ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሦስት
"አመክንዮ"
“ዐቅል” عَقْل ማለት እንደየ ዐውዱ "አመክንዮ" "ግንዛቤ" "አእምሮ" ማለት ነው፥ የአመክንዮ አውራ እና አንኳር ነጥብ ሙግት ነው። ወደ አሏህ ስንጣራ መልካም የሆነ ስሙር ሙግት መጠቀም አለብን፦
16፥125 *”ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃት እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ በዚያችም እርሷ መልካም በኾነችው ዘዴ ተሟገቷቸው”*፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ وَجَادِلْهُم بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተሟገት” ለሚለው ቃል የገባው ቃል “ጃዲል” جَادِلْ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ “ጀደል” جَدَل ማለት እራሱ "ሙግት”argument” ማለት ነው። "መንጢቅ" مَنْطِق ማለት "ሥነ-አመክንዮ" ማለት ነው፥ በሥነ-አመክንዮ ጥናት"Logic" ውስጥ "ሙግት" ዐቢይ ጭብጥ ነው። የሙግት አወቃቀር፣ አደረጃጀት፣ አሰላለፍ እና አሰነዛዘር ተረድቶ ወደ አሏህ መጣራት ስሙር ሙግት"Valid argument" ነው፦
29፥46 *"የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ሙግት እንጂ አትሟገቱ! ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር"*። وَلَا تُجَادِلُوا أَهْلَ الْكِتَابِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِلَّا الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ

"እነዚያን የበደሉት" የተባሉት ከአህሉል ኪታብ መካከል ዕውር ድንብር የሆነ ጸለምተኛ አመለካከል ያላቸው ናቸው፥ ስሙር ሙግት መልካም የሆነ ሙግት ነው። በ 16፥125 እና 29፥46 ላይ "አሕሠን" أَحْسَن የሚለው ገላጭ ቅጽል "ሐሠን" حَسَن ለሚለው ጡዘታዊ ደረጃ"Superlative Degree" የመጣ ሲሆን መልካም ሙግት በውስጡ ሥነ-ምግባን እንደሚያቅፍ ፍትንውና ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።

ነጥብ አራት
"ምግባር"
"ኹሉቅ" خُلُق ማለት "ምግባር" "ጠባይ" ማለት ሲሆን የኹልቅ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አኽላቅ" أَخْلَاق ነው፦
68፥4 *አንተም “በታላቅ ጠባይ” ላይ ነህ"*። وَإِنَّكَ لَعَلَىٰ خُلُقٍ عَظِيمٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጠባይ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ኹሉቅ” خُلُق መሆኑን ልብ አድርግ! መልካም "ሥነ-ምግባር”ethics” ማለት "ትህትና" "ትእግስት" "አክብሮት" "ሥነ-ሥርዓት"Discipline" ወዘተ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” የተላኩት ይህንን መልካም ሥነ-ምግባር ሊያሟሉ ነው፦
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 273
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“እኔ የተላኩትን መልካም ሥነ-ምግባርን ላሟላ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ صَالِحَ الأَخْلاق

እዚህ ሐዲስ ላይ "ሥነ-ምግባር" ለሚለው የገባው ቃል "አኽላቅ" أَخْلَاق ነው። ገርን ጠባይ የሰው መልካም አኽላቅ ነው፦
7፥199 *"ገርን ጠባይ ያዝ! በመልካምም እዘዝ፡፡ ባለጌዎቹንም ተዋቸው"*፡፡ خُذِ الْعَفْوَ وَأْمُرْ بِالْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ الْجَاهِلِينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 165
ዐብደሏህ ኢብኑ አዝ-ዙበይር እንደተናገረው፦ *"ገርን ጠባይ ያዝ! በመልካምም እዘዝ" የሚለውን አሏህ ያወረደው ስለ ሰው አኽላቅ እንጂ ሌላ አይደለም"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ الزُّبَيْرِ، ‏{‏خُذِ الْعَفْوَ وَأْمُرْ بِالْعُرْفِ‏}‏ قَالَ مَا أَنْزَلَ اللَّهُ إِلاَّ فِي أَخْلاَقِ النَّاسِ‏.‏

መዘራረጥ፣ መነዋወር፣ መበሻሸቅ፣ ማብጠልጠቅ፣ ማበሻቀጥ የዋልጌ እና የባለጌ መገለጫ ነው። ከባለጌዎች ጋር ጊዜን፣ ጉልበትን እና ዐቅምን ማባከን ስለሌለብን "ባለጌዎቹንም ተዋቸው" የሚል ትእዛዝ አለ። እንግዲህ የደዕዋህ ግብና ዓላማው፥ ፋይዳና ሚናው ሰዎችን ወደ አሏህ በመልካም ሥነ-ምግባር መጣራት ነው፦
41፥33 *"ወደ አላህ ከጠራ እና መልካምንም ከሠራ እና «እኔ ከሙሥሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?* وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ
41፥34 *"መልካሚቱ እና ክፉይቱም ጠባይ አይተካከሉም፡፡ በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ጠባይ መጥፎይቱን ገፍትር፡፡ ያን ጊዜ ያ በአንተ እና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ ይኾናል"*፡፡ وَلَا تَسْتَوِي الْحَسَنَةُ وَلَا السَّيِّئَةُ ۚ ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ فَإِذَا الَّذِي بَيْنَكَ وَبَيْنَهُ عَدَاوَةٌ كَأَنَّهُ وَلِيٌّ حَمِيمٌ
41፥35 *"ይህችንም ጠባይ እነዚያ የታገሱት እንጅ ሌላው አያገኛትም፡፡ የትልቅም ዕድል ባለቤት እንጅ ማንም አይገጠማትም"*፡፡ وَمَا يُلَقَّاهَا إِلَّا الَّذِينَ صَبَرُوا وَمَا يُلَقَّاهَا إِلَّا ذُو حَظٍّ عَظِيمٍ

መልካሚቱ ጠባይ መጥፎይቱን ላይ ሲለቀቅ ደዕዋህ የምንጠራው ጠበኛ አሊያም ፀረኛ ሰው እንደ አዛኝ ዘመድ የመሆን አጋጣሚው ሰፊ ነው። ይህችንም ጠባይ እነዚያ የታገሱት እንጅ ሌላው አያገኛትም፥ የትልቅም ዕድል ባለቤት እንጅ ማንም አይገጠማትም። አንድ ዳዒ ወደ ሐቅ ከጠራ ሐቁን የተቀበለው ሰው ከሚያገኘው አጅር ላይ ሳይጎድል በተመሳሳይ ያገኛል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 206
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ማንም ወደ ምሪት የሚጣራ ጠሪ ጥሪውን የተከተሉት ከሚያገኙትን ምንዳ ከእነርሱ ላይ ሳይጓደል በተመሳሳይ ያገኛል”። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏ “‏ مَنْ دَعَا إِلَى هُدًى كَانَ لَهُ مِنَ الأَجْرِ مِثْلُ أُجُورِ مَنِ اتَّبَعَهُ لاَ يَنْقُصُ ذَلِكَ مِنْ أُجُورِهِمْ شَيْئًا ‏”‏ ‏.‏

አምላካችን አሏህ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በአመክንዮ እና በመልካም ምግባር ወደ እርሱ የምንጣራ ዳዒዎች ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እስማኤላውያን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

43፥28 *"በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ በአንድ አምላክ የማመን ቀሪ ቃል አደረጋት"*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةًۢ بَاقِيَةًۭ فِى عَقِبِهِۦ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

"ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት "አንዱን አምላክ አምላኪ፣ ተገዢ እና ታዛዥ" ማለት ነው፥ ኢብራሂም እና ልጁ ኢሥማዒል አሏህን፦ “ጌታችን ሆይ! ለአንተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች ሕዝቦችን አድርግ” ብለው ለምነዋል፦
2፥128 *«ጌታችን ሆይ! ለአንተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች ሕዝቦችን አድርግ»*። رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ

ከዘሮቻቸውም ለአሏህ “ሙሥሊሚን” مُسْلِمَيْن አድርግ ብለው ፀልየዋል፥ “ሙሥሊሚን” مُسْلِمَيْن የሚለው "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን "አምላኪዎች፣ ተገዢዎች እና ታዛዦች" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ይህንን የአንድ አምላክ እሳቤ በኢብራሂም ዝርዮች በእስማኤላውያን ዘንድ አድርጓል፦
43፥28 *"በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ በአንድ አምላክ የማመን ቀሪ ቃል አደረጋት"*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةًۢ بَاقِيَةًۭ فِى عَقِبِهِۦ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

እስማኤላውያን "አንዱ አምላክ አንድ ማንነት ነው" የሚለው እሳቤ ከአባታቸው ከኢብራሂም ያገኙት ቀሪ ቃል ነው። ከነቢያችን"ﷺ" መላክ በፊት ቅዱስ ኤፍሬም ከ 306-373 ድኅረ-ልደት በኖረበት ዘመን ይኖር የነበረ አባ ሕርያቆስ ስለ እስማኤላውያን እንዲህ ይላል፦
"በሚስጥረ ሥላሴ እግዚአብሔር በስም፣ በግብር፣ በአካል ሦስት በባሕርይ፣ በመለኮት፣ በህልውና አንድ መሆኑን እየገለጠ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ መሆኑን እየሰበከ *"አንድ ገጽ" የሚሉትን አይሁድን፣ ሰባልስዮን፣ "እስማኤላውያንን"* ወልድ ፍጡር የሚለውን አርዮስን፥ መንፈስ ቅዱስ ሕጹጽ ነው መቅዶንዮስን ሎሎችንም መናፍቃንን ከነወገኖቻቸው ይቃወማል"። (ሃይማኖተ አበው)

እስማኤላውያን እና አይሁዳውያን አምላክ "አንድ ገጽ" ማለታቸውን ይህ ማስረጃ ነው፥ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይም ለጥቆ እንዲህ ይላል፦
"ክፉዎች አይሁድ ባለማወቃቸው "የእግዚአብሔርን "ገጽ" እና አካል አንድ ነው የሚሉ በደለኞችን፥ የእስማኤል ወገኖችንም እነሆ እንሰማቸዋለን ልቦናቸውን ያሳወሩ ናቸው"*። ቅዳሴ ማርያም ገፅ 69

"ገጽ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል በግሪኩ "ፕሮሶፖን" πρόσωπον ሲሆን "ቅዋሜ-ማንነት"person" ማለት ነው። እስማኤላውያን እና አይሁዳውያን "አንዱ አምላክ አንድ ማንነት ነው" የሚል እሳቤ ያላቸው ከአባታቸው ከኢብራሂም የተማሩት ነው፦
ዘፍ 18፥18-19 ጽድቅን እና ፍርድን በማድረግ *የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹን እና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው*።

"ልጆቹን እና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና" የሚለው ይሰመርበት። የኢብራሂም ልጆች ኢሥማዒል እና ይስሓቅ ናቸው፥ ለእነዚህ ልጆች ኢብራሂም የአምላክን መንገድ ስላሳያቸው የተውሒድ እሳቤ ይዘዋል። እስማኤላውያን "ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን ነው? ተብለው ሲጠየቁ "በእርግጥ አሏህ ነው" ያሉት አሏህ በእነርሱ ያኖረው ቀሪ ቃል ስላለ ነው፦
29፥61*ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ?*፡፡ وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَسَخَّرَ ٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ ۖ فَأَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢየሱስ ክርስቶስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥17 *እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ዐበይት ክርስትናን ማለትም ኦርቶዶክንስ፣ ካቶሊክን፣ አንግሊካንን እና ፕሮቴስታንትን፦ "ፍጡር እና ሰው ታመልካላችሁን? ብለን ስንጠይቃቸው "እረ በፍጹም" የሚል መልስ ይሰጣሉ፥ "ኢየሱስን ታመልኩ የለ? ኢየሱስ አምላክ እና ሰው ወይም በአምላክነቱ ፈጣሪ በሰውነቱ ፍጡር ነው" ትሉ የለ? ለሚለው ጥያቄ ኦርቶዶክን፣ ካቶሊክ እና አንግሊካን፦ "አዎ! ሰውነቱ መለኮት ስላለበት ሰውነቱ ይመለካል" በማለት ፍጡርነቱ እንደሚመለክ ይናገራሉ፥ ስለዚህ ፍጡርና ሰው ያመልካሉ።
ፕሮቴስታንት እንደ ዐቅሚቲ፦"የምናመልከው ሰውነቱን ሳይሆን በሰውነቱ ውስጥ ያለው አምላክነቱን ነው" የሚል ምላሽ ይሰጣሉ። ይህም ችግር የሚመለክ እና የማይመለክ ሁለት ኢየሱስ ወደሚለው ወደ ንስጥሮሳውያን ትምህርት ይጠጋል።
ቅሉ ግን ኢየሱስ እና ክርስቶስ የሚለው ስም በራሱ የፍጡር ስም ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ነው፥ መመለክ በፍጹም የለበትም። ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ኢየሱስ"
"ኢየሱስ" የሚለው ስም "የህ-ሹአ" יְהוֹשׁוּעַ በቀዳማይ ዕብራይስጥ፣ "የሽ-ሹአ" יֵשׁוּעַ‎ በደኃራይ ዕብራይስጥ፣ "ዒሣ" عِيسَى በቀዳማይ ዐረቢኛ፣ "የሡዕ" يَسُوع በደኃራይ ዐረቢኛ፣ "ዔሣዩ" ܝܫܘܥ በዐረማይክ፣ "ኤሱስ" Ἰησοῦς በግሪክ ሰፕቱአጀንት ሲሆን ትርጉሙ "የሕ መድኃኒት" ማለት ነው፥ "የሕ" ወይም "ያሕ" יָהּ‎ የቴትራግራማተን ምጻረ-ቃል ሲሆን ለፍጡራን ስም በመነሻ ቅጥያ አሊያም በመድረሻ ቅጥያ ሆኖ ይመጣል። ይህ "ኢየሱስ" የሚለው የፍጡር ስም የናዝሬቱ ኢየሱስ ከመፀነሱ በፊት ብሉይ ኪዳን ላይ ለብዙ ሰዎች ስም ሆኖ ያገለግል ነበር፥ ከዚያ መካከል የነዌ ልጅ ኢየሱስ ነው፦
1. የግዕዝ እትም፦
ዘኍልቍ 11፥28 ወይቤሎ ኢየሱስ ዘነዌ ዘይቀውም ቅድሜሁ ለሙሴ ዘውእቱ ኅሩዩ ይቤሎ እግዚእየ ሙሴ ክልኦሙ።
2. ትርጉም፦
“ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢየሱስ፦ ጌታዬ ሙሴ ሆይ፥ ከልክላቸው አለው።”
3. ዕብራይስጥ፦
וַיַּעַן יְהוֹשֻׁעַ בִּן-נוּן, מְשָׁרֵת מֹשֶׁה מִבְּחֻרָיו–וַיֹּאמַר: אֲדֹנִי מֹשֶׁה, כְּלָאֵם.
4. ግሪክ ሰፕቱጀንት፦
καὶ ἀποκριθεὶς ᾿Ιησοῦς ὁ τοῦ Ναυὴ ὁ παρεστηκὼς Μωυσῇ, ὁ ἐκλεκτός, εἶπε· κύριε Μωυσῆ, κώλυσον αὐτούς.

ግዕዙ "ኢየሱስ" እንዳለው፣ ዕብራይስጡ "የህ-ሹአ" יְהוֹשֻׁ֣עַ እንዳለው፣ የግሪኩ ሰፕቱጀንት "ኤሱስ" Ἰησοῦς እንዳለው አንባቢ ልብ ይለዋል። በተመሳሳይም የአዲሱ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ ሐዋ 7፥45 ላይ የነዌ ልጅን "ኤሱስ" Ἰησοῦς ብሎ አስቀምጦታል፦
ἣν καὶ εἰσήγαγον διαδεξάμενοι οἱ πατέρες ἡμῶν μετὰ Ἰησοῦ ἐν τῇ κατασχέσει τῶν ἐθνῶν ὧν ἐξῶσεν ὁ θεὸς ἀπὸ προσώπου τῶν πατέρων ἡμῶν ἕως τῶν ἡμερῶν Δαυείδ·
Act 7፥45 Which also our fathers that came after brought in with Jesus into the possession of the Gentiles, whom God drave out before the face of our fathers, unto the days of David

ዐማርኛው ላይ "ኢያሱ" እያሉ ሊያስቀይሱ ቢሞክሩም እንግሊዝኛው ላይ ሳያቅማሙ እንቅጩን ፍርጥ አርገው "Jesus" ብለው አስቀምጠውታል፥ ይህ ስም አዲስ ኪዳን ላይም ለብዙ ሰዎች ስም ሆኖ ያገለግል ነበር።
፨ ሲጀመር "ኢየሱስ" የሚለው የፍጡር ስም ባይሆን ኖሮ ፈጣሪ፣ ነቢያት እና ሐዋርያት ለፍጡራን ስም አርገው አይጠቀሙም ነበር።
፨ ሲቀጥል እራሱ ፈጣሪ አብሮት ያልነበረው ከጊዜ በኃላ የፍጡር ስም ይጠቀማል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው።
፨ ሢሰልስ ናዝሬት ላይ ከማርያም የተወለደው ልክ እንደ እስማኤል በመልአክ ከጊዜ በኃላ የወጣለት ስም ነው፦
ዘፍጥረት 16፥11 የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።

ስለዚህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት "ኢየሱስ" የሚለው የፍጡር ስም ከሆነ ኢየሱስን ማምለክ እራሱ ሺርክ ነው።

ነጥብ ሁለት
"ክርስቶስ"
በብሉይ ግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ "ክርስቶስ" χριστός የሚለው እና በብሉይ ዕብራይስጥ ማሶሬቲክ ላይ "መሢሕ מָשִׁיחַ‎ የሚለው የማዕረግ ስም ትርጉሙ "የተቀባ" ወይም "ቅቡዕ" ማለት ሲሆን ይህ ስም ለነቢያት፣ ለካህናት እና ለነገሥታት የሚያገለግል የፍጡር ስም ነው፦
1ኛ ሳሙ 12፥3 እነሆኝ በእግዚአብሔር እና “በመሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ፊት መስክሩብኝ የማንን በሬ ወሰድሁ?
1. ዕብራይስጡ፦
הנני ענו בי נגד יהוה ונגד משיחו את שור מי לקחתי וחמור מי לקחתי ואת מי עשקתי את מי רצותי ומיד מי לקחתי כפר ואעלים עיני בו ואשיב לכם׃
2. ግሪክ ሰፕቱጀንት፦
ἰδοὺ ἐγώ, ἀποκρίθητε κατ᾿ ἐμοῦ ἐνώπιον Κυρίου καὶ ἐνώπιον χριστοῦ αὐτοῦ· μόσχον τίνος εἴληφα ἢ ὄνον τίνος εἴληφα ἢ τίνα κατεδυνάστευσα ὑμῶν ἢ τίνα ἐξεπίεσα ἢ ἐκ χειρὸς τίνος εἴληφα ἐξίλασμα καὶ ὑπόδημα; ἀποκρίθητε κατ᾿ ἐμοῦ, καὶ ἀποδώσω ὑμῖν.

እዚህ አንቀጽ ላይ በግሪኩ ሰፕቱጀንት "ክርስቶስ" χριστός እና በዕብራይስጡ ማሶሬቲክ "መሢሕ מָשִׁיחַ‎ ነቢዩ ሳሙኤል ንጉሥ ሳኦልን የጠራበት ስም መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ፈጣሪ ቀቢ ከሆነ ተቀቢ ፍጡር ነው፥ እግዚአብሔር ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ ስለቀባው እግዚአብሔር አምላኩ ቀቢ ኢየሱስ ተቀቢ ነው፦
ሐዋ 10፥38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም “ቀባው”፥
ዕብራውያን 1፥9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ "እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ"፥ ይላል።

ስለዚህ ኢየሱስ ሆነ ክርስቶስ የፍጡራን የተፀውዖ ወይም የማዕረግ ስም ከሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ነው። ፍጡር ደግሞ በምንም መልኩ አይመለክም፥ ፍጡርን ማምለክ በራሱ ሺርክ ነው። ይህ ዓይን ያስፈጠጠ እና ጥርስ ያስገጠጠ ኩፍር ነው፥ እነዚያ የፈጠራቸውን አምላክ አሏህን እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥17 *እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጎረቤት ሐቅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥36 አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ *”በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው፣ መልካምን ሥሩ”*። አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

በማኅበራዊ እሴት ውስጥ በሚኖረን ጉልኅ ሚና ለቅርብ ጎረቤት እና ለሩቅ ጎረቤት መልካምን ሥራ እንድንሠራ አምላካችን አሏህ ያዘናል፦
4፥36 አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ *”በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው፣ መልካምን ሥሩ”*። አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

በተለይ በቅርብ ጎረቤት ያለው የጎረቤት ሐቅ በኢሥላም ትልቅ ቦታ አለው፥ የትዳር አጋር ውኃ አጣጭ እንደሆነ ሁሉ ጎረቤትም ቡና አጣጭ ነው። አንድ ሙሥሊም ለራሱ የሚወደውን ለጎረቤቱ እስካልወደደ ድረስ አማኝ አይደለም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 77
አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ከእናንተ አንድም አላመነም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ ወይም ለራሱ የሚወደውን ለጎረቤቱ እስካልወደደ ድረስ”*፡፡ يُحَدِّثُ عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لاَ يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لأَخِيهِ – أَوْ قَالَ لِجَارِهِ – مَا يُحِبُّ لِنَفْسِه

አንድ አማኝ እራሱ መሰደብ፣ መነቀፍ፣ መራብ እንደማይፈልግ ጎረቤቱ እንዲሰደብ፣ እንዲነቀፍ፣ እንዲራብ አይፈልግም፥ እራሱ መከበር፣ መወደድ፣ መጥገብ እንደሚፈልግ ሁሉ ለራሱ የሚወደውን ለጎረቤቱ ይወዳል። ይህ ወርቃማው ሕግ ነው፥ ጎረቤት እየተራበ የራስን ሆድ መሙላት የኢማን ጉድለት ነው። በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ጎረቤቱን አይጎዳም፦
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 12
ኢብኑ ዐባሥ ነቢዩ"ﷺ" ሲናገሩ ሰምቶ ለኢብኑ አዝ-ዙበይር እንደነገረው፦ እርሳቸውም፦ *"ጎረቤቱ እየተራበ የራሱን ሆድ የሚሞላ ሙእሚን አይደለም"* አሉ"*። سَمِعْتُ ابْنَ عَبَّاسٍ يُخْبِرُ ابْنَ الزُّبَيْرِ يَقُولُ‏:‏ سَمِعْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ‏:‏ لَيْسَ الْمُؤْمِنُ الَّذِي يَشْبَعُ وَجَارُهُ جَائِعٌ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 81
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን ጎረቤቱን አይጎዳም"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلاَ يُؤْذِي جَارَهُ
ሙእሚን ማለት ጎረቤቱን በዘሩ፣ በብሔሩ፣ በቀለሙ፣ በዘውጉ፣ በቋንቋው የማይጎዳ እና ለጎረቤቱ ስጋት የማይሆን ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 47
አቢ ሹረይሕ እንደተረከው፦ ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በአሏህ እምላለሁ አላመነም፣ በአሏህ እምላለሁ አላመነም፣ በአሏህ እምላለሁ አላመነም። "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! እርሱ ማን ነው? አሉአቸው፥ እርሳቸውም፦ "እርሱ ያ ጎረቤቱ የሚሰጋበት" አሉ"*። عَنْ أَبِي شُرَيْحٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ وَاللَّهِ لاَ يُؤْمِنُ، وَاللَّهِ لاَ يُؤْمِنُ، وَاللَّهِ لاَ يُؤْمِنُ ‏"‌‏.‏ قِيلَ وَمَنْ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏"‏ الَّذِي لاَ يَأْمَنُ جَارُهُ بَوَايِقَهُ ‏"‌‏

"ስጋት" ማለት "ከአሁን አሁን ምን ያደርግብኝ ይሆን" ብሎ መሳቀቅ ነው። ኢሥላም ሁሉንም ዘር፣ ብሔር፣ ዘውግ እና ቋንቋ አካታችና አቃፊ እንጂ አግላይና ነቃፊ አይደለም፥ ሙሥሊምም ለመላው ዘር፣ ብሔር፣ ዘውግ እና ቋንቋ ስጋት በፍጹም አይደለም። እንደውም ጎረቤቱን በስጋት የሚያሳቅቅ ሰው ጀነት አይገባም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 69
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ጎረቤቱ የሚሰጋበት ሰው ጀነት አይገባም"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ يَدْخُلُ الْجَنَّةَ مَنْ لاَ يَأْمَنُ جَارُهُ بَوَائِقَهُ ‏"‏ ‏.‏

አንድ ሰው "ሀዲያህ" هَدِيَّة ማለትም "ስጦታ" ቢኖረው ቅድሚያ መስጠት ያለበት ለቅርብ ጎረቤት ነው፥ ቦታ ኖሮት መሸጥ ከፈለ እንኳን ቅድሚያ መሸጥ ያለበት ለቅርብ ጎረቤቱ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 78, ሐዲስ 51
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ እንዲህን አለች፦ *"የአሏህ መልክተኛ ሆይ"ﷺ" ሁለት ጎረቤት አሉኝ፥ ሶጦታዬን ለማናቸው ልስጥ? እርሳቸውም፦ "ከበር ቅርብ ለሆነልሽ" አሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّ لِي جَارَيْنِ فَإِلَى أَيِّهِمَا أُهْدِي قَالَ ‏ "‏ إِلَى أَقْرَبِهِمَا مِنْكِ بَابًا ‏"‌‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 17, ሐዲስ 2588
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"መሬት ያለው እና ሊሸጠው የሚፈልግ ለጎረቤቱ ያቅርብ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ كَانَتْ لَهُ أَرْضٌ فَأَرَادَ بَيْعَهَا فَلْيَعْرِضْهَا عَلَى جَارِهِ ‏"‏ ‏

የጎረቤት ሐቅ ይህንን ያክል ከባድ ሐቅ ከሆነ ታዲያ ለጎረቤት የሚገባው ሐቅ ተትቶ ጎረቤትን ማንጓጠጥ፣ ማግለል፣ መሳደብ ከዚያም አልፎ መግደል ምን ይባላል? አዎ! ይህ የመጨረሻው ዘመን ትንቢት ነው፦
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 6, ሐዲስ 18
አቢ ሙሣ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሰው ጎረቤቱን፣ ወንድሙን እና አባቱን እስኪገድል ድረስ ሰዓቲቱ አትቆምም"*። عَنْ أَبِي مُوسَى‏:‏ قَالَ رَسُولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم‏:‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَقْتُلَ الرَّجُلُ جَارَهُ وَأَخَاهُ وَأَبَاهُ‏.‏

አምላካችን አሏህ የጎረቤት ሐቅ ከሚጠብቁ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥያቄአችን!

ፈጣሪ ሰውን አይፈትንም ወይስ ይፈትናል?

A. አይፈትንም፦
ያዕቆብ 1፥13 ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ፡ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።

B. ይፈትናል፦
ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው፦ አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፦ እነሆ፥ አለሁ፡ አለ።

አንዳንድ ሰዎች ይህንን ዓይን ያስፈጠጠ እና ጥርስ ያስገጠጠ ግጭት በቋንቋ ሊደበቁ ይሞክራሉ። በቋንቋ ሙግትም እንመልከት፦
ያዕቆብ 1፥13 ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ፡ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም። Μηδεὶς πειραζόμενος λεγέτω ὅτι Ἀπὸ Θεοῦ πειράζομαι· ὁ γὰρ Θεὸς ἀπείραστός ἐστιν κακῶν, πειράζει δὲ αὐτὸς οὐδένα.

እዚህ አንቀጽ ላይ በአፍራሽ ቅጽል ታክሎ የመጣው ግሥ "ፔይራዜይ" πειράζει ሲሆን ፈጣሪ ማንንም እንደማይፈትን ይናገራል። በተቃራኒው ፈጣሪ አብርሃምን እንደፈተነው ዘፍጥረት ላይ ተዘግቧል፦
ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው፦ አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፦ እነሆ፥ አለሁ፡ አለ። ΚΑΙ ἐγένετο μετὰ τὰ ρήματα ταῦτα ὁ Θεός ἐπείρασε τὸν ῾Αβραὰμ καὶ εἶπεν αὐτῷ·

እዚህ አንቀጽ ላይ ግሪክ ሰፕቱአጀንትን ላይም "ፈተነው" ለሚለው ግሥ የገባው ቃል በተመሳሳይ "ፔይራዞኢ" ἐπείρασε ነው።

ማንን እንስማ? አይፈትንም የሚለውን ወይስ ይፈትናል የሚለውን?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
አልገደሉትም

@ገቢር አንድ
https://tttttt.me/Wahidcom/656

@ገቢር ሁለት
https://tttttt.me/Wahidcom/658

@ገቢር ሦስት
https://tttttt.me/Wahidcom/667

@ገቢር አራት
https://tttttt.me/Wahidcom/679

@ገቢር አምስት
https://tttttt.me/Wahidcom/681

ስለ ስቅለት እና በስቅለት ዙሪያ ማብራሪያ ነው። ያንብቡ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዘካቱል ማል ዙሪያ የሸይኽ ኢልያስን ማብራሪያ እንዲመለከቱ በትህትና እጠይቃለው።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የወር ደመወዝተኛን የሚመለከት የዘካህ አወጣጥ!
በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
የሩሃማ ኢፍጧር

"ሩሐማእ" رُحَمَاء የቁርኣኑ ቃል ከሆነ ፊደሉ "ሩሐማእ" እንጂ "ሩሃማ" አይደለም፦
48፥29 የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት ወዳጆቹ በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አዛኞች" ለሚለው የገባው ቃል "ሩሐማእ" رُحَمَاء ነው። የኢፍጧሩ ስም ግን "ሩሃማ" ከሆነ "ሩሃማ" የሚለው ባይብል ውስጥ ያለ ስም ነው፥ ትርጉሙ "ምሕረት የተገባት" ማለት ነው፦
ሆሴዕ 2፥1-2 ወንድሞቻችሁን፦ ዓሚ፥ እኅቶቻችሁንም፦ #ሩሃማ" በሉአቸው። #እናታችሁ #ሚስቴ አይደለችምና እኔም ባልዋ አይደለሁምና ተምዋገቱ፤ ከእናታችሁ ጋር ተምዋገቱ። ግልሙትናዋን ከፊትዋ፥ ምንዝርናዋንም ከጡቶችዋ መካከል ታስወግድ፤

የሩሃማ እናት የፈጣሪ ሚስት አይደለችም ይላል። ግልሙትናዋ እና ጡቶችዋ እያለ የሚናገረው የሩሃማን እናት ነው። "ሎሩሃማን" ማለት "ምሕረት የማይገባት" ማለት ነው። ሎሩሃማን ብሉይ ኪዳን ላይ የነበረውን ዓመተ ፍዳ፣ ኩነኔ፣ ዓለም የሚያሳይ ሲሆን ሩሃማ በስቅለት ሞት ዓመተ ምሕረትን ያሳያል ብለው ያምናሉ። ሩሃማ ከሆነ በምን ሒሣብ ነው ይህ እሳቤ እና ስያሜ የሙሥሊም ኢፍጧር ላይ ስም የሆነው?

ዲን መቀለጃ አይደለም። አትቀላቅሉ! የሰዎችን ከንቱ ዝንባሌ አንከተል፦
42፥15 ለዚህም ድንጋጌ ሰዎችን ጥራ፣ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፣ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል!፡፡ فَلِذَٰلِكَ فَادْعُ ۖ وَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ጥሪያችን የተሰኘው የብዙ ንፅፅር ኡሥታዞች የያዘ ድረ-ገጽ(ዌብ ሳይት) የሚሽነሪዎችን ሴራ እና ደባ ዶግ አመድ ለማድረግ እና ድባቅ ለማስገባት የተለያየ አርዕስት ይዞ ብቅ ብሏል። ጊዜ ካለዎት ሊንኩን በማስፈንጠር ይጎብኙት! ሼር በማድረግ ያስጎብኙ፦https://tiriyachen.org/
ፍልስጥኤም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥251 *"በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"*፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ

"ፊልሥጢን" فِلَسْطِين ማለት "ፍልስጥኤም" ማለት ሲሆን በአንድ ወቅት የፍሊሥጢን ንጉሥ "ጃሉት" جَالُوت ማለትም "ጎልያድ" እና ሠራዊቱ ከጧሉት ማለትም ከሳኦል ሠራዊት ተዋግተዋል፦
2፥249 *ጧሉትም በሠራዊቱ ታጅቦ በወጣ ጊዜ፡- «አላህ በወንዝ ፈታኛችሁ ነው፥ ከርሱም የጠጣ ሰው ከእኔ አይደለም፡፡ ያልቀመሰውም ሰው በእጁ መዝገንን የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው» አለ፡፡ ከእነርሱም ጥቂቶች ሲቀሩ ከርሱ ጠጡ፡፡ እርሱ እና እነዚያም ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሎትን እና ሠራዊቱን በመዋጋት ለኛ ዛሬ ችሎታ የለንም» አሉት፡፡ እነዚያ እነርሱ አላህን ተገናኝዎች መኾናቸው የሚያረጋግጡት፡- «ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህም ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ*፡፡ فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِالْجُنُودِ قَالَ إِنَّ اللَّهَ مُبْتَلِيكُم بِنَهَرٍ فَمَن شَرِبَ مِنْهُ فَلَيْسَ مِنِّي وَمَن لَّمْ يَطْعَمْهُ فَإِنَّهُ مِنِّي إِلَّا مَنِ اغْتَرَفَ غُرْفَةً بِيَدِهِ ۚ فَشَرِبُوا مِنْهُ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ ۚ فَلَمَّا جَاوَزَهُ هُوَ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ قَالُوا لَا طَاقَةَ لَنَا الْيَوْمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ ۚ قَالَ الَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَاقُو اللَّهِ كَم مِّن فِئَةٍ قَلِيلَةٍ غَلَبَتْ فِئَةً كَثِيرَةً بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ مَعَ الصَّابِرِينَ

ከዚያም በጦርነቱ ተፋልመው ተስፋ በቆረጡ ጊዜ ዳውድ ጃሉትን ገሎታል፦
2፥250 *ለጃሉት እና ለሠራዊቱ በተሰለፉም ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አንቧቧ፤ ጫማዎቻችንንም አደላድል፤ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን» አሉ፡፡ وَلَمَّا بَرَزُوا لِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ قَالُوا رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ
2፥251 *"በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"*፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ

ቁርኣን ላይ ስለ ፍልስጥኤማውያን የሚናገረው እነዚህ አናቅጽ ላይ ነው። ሚሽነሪዎች፦ "ፍልስጥኤማውያን ፍልስጥኤም የምትባል አገር የላቸውም" እያሉ ባላነበቡት ነገር ይዘባርቃሉ። ፈጣሪ እስራኤልን ከግብጽ ምድር እንዳወጣ ሁሉ በጥንት ጊዜ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር አውጥቶ የራሳቸው ግዛት ሰቷቸዋል፦
አሞጽ 9፥7 እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ *ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?*
ኢዮኤል 3፥4 ጢሮስና ሲዶና *የፍልስጥኤምም ግዛት ሁሉ ሆይ*፥ ከእናንተ ጋር ለእኔ ምን አለኝ? በውኑ ብድራትን ትመልሱልኛላችሁን?

"የፍልስጥኤምም ግዛት" የሚለው ይሰመርበት። ፍልስጥኤም ግዛት ከነበረች ለምን መብቷ አይከበረም? እስራኤላውያን ቦታቸው መጥተው ሰፈሩባቸው እንጂ ጥንትም ቢሆን የእስራኤል ቅም አያት አብርሃም ከከላዳውያን ኡር በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 21፥34 *"አብርሃምም በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀመጠ"*።

ፍልስጥኤም መጤ ሳትሆን የራሷ ምድር ስለሆነ "በፍልስጥኤም ምድር" የሚል ኃይለ-ቃል ተጽፏል። ባይብል ላይ ብዙ ቦታ "የፍልስጥኤም ምድር" እያለ ይናገራል፦
ኤርምያስ 25፥20 የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ *የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዞጦንንም ቅሬታ"*።
ዘጸአት 13፥17 እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር *በፍልስጥኤማውያን ምድር* መንገድ አልመራቸውም።

ፍልስጥኤማውያን የራሳቸው አገር አላቸው፥ እስራኤላውያን የሰፈሩበት ከነዓን ሁሉ ሳይቀር የፍልስጥኤማውያን ምድር ነው፦
2ኛ ነገሥት 8፥2 ሴቲቱም ተነሥታ እንደ እግዚአብሔር ሰው ቃል አደረገች፤ ከቤተ ሰብዋም ጋር ሄዳ *"በፍልስጥኤም አገር ሰባት ዓመት ተቀመጠች"*።
ሶፎንያስ 2፥5 *"የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ"*፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው።

ዛሬ አገር እና ግዛት እንደሌላቸው እና መጤ እንደሆኑ ታይቶ እየተፈናቀሉ ነው፥ አሏህ ነስሩን ያቅርብላቸው! አሚን። ይህንን የምንለው ስለ ሐቅ እና ስለ ፍትሕ ነው፥ "ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው" ስንል ዕውር ድንብ ጸለምተኛ ሙግት ይዘን ሳይሆን ጠቅሰንና አጣቅሰን በመሞገትና በመሟገት ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያ ሙሥሊሙን ወሙሥሊማት ፈሠላሙሏሂ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ!
እንኳን የዒዱል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
"ተቀበለሏህ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል፥ ዒድ ሙባረክ! تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال! عيد مبارك
ሸዋል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ሚሽነሪዎች የማያውቁትን ከመጠየቅ ይልቅ፦ “ዘካህ ከመቶ 2.5% ስጡ የሚል መረጃ የለም፣ ሪባ ማለት አራጣ ማለት እንጂ ወለድ ማለት አይደለም፥ የቁርኣን አወራረድ ሁለት አይነት ነው የሚል መረጃ ከቁርኣንም ከሐዲስም መረጃ የለም” እያሉ ዲስኩራቸውን ሲደሶክሩ ነበር። ለእናንዳንዱ አርስት ከቁርኣና ከሐዲስ ከዚህ ቀደም ምላሽ ሰተናል። ዛሬ ደግሞ፦ “ሸዋልን ጹሙ! የሚል ቁርኣን ላይ የለም” እያሉ ይደሶክራሉ። ሚሽነሪዎች ሆይ! ጮቤ ረግጣችሁ አንባጒሮ አትፍጠሩ። ተረጋጉ! የጅብ ችኩል አትሁኑ! በሰላና በሰከነ መንፈስ ጠይቁ መልስ ይሰጣችኃል። ከሆያ ሆዬ ወደ አንቺ ሆዬ ትንሽ እንኳን እደጉ።
የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ እነዚህም፦
1ኛ ወር ሙሐረም
2ኛ ወር ሰፈር
3ኛ ወር ረቢዑል-አወል
4ኛ ወር ረቢዑ-ሣኒ
5ኛ ወር ጀማዱል-አወል
6ኛ ወር ጀማዱ-ሣኒ
7ኛ ወር ረጀብ
8ኛ ወር ሻዕባን
9ኛ ወር ረመዷን
10ኛ ወር ሸዋል
11ኛ ወር ዙል-ቀዒዳህ
12ኛ ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦
9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ

ከእነዚህ አስራ ሁለት ወራት አንዱ 10ኛ ወር “ሸዋል” ነው፥ “ሸዋል” شَوَّال ማለት “ማንሳት” ወይም “መሸከም” ማለት ሲሆን የወር ስም ነው። ነቢያችን”ﷺ” እንድናደርገው ሙስተሐብ አድርገው ከሰጡት ሱና መካከል ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን መጾም ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78
አቢ አዩብ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው”*። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ ‏

የረመዷን ሰላሳ ቀን እና የሸዋል ስድስት ቀን ጾም ጾመን ዓመት እንደጾምን የሚያስቆጥርበትን ስሌት ማወቅ ይቻላል። አምላካችን አላህ አንድ መልካም ሥራ ምንዳው አሥር እጥፍ እንደሆነ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦
6፥160 *”በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት”*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

ስለዚህ አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት የረመዷን አንድ ወር መጾም የአሥር ወር ምንዳ አለው። 1×10=10 ወር ይሆናል። እንዲሁ የሸዋል ስድስት ቀን መጾም የስድሳ ቀን ምንዳ አለው፥ ስድስት ቀናት በአሥር እጥፍ ስድሳ ቀን ነውና፥ 6×10=60 ቀን ወይም 2 ወር ይሆናል። ሲጠቀለል የረመዷን የአሥር ወር ምንዳ እና የሸዋል ሁለት ወር ምንዳ 12 ወር ይሆናል፥ 10+2=12 ወር ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ 12 ወር መሆኑ እሙን ነው። አሊያም ሠላሳ የረመዳን ቀን እና ስድስት የሸዋል ቀን በአስር ምንዳ ሲባዛ 360 ቀናት ይሆናሉ፥ 36×10= 360 ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ ጨረቃ ወፀሐይ"lunisolar" የሆነው የአይሁዳውያን አቆጣጠር 360 ቀናት መሆኑ ቅቡል ነው።
አምላካችን አሏህ በተከበረ ቃሉ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት” ይለናል፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ስለዚህ ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሑትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ክርስቲያን ወንድሞቻችን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

49፥10 *"ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው"*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ

"አኽ" أَخ ማለት "ወንድም" ማለት ሲሆን "ኡኽት" أُخْت ማለት "እኅት" ማለት ነው፥ "ኢኽዋህ" إِخْوَة ወይም "ኢኽዋን" إِخْوَان የአኽ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ወንድማማቾች" ማለት ነው። "ኡኹዋህ" أُخُوَّة‎ ማለት "ወንድማማችነት" ማለት ሲሆን ወንድማማችነት እንደየ ዐውዱ የተለያየ አገባብ አለው። "ክርስቲያን" የሚለው ቃል "ሃይማኖትን" ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ቃል ነው፥ ለአንድ ሙሥሊም የሃይማኖት ወንድሙ ሙሥሊም እንጂ ክርስቲያን በፍጹም አይደለም። ሰዎች የሃይማኖት ወንድሞቻችን እንዲሆኑ ከተፈለገ ተውበት ወደ አሏህ ሊያደርጉ፣ ሶላትንም ሊሰግዱ፣ ዘካንም ሊሰጡ በጥቅሉ ምን አለፋን ሙሥሊም መሆን አለባቸው፦
9፥11 *"ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው"*፡፡ فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ
49፥10 *"ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው"*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ

ቁርኣን ላይ "ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው" የሚል እንጂ "ክርስቲያን ወንድሞቻችሁ ናቸው" የሚል ኃይለ-ቃል የለም። በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ኖርዌይ በኖቤል ሽልማቱ ጊዜ፦ "ምእመናኖች ወንድማማቾች ናቸው" የሚለውን ቆርጦ በመቀጠል "ሰብአዊነት አንድ ወንድማማችነት ነው"Humanity is but a single Brotherhood" ብለው ለፓለቲካ ንግድና ትርፍ ተጠቅመውበታል፥ ይህ ትልቅ ስህተት ነው።
ወደ ነጥቤ ስገባ "ክርስትና" በቁርኣን ውስጥ መለኮታዊ ዕውቅና ያለው "ሃይማኖት" አይደለም፦
3፥19 *"አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው"*፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ
3፥85 *"ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው"*፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ

ቁርኣን ከኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን ዕውቅና ካልሰጠ እና ዕውቅና መስጠቱ እራሱ በአኺራ ላይ ኪሳራ ከሆነ "ክርስቲያን ወንድሞቻችን" እያላችሁ የምትሉ ይህንን ኪሳራ እያያችሁ ግቡበት። አገራዊ ወንድማማችነት ከሃይማኖት ወንድማማችነት ይለያል፥ የሕዝብ ወንድማማችነት በቁርኣን ውስጥ ብዙ ቦታ ተጠቅሷል፦
7፥56 ወደ ዓድም *ወንድማቸውን ሁድን ላክን*፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ የአላህን ቅጣት አትፈሩምን» አላቸው፡፡ وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ
11፥61 *ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን*፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ
11፥84 *ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን*፡፡ አላቸው «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ وَلَا تَنقُصُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ ۚ إِنِّي أَرَاكُم بِخَيْرٍ وَإِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ مُّحِيطٍ

ዐድ፣ ሰሙድ፣ መድየም ወዘተ የሕዝብ ስም እንጂ የሃይማኖት ስም ስላልሆነ በተመሳሳይ "ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችን" ማለት ይቻላል። ከእናቴ እና ከአባቴ አብራክ የተገኘውን ወንድሜን እራሱ "ወንድሜ" ማለት ይቻላል፦
12፥5 አባቱም አለ «ልጄ ሆይ! ሕልምህን *ለወንድሞችህ* አታውራ፡፡ ላንተ ተንኮልን ይሰሩብሃልና፡፡ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና፡፡» قَالَ يَا بُنَيَّ لَا تَقْصُصْ رُؤْيَاكَ عَلَىٰ إِخْوَتِكَ فَيَكِيدُوا لَكَ كَيْدًا ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ لِلْإِنسَانِ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
7፥151 ሙሳም፡- «ጌታዬ ሆይ! *ለእኔም ለወንድሜም ማር*፡፡ በእዝነትህም ውስጥ አግባን፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» አለ፡፡ قَالَ رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِأَخِي وَأَدْخِلْنَا فِي رَحْمَتِكَ ۖ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

ስለዚህ ለመወደድ ብለን "ክርስቲያን ወንድሞቻችን" በማለት ዲናችን የማይለውን አንበል! ኢትዮጵያውያን እርስ በእርስ ሊያስተሳስረን የሚችል ብዙ የጋራ እሴት እያለን በማናምንበት ነገር ውስጥ ባንነካካ እና የሌላ እምነት አምልኮ ባንፈጽም ሰናይ ነው። አሏህ ሂዳያህ ለሁላችንም ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አል-አርዱል ሙቀደሣህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥21 *«ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ፡፡ ወደ ኋላችሁም አትመለሱ፡፡ ከሳሪዎች ኾናችሁ ትመለሳላችሁና፡፡»* يَا قَوْمِ ادْخُلُوا الْأَرْضَ الْمُقَدَّسَةَ الَّتِي كَتَبَ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَرْتَدُّوا عَلَىٰ أَدْبَارِكُمْ فَتَنقَلِبُوا خَاسِرِينَ

ስለ አል-አርዱል ሙቀደሣህ ከነቢዩሏህ ኢብራሂም እስከ ነቢያችን"ﷺ" ያለውን ክስተት ከቁርኣን እና ከሐዲስ በግርድፉና በሌጣው ኢንሻሏህ እናያለን። "አሽ-ሻም” اَلـشَّـام‎ ማለት በቋንቋ ደረጃ ከሄድን “አሽ-ሸማል” الشِّمَال ማለትም “ግራ” ማለት ነው፥ ለምሳሌ የአሽ-ሻም ተቃራኒ “አል-የመን” اَلْـيَـمَـن ማለት “አል-የሚን” الْيَمِين ማለትም “ቀኝ” ማለት ነው። ነቢያችን”ﷺ” ከሚኖሩበት በስተ ግራ ያለችው አሽ-ሻም ስትሆን በስተ ቀኝ ያለችው አል-የመን ናት። አምላካችን አሏህ በየመን አገር እና በሻም አገር መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አድርጓል፦
34፥18 *”በእነርሱ እና በዚያች በውስጧ በባረክናት ምድር መካከልም ቅጥልጥል ከተሞችን አደረግን”*፡፡ وَجَعَلْنَا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ الْقُرَى الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا قُرًى ظَاهِرَةً

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባረክና" بَارَكْنَا ማለት "የባረክን" ማለት ሲሆን የተባረከችውም ምድር የሻም ምድር ናት፥ አምላካችን አሏህ ኢብራሂምን እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረካት ምድር በመውሰድ አዳናቸው፦
21፥71 *”እርሱን(ኢብራሂምን) እና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት ወደ ባረክናት ምድር በመውሰድ አዳን”*፡፡ وَنَجَّيْنَاهُ وَلُوطًا إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا لِلْعَالَمِينَ

አምላካችን አሏህ በአል-መሥጂዱል አቅሳ ዙሪያውን ያለውን ሶሪያን፣ ፍልስጥኤም፣ ዮርዳኖስን፣ ሊባኖስን ወዘተ ባርኮታል፦
17፥1 *ያ ባሪያውን “ከተከበረው መስጊድ” ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ “ሩቁ መስጊድ” በሌሊት ውስጥ ያስኼደው ጥራት ይገባው፤ ከታምራቶቻችን ልናሳየው አስኼድነው"*። እነሆ እርሱ አላህ ሰሚው ተመልካቺው ነው። سُبْحَٰنَ ٱلَّذِىٓ أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِۦ لَيْلًۭا مِّنَ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ إِلَى ٱلْمَسْجِدِ ٱلْأَقْصَا ٱلَّذِى بَٰرَكْنَا حَوْلَهُۥ لِنُرِيَهُۥ مِنْ ءَايَٰتِنَآ ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

"ዙሪያውን ወደ ባረክነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ሰገደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው፥ የጥንት ሰዎች መሥጂድ አርገው የሚሠሩት ድንኳን ነበር። በመካህ የተመሠረተው የመጀሪያው መሥጂድ “አል-መሥጂዱል ሐረም” الْمَسْجِدِ الْحَرَام ማለትም “የተከበረ መሥጂድ” ሲሆን ሁለተኛው መሥጂድ ደግሞ በሻም ምድር የተመሠረተው "አል-መሥጂዱል አቅሷ” الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى ማለትም “የሩቅ መሥጂድ” ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 45
አቢ ዘር ሰምቶ እንደተረከው፦ “እኔም፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በምድር ላይ መጀመሪያ የተመሠረተው የትኛው መሥጂድ ነው? አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል ሐረም” አሉ። እኔም፦ “ከዚያስ ቀጥሎ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አል-መሥጂዱል አቅሷ” አሉ። እኔም፦ “በሁለቱ መካከል ምን ያህል የጊዜ ልዩነት አለ? ብዬ አልኩኝ። እርሳቸውም፦ “አርባ ዓመት” አሉ”*። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَىُّ مَسْجِدٍ وُضِعَ فِي الأَرْضِ أَوَّلُ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الْحَرَامُ ‏”‌‏.‏ قَالَ قُلْتُ ثُمَّ أَىٌّ قَالَ ‏”‏ الْمَسْجِدُ الأَقْصَى ‏”‌‏.‏ قُلْتُ كَمْ كَانَ بَيْنَهُمَا قَالَ ‏”‏ أَرْبَعُونَ سَنَةً،

“ዉዲዐ” وُضِعَ ማለት “ተመሠረተ” ማለት ነው፥ በሁለቱ መሣጂጅ መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት 40 ዓመት ነው፥ እነዚህ መሣጂድ የተመሠረቱት በኢብራሂም ጊዜ ነው፦
2፥127 *"ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ "ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
"አል-አርዱል ሙቀደሣህ" الْأَرْضَ الْمُقَدَّسَة ማለት "ቅድስት መሬት"The Holy Earth" ማለት ነው፥ ሙሣም ለሕዝቦቹ ይህቺን ምድር፦ "የተቀደሰችውን መሬት" ብሏታል፦
5፥21 *«ሕዝቦቼ ሆይ! ያችን አላህ ለእናንተ ያደረጋትን የተቀደሰችውን መሬት ግቡ፡፡ ወደ ኋላችሁም አትመለሱ፡፡ ከሳሪዎች ኾናችሁ ትመለሳላችሁና፡፡»* يَا قَوْمِ ادْخُلُوا الْأَرْضَ الْمُقَدَّسَةَ الَّتِي كَتَبَ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَرْتَدُّوا عَلَىٰ أَدْبَارِكُمْ فَتَنقَلِبُوا خَاسِرِينَ

አሏህ ለሙሣ ሕዝቦች ቅድስት ምድር ያደረጋት ሲሆን የሙሣ ሕዝቦች በምድረ በዳ በአላህ ላይ በማመጻቸው የተቀደሰችው መሬት በእነርሱ ላይ አርባ ዓመት እርም ሆነች፥ በምድረ በዳ ተንከራተቱ፦
5፥26 *”እርስዋም የተቀደሰችው መሬት በእነርሱ ላይ አርባ ዓመት እርም ናት፡፡ በምድረ በዳ ይንከራተታሉ”*፡፡ «በአመጸኞችም ሕዝቦች ላይ አትዘን» አለው፡፡ قَالَ فَإِنَّهَا مُحَرَّمَةٌ عَلَيْهِمْ ۛ أَرْبَعِينَ سَنَةً ۛ يَتِيهُونَ فِي الْأَرْضِ ۚ فَلَا تَأْسَ عَلَى الْقَوْمِ الْفَاسِقِينَ

ከዚያም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች በውስጧ የባረካትን የሻም ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረሳቸው፦
7፥137 *”እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ሕዝቦች ያችን በውስጧ የባረክናት ምድር ምሥራቆችዋንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው፡፡ የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስራኤል ልጆች ላይ በመታገሳቸው ተፈጸመች”*፡፡ وَأَوْرَثْنَا الْقَوْمَ الَّذِينَ كَانُوا يُسْتَضْعَفُونَ مَشَارِقَ الْأَرْضِ وَمَغَارِبَهَا الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا ۖ وَتَمَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ الْحُسْنَىٰ عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ بِمَا صَبَرُوا ۖ

ከዚያም አምላካችን አላህ ዙሪያውን በባረከው በሁለተኛው የሩቁ መሥጂድ ለሱለይማንም በትእዛዙ በኃይል የምትነፍስ ነፋስ ስትኾን ገራለት፥ ሱለይማን እዛው አቅሳ መስገጃው ላይ ሕንጻ አል-በይቱል መቅዲሥ ገነባ፦
21፥81 *”ለሱለይማንም በትእዛዙ በኃይል የምትነፍስ ነፋስ ስትኾን በእርሷ ውስጥ ወደባረክናት ምድር የምትፈስ ስትኾን ገራንለት”*፡፡ በነገሩ ሁሉም ዐዋቂዎች ነበርን፡፡ وَلِسُلَيْمَانَ الرِّيحَ عَاصِفَةً تَجْرِي بِأَمْرِهِ إِلَى الْأَرْضِ الَّتِي بَارَكْنَا فِيهَا ۚ وَكُنَّا بِكُلِّ شَيْءٍ عَالِمِينَ
34፥13 *”ከምኩራቦች፣ ከምስሎችም እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል”*፡፡ አልናቸውም፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ

አሏህ ለሱለይማን ከጥንት በተመሠረተው መሥጂድ ላይ “መሐሪብ” እንዲሠራ ከጂኒዎች የሚሻውን ሁሉ እንዲሠሩለት ገራለት። እዚህ አንቀጽ ላይ “ምኩራብ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “መሐሪብ” مَّحَٰرِيب ሲሆን “አል-በይቱል መቅዲሥ” ٱلْبَيْت الْمَقْدِس ነው። “አል-በይቱል መቅዲሥ” ማለት “የተቀደሰ ቤት” ማለት ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1473
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሡለይማን ኢብኑ አቢ ዳዉድ በይቱተል መቅዲሥን ገንብቶ በጨረሰ ጊዜ አላህን ሦስት ነገሮች ጠይቋል። አንደኛ በፍርዱ የሚያስማማበትን ፍርድ ጠየቀ፥ ያም ተሰጠው፣ ሁለተኛ ከእርሱ በኃላ ማንም የማይኖረውን ንግሥና፣ ሦስተኛ ሶላት ለማድረግ እንጂ ወደዚህ መሥጂድ የሚመጣውን ልክ እናቱ ስትወልደው ከኀጢአት ነጻ እንደሆነ እንዲሆን”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ لَمَّا فَرَغَ سُلَيْمَانُ بْنُ دَاوُدَ مِنْ بِنَاءِ بَيْتِ الْمَقْدِسِ سَأَلَ اللَّهَ ثَلاَثًا حُكْمًا يُصَادِفُ حُكْمَهُ وَمُلْكًا لاَ يَنْبَغِي لأَحَدٍ مِنْ بَعْدِهِ وَأَلاَّ يَأْتِيَ هَذَا الْمَسْجِدَ أَحَدٌ لاَ يُرِيدُ إِلاَّ الصَّلاَةَ فِيهِ إِلاَّ خَرَجَ مِنْ ذُنُوبِهِ كَيَوْمَ وَلَدَتْهُ أُمُّهُ

“ቢናእ” بِنَاء የሚለው ቃል “በና” بَنَىٰ ማለትም “ገነባ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግንባታ” ወይም “ሕንጻ” ማለት ነው። ሡለይማን የገነባው ጥንት በተመሠረተው መሥጂድ ላይ ነው፥ እርሱ ገንቢ እንጂ መሥራች አለመሆኑ እሙልና ቅቡል ነው። ከዚያ የእስራኤል ልጆች ሁለት ጊዜ አጠፉ፥ ከሁለቱ የመጀመሪያይቱ ቀጠሮ በመጣም ጊዜ ለአላህ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የኾኑትን ናቡነደፆርን እና ሰራዊቱን በ 606 ቅድመ-ልደት”BC” ተነስተው ይህንን መሐሪብ ማለኪያ አጥፍተውታል። ይህ ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር፦
17፥4 *ወደ እስራኤልም ልጆች በመጽሐፉ ውስጥ እንዲህ በማለት አወረድን፡፡ በምድር ላይ በእርግጥ ሁለት ጊዜ ታጠፋላችሁ፡፡ ትልቅንም ኩራት ትኮራላችሁ*፡፡ وَقَضَيْنَا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ فِي الْكِتَابِ لَتُفْسِدُنَّ فِي الْأَرْضِ مَرَّتَيْنِ وَلَتَعْلُنَّ عُلُوًّا كَبِيرًا
17፥5 *"ከሁለቱ የመጀመሪያይቱ ቀጠሮ በመጣም ጊዜ ለእኛ የኾኑን ባሮች የብርቱ ኃይል ባለቤቶች የኾኑትን በእናንተ ላይ እንልካለን፡፡ በቤቶችም መካከል ይበረብሩታል፡፡ ይህ ተፈጻሚ ቀጠሮም ነበር*፡፡ فَإِذَا جَاءَ وَعْدُ أُولَاهُمَا بَعَثْنَا عَلَيْكُمْ عِبَادًا لَّنَا أُولِي بَأْسٍ شَدِيدٍ فَجَاسُوا خِلَالَ الدِّيَارِ ۚ وَكَانَ وَعْدًا مَّفْعُولًا
የኋለኛይቱም ጊዜ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ መሥጂዱን በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ እና ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ በ 70 ድህረ-ልደት”AD” የሮም ጦር መሪ የሆነው ጀነራል ቲቶ እና ሰራዊቱ ከበው አጥፍተዋል፦
17፥7 *”የኋለኛይቱም ጊዜ ቀጠሮ በመጣ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፣ መስጁዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡት ሊገቡ እና ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ እንልካቸዋልን”*፡፡ فَإِذَا جَآءَ وَعْدُ ٱلْـَٔاخِرَةِ لِيَسُۥٓـُٔوا۟ وُجُوهَكُمْ وَلِيَدْخُلُوا۟ ٱلْمَسْجِدَ كَمَا دَخَلُوهُ أَوَّلَ مَرَّةٍۢ وَلِيُتَبِّرُوا۟ مَا عَلَوْا۟ تَتْبِيرًا

ወደዚህ በይቱል መቅዲሥ ነቢያችን"ﷺ" እና ሶሓባዎች ለአስራ ስድስት ወይም ለአስራ ሰባት ወራት ያክል ቂብላህ አርገው ወደዚያ ይጸልዩ ነበር፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 656
አነሥ እንደተረከው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" እና ሶሓባዎች ወደ በይቱል መቅዲሥ ይጸልዩ ነበር፥ ይህቺ አንቀጽ በወረደች ጊዜ፦ "ስለዚህ ፊትህን ወደ ተከበረው መሥጂድ አግጣጫ አዙር! የትም ስፍራ ብትኾኑም ፊቶቻችሁን ወደርሱ አግጣጫ አዙሩ" የሚል መጣ"*። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَأَصْحَابَهُ كَانُوا يُصَلُّونَ نَحْوَ بَيْتِ الْمَقْدِسِ فَلَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ وَحَيْثُ مَا كُنْتُمْ فَوَلُّوا وُجُوهَكُمْ شَطْرَهُ ‏}‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 19
በሯእ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *" ለአስራ ስድስት ወይም ለአስራ ሰባት ወራት ያክል ከነቢዩም"ﷺ" ጋር ወደ ወደ በይቱል መቅዲሥ እንጸልይ ነበር፥ ከዚያም አሏህ እርሳቸው ወደ ተከበረው መሥጂድ እንዲቀጣጩ አዘዛቸው"*። قَالَ سَمِعْتُ الْبَرَاءَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ صَلَّيْنَا مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم نَحْوَ بَيْتِ الْمَقْدِسِ سِتَّةَ عَشَرَ ـ أَوْ سَبْعَةَ عَشَرَ ـ شَهْرًا، ثُمَّ صَرَفَهُ نَحْوَ الْقِبْلَةِ‏.‏

“ቂብላህ” قِبْلَة የሚለው ቃል “አቅበለ” أَقْبَلَ “ተቀጣጨ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “አቅጣጫ”direction” ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ አቅጣጫ በመቀጣጨት የሚደረግ “የውዳሴ ነጥብ”point of adoration” ነው። ቂብላህ ወደ አል-መሥጂዱል ሐረም ከመታዘዙ በፊት ወደ በይቱል መቅዲሥ እየጸለዩ እያሉ ስለሞቱት አሏህ፦ "አላህ እምነታችሁን ስግደታችሁን የሚያጠፋ አይደለም" ብሎ ተናግሯል፦
2፥143 *"አላህም እምነታችሁን ስግደታችሁን የሚያጠፋ አይደለም፥ አላህ ለሰዎች በጣም ርኅሩኅ አዛኝ ነውና"*፡፡ وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُضِيعَ إِيمَانَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ بِالنَّاسِ لَرَءُوفٌ رَّحِيمٌ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3227
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" ፊታቸውን ወደ ከዕባህ በተቀጣጩ ጊዜ ሶሓባዎች፦ "የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! እነዚያ ወደ በይቱል መቅዲሥ እየጸለዩ እያሉ ስለሞቱት ወንድሞቻችን እንዴት ይሆናሉ? አሏህም፦ "አላህ እምነታችሁን ስግደታችሁን የሚያጠፋ አይደለም" የሚል አንቀጽ አወረደ"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ لَمَّا وُجِّهَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِلَى الْكَعْبَةِ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ بِإِخْوَانِنَا الَّذِينَ مَاتُوا وَهُمْ يُصَلُّونَ إِلَى بَيْتِ الْمَقْدِسِ فَأَنْزَلَ اللَّهُ‏:‏ ‏(‏وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُضِيعَ إِيمَانَكُمْ ‏)‏

አምላካችን አሏህ ነቢያችንን”ﷺ” ከመሥጂዱል ሐረም ወደ መሥጂዱል አቅሷ በሌሊት አስኪዷቸዋል፦
17፥1 *”ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው አስኼድነው”*፡፡ እነሆ እርሱ አላህ ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡ سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ያስኼደው” ለሚለው የገባው የግስ መደብ “አሥሯ” أَسْرَىٰ ሲሆን “ኢሥሯ” إِسْرَا የሚለው የስም መደብ እራሱ “ሣረ” سَارَ ማለትም “ተጓዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጉዞ” ማለት ነው። “ለይለቱል ኢሥሯ” لَيْلَة الإِسْرَا ማለት “የሌሊት ጉዞ” ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ነቢያችንን”ﷺ” ከበይቱል ሐረም ወደ በይቱል መቅዲሥ በሌሊት ያስኬዳቸው “አል-ቡራቅ” በሚባል እንስሳ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 318
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከአህያ ከፍ ብሎ ከበቅሎ ያነሰ፥ ነጭና ረዘም ያለ እንስሳ አል-ቡራቅ መጣልኝ። የእይታው መጨረሻ ላይ ኮቴውን ያሳርፋል፥ በእርሱ እስከ በይቱል መቅዲሥ ተጓዝኩኝ”*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ أُتِيتُ بِالْبُرَاقِ – وَهُوَ دَابَّةٌ أَبْيَضُ طَوِيلٌ فَوْقَ الْحِمَارِ وَدُونَ الْبَغْلِ يَضَعُ حَافِرَهُ عِنْدَ مُنْتَهَى طَرْفِهِ – قَالَ فَرَكِبْتُهُ حَتَّى أَتَيْتُ بَيْتَ الْمَقْدِسِ

“አል-ቡራቅ” الْبُرَاق የሚለው ቃል “በረቀ” بَرَقَ ማለትም “በረቀ” “በለጨ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ብርቅታ” “ብልጭታ” ማለት ነው፥ “መብረቅ” እራሱ “በርቅ” بَرْق ይባላል። ይህ እንስሳ ከአህያ ከፍ ብሎ ከበቅሎ ያነሰ፥ ነጭና ረዘም ያለ እንስሳ ነው። ስለ አል-አርዱል ሙቀደሣህ ከነቢዩሏህ ኢብራሂም እስከ ነቢያችን"ﷺ" ያለውን ክስተት ከቁርኣን እና ከሐዲስ በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰገደለት ወይስ ሰገደበት?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

25፥60 *"ለእነርሱም፦ "ለአልረሕማን ስገዱ" በተባሉ ጊዜ "አልረሕማን ማነው? ለምታዘን እንሰግዳለን? ይላሉ፡፡ ይህ መራቅንም ጨመራቸው"*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ اسْجُدُوا لِلرَّحْمَـٰنِ قَالُوا وَمَا الرَّحْمَـٰنُ أَنَسْجُدُ لِمَا تَأْمُرُنَا وَزَادَهُمْ نُفُورًا ۩

"ሡጁድ" سُّجُود የሚለው ቃል "ሠጀደ" سَجَدَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስግደት" ማለት ነው፥ ሥጁድ ሶላት ውስጥ ከሚከወኑ ዒባዳህ መካከል አንዱ ነው፦
22፥77 *"እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ በስግደታችሁ አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም አምልኩ፣ በጎንም ነገር ሥሩ፣ ልትድኑ ይከጀልላችኋልና"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩

"በግንባራችሁም ተደፉ" ለሚለው ትእዛዛዊ ግስ የገባው ቃል "ኢሥጁዱ" اسْجُدُوا ሲሆን በሶላት ውስጥ ያለው ሥጁድ ለአሏህ ብቻ የሆነ መተናነስ፣ መጎባደድ፣ ማሸርገድ ነው፦
25፥60 *"ለእነርሱም፦ "ለአልረሕማን ስገዱ" በተባሉ ጊዜ "አልረሕማን ማነው? ለምታዘን እንሰግዳለን? ይላሉ፡፡ ይህ መራቅንም ጨመራቸው"*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ اسْجُدُوا لِلرَّحْمَـٰنِ قَالُوا وَمَا الرَّحْمَـٰنُ أَنَسْجُدُ لِمَا تَأْمُرُنَا وَزَادَهُمْ نُفُورًا ۩

"ለ-አር-ረሕማን ስገዱ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "አር-ረሕማን" لرَّحْمَـٰن በሚለው ስም መነሻ ላይ "ሊ" لِ ማለት "ለ" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ በሶላት ውስጥ ያለው ሥጁድ "ለ"አሏህ መሆኑ እሙንና ቅቡል መሆኑን ያስረግጣል። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ ሚሽነሪዎች የሚሰገድበት ነገር የሚሰገድለት ነገር አድርገው ያጣመሙትን ሐዲስ እንመልከት፦
ቡሉጉል መራም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 40
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ሐጀሩል አሥወድን ሳመው እና ሰገደበት"*። وَعَنْ اِبْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اَللَّهُ عَنْهُمَا: { أَنَّهُ كَانَ يُقَبِّلُ اَلْحَجَرَ اَلْأَسْوَدَ وَيَسْجُدُ عَلَيْهِ }

እዚህ ሐዲስ ላይ በሐጅሩል አሥወድ ላይ መሰገዱ በራሱ ሐጅሩል አሥወድ የሚሰገድበት እንጂ የሚሰገድለት አለመሆኑ ፍንትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። እንደሚሽነሪዎች ቅጥፈት "ሰገደለት" ለማለት መግባት የነበረበት ቃል "የሥጁዱ ለ-ሁ" يَسْجُدُ لَهُ እንጂ "የሥጁዱ ዐለይ-ሂ" يَسْجُدُ عَلَيْهِ አይደለም፥ ቅሉና ጥቅሉ ግን ሐዲሱ ላይ የሚለው "የሥጁዱ ዐለይ-ሂ" يَسْجُدُ عَلَيْهِ ነው። "የሥጁዱ ዐለይ-ሂ" يَسْجُدُ عَلَيْهِ ማለት "ሰገደበት" ማለት እንጂ "ሰገደለት" ማለት እንዳልሆነ የምንረዳው ለመስገጃ ምንጣፍ የምንጠቀምበት ሰዋስው መሆኑ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4, ሐዲስ 321
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ እንደዘገበው፦ "ነቢዩን"ﷺ" ጎብኝቷቸው እንዲህ አለ፦ *"በምንጣፉ ላይ እየጸለዩ ሲሰግዱበት ዐየኃቸው"*። حَدَّثَنِي أَبُو سَعِيدٍ الْخُدْرِيُّ، أَنَّهُ دَخَلَ عَلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ فَرَأَيْتُهُ يُصَلِّي عَلَى حَصِيرٍ يَسْجُدُ عَلَيْهِ

"ሲሰግዱበት" ለሚለው የገባው ቃል በተመሳሳይ "የሥጁዱ ዐለይ-ሂ" يَسْجُدُ عَلَيْهِ መሆኑን ልብ በል! ምንጣፍ "የሚሰገድበት" ሆኖ ሳለ "የሚሰገድለት" ብሎ አንሸዋሮ እና አሳክሮ ሲነግሩት ቂል ሰው ካልሆነ በስተቀር እንደማይቀበል ሁሉ ሐጀሩል አሥወድ ሰገደበት የሚለውን ሰገደለት ብሎ ሲነገረው የሚቀበል ቂል ሰው ብቻ ነው። ስለዚህ ሐጀሩል አሥወድ የተሰገድበት ምንጣፉ ተሰገደበት በተባለበት ቃላት ከነበረ አንሸዋሮ "ተሰግዶለታል" የሚለው ቅጥፈት ድባቅ ይገባል ማለት ነው፥ ውሸት በእውነት ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ፀሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

47፥19 *እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ*፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه

ከንፈር እና ከንፈር ሳይነካካ በምላስ የሚዘከር ዚክር ቢኖር “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” ብቻ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ”፦ "በላጩ ዚክር ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ነው" ብለውናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 14
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ”ረ.ዐ” ሰምቶ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”በላጩ ዚክር "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ነው"*። قَالَ سَمِعْتُ جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ، رضى الله عنهما يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ أَفْضَلُ الذِّكْرِ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ

ይህ በላጭ የዚክር ዓይነት ተህሊል ይባላል፥ “ተህሊል” تَهْلِيل‎ የሚለው ቃል “ሐለለ” هَلَّلَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ማለት ነው፥ “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ማለት “አምላክ የለም፥ ከአሏህ በስተቀር” ማለት ነው። ይህ ተህሊል ሁለት ማዕዘናት አሉት፥ እነርሱም፦ “ነፍይ” እና “ኢስባት” ናቸው። “ነፍይ” نَفْي የሚለው ቃል “ነፋ” نَفَى‎ ማለትም “አፈረሰ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማፍረስ” ማለት ነው። ነፍይ “ላ ኢላሀ” لَا إِلَـٰهَ ማለትም “አምላክ የለም” በማለት ጣዖታትን የምናፈራርስበት አዋጅ ነው፦
2፥256 “በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ”፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا

“ኢስባት” إِثْبَات የሚለው ቃል “አስበተ” أَثْبَتَ‎ ማለትም “አጸደቀ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማፅደቅ” ማለት ነው፥ ኢስባት "ኢለል ሏህ” إِلَّا اللّٰه ማለትም “ከአሏህ በቀር” በማለት የምናጸድቅበት አዋጅ ነው። “ላ ኢላሀ” ስንል በጣዖት መካዳችን ሲሆን "ኢለል ሏህ” ስንል ደግሞ በሐቅ የሚመለክ አሏህ ብቻ መሆኑን ማመናችን ነው፥ በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ ይህ የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ዘለበት የጨበጠ ሰው ሙሥሊም ይባላል፦
31፥22 *"እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ"*፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ

2፥256 እና 31፥22 ላይ "ዘለበት" ለሚለው የገባው ቃል "ዑርዋህ" عُرْوَة ሲሆን በጣዖትም የሚክድ እና በአሏህ የሚያምን ሰው ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥ ሰው ነው፥ "የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል እራሱ "ዩሥሊም" يُسْلِمْ መሆኑ በራሱ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ዘለበት በትክክል ዐውቆ እራሱ ለአሏህ የሰጠ ማለት ነው፦
47፥19 *እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ*፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه

እዚህ አንቀጽ ላይ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የሚል አዋጅ አለ፥ "ዕወቅ" የሚለው ደግሞ ከአሏህ ሌላ አምላክ አለመኖሩን ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለውን በትክክል ዐውቆ እና አሏህን በብቸኝነት አምልኮ እንዲሁ በአሏህ ላይ ምንም ነገር ያላሻረከ ጀነት ይገባል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 43
ዑስማን እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንም "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለውን በትክክል ዐውቆ የሞተ ጀነት ገባ"*። عَنْ عُثْمَانَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ مَاتَ وَهُوَ يَعْلَمُ أَنَّهُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏"‏ ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 176
ጃቢር ኢብኑ ዐብዱል ሏህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንም በአሏህ ላይ ምንም ነገር ሳያጋራ አሏህን የሚገናኝ ጀነት ገባ"*። حَدَّثَنَا جَابِرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ مَنْ لَقِيَ اللَّهَ لاَ يُشْرِكُ بِهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ