YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩

በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
ተዘግቶ የነበረው መንገድ ተከፍቷል!

ሸኖ ላይ ለሰዓታት ተዘግቶ የቆየው መንገድ ትናንት ከምሽቱ 5:00 ሰዓት አካባቢ ተከፍቶ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል።መንገዱ በሁለቱም አቅጣጫ ነው የተከፈተው። ደብረ ብርሃን ላይ ታሰሩ የተባሉት ወጣቶችም መፈታታቸው ሰምተናል።

@YeneTube @FikerAssefa
ውዝግብ የተነሳባቸው 23 ሺህ የጋራ መኖርያ ቤቶች “ለልማት ተነሽ” አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ነገ ይሰጣሉ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት መርሀ ግብር ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተገነቡ 20/80 የጋራ መኖርያ ቤት ኮንደሚኒየሞች ውስጥ 22915 ቤቶች ነገ በአዲስ አበባ ዳርቻ ለልማት በሚል ተነስተዋል ለተባሉ አርሶ አደር አባወራዎችና 18 አመት ለሞላቸው ልጆቻቸው ለመስጠት ዝግጅቶች ተጠናቋል።ዋዜማ ራዲዮ ቤቶቹን ለመረከብ ከጫፍ ደርሰዋል ከተባሉ ግለሰቦች መረጃ ያሳያል ብሎ በሰራው ዘገባ ተነሽ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ነገ ማክሰኞ መስከረም 27 ቀን 2012 አ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የትኛው ሳይት ምን አይነት ቤት እንደደረሳቸው ይገለጽላቸዋል ተብሏል።ቀደም ብሎም የእጣ ቁጥር እንደተሰጣቸውም ታውቋል።

     ነገ ለሚከናወነው ስነስርአትም ሲባል ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተመረጡት የጋራ መኖርያ ቤቱ ተጠቃሚዎች ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ የሚወስዳቸው ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል። ጉዳዩንም የቤቱ ተጠቃሚዎች በከፍተኛ ሚስጥር እንዲይዙት የተነገራቸው መሆኑን ፣ መረጃው ከወጣም ለሂደቱ እንቅፋት ይሆናል በሚል ተነግሯቸው እንደነበር ገልጸዋል።ለአባወራ አርሶ አደር ባለ ሶስት መኝታ ቤት ኮንደሚኒየም የሚሰጥ ሲሆን 18 አመት ለሞላቸው ለእያንዳንዱ ልጆቻቸው ደግሞ በእጣ ባለ አንድም ባለ ሁለት ክፍል ኮንደሚኒየም ይሰጣቸዋል ተብሏል። ቀሪ 106 ቤቶችም ለተጠባባቂ ሰዎች መያዙንም ሰምተናል።ለአርሶአደር የልማት ተነሺዎች ከሚተላለፉት የጋራ መኖርያ ቤቶች ውስጥም በካራ ቆሬ በረከት ሳይት ከተገነቡት ውስጥ 3,500 ቤቶች እንዲሁም ኮዬ ፈጬ የተገነቡት ይገኙበታል። በዚህ ጉዳይ ላይ ልናናግራቸው የሞከርን ሀላፊዎች ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የተወሰኑት ደግሞ ጉዳዩን እንደማያውቁትም ነው የገለጹልን።

     የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ባለፈው አመት የካቲት ወር መጨረሻ የ40 /60 እና የ20/80 የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ማውጣት ስነ ስርአት ላይ ባደረጉት ንግግር መንግስት በአዲስ አበባ በልማት ምክንያት ለተነሱ አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው የጋራ መኖርያ ቤት እንደሚሰጣቸው መግለጻቸው ይታወሳል።የእጣ እድለኞች የሆኑ ቆጣቢዎች በኦሮሞ መብት ተከራካሪ ግለሰቦች አስተባባሪነት በተነሳ የወሰንና የአርሶ አደሮች የካሳ ያንሳቸዋል አመጽ የቆጠቡበትና እድለኛ የሆኑበት ቤት የወሰን ጥያቄ ኮሚቴ ተቋቁሞ ይታያል በመባሉ እስካሁን አልተላለፈላቸውም። ነገር ግን የልማት ተነሽ የተባሉ አርሶ አደሮችንና ልጆቻቸውን የመመዝገብ ስራ በሰፊው ሲሰራ መቆየቱን ከዚህ ቀደም ዋዜማ ራዲዮ መዘገቧም የሚታወስ ነው። በዚህም መሰረት የቤት ተጠቃሚ የሚሆኑት ሰዎች ቁጥር 22, 915 መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።እነዚህ የልማት ተነሽ እንደሆኑ የተነገረላቸው የቤት ተረካቢዎች ለሚሰጣቸው የጋራ መኖርያ ቤትም ምንም አይነት ክፍያ አይከፍሉም። ሂደቱም ከፍተኛ የህጋዊነትና የፍትሀዊነት ጥያቄን አስነስቷል።

 በመጀመርያ አሁን የጋራ መኖርያ ቤት እንዲያገኙ የሚደረጉት የልማት ተነሽ የተባሉት አርሶ አደሮችና ልጆቻቸው ቁጥራቸው ተጋኗል የሚል ነው።የልማት ተነሽ ያልነበሩ ግለሰቦችም በሰፊው ገብተውበታል ማንነት ላይ የተመሰረተ ምልመላም ተደርጎበታል የሚል ስሞታ በሰፊው እየቀረበ ነው።አሁን የጋራ መኖርያ ባለቤት ይሆናሉ ከተባሉት ውስጥ የዛሬ አምስት አመት አካባቢ ከካራ ቆሬ ለልማት ተብለው የተነሱት አርሶ አደሮች ይገኙበታል። በወቅቱ ከዚህ ስፍራ የተነሱ አርሶ አደር ያልሆኑ ቤተሰቦችም ነበሩ። ይሁን እንጂ የቱንም ያክል ይዞታ የነበራቸው ቢሆንም የተሰጣቸው ግን 75 ካሬ ሜትር ልዋጭ መሬት ብቻ ነው። ልዋጭ መሬቱም ለአባ ወራ ብቻ እንጂ ልጆችን አላካተተም። ቤት መስሪያ ተብሎ የተሰጣቸው ብርም በዛ ቢባል ስምንት ሺህ ብር ነበር።

    አርሶ አደር ለነበሩት ተነሺዎች ግን እስከ 500 ሺህ ብር በጥሬ ተሰጥቷቸዋል። ምትክ ቦታም ለአባወራ 500 ካሬ ሜትር ለልጆቻቸው ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 250 ካሬ ሜትር ተሰጥቷቸዋል። ከነዚህ ተነሽ አርሷ አደሮች ውስጥ አሁን ላይ በጥሩ ኑሮ ደረጃ ላይ ያሉት አሁንም ያለ ምንም ክፍያ የጋራ መኖርያ ተጠቃሚ ይሆናሉ። በተመሳሳይ ጊዜ በዚሁ ካራ ቆሬ 73 አርሶ አደር ያልሆኑ አባወራዎች ህገ ወጥ ናችሁ በሚል ያለ ምንም ካሳ ቤታቸው ፈርሶ እስካሁን ችግር ውስጥ ያሉ አሉ። ከዚህ ቀደም ከመሀል አዲስ አበባ ለልማት ተብለው የተነሱ ነዋሪዎች ኮንደሚኒየም ሲሰጣቸው ክፍያ ይጠየቁ እንደነበር ይታወሳል።እንዲሁም መንግስት ከቆጣቢ ዜጎች የሰበሰበውን ገንዘብ ጨምሮ የሰራውን የጋራ መኖርያ ቤት የ20/80 ባለእድለኛ ለሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እንዳይተላለፍ የተደረገውን እገዳ ለማንሳት ጥረት ባልተደረገበት ሁኔታ 23 ሺህ የሚደርሱ የጋራ መኖርያ ቤቶችን ለማስተላለፍ መወሰኑ የፍትሀዊነት ጥያቄን አስነስቷል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneRube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ላይ ድርሻ ሊገዛ ነው!

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ ድርሻ ለመግዛት ሃሳብ ማቅረቡ ታወቀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አሰፈፃሚ ተወልደ ገብረማሪያም እንዳስታወቁት የደቡብ አፍሪካን አየር መንገድ ለመርዳት እና የደቡብ አፍሪካ መንግሰት ፈቃደኝቱን ካሳየ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከደቡብ አፍሪካው አቻ አየር መንገዱ ላይ ድርሻ ለመግዛት ፍላጎት እንዳለው መጠቆማቸውን ዲጂታል ስታንዳርድ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ኮተቤ ሜትሮፕሊታንት ዩንቨርስቲ ⬆️
@YeneTube @Fikerassefa
በአጣዬ 8 ሰዎች ተገደሉ ተባለ።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና አካባቢዉ ከትናንት በስቲያ በተቀሰቀሰዉ ግጭት የ5 ሰላማዊ ዜጎች እና ሕይወት ማለፉ ተገለፀ። በግጭቱ ከመንግሥት ወገን 3 የፀጥታ ኃይላት መሞታቸውንና 5 መቁሰላቸውም ተገልጧል።


ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️

https://telegra.ph/Ataye-10-07
@YeneTube @Fikerassefa
የኤልያስ መልካ አስከሬን ወደ መጨረሻው ማረፊያ እየተወሰደ ነው ።

@YeneTube @Fikerassefa
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመክፈቻ ንግግር ለሁለቱ ምክር ቤቶች እያቀረቡ ነው!

የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በይፋ ተከፍቷል።ይህንንም ተከትሎ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመክፈቻ ንግግር በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።

በንግግራቸውም፦👇👇👇👇👇

https://telegra.ph/joint-opening-session-10-07

Via EBC/FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የሂልተን ሆቴል ይዞታ 70 በመቶ ወደ ግል ሊዘዋወር ነው!

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በ 2012 በጀት ዓመት ሂልተን ሆቴልን 70 በመቶ ድርሻ ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን፣ የሆቴሉ የሀብት ግመታ ጥናት እንደተረጋገጠም በሚወጣ ጨረታ ድርሻው እንደሚዘዋወር የኤጀንሲው ዳይሬክተር ጄነራል በየነ ገ/መስቀል ባሳለፍነው ሳምንት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።በዓለም አቀፉ የሂልተን ባለቅርንጫፍ ሆቴሎች አስተዳደር ስር የሆነውና ንብረትነቱ በኢትዮጵያ መንግስት ባለቤትነት የተያዘው ሂልተን ሆቴል ለገበያ እንደሚቀርብ ለአመታት ቢነገርም ቀን ግን ሳይቆረጥለት ቆይቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በፍል ውሃ አገልግሎት ድርጅት ስር ላንጋኖ የሚገኘው ሆቴል እንዲሁም ሶስት የማኑፋክቸሪንግና ስድስት የስኳር ፋብሪካዎች በዚህ ዓመት ወደ ግል ይዞታ እንደሚተላለፉ ዳይሬክተሩ ጨምረው አስታውቀዋል።በ2011 እንደ አዲስ የተዋቀረው የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አሁን በስሩ 23 የልማት ድርጅቶችን የያዘ ሲሆን፣ በዚህ ዓመትም አዶላ ወርቅና የመንግስት ነዳጅና ባዮፊዩል ኮርፖሬሽን ተዋህደው ቁጥሩ ወደ 21 ዝቅ እንደሚል ተገልፃል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በአጣዬና አካባቢው ያለውን አለመረጋት ለመቀነስ እየተሠራ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድማገኝ ተናግረዋል፡፡

‹‹የተኩስ ልውውጡ አሁን ላይ የቆመ ሲሆን በደረሰዉ ጥቃት እስካሁን የአምስት ሰዎች ሕይወት አልፏል›› ብለዋል፡፡ ሌሎች ስምንት ሰዎች ቆስለዉ ክትል እየተደረገላቸዉ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን ዘንድ የሟቾች ቁጥር ስምንት ተብሎ መዘገቡ የተሳሳተ መሆኑም ተገልጿል፡፡ተጨማሪ የሰዉ ሕይወት እንዳይጠፋና ጉዳት እንዳይደርስ ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከልዩ ኃይል ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ዛሬ ከአጣዬ ውጭ በማጀቴ አካባቢ ጥቃት ለማድረስ የተሞከረ መሆኑን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪዉ የፀጥታዉን ጉዳይ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ‹‹የታጠቁ ኃይሎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ከአጎራባች ዞኖች ጋር እየሠራን ነው›› ያሉት አቶ ተፈራ ኅብረተሰቡ እገዛ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ በፊት በአካባቢዉ በተቀሰቀሰዉ ግጭት እጃቸዉ አለበት ተብለዉ የሚጠረጠሩ አካላትን በቁጥጥር ስር በማዋል ለኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መሰጠታቸውንም ዋና አስተዳዳሪው አስታውቀዋል፡፡ ‹‹ሕግ የማስከበር ሥራዎችን ሥንሠራ ከብሔር ጋር ማያያዝ ተገቢነት የለውም የማደኛ ትዕዛዛ የወጣባቸዉ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ነዉ የያዝነዉ›› ብለዋል፡፡በአጣዬና አካባቢዉ ያለዉ አለመረጋጋት አሁን ላይ በአመዛኙ የተሻለ መሆኑን ያመለከቱት ዋና አስተዳዳሪው ኅብረተሰቡ በንቃት አካባቢዉን መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ የመከላከያና የልዩ ኃይል በቅንጅት አካባቢዉን ወደ ሠላም ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉእንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
የሙዚቃ አቀናባሪው የኤልያስ መልካ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ።

በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ አንጋፋ እና ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች፣ ቤተሰቡ፣ የሙዚቃ አፍቃሪያን እንዲሁም በያሬድ ትምህርት ቤት ያስተማሩት መምህራን እና ሌሎችም በርካታ ሰዎች ተገኝተዋል። የአርቲስቱ ስርዓተ ቀብር ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በጴጥሮስ ወ-ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ባሳለፍነው ቅዳሜ ረፋድ መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም በስኳርና በኩላሊት ህመም ምክንያት ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ጊታሪስት የሆነው ኤልያስ መልካ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያኖረ አርቲስት ነው።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2012 የትምህርት ዘመን #በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት #አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ #ጥቅምት_01 ቀን እና #ጥቅምት_02 ቀን 2012 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ አሳውቋል፡፡

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ፣
➡️ ብርድልብስና አንሶላ፣
➡️ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣
➡️ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡
➡️ የስፖርት ትጥቅ

📌 በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡
📌 ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡
📌 ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲን ድረገጽ https://
portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን
📌 ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ጥቅምት 03 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡
📌 ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
📌 ተማሪዎች ከወላጆቻቸውና በአካባቢያቸው ከሚገኙ ወረዳዎች ጋር ውል ተፈራርመው የማረጋገጫ ወረቀት ካላመጡ ዩኒቨርስቲው የማይቀበል መሆኑን በጥብቅ ያሳስባል፡፡
📌 በተጨማሪም ባለፈው ስርዓተ ትምህርት መሠረት በመጀመሪያ ዓመት 1ኛ እና 2ኛ ሴሚስተር በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች ከዘድሮ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2012 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር መልሶ ቅበላ እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡እንዲሁም መደበኛ የድህረ ምረቃ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 06 2012 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Via አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢጋድ አባል አገራት በአጠቃላይ ከ9 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የውስጥ መፈናቀል መከሰቱን በ12ተኛው የኢጋድ አባል አገራትጉባዔ ላይ ተገልጿል። የኢጋድ አባል አገራት የፈረሙትና ኢትዮጵያ የሌለችበት የካምፓላ ስምምነት በደቡብ ሱዳን ተግባራዊ ተደርጎ ለውጥ በማምጣት ላይ መሆኑ ታዉቋል። ጉባዔው ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን የሚፈናቀሉ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው በመመለስ ለዘለቄታው ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየመከረ ነው።

(ኢቢሲ)
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩

በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
የኅዳሩ የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ በምርጫ ሕግጋቱ መሠረት እንደሚደረግ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡ ለሕዝበ ውሳኔ የተዘጋጀ ሌላ ሕግ ሀገሪቱ የላትም፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ለኢቢሲ እንደተናገሩት፣ ከክልሉ አልቀው መምጣት ያለባቸው የአስተዳደር እና ሕግ ማዕቀፎ ሰነዶች እስካሁን ለቦርዱ አለቀረቡም፡፡ ቀነ ገደቡ ከመስከረም 12 ወደ 30 ተራዝሟል፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ዞኑና ክልሉ ካልተስማሙ፣ ቦርዱ የሕዝበ ውሳኔውን ሂደት ሰላማዊነት ለማረጋገጥ ይቸገራል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በአዊ ብሔ/አስ/ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ ፡፡

ከእንጅባራ ከተማ ወጣ ብሎ በአካይታ ቀበሌ በቀን 26/1/2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ስዓት አካባቢ ከእንጅባራ አምበላ ተሳፋሪ ጭኖ ይጓዝ የነበረ ኮድ 3-13645 አማ ታርጋ የሆነ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ከአዲስ አበባ ወደ እንጅባራ አቅጣጫ ከሚመጣ ሎቤድ ኮድ 3-84604 ኢት ጋር በመጋጨቱ ወዲያውኑ የ1 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሌሎቹ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በእንጅባራ አጠቃላይ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የባንጃ ወረዳ የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኢ/ር አስማረ ገብረኪዳን ተናግረው እንዲሁም በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይም ሌሎች መረጃዎችን ተከታትለን የምናደረስ ይሆናል ብሏል የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኔቲዩብ የዕለቱ ዜና YeneTube Daily News

💥የኔቲዩብን ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩን⬇️

https://youtu.be/hq6tl4ED7eM
በድሬደዋ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ።

ግጭቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ #ተደርጓል

በድሬዳዋ ከተማ በተለምዶ ገንደ ጋራ ፣ደቻቱና አምስተኛ ተብለዉ በሚጠሩ ቦታዎች ትናንት ረፋድ ጀምሮ በአካባቢዉ ነዋሪዎች መካከል ማንነት ላይ ያነጣጠረ ግጭት ተቀስቅሷል።

ይህንን በመቃወምም በደቻቱ አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች «መንግስት መፍትሄ ይስጠን» ሲሉ የከተማዋን አስተዳደር በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።

ከሰልፈኞቹ መካከል ተመርጠው ከአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያካሄዱት ነዋሪዎች "ብሄርና ማነትታችንን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እየደረሱብን ነው። አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ እና መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።

ነዋሪዎቹ "የአካባቢ /መንደር ግጭትን መፍታት ለመንግስት እንዴት አንደተሳነው አልገባንም? ምላሽ ይሰጠን ?"ሲሉም ጠይቀዋል።እንደ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ "ከአስተዳደሩ አመራር አካላት ጭምር ችግሩን በየጊዜው የሚያባብስ አካል አለ ፤ አስተዳደሩም ሆነ የፀጥታ ኃይሉ ሰላማችንን እና ደህንነታችንን በተገቢው መንገድ ሊያስጠብቅ ባለመቻሉ የፌደራል መንግስት ጣልቃ ሊገባና ለችግራችን አንድ መፍትሄ ሊሰጠን ይገባል» ብለዋል።

በድሬደዋ ከአዲስ አመት ዋዜማ ጀምሮ የተቀሰቀሰው የደቻቱ አምስተኛ፣ ገንደጋራ እና አዲስ ከተማ አካባቢዎች ግጭት ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ የቀጠለ ሲሆን በግጭቱ ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት፣ ለአካል መጉደል እንዲሁም ለንብረት ዉድመትና ዝርፊያ ምክንያት ሆኗል። የእነዚህ አካባቢዎች ትልቁ የገበያ ማዕከል ቀፊራም ተገቢውን የንግድ እንቅስቃሴ ማካሄድ ተስኖታል።

ዛሬ ለአቤቱታና ተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎችን ያነጋገሩት የአስተዳደ የድርጅት እና መንግስት ስራ ኃላፊዎች በበኩላቸዉ አስተዳደሩ በአካባቢው እየተፈጠሩ የሚገኙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ፣የችግሩ ጠንሳሽ እና አባባሽ ያላቸውን አካላት ወንጀል በማጣራና በቁጥጥር በማዋል ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ እየሰራን ነው ብለዋል ።
በሌላ በኩል ከህዝቡ ጋር ወርዶ በመወያየት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።

Via:-DW
@YeneTube @Fikerassefa
በአማራ ክልል ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ ላይ ባልታወቁ ሰዎች ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ።

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድምአገኘሁ ዛሬ በሰጠት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት የተፈጠረውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የሚያስችሉ ስራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ ነው።

በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ቦታዎች አካባቢ የተከሰተው ግጭት በጸረ-ሰላም ኃይሎች ምክንያት እንጂ በህዝቦች መካከል የተነሳ እንዳልሆነም አስረድተዋል።

ከአራት ወራት በፊት በነዚህ አካባቢዎች በተመሳሳይ መልኩ በተከሰተ ግጭት የአጣየና አካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አውስተዋል።

“ከዛ ጊዜ ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው የአስፓልት መንገድ ግራና ቀኝ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መቀሳቀስ ክልክል መሆኑ በኮማንድ ፖስት ታውጆ ነበር” ብለዋል።

ይሁን እንጂ ሰሞኑን የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሁለት ግለሰቦች አጣየ ከተማ ገበያ ሊገቡ ሲሉ በአካባቢው በጥበቃ ላይ በነበሩ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት ሊያዙ ሲሉ ተኩስ በመክፈታቸው ግጭት መፈጠሩን ተናግረዋል።

በእለቱም ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ሀይሎች የአጣየን ከተማ ለመውረርና ግጭቱን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋት ያደረጉት ሙከራ በክልሉ ልዩ ሃይል፣ በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት በተደረገ ጥረት መክሸፉን ገልጸዋል።

ይሔንን ተከትሎ በነበረው የተኩስ ልውውጥም አምስት ሰዎች ሲሞቱ አራት መቁሰላቸውን ገልጸው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሁለቱም ዞኖች አመራሮች፣ ህዝቡና የሚመለከታቸው አካላት በጋራ እየሰሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

#ENA
@YeneTube @Fikerassefa