ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
እነዚህ የሞት መላእክት በጥቅሉ ለሁለት ይከፈላሉ፦ አንደኞቹ “አን-ናዚዓት” النَّازِعَات ሲባሉ፤ አን-ናዚዓን በመባል የሚታወቁት የሞት መላእክት የከሃድያንን ሩሕ በኃይል አውጪዎች ናቸው፤ ከሃድያንም ይሰሩት በነበረው መጥፎ ሥራ እሳት ይገባሉ፦
79፥1 *በኃይል አውጪዎች በኾኑት*፤ وَالنَّازِعَاتِ غَرْقًا
8፥50 *እነዚያንም የካዱትን መላእክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» እያሉ በሚወስዷቸው ጊዜ* ብታይ ኖሮ አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር፡፡ وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ يَتَوَفَّى الَّذِينَ كَفَرُوا ۙ الْمَلَائِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَارَهُمْ وَذُوقُوا عَذَابَ الْحَرِيقِ

ሌሎቹ “አን-ናሺጧት” النَّاشِطَات ሲባሉ፤ አን-ናሺጧት በመባል የሚታወቁት የሞት መላእክት ደግሞ የአማንያንን ሩሕ በቀስታ በመምዘዝ የሚያወጡ ናቸው፤ አማንያንም ይሰሩት በነበረው መልካም ሥራ ጀነት ይገባሉ፦
79፥2 *በቀስታ መምዘዝንም መዘዦች በኾኑት*፤ وَالنَّاشِطَاتِ نَشْطًا
16፥32 እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው *መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚወስዷቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ»* ይባላሉ፡፡ الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ طَيِّبِينَ ۙ يَقُولُونَ سَلَامٌ عَلَيْكُمُ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

የአማንያን ሩሕ በዒሊዪን ሲሆን የከሃድያን ሩሕ ደግሞ በሢጂን ነው። “ዒሊዪን” عِلِّيِّين “ማለት “ከፍተኛ” ወይም “አርያም” ማለት ሲሆን “ዐሊየት” عَالِيَة ማለት ደግሞ “ከፍተኛይቱ” ማለት ነው፤ የምእምናን መጽሐፍ በእርግጥ በዒሊዮን ውስጥ ነው፦
88፥10 *በከፍተኛ ገነት* ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
69፥22 *በከፍተኛይቱ ገነት* ውስጥ፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

“ሢጂን” سِجِّين የሚለው ቃል “ዩሥጀነ” يُسْجَنَ ማለትም “ታሰረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እስር” ወይም “እንጦሮጦስ” ማለት ነው፤ “ሠጅን” سِّجْن ማለት “መታሰር” ማለት ሲሆን “መሥጁኒን” مَسْجُونِين ደግሞ “እስረኞች” ማለት ነው፤ የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢሥራፊል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

50፥41 *የሚነገርህን አዳምጥም፡፡ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ*፡፡ وَاسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ الْمُنَادِ مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ

“ኢሥራፊል” إِسْـرَافِـيْـل‎ ማለት “ሩፋኤል” ሲሆን ከመላእክት አለቃ አንዱ ነው። እነዚህ የመላእክት አለቃ “ጂብሪል” جِبريل ማለትም “ገብርኤል”፣ “ሚካል” مِيكَال ማለትም “ሚካኤል”፣ “ዐዝራዒል” ማለት عَزرائيل‎ “ዑራኤል” ወዘተ ናቸው። ይህ መልአክ በሐዲስ ስሙ ተጠቅሷል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ: መጽሐፍ 48, ሐዲስ 51
አቡ ሠለማህ እንደነገረን እኔም አዒሻህን”ረ.ዐ.” ነብዩ”ﷺ” ሶላታቸውን ሊከፍቱ በሌሊት በሚቆሙ ጊዜ ምን ይጠቀሙ ነበር? እርሷም፦ *”ሶላታቸውን ሊከፍቱ በሌሊት በሚቆሙ ጊዜ፦ “አላህ ሆይ! የጂብሪል፣ የሚካል፣ “የኢሥራፊል” ጌታ፤ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ፣ ስውሩንና ግልጹን ዐዋቂ፤ በባሮችህ መካከል በሚለያዩበት ነገር የምትፈርድ፤ በእውነት ነገር በተለያዩበት አንተ ምራኝ፤ አንተ ቀጥተኛውን መንገድ መሪ ነህ*። حَدَّثَنَا أَبُو سَلَمَةَ، قَالَ سَأَلْتُ عَائِشَةَ رضى الله عنها بِأَىِّ شَيْءٍ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَفْتَتِحُ صَلاَتَهُ إِذَا قَامَ مِنَ اللَّيْلِ قَالَتْ كَانَ إِذَا قَامَ مِنَ اللَّيْلِ افْتَتَحَ صَلاَتَهُ فَقَالَ ‏ “‏ اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرِيلَ وَمِيكَائِيلَ وَإِسْرَافِيلَ فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضِ وَعَالِمَ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ أَنْتَ تَحْكُمُ بَيْنَ عِبَادِكَ فِيمَا كَانُوا فِيهِ يَخْتَلِفُونَ اهْدِنِي لِمَا اخْتُلِفَ فِيهِ مِنَ الْحَقِّ بِإِذْنِكَ إِنَّكَ تَهْدِي مَنْ تَشَاءُ إِلَى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ ‏”

“ሱር” صُّور ማለት የመለከት “ቀንድ” ሲሆን በትንሳኤ ቀን ነጋሪት የሚነፋበት መለከት”Trumpet” ነው፤ ይህንን መለከት በትንሳኤ ቀን የሚነፋው ኢሥራፊል ነው፦
50፥20 *በቀንዱም ውስጥ ይነፋል፡፡ ያ ቀን የዛቻው መፈጸሚያ ቀን ነው*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْوَعِيدِ
53፥6 ከእነርሱም ዙር፡፡ *ጠሪው መልአክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ*፡፡ فَتَوَلَّ عَنْهُمْ ۘ يَوْمَ يَدْعُ الدَّاعِ إِلَىٰ شَيْءٍ نُّكُرٍ

ነጥብ አንድ
“ቀዳማይ መለከት”
በትንሳኤ ቀን ይህ የመለከት ቀንድ የሚነፋው ሁለቴ ነው፤ የመጀመሪያው የመለከት ቀንድ ሲነፋ ፍጥረተ-ዓለም ይጠፋል፦
27፥87 *በቀንዱም በሚነፋ ቀን በሰማያት ውስጥ ያሉት እና በምድርም ውስጥ ያሉት ሁሉ አላህ የሻው ነገር ብቻ ሲቀር በሚደነግጡ ጊዜ የሚኾነውን አስታውስ*፡፡ ሁሉም የተናነሱ ኾነውም ወደ እርሱ ይመጣሉ፡፡ وَيَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ فَفَزِعَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَن شَاءَ اللَّهُ ۚ وَكُلٌّ أَتَوْهُ دَاخِرِينَ
39፥68 *በቀንዱም ይነፋል፤ በሰማያት ውስጥ ያለው ፍጡር እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ አላህ የሻው ሲቀር በድንጋጤ ይሞታል፡፡ ከዚያም በእርሱ ሌላ መንነፋት ይነፋል፤ ወዲያውም እነርሱ የሚሠራባቸውን የሚጠባበቁ ኾነው ቋሚዎች ይኾናሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَصَعِقَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ إِلَّا مَن شَاءَ اللَّهُ ۖ ثُمَّ نُفِخَ فِيهِ أُخْرَىٰ فَإِذَا هُمْ قِيَامٌ يَنظُرُونَ

በሰማያት ውስጥ ያሉት ፍጥረታት መላእክትም እና በምድርም ውስጥ ያለው ፍጡር ሁሉ ይሞታል፤ አላህ የሻው መልአከ-ሞት ዐዝራዒል እና ኢሥራፊል ሲቀሩ፤ እነርሱም ተራ በተራ ቅድሚያ ኢሥራፊል መጨረሻ ዐዝራዒል ይጠፋሉ፤ ከአላህ ማንነት በስተቀር ሁሉን ነገር ወይም ሁሉን ነፍስ ጠፊና ሟች ነው፤ የማይሞት አንዱ አምላክ ብቻ ነው፦
28፥88 ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው*፡፡ ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ وَلَا تَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ ۘ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَيْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُ ۚ لَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
25፥58 በዚያም *በማይሞተው ሕያው አምላክ* ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا

ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት “ነፍሥ” نَفْس ማለት “የራስ ማንነት”own self-hood” ማለት ነው፦
4፥79 ከደግም የሚያገኝህ ከአላህ ነው፤ ከፉዉም የሚደርስብህ *ከራስህ* ነው፤ مَّا أَصَابَكَ مِنْ حَسَنَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ۖ وَمَا أَصَابَكَ مِن سَيِّئَةٍ فَمِن نَّفْسِكَ ۚ وَأَرْسَلْنَاكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا

“ራስህ” የሚለው ቃል “ነፍሲከ” نَفْسِكَ ሲሆን ማንነትን”identity” ያሳያል፤ የፍጡራን ማንነት መነሻ እንዳለው ሁሉ መዳረሻ አለው፤ መነሻው ሕያውነት ነው፤ መዳረሻው ሞትን መቅመስ ነው፦
3፥185 *ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት*፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ
29፥57 *ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት*፤ ከዚያም ወደ እኛ ትመለሳላችሁ፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۖ ثُمَّ إِلَيْنَا تُرْجَعُونَ

ሰማይና ምድር ይጠቀለላል፤ ፍጥረተ-ዓለም ሲጀመር ህልውና አልባ እንደነበር ወደ ህልውና አልባ ይመለሳል፦
21፥104 *ለመጽሐፎች የኾኑ ገጾች እንደሚጠቀለሉ ሰማይን የምንጠቀልልበትን* ቀን አስታውስ፡፡ *የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን*፡፡ يَوْمَ نَطْوِي السَّمَاءَ كَطَيِّ السِّجِلِّ لِلْكُتُبِ ۚ كَمَا بَدَأْنَا أَوَّلَ خَلْقٍ نُّعِيدُهُ ۚ
ነጥብ ሁለት
"ደኃራይ መለከት"
ከዚያ ሁለተኛ የመለከት ቀንድ ሲነፋ ወደ አለመኖር ጠፍቶ የነበረው ፍጥረተ-ዓለም ወደ መኖር ይመጣል፤ ሙታንም የኢሥራፊልን ጥሪ ሲሰሙ ወዲያውኑም ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ፦
36፥51 *በቀንዱም ይነፋል፤ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ
50፥41 *የሚነገርህን አዳምጥም፡፡ ጠሪው ከቅርብ ስፍራ በሚጠራበት ቀን ከመቃብራቸው ይወጣሉ*፡፡ وَاسْتَمِعْ يَوْمَ يُنَادِ الْمُنَادِ مِن مَّكَانٍ قَرِيبٍ
54፥8 *ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎች ቸኳዮች ኾነው ይወጣሉ፡፡ ከሓዲዎቹ ያን ጊዜ ምን ይላሉ? «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ*፡፡ مُّهْطِعِينَ إِلَى الدَّاعِ ۖ يَقُولُ الْكَافِرُونَ هَـٰذَا يَوْمٌ عَسِرٌ

ይህ ጠሪ ሲጣራ ሁሉም፤ ይሰበሰባል፤ እንስሳትም ሳይቀሩ፦
20፥108 *በዚያ ቀን ለመሰብሰብ ጠሪውን ለእርሱ መጣመም የሌለውን መከተል ይከተላሉ፡፡ ድምጾችም ለአልረሕማን ጸጥ ይላሉ*፡፡ ስለዚህ ሹክሹክታን እንጂ አትሰማም፡፡ يَوْمَئِذٍ يَتَّبِعُونَ الدَّاعِيَ لَا عِوَجَ لَهُ ۖ وَخَشَعَتِ الْأَصْوَاتُ لِلرَّحْمَـٰنِ فَلَا تَسْمَعُ إِلَّا هَمْسًا
81፥5 *እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ*፤ وَإِذَا الْوُحُوشُ حُشِرَتْ
6፥38 *ከተንቀሳቃሽም በምድር የሚኼድ፤ በሁለት ክንፎቹ የሚበርም በራሪ መሰሎቻችሁ ሕዝቦች እንጅ ሌላ አይደሉም*፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ምንንም ነገር አልተውንም፤ *ከዚያም ወደ ጌታቸው ይሰበሰባሉ*፡፡ وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا طَائِرٍ يَطِيرُ بِجَنَاحَيْهِ إِلَّا أُمَمٌ أَمْثَالُكُم ۚ مَّا فَرَّطْنَا فِي الْكِتَابِ مِن شَيْءٍ ۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يُحْشَرُونَ

በዚያም ቀን ዘመድ ዘመዱን አያስጥልም፤ የሚናገሩት ሁሉ በእነርሱ ላይ ይሰውሩባቸዋል፤ ስለዚህ አንዱ የሌላውን ጉዳይ አይጠያየቁም፤ የተለያዩ ጭፍሮች ኾነው የሚመጡበት ቀን ነው፦
23፥101 *በቀንዱም በተነፋ ጊዜ በዚያ ቀን በመካከላቸው ዝምድና የለም፡፡ አይጠያየቁምም*፡፡ فَإِذَا نُفِخَ فِي الصُّورِ فَلَا أَنسَابَ بَيْنَهُمْ يَوْمَئِذٍ وَلَا يَتَسَاءَلُونَ
28፥66 *በዚያም ቀን ወሬዎቹ ሁሉ በእነርሱ ላይ ይሰውሩባቸዋል፡፡ እነርሱም አይጠያየቁም*፡፡ فَعَمِيَتْ عَلَيْهِمُ الْأَنبَاءُ يَوْمَئِذٍ فَهُمْ لَا يَتَسَاءَلُونَ
78፥18 *በቀንዱ በሚነፋና የተለያዩ ጭፍሮች ኾናችሁ በምትመጡ ቀን ነው*፡፡ يَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ فَتَأْتُونَ أَفْوَاجًا

እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአላህ ብቻ ነው፤ ያ ቀን በከሓዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው፦
40፥16 *እነርሱ ከመቃብር በሚወጡበት ቀን በአላህ ላይ ከእነርሱ ምንም ነገር አይደበቅም፡፡ «ንግሥናው ዛሬ ለማን ነው?» ይባላል፤ «ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው» ይባላል*፡፡ يَوْمَ هُم بَارِزُونَ ۖ لَا يَخْفَىٰ عَلَى اللَّهِ مِنْهُمْ شَيْءٌ ۚ لِّمَنِ الْمُلْكُ الْيَوْمَ ۖ لِلَّهِ الْوَاحِدِ الْقَهَّارِ
25፥26 *እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልራሕማን ብቻ ነው*፡፡ በከሓዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡ الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ لِلرَّحْمَـٰنِ ۚ وَكَانَ يَوْمًا عَلَى الْكَافِرِينَ عَسِيرًا
6፥73 *እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን አስታውስ*፡፡ ቃሉ እውነት ነው፡፡ *በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው*፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ ۖ وَيَوْمَ يَقُولُ كُن فَيَكُونُ ۚ قَوْلُهُ الْحَقُّ ۚ وَلَهُ الْمُلْكُ يَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ ۚ

ያ ቀን አላህ "ኹን" የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን ነው፤ አላህ ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ "ኹን" በሚለው ንግግሩ ፈጥሮ አቁሟቸዋል፦
2፥117 *ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው፤» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
30፥25 *ሰማይና ምድርም ያለምሰሶ በትዕዛዙ መቆማቸው፣ ከዚያም መልአኩ ለትንሣኤ ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَن تَقُومَ السَّمَاءُ وَالْأَرْضُ بِأَمْرِهِ ۚ ثُمَّ إِذَا دَعَاكُمْ دَعْوَةً مِّنَ الْأَرْضِ إِذَا أَنتُمْ تَخْرُجُونَ

መልአኩ ለትንሣኤ ከምድር ጥሪን በጠራ ጊዜ አምላካችን አላህ "ኹን" በሚለው ቃል የሰማይና የምድር ብጤ ሌላ ሰማይና ምድር ይፈጥራል፦
14፥48 *ምድር በሌላ ምድር የምትለወጥበትን ሰማያትም እንደዚሁ፤ ፍጡራን ሁሉ አንድ አሸናፊ ለኾነው አላህም የሚገለጹበት ቀን አስታውሱ*፡፡ يَوْمَ تُبَدَّلُ الْأَرْضُ غَيْرَ الْأَرْضِ وَالسَّمَاوَاتُ ۖ وَبَرَزُوا لِلَّهِ الْوَاحِدِ الْقَهَّارِ
36፥81 *ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? ነው እንጅ፡፡ እርሱም በብዙ ፈጣሪው ዐዋቂው ነው*፡፡ أَوَلَيْسَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يَخْلُقَ مِثْلَهُم ۚ بَلَىٰ وَهُوَ الْخَلَّاقُ الْعَلِيمُ
36፥82 *ነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ "ኹን" ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይኾናልም*፡፡ إِنَّمَا أَمْرُهُ إِذَا أَرَادَ شَيْئًا أَن يَقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

መልአኩ ለትንሣኤ ከምድር ጥሪን በጠራን ጊዜ እኛም ወዲያውኑ ከመቃብር የምንወጣ መሆናችን ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፤ አምላካችን አላህ እኛን ሕያው ለማድረግ በቃሉ "ኹን" ሲለን እንነሳለን፦
40፥68 *እርሱ ያ ሕያው የሚያደርግ የሚያሞትም ነው፡፡ አንዳችን ነገር በሻም ጊዜ ለእርሱ የሚለውን «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ هُوَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ فَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ «ኹን» ማለት ብቻ ነው፤ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኪራመን ካቲቢን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

50፥17 *ሁለቱ ቃል ተቀባዮች መላእክት ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ*፡፡ إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ

"ኪራመን ካቲቢን" كِرَامًا كَاتِبِين ማለት "የተከበሩ ጸሐፊዎች" ማለት ነው፤ እነዚህ ጸሐፊዎች በእያንዳንዱ ሰው ቀኝ እና ግራ ያሉ ሁለት መላእክት ናቸው፤ በቀኝ ያለው ሰናይ ተግባራትን ይመዘግባል፤ በግራ ያለው ደግሞ እኩይ ተግባራትን ይመዘግባል፦
82፥11*የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ ተጠባባቂዎች*፡፡ كِرَامًا كَاتِبِينَ
82፥10 *በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ ስትኾኑ*፤ وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِين
82፥12 *የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ*፡፡ يَعْلَمُونَ مَا تَفْعَلُونَ

አነዚህ ሁለት መላእክት በቀኝና በግራችን ስላሉ በሚስጥር የምንሠራውን፣ የምንናገረውን፣ የምንመካከረው እና የምንወያየውን ሁሉ ያውቃሉ፤ እነዚህ ሁለት መላእክት ሥራችንን፣ ንግግራችንን፣ ውይይታችንን እና ምክክራችንን ተጠባብቀው ዝግጁ ሆነው ስለሚመዘግቡ የማዕረግ ስማቸው ደግሞ "ረቂብ" رَقِيب ማለትም "ተጠባባቂ" እና "አቲድ" عَتِيدٌ ማለትም "ዝግጁ" ነው፦
50፥17 *ሁለቱ ቃል ተቀባዮች መላእክት ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ*፡፡ إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ
50፥18 *ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂ እና ዝግጁ የኾኑ መላእክት ያሉበት ቢኾን እንጅ*፡፡ مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ
10፥21 *አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን ነገር በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው*፡፡ قُلِ اللَّهُ أَسْرَعُ مَكْرًا ۚ إِنَّ رُسُلَنَا يَكْتُبُونَ مَا تَمْكُرُونَ
43፥ 80 ወይም እኛ ምስጢራቸውን እና ውይይታቸውን የማንሰማ መኾናችንን ያስባሉን? አይደለም፤ *መልክተኞቻችንም እነርሱ ዘንድ ይጽፋሉ*፡፡ أَمْ يَحْسَبُونَ أَنَّا لَا نَسْمَعُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَاهُم ۚ بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيْهِمْ يَكْتُبُونَ

የምእምናን መጽሐፍ በእርግጥ በዒሊዮን ውስጥ ነው፤ “ዒሊዪን” عِلِّيِّين “ማለት “ከፍተኛ” ወይም “አርያም” ማለት ሲሆን “ዐሊየት” عَالِيَة ማለት ደግሞ “ከፍተኛይቱ” ማለት ነው፦
88፥10 *በከፍተኛ ገነት* ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
69፥22 *በከፍተኛይቱ ገነት* ውስጥ፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፤ “ሢጂን” سِجِّين የሚለው ቃል “ዩሥጀነ” يُسْجَنَ ማለትም “ታሰረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እስር” ወይም “እንጦሮጦስ” ማለት ነው፤ “ሠጅን” سِّجْن ማለት “መታሰር” ማለት ሲሆን “መሥጁኒን” مَسْجُونِين ደግሞ “እስረኞች” ማለት ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ

የትንሳኤ ቀን ይህ የሥራ መዝገብ ይቀርባል፤ ለሰዎች ያስተማሩት ነብያት እና ኪራመን ካቲቢን ምስክሮች ሆነው ይመጣሉ፤ ሰውንም ሁሉ በራሪውን ሥራው ተከትቦ በአንገቱ ላይ ይይዝና በትንሣኤ ቀን የተዘረጋ መጽሐፍ ሆኖ ይወጣለታል፤ መላእክት የከተቡትን ያንን የሥራውን መዝገብ አንብብ ይባላል፦
39፥69 ምድርም በጌታዋ ብርሃን ታበራለች፡፡ *መጽሐፉም ይቅቀረባል፡፡ ነቢያቱ እና ምስክሮቹም ይመጣሉ፡፡ በመካከላቸውም በእውነት ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ وَأَشْرَقَتِ الْأَرْضُ بِنُورِ رَبِّهَا وَوُضِعَ الْكِتَابُ وَجِيءَ بِالنَّبِيِّينَ وَالشُّهَدَاءِ وَقُضِيَ بَيْنَهُم بِالْحَقِّ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
17፥13 *ሰውንም ሁሉ በራሪውን ሥራውን በአንገቱ አስያዝነው፡፡ ለእርሱም በትንሣኤ ቀን የተዘረጋ ኾኖ የሚያገኘው የኾነን መጽሐፍ እናወጣለታለን*፡፡ وَكُلَّ إِنسَانٍ أَلْزَمْنَاهُ طَائِرَهُ فِي عُنُقِهِ ۖ وَنُخْرِجُ لَهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ كِتَابًا يَلْقَاهُ مَنشُورًا
17፥14 *«መጽሐፍህን አንብብ፤ ዛሬ በአንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ በቃ» ይባላል*፡፡ اقْرَأْ كِتَابَكَ كَفَىٰ بِنَفْسِكَ الْيَوْمَ عَلَيْكَ حَسِيبًا

በዒሊዮን ውስጥ ያለው የምእምናን መጽሐፍ በእርግጥ ለአማንያን በቀኙ ይሰጠዋል፤ በተቃራኒው በሲጂን ውስጥ ያለው የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ ለከሃድያን በግራው ይሰጠዋል፦
69፥19 *መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ ለጓደኞቹ «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል*፡፡ فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ فَيَقُولُ هَاؤُمُ اقْرَءُوا كِتَابِيَهْ
69፥25 *መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል*፡፡ وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِشِمَالِهِ فَيَقُولُ يَا لَيْتَنِي لَمْ أُوتَ كِتَابِيَهْ

መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰው ምንኛ የተከበረ የቀኝ ጓድ ነው፤ መጽሐፉን በግራው የተሰጠ ሰው ምንኛ የተዋረደ የግራ ጓድ ነው፦
56፥27 *የቀኝም ጓዶች ምንኛ የከበሩ የቀኝ ጓዶች! ናቸው?*። وَأَصْحَابُ الْيَمِينِ مَا أَصْحَابُ الْيَمِين
56፥41 *የግራ ጓደኞችም ምንኛ የተዋረዱ የግራ ጓዶች! ናቸው?*፡፡ وَأَصْحَابُ الشِّمَالِ مَا أَصْحَابُ الشِّمَالِ

አላህ በዒሊዮን ውስጥ ያለው የምእምናን መጽሐፍ በቀኛችን ሰጥቶ የቀኝ ጓዶች ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በርዘኽ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

23፥100 *ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አለ*፡፡ ۖ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

ሞት በመጣ ጊዜ "ሙንከር" مُنْكَر እና "ነኪር" نَّكِير የተባሉት ሁለት መላእክት ለሟቹ በሩሑ፦ "ጌታህ ማን ነው? ዲንህ ምንድን ነው? ነቢይህ ማን ነው?" ብለው በቀብር ውስጥ ይጠይቃሉ፤ አማኝም ከሆነ፦ "ጌታዬ አላህ ነው፣ ዲኔ ኢስላም ነው፣ ነብዬም የአላህ መልእክተኛ ነው" ብሎ ይመልሳል፤ ለእርሱ ጀነት እዲገባ ይከፈትለታል። ከሃዲ ከሆነ፦ "ዐላውቅም፣ ዐላውቅም፣ ዐላውቅም" ብሎ ይመልሳል፤ ለእርሱ እሳት እዲገባ ይከፈትለታል። አቢ ዳውድ እና ተርሚዚ ዘግበውታል፤ ሐዲሱ እረጅም ስለሆነ ገብተው ያንብቡ፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 158
ጃምዒ አት-ተርሚዚ: መጽሐፍ 10, ሐዲስ 107

“በርዘኽ” برزخ ማለት የቃሉ ትርጉም “ጋራጅ” ወይም "ግርዶ" ማለት ነው፤ ጥቁር ባሕር፣ አትላንቲ ውቂያኖስ፣ ባልቲክ ባሕር፣ ፓስፊክ ውቂያኖስ፣ ሜድትራኒያን ባሕር፣ ኢንዲያን ውቂያኖስ፣ ቀይ ባሕር በውስጣቸው መራራ ውኃ እና ጣፋጭ ውኃ ይዘዋል፤ እነዚህ ሁለቱ ባሕሮች እንዳይገናኙ በመካከላቸው "በርዘኽ" አለ፦
55፥19 *ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው*፡፡ مَرَجَ الْبَحْرَيْنِ يَلْتَقِيَانِ
55፥20 *እንዳይገናኙ በመካከላቸው ጋራጅ አለ፡፡ አንዱ ባንዱ ላይ ወሰን አያልፉም*፡፡ بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌ لَّا يَبْغِيَانِ
25፥53 *እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች፣ አጐራብቶ የለቀቀ ነው፤ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፤ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፤ በመካከላቸውም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን “ግርዶ” ያደረገ ነው*። وَهُوَ ٱلَّذِى مَرَجَ ٱلْبَحْرَيْنِ هَٰذَا عَذْبٌۭ فُرَاتٌۭ وَهَٰذَا مِلْحٌ أُجَاجٌۭ وَجَعَلَ بَيْنَهُمَا بَرْزَخًۭا وَحِجْرًۭا مَّحْجُورًۭا
27፥61 *በሁለቱ ባሕሮችም በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል "ግርዶን" ያደረገ ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?* ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም። أَمَّن جَعَلَ ٱلْأَرْضَ قَرَارًۭا وَجَعَلَ خِلَٰلَهَآ أَنْهَٰرًۭا وَجَعَلَ لَهَا رَوَٰسِىَ وَجَعَلَ بَيْنَ ٱلْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

በተመሳሳይ ከሞት በኃላ የገነትም ሰዎች እና የእሳትን ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከላቸውም ግርዶሽ አለ፦
7፥46 *በመካከላቸውም "ግርዶሽ" አለ፤ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለእናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም የአዕራፍ ሰዎች የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም*፡፡ وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ ۚ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ ۚ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ ۚ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُون
"አዕራፍ" أَعْرَاف በጀነት ሰዎች እና በእሳት ሰዎች መካከል ያለ ስፍራ ሲሆን ሚዛናቸው እኩል የሆኑ ሰዎች ደግሞ የአዕራፍ ሰዎች ይባላሉ፤ የገነት ሰዎች የእሳት ሰዎችን እንዲሁ የእሳት ሰዎች የገነት ሰዎችን ያነጋግሯቸዋል፦
7፥44 *የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎች፦ «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፡፡ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን» ሲሉ ይጣራሉ፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል*፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ
7፥50 *የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎች፦ «በእኛ ላይ ከውሃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ጣሉልን» ብለው ጠሩዋቸዋል፡፡ እነርሱም «አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም አድርጓቸዋል» ይሏቸዋል*፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ النَّارِ أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَنْ أَفِيضُوا عَلَيْنَا مِنَ الْمَاءِ أَوْ مِمَّا رَزَقَكُمُ اللَّهُ ۚ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ حَرَّمَهُمَا عَلَى الْكَافِرِينَ

ምን ዋጋ አለው አይደለም ሰውን ጌታን ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ ብሎ ማናገር ከንቱ ቃል ናት፦
39፥58 *ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ ወደ ምድረ ዓለም አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝ እና ከበጎ አድራጊዎቹ በኾንኩ» ማለቷን ለመፍራት መልካሙን ተከተሉ*፡፡ أَوْ تَقُولَ حِينَ تَرَى الْعَذَابَ لَوْ أَنَّ لِي كَرَّةً فَأَكُونَ مِنَ الْمُحْسِنِينَ
23፥99 አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል፦ *«ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ
23፥100 *«በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡»* ይህን ከማለት ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት*፡፡ لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا

እንግዲህ በርዘኽ የሚባለው የገነት ሰዎች እና የእሳት ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከላቸውም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ መካከል ያለ ሁኔታ"Intermediate zone ነው፦
23፥100 *ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አለ*፡፡ ۖ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

ይህ በርዘኽ ውስጥ የገነት ሰዎች ሩሕ በዒሊዪን ሲሆን “ዒሊዪን” عِلِّيِّين “ማለት “ከፍተኛ” ወይም “አርያም” ማለት ነው፤ “ዐሊየት” عَالِيَة ማለት ደግሞ “ከፍተኛይቱ” ማለት ነው፦
88፥10 *በከፍተኛ ገነት* ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

የእሳት ሰዎች ሩሕ ደግሞ በሢጂን ነው፤ “ሢጂን” سِجِّين የሚለው ቃል “ዩሥጀነ” يُسْجَنَ ማለትም “ታሰረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እስር” ወይም “እንጦሮጦስ” ማለት ነው፤ “ሠጅን” سِّجْن ማለት “መታሰር” ማለት ሲሆን “መሥጁኒን” مَسْجُونِين ደግሞ “እስረኞች” ማለት ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ

ሩሕ በትንሳኤ ቀን ከአካል ጋር ተዋሕዶ ፍርድ እስከሚሰጠው ድረስ በበርዘኽ ያለው ጊዚያዊ ቆይታ በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል። "ሩሕ" رُّوح ማለት "መንፈስ" ማለት ሲሆን ይህ የሰው መንፈስ ሥረ-መሰረቱ ከዐፈር ሳይሆን ከጌታችን ነገር ነው፤ ስለ “ሩሕ” የተሰጠን ዕውቀት ጥቂት ብቻ ነው፦
17፥85 *ስለ ሩሕም ይጠይቁሃል፤ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፤ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِ ۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّى وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًۭا

አላህ በዒሊዮን ውስጥ ከሚደሰቱ ባሮቹ ያድርገን፤ ከሢጂን ውስጥ ቅጣት ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማሊክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6:21በአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? እነሆ በደለኞች አይድኑም፡፡

መግቢያ
በቁርአን ከተገለፁት የአላህ ስሞች መካከል “አል-ማሊክ” المَٰلِك ሲሆን “ባለቤት” ወይም “ባለ-መብት” ማለት ነው፤ “ሚም” م ፈትሃ አሊፍ ስኩን “ማ” مَٰ የነበረው “ሚም” م ፈትሃ ‘መ” مَ በሚል ሲቀራ “መሊክ” مَلِك ይሆናል፤ ትርጉሙም “ንጉሥ” ማለት ነው፤ አላህ የንግሥና እና የፍርዱ ቀን ባለቤት ነው፦
1፥4 የፍርዱ ቀን “ባለቤት” مَٰلِكِ ለኾነው مَٰلِكِ يَوْمِ ٱلدِّينِ ፡፡
3፥26 በል፡- «የንግስና “ባለቤት” مَٰلِكَ የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ قُلِ ٱللَّهُمَّ مَٰلِكَ ٱلْمُلْكِ تُؤْتِى ٱلْمُلْكَ مَن تَشَآءُ وَتَنزِعُ ٱلْمُلْكَ مِمَّن تَشَآءُ ፡፡

የአላህን ስም ከፍጡራን ስም ማመሳሰል ሺርክ ነው፤ ግራም ነፈሰ ቀኝ ሲጀመር “ማሊክ” የሚለው ቃል ተመሳሳይ ቃልና ትርጉም አለው ማለት ተመሳሳይ ሃሳብ አለው ማለት አይደለም፤ የአንድን ቃል አማራጭ ሃሳብ የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ለምሳሌ ሰዎች “መሊክ” ተብለዋል፦
36፥71 እኛ እጆቻችን ከሠሩት ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ “ባለ መብቶች” ናቸው أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَآ أَنْعَٰمًۭا فَهُمْ لَهَا مَٰلِكُونَ ፡፡

“ባለ መብቶች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ማሊኩን” مَٰلِكُونَ ሲሆን የማሊክ ብዙ ቁጥር ነው፤ አላህ አል-ማሊክ የተባለበት የባህርይ ስሙ ሲሆን ሰዎች ደግሞ አላህ በእንስሳት ላይ ስልጣን መኖራቸውን የሰጣቸውን ፀጋ የሚያሳይ የማዕረግ ስም ነው፤ “ማሊክ” የጀሃነም ዘበኛ ከሆኑት አሥራ ዘጠኝ መላእክት መካከል የአንዱ መልአክ የተፀውኦ ስም ሆኖ ተገልጿል፦
43:75-77 ከእነሱ ቅጣቱ አይቀልላቸውም፤ እነርሱም በርሱ ውስጥ ተስፋ ቆራጮች ናቸው። አልበደልናቸውምም፤ ግን በዳዮቹ እነርሱው ነበሩ። “ማሊክ ሆይ”! يَا مَالِكُ “ጌታህ” በኛ ላይ በሞት ይፍረድ እያሉ ይጣራሉም፤ እናንተ በቅጣቱ ውስጥ ዘላለም ኗሪዎች ናችሁ “”ይላቸዋል””።

እዚህ ጋር ነው የመጣጥፌ ጭብጥ፤ አንቀፁ ላይ “ጌታህ” የሚል ቃል ስላለ፤ አላህ ማሊክ ተብሏልና የአላህ ጌታ ማን ነው? በማለት ሚሽሩሪዎች ይጠይቃሉ፤ ይህ እጅግ የወረደ ጥያቄ ነው፤ ይህ ሙግት ኢየሱስ ጌታ ሆኖ አምላክ ስላለው ለዛ ሙግት ማስተባበያ መሆኑ ነው፤ ይህንን የደፈረሰና የተውረገረገ መረዳት ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንመልከተው፦

ነጥብ አንድ
“የእሳት ሰዎች”
“የእሳት ሰዎች” አላህ የእሳት ሰዎች ከመሆን ይጠብቀን፤ እነርሱ የሚጠይቁት እና የሚመልስላቸው “ማሊክ” የተባለውን መልአክ ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም የጀሃነም ዘበኞችን የሆኑትን መላእክት ይጠይቃሉ እነርሱም ይመልሳሉ፦
40:49 እነዚያም በእሳት ውስጥ ያሉት፦ “ለገሀነም ዘበኞች” “”ጌታችሁን”” ለምኑልን፤ ከኛ ላይ ከቅጣቱ አንድን ቀን ያቃልልን፤ “ይላሉ”።
39:71 እነዚያ የካዱትም፣ የተከፋፈሉ ጭፍሮች ሆነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፤ በመጧትም ጊዜ ደጃፎችዋ ይከፈታሉ፤ ዘበኞችዋም፦ “”ከእናንተ የሆኑ መልክተኞች የጌታችሁን አንቀጾች በእናንተ ላይ የሚያነቡላችሁ የዚህንም ቀን መገናኘት የሚያስጠነቅቋችሁ አልመጡዋችሁምን? ፤ የለም “”ይሏቸዋል””፤ መጥተውናል ግን የቅጣቲቱ ቃል በከሐዲዎች ላይ ተረጋገጠች “”ይላሉ””።
67:8 ከቁጭትዋ የተነሳ ልትቆራረጥ ትቀርባለች፤ በውስጧ ጭፍሮች በተጣሉ ቁጥር “ዘበኞችዋ”፦ “አስጠንቃቂ አልመጣችሁምን? በማለት “ይጠይቋቸዋል”።

ልብ አድርግ የእሳት ሰዎች ማሊክን “ጌታህ” ባሉበት ሒሳብ ነው የገሃነም ዘበኞችን “ጌታችሁ” ያሉት፤ የእሳት ሰዎች ማሊክን በጠየቁበት ስሌት ነው የገሃነም ዘበኞችን የጠየቁት፤ ማሊክ ለእሳት ሰዎች በመለሰበት ቀመር ነው የእሳት ዘበኞች ለእሳት ሰዎች የመለሱት።
ነጥብ ሁለት
“የእሳትን ዘበኞች”
ሙፈሲሪን በሐዲስ ላይ በተገኘው ሪዋያህ “ማሊክ” የጀሃነም እሳት ዘበኛ መሆኑን ገልፀዋል፤ ይህም ዘገባ በሐዲስ ላይ ማሊክ የእሳት ዘበኛ መሆኑ ቁልጭ ባለ መልኩ ተጠቅሷል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 47:
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “በሌሊት ላይ ሁሉት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፤ ከእነርሱ አንዱ እንዲህ አለ፦ ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን “የእሳት ዘበኛ” ነው፤ እኔ ጂብሪል ነኝ፣ ይህ ሚካኤል ነው قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ።

ምን ትፈልጋላችሁ? ማሊክ የእሳት ዘበኛ መሆኑ ከታወቀ ከአሥራ ዘጠኝ የእሳትንም ዘበኞች አንዱ ነው፤ የእሳትንም ዘበኞች በቁጥር አሥራ ዘጠኝ ሲሆን ከእነርሱ መካከል የልኡካኑ ቡድን አለቃ ማሊክ ነው፦
74:30-31 በእርሷም ላይ አሥራ ዘጠኝ “ዘበኞች” አሉባት፤ አመጠኞች በገሀነም ስቃይ ውስጥ በእርግጥ ዘውታሪዎች ናቸው። የእሳትንም ዘበኞች፣ “መላእክት” እንጅ ሌላ አላደረግንም፤ ቁጥራቸውንም፣ ለነዚያ ለካዱት መፈተኛ እንጅ አላደረግንም፤

ስለዚህ የእሳት ሰዎች “ማሊክ ሆይ!” ያሉት የእሳት ዘበኛ የሆነውን መልአክ ሲሆን “ጌታህ” ያሉት ደግሞ የመላእክት ጌታ የሆነውን አላህ ነው፤ ሆን ብሎ በአላህ ላይ ውሸት መዋሸትና ይህ እውነት ሲመጣ ያስተባበለ ሰው በዳይ ነው፤ ለከሃድያን መኖሪያ ገሃነም ነው፦
39:32 በአላህ ላይም ከዋሸ እውነቱንም በመጣለት ጊዜ ከአስተባበለ ሰው ይበልጥ በላይ በዳይ ማን ነው? በገሀነም ውስጥ ለከሐዲዎች መኖሪያ የለምን?

መደምደሚያ
ድምዳሜዬን በአንድ ማነፃፀሪያ የባይብል ሙግት ልደምድም፤ “ሞሎክ” ወይም “መለክ” מֹלֶךְ ትርጉሙ “ንጉሥ” ማለት ነው፤ ይህ ስም የከነዓን እና የአሞናውያን ጣኦት ስም ነው፤ ይህ ጣዖት የተበጀለት ማንነት የእሳት መልአክ እንደሆነ ስለሚያምኑ ከነዓናውያን በእሳት እንዳይቀጣቸው የበኩር ልጃቸው በሄኖም ሸለቆ ላይ “ቶፌት” ማለትም የእሳት ምድጃ” ሰርተው መስዋዕ ያቀርቡለት፣ ይሰግዱለትና ያመልኩት ነበር፦
ዘሌዋውያን 18፥21 ከዘርህም “ለሞሎክ” לַמֹּ֑לֶךְ በእሳት አሳልፈህ አትስጥ፥ የአምላክህንም ስም አታርክስ፤ እኔ ያህዌህ ነኝ።
ዘሌዋውያን 20፥2 ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው ዘሩን “ለሞሎክ” לַמֹּ֖לֶךְ ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው።
አሞጽ 5:26 ለራሳችሁም የሠራችኋቸውን ምስሎች፥ “የሞሎክን” ድንኳንና የአምላካችሁን የሬፋን ኮከብ አነሣችሁ።
ራእይ14፥18 “”በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ”” ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን፦ ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ።

አሞጽ 5:26 ላይ “ሞሎክ” מֹלֶךְ ተብሎ የተቀመጠውን ግሪክ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ባሲለዩስ” βασιλεύς ብለውታል፤ ትርጉሙም “ንጉሥ” ማለት ነው፤ ልብ አድርግ “ሞሎክ” ወይም “መለክ” מֹלֶךְ ቃሉና ትርጉሙ አንድ ነው ማለት ቃሉና ትርጉሙ የወከለው ሃሳብ አንድ ነው ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም ይህ ስም ለጣኦቱ የተፀውኦ ስም ቢሆንም ለፈጣሪ ግን የባህርይ ስም ሆኖ ተገልፃል፤ ታዲያ ፈጣሪ የከነዓን እና የአሞናውያን ጣኦት ነውን? እንደማትሉኝ ግልፅ ነው፤ ፈጣሪ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር “ንጉሥ” ነው፤ እርሱ ታላቅ ንጉሥ ነው፦
መዝሙር 74፥12 ያህዌህ ግን ከዓለም አስቀድሞ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነው፥
መዝሙር 95፥3 ያህዌህ ታላቅ አምላክ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነውና።
መዝሙር 47፥2 ያህዌህ ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነውና።
መዝሙር 47፥7 ያህዌህ ለምድር ሁሉ “ንጉሥ” מֶ֖לֶךְ ነውና፤

ከላይ ያለውን የቁርአን ሃሳብ በዚህ ስሌት ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ለዲያብሎስ እርድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥34 *ለሕዝብም ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን፡፡ ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ አዘዝናቸው፡፡ አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۗ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا

“መንሠክ” مَنسَك ማለት “መስዋዕት” ወይም “ሥርዓተ ሃይማኖት” ማለት ሲሆን “ሀድይ” هَدْي ማለት “የእርድ እንስሳ” ማለት ነው፤ ይህም እርድ ጊደር፣ በግ፣ ፍየል፣ ጥጃ፣ ግመል ነው፤ ይህ ለአላህ የሚቀርበው መስዋዕት “ቁርባን” ይባላል፤ “ቁርባን” قُرْبَان የሚለው ቃል “ቀርረበ” قَرَّبَ ማለትም “አቀረበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መቃረቢያ” “አምሃ” “እጅ መንሻ” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ለሕዝብም ሁሉ ወደ እርሱ መስዋዕት ማቅረብን አዟል፦
22፥34 *ለሕዝብም ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን፡፡ ከቤት እንስሳት በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ብቻ ያወሱ ዘንድ አዘዝናቸው፡፡ አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۗ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا

ይህ ሆኖ ሳለ ግን በባይብል ላይ መስዋዕት ለሁለት ምንነቶች እንዲቀርብ ታዟል፤ አንዱ ለፈጣሪ ሲሆን ሁለተኛው ለዲያብሎስ ነው፦
ዘሌዋውያን 16፥8 አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ *አንዱን ዕጣ ለያህዌህ ሌላውንም ዕጣ ለዐዛዝኤል*።

ዕብራይስጡ፦
וְנָתַן אַהֲרֹן עַל-שְׁנֵי הַשְּׂעִירִם, גֹּרָלוֹת--גּוֹרָל אֶחָד לַיהוָה, וְגוֹרָל אֶחָד לַעֲזָאזֵל.
ዐረቢኛው፦
وَيُلْقِي هَارُونُ عَلَى التَّيْسَيْنِ قُرْعَتَيْنِ: قُرْعَةً لِلرَّبِّ وَقُرْعَةً لِعَزَازِيل
ኢንግሊሹ፦
"There he shall draw lots, using two stones, one marked *"for the LORD"* and the other *"for Azazel*."(Good News Translation)

ሁለት ፍየል እጣ ይጣልበታል፤ አንዱ ለያህዌህ ሁለተኛ ለዐዛዝኤል ነው፤ ተርጓሚዎች "ዐዛዝኤል" የሚለው ቃል "መለቀቅ" " የምድረ-በዳ ፍየል" እያሉ ትርጉሙን ሊያዛቡ ቢፈልጉም የዕብራይስጡ "ዐዛዝኤል" עֲזָאזֵל የዐረቢኛው "ዐዛዚል" عَزَازِيل ብሎ በግልጽ አስቀምጦታል፤ "ዐዛዝኤል" ታዲያ ማን ነው? የጥንት ሆነ የአሁን የባይብል ማብራሪያዎች ጋኔን ነው ብለው አስቀምጠውታል፤ ይህ ጋኔን ስሙ በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ከሃያ አንዱ አጋንንት አስረኛው ጋኔን ዐዛዝኤል ነው፦
ሄኖክ 19፥10-12 *የእነዚያ የአጋንንት ስማቸው እንደዚህ ነው*፦
አለቃቸው ስማዝያ፣ ሁለተኛውም አርስጢኪፋ ነው፣ ሥስተኛውም አርሚን ነው፣ አራተኛውም ኮክብኤል ነው። አምስተኛውም ጡርኤል ነው፣ ስድስተኛውም ሩምያል ነው፣ ሰባተኛውም ዳንኤል ነው፣ ስምንተኛውም ምቃኤል ነው፣ ዘጠነኛውም በራቃኤል ነው፣ *አስረኛውም "አዛዝኤል" ነው*፣ አስራ አንደኛውም አርማሮስ ነው፣ አስራ ሁለተኛውም በጠርያል ነው*።
ሄኖክ 3፥10 *በዐዛዝኤል ሥራና ትምህርት ምድር ሁሉ ጠፋች፤ የሰውን ሁሉ ኃጢአት በእርሱ ጻፍበት አለው*።
ሄኖክ 15፥7 *በአዛዝኤል ይፈረድበታል፤ በወገኖችሁ ሁሉ፤ በመላእክት ጌታ ስም ባላመኑ በሰራዊቱም ሁሉ ይፈረድባቸዋል*።

ዐዛዝኤል በግዕዝ ትውፊታዊ አጠራሩ "ሳጥናኤል" ይባላል፤ ከሥነ-አምክኖ አንጻር እስቲ እዩት አንዱ ለፈጣሪ ሁለተኛው ለመለቀቅ ወይም ለምድረ-በዳ ፍየል ይገበርለት እንበልና፤ ለምንስ ለመለቀቅ ወይም ለምድረ-በዳ ፍየል ይገበራል? ከያህዌህ በስቀር ለሌላ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ ተብሏል እኮ፦
ዘጸአት 22፥20  *ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ*።

ከአንዱ አምላክ ውጪ ለሌላ ማንነትና ምንነት መስዋዕት መሰዋት ይህንን ያክል ከባድ ወንጀል ከሆነ እንግዲያውስ ለሳጥናኤል የፍየል መስዋዕት አቅርብ የሚለውን የብርዘት ውጤት ትታችሁ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ብቻ እንድትሰዉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፤ ሙስሊም መስዋዕቱ ለፈጠረው ብቻ ነው፦
6፥162 *«ሶላቴ፣ "መስዋዕቴም"፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው»* በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኒፋቅ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا

"ኒፋቅ" نِفَاق የሚለው ቃል "ናፈቀ" نَافَقَ ማለትም "ነፈቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ኑፋቄ" ወይም "ምንፍቅና" አሊያም "አስመሳይነት" ማለት ነው፤ "ኑፋቄ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ነፈቀ" ማለትም "ከፈለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ክፍልፍል" ወይም "አራጥቃ" ማለት ነው፤ ዓመት ለሁለት ስንከፍለው ስድስት ወሩ "መንፈቅ" ይባላል።አለቃ ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ገፅ 645።

ኒፋቅ በውስጥ ኩፍር በውጪ ኢማን የሆነ ሁለት አይነት ገጽታ ያለው ነገር ነው፤ ኒፋቅ ያለበት ግለሰብ ደግሞ በነጠላ "ሙናፊቅ" مُنَٰفِق ሲባል በብዜት "ሙናፊቁን" مُنَٰفِقُون ወይም "ሙናፊቂን" مُنَٰفِقِين ይባላል፤ በአማርኛችን "መናፍቅ" "መናፍቃን" ማለት ነው። አላማቸው ኡማውን መከፋፈልና መበታተን ነው፦
63፥7 *እነርሱ እነዚያ ፡- «አላህ መልክተኛ ዘንድ ላሉት ሰዎች እስከሚበታተኑ ድረስ አትቀልቡ» የሚሉ ናቸው፡፡ የሰማያትና የምድር ድልቦችም የአላህ ናቸው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም*፡፡ هُمُ الَّذِينَ يَقُولُونَ لَا تُنفِقُوا عَلَىٰ مَنْ عِندَ رَسُولِ اللَّهِ حَتَّىٰ يَنفَضُّوا ۗ وَلِلَّهِ خَزَائِنُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَـٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَفْقَهُونَ

ውጪአቸው አማኝ ነው ውስጣቸው ግን ክህደት አለ፤ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፤ አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም፤ ወደ ቁርኣንና ወደ ሐዲስ አይመጡም፦
4፥142 *መናፍቃን አላህን ያታልላሉ፡፡ እርሱም አታላያቸው ነው፡፡ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا
2፥8 *ከሰዎችም «በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ አሉ፤ እነርሱም አማኞች አይደሉም*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَقُولُ آمَنَّا بِاللَّهِ وَبِالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَا هُم بِمُؤْمِنِينَ
2፥9 *አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም*፡፡ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَمَا يَخْدَعُونَ إِلَّا أَنفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ
3፥167 *እነዚያንም የነፈቁትን* እና ለእነርሱ «ኑ፤ በአላህ መንገድ ተጋደሉ፤ ወይም ተከላከሉ፤» የተባሉትን ሊገልጽ ነው፡፡ «መዋጋት መኖሩን ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር» አሉ፡፡ *እነርሱ ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው፡፡ በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ፡፡ አላህም የሚደብቁትን ዐዋቂ ነው*፡፡ وَلِيَعْلَمَ الَّذِينَ نَافَقُوا ۚ وَقِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا قَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَوِ ادْفَعُوا ۖ قَالُوا لَوْ نَعْلَمُ قِتَالًا لَّاتَّبَعْنَاكُمْ ۗ هُمْ لِلْكُفْرِ يَوْمَئِذٍ أَقْرَبُ مِنْهُمْ لِلْإِيمَانِ ۚ يَقُولُونَ بِأَفْوَاهِهِم مَّا لَيْسَ فِي قُلُوبِهِمْ ۗ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يَكْتُمُونَ
4፥61 ለእነርሱም፡- *«አላህ ወደ አወረደው ቁርኣን እና ወደ መልክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ መናፍቃን ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا إِلَىٰ مَا أَنزَلَ اللَّهُ وَإِلَى الرَّسُولِ رَأَيْتَ الْمُنَافِقِينَ يَصُدُّونَ عَنكَ صُدُودًا
2፥14 *እነዚያንም ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ ወደ ሰይጣኖቻቸውም ባገለሉ ጊዜ «እኛ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን»* ይላሉ፡፡ وَإِذَا لَقُوا الَّذِينَ آمَنُوا قَالُوا آمَنَّا وَإِذَا خَلَوْا إِلَىٰ شَيَاطِينِهِمْ قَالُوا إِنَّا مَعَكُمْ إِنَّمَا نَحْنُ مُسْتَهْزِئُونَ

የመናፍቃን ቅጣቱ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፦
4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا
9፥68 *መናፍቃንንና መናፍቃትን፣ ከሓዲዎችንም አላህ የገሀነምን እሳት በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ እርሷ በቂያቸው ናት፡፡ አላህም ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው*፡፡ وَعَدَ اللَّهُ الْمُنَافِقِينَ وَالْمُنَافِقَاتِ وَالْكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ هِيَ حَسْبُهُمْ ۚ وَلَعَنَهُمُ اللَّهُ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ مُّقِيمٌ
የሙናፊቅ ምልክቶች ሦስት ናቸው፦ ሲናገር ይዋሻል፣ ሲያምኑት ይከዳል፣ ቃል የገባውን ያፈርሳል፦
 ኢማም ቡኻሪይ  መጽሐፍ 55, ሐዲስ 12
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው ነብዩ"ﷺ" ሲናገሩ፦ *"የሙናፊቅ ምልክቶች ሦስት ናቸው፦ ሲናገር ይዋሻል፣ ሲያምኑት ይከዳል፣ ቃል የገባውን ያፈርሳል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ آيَةُ الْمُنَافِقِ ثَلاَثٌ، إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ، وَإِذَا اؤْتُمِنَ خَانَ، وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ ‏.‏

ነጥብ አንድ
"ሲታመን ይከዳል"
አምላካችን አላህ አማና ሲጣልብን አማናችን መወጣት እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥58 *አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል*፡፡ በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ النَّاسِ أَن تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا
8፥27 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን አትክዱ፡፡ *አደራዎቻችሁንም እናንተ እያወቃችሁ አትክዱ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَخُونُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ وَتَخُونُوا أَمَانَاتِكُمْ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ

ነጥብ ሁለት
"ሲናገር ይዋሻል"
ሙስሊም ከዋሸ ቀኑ ተበላሸ ይላል ያገሬ ሰው፤ አንድ ሙናፊቅ "አባይ" "ቀላማጅ" "ዋሾ" "በጥራቃ" "ውሸታም" "ሐሰተኛ" "ወሽከታ" ነው፤ አምላካችን አላህ፦ "ሐሰትንም ቃል ራቁ" "ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ" ብሎ ያዘናል፦
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَاجْتَنِبُوا الرِّجْسَ مِنَ الْأَوْثَانِ وَاجْتَنِبُوا قَوْلَ الزُّورِ
33፥70 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ *ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا

ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ይቀጥላል...

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኒፋቅ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا

ነጥብ ሦስት
"ቃል ገብቶ ያፈርሳል"
ቃል ገብቶ ማፍረስ ከመሃላ አይተናነስም፤ አምላካችን አላህ፦ "በቃል ኪዳኖች ሙሉ" ይለናል፦
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በቃል ኪዳኖች ሙሉ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
17፥34 የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ፡፡ *በኪዳናችሁም ሙሉ፤ ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና*፡፡ وَلَا تَقْرَبُوا مَالَ الْيَتِيمِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ حَتَّىٰ يَبْلُغَ أَشُدَّهُ ۚ وَأَوْفُوا بِالْعَهْدِ ۖ إِنَّ الْعَهْدَ كَانَ مَسْئُولًا

ነገር ግን ይህ ምልክት የሚታይበት ሁሉ ሙናፊቅ ላይሆን ይችላል፤ ግን መናፍቅ የሚያሰኘው ጉዳይ ነብያችን"ﷺ" እንዲህ ይነግሩናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 116
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር"ረ.ዐ." እንደነገረን የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፡- *“አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ግልጽ መናፍቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ውስጥ አንዱ ያለበት ሰው ደግሞ እስኪተወው ድረስ ከኑፋቄ ከፊሉ ጠባይ አለበት ማለት ነው፤ አራቱ ነገሮች፡- ሲታመን ይከዳል፣ ሲናገር ይዋሻል፣ ቃል ገብቶ ያፈርሳል፣ ሲሟገት ያስተባብላል*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ أَرْبَعٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ كَانَ مُنَافِقًا خَالِصًا وَمَنْ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْهُنَّ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْ نِفَاقٍ حَتَّى يَدَعَهَا إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ وَإِذَا عَاهَدَ غَدَرَ وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ وَإِذَا خَاصَمَ فَجَرَ ‏"‏ ‏

ነጥብ አራት
"ሲሟገት ያስተባብላል"
መናፍቃን የአላህ አንቀጾች ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ መከራከር ይወዳሉ፦
45፥25 *አንቀጾቻችንም ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ ክርክራቸው* «እውነተኞች እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡ» *ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም*፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمْ إِلَّا أَن قَالُوا ائْتُوا بِآبَائِنَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
10፥95 *ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና*፡፡ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ الْخَاسِرِينَ
4፥107 *ከነዚያም እራሳቸውን ከሚበድሉት ላይ አትከራከር*፤ አላህ ከዳተኛ ኀጢአተኛ የሆነን ሰው አይወድምና። وَلَا تُجَادِلْ عَنِ الَّذِينَ يَخْتَانُونَ أَنفُسَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ خَوَّانًا أَثِيمًا

ነጥብ አምስት
"በጥቂት አለመብቃቃት"
በጥቂት መብቃቃትን የአማኞች ባህርይ ነው፤ በጥቂት አለመብቃቃት የመናፍቃን ባህርይ ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ: መጽሐፍ 70, ሐዲስ 22
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል፤ ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ الْمُؤْمِنَ يَأْكُلُ فِي مِعًى وَاحِدٍ، وَإِنَّ الْكَافِرَ ـ أَوِ الْمُنَافِقَ فَلاَ أَدْرِي أَيَّهُمَا قَالَ عُبَيْدُ اللَّهِ ـ يَأْكُلُ فِي سَبْعَةِ أَمْعَاءٍ ‏”‌‏.

ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል ማለት ሲበላ በቢሥሚላህ ስለሚጀምር በረካ አለው፣ ያጣቅመዋል እና ይብቃቃል ማለት እንጅ አንድ ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። በተጨማሪም ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል ማለት በቢሥሚላህ ስለማይጀምር በረካ የለውም፣ አያጣቅመውም እና አይብቃቃም ማለት እንጅ ሰባት ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። ይህ “መዕነዊይ” ማለትም “ፍካሬአዊ” አነጋገር እንጂ “ሒስሲይ” ማለትም “እማሬአዊ” አይደለም።
ነጥብ ስድስት
"ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ"
ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 288,
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *“ቁርአንን የሚቀራ አማኝ ምሳሌው ልክ “እንደ” ትርንጎ ነው፤ ሽታው ጥሩ ነው ጣዕሙም ጥሩ ነው። ቁርአንን የማይቀራ አማኝ ደግሞ ልክ እንደ ተምር ነው፤ ሽታ የለውም ጣዕም ግን አለው። ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ አምሳያው ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል። ቁርአንን የማይቀራ ሙናፊቅ ደግሞ ልክ እንደ እንቧይ ነው ሽታ የለውም፤ ጣዕሙም መራራ ነው”* عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْمُؤْمِنُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالأُتْرُجَّةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَرِيحُهَا طَيِّبٌ، وَالْمُؤْمِنُ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالتَّمْرَةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَلاَ رِيحَ لَهَا، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالرَّيْحَانَةِ، رِيحُهَا طَيِّبٌ وَطَعْمُهَا مُرٌّ، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالْحَنْظَلَةِ، طَعْمُهَا مُرٌّ ـ أَوْ خَبِيثٌ ـ وَرِيحُهَا مُرٌّ ‏”

ኒፋቅ በሁለት ይከፈላል፤ አንደኛው ኒፋቁል አስገር ሲሆን ይህ ባህርይ ያለበት ሙናፊቅ ባይሰኝም ግን ከላይ የተዘረዘሩት የታመኑት ጊዜ መካድ፣ ሲናገሩ መዋሸት፣ ቃል ገብቶ ማፍረስ፣ ቀጠሮን ማዛባት፣ ሲከራከር ማስተባበል ናቸው።
ሁለተኛው ኒፋቁል አክበር ሲሆን ይህ ሰው ሙናፊቅ ይባላል፤ የትልቁ ኒፋቅ ምልክቶች የአላህን መልእክተኛ ማስተባበል፣ የተቀበሉትን መልእክት በከፊሉ ማስተባበል፣ እሳቸውን መጥላት፣ መልእክታቸውን መጥላት፣ በኢስላም ዝቅ ማለት መደሰት፣ የኢስላም የበላይነትን መጥላት ናቸው ወዘተ ናቸው። ሙናፊቅ ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ነው። ምክንያቱም ኒፋቅ ልብ ላይ ያለ በሽታ ነው፦
4፥63 *እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፤ እነርሱንም ተዋቸው፤ ገሥጻቸውም፤ ለእነርሱም በራሳቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው*። ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﻠَﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣَﺎ ﻓِﻲ ﻗُﻠُﻮﺑِﻬِﻢْ ﻓَﺄَﻋْﺮِﺽْ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﻭَﻋِﻈْﻬُﻢْ ﻭَﻗُﻞْ ﻟَﻬُﻢْ ﻓِﻲ ﺃَﻧْﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻗَﻮْﻟًﺎ ﺑَﻠِﻴﻐًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ
3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፤ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፤ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፥ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸዉ በእርግጥ ተገለጸች። ልቦቻቸዉም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነዉ*። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራራያዎችን በእርግጥ ገለጽን። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

አላህ የቀልብ በሽታ ከሆነው ከኒፋቅ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቅጥፈት ይብቃ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥105 *ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ግብጻዊ ቄስ ዘካሪያስ ሁልጊዜ ለሚቀጥፈው ቅጥፈት ምላሽ ሲሰጠው እየተገለባበጠ ኢስላምን የሚያጠለሽበት ጥላሸት ለመፈለግ ቀን ከሌሊት ይዳክራል፤ ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው፦
16፥105 *ውሸትን የሚቀጣጥፉት እነዚያ በአላህ አንቀጾች የማያምኑት ብቻ ናቸው፤ እነዚያም ውሸታሞቹ እነርሱ ብቻ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا يَفْتَرِي الْكَذِبَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْكَاذِبُونَ

ከቀጠፈው ቅጥፈት አንዱ ነብያችንን"ﷺ" ከሬሳ ጋር ተራክቦ እንዳደረጉ አድርጎ መቅጠፉ ነው፤ ወሊ-አዑዝቢሏህ እኔ ለደገሙት ቃል ሰቀጠጠኝ፤ ህሊናውን ለሸጠ ሰው እና ሃሰትን ለተከናነበ ሰው ይህን ማድረግ ውስጡን ሰላም አይሰጠውም፤ እስቲ የሚያነሳቸውን ሐዲሳት እንመልከት፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 23, ሐዲስ 98
አነሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሴት ልጅ የቀብር ሥርአት ላይ ነበርን፤ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" በመቃብር አቅራቢያ ተቀምጠው ዓይኖቻቸው በእንባ ሞልተው አየዋቸው፤ እርሳቸውም፦ "ከመካከላችሁ በዚህ ሌሊት ከሚስቱ ጋር ተራክቦ ያላደረገ አለን? አሉ፤ አቡ ጠልሓህም፦ "እኔ አለሁ" ብሎ መለሰ፤ እርሳቸውም፦ "ወደ መቃብሯ ውረድ" አሉት፤ እርሱም ወደ መቃብሯ ወረዶ ቀበራት*። عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ شَهِدْنَا بِنْتَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَرَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم جَالِسٌ عَلَى الْقَبْرِ، فَرَأَيْتُ عَيْنَيْهِ تَدْمَعَانِ فَقَالَ ‏"‏ هَلْ فِيكُمْ مِنْ أَحَدٍ لَمْ يُقَارِفِ اللَّيْلَةَ ‏"‌‏.‏ فَقَالَ أَبُو طَلْحَةَ أَنَا‏.‏ قَالَ ‏"‏ فَانْزِلْ فِي قَبْرِهَا ‏"‌‏.‏ فَنَزَلَ فِي قَبْرِهَا فَقَبَرَهَا‏.‏

ከመነሻው እዚህ ሐዲስ ላይ እከሌ ከሬሳ ጋር ወሲብ ፈጸመ የሚል ሽታው እንኳን ቢፈለግ የለም፤ ውሸት ሲጋለጥ ከዚህ ይጀመራል።
ሲቀጥል "ኔክሮፊሊያ"Necrophilia" ማለት ከሬሳ ጋር የሚደረግ ተራክቦ ነው፤ በኢስላም አይደለም ከሞተ ሰው ይቅርና በቁም ካለ ሰው ጋር ተራክቦ ለማድረግ ኒካሕ ይወጅባል። እስቲ ሁለተኛውን ሐዲስ እንመልከት፦
ከንዙል ዑማል 242218
ኢብኑ አባስ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አሉ፦ *"የጀነትን ልብስ እስከምትለብስ ልብሴን አለበስኳት፤ በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ፤ ምናልባት የመቃብሩ ጫና ይቀንሳል ብዬ፤ ለእኔ ከአቡ ጠሊብ በኃላ ከአላህ ፍጥረት በላጭ ናት። ነብዩም"ﷺ" ይህንን ያሉት የዐሊይ እናት ስለሆነችው ስለፋጢማ ነበር*።
"ከንዙል ዑማል" كنز العمال ማለት "የሰናይ ገባሪ ጥሪኝ" ማለት ነው፤ ዐሊ ኢብኑ ዐብዱል ማሊክ አል-ሂንዲ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1517 ድህረ-ልደት ያዘጋጀው ሐዲስ ነው፤ ይህ ሐዲስ ከመነሻው ደኢፍ ነው።
ሲቀጥል የዐሊይ እናት ለነብያችን"ﷺ" አክስት ናት፤ ከአክስት ጋር አይደለም ሞቷ ወሲብ ይቅርና በቁምም ከአክስት ጋር ጋብቻ ክልክል ነው፦
4፥23 እናቶቻችሁ፣ ሴት ልጆቻችሁም፣ እኅቶቻችሁም፣ *አክስቶቻችሁም፣ የሹሜዎቻችሁም፣* የወንድም ሴቶች ልጆችም፣ የእኅት ሴቶች ልጆችም፣ እነዚያም ያጠቡዋችሁ እናቶቻችሁ፣ ከመጥባት የኾኑትም እኅቶቻችሁ፣ የሚስቶቻችሁም እናቶች፣ እነዚያም በጉያዎቻችሁ ያሉት የእነዚያ በእነርሱ የገባችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴቶች ልጆች፣ *ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ*፡፡ حُرِّمَتْ عَلَيْكُمْ أُمَّهَاتُكُمْ وَبَنَاتُكُمْ وَأَخَوَاتُكُمْ وَعَمَّاتُكُمْ وَخَالَاتُكُمْ وَبَنَاتُ الْأَخِ وَبَنَاتُ الْأُخْتِ وَأُمَّهَاتُكُمُ اللَّاتِي أَرْضَعْنَكُمْ وَأَخَوَاتُكُم مِّنَ الرَّضَاعَةِ وَأُمَّهَاتُ نِسَائِكُمْ وَرَبَائِبُكُمُ اللَّاتِي فِي حُجُورِكُم مِّن نِّسَائِكُمُ اللَّاتِي دَخَلْتُم بِهِنَّ فَإِن لَّمْ تَكُونُوا دَخَلْتُم بِهِنَّ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ وَحَلَائِلُ أَبْنَائِكُمُ الَّذِينَ مِنْ أَصْلَابِكُمْ وَأَن تَجْمَعُوا بَيْنَ الْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ غَفُورًا رَّحِيمًا

የአባት እህት ሹሜ ስትባል የእናት እህት አክስት ትባላለች፤ ሲሰልስ "በመቃብሯ ውስጥ አብሬ ተጋደምኩኝ" اضْطَجَعَ معها في قبرها ማለት "ወሰብኩኝ" "ተራከብኩኝ" ብሎ የተረጎመላችሁ ማን ነው? "አድጠጀዐ" اضْطَجَعَ ማለት "ተኛ" ማለት እንጂ "ወሰበ" አሊያም "ተራከበ" ማለት አይደለም። ይህ ዐረቢኛው ባይብል ላይ ኤልሳዕ ከሕፃኑ ጋር የተኛውን ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል፦
2 ነገሥት 4፥34 መጥቶም በሕፃኑ ላይ *ተኛ*፤ አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ *ተጋደመበት*፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ። ثُمَّ صَعِدَ وَاضْطَجَعَ فَوْقَ الصَّبِيِّ وَوَضَعَ فَمَهُ عَلَى فَمِهِ وَعَيْنَيْهِ عَلَى عَيْنَيْهِ وَيَدَيْهِ عَلَى يَدَيْهِ

"ተኛ" የሚለው ቃል "አድጠጀዐ" اضْطَجَعَ ነው፤ ታዲያ ኤልያስ ከሕጻኑ ጋር ወሲብ አደረገ ማለት ነውን? አዎ ካላችሁን ነብዩ ኤልሳዕ ግብረ ሰዶማዊ ነው ልትሉ ነው? ምክንያቱም ሕጻኑ ወንድ ሕጻን ነውና፤ አይ "ተወሰበ" "ተራከበ" ለሚለው ቃል "ነከሐ" نَكَحَ እንጂ "አድጠጀዐ" اضْطَجَعَ አይደለም ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈታችሁን እዚህ ጋር ይብቃ። ምነው በተመሳሳይ ሙሴ ከአባቶቹ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ እግዚአብሔር ነግሮታል፤ ኢዮብም ሰው ከአጥንቱ ጋር በመቃብር እንደሚተኛ ተናግሯል፤ ኢሳይያስም ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል ብሏል፦
ዘዳግም 31፥16 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ እነሆ፥ *ከአባቶችህ ጋር ትተኛለህ*፤ وَقَال الرَّبُّ لِمُوسَى: «هَا أَنْتَ تَرْقُدُ مَعَ آبَائِك
ኢዮብ 20፥11 አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፤ ነገር ግን *ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል*። عِظَامُهُ مَلآنَةٌ قُوَّةً وَمَعَهُ فِي التُّرَابِ تَضْطَجِعُ.
ኢሳይያስ 11፥6 ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ *ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል*፤ فَيَسْكُنُ الذِّئْبُ مَعَ الْخَرُوفِ وَيَرْبُضُ النَّمِرُ مَعَ الْجَدْيِ وَالْعِجْلُ

ሰው በመሬት ውስጥ "ይተኛል" ለሚለው ቃል የወደፊት ግስ የተጠቀመበት "ተድጠጂዑ" تَضْطَجِعُ ሲሆን የእርሱ አላፊ ግስ "አድጠጀዐ" اضْطَجَعَ ነው፤ እና ሰው አፈር ውስጥ ወሲብ ያረጋል ማለቱ ነውን? እረ "መተኛት" ሲባል ተራክቦ ወይም ወሲብ ማለት አይደለም ካላችሁ እንግዲያውስ ቅጥፈት ይብቃ! ከላይ ያለውን ደኢፍ ሐዲስ በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። አላህ ሂዳያህ ይስጣችሁ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አብ እና ኢየሱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ዮሐንስ 8፥26 *የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ*፤ አላቸው።

ኢየሱስን የላከው አብ ነው፤ ኢየሱስ ከአብ እየሰማ የሚናገር ማንነት ነው፤ ኢየሱስ ወደ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከእግዚአብሔር መጥቶ መጽሐፍን ተቀብሏል፦
ራእይ 5፥7 *መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው*።
ራእይ 19፥4 *በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር፦ አሜን፥ ሃሌ ሉያ እያሉ ሰገዱለት*።

በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው አብ እና ከአብ መጽሐፉን የወሰደው ኢየሱስ ይለያያሉ፤ ኢየሱስ በአብ ፊትይመሰክራል፦
ማቴዎስ 10፥32 ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ *እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ*፤

መስካሪው ኢየሱስ የሚመሰክረው በአብ ፊት መሆኑ አብ እና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ማንነቶች መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ኢየሱስ ከአብ "ጋር" በሚል መስተዋድድ ተለይቷል፦
ራእይ 3፥21 *እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ*።

ኢየሱስ አባቴ ከሚለው ማንነት "ጋር" በሚል መስተዋድድ ተለይቷል፤ አማኝ "ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጣል" ማለት አማኙ እና ኢየሱስ በማንነት እንደሚለያዩ ሁሉ ኢየሱስ እና አብ በማንነት ይለያያሉ፤ አብም ወልድን በቀኜ ተቀመጥ አለው፦
ሐዋ. ሥራ 2፥34 *ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፥ አለው*፤ he saith himself, The *LORD* said unto my *Lord*, Sit thou on my right hand,(KJV)

ትልቁ ጌታ"LORD አብ ትንሹን ጌታ"Lord" ወልድን በቀኜ ተቀመጥ ብሎ ሲያናግረው ተመልከቱ፥ አብ ኢየሱስን ጌታ አደረገው፦
ሐዋ. ሥራ 2፥36 *ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው* የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።

አብ ማለት ኢየሱስ ውስጥ ያለው የኢየሱስ መንፈስ ቢሆን ኖሮ ኢየሱስ አብን ነው ለአብ በእጁ አደራ የሰጠው? የማይመስል ነገር፦
ሉቃስ 23፥46 *ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ፦ "አባት ሆይ፥ መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ" አለ። ይህንም ብሎ መንፈሱን ሰጠ*። And when Jesus had cried with a loud voice, he said, Father, into thy hands I commend my *spirit*: and having said thus, he gave up *the spirit*. (KJV)

ስለዚህ ኢየሱስ ከአብ ተለይቶ እራሱን የቻለ የራሱን መንፈስ ነበረው፤ መንፈሱ ይታወክ እና ያዝን ነበር፤ አብ ነበር ሲያዝንና ሲታወክ የነበረው? ኢየሱስ፦ ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ ነው፤ እርሱም የላከኝ አብ ነው ብሏል፦
ዮሐንስ 5፥31-32 *እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም፤ ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ ነው፥ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ*።
ዮሐንስ 8፥18 *ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል*።

አብን "እኔ ነኝ" ሳይሆን ያለው "ሌላ ነው" ብሎ ተናግሯል፤ ሌላ ነው እያለ እራስክ ነህ ማለት ቂልነት ነው፤ አብ ኢየሱስን "አንተ" እያለ ሲያናግረው ኢየሱስም አብን "አንተ" እያለ ያናግረው ነበር፤ "እኔ" "አንተ" እርሱ" ማንነትን ያሳያል፦
ማርቆስ 1፥10 የምወድህ ልጄ *አንተ* ነህ፥ *በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ*።
ዮሐንስ 17፥13 *አሁንም ወደ አንተ እመጣለሁ*፤

"ወደ" የሚለው መስተዋድድ በሁለት ማንነቶች መካከል የምንጠቀምበት ነው፤ ይህ ሁሉ ጥቅስ እየተዥጎደጎደ ኢየሱስ እራሱ የላከ አብ ነው ማለት ኢየሱስ በሰዎች ላይ ሚስጥር እየተመሳጠረ እና ድራማ፣ ተውኔት፣ ቁማር እየተጫወተ ነበር ብሎ መሳደብ ነው፤ ሰዎች ነን፤ እኛ በሌጣው እንኳን አንብበን ሊገባን በሚችል ቋንቋ ኢየሱስ እና አብ ሁለት ማንነቶች እንደሆኑ እንረዳለን። አብ ደግሞ አንዱ አምላክ ሲሆን ከአንዱ በቀር አምላክ የለም። ኢየሱስ በአንዱ አምላክ እና በሰዎች መካከል ያለ ሰው ነው፦
1 ቆሮንቶስ 8፥4 *ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ* እንደሌለ እናውቃለን።
1 ጢሞቴዎስ 2፥5 *አንድ አምላክ አለና፥ በአምላክ እና በሰዎች መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ*፥ እርሱም *ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው*፤ For there is *one God*, and *one mediator* between God and men, *the man* Christ Jesus; (KJV)

ከላይ የጠቀስናቸው ጥቅሶች ለሃዋርያት ቤተ ክርስቲያን በተለምዶ ኦንልይ ጂሰስ ለሚባሉት እራስ ምታት ናቸው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ከእኛ እንደ አንዱ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

14፥52 *ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት እና የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው*፡፡ هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ቁርኣን ከወረደበት አንዱ ፈጣሪ አላህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት ነው፦
14፥52 *ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት እና የአእምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው*፡፡ هَـٰذَا بَلَاغٌ لِّلنَّاسِ وَلِيُنذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

ይህ የአንድ አምላክ እሳቤ በመለኮታዊ ቅሪት እንዲህ ተቀምጧል፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው*። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.

ያህዌህ አንድ ያህዌህ ሲሆን እርሱ ሌሎችን ማንነቶችን ጨምሮ፦ "ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" ብሏል፦
ዘፍጥረት 3፥22 *ያህዌህ አምላክም አለ፦ *እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ*፤ וַיֹּאמֶר יְהוָה אֱלֹהִים, הֵן הָאָדָם הָיָה כְּאַחַד מִמֶּנּוּ, לָדַעַת, טוֹב וָרָע; וְעַתָּה פֶּן-

"እንደ አንዱ" እና "እኛ" ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ነጥብ በነጥብ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን እናየዋለን፦

ነጥብ አንድ
"እንደ አንዱ"
"ከ-አሐድ" כְּאַחַ֣ד ማለት "እንደ አንዱ"as one of" ማለት ነው፤ ያ ማለት በከፊል መመሳሰልን ያሳያል፦
1ኛ ሳሙኤል 17፥36 *እኔ ባሪያህ “አንበሳ እና ድብ” መታሁ፤ ይህም ያልተገረዘው ፍልስጥኤማዊ የሕያውን አምላክ ጭፍሮች ተገዳድሮአልና “ከእነርሱ እንደ አንዱ” ይሆናል*። גַּם אֶת-הָאֲרִי גַּם-הַדֹּב, הִכָּה עַבְדֶּךָ; וְהָיָה הַפְּלִשְׁתִּי הֶעָרֵל הַזֶּה, כְּאַחַד מֵהֶם, כִּי חֵרֵף, מַעַרְכֹת אֱלֹהִים חַיִּים.

"ከ-አሐድ ሜሄም" כְּאַחַד מֵהֶם ማለት "ከእነርሱ እንደ አንዱ"as one of them" ማለት ሲሆን ፍልስጥኤማዊ ጎልያድ በዳዊት በመገደል ደረጃ “እንደ አንበሳ እና ድብ” ይሆናል ማለት ነው እንጂ ጎልያድ አውሬ ይሆናል ማለት አይደለም፣ “እንደ” የሚለው ተውሳከ-ግስ የተወሰነን መመሳሰል ለማመልከት የሚገባ ነው፣ ልክ እንደዚሁ አደም መልካምና ክፉ በማወቅ እንደ እንደ እነርሱ ሆኗል፤ ለዛ ነው "ከ-አሐድ ሜንሁ" כְּאַחַ֣ד מִמֶּ֔נּוּ ማለትም "ከእኛ እንደ አንዱ"as one of us" የሚለው፤ ያህዌህ ታዲያ ማንን ጨምሮ ነው "እኛ" የሚለው?

ነጥብ ሁለት
"እኛ"
ያህዌህ "እኛ" የሚለው ማንን ጨምሮ ነው የሚለው ለመረዳት እዚሁ ዐውድ ላይ አዳም ከእኛዎቹ እንደ አንዱ የሚሆነው "መልካምንና ክፉን ለማወቅ" እንደሆነ ይሰመርበት፤ እዛው ዐውድ ላይ አዳም ቢበላ "እንደ አማልክትም መልካምንና ክፉን የሚያውቁ" እንደሆነ ተነግሯል፦
ዘፍጥረት 3፥5 ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ *“እንደ አማልክትም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ"* ያህዌህ ስለሚያውቅ ነው እንጂ። כִּי, יֹדֵעַ אֱלֹהִים, כִּי בְּיוֹם אֲכָלְכֶם מִמֶּנּוּ, וְנִפְקְחוּ עֵינֵיכֶם; וִהְיִיתֶם, כֵּאלֹהִים, יֹדְעֵי, טוֹב וָרָע.

የግዕዙ ዕትም፦
ዘፍጥረት 3፥5 *“ዘይቤ ከመ ኢትኩኑ አማልክተ ወኢታምሩ ሠናየ ወእኩየ”*

የኢንግሊሹ ዕትም፦
For God doth know that in the day ye eat thereof, then your eyes shall be opened, and *ye shall be as gods, knowing good and evil*.(KJV)

ግሪክ ሰፕቱአጀንት”LXX”፦
ዘፍጥረት 3፥5 ᾔδει γὰρ ὁ Θεός, ὅτι ᾗ ἂν ἡμέρᾳ φάγητε ἀπ᾿ αὐτοῦ, διανοιχθήσονται ὑμῶν οἱ ὀφθαλμοὶ καὶ ἔσεσθε ὡς *θεοί*, γινώσκοντες καλὸν καὶ πονηρόν.

የግዕዙ ዕትም ላይ "አማልክት" ብሎ እንዳስቀመጠው አስተውል፤ "ኤሎሂም" כֵּֽאלֹהִ֔ים ማለት "አማልክት" ማለት ነው፤ ይህ ቃል ለነጠላ ማንነት ወይንም ለብዙ ማንነት ይውላል፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ለብዙ መባሉን በግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ “ቴኦ” θεοί ማለትም "አማልክት" ብሎ በብዙ ቁጥር አስቀምጦታል፤ ልብ አድርግ የቴኦ ነጠላ “ቴኦስ” Θεὸς ነው፤ "ቴኦስ" ብሎ በነጠላ አለማስቀመጡ ለብዙ ማንነቶች መሆኑን ያሳያል፤ በኢንግሊሹም ደግሞ በብዙ ቁጥር “gods" መባሉን አስተውል። በብሉይ ደግሞ ብዙ ቦታ አማልክት የተባሉት መላእክት ናቸው፦
መዝሙር 97፥7 *"አማልክትም” כֵּֽאלֹהִ֔ים ሁሉ ስገዱለት*።
መዝሙር 104፥4 *“አማልክትን” כֵּֽאלֹהִ֔ים መንፈስ የሚያደርግ፥*
መዝሙር 8፥5 *“ከአማልክትን” כֵּֽאלֹהִ֔ים እጅግ ጥቂት አሳነስኸው*፤
መዝሙር 103፥20 የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ *“አማልክቱ” כֵּֽאלֹהִ֔ים ሁሉ ያህዌህን ባርኩ*።
መዝሙር 138፥1 *"በአማልክት כֵּֽאלֹהִ֔ים ፊት እዘምርልሃለሁ*።

ስለዚህ አዳም ዛፉን ሲበላ መልካም እና ክፉውን በማወቅ እንደ መላእክት ከሆነ ያህዌህ ደግሞ መልካምና ክፉ ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ የሚለው እነዚህን አማልክት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፦
ሆሴዕ 12፥4 *በጕልማስነቱም ጊዜ “ከአምላክ” ጋር ታገለ፤ “ከመልአኩም” ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም “ከእኛ” ጋር ተነጋገረ*።

ያዕቆብ የተነጋገረው ከመልአኩ ጋር እና ከያህዌህ ጋር ነው፤ ያህዌህ መልአኩን ጨምሮ "ከእኛ" እንዳለ አንባቢ ልብ ይለዋል። አይ ያህዌህ እኛ የሚለው ሥላሴን ያሳየል ከተባለ ዕውዱ ላይ ስለ ሥላሴ የሚያሳይ ሃይለ-ቃል ፈልቅቆ ማሳየት ይጠበቅባችኃል፤ ወይም ይህ አንቀጽ ስለ ሥላሴ ያወራል ብሎ የተናገረ ነብይ ወይም ሐዋርያ ጠቅሳችሁና አጣቅሳችሁ መሞገትና መሟገት ይጠበቅባችኃል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዒድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፤ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፤ ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

ታዲያ በየዓመቱ የሚከበረው ሥስተኛው በዓል መውሊድ ምንድን ነው? አዎ ይህ ድብን ያለ ቢድዓ ነው፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።
ሲጀመር ነብያችን”ﷺ” የተወለዱበት ሳምንት እንጂ የተወለዱበት ቀን በሐዲስ አልሰፈረም።
ሲቀጥል አላህም እና መልእክተኛው መውሊድ አክብሩ አላሉም።
ሢሰልስ ነቢያችን”ﷺ” የተወለዱበትን ቀን ከቀደምት ሰለፎች ማለትም ሶሐባህ ወይም ታቢኢይ አሊያም አትባኡ ታቢኢይ ያከበረ የለም።
ስለዚህ መውሊድ በቁርኣንና በሐዲስ አሕካሙ ካልተቀመጠ እና አይ የፈለግነውን በዲኑ ላይ እንጨምራለን ከሆነ ቢድዓ ነው፤ ሑክም የአላህ እና የመልክተኛ ብቻና ብቻ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏

“ከትእዛዛችን” የሚለው ይሰመርበት። አንድ ነገር ፈርድ ነው፣ ሙስተሐብ ነው፣ ሙባሕ ነው፣ መክሩህ ነው፣ ሐራም ነው ማለት የሚቻለው ከአላህ እና ከመልእክተኛ ትእዛዝ ሲመጣ ብቻና ብቻ ነው፦
3፥32 *አላህን እና መልክተኛውን ታዘዙ*፡፡ ብትሸሹም አላህ ከሓዲዎችን አይወድም» በላቸው፡፡ قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ ۖ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ
4፥80 *መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው አያሳስብህ*፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا

“ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም” የሚለው የነብያችን”ﷺ” ንግግር ይሰመርበት፤ ማንኛውም መመሪያ ቁርአን እና የነብያችን”ﷺ” ሐዲስ ላይ ይገኛል፤ አላህን የሚወድ መልእክተኛውን ይከተላል፤ አላህም፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ብሎናል፦
3፥31 *በላቸው፡- አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ “ተከተሉኝ*፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኀጢኣቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና፤ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው” قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ፡፡
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ ፡፡
ጥሩ ቢድዓ ካለ የሌሎችን ነብያት ልደት ለምን አይከበርም? ለምሳሌ “ገና” የዒሳ ልደት አይከበርም? ነብያችን”ﷺ” ወሕይ የመጣላቸው ቀን፣ ያረፉበት ቀን ወዘተ እየተባለ ልክ እንደ ኦርቶዶክስ ሰላሳውም ቀን ለምን አይከበርም? ይህ ደግሞ ዲኑን ያባሻል። አይ ዝንባሌአችን ደስ ያለውን መልካም ነገር በዒባዳህ ላይ እናካትት ማለት ዲኑ ሙሉ ነው የሚለንን አምላካችን አላህን እየተቃረንን ነው፦
5፥3 *ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ*፡፡ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا

“ነፍስያ” نفسيه ማለትም “የራስ ዝንባሌ” ጌታችን የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ነው፤ ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፦
12፥53 ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥164 በላቸው እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ቢድዓ፣ ኩርፍ፣ ሽርክ እና ኒፋቅ ምንጫቸው ዝንባሌ ነው፤ ብዙ ጊዜ ሰርጎ-ገብ የሆኑት ቡድንተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት መነሻቸው ዝንባሌ ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

አላህ ከነፍሲያ ከሚመጣ ዝንባሌ ጠብቆን፤ እርሱንና መልእክተኛው ባስቀመጡልን ሑክም የምንመራ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርኣን ልኬት

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

"አል-ተቅዪሥ" التقييس ማለት "ልኬት"Standardization" ማለት ነው፤ ቁርኣን በወረደበት ጊዜ ዐረቦች የተለያየ "ለህጃህ" لهجة ማለትም "ዘዬ"dialect" ነበራቸው፤ እነርሱም፦ "ቁሬይሽ" "ሁድኸይል" "ጠቂፍ" "ሃዋዚን" "ኪናነህ" "ተሚን" "የመኒ" የመሳሰሉት ነበሩ፣ እነዚህ ዘዬዎች የአነባነብ ሥርአታቸው ላይ "ተሽኪል" تَشْكِيل ማለትም "አናባቢ ድምጽ"Vowelling mark" ይለያያሉ፤ ይህም ልዩነት በማጥበቅና በማላላት፣ በመጎተትና በመጠቅለል የቃሉን መልእክት የተለያየ ትርጉም እንዲኖረው ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ በአገራችን፦
"ገና" ብለን "ገ" ሆሄን ስናጥብቀው "ልደት" ማለት ሲሆን ስናላላው "መዘግየት" የሚል ትርጉም ይኖረዋል።
"የማይገባው" ብለን "ገ" ሆሄን ስናጥብቀው "ብቃት" ማለት ሲሆን ስናላላው ደግሞ "መረዳት" የሚል ትርጉም ይኖረዋል።
"የማይረዳኝ" ብለን "ዳ" ሆሄን ስናጥብቀው "ሃሳቤን የማይገባው" ማለት ሲሆን ስናላላው "የችግሬ መፍትሄ የማይሆን" የሚል ትርጉም ይኖረዋል።
"ዋና" ብለን "ዋ" ሆሄን ስናጥብቀው "ዐብይ" ማለት ሲሆን ስናላላው "መዋኘት" የሚል ትርጉም ይኖረዋል። እንዲሁ በዐረቢኛ ለምሳሌ፦
"አሊም" أَلِيم የሚለው በመነሻ ላይ በሃራካ "ሀምዛህ" ا ፈትሓህ "አ" أ አድርገን ስንቀራ "ህመም" ማለት ሲሆን "ዐሊም" عَلِيم የሚለውን በመነሻ ላይ በሃረካ "ዐይን" ع ፈትሓህ "ዐ" عَ አድርገን ስንቀራ ደግሞ "ዐዋቂ" ማለት ነው፡፡
"ከፈረ" كَفَرَ የሚለውን በግንድ ላይ በሃረካ "ፋ" ف ፈትሓህ "ፈ" فَ አድርገን ስንቀራ "ካደ" ማለት ሲሆን “ከፈረ” كَفَّرَ የሚለውን በግንድ ላይ በሸዳ "ፋ" ف ተሽዲድ ፈትሓህ "ፍፈ" فَّ አድርገን ስንቀራ "ሸፈነ" ማለት ነው።
"ነዘለ" نَزَلَ የሚለውን በግንድ ላይ በሃረካ "ዛል" ز ፈትሓህ "ዘ" زَ አድርገን ስንቀራ "ወረደ" ማለት ሲሆን "ነዘለ" نَزَّلَ የሚለውን በግንድ ላይ በሸዳ "ዛል" ز ፈትሓህ ተሽዲድ ፈትሓ "ዝዘ" زَّ አድርገን ስንቀራ "አወረደ" ማለት ነው። ብዙ ናሙና ማቅረብ ይቻል ነበር፤ ግን ይህ በቂ ነው፤ ይህ ሙግት የሥነ-አናባቢ ጥናት"orthography" ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው።

ሌላው "አብጀድ" أَبْجَد ማለትም "ተነባቢ ፊደላት"consonant" ላይም ልዩነት አላቸው፤ ድምጽ ያላቸው ሐርፎች 28 ሲሆን "አሊፍ" ا ደግሞ "አጫዋች ፊደል"stretch letter" ነው፤ በጥቅሉ 29 ሐርፎች ሲሆኑ በመካከላቸው ስናነባቸው የሚቀጥኑ ሐርፎች 19 ሲሆኑ "ተርቂይቅ" تَرْقِيْقٌ ይባላሉ፣ የሚወፍሩ ሐርፎች ደግሞ 7 ሲሆኑ "ተፍኺይም" تَفْخِيْمُ ይባላሉ፣ የሚወፍርና የሚቀጥኑ ሐርፎች ደግሞ ሁለት ሲሆኑ አንደኛው "ሯ" ر በፈትሓህ እና በደማ ሲቀራ ይወፍራል፤ በከስራ ሲቀራ ይቀጥናል። ሁለተኛ "ላም" ل በለፍዙል ጀላላ ማለትም በአላህ ስም ላይ ሲቀራ ይወፍራል፤ በሌሎች ላይ ሲቀራ ይቀጥናል።
በእነዚህ ተነባቢ ፊደላት ላይ "ኑቅጧህ" نُقْطَة‎ ማለትም "ነጥብ" ያላቸው 16 ሐርፎች "ሙአጀማ" ሲባሉ ነጥብ የሌላቸው 14 ሐርፎች ደግሞ "ሙሃመላ" ይባላል፣ አንዷ ሐርፍ "ያ" ي ደግሞ ሁለቱንም ናት።
ሐርፎች በመነሻ ቅጥያ"Prefix" ላይ፣ በግንድ"stem" ላይ እና በመዳረሻ ቅጥያ"Suffix" ላይ ቅርጻቸው ሲቀያየር "ረሥም" رَسْم ይባላል።
ይህ ሙግት የሥነ-ተናባቢ ጥናት"Typography" ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው።