በኢጋድ አባል አገራት በአጠቃላይ ከ9 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የውስጥ መፈናቀል መከሰቱን በ12ተኛው የኢጋድ አባል አገራትጉባዔ ላይ ተገልጿል። የኢጋድ አባል አገራት የፈረሙትና ኢትዮጵያ የሌለችበት የካምፓላ ስምምነት በደቡብ ሱዳን ተግባራዊ ተደርጎ ለውጥ በማምጣት ላይ መሆኑ ታዉቋል። ጉባዔው ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን የሚፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው በመመለስ ለዘለቄታው ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው።
(ኢቢሲ)
@YeneTube @FikerAssefa
(ኢቢሲ)
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩
በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg

የኅዳሩ የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ በምርጫ ሕግጋቱ መሠረት እንደሚደረግ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ ለሕዝበ ውሳኔ የተዘጋጀ ሌላ ሕግ ሀገሪቱ የላትም፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ለኢቢሲ እንደተናገሩት፣ ከክልሉ አልቀው መምጣት ያለባቸው የአስተዳደር እና ሕግ ማዕቀፎ ሰነዶች እስካሁን ለቦርዱ አለቀረቡም፡፡ ቀነ ገደቡ ከመስከረም 12 ወደ 30 ተራዝሟል፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ዞኑና ክልሉ ካልተስማሙ፣ ቦርዱ የሕዝበ ውሳኔውን ሂደት ሰላማዊነት ለማረጋገጥ ይቸገራል፡፡
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በአዊ ብሔ/አስ/ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ ፡፡
ከእንጅባራ ከተማ ወጣ ብሎ በአካይታ ቀበሌ በቀን 26/1/2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ስዓት አካባቢ ከእንጅባራ አምበላ ተሳፋሪ ጭኖ ይጓዝ የነበረ ኮድ 3-13645 አማ ታርጋ የሆነ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ከአዲስ አበባ ወደ እንጅባራ አቅጣጫ ከሚመጣ ሎቤድ ኮድ 3-84604 ኢት ጋር በመጋጨቱ ወዲያውኑ የ1 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሌሎቹ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በእንጅባራ አጠቃላይ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የባንጃ ወረዳ የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኢ/ር አስማረ ገብረኪዳን ተናግረው እንዲሁም በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም ሌሎች መረጃዎችን ተከታትለን የምናደረስ ይሆናል ብሏል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፡፡

በድሬደዋ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ።
ግጭቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ #ተደርጓል።
በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ገንደ ጋራ ፣ደቻቱና አምስተኛ ተብለዉ በሚጠሩ ቦታዎች ትናንት ረፋድ ጀምሮ በአካባቢዉ ነዋሪዎች መካከል ማንነት ላይ ያነጣጠረ ግጭት ተቀስቅሷል።
ይህንን በመቃወምም በደቻቱ አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች «መንግስት መፍትሄ ይስጠን» ሲሉ የከተማዋን አስተዳደር በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።
ከሰልፈኞቹ መካከል ተመርጠው ከአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያካሄዱት ነዋሪዎች "ብሄርና ማነትታችንን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እየደረሱብን ነው። አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ እና መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።
ነዋሪዎቹ "የአካባቢ /መንደር ግጭትን መፍታት ለመንግስት እንዴት አንደተሳነው አልገባንም? ምላሽ ይሰጠን ?"ሲሉም ጠይቀዋል።እንደ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ "ከአስተዳደሩ አመራር አካላት ጭምር ችግሩን በየጊዜው የሚያባብስ አካል አለ ፤ አስተዳደሩም ሆነ የፀጥታ ኃይሉ ሰላማችንን እና ደህንነታችንን በተገቢው መንገድ ሊያስጠብቅ ባለመቻሉ የፌደራል መንግስት ጣልቃ ሊገባና ለችግራችን አንድ መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል» ብለዋል።
በድሬደዋ ከአዲስ አመት ዋዜማ ጀምሮ የተቀሰቀሰው የደቻቱ አምስተኛ፣ ገንደጋራ እና አዲስ ከተማ አካባቢዎች ግጭት ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለ ሲሆን በግጭቱ ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት፣ ለአካል መጉደል እንዲሁም ለንብረት ዉድመትና ዝርፊያ ምክንያት ሆኗል። የእነዚህ አካባቢዎች ትልቁ የገበያ ማዕከል ቀፊራም ተገቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ማካሄድ ተስኖታል።
ዛሬ ለአቤቱታና ተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎችን ያነጋገሩት የአስተዳደ የድርጅት እና መንግስት ስራ ኃላፊዎች በበኩላቸዉ አስተዳደሩ በአካባቢው እየተፈጠሩ የሚገኙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ፣የችግሩ ጠንሳሽ እና አባባሽ ያላቸውን አካላት ወንጀል በማጣራና በቁጥጥር በማዋል ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ እየሰራን ነው ብለዋል ።
በሌላ በኩል ከህዝቡ ጋር ወርዶ በመወያየት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።
Via:-DW
@YeneTube @Fikerassefa

በአማራ ክልል ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ ላይ ባልታወቁ ሰዎች ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድምአገኘሁ ዛሬ በሰጠት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት የተፈጠረውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የሚያስችሉ ስራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ ነው።
በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ቦታዎች አካባቢ የተከሰተው ግጭት በጸረ-ሰላም ኃይሎች ምክንያት እንጂ በህዝቦች መካከል የተነሳ እንዳልሆነም አስረድተዋል።
ከአራት ወራት በፊት በነዚህ አካባቢዎች በተመሳሳይ መልኩ በተከሰተ ግጭት የአጣየና አካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አውስተዋል።
“ከዛ ጊዜ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው የአስፓልት መንገድ ግራና ቀኝ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መቀሳቀስ ክልክል መሆኑ በኮማንድ ፖስት ታውጆ ነበር” ብለዋል።
ይሁን እንጂ ሰሞኑን የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሁለት ግለሰቦች አጣየ ከተማ ገበያ ሊገቡ ሲሉ በአካባቢው በጥበቃ ላይ በነበሩ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት ሊያዙ ሲሉ ተኩስ በመክፈታቸው ግጭት መፈጠሩን ተናግረዋል።
በእለቱም ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሀይሎች የአጣየን ከተማ ለመውረርና ግጭቱን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት ያደረጉት ሙከራ በክልሉ ልዩ ሃይል፣ በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት በተደረገ ጥረት መክሸፉን ገልጸዋል።
ይሔንን ተከትሎ በነበረው የተኩስ ልውውጥም አምስት ሰዎች ሲሞቱ አራት መቁሰላቸውን ገልጸው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሁለቱም ዞኖች አመራሮች፣ ህዝቡና የሚመለከታቸው አካላት በጋራ እየሰሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
#ENA

ማስተካከያ!
ዛሬ የአሜሪካ Ambassador Micheal Raynor በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የነበራቸው አጭር ቆይታ ዋና አጀንዳ በኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት ሂደት ዙርያ ያሉትን ተግዳሮቶች በሚመለከት የባለሙያዎች እይታን ለመስማት ነበር። ፕሮፌሰር ክንደያ እና የፖለቲካ ምሁሩ መረሳ ፀሃየ በጉዳዩ ለአምባሳደሩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከአምባሳደሩ ጋር በተገኙት የፖለቲካ አማካሪያቸው ጥሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ስብሰባው ላይ ተገኝተው በጉዳዩ ዙርያ የትግራይ መንግስት እና ህዝብ ሃሳብ ገልፀዋል፣ ለጥያቄዎቹም መልስ ሰጥተዋል! ከዚህ ስብሰባ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ሚድያዎች እየተዘገቡ ያሉት ሌሎች ዜናዎች ስህተት መሆናቸውን እንገልፃለን!
-Mekele University

ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ ድልድይ ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል
ከሐረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ ኤረር ቀበሌ ገበሬ ማህበር ላይ የሚገኘው ድልድይ በመሰንጠቁ አገልግሎት መስጠት በማቋረጡ አሽከርካሪዎችና ተገልጋዮች እየተቸገሩ መሆኑን ተናገሩ።
ከድሬዳዋ ወደ ጎዴ አልሚ የእርዳታ እህል ጭኖ እየተጓዘ ሳለ በመንገዱ መበላሸት ምክንያት በአካባቢው ቆሞ ያገኘነው የከባድ መኪና አሽከርካሪ አቶ ደረጀ የማነህ እንደሚገልጸው አደጋ የደረሰበት ድልድይ በወቅቱ ባለመጠገኑ ለሰባት ቀናት የጫነው እቃ ሳናራግፍ በስፍራው ለመቆየት ተገደናል።
በአካባቢውም የተደራጀ ጥበቃ ባለሞኖሩ ንብረቱ ለስርቆት እየተዳረገ ነው፤ ተሽከርካሪም ለማለፍ ሲሉ ለትራፊክ አደጋ እየተዳረግን ነው ፡፡
ባካባቢው የምግብና ውሃ አቅርቦት ባለመኖሩም እየተቸገሩ መሆናቸውን ገልጾ ለዚህ ሁሉ ችግሩ መንገዱ በወቅቱ አለመሰራተሩና ተሽከርካሪዎች በስፍራው ላይ መበራከት በመሆኑ መፍትሄ ሊሰጥበት ይገባል ሲል ተሯል።
የነዳጅ ቦቴ አሽከርካሪው አቶ መኮንን ቦጋለ እንደተነገሩት ተለዋጭ መንገዱን ባግባቡ ሰርቶ የሚያሳልፈን አካል በማጣታችን የያዝነውን ጭነት ሳናራግፍ ለእንግልት ተደርገናል ሲሉ ተነግረዋል ፡፡
ግማሽ ኪሎ ሜትር የማይሞላ ተወለዋጭ መንገድን በአንድ ቀን መስራት ሲቻል ከጅቡቲ ድረስ ተጉዘን ለህዝብ ማድረስ የሚገባንን ንብረት ሳናደርስና የተሽከርካሪው ባለንብረትና መንግስት ከዘርፉ ሊያገኝ የሚችለውን ገቢ እያጡ ነው።
Harari Government communication Office

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የአበርገሌ ወረዳ አራት አመራሮች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ። ባለሥልጣናቱ ትናንት ለስብሰባ ሰቆጣ ላይ በተገኙበት ነው የታሠሩት። የእስራቸው ምክንያት ያልታወቀው ባለሥልጣናት ካልተለቀቁ በሚል የአካባቢው ኅብረተሰብ የመንግሥት ሠራተኞች ወደሥራ እንዳይገቡ እንዳገደ የወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ ለዶቼ ቬለ DW ተናግረዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
263 ኢትዮጵያን ከሊባኖስ ወደአገራቸው ተመለሱ!
ባለፉት 3 ተከታታይ ቀናት በአጠቃላይ 263 ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ከልጆቻቸው ጋር ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ባለፉት 3 ተከታታይ ቀናት በአጠቃላይ 263 ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ከልጆቻቸው ጋር ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ #አዲስ_መደበኛ የቅድመ-ምረቃና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ የ2012 የትምህርት ዘመን የመግቢያ ጊዜ #ጥቅምት 8-9 ቀን 2012 ዓ/ም መሆኑን እየገለፅን
📌 በቅድመ-ምረቃ በNatural Science የተመደባችሁ ወንድ ተማሪዎች የስማችሁ የመጀመርያው ፊደል ከA እስከ D እና ሴት ተማሪዎች ከA እስከ E የሆናችሁ በሽረ ካምፓስ እንዲሁም ሌሎች ሁሉም አዲስ ተማሪዎች በዋና ግቢ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን። በተጨማሪም በ2011 ዓ/ም የአንደኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የነበራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድረው ያደረጋችሁና የመልሶ ቅበላ መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች የስርዓተ-ትምህርት ( ካሪክለም) ለውጥ የተደረገ በመሆኑ በተጠቀሰው ቀን ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፡
ሁሉም የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ፡
📌 የ10ኛ ክፍል ሰርቴፊኬት፣ የመሰናዶ ትምህርት ትራንስክሪፕት እና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ሰርቴፊኬት ዋናውንና ፎቶኮፒ
📌 የፓስፖርት መጠን ያለው የቅርብ ጊዜ 8 ጉርድ ፎቶግራፍ
📌 የግል መጠቀሚያ አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ-ልብስ፣የስፖርት ትጥቅ
📌 የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ክብ ማህተም ያረፈበት የተማሪ፣ ወላጅ እና ዩኒቨርሲቲ ውል በመያዝ በግቢያችሁ እንድትገኙ እያሳሰብን
📌 የሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች የአንደኛ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕታችሁን ከተማራችሁበት ዩኒቨርሲቲ ቀድማችሁ እንድታስልኩ እናሳውቃለን።
-የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
📌 በቅድመ-ምረቃ በNatural Science የተመደባችሁ ወንድ ተማሪዎች የስማችሁ የመጀመርያው ፊደል ከA እስከ D እና ሴት ተማሪዎች ከA እስከ E የሆናችሁ በሽረ ካምፓስ እንዲሁም ሌሎች ሁሉም አዲስ ተማሪዎች በዋና ግቢ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን። በተጨማሪም በ2011 ዓ/ም የአንደኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የነበራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድረው ያደረጋችሁና የመልሶ ቅበላ መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች የስርዓተ-ትምህርት ( ካሪክለም) ለውጥ የተደረገ በመሆኑ በተጠቀሰው ቀን ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፡
ሁሉም የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ፡
📌 የ10ኛ ክፍል ሰርቴፊኬት፣ የመሰናዶ ትምህርት ትራንስክሪፕት እና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ሰርቴፊኬት ዋናውንና ፎቶኮፒ
📌 የፓስፖርት መጠን ያለው የቅርብ ጊዜ 8 ጉርድ ፎቶግራፍ
📌 የግል መጠቀሚያ አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ-ልብስ፣የስፖርት ትጥቅ
📌 የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ክብ ማህተም ያረፈበት የተማሪ፣ ወላጅ እና ዩኒቨርሲቲ ውል በመያዝ በግቢያችሁ እንድትገኙ እያሳሰብን
📌 የሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች የአንደኛ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕታችሁን ከተማራችሁበት ዩኒቨርሲቲ ቀድማችሁ እንድታስልኩ እናሳውቃለን።
-የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩
በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
ለአትሌቲክስ ቡድናችን የምስጋናና የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ።
በዶሃ በተካሄደው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የአገራችን የአትሌቲክስ ቡድን ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብር፣ አንድ ነሐስ በድምሩ ስምንት ሜዳሊያዎችን በማስገኘት አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል። በዚህ ውጤት መሰረትም አገራችን በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ከዓለም 5ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ በአፍሪካ ደግሞ ከኬንያ በመቀጠል በሁለተኛነት ተቀምጣለች።ቡድኑ ያስመዘገበውን ስኬት ተከትሎም ኤምባሲያችን በትላንትናው እለት የምስጋና እና የሽኝት ፕሮግራም አዘጋጅቷል። በፕሮግራሙ ላይም መላው የአትሌቲክስ ቡድን፣ በዶሃ የሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ አደረጃጀት አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ እንዲሁም የቀጠር ዋና ዋና ሚዲያዎች ታድመዋል።
በዚህ ፕሮግራም ላይ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት በቀጠር የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ አትሌቶቻችን የዶሃን ከባድ የአየር ሁኔታ ተቋቁመው ባደረጉት ብርቱ ጥረት የአገራችንን ስም እና ሰንደቅ አላማ በዓለም መድረክ ከፍ እንዲል ለከፈሉት ታላቅ መስዋትነት ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከዚህ ባሻገርም በዶሃ የሚኖሩ ዜጎቻችን ያለምንም መሰልቸት እና ድካም በውድድሩ ቆይታ ወቅት ዓለምን ያስደመመ ድጋፍ እና አለኝታነት ማሳየታቸው ለድሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው አስታውሰው፣ ዜጎቻችን በምስጉንነት እና በፍጹም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት አገራችንን ከማስተዋወቅም ባለፈ ለስፖርቱ ማህበረሰብ ተስፋ ባለመቁረጥ ያላሰለሰ ድጋፍ በመስጠታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ምንጭ: በዶሃ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

የሐረር ቢራ ምርት አሽቆለቆ
በሄኒከን ኢትዮጵያ ባለቤትነት የሚተዳደረው ሐረር ቢራ ፋብሪካ ለውሃ አቅርቦት የሚጠቀምበትን በሐረሪ ክልል ፍንቅሌ ወረዳ ውስጥ የሚገኘውን የውሃ መሳቢያ መስመሮቹን እና ጄነሬተሮቹን እንዳይጠቀም ላላፉት ሁለት ዓመታት በአርሶ አደሮችና በወጣቶች በመከልከሉ ምክንያት ምርቱ ማሽቆልቆሉ ታወቀ።
ድርጅቱ 200 ሚሊየን ብር አውጥቶ የገዛቸው ጀነሬተሮችና ሌሎች መሳሪያዎችም አገልግሎት መስጠት አቁመው በፈሳሽ ማመላለሻ መኪና ውሃ ከሌሎች አካባቢዎች በማምጣት የቢራ ምርቱን መቀጠሉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የአዲስ ማለዳ ምንጮች ገልጸዋል።
Via:- Addis Maleda

የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ቀን⬆️
ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ቴሌቭዥንና በፌስቡክ ፔጃችን እንደገለጽነው የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 29 እና 30 ቀን 2012 ዓም ነው። የጂንካ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ-ምዕራብ 750 ኪሜ ላይ ትገኛለች። በአውቶብስ የሚትጓዙ በአርባ ምንጭ በኩል አድርጋችሁ ጂንካ ትደርሳላችሁ። መስከረም 29 ቀን 2012 ዓም ዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎችን ከአርባ ምንጭ ወደ ጂንካ ያጓጉዛል። ወደ ፍቅር መዲናዋ ጂንካ በሰላም
ድረሱ!
መልካም ጉዞ!
የጂንካ ዩኒቨርሲቲ
@Yenetube @Fikerassefa

ወራቤ ዩንቨርስቲ አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ መግቢያ ቀን ጥቅምት 5 ና 6 መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን ወደ ግቢ እንደትመጡ አስታውቋል ።
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
በቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ዙሪያ አዲስ አበባ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
በአማራ ክልል መንግሥት አስተባባሪነት የተዘጋጄና በቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጉዳይ የሚመክር ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌትነት ይርሳው በውይይ መክፈቻ ላይ ባሰሙት ንግግር ‹‹በቅማንት ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን አለመረጋጋት ከኮሚቴው ጋር በመሆን ሌላ ዓይነት መልክ እንዲይዝ በተቀናጀ መልኩ እየሠሩ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት እየሠራ ነው›› ብለዋል፡፡ጉዳዩን የመገናኛ ብዙኃን ባልተገባ መልኩ የአንድ ወገንን ሐሳብ ብቻ በመያዝ ማቀጣጠላቸው ተገቢ እንዳልሆነና ሊታረሙ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ጥያቄውን ለመመለስ የክልሉ መንግሥት ኃላፊነቱን ተወጥቷል፤ ቀሪ ጥያቁዎችም ካሉ በሠላማዊ መንግድ ለማስናገድ እየሠራ ነው›› ብለዋል አቶ ጌትነት በንግግራቸው፡፡
Via AMMA

የእነብርጋዲዬር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለጥቅምት 12 ቀን ተቀጠረ፡፡
የእነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የምርመራ ጉዳይ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፖሊስ ምርመራ ቡድን የጠየቁት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል፡፡
ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ረፋድ ባስቻለው ችሎት የመርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን የተጨማሪ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ አደርጓል፡፡ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም ድረስም ክስ እንዲመሠርት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡መርማሪ ቡድኑ ይግባኝ ከጠየቀበት ጊዜ ጀምሮ ተጠርጣሪዎቹ ለ64 ቀናት በማረፊያ ቤት የቆዩ በመሆናቸውና መርማሪ ቡድኑ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ መረጃ እያጣራ ያለ መሆኑን፣ ቀሪ ምስክሮችም ጥቂት መሆናቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም ክስ እንዲመሠረት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡