፡

Via EAF
@YeneTube @FikerAssefa
ሸጎሌ የአውቶቡስ ዴፖን ሊመረቅ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ሸጎሌ የአውቶቡስ ዴፖን ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ ሊያስመርቅ ነው::በምረቃ ስነ ስርዓቱ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች የአዲስ አበባና የፌደራል ከፍተኛ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ፡፡ዴፖው በሃይለ ስላሴ ዘመነ - መንግስት ከእንጨትና ከቆርቆሮ ተዘጋጅቶ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት በዘመናዊ መልኩ ተገንብቶ በመዲናዋ የአውቶቡስ ዴፖ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ሸጎሌ የአውቶቡስ ዴፖ በመሬት ላይ ብቻ የሚጠናቀቅ ሆኖ በአንድ ጊዜ ከ250 እስከ 300 አውቶቡሶችን በተመቻቸ ሁኔታ የማቆም አቅም አለው። 52 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ይህ ዴፖ ለግንባታው ሙሉ በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድሩ የሚሸፈን 555 ሚሊየን ብር በጀት ወጪ ተደርጎበታል፡፡ ዴፖው አዉቶቡሶቹ በአንድ ማዕከል ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት በሚያስችል በዘመናዊ መንገድ የተገነባ ነው፡፡ዘመናዊ ጋራዥን ጨምሮ ደህንነትና ንጽህናቸዉ የሚጠበቅበትና ከአንድ ማዕከል ሥምሪት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተገንብቷል፡፡

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
በጭልጋ ወረዳ 45 የአማራ ልዩ ኃይል ሕይወት አለፈ!!

በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ከአይከል ከተማ፣ ጓንግ እና ቡሆና ድረስ ከመስከረም 17/2012 ጀምሮ ለአምስት ቀናት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የነበሩ ታጣቂዎች በከፈቱት ድንገተኛ ተኩስ ሰላም በማስከበር ላይ የሚገኙ 45 የአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላትን መግደላቸውን የአዲስ ማለዳ ምንጮች አረጋገጡ።

ማክሰኞ መስከረም 20/2012 በባህርዳር በሚገኘው ጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የተናገሩት የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አገኘሁ ተሻገር፣ የፀጥታ አካላት ወደ ማደሪያ ካምፓቸው ሲገቡ ከበባ እንደተፈፀመባቸው እና ‹‹ከደረሰባቸው ውርጅብኝ›› ራሳቸውን መከላከላቸውን ይናገራሉ።

ተጨማሪ⬇️
https://telegra.ph/Amhara-10-09

@YeneTube @Fikerassefa