ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.2K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሁለት
“አማላጅ የለም”
ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አላህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦
10፥3 *ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አላህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት፤ አትገሰጹምን?* مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

“ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት “አንድም አማላጅ የለም” ነገር ግን “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ”።
ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፤ እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦
10፥18 *ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ*፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ
6፥94 *እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአላህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ ያማልደናል የምትሉት ጠፋ* ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ

እነዚያ ጣዖታውያን በአላህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አላህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦
6፥51 *እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ*፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
40፥18 *ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም*፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع
32፥4 *ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት እናም አማላጅም ምንም የላችሁም፤ አትገሰጹምን?* مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون

“አትገሰጹምን” የሚለው ያልተገሰጹትን በዳዮች ነው፤ “ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም” የሚለው ይሰመርበት፤ “ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአላህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፤ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም ከሰዋስው አንፃር አላህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
18፥26 *ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፤ በፍርዱም አንድንም አያጋራም*። أَبْصِرْ بِهِ وَأَسْمِعْ ۚ مَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِي حُكْمِهِ أَحَدًا

አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሀረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተዋድድ ይጠቀማል፤ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው፤ “ላ” لَا የሚለው “ሐርፉ ነፍይ” አፍራሽ ቃል ነው፤ ስለዚህ በመጀመሪያው ሀረግ ላይ “ማ” مَا የሚለው “መስደሪያ” አፍራሽ ቃል ሆኖ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሃረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው አፍራሽ ቃል መደገሙ ጣኦታውያን ጣኦቶቻቸውን ወደ አላህ በማማለድ ያቀርቡናል ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፤ ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም፦
30፥13 *ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም*፤ وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ

ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለት አሊያም አላህ አማላጅ ነው ማለት አይደለም። ከአላህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፤ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አላህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሲሮችም በዚህ መልኩ ነው ተረድተው ያስቀመጡት:-
ተፍሲሩል ኢብኑ ከሲር 32፥4
*”ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው*።
( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع )
أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه .

መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ያማልዳሉ ማለት እና እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ይለያያል፤ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ሺርክ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዱዓ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

1፥5 አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ ፡፡

“ዱዓ” دُعَآء የሚለው ቃል በቁርአን 22 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ትርጉሙ “ልመና” “ጥሪ” “ፀሎት” የሚል ፍቺ ሲኖረው ለአንዱ አምላክ የሚቀርብ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ፣ መለማመንን ያሳያል፣ ዱዓ በቀውል ከሚደረጉ የአምልኮ አይነት አንዱ ነው፣ አብዛኛው ሰው ወደ ፍጡራን ዱዓ ያደርጋል፤ ነገር ግን ፍጡራን ወደ እነርሱ የሚደረግላቸው ዱዓ እስከ ቂያማ ቀን አያቁም ዝንጉዎች ናቸው፣ በቂያማ ቀን ግን ያንን ዱዓ ሰምተው እንደማያውቁ ይመሰክሩባቸዋል፣ በሰው ልብ ያለውን የሚያውቅ፣ የሁሉንም ልመና በአንድ ጊዜና በተለያየ ቦታ አይቶና ሰምቶ የሚመልስ አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
2:186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ ፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ፡፡ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡
40፥60 ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከማምለክ የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدْعُونِىٓ أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِى سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ ፡፡
60:1 እኔ የምትደብቁትንና የምትገልጹትን የማውቅ ስሆን ወደነርሱ በፍቅር ትመሣጠራላችሁ፤
34:11 እኔ የምትሠሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነኝና።

መለመን፣ መጎባደድ፣ ማሸርገድ፣ መተናነስ አላህን ብቻ ነው፤ እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም፦
7፥197 እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ ፡፡
1፥5 አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ ፡፡

የሚገርመው አጋሪዎች ዱዓ በማድረግ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው የሚይዙት አላህ፦ “ባሮቼ” የሚላቸውን መላእክትንና ነቢያትንም ነው፦
18፥102 እነዚያ የካዱት *ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን* የማያስቆጣኝ አድርገው አሰቡን? እኛ ገሀነምን ለከሓዲዎች መስተንግዶ አዘጋጅተናል أَفَحَسِبَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَن يَتَّخِذُوا۟ عِبَادِى مِن دُونِىٓ أَوْلِيَآءَ ۚ إِنَّآ أَعْتَدْنَا جَهَنَّمَ لِلْكَٰفِرِينَ نُزُلًۭا ፡፡
3:80 “መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ” ሊያዛችሁ አይገባዉም፤ እናንተ ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክሕደት ያዛችኋልን?
43:19 “መላክትን እነርሱ የአልረሕማን ባሮች” የሆኑትን ሴቶች አደረጉ፤ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በርግጥ ትጻፋለች፤ ይጠየቃሉም።
38:45 “ባሮቻችንንም” ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆበንም፣ የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የኾኑን አውሳላቸው፡፡

አንድ ሰው አንድ ነገር አምላክ አርጎ ያዘ ማለት አምላክ ብሎ መጥራት ብቻ ሳይሆን አምላክ አድርጎ መያዝም ነው፣ ያ ማለት ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠትን ያመለክታል፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25:43 ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን اتَّخَذَ ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?

ሰዎች ከአላህ ሌላ አማልክትን ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው ቢይዙም የትንሳኤ ቀን እነዚያ ዱዓ ሲደረግላቸው የነበሩት አካላት ከአምላኪዎች ተቃራኒ በመሆን አምልኮ እንዳልተቀበሉ ይክዳሉ፦
19፥81-82 *ከአላህም ሌላ አማልክትን* ለእነርሱ መከበሪያ እንዲኾኑዋቸው *ያዙ* وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةًۭ لِّيَكُونُوا۟ لَهُمْ عِزًّۭا ፡፡ ይከልከሉ፤ *ማምለካቸውን በእርግጥ ይክዷቸዋል፡፡ በእነሱም ላይ ተቃራኒ ይኾኑባቸዋል* كَلَّا ۚ سَيَكْفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمْ وَيَكُونُونَ عَلَيْهِمْ ضِدًّا ፡፡
28:62-63 አላህ የሚጠራባቸውንና እነዚያ ተጋሪዎቼ ትሏቸው የነበራችሁት የት ናቸው የሚልበትን ቀን አስታውስ፤ እነዚያ በእነርሱ ላይ ቃሉ የተረጋገጠባቸው ይላሉ «ጌታችን ሆይ! እነዚህ እነዚያ ያጠመምናቸው ናቸው፡፡ እንደጠመምን አጠመምናቸው፡፡ ከእነርሱ ወደ አንተ ተጥራራን፡፡ *”እኛን ያመልኩ አልነበሩም”*፡፡
አላህ እነርሱን እና ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸውንም የሚሰበስብባቸውን እና እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነርሱው መንገድን ሳቱ? ብሎ ይጠይቃቸዋል፦
25፥17-18 እነርሱን እና ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸውንም የሚሰበስብባቸውን እና *«እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነሱው መንገድን ሳቱ?» የሚልበትን ቀን* አስታውስ፡፡ «ጥራት ይገባህ፤ ከንተ ሌላ ረዳቶችን ልንይዝ ለእኛ ተገቢያችን አልነበረም፡፡ ግን *እነርሱንም አባቶቻቸውንም መገንዘብን እስከተዉ ድረስ* አጣቀምካቸው፡፡ ጠፊ ሕዝቦችም ኾኑ» *”ይላሉ”*፡፡

ዱዓ በቀውል ከሚደረጉ የአምልኮ አይነት አንዱ ነው፣ ሰውን በአካል ማየት፣ መስማት፣ መናገር እስከቻለ ድረስ ማነጋገሩ ተፈጥሯዊ ነው፣ ነገር ግን የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ፣ የሚናገርበት አፍ በሞት ጊዜ ስለሚፈራርሱ አይሰማም፣ አይናገርም፣ አያይም። በክርስትና ማለትም ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስና አንግሊካል ለምሳሌ ወደ ማርያም ጥሪ፣ ልመና፣ መተናነስ፣ መጎባደድ ይደረጋል፣ ይህ አይን ያፈጠጠና ጥርስ ያስገጠጠ ሃቅ ነው፣ ታዲያ ማርያም ይህን ዱዓ ትሰማለች ወይ? አይ ከተባለ ለምን ወደ ማርያም ዱዓ ይደረጋል? አዎ ትሰማለች ከተባለ በምኗ? ሰውን የምትገናኝበት ህዋሳቷ አፈር ሆኖ የለ እንዴ? በሰው ልብ ያለውን መለኮት ካልሆነች እንዴት ታውቃለች? ከአላህ ሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መለማመን፣ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ መጥራት ሽርክ ነው፦
46:5 እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለት ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُۥٓ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَٰمَةِ وَهُمْ عَن دُعَآئِهِمْ غَٰفِلُونَ ::

“መን” مَنْ የሚለው አንፃራዊ ተውላጠ ስም “ማንነት” ያላቸውን ኑባሬ ሲያመለክት፤ እነዚህ የአላህ ባሮች ዱዓን አይሰሙም፤ የሚጠሯቸው እንደ እነርሱ አላህን አምላኪዎች ናቸው፦
7:194 እነዚያ ከአላህ ሌላ *የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው*፤ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው እና ለእናንተ ይመልሱላችሁ አይችሉም إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَٱدْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ ።

እነዚህን የአላህ ባሮች ቅርፅ አበጅተው ቢለማመኑም እነርሱና የተለማመኗቸው ጣኦታት እጣ ፋንታ የገሃነም ማገዶ መሆን ነው፦
21፥98 እናንተ ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸውም የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ፡፡ እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ إِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمْ لَهَا وَٰرِدُونَ ፡፡

“ኢነኩም” إِنَّكُمْ “እናንተ” የሚለው ሁለተኛ መደብ ላይ ያሉት ሙሽሪኮች ሲሆኑ ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸው ጣዖታትም የገሃነም ማገዶዎች ናቸው፤ “ማ” َمَا የሚለው አንፃራዊ ተውላጠ-ስም አቅል የሌላቸውን ጣኦታት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ አቅል ያላቸውን ማንነቶች “መን” مَّن የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም የሚጠቀመው፤ ግን እዚህ አንቀፅ ላይ “ማ” የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም መጠቀሙ አቅል የሌላቸውን ጣኦታት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ ይህ የሰዋስው ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው። በተጨማሪም ሌላ አንቀፅ ላይ የጀሃነም መቀጣጠያ ማገዶ ድንጋይ መሆናቸው ተገልጿል፦
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን* መቀጣጠያዋ *ሰዎች እና ደንጋዮች* ከኾነች *እሳት ጠብቁ* يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًۭا وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَٰٓئِكَةٌ غِلَاظٌۭ شِدَادٌۭ لَّا يَعْصُونَ ٱللَّهَ مَآ أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ ፡፡
2፥24 ይህንን ባትሠሩ ፈጽሞም አትሠሩትምና ያችን *”መቀጣጠያዋ ሰዎችና ድንጋዮች”* የኾነችውን እሳት ተጠበቁ፤ ለከሓዲዎች ተደግሳለች፡፡ فَإِن لَّمْ تَفْعَلُوا۟ وَلَن تَفْعَلُوا۟ فَٱتَّقُوا۟ ٱلنَّارَ ٱلَّتِى وَقُودُهَا ٱلنَّاسُ وَٱلْحِجَارَةُ ۖ أُعِدَّتْ لِلْكَٰفِرِينَ

ስለዚህ ለፍጡራን ዱዓ የምታደርጉ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደሆነች ቃል ኑ፤ ይህም ቃል አላህ አንድ አምላክ ነውና ከአላህ ሌላን ላናመልክ፤ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን *ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጐ ላንይዝ ነዉ፦
3:64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደሆነች ቃል ኑ፤ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፤ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን *ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጐ ላንይዝ ነዉ*፤ በላቸዉ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማለደ እና አማለደ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ሮሜ 8፥34 *ይልቁንም* የሞተው፥ ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ *የሚማልደው* ἐντυγχάνει ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

ሮሜ8፥33 ላይ የግዕዙ ባይብል ላይ፦ “ወይትዋቀሥ በእንቲአነ” ይለዋል፤ “ይትዋቀስ” የሚለው ግስ “ተዋቀሠ” ማለትም “ተከራከረ” “ተሟገተ” ከሚል ስርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሚከራከር” “የሚሟገት” የሚል ፍቺ አለ፤ ያ ነጥብ ስለገባቸው አንድምታው ላይ፦ “ስለ እኛ ይከራከራል” ብሎ አስቀምጠውታል፤ አንዳንድ እትሞች ግሪኩን እና ግዕዙን መሰረት ያላደረገ፦ “ስለ እኛ የሚፈርደው” ብለው ተርጉመውታል፤ ይህ ከሁለት አንጻር እንደሆነ ይናገራሉ፤ አንደኛ ማማለድ የፍጡር ባህርይ ስለሆነ፤ ሁለተኛ ዐውዱ ስለ ፍርድ ስለሚያወራ ይላሉ። ግን ዐውዱ ስለ ፍርድ ይናገራል ወይ? እስቲ እንየው፦
ሮሜ 8፥31 እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ *ማን ይቃወመናል?*
ሮሜ 8፥33 እግዚአብሔር የመረጣቸውን *ማን ይከሳቸዋል*? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ *የሚኰንንስ ማን ነው?*

ዐውዱ ላይ ስለማንም ፈራጅነት አያወራም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? መልሱ ማንም።
እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? ማንም።
እግዚአብሔር ካጸደቀ የሚኰንንስ ማን ነው? ማንም።
ስንጠቀልለው፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማንም አይቃወመንም።
እግዚአብሔር ከመረጠ ማንም አይከስም።
እግዚአብሔር ካጸደቀ ማንም አይኮንንም።
ይህ ነው መልእክቱ። እከሌ ያጸድቃል ይኮንናል የሚል ሃይለ-ቃል በአንቀጹ ላይ የለም። ቀጥሎ አንቀጹ፦
ሮሜ 8፥34 *ይልቁንም* የሞተው፥ ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ *የሚማልደው* ἐντυγχάνει ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

ይህ ጥቅስ በግልጽና በማያሻማ መልኩ ኢየሱስ አማላጅ መሆኑ አስቀምጧል፣ ምክንያቱም “ዴ” δὲ ማለትም “ይልቁንም”moreover” የሚል ለይ መስተጻምር በመጠቀም ስለ ኢየሱስ አማላጅነት ይናገራል፣ “የሚማልደው” የሚለው የግሪኩ ቃል “ኢንትይንች” ἐντυγχάνει ሲሆን የሚፈርደው እያሉ ለሚቀያይሩት ሰዎች ማምለጫ መንገድ የላቸውም፣ “ኢንትይንች” ἐντυγχάνει የሚለው ቃል ግስ ሲሆን “ኢንቲአኖ” ἐντυγχάνω ማለትም “አማለደ” ከሚለው ስርወ-ቃል የመጣ ነው፣ አሁን ምን ይዋጣቸው ኢየሱስ አያማልድም ለሚሉ? ማጠናከሪያ ተመሳሳይ ቃላት፦
ዕብራውያን 7፥25 ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል፣ ስለ እነርሱም *ሊያማልድ* ἐντυγχάνειν ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ።

ሰዎች ወደ እግዚአብሔር የሚመጡት በክርስቶስ ነው ካለን፣ እግዚአብሔር ተማላጅ ነው ማለት ነው፣ በክርስቶስ ወደ እግዚአብሔር ለሚመጡት ሰዎች ደግሞ ክርስቶስ ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ይለናል፣ “ሊያማልድ” የሚለው የግሪኩ ቃል “ኢንቲቻኔን” ἐντυγχάνειν ሲሆን አሁንም “ኢንቲአኖ” ἐντυγχάνω “አማለደ” ከሚለው ስርወ-ቃል የመጣ ነው፣ አሁን ምን ይዋጣቸው ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ለሚሉት? ይህ ነጥብ የገባው ሊቀ-ጠበብት ዘሪሁን ሙላቱ በአንድ ጥያቄና መልስ መርሃ-ግብር ላይ፦ “የሚማልድ” ማለት እና “የሚያማልድ” ማለት ይለያል፤ ወይም “ማለደ” ማለት እና “አማለደ” ማለት ይለያያል ብሏል።
ልዩነቱን ሲያስቀምጥ፦ “ማለደ” ማለት “ፈረደ” ማለት ሲሆን “አማለደ” ማለት ደግሞ “ለመነ” ማለት ነው” ብሏል፤ ይህ የቃላት ጨዋታ የትኛውም የአማርኛ ሆነ የግዕዝ ሙዳየ-ቃላት ላይ ማለትም አለቃ ታዬ፣ አለቃ ኪዳነ ወልድ፣ አለቃ ከሳቴ ብርሃን ሙዳየ-ቃላት ላይ ይደግፈውም፤ የጠበብት አለቃ የተባለው ይህ ሰው በመሰለኝና በደሳለኝ የተናገረውን የቃላት ጨዋታ ይህ ጥቅስ ድባቅ ያስገባዋል፤ “የሚማልድ” ማለት “የሚፈርድ” ማለት ከሆነ “የሚማልዱኝ” ማለት “የሚፈርዱኝ” ማለት ነውን? ትርጉም አይሰጥም፦
ሶፎንያስ3፥10 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ *የሚማልዱኝ*፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።

ማለደ” ማለት “ፈረደ” ማለት ከሆነ ስለ ዓመፀኞችም “ማለደ” ማለት ስለ ዓመፀኞችም “ፈረደ” ማለት ነው? ስለ ዓመፀኞችም ከፈረደማ ወንጀል ተባባሪ ሆነ፤ ባይሆን ስለ ታዛዦችም ፈረደ መባል ነበረበት፦
ኢሳይያስ 53፥12 ስለ ዓመፀኞችም *”ማለደ”*።

ማለደ” ማለት “ፈረደ” ማለት ከሆነ እነዚህን ጥቅሶች እንዴት ትረዳዋለክ? ሙግትክ ውሃ የማያነሳና የማይቋጥር ስሁት ሙግት ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 16:38 የሮሜ ሰዎች እንደሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ መጥተውም *ማለዱአቸው* ።
የሐዋርያት ሥራ 25:3 ወደ ኢየሩሳሌምም እንዲያስመጣው *ማለዱት*።

ማለደ ማለት ፈረደ ማለት ነው ብሎ መሞገት የቋንቋ ሙግት መረጃ የሌለው እና ጉንጭ አልፋ ንትርክ ብቻ ነው። ኢየሱስ አማላጅ ከሆነ ደግሞ ተማላጅ የሚሆነው እግዚአብሔር ነው። ፊሽካው ተነፋ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ተነጥሎ ፍጡር ይሆናል።
ኢየሱስ ተማላጅ ነው የሚል ባይብል ላይ የለም ፣ ከሌለ ደግሞ ክርስቶስ እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው፣ እግዚአብሔር ወደ እግዚአብሔር ይጸልያልን? አይጸልይም የጸለየው ፍጡር ነው፦
ሉቃስ 6፥12 ሌሊቱንም ሁሉ *ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ*።

እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ቀባውን? እግዚአብሔርን ማንም አይቀባውም፤ የተቀባው ፍጡር ነው፦
ሐዋርያት ሥራ 10፥38 *እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው*፥

እግዚአብሔር ለእግዚአብሔር የበላይ ነውን? በፍጹም፤ እግዚአብሔር የፍጡራን የበላይ ነው፦
1ኛ ቆሮ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ* ልታውቁ እወዳለሁ።

እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ነውን? በፍጹም፤ ሁሉን የእርሱ እንጂ እርሱ የማንም አይደለም፦
1ኛ ቆሮ 3፥23 *ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማሻረክ ነውን?

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥36 *አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ*፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا

አምላካችን አላህ በእርሱ አምልኮ ላይ ምንንም ነገር ማንም እንዳያጋራ ከልክሏል፦
6፥151 *«ኑ፤ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር ላንብብላችሁ» በላቸው፡፡ «በእርሱ ምንንም ነገር አታጋሩ*፡፡ قُلْ تَعَالَوْا أَتْلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمْ عَلَيْكُمْ ۖ أَلَّا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا
4፥36 *አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ*፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا

ብዙ አንቀጾች ላይ “ እኔን ብቻ አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ተናግሯል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ

ይህ እንዲህ በእንዲህ እያለ በተቃራኒው ሚሽነሪዎች፦ "አላህ መልእክተኛውን ነብያችን”ﷺ” ከራሱ ጋር አሻርኮታል" ብለው ውሃ የማያነሳ ስሁት ሙግት ያቀርባሉ፤ ለዚህም እንደመነሻ የሚያነሷቸው አናቅጽ አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾች ላይ፦ "አላህ እና መልእክተኛው ታዘዙ" "አላህ እና መልእክተኛው እመኑ" "አላህ እና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ" ማለቱን ነው፤ እውን እነዚህ ዓረፍተ-ነገር ወደዚያ ድምዳሜ ላይ ያደርሳሉን? እስቲ የሚጠቅሷቸውን ጥቅሶች በሰላ እና በሰከነ አይዕምሮ እንመልከታቸው፦

ነጥብ አንድ
"ታዘዙ"
አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾች ላይ "አላህን እና መልክተኛውን ታዘዙ" ይላል፦
3፥32 *«አላህን እና መልክተኛውን ታዘዙ*፡፡ ብትሸሹም አላህ ከሓዲዎችን አይወድም» በላቸው፡፡ قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ ۖ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ፦ "አላህን ታዘዙ" ማለት የአላህ ንግግር የሆነውን ቁርአን መመሪያ አድርጉ ማለት ነው፤ "መልእክተኛው ታዘዙ" ማለት ነብያችን”ﷺ” በሐዲስ የተናገሩትን መመሪያ አድርጋችሁ ያዙ ነው፤ "ታዘዙ" ማለት "አምልኩ" ማለት አይደለም፤ "አዕብዱ" اعْبُدُوا ማለት "አምልኩ" ማለት ሲሆን "አጢዑ" أَطِيعُوا ማለት ደግሞ "ታዘዙ" ማለት ነው፤ እዚህ ጥቅስ ላይ የመጣው "አጢዑ" ለአሚሮችም አገልግሎት ላይ ውሏል፦
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *አላህን ታዘዙ፣ መልክተኛውን እና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ

"የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ" ስለተባለ የስልጣን ባለቤቶችን መታዘዝ አላህ ላይ ማጋራት ነውን? በፍጹም! "ታዘዙ" ማለት "አምልኩ" ማለት ቢሆን ኖሮ ኑሕ ሹዕይብ፣ ዒሣ የመሳሰሉት መልእክተኞች "ታዘዙኝ" ባላሉ ነበር፦
71፥3 «አላህን ተገዙት፣ ፍሩትም፣ *ታዘዙኝም" በማለት አስጠንቃቂ ነኝ፡፡ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاتَّقُوهُ وَأَطِيعُونِ
26፥179 «አላህንም ፍሩ፤ *ታዘዙኝም*፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
43፥63 «አላህንም ፍሩ፤ *ታዘዙኝም*፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ

እናማ ቁርኣኑ የሚለው፦ "አላህን ብቻ ታዘዙ" ነው፤ ብለው አሁንም ይሞግታሉ፦
22፥34 *አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِين

እውነት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ “ታዘዙ” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “አሥሊሙ” أَسْلِمُوا ሲሆን “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፤ ይህ ቃል ለአላህ ብቻ የሚውል ቃል ነው፤ "አጢዑ" ከሚለው ጋር በቃላትም አይመሳሰልም። “አሥሊሙ” ግን “ሙሥሊም” مُسْلِم ለሚለው ቃል ትእዛዛዊ ግስ ነው፤ አላህ ለኢብራሂም “አሥሊም” أَسْلِمْ ማለትም “ታዘዝ” ብሎ ሲለው እርሱም ለዓለማት ጌታ “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ማለትም “ታዘዝኩ” አለ፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ *”ታዘዝ”* ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ *”ታዘዝኩ”* አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

“ኢሥላም” إِسْلَٰم ደግሞ የሙስሊም ሃይማኖቱ ሲሆን "መታዘዝ" መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው፤ አላህ፦ "ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ" የሚለን፤ “መታዘዝ” ለሚለው ቃል የገባው “ሲልም” سِّلْم መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፦
2፥208 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱدْخُلُوا۟ فِى ٱلسِّلْمِ كَآفَّةًۭ
ነጥብ ሁለት
"ፍርድ"
“አል-ሐከም” الحَكَم ከአላህ ስሞች አንዱ ሲሆን ትርጉሙ “ፈራጅ ወይም ዳኛ” ማለት ሲሆን “ሁክም” حُكْم ማለትም "ፍርድ" ደግሞ የእርሱ ባህርይ ነው፤ አምላካችን አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ ነው፤ በፍርዱ ቀን ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው፤ እርሱ የፍርዱ ቀን ባለቤት ነው፤ በዚያ ቀን በፍርዱ ማንንም አያጋራም፦
95፥8 *አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? ነው*፡፡ أَلَيْسَ اللَّهُ بِأَحْكَمِ الْحَاكِمِين
10፥109 ወደ አንተም የሚወረደውን ተከተል፡፡ *አላህም በእነርሱ ላይ እስከሚፈርድ ድረስ ታገስ፡፡ እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነው*፡፡ وَاتَّبِعْ مَا يُوحَىٰ إِلَيْكَ وَاصْبِرْ حَتَّىٰ يَحْكُمَ اللَّهُ ۚ وَهُوَ خَيْرُ الْحَاكِمِينَ
1፥4 *የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው*፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
6፥62 *ከዚያም እውነተኛ ወደ ኾነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡ ንቁ! ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው*፡፡ እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው፡፡ ثُمَّ رُدُّوا إِلَى اللَّهِ مَوْلَاهُمُ الْحَقِّ ۚ أَلَا لَهُ الْحُكْمُ وَهُوَ أَسْرَعُ الْحَاسِبِينَ
18፥26 ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ *በፍርዱም አንድንም አያጋራም*፡፡ مَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِي حُكْمِهِ أَحَدًا

አምላካችን አላህ የፈራጆች ሁሉ ፈራጅ ሲሆን በዱኒያህ ግን ለሁሉም ነብያት ማለትም ለሉጥ፣ ለዩሱፍ፣ ለሙሳ፣ ለዳውድ፣ ለሱለይማን ወዘተ የሚፈርዱበት ፍርድ ሰቷቸዋል፦
21፥74 *ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا
12፥22 *ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ፍርድን እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንደዚሁም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
28፥14 ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ *ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንዲሁም መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ وَاسْتَوَىٰ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
21፥79 *ለሱለይማንም ትክክለኛይቱን ፍርድ አሳወቅነው፡፡ ለሁሉም ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠን*፡፡ فَفَهَّمْنَاهَا سُلَيْمَانَ ۚ وَكُلًّا آتَيْنَا حُكْمًا وَعِلْمًا

አላህ ለሁሉም ፍርድ እና ዕውቀትን እንደሰ ለነብያችንም"ﷺ" ቁርኣንን እና ሱናው ፍርድ አድርጎ ሰጥቷል፦
5፥49 *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ*፡፡ وَأَنِ احْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ
5፥42 *ብትፈርድም በመካከላቸው በትክክል ፍረድ፤ አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና*፡፡ وَإِنْ حَكَمْتَ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِالْقِسْطِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

"ፈራጆች" የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ስለዚህ ለነብያችን”ﷺ” በመታዘዝ እና ለአላህ በመገዛት ፍርድን በዱንያህ እንቀበላለን፤ "አላህ እና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ" የሚለው ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ እንጂ በፍርድ ቀን ስለሚፈረደው ፍርድ በፍጹም አይደለም፦
24፥51 *የምእምናን ቃል የነበረው ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ፦ "ሰማን እና ታዘዝንም" ማለት ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا كَانَ قَوْلَ الْمُؤْمِنِينَ إِذَا دُعُوا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ لِيَحْكُمَ بَيْنَهُمْ أَن يَقُولُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا
33፥36 *አላህ እና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ*፡፡ وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ وَلَا مُؤْمِنَةٍ إِذَا قَضَى اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَمْرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ مِنْ أَمْرِهِمْ ۗ وَمَن يَعْصِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا مُّبِينًا

"የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ" የሚለው ይሰመርበት፤ "ትእዛዝ" የሚለው "ፍርድ" በሚል ተለዋዋጭ ቃል እንደመጣ ልብ በል፤ ስለዚህ ይህ ከማጋራት ጋር አንዳች ግንኙነት የለውም። ኢንሻላህ በክፍል ሁለት የተቀረውን ነጥብ እንጨርሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማሻረክ ነውን?

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥36 *አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ*፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا

ነጥብ ሦስት
“እመኑ”
አምላካችን አላህ፦ “በአላህ እና በመልክተኛው እመኑ” ብሏል፤ በእርሱ እና በመልክተኛው ያላመነም ሰው ለእርሱ እሳትን አዘጋጅቷል፦
57፥7 *በአላህ እና በመልክተኛው እመኑ*፡፡ آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ
48፥13 *በአላህ እና በመልክተኛው ያላመነም ሰው እኛ ላከሓዲዎች እሳትን አዘጋጅተናል*፡፡ وَمَن لَّمْ يُؤْمِن بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ فَإِنَّا أَعْتَدْنَا لِلْكَافِرِينَ سَعِيرًا

አላህ በነብያችን”ﷺ” “እመኑ” ያለው ለእኛ ብቻ ሳይሆን በዒሣ ዘመንም ለሐዋርያት፦ “በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ” ብሏል፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም *«በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ»* በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي

እረ እንደውም ቁርኣን ሲወርድም፦ “በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ” ብሏል፤ በሁሉም መልእክተኞ ለካዱት ሰዎች እሳት ተዘዛግቶላቸዋል፦
4፥171 *በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ*፡፡ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِه
3፥79 *በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ*፡፡ فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرُسُلِه
11፥27 *ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው*! فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ كَفَرُوا مِنَ النَّارِ

ስለዚህ “እመኑ” ማለት “አምልኩ” ማለት አይደለም፤ “እመኑ” ማለት ማሻረክ ቢሆን ኖሮ “በአላህ እና በመልክተኞቹም እመኑ” በማለት ሁሉንም መልእክተኞ ያካትት ነበርን? ይህ ሥነ-አመክኖአዊ ተፋልሶ”logical fallacy” ነው።

መደምደሚያ
አምላካችን አላህ የነገረን፦ “በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው” በማለት ነው፤ ይህን መመሪያ የተቀበለ ሙስሊም ይባላል፤ እርሱ ስለ ሙስሊም ሲናገር፦ “በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያመልኩኛል” በማለት ነው፦
29፥8 *ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው*፡፡ وَإِن جَاهَدَاكَ لِتُشْرِكَ بِي مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا
24፥55 *በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያመልኩኛል*፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡ يَعْبُدُونَنِي لَا يُشْرِكُونَ بِي شَيْئًا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ

ከፈጣሪ ጋር አብረው የተጠቀሱ አካላት ማሻረክ ከሆነ እኛም በተራችን ከባይብል ጥያቄ እንጠይቃለን፤ ሳኦል ከእግዚአብሔር ጋር እና በሚል መስተጻምር ተያይዟል፦
1ሳሙ 12፥3 እነሆኝ *በእግዚአብሔር እና “በመሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ፊት መስክሩብኝ* የማንን በሬ ወሰድሁ?
1ሳሙ 12፥5 እርሱም፦ በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ *እግዚአብሔር እና “መሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው* አላቸው፤

“ፊት” በሚል በነጠላ ስም እና በአያያዥ መስተጻምር ሳኦል ከእግዚአብሔር ጋር ስለተቀመጠ ሳኦል አምላክ ነውን? የእስራኤል ጉባኤውም ሁሉ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔር እና ለንጉሡ ለዳዊት ሰገዱ፦
1ኛ ዜና መዋዕል 29፥20 ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው *”ለእግዚአብሔር እና ለንጉሡ ሰገዱ”*።

“ሰገዱ” በሚል በነጠላ ግስ እና በአያያዥ መስተጻምር ዳዊት ከእግዚአብሔር ጋር ስለተቀመጠ ዳዊት አምላክ ነውን? እግዚአብሔርን እና ንጉሡን ሰለሞንን ፍራ ተብሎ በአንድ መደብ ተቀምጧል፦
ምሳሌ 24፥21-22 ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን እና ንጉሥን *”ፍራ”*፥ ከዓመፀኞችም ጋር አትደባለቅ። *”መከራቸው”* ድንገት ይነሣልና፤ *”ከሁለቱ የሚመጣውን”* ጥፋት ማን ያውቃል?

“ፍራ” በሚል በነጠላ ግስ እና በአያያዥ መስተጻምር ሰለሞን ከእግዚአብሔር ጋር ስለተቀመጠ ሰለሞን አምላክ ነውን? የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር እና በሙሴ አመኑ፦
ዘጸአት 14፥31 ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፥ *በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ*።

“አመኑ” በሚል በነጠላ ግስ እና በአያያዥ መስተጻምር ስለተቀመጠ ሙሴ አምላክ ነውን? በእግዚአብሔር እመኑ በነብያትም እመኑ ተብላል፦
 2ኛ ዜና 20፥20 *በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ*፥ ትጸኑማላችሁ፤ *በነቢያቱም እመኑ*፥ ነገሩም ይሰላላችኋል አለ።
ዮሐንስ 14፥1 *በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ*።

“በእግዚአብሔር እመኑ” ማለት እግዚአብሔር ላኪ መሆን እመኑ ማለት ሲሆን “በነቢያቱም እመኑ” ማለት ደግሞ ነብያት ተላኪ መሆናቸውን እመኑ ማለት ነው።
በዚህ አጋጣሚ እግዚአብሔር እና ኢየሱስ በሁለት መደብ ብዙ ጊዜ መቅረባቸው ማሻረክ እንዳልሆነ እግረ-መንገዴን ጠቁሜ ልለፍ፦
መዝሙር 2፥2-3 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም *በእግዚአብሔር እና በመሢሑ* ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ፦ *ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም* ከእኛ እንጣል።

እግዚአብሔር እና ኢየሱስ “ማሰሪያቸው” “ገመዳቸው” በሚል እንጂ “ገመዱ” ማሰሪያው” በሚል አለመቅረቡ ሁለት የተለያዩ ህልውናዎች መሆናቸውን ያሳያል፦
ራእይ 21፥22 *ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸውና*።

“ናቸው” እንጂ “ነው” አለመሆኑ ሁሉንም የሚገዛ አንድ ጌታ አምላክ እና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ህልውናዎች መሆናቸውን ያሳያል፦
2 ተሰሎንቄ 2፥17 ራሱ *ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን* ልባችሁን *ያጽናኑት* በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ *ያጽኑአችሁ*።

“ያጽናኑት” “ያጽኑአችሁ” የሚሉት የብዜት ግስ ኢየሱስ እና እግዚአብሔር ሁለት የተለያዩ ህልውናዎች መሆናቸውን ያሳያል። ብዙ ማቅረብ ይቻል ነበር ግን ይህ በቂ ነው። በሰፈሩት ቁና መስፈር ይሉሃል እንደዚህ ነው።

 ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ንብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥68 *ጌታህም ወደ ንብ* እንዲህ ሲል አስታወቀ፦ *"ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ"*፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ

ንብ በራሪ ነፍስ"insect" ናት፤ ከሶስት አፅቂዎች የምትመደብ ስትሆን ልክ እንደ ጉንዳን ካሉ "Hymenoptera" ቤተሰብ ትመደባለች፤ ይህቺ በራሪ ነፍስ በማር እና በሰም ምርቷ ትታወቃለች፤ በምድራችን ላይ ከ20,000 በላይ የታወቁ የንብ ዝርያዎች ሲኖሩ እነዚህም በዘጠኝ ታዋቂ ቤተሰቦች ተከፋፍለዋል፤ ምን አለፋን ከተጠቀሰው ቁጥር በላይ ዝርያዎች ሊኖሯቸውም ይችላል።
ንብ የራሷን ቤቶች የምትሰራው ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ነው፤ ይህንን ሥርአት ያሳወቃት ንድፍ አውጪው አምላካችን አላህ ነው፦
16፥68 *ጌታህም ወደ ንብ* እንዲህ ሲል አስታወቀ፦ *"ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ"*፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ

ንብ አበባዎች ባሉበት ሁሉ ትገኛለች፤ የንብ አካላቷ በሦስት ክፍል ይከፈላል፤ አንደኛው ክፍል የምታሸትበት፣ የምትዳስስበት፤ የምትሰግበት፣ በግንባሯ በስተቀኝና በስተግራ ሁለት ቀጫጭን ነገሮች እንደ ቀንድ የሆኑ አሏት፤ ደግሞ በዚህ በገጿ ላይ ሁለት ትልልቅ ጠፍጣፋ ዓይኖች በግራና በቀኝ ሆነው ለማየት የሚያስችሏት በሌሎች ትንንሽ ዓይኖች የተሞሉ አሏት።
ሁለተኛው ክፍል የአካሏ ክፍል ፀጉራሞች የሆኑ በአበባ ውስጥ ያለውን ኔክታር ማለትም ፈሳሽ ነገር ስትመጥ የአበባ ዱቄት የምታመጣባቸው ስድስት እግሮች፣ ሁለት ወፈር ያሉ ክንፎችና ሌሎች ሁለት ሳሳ ያሉ ክንፎች በጠንካሮች ሥር የሆኑ አሏት።
በሦስተኛው የአካላት ክፍሏ እንደ አንጓ ክርክር ያላቸው መተንፈሻዎች የምትነድፍበትና የተበላሸውን የምታስወጣበት አሏት።
ከፍራፍሬ ከሚገኘው የአበባ ዱቄት ምግቧን ትብላለች፤ ይህንን የተፈጥሮ ሥርአት የነደፈላት አምላካችን አላህ ነው፦
16፥69 «ከዚያም *ከ*ፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ ثُمَّ كُلِي مِن كُلِّ الثَّمَرَات

"ፍሬዎች" በሚለው ቃል ላይ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መግባቱ ከፍሬዎች ሁሉ መካከል መብላቷን ያሳያል እንጂ ፍሬዎችን ሁሉ አያሳይም። ንብ ወለላን ቱቦ በመሰለው ምላሷ ከፍራፍሬ ከሚገኘው የአበባ ዱቄት ቅሥም አውላ እየቀሰመች በሆዷ ውስጥ ባለ የማር ቋት ውስጥ ታጠራቅማለች፤ አምላካችን አላህ፦ "ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል" የሚለው ይህንኑ ነው፤ ከዚያም ተሸክማ ወደ ወደ ቀፎዋ ትወስደዋለች፤ ቀጥሎም ፈሳሽ የአበባ ወለላውን ወደ ሌሎች ንቦች ታዘዋውረዋለች፤ ወለላውን በአፏ ውስጥ ካሉት እጢዎች ከሚመነጭ ኢንዛይም ጋር እያዋሐደች ለአንድ ሰዓት ከግማሽ ያህል ታላምጠዋለች፤ ከዚያም ከሰም በተሠሩ ባለ ስድስት ማዕዘን ክፍሎች ውስጥ ታስቀምጥና እርጥበቱ እንዲተን በክንፎቿ ታራግባለች፤ የውኃው መጠን ከ18 በመቶ በታች ሲሆን ክፍሎቹን በሰም በስሱ ትሸፍነዋለች፤ በዚህ መልኩ የተሸፈነ ማር ሳይበላሽ ለዘመናት ሊቆይ ይችላል። ይህ ማር ምግብ ከመሆኑም ባሻገር በቫይታሚን ቢ፣ በተለያዩ ማዕድናት እና አንቲኦክሲደንትስ በተባሉ ንጥረ ነገሮች የበለጸገ መሆኑ መድኃኒት ነው፤ ማር ቁስልን፣ የተቃጠለ የአካል ክፍልን፣ የዓይን ቆዳ መሸብሸብን እና በቆዳ ላይ የሚወጣ ቁስልን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ የጤና ችግሮችን ለማከም ዛሬ አገልግሎት ላይ ይውላል፤ ንብ በአበባ ፈሳሹ ላይ ኢንዛይም ስለምትረጭ ማር ለስለስ ያለ የፀረ ባክቴሪያነትና አንቲባዮቲክነት ባሕርይ እንዳለው ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይህንን ያገራላት አምላካችን አላህ ነው፤ በማር ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት እና ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለበት፦
16፥69 *የጌታሽንም መንገዶች ላንቺ የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለበት*፡፡ فَاسْلُكِي سُبُلَ رَبِّكِ ذُلُلًا ۚ يَخْرُجُ مِن بُطُونِهَا شَرَابٌ مُّخْتَلِفٌ أَلْوَانُهُ فِيهِ شِفَاءٌ لِّلنَّاسِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ምሪት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥9 *ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል*፡፡ إِنَّ هَـٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ

ነብያችን”ﷺ” ቁርኣን ወደ እርሳቸው መወረዱን ተስፋ ሳያደርጉ ከቁርኣን በፊት ምንም ሳይሉ ማለትም፦ “ነብይ ወይም መልእክተኛ ነኝ” ሳይሉ ብዙ ዕድሜ 40 ዓመት በእርግጥ ኖረዋል፦
28፥86 *መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም፡፡ ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ፡፡ ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን*፡፡ وَمَا كُنتَ تَرْجُو أَن يُلْقَىٰ إِلَيْكَ الْكِتَابُ إِلَّا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۖ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرًا لِّلْكَافِرِينَ
10፥16 አላህ በሻ ኖሮ በእናንተ ላይ ባለነበብኩትም፤ አላህ እርሱን ባላሳወቃችሁም ነበር፡፡ *በእናንተም ውስጥ ከእርሱ በፊት ምንም ሳልል ብዙን ዕድሜ በእርግጥ ኖሬአለሁ፤ አታውቁምን?* በል። قُل لَّوْ شَاءَ اللَّهُ مَا تَلَوْتُهُ عَلَيْكُمْ وَلَا أَدْرَاكُم بِهِ ۖ فَقَدْ لَبِثْتُ فِيكُمْ عُمُرًا مِّن قَبْلِهِ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

ከቁርኣን መውረድ በአርባ ዓመት ውስጥ መጽሐፍን የሚያነቡ በቀኛቸውም የሚጽፉ አልነበሩም፤ አላህ ምንም የማያውቁ ሆነው ሳሉ ቁርኣንን በማውረድ መራቸው፦
29፥48 *ከእርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም*፡፡ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራጠሩ ነበር፡፡ وَمَا كُنتَ تَتْلُو مِن قَبْلِهِ مِن كِتَابٍ وَلَا تَخُطُّهُ بِيَمِينِكَ ۖ إِذًا لَّارْتَابَ الْمُبْطِلُونَ
93፥7 *የሳትክም ኾነህ አገኘህ መራህም*፡፡ وَوَجَدَكَ ضَالًّا فَهَدَىٰ

"የሳትክ" የሚለው ቃል "አዷል" أَضَلّ ሲሆን "ባዶ" "ምንም"lost" የሚል ፍቺ አለው፤ "ባዶ" "ምንም" ነበርክ ማለት "መጽሐፉም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም" ማለት ነው፤ "መራንህ" የሚለው "የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው" በሚል መጥቷል፦
42፥52 እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን አወረድን፡፡ *መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም*፡፡ ግን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ *የምንመራበት ብርሃን አደረግነው*፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَـٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

ስለዚህ የሳትክ ነበር ማለት መጽሐፉም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም ማለት ሲሆን ቁርኣንን የሚመራበት ብርሃን አድርጎ መራቸው ማለት ነው። ይህ ቁርኣን ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራል፦
17፥9 *ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል*፡፡ إِنَّ هَـٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ

አንቀጹ ይቀጥልና፦ "ድኻም ኾነህ አገኘህ አከበረህም" ይላል፤ ሃብት ሙሉነት ሲሆን ድህነት ባዶነት እውነተኛ ሃብት ደግሞ የነፍስ ሃብት ቁርኣን ነው፤ ስለዚህ የሳት ነበርክ ማለት የቁርኣን ዕውቀቱ አልነበረክም ደሃ ነበርክ፤ መራንህ ማለት የነፍስ ሃብት በሆነው ቁርኣን አከበርንህ ማለት ነው፤ ታላቁ ሙፍሲር ኢብኑ ከሲር በዚህ መልኩ ነው ያስቀመጠው፦
93፥8 *ድኻም ኾነህ አገኘህ አከበረህም*፡፡ وَوَجَدَكَ عَائِلًا فَأَغْنَىٰ
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 81, ሐዲስ 35
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ሃብት ማለት መጠነ ሰፊ ንብረት መያዝ አይደለም። ነገር ግን ሃብት ማለት የነፍስ ሃብት ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لَيْسَ الْغِنَى عَنْ كَثْرَةِ الْعَرَضِ، وَلَكِنَّ الْغِنَى غِنَى النَّفْسِ ‏"‌‏.‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ተሸካሚ ነፍስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም*፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ

በቁርአን እስተምህሮት ውስጥ እንደ ክርስትናው “ጥንተ-ተአብሶ”Original sin” ማለትም እንደ ስኳርና ሳይነስ ለትውልድ በዘር የሚተላለፍ ኃጢአት የለም፤ ኃጢአት ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም፤ አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾቹ ላይ፦ "ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን
ኃጢአት አትሸከምም" እያለ ይነግረናል፦
17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም*፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ

ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሚሽነሪዎች፦ "በኢስላም አስተምህሮት ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት ትሸከማለች" በማለት ሐዲሱ ለማለት ያልፈለገውን እጁን ጠምዝዘው ለማስባት ይሞክራሉ፤ ይህ በሥነ-አፈታት ጥናት"hermeneutics" ውስጥ "ስሁት ትርጓሜ"Eisegesis" ይባላል፤ አብዛኛውን ሳይፈሩና ሳያፍሩ ሳይማሩና ሳይመራመሩ ስሁታን የሆኑ ታካቾች ይጠቀሙበታል። በተቃራኒው ተረድቶ ለማስረዳት ዐውቆ ለማሳወቅ አምኖ ለማሳመን የአንድ ዓረፍተ-ነገር ዐውዱ ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ተብሎ እራሱ እንዲናገር ማድረግ ደግሞ "ስሙር ትርጓሜ"Exegesis" ይባላል፤ ይህንን አብዛኛው ጊዜ የሚጠቀሙበት ሊኅቃን የሆኑ ምሁራን ናቸው። እስቲ ሐዲሱን በአጽንኦትና በአንክሮት እንየው፦
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 50, ሐዲስ 60
አቢ ቡርዳ እንዳስተላለፈው ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ *"በትንሳኤ ቀን ከሙስሊሞች ሰዎች እንደ ተራራ ከሚመስል ወንጀላቸው ይመጣሉ፤ አላህም ይቅር ይላቸዋል። በእነርሱ ምትክ አይሁዳውያንን እና ክርስቲያኖችን ያስቀምጣል*። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ يَجِيءُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ نَاسٌ مِنَ الْمُسْلِمِينَ بِذُنُوبٍ أَمْثَالِ الْجِبَالِ فَيَغْفِرُهَا اللَّهُ لَهُمْ وَيَضَعُهَا عَلَى الْيَهُودِ وَالنَّصَارَى ‏"

እዚህ ሐዲስ ላይ የሙስሊሞችን ኃጢኣት አይሁድ እና ክርስቲያን ይሸከማሉ የሚል ሽታው እንኳን የለም፤ ከሙስሊሞች እንደ ተራራ ከሚመስል ወንጀላቸው ሲመጡ አላህ ይቅር ይላቸዋል፤ አንደኛ ይቅርታ የሚያገኙት በነብያችን"ﷺ" ምልጃ ሁለተኛ እስካላሻረኩት ድረስ ተቀጥተው ምህረትን ያገኛሉ እንጂ የእነርሱ ኃጢኣት በአይሁድ እና በክርስቲያን ላይ ያደርጋል የሚል ሽታው እንኳን የለም፤ ታዲያ "ምትክ" የሚለው ምንድን ነው? ሐዲሱ እዛው ላይ ይቀጥላል፦
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 50, ሐዲስ 58
አቢ ቡርዳ እንዳስተላለፈው ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ሙስሊም አይሞት የእርሱ ቦታ አላህ አይሁድ ወይም ክርስቲያንን በእሳት ቢያደርግ እንጂ*። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ يَمُوتُ رَجُلٌ مُسْلِمٌ إِلاَّ أَدْخَلَ اللَّهُ مَكَانَهُ النَّارَ يَهُودِيًّا أَوْ نَصْرَانِيًّا ‏ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 50, ሐዲስ 57
አቡ ሙሣ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ የትንሳኤ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ *አላህ ለሁሉም ሙስሊም አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን ያስቀምጣል፤ "ይህ ከእሳት የእናንተ ምትክ ነው" ይባላል*። عَنْ أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِذَا كَانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ دَفَعَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ إِلَى كُلِّ مُسْلِمٍ يَهُودِيًّا أَوْ نَصْرَانِيًّا فَيَقُولُ هَذَا فَكَاكُكَ مِنَ النَّارِ ‏"
አንድ አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን ቢያምን ኖሮ በጀነት የሚያገኘውን ቦታ ስላላመነ ሙስሊሙ በማመኑ የእርሱን ቦታ በገነት ያገኛል። በተቃራኒው አንድ ሙስሊም ቢክድ ኖሮ በገሃነም የሚያገኘውን ቦታ ስላልካደ አንድ አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን በመካዱ የእርሱን ቦታ በገሃነም ያገኛል። ይህ ነው የሐዲሱ እሳቤ እንጂ ስለ ኃጢኣት መሸከም አይናገርም። የሚናገረው ስለ ጀሃነም ቦታ ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ: መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4485
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ሁለት ቦታ የሌለው ከእናንተ ማንም የለም፤ አንዱ መኖሪያ በጀነት ሌላው መኖሪያ በጀሃነም፤ የካደ ቢሞትና ጀሃነም ቢገባ የጀነት ባለቤት የእርሱን ቦታ ይወርሳል፤ ይህንን አላህ ሲናገር፦ "እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው" ብሏል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ مَا مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلاَّ لَهُ مَنْزِلاَنِ مَنْزِلٌ فِي الْجَنَّةِ وَمَنْزِلٌ فِي النَّارِ فَإِذَا مَاتَ فَدَخَلَ النَّارَ وَرِثَ أَهْلُ الْجَنَّةِ مَنْزِلَهُ فَذَلِكَ قَوْلُهُ تَعَالَى ‏{أُولَئِكَ هُمُ الْوَارِثُونَ }‏ ‏"‏
23፥10 *እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው*፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْوَارِثُون
23፥11*እነዚያ ፊርደውስን የሚወርሱ ናቸው፡፡ እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው*፡፡ الَّذِينَ يَرِثُونَ الْفِرْدَوْسَ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

ስለዚህ ካፊር በመክፈሩ ጀሃነም ይገባል፤ ባይከፍር በጀነት የሚያገኘውን ቦታ ሙዕሚኑ ይወርሰዋል፤ ሙዕሚን በማመኑ ጀነት ይገባል፤ ባያምን በጀሃነም የሚያገኘውን ቦታ ካፊሩ ይወርሰዋል። ይህ ነው የሐዲሳት ጭብጥ፤ የነብያችንን"ﷺ" መልእክት ሰምቶ ያላመነ አይሁድ ወይም ክርስቲያን ጀሃነም እንደሚገባ እሙንና ቅቡል ነው፦
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 1, ሐዲስ 293
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው እምላለው፤ ከዚህ ሕዝብ አይሁዳዊም ሆነ ክርስቲያን የእኔን መላክ ሰምቶ ሳያምን ቢሞት የጀሃነም ጓድ እንጂ ሌላ አይሆንም"*። حَدَّثَهُ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ "‏ وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ لاَ يَسْمَعُ بِي أَحَدٌ مِنْ هَذِهِ الأُمَّةِ يَهُودِيٌّ وَلاَ نَصْرَانِيٌّ ثُمَّ يَمُوتُ وَلَمْ يُؤْمِنْ بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ إِلاَّ كَانَ مِنْ أَصْحَابِ النَّارِ ‏"

ቅሉ ግን አይሁዳዊም ሆነ ክርስቲያን የእርሳቸውን መላክ ሰምቶ ሳያምን ከመሞቱ በፊት ካመኑ ሊያገኙት የሚችሉት የጀነት ቦታ ለማግኘት ቶሎ መስለም ነው፤ አይ አስተባብዬ እሞታለው ካላችሁ ብታምኑ የምታገኙትን ቦታ ያመነ ሙስሊም ቦታችሁን ይወርሰዋል። እርሱ ቢክድ የሚያገኘውን የጀሃነም ቦታ በማመኑ የእርሱ ቦታ እናንተ ትወርሳላችሁ። የንስሃ በሩ ሳይዘጋ በጊዜ ሰልሞ ማምለጥ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአእምሮ ባለቤት

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

38፥29 ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ *የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው*፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَاب

"ተደቡር" تَدَبُر ማለት "ማስተንተን" ማለት ነው፤ "ዱቡር" دُبُر ማለት "ጀርባ" ማለት ሲሆን ከቁርኣን ሑሩፍ በስተ-ጀርባ ያለውን ዕውቀት መረዳት ተደቡር ይባላል፤ ይህ ቁርኣን የወረደው የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ ነው፦
38፥29 ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ *የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው*፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَاب

የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን ሲያስተነትኑ ቁርኣን ከአላህ ዘንድ መውረዱን ይረዳሉ፤ ከተረዱ በኃላ እንዲገሰጹ ነው፤ ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ማንነትና ምንነት ቢገኝ ኖሮ በውስጡ ብዙ መለያየት በተገኘ ነበር፦
4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

"ኢኽቲላፍ" ٱخْتِلَٰف ማለት "መለያየት" "ግጭት"contradiction" ማለት ነው፤ የአእምሮ ባለቤቶችም ቁርኣን የአላህ ንግግር ብቻ መሆኑን አንዳች መለያየት እንደሌለበት እንዲያስተነትኑ ይጋብዛል፤ የቁርኣን ተናጋሪ የዐለማቱ ጌታ አላህ ነው፤ ቁርኣን አንድ እሳቤ በአንድ ሱራህ ላይ ያንጠለጥል እና በሌላ ሱራህ የተቀሩትን እሳቤ ይጨርሰዋል፤ ይህ የቁርኣን አንዱ ውበት ነው፦
39፥23 *አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ*፡፡ اللَّهُ نَزَّلَ أَحْسَنَ الْحَدِيثِ كِتَابًا مُّتَشَابِهًا مَّثَانِيَ تَقْشَعِرُّ

"ሙተሻቢህ" مُتَشَٰبِه ማለትም "ተመሳሳይ" ማለት ሲሆን አንቀጾችን አንዱ ሱራህ ላይ ተናግሮ ሌላ ሱራህ ላይ ተመሳሳዩን የተቀረውን ይናገራል፤ አላህ ከነብያችን"ﷺ" በፊት የነበረውን ክስተትና መስተጋብር አንዱ ሱራህ ላይ ተናግሮ ያንጠለጥለው እና እንደገና በሌላ ሱራህ የተቀሩትን ይደግመዋል፤ "መሳኒይ" مَّثَانِى ማለት "ተደጋጋሚ" ማለት ነው። ይህንን በተለያዩ ሱራዎች የተለያዩ ናሙናዎችን ማየት እንችላለን፦

ናሙና አንድ
ኢብራሂም ለመላእክቶቹ ያላቸው ሙሉ ንግግሩ፦ "ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤ እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን" ሲሆን አላህ ግን ይህንን የኢብራሂም ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
51፥24 *የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?* هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ الْمُكْرَمِينَ
51፥52 በእርሱ ላይ በገቡ እና ሰላም ባሉት ጊዜ አስታውስ፤ እርሱም፦ *«ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ»* አላቸው፡፡ إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ قَوْمٌ مُّنكَرُونَ
15፥51 *ከኢብራሂም እንግዶችም ወሬ ንገራቸው*፡፡ وَنَبِّئْهُمْ عَن ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ
15፥52 በእርሱ ላይ በገቡ እና ሰላም ባሉት ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤ እርሱም፦ *«እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን»* አላቸው፡፡ إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا قَالَ إِنَّا مِنكُمْ وَجِلُونَ

ናሙና ሁለት
ሙሳ ለጌታው ያለው ሙሉ ንግግሩ፦ "ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ፣ ለእነርሱም በእኔ ላይ የደም ወንጀል አለ" ሲሆን አላህ ግን ይህንን የሙሳን ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
28፥33 ሙሳም አለ፦ *«ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ*፤ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ፡፡ قَالَ رَبِّ إِنِّي قَتَلْتُ مِنْهُمْ نَفْسًا فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُون
26፥14 ሙሳም አለ፦ *«ለእነርሱም በእኔ ላይ የደም ወንጀል አለ*፤ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ። وَلَهُمْ عَلَيَّ ذَنبٌ فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُونِ

ናሙና ሦስት
ፈርዖን የተናገረው ሙሉ ንግግሩ ፦ "ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ትልቃችሁ ነው፤ ወደፊትም የሚያገኛችሁን በእርግጥ ታውቃላችሁ፤ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ፡፡ ከዚያም ሁላችሁንም በእርግጥ በዘምባባም ግንዶች ላይ እሰቅላችኋለሁ፡፡ ማንኛችንም ቅጣቱ በጣም ብርቱ የሚቆይም መኾኑን ታውቃላችሁ" ሲሆን አላህ ግን ይህንን የፈርዖንን ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
26፥49 *«ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ትልቃችሁ ነው፡፡ ወደፊትም የሚያገኛችሁን በእርግጥ ታውቃላችሁ፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ እቆረርጣለሁ፡፡ ከዚያም ሁላችሁንም በእርግጥ እሰቅላችኋለሁም»* አለ፡፡ قَالَ آمَنتُمْ لَهُ قَبْلَ أَنْ آذَنَ لَكُمْ ۖ إِنَّهُ لَكَبِيرُكُمُ الَّذِي عَلَّمَكُمُ السِّحْرَ فَلَسَوْفَ تَعْلَمُونَ ۚ لَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَافٍ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ أَجْمَعِينَ
20፥71 *«ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለእርሱ አመናችሁን? እርሱ በእርግጥ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ትልቃችሁ ነው፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ እቆራርጣችኋለሁ፡፡ ከዚያም ሁላችሁንም በእርግጥ በዘምባባም ግንዶች ላይ እሰቅላችኋለሁ፡፡ ማንኛችንም ቅጣቱ በጣም ብርቱ የሚቆይም መኾኑን ታውቃላችሁ»* አለ፡፡ قَالَ آمَنتُمْ لَهُ قَبْلَ أَنْ آذَنَ لَكُمْ ۖ إِنَّهُ لَكَبِيرُكُمُ الَّذِي عَلَّمَكُمُ السِّحْرَ ۖ فَلَأُقَطِّعَنَّ أَيْدِيَكُمْ وَأَرْجُلَكُم مِّنْ خِلَافٍ وَلَأُصَلِّبَنَّكُمْ فِي جُذُوعِ النَّخْلِ وَلَتَعْلَمُنَّ أَيُّنَا أَشَدُّ عَذَابًا وَأَبْقَىٰ

ኢንሻላህ ሌሎች ናሙናዎችን በክፍል ሁለት እንቀጥላለን...

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአእምሮ ባለቤት

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ናሙና አራት
ኑሕ ለጌታው የጸለየው ሙሉ ጸሎት፦ "ጌታዬ ሆይ! ባስተባበሉኝ ምክንያት እርዳኝ፤ ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው" ሲሆን አላህ ግን ይህንን የኑሕን ጸሎት በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
23፥26 ኑሕም፦ *«ጌታዬ ሆይ! ባስተባበሉኝ ምክንያት እርዳኝ»* አለ፡፡قَالَ رَبِّ انصُرْنِي بِمَا كَذَّبُونِ
71፥26 ኑሕም፦ *«ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው»* አለ፡፡ وَقَالَ نُوحٌ رَّبِّ لَا تَذَرْ عَلَى الْأَرْضِ مِنَ الْكَافِرِينَ دَيَّارًا

ናሙና አምስት
አላህ ለመላእክት የተናገረው ሙሉ ንግግር፦ "እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ" ሲሆን አላህ ግን ይህንን የራሱን ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- *«እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፤ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً
15፥28 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن صَلْصَالٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ
38፥71 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

ናሙና ስድስት
አላህ ለኢብሊስ የተናገረው ሙሉ ንግግር፦ "ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ? ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክን?" ሲሆን አላህ ግን ይህንን የራሱን ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
7፥12 አላህም፦ *«ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?»* አለው፡፡ ኢብሊስም፦ *«እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው»* አለ፡፡ قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ ۖ قَالَ أَنَا خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِي مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُ مِن طِينٍ
38፥75 አላህም፦ *«ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ? ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክን?»* አለው፡፡ قَالَ يَا إِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَيَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ الْعَالِينَ
38፥75 ኢብሊስም፦ *«እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው»* አለ። قَالَ أَنَا خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِي مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُ مِن طِينٍ

ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ብዙ ናሙናዎችን ማቅረብ ይቻል ነበር፤ ግን ለአብባቢ ጊዜን እንዲሁ ለንባብ ደግሞ ቦታ ማጣበብ ይሆናል፤ ቅሉ ግን በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ይህ በቂ ነው፤ ይህ አይነት አፈሳሰር ተዛማች ሙግት"textual approach" ይባላል።
ከላይ የዘረዘርናቸው ክስተትና መስተጋብር ሲከሰቱ ነብያችን”ﷺ” አልነበሩም፤ ነገር ግን አምላካችን አላህ ተፈላጊውን ትረካ የአእምሮ ባለቤቶችም እንዲገሰጹ ተርኮልናል። ይህንን ከእሳቸው በፊት የነበረውን የሩቅ ወሬ “ነቁስሱ ዐለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ ማለትም “እንተርክልሃለን” በማለት ለነብያችን”ﷺ” ይተርካል፤ “ወሬ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ነበእ” نَبَإِ ሲሆን “ነቢይ” نبي የሚለው ቃል የመጣበት ሥርወ-ቃል ነው፤ ለነብያችን”ﷺ” መተረኩ ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው፦
20፥99 እንደዚሁ በእርግጥ *ካለፉት ወሬዎች በአንተ ላይ እንተርካለን*፡፡ كَذَٰلِكَ نَقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ مَا قَدْ سَبَقَ
11:120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር *ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ* መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
እንፍጠር ወይስ ልፍጠር?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

38፥71 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

አምላካችን አላህ ለመላእክት የተናገረው፦ “እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ” የሚል ነው እንጂ “እንፍጠር” አላላቸውም፦
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- *«እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፤ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً
38፥71 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

“እንፍጠር” የሚባለው መፍጠር ለሚችል ማንነትና ምንነት ብቻ ነው፤ በባይብልም ከሄድን ያህዌህ ለመላእክት ያለው፦ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለው” የሚል ነው፦

1ኛ. ዕብራይስጡ፦
ዘፍጥረት 2፥18 וַיֹּאמֶר יְהוָה אֱלֹהִים, לֹא-טוֹב הֱיוֹת הָאָדָם לְבַדּוֹ; אֶעֱשֶׂה-לּוֹ עֵזֶר, כְּנֶגְדּוֹ.

2ኛ. ኢንግሊሹ፦
Genesis 2፥18 The LORD God said, “It is not good for the man to be alone. I will make a helper suitable for him.” NIV

3ኛ. አዲሱ መደበኛ ትርጉም፦
ዘፍጥረት 2፥15 ያህዌህ ኤሎሂም፦ “ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለምና የሚስማማውን ረዳት አበጅለታለው” አለ።

የዕብራይስጡ ላይ “ኤሴህ” אֶֽעֱשֶׂהּ ማለትም “ልፍጠር” አለ እንጂ “እንፍጠር” አላለም፤ እንግሊዘኞቹም፦ “I will make” ብለው አስቀምጠውታል። ታዲያ “እንፍጠር” ከየት መጣ? አዎ ግሪክ ሰፕቱአጀን”LXX” እና ግዕዙ ላይ “እንፍጠር” የሚል አለ፦

1ኛ. ግሪክ ሰፕቱአጀን፦
Καὶ εἶπε Κύριος ὁ Θεός· οὐ καλὸν εἶναι τὸν ἄνθρωπον μόνον· ποιήσωμεν αὐτῷ βοηθὸν κατ᾿ αὐτόν.

2ኛ. ግዕዙ፦
ወይቤ እግዚአብሔር ኢኮነ ሠናይ ለእጓለ እመሕያው ይንበር ባሕቲቱ *ንግበር* ሎቱ ቢጸ ዘይረድኦ።

3ኛ. አማርኛ 1954 እትም፦
ዘፍጥረት 2፥18 እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት *እንፍጠርለት*።

የግሪክ ሰፕቱአጀን ላይ “ፓኢሴሜን” ποιήσωμεν ማለት “እንፍጠር” ብሎ አስቀምጦታል፤ ግዕዙም፦ “ንግበር” ማለትም “እንፍጠር” ብሎ አስቀምጠውታል። ታዲያ “እንፍጠር” ያለውም ለማን ነው? ስንል ኩፋሌ ላይ ደግሞ ለፍጡራን እንዳለ ይናገራል፦

1ኛ. ግዕዙ፦
ኩፋሌ 4፥4 *ወይቤለነ እግዚአብሔር ለነ*፤ አኮ ሰናይ የሀሉ ብእሲ ባሕቲቱ፤ አላ *ንግበር* ሎቱ መርድአ ዘከማሁ፤ መወየደ *እግዚአብሔር አምላክነ* ሕድመተ ላዕሌሁ ወኖመ”

2ኛ. አማርኛው፦
ኩፋሌ 4፥4 *ፈጣሪያችን* እግዚአብሔር ለእኛ *እንዲህ አለን*፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት *”እንፍጠርለት”*።

“ፈጣሪያችን” የሚል ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ እግዚአብሔር እንፍጠር ያለው ለፈጠራቸው መሆኑን ለማሳየት እዛው አንቀጽ ላይ፦ “እንዲህ አለን” ይላሉ፤ ያላቸውም፦ “እንፍጠርለት” ነው፤ እነዚህ ማንነቶች እነማን ናቸው? ብለን ስንሞግት “መላእክት ናቸው” ይሉናል፤ አንቀጹ ላይ መላእክት ስለመሆናቸው ምንም ሽታው እንኳን የለም። ነገር ግን ኩፋሌ 1፥25 ኩፋሌ 2፥1 ኩፋሌ 2፥4 ኩፋሌ 4፥1 ለሙሴ የፊቱ መልአክ እየተናገረ ነው በሚል መላእክት ናቸው እንበልና ሙግቱን እናጥበው፤ መላእክት ይፈጥራሉ እንዴ? እኔ “እንብላ” ብዬ ብል የሚበላ ማንነትን እያናገርኩኝ ነው፤ የማይበላ ከሆነ “ልብላ” ብዬ ነው የምለው እንጂ “እንብላ” አልለውም፤ የማይፈጥር ማንነት እንፍጠር ወይስ ልፍጠር? የቱ ነው ስሜት የሚሰጠው? የባሰው ደግሞ በክሌመንት ላይ፦ “እግዚአብሔር አብ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ እንፍጠር” አላቸው ይለናል፦

1ኛ. ግዕዙ፦
ቀለሚንጦስ 1፥33 *ወይቤሎሙ እግዚአብሔር አብ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ ንዑ ንግበር ሰብእ በአርአያነ ወበአምሳሊነ*።

2ኛ. አማርኛው፦
ቀለሚንጦስ 1፥33 *እግዚአብሔር አብ ለወልድ እና ለመንፈስ ቅዱስ በአርአያችንና በአምሳላችን ሰውን እንፍጠር አላቸው*።

ታዲያ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ፍጡር ናቸውን? ምክንያቱም ኩፋሌ ላይ “ፈጣሪያችን” ብለዋልና። ይህንን የሥላሴ ውዝግብና ትርምስ የሚፈታው የዐለማቱ ጌታ አላህ ለመላእክት ምን ብሎ እንደነበር በሚናገርበት አንቀጽ ነው፦
38፥71 ጌታህ ለመላእክት *«እኔ ሰውን ከጭቃ እፈጥራለሁ»* ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ

ቁርኣን ከወረደበት ግብና አላማ፣ ፋይዳና ሚና አንዱ ከእነርሱ ጋር ያለውን መለኮታዊ እውነት ለማረጋገጥ እና ቀጥፈው የጨመሩትን ሐሰት ሊያርም ነው፤ ከእነርሱ ጋር ያለውን እውነትን ስለሚያረጋግጥ “ሙሰዲቃን” مُصَدِّقًا ማለትም “አረጋጋጭ” ሲባል፤ የሰዎች ንግግር የገቡበትን በማረሙ ደግሞ “ሙሃይሚን” مُهَيْمِنًا ማለትም “አራሚ” correcter” ወይም “ተቆጣጣሪ”supervisor” የሚል ስም አለው፦
5፥48 *ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭ እና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን*። وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሰይጣናት

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥208 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

“ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፤ “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው፤ ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፤ ሰው የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ዐፈር እንደሆነ፤ መልአክ የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ብርሃን እንደሆነ ሁሉ ጂን የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ደግሞ እሳት ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

ጂኒዎች የተፈጠሩበት አላማ የፈጠራቸው አላህ እንዲያመልኩ ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጂኒዎች እንደ ሰው ወንድና ሴት ሆነው የሚወለዱና የሚወልዱ፣ የሚኖሩና የሚሞቱ፤ የሚበሉና የሚጠጡ ፍጡሮች ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 87, ሐዲስ 13
ኢብኑ ዐባስ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ ይሉ ነበር፦ *”በሃያልነትህ እጠበቃለው፤ በእውነት የሚመለክ ከአንተ ከማትሞተው ሌላ የለም፤ ጂን እና ሰው ግን ይሞታል”*። أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَقُولُ ‏ أَعُوذُ بِعِزَّتِكَ الَّذِي لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، الَّذِي لاَ يَمُوتُ وَالْجِنُّ وَالإِنْسُ يَمُوتُونَ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 312 
ዘይድ ኢብኑ አርቀም እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ "ቆሻሻ ቦታዎች በሰይጣናት ይጎበኛሉ፤ ከእናንተም ወደዚያ ሲገባ፦ *"አላህ ሆይ! ከወንድ እና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለው"* ይበል። عَنْ زَيْدِ بْنِ أَرْقَمَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ إِنَّ هَذِهِ الْحُشُوشَ مُحْتَضَرَةٌ فَإِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْخُبُثِ وَالْخَبَائِثِ ‏"‏ ‏.‏

ጂኒዎች እንደ ሰው ነጻ ምርጫ ያላቸው ፍጡሮች ናቸው፤ በምርጫቸው ጀነት ወይም ጀሃነም መግባት ይችላሉ፦
11፥119 የጌታህም ቃል፣ *ገሀነምን ከጂኒዎ እና ከሰዎች ከሁሉም በእርግጥ እሞላታለሁ* በማለት ተፈጸመች። وَتَمَّتْ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ
55፥45 *ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?* فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَان
55፥46 *በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሁለት ገነቶች አሉት*፡፡ وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ

በተለይ “ጌታችሁ” የሚለው ቃል “ረቢኩማ” رَبِّكُمَا ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል፤ “ታስተባብላላችሁ” የሚለው ቃል “ቱከዚባኒ” تُكَذِّبَانِ ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱንም ማለትም ሰውንና ጃንን ያመለክታል፤ የትንሳኤ ቀን ለሁለቱም የተቀጠረ ቀጠሮ ነው፦
55፥39 *በዚያም ቀን ሰውም ጃንም ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም*፡፡ فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُسْأَلُ عَن ذَنبِهِ إِنسٌ وَلَا جَانٌّ
44፥40 *የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው*፡፡ إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ
6፥130 *የጂኒዎች እና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ! አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስጠነቅቋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልክተኞች አልመጧችሁምን? ይባላሉ*፡፡ يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَـٰذَا
6፥128 *ሁሉንም የሚሰበስብባቸውንም ቀን አስታውስ፡፡ የጂኒዎች ጭፍሮች ሆይ! ከሰዎች ጭፍራን በማጥመም በእርግጥ አበዛችሁ* ይባላሉ፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ قَدِ اسْتَكْثَرْتُم مِّنَ الْإِن

ለጂኒዎች ጀነት እና ጀሃነም እንዲሁ የትንሳኤ ቀን ቀጠሮ እንዳላቸው እና የተፈጠሩበት አላማ ካየን ዘንዳ በነጻ ምርጫቸው ሙሥሊም አልያም ካፊር የመሆን ምርጫ አላቸው፦
72፥14 *«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አልሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አልሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»* وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا

ከጂኒዎች መካከል አማንያን እንዳሉ ሁሉ ከሃድያንም አሉ፤ ከሃድያኑ ሰይጣናት ይባላሉ። ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ሰይጣናት እንዳስሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሰይጣናት

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

2፥208 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

"ሸይጧን" شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ ሸይጧን የባህርይ ስም እንጂ የተፀውኦ ስም አይደለም፤ ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ
7፥200 *ከሰይጣንም በኩል ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና*፡፡ وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

“ወሥዋሥ” وَسْوَاس ማለት "ጉትጎታ" ማለት ሲሆን ይህ ጉትጎታ የሚመጣው ከጂኒ ሰይጣናት ብቻ ሳይሆን ከሰውም ሰይጣናት ነው፤ ከዚህ ውስዋስ የምንጠበቀው በተዐዉዝ ነው፤ አላህ የሙናፊቂን መሪዎቻቸውን ፦ "ሰይጣኖቻቸው" ብሏል፤ ይህ የሚያሳየው የሰው ሸይጧን እንዳለ ነው፤ ሸይጧን ከአላህ ራህመት የተገለለ የራቀ ማለት መሆኑ ልብ በል፦
2፥14 እነዚያንም ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ *ወደ ሰይጣኖቻቸውም* ባገለሉ ጊዜ «እኛ ከናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡ وَإِذَا لَقُوا الَّذِينَ آمَنُوا قَالُوا آمَنَّا وَإِذَا خَلَوْا إِلَىٰ شَيَاطِينِهِمْ قَالُوا إِنَّا مَعَكُمْ إِنَّمَا نَحْنُ مُسْتَهْزِئُونَ

እዚህ ድረስ ስለ ሸይጧን እሳቤ ከተረዳን ዘንዳ ረመዷን ላይ የሚታሰሩት ሸያጢን ከኩፋሩል ጂን ሲሆኑ ከእነርሱም የሚታሰሩት መሪዎቻቸው ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 30, ሐዲስ 9
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የረመዷን ወር ሲጀመር የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ፤ የጀሃነም ደጆች ይዘጋሉ፤ ሰይጣናትም ይታሰራሉ"* سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِذَا دَخَلَ شَهْرُ رَمَضَانَ فُتِّحَتْ أَبْوَابُ السَّمَاءِ، وَغُلِّقَتْ أَبْوَابُ جَهَنَّمَ، وَسُلْسِلَتِ الشَّيَاطِينُ ‏"‌‏
ኢማም አብኑ ኹዘይማህ: መጽሐፍ 3, ቁጥር 188
ነብዩም"ﷺ"፦ *"ሰይጣናት ይታሰራሉ" ያሉት ከእነርሱ አመጸኞቹ እንጂ ሁሉም ሰይጣናት አይደለም*። باب ذكر البيان أن النبي - صلى الله عليه وسلم - إنما أراد بقوله : " وصفدت الشياطين " مردة الجن منهم ، لا جميع الشياطين "
ሚሽነሪዎች፦ "ሰይጣናት ከታሰሩ ሰው እንዴት በረመዷን ወር ይሳሳታል?" ብለው ይጠይቃሉ፤ ጥሩ ጥያቄ ነው። ሲጀመር በረመዷን ወር ሁሉም ሰይጣናት አልታሰሩም። ሲቀጥል የታሰሩት በሁለተኛ ደረጃ ያሉትን "ማሪድ" مَّارِد የተባሉትን መሪዎች ናቸው፤ የመጀመሪያው ዋናው ሸይጧን ኢብሊስ ነውና። ሲሰልስ ሰውን የሚወሰውሱ የሰው ሰይጣናት እራሳቸው አልታሰሩም፤ እነርሱን በረመዳን ወር ሊወሰውሱ ይችላሉ። ሲያረብብም ሰይጣን ቢታሰርም እርምጃዎቹ አልታሰሩም፤ አላህ አትከተሉ ያለው ሰይጣንን ብቻ ሳይሆን የሰይጣንን እርምጃዎች ጭምር ነው፦
2፥208 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ادْخُلُوا فِي السِّلْمِ كَافَّةً وَلَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

የሰይጣን እርምጃዎች “አህዋዕ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” እና “ነፍስያ” نفسيه ናቸው፤ አህዋዕ ሊመለክ የሚችል ክፉ አዛዥ ነው፤ በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا
79፥40 *በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ* وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 *ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

ነፍስያ አላህ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና፤ ነፍሲያ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥164 በላቸው «እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ሰይጣን የትንሳኤ ቀን፦ "ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልበረኝም፤ ግን ጠራኋችሁ፡፡ ለእኔም ታዘዛችሁ፤ ስለዚህ አትውቀሱኝ፤ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ" ይላል፦
14፥22 ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን ይላቸዋል፦ *«አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ፡፡ ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ፤ አፈረስኩባችሁም፡፡ ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ስልጣን አልበረኝም፡፡ ግን ጠራኋችሁ፡፡ ለእኔም ታዘዛችሁ፡፡ ስለዚህ አትውቀሱኝ፤ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ፡፡ እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም፡፡ እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም፡፡ እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ካድኩ፡፡ በዳዮቹ ለእነርሱ በእርግጥ አሳማሚ ቅጣት አላቸው»። وَقَالَ الشَّيْطَانُ لَمَّا قُضِيَ الْأَمْرُ إِنَّ اللَّهَ وَعَدَكُمْ وَعْدَ الْحَقِّ وَوَعَدتُّكُمْ فَأَخْلَفْتُكُمْ ۖ وَمَا كَانَ لِيَ عَلَيْكُم مِّن سُلْطَانٍ إِلَّا أَن دَعَوْتُكُمْ فَاسْتَجَبْتُمْ لِي ۖ فَلَا تَلُومُونِي وَلُومُوا أَنفُسَكُم ۖ مَّا أَنَا بِمُصْرِخِكُمْ وَمَا أَنتُم بِمُصْرِخِيَّ ۖ إِنِّي كَفَرْتُ بِمَا أَشْرَكْتُمُونِ مِن قَبْلُ ۗ إِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

ስለዚህ ለምንሰራው መጥፎ ሥራ ሰይጣንን ተጠያቂ ማድረግ አንችልም፤ ሰይጧን ለእኛ ግልጽ ጠላት ነው፤ እርሱ የሚያጠቃን በእርምጃዎቹ ነው። አላህ ከሸይጧን እርምጃዎች ይጠብቀን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
መኃልየ መኃልይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2:79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለእነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው*፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

"መኃልይ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "ሺይር" שִׁיר ሲሆን "ሙዚቃ" "ዘፈን" መዝሙር" የሚል ፍቺ አለው፦
መኃልየ 1፥1 *ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር*።

ይህ ዘፈን በንጉሥ ሰለሞን እና በሱላማጢስ ልጃገረጅ መካከል የነበረ ምልልስ ነው፦
መኃልየ 6፥13 *አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት*።

ሱናማጢስ በሱነም የሚኖሩ ልጃገረድ ሴቶች ናቸው፤ በሱነም የሚኖሩ ልጃገድ "ሱነማይት" ይባላሉ። "ሱነም" የይሳኮር ነገር የወረሰባት ቦታ ስም ነው፤ ይህንን ቦታ ፍልስጥኤማውያን መጥተው ያረፉበት ቦታ ነው፦
ኢያሱ 19፥17 አራተኛውም ዕጣ ለይሳኮር ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ።
18፤ ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥ ወደ ከስሎት፥ *ወደ ሱነም፥*
1ኛ ሳሙ *ፍልስጥኤማውያንም ተሰብስበው መጡ በሱነምም ሰፈሩ*፤

ነብዩ ኤልሳዕም ወደ ሱነም አልፎ ከሱነም ታላቅ ሴት ጋር ተጋብዟል፤ ንጉሥ ዳዊትም በስተርጅናው እንድታሞቀው የሱነማይት ቆንጆ አምጥተውለት ነበር፦
2 ነገሥት 4፥8 አንድ ቀንም እንዲህ ሆነ፤ ኤልሳዕ *ወደ ሱነም አለፈ፥ በዚያም ታላቅ ሴት ነበረች*፤ እንጀራ ይበላ ዘንድ የግድ አለችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር እንጀራ ሊበላ ወደዚያ ይገባ ነበር።
1 ነገሥት 1፥3-4 በእስራኤልም አገር ሁሉ የተዋበች ቈንጆ ፈለጉ፤ *ሱነማይቱን አቢሳንም አገኙ፥ ወደ ንጉሡም ይዘዋት መጡ። ቈንጆይቱም እጅግ ውብ ነበረች፤ ንጉሡንም ትረዳውና ታገለግለው ነበር፥ ንጉሡ ግን አያውቃትም ነበር*።

እዚህ ድረድ ከተግባባ ይህቺ ልጃገድ በሰለሞን ፍቅር እብድ ያለች ፀሐይ መልኳን ያከሰለው ጥቁር ናት፤ ንጉሡ ሰለሞንም የከንፈር ወዳጇ ነው፦
መኃልየ 1፥5-6 እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ *እኔ ጥቁር ነኝ ነገር ግን ውብ ነኝ*፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች። *ፀሐይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አትዩኝ* የእናቴ ልጆች ተጣሉኝ፥
መኃልየ 1፥2 *በአፉ መሳም ይሳመኝ*፥ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና።

ንጉሥ ሰለሞን ይህቺን የሱናማይቱ ልጃገድ አካል ዐይንሽ፣ ከንፈርሽ፣ ጥርስሽ፣ አፍሽ፣ አንገትሽ፣ ጡትሽ፣ እምብርትሽ፣ ዳሌሽ እያለ ሲያብድ፤ እርሷም በተራዋ ቀሚሷን አውልቃ ንጉሡ እጁን በአፍረተ ስጋዋ ውስጥ ሲከተው አንጀቷ ተላወሰ፤ ለእርሱም የደጅዋን መወርወሪያ ማለት እግሯን ከፈተችለት፤ እርሷም ስሜቷን አፈሰሰች፤ ምን አለፋችሁ ይህንን የወሱብ ዘፈን አንብቡት፦
መኃልየ 5፥3-5 *ቀሚሴን አወለቅሁ እንዴት እለብሰዋለሁ? እግሬን ታጠብሁ እንዴት አሳድፈዋለሁ? ውዴ እጁን በቀዳዳ ሰደደ፥ አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ። ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ እጆቼ በደጅ መወርወሪያ ላይ ከርቤን አፈሰሱ፥ ጣቶቼ ፈሳሹን ከርቤ አንጠበጠቡ*።

ማኖ አስነክቷት ንጉሡ ሄደ፤ እርሷን የኢየሩሳሌምን ቆነጃጅት አፋልጉኝ አለቻቸው፤ እነርሱም አወዳደሷት፤ ንጉሡ ብዙ ንግሥቶችን አማልሏል፤ ቁባት ማለትም የጭን ገረድ በአገራችን
ወሽማ ስላሉት እዛ ሄዷል። እንግዲህ እዚህ መጽሐፍ ላይ የእግዚአብሔር ስም የተነሳው አንዴ ነው፤ ያነሳችው ልጃገረዲቱ ናት እንጂ የፈጣሪ ንግግር ሽታውን ብንፈልግ አናገኝም። ይህ ንግግር በንጉሥ ሰለሞን እና በልጃገረዲቱ መካለል የነበረ የወሲብ ንግግር እንጂ በአብ እና በማርያም አሊያም በክርስቶስ እና በቤተክርስቲያን መካከል የነበረ መስተጋብር በፍጹም አይደለም። እስቲ ከነብያት እና ከሃዋርያት መካከል ከዚህ መጽሐፍ ጠቅሶና አጣቅሶ በአብ እና በማርያም አሊያም በክርስቶስ እና በቤተክርስቲያን መካከል የነበረ መስተጋብር ነው ያለበትን መረጃ ይቅረብ።

አይሁዳውያን ይህንን የወሲብ መጽሐፍ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 90 ዓመተ ልደት"AD" በጀሚኒያ ጉባኤ የአምላክ ንግግር ነው ብለው የቀኖና መጽሐፍ ሲያደርጉ ክርስቲያኖች ደግሞ በ 397 ዓመተ ልደት"AD" በካርቴጅ ጉባኤ የአምላክ ንግግር ነው ብለው የቀኖና አድርገውታል። ለእነዚህ መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት "ይህ ከፈጣሪ ዘንድ ነው" ለሚሉ ወዮላቸው፤ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፦
2:79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለእነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው*፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አማልክት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

23፥66 «እኔ ከጌታዬ አስረጂዎች በመጡልኝ ጊዜ *እነዚያን ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸውን እንዳላመልክ ተከልክያለሁ፡፡ ለዓለማት ጌታም እንድገዛ ታዝዣለሁ»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّي نُهِيتُ أَنْ أَعْبُدَ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَمَّا جَاءَنِيَ الْبَيِّنَاتُ مِن رَّبِّي وَأُمِرْتُ أَنْ أُسْلِمَ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ

ነብያችን"ﷺ" በተላኩበት ጊዜ ከሓዲዎች ከአላህ ሌላ ምንንም የማይፈጥሩን፣ ለነፍሶቻቸውም ጉዳትን ለመከላከል ጥቅምንም ለማምጣት የማይችሉን እና ሞትንና ሕይወትንም መቀስቀስንም የማይችሉን አማልክት አድርገው ያዙ፦
25፥3 *ከሓዲዎች ከእርሱም ሌላ ምንንም የማይፈጥሩን፣ እነርሱም የሚፈጠሩን፣ ለነፍሶቻቸውም ጉዳትን ለመከላከል ጥቅምንም ለማምጣት የማይችሉን ሞትንና ሕይወትንም መቀስቀስንም የማይችሉን፣ አማልክት ያዙ*፡፡ وَاتَّخَذُوا مِن دُونِهِ آلِهَةً لَّا يَخْلُقُونَ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ وَلَا يَمْلِكُونَ لِأَنفُسِهِمْ ضَرًّا وَلَا نَفْعًا وَلَا يَمْلِكُونَ مَوْتًا وَلَا حَيَاةً وَلَا نُشُورًا

ይህ አልበቃ ብሏቸው ከእነርሱ የሆነ አስጠንቃቂም ስለ መጣላቸው አላህን በብቸኝነት በማምለክ ፋንታ ተደንቀው ነብያችንን"ﷺ"፦ "ይህ ድግምተኛ ውሸታም ነው፤ አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው" አሉ፦
38፥4 ከእነርሱ የሆነ አስጠንቃቂም ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ *ከሓዲዎቹም* አሉ፦ *«ይህ ድግምተኛ ውሸታም ነው»* ፡፡ وَعَجِبُوا أَن جَاءَهُم مُّنذِرٌ مِّنْهُمْ ۖ وَقَالَ الْكَافِرُونَ هَـٰذَا سَاحِرٌ كَذَّابٌ
38፥5 *«አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው»* አሉ፡፡ أَجَعَلَ الْآلِهَةَ إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ إِنَّ هَـٰذَا لَشَيْءٌ عُجَابٌ

እዚህ አናቅጽ ላይ፦ "ቃለ" َقَالَ ማለትም "አሉ" የሚል ወሳኝ ቃላት አለ፤ እነማን ናቸው ያሉት? "ከሓዲዎቹም" ይለናል፤ ምን አሉ? ፦ "ይህ ድግምተኛ ውሸታም ነው፤ አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን?" አሉ፤ ያሉትን ደግሞ አላህ በአውንታዊ ሳይሆን በአሉታዊ እየነገረን ነው፤ ያሉትን ነገር ግን ትክክል አይደለም፤ ነብያችንም"ﷺ" ድግምተኛ ውሸታም አይደሉም፤ በተጨማሪም አማልክቶቹን አንድ አምላክ አላደረጉም፤ ከዚያ ይልቅ ወሕይ ሲመጣላቸው እነዚያን ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸውን እንዳመልኩ እና ለዓለማት ጌታም ብቻ እንዲገዙ ታዘዋል፦
23፥66 «እኔ ከጌታዬ አስረጂዎች በመጡልኝ ጊዜ *እነዚያን ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸውን እንዳላመልክ ተከልክያለሁ፡፡ ለዓለማት ጌታም እንድገዛ ታዝዣለሁ»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّي نُهِيتُ أَنْ أَعْبُدَ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَمَّا جَاءَنِيَ الْبَيِّنَاتُ مِن رَّبِّي وَأُمِرْتُ أَنْ أُسْلِمَ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ

"እንድገዛ" የሚለው ቃል "አሥሊመ" أُسْلِمَ ሲሆን “ሙሥሊም” مُسْلِم ለሚለው ቃል የግስ መደብ ነው፤ ስለዚህ ከላይ ያለው "አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸው" የሚለው ትችት የከሃድያን ትችት ብቻ ነው፤ ከሃድያን እኮ፦ "በእውነቱ ቁርኣኑ የሕልሞች ቅዠቶች ነው" ብለዋል፤ እነርሱ ያንን አሉ ማለት በአውንታዊ መልኩ ትክክል ናቸው ማለት ሳይሆን በአሉታዊ መልኩ እንደተቀመጠ ሁሉ ከላይ ያለውን በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት፦
21፥5 «በእውነቱ ቁርኣኑ የሕልሞች ቅዠቶች ነው» *አሉ*፡፡ بَلْ قَالُوا أَضْغَاثُ أَحْلَامٍ بَلِ افْتَرَاهُ بَلْ هُوَ شَاعِرٌ فَلْيَأْتِنَا بِآيَةٍ كَمَا أُرْسِلَ الْأَوَّلُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
መልአከ-ሞት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት *”ይወስዳችኃል”*፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ

“መለኩል መውት” مَلَكُ المَوت ማለትም “መልአከ-ሞት” ወይም “የሞት መልአክ” ማለት ነው፤ መልአከ ሞት የሚባሉት መላእክት ብዙ ሲሆኑ የእነርሱ የልዑካን ቡድን መሪና አለቃ “ዐዝራዒል” عَزرائيل‎ ነው፤ “ዐዝራዒል” ማለት “ዑራኤል” ማለት ሲሆን ከመላእክት አለቃ አንዱ ነው። እነዚህ የመላእክት አለቃ “ጂብሪል” جِبريل ማለትም “ገብርኤል”፣ “ሚካል” مِيكَال ማለትም “ሚካኤል”፣ “ኢሥራፊል” إِسْـرَافِـيْـل‎ ማለትም “ሩፋኤል” ወዘተ ናቸው።
ወደ ነጥባችን ስንመለስ አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፤ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፦
39፥42 *አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ”ይወስዳል”፡፡ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ”ይወስዳታል”*፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

የእንቅልፍ ዓለም መንፈሳችን ከአካላችን ጋር እንዴት እንደምትለያይ ልምምድ ላይ ናት፤ አላህ መንፈሳችንን በሞታችን ጊዜ ይወስዳታል፤ እዚህ አንቀጽ ላይ “ይወስዳል” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፈ” يَتَوَفَّى ሲሆን ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ ደግሞ በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፤ በሌላ አንቀፅ ላይ “የሚያስተኛችሁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ሲሆን አላህ ሩሃችንን በሌሊት በእንቅልፍ ጊዜ እንደሚወስድ ያሳያል፦
6፥60 እርሱም ያ በሌሊት *”የሚያስተኛችሁ”* በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ *”የሚቀሰቅሳችሁ”* ነው፡፡ ከዚያም *”መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው”*፡፡ ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ وَهُوَ ٱلَّذِى يَتَوَفَّىٰكُم بِٱلَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِٱلنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰٓ أَجَلٌۭ مُّسَمًّۭى ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

አላህ መልአከ ሞትን ልኮ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ “ይወስዳችኃል” ይላል፤ አሁንም “ይወስዳችኃል” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ነው፦
16፥70 አላህም ፈጠራችሁ፤ *ከዚያም “ይወስዳችኃል”*፡፡ وَٱللَّهُ خَلَقَكُمْ ثُمَّ يَتَوَفَّىٰكُمْ
32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት *”ይወስዳችኃል”*፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ
7፥37 የሞት መልክተኞቻችንም *”የሚወስዷቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ”* «ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው የነበራችሁት የት አሉ» ይሏቸዋል፡፡ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوٓا۟ أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّه

በሞትም ጊዜ ግን የሚያሞት አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
15፥23 እኛም ሕያው የምናደርግ እና *የምንገድል እኛው ብቻ ነን*፡፡ እኛም ፍጡርን ሁሉ የምንወርስ ቀሪ ነን፡፡ وَإِنَّا لَنَحْنُ نُحْيِي وَنُمِيتُ وَنَحْنُ الْوَارِثُونَ
10፥56 እርሱ ሕያው ያደርጋል፤ *ይገድላልም* ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ هُوَ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

“ይገላል” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዩሚቱ” يُمِيتُ ሲሆን “ያሞታል” ማለት ነው፤ “መውሰድ” እና “ማሞት” ይለያያል፤ “ያሞታል” ለሚለው የሚጠቀመው ቃል “ዩሚቱ” يُمِيتُ ሲሆን “ይወስዳል” ለሚለው ደግሞ “የተወፍፋ” يَتَوَفَّا ነው።
“መልአክ” ملاك ማለት ትርጉሙ “መልእክተኛ” ማለት ከሆነ በላኪው ትእዛት የሞት መልአክ ይወስዳል ማለት ነው፦
6፥61 በእናንተም ላይ ጠባቂዎችን መላእክት ይልካል፡፡ *አንዳችሁንም ሞት በመጣበት ጊዜ የሞት መልእክተኞቻችን እነርሱ ትእዛዛትን የማያጓድሉ ሲኾኑ “ይወስዱታል”*፡፡ وَيُرْسِلُ عَلَيْكُمْ حَفَظَةً حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ تَوَفَّتْهُ رُسُلُنَا وَهُمْ لَا يُفَرِّطُونَ