ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አላህ አቅኚ ወይስ አጥማሚ?


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው ።

“ሂዳያህ” هداية የሚለው ቃል “ምሪት” ማለት ሲሆን “ሁዳ” هُدً ማለትም “መሪ” ከሚለው ቃል የመጣ ነው፣ የሂዳያህ ተቃራኒ ደግሞ “ደላላህ” ضاله ሲሆን “ጥመት” ማለት ሲሆን “ደላል” ضلال ማለትም “ጠማማ” ከሚለው ቃል የመጣ ነው፣ አላህ በቁርአን ከገለጻቸው ስሞቹ መካከል “አል-ሃዲ” اللَهَادِ ሲሆን ትርጉሙ “አቅኚ” አሊያም “መሪ” ማለት ነው፦
22:54 አላህም እነዚያን ያመኑትን ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ “መሪ” لَهَادِ ነው፥
25:31 “መሪ” هَادِيًا እና ረዳትም በጌታህ በቃ።
ተብሎ
“ሃዲ” لَهَادِ ማለት “አቅኚ” ከሆነ የአቅኚ ተቃራኒ ቃል ደግሞ “ሙዲል” مُضِلٌّ ሲሆን ትርጉሙ “አሳሳች” አሊያም “አጥማሚ” ማለት ነው፣ በቁርአን አንድም ቦታ ላይ አላህ “ሙዲል” አይታወቅም፣ የሚሺነሪዎች ሙግት ዜሮ ገባ፣ ነገር ግን ሙዲል የተባለው ሸይጣን ነው፦
28:15 ይህ ከሰይጣን ሥራመሆኑ ነው፡፡ እርሱ ግልጽ “አጥማሚ” مُضِلٌّ ጠላት ነውና አለ፡፡

ሸይጣን አጥማሚነቱ የተገለጸው በስም መደብ “አጥማሚ” ተብሎ ነው፣ ይህም የሸይጣን መደበኛ ባህርይ ያስገነዝባል፣ ነገር ግን አላህ አቅኝነቱ የተገለጸው በስም መደብ “አቅኚ” ተብሎ ሲሆን ይህም የአላህን መደበኛ ባህርይ መሆኑ ያስገነዝባል፣ በቁርአን አላህ እደሚያጠም በግስ መደብ “ያጠማል” የሚል ቃል ተቀምጧል፣ ያ ምን ማለት ነው? ነጥብ በነጥብ በአጽንኦትና በአንክሮት እናየዋለን፦

ነጥብ አንድ
“ቅኑ እና ጠማማው መንገድ”
አላህ በቅድሚያ ለሰዎች ይህ ሃላል ነው ይህ ሃራም ነው፣ ይህ ኸይር ነው ይህ ሸር ነው፣ ይህ ሃቅ ነው ይህ ባጢል ነው ብሎ ቅኑን መንገድ ከጠማማምከቃሉ ያሳውቃል፣ ከዚያ ይህ አምኖ የመቀበል አሊያም ክዶ ማስተባበል የግለሰቡ ነጻ ምርጫ ነው፣ አላህ ክህደትን ሆነ በደልን፣ አመጽን ሆነ ወሰን ማለፍ ለባሮቹ ሆነ ለዓለማት አይፈልግም፤ ይህን ከራሱ መረዳት ይቻላል፦
92:12 ቅኑን መንገድ መግለፅ በኛ አለብን።
2:256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ፡፡
76:3 እኛ፥ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሐዲ ሲሆን መንገዱን መራ ነዉ፤ ገለጽንለት።
90:10 ሁለት መንገዶችም አልመራነውምን?
ተገለጠ18:29 እውነቱም፥ ከጌታችሁ ነው፤ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ፣ በላቸው፤
78:39 ይህ የተረጋገጠው ቀን ነው። የሻም ሰው ወደ ጌታው መመለስን ይይዛል።
39:7 ብትክዱ አላህ ከናንተ የተብቃቃ ነው። ለባሪያዎቹም ክህደትን አይወድም ፤ ብታመሰግኑም፤ እርሱን ይወድላችኋል፤
3:108 አላህም ለዓለማት በደልን የሚሻ አይደለም።
ነጥብ ሁለት
“መመራትና መጥመም”
የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፣ የሚመራ ከሆነ ደግሞ ለሌሎች ይተርፋል፣ የተሳሳተ ሰው መሳሳቱ ጉዳቱ ለራሱ ነው፣ የሚያሳስት ከሆነ ግን ሌሎችን ባሳሳተበት ይጠየቅበታል፣ አንድ ሰው በነጻ ምርጫው መጥመም መቅናት ይችላል፣ ይህ የመጀመሪያው ለተጠያቂነት የሚያበቃ ውሳኔ ነው፦
17:15 የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፤ አሊያምየተሳሳተም ሰው፣ የሚሳሳተው ጉዳቱ በርሷ ላይ ነው፤
10:108 የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በራሱ ላይ ነው፡፡በቅንነት
39:41 የተመራም ሰው ለነፍሱ ነው፤ የጠመመም ሰው የሚጠመው ጉዳቱ በርሷ ላይ ነው፤
2:175 እነዚያ ጥመትን ቅጣትንም በምሕረት የገዙ ናቸው፡፡ በእሳት ላይም ምን ታጋሽ አደረጋቸው!


ነጥብ ሶስትወደ
“አላህ የሚመራው”
አላህ የሚመራው ነጻ ምርጫውን ተጠቅሞ አላህ ለማግኘት የሚታገለውን እሾትና ጥማት ያለውን፣ ወደ አላህ በተውበት የሚመለሰውን፣ ውዴታውን የተከተለውን፣ ብርሃኑ የሚመጣውን፣ በአላህም የሚያምነውን ነው፦
29:69 እነዚያም በኛ መንገድ *የታገሉ* መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፤
13:27 አላህ የሚሻውንቀጥተኛው ያጠማል፤ *የተመለሰውንም* ሰው ወደርሱ ይመራል፥ በላቸው።
22:54 አላህም እነዚያን ያመኑትን ወደ መንገድ በእርግጥ መሪ ነው፥
64:11 በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን ይመራዋል፤
5:16 አላህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገዶች በርሱ ይመራቸዋል። በፈቃዱም ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል። ወደ ቀጥተኛም መንገድ ይመራቸዋል።


ነጥብ አራት
“አላህ የማይመራው”
@አላህ የማይመራው በነጻ ምርጫው በአላህና በመላክቱም፣ በመጽሐፎቹም፣ በመልክተኞቹም፣ በመጨረሻውም ቀን የካደውን ከሐዲ ነው፦
4:136 በአላህና በመላክቱም፣ በመጽሐፎቹም፣ በመልክተኞቹም፣ በመጨረሻውም ቀን የካደ ሰው፣ የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ።
16:104 እነዚያን በአላህ የማያምኑትን አላህ አይመራቸውም፤
39:3 አላህ እርሱ ውሸታም ከሐዲ የሆነን ሰው አያቀናም።
9:37 አላህም ከሐዲያን ሕዝቦችን አይመራም።
አንቀጾች2:264 አላህም ከሓዲያንን ሕዝቦች አይመራም፡፡
5:67 አላህ ከሐዲዎችን ሕዝቦች አያቀናምና።

@አላህ የማይመራው በአላህ ላይ ውሸትን የቀጠፈውንና ዝንባሌውን ተከትሎ የበደለውን በደለኛ ነው፦
6:144 በአላህ ላይ ውሸትንም ከቀጠፈ ሰው ይበልጥ በደለኛበደለኞች ማን ነው አላህ በደለኞችን ሕዝቦች አይመራም፡፡»
28:50 ከአላህም የኾነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፡፡ አላህ ሕዝቦችን አይመራምና፡፡
3:86 የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸዉ በኋላ የካዱን ሕዝቦች፥ አላህ አንዴት ያቀናል? አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች ።
9:109 አላህም በደለኞች ሕዘቦችን አይመራም።
በተዘነበሉም
@አላህ የማይመራው ከእውነት በአመጽ የተዘነበሉ ማለትም አያቀናምየሸሹ፣ በአመጽ በነፍሶቻቸው ያለውን ሁኔታ የለወጡ አመጠኞች ነው፦
61:5 ከእውነት ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው አላህም አመጠኞችን ሕዝቦች አያቀናም።
13:11 አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ፥ በነፍሶቻቸው ያለውን ሁኔታ እስከሚልውጡ ድረስ አይለውጥም፤
5:51 አላህ አመጠኞችን ሕዝቦች አያቀናም።
5:108 አላህም አመጠኞች ሕዝቦችን አይመራም።
ነጥብ አምስት
“አላህ የሚያጠመው”
አላህ የሚያጠመው ማለት ትርጉሙ አላህ ያላቀናው ማለትሂዳያህ ነው፣ ለምሳሌ አንድ ሰው የጸሐይ ብርሃን አልፈልግም ብሎ ወደቤት ቢገባ ጸሀይ ብርሃኗን ትነሳዋለች፣ ብርሃኗን ለፈለ ትሰጣለች ቢባል፣ አዳላች ማለት አይደለም፣ አንድ ሰው ሂዳያህ አልፈልግም ካለ አላህ አይሰጠውም ማለት ጠሟል ማለት ነው፣ ያ የጠመመውን ሰው አላህ በነጻ ምርጫው እስኪያምን ድረስ አላህ ያጠመዋል፣ አላህ እንዲህ ያለውን ከሃዲና ወሰን አላፊ አጥሞታል፦
14:27 “ከሐዲዎችንም” አላህ ያጠማቸዋል وَيُضِلُّ ፤
40:74 እንደዚሁ አላህ ከሀዲዎችን ያጠማል يُضِلُّ ።
40:34 አላህ እንደዚሁ ድንበር አላፊ፣ ተጠራጣሪ የሆነን ሰው ያጠማል يُضِلُّ ።

ማጠቃለያ
ሚሽነሪዎች የራሳቸው እያረረባቸው የሰውን ማማሰል ልማዳቸው ከሆነ ሰንበትበት አለ፣ ለመሆኑ ባይብል ላይ አምላክ አታላይ፤ አጥማሚና እንደተባለ ያውቃሉን ማጥመም እና ማቅናት የእርሱ ሥራ እንደሆነ ይናገራል፦
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ “ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው” አሳሳችይችላል?

ነቢዩም ቢታለል ያንን ያታለለው እግዚአብሔር ነው ይላል፤ ሕዝቅኤልን፣ ኤርሚያስን እና ኢሳይያስን ያታለለው እርሱ እንደሆነ እራሳቸው ይናገራሉ፦
ሕዝቅኤል 14:9፤ ነቢዩም ቢታለል ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ *ያታለልሁ* እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥
ኤርሚያስ 20:7 አቤቱ፥ *አታለልኸኝ* እኔም ተታለልሁ፥
ኤርሚያስ 4:10 እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ፥ አንተ ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ። ሰላም ይሆንላችኋል ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ *አታለልህ* አልሁ።እንደሆነ
ኢሳይያስ 63:17 አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን “አሳትኸን”? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።

ስህተት ሲፈጠር የሚያሳስተውና የሚሳሳተው ለአምላክ ያውቃሉን? እንዴት? ካሉ እግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎ ያሳስታል፦
ኢዮብ 12:16፤ ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ *የሚስተውና የሚያስተው* ለእርሱ ናቸው።
1ኛ ነገሥት 22:20-23 እግዚአብሔርም። ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው? አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ። እኔ አሳስተዋለሁ አለ። እግዚአብሔርም። በምን? ፤ እርሱም። ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ። እግዚአብሔርም። ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም፤ ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ። አሁንም። እነሆ፥ አለውእግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።


ከዚህ ሁሉ ግን የሚገርመው እራሱ እግዚአብሔር በሰይጣን መሳሳቱ ነው፦
ኢዮብ 2:3፤ እግዚአብሔርም ሰይጣንን። በውኑ ባሪእስከ ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም፤ በከንቱም አጠፋው ዘንድ አንተ በእርሱ ላይ ምንም “ብታሳስተኝ” וַתְּסִיתֵ֥נִי፥ እስከ አሁን ፍጹምነቱን ይዞአል።

“ብታንቀሳቅሰኝ” ብለው ያስቀመጡት የዕብራይስጡ ቃል “ታሲተኒ” וַתְּסִיתֵ֥נִי ሲሆን “ሱት” סוּת ማለትም “አሳሳተ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ለሃሰተኛ ነብይ ማሳሳት “የስቲአከ” יְסִֽיתְךָ֡ ማለትም “ቢያስትህ” በሚል መጥቷል፦
ዘዳግም 13.6 አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ יְסִֽיתְךָ֡፥

ይህ የቋንቋ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ ይህ እንተወውና “ታሲተኒ” וַתְּסִיתֵ֥נִי ማለት “ አማርኛ “ብታንቀሳቅሰኝ” እንደበሚለው እንውሰደውና ፈጣሪ እንዴት በፍጡር ይንቀሳቀሳል? ለዛው በሰይጣን? ማንቀሳቀስስ ምን ማለት ነው? ፈጣሪስ እንዴት ያሳስታል እንዴትስ ያጠማል?
እግዚአብሔር ክፉን መንፈስን፣ የስሕተትን አሠራር፣ ጨለማን እና ክሳትን እንደሚልክ ባይብልይላቸው ይናገራል፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 ምክንያት*እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
መዝሙር 105፥28 *ጨለማን ላከ* ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ።
መዝሙር 106፥15 የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን *ክሳትን ላከ*።

ይሄ ክፉም መንፈስ እንደ ኡቃቤ ከእግዚአብሔር ዘንድ እየተላከ ሳኦልን አሠቃየው፦
1ኛ ሳሙኤል 16፥14 የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ *ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው*።
1ኛ ሳሙኤል 18፥10 በነጋውም ሳኦልን *ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው*፥


እግዚአብሔር ሰዎች የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ይሰጣል፦
የሐዋርያት ሥራ 7፥42 እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ *የሰማይንም ጭፍራአሳልፎ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው*፥

እግዚአብሔር ሰዎች በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ *እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ይሰጣል፦እግዚአብሔርን
ሮሜ 1፥26 ስለዚህ *እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥28 ለማወቅ ባልወደዱት መጠን *እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ይሰጣል፦እስከ
ሮሜ 11፥8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን ዛሬ ድረስ ሰጣቸው* ተብሎ ተጽፎአል።

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦
ኢሳይያስ 29፥10 *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል*።

እግዚአብሔር ለጳውሎስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳይታበይ የሥጋው መውጊያ፥ እርሱምስለዚህም የሚጎስመው የሰይጣን መልእክተኛ ሰቶታል፦
2 ቆሮንቶስ 12፥7 በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ *የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ*፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።
ባይብል ላይ ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ኃይሉ ይገልጥበት ዘንድ እና ስሙ በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ነው፦
ዘጸአት 9፥16 ነገር ግን *ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ*።
ሮሜ 9፥17 መጽሐፍ ፈርዖንን፦ ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና።

“ቃሻህ” קָשָׁה ማለት “ማደንደን” ማለት ሲሆን እግዚአብሔር ፈርዖን የእስራኤል ልጆችን እንዳይለቅ እና ሙሴን እንዳይሰማ የፈርዖንን ልብ አደንድኖታል፦
ዘጸአት 7፥3 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ אַקְשֶׁ֖ה * ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ።
ዘጸአት 14፥4 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ וְחִזַּקְתִּ֣י * ፥ እርሱም ያባርራቸዋል፤
ዘጸአት 9፥12 እግዚአብሔርም *የፈርዖንን ልብ አደነደነ וַיְחַזֵּ֤ק *፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም።
ዘጸአት 14፥8 እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ *የፈርዖንን ልብ አደነደነ* וַיְחַזֵּ֣ק ፥

እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ልብን ስላደነደነው የፈርዖን ልብ ደነደነ፦
ዘጸአት 7፥13 *እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፥ የፈርዖን ልብ ደነደነ וַיֶּחֱזַק֙:*፥ አልሰማቸውምም።
ዘጸአት 7፥14 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ *የፈርዖን ልብ ደነደነ*፥ ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ።
ዘጸአት 9፥7 ፈርዖንም ላከ፥ እነሆም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አልሞተም። *የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ*፥ ሕዝቡንም አልለቀቀም።

እውን ፈርዖን ተጠያቂ ነውን? ልቡንስ ካደነደነው ህዝቤን ልቀቅ ብሎ ሙሴና አሮንን መላክ ለምን አስፈለገ? ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ ብሎ ፈርዖንን መውቀስ ለምን አስፈለገ? በዚህ አላበቃም፤ እግዚአብሔር የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን መንፈሱን አደንድኖታል፦
ዘዳግም 2፥30 የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ *እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና*፥ልቡንም አጸንቶታልና


ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

ማቴዎስ 28፥19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

መግቢያ
ከላይ የጠቀስኩት ጥቅስ ብዙ ጊዜ ሥላሴአውያን ለሥላሴ አስተምህሮት ይደግፋል ብለው አዘውትረው ከሚጠቅሷቸው ተወዳጅ ጥቅሶች መካከል አንዱ ነው፣ ይህ ጥቅስ ከመነሻው እውን የኢየሱስ ንግግር ነበርን? ባይሆንስ ሥላሴን ያሳያልን? ለሚለው ሙግት ስለ ማቴዎስ ወንጌል መንደርደሪያ አይተን ወደ ፍሬ ሃሳቡ መግባት ይቻላል፣ ከሃዋርያት መካከል አንዱ ማቴዎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ለዕብራውያን ከ 46-50 AD በሚገመት ጊዜ ውስጥ ጽፎላቸው እንደነበረና ያ ጽሁፍ የት እንደገባ እንደማይታወቅና ብዙ ጊዜ የቂሳርያው ኤጲጵ ቆጶስ አውሳቢዮስ ከዚህ ዕብራይስጥ መዝገብ ላይ ይጠቅስ እንደነበረ ምሁራን ይናገራሉ፣ በመቀጠል የሄራፕሊሱ ኤጲጵ ቆጶስ ፓፒያስ በማቴዎስ ስም የማቴዎስ ወንጌል ኮይኔ በተባለ ግሪክ ቋንቋ እንዳዘጋጀ ያትታሉ፣ አበይት ምሁራን የማቴዎስ ወንጌል የተጻፈው ከ 80-90 AD ነው ብለው ሲናገሩ ንኡሳን ምሁራን ደግሞ ከ80-110 AD የተጻፈው ነው ይላሉ፣ ዋቢ መጽሃፍት ይመልከቱ፦
1. Harrington, Daniel J. (1991). The Gospel of Matthew. Liturgical Press.p. 8
2. Ehrman, Bart D. (1999). Jesus: Apocalyptic Prophet of the New Millennium.p. 43.
3. Kupp, David D. (1996). Matthew's Emmanuel: Divine Presence and God's People in the First Gospel.

1.የታሪክ ሙግት
ከሃዋርያት መካከል አንዱ ማቴዎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ለዕብራውያን ከ 46-50 AD በሚገመት ጊዜ ውስጥ ጽፎላቸው እንደነበረና ማቴዎስ 28፥19-20 ላይ ኢየሱስ፦ *እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው* ሳይሆን ያለው *እንግዲህ ሂዱና ህዝቡን ሁሉ በስሜ ደቀ መዛሙርት አድርጉ* ነው ያለው ብሎ ከዕብራይስጥ መዝገብ ላይ ብዙ ጊዜ የቂሳርያው ኤጲጵ ቆጶስ አውሳቢዮስ ይጠቅሳል፣
በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም በግሪኩ እደ-ክታብ*manu-scrip* ላይ እንጂ በመጀመሪያው ማቴዎስ ኢየሱስ ተናገረ በተባለው ላይ የለም፣ ከዚያም ባሻገር ከ80-110 AD ተጻፈ በሄራፕሊሱ ኤጲጵ ቆጶስ ፓፒያስ ተጻፈ የተባለው ኦርጂናል ስረ-መሰረት*Autograph* የለም: አሁን ያለው ቅጂ ብቻ ነው። ዋቢ መጽሃፍት ይመልከቱ፦
1. ”Black’s Bible Dictionary The Interpreters Dictionary of the Bible, 1962, page 351
2.The Anchor Bible Dictionary, Vol. 1, 1992, page 585:
3. The International Standard Bible Encyclopedia, Vol. 4, page 2637,
4.The Tyndale New Testament Commentaries, I, 275: i Secondly
2. የሰዋስው ሙግት
ሁሉም ክርስቲያኖች ባይሆኑም አንዳንድ የዋህ ክርስቲያኖች፦ *በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም* ተብላልና *ስም* የሚለው በነጠላ መጠቀሙ አንድ አምላክ መሆናቸውን ያሳያሉ ብለው በደረቁ ሲነታረኩ ይሰማል፣ ይህ አነጋገራቸው አንደኛ አምላክ በስም፣ በግብር፣ በአካል ሶስት ነው ከሚሉት ከመሰረታዊ አስተምህሮታቸው ጋር ይጣረሳል፣ ሁለተኛ *ስም* የሚለው በተለያየ አካላት ላይ ነጠላ መሆኑ አንድ አካልን አሊያም አንድ አምላክን ያሳያል ያለህ ማን ነው? ሲቀጥል በየትኛው ሰዋስው ነው ስሞች ተብሎ የሚባለው? በእኔና በባለቤቴ ስም ይህን አበረክታለው እንጂ በእኔና በባለቤቴ ስሞች አይባልም፣ ይህን የሰዋስው ሙግት ከራሳችሁ ባይብል ተመልከቱ፦
ዘፍጥረት 5፥2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። *ስማቸውንም* በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው።
ዘፍጥረት 25፥13 የእስማኤልም የልጆቹ *ስም* በየስማቸውና በየትውልዳቸው እንዲህ ነው፤
ዘፍጥረት 36፥10 የዔሳው ልጆች *ስም* ይህ ነው፤
ዘፍጥረት 46፥8 ወደ ግብፅም የገቡት የእስራኤል ልጆች *ስም* ይህ ነው፥
ዘፍጥረት 48፥6 ከእነርሱም በኋላ የምትወልዳቸው ልጆች ለአንተ ይሁኑ፤ በርስታቸው በወንድሞቻቸው *ስም* ይጠሩ።
ዘፍጥረት 48፥16 ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም *ስም* በእነርሱ ይጠራ፤

አዳምና ሄዋን፣ የእስማኤልም የልጆቹ፣ የዔሳው ልጆች፣ የእስራኤል ልጆች፣ አብርሃምና ይስሃቅ የተለያዩ ሰዎች ሆነው ነገር ግን ስም እንጂ ሶሞች የሚል አልተቀመጠም፥ ስም ነጠላ ሆኖ መቀመጥ አንድ አምላክ የሚለውን ቢገልጽማ እነዚህ ሰዎች ተጨፍልቀው አንድ አምላክ ይሆኑ ነበር፣ ልጨምርላች ሁ የአህዛብ አማልክት ብዙ ሲሆኑ ስም በሚል ነጠላ ቃል ተጠቅሟል፦፦
ዘጸአት 23፥13 ያልኋችሁንም ነገር ሁሉ ጠብቁ፤ የሌሎችንም አማልክት *ስም* አትጥሩ፥ ከአፋችሁም አይሰማ።
ኢያሱ 23፥7 በእናንተ መካከል ወደ ቀሩት ወደ እነዚህ አሕዛብ አትግቡ የአማልክቶቻቸውንም *ስም* አትጥሩ፥
ዘዳግም 18፥20 ነገር ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን በስሜ በድፍረት የሚናገር ወይም በሌላ አማልክት *ስም* የሚናገር ነቢይ፥ እርሱ ይገደል።

የሌሎችንም አማልክት ስሞች ሳይሆን ያለው ስም በነጠላ ነው፣ ታዲያ የአህዛብ አማልክት አንድ አምላክ ነበሩ? ይህ ውሃ የሚያነሳ ሙግት አይደለም።
3. የአውድ ሙግት
መቼም ይህን ጥቅስ ኢየሱስ እንዳልተናገረው ቅቡል ቢሆንም ሙግቱን ለማጥበብ እርሱ ተናገረው እንበል ታዲያ የቱ ጋር ነው አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው ያለው? አሊያም አንዱ አምላክ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ነው ያለው? አብ እግዚአብሔር ተብሏል፣ ወልድ ኢየሱስ ተብሏል፣ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ መንፈስ ተብሏል፣ ያ የሚያሳየው አብ ብቻውን አንድ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ነው፦
2ኛ ቆሮ 13፥14 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

በተለይ ግሪኩ እግዚአብሔርን ከኢየሱስና ከመንፈስ ቅዱስ ለመለየት ካይ καὶ *እና* የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፣ ያ ማለት እግዚአብሔር የሚባለው አብ ብቻ እንጂ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ናቸው የሚል የለም፦
1ኛ ቆሮ 12፥4-6 የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።

መንፈስ ግን አንድ ነው ሲል መንፈስ ቅዱስን፣ ጌታ ግን አንድ ነው ሲል ወልድን፣ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው ሲል አብን ያመለክታል ይሉናል፣ ታዲያ ዋናው ነጥባችን ይህ አይደል? አንዱ እግዚአብሔር አብ ብቻ ነው፦
1ኛ ቆሮ 8፥4-6 *ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ* እንደሌለ እናውቃለን።..,ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን *አንድ አምላክ አብ* አለን፥
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ* የሁሉም *አባት* አለ።

4. የስነ-አምክኖ ሙግት
አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ ላይ መደርደራቸው በስልጣን እኩል አሊያም አንድ አምላክ መሆናቸውን ያመለክታል ይላሉ፣ እኛ ደግሞ አያመለክትም እንላለን ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንደተደረደሩ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ኢየሱስና መላእክትም ተደርድረዋል፦
1ኛ ጢሞ 5፥21 እነዚህን ያለ መዘንበል እንድትጠብቅ፦
በእግዚአብሔርና
በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ
በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።

ታዲያ ለምን መላእክት በስልጣን እኩል አሊያም አንድ አምላክ አልሆኑም?


ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
እርግጠኝነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ፣ በጣም አዛኝ በሆነው።

15:99 “እርግጠኝነቱም” الْيَقِينُ እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን አምልከው፡፡

መግቢያ
ቁርአን የመጨረሻይቱ ዓለም፣ ሀገር እና ህይወት ለሚያረጋግጡት መሪ፣ እዝነት እና ብስራት ነው፦
31:1 አ.ለ.መ. ይህች ጥበብ ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፤ ለበጎ አድራጊዎች መሪና እዝነት ስትሆን፤ ለነዚያ ሶላትን አስተካክለው ለሚያደርሱት፤ ዘካንም ለሚሰጡት፤ እነሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነርሱ “የሚያረጋግጡ” يُوقِنُونَ ለሆኑት።
2:1-4 አ.ለ.መ ይህ መጽሐፍ ከአላህ ለመኾኑ ጥርጥር የለበትም፤ ለፈራህያን መሪ ነው፡፡ ለነዚያ በሩቁ ነገር የሚያምኑ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚቸሩ ለኾኑት፤ ለእነዚያም ወደ አንተ በተወረደውና ከአንተ በፊትም በተወረደው የሚያምኑ በመጨረሻይቱም ዓለም እነርሱ “የሚያረጋግጡ” يُوقِنُونَ ለኾኑት መሪ ነው፡፡
27:1 ጠ. ስ. ይህቺ ከቁር አኑና ከገላጩ መጽሐፍ አንቀጾች ናት። ለምእመናን መሪና ብስራት ናት። ለነዚያ ሶላትን ለሚሰግዱት ዘካንም ለሚሰጡት እነሱም በመጨረሻይቱ ሕይወት እነሱ “የሚያረጋግጡት” يُوقِنُونَ ለሆኑት።

ታዲያ ያ ናፋቂውን የመጨረሻይቱን ሀገር፣ ዓለም እና ህይወት በምንድን ነው የምናረጋግጠው? ስንል ቁርአን በአፅንኦትና በአንክሮት ስለ “የቂን” يَقِين ይናገራል፤ “የቂን” ማለት “እርግጠኝነት”certainity” ማለት ነው፦
15:99 “እርግጠኝነቱም” الْيَقِينُ እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን አምልከው፡፡
74:46 በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፤ “እርግጠኛው” الْيَقِينُ እስከመጣ ድረስ።

“የቂን” ደግሞ በቁርአን በሶስት ይከፈላል፤ እነርሱም፦

ነጥብ አንድ
“ዒልመል የቂን”
አምላካችን አላህ በንግግሩ ስለ የመጨረሻይቱን ሀገር፣ ዓለም እና ህይወት ያሳወቀን እርግጠኛነት “ዒልመል የቂን” عِلْمَ الْيَقِينِ “እርግጠኛ ዕውቀትን” ይባላል፤ የመጨረሻይቱን ሀገር፣ ዓለም እና ህይወት እርግጠኛ የሆነው አላህ በነገረን እውቀት ነው፦
102:5 በእውነቱ የሚጠብቃችሁን “እርግጠኛ ዕውቀትን” عِلْمَ الْيَقِينِ ብታውቁ ኖሮ፤ ባልዘናጋችሁ ነበር።
ነጥብ ሁለት
“ዐይነል የቂን”
የዓለማቱ ጌታ አላህ “እርግጠኝነቱም” الْيَقِينُ እስኪመጣህ ድረስ” ብሎ ቃል የገባው የመጨረሻይቱን ሀገር፣ ዓለም እና ህይወት ደርሶ በአይናችን ስናረጋግጥ ያ እርግጠኝነት “ዐይነል የቂን” عَيْنَ الْيَقِينِ “እርግጠኛ ማየት” ይባላል፤ በጆሮአችን የተነገረን እውቀት በአይን ማረጋገጥ ሁለተኛው የእርግጠኝነት ደረጃ ነው፦
102:7 ከዚያም “እርግጠኛን ማየት” عَيْنَ الْيَقِينِ ታዩዋታላችሁ፤

ነጥብ ሶስት
“ሐቁል የቂን”
የኢብራሒም አምላክ አላህ እርግጠኛ ለነበሩት ባሮቹ ጀነትን ለከሃድያን ደግሞ ጀሃነምን በአምስቱ የስሜት ህዋሳት እንዲያጣጥሙት ሲያደር ያ የቂን “ሐቁል የቂን” حَقُّ الْيَقِين “እርግጠኛ እውነት” ይባላል፤ ይህ እርግጠይነት በአይናችም ካየነው ባሻገር በህዋሳችን የምናጣጥምበት ሶስተኛው የእርግጠኝነት ደረጃ ነው፦
56:94-95 በገሃነም መቃጠልም አለው። ይህ እርሱ “እርግጠኛ እውነት” حَقُّ الْيَقِينِ ነው።

ማጠቃለያ
አምላካችን አላህ ዘካን የሚለግሱትን “ራዚቂን” رَّٰزِقِين “ሰጪዎች”፣ ሶላትን አስተካክለው የሚቆሙትን “ሙቂሚን” مُّقِيم “ቋሚዎች”፣ ኢህሳን ኖሮአቸው በጎ የሚሰሩትን “ሙህሲን” مُحْسِن “በጎ አድራጊዎች”፣ ተቅዋ ኖሮአቸው የሚፈሩትን “ሙተቂን” مُتَّقِين “ፈራህያን”፣ ኢማን ያላቸውን ደግሞ “ሙዑሚን” مُؤْمِن “ምእመናን” ብሎ ብዙ አንቀፆች ላይ እንደሚያወሳቸው ሁሉ “ሙቂኒን” مُّوقِنِين የሚባሉትን ባሮቹን ያነሳቸዋል፤ “ሙቂኒን” ማለት “እርግጠኞች” ወይም “አረጋጋጮች” ማለት ነው፤ የመጨረሻይቱን ሀገር፣ ዓለም እና ህይወት ዱንያ ላይ እያሉ በእውቀት የሚያረጋግጡ የዓርሹ ጌታ ባሮች ናቸው፦
6:75 እንደዚሁም ኢብራሂምን እንዲያውቅና “ከአረጋጋጮቹም” الْمُوقِنِينَ ይኾን ዘንድ የሰማያትንና የምድርን መለኮት አሳየነው፡፡
26:24 ሙሳ «የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ ነው፡፡ “የምታረጋግጡ” مُوقِنِينَ ብትኾኑ ነገሩ ይህ ነው» አለው፡፡
32:12 አመጠኞችም በጌታቸው ዘንድ እራሳችውን ያቀረቀሩ ኾነው ፦ጌታችን ሆይ አየን፤ ሰማንም፤ መልካምን እንሰራለንና ወደ ምድረ ዓለም መልሰን፤ እኛ “አረጋጋጮች” مُوقِنُونَ ነን፤ የሚሉ ሲሆኑ ብታይ ኖሮ አስድንጋጪን ነገር ታይ ነበር፤

አላህ ሙቂኒን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጥበብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥269 *ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብንም የሚሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠ*፡፡ የአእምሮዎች ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡ يُؤْتِى ٱلْحِكْمَةَ مَن يَشَآءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ ٱلْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِىَ خَيْرًۭا كَثِيرًۭا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ

መግቢያ
“ሐኪም” حَكِيم ማለት “ጥበበኛ” ማለት ሲሆን “ሓኪም” حَٰكِمِين ማለት ደግሞ “ፈራጅ” ማለት ነው፤ ሁለቱም “ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” “ተጠበበ” ከሚል ግስ የመጡ ናቸው፤ “ሒክማህ” حِكْمَة ማለት “ጥበብ” ማለት ሲሆን “ሑክም” حُكْم ደግሞ “ፍርድ” ማለት ነው፤ ጥበብ እና ፍርድ የጥበበኛው እና የፈራጁ አላህ ባህርያት ናቸው፤ አላህ እጅግ በጣም ጥበበኛ ነው፦
28፥9 «ሙሳ ሆይ! እነሆ እኔ አሸናፊው *ጥበበኛው* አላህ ነኝ፡፡ يَٰمُوسَىٰٓ إِنَّهُۥٓ أَنَا ٱللَّهُ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
3፥6 እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው *ጥበበኛው* ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى يُصَوِّرُكُمْ فِى ٱلْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَآءُ ۚ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

አላህ ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብን ከአላህ የተሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጦታል፦
2፥269 *ለሚሻው ሰው ጥበብን ይሰጣል፤ ጥበብንም የሚሰጠው ሰው ብዙን መልካም ነገር በእርግጥ ተሰጠ*፡፡ የአእምሮዎች ባለቤቶች እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡ يُؤْتِى ٱلْحِكْمَةَ مَن يَشَآءُ ۚ وَمَن يُؤْتَ ٱلْحِكْمَةَ فَقَدْ أُوتِىَ خَيْرًۭا كَثِيرًۭا ۗ وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّآ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَٰبِ

አላህ ጥበብን ለሰው ልጆች በዐቅል እና በነቅል ይሰጣል፤ እነዚህ ሁለት የጥበብ ጭብጦችን ነጥብ በነጥብ እንይ፦

ነጥብ አንድ
“ዐቅል”
“ዐቅል” عقل ማለት “ግንዛቤ”Metacognition” ማለት ሲሆን አላህ በቁርአን “ለዐለኩም ተዕቂሉን” لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُون ይለናል፦
12:2 በእርግጥ እኛ *ትገነዘቡ ዘንድ* ዐረብኛ ቁርአን ሲሆን አወረድነው። إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ قُرْءَٰنًا عَرَبِيًّۭا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
2:242 እንደዚሁ አላህ አንቀጾቹን *ትገነዘቡ ዘንድ* ለእናንተ ያብራራላችኋል፡፡ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

“ትገነዘቡ ዘንድ” የሚለው ቃላት በአጽንዖትና በእንክሮት ልናጤነው የሚገባ ሃይለ ቃል ነው፤ የሰው ልጅ “አዕምሮ” እራሱ “ዐቅል” ይባላል፤ ዐቅል የጥበብ ተውህቦ”faculty” ነው፤ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ጥበብን ይወዳል፤ “ፊሎሶፍይ” φιλοσοφία የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ፊሎስ” φίλος “ፍቅር” እና “ሶፎስ” σοφός “ጥበብ” ሲሆን “የጥበብ ፍቅር” ማለት ነው፤ ይህም ሥነ-ጥበብ በውስጡ፦
ሥነ-አመክንዮ”logic”፣ ሥነ-ኑባሬ”Ontology”፣
ሥነ-እውነት”metaphysics”፣
ሥነ-ዕውቀት”epistemology”፣
ሥነ-መለኮት”theology”፣
ሥነ-ምግባር”ethics”፣
ሥነ-ውበት”esthetics”፣
ሥነ-መንግሥት”politics”፣
ሥነ-ቋንቋ”Linguistics”
የመሳሰሉት እሳቦት ይዟል። ጥበብ”craft” ሥነ-ጥበብ፣ እደ-ጥበብ፣ ኪነ-ጥበብና አውደ-ጥበብ ለአሉታዊ ነገር ከተጠቀሙበት ምግባረ-እኩይ”witch-craft” ሲሆን በአውንታዊ ከተጠቀምንበትምግባረ-ስናይ”art-craft” መማሪያም ነው፤ አላህ፦ “አፈላ ተዕቂሉን” أَفَلَا تَعْقِلُون ይለናል፦
21:10 *ክብራችሁ በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደ እናንተ በእርግጥ አወረድን፤ አትገነዘቡምን*? لَقَدْ أَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ كِتَٰبًۭا فِيهِ ذِكْرُكُمْ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

“አትገነዘቡምን?” የሚለው ቃላት በአጽንዖትና በእንክሮት ልናጤነው የሚገባ ሃይለ ቃል ነው፤ ቁርአን ክብራችን በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ነው፤ አዎ የሰው ልጆች ሊከብሩበት የሚችሉበት ጥበብ ይዟል።
ነጥብ ሁለት
“ነቅል”
“ነቅል” نفل ማለት “አስተርዮ”epiphany” ማለት ሲሆን “ወሕይ” وَحْى ነው፤ አምላካችን አላህ ወደ ነብያችን””ﷺ”” ጥበብን አውርዷል፦
4፥113 አላህም በአንተ ላይ መጽሐፍንና *ጥበብን* አወረደ፡፡ *የማታውቀውንም ሁሉ አስተማረህ*፡፡ የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው፡፡ وَأَنزَلَ ٱللَّهُ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَعَلَّمَكَ مَا لَمْ تَكُن تَعْلَمُ ۚ وَكَانَ فَضْلُ ٱللَّهِ عَلَيْكَ عَظِيمًۭا

ይህም ጥበብ ክብራችን በውሥጡ ያለበትን መጽሐፍ ቁርአን ነው፤ ቁርአን ጥበብ የተሞላ መጽሐፍ ነው፦
10፥1 “አሊፍ ላም ራ” ይህቺ *ጥበብ* ከተመላው መጽሐፍ ከቁርኣን አንቀጾች ናት፡፡ الٓر ۚ تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْحَكِيمِ
30፥2 ይህች *ጥበብ* ከተመላው መጽሐፍ አንቀጾች ናት፡፡ تِلْكَ ءَايَٰتُ ٱلْكِتَٰبِ ٱلْحَكِيمِ
36፥2 *ጥበብ* በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡ وَٱلْقُرْءَانِ ٱلْحَكِيمِ

ስለዚህ ክብራችን በውስጡ ያለበትን ይህንን ጥበብ የተሞላ መጽሐፍ መገንዘብ ግድ ይላል ማለት ነው፤ የእሳት ሰዎች “የምናገናዝብ” በነበርን ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልሆን ነበር ብለው ይፀፀታሉ፦
67:10 የምንሰማ ወይንም *”የምናገናዝብ”* በነበርን ኖሮ በነዳጅ እሳት ጓዶች ውስጥ ባልሆን ነበር ይላሉ። وَقَالُوا۟ لَوْ كُنَّا نَسْمَعُ أَوْ نَعْقِلُ مَا كُنَّا فِىٓ أَصْحَٰبِ ٱلسَّعِيرِ


ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
የአላህ ቤት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

106፥3 ስለዚህ *የዚህን ቤት ጌታ ያምልኩ*፡፡ فَلْيَعْبُدُوا رَبَّ هَـٰذَا الْبَيْتِ

አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾች ላይ "አምልኩኝ" እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥82 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

አላህ የሚመለክበት ቦታ ደግሞ የእርሱ ቤት እንደሆነ ለማመልከት ለኢብራሂምም፦ "በይቲይ" بَيْتِىَ ማለትም "ቤቴ" በማለት ይናገራል፦
22:26 ለኢብራሂምም፦ *”የቤቱን” ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በእኔ ምንንም አታጋራ፤ ”ቤቴንም”* ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ”ባልነው ጊዜ አስታውስ”*። وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًۭٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ

አላህ፦ "በእኔ ምንም አታጋራ" ማለቱ አላህ ነባቢ መለኮት መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ይህም ቤቱ በመካ የሚገኝ የመጀመሪያው እና ጥንታዊ ቤት ነው፦
3:96 ለሰዎች *”መጀመሪያ የተኖረዉ ቤት”* ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው። إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍۢ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِى بِبَكَّةَ مُبَارَكًۭا وَهُدًۭى لِّلْعَٰلَمِينَ
22፥29 ከዚያም ትርፍ አካላቸውንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፡፡ ስለቶቻቸውንም ይሙሉ፤ *በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ*፡፡ ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ
ይህ ቤት ታላቁ ቤት ስለሆነ "በይተል ሐረም" ْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ ማለትም "የተከበረው ቤት" ይባላል፤ አላህ የሚመለክበት ቤት ስለሆነ “መስጂደል ሐረም” الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ማለት “የተከበረ መስጊድ”  ይባላል፦
5፥2 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህ ክልክል ያደረጋቸውን ምልክቶች የተፈቀዱ አታድርጉ፤ የተከበረውንም ወር በመጋደል አትድፈሩ፡፡ ወደ መካ የሚነዱትን መስዋዕትና የሚታበቱባቸውንም ገመዶች ከጌታቸው ችሮታንና ውዴታን ፈልገው *ወደ ተከበረው ቤት* አሳቢዎችንም ሰዎች አትንኩ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تُحِلُّوا۟ شَعَٰٓئِرَ ٱللَّهِ وَلَا ٱلشَّهْرَ ٱلْحَرَامَ وَلَا ٱلْهَدْىَ وَلَا ٱلْقَلَٰٓئِدَ وَلَآ ءَآمِّينَ ٱلْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ يَبْتَغُونَ فَضْلًۭا مِّن رَّبِّهِمْ وَرِضْوَٰنًۭا
2፥149 ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን *ወደ ተከበረው መስጊድ* አግጣጫ አዙር፡፡ وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ

"መሥጂድ" مَسْجِد የሚለው ቃል "ሠጀደ" ማለትም "ሰገደ" سَجَدَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መስገጃ" ማለት ሲሆን "ሡጁድ" سُّجُود ደግሞ "ስግደት" ማለት ነው፤ በምድር ላይ ያሉት መስጊዶች ሁሉ የአላህ ብቻ ናቸው፤ በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አንገዛም፤ ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ እናወድሰዋለን፤ በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ እናጠራለን፦
72፥18 *እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው። በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ"* ማለትም፡፡ وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا
24፥36 *አላህ እንድትከበርና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ አወድሱት፡፡ በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ*፡፡ فِى بُيُوتٍ أَذِنَ ٱللَّهُ أَن تُرْفَعَ وَيُذْكَرَ فِيهَا ٱسْمُهُۥ يُسَبِّحُ لَهُۥ فِيهَا بِٱلْغُدُوِّ وَٱلْـَٔاصَالِ

"ቤቶች" የሚለው ይሰመርበት፤ መስጊዶች ሁሉ የአላህ ቤቶች ናቸው፤ ታላቁ ቤት ንድፉ “አንኳር” ስለሆነ “ከዕባህ” ተብሏል፤ “ከዕባህ” الكعبة ማለት “አንኳር“The Cube” ማለት ነው፤ አንኳር "ምልዓት" ነው፤ ምልአት ባለ ሦስት ቅጥ ነው፤ ይህም ቁመት፣ ርዝምት እና ስፋት ነው፦
5፥97 *ከዕባን የተከበረውን ቤት፤* ክልክል የኾነውንም ወር፣ መስዋዕቱንና ባለ ምልክቶቹንም መንጋዎች አላህ ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ፡፡ جَعَلَ ٱللَّهُ ٱلْكَعْبَةَ ٱلْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ قِيَٰمًۭا لِّلنَّاسِ وَٱلشَّهْرَ ٱلْحَرَامَ وَٱلْهَدْىَ وَٱلْقَلَٰٓئِدَ

ሁላችንም ቂብላችን ወደዚህ ቤት ነው፤ “ቂብላህ” قِبْلَة የሚለው ቃል “አቅበለ” أَقْبَلَ ማለትም “ተቀጣጨ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “አቅጣጫ”direction” ማለት ነው፤ የትም ቦታ ሆነን ለአንድነት ለአላህ የምንሰግደው ወደ ከዕባህ ነው፦
2፥149 ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን *ወደ ተከበረው መስጊድ* አግጣጫ አዙር፡፡ وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ

”ወደ” ከዕባህ ”ለ” ከዕባህ መስገድ ይለያያል፤ "ወደ" ምድር መስገድ እና "ለ" ምድር መስገድ አንድ ነው? "ለ" እና "ወደ" የተባሉት መስተዋድዶች ትርጉሙን ሁለት ያረጉታል፤ ስግደታችን ”ለ”አላህ ሲሆን አቅጣጫው ”ወደ” ከዕባህ ነው፤ የምናመልከውም ቤቱን ሳይሆን የቤቱን ጌታ አላህን ብቻ ነው፦
106፥3 ስለዚህ *የዚህን ቤት ጌታ ያምልኩ*፡፡ فَلْيَعْبُدُوا رَبَّ هَـٰذَا الْبَيْتِ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩ
ቂብላህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2:148 *“ለሁሉም እርሱ የሚያዞርባት አግጣጫ አለችው”*። وَلِكُلٍّ وِجْهَةٌ هُوَ مُوَلِّيهَا

“ቂብላህ” قِبْلَة የሚለው ቃል “አቅበለ” أَقْبَلَ ማለትም “ተቀጣጨ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “አቅጣጫ”direction” ማለት ነው፤ ይህም "የውዳሴ ነጥብ"point of adoration" ነው፦
10፥87 ወደ ሙሳና ወደ ወንድሙ፡- «ለሕዝቦቻችሁ *በምስር ቤቶችን ሥሩ፡፡ ቤቶቻችሁንም መስገጃ አድርጉ*፡፡ ሶላትንም በደንቡ ስገዱ፡፡ ለሙሳም ምእምናኖቹንም አብስር» ስንል ላክን፡፡ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ وَأَخِيهِ أَن تَبَوَّآ لِقَوْمِكُمَا بِمِصْرَ بُيُوتًا وَاجْعَلُوا بُيُوتَكُمْ قِبْلَةً وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ

"መስገጃ" ለሚለው ቃል የተቀመጠው "ቂብለተን" قِبْلَةً ሲሆን "መቀጣጫ" ማለት ነው፤ ስለዚህ ቂብላህ ማለት ለመስገጃ መቀጣጫ ነው፦
2፥149 ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን *ወደ ተከበረው መስጊድ* አግጣጫ አዙር፡፡ وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ

ቁርኣን ከመውረዱ በፊት እና ነብያችን"ﷺ" ነብይ ሆነው ከመላካቸው በፊት አይሁዳውያን የሚቀጣቹት የነበረው ወደ መስጂደል አቅሳ ነው፦
17:1 ያ ባሪያውን *“ከተከበረው መስጊድ” ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ “ሩቁ መስጊድ”* በሌሊት ውስጥ ያስኼደው ጥራት ይገባው፤ ከታምራቶቻችን ልናሳየው አስኼድነው ፤ እነሆ እርሱ አላህ ሰሚው ተመልካቺው ነው። سُبْحَٰنَ ٱلَّذِىٓ أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِۦ لَيْلًۭا مِّنَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ إِلَى ٱلْمَسْجِدِ ٱلْأَقْصَا ٱلَّذِى بَٰرَكْنَا حَوْلَهُۥ لِنُرِيَهُۥ مِنْ ءَايَٰتِنَآ ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
2:145 እነዚያንም መጽሐፍን የተሰጡትን በአስረጅ ሁሉ ብትመጣቸው *“ቂብላህን” አይከተሉም፡፡ አንተም “ቂብላቸውን” ተከታይ አይደለህም፡፡ ከፊላቸውም የከፊሉን “ቂብላ” ተከታይ አይደሉም*። وَلَئِنْ أَتَيْتَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ بِكُلِّ ءَايَةٍۢ مَّا تَبِعُوا۟ قِبْلَتَكَ ۚ وَمَآ أَنتَ بِتَابِعٍۢ قِبْلَتَهُمْ ۚ وَمَا بَعْضُهُم بِتَابِعٍۢ قِبْلَةَ بَعْضٍۢ ۚ وَلَئِنِ ٱتَّبَعْتَ أَهْوَآءَهُم مِّنۢ بَعْدِ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ ۙ إِنَّكَ إِذًۭا لَّمِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

"ቂብለተሁም" قِبْلَتَهُمْ የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ አይሁዳውያን ወደዚህ ቤት ይጸልያሉ ወይም ይሰግዳሉ፦
1ኛ ነገሥት 8፥49 ለስምህም *”ወደ ሠራሁት ቤት ቢጸልዩ”፥ ጸሎታቸውንና ልመናቸውን በማደሪያህ በሰማይ ስማ*፥
መዝሙር 5:7 እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት *”ወደ ቤትህ” እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት ”ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ”*።
መዝሙር 138:2 *”ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ”*፤

ለዚያ ነው አምላካችን አላህ ለሁሉም እርሱ የሚያዞርባት አግጣጫ አለችው ብሎ የነገረን፦
2:148 *“ለሁሉም እርሱ የሚያዞርባት አግጣጫ አለችው”*። وَلِكُلٍّ وِجْهَةٌ هُوَ مُوَلِّيهَا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አደም እና ሐዋ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው ።


"አደም" آدَم የሚለው ቃል 25 ጊዜ በቁርኣን የመጣ ሲሆን "አዳም" ማለትም "አፈር" "መሬት" "ቀይ" ወይም "ሰው" ከሚል ሴማዊ ቃል የመጣው ነው፤ አላህ አደምን የፈጠረው ከምድር አፈር ነው፦
15:28 ጌታህም ለመላእክት ባለጊዜ አስታውስ፡፡ *እኔ ሰውን ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጭቃ እፈጥራለሁ*፡፡ وَإِذْ. قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن صَلْصَالٍ مِّنْ حَمَإٍ مَّسْنُونٍ
38:71 ጌታህ «ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي خَالِقٌ بَشَرًا مِّن طِينٍ
71:17 አላህም *ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ*። وَاللَّهُ أَنبَتَكُم مِّنَ الْأَرْضِ نَبَاتًا
71፥18 *ከዚያም በውስጧ ይመልሳችኋል። ማውጣትንም ያወጣችኋል*። ثُمَّ يُعِيدُكُمْ فِيهَا وَيُخْرِجُكُمْ إِخْرَاجًا
20፥55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ፤ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፤ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን*። مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ

አላህ ምድር ላይ የተለያየ ከለር አብቅሏል፤ ከአፈር ብዙ ዓይነቶችም ቀለማት አድርጎ አበቀለን፦
50፥7 ምድርንም ዘረጋናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ጋራዎችን ጣልንባት፡፡ በውስጧም ከሚያስደስት *"ዓይነት ሁሉ አበቀልን"*፡፡ وَٱلْأَرْضَ مَدَدْنَٰهَا وَأَلْقَيْنَا فِيهَا رَوَٰسِىَ وَأَنۢبَتْنَا فِيهَا مِن كُلِّ زَوْجٍۭ بَهِيجٍۢ
78፥7 *"ብዙ ዓይነቶችም"* አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ وَخَلَقْنَٰكُمْ أَزْوَٰجًۭا
71፥17 አላህም *"ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ"*፡፡ وَٱللَّهُ أَنۢبَتَكُم مِّنَ ٱلْأَرْضِ نَبَاتًۭا
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁ እና *"የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ተዓምራቶቹ ነው"*፡፡ በዚህ ውስጥ *"ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት"*፡፡ وَمِنْ ءَايَٰتِهِۦ خَلْقُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَٱخْتِلَٰفُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَٰنِكُمْ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّلْعَٰلِمِينَ

አላህ አደምን ከተለያየ የአፈር አይነት መፍጠሩ በዘሮቹ የቀለም ልዩነት ለማኖር ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3213
አቡ ሙሳ እንደተረከው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከፍ ያለው አላህ አደምን ከጭብጥ አፈር ፈጠረው፤ እርሱም ከሁሉም የምድር ክፍል ወስዶ ፈጠረው፤ ስለዚህ የአደም ልጆች አንዳንዶቹ ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ ጠይም ወዘተ...ሆኑ። عَنْ أَبِي مُوسَى الأَشْعَرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى خَلَقَ آدَمَ مِنْ قَبْضَةٍ قَبَضَهَا مِنْ جَمِيعِ الأَرْضِ فَجَاءَ بَنُو آدَمَ عَلَى قَدْرِ الأَرْضِ فَجَاءَ مِنْهُمُ الأَحْمَرُ وَالأَبْيَضُ وَالأَسْوَدُ وَبَيْنَ ذَلِكَ وَالسَّهْلُ وَالْحَزْنُ وَالْخَبِيثُ وَالطَّيِّبُ ‏"‏

"ሐዋ" حَوَّاء‎ የሚለው ቃል በሐዲስ የመጣ ሲሆን "ሐዋህ" ማለትም "ሕያው" ከሚል ሴማዊ ቃል የመጣው ነው፤ አላህ ስለ ሐዋ በሚናገርበት አንቀጽ ላይ የአደም "መቀናጃ" ብሎ ያስቀምጣታል፦
39:6 *ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን አደረገ*። خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ ثُمَّ جَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ الْأَنْعَامِ ثَمَانِيَةَ أَزْوَاجٍ
7:189 እርሱ ያ *ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁ ከርሷም መቀናጆዋን* ወደ እርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው። هُوَ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَجَعَلَ مِنْهَا زَوْجَهَا لِيَسْكُنَ إِلَيْهَا
4:1 እላንተ ሰዎች ሆይ! ያንን *ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን*፣ ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ። يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً

“ነፍሥ” نَفْس የሚለው ቃል “ደሚሩል-ነፍሢያ” ማለትም "ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun” ሲሆን አደምን ያሳያል፤ “መቀናጃዋ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል ”ዘውጀሃ” زَوْجَهَا ሲሆን የአደም ጥንድን ያሳያል፤ ይህቺም ጥንድ ሐዋ ስትሆን የተፈጠረችው ከአደም የጎን አጥንት ነው፤ ይህንን በነብያችን"ﷺ" ሐዲስ ላይ እናገኛለን፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 567
ዐሊይ"ረ.ዐ." እንደተረከው ነብዩም"ﷺ" አሉ፦
እጅግ የላቀው አላህ አደምን ፈጠረው፤ ሐዋን ከእርሱ አጭር አጥንት። قَالَ إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى لَمَّا خَلَقَ آدَمَ خُلِقَتْ حَوَّاءُ مِنْ ضِلَعِهِ الْقَصِيرِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 17, ቁጥር 80"
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደነገረን የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ማንም በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን በምንም ነገር ሲመሰክር መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል፣ ሴትን በደግነት ተንከባከቡ፣ ሴት የተፈጠረችው ከጎን አጥንት ነውና። مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَإِذَا شَهِدَ أَمْرًا فَلْيَتَكَلَّمْ بِخَيْرٍ أَوْ لِيَسْكُتْ وَاسْتَوْصُوا بِالنِّسَاءِ فَإِنَّ الْمَرْأَةَ خُلِقَتْ مِنْ ضِلَعٍ

ስለ አደም እና ሐዋ አፈጣጠር ደርዝ እና ፈርጅ ባለ መልኩ ሳይሆን በግርድፉና በሌጣ ከላይ አቅርበናል፤ በመቀጠል በእነርሱ ዙሪያ ስላሉት እሳቤ ማለትም ስለ ሞት፣ ኢብሊስ፣ ጀነት ወዘተ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ነጥብ በነጥብ ኢንሻላህ እናያለን፦
ነጥብ አንድ
"ሞት"
ሕይወት ሰጥቶ ሕያው የሚያደርግ እንዲሁ በሞት የሚያሞትም አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
15፥23 *እኛም ሕያው የምናደርግ እና የምናሞት እኛው ብቻ ነን"*፡፡ እኛም ፍጡርን ሁሉ የምንወርስ ቀሪ ነን፡፡ وَإِنَّا لَنَحْنُ نُحْىِۦ وَنُمِيتُ وَنَحْنُ ٱلْوَٰرِثُونَ
10፥56 *"እርሱ ሕያው ያደርጋል፤ ያሞታልም ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ"*፡፡ هُوَ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

ሕይወት የመልካም ሥራ ሽልማት እንዳልሆነም ሁሉ ሞትም የመጥፎ ሥራ ቅጣት አይደለም፤ አላህ የትኛው ሥራችን ያማረ መሆኑን ሊፈትነን ሞትንና ሕይወትን ፈጠረ፦
67፥2 *ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊፈትናችሁ "ሞትንና ሕይወትን" የፈጠረ ነው"*፤ እርሱም አሸናፊው መሐሪው ነው። الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ
6፥165 *"እርሱም ያ በምድር ምትኮች ያደረጋችሁ በሰጣችሁም ጸጋ ሊፈትናችሁ"* ከፊላችሁን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች ከፍ ያደረገ ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي جَعَلَكُمْ خَلَائِفَ الْأَرْضِ وَرَفَعَ بَعْضَكُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَبْلُوَكُمْ فِي مَا آتَاكُمْ ۗ إِنَّ رَبَّكَ سَرِيعُ الْعِقَابِ وَإِنَّهُ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

"በምድር ምትኮች" የሚለው ይሰመርበት፤ "ኸሊፋህ" خَلِيفَة ማለት "ምትክ" ማለት ሲሆን ይህም ቃል በመወለድና በሞት ሰው ሰውን እንደሚተካ ያሳያል፣ ሰው ከመፈጠሩ በፊት አላህ ለመላእክት ያለው፦ "በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ" የሚል ቃል ነው፦
2:30 ጌታህ ለመላእክት፡-«እኔ፦ *በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ*» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ። وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً

ከማንኛው ነገር አላህ በፈጠረውም ሁሉ የሞት ጊዜ አለው፤ ሞት የልደት ሌላይኛው ገጽታ ነው፣ ምክንያቱም ሰው፣ እንስሳት፣ እጽዋት ህይወት እንዳላቸው ሁሉ ይሞታሉ፦
7፥185 *በሰማያትና በምድር ግዛት ውስጥ ከማንኛው ነገር አላህ በፈጠረውም ሁሉ የሞት ጊዜያቸውም በእርግጥ መቅረቡ የሚፈራ መኾኑን አያስተውሉምን?* ከእርሱም ከቁርኣን ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?፡፡ أَوَلَمْ يَنظُرُوا فِي مَلَكُوتِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا خَلَقَ اللَّهُ مِن شَيْءٍ وَأَنْ عَسَىٰ أَن يَكُونَ قَدِ اقْتَرَبَ أَجَلُهُمْ ۖ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَهُ يُؤْمِنُونَ

አላህ ዕቅዱ ሰውን በምድር ላይ ለማኖርና ለማሞት ነው፤ ሰውን ለዘላለም የማኖር ዕቅድ በአላህ መርሃ-ግብር ውስጥ የለም፤ ይህንን አደምና ሐዋ ስለሚያውቁ ከዚህ በተቃራኒው ኢብሊስ እነርሱን፦ "በመዘውተሪያ ዛፍ በማይጠፋ ንግሥናም ላይ ላመላክትህን፣ ጌታችሁም መልአኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም" በማለት መወስወሱ ይህንን ያሳያል፦
20፥120 ሰይጣንም ወደ እርሱ ጎተጎተ፦ *"አደም ሆይ! በመዘውተሪያ ዛፍ በማይጠፋ ንግሥናም ላይ ላመላክትህን?" አለው*፡፡ فَوَسْوَسَ إِلَيْهِ الشَّيْطَانُ قَالَ يَا آدَمُ هَلْ أَدُلُّكَ عَلَىٰ شَجَرَةِ الْخُلْدِ وَمُلْكٍ لَّا يَبْلَىٰ
7፥20 ሰይጣንም ከሐፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ለእነርሱ ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው፦ *"ጌታችሁም መልአኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም" አላቸው*፡፡ فَوَسْوَسَ لَهُمَا الشَّيْطَانُ لِيُبْدِيَ لَهُمَا مَا وُورِيَ عَنْهُمَا مِن سَوْآتِهِمَا وَقَالَ مَا نَهَاكُمَا رَبُّكُمَا عَنْ هَـٰذِهِ الشَّجَرَةِ إِلَّا أَن تَكُونَا مَلَكَيْنِ أَوْ تَكُونَا مِنَ الْخَالِدِينَ

አደምና ሐዋ ዛፉን ባለመብላታቸው ለዘላለም የሚዘወተሩ አሊያም በመብላታቸው በሞት የማይዘወተሩ አይደለም። በመብላታቸው ሞት መጣባቸው የሚል እሳቤ በቁርኣን ላይ ሽታው አይገኝም። እንደማይዘወተሩ ስለሚያውቁ ኢብሊስ፦ "አላህ የከለከላችሁ እንዳትሞቱ ነው፤ ብትበሉ ትዘወተራላችሁ ብሎ አሳሳታቸው፤ "ዛፉን የመዘውተሪያ ዛፍ ነው፤ ዘላለም ነዋሪ የሚያረግ ነው" ብሎ ዋሻቸው፤ የበሉትም በመብላት የሚዘወተሩ መስሏቸው ነው፤ ይህ የሚያሳየው ለዘላለም መኖር የሚለው እሳቤ የኢብሊስ እንጂ የአላህ ወይም የእነርሱ አይደለም። የሞት ጊዜ ካለበት ፍጡር መካከል አንዱ የጅን ሞት ነው፤ ነብያችንም”ﷺ” ይህንን ነግረውናል፤ ጂን ደግሞ ከሰው በፊት የተፈጠረ ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 87, ሐዲስ 13
ኢብኑ ዐባስ"ረ.ዐ." እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ ይሉ ነበር፦ *"በሃያልነትህ እጠበቃለው፤ በእውነት የሚመለክ ከአንተ ከማትሞተው ሌላ የለም፤ ጂን እና ሰው ግን ይሞታል”*። أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَقُولُ ‏ أَعُوذُ بِعِزَّتِكَ الَّذِي لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، الَّذِي لاَ يَمُوتُ وَالْجِنُّ وَالإِنْسُ يَمُوتُونَ
ነጥብ ሁለት
"ኢብሊስ"
ኢብሊስ ተፈጥሮው ከመልአክ ሳይሆን ከጂን ነበር፤ “ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፤ “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው፤ ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፤ ሰው የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ዐፈር እንደሆነ፤ መልአክ የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ብርሃን እንደሆነ ሁሉ ጂን የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ደግሞ እሳት ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
18:50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር*፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ፡፡
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥረዋል"*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

በመላእክት እና በጂኒዎች መካከል የተፈጥሮ ልዩነት ለማሳየት "ወ" وَ የሚል መስተጻምር አለ፤ ስለዚህ ኢብሊስ መልአክ አልነበረም። አላህ አደም ሲፈጥር ከምድር ዐፈር ምድር ላይ እንዲኖር ነው፤ ከዚያም በመላእክትን የተጠሪዎቹን እንስሳት፣እፅዋትና ማዕድናት ስሞች እንዲናገሩ "አቀረባቸው" ፤ የእነዚህን ተጠሪዎች ስሞች አላወቁም፤ ከዚያም ለእነርሱ እና ለኢብሊስ ለአደም ስገዱ አላቸው ወዲያውም ሰገዱ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር፦
2፥31 *አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው፡፡ ከዚያም በመላእክት ላይ ተጠሪዎቹን "አቀረባቸው" ፡፡ «እውነተኞችም እንደኾናችሁ የእነዚህን ተጠሪዎች ስሞች ንገሩኝ» አላቸው*፡፡
7፥12 አላህ፦ *"ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ? አለው፡፡ «እኔ ከእርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፡፡ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው» አለ*፡፡ قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ ۖ قَالَ أَنَا خَيْرٌ مِّنْهُ خَلَقْتَنِي مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُ مِن طِينٍ
18:50 *ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ*፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

"ባዘዝኩህ ጊዜ እና ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ" የሚሉት ሃይለ-ቃላት ለአደም መስገድ የታዘዙት መላእክት ብቻ ሳይሆኑም ኢብሊስም እንደታዘዘ ያሳያል፤ አላህም ኢብሊስን አደምን ከፈጠረበት ቦታ ውጣ አለው፤ ከራህመቱም ተባረረ፦
7፥13 *ከእርሷ ውረድ፤ በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና፡፡ "ውጣም" አንተ ከወራዶቹ ነህና አለው*፤ قَالَ فَٱهْبِطْ مِنْهَا فَمَا يَكُونُ لَكَ أَن تَتَكَبَّرَ فِيهَا فَٱخْرُجْ إِنَّكَ مِنَ ٱلصَّٰغِرِينَ

"ሃ" هَا ማለትም "እርሷ" የተባለችው አደም የተፈጠረበት ቦታ ናት፤ ይህቺ ቦታ መላእክቶችን እና አደም ስም ያወጣላቸው ተጠሪዎቹን ያቀረበበት ቦታ ናት፤ ኢብሊስ በአላህ ላይ ሲያምፅ ሸይጧን ሆነ፤ “ሸይጧን” شيطان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شياطين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ ሸይጧን የባህርይ ስም እንጂ የተፀውኦ ስም አይደለም፤ ከአላህ ራህመት የሚርቁ “ሸያጢን” ይባላሉ፤ ከአላህ የሚገለሉና የሚርቁ ሁሉ በዚህ ደረጃ በመውረድ ወራዶቹ ናቸው።

ኢንሻላህ ትምህርቱ ይቀጥላል...


ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
ሕያዋን እና ሙታን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

35፥22 *ሕያዋንና ሙታንም አይስተካከሉም*፡፡ አላህ የሚሻውን ሰው ያሰማል፡፡ *አንተም በመቃብር ውስጥ ያሉትን አሰሚ አይደለህም*፡፡ وَمَا يَسْتَوِى ٱلْأَحْيَآءُ وَلَا ٱلْأَمْوَٰتُ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُسْمِعُ مَن يَشَآءُ ۖ وَمَآ أَنتَ بِمُسْمِعٍۢ مَّن فِى ٱلْقُبُورِ

መግቢያ
አምላካችን አላህ ለሰው መስሚያዎችን፣ ማያዎችን እና ልቦችንም የፈጠረ ነው፦
16፥75 አላህም ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ አወጣችሁ፡፡ ታመሰግኑም ዘንድ *ለእናንተ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም አደረገላችሁ*፡፡ وَٱللَّهُ أَخْرَجَكُم مِّنۢ بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْـًۭٔا وَجَعَلَ لَكُمُ ٱلسَّمْعَ وَٱلْأَبْصَٰرَ وَٱلْأَفْـِٔدَةَ ۙ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ
23፥78 እርሱም ያ *መስሚያዎችን፣ ማያዎችን እና ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው*፡፡ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡ وَهُوَ ٱلَّذِىٓ أَنشَأَ لَكُمُ ٱلسَّمْعَ وَٱلْأَبْصَٰرَ وَٱلْأَفْـِٔدَةَ ۚ قَلِيلًۭا مَّا تَشْكُرُونَ

እነዚህን የያዘው አካላችን ይሞታል፤ በትንሳኤ ቀን ደግሞ ይነሳል፤ ስንሞት ሙታን ስንነሳ ደግሞ ሕያዋን ነን፤ ይህ “ሒስሲይ” ማለትም “እማሬአዊ"outward truth" ነው፦
22፥6 ይህ አላህ እርሱ መኖሩ የተረጋገጠ፣ እርሱም *ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፣ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው*፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْحَقُّ وَأَنَّهُۥ يُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ وَأَنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ قَدِيرٌۭ
30፥50 ምድርንም ከሞተች በኋላ እንዴት ሕያው እንደሚያደርጋት ወደ አላህ ችሮታ ፈለጎች ተመልከት፡፡ *ይህ ሙታንንም በእርግጥ ሕያው አድራጊ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው*፡፡ فَٱنظُرْ إِلَىٰٓ ءَاثَٰرِ رَحْمَتِ ٱللَّهِ كَيْفَ يُحْىِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَآ ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ لَمُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ قَدِيرٌۭ
36፥12 *እኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ

ሰው አካሉ ላይ ያሉት ማየት፣ መስማት፤ መዳሰስ፣ ማሽተት፣ መቅመስ ከእንስሳ ጋር የሚጋራው ባህርይ ሲሆን፤ ነገር ግን ከእንስሳ የሚለይበት ውስጣዊ ዓይን፣ ጆሮ፣ አፍ፣ ልብ አለው፤ ይህ “መዕነዊይ” ማለትም “ፍካሬአዊ"inward truth" ይባላል፤ ይህ ውስጣዊ ምንነት ዒልም፣ ኢማን፣ ኢስላምን ካገኘ ሰውየው ሕያው ይባላል፤ በተቃራኒው ጀህል፣ ኩፍር፣ ሺርክ ካገኘው ሰውዬው ሙታን ይባላል። ሰውዬው የውስጡ ዓይን፣ ጆሮ፣ ልብ ቢኖረውም ዓይኑ ካላየበት፣ ጆሮውን ካልሰማበት እና ልቡን ካላወቀበት እንደ እንስሳ ነው፦
7፥179 ከጋኔንም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ *ለእነርሱ በእርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፣ ለእነሱም በእሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፣ ለእነሱም በእሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡* ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው፤ وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًۭا مِّنَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌۭ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌۭ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ ءَاذَانٌۭ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَآ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ كَٱلْأَنْعَٰمِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْغَٰفِلُونَ
25፥44 *ይልቁንም አብዛኛዎቻቸው የሚሰሙ ወይም የሚያውቁ መኾናቸውን ታስባለህን? እነርሱ እንደ እንስሳዎች እንጂ ሌላ አይደሉም*፡፡ ከቶውንም እነሱ ይልቅ መንገድን የተሳሳቱ ናቸው፡፡ أَمْ تَحْسَبُ أَنَّ أَكْثَرَهُمْ يَسْمَعُونَ أَوْ يَعْقِلُونَ ۚ إِنْ هُمْ إِلَّا كَٱلْأَنْعَٰمِ ۖ بَلْ هُمْ أَضَلُّ سَبِيلًا

ሰው የውስጥ ተፈጥሮውን ካልተጠቀመበት እንደ እንስሳ ነው፤ ወይም ሙታን፣ እውር፣ ደንቆሮ፣ ዲዳ ነው። ይህን እሳቤ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦
ነጥብ አንድ
"ብርሃን እና ጨለማ"
አምላካችን አላህ ለሰው ልጆች በየዘመናቱ የሚያወርዳቸው ግልጠተ-መለኮት ብርሃን ናቸው፤ ለናሙና ያክል ተውራት እና ቁርአን ተጠቃሽ ናቸው፦
4፥174 እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ዘንድ በእርግጥ አስረጅ መጣላችሁ፤ *ወደ እናንተም ገላጭ የኾነን ብርሃን ቁርኣንን አወረድን*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَكُم بُرْهَٰنٌۭ مِّن رَّبِّكُمْ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ نُورًۭا مُّبِينًۭا
5፥44 እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና *ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን*፡፡ إِنَّآ أَنزَلْنَا ٱلتَّوْرَىٰةَ فِيهَا هُدًۭى وَنُورٌۭ ۚ يَحْكُمُ بِهَا ٱلنَّبِيُّونَ ٱلَّذِينَ أَسْلَمُوا۟ لِلَّذِينَ هَادُوا۟ وَٱلرَّبَّٰنِيُّونَ

ይህ ብርሃን የሃይድጂን ወይም የሂልየም አሊያም የአርገን ብርሃን ሳይሆን የልብ ብርሃን ነው፦
45፥20 ይሀ ቁርኣን *ለሰዎች የልብ ብርሃኖች ነው*፡፡ ለሚያረጋግጡም ሕዝቦች መሪና እዝነት ነው፡፡ هَٰذَا بَصَٰٓئِرُ لِلنَّاسِ وَهُدًۭى وَرَحْمَةٌۭ لِّقَوْمٍۢ يُوقِنُونَ
28፥43 የፊተኞቹን የክፍለ ዘመናት ሕዝቦችም ከአጠፋን በኋላ *ለሰዎች የልብ ብርሃን መሪም እዝነትም ሲኾን ይገሰጹ ዘንድ ለሙሳ መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው*፡፡ وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ مِنۢ بَعْدِ مَآ أَهْلَكْنَا ٱلْقُرُونَ ٱلْأُولَىٰ بَصَآئِرَ لِلنَّاسِ وَهُدًۭى وَرَحْمَةًۭ لَّعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ

ነብያት የሚላኩት በዚህ የልብ ብርሃን ሰዎችን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ለማውጣት ነው፦
14፥1 አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርአን ሰዎችን በጌታቸው ፈቃድ *ከጨለማዎች ወደ ብርሃን* አሸናፊ ምስጉን ወደ ኾነው ጌታ መንገድ ታወጣ ዘንድ ወደ አንተ ያወረድነው መጽሐፍ ነው፡፡
14፥5 *ሙሳንም ወገኖችህን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አውጣ* አላህንም ቀኖች አስገንዝባቸው በማለት በተዓምራታችን *በእርግጥ ላክነው*፡፡ በዚህ ውስጥ በብዙ ታጋሽና በብዙ አመስጋኝ ለኾኑት ሁሉ *በእርግጥ ተዓምራቶች አሉ*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ أَنْ أَخْرِجْ قَوْمَكَ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَذَكِّرْهُم بِأَيَّىٰمِ ٱللَّهِ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّكُلِّ صَبَّارٍۢ شَكُورٍۢ

ይህ ብርሃን ከአላህ ዘንድ ሲመጣ በውስጥ ዓይኑ የተመለከተም ሰው ጥቅሙ ለራሱ ብቻ ነው፤ የታወረም ሰው ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው፤ እነሆ የውጪ ዓይኖች አይታወሩም፤ ነገር ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፦
6፥104 *«ከጌታችሁ ዘንድ ብርሃኖች በእርግጥ መጡላችሁ፡፡ የተመለከተም ሰው* ጥቅሙ ለራሱ ብቻ ነው፡፡ *የታወረም ሰው* ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው፤ እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም» በላቸው፡፡ قَدْ جَآءَكُم بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَنْ أَبْصَرَ فَلِنَفْسِهِۦ ۖ وَمَنْ عَمِىَ فَعَلَيْهَا ۚ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيْكُم بِحَفِيظٍۢ
22፥46 ለእነርሱም በእነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በእነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮች ይኖሯቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? *እነሆ ዓይኖች አይታወሩም ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ*፡፡ أَفَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَتَكُونَ لَهُمْ قُلُوبٌۭ يَعْقِلُونَ بِهَآ أَوْ ءَاذَانٌۭ يَسْمَعُونَ بِهَا ۖ فَإِنَّهَا لَا تَعْمَى ٱلْأَبْصَٰرُ وَلَٰكِن تَعْمَى ٱلْقُلُوبُ ٱلَّتِى فِى ٱلصُّدُورِ

ዒልም፣ ኢማን፣ ኢስላምን ብርሃን ነው፤ ይህንን ብርሃን አስተባብለው በአላህ አንቀጾች ያስዋሹ ደንቆሮች ድዳዎችም በጨለማዎች ውስጥ ናቸው፤ ምንም እንደ እንስሳ በውጪ ዓይን፣ ጆሮ፣ አፍ ቢኖሩም እነርሱ በውሳጣዊ ጆሮ ደንቆሮዎች፣ በውሳጣዊ አፍ ዲዳዎች፣በውሳጣዊ ዓይን ዕውሮች ናቸው፦
6፥39 እነዚያም በአንቀጾቻችን ያስዋሹ *ደንቆሮች ድዳዎችም በጨለማዎች ውስጥ ያሉ ናቸው*፡፡ وَٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا صُمٌّۭ وَبُكْمٌۭ فِى ٱلظُّلُمَٰتِ
2፥171 የነዚያም የካዱት ምሳሌ እንደዚያ ድምጽንና ጥሪን በስተቀር ሌላን በማይሰማ እንስሳ ላይ እንደሚጮህ ብጤ ነው፡፡ *እነርሱ ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው*፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡ وَمَثَلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ كَمَثَلِ ٱلَّذِى يَنْعِقُ بِمَا لَا يَسْمَعُ إِلَّا دُعَآءًۭ وَنِدَآءًۭ ۚ صُمٌّۢ بُكْمٌ عُمْىٌۭ فَهُمْ لَا يَعْقِلُونَ
2፥18 እነርሱ *ደንቆሮዎች፣ ዲዳዎች፣ ዕውሮች ናቸው፤* ስለዚህ እነርሱ አይመለሱም፡፡ صُمٌّۢ بُكْمٌ عُمْىٌۭ فَهُمْ لَا يَرْجِعُونَ