YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ #አዲስ_መደበኛ የቅድመ-ምረቃና ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ የ2012 የትምህርት ዘመን የመግቢያ ጊዜ #ጥቅምት 8-9 ቀን 2012 ዓ/ም መሆኑን እየገለፅን

📌 በቅድመ-ምረቃ በNatural Science የተመደባችሁ ወንድ ተማሪዎች የስማችሁ የመጀመርያው ፊደል ከA እስከ D እና ሴት ተማሪዎች ከA እስከ E የሆናችሁ በሽረ ካምፓስ እንዲሁም ሌሎች ሁሉም አዲስ ተማሪዎች በዋና ግቢ በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን። በተጨማሪም በ2011 ዓ/ም የአንደኛ ዓመት ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የነበራችሁ በተለያዩ ምክንያቶች ዊዝድረው ያደረጋችሁና የመልሶ ቅበላ መስፈርት የምታሟሉ ተማሪዎች የስርዓተ-ትምህርት ( ካሪክለም) ለውጥ የተደረገ በመሆኑ በተጠቀሰው ቀን ቀርባችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ፡
ሁሉም የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ፡
📌 የ10ኛ ክፍል ሰርቴፊኬት፣ የመሰናዶ ትምህርት ትራንስክሪፕት እና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ሰርቴፊኬት ዋናውንና ፎቶኮፒ
📌 የፓስፖርት መጠን ያለው የቅርብ ጊዜ 8 ጉርድ ፎቶግራፍ
📌 የግል መጠቀሚያ አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ-ልብስ፣የስፖርት ትጥቅ
📌 የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ክብ ማህተም ያረፈበት የተማሪ፣ ወላጅ እና ዩኒቨርሲቲ ውል በመያዝ በግቢያችሁ እንድትገኙ እያሳሰብን
📌 የሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች የአንደኛ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕታችሁን ከተማራችሁበት ዩኒቨርሲቲ ቀድማችሁ እንድታስልኩ እናሳውቃለን።

-የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa