ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የሩሃማ ኢፍጧር

"ሩሐማእ" رُحَمَاء የቁርኣኑ ቃል ከሆነ ፊደሉ "ሩሐማእ" እንጂ "ሩሃማ" አይደለም፦
48፥29 የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት ወዳጆቹ በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ اللَّهِ ۚ وَالَّذِينَ مَعَهُ أَشِدَّاءُ عَلَى الْكُفَّارِ رُحَمَاءُ بَيْنَهُمْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አዛኞች" ለሚለው የገባው ቃል "ሩሐማእ" رُحَمَاء ነው። የኢፍጧሩ ስም ግን "ሩሃማ" ከሆነ "ሩሃማ" የሚለው ባይብል ውስጥ ያለ ስም ነው፥ ትርጉሙ "ምሕረት የተገባት" ማለት ነው፦
ሆሴዕ 2፥1-2 ወንድሞቻችሁን፦ ዓሚ፥ እኅቶቻችሁንም፦ #ሩሃማ" በሉአቸው። #እናታችሁ #ሚስቴ አይደለችምና እኔም ባልዋ አይደለሁምና ተምዋገቱ፤ ከእናታችሁ ጋር ተምዋገቱ። ግልሙትናዋን ከፊትዋ፥ ምንዝርናዋንም ከጡቶችዋ መካከል ታስወግድ፤

የሩሃማ እናት የፈጣሪ ሚስት አይደለችም ይላል። ግልሙትናዋ እና ጡቶችዋ እያለ የሚናገረው የሩሃማን እናት ነው። "ሎሩሃማን" ማለት "ምሕረት የማይገባት" ማለት ነው። ሎሩሃማን ብሉይ ኪዳን ላይ የነበረውን ዓመተ ፍዳ፣ ኩነኔ፣ ዓለም የሚያሳይ ሲሆን ሩሃማ በስቅለት ሞት ዓመተ ምሕረትን ያሳያል ብለው ያምናሉ። ሩሃማ ከሆነ በምን ሒሣብ ነው ይህ እሳቤ እና ስያሜ የሙሥሊም ኢፍጧር ላይ ስም የሆነው?

ዲን መቀለጃ አይደለም። አትቀላቅሉ! የሰዎችን ከንቱ ዝንባሌ አንከተል፦
42፥15 ለዚህም ድንጋጌ ሰዎችን ጥራ፣ እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፣ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል!፡፡ فَلِذَٰلِكَ فَادْعُ ۖ وَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom