ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አስተምህሮተ ሥላሴ ሲጋለጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ዘፍጥረት 11.6-7 እግዚአብሔርም አለ፦ እነሆ፥ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፥ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም። ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።

ነጥብ አንድ
*ኑ*
ይህ ጥቅስ ግነትን የሚያሳይ ሳይሆን አንዱ እግዚአብሔር ከሌላ አካላት ጋር የሚያደርገው ንግግር ነው፣ ምክንያቱም *ኑ* የሚለው ትዕዛዛዊ ግስ በስነ-ሰዋስው ሙግት በተለያየ አካላት መካከል ለሚደረግ ንግግር የሚያገለግል ቃላት ነው፦
ዘፍጥረት 11.3 እርስ በርሳቸውም፦ *ኑ* ጡብ እንሥራ፥ በእሳትም እንተኵሰው ተባባሉ።
ዘፍጥረት 37፥20 አሁንም *ኑ* እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፦
ዘኍልቍ 14፥4 እርስ በርሳቸውም፦ *ኑ* አለቃ ሾመን ወደ ግብፅ እንመለስ ተባባሉ።
ሳሙኤል ቀዳማዊ 11፥14 ሳሙኤልም ሕዝቡን፦ *ኑ* ወደ ጌልገላ እንሂድ፥ በዚያም መንግሥቱን እናድስ አላቸው።

ነጥብ ሁለት
እንውረድ
ታዲያ አንድ እግዚአብሔር ካለ፣ ያ አንድ እግዚአብሔር ለማን ነው እንውረድ ያለው? ስንል፣ በ 1952 AD በአራተኛው ቁምራን ዋሻ የሙት ባህር ጥቅል ተገኘ፣ ይህ መጽሐፍ የስነ-ቅርጽ ጥናት በካርበን ዳቲንግ እንደሚያሳየን ከሆነ ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው፣ ስሙም ጁብልይ ይባላል፣ የሚገርመው ግን በሃገራችን ይህን ጥንታዊ መጽሐፍ ኩፋሌ ይባላል፣ ይህ መጽሐፍ አንዱ እግዚአብሔር ለማን እንውረድ እንዳለ ይነግረናል፦
ግዕዙ፦
ኩፋሌ 10፣13 ወይቤለነ እግዚአብሔር አምላክነ ለነ፤ ናሁ ሕዝብ አሐዱ፤ መወጠነ ይግበር፤ ወይእዜኒ ኢናኀርቅ እምኔሆሙ ንዑ ንረድ ወንከዐው ልሳናቲሆሙ።
አማርኛ፦
ኩፋሌ 10፣13 *ፈጣሪአችን* እግዚአብሔር እኛን እንዲህ አለን፦ አንድ ቋንቋ የሆነ ወገን ግንብ ይሰሩ ጀመር *ኑ* ወርደን በቋንቋ እንለያቸው፣

የአይሁድ ኮመንታርይ ባጠቃላይ እግዚአብሔር ኑ እንውረድ ያለው ከመላእክት ጋር ነው ቢለንም፣ የበለጠ ይህ መጽሐፍ እግዚአብሔር ለመላእክት እንውረድ ማለቱን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፣ *ፈጣሪአችን* የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፣ አስተምህሮተ ሥላሴን ያጋለጠ እንደዚህ መጽሃፍ አላየሁም።

ዋቢ መጽሐፍት
1. Archaeology and the Dead Sea Scrolls Oxford: Oxford University Press, 1973
2. Solving the Mysteries of the Dead Sea Scrolls: New Light on the Bible, Grand Rapids, 1994
3.The Archaeology of Qumran and the Dead Sea Scrolls, Grand Rapids: Eerdmans, 2002.

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማጣመም አይቻልም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ፣ በጣም አዛኝ በሆነው።

15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ፡፡

መግቢያ
ከላይ የተጠቀሰው ጥቅስ ላይ “ቁርአንን” የሚለውን ቃል በአረቢኛ ላይ “ዚክር” ذِكْر ሲሆን በእንግሊዝኛ ትርጉሞች ላይ “Reminder” ማለትም “መገሰጫ” ተብሎ ተቀምጣል፣ ይህም የቁርአን ሌላኛው ስሙ ስለሆነ አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ሆነ የአማርኛ ተርጓሚዎች “ቁርአን” ብለው አስቀምጠውታል፣ “ዚክር” የቁርአን ሌላ ስሙ መሆኑን መረጃ አለ፦
16:44በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት ላክናቸው፤ ወደ አንተም፣ ለሰዎች ወደነሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ “ቁርአንን” الذِّكْرَ አወረድን።
38:8 «ከመካከላችን በእርሱ ላይ “ቁርኣን” الذِّكْرُ ተወረደን?» አሉ፡፡ በእውነት እነርሱ “ከግሳጼዬ” مِنْ ذِكْرِي በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ በእርግጥም ቅጣቴን ገና አልቀመሱም፡፡

ታዲያ ምንድን ነው? የተጣመመው ትሉ ይሆናል፣ ሚችነሪዎች “ዚክር” የተባለው “መጽሐፍ ቅዱስ” ነው ብለው እርፍ አሉት፣ እንዴት? ሲባል “”አላህ “የዚክር ባለቤቶች” የሚለው እኛን ሲሆን “ዚክር” የተባለው ደግሞ “መጽሐፍ ቅዱስ” ነው ስለዚህ ዚክሩን አወረድኩና ጠባቂው ነኝ ያለው የእኛን መጽሐፍ ቅዱስ ነው”” ብለው ይህንን ጥቅስ ለማጣመም ይጠቀማሉ፦
21:7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ የምናወርድላቸው የኾኑ ሰዎች እንጂ ሌላን አልላክንም፤ የማታውቁም ብትኾኑ “የመጽሐፉን ባለቤቶች” أَهْلَ الذِّكْرِ ጠይቁ።

“የመጽሐፉን ባለቤቶች” የሚለውን ቃል በአረቢኛ ላይ “አህለል ዚክር” أَهْلَ الذِّكْرِ ሲሆን በእንግሊዝኛ ትርጉሞች ላይ “the people of the Reminder” ማለትም “የመገሰጫን ባለቤቶች” ተብሎ ተቀምጣል፣ ይህም “የመጽሐፉን ባለቤቶች” ሌላኛው ስም ስለሆነ አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ሆነ የአማርኛ ተርጓሚዎች “የመጽሐፉን ባለቤቶች” ብለው አስቀምጠውታል፣ ሲጀመር እዚህ ጥቅስ ላይ “ባይብል” አሊያም “መጽሐፍ ቅዱስ” የሚል ቃል የለም፣ ሲቀጥል ዚክር የተባለው ከአውዱ የምንረዳው አላህ ከነቢያችን በፊት ለነበሩት ነቢያት ያወረደውን መጽሐፍ እንጂ በእጆቻቸው ጽፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉት ጭማሬ አይደለም፣ ሲሰልስ እዚህ ጥቅስ ላይ ዚክር የተባለውና አላህ አወረድኩትና እጠብቀዋለው ብሎ ቃል የገባለት ዚክር አንድ አይደለም፣ ይህ ከአውድ ሙግት፣ ከጽሑፍ ሙግት፣ ከቋንቋ ሙግት እና ከሰዋስው ሙግት ማየት ይቻላል፦
15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ፡፡
1. የአውድ ሙግት”contextual approach”
አውዱ ላይ አላህ “አንተ ያ በእርሱ ላይ “ዚክር الذِّكْرُ የተወረደለት ሆይ” ይላል፣ አላህ “አንተ” ብሎ በሁለተኛ መደብ እያናገረ ያለው ሙሳን አሊያም ኢሳን ሳይሆን ነብያችንን ነው፣ ይህም ዚክር የተባለው ቁርአን መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
15:6 «አንተ ያ በእርሱ ላይ “ቁርኣን” الذِّكْرُ የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ» አሉም፡፡

2. ጽሑፋዊ ሙግት”textual approach”
አላህ ቁርአንን የሚጠብቅበት ምክንያት ከነቢያችን በኋላ የሚመጣ ነብይ፣ የሚላክ መልእክተኛ የሚወርድ መጽሐፍ ስለሌለ የጥበቃን ሃላፍትና እራሱ ወስዷል፣ ነገር ግን የቀድሞዎቹን መጽሃፍት ግን በቀጣይ የሚመጣው ነብይና የሚወርደው ኪታብ ስለሚያርሙት እንዲጠብቁ ሃላፍትናውን የሰጠው ለሰዎች ነው፦
5:44 እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትሆን አወረድን፤ እነዚያ ትእዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በነዚያ ይሁዳውያን በሆኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፤ ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም “ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ” اسْتُحْفِظُوا በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በሆኑት ይፈርዳሉ፤

“ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉት” የሚለው ይሰመርበት፣ “ኡስቱህፊዙ” اسْتُحْفِظُوا “እንዲጠብቁ” ተብሎ ለሰዎች የተቀመጠበት ግስ እና “ሃፊዝ” حَفِيظ “ጠባቂ” ተብሎ ለአላህ የገባበት ቃል ስርወ-ግንዱ “ሐፊዘ” حَفِظَ “ጠበቀ” ሲሆን የቀድሞ የአላህ መጽሃፍን የሚጠብቁት ሰዎች መሆናቸውና ቁርአንን የሚጠብቀው አላህ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፣ ሰዎች ሃላፍትና የተሰጣቸው መጽሃፍትማ እያወቁ የሚለውጡት ሲኾኑ እንደማያውቁ ኾነው በእጆቻቸው እየጻፉ «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» በማለት ዋናውን ኦርጂናል ከጀርባዎቻቸው ኋላ ጥለውታል፦
2:7 ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች :የአላህን ቃል” የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ “እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት” ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?
2:79 ለነዚያም “መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉ” እና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ “እጆቻቸው ከጻፉት” ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ወዮላቸው፡፡
2:101 እነርሱ ጋርም ላለው መጽሐፍ አረጋጋጭ የኾነ መልክተኛ ከአላህ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ ከነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ከፊሉ እነርሱ “እንደማያውቁ ኾነው የአላህን መጽሐፍ ከጀርባዎቻቸው ኋላ ጣሉ ።

3. የቋንቋ ሙግት”lingustical approach”
3:3 ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን መጽሐፉን ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእዉነት አወረደ” نَزَّلَ ። ተዉራትንና ኢንጅልንም “አውርዷል” وَأَنْزَلَ።

አላህ ወደ ነብያችን የወረደውን መጽሐፍ ለማመልከት “ነዝዘለ” نَزَّلَ “አወረደ” ብሎ ሲጠቀም ነገር ግን ተውራትና ኢንጅልን ለማመልከት ግን “አንዘለ” أَنْزَلَ “አወረደ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል፣ ምንድን ነው ልዩነቱ? ካልን “ነዝዘለ” ቀስ በቀስ መውረድን የሚያመለክት ሲሆን ለቁርአን ብቻ የሚያገለግለው ቃል ነው፣ ምክንያቱም ቁርአን ቀስ በቀስ ስለወረደ፣ ነገር ግን የቀድሞ መጽሃፍት ወደ ነቢያት የሚወርዱት በአንድ ጊዜ ስለሆነ “አንዘለ” የሚለውን ቃል ይጠቀማል፣ አላህ የቀድሞ መጽሃፍትን ያወረደበትን ቃል የሚጠቀመው “አንዘልና” أَنْزَلْنَا “አወረድን” ነው፦
57:25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ “አወረድን” وَأَنْزَلْنَا ።
25:32 እነዚያ የካዱትም፦ “ቁርአን በርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም?”” لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً አሉ፤ እንደዚሁ በርሱ ልብህን ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፤ ቀስ በቀስ መለያየትም ለየነው።

አላህ እጠብቀዋለው ባለበት አንቀጽ ላይ ያወረደበትን ቃል የሚጠቀመው “አንዘልና” أَنْزَلْنَا ሳይሆን “ነዝዘልና” نَزَّلْنَا “አወረድን” ነው፣ ይህ አላህ እጠብቀዋለው ያለው ቁርአንን ብቻ መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፦
15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው “አወረድነው” نَزَّلْنَا፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን ፡፡
17:106 ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፤ ቀስ በቀስ “ማውረድንም አወረድነው” وَنَزَّلْنَاهُ تَنْزِيلًا ።

4. የሰዋስው ሙግት”grammatical approach”
አላህ እኛ “ለእርሱ” ማለትም ለቁርአን ጠባቂዎቹ ነን ብሎ የተጠቀመበት መስተዋድድ ያለበት ተሳቢ ተውላጠ-ስም “ለሁ” لَهُ “ለእርሱ” በነጠላ እንጂ “ለሁም” لَهُم “ለእነርሱ” በብዜት አይደለም፣ “ሁ” هُ “እርሱ” ነጠላ ሲሆን “ሁም” هُمْ “እነርሱ” ብዜት ነው፣ የቀድሞ መጽሐፍት ደግሞ ብዙ ስለነበሩ “ሁም” ተብሎ የሚቀመጥ የሰዋስው ሙግት ነው፦
2:136 በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት “ከእነርሱ” مِنْهُمْ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ ለአላህ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡

ብዙ ሙግት ማቅረብ ይቻል ነበር፤ ሚሽነሪዎች ዳተኛና ልግመኛ በመሆን የተያያዙት እንጥል መቧጠጥ ነው፤ አሌ ቡም ጨዋታ ባይብል ላይ እንጂ ቁርአን ላይ አይሰራም፤ ቅጥፈት ለልበ-እውራን ሆነ ለእይምሮ ስንኩላህ የተቆላ ገብስ ነው ሲበሉት ይጣፍጣል ግን ሲዘሩ አይበቅልም፤ ከዚህ ሁሉ ያስደመመኝ የዓለማቱ ጌታ አላህ ህያው መሆኑን ተቀብለው ባይብላቸውን እንደሚጠብቅ መናገሩን ማመናቸው ነው፤ ይህ አንድ እርምጃ ሲሆን ሁለተኛው እርምጃ ቁርአንን ሰለፈል ሳሊሂን በተረዱበት መረዳት ተቀብሎ ሸሃደተይን መያዝ ይቀራቸዋል፤ አላህ ልበ-ብሩሃን ያድርገን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አባት እና ልጅ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

“ዋሊዳእ” وَٰلِدَي ማለት “ወላጅ” ማለት ነው፤ አባት የሆነ ወላጅ “ዋሊድ” وَالِد ወይም “መውሉድ” مَوْلُود ሲባል እናት የሆነች ወላጅ ደግሞ “ዋሊዳ” وَٰلِدَٰت ወይም “ዋሊደ” وَٰلِدَة ትባላለች፤ ከወላጅ የሚገኝ ልጅ ደግሞ “ወለድ” وَلَد ወይም “ወሊድ” وَلِيد ይባላል፤ ሁሉም የስም መደብ የመጡት “ወለደ” وَلَدَ ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጡ ናቸው። አላህ ፃታ የለውም፤ ወንድም ሴትም አይደለም፤ አባት ሆኖ አልወለደም ልጅ ሆኖ አልተወለደም፦
112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

የሥላሴ አማንያን ኢየሱስ ልጅ ሲሆን አባቱ እግዚአብሔር ነው ይላሉ፤ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አብን መስሎና አህሎ ከአብ ማንነትና ምንነት የተገኘ ነው የሚል እሳቤ አላቸው፤ “ተወለደ” ሲባል “ተገኘ” ማለት ነው ይሉናል፤ አብ ማለት “አስገኚ” ሲሆን ወልድ ደግሞ “ግኝት” ማለት ነው፤ በ 325 AD የተሰበሰበው የኒቅያ ጉባኤም፦
በግሪክ፦
Φῶς ἐκ Φωτός, Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ,
በግዕዝ፦
“ብርሃን ዘምብርሃን፤ አምላክ ዘምአምላክ”
በአማርኛ፦
*“ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከአምላክ የተገኘ አምላክ”* ብሎታል።

አምላክ አምላክን ካስገኘ ሁለት አምላክ አይሆንም ወይ? አምላክ ተገኘ የሚለው ሲያስገርም አምላክ ተፈጠረ ደግሞ ያስደምማል፦
አማርኛ፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)
ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)
ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ሔዋን “አገኘሁ” ብላ ለተጠቀመችበት የዋለው ቃል “ቃኒቲ” קָנִ֥יתִי ሲሆን ዳዊት ደግሞ ኲላሊቴን “ፈጥረሃል” ለሚለው የተጠቀመው “ቃኒታ” קָנִ֣יתָ ብሎ ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር *አገኘሁ* קָנִ֥יתִי አለች።
መዝሙር 139፥13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን *ፈጥረሃልና* קָנִ֣יתָ ፥
ዘዳግም 32፥6፤ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? *የፈጠረህ* קָּנֶ֔ךָ እና ያጸናህ እርሱ ነው።

የመጨረሻው ጥቅስ ላይ “የፈጠረህ” ለሚለው የገባው “ቃነካ” קָּנֶ֔ךָ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እግዚአብሔር “የገዛህ አባትህ” መባሉ “አባት” ማለት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ማለት እንደሆነ ይህ ጥቅስ ያስረዳል።
እንግዲህ መገኘትና መፈጠር ተለዋዋጭ ቃል ከሆነ ኢየሱስ ፍጡርና ግኝት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህንን ጥቅስ ተሃድሶና እና ፕሮቴስታት ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሽምጥጥ አርገው ቢክዱም፤ ቀደምት ኦርቶዶክስ፣ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የኒቂያ ጉባኤ ስለ ኢየሱስ ፍጥረት ሳይፈጠር መወለዱን ያሳያል ይላሉ፤ አርዮስንና አትናቲዎስ ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ክርክራቸው ይህ ጥቅስ ነበር፤ አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያንም ይህ ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሊያቅማሙ ሲሞክሩ አንድምታው ሆነ ሃይማኖተ-አበው አጋልጧቸዋል፤ ቄርሎስ በሃይማኖተ-አበው ላይ ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:12
ቄርሎስም አለ፦
“ተፈጥረ ጥበብ ዘውእቱ ቃል”
ትርጉም፦
*“ጥበብ ተፈጠረ ይኸውም ቃል ነው”*
ቄርሎስም አለ፦
“ወይእዜኒ ጥበብ ትቤ ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ትርጉም፦
*“ከፍጥረት አስቀድሞ የነበርኩኝ በቀድሞ ተግባሩ ጌታ ፈጠረኝ አለች”*

የመቃብያን ጸሐፊም ሰሎሞን በምሳሌ መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ፦ “ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ” ማለቱን ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 4፥18 ሰሎሞን ፦ *“ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ”* ብሎ ተናገረ፤

እንግዲህ አባት ማለት “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” መሆኑን እንዲሁ ልጅ ማለት “ተገኚ” ወይም “ፍጡር” መሆኑን ካየን ዘንዳ ኢንሻላህ በገቢር ሁለት አብ ማን ነው? ወልድ ማን ነው? የሚለውን እናብራራለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አባት እና ልጅ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

“ኣብ” אַבָּא ማለት በዕብራይስጥ “አስገኚ”orginator” ማለት ሲሆን የሚገርመው አበይት ክርስቲያኖች ማለትም ኦርቶዶስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት እና አንግሊካን፦ "ኢየሱስ አብ ሳይሆን ወልድ ብቻ ነው" ይላሉ፤ ትክክል! ምክንያቱም ኢየሱስ የእራሱን ማንነት ከአብ ነጥሎ አስቀምጧል፦
ዮሐንስ 5፥31-32 *እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም*፤ ስለ እኔ የሚመሰክር *ሌላ ነው፥ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ።
ዮሐንስ 8፥18 *ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል*።
ዮሐንስ 12፥49 *እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*።

ወልድ ማን ነው? ስንል ኢየሱስ ይሉናል፤ አብ ማን ነው? አብ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፦
ቆላስይስ 1፥3 *የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን* ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤
ሮሜ 15፥5 *እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት*፥ ታከብሩ ዘንድ፥
1ቆሮንቶስ 15፥24 በኋላም፥ መንግሥቱን *ለእግዚአብሔር ለአባቱ* አሳልፎ በሰጠ ጊዜ፤
ዮሐንስ 5፥18 *እግዚአብሔር አባቴ ነው* ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።

የኢየሱስ አባት እግዚአብሔር ከሆነ ኢየሱስ እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው፤ ምክንያቱም አብ እግዚአብሔር ነውና፤ እግዚአብሔር ደግሞ አንድ ነው፤ እስራኤላውያን አምላካችን የሚሉት አንዱን እግዚአብሔር ነው፣ ኢየሱስም፦ "እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው" ብሏል፦
ዘዳ.6:4፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው*፤
ዮሐ.8:54 *እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው*፤

ይህ አንድ አምላክ የሁሉም አንድ አባት ነው፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ማቴዎስ 23፥9 *አባታችሁ አንዱ* እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ *ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ*።
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።
ዮሐንስ 20፥17 *እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ* ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ "የእግዚአብሔር አባት"የሚል ቃል ታገኙ ነበር፤ ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር ስላልሆነ 42 ቦታ ላይ "የእግዚአብሔር ልጅ" ብቻ ተብሏል፦
ሉቃስ 1፥35 ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ *የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ "እግዚአብሔር ወልድ"የሚል ቃል ታገኙ ነበር፤ ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር ስላልሆነ እግዚአብሔር የሚባለው አብ ብቻ ስለሆነ "እግዚአብሔር አብ" የሚል ቃላት 13 ቦታ እናገኛለን፦
ያዕቆብ 1፥27 ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ *በእግዚአብሔር አብ* ዘንድ ይህ ነው፤

ባይብሉ እግዚአብሔር እና ኢየሱስን አባት እና ልጅ አርጎ ነው የሚያስቀምጠው፤ አባት ልጅ አይደለም ልጅም አባት አይደለም ካላችሁ እግዚአብሔር ኢየሱስ አይደለም፤ ኢየሱስም እግዚአብሔር አይደለም። እግዚአብሔር ለኢየሱስ ግህደተ-መለኮት"revelation" ማለትም "ወሕይ" ሰቶቷል፦
ራእይ 1፥1 *እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ግልጠት በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው*፥ The Revelation of Jesus Christ, which God gave unto him,
ዮሐንስ 7፥16-17 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ *ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም*፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ *ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ* የምናገር ብሆን ያውቃል።

"ከእግዚአብሔር ወይም እኔ ከራሴ" የሚለው ይሰመርበት፤ የሚገርመው እራሱን ከእግዚአብሔር በመለየት "እራሴ" በሚል ድርብ ተውላጠ-ስም"reflexive pronoun " ተጠቅሟል፤ ትምህርቱ ከላከው ከእግዚአብሔር እንጂ ከራሱ አይደለም። እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠው ግልጠት በግሪክ "አፓልካሊፕስ" Ἀποκάλυψις ይባላል፤ ኢየሱስ በአንድ እግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል እየሰማ የሚናገር ሰው ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 2፥5፤ *አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው*፤
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን *ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?
ሐዋ ሥራ 2፥22 *የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ*፤

እግዚአብሔር አንድ ከሆነ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲናገር ከአንድ እግዚአብሔር የተላከ መልእክተኛና አገልጋይ ነው፦
ዮሐንስ 3፥34 *እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና*፤
ሐዋ ሥራ 3፥26፤ ለእናንተ አስቀድሞ *እግዚአብሔር አገልጋዩን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ላከው*። NIV

እግዚአብሔር አንድ ከሆነ ኢየሱስ ሌሊቱንም ሁሉ ሲጸልይ ያደረው ወደዚህ ወደ አንድ እግዚአብሔር ነው፤ ይህ አንድ እግዚአብሔር ኢየሱስን ቀብቶታል፤ ለዲያብሎስም የተገዙትን እንዲፈውስ እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ነበረ፦
ሉቃስ 6፥12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ *ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ*።
ሐዋ ሥራ 10፥38 *እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው*፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ *እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና*፤

ክርስቶስ የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር የክርስቶስ ራስ ማለትም የበላይ ነው፦
1 ቆሮንቶስ 3፥23 *ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው*።
1 ቆሮንቶስ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ*።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ለምትሉ አልቆላችኃል። ምክንያቱም እግዚአብሔር የኢየሱስ አባት ነው ተብላችኃል፤ ኢየሱስ ደግሞ አብ አይደለም ብላችኃል።
ስለዚህ ኢየሱስ አብ ማለትም እግዚአብሔር ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እግዚአብሔርም ወልድ ማለትም ኢየሱስ ሳይሆን አብ"አባት" ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ግብረ-ሰዶም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥74 *ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ

ሥነ-ጋብቻ ጥናት""matrimony" ስለ ጋብቻ ሲናገር በዋነኝነት ለሁለት ይከፍሉታል፦ አንደኛ "ተቃራኒ ጾታ ጋብቻ"Hetero-sexual" ሲሆን ሁለተኛው "ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ”homo-sexual” ” ነው።
ተቃራኒ ጾታ ጋብቻ በመለኮት መጽሐፍት ውስጥ የተቀመጠ ሲሆን ተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ግን በመለኮት መጽሐፍት ውስጥ አንዳች ድጋፍ የሌለው ነው።
ግብረ-ሰዶም"homosexual" ማለት የሰዶማውያን ሥራ ማለት ነው፤ ግብረ-ሰዶም በራሱ ለሁለት ይከፈላል፤ እርሱም፦ በወንድ እና በወንድ መካከል ያለው የግብረ ሰዶማዊ ግንኙነት"Gays" አንዱ ሲሆን ሌላው ደግሞ በሴት እና በሴት መካከል ያለው የግብረ ሰዶማዊ ግንኙነት"Lesbians" ነው። አምላካችን አላህ ነብዩ ሉጥን በዚህ ድርጊት በተሰማሩ ሕዝቦች መካከል ፍርድንና ዕውቀትን ሰጥቶ ላከው፤ ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ አንዱ ነው፦
37፥133 *ሉጥም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነው*። وَإِنَّ لُوطًا لَّمِنَ الْمُرْسَلِينَ
21፥74 *ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ ከዚያችም መጥፎ ሥራዎችን ትሠራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው፡፡ እነሱ ክፉ ሰዎች አመጸኞች ነበሩና*፡፡ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا وَنَجَّيْنَاهُ مِنَ الْقَرْيَةِ الَّتِي كَانَت تَّعْمَلُ الْخَبَائِثَ ۗ إِنَّهُمْ كَانُوا قَوْمَ سَوْءٍ فَاسِقِينَ

የሰዶም ከተማ ክፉ ሰዎችና አመጸኞች ይሰሩት የነበረው መጥፎ ሥራ ይህ ነው፤ ሉጥንም ለሕዝቦቹ፦ "እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ፀያፍን ነገር ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም" አላቸው፦
27፥54 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *"እናንተ የምታዩ ስትኾኑ ፀያፍን ነገር ትሠራላችሁን?"* وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ
29፥28 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *"እናንተ ጠያፍን ስራ ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም"*፡፡ وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ
7፥80 ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *"አስቀያሚን ሥራ ትሠራላችሁን? በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም"*፡፡ وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ

ወንዶቹ ሴቶች እያሉ ከወንድ ጋር መዳራታቸው ወሰን ማለፍ ነው፦
7፥81 *"እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል በእርግጥ ትመጡባቸዋላችሁን? በእውነቱ እናንተ ወሰንን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ"*፡፡ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ النِّسَاءِ ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ مُّسْرِفُونَ
26፥166 *"ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን? በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦ ናችሁ"*፡፡ وَتَذَرُونَ مَا خَلَقَ لَكُمْ رَبُّكُم مِّنْ أَزْوَاجِكُم ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ عَادُونَ
ይህንን ድርጊት በጀመሩት በሰዶማውያን ላይ አላህ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን በመላክ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነበባቸው፦
54፥34 *እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስን ላክን፡፡ የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱን በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው*፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَا عَلَيْهِمْ حَاصِبًا إِلَّا آلَ لُوطٍ ۖ نَّجَّيْنَاهُم بِسَحَرٍ
15፥74 *ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
7፥84 *በእነርሱም ላይ ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት*፡፡ وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُجْرِمِينَ
26፥173 *በእነርሱም ላይ የድንጋይን ዝናምን አዘነምንባቸው፤ የተስፈራሪዎቹም ዝናም ምንኛ ከፋ*፡፡ وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَسَاءَ مَطَرُ الْمُنذَرِينَ

ይህ ድርጊት አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ ስለነበር ከተማዎቹ ላይዋንም ከታችዋ ተገለበጡ፦
15፥74 *ላይዋንም ከታችዋ አደረግን፡፡ በእነሱም ላይ የሸክላ ደንጊያዎችን አዘነብንባቸው*፡፡ فَجَعَلْنَا عَالِيَهَا سَافِلَهَا وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِمْ حِجَارَةً مِّن سِجِّيلٍ
9፥70 የእነዚያ ከእናንተ በፊት የነበሩት የኑሕ ሕዝቦች፣ የዓድና የሰሙድም፣ የኢብራሂምም ሕዝቦች የመድየን ባለቤቶች እና *የተገልባጮቹም ከተሞች ወሬ አልመጣላቸውምን?* أَلَمْ يَأْتِهِمْ نَبَأُ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ قَوْمِ نُوحٍ وَعَادٍ وَثَمُودَ وَقَوْمِ إِبْرَاهِيمَ وَأَصْحَابِ مَدْيَنَ وَالْمُؤْتَفِكَاتِ
53፥53 *የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ*፡፡ وَالْمُؤْتَفِكَةَ أَهْوَىٰ

ከላይ ያየነው የሰዶማውያን ሥራ ወሰን ማለፍ እንደሆነ ሉጥ እንዳስጠነቀቃቸው ሀሉ አላህም በቁርኣን የነገረን ከተቃራኒ ጾታ ውጪ የያደርጉ እነርሱ ወሰን አላፊዎች አላፊዎች ናቸው፤ ወሰንንም አትለፉ ተብለናል፦
23፥6 *በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው ላይ ሲቀር፤ እነርሱ በእዚህ የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው*፡፡ إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ
11፥112 *እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና*፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

ይህ ድርጊት በማድረግ ወሰን ያለፈ የሚጠብቀው ቅጣት በአኺራ እሳት ነው፦
4፥30 *ወሰን በማለፍና በመበደልም ይህንን የሠራ ሰው እሳትን እናገባዋለን*፡፡ ይኸም በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَانًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا

በዱኒያህ ደግሞ ያለው ቅጣት በኢስላም የሙስሊም ሸሪዓ ባለበት ህገ-መንግሥት ግድያ ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 20, ሐዲስ 2658
ከኢብኑ ዐባሥ እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አሉ፦ *"ማንም የሉጥ ሕዝብ የሚያደርጉት ድርጊት ሲያደርጉ ብታገኙ ሁለቱንም ግደሏቸው"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ وَجَدْتُمُوهُ يَعْمَلُ عَمَلَ قَوْمِ لُوطٍ فَاقْتُلُوا الْفَاعِلَ وَالْمَفْعُولَ بِهِ ‏"‏ ‏

ሚሽነሪዎች፦ “በኢስላም ግብረ-ሰዶም ሃራም የሆነበት ጥቅስና ቅጣት የለም” ብለው ሲቀጥፉ ተመልሰው ደግሞ፦ “እንዴት ይገደላል? መብቱ ነው” ይላሉ፤ ይህንን የሚሉት የምዕራባውያንን እሳቦትና ዕርዮት ይዘው ነው። መብቱ ከሆነ ለምን ፈጣሪ ሰዶማውያንን በዚህ ድርጊታቸው አጠፋቸው? ለምንስ ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙ ይገደሉ አለ?፦
ዘፍጥረት 19፥24 *እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤ እነዚያንም ከተሞች፥ በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ፥ በከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ፥ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ*።
ዘሌዋውያን 20፥13 *ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው*።

ይህ ብሉይ ኪዳን ላይ ነው እንዳትሉ በአዲስ ኪዳን የተፈቀደበትን ጥቅስ ማምጣት ይጠበቅባችኃል። በአዲስ ኪዳን መፍቀድም መከልከልም የሚችል ነብይ ኢየሱስ ነው፤ ኢየሱስ ሕግን ለመሻር አልመጣሁም ብሏል፤ እንደውም ሰማይና ምድር እስከሚያልፍ ድረስ የሙሴ ሕግ እንደሚሰራ ይናገራል፦
ማቴዎስ 5፥17 *እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ተራዊህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

“ዒባዳህ” عِبَادَة ማለትም “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው። “ኢቲባዕ” إتباع የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ “ተከተለ” ከሚለው የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢቲባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*፤ اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ
6፥106 *ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል* ፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢቲባዕ” إتباع ማለት እንግዲህ ከአላህ ወደ ነብያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ነው፤ ወደ ነብያችን”ﷺ” የተወረደው ደግሞ ቁርኣን እና ሰሒህ ሐዲስ ነው።

“ቢድዓ” بدع ደግሞ “በደዐ” بدع ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ኢብቲዳዕ” ابتداع ማለትም “ፈጠራ” ማለት ነው፤ ቢድዓ የኢቲባዕ ተቃራኒ ነው። ቢድዓ ማለት ከአምስቱ አሕካም ውጪ አዲስ ፈጠራ ማለት ነው፤ ስለ ቢድዓ ነብያችን”ﷺ” እንዲህ ይሉናል፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም"* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ *“አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ .

ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ቢድዓ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው “ሙብተዲዕ” مبتدئ ይባላል።
ይህንን ለቅምሻ ያክል በወፍ በረር ካየን ዘንዳ ሚሽነሪዎች፦ "ተራዊህ" تراويح‌‎ ማለትም "በረመዳን የሌሊት ሶላት" ነብያችን"ﷺ" የማያውቁትና ያልሰሩት ነው ብለው ለሚቀጥፉት ቅጥፈት ምላሽ መስጠት ግድ ይላል፤ ስለ ተራዊህ ከነብያችን"ﷺ" ሱና በቁና ማቅረብ ይቻላል፦
ኢማም ቡኻርይ: Book 31, Hadith 4
የነብዩ"ﷺ" ባልተቤት ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" በረመዳን ሌሊት ይጸልዩ ነበር"*። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها زَوْجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم صَلَّى وَذَلِكَ فِي رَمَضَانَ‏.‏
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 31, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ስለ ረመዳን እንደተናገሩት፦ *"ማንም በረመዳን ሌሊት በእምነት እና ከአላህ ወሮታ አገኛለው ብሎ ተስፋ አድርጎ ከቆመ ያለፈው ወንጀሉ ሁሉ ይቅር ይባልለታል"*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ لِرَمَضَانَ ‏ "‏ مَنْ قَامَهُ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ‏"‌‏.‏

አምላካችን አላህ፦ "መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ" ስላለን ተራዊህ መልእክተኛው የነገሩን ነገር ስለሆነ ቢድዓ አይደለም፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የእግዚአብሔር ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ክርስቲያኖች ኢየሱስ "የእግዚአብሔር ልጅ" ነው ይላሉ፤ "ልጅ" ማለት ምን ማለት ነው? ስንላቸው፦ "አብን አህሎና መስሎ ከአብ “ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል” ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ" ይሉናል። እረ ከሰማናቸው፦ “አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ" ይሉናል። ከእዚህ እሳቤ ቁርኣን በተቃራኒው፦ "አላህ ወለደ" ያሉ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፤ አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፤ እንደውም አላህ ቁርኣን ካወረደበት ምክንያት አንዱ እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ነው፦
37፥152 ፦ *“አላህ ወለደ” አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው*፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ይህንን የቁርኣን እሳቤ ካየን ዘንዳ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አባት መባሉ "አገኚ" ወይም "ፈጣሪ" በሚል ፍካሬአዊ ቃል መጥቷል፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ለምሳሌ መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስቱ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠራቸው እንደሆነ ቅቡል ነው፤ አዳምም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል፦
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።
አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠረው እንደሆነ እሙን ነው፤ ታዲያ ያለ አባት በእናት ብቻ የተፈጠረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢባል ምን ይደንቃል? ከማርያም ተጸንሶ የተወለደው ሰው መሆኑን አንርሳ፦
ሉቃስ 1፥35 ስለዚህ ደግሞ *ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።
ገላትያ 4 ፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ *እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ*፤

ማርያም የወለደችው መለኮትን ሳይሆን ሰው ብቻ ነው፤ ያም ሰው የእግዚአብሔር ልጅ መባሉ ፈጣሪ ያለ አባት ከእርሷ መፍጠሩን ያሳያል። አይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወለደው ይሉናል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ *እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወለድሁህ”*።
ዕብራውያን 1:5 ከመላእክትስ። *እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወልጄሃለሁ”*፥ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጭራሽ ይህ ጥቅስ “ዛሬ” የምትለዋ ቃል መነሻ ጊዜን ታመለክታለች፣ ይህም የኢየሱስ መፈጠር በጊዜ ውስጥ መሆኑን ያሳያል፤ ሲቀጥል "ወለደ" የሚለው በግሪኩ “ጄኑስ” γένος ማለት “ፈጠረ” ሲሆን አይሁዳውያን አምላክ ፆታ ስለሌለውን “መወለድ” መፈጠር ነው ብለው ያምናሉ፤ ምክንያቱን ተራራ እንደተወለደ ስለሚናገር፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
መዝሙር 90:2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”* γεννήθηκαν፥
አሞፅ 4:13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥

ተራሮች "ሳይወለዱ" የሚለው ይሰመርበርበት፤ ተራራ ይወለዳል እንዴ? ስንል መልሱ "ይወለዳል" የሚለው እማራዊ ቃል “ይሰራል” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

"ይሽሩ" የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን "ወለደ" ወይስ "ፈጠረ" ? አይ ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በእማሬአዊ ቃል ወለደ ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ ቃል ፈጠረ ለማለት ነው ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። አንዳንድ ቂሎች "መወለድ" ከአብ "መውጣት" ነው ይላሉ፤ ምነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ ነው ትሉ የለ እንዴ? ለምን መንፈስ ቅዱስን የአብ ልጅ አትሉትም? አይ "መውጣት" ማለት "መስረጽ" ነው ካላችሁ ለምንስ ወልድን ከአብ የሰረጸ ነው አትሉትም? ምክንያቱም ወልድም ከአብ የወጣ ነው ስለሚል፤ አይ መውጣት መላክ ማለት ነው ካላችሁ ጥሩ። ካልሆነ ልጅ ማለት፦ "አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ፤ አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ" ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ፍቅር

በዓለም ላይ ትልቁ ቁጥር ሴንቲሊዮን"Centillion" ነው፤ ባለ ስድስት መቶ ዜሮ የያዘ ነው። ይህንን ትልቅ ቁጥር ግን ከፊት ለፊቱ አንድ"1" ቁጥር ብትነሳ እነዚያ ሁሉ ዜሮ ሆነው ይቀራሉ። ከፊት ለፊት ዕውቀት፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ሃብት፣ ውበት ወዘተ ቢደረደሩም ከፊታቸው እንደ አንድ ቁጥር "ፍቅር" ከሌለ እንዚህ ሁሉ ዜሮ ናቸው። ፍቅር የሁሉ ነገር መነሻ ነው። ዓለማችን ሥርአቷን ጠብቃ በመሰሳብ እንዳትዛነፍ ያረጋት ይህ የፍቅር ሕግ ስበት"gravity" ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ኸምር

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥219 *አእምሮን ከሚቃወም መጠጥና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا

ከሚሽነሪዎች የሚሰነዘሩ ጥያቄዎች አብዛኛውን አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ ናቸው፤ “አስካሪ መጠጥ በኢስላም ይፈቀዳል” የሚል ጥራዝ ነጠቅ መረጃ ይነዛሉ። ጠይቆ ከስሩ በአጽንኦትና በአንክሮት መረዳት የእናት ነው፤ “ነገርን ከስሩ ውሃን ከጡሩ” ይላል ያገሬ ሰው።
እስቲ ስለ ኸምር ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናስተንትን፤ “ኸምር” خَمْر ማለት “ወይን ጠጅ” ማለት ሲሆን ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚሰራ ጠጅ ነው፦
16፥67 *ከዘምባባዎች እና ከወይኖችም ፍሬዎች እንመግባችኋለን፡፡ ከእርሱ ጠጅን እና መልካም ምግብንም ትሠራላችሁ፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አለ*፡፡ وَمِن ثَمَرَاتِ النَّخِيلِ وَالْأَعْنَابِ تَتَّخِذُونَ مِنْهُ سَكَرًا وَرِزْقًا حَسَنًا ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

አላህ ከዘንባባ እና ከወይን ፍሬ ማብቀሉ በእርግጥ ታምር አለበት፤ ከዚህም ሰው በሰናይ መልካም ምግብ ማለትም ጭማቂ ሲሰራ በተቃራኒው እኩይ የሆነውን አስካሪ ጠጅን ይሰራል፤ “ዛሊከ” ذَٰلِكَ ማለትም “በዚህም” የተባለው አመልካች ተውላጠ-ስም”demonstrative pronoun ከበፊቱ ያለው “ሁ” هُ ማለትም “እርሱ” የተባለው ተሳቢ ተውላጠ-ስም”objective pronoun” የሚያመለክት ነው፤ ይህም “እርሱ” የተባለው ፍራፍሬው ነው፦
16፥11 *በእርሱ ለእናንተ አዝመራን፣ ወይራንም፣ ዘምባባዎችንም፣ ወይኖችንም፣ ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ታምር አለ*። يُنبِتُ لَكُم بِهِ الزَّرْعَ وَالزَّيْتُونَ وَالنَّخِيلَ وَالْأَعْنَابَ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ ۗ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ዛሊከ” ذَٰلِكَ የተባለው የአዝመራን፣ የወይራንም፣ የዘምባባዎችንም፣ የወይኖችንም ፍራፍሬ ነው፤ ተጨማሪ አናቅጽ፦ 6፥99 13፥3 ይመልከቱ። ፍራፍሬ ሲቆይ ስኳርነቱ ወደ አሲድ ይቀየርና ያሰክራል፤ ይህ ሂደት በሥነ-ምርምር ጥናት ቆምጣጣነት”Fermentation” ይባላል፤ አሊያም ጌሾና ብቅል ሲቀላቀልበት ያሰክራል። ይህ ሂደት በሥነ-ምርምር ጥናት ፓስቸራዜሽን”Pasteurization” እና ኒዩትራላይዜሽን”Neutralization” ይባላል፤ ቢራ ፣ ቮድካ፣ ውስኪ የመሳሰሉት የዛ ውጤት ናቸው። ይህ ኣስካሪ መጠጥ አልኮልነት ሲኖረው የሰውን ህይወት በእጅጉ ይጎዳል፤ ነገር ግን በተፈጥሮ ሰውነታችን ውስጥ አልኮል ስላለ አልኮል ለጎደለው ሰውነት ጥቅም አለው፣ ከዚያም ባሻገር ጊዜአዊ ደስታ አለው። ነገር ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል። አምላካችን አላህ ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ይለናል፦
2፥219 *አዕምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣት እና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا

ቁማር ጥቅሙ ገንዘብ ቢሆንም የሰው ሃቅ ነውና ታላቅ ኃጢኣት ነው። አስካሪ መጠጥ ጥቅሙ ጊዚያዊ ደስታ ቢሆንም አዕምሮን የሚያደንዝና ለጥል፣ ለጥላቻ፣ ለዝሙት፣ ለጣዖት አምልኮ የሚዳርግ፤ ከሰላትና አላህ ከማውሳት የሚያዘናጋ እኩይ ነገር ስለሆነ ከሸይጧን ነው፦
5፥90 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ ቁማርም ጣዖታትም አዝላምም ከሰይጣን ሥራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፡፡ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْخَمْرُ وَالْمَيْسِرُ وَالْأَنصَابُ وَالْأَزْلَامُ رِجْسٌ مِّنْ عَمَلِ الشَّيْطَانِ فَاجْتَنِبُوهُ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
5፥91 *ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል፤ አላህን ከማውሳት እና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ተከልካዮች ናችሁን ተከልከሉ*፡፡ إِنَّمَا يُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَن يُوقِعَ بَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ فِي الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ وَيَصُدَّكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ وَعَنِ الصَّلَاةِ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّنتَهُونَ

ነብያችንም”ﷺ” በሐዲስ ላይ አስካሪ መጠጥ መጠጣት ከልክለዋል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 81
ዐብደላህ ኢብኑ ቡረይዳህ አባቱ እንዳለው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *በኮዳ በስተቀር ከነቢድ የሚዘጋጅ ነገር እንዳትጠጡ ከልክያችሁ ነበር፤ ግን አሁን በሁሉም ሰፍነግ መጠጣት ትችላላችሁ። ነገር ግን አስካሪ መጠጥ እንዳትጠጡ*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ بُرَيْدَةَ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ نَهَيْتُكُمْ عَنِ النَّبِيذِ إِلاَّ فِي سِقَاءٍ فَاشْرَبُوا فِي الأَسْقِيَةِ كُلِّهَا وَلاَ تَشْرَبُوا مُسْكِرًا ‏”‏

“ነቢድ” نَّبِيذ ማለት ከዘምባባ እና ከወይን ፍሬ የሚጠጣ ጭማቂ ነው፤ ይህ ሃላል ሲሆን ይህ ጭማቂ ከሁለት ቀናት አሊያም ከሦስት ቀናት በኃላ “ሙሥኪር” مُسْكِر ወይም “ሠከር” سَكَر ማለትም “አስካሪ”intoxicant” ይሆናል፤ ይህንን መጠጣት ሃራም ነው፤ አይደለም ኸምር ጠጪው ይቅርና ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ተጠያቂዎች ናቸው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 6: 
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “አላህ ኸምርን ጠጪውን፣ ቀጂውን፣ ሻጩንም፣ ገዢውንም፣ ጨማቂውን፣ አስጨማቂውን፣ ተሸካሚውን እና የሚሸከሙለትንም ሁሉ ረግሟቸዋል” أَنَّهُمَا سَمِعَا ابْنَ عُمَرَ، يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَعَنَ اللَّهُ الْخَمْرَ وَشَارِبَهَا وَسَاقِيَهَا وَبَائِعَهَا وَمُبْتَاعَهَا وَعَاصِرَهَا وَمُعْتَصِرَهَا وَحَامِلَهَا وَالْمَحْمُولَةَ إِلَيْهِ ‏”‏

በዱኒያህ ያለው ኸምር አስካሪ እና ሃምራ ከሆነ ታዲያ በጀነት ያለው ኸምር ምንድን ነው? ኢንሻላህ ይህንን ነጥብ በክፍል ሁለት እንዳስሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኸምር

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

32፥17 ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ *”የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም”*፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

“ጀነት” جَنَّة የሚለው ቃል እራሱ “ጀነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ወይም “ስውር” ማለት ነው፤ በጀነት ውስጥ ያለው ለሙስሊሞች የተደበቀላቸውን ፀጋ ደግሞ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፦
32፥17 *"ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን ጸጋ ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም”*፡፡ فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

አላህ በሐዲሰል ቁድሲይ ላይ የጀነት ፀጋ አይን አይቶት፣ ጆሮ፣ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ ለባሮቹ ያዘጋጃት እንደሆነች ነግሮናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 123:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ብለው አሉ፦ *"አላህም እንዲህ አለ፦ እኔ ለደጋግ ባሮቼ አይን አይቶት የማያውቅ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅና በሰው ልቦና ውል ብሎ የማያውቅ ጸጋን አዘጋጅቻለው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ قَالَ اللَّهُ أَعْدَدْتُ لِعِبَادِي الصَّالِحِينَ مَا لاَ عَيْنٌ رَأَتْ، وَلاَ أُذُنٌ سَمِعَتْ، وَلاَ خَطَرَ عَلَى قَلْبِ بَشَرٍ ‏”

ታላቁ ሰሓቢይ ዐብደሏህ ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” እንዲህ ይላሉ፦ *"በጀነት ውስጥ ካሉ ነገሮች ዱንያ ውስጥ ምንም የለም ግን ከስሞች መመሳሰል በስተቀር”* (ተፍሲሩ አጥ-ጦበሪይ)

ስለዚህ በጀነት ውስጥ ያሉትን አላህ ለባሮቹ ያዘጋጃቸው ፀጋዎች አይን አይቶት፣ ጆሮ፣ ሰምቶት፣ ልብ አስቦት የማያውቅ ነገር ከሆነ ሙዝ፣ ዘንባባ፣ ወይን፣ ተምር የመሳሰሉት የስም መመሳሰል እንጂ ቅርጽና ይዘቱ፣ ጥፍጥናውና ጣእሙ ከዚህ ዓለም ጋር አንድ አይደለም፤ ይህን አምላካችን አላህ ሲናገር፦
47፥15 *የዚያች ጥንቁቆች ተስፋ የተሰጧት ገነት "ምሳሌ" በውስጧ ሺታው ከማይለወጥ ውሃ ወንዞች ጣዕሙ ከማይለውጥ ወተትም ወንዞች ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች፤ ከተነጠረ ማርም ወንዞች አሉባት፤ ለእነሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ በያይነቱ ከጌታቸው ምሕረትም አላቸው*። مَّثَلُ الْجَنَّةِ الَّتِي وُعِدَ الْمُتَّقُونَ ۖ فِيهَا أَنْهَارٌ مِّن مَّاءٍ غَيْرِ آسِنٍ وَأَنْهَارٌ مِّن لَّبَنٍ لَّمْ يَتَغَيَّرْ طَعْمُهُ وَأَنْهَارٌ مِّنْ خَمْرٍ لَّذَّةٍ لِّلشَّارِبِينَ وَأَنْهَارٌ مِّنْ عَسَلٍ مُّصَفًّى ۖ وَلَهُمْ فِيهَا مِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ وَمَغْفِرَةٌ مِّن رَّبِّهِمْ ۖ كَمَنْ هُوَ خَالِدٌ فِي النَّارِ وَسُقُوا مَاءً حَمِيمًا فَقَطَّعَ أَمْعَاءَهُمْ
2፥25 *ከእርሷ ከፍሬ ዓይነት ሲሳይን በተመገቡ ቁጥር ፍሬዎችዋ ስለሚመሳሰሉ «ይህ ያ ከአሁን በፊት የተገመብነው ነው» ይላሉ፡፡ እርሱንም ተመሳሳይ ኾኖ ተሰጣቸው*፡፡ ۖ كُلَّمَا رُزِقُوا مِنْهَا مِن ثَمَرَةٍ رِّزْقًا ۙ قَالُوا هَـٰذَا الَّذِي رُزِقْنَا مِن قَبْلُ ۖ وَأُتُوا بِهِ مُتَشَابِهًا ۖ وَلَهُمْ فِيهَا أَزْوَاجٌ مُّطَهَّرَةٌ ۖ وَهُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

"መሰል" مَثَل ማለት "ምሳሌ" ማለት ሲሆን እዚህ ላይ የተዘረዘሩት ውሃ፣ ወተት፣ የወይን ጠጅም፣ ማር፣ ፍሬዎች "ምሳሌ" ናቸው፤ ምክንያቱም የዚህ ዓለም ውሃ ሲቆይ ይሸታል፣ ወተት ሲቆይ ረግቶ ይቀየራል፣ ማርና ወይንም ጥፍጥናው ይሰለቻል፤ ነገር ግን የጀነት ውሃ፣ ወተት፣ የወይን ጠጅም፣ ማር፣ፍሬዎች ግን የተለየ ነው፤ የዚህ ዓለም ወይን ከቆየ ይቆመጥጥና ያሰክራል፤ እራስምታት ያመጣል፤ ከዚያም መጥፎ ንግግር ሰው እንዲናገር ያደርጋል፣ በመቀጠልም ወንጀልም ያሰራል። ነገር ግን የጀነት ወይን ጠጅ አያሰክርም፣ ራስምታት የለውም፣ ውድቅ ንግግር እና ወንጀልም አያሰራም፤ ምክንያቱም ምንም አልኮል የሌለበት "ንጹህ" የሆነ ነው፦
56፥19 *ከእርሷ የራስ ምታት አያገኛቸውም፤ አይሰክሩምም*። لَّا يُصَدَّعُونَ عَنْهَا وَلَا يُنزِفُونَ
37፥47 *በእርሷ ዉስጥም ራስ ምታት የለባትም። እነርሱም ከእርሷ የሚሰክሩ አይደሉም*። لَا فِيهَا غَوْلٌ وَلَا هُمْ عَنْهَا يُنزَفُونَ
52፥23 *በውስጧ መጠጥን ይሰጣጣሉ፤ በውስጧ ውድቅ ንግግር እና ወንጀልም የለም*። يَتَنَازَعُونَ فِيهَا كَأْسًا لَّا لَغْوٌ فِيهَا وَلَا تَأْثِيمٌ
76፥21 *ጌታቸውም ንጹህ የሆኑን መጠጥ ያጠጣቸዋል*። رَبُّهُمْ شَرَابًا طَهُورًا

"ንጹህ" የሚለው ቃል "ጠሁር" طَهُور ሲሆን ይህም ከአልኮልነት ነጻ የሆነ የተጣራ ወይን ነው፦
83:25 *ተጣርቶ ከታተመ ጠጅ ይጥጠጣሉ*። يُسْقَوْنَ مِن رَّحِيقٍ مَّخْتُومٍ

ይህም ንጹህ ወይን መበረጃው "ካፉር" كَافُور "ዘንጀቢል" زَنجَبِيل "ተሥኒም" تَسْنِيم ነው፦
76፥5 በጎ አድራጊዎች፥ *መበረዣዋ ካፉርው ከሆነች ጠጅ ይጠጣሉ*። إِنَّ الْأَبْرَارَ يَشْرَبُونَ مِن كَأْسٍ كَانَ مِزَاجُهَا كَافُورًا
76፥17 በእርሷም *መበረዣዋ ዘንጀቢል የሆነችን ጠጅ ይጠጣሉ*። وَيُسْقَوْنَ فِيهَا كَأْسًا كَانَ مِزَاجُهَا زَنجَبِيلًا
83፥27 *መበረዣውም ከተሥኒም ነው*። وَمِزَاجُهُ مِن تَسْنِيمٍ

"እሺ የማያሳክር ወይን ከሆነ እንዴት ጀነት ውስጥ ወይን ይኖራል?" ብለው ሚሽነሪዎች ይሞግታሉ፤ ምነው በእናንተ መንግሥተ-ሰማይ ውስጥ የሚበላ ዛፍ እና የሚጠጣ ወይን የለም እንዴ? አንብቡት፦
ማቴዎስ 26፥29 *ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር አዲሱን ወይን ፍሬ እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ ከዚህ ከወይን ፍሬ አልጠጣም*። But I say unto you, I will not drink henceforth of this fruit of the vine, until that day when I drink it new vine with you in my Father's kingdom.
ራእይ 2፥7 *ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ቤት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥33 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡

መግቢያ
መቼም ሚሽነሪዎች የኢስላም ብርሃን በምን እናጠልሸው ብለው ከተነሱ ጊዜያት አለፉ፤ የኢስላምን መሰረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ ያልተረዱ ስለሆኑ መደበኛ በሆነ መርሃ-ግብርና መዋቅር ከመማር ይልቅ ጎግል ላይ በሰፈረው የተለቃቀመ ጥራዝ-ነጠቅ መረጃ ድምዳሜ ላይ ሲደርሱ ማየት እጅጉን ያማል፣ አንዱ ሚሽነሪ፦ ነብያችንን”ﷺ” የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ ሲለብሱ እና ከእርሷ ጋር ተራክቦ ሲያደርጉ ብቻ ነው ወህይ የሚወርድላቸው ብሎ በትክክል እንኳን ማንበብ የማይችለውን ጩቤ ጥቅስ ጠቅሶ የጨባራ ለቅሶ እና ተስካር የሆነው ውሃ የማይቋጥ ሙግት ሲሟገተኝ ነበር፤ ይህ ስሁት የሆነ ሙግት ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በእጥቡ ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው ከመነሻው አከርካሪውን መመታት አለበት፤ እስቲ ሐዲሱን እንመልከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 51 , ሐዲስ 16:
ሂሻም ኢብኑ ኡርዋህ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደተረከው….የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ለኡሙ ሰላማ”ረ.ዓ.” በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም “ከአይሻ ልብስ በስተቀር አሏት”፤ فَقَالَ لَهَا ‏”‏ لاَ تُؤْذِينِي فِي عَائِشَةَ، فَإِنَّ الْوَحْىَ لَمْ يَأْتِنِي، وَأَنَا فِي ثَوْبِ امْرَأَةٍ إِلاَّ عَائِشَةَ ‏”‌‏ ።

ምን ያህል ቅጥፈት እንዳለ ተመልከቱ፤ እዚህ ሐዲስ ላይ የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ ለበሱ የሚል የት አለ? ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ጋር ተራክቦ ሳደርግ የሚል የት አለ? ወህይ የሚመጣልኝ ከአይሻ ልብስ ውስጥ ብቻ ነው የሚል የት አለ? ይህ ሁሉ ገለባ ሂስ ነው፤ ነብያችን ወህይ የሚመጣላቸው በተለያየ ሁኔታ ቢሆንም ከሌሎች ባለቤቶታቸው ይልቅ የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ቤት እያሉ ብቻ ነው ወህይ የሚመጣላቸው ማለት “ይልቅ” የሚለው ማነፃፀሪያ ከሴቶቹ ጋር እንጂ አጠቃላይ አይደለም፤ “ሠውብ” ثَوْب የሚለው ቃል በብዙ ይመጣል፦
“ሂጃብ” حِجَاب “መጋረጃ”፣
“ፊራሽ” فِرَٰش ምንጣፍ”፣
“ሊሃፍ” لِحَاف “ፍራሽ”
“በይት” بَيْت “ቤት”
“ሊባሥ” لِبَاس “ልብስ” በሚል ይመጣል፤ ይህንን በተለያዩ ነጥቦች ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
“ሊሃፍ”
“ሊሃፍ” لِحَاف የሚለው ቃል “ፍራሽ” ማለት ሲሆን “ከአይሻ ልብስ በስተቀር” የሚለው “ከአይሻ ፍራሽ በስተቀር” በሚለው መጥቷል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 62 , ሐዲስ 122:
ኡሙ ሰላማ ሆይ በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ፍራሽ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም “ከአይሻ ፍራሽ በስተቀር” “‏ يَا أُمَّ سَلَمَةَ لاَ تُؤْذِينِي فِي عَائِشَةَ، فَإِنَّهُ وَاللَّهِ مَا نَزَلَ عَلَىَّ الْوَحْىُ وَأَنَا فِي لِحَافِ امْرَأَةٍ مِنْكُنَّ غَيْرِهَا ‏”‌‏.‏ ፤

ነጥብ ሁለት
“በይት”
“በይት” بَيْت ማለት “ቤት” ሲሆን “ከአይሻ ልብስ በስተቀር” የሚለው “ከአይሻ ቤት” በሚለው መጥቷል፤ ቤት የሚከፋፈለው በመጋረኛ ስለሆነ “ሠውብ” የሚለው በሌላ ሪዋያ ላይ “በይት” بَيْت “ቤት” በሚል መጥቷል፦
ኢማሙ አህመድ መጽሐፍ 6 ሐዲስ 293
የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ኡሙ ሰላማ ሆይ በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ቤት ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከአይሻ ቤት በስተቀር፤ رسول الله صلى الله عليه و سلم ثم قال يا أم سلمة لا تؤذيني في عائشة فإنه والله ما نزل على الوحي وأنا في بيت امرأة من نسائي غير عائشة ።

ነጥብ ሶስት
“ሊባሥ”
“ሊባሥ” لِبَاس ማለት ትርጉሙ “ልብስ” ማለት ሲሆን “ሠውብ” ማለት “ሊባሥ” ነው ብንል እንኳን “ልብስ” የሚለው ቃል ሁልጊዜ ሱሪን፣ ቀሚስን፣ ጃኬትን ብቻ ሳይሆን የሚያመለክተው መጠለያን፣ መከለያ፣ መሸሸጊያ ለማመልከት ይመጣል፤ አምላካችም አላህ ለምሳሌ ሴት የወንድ ልብስ ናት ወንድ የሴት ልብስ ነው ይለናል፦
2፥187 በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለእናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ እነርሱ ለእናንተ “ልብሶች” ናቸው፤ እናንተም ለእነርሱ “ልብሶች” ናችሁ أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ ٱلصِّيَامِ ٱلرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَآئِكُمْ ۚ هُنَّ لِبَاسٌۭ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌۭ لَّهُن ፡፡

መቼም ልብስ የሚለውን አንዱ የአንዱ መሸሸጊያ ማለት እንጂ አንዱ የአንዱ ጃኬት ወይም ቀሚስ አሊያም ሱሪ ማለት ነው የሚል ቂል የለም፤ አላህ ሌሊትን ልብስ አደረገ፤ ያ ማለት “መጠለያ” ማለት ነው፦
25:47 እርሱም ያ ለእናንተ “ሌሊትን” ልብስ፣ እንቅልፍንም ማረፊያ ያደረገ፤ ቀንንም መበተኛ ያደረገላችሁ ነው وَهُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا وَٱلنَّوْمَ سُبَاتًۭا وَجَعَلَ ٱلنَّهَارَ نُشُورًۭا ።
78:10 ሌሊቱንም ልብስ አደረግን وَجَعَلْنَا ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا ።

ይህንን ካየን ነብያችን”ﷺ”፦ “ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ በስተቀር” ሲሉ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ፍራሽ ወይም ቤት ማለታቸው እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው እንጂ ቃላትን ማንሸዋረር እና ማውረግረግ አይቻልም። እንዴት የአንድ ሴት ልብስ ውስጥ አንድ ወንድ ቃል በቃል ሊገባስ ይችላል? ይህ ሆን ተብሎ ድርቅና አላህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትወዛገቡበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፦
18፥68-69 ቢከራከሩህም «አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ አላህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትወዛገቡበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቁርአንን አያስተነትኑምን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ *ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ٱلْقُرْءَانَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ ٱللَّهِ لَوَجَدُوا۟ فِيهِ ٱخْتِلَٰفًۭا كَثِيرًۭا

ቁርአን ከወረደበት ምክንያት አንዱ የአዕምሮ ባለቤቶች አንቀፁን እንዲያስተነትኑ ነው፦
38:29 ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፤ አንቀጾቹን *እንዲያስተነትኑ* እና *የአዕምሮ ባለቤቶችም* *እንዲገሰጹ* አወረድነው كِتَٰبٌ أَنزَلْنَٰهُ إِلَيْكَ مُبَٰرَكٌۭ لِّيَدَّبَّرُوٓا۟ ءَايَٰتِهِۦ وَلِيَتَذَكَّرَ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ ፡፡

ቁርአን የዓለማቱ ጌታ የአላህ ንግግር ነው፤ አላህ እውነተኛ አምላክ ስለሆነ የሚናገረው ንግግር እርስ በእርሱ አይጋጭም፣ አይቃረንም፣ አይፈለስም፣ አይጣረስም፤ አይ እርስ በእርስ ይጋጫል የሚል ሃያሲ ካለ ግን አንተንትኖ ማምጣት አለበት የሚል ተግዳት”Falsification test” ያቀርባል፦
4፥82 ቁርኣንን አያስተነትኑምን? ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ *ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ٱلْقُرْءَانَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ ٱللَّهِ لَوَجَدُوا۟ فِيهِ ٱخْتِلَٰفًۭا كَثِيرًۭا

እኛ ሙስሊሞሽ ለሚሽነሪዎች ልዩነት የሚመስሏቸው ጉዳዮች ቁርአን የወረደበትን ቋንቋ፣ሰዋስው እና አውድ ካለመረዳት የሚመጣ ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ነው የሚል ሙግት አለን፤ ጭራሽ በሂስ የሚቀርቡት አንቀፆች በአፅንኦትና በአንክሮት ከተጠና የቁርአን ታምር ነው፤ ይህንን ነጥብ በጥራዝ ጠለቅ ዕውቀት እናስተንትን፦
39፥71 እነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ ይከፈታሉ*፡፡ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

የጀሃነም ደጆች “ይከፈታሉ” የሚለው ቃል ላይ “ፉቲሐት” فُتِحَتْ ሲሆን መነሻው ላይ “ወ” و የሚል ቃል የለውም፤ ግን የጀነት ደጆች “የተከፈቱ” የሚለው ቃል ግን “ወፉቲሐት” وَفُتِحَتْ ሲሆን “ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ “ወ” የሚል መነሻ ቅጥያ አለ፦
39፥73 እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገነት ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ “የተከፈቱ”* ሲኾኑ፤ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ رَبَّهُمْ إِلَى ٱلْجَنَّةِ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا وَفُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

እስቲ ይህ “ዋው” و የሚለው ቃል”ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ የሌለበትን ምክንያት እናስተንትን፤ ገሃነም ሰባት ደጆች አሏት፦
15፥43-44 «ገሀነምም ለእርሱና ለተከተሉት ለመላውም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት፡፡ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوْعِدُهُمْ أَجْمَعِينَ «ለእርሷ *ሰባት ደጃፎች* አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ፡፡ لَهَا سَبْعَةُ أَبْوَٰبٍۢ لِّكُلِّ بَابٍۢ مِّنْهُمْ جُزْءٌۭ مَّقْسُومٌ
39፥71 እነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ* ይከፈታሉ፡፡ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

ቀጥሎ “ዋው” و የሚለው ቃል”ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይእናስተንትን ያለበትን ምክንያት ፤ ጀነት ስምንት ደጆች አሏት፦
7፥40 እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ *የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም*፡፡ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ *ገነትን አይገቡም*፡፡ እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسْتَكْبَرُوا۟ عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَٰبُ ٱلسَّمَآءِ وَلَا يَدْخُلُونَ ٱلْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ ٱلْجَمَلُ فِى سَمِّ ٱلْخِيَاطِ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُجْرِمِينَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 67:
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ጀነት ስምንት ደጃፎች አሏል*፤ ከእነርሱ አንዷ ስሟ አር-ረይያን ፆመኛ እንጂ ሌላ አይገባባትም። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ فِي الْجَنَّةِ ثَمَانِيَةُ أَبْوَابٍ، فِيهَا باب يُسَمَّى الرَّيَّانَ لاَ يَدْخُلُهُ إِلاَّ الصَّائِمُونَ ‏”‌‏
ነጥቡ ያለው እዚህ ጋር ነው፤ ቁርአን ላይ ሰባት ቁጥር ተነግሮ ስምንት ቁጥር ከመጣ ሰባት ላይ ዋው የለውም ግን ስምንት ላይ ዋው አለ፤ ምሳሌ አንድ፦
18፥22 በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው በጥርጣሬ «ሦስት ናቸው፤ አራተኛቸው ውሻቸው ነው» ይላሉ፡፡ «አምስት ናቸው፤ ስድስተኛቸው ውሻቸው ነውም» ይላሉ፡፡ «ሰባት ናቸው፤ *ስምንተኛቸውም* ውሻቸው ነው» ይላሉም፡፡ سَيَقُولُونَ ثَلَٰثَةٌۭ رَّابِعُهُمْ كَلْبُهُمْ وَيَقُولُونَ خَمْسَةٌۭ سَادِسُهُمْ كَلْبُهُمْ رَجْمًۢا بِٱلْغَيْبِ ۖ وَيَقُولُونَ سَبْعَةٌۭ وَثَامِنُهُمْ كَلْبُهُمْ ۚ

“ወ” የሚል ቃል “ሳሚን” ثَامِن ማለትም “ስምንተኛ” በሚል ቃል ላይ መጥቷል፤ “*ወ*ሳሚኑሁም” وَثَامِنُهُمْ ። ነገር ግን “ሠብዐቱን” سَبْعَةٌ ማለትም “ሰባተኛ” በሚለው ቃል ላይ ግን አልመጣም፤ ምሳሌ ሁለት፦
69፥7 ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶች *እና ስምንት* መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ سَخَّرَهَا عَلَيْهِمْ سَبْعَ لَيَالٍۢ وَثَمَٰنِيَةَ أَيَّامٍ حُسُومًۭا فَتَرَى ٱلْقَوْمَ فِيهَا صَرْعَىٰ كَأَنَّهُمْ أَعْجَازُ نَخْلٍ خَاوِيَةٍۢ

“ወ” የሚል “ሰማኒን” ثَمَٰنِين ማለትም “ስምንት” በሚል ቃል ላይ መጥቷል፤ “ወሰማኒየታህ” وَثَمَانِيَةَ ። ነገር ግን “ሠብዐ” سَبْعَ ማለትም “ሰባት” በሚለው ቃል ላይ ግን አልመጣም። “ዋው” እዚህ ጋር አርፉል አጥፍ ሳይሆን ዋው ሙተና ነው፤ ዋው ሁልጊዜ መነሻ ቅጥያ ላይ ሆኖ ሲመጣ አያያዥ መስተጻምር ነው ተብሎ አይደመደምም፤ ለምሳሌ “ወላሂ” وَٱللّٰهِ እንላለን፤ እዚህ ጋር “ወ” و የሚለው “ቢ” بِا በሚል ሲመጣ “ቢላህ” بِالله “በአላህ” እንደማለት ነው። አንድ ቃል ሁልጊዜ አንድ ትርጉም ይኖረዋል ማለት አይደለም፤ ለምሳሌ “ለው” َلَوْ ማለት “ቢሆን”if” ሲሆን “ኢን” إِن በሚል ይመጣል። ለናሙና ያክል ሌላ ሰዋስው ከቁርኣን ብንመለከት ለምሳሌ “ላ” َلَا የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም ይኖረዋል፦
1ኛ. “ላ” የሚለው ቃል ለቀድ” َلَقَدْ ማለትም “እርግጥ” የሚል ሆና ትመጣለች፤ ለምሳሌ፦
70፥40 በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ فَلَآ أُقْسِمُ بِرَبِّ ٱلْمَشَٰرِقِ وَٱلْمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ

2ኛ. “ላ” የሚለው ቃል “ማ” مَا ማለትም “አፍራሽ ቃል” ሆና ትመጣለች፤ ለምሳሌ፦
4፥71 «ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ

ስለዚህ ዋው መጀመሪያ ስለ ጀሃነም በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ አለመኖሩ እና ሁለተኛው ስለ ጀነት በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ መኖሩ ያለው ጥበብ በአጋጣቢ የሆነ ሳይሆን አላህ የጀሃነም ደጆች ያላቸው ውርደት የሚያመለክ ሲሆን የጀነት ደጆች ደግሞ ያላቸውን ክብር ያሳያል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በሕይወትም እስካለሁ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥31 *በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል*፡፡ وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنتُ وَأَوْصَانِي بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ مَا دُمْتُ حَيًّا

ዒሳ ኢብኑ መርየም፦ "በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል" ማለቱ "አሁን ዘካን ሰለማይሰጥ በሕይወት የለም ሞቷል ወይም በሰማይ በሕይወት ካለ እዛ ዘካ እየሰጠ ነው ወይ?" ብለው ስሁታን ተሟጓቾች ብዙ ጊዜ አድሮ ቃሪያና ከርሞ ጥጃ በመሆን ይጠቅሳሉ፤ ይህንን የሚጠይቁት አለስልሶና አቅለስልሶ ለመንቀፍ እንጂ ለመረዳት አይደለም፤ ይህ ደግሞ እያነቡ እስክስታ ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ! የሚያስብል ስሙር ሙግት እንሞግት እስቲ፦
19፥31 *በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል*፡፡ وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنتُ وَأَوْصَانِي بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ مَا دُمْتُ حَيًّا

"በየትም ስፍራ" ማለት በምድርም በሰማይም አላህ ዒሳን ብሩክ አድርጎታል፤ ቀጥሎ "እስካለው" የሚል ሃይለ-ቃል "ዱምቱ" دُمْتُ ሲሆን ይህም ቃል "በእስራኢል ልጆች መካከል እስካለ ድረስ" መሆኑን ለማመልከት በሌላ አንቀጽ ተጠቅሷል፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ *"በውስጣቸውም እስካለሁ ድረስ" በእነርሱ ላይ ”ምስክር” ነበርኩ*፡፡ *”በወሰድከኝም” ጊዜ አንተ በእነርሱ ላይ *”ተጠባባቂ”* ነበርክ*፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡» مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۚ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًۭا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ ۖ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِى كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ شَهِيدٌ

"ዱምቱ" دُمْتُ ማለትም "እስካለው" ድረስ የሚለው ሃይለ-ቃል በምድር ላይ ያለውን ቆይታ ያመለክታል፤ ምክንያቱም ቀጥሎ ያለው "በወሰድከኝ ጊዜ" የሚለው ሃይለ-ቃል ወደ ሰማይ መወሰዱን ስለሚያመለክት "እስካለው" የሚለው ሃይለ-ቃል በምድር ላይ በሕይወት እያለ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ስለዚህ በሕይወት በምድር ላይ እያለ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አሳልፏል፤ አላህ ወደ ሰማይ በወሰደው ጊዜ ግን የዘካ አገልግሎት ይቆማል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢኽላስ እና ሪያዕ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

76፥9 *«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም*፡፡ إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا

ነጥብ አንድ
"ኢኽላስ"
“ዒባዳህ” عِبَادَة ማለትም “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉ፤ እነርሱም፦ አንደኛ “ኢማን” إِيمَٰن ሁለተኛ “ኢኽላስ” إخلاص ሦስተኛ “ኢቲባዕ” إتباع ናቸው። “ኢኽላስ” إخلاص ማለት ከእዩልይና ስሙልኝ እና ከሙገሳና ወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚነየት መተናነስ፣ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ እና ማጥራት ነው፣ እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ አምልኳቸውን የፈጸሙ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው፦
13፥22 እነዚያም *የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ፣ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ፣ እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ኾነ በግልጽ የመጸወቱ፣ ክፉውንም ነገር በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው*፡፡ እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው*፡፡ وَالَّذِينَ صَبَرُوا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً وَيَدْرَءُونَ بِالْحَسَنَةِ السَّيِّئَةَ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عُقْبَى الدَّارِ

ፊትን የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከአላህ የሚፈራ ሙስሊም ከሰው ዋጋ እና ምስጋና ፈልጎ ሳይሆን የሚያደርገውን ሁሉ ለአላህ ውዴታ ብሎ ያደርጋል፦
76፥9 *«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም*፡፡ إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا
76፥10 *«እኛ ፊትን የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» ይላሉ*፡፡ إِنَّا نَخَافُ مِن رَّبِّنَا يَوْمًا عَبُوسًا قَمْطَرِيرًا

ኢኽላስ ያለው ሙስሊም ምሳሌ በተስተካከለች ከፍተኛ ስፍራ ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው፦
2፥265 *የእነዚያም የአላህን ውዴታ ለመፈለግና ለነፍሶቻቸው እምነትን ለማረጋገጥ ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱ ሰዎች ምሳሌ በተስተካከለች ከፍተኛ ስፍራ ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው*፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ وَمَثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمُ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ وَتَثْبِيتًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ كَمَثَلِ جَنَّةٍ بِرَبْوَةٍ أَصَابَهَا وَابِلٌ فَآتَتْ أُكُلَهَا ضِعْفَيْنِ فَإِن لَّمْ يُصِبْهَا وَابِلٌ فَطَلٌّ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

በዓለም ላይ ትልቁ ቁጥር መቼም ሴንቲሊዮን ነው፤ እርሱም ባለ ስድስት መቶ ዜሮ የያዘ ነው፤ ይህንን ትልቅ ቁጥር ግን ከፊት ለፊቱ አንድ ቁጥር ብትነሳ እነዚያ ሁሉ ዜሮ ሆነው ይቀራሉ እንጂ ዋጋ የላቸው። እንደዚሁ ልግስና፣ ዕውቀት፣ ሰማዕትነት፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ሃብት፣ ውበት ወዘተ... ቢደረደሩም ከፊታቸው እንደ አንድ ቁጥር "ኢኽላስ" ከሌለ እንዚህ ሁሉ ዜሮ ናቸው። ኢኽላስ ያለው ሙስሊም "ሙኽሊስ" مُخْلِص ማለትም "አጥሪ" "ምርጥ" ይባላል፦
40፥14 *አላህንም ከሓዲዎች ቢጠሉም ሃይማኖትን ለእርሱ "አጥሪዎች" ኾናችሁ ተገዙት*፡፡ فَادْعُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُون
37፥40 *ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ቅጣትን አይቀምሱም*፡፡ إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ
38፥82 እርሱም አለ፦ *"በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ"*፡፡ قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ
38፤83 *"ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ"*፡፡ إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ الْمُخْلَصِينَ

"ሙኽሊሲን" مُخْلِصِين የሙኽሊስ ብዙ ቁጥር ነው፤ ሸይጧን ቃል የገባው ከአላህ ባሮች ሙኽሊሲን የሚባሉትን ላለማሳሳት ነው፤ ሙኽለሲን በአላህ መንገድ የሚለግሱ፣ መመጻደቅንና ማስከፋትን የማያስከትሉ ሲሆኑ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፤ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም፦
2፥262 *እነዚያ ገንዘቦቻቸውን “በአላህ መንገድ የሚለግ ከዚያም የሰጡትን ነገር “መመጻደቅንና ማስከፋትን የማያስከትሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም*፡፡ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ثُمَّ لَا يُتْبِعُونَ مَا أَنفَقُوا مَنًّا وَلَا أَذًى ۙ لَّهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُون

ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ሪያዕ እንቀጥላለን.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አትሁን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

28፥86 *መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም፡፡ ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ፡፡ ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን*፡፡ وَمَا كُنتَ تَرْجُو أَن يُلْقَىٰ إِلَيْكَ الْكِتَابُ إِلَّا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۖ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرًا لِّلْكَافِرِينَ

አምላካችን አላህ ስለ ነብያችን"ﷺ" አለመጠራጠር እና ማመን ሲናገር፦
2፥285 *መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ

ይህ አንቀጽ በቂ ነው፤ ሌላ ጥቅስ ላይ አምላካችን አላህ ለነብያችን"ﷺ"፦ "ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን" ይላል፤ "ብትሆን" ማለት እና "ነህ" ማለት በይዘም ሆነ በአይነት፤ በመንስኤም ሆነ በውጤት ሁለት ቃላት እና ትርጉም ናቸው፦
10፥94 *ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ*፡፡ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፡፡ *ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን*፡፡ فَإِن كُنتَ فِي شَكٍّ مِّمَّا أَنزَلْنَا إِلَيْكَ فَاسْأَلِ الَّذِينَ يَقْرَءُونَ الْكِتَابَ مِن قَبْلِكَ ۚ لَقَدْ جَاءَكَ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُمْتَرِين

"ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን" ማለት "ከተጠራጣሪዎቹም ነህ" ማለት አይደለም። ይህንን ሃይለ-ቃል ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት የሚቀጥለውን አንቀጽ እንመልከት፦
10፥95 ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች *ከአስተባበሉት አትሁን*፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና፡፡ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ الْخَاسِرِينَ

"ከአስተባበሉት አትሁን" ማለት አስተባብለካል ማለት ሳይሆን ምክርና ማስጠንቀቂያ ነው፤ አውዱ ይቀጥልና "ከአጋሪዎቹም አትሁን" ይላል፤ ያ ማለት አጋርተሃል ማለት አይደለም፦
10፥105 ፊትህንም ወደ ቀጥታ ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ *ከአጋሪዎቹም አትሁን*፡፡ وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

በለይለቱል ኢስራእ ወል ሚራጅ ነብያችን"ﷺ" ሙሳን ከማግኘታቸው በፊት እንደሚያገኙት አምላካችን አላህ ሲናገር፦ "እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን" ብሏል፦
32፥23 ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ *እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን*፡፡ ለእስራኤል ልጆችም መሪ አደረግነው፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ فَلَا تَكُن فِي مِرْيَةٍ مِّن لِّقَائِهِ ۖ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ሙሳን እንደሚያገኙት አውቀው ተጠራጥረው ሳይሆን አትሁን ምክር እና ማስጠንቀቂያ እንጂ እርሱን ከመገናኘት በመጠራጠር ውስጥ ነበሩ የሚለውን እንደማይይዝ ሁሉ በተመሳሳይም "ከአስተባበሉት አትሁን" "ከአጋሪዎቹም አትሁን" "ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን" ማለት ምክርና ማስጠንቀቂያ እንጂ "አስተባባይ" "አጋሪ" "ተጠራጣሪ" ነበርክ የሚል ፍቺ አይኖረውም። መዲና ላይ የነበሩት አይሁዳውያን ከመካዳቸው በፊት አላህ፦ "የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ" ብሏቸዋል፦
2፥41 ከእናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም እመኑ፡፡ *በእርሱም የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ*፡፡ وَآمِنُوا بِمَا أَنزَلْتُ مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَكُمْ وَلَا تَكُونُوا أَوَّلَ كَافِرٍ بِهِ

"የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ" ማለት ክደው ነበር ማለት ሳይሆን እንዳይክዱ ምክርና ማስጠንቀቂያ እንደሆነ ሁሉ ከላይ ያለው ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን የሚለው ሃይለ-ቃል ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው። "ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን" ማለት እረዳት ሆነው ነበር ማለትን ያስይዛልን? በፍጹም። ነብያችን"ﷺ" መጽሐፉ ወደ እርሳቸው መወረዱን ተስፋ የሚያደርጉ አልነበሩም፤ መጽሐፉም ምን እንደኾነ የሚያውቁ አልነበሩም፤ ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደላቸው፤ እሳቸው ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚመሩ ሆነው ሕይወታቸውን አሳልፈዋል እንጂ አንድም ቀን በቁርኣን አስተባብለው፣ በመልእክቱ ተጠራጥረው እና በአላህ ላይ አጋርተው አያውቁም፦
28፥86 *መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም፡፡ ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ፡፡ ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን*፡፡ وَمَا كُنتَ تَرْجُو أَن يُلْقَىٰ إِلَيْكَ الْكِتَابُ إِلَّا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۖ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرًا لِّلْكَافِرِينَ
42፥52 እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን አወረድን፡፡ *መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም*፡፡ ግን መንፈሱን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ *አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَـٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

ተጠራጥረው ቢሆን ኖሮ "ነህ" የሚል ቃል ይጠቀም ነበር፤ ነገር ግን "ነህ" የሚለውን የሚጠቀመው ለአሉታዊ ብቻ ነው፤ "አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ" "በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ" "ከመልክተኞቹ ነህ" የሚል ነው፤ ለናሙና ያክል ይህ በቂ ነው፦
68፥4 *አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ*፡፡ وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ
36፥4 በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ፡፡ عَلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ
2፥252 *እነዚህ አንቀጾች በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ አንቀጾች ናቸው፤ አንተም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ*፡፡ تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ ۚ وَإِنَّكَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
36፥3 *አንተ በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ*፡፡ إِنَّكَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አማላጅ ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

34፥23 *ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ

“ሸፋዐህ” شَفَٰعَهማለት “ምልጃ” ማለት ሲሆን ምልጃ ሥስት ማንነቶችን ያቅፋል፤ እነርሱም፦ አንደኛው የሚማለደው ተማላጅ፣ ሁለተኛው የሚማለድለት ተመላጅ እና ሥስተኛው የሚማልደው አማላጅ ናቸው፤ አላህ የሁሉም ነገር ፈጣሪና አስተናባሪ በመሆኑ የሚማለድ ተማላጅ ነው፤ ከፍጡሮቹ መካከል ደግሞ እርሱ የፈቀደላቸው ፍጡሮቹ ደግሞ ተመላጆች እና አማላጆች ናቸው። ይህ ሦስቱ ሂደት “ምልጃ” ሲባል ይህ የምልጃ ፈቃድ የአላህ ብቻ ነው፦
39፥44 *”ምልጃ በሙሉ የአላህ ብቻ ነው፤ የሰማያትና የምድር ሥልጣን የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ”* በላቸው፡፡ قُل لِّلَّهِ الشَّفَاعَةُ جَمِيعًا ۖ لَّهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
34፥23 *ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ
20፥109 *በዚያ ቀን ለእርሱ አልረሕማን የፈቀደለትን እና ለእርሱም ቃልን የወደደለትን ሰው ቢኾን እንጅ ምልጃ አንድንም አትጠቅምም*፡፡ يَوْمَئِذٍ لَّا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَـٰنُ وَرَضِيَ لَهُ قَوْلًا

ነጥብ አንድ
“አማላጅ”
“ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአላህ ፈቃድ የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት፣ ሙዑሚን ናቸው፤ ለምሳሌ መላእክት፦
53፥26 *በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም*፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ
21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ *ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም*፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ

“ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ሃይለ-ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፤ ሌላው አማላጆች አላህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነብያት ናቸው፦
19፥87 *አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም*፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا
2፥255 *ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?* مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ
33፥7 *ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን*፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا