ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ከላይ ያለውን አንቀፅ ሲተቹ ባይብሉን በቅጡ ያዩት አይመስለኝም፤ ባይብል ፀሐይ መግቢያና መውጫ አላት ይላል፦
ሚልክያስ 1፥11 ከፀሐይ #መውጫ ጀምሮ እስከ #መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፡፡
መዝሙረ ዳዊት 50፥1 ከፀሓይም #መውጫ ጀምሮ እስከ #መግቢያዋ ድረስ ምድርን ጠራት።
መዝሙረ ዳዊት 113፥3 ከፀሐይ #መውጫ ጀምሮ እስከ #መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን።

የፀሐይ መግባትና መውጣት ሰው ገባና ወጣ በተባለበት ሂሳብ ነው የቀረበው፦
ሳሙኤል ካልዕ 3፥25 የኔር ልጅ አበኔር ያታልልህ ዘንድ፥ *#መውጫህንና #መግቢያህንም* ያውቅ ዘንድ፥ የምታደርገውንም ነገር ሁሉ ያስተውል ዘንድ እንደ መጣ አታውቅምን? አለው።
ነገሥት ቀዳማዊ 3፥7 አሁንም፥ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪያህን በአባቴ በዳዊት ፋንታ አንግሠኸኛል እኔም *#መውጫንና #መግቢያን* የማላውቅ ታናሽ ብላቴና ነኝ።

የፀሐይ መግባትና መውጣት ሰው ገባና ወጣ በተባለበት ሂሳብ መሆኑን የምናቅበት ምድር ቋሚ ሆና ፀሐይ ከእንቅስቃሴ መቋረጧ ነው፦
ኢያሱ 10፥13 ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ #ፀሐይ #ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ።
ዕንባቆም 3፥11 #ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው #ቆሙ
ኢዮብ 9፥7 ፀሐይን #ያዝዛታል#አትወጣምም
አሞጽ 8፥9 በዚያም ቀን ፀሐይ በቀትር #እንድትገባ አደርጋለሁ፥

ጥያቄ ፀሐይ የምትጠልቀው የት ነው?
1.በታላቁ ባሕር?
ኢያሱ 1፥4 ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጢያውያን ምድር ሁሉ *እስከ ፀሐይ #መግቢያ እስከ #ታላቁ #ባሕር * ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።

2.በዮርዳኖስ ማዶ?
ዘዳግም 11፥30 እነርሱም *#በዮርዳኖስ #ማዶ፥ ከፀሐይ #መግቢያ ካለችው መንገድ* በኋላ፥

3.በነቢያት ላይ?
ሚክያስ 3፥6 #ፀሐይም *#በነቢያት ላይ* #ትገባለች

4. በሰራዊቱ መካከል?
1ኛ ነገሥት 22:36 በሠራዊቱም መካከል ፀሐይ ስትገባ። ንጉሡ ሞቶአልና እያንዳንዱ ወደ ከተማው፥ እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሂድ የሚል ጩኸት ሆነ።
የቱ ነው ትክክል?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም