YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
"አከተመ በቃ" የኤልያስ መልካ የቀድሞ መምህር

መምህራኑ ጭምር «በልጅነቱ የነበረው ችሎታ የሚገርም ነበር» ሲሉ የሚመሰክሩለት ኤልያስ መልካ በ42 አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ከ40 በላይ አልበሞች ከ400 በላይ ሙዚቃዎች እንደሰራ የሚነገርለት ኤልያስ ባለሙያዎች ፍትኃዊ ክፍያ ያገኙ ዘንድ እስከ ዕለተ ሞቱ ሲታገል ቆይቷል።

ሙሉውን ያንብቡ👇👇👇

https://telegra.ph/EliasMelka-10-05

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
[ Irreecha hora Finfinnee ]

የኢሬቻ በዓል አከባበር ልዩ ዝግጅት በቃላችን መሰረት የመጀመሪያ ቪዲዮ በየኔቲዩብ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ለቀናል ተመልከቱት።

አዝናኝ እንዲሁም አስተማሪ የሆነ ቪዲዮ ነው
እንድትመለከቱት ጋብዘኖታል።

መልካም በዓል !!

ቪዲዮውን ለመመልከት ሊንኩን ⬇️⬇️⬇️

https://youtu.be/el-XLVO-ZGU

ከሆራ ፊንፊኔ ጋር የተያያዘ ቀጣይ ክፍል ሰኞ የሚለቀቅ ይሆናል።

💥እንዳይረሱ ሰብስክራይብ ማድረጎን!! 💥
@YeneTube @Fikerassefa
ከወደ ካይሮ የደረሰኝ ሰበር መረጃ!

የግብፅ ፕረዚደንት ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ አሜሪካ በህዳሴ ግድብ ዙርያ የማደራደር ሚና እንድትጫወት እንደሚፈልግ ገልፁዋል!

ይህ መግለጫ የወጣው ለቀናት በካርቱም ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ የውሀ ሚኒስትሮች ውይይት ካለ ውጤት ዛሬ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። በዚህም ምክንያት ግብፅ አለም አቀፍ አደራዳሪዎች እንደሚያስፈልጉ ገልፃ ለዚህም አሜሪካንን እንዳጨች ተሰምቷል።

አሁን በደረሰኝ መረጃ ደግሞ የኢትዮጵያው ወሀ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ በካርቱም ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ነው። ዝርዝሩ እንደደረሰኝ አቀርበዋለሁ።

Via :- Elias Meseret
@YeneTube @Fikerassefa
የኢትዮጵያ መንግስት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ የተጀመረውን የሶስትዮሽ ቴክኒካዊ ምክክር ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነትን እንደማይደግፍ የኢትዮጵያው ውሃና ኢነርጂ ሚንስትር ተናግረዋል!

የግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የውሀ ጉዳይ ሚኒስትሮች መስከረም 5 እና 6 ቀን 2012 ዓ.ም በካይሮ ባካሄዱት ስብሰባ ባስቀመጡት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በካርቱም የሶስትዮሽ ስብሰባቸውን አካሂደዋል፡፡ ከሚኒስትሮቹ ስብሰባ አስቀድሞ የአገራቱ ገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን ከመስከረም 19 እስከ 22 ቀን 2012 ዓ.ም በካርቱም አምስተኛ ዙር ስብሰባውን አካሂዶ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በአገራቱ መካከል የሚደረገው ቴክኒካዊ ምክክር ብቸኛው የመፍትሄ አማራጭ በመሆኑ መቀጠል እንደሚኖርበት ያምናል፡፡የሳይንሳዊ ቡድኑ አራት ስብሰባዎችን አድርጎ አበረታች ውጤት እያሳየ ባለበት ወቅት ግብጽ በተናጠል ያቀረበችው የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅን የሚመለከተው ሰነድ ከትብብር ማዕቀፉ ውጪ የሆነ እና ሂደቱን ያናጠበ ሆኗል፡፡ ሆኖም የውሃ ሚኒስትሮች የኢትዮጵያ የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅ እቅድ፣ የግብጽ መንግስት የሚያቀርበው ሰነድ እንዲሁም ሱዳን በጉዳዩ ላይ የምታቀርበው ሰነድ ለሳይንሳዊ ቡድኑ ቀርቦ ዝርዝር ትንታኔ እንዲደረግበት እና ምክረ ሃሳብ እንዲቀርብለት በመስከረም ወር 2012 ዓ.ም በካይሮ በተደረገው ስብሰባ ወስነዋል፡፡

በካርቱም አራት ቀናትን ወስዶ በተካሄደው ስብሰባ የሳይንሳዊ ቡድኑ በመስከረም ወሩ የካይሮ ስብሰባ በተሰጠው አቅጣጫ መሠረት የኢትዮጵያን የግድብ ሙሌት እና የውሃ አለቃቅ ዕቅድ፣ እንዲሁም ሱዳን እና ግብጽ ያቀረቡትን የሙሌት እና የውሃ አለቃቅ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን የሚዳስሰውን ሃሳብ አዳምጦ ውይይቶችን አካሂዷል፡፡ ውይይቱ ሶስቱም ቡድኖች በተስማሙበት የርዕሰ ጉዳይ መዘርዝር ላይ የተመሰረተ ሲሆን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከመስማማት ተደርሶ በሌሎቹ ላይ የሃሳብ መለያየቶች ተመዝግበዋል፡፡

እነዚህ የሃሳብ #ልዩነቶች በሳይንሳዊ እና ጥናት ቡድኑ ውይይት እና ትንተና መግባባት ሊደረስባቸው የሚችሉ ናቸው፡፡ኢትዮጵያ ግድቡን እሰከ ሰባት አመት ድረስ በሚወስድ ሂደት ለመሙላት ያቀረበችው እቅድ የታችኛውን ተፋሰስ አገራት ጥቅም ለመጠበቅ ያላትን አቋም ያሳያል፡፡ ይህም በተጨማሪም ኢትዮጵያ እና ሱዳን ማናቸውም ቱክኒካዊ ጉዳዮች ለሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ ቀርበው ትንተና እንዲደረግባቸው ገንቢ እና አካታች የውይይት አካሄድ ቢከተሉም የግብጽ ወገን ያቀረብኳቸው ሃሳቦች በሙሉ ተቀባይነት ካላገኙ ውይይቱ ሊቀጥል አይችልም በሚለው የማያሰራ አቋሙ በመቀጠሉ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ ስራውን በተሟላ አኳኋን ማከናወን ሳይችል ቀርቷል፡፡ ይህ የግብጽ አቋም የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ ስብሰባ እንዲሁም የሚኒስትሮች ስብሰባው ስምምነት በተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ ጭምር ሪፖርት እንዳያዘጋጁ አድርጓል፡፡
ይህ የግብጽ አካሄድ አዲስ ሳይሆን ከዚህ ቀደምም በግድቡ ላይ ሶስቱ አገራት ሊያከናውኑት የነበረውን የውሃ፣ የአካባቢያዊ እና ማህበራዊ ተጽእኖ ጥናት በግብጽ ወገን እንዲስተጓጎል በተደረገ ጊዜ የታየ የሳይንስ እና የምክክር የመፍትሄ አማራጭን የማፋለስ ዘዴ ነው፡፡

ኢትዮጵያ አለመግባባት መፍቻ ዘዴን የሚደነግገውን የመርህ መግለጫ ስምምነቱን አንቀጽ 10 ጠቅሶ መፍትሄ ለመፈለግ ጊዜው እንዳልሆነ እና ቴክኒካዊ ምክክሩ ሊቀጥል እንደሚገባ ታምናለች፡፡የውሃ ሚኒስትሮቹ በሁለት ቀናት ስብሰባቸው የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ የደረሰበትን ተመልክተው አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም የግብጽ ወገን ቀድሞውኑ የምክክር ሂደቱ #እንዲፋረስ አቋም ይዞ የመጣ በመሆኑ ጉባኤው የሳይንሳዊ ጥናት ቡድኑ በቀጣይነት ማከናወን ስላለበት ተግባር መመሪያ ሳያስተላልፍ ቀርቷል፡፡የግብጽ መንግስት ሶስተኛ ወገን በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ እያቀረበ ያለው ሃሳብ በሶስቱ አገራት የትብብር መድረክ የታየውን አበረታች ሂደት የሚያጣጥል እና ሶስቱም አገራት በመጋቢት #2007 ዓ.ም. የፈረሙትን የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት የሚጥስ ተግባር ነው፡፡ #የሶስተኛ_ወገን_ጣልቃ-ገብነት ኢትዮጵያ እና ሱዳን የማይቀበሉት እና ተገቢ ያልሆነ፤ በአገራቱ መካከል ያለውን ዘላቂ ትብብር የሚጎዳ፤ ለውይይት ያለውን በቂ እድል ወደጎን የሚያደርግ እና ገንቢ የሆነውን የውይይት መንፈስ የሚያደፈርስ ነው፡፡

ቴክኒካዊ ምክክር የሚጠይቀው የግድብ ሙሌት እና ውሃ አለቃቀቅ ጉዳይ ለፖለቲካ ምክክር እንዲቀርብ የሚጠይቀው ሃሳብም የጉዳዩን ጠባይ ያላገናዘበ፣ የሶስቱ አገራት መሪዎች የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉዳዩን ለመፍታት የሰጡትን መመሪያ የጣሰ እንዲሁም ተገቢ መፍትሄ ለመስጠት የማያስችልም ነው፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ልዩነቶችን ለመፍታት እድል የሚፈጥረውን የምክክር ሂደት ለማጠናከር እንደሚሰራ እየገለጸ በጉዳዩ ላይ የሚሰራጨው የመገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ሌላ አሉታዊ ዘመቻ የሶስቱን አገራት መተማመን ከመሸርሸር ያለፈ ውጤት እንደማይኖረው ይገልጻል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋሚ እንደገለጸው የአባይን ውሃ የኢትዮጵያ ህዝቦችን የአሁን እና የወደፊት ፍላጎት ለማሟላት እና ብሄራዊ ጥቅምን ለማረጋገጥ ማልማቱን በመቀጠል ርትዕን የጠበቀ እና በማናቸውም የተፋሰሱ አገራት ላይ ጉልህ ጉዳት የማያደርስ አጠቃቀም እንዲኖር ይሰራል፡፡በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በሕዳሴ ግድብ ላይ በሚደረገው ውይይት የሚከተለው አቅጣጫ የናይል ውሃን አስመልክቶ ለተደረጉት እና በኢትዮጵያ ላይ ምንም አይነት ተፈጻሚነት የሌላቸውን ስምምነቶች እውቅና የማይሰጥ እንዲሁም የላይኛውን የናይል ተፋሰስ አገራት መብት የማይጥስ እንዲሆን ነው፡፡

ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩

በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
ሌሊት በተካሄደው የወንዶች ማራቶን ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ወርቋን እንዲሁም አራተኛ ብሯን አግኝታለች!

ሌሊት በተካሄደ የወንዶች ማራቶን:

1ኛ 🇪🇹ሌለሣ ዴሲሳ 2:10.40 በሆነ ጊዜ ወርቅ፣🇪🇹

2ኛ 🇪🇹ሞስነት ገረመው 2:10.44 በሆነ ጊዜ ብር፣ አግኝተዋል።🇪🇹

Via EAF
@YeneTube @FikerAssefa
የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ እየተከበረ ነው::

የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በድምቀት በመከበር ላይ ነው።በአሉ በአባገዳዎች ምርቃት ተጀምሯል።በአሉ የኦሮሞ ህዝብ የክረምት ወቅት ማለፉንና የጸደይ ወቅት መምጣቱን አስመልክቶ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው፡፡በትላንትናው እለት ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በአል በአዲስ አበባ በድምቀት መከበሩ ይታወሳል።

Via AMN
@YeneTube @FikerAssefa
በአጣዬ አካባቢ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ ወደ መረጋጋቱ ተመልሷል፤ ከኅብረተሰቡ ጋርም ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ አካባቢ ትናንት የታጠቁ ኃይሎች የፀጥታ ማደፍረስ ሙከራ አድርገው መክሸፉን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸው በቀለ እንደገለጹት ደግሞ ዛሬ ጠዋት አካባቢም የታጠቁ ኃይሎቹ ተኩስ ከፍተው ነበር፤ ነገር ግን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል፣ የፌዴራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ ሠራዊት በተቀናጀ አግባብ ሁኔታውን ተቆጣጥረውታል፡፡የፌዴራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ ሠራዊትም ከነዋሪዎች ጋር ስለሆኔታው እየተወያዩ እንደሆነ ከንቲባው ተናግረዋል፡፡

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ሳዑዲ ያልተጋቡ ጥንዶች ሆቴል እንዲከራዩ ፈቀደች።

ከዚህ ቀደም ጥንዶች በጋብቻ መተሳሰራቸውን የሚያሳይ ማረጋገጫ ካላቀረቡ ሆቴል መከራየት እንደማይችሉ የሚከለክለው ሕግ አሁን ላይ ለውጭ አገር ዜጎች ተፈቅዷል።ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን በቅርቡ ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩና ያለምንም ጠባቂ ሴቶች ከአገር ውጭ ጉዞ እንዲያደርጉ የሚያዘውን ሕግ ጨምሮ በጣም የከረሩ ሕጎች ላይ የተወሰነ ማሻሻያ ማድረጋቸው ይታወቃል።

ምንጭ:BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በምዕራብ ጎንደር ዞን ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ 53 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ሰላምና ደኅንነት ግንባታ መምሪያ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2012 ዓ.ም የሥራ ዘመን ነገ ይጀምራል!

የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ነገ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ያካሄዳሉ።በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ንግግር የያደርገጋሉ።በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማሲ ማኅበረሰብ አካላት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላትም በፕሮግራሙ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የጭነት ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ በከፊል ተነሳ!

በአዲስ አበባ ከተማ በከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ በከፊል መነሳቱ ተገልጿል።የከተማ አስተዳድሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው ከዚህ በኋላ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ከስራ ሰዓት መግቢያና መውጪያ ሰዓት ውጪ በሆኑት የትራፊክ መጨናነቅ በማይኖርባቸው ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ በከተማዋ እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዷል።በቀጣይ በመዲናዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ የተለያዩ የመፍትሄ ሃሳቦች እየተጠኑ መሆኑን ከከተማ አስተዳድሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የጭነት ተሸካርካሪዎች በመዲናዋ በሚኖራቸው እንቅስቃሴ ላይ ከሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የጊዜ ገደብ የሚያስቀምጥ መመሪያ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወሳል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ዘሪቱ ከበደ "የኤልያስ መልካ ስንብት መስከረም 26 ቀን ከቀኑ 5 :30 በብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል" ብላለች። ስንብቱ በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ይደረጋል ተብሎ ነበር። የቀብር ሥነ ስርአቱ ከቀኑ በ9 ሰአት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይከናወናል!

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የአበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ!

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአበርገሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ሁለት የድርጅት ጉዳይ የሥራ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ እንደገለጹት የሥራ ኃላፊዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ዛሬ ረፋድ ነው፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ የአማራ ክልልን ሰላምና ደኅንነት ከማይፈልጉ አካላት ጋር በድብቅ ትሥሥር አላቸው በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከፀጥታ አካላት የተገኘው መረጃ ያሳያል ሲል አብመድ ዘግቧል።
@YeneTube @Fikerassefa
ከግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በአል ተመላሾች በአሁኑ ሰአት ሸኖ ላይ ከፊትም ከኃላም መንገድ ተዘግቶባቸው ቆመዋል! ከእሬቻ ክብረ በዐል ሲመለሱ ደብረ ብርሃን የታሰሩ ወጣቶች ካልተፈቱ መንገዱን አንክፍትም ተብለዋል::

Via Atnaf Berhane
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🤩🤩🤩🤩የምስራች 🤩🤩🤩

በአ.አ በቀላሉ የማይገኙ ፤ ወደ12ሺ ሰዓቶች እና ቦርሣዎች ለትዛዝ ፤ ከ 1ሺ በላይ እቃዎች በ እጃችን መርጠው ይዘዙን ወደ ክልልም እንልካለን
ከታች ባለው ሊንክ ይጎብኙን
👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
ባለፉት 17 ቀናት ከ71ሚሊየን 393ሺ ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ተያዘ!

በጉምሩክ ኮሚሽን ህገ ወጥ ነጋዴዎችን የመቆጣጠሩ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚሁ መሰረት ባለፉት 17 ቀናት በገቢ ኮንትሮባንድነት 1,293,350 ብር የሚገመት የጦር መሳሪያን ጨምሮ ሌሎች 54,371,441 ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ጨምሮ በድምር 55,664,791 ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ ዕቃ ተይዟል፡፡በወጪ ኮንትሮባንድም 7,703,985 ብር የሆነ የዉጪ ምንዛሬ፤2,540,240 ብር የሚያወጣ የቁም እንስሳት፤1,850,000 ብር የሚያወጣ ነዳጅና ሌሎች 3,634,093 ብር የሚያወጡ እቃዎች በድምሩ 15,728,318 ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች ከአገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል፡፡

በአጠቃላይ በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድም ባለፉት 17 ቀናትj 71,393,109( ሰባ አንድ ሚሊየን ሶስት መቶ ዘጠና ሶስት ሺ አንድ መቶ ዘጠኝ ብር) የሚያወጣ የኮንትሮባንድ እቃ ተይዟል፡፡ህገ ወጥነት ከህግ በላይ ሊሆንና ከህዝቡም ሊሰወር ስለማይችል ህግን በማክበር እንስራ የገቢዎች ሚኒስቴር መልዕክት ነዉ፡፡

ምንጭ: የገቢዎች ሚንስቴር
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ፣ ‹‹የደንብ ልብሱን ለምን መቀየር አስፈለገ?›› ለሚለው ጥያቄ፣ ‹‹ነባሩ የፖሊስ የደንብ ልብስ አልተቀየረም፡፡ ወደፊት እንደ አስፈላጊነቱ በተጨማሪነት ሊሰጥ ይችላል፡፡ አዲሱ የደንብ ልብስ የተዘጋጀው በሌሎች ክልሎችም እንዳለው ሁሉ፣ ከመደበኛ ፖሊስ በተለየ በከተማው ውስጥ ሁከት ሲፈጠርና ከመደበኛው ፖሊስ አቅም በላይ ሲሆን፣ ያንን #ለሚቆጣጠር ቋሚና ተወርዋሪ ኃይል የተዘጋጀ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ቋሚና ተወርዋሪ›› ኃይሉ በዋና ዳይሬክተር የሚመራና ሙሉ ትጥቅ ያለው ኃይል ሲሆን፣ ለከተማ አስተዳደሩ ጥበቃ የተዘጋጀ የ‹‹ክብር ዘብ›› መሆኑንም ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ ⬇️
https://telegra.ph/YeneTube-10-06
በ17ኛው የኳታር ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና #ማጠቃለያ ዕለት በተካሄደው #የ10,000 ሜትር ወንዶች ሩጫ፤ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያን አግኝታለች።

ዮሚፍ ቀጀልቻ - 26:49.34 -2ኛ (ብር)

አንዱ አምላክ በልሁ, - 26:56.71 -5ኛ

ሃጎስ ገ/ህይወት - 27:11.37-8ኛ

የዩጋንዳ ተወዳዳሪ ወርቅ አግኝቷል

@YeneTube @Fikerassefa