ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሁለት
“የወር አበባ”
አምላካችን አላህ “የተበከለ” ወይም “ቆሻሻ” የሚለው ሴቷን ሳይሆን ከሴቷ የሚወጠውን የወር አበባ ነው፤ በዚህ ጊዜ ተራክቦ ማድረግ ሃራም ነው፤ “ራቋቸው” እና “አትቅረቡዋቸው” የሚለው ቃል የ”ተገናኙዋቸው” ተቃራኒ ሆኖ ስለመጣ ራቁ ማለትና አትቅረቡ ማለት ተራክቦ አታድርጉ ማለት ነው፤ ለምሳሌ ዝሙት ማለት ከጋብቻ ውጪና በፊት የሚደረግ ተራክቦ ነው፤ ይህንን ተራክቦ “አትቅረቡ” ይላል፤ ያ ማለት “አትገናኙ” ማለት እንጂ ከሰው ጋር ጤናማ ግኑኝነት አይኑራችሁ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ሴት ራቁ ማለትና አትቅረቡ ማለት ተራክቦ አታድርጉ ማለት እንጂ አትቀፏቸው፣ አትሳሟቸው፣ አብራችሁ አትተኙ ማለት አይደለም፦
2፥222 ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ “የተበከለ” ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ “ራቋቸው”፡፡ ንጹሕ እስከሚኾኑም ድረስ “አትቅረቡዋቸው”፡፡ ንጹሕ በኾኑም ጊዜ አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ “ተገናኙዋቸው”፡፡ አላህ ከኃጢኣት ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْمَحِيضِ ۖ قُلْ هُوَ أَذًۭى فَٱعْتَزِلُوا۟ ٱلنِّسَآءَ فِى ٱلْمَحِيضِ ۖ وَلَا تَقْرَبُوهُنَّ حَتَّىٰ يَطْهُرْنَ ۖ فَإِذَا تَطَهَّرْنَ فَأْتُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ أَمَرَكُمُ ٱللَّهُ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلتَّوَّٰبِينَ وَيُحِبُّ ٱلْمُتَطَهِّرِينَ ፡፡
17፥32 ዝሙትንም “አትቅረቡ”፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ وَلَا تَقْرَبُوا۟ ٱلزِّنَىٰٓ ۖ إِنَّهُۥ كَانَ فَٰحِشَةًۭ وَسَآءَ سَبِيلًۭا !

በተለይ ሱረቱል በቀራህ 2፥222 የወረደበት ምክንያት አይሁዳውያን ሴት በወር አበባ ጊዜ ስትሆን ምግብ አብረው አይበሉም በቤታቸውም አይኖሩም ስለነበርና ሰሃባዎችም ይህንን ጉዳይ ወደ ነብያችን”ﷺ” ጥያቄውን በማምራታቸው ነው፤ ነብያችንም”ﷺ” የመለሱት በወር አበባ ጊዜ ከተራክቦ በስተቀር ሁሉንም ማድረግ እንደሚቻል ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 3 , ሐዲስ 16:
አነሥ”ረ.ዓ.” እንደተረከው፦
አይሁዳውያን ሴት በወር አበባ ጊዜ ስትሆን ምግብ አብረው አይበሉም በቤታቸውም አይኖሩም፤ የነብዩም”ﷺ” ባልደረቦች ነብዩን”ﷺ” ስለ ጉዳዩ ጠየቁ፤ ከሁሉ የላቀው አላህም ይህንን አንቀፅ አወረደ፦
2፥222 ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ “የተበከለ” ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ “ራቋቸው”፡፡
የአላህም መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ሁሉን ነገር አድርጉ ከተራክቦ በስተቀር” عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ الْيَهُودَ، كَانُوا إِذَا حَاضَتِ الْمَرْأَةُ فِيهِمْ لَمْ يُؤَاكِلُوهَا وَلَمْ يُجَامِعُوهُنَّ فِي الْبُيُوتِ فَسَأَلَ أَصْحَابُ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الْمَحِيضِ قُلْ هُوَ أَذًى فَاعْتَزِلُوا النِّسَاءَ فِي الْمَحِيضِ‏}‏ إِلَى آخِرِ الآيَةِ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ اصْنَعُوا كُلَّ شَىْءٍ إِلاَّ النِّكَاحَ ‏” ።

መደምደሚያ
ከላይ የቁርአኑ አናቅፅ ላይ የሴትን ክቡድና ክቡር መሆን የሚነካ ሀይለ ቃል ሽታው እንኳን ካልተገኘ አይሁዳውያንና ክርስቲያኖች ምንን ሚዛን አድርገው ነው ሂስ ሊሰጡ የቃጣቸው? ስንል፤ የራሳቸው ባይብል ሴት በወር አበባ ጊዜዋ “እርኩስ” ናት ስለሚል ነው፤ ምን እርሷ ብቻ በንክኪ እርሷን፣ የተኛችበትና የተቀመጠችበት የሚነካትም ሆነ የምትነካው ሁሉ እርኩስ ነው፤ የወር አበባዋ የፈራረሰ እንቁላል መሆኑ ተረስቶ “እርግማን” ነው ይለናል፦
ዘሌዋውያን 15፥25 #ሴትም #ከመርገም ቀን ሌላ ደምዋ ብዙ ቀን ቢፈስስ፥ ወይም ደምዋ #ከመርገምዋወራት የሚበልጥ ቢፈስስ፥ በመርገምዋ ወራት እንደ ሆነች እንዲሁ በፈሳሽዋ #ርኵስነት ወራት ትሆናለች፤ *#ርኩስ #ናት*።
ዘሌዋውያን 15፥19 *#ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት* በሥጋዋም ያለው ፈሳሽ ነገር *#ደም ቢሆን*፥ *#በመርገምዋ* ሰባት ቀን ትቀመጣለች፤ የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ *#ርኩስ* ነው።
ዘሌዋውያን 15፥20 #መርገምም ስትሆን #የምትተኛበት ነገር ሁሉ *#ርኩስ* ነው፤ #የምትቀመጥበትምነገር ሁሉ *#ርኩስ* ነው።
ዘሌዋውያን 15፥21 መኝታዋንም #የሚነካ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ *#ርኩስ* ነው።
15፥22 #የምትቀመጥበትንም ነገር ሁሉ #የሚነካ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም *#ርኩስ* ነው።

ሙሽሪኪን ቢጠሉም አላህ መልክተኛውን በመምሪያ መጽሐፍ በእውነተኛው ሃይማኖትም በኢስላም ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው፦
48፥28 እርሱ ያ መልክተኛውን በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት በሃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው የላከ ነው፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ ۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدًۭا ፡፡
9፥33 እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُونَ ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም