ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
በዚህ ሰአት ከእውነት “በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ” ሆነው “አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?” የሚለው አንቀፅ ሲነበብ በሚንጫጩት ልብ ውስጥ ፈተና ሊያደርግ ሸይጣን ልብስብስን ቃልን ጣለ፤ ሁልጊዜ በእያንዳንዱ ነብይ ዘመን ነብዩ ባነበበ ጊዜ ሰይጣን ልቦቻቸውም ደረቆች በሆኑት ውስጥ ልብስብስን ቃልን ይጥላል፤ ይህን የሚያደርገው የቀጠፈውን እንዲቀጣጥፉ ነው፦
22፥53 ሰይጣን የሚጥለውን ነገር ለእነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ላለባቸው ልቦቻቸውም ደረቆች ለሆኑት ፈተና ሊያደርግ ይጥላል፡፡ በዳዮችም ከእውነት “በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ” ናቸው لِّيَجْعَلَ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ فِتْنَةًۭ لِّلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌۭ وَٱلْقَاسِيَةِ قُلُوبُهُمْ ۗ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَفِى شِقَاقٍۭ بَعِيدٍۢ ፡፡
6:112-113 እንደዚሁም *ለነቢያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን*፡፡ ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል *ልብስብስን ቃል ይጥላሉ*፡፡ ጌታህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ *ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው*፡፡ *የሚጥሉትም ሊያታልሉ* እና የእነዚያም በመጨረሻይቱ ሕይወት የማያምኑት ሰዎች ልቦች ወደእርሱ እንዲያዘነብሉ እንዲወዱትም እነርሱ *ይቀጥፉ የነበሩትንም እንዲቀጣጥፉ* ነው፡፡
22፥52 ከመልክተኛና ከነቢይም ከአንተ በፊት አንድንም አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ የሚጥል ቢሆን እንጅ፡፡ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍۢ وَلَا نَبِىٍّ إِلَّآ إِذَا تَمَنَّىٰٓ أَلْقَى ٱلشَّيْطَٰنُ فِىٓ أُمْنِيَّتِهِۦ فَيَنسَخُ ٱللَّهُ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ ثُمَّ يُحْكِمُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦ ۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌۭ ፡፡

ይህ አንቀፅ ሙጅመል ማለትም ጥቅላዊ ነው፤ ምክንያቱም *”ከአንተ በፊት”* የሚለው ገለጻ ከነብያችን በፊት በነበሩት ነብያትና መልእክተኞችም ላይም ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ለማታለል *ልብስብስን ቃል* ይጥላሉ፤ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል፤ ሸኹል ኢስላም ኢብኑ ተምያህ ይህንን እይታ ይጋራሉ። ነገር ግን በወቅቱ ነብያችን”ﷺ” “አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?” የሚለው አንቀጽ በአሉታዊ መልኩ አንብበው ሲጨርሱ በንባቡ ላይ ሸይጣን፦ “እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው” የሚለውን ለሙሽሪኮች ሲያነብ ሙሽሪኮች ይህን ቃል ሲሰሙ፦ “ነቢዩ”ﷺ” አማልክቶቻችንን አወድሷል” ሲሉ ዋሹ፤ የዚህ ቅጥፈት ዜና ወደ ሐበሻ ከተሰደዱ ሰሐቦች ዘንድ ከእውነታው እጅግ በተለየና በራቀ መልኩ ተሰማ፤ አላህም ነብያችንን”ﷺ” “ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፡፡ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር” በማለት ይህ ቅጥፈት ለማስዋሸት ፈተና መሆኑን እና ቢዋሹ ወዳጆች አድርገው ይይዧቸው እንደነበር ተናገረ፦
17፥73 እነሆ ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፡፡ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር وَإِن كَادُوا۟ لَيَفْتِنُونَكَ عَنِ ٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ لِتَفْتَرِىَ عَلَيْنَا غَيْرَهُۥ ۖ وَإِذًۭا لَّٱتَّخَذُوكَ خَلِيلًۭا ፡፡

ሙሽሪኮች ጠላት መሆናቸው በራሱ ከአላህ ቃል ሌላ ቃልን እንዳልተናገሩ በቂ ማስረጃ ነው፤ ምክንያቱም ነብያችንን”ﷺ” ወዳጅ አድርገው አለመያዛቸው ነው፤ በተጨማሪም በመቀጠል ከአላህ ውጪ ከሌላ ማንነት ሆነ ምንነት ከፊል ቃልን አምጥቶ ቢቀጥፉ የልብ ስራቸውን እንደሚቆርጥ በመናገር ከሌላ ህልውና ምንም እንዳላሉ መስክሮላቸዋል፤ ፦
69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን “በቀጠፈ” ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

“”የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር “”ብሎ ማለት የቱን ያህል በግህደተ-መለኮት ቀልድ እንደሌለ የሚያሳይ ሃይለ-ቃል ነው። ከአላህ ወዲህ የትኛው ንግግር ማስረጃ ሊሆን ይችላል? ቁርአንን አላህ ነው ያወረደው፤ አላህ ከሰው ሆነ ከሸይጣን ቃላት ጠብቆታል፣ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፦
15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
41:42 ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከሆነውጌታ የተወረደ ነው።
መደምደሚያ
ይህንን የተመታ እና የተመምታታ ውሃ የማያነሳ ሙግት ሳልማን ሩሽዲ በ 1988 AD “ሰይጣናዊ አንቀፅ” የሚል መጽሐፉን ሲያራግቡ ከነበሩት መካከል ሚሽነሪዎች አንዶቹ ናቸው፤ እስቲ በዚህ ሂስ ባይብል ላይ ያለውን ዳዊት እንመልከተው፤ ይህን ሙግት የዳዊትን ነብይነት ለማስተባበል ሳይሆን እሾህክን በእሾክ እንዴት እንደሆነ ለማሳየት ነው፤ ዳዊት እስራኤልን ቁጠር ሳይባል ቆጥሮ ዳዊት በሰራው ስህተት እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ልኮ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች በመቅሰፍት ገደለ፦
2ኛ ሳሙኤል 24.14 እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ሰደደ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች ወደቁ።

ይህ ስህተት የራሱ የዳዊት እንደሆነ አምኗል፣ ይቅርታም ጠይቋል፣ ከዚያም ባሻገር ይህ የእኔ ስህተት ነው ህዝቡን አትንካ ብሎ ጸለየ፣ ነገር ግን የዳዊት ልመናም አልሰራም፦
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥8 ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ይህን በማድረግ እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታስወግድ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው።
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥17 ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ሕዝቡ ይቈጠር ዘንድ ያዘዝሁ እኔ አይደለሁምን? የበደልሁና ክፉ የሠራሁ እኔ ነኝ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አድርገዋል? አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን፥ ነገር ግን ይቀሠፍ ዘንድ በሕዝብህ ላይ አትሁን አለው።

ታዲያ ዳዊት ማን ቁጠር ብሎት ነው የቆጠረው? ስንል
ዳዊት እስራኤልን የቆጠረው ሰይጣን “ቁጠር” ብሎት ነው ይለናል፦
2ኛ ሳሙኤል 24.1 ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትንም፦ *ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር* ብሎ በላያቸው አስነሣው።

ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር ያለው ሰይጣን ነው፥ እርሱ የተባለው ህቡዕ ተውላጠ-ስም ሰይጣን መሆኑን ሌላ ጥቅስ ይነግረናል፦
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን “አንቀሳቀሰው”።

“አንቀሳቀሰው” ብለው ያስቀመጡት የዕብራይስጡ ቃል “የሰት” תְּסִיתֵ֥נִי ሲሆን “ሱት” סוּת ማለትም “አሳሳተ” ከሚል ግስ የመጣ ነው ፣ ለሃሰተኛ ነብይ ማሳሳት “የስቲአከ” יְסִֽיתְךָ֡ ማለትም “ቢያስትህ” በሚል መጥቷል፦
ዘዳግም 13.6 አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ יְסִֽיתְךָ֡፥

ዳዊትም ከሰይጣን መልዕክት የተቀበለውን ለኢዮአብንና ለሕዝቡ አለቆች ቍጠሩ ብሎ አስተላልፏል፦
ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 21.8 ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች፦ ሂዱ፥ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፥ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ አላቸው።

አንዱ ይህንን ሙግት ሳቀርብለት ዳዊት ነብይ አይደለም ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ሊክደኝ ሞክሯል፤ በባይብል የተብራራው ዳዊት የፈጣሪ ነብይ እንደሆነ ይናገራል፦
የሐዋርያት ስራ 2፡29-30 ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው። *ነቢይ ስለ ሆነ*፥

አዎ ዳዊት ነብይ ነበረ ከተባለ፤ የነብይ መስፈርቱ ከፈጣሪ መልዕክት መቀበል ወይስ ከሰይጣን መልዕክት መቀበል ? ፍርዱን ለህሊና።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
ብዙ ሚስት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

መግቢያ
ስለ ጋብቻ የሚያጠናው የትምህርት ዘርፍ በምሁራን ዘንድ ማትሪሞኒ”matrimony” ይባላል፤ ይህም ስነ-ጋብቻ ጥናት የሚያጠኑ ምሁራን በዋነኝነት ለሁለት ይከፍሉታል፦
1. ተመሳሳይ ፃታ ግንኙነት ሆሞ-ሴክሹአል”homosexual”
2. ተቃራኒ ፃታ ሄትሮ-ሴክሹአል”Heterosexual” ይባላሉ። መቼም ተመሳሳይ ፃታ ግንኙነት ለጊዜው አርስታችን ስላልሆነ ወደ ተቃራኒ ፃታ ጋብቻ እንሂድ፤ ተቃራኒ ፆታ ጋብቻ እራሱ በአራት ይከፈላል፤ እነርሱም፦
1ኛ. አንድ ወንድ ለአንድ ሴት አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ሲሆን ሞኖጋሚ”Monogamy” ይባላል፤ “Monogamy” የግሪክ ቃል ነው፥ “mono” ማለት “ብቻ” ማለት ሲሆን “gamy” ደግሞ “ጋብቻ” ማለት ነው።
2ኛ. አንድ ወንድ ለብዙ ሴት አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ሲሆን ፓሊጋሚ”Polygamy” ይባላል፤ “polygamy” የግሪክ ቃል ነው፥ “poly” ማለት “ብዙ” ማለት ሲሆን “gamy” ደግሞ “ጋብቻ” ማለት ነው።
3ኛ. አንድ ወንድ ለብዙ ሴት ሲሆን ፓሊአንድሪ”Polyandry” ይባላል፤ “Polyandry” የግሪክ ቃል ነው፥ “poly” ማለት “ብዙ” ማለት ሲሆን “andry” ደግሞ “ወንድ” ማለት ነው።
4ኛ. አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ሲሆን ፓሊጂኒ”Polygyny” ይባላል፤ “Polygyny” የግሪክ ቃል ነው፥ “poly” ማለት “ብዙ” ማለት ሲሆን “gyny” ደግሞ “ሴት” ማለት ነው፤ ይህኛው ጋብቻ በማህበራዊ ጥናት”sociology” ላይ የተቀመጠ መረጃ እንጂ ስነ-መለኮታዊ ጥናት”theology” ላይ አልተቀመጠም።
ይህን በግርድፉ እና በሌጣ ካየን ዘንዳ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ስለ አንድ ወንድ ለብዙ ሴት”Polyandry” ከቁርአን እና ከባይብል እናያለን፦

ነጥብ አንድ
“ብዙ ሚስት በቁርአን”
“አሕካም” أحكام “የሑክም” حُكْم ብዙ ቁጥር ሲሆን “ፍርድ” ወይም “ህግ” ማለት ነው፤ በኢስላም “ህጎች” በአምስት ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦ 1ኛ. “ፈርድ” فرض ማለትም “የታዘዘ”
2ኛ. “ሙስተሐብ” مستحب” ማለትም “የተወደደ”
3ኛ. “ሙባሕ” مباح ማለትም “የተፈቀደ”
4ኛ. “መክሩህ” مكروه” ማለትም “የተጠላ”
5ኛ. “ሐራም” حرام” ማለትም “የተከለከለ ናቸው።
ይህ “ፊቅህ” فقه የተባለውን የስነ-ህግ ጥናት ዋቢና ታሳቢ ያደረገ ነው፤ “ፊቅህ” ስነ-ህግ ጥናት”the study of law” ሲሆን ህግ አዋቂ ደግሞ “ፈቂህ” فقيه ይባላል፤ ይህንን ነጥብ ያነሳሁት ስለ አሕካም ለመዳሰስ ሳይሆን አንድ ወንድ ለብዙ ሴት”Polyandry” የተባለው የጋብቻ አይነት በኢስላም በኒያ ሙስተሐብ ሲሆን በፍትህ ሙባሕ ነው፤ ነገር ግን ፈርድ አይደለም፦
4:3 በየቲሞችም ማግባት አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ፣ ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ፤ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስትም፣ አራት አራትም አግቡ። አለማስተካከልንም ብትፈሩ፣ “”አንዲትን ብቻ””፣ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፤ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው።

በኢስላም በፍትህ ማስተካከል ከተቻለ እስከ አራት ማግባት ይቻላል፤ ነገር ግን ያ ካልሆነ አንዲት ብቻ ነው ማግባት ያለበት፤ እዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ጥያቄ አላህ የጋብቻን ገደብ እስከ አራት ካለ ለምንድን ነው ነብያችን እስከ ዘጠኝ ያገቡት? የሚል ነው፤ አንደኛ ምላሽ የሚሆነው አምላካችን አላህ ስለፈቀደ ነው፤ ሁለተኛ እንደሚታወቀው ቁርአን በአንድ ጊዜና ቦታ የወረደ ግህደተ-መለኮት ሳይሆን በሒደት የወረደ ግህደተ-መለኮት ነው፤ መካ ላይ ለአስር ዓመታትን ሲወርድ መዲና ላይ ደግሞ ለአስራ ሶስት ዓመታትን ወርዷል፤ የዓለማቱ ጌታ አላህ ጋብቻን የመጨረሻ ገደብ አራት ብቻ መሆኑን የሚያበስረው አንቀፅ ሲያወርድ ነብያችን ቀደም ብለው ዘጠኝ ሚስቶች ነበሯቸው፤ ይህ የቁርአን ታሪካዊ ዳራ ከአለመረዳት የሚመጣ ጥያቄ ነው።
ነጥብ ሁለት
“ብዙ ሚስት በባይብል”
ከአንድ በላይ ማግባት በባይባል የተከለከለበት አንድ ጥቅስ የለም፤ ከዚያ ይልቅ ከአንድ በላይ ያገቡ ነቢያት በቁና ሰፍሯል፦
ዘፍጥረት 31፥17 ያዕቆብም ተነሣ፥ ልጆቹንና “ሚስቶቹንም” በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤
መሣፍንት 8፥30 ለጌዴዎንም “ብዙ ሚስቶች” ነበሩትና ከወገቡ የወጡ ሰባ ልጆች ነበሩት።
1ኛ ሳሙኤል 1፥2 ሕልቃ…””ሁለትም ሚስቶች” ነበሩት፤ የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና ነበረ፤
1ኛ ሳሙኤል 25፥43 ዳዊትም ደግሞ ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ወሰደ፤ “”ሁለቱም ሚስቶች” ሆኑለት።
1ኛ ነገሥት 11፥3 ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ “”ሰባት መቶ ሚስቶች”” ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤
1ኛ ዜና መዋዕል 4፥5 ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ “”የተባሉ ሁለት ሚስቶች”” ነበሩት።
1ኛ ዜና መዋዕል 14፥3 ዳዊትም በኢየሩሳሌም “”ሚስቶችን”” ጨምሮ ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ወለደ።

አይ እነርሱ አደረጉት እንጂ ፈጣሪ አልፈቀደላቸውም ከተባለ ፈጣሪ አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ካሉት እንዴት መንከባከብ እንዳለበት የተናገረው ሳይፈቅድ ነውን? እስቲ እንይ፦
ዘዳግም 21፥15-17 ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች “”ሁለት ሚስቶች”” ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥ ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው።

እግዚአብሔር ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክል ኖሮ ለዳዊት ለዛውን  የሰውን ሚስቶችን ይሰጠው ነበርን? የጌታው  የሳኦን ሚስቶች ሰቶት ነበር፤ ከዚያ የበለጠም ካስፈለገ እንደሚጨምርለት ቃል ገብቶለታል፦
               2ኛ ሳሙኤል 12 : 8 የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ “”የጌታህንም ሚስቶች” በብብትህ “”ጣልሁልህ””፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ “”ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር””።”

ሌላው የአዲስ ኪዳን ነብይ ኢየሱስ ነው፤ ኢየሱስ ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው አላለም፤ በብሉይ የነበረውን ህግ አልሻረም። ሌላው እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ ነው፤ ሲጀመር ጳውሎስ ነብይ አይደለም፤ ሲቀጥል የሚናገረው በሞኝነት እንጂ ጌታ አዞት አይደለም፤ ንግግሩ የራሱ እንጂ የጌታ አይደለም፦
1ኛ ቆሮ 7፥12 ሌሎችንም “””እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም””፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር እርስዋም ከእርሱ ጋር ልትቀመጥ ብትስማማ፥ አይተዋት፤”
2ኛ ቆሮ 11፥17እንደዚህ ታምኜ ስመካ “”የምናገረው፥ በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አልናገርም””።”

ሲሰልስ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ባል ይኑራት አለ እንጂ ለእያንዳንዱ ለራሱ አንድ ሚስት ትኑረው አንድ ባል ይኑራት አላለም፦
1ኛ ቆሮ 7፥2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።”

ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው ያሉት ምዕራባውያን እንጂ ባይብል አይደለም፤ ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክሉም ከአንድ በላይ ዝሙት ማድረግ የአንድ ሰው መብቱና ነፃነቱ ነው የሚል መርህ አላቸው፤ ምዕራባውያን በ 17ኛው ክፍለ-ዘመን ሰው እንዲዋለድና እንዲባዛ ስላልፈለጉ እንጂ የመጡበትን ዳራ መሰረት አድርገው አይደለም፤ ለዛ ነው ግብረ-ሰዶም እንዲስፋፋ የተፈለገው፤ ይህንን እንደ ሥልጣኔ ቤተ-ክርስቲያን ግብረ-ሰዶም ታጋባለች፤ ይህ ደግሞ መሠልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው፤ ሥልጣኔ በምጣኔ ካልሆነ ጥፋት ነው፤ ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ዝሙት ሲፈቅዱ ኢስላም ደግሞ ከአንድ በላይ በሃላል ኒካ ማድረግ ይፈቅዳል፦
24:32 ከእናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፤ “ከወንዶች ባሮቻችሁ” عِبَادِكُمْ እና “ከሴቶች ባሮቻቹሁም” وَإِمَائِكُمْ ለጋብቻ ብቁ የሆኑትን “አጋቡ” وَأَنْكِحُوا፤ ድሆች ቢሆኑ፤ አላህም ከችሮታው ያከብራቸዋል፤ አላህም ስጦታ ሰፊ ዓዋቂ ነው።
2:221አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ “አታግቡዋቸው” وَلَا تَنْكِحُوا ፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ “ያመነችው ባሪያ” وَلَأَمَةٌ مُؤْمِنَةٌ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ “አትዳሩላቸው” وَلَا تُنْكِحُوا ፡፡ ከአጋሪው ምንም ቢደንቃችሁ “ምእምኑ ባሪያ” وَلَعَبْدٌ مُؤْمِنٌ በላጭ ነው፡፡
4:25 ከእናንተም ውስጥ “ጥብቆች” ምእምናት” الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ የሆኑትን “ለማግባት” يَنْكِحَ ሀብትን ያልቻለ ሰው፣ “እጆቻችሁ ካደረጓቸው” مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ከምእመናት “ባሪያን” فَتَيَاتِكُمُ الْمُؤْمِنَاتِ “ያግባ”፤

በወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ተሕሪም


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

66:1 አንተ ነቢዩ ሆይ አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን በአንተ ላይ ለምን “እርም” ታደርጋለህ?፤ አላህ እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَ ۖ تَبْتَغِى مَرْضَاتَ أَزْوَٰجِكَ ۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ ።

መግቢያ
ሚሽነሪዎች ኢስላምን ለማጠልሸት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም ብዬ ብናገር ግነት፣ እብለት ወይም ቅጥፈት አይሆንብኝም፤ በባይብል ላይ ስለ ነብያት የተዘገበው ለሰሚም ለተመልካችም ግራ የሆነው ትረካ በዋል ፈሰስ አስቀርተው የነብያት መደምደሚያ የሆኑትን ነብያችንን”ﷺ” ሊወርፉ ሲነሱ ማየት የሚያጅብ ነው፤ ለማንኛውም እግር እራስን አያክምና ቅድሚያ የራሳችሁን ባይብል ፈትሹት፤ ወደ አርስታችን ስንገባ ሱረቱ አተሕሪም የተባለው ሱራህ የወረደበት ሰበብ ሪዋያህ ነጥብ በነጥብ እንመለከታለን፦

ነጥብ አንድ
“እርም”
“ተሕሪም” تَحريم የሚለው ቃል “ሐርረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “እርም” ወይም “ክልክል” ማለት ነው፤ “ሐራም” حَرَام “የተከለከለ” የረባበት ግስ እና ተሕሪም አንድ ሥርወ-ግንድ ነው፤ አንድ ጊዜ ነብያችን”ﷺ” ከባለቤታቸው ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ሄደው ማር አጠጥታቸው፤ ሌሎች የነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶች ይህንን ሲያውቁ ቅናት ተሰምቷቸው በመመካከር፦ ምንድን ነው የበላኸው? የአፍህ ጠረን “መጋፊር” مَغَافِيرَ ይሸታል፤ መጋፊር በልተሃል ወይ? በማለት ጠየቁ፤ “መጋፊር” ማለት የአበባ አይነት ሲሆን ጠረኑ መጥፎ ሲሆን ይህንን በልተው የአፋቸው ሽታ እንደተቀየረ ለማስመሰል ተናገሩ፤ ከዚያ ነብያችንም”ﷺ” ከዛሬ በኃላ ማር አልጠጣም ብለው ባለቤቶቻቸውን ለማስደሰት እርም አሉ፤ አላህም፦ ሚስቶችን ለማስወደድ ብለህ ለምን አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር በአንተ ላይ ለምን እርም ታደርጋለህ? የሚለውን አንቀፅ አወረደ፦
66:1-4 አንተ ነቢዩ ሆይ አላህ ለአንተ “የፈቀደልህን” ነገር “ሚስቶችህን ማስወደድን” የምትፈልግ ስትሆን በአንተ ላይ ለምን “እርም” ታደርጋለህ?፤ አላህ እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَ ۖ تَبْتَغِى مَرْضَاتَ أَزْوَٰجِكَ ۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ ።

ነጥብ ሁለት
“መሓላ”
የነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶች መጋፊር በልተው የአፋቸው ሽታ እንደተቀየረ ለማስመሰል ስለነገሯቸው ነብያችን”ﷺ”፦ “በፍፁም ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ ግን አልጠጣም” ብለው ምለው ተገዝተው ነበር፤ ለማሃላቸው ማካካሻ ካደረጉ አላህ እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው፤ “የመሓሎቻችሁን መፍቻ” ማድረጉ እርሱም ዐዋቂው ጥበበኛው ነው፦
66፥2 አላህ ለእናንተ የመሓሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፤ አላህም እረዳታችሁ ነው፤ እርሱም ዐዋቂው ጥበበኛው ነው قَدْ فَرَضَ ٱللَّهُ لَكُمْ تَحِلَّةَ أَيْمَٰنِكُمْ ۚ وَٱللَّهُ مَوْلَىٰكُمْ ۖ وَهُوَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ ፡፡

የማለ ሰው መሃላውን ቢፈታ ዐስርን ምስኪኖች ማብላት፣ ወይም እነርሱን ማልበስ ወይንም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፤ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መጾም ነው፤ ይህ የመሐላዎቻችሁ ማካካሻ ነው፦
5፥89 አላህ በመሐላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፤ ነገር ግን መሐላዎችን ባሰባችሁት ይይዛችኋል፡፡ ማስተሰሪያውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ ዐስርን ምስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ ወይንም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፤ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መጾም ነው፤ ይህ በማላችሁ ጊዜ የመሐላዎቻችሁ ማካካሻ ነው፡፡ መሐላዎቻችሁንም ጠብቁ፡፡ እንደዚሁ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ያብራራል፡፡ እናንተ ልታመሰግኑ ይከጀላልና لَا يُؤَاخِذُكُمُ ٱللَّهُ بِٱللَّغْوِ فِىٓ أَيْمَٰنِكُمْ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ ٱلْأَيْمَٰنَ ۖ فَكَفَّٰرَتُهُۥٓ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَٰكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍۢ ۖ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٍۢ ۚ ذَٰلِكَ كَفَّٰرَةُ أَيْمَٰنِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ ۚ وَٱحْفَظُوٓا۟ أَيْمَٰنَكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ ፡፡
ነጥብ ሶስት
“ሚስጥር”
ነብያችን”ﷺ” ከባለቤታቸው አንዷ ለሆነችው ለሃፍሳ”ረ.ዓ.” “በፍፁም ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ ግን አልጠጣም” ብለው ይህ ወሬ በሚስጥር በመሰጠሯት ጊዜ ሄዳ ለዓኢሻ”ረ.ዓ.” ተናገረች፤ ነብይ ማለት የሩቅ እውቀት የሚገለጥለት ነውና ለዓኢሻ”ረ.ዓ.” በተናገረች ጊዜ የተናገረችውን ከፊሉን አሳውቀዋት ከፊሉን ችላ ብለው ሲተዉት፤ በዚያ በነገሯት ነገር ሃፍሳ”ረ.ዓ.”፦ ይህን ማን ነገረህ? ብላ አለቻቸው፤ ነብያችንም”ﷺ”፦ «ዐዋቂው ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አሏት፤ ይህንን ጉዳይ አምላካችን አላህ እንዲህ ይነግረናል፦
66፥3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ፡፡ እርሱንም በነገረች እና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት وَإِذْ أَسَرَّ ٱلنَّبِىُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَٰجِهِۦ حَدِيثًۭا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِۦ وَأَظْهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُۥ وَأَعْرَضَ عَنۢ بَعْضٍۢ ۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتْ مَنْ أَنۢبَأَكَ هَٰذَا ۖ قَالَ نَبَّأَنِىَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْخَبِيرُ ፤

ነጥብ አራት
“ተውበት”
አላህ በተከበረው ንግግሩ፦ ለነብያችን”ﷺ” ሁለቱ ባለቤቶቻቸው ለዓኢሻ”ረ.ዓ.” እና ለሃፍሳ”ረ.ዓ.”፦ ወደ አላህ በተውበት ብትመለሱ ልቦቻው ተዘንብለዋልና፤ አይ ካላችሁ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፣ ጂብሪልም፣ ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው። ከዚያም ባሻገር ቢፈታችሁ አላህ ከእናንተ የበለጡ ሚስቶችን ሙስሊሞች፣ አማኞች፣ ታዛዦች፣ ተጸጻቾች፣ አምላኪዎች፣ ጾመኞች፣ ፈቶች፣ ደናግልም የኾኑትን ሊያመጣለት ይችላል በማለት መለሰ፦
66፥4-5 ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና ትስማማላችሁ፡፡ በእርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፣ ጂብሪልም፣ ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው إِن تَتُوبَآ إِلَى ٱللَّهِ فَقَدْ صَغَتْ قُلُوبُكُمَا ۖ وَإِن تَظَٰهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ هُوَ مَوْلَىٰهُ وَجِبْرِيلُ وَصَٰلِحُ ٱلْمُؤْمِنِينَ ۖ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ بَعْدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ ። ቢፈታችሁ ከእናንተ የበለጡ ሚስቶችን ሙስሊሞች፣ አማኞች፣ ታዛዦች፣ ተጸጻቾች፣ አምላኪዎች፣ ጾመኞች፣ ፈቶች፣ ደናግልም የኾኑትን ጌታው ሊለውጠው ይከጀላል عَسَىٰ رَبُّهُۥٓ إِن طَلَّقَكُنَّ أَن يُبْدِلَهُۥٓ أَزْوَٰجًا خَيْرًۭا مِّنكُنَّ مُسْلِمَٰتٍۢ مُّؤْمِنَٰتٍۢ قَٰنِتَٰتٍۢ تَٰٓئِبَٰتٍ عَٰبِدَٰتٍۢ سَٰٓئِحَٰتٍۢ ثَيِّبَٰتٍۢ وَأَبْكَارًۭا ፡፡


መደምሚያ
ተፍሲሩል ኢብኑ ከሲር ኢማም ቡኻሪይ መሰረት አድገው እና ተፍሲሩል ቁርጡቢ ኢማም ሙስሊም መሰረት አድርገው ይህን ሱራህ ፈስረውቷል፤ ይህንን ወህይ መውረድ ምክንያት አራት ሙሐዲሲን አስቀምጠውታል፤ እነርሱም ኢማን ቡኻሪይ፣ ኢማም ሙስሊም፣ ኢማም አቢ ዳውድ እና ኢማም ነሳኢ ናቸው፦
1ኛ. ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 68 , ሐዲስ 17:
ዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደተናገረችው፦ ነብዩ”ﷺ” ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ጋር ትንሽ ጊዜ በመቆየት እና ከእርሷ ቤት ማር ይጠጡ ነበር፤ ስለዚህ ሃፍሳ”ረ.ዓ.” እና እኔ ፦”ነብዩ”ﷺ”
ወደ እኛ ከመጡ እርሷ፦ የመጋፊር ሽታ ሸተኸኛል እንድትል ወሰንን፤ መጋፊር በልተሃልን? ከዚያም ነብዩ”ﷺ” ከእነርሱ አንዷን ሲዘይሩ እንዲሁ በተመሳሳይ አለቻቸው፤ ነብዩም”ﷺ” ፦ “በፍፁም ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ ግን አልጠጣም” አሉ፤ ስለዚህ ይህ አንቀፅ ወረደ፦
66:1 አንተ ነቢዩ ሆይ አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን በአንተ ላይ ለምን እርም ታደርጋለህ?
66፥4 “ወደ አላህ ሁለታችሁ ብትመለሱ” ይህ የሚያመለክተው ዓኢሻ”ረ.ዓ.” እና ሃፍሳን”ረ.ዓ.” ነው፤
66፥3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ”
ማለትም “እኔ ግን ጥቂት ማር ጠጥቻለው” አሉ።
يَقُولُ سَمِعْتُ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ ابْنَةِ جَحْشٍ، وَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً، فَتَوَاصَيْتُ أَنَا وَحَفْصَةُ أَنَّ أَيَّتَنَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ، أَكَلْتَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُمَا فَقَالَتْ لَهُ ذَلِكَ، فَقَالَ ‏”‏ لاَ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ ابْنَةِ جَحْشٍ وَلَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‌‏.‏ فَنَزَلَتْ ‏{‏يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ‏}‏ إِلَى ‏{‏إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ ‏{‏وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً ‏”‌‏
2ኛ. ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 18, ሐዲስ 27:
وَحَدَّثَنِي مُحَمَّدُ بْنُ حَاتِمٍ، حَدَّثَنَا حَجَّاجُ بْنُ مُحَمَّدٍ، أَخْبَرَنَا ابْنُ جُرَيْجٍ، أَخْبَرَنِي عَطَاءٌ، أَنَّهُ سَمِعَ عُبَيْدَ بْنَ عُمَيْرٍ، يُخْبِرُ أَنَّهُ سَمِعَ عَائِشَةَ، تُخْبِرُ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ فَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً قَالَتْ فَتَوَاطَأْتُ أَنَا وَحَفْصَةُ أَنَّ أَيَّتَنَا مَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ أَكَلْتَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُمَا فَقَالَتْ ذَلِكَ لَهُ ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ وَلَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‏ ‏.‏ فَنَزَلَ ‏{‏ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ‏}‏ إِلَى قَوْلِهِ ‏{‏ إِنْ تَتُوبَا‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ ‏{‏ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً ‏”‏ ‏.‏
3ኛ. ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 27 , ሐዲስ 33:
أَخْبَرَنَا قُتَيْبَةُ، عَنْ حَجَّاجٍ، عَنِ ابْنِ جُرَيْجٍ، عَنْ عَطَاءٍ، أَنَّهُ سَمِعَ عُبَيْدَ بْنَ عُمَيْرٍ، قَالَ سَمِعْتُ عَائِشَةَ، زَوْجَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ وَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً فَتَوَاصَيْتُ وَحَفْصَةَ أَيَّتُنَا مَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُمَا فَقَالَتْ ذَلِكَ لَهُ فَقَالَ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ – وَقَالَ – لَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‏ ‏.‏ فَنَزَلَ ‏{‏ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ ‏}‏ ‏{‏ إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ ‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ ‏{‏ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا ‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاَ ‏”‏ ‏.‏ كُلُّهُ فِي حَدِيثِ عَطَاءٍ ‏.‏
4ኛ. ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 27 , ሐዲስ 46:
حَدَّثَنَا أَحْمَدُ بْنُ مُحَمَّدِ بْنِ حَنْبَلٍ، حَدَّثَنَا حَجَّاجُ بْنُ مُحَمَّدٍ، قَالَ قَالَ ابْنُ جُرَيْجٍ عَنْ عَطَاءٍ، أَنَّهُ سَمِعَ عُبَيْدَ بْنَ عُمَيْرٍ، قَالَ سَمِعْتُ عَائِشَةَ، – رضى الله عنها – زَوْجَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم تُخْبِرُ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ فَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً فَتَوَاصَيْتُ أَنَا وَحَفْصَةُ أَيَّتُنَا مَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُنَّ فَقَالَتْ لَهُ ذَلِكَ فَقَالَ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ وَلَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‏ ‏.‏ فَنَزَلَتْ ‏{‏ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ تَبْتَغِي ‏}‏ إِلَى ‏{‏ إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ ‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ رضى الله عنهما ‏{‏ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا ‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً ‏”‏ ‏.‏

እንዲህ በሰሒሕ እና በሐሠን ሪዋያህ መረዳት ነው እንጂ ሪዋያህ በሌላቸው ከሼኽ ጎግል በሚለቃቀመው ደኢፍ እና መውዱዕ ጥንቅሮች መፎተት እራስን ማታለል ነው፤ አላህ በእርሱ መንገድ ላይ እርሱን ለማግኘት እሾት ያላቸውን ሰዎች ሂዳያ ይስጣቸው ለእኛም ፅናቱን ይስጠን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የምስራች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥25 *እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው*፡፡ وَبَشِّرِ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ

"ቡሽር" بُشْر ወይም "ቡሽራ" بُشْرَىٰ የሚለው ቃል "ቡሺረ" بُشِّرَ ማለትም "አበሰረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የምስራች" ማለት ነው፤ አብሳሪ ማንነት "ሙበሺር" مُبَشِّر ሲባል ተበሳሪ ማንነቶች ደግሞ "ሙተበሽረት" مُّسْتَبْشِرَة "ተበሳሪዎች" ይባላሉ። ለምሳሌ ወደ ኢብራሂም የመጡት መላእክት ዐዋቂ በኾነ ወንድ አብስረውታል፦
11፥69 *መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በልጅ ብስራት በእርግጥ መጡለት*፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡ وَلَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ ۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَاءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ
15፥53 «አትፍራ፤ *እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ እናበስርሃለን*» አሉት፡፡ قَالُوا لَا تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَامٍ عَلِيمٍ

"እናበስርሃለን" ለሚለው ቃል የተጠቀመው የግስ መደብ "ኑበሺሩከ" نُبَشِّرُكَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ "ብስራት" የወደፊት ትንቢት የያዘ መሆኑን ኢብራሂም ከመውለዱ በፊት በተነገረው ብስራት ማወቅ ይቻላል፤ ሌላ ምሳሌ ዒሳም ከኃላው የነበረውን ተውራትን የሚያረጋግጥ እና ከእርሱ በኃላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የሚያበስር ነው፦
61፥6 የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥ እና *ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ*፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِن بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ ۖ فَلَمَّا جَاءَهُم بِالْبَيِّنَاتِ قَالُوا هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ

ሌላው ቁርኣን ከበፊቱ ለነበሩት መለኮታዊ መጽሐፍት አረጋጋጭ፣ ወቅቱን ያማከለ ሕግና ሥርአት የያዘ መመሪያ እና የወደፊቱን ሩቅ ነገር የያዘ የምስራች ነው፦
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ *እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪ እና ብስራት ሲኾን* በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
46፥12 ከበፊቱም የሙሳ መጽሐፍ መሪና ጸጋ ሲኾን አለ፡፡ *ይህም* እነዚያን የበደሉትን ሊያስጠነቅቅ በዐረብኛ ቋንቋ ሲኾን የበፊቱን አረጋጋጭ መጽሐፍ ነው፡፡ *ለበጎ አድራጊዎችም ብስራት ነው*፡፡ وَمِن قَبْلِهِ كِتَابُ مُوسَىٰ إِمَامًا وَرَحْمَةً ۚ وَهَـٰذَا كِتَابٌ مُّصَدِّقٌ لِّسَانًا عَرَبِيًّا لِّيُنذِرَ الَّذِينَ ظَلَمُوا وَبُشْرَىٰ لِلْمُحْسِنِينَ
27፥2 (ይህቸ አንቀጽ) *ለምእምናን መሪ እና ብስራት ናት*፡፡ هُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ይህም የምስራች እነዚያን እነዚያም ጣዖታትን የሚግገዟት ከመኾን እርቀው ያመኑትን እና መልካሞችንም የሠሩትን ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባት ገነት ናት፦
2፥25 *እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችንም የሠሩትን ለእነርሱ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች ያሏቸው መኾኑን አብስራቸው*፡፡ وَبَشِّرِ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ
39፥17 *እነዚያም ጣዖታትን የሚግገዟት ከመኾን የራቁ ወደ አላህም የዞሩ ለእነርሱ ብስራት አላቸው፡፡ ስለዚህ ባሮቼን አብስር*፡፡ وَالَّذِينَ اجْتَنَبُوا الطَّاغُوتَ أَن يَعْبُدُوهَا وَأَنَابُوا إِلَى اللَّهِ لَهُمُ الْبُشْرَىٰ ۚ فَبَشِّرْ عِبَادِ
57፥12 ምእመናንንና ምእምናትን በስተፊቶቻቸው፣ በቀኞቻቸውም ብርሃናቸው የሚሮጥ ሲኾን በምታያቸው ቀን ምንዳ አላቸው፡፡ *ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው* ይባላሉ፡፡ ይህ እርሱ ታላቁ ዕድል ነው፡፡ يَوْمَ تَرَى الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ يَسْعَىٰ نُورُهُم بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَانِهِم بُشْرَاكُمُ الْيَوْمَ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሙርተድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ፦ "ያቺንም እርም ያደረጋትን ነፍስ በሕግ ቢኾን እንጂ ”አትግደሉ" ይለናል፦
17:33 ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ “”አትግደሉ””፤
6:151 «ኑ፤ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር በእርሱም ያዘዛችሁን ላንብብላችሁ» በላቸው፡፡ «በእርሱ ምንንም ነገር አታጋሩ፡፡ ለወላጆችም በጎን ሥራ ሥሩ ፡፡ ልጆቻችሁንም ከድህንት ፍራቻ አትግደሉ፡፡ እኛ እናንተንም እነርሱንም እንመግባችኋለንና፡፡ መጥፎ ሥራዎችንም ከእርሷ የተገለጸውንም የተደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡ፡፡ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሕግ ቢኾን እንጂ “”አትግደሉ””፡፡
25:68 ምእመናን ማለት እነዚያም፣ ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይግገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ “”የማይገድሉት””፤ የማያመነዝሩትም ናቸው፤

ሰውን መግደል ሃራም ነው በህግ ቢሆን እንጂ፤ በኢስላም የሙስሊም ሸሪዓ ባለበት ህገ-መንግሥት ላይ ሰዎች ወንጀል ሲሰሩ ዝም ተብለው አይታዩም፤ ባይሆን በህግ ይጠየቃሉ ይገደላሉም፤ ሙስሊም የሆኑ ሰዎች ደግሞ በሶስት ወንጀሎች ምክንያት ይገደላሉ፤ ይህንን ከነብያችን ሐዲስ እንዲህ ይነበባል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 28 ሐዲስ 34
አብደላህ ኢብኑ መሱድ እንዳስተላለፈው፤ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አሉ፦ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ እኔንም የአላህ መልእክተኛ መሆኔን የመሰከረ የሙስሊም ህይወት መግደል አይቻልም ከሶስት ጉዳይ በስተቀር፦ በጋብቻ ላይ ዝሙት ከሰራ፣ የሰው ህይወት ካጠፋ እና ""ሃይማኖቱን ቀይሮ ጀመዓውን የሚከፋፍል ከሆነ በስተቀር""። قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " لاَ يَحِلُّ دَمُ امْرِئٍ مُسْلِمٍ يَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلاَّ بِإِحْدَى ثَلاَثٍ الثَّيِّبُ الزَّانِ وَالنَّفْسُ بِالنَّفْسِ وَالتَّارِكُ لِدِينِهِ الْمُفَارِقُ لِلْجَمَاعَةِ "

ሶስቱ ጉዳይ በዝርዝር ሲቀመጥ፦
1ኛ. በጋብቻ ላይ ዝሙት ከሰራ፣
2ኝ. የሰው ህይወት ካጠፋ
3ኝ. ""ሃይማኖቱን ቀይሮ ጀመዓውን የሚከፋፍል""
ሃይማኖቱን ቀይሮ ጀመዓውን የሚከፋፍል "ሙርተድ" مرتد ይባላል፤ ሙርተድ ማለት አንድ ሙስሊም ከኢስላም ወጥቶ ወደ ኩፍር በመሔድ የሙስሊሙን ጀመዓ ወደ ኩፍር የሚጠራ ሲሆን የሚሰራው ስራው ደግሞ "ኢርቲዳድ" ارتداد ይባላል፤ ሐዲሱ ላይ "አል-ሙፈሪቅ"الْمُفَارِقُ "መከፋፈል" የሚል ቃል አለ፤ አንድ ሙርተድ የሙስሊሙን ጀመዓ ከከፋፈለ በኢስላም ሸሪዓ ህገ-መንግሥት ይገደላል፤ ችግሩ ምንድን ነው? ለምሳሌ እኔና ባለቤቴ ልጃችንን 1+1=2 ብለን ሀቁን አስተማርን፤ ነገር ግን በጎን ሰራተኛችን 1+1=3 ነው ብትል ቅድሚያ በጠረጴዛ ዙርያ 1+1=3 ነው ያለችበት ሥነ-አመክንዮ ይጠየቃል፤ አይ እኔ ተመችቶኛል ስለዚህ ባጢል የሆነውን ትምህርት ማስተማሬን እቀጥላለው ካለች ያለው ምርጫ ማባረር ነው፤ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ሙርተድ በሙስሊም ጀመዓ በባጢል ትምህርት ዑማውን እከፋፍላለው ቢል ቅድሚያ በዓሊሞች ውይይት ይመከራል፤ አልሰማ ካለ ለዑማው ንፅህና ይገደላል፤ ኡስታዛችን ሷዲቅ ይህንን የተናገረበትን ሙሉውን ትምህርት ከማቅረብ ይልቅ ከፊትና ከኃላ ቆርጠው "ከኢስላም የሚወጣ ሰው ግደሉ" ብሏል ብለው ፕሮፓጋንዳቸውን መንዛት ከጀመሩ ይኸው ድፍን 5 ዓመት ሞላው፤ እንግዲያውስ ሙሉ ትምህርቱ ይህ ነበር፤ በተጨማሪ ቁርአን ስለ ሙርተድ እንዲህ ይናገራል፦
3:90 እነዚያ ከእምነታቸዉ በኋላ የካዱ፣ ከዚያም ክህደትን የጨመሩ፣ ጸጸታቸዉ ፈጽሞ ተቀባይ የላትም፥ እነዚያም የተሳሳቱ እነርሱ ናቸዉ።

በተረፈ "ቢያፈገፍጉም ያዙዋቸው፤ ማርኩዋቸው ባገኛችሁበትም ስፍራ ግደሉዋቸው" እያለ የሚናገረው በጦርነትላይ በልባቸው ኩፍር ይዘው በአፋቸው ምእመናን ነው ስላሉት ስለ ""10 መናፍቃን" እንጂ ስለ ሙርተድ እንዳልሆነ ኢብኑ አባስ"ረ.አ." በተፍሲሩ አስቀምጦታል፤ አውዱን ስናነብ የምንረዳው ስለ መናፍቃንም ነው፦
4:88-89 ""በመናፍቃንም ነገር"" አላህ በስራዎቻቸው ወደ ክሕደት የመለሳቸው ሲሆኑ ሁለት ክፍሎች የሆናችሁት ለናንተ ምን አላችሁ? አላህ ያጠመመውን ልታቀኑ ታስባላችሁን? አላህም ያሳሳተውን ሰው ለእርሱ መንገድን ፈጽሞ አታገኝለትም፤ እነርሱ እንደካዱ ብትክዱና እኩል ብትሆኑ ተመኙ! በአላህም ሃይማኖት እስከሚሰደዱ ድረስ ከእነርሱ ወዳጆችን አትያዙ፤ ቢያፈገፍጉም ያዙዋቸው፤ ማርኩዋቸው ባገኛችሁበትም ስፍራ ግደሉዋቸው፤ ከእነርሱም ወዳጅንና ረዳትን አትያዙ።

እስቲ ይህ የተነቀፈበትን የነቢያችን ሐዲስ በምን ሚዛን ይሆን ሒስ የሚሰጥበት? በምዕራባውያን የኢ-አማኝነት ዝገት ወይስ በባይብል? የሰዎችን ህይወት የሚቦረቡረው የምዕራባውያን እሳቦት የሙስሊምን ሸሪዓ ሊመዝን በፍፁም አይችልም። አይ ባይብል ነው ከተባለ እንግዲያውስ ማህበረሰው ስለሚያቆሽሽ በጋብቻ ላይ ዝሙት፣ የሰው ህይወት ማጥፋት እና ሃይማኖቱን ቀይሮ ጀመዓውን መበከል እስቲ ከራሳችሁ ባይብል እንይ፦

ነጥብ አንድ
"ዝሙት"
ሴት ልጅ በጋብቻ ጊዜ ድንግልናዋ ካልተገኘ በድንጋይ ተወግራ ትገደላለች፦
ዘዳግም 22፥21 ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች ""እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩአት""፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ከጋብቻ በፊት ለጋብቻ የታጨች ከሆነችና ግን ከሌላው ወንድ ጋር አንሶላ ብትጋፈፍ እርሷም ያቀበጣት ወንድ በድንጋይ ይወገራሉ፦
ዘዳግም 22፥23-24 ማናቸውም ሰው ድንግልና ያላትን ልጃገረድ ቢያጭ፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥ ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና ""እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው""፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ነጥብ ሁለት
"መግደል"
ኢየሱስ ፈጣሪ ለሙሴ የሰጠው ህግ ጠቅሶ ""የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል"" መባሉን ተናግሯል፦
ማቴዎስ 5፥21ለቀደሙት። አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ ""የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል""።
ዘሌዋውያን 24:17 ሰውንም እስኪሞት ድረስ የሚመታ ፈጽሞ ""ይገደል""።

ልብ አድርጉ የገደለም ሁሉ "ፍርድ ይገባዋል"" ማለት ይገደላል ማለት ነው፤ ታዲያ ኢየሱስ ሲመጣ ""የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" የሚለውን ሻረውን? በፍፁም እንኳን የገደለ ይቅርና በሰው ላይ የተቆጣ እና የተሳደበ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል ብሎ አረፈው፤ የሸንጎ ፍርድ ማለት በተሾሙ ፈራጆች የሚሰጥ የሞት ብይን ነው፦
ማቴዎስ 5:22 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ "ፍርድ ይገባዋል"፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ "የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል"፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።"

ኢየሱስ በግልፅና በማያሻ መልኩ የገደለ ይገደል ብሎ የለ እንዴ? ""በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል ብሏል፦
ራእይ 13:10 ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ ""በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል""።
ነጥብ ሶስት
"ሙርተድ"
አንድ ሰው ከቤተስብ መካከል ከአንዱ አምላክ በስተቀር ሌላ አምላክ እናምልክ ቢል ለምን አልክ ተብሎ ውይይት እናድርግ የሚባል ሳይሆን በቀጥታ ይገደላል፦
ዘዳ.13:6-11 አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው፥ አትስማውም፤ ዓይንህም አይራራለት፥ እትማረውም፥ አትሸሽገውም፤ ነገር ግን ፈጽመህ "ግደለው" וַיִּשְׁחָטֵ֖ם ፤ እርሱን ለመግደል በፊት የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን። ከግብፅ ምድርይቅርና ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።

አይደለም ወደ ሽርክ የሚጠራ በግሉ ሌላ አምላክን ሲያምልክ ከተገኘ ይገደል የሚል ወፍራም ትእዛዝ አለ፦
ዘጸ 22:20 ከእግዚአብሔር በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ "ይገደል" וְהִרְג֧וּ ።
ዘዳግም 17፥1-5 ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥ ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያንን ፈጽመህ መርምር እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ ""እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ""።

በተግባርም እስራኤላውያን ሆነ ክርስትናው በአውሮፓ ላይ እስከ 19ኛ ክፍለ-ዘመን ይህንን መርህ ይተገብሩት እንደነበር ታሪክ በወርቃማ ብዕሩ ያሰፈረው ነገር ነው፤ መጽሐፋችሁን አትመሩበትም ማለት መፅሐፋችሁ ስለ ሙርተድ አይናገርም ማለት አይደለም፤ "የእስራኤልንም አምላክ የማይፈልግ እንዲገደል መሃላ አለ፦
2ዜና 15:12-13 በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ፤ "የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ"፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ "ይገደል" ዘንድ ማሉ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
መለከት-የሚን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥25 ከእናንተም ውስጥ *ጥብቆች ምእምናት የኾኑትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምእምናት ወጣቶቻችሁ ያግባ*፡፡ وَمَن لَّمْ يَسْتَطِعْ مِنكُمْ طَوْلًا أَن يَنكِحَ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ فَمِن مَّا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُم مِّن فَتَيَاتِكُمُ الْمُؤْمِنَاتِ

“ኒካሕ” نِكَاح ማለት “ጋብቻ” ወይም “ትዳር” ማለት ሲሆን ይህም ትዳር ከሁለት ማእዘን ማግባት እንደሚቻል አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ ይነግረናል።
አንዱ “ሙህሰናት” مُحْصَنَٰت ማለት “ጥብቆች” ከሚባሉት ነው፤ "ሙህሲናት" የሚባሉት ምእመናን ከመምሉክ ናቸው፤ “መምሉክ” مَّمْلُوك ማለት “ገዢ” ወይም “ከበርቴ” አሊያም “ባለቤት” ሲሆኑ እነዚህም “ሁር” حُرّ ማለይም “ነጻ” ናቸው።
ሁለተኛው “ፈተያት” فَتَيَٰت ማለት “አገልጋዮች” ሲሆኑ "መለከት-የሚን" ናቸው፤ “መለከት-የሚን” مَلَكَتْ يَمِين ማለትም “ተገዢ” ወይም “አገልጋይ” ማለት ነው።
አላህ ምእመናን ከሆኑ ከእነዚህ ጋር መጋባት ፈቅዷል፤ ከሙህሰናት በፍትህ እኩል ማስተካከል ከተቻለ ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስትም፣ አራት አራትም ማግባት ይቻላል፤ በፍትህ እኩል ማስተካከል ካልተቻለ ከሙህሰናት አንዲቷን አሊያም ከመለከት-የሚን ማግባት ተፈቅዷል፦
4፥3 *ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ*፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡ وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا
4፥25 ከእናንተም ውስጥ *ጥብቆች ምእምናት የኾኑትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምእምናት ወጣቶቻችሁ ያግባ*፡፡ وَمَن لَّمْ يَسْتَطِعْ مِنكُمْ طَوْلًا أَن يَنكِحَ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ فَمِن مَّا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُم مِّن فَتَيَاتِكُمُ الْمُؤْمِنَاتِ
24፥32 *ከእናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን አጋቡ*፡፡ ድኾች ቢኾኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል፡፡ አላህም ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡ وَأَنكِحُوا الْأَيَامَىٰ مِنكُمْ وَالصَّالِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَائِكُمْ ۚ إِن يَكُونُوا فُقَرَاءَ يُغْنِهِمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ

እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው የሚለው ቃል ላይ የገባው “መለከት-የሚን” مَلَكَتْ يَمِين ሲሆን አገልጋዮችን ያመለክታል፤ "አጋቡ" የሚለው የግስ መደብ "አንኪሑም" َأَنْكِحُوا ሲሆን የስም መደቡ ደግሞ “ኒካሕ” نِكَاح ነው፤ ሁለቱም የረቡበት ሥርወ-ቃል "ነከሐ" نَكَحَ ማለትም "አገባ" የሚል ነው፤ ስለዚህ ከመለከት-የሚን ጋር ኒካሕ ማሰር ይቻላል ማለት ነው። የቱ ጋር ነው ቁርኣን ላይ ከመለከት-የሚን ጋር ዚና ማድረግ የተፈቀደበት? ይህ ቅጥፈት ነው። አላህ ከሙህሰናት አሊያም ከመለከት-የሚን የሚደረግ ተቃራኒ ጾታ ግንኙነት"hetro-sexual" ኒካሕ ፈቅዷል፤ ከዚያ ወሰን ያለፈ ለምሳሌ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት”homo-sexual” ወዘተ.. ወሰን ማለፍ የሆነ ዝሙት ነው፦
23፥6 *በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዟቸው ላይ ሲቀር፤ እነርሱ በእዚህ የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው*፡፡ إِلَّا عَلَىٰ أَزْوَاجِهِمْ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ فَإِنَّهُمْ غَيْرُ مَلُومِينَ فَمَنِ ابْتَغَىٰ وَرَاءَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْعَادُونَ

“ሚስቶች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “አዝዋጅ” أَزْوَاجً ሲሆን ” ዘውጅ” زَوْج የሚለው ቃል ብዜት ነው፤ ይህም ሙህሲናትን ያመለክታል፤ “መለከት-የሚን” مَلَكَتْ يَمِين ደግሞ አገልጋዮችን ያመለክታል፤ ከዚያ ውጪ ያሉት ኒካሕ የሚያደርጉ ወሰን አላፊዎች ናቸው፤ ሉጥንም ለሕዝቦቹ፦ "አስቀያሚን ሥራ" ያለው ይህንኑ ሥራ ነው፤ አላህም በሰዶማውያን ላይ የእሳት ዝናብን አዘነበባቸው፦
7፥80 *ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ «አስቀያሚን ሥራ ትሠራላችሁን በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም*፡፡» وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ أَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ
7፥ 81 *«እናንተ ከሴቶች ሌላ ወንዶችን በመከጀል በእርግጥ ትመጡባቸዋላችሁ፡፡ በእውነቱ እናንተ ወሰንን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ*» إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ شَهْوَةً مِّن دُونِ النِّسَاءِ ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ مُّسْرِفُونَ
7፥84 *በእነርሱም ላይ የእሳት ዝናብን አዘነብንባቸው፡፡ የኃጢአተኞችም መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከት*፡፡ وَأَمْطَرْنَا عَلَيْهِم مَّطَرًا ۖ فَانظُرْ كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُجْرِمِينَ
ሕጋዊ ያልሆነ ፃታዊ ግንኙነት “ዚና” زِّنَىٰٓ ማለትም “ዝሙት” ይባላል፤ "ዝሙት" ማለት ከጋብቻ በፊት እና ውጪ የሚደረግ ተራክቦ ነው፤ በቁርአን ዝሙት ብቻ ሳይሆን የዝሙት መቃረቢያዎች መዳራትንም ጨምሮ እንድንርቅ ያዘናል፤ ፍፁም ምዕመናን ማለት የማያመነዝሩትም ናቸው፦
17፥32 *ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!* وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَىٰ ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا
25:68 እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ *የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል*፡፡ وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

መለከት-የሚን “ኢስቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለትም “ግድባዊት”Exceptional” ነው። መለከት-የሚን ለማስቀረት አንደኛ ዘካህ በመስጠት ነው፦
9፥60 ግዴታ ምጽዋቶች የሚከፈሉት ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም በእስልምና ለሚለማመዱት፣ *ጫንቃዎችንም በባርነት ተገዢዎችን) ነጻ በማውጣት*፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِّنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

ሁለተኛ መሃላን ያፈረሰ ሰው ከተሰጡት ምርጫ መካከል ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፦
5፥ 89 አላህ በመሐላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፡፡ ግን መሐላዎችን ባሰባችሁት ይይዛችኋል፡፡ ማስተሰሪያውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ ዐስርን ምስኪኖች ማብላት ወይም *እርነሱን ማልበስ ወይም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው*፤ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መጾም ነው፤ ይህ በማላችሁ ጊዜ የመሐላዎቻችሁ ማካካሻ ነው፡፡ መሐላዎቻችሁንም ጠብቁ፡፡ እንደዚሁ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ያብራራል፡፡ እናንተ ልታመሰግኑ ይከጀላልና፡፡ لَا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ وَلَـٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ الْأَيْمَانَ ۖ فَكَفَّارَتُهُ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَاكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍ ۖ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَاثَةِ أَيَّامٍ ۚ ذَٰلِكَ كَفَّارَةُ أَيْمَانِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ ۚ وَاحْفَظُوا أَيْمَانَكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

ሦስተኛ ምእመንንም በስህተት የገደለ ሰው ያመነችን ጫንቃ ባሪያ ነጻ ማውጣትና ወደ ቤተሰቦቹም የምትሰጥ ጉማ ምሕረት ካላደረጉለት በስተቀር መክፈል አለበት፦
4፥92 ለምእመንም በስሕተት ካልኾነ በቀር ምእመንን መግደል አይገባውም፡፡ *ምእመንንም በስህተት የገደለ ሰው ያመነችን ጫንቃ ባሪያ ነጻ ማውጣትና ወደ ቤተሰቦቹም የምትሰጥ ጉማ ምሕረት ካላደረጉለት በስተቀር መክፈል አለበት*፡፡ وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ أَن يَقْتُلَ مُؤْمِنًا إِلَّا خَطَأً ۚ وَمَن قَتَلَ مُؤْمِنًا خَطَأً فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مُّؤْمِنَةٍ وَدِيَةٌ مُّسَلَّمَةٌ إِلَىٰ أَهْلِهِ إِلَّا أَن يَصَّدَّقُوا ۚ فَإِن كَانَ مِن قَوْمٍ عَدُوٍّ لَّكُمْ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مُّؤْمِنَةٍ ۖ وَإِن كَانَ مِن قَوْمٍ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُم مِّيثَاقٌ فَدِيَةٌ مُّسَلَّمَةٌ إِلَىٰ أَهْلِهِ وَتَحْرِيرُ رَقَبَةٍ مُّؤْمِنَةٍ ۖ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ تَوْبَةً مِّنَ اللَّهِ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነብዩ ኑሕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥14 *ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ በውስጣቸውም ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ፡፡ እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውሃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَلَبِثَ فِيهِمْ أَلْفَ سَنَةٍ إِلَّا خَمْسِينَ عَامًا فَأَخَذَهُمُ الطُّوفَانُ وَهُمْ ظَالِمُونَ

ኑሕ"ዐለይሂ ሰላም" የአላህ መልእክተኛ ነው፤ አላህ ወደ እርሱ ወሕይ አውርዷል፦
4፥163 እኛ ወደ ኑሕ እና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ
11፥36 *ወደ ኑሕም እነሆ፦ «ከሕዝቦችህ በእርግጥ ካመኑት በስተቀር ወደፊት አያምኑም፡፡ ይሠሩትም በነበሩት ክህደት አትዘን» ማለት ተወረደ፡፡* وَأُوحِيَ إِلَىٰ نُوحٍ أَنَّهُ لَن يُؤْمِنَ مِن قَوْمِكَ إِلَّا مَن قَدْ آمَنَ فَلَا تَبْتَئِسْ بِمَا كَانُوا يَفْعَلُونَ

አምላካችን አላህ ወደ ኑሕ፦ "ሕዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ" በማለት ላከው፤ እርሱም፦ "ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ" በማለት አስጠነቀቃቸው፦
71፥1 *እኛ ኑሕን «ሕዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ» በማለት ወደ ሕዝቦቹ ላክነው።* إِنَّا أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ أَنْ أَنذِرْ قَوْمَكَ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
7፥59 ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ለእናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡» لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ

ሕዝቦቹም፦ "ኑሕ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን፡፡ እኛን መከራከርህንም አበዛኸው፡፡ ከእውነተኞቹም እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው፤ አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው" አሉት፦
11፥32 *«ኑሕ ሆይ! በእርግጥ ተከራከርከን፡፡ እኛን መከራከርህንም አበዛኸው፡፡ ከእውነተኞቹም እንደሆንክ የምታስፈራራብንን ቅጣት አምጣው» አሉ*። قَالُوا يَا نُوحُ قَدْ جَادَلْتَنَا فَأَكْثَرْتَ جِدَالَنَا فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ
71፥23 አሉም *«አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው*፡፡ وَقَالُوا لَا تَذَرُنَّ آلِهَتَكُمْ وَلَا تَذَرُنَّ وَدًّا وَلَا سُوَاعًا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْرًا

ኑሕም፦ "ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው" ብሎ ወደ አላህ ተጣራ፤ አላህም ጥሪውን ተቀበለው፦
71፥26 ኑሕም አለ «ጌታዬ ሆይ! ከከሓዲዎቹ በምድር ላይ አንድንም አትተው፡፡ وَقَالَ نُوحٌ رَّبِّ لَا تَذَرْ عَلَى الْأَرْضِ مِنَ الْكَافِرِينَ دَيَّارًا
21፥76 ኑሕንም ከዚያ በፊት ጌታውን በጠራ ጊዜ አስታውስ፡፡ ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን፡፡ وَنُوحًا إِذْ نَادَىٰ مِن قَبْلُ فَاسْتَجَبْنَا لَهُ فَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ
37፥75 ኑሕም በእርግጥ ጠራን፡፡ ጥሪውን ተቀባዮቹም ምንኛ አማርን! وَلَقَدْ نَادَانَا نُوحٌ فَلَنِعْمَ الْمُجِيبُونَ

ኑሕ መርከብ ሠራ በመርከቡ ከሁሉም ሁለት ዓይነቶችን ቤተሰቦችህንም ከእነርሱ ጠፊ በመኾን ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር አስገባ፦
11፥40 ትእዛዛችንም በመጣ እና *እቶኑም በፈነዳ ጊዜ* «በእርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን» አልነው፡፡ ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَمْرُنَا وَفَارَ التَّنُّورُ قُلْنَا احْمِلْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ الْقَوْلُ وَمَنْ آمَنَ ۚ وَمَا آمَنَ مَعَهُ إِلَّا قَلِيلٌ
23፥27 ወደ እርሱም እንዲህ ስንል ላክን፦ «በተመልካችነታችንና በትእዛዛችንም ታንኳን ሥራ በመጣ እና *እቶኑ በፈነዳ ጊዜ* በውስጧ ከሁሉም ሁለት ዓይነቶችን ቤተሰቦችህንም ከእነርሱ ጠፊ በመኾን ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር፤ አግባ፡፡ በእነዚያም በበደሉት ሰዎች ነገር አታነጋግረኝ፡፡ እነርሱ ተሰጣሚዎች ናቸውና፡፡ فَأَوْحَيْنَا إِلَيْهِ أَنِ اصْنَعِ الْفُلْكَ بِأَعْيُنِنَا وَوَحْيِنَا فَإِذَا جَاءَ أَمْرُنَا وَفَارَ التَّنُّورُ ۙ فَاسْلُكْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ الْقَوْلُ مِنْهُمْ ۖ وَلَا تُخَاطِبْنِي فِي الَّذِينَ ظَلَمُوا ۖ إِنَّهُم مُّغْرَقُونَ
"እቶን" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ተኑር" تَّنُّورُ ማለት "የሚፈነዳ" ማለት ሲሆን ከምድር የፈነዳው ምንጭ ውሃ ያመለክታል፦
54፥11 *ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን*፡፡ فَفَتَحْنَا أَبْوَابَ السَّمَاءِ بِمَاءٍ مُّنْهَمِرٍ
54፥12 *የምድርንም ምንጮች አፈነዳን፡፡ ውሃውም የሰማዩና የምድሩ በእርግጥ በተወሰነ ኹነታ ላይ ተገናኘ*፡፡ وَفَجَّرْنَا الْأَرْضَ عُيُونًا فَالْتَقَى الْمَاءُ عَلَىٰ أَمْرٍ قَدْ قُدِرَ
69፥11 *እኛ ውሃው ባየለ ጊዜ በተንሻላይቱ ታንኳ ውስጥ ጫንናችሁ*፡፡ إِنَّا لَمَّا طَغَى الْمَاءُ حَمَلْنَاكُمْ فِي الْجَارِيَةِ

ከዚያ፦ "ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ፡፡ ሰማይም ሆይ ዝናብሽን ያዢ" ተባለ ውሃውም ሰረገ፤ ቅጣቱም ተፈጸም፤ ጁዲይ ማለትም አራራት በሚባልም ተራራ ላይ መርከቢቱ ተደላደለች፦
11፥44 ተባለም፡- *«ምድር ሆይ! ውሃሽን ዋጪ፡፡ ሰማይም ሆይ ዝናብሽን ያዢ፡፡ ውሃውም ሰረገ*፡፡ ቅጣቱም ተፈጸም፡፡ ጁዲይ በሚባልም ተራራ ላይ መርከቢቱ ተደላደለች፡፡ ለከሓዲዎችም ሰዎች ጥፋት ተገባቸው ጠፉ» ተባለ፡፡ وَقِيلَ يَا أَرْضُ ابْلَعِي مَاءَكِ وَيَا سَمَاءُ أَقْلِعِي وَغِيضَ الْمَاءُ وَقُضِيَ الْأَمْرُ وَاسْتَوَتْ عَلَى الْجُودِيِّ ۖ وَقِيلَ بُعْدًا لِّلْقَوْمِ الظَّالِمِينَ
21፥76 ኑሕንም ከዚያ በፊት ጌታውን በጠራ ጊዜ አስታውስ፡፡ ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ *እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን*፡፡ وَنُوحًا إِذْ نَادَىٰ مِن قَبْلُ فَاسْتَجَبْنَا لَهُ فَنَجَّيْنَاهُ وَأَهْلَهُ مِنَ الْكَرْبِ الْعَظِيمِ

"ቤተሰቦቹንም" የሚለው ይሰመርበት፤ ኢብኑ ከሲር ላይ ቂሰቱል አንቢያህን መሰረት አድርጎ ቤተሰቦቹ ልጆቹ ሲሆኑ እነርሱም፦ ሴም፣ ካም እና ያፌት ናቸው፤ አራተኛው ልጅ ያም ነው ይለናል፤ ያም በክህደቱ እንደ ቤተሰብ አይቆጠርም፦
11፥40 ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በእርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት *ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ* ጫን» አልነው፡፡ ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَمْرُنَا وَفَارَ التَّنُّورُ قُلْنَا احْمِلْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ الْقَوْلُ وَمَنْ آمَنَ ۚ وَمَا آمَنَ مَعَهُ إِلَّا قَلِيلٌ
11፥45 *ኑሕም ጌታውን ጠራ፡፡ አለም «ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ ነው*፡፡ ኪዳንህም እውነት ነው፡፡ አንተም ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ዐዋቂ ነህ፡፡» وَنَادَىٰ نُوحٌ رَّبَّهُ فَقَالَ رَبِّ إِنَّ ابْنِي مِنْ أَهْلِي وَإِنَّ وَعْدَكَ الْحَقُّ وَأَنتَ أَحْكَمُ الْحَاكِمِينَ
11፥46 *አላህም «ኑሕ ሆይ! እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም፤ እርሱ መልካም ያልሆነ ሥራ ነው፤ በርሱ ዕውቀት የሌለህንም ነገር አትጠይቀኝ፤ እኔ ከሚሳሳቱት ሰዎች እንዳትሆን እገስጽሀለሁ» አለ*፡፡ قَالَ يَا نُوحُ إِنَّهُ لَيْسَ مِنْ أَهْلِكَ ۖ إِنَّهُ عَمَلٌ غَيْرُ صَالِحٍ ۖ فَلَا تَسْأَلْنِ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۖ إِنِّي أَعِظُكَ أَن تَكُونَ مِنَ الْجَاهِلِينَ
11፥42 እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በእነርሱ ይዛቸው የምትንሻለል ስትሆን፤ ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ *«ልጄ ሆይ! ከእኛ ጋር ተሳፈር ከከሓዲዎቹም አትሁን*» ሲል ጠራው፡፡ وَهِيَ تَجْرِي بِهِمْ فِي مَوْجٍ كَالْجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ابْنَهُ وَكَانَ فِي مَعْزِلٍ يَا بُنَيَّ ارْكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ الْكَافِرِينَ
11፥43 *ልጁም «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ» አለ፡፡ አባቱም፡- «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም እርሱ ያዘነለት ካልሆነ በቀር» አለው፡፡ ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ፡፡ ከሰጣሚዎቹም ሆነ*፡፡ قَالَ سَآوِي إِلَىٰ جَبَلٍ يَعْصِمُنِي مِنَ الْمَاءِ ۚ قَالَ لَا عَاصِمَ الْيَوْمَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ إِلَّا مَن رَّحِمَ ۚ وَحَالَ بَيْنَهُمَا الْمَوْجُ فَكَانَ مِنَ الْمُغْرَقِينَ

ከዚያም የኑሕ ሚስት ኑሕን ከዳችው የእሳት ሆነች፤ እሳት የሚለው የጀሃነምን እሳት ነው፦
66፥10 *አላህ ለእነዚያ ለካዱት ሰዎች የኑሕን ሴትና የሉጥን ሴት ምሳሌ አደረገ*፡፡ ከባሮቻችን ከኾኑ ሁለት መልካም ባሪያዎች ሥር ነበሩ፡፡ ከዱዋቸውም፡፡ ከአላህም ቅጣት ከሚስቶቻቸው ምንም አልገፈተሩላቸውም፡፡ *ከገቢዎቹም ጋር «እሳትን ግቡ» ተባሉ*፡፡ ضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا لِّلَّذِينَ كَفَرُوا امْرَأَتَ نُوحٍ وَامْرَأَتَ لُوطٍ ۖ كَانَتَا تَحْتَ عَبْدَيْنِ مِنْ عِبَادِنَا صَالِحَيْنِ فَخَانَتَاهُمَا فَلَمْ يُغْنِيَا عَنْهُمَا مِنَ اللَّهِ شَيْئًا وَقِيلَ ادْخُلَا النَّارَ مَعَ الدَّاخِلِينَ
69፥31 *«ከዚያም በእሳት ውሰጥ አግቡት*፡፡ ثُمَّ الْجَحِيمَ صَلُّوهُ
3፥131 *ያችንም ለከሓዲዎች የተደገሰችውን እሳት ተጠንቀቁ*፡፡ وَاتَّقُوا النَّارَ الَّتِي أُعِدَّتْ لِلْكَافِرِينَ
ኑሕ የቆየበት ጊዜ ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ማለትም 950 ዓመት ነው፤ በቁርኣን ውስጥ እድሜው የተጠቀሰ ነብይ ኑሕ ነው፦
29፥14 *ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ በውስጣቸውም ሺህ ዓመትን አምሳ ዓመት ሲቀር ተቀመጠ፡፡ እነርሱ በዳዮች ኾነውም የውሃው ማጥለቅለቅ ያዛቸው*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَلَبِثَ فِيهِمْ أَلْفَ سَنَةٍ إِلَّا خَمْسِينَ عَامًا فَأَخَذَهُمُ الطُّوفَانُ وَهُمْ ظَالِمُونَ

ከላይ ያሉት የኑሕ ተልእኮ ምን እንደነበር አምላካችን አላህ ለነብያችን”ﷺ” ፦ "የኑሕንም ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው" በማለት ወሕይ ያወርዳል፦
10፥71 *የኑሕንም ወሬ በእነርሱ ላይ አንብብላቸው*፡፡ وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ نُوحٍ
11፥49 *ይህቺ ከሩቁ ወሬዎች ናት፡፡ ወደ አንተ እናወርዳታለን*፡፡ تِلْكَ مِنْ أَنبَاءِ الْغَيْبِ نُوحِيهَا إِلَيْكَ

“ወሬ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ነበእ” نَبَإِ ሲሆን “ነቢይ” نبي የሚለው ቃል የመጣበት ሥርወ-ቃል ነው፤ "እናወርዳታለን" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ኑሒሕ" نُوحِيهَا ሲሆን "ወሕይ" وَحْى የሚለው ቃል የረባበት "አውሓ" أَوْحَىٰٓ ነው፤ ስለዚህ አላህ ያለፈውን የሩቅ ወሬ ለነብያችን”ﷺ” መተረኩ ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው፦
11:120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር *ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ* መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሥነ-ምግባር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥25 *"መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን"*፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *"መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን"*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ

“አኽላቅ” أخلاق ማለት ሥነ-ምግባር”ethics” ማለት ሲሆን “አደብ” أدب ማለት ደግሞ ግብረ-ገብ”manners” ማለት ነው፤ አንድ ነገር ትክክል ነው ወይም ስህተት ነው፣ እውነት ነው ወይም ሐሰት ነው፣ አሊያም ክፉ ነው ወይም ጥሩ ነው የምንልበት ተስተምህሮት ሥነ-ምግባር ይሰኛል። ነገር ግን ይህ ግብረ-ገብ ከባህል ወደ ባህል፣ ከልማድ ወደ ልማድ፣ ከእምነት ወደ እምነት ይለያያል፤ አንድ ነገር ትክክል ነው ወይም ስህተት ነው፣ አሊያም እውነት ነው ወይም ሐሰት ነው የምንልበት ለሰው ልጆች የሚሆን መመዘኛ አላህ ወደ ነብያት አውርዷል፦
57፥25 *"መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን"*፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *"መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን"*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ
42፥17 አላህ ያ *"መጽሐፉን በእውነት ያወረደ ነው፡፡ ሚዛንንም እንደዚሁ*"፡፡ ሰዓቲቱ ምንአልባት ቅርብ መኾንዋን ምን ያሳውቅሃል? ٱللَّهُ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ وَٱلْمِيزَانَ ۗ وَمَا يُدْرِيكَ لَعَلَّ ٱلسَّاعَةَ قَرِيبٌۭ

"ሚዛን" مِيزَان እውነትን ከሐሰት፣ ትክክለኛውን ከስህተት፣ ሰናዩን ከእኩይ የምንለይበት መመዘኛ ነው፤ ይህ ሚዛን "ፉርቃን" فُرْقَان ይባላል፤ ቁርኣን እውነትን ከሐሰት፣ ትክክለኛውን ከስህተት፣ ሰናዩን ከእኩይ የምንለይበት ፉርቃን ነው፦
25፥1 ያ *"ፉርቃንን"* በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው፡፡ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا
3፥4 ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፡፡ *"ፉርቃንንም አወረደ"*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ ٱلْفُرْقَانَ

ለሙሳ የወረደለት ተውራትም ፉርቃን ተብሏል፦
2፥53 ሙሳንም *"መጽሐፍንና ፉርቃንንም"* ትመሩ ዘንድ በሰጠነው ጊዜ አስታውሱ፡፡ وَإِذْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْفُرْقَانَ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
21፥48 ለሙሳና ለሃሩንም *"ፉርቃንን ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው"*፡፡ وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَٰرُونَ ٱلْفُرْقَانَ وَضِيَآءًۭ وَذِكْرًۭا لِّلْمُتَّقِينَ

አላህ ለሁሉም መልእክተኞች ሕግን እና መንገድን አድርጓል፦
5፥48 ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡ በመካከላቸውም *"አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ"*፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ *"ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን"*፡፡ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

“ሕግ” የሚለው ቃል በቁርኣኑ “ሺርዓ” شِرْعَة ሲሆን “ሸሪዓ” شَرِيعَة ደግሞ “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው፤ “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ሲሆን “መንሃጅ” منہاج ማለት ነው፤ "አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ" ስለሚል፥ አንድ ነገር ትክክል ነው ወይም ስህተት ነው፣ እውነት ነው ወይም ሐሰት ነው፣ አሊያም እኩይ ነው ወይም ሰናይ ነው የምንለው አላህ ባወረደው ሕግ ስንመዝን ብቻ ነው።
በዓለማችን ላይ ባሉት አበይት የሃይማኖት መጽሐፍት ላይ የመለኮት ቃል ቅሪት ስላለ የሥነ-ምግባር ጤናማ ማህበረሰብ በመጠኑም ቢሆን ገንብቷል፤ ነገር ግን ስለ ሥነ-ምግባር ያለው የምዕራባውያን እሳቦት እና እርዮት ከሰው ዝንባሌ እና ፍልስፍና የበቀሉ ሲሆኑ፣ ከበስተኃላ የካባላ፣ የፍሪ ሜሶን እና የኢሉሚኔቲቭ ንድፈ ሃሳብ ይዟል። ዋናው አጀንዳው የመለኮት ሥነ-ምግባርን እሳቤ አጥፍቶ ለዘብተኛ ፍልስፍናን ማከናነብ ነው። አላህ ከእነርሱ ሴራና ደባ ይጠብቀን፤ በፉርቃን ያጽናን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
ዒሣ ቃል ነውን?


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኀሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው ።

ሚሽነሪዎች በራሳቸው መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ እምላክነት በማስረጃ ማስረዳት ሲያቅታቸው ዞር አሉና፦ “ቁርአን ኢሳን ቃል ይለዋል፤ ቃል ደግሞ የአላህ ባህርይ ስለሆነ አልተፈጠረም” ብለው እርፍ አሉት፤ ወደተነሱት ጥቅሶች ከመሞገቴ በፊት ስለ ቃል ለመግቢያ ያክል ልበል፤ “ከላም” كَلَٰم የሚለው ቃል “ከለመ” كَلَّمَ ማለትም “ተናገረ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ንግግር” ማለት ነው፤ “ከሊማህ” كَلِمَة ደግሞ የከላም አንስታይ ሲሆን ነው፤ የአላህ ንግግር በሁለት ይከፈላል፤ እርሱም፦ ከላም ተክውኒይ እና ከላም ተሸሪዒይ ነው፤ ከላም ተክውኒይ ማለት አላህ ፍጥረታትን ሲፈጥር “ሁን” በሚለው “ንግግር” ነው የሚያስገኘው ፤ ይህ ንግግሩ “ከላም ተክውኒይ” ይባላል። ከላም ተሸሪዒይ ማለት ደግሞ አላህ ወደ ነቢያቶቹ ለማስተላለፍ የሚያወርደው ሸሪዓዊ ህግ፣ ትእዛዝ፣ መልእክት፣ የምስራች ሆነ የሩቅ ወሬ ነው፤ ይህም ንግግር “ከላም ተሸሪዒይ” ይባላል፤ ይህንን እሳቤ ይዘን ወደተነሱት ጥቅሶች እንሞግት፦

ሙግት አንድ
“የምስራች ቃል”
3:45 መላእክት ያሉትን አስታዉስ ፡- መርየም ሆይ አላህ ከእርሱ مِنْهُ በሆነዉ ቃላት بِكَلِمَةٍ ፣ ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣ ከባለማሎችም በሆነ “ያበስረሻል”፤

“ዩበሺሩኪ ቢከሊመቲን” يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ “በቃላት ያበስርሻል” የሚለው ሃረግ ይሰመርበት፤ አላህ መርየምን ምን በሚል የምስራች ቃል ነው ያበሰራት? ስንል ከእርሱ በሆነዉ የምስራች ቃል ነው፤ ይህም የምስራች ቃል፦
1. ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ፣
2. በዚህ ዓለምና በመጨረሻዉም ዓለም የተከበረ፣
3. ከባለማሎችም የሆነ መሆኑ ነው።
እዚህ አውድ ላይ ኢሳ ቃል ነው የሚል ሽታው እንኳን የለም፤ ከእዛ ይልቅ መርየም ከአላህ በሆነው የምስራች ቃል መበሰሯን የሚያመለክት ቢሆን እንጂ፤ የኢሳ እናት ከአላህ በሆነው ቃል መበሰሯ ኢሳ ቃል ካሰኘማ የየህያህ አባት ከአላህ በሆነው የምስራች ቃል መበሰሩ የህያህን ቃል ያደርገው ነበር፦
3:39 እርሱም በጸሎት ማድረሻዉ ክፍል ቆሞ ሲጸልይ መላእክት ጠሩት። አላህ በየሕያ “ከአላህ በሆነ ቃል” كَلِمَةٍ የሚያረጋግጥ ጌታም ድንግልም፣ ከደጋጐቹ ነቢይም ሲሆን ያበስርሃል፤

አላህ ዘከርያን ምን በሚል የምስራች ቃል ነው ያበሰረው? ስንል ከእርሱ በሆነዉ የምስራች ቃል ነው፤ ይህም የምስራች ቃል፦
1.”ሠይድ” سَيِّد ማለትም “ክቡር”the noble”
2. “ድንግልም”፣
3. ከደጋጐቹ ነቢይም መሆኑን ነው።
እዚህ አውድ ላይ የህያህ ቃል ነው የሚል ሽታው እንደሌለ እና ከእዛ ይልቅ ዘከርያ ከአላህ በሆነው የምስራች ቃል መበሰሩን የሚያመለክት መሆኑን ካየን የኢሳንም በዚህ ስሌትና ቀመር እንረዳዋለን እንጂ የህያን ጥሎ ኢሳን አንጠልጥሎ መሞገት ውሃ የሚቋጥር ሙግት አይደለም። መርየምም በመልአኩ የተነገረውን የጌታዋን ቃላት አረጋግጣለች፦                                                    
66፥12 የዒምራንን ልጅ መርየምንም ያችን ብልቷን የጠበቀችውን ምሳሌ አደረገ፡፡ በእርሱም ውስጥ ከመንፈሳችን ነፍፋን፡፡ በጌታዋ ቃላትና በመጻሕፍቱም አረጋገጠች፡፡ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡
ሙግት ሁለት
“የይሁን ቃል”
4:171 እላንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም وَكَلِمَتُهُ ከእርሱ مِنْهُ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፤

እዚህ አንቀጽ ላይ *ወከሊመቱል ቃሃ ኢላ መርየም* وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ ማለትም "ወደ መርየም የጣላት ቃል ነው” የሚለው ሃረግ ይሰመርበት፤ ታዲያ አላህ ወደ መርየም የጣለው ሁን የሚል ቃል ኢሳ እንዲፈጠር አይደለምን? እርሷስ ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? ብላ ለጠየቀች ጥያቄ “ቃል ከሰማይ ወርዶ ያንቺን ስጋ ይለብሳል ነው ያላት? በፍፁም፤ ከዛ ይልቅ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል” የሚል ነው፦
3፥47 ፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ *አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል* فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ አላት፡፡

አላህ መርየም ማህፀን ያለውን የእንቁላል ህዋስ በቃሉ ሁን ሲለው ኢሳ ያለ አባት ተፈጠረ፤ አላህ ኢሳን በቃሉ ስለፈጠረው ከአላህ የተወለደ የእርሱ ልጅ አይባልም፤ ባይሆን የይሁን ቃል ውጤት ቢሆን እንጂ፦
19:35 ለአላህ “ልጅን መያዝ አይገባዉም”፤ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፤ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለዉ “ኹን” كُنْ ነዉ ውዲያዉም ይኾናል።
2:116-17 “አላህም ልጅ አለው አሉ”፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው፡፡ ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው፡- «ኹን كُنْ ነው፤» ወዲያውም ይኾናል፡፡

ኢሳ ብቻ ሳይሆን በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፤ አላህ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ «ኹን» كُنْ ነው የሚለው ወዲያውም ይኾናል፤ የአደምን አካል ከአፈር ሁን ሲለው ህያው ሰው እንዳረገ ሁሉ የኢሳንም አካል ከመርየም ያለ ተራክቦ ያለ የወንድ የዘር ህዋስ ሁን በሚል ቃል ፈጥሮታል፦
3:59 አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ፥ እንደ አዳም ብጤ ነዉ፤ ከዐፈር ፈጠረዉ፤ ከዚያም ለእርሱ ሁን كُنْ አለዉ፥ ሆነም።

ታዲያ ለምን አደምን ቃል ነው አላላችሁትም? አላህ ማንኛውንም ነገር ሲፈጥር በቃሉ “ኩን” كُنْ ሁን ማለት ነው ወዲያው ይሆናል፦
16:40 ለማንኛውም ነገር መሆኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለርሱ ሁን كُنْ ማለት ብቻ ነው፤ ወዲያውም ይሆናል።
36:82 ነገሩም አንዳች ባሻ ጊዜ ሁን كُنْ ማለት ነው ወዲያው ይሆናልም።
40:68 አንዳችን ነገር ባሻም ጊዜ የሚለው ሁን كُنْ ነው፤ ወዲያውም ይሆናል።

ሙግት ሦስት
"እውነተኛ ቃል"
19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው፡፡ *ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው*፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ ٱلْحَقِّ ٱلَّذِى فِيهِ يَمْتَرُونَ

“የምተሩነ” يَمْتَرُونَ ማለትም “የሚከራከሩበት” የሚለው የግስ መደብ ይሰመርበት፤ ይህ “መከራከር” የሚለው ቃል “ሚርያህ” مِرْيَة ሲሆን “ጭቅጭቅ” “ንትርክ” ክርክር” ማለት ነው፤ በዒሳ ጉዳይ ሰዎች በመወዛገብ መጨቃጨቃቸውን፣ መነታረካቸውን እና መከራከራቸውን ያሳያል፤ ልብ አድርግ “ያ እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው” አላለም፤ ያንን ቢል ኖሮ ዒሳ እውነተኛ ቃል ብለን እንደመድም ነበር፤ ነገር ግን የሚለው “ያ “በ”እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው” የሚል ነው፤ “እርሱ” በሚለው ቃል ላይ “በ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህ የሚያመለክተው ስለ ዒሳ አላህ የነገረን ንግግር ሁሉ እውነተኛ ቃል ነው ማለት ነው፤ “በ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ፊ” فِي  ሲሆን “ስለ”about” ማለት ነው፦ That is Jesus, son of Mary. ˹And this is˺ a word of truth, “about” which they dispute. ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት
ነጥብ አንድ
““ቀሰስ””
“ቀሰስ” قَصَص የሚለው ቃል “ቀሰሰ” قصص “ተረከ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “ትረካ” ማለት ነው፤ አላህ ሁሉን የሚያይ፣ ሁሉን የሚሰማና ሁሉን የሚያውቅ ስለሆነ ያለፈውን ክስተት “ነቁስሱ አለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ “እንተርክልሃለን” በማለት በነብያችን”ﷺ” ላይ ይተርካል፦
11:120 ከመልክተኞቹም “ወሬዎች” ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በርሱ የምናረካበትን *“እንተርክልሃለን”* نَقُصُّ عَلَيْكَ፤
20:99 እንደዚሁ በእርግጥ ካለፉት ወሬዎች በአንተ ላይ *“እንተርካለን”* نَقُصُّ عَلَيْكَ፤

ስለዚህ ከመልክተኞች ታሪክ አንዱ የዒሳ ታሪክ ስለሆነ ይህ ታሪክ ሲከሰት ነብያችን”ﷺ” በህልውና ደረጃ ስላልነበሩ ሁሉን ዐዋቂው አምላክ ለነብያችን”ﷺ” ይህንን ታሪክ ያወርዳል፦
3:44 *”ይህ ወደ አንተ የምናወርደዉ የሆነ ከሩቅ ወሬዎች ነዉ”*፤ መርየምንም ማን እንደሚያሳድግ ብርዖቻቸዉን ለዕጣ በጣሉ ጊዜ *”እነርሱ ዘንድ አልነበርክም፤ በሚከራከሩም ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም”*።

ነጥብ ሁለት
“ዒሳ”
አላህ ስለ ዒሳ ማንነት የሚነግረን አፈጣጠሩንም ጭምር ነው፦
3፥59 *”አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው”*፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

አደም ከአፈር የተፈጠረ ሲሆን ዒሳ ደግሞ ከመርየም የተፈጠረ ነው፣ ታዲያ ሁለቱ የተመሳሰለበት ነገር ምንድን ነው? ስንል፤ ሁለቱ የተመሳሰሉበት ነጥብ የተፈጠሩበት ንጥረ-ነገር ሳይሆን የተፈጠሩበት ሁኔታ ነው፣ ሁለቱም በታምር ሁን በሚለው ቃል መፈጠራቸው ነው፤ “ሁ” هُ ማለት “እርሱ”it” ማለት ሲሆን ንጥረ-ነገሩን የሚያሳይ ነው፣ ለአፈሩና ለማርያም ማህጸን የሚያመሳስላቸው ነገር ሁኔታ ነው፣ ለሁለቱም “ኩን” كُنْ በሚል ትዕዛዛዊ-ግስ “imperative verb” መፈጠራቸው ነው፣ ይህ ከተዓምራቶችና ጥበብን ከያዘው ተግሳጽ ሲኾን አላህ በነብያችን”ﷺ” ላይ ይተርከዋል፦
3፥58 *”ይህ ከተዓምራቶችና ጥበብን ከያዘው ተግሳጽ ሲኾን በአንተ ላይ እናነበዋለን”*፡፡ ذَٰلِكَ نَتْلُوهُ عَلَيْكَ مِنَ ٱلْـَٔايَٰتِ وَٱلذِّكْرِ ٱلْحَكِيمِ

ይህ ስለ ዒሳ አላህ የሚናገረው ከራሱ ዘንድ የኾነ  እውነት ነው፤ ዕውቀቱ ከመጣ በኋላ በዒሳ የተከራከሩህን ሰዎችን «ኑ፤ ልጆቻችንንና ልጆቻችሁን፣ ሴቶቻችንንና ሴቶቻችሁንም፣ ነፍሶቻችንንና ነፍሶቻችሁንም እንጥራ፡፡ ከዚያም አጥብቀን አላህን እንለምን፤ የአላህንም ቁጣ በውሸታሞቹ ላይ እናድርግ» የሚል ተግዳሮት ያቀርብባቸዋል፦
3፤60 *”ይህ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት ነው”*፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን፡፡ ٱلْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْمُمْتَرِينَ
3፥61 *”ዕውቀቱም ከመጣልህ በኋላ በእርሱ(በዒሳ) የተከራከሩህን ሰዎች”* «ኑ፤ ልጆቻችንንና ልጆቻችሁን፣ ሴቶቻችንንና ሴቶቻችሁንም፣ ነፍሶቻችንንና ነፍሶቻችሁንም እንጥራ፡፡ ከዚያም አጥብቀን አላህን እንለምን፤ የአላህንም ቁጣ በውሸታሞቹ ላይ እናድርግ» በላቸው፡፡ فَمَنْ حَآجَّكَ فِيهِ مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ فَقُلْ تَعَالَوْا۟ نَدْعُ أَبْنَآءَنَا وَأَبْنَآءَكُمْ وَنِسَآءَنَا وَنِسَآءَكُمْ وَأَنفُسَنَا وَأَنفُسَكُمْ ثُمَّ نَبْتَهِلْ فَنَجْعَل لَّعْنَتَ ٱللَّهِ عَلَى ٱلْكَٰذِبِينَ

ስለ ዒሳ ማንነት እርግጠኛ ዕውቀት የላቸውም። አላህ ስለ ዒሳ ማንነት የተናገራቸው እውነተኛ ቃል ብዙ ማቅረብ ይቻል ነበር፤ ለናሙና ያክል ይህ በቂ ነው፤ ይህ ስለ ዒሳ ትረካ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው፦
3፥62 *”ይህ እርሱ በእርግጥ እውነተኛ ታሪክ ነው”*፡፡ አምላክም ከአላህ በስተቀር ምንም የለም፡፡ አላህም እርሱ በእርግጥ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْقَصَصُ ٱلْحَقُّ ۚ وَمَا مِنْ إِلَٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

“እውነተኛ ቃል ነው” የሚለው ኢየሱስ እውነተኛ ቃል መሆኑን ያሳያል ከተባለ “እውነተኛ ታሪክ ነው” የሚለውን ኢየሱስ እውነተኛ ታሪክ ነው ለምን አትሉም? ይህ ውሃ የሚቋጥርና የሚያነሳ ሙግት አይደለም፤ ስለዚህ አላህ ስለ ዒሳ የነገረን ቃልና ታሪክ እውነተኛ ቃልና ታሪክ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
ገለባ ክስ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፡95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ ፡፡

መግቢያ
ለእስልምና መልስ በሚል ድህረ-ገፅ ላይ የነቢያችንን"ﷺ" ነብይነትን ከንቱ ለማድረግ ሳም ሻሙስ የተባለ ተሳላቂ ነብያችን"ﷺ" ትንቢት ተናግረው ያ ትንቢት እንዳልተፈፀመና አንድ ነብይ ትንቢት ተናግሮ ያ ትንቢት ካልተፈፀመ ሐሳዌ ነብይ እንደሚያስብለው ሁሉ ነብያችንን"ﷺ" ሐሳዌ ነብይ ለማድረግ ወሊአዑዙቢላህ ሲቃጣው ይታያል፤ አንድ ሐሳዌ ነብይ ነብይነቱ ውድቅ የሚሆንበት በሁለት ምክንያት ነው፤ አንደኛ የሚናገረው ከገዛ ልቡ ከሆነ እና ሁለተኛ ከሸይጣን ከሆነ ነው፤ ነገር ግን ነብያችን"ﷺ" ከገዛ ልባችው ወይም ከሌላ አካል አላህ ካላቸው ውጪ ምንም እንደማይናገሩ ለተሳላቂዎች ትችት በቅቶላቸዋል፦
53፥3-4 ከልብ ወለድም አይናገርም وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلْهَوَىٰٓ ፡፡
እርሱ ንግግሩ የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْىٌۭ يُوحَىٰ ፡፡
69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን በቀጠፈ ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

ይህንን እሳቤ ይዘን በነቢያችንን"ﷺ" ላይ የተሰጡት ገለባ ክሶች አንድ በአንድ በአላህ ፈቃድ ጥርስ እና ምላሱን እየነቀስን ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናየዋለን፦
ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 39, ሐዲስ 6
የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ በታላቁ ጦርነት እና በከተማይቱ ውድቀት መካከል ያለው ጊዜ ስድስት ዓመት ነው፤ በሰባተኛው ዓመት ደጃል ይወጣል፤ ዘገባው ደኢፍ ነው أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ بَيْنَ الْمَلْحَمَةِ وَفَتْحِ الْمَدِينَةِ سِتُّ سِنِينَ وَيَخْرُجُ الْمَسِيحُ الدَّجَّالُ فِي السَّابِعَةِ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو دَاوُدَ هَذَا أَصَحُّ مِنْ حَدِيثِ عِيسَى ‏.‏ ضعيف ።

ትችቱ ሲጀምር፦ "ቆንስጣንጥኒያ የወደቀችው እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ግንቦት 29 በ 1453 AD ነው፤ ከ 1453-1461 ደጃል መምጣት ነበረበት፤ ይህ ትንቢት ሳይፈፀም ይኸው 556 ዓመት አስቆጠረ፤ ስለዚህ ትንቢቱ ከሽፏል" ወሊአዑዙቢላህ፤ ሲጀመር ሐዲሱ ላይ "አል-መዲናህ" الْمَدِينَةِ ማለትም "ከተማይቱ" አለ እንጂ በስም መቼ ተጠቀሰ? ሲቀጥል ከተማይቱ የሚለው ቆንስጣንጥኒያ ብንል እንኳን በሰለፎች አረዳድ ቆንስጣንጥኒያ መላውን አውሮፓ እንጂ ኦቶማን ግንቦት 29 1453 AD የተቆጣጠራትን ከተማ ነው ማን ነው ያለው?፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 167
ጃቢር አለ፦ ደጃል አይመጣም እናንተ ከሮማዎች ሳትታገሉ قَالَ جَابِرٌ فَمَا يَخْرُجُ الدَّجَّالُ حَتَّى تُفْتَحَ الرُّومُ ‏ ።

እንግዲህ ከተማይቱ የሚለው በዚህ ሪዋያ ሮማዎች ማለትም አውሮፓውያን እንደሆኑ ስለተገለፀ ኦቶማን የያዛት ከተማት ናት የሚለው ገለባ ክስ ድባቅ ይገባል። ሲሰልስ ሐዲሱ ደረጃው በሸኽ አልባኒ ከመነሻው "ደኢፍ" ضعيف ነው ተብሎ መዝጊያው ላይ ተቀምጧል፤ የሚሽነሪዎች ትልቁ ችግራቸው አንደኛ ታማኝ የሆኑ ምንጮች አለመጠቀማቸው ሲሆን ሁለተኛ የኢስላም ሥረ-መሰረቱ"orgin" አረቢኛው እያለ ከጎግል በሚገኘው ትርጉም ላይ መንጠልጠላቸው ነው፤ ሚሽነሪዎች ሥነ-ሐዲስ ጥናት መሰረታዊ ጭብጦች ለማወቅ ፍላጎቱም የላቸውም፤ ምክንያቱም ኃሳውያን ሚሽነሪዎች ኃሳዊ ትምህርታቸው ጽርፈት ማለትም ክህደት ነውና፤ ለዛ ነው ዓሊሞቻችን ያስቀመጡትን የደርስ መዋቅርና መርሃ ግብር ዕቡይ ተግዳሮት የሚሆንባቸው፤ እኔ ለአንባቢያን ስለ ሐዲስ በግርድፉና በሌጣው ከሙስጠለሑል ሐዲስ ልጀምር፤ “ሙስጠለሑል ሐዲስ” مُصْطَلَحُ الحَدِيْث‌‎ ማለት የሐዲስ ስያሜ”Hadith terminology” ናቸው፤ እነርሱም፦ ሰሒሕ፣ ሐሠን፣ ደኢፍ እና መውዱዕ ናቸው፤ ከላይ የተተቸበት ሐዲስ ደኢፍ ይባላል። “ደኢፍ” ضَعِيْف ማለት “ደካማ”weak” ማለት ሲሆን አንድን ዘገባ ደካማ የሚያሰኘው ወደ ሙሐዲስ የሚመጣበት አካሔድ ደካማ መሆኑ ነው። “ሙሐዲስ”محديث‎ ማለት “ዘጋቢ”collector” ማለት ሲሆን እነዚህም ሙሐዲሲን ኢማም ቡኻሪይ፣ ኢማም ሙስሊም፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጃህ፣ አቢ ዳውድ፣ ነሳኢ ወዘተ ናቸው፤ አንድ ዘገባ ደካማ ነው የሚያሰኘው አምስት ሸርጦች አሉት፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ሙአለቅ”
“ሙአለቅ” مُعَلَّق ማለት በሙሐዲስ እና በነብያችን”ﷺ” መካከል ምንም አይነት ተራኪና ትረካ ሳይኖር ሲቀር “ሙአለቅ” ይባላል።
2ኛ. “ሙርሰል”
“ሙርሠል”مُرْسَل ማለት በነብያችን”ﷺ” እና በዘጋቢው መካከል ተራኪ ከሌለው ግን ትረካ ካለው “ሙርሰል” ይባላል።
3ኛ. “ሙንቀጢዕ”
“ሙንቀጢዕ” مُنْقَطِع ማለት በነብያችን”ﷺ” እና በተራኪው መካከል ትረካ ከሌለው “ሙንቀጢዕ” ይባላል።
4ኛ. “ሙንከር”
“ሙንከር” مُنْكَر በደካማ ተራኪ ተተርኮ ትረካው ከሰሒሕ ዘገባ ጋር ከተጋጨ “ሙንከር” ይባላል።
5ኛ. “ሙጠሪብ”
“ሙጠሪብ” مُضْطَرِب ማለት አንድ ሐዲስ የተቃረኑ የዘገባ ሰነዶች ሲኖሩት ወይንም ዘገባው የተቃረኑ መትኖች ሲኖሩት “ሙጠሪብ” ይባላል።

ይህ ትውልድ የኢስላም ታሪክ ምፀት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይላል፤ ሚሽነሪዎች እየቀጠፉ አይኖሯትም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።