ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ውሳጣዊ ሀብት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

23፥62 *ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም*፡፡ وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا

“ነፍሥ” نَفْس ማለት “ራስነት”own self-hood” ማለት ሲሆን የሰው እኔነቱ ወይም ማንነቱ ነው፥ አምላካችን አሏህ በነፍሥ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፦
2፥284 *”በራሳችሁ ውስጥ ያለውን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት አላህ በእርሱ ይቆጣጠራችኋል*”፡፡ وَإِن تُبْدُوا مَا فِي أَنفُسِكُمْ أَوْ تُخْفُوهُ يُحَاسِبْكُم بِهِ اللَّهُ ۖ

“አንፉሥ” أَنْفُس የነፍሥ ብዙ ቁጥር ሲሆን እዚህ አንቀጽ ላይ "ራሳችሁ" ለሚለው የገባው ቃል "አንፉሢኩም" أَنفُسِكُمْ ነው፥ ሰው ውስጡ ያለውን በንግግሩ ይግለጸው ወይም በልቡ ይደብቀው አሏህ ያውቀዋል። “ነፍሥ” نَفْس ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል የገባው "ቀልብ" قَلْب ሲሆን "ልብ" ማለት ነው፦
15፥51 *”አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል*፡፡ አላህም ዐዋቂ ታጋሽ ነው፡፡ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا فِي قُلُوبِكُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَلِيمًا

"ቁሉብ" قُلُوب የቀልብ ብዙ ቁጥር ሲሆን እዚህ አንቀጽ ላይ "ልቦቻችሁ" ለሚለው የገባው ቃል "ቁሉቢኩም" قُلُوبِكُمْ ነው፥ አምላካችን አሏህ የሚመለከተው ይህንን ውስጣዊ ምንነት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 42
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አሏህ ወደ ልባችሁ እና ወደ ሥራችሁ እንጂ ወደ ቅርጻችሁ እና ወደ ገንዘባችሁ አይመለከትም"*፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنْظُرُ إِلَى صُوَرِكُمْ وَأَمْوَالِكُمْ وَلَكِنْ يَنْظُرُ إِلَى قُلُوبِكُمْ وَأَعْمَالِكُمْ ‏"‏

“ዐመል” عَمَل ማለት “ገቢር” ወይም “ድርጊት” አሊያም "ሥራ" ማለት ሲሆን የዐመል ብዙ ቁጥር ደግሞ "አዕማል" أَعْمَال ነው፥ ሰው የሚሠራው ሥራ ልቡ ውስጥ ያለው እሳቤ ነው። በሰው ውስጥ ያለው ይህ እሳቤ እና ችሎታ እውነተኛ ሀብት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 81, ሐዲስ 35
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ሀብት ማለት መጠነ ሰፊ ንብረት መያዝ አይደለም። ነገር ግን ሀብት ማለት የነፍስ ሀብት ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لَيْسَ الْغِنَى عَنْ كَثْرَةِ الْعَرَضِ، وَلَكِنَّ الْغِنَى غِنَى النَّفْسِ ‏”‌‏.‏

ሰው የአስተሳሰቡ ውጤት ነው። ይህ የአስተሳሰብ ቅኝት ያላቸው ሰዎች በሦስት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦
፨ አንደኛ ታናሽ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ከራሳቸው ይልቅ ስለ ሰው በማወቅ፣ በማሰብ እና በማውራት የተጠመዱ ናቸው። ለምሳሌ የባልቴት ቡና ወሬ በሆነው በሐሜት ላይ ተጥደው የሚውሉ ቦዘኔዎችና አቦዝናዎች ናቸው።
፨ ሁለተኛ መካከለኛ አስተሳሰን ያላቸው ስለ ወቅታዊ ነገር በማወቅ፣ በማሰብ እና በማውራት የተጠመዱ ናቸው። ለምሳሌ ኳስ እና የኩፍር ከፋፋይ ፓለቲካ አንዱ ማሳያ ነው፥ ይህ የመረጃ ዕውቀት ወቅታዊ እንጂ ዘለቄታዊ ይዘት የሌለው ነው።
፨ ሦስተኛ ታላቅ አስተሳሰብ ያላቸው "ሥን"logy" ያማከለ ዕውቀት ያላቸው እና የአሳብን ልዕልና፣ ሉዓላዊት እና ዘውግ ይዘውና አንግበው የሚሞግቱ ነባቢያን ናቸው፥ እነዚህ ልባውያን ከውጪ ክብሪት"methodology" በመጠቀም ውስጣቸው ያለውን የእሳቤ ነዳጅ"generated knowledge" በማብራት ራእያቸውን አበርክተው ያልፋሉ።
ትልቁ የምድራችን ሀብት ያለው በሰው ውስጥ ነው፥ ዛሬ ላይ የምንጠቀምበት ሞባይል፣ ኢንተርኔት፣ መኪና፣ አውሮፕላን ወዘተ ከሰው ውስጥ የወጡ እሳቦት ናቸው። ይህ አሏህ ለነፍሥ የሰጣት ድንቅ ችሎታ ነው፦
23፥62 *ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም*፡፡ وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا

"ውሥዕ" وُسْع ማለት "ችሎታ" ማለት ሲሆን ይህ ችሎታ ውሳጣዊ ሀብት ነው፥ ይህንን ሀብት አውጥተህ መጠቀምና መጥቀም ትፈልጋለህ ወይስ በመቃብር ውስጥ ይዘውት ከቀበሩት አንዱ ለመሆን ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ለራስህ ጊዜ ሰጥተህ ከራስህ ጋር አውራ! ከዲያሎግ በፊት ሞኖሎግ ብታስቀድም ውስጥ ያለው የነፍሥ ሀብት ይወጣል። አሏህ የውስጥ ሀብት ከሚጠቀሙ እና ከሚጠቅሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ግመል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

88፥17 *“ከሓዲዎች አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!”*። أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ

የሚሽነሪዎች ጥያቄ አንዳንዴ ውጥን ቅጡ፣ መላ ቅጡ፣ ቅጥ አንባሩ እና ውጥ አንባሩ የጠፋበት ነው ብል ግነት ወይም እብለት አይሆንብኝም፥ ብስለትን ሳይሆን ብሶትን ታሳቢ ያደረገ ጥያቄ ሁሌም የእልህ ጉዳይ እንደሆነ ያሳብቃል። አሁን ደግሞ፦ "ቁርኣን በዐረብ ምድር ስለ ግመል የሚነገረውን ምናባዊ ትርክት ይተርካል፥ ግመል ወደ ሰማይ ከፍ ያለች፣ ወደ ምድር የተዘረጋች እንደሆነች እና ርዝመቷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ እንደሆነች ይናገራል" ይላሉ፥ ይህ ምልከታ የሳም ሻሙን ሆነ የዴቪድ ዉድ የቁርኣኑን ዐውደ-ንባብ በቅጡ ካለማወቅ የመጣ የተንሸዋረረ፣ የተውረገረገ፣ የተሳከረ እና የደፈረሰ ምልከታ ነው። እስቲ የቁርኣኑን አናቅጽ በሰላላ እና በተረጋጋ አእምሮ እንመልከት፦
88፥17 *“ከሓዲዎች አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!”*። أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى الْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ

ይህ አንቀጽ ላይ አምላካችን አሏህ ከሓዲዎች ይመልከቱ ብሎ ካቀረባቸው ፍጥረት መካከል ግመል አንዷ ናት፥ ቀጥሎ ስለ ሰማይ አፈጣጠር ይናገራል፦
88፥18 *"ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!"* وَإِلَى السَّمَاءِ كَيْفَ رُفِعَتْ

ሲጀመር እዚህ አንቀጽ ላይ "ወ" وَ የሚል መስተጻምር ከላይ ካለው አንቀጽ ለመለየት የገባ ሲሆን ከፍ ተደረገች የሚለው ግመሏን ሳይሆን ሰማይን ነው፥ "ኢላ" إِلَى ማለትም "ወደ" የሚለው መስተዋድድ ሓዲዎች እንዲመለከቱ የገባ እንጂ ግመሏ ወደ ሰማይ ከፍ ተደረገች የሚል ምንም ሽታው የለም። በሌሎች የቁርኣን አናቅጽ ከፍ የተደረገችው ሰማይ እንደሆነች ፍትንው ብሎ ተቀምጧል፦
52፥5 “ከፍ በተደረገው ጣሪያም”፡፡ وَالسَّقْفِ الْمَرْفُوعِ
21፥32 “ሰማይንም የተጠበቀ ጣሪያ አደረግን”፡፡ وَجَعَلْنَا السَّمَاءَ سَقْفًا مَّحْفُوظًا

ሲቀጥል "ኢላ" إِلَى የሚለው መስተዋድድ በቀጣይ "ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ አይመለከቱምን" በማለት ይናገራል፦
88፥19 *"ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!"* وَإِلَى الْجِبَالِ كَيْفَ نُصِبَتْ

አያችሁ ግመልን በአንስታይ እና በነጠላ "እነደተፈጠረች" የሚል ስላለ እና በተመሳሳይ ሰማይን በአንስታይ እና በነጠላ "ከፍ እንደ ተደረገች" የሚል ስላለ ተምታታባችሁ እንጂ ስለ ተራራዎች በብዜት "እንደ ተቸከሉ" የሚለው ተራሮችን ብቻ ካመለከተ በተመሳሳይ ሰዋስው "ከፍ እንደ ተደረገች" የሚለው ሰማይን እንጂ ግመልን አመላካች አይደለም። ቀጣዩ አንቀጽ ደግሞ ከሓዲዎች ምድር እንዴት እንደተዘረጋች እንዲመለከቱ ይጋብዛል፦
88፥20 *"ወደ ምድርም እንዴት እንደተዘረጋች አይመለከቱምን?"*። وَإِلَى الْأَرْضِ كَيْفَ سُطِحَتْ

እዚህ አንቀጽ ላይ የተዘረጋችው ምድር እንጂ ግመል እንደሆነ የሚያሳይ ፍንጭ የለም። በሌሎች የቁርኣን አናቅጽ የተዘረጋችው ምድር እንደሆነች ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል፦
51፥48 *”ምድርንም ዘረጋናት፡፡ ምን ያማርንም ዘርጊዎች ነን!”* وَالْأَرْضَ فَرَشْنَاهَا فَنِعْمَ الْمَاهِدُونَ
79፥30 *”ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት”*፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا

ስለዚህ ቁርኣን "ግመል ወደ ሰማይ ከፍ አለች፥ ወደ ምድር ተዘርግታለች" የሚል ቅጥፈት ሆኖ ተብሎ ቁርኣንን ለማጠልሸት ነው። ዐውዱ ግመልን፣ ሰማይን፣ ተራራን እና ምድርን ለመለየት "ወ" وَ የሚል መስተጻምር በእያንዳንዱ አንቀጽ መጠቀሙን አንባቢ ልብ ይለዋል።
ቀጥሎ ግመል ርዝመቷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ እንደሆነ ይናገራል ያሉበትን አናቅጽ እንመልከት፦
77፥32 *"እርሷ እንደ ታላላቅ ሕንጻ የኾኑን ቃንቄዎች ትወረውራለች"*፡፡ إِنَّهَا تَرْمِي بِشَرَرٍ كَالْقَصْرِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "እርሷ" የተባለችው "እሳት" ስትሆን እርሷ ሸረር ትወረውራለች፥ "ሸረር" شَرَر ማለት "ፍንጣሪ ብልጭታ"spark" ሲሆን "ቃንቄ" ተብሏል። ቋንቄ ይዘቱ ልክ እንደ ታላላቅ ሕንጻ ሲሆኑ መልካቸው ደግሞ እንደ ዳለቻ ግመል ነው፦
77፥33 *"ቃንቄውም ልክ ዳለቻዎች ግመሎችን ይመስላል"*፡፡ كَأَنَّهُ جِمَالَتٌ صُفْرٌ

"አምባላይ" ማለት "ነጭ"፣ "ዳማ" ማለት "ቀይ"፣ "ጒራቻ" ማለት "ጥቁር"፣ "ሐመር" ማለት "አረንጓዴማ"፣ "ዳለቻ" ማለት "ቢጫ" ማለት ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ ግመል ልክ እንደ ሕንጻ ትልቅ ናት የሚል ፍንጭ በባትሪ ብትፈልጉ አታገኙም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሐላል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥116 *"በአላህም ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፥ ይህም እርም ነው» አትበሉ"*፡፡ وَلَا تَقُولُوا لِمَا تَصِفُ أَلْسِنَتُكُمُ الْكَذِبَ هَـٰذَا حَلَالٌ وَهَـٰذَا حَرَامٌ لِّتَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ

“ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” “ሕግ” "መርሕ" ማለት ነው፥ “አሕካም” أَحْكَام‎ ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕግጋት” ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ሲከፈሉ፥ ከአምስቱ አንዱ "ሐላል" ነው። "ሐላል" حَلاَل ማለት "የተፈቀደ" ማለት ነው፦
16፥116 *"በአላህም ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት «ይህ የተፈቀደ ነው፥ ይህም እርም ነው» አትበሉ"*፡፡ وَلَا تَقُولُوا لِمَا تَصِفُ أَلْسِنَتُكُمُ الْكَذِبَ هَـٰذَا حَلَالٌ وَهَـٰذَا حَرَامٌ لِّتَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ الْكَذِبَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “የተፈቀደ” ለሚለው የገባው ቃል “ሐላል” حَلاَل መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አንድ ጉዳይ ሐላል ወይም ሐራም ማለት የሚችለው የዓለማቱ ጌታ አሏህ በነቢዩ”ﷺ” ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐላል የሆነ ጉዳይ ሆነ ሐራም የሆነ ጉዳይ በሸሪዓችን በግልጽ የተቀመጡት ብቻ ናቸው፦
7፥157 *"መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል፥ መጥፎ ነገሮችንም በእነርሱ ላይ እርም ያደርግባቸዋል"*፡፡ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 23, ሐዲስ 4
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሐላል ግልጽ ነው፥ ሐራምም ግልጽ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ግን አጠራጣሪ ነገር ነው”። قَالَ سَمِعْتُ النُّعْمَانَ بْنَ بَشِيرٍ، – وَلاَ أَسْمَعُ أَحَدًا بَعْدَهُ يَقُولُ – سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ إِنَّ الْحَلاَلَ بَيِّنٌ وَإِنَّ الْحَرَامَ بَيِّنٌ وَبَيْنَهُمَا أُمُورٌ مُشْتَبِهَاتٌ ‏”‏

አንድ ጉዳይ በግልጽ መፈቀዱ እና መከልከሉ ካልተገለጸ "ተፈቅዷል" "ተከልክሏል" ማለት የለብንም፥ ያልተፈቀደ እና ያልተከለከለ ነገር ጉዳይ አጠራጣሪ ነው፥ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ፦ "የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል" ብለውናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 2708
አቢል ሐውራእ አሥ-ሠዕዲይ እንደተረከው፦ "እኔ ለሐሠን ኢብኑ ዐሊይ፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ምን ሐፈዝክ? ብዬ አልኩኝ፥ እርሱም፦ "ከአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሐፈዝኩኝ፦ *"የሚያጠራጥርህን ትተህ ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት ያረጋጋል፥ ውሸት ግን ያጠራጥራል"*። عَنْ أَبِي الْحَوْرَاءِ السَّعْدِيِّ، قَالَ قُلْتُ لِلْحَسَنِ بْنِ عَلِيٍّ مَا حَفِظْتَ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ حَفِظْتُ مِنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ دَعْ مَا يَرِيبُكَ إِلَى مَا لاَ يَرِيبُكَ فَإِنَّ الصِّدْقَ طُمَأْنِينَةٌ وَإِنَّ الْكَذِبَ رِيبَةٌ ‏"‏

ቅሉ ግን ከዚያ በተቃራኒ ሸሪዓህ በመቃረን ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ በአሏህ ላይ አሻርከዋል፦
42፥21 *"ከሃይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ “የደነገጉ” ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን?"* أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ

እዚህ አንቀጽ ላይ “የደነገጉ” ለሚለው የገባው ቃል “ሸረዑ” شَرَعُوا ሲሆን መለኮታዊ ያልሆነ ከዝንባሌአቸው ሸሪዓህ መደንገጋቸው የሚያሳይ ቃል ነው። “ሸሪክ” شَرِيك ማለት “ተጋሪ” ማለት ነው፥ የሸሪክ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሹረካእ” شُرَكَاء ሲሆን “ተጋሪዎች” ማለት ነው፥ አሏህ በእርሱ ያልፈቀደውን ነገር ሐላል ማድረግ ለእነርሱ የደነገጉ በአላህ ሐቅ ላይ ተጋሪዎች አሏቸው። እነዚህ የአሏህን ሐቅ የሚጋሩ ሰዎች እራሳቸው ተሕሊል እና ተሕሪም በማድረጋቸው ጣዖታት ናቸው፦
4፥60 ወደ እነዚያ እነርሱ በአንተ ላይ በተወረደው እና ከአንተ በፊትም በተወረደው አምነናል ወደሚሉት አላየህምን? “በእርሱ እንዲክዱ በእርግጥ የታዘዙ ሲኾኑ ወደ ጣዖት መፋረድን ይፈልጋሉ”፡፡ أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ يَزْعُمُونَ أَنَّهُمْ آمَنُوا بِمَا أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَا أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ يُرِيدُونَ أَن يَتَحَاكَمُوا إِلَى الطَّاغُوتِ وَقَدْ أُمِرُوا أَن يَكْفُرُوا بِهِ

አንድ ሰው አሏህ ካወረደው ውጪ፦ "ይህ ነገር ሐራም ነው፥ ይህ ነገር ሐላል ነው" ካለ እርሱ ጣዖት ነው። “ጧጉት” طَّٰغُوت የሚለው ቃል “ጦጋ” طَغَىٰ ማለትም “ወሰን አለፈ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “በአላህ ሐቅ ላይ ወሰን ማለፍ” ማለት ነው። ስለዚህ "ሐላል ሙዚቃ፣ ሐላል ድራማ፣ ሐላል ፊልም፣ ሐላል ኮሜዲ፣ ሐላል መዝናኛ፣ ሐላል ሜካፕ" እያልን ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በግልጽ ሐላል ያልተባለን ጉዳይ ሐላል የምንል ሰዎች ቆም ብለን ከላይ ያሉትን የአምላካችን የአሏህን ንግግር እና የነቢዩን"ﷺ" ሐዲስ እናስተውል! ያለበለዚያ የነቢያችን"ﷺ" ትንቢት በእኛ እንዳይፈጸም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 16
አቡ ዐሚር ወይም አቡ ማሊኩል አሽዐሪይ እንደተረከው፦ “ወሏሂ አልዋሸውም! ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ *”ከኡመቴ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ለራሳቸው ዝሙትን፣ ሐር ልብስን፣ አስካሪ መጠጥን እና ሙዚቃን ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ”*። قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو عَامِرٍ ـ أَوْ أَبُو مَالِكٍ ـ الأَشْعَرِيُّ وَاللَّهِ مَا كَذَبَنِي سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ “‏ لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ

አምላካችን አሏህ ሸሪዓችን፦ "ሐላል ያለውን ሐላል፥ ሐራም ያለውን ሐራም" የምንለን ያድርገን! ዝንባሌአችንን ከመከተል ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነቢዩ የዕቁብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥72 *"ለእርሱም ኢሥሓቅን እና የዕቁብን ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው፡፡ ሁሉንም መልካሞች አደረግን"*። وَوَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ نَافِلَةً ۖ وَكُلًّا جَعَلْنَا صَالِحِينَ

በቁርኣን ውስጥ ስማቸው ከተጠቀሱት ከሃያ አምስቱ ነቢያት አንዱ የኢሥሓቅ ልጅ የዕቁብ ነው፥ አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም ኢሥሓቅን ልጅ እንዲሁ የዕቁብን የልጅ ልጅ አድርጎ ሰቶታል፦
29፥27 *"ለእርሱም ኢሥሓቅን እና የዕቆብን ሰጠነው፥ በዘሩም ውስጥ ነብይነትን እና መጽሐፍን አደረግን"*፡፡ وَوَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَجَعَلْنَا فِي ذُرِّيَّتِهِ النُّبُوَّةَ وَالْكِتَابَ
21፥72 *"ለእርሱም ኢሥሓቅን እና የዕቆብን ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው፡፡ ሁሉንም መልካሞች አደረግን"*። وَوَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ نَافِلَةً ۖ وَكُلًّا جَعَلْنَا صَالِحِينَ

ይህ እንዲህ በእንዲህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች፦ "ቁርኣን የዕቁብ የኢብራሂም ልጅ እና የኢሥሓቅ ወንድም በማድረግ ታሪኩን አዛብቷል" በማለት ቁርኣንን ሊያጠለሹ ይሞክራሉ፥ እኛም እዚህ ድምዳሜ ላይ ያደረሳችሁ የትኛው ኃይለ-ቃል ነው? ስንል እነርሱም፦ "ለኢብራሂም ኢሥሓቅን እና የዕቆብን ሰጠነው" ስለሚል ይላሉ። "ለእርሱም ኢሥሓቅን እና የዕቆብን ሰጠነው" በሚል ኃይለ-ቃል ውስጥ የዕቁብ የኢብራሂም ልጅ እና የኢሥሓቅ ወንድም ስለመሆኑ የሚያሳይ ምንም ሽታው የለም፥ ከዚያ ይልቅ ኢሥሓቅ የየዕቁብ አባት እንደሆነ ተገልጿል፦
2፥133 *"የዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ፦ "ከእኔ በኋላ ማንን ታመልካላችሁ? ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? እነርሱም፦ አምላክህን እና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢስማዒልን እና የኢሥሓቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለእርሱ ፍፁም ታዛዦች ኾነን እናመልካለን" አሉ"*፡፡ أَمْ كُنتُمْ شُهَدَاءَ إِذْ حَضَرَ يَعْقُوبَ الْمَوْتُ إِذْ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعْبُدُونَ مِن بَعْدِي قَالُوا نَعْبُدُ إِلَـٰهَكَ وَإِلَـٰهَ آبَائِكَ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ إِلَـٰهًا وَاحِدًا وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ የዕቁብ ልጆች ለአባታቸው ኢሥሓቅ አባትህ ብለውታል። እናንተ እንደምትቀጥፉት ኢሥሓቅ ለየዕቁብ ወንድም ከሆነ ወንድም አባት እንዴት ሊባል ይችላል? ኢሥማዒል የየዕቁብ አጎት ስለሆነ አባት ሊባል ይችላል፥ ምክንያቱም ኢሥማዒል እና ኢሥሓቅ ወንድማማቾች ናቸውና፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 45
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ለሐሠን እና ለሑሠይን ኢሥቲዓዛህ እያረጉ እንዲህ ይሉ ነበር፦ "አባታችሁ ኢብራሂም ለኢሥማዒል እና ለኢሥሓቅ፦ "ፍጹም በሆነው በአሏህ ቃላትን ከሁሉም ሸይጧን፣ ከመርዛማነት እና ከሸረኛ ዓይን ኢሥቲዓዛህ አረጋለው" ይል ነበር*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يُعَوِّذُ الْحَسَنَ وَالْحُسَيْنَ وَيَقُولُ ‏ "‏ إِنَّ أَبَاكُمَا كَانَ يُعَوِّذُ بِهَا إِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ، أَعُوذُ بِكَلِمَاتِ اللَّهِ التَّامَّةِ مِنْ كُلِّ شَيْطَانٍ وَهَامَّةٍ، وَمِنْ كُلِّ عَيْنٍ لاَمَّةٍ ‏"‌‏.‏
ሐሠን እና ሑሠይን ወንድማማቾች በተባሉበት ሒሣብ ኢሥማዒል እና ኢሥሓቅ ወንድማማቾች ተብለዋል፥ ኢብራሂም ለሐሠን እና ለሑሠይን አባት የተባለው በዝርያ ደረጃ እንጂ በመውለድ ደረጃ እንዳለሆነ ሁሉ ኢብራሂም ለየዕቁብ "አባት" የተባለው የልጅ ልጁ ስለሆነ ብቻ ነው። ኢብራሂም ለዩሡፍ አባት ተብሏል፦
12፥38 የአባቶቼን የኢብራሂምን፣ የኢሥሓቅን እና የየዕቁብን ሃይማኖት ተከትያለሁ"*፡፡ وَاتَّبَعْتُ مِلَّةَ آبَائِي إِبْرَاهِيمَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ

ዩሡፍ ወላጁን የዕቁብን፣ አያቱን ኢሥሓቅን እና ቅድመ-አያቱን ኢብራሂምን "አባቶቼ" ብሏል፥ ኢሥሓቅ ለዩሡፍ አያቱ መሆኑ መገለጹ እና የዕቁብ ለኢሥሓቅ ልጅ መሆኑ መገለጹ በራሱ ኢብራሂም የየዕቆብ ወላጅ እንዳልሆነ ማሳያ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 56
አቢ ዑመር"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የክቡር ልጅ፣ የክቡር ልጅ፣ የክቡር ልጅ ክቡር ነው። ሰላም በእነርሱ ላይ ይሁን! የየዕቆብ ልጅ፣ የኢሥሓቅ ልጅ፣ የኢብራሂም ልጅ ዩሡፍ ነው"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ "‏ الْكَرِيمُ ابْنُ الْكَرِيمِ ابْنِ الْكَرِيمِ ابْنِ الْكَرِيمِ يُوسُفُ ابْنُ يَعْقُوبَ بْنِ إِسْحَاقَ بْنِ إِبْرَاهِيمَ ـ عَلَيْهِمُ السَّلاَمُ ‏"‌‏.‏

ይህ ሐዲስ የዕቁብ ለኢሥሓቅ ልጅ መሆኑ ፍትንውና ቁልጭ አድርጎ ካሳየ ከዚህ በላይ ማስረጃ ምን ትፈልጋላችሁ? "ቁርኣን የዕቁብ የኢብራሂም ልጅ እና የኢሥሓቅ ወንድም ይላል" የሚለው ውኃ የማያነሳ እና የማይቋጥር ቅሪላ፣ እንኩቶ፣ አንኮላ ሙግት ነው። ይልቁንስ አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም ኢሥሓቅን ልጅ እንዲሁ የዕቁብን የልጅ ልጅ አርጎ ከመስጠትም ባሻገር ኢብራሂምን፣ ኢሥሓቅን እና የዕቁብን ነቢይ እንዳደረጋቸው ይናገራል፦
19፥49 *"እነርሱንም ከአላህ ሌላ የሚያመልኩትት በራቀ ጊዜ ለእርሱ ኢሥሓቅ እና የዕቁብን ሰጠነው፥ ሁሉንም ነቢይ አደረግንም"*፡፡ فَلَمَّا اعْتَزَلَهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ وَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ ۖ وَكُلًّا جَعَلْنَا نَبِيًّا

"ሁሉንም ነቢይ አደረግንም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! የዕቆብ ወሕይ የሚመጣለት ነቢይ ስለነበረ ከነ ልጆቹ አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት የሚያመልኩ ሙሥሊሞች ነበሩ፦
2፥133 *"የዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ፦ "ከእኔ በኋላ ማንን ታመልካላችሁ? ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? እነርሱም፦ አምላክህን እና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢሥማዒልን እና የኢሥሓቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለእርሱ ፍፁም ታዛዦች ኾነን እናመልካለን" አሉ"*፡፡ أَمْ كُنتُمْ شُهَدَاءَ إِذْ حَضَرَ يَعْقُوبَ الْمَوْتُ إِذْ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعْبُدُونَ مِن بَعْدِي قَالُوا نَعْبُدُ إِلَـٰهَكَ وَإِلَـٰهَ آبَائِكَ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ إِلَـٰهًا وَاحِدًا وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

የዕቆብ ልጆች የሚያመልኩት የአባታቸውን የየዕቁብን፣ የኢሥማዒልን፣ የኢሥሓቅን እና የኢብራሂምን አምላክ ነው፥ ይህንን አንድ አምላክ ስለሚያመልኩ እኛ ለአሏህ "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ኾነን እናመልካለን" አሉ። ስለዚህ ቁርኣን ላይ ሕጸጽ እና ግድፈት ከምትፈልጉ ይልቅ የነቢያትን አምላክ በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቀሪን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥95 *”ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል”*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ

የአእምሮ ስንኩላን ከትልቅ እስለ ደቂቅ ያለ አንዳች ከልካይ የባልቴት የቡና ወሬ ሲነዙ ማየት ዐላዋቂነትን ከማሳበቅ ውጪ አንዳች የሚፈይዱት ነገር የለም። በኢሥላም ያሉ የመስኩ ሊሒቃን፦ “ውኃን ከጡሩ፥ ነገርን ከሥሩ” ይላሉና እኛም ከሥሩ ስለ ቀሪን የተነሳውን የወይዛዝርት የቡና ወሬ በትክክለኛ የአስተላለፍና የአስነዛዘር ሙግት እንሞግታለን። “ቀሪን” قَرِين የሚለው ቃል 8 ጊዜ በቁርኣን የተጠቀሰ ሲሆን “ጓደኛ” ማለት ነው፦
37፥51 ከእነርሱ የሆነ ተናጋሪ ይላል፦ *”እኔ ጓደኛ ነበረኝ”*፡፡ قَالَ قَائِلٌ مِّنْهُمْ إِنِّي كَانَ لِي قَرِينٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀሪን” قَرِين የተባለበው ሰው ለሰው “ጓደኛ” በሚሆንበት ስሌት ነው። ስለዚህ “ቀሪን” ማለት “ሸይጧን” ማለት ሳይሆን “ጓደኛ” ማለት ብቻ ነው። ለምሳሌ ሥራችንን የሚመዘግቡ መልአክ “ቀሪን” قَرِين ተብለዋል፦
50፥23 *”ቁራኛውም መልአክ”* «ይህ ያ እኔ ዘንድ ያለው ቀራቢ ነው» ይላል፡፡ وَقَالَ قَرِينُهُ هَـٰذَا مَا لَدَيَّ عَتِيد

“ቀሪኑሁ” قَرِينُهُ ማለት “ጓደኛው” ማለት ነው። ሰው ለሰው ጓደኛ እንደተባለ ሁሉ ወይም ለአማንያን መልአክ ጓደኛ እንደተባለ ሁሉ ሸይጧን ለከሃድያን “ጓደኛ” ነው፦
43፥36 *ከአልረሕማን ግሣጼ ከቁርኣን የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን፡፡ ስለዚህ እርሱ ለእርሱ “ቀሪን” ነው*፡፡ وَمَن يَعْشُ عَن ذِكْرِ الرَّحْمَـٰنِ نُقَيِّضْ لَهُ شَيْطَانًا فَهُوَ لَهُ قَرِينٌ
4፥38 እነዚያም ለሰዎች ይውልኝ ሲሉ ገንዘቦቻቸውን የሚሰጡ በአላህና በመጨረሻውም ቀን የማያምኑ ይቀጣሉ፡፡ *”ሰይጣንም ለእርሱ ጓደኛው የኾነ ሰው ጓደኛነቱ ከፋ!* وَالَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ رِئَاءَ النَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَلَا بِالْيَوْمِ الْآخِرِ ۗ وَمَن يَكُنِ الشَّيْطَانُ لَهُ قَرِينًا فَسَاءَ قَرِينًا

ልብ አድርግ “ጓደኛ” ለሚለው ቃል እዚህ ጋር የገባው “ቀሪን” قَرِين ነው። ለሰው ከሰው፣ ለሰው ከመልአክ እና ለሰው ከጂን ጓደኛ ሊኖረው ይችላል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 52, ሐዲስ 62
ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከእናንተ መካከል ማንም የለም ከጂን የሆነ ጓደኛ ቢኖረው እንጂ። እነርሱም(ሠሐባዎች)፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” ሆይ! እርስዎም ቢሆኑ? አሉ። እርሳቸውም፦ “እኔም ብሆን፥ ግን አላህ በእርሱ ላይ እረድቶኛል። በመልካም እንጂ እንዳያዘኝ አሥልሞታል”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَا مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلاَّ وَقَدْ وُكِّلَ بِهِ قَرِينُهُ مِنَ الْجِنِّ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا وَإِيَّاكَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏”‏ وَإِيَّاىَ إِلاَّ أَنَّ اللَّهَ أَعَانَنِي عَلَيْهِ فَأَسْلَمَ فَلاَ يَأْمُرُنِي إِلاَّ بِخَيْر

እዚህ ሐዲስ ላይ “ጓደኛ” ለሚለው ቃል “ቀሪን” قَرِين የሚለው ቃል መግባቱ አንባቢ ልብ ይለዋል። እዚሁ ሐዲስ ላይ “አሥለመ” َأَسْلَم ማለት ሁለት ትርጉም አለው፤ አንደኛ “ታዘዘ” ማለት ሲሆን የስም መደቡ “ሙሥሊም” مُسْلِم ማለት ነው፥ የእርሳቸው ጓደኛ ሙሥሊም ጂን እንጂ ካፊር ጂን አለሞሆኑን እንረዳለን። ሁለተኛ “ጠበቀ” ሲሆን የስም መደቡ “ሙሠለም” مُسَلَّم ማለትም “የተጠበቀ” ማለት ነው፥ እርሳቸው ከእርሱ እኩይ የተጠበቁ መሆናቸውን እንረዳለን።
ዋቢ ማብራሪያ፦ “ኢማም ነወዊ አል-ሚንሃጅ ሸርሕ ሰሒሕ ሙሥሊም መጽሐፍ 52, ሐዲስ 62 ተመልከት።

ጂን ደግሞ ልክ እንደ ሰው ነጻ ፈቃድ ያላቸው ፍጡራን ናቸው። “ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፥ “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው። ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

ጂኒዎች የተፈጠሩበት ዓላማ የፈጠራቸው አላህ እንዲያመልኩ ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
ጂኒዎች እንደ ሰው ነጻ ምርጫ ያላቸው ፍጡሮች ናቸው፥ በነጻ ምርጫቸው ሙሥሊም አልያም ካፊር የመሆን ምርጫ አላቸው፦
72፥14 *«እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አሉ፡፡ የሰለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡»* وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا

ከጂኒዎች መካከል አማንያን እንዳሉ ሁሉ ከሃድያንም አሉ፥ ከሃድያኑ “ሰይጣናት” ይባላሉ። “ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፥ “ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው። “ሸይጧን” ልክ እንደ “ሌባ” “ውሸታም” “ባለጌ” የባህርይ ስም እንጂ የተጸውዖ ስም አይደለም። ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጂን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ
7፥200 *ከሰይጣንም በኩል ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና*፡፡ وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

ይህንን ከተረዳን “ቀሪን” እና “ጂን” የሚለውን በአሉታዊ መረዳት የለብንም። ሚሽነሪዎች በመቅድመ ግንዛቤአቸው፦ “ቀሪን” እና “ጂን” ማለት “ሸይጧን” ማለት ነው” ብለው ስለተረዱት ነቢያችን”ﷺ” እርስዎ ቢሆኑ? ተብለው ሲጠየቁ፦ “እኔም ብሆን” ስላሉ “እርሳቸው ሸይጧን ተጸናውቷቸው ነበር” ብለው መረዳታቸው የቡና ወሬ ነው። የጂኒ ቀሪን እንዲህ ካብከነከናችሁ ሰይጣን ኢየሱስን ወደ ከተማ እና ወደ ተራራ በማንጦልጦል እየወሰደ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም ያሳየው ነበር፦
ማቴዎስ 4፥5 ከዚህ በኋላ *”ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደው”* እና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ።
ማቴዎስ 4፥8 ደግሞ *”ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው”*፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ።

“ወሰደው” እና “አሳየው” የሚሉት ኃይለ-ቃላት ይሰመርባቸውም። እስከ ዶቃ ማሰሪያ ድረስ መናገርና ቋንጃን መስበር ይቻል ነበር፥ ነገር ግን ስለማይገባውና ስለማያገባው ሰው ውጥረትና እጥረት ስለሚፈጥር ትተነዋል። ጨውን ሺ ጊዜ እሬት ብትለው ስሙን እንጂ ጣዕሙን መቀየር አትችልም፥ እንዲሁ ነቢያችንን”ﷺ” ሺ ጊዜ ውሸተኛ ለማድረግ ብትጥርም ስማቸውን እንጂ የምታጠለሸው መለኮታዊ ነቢይነታቸውን መቀየር አትችልም። አምላካችን አላህ”ﷻ” ነቢያችን”ﷺ” ላይ ለሚሳለቁት ተሳላቂዎች በተከበረ ቃሉ በቂ መልስ ሰጥቷል፦
15፥95 *”ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል”*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ገርነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥185 *"አላህ በእናንተ ገሩን ነገር ይሻል፥ በእናንተም ችግሩን አይሻም"*፡፡ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ

አምላካችን አሏህ በእኛ ላይ ገሩን ነገር ይሻል፥ በእኛ ላይ ችግርን አይሻም፦
2፥185 *"አላህ በእናንተ ገሩን ነገር ይሻል፥ በእናንተም ችግሩን አይሻም"*፡፡ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ

"ዩሥር" يُسْر የሚለው ቃል "የሡረ" يَسُرَ ማለትም "አቀለለ" "አገራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቀላል" "ገር" "ቀላልነት" "ገርነት" ማለት ነው፥ የዩሥር ተቃራኒ ደግሞ "ዑሥር" عُسْر ሲሆን "ከባድ" "ችግር" ማለት ነው። የእዚህ መጣጥፍ ዐውድ ላይ "ገርነት" ስንል "ገራገርነት" ወይም "ደርባባነትን" አሊያም የግትርነት ተቃራኒ ሳይሆን "ቀላልነትን" ለማለት እንደሆነ አንባቢያን ይረዳሉ። አሏህ በእኛ ላይ ከአቅማችን በላይ የሆነ ከባድ ነገር አይሻም፦
5፥6 *"አላህ በእናንተ ላይ ምንም ችግር ሊያደርግ አይሻም"*፡፡ ግን ታመሰግኑ ዘንድ ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይሻል፡፡ مَا يُرِيدُ اللَّهُ لِيَجْعَلَ عَلَيْكُم مِّنْ حَرَجٍ وَلَـٰكِن يُرِيدُ لِيُطَهِّرَكُمْ وَلِيُتِمَّ نِعْمَتَهُ عَلَيْكُمْ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

ዐቅም ከሌለህ ቁጭ ብለክ ከባሰም ተኝተህ ሶላትህን መፈጸም ትችላለክ፣ ከታመምክ ወይም በዕድሜ መግፋት ዐቅም ካጣክ አሊያም መንገደኛ ከሆንክ አለመጾም ትችላከክ፣ የንዋይ እጥረት ካለብክ ዘካህ እና ሐጅ አይወጅብብህም፣ በረሃብ ጊዜ ከሆንክና ምንም ምግብ ከሌለ ክልክል የሆነው የእርያ ሥጋ መብላት ትችላለህ፣ በጥም ጊዜ ከሆንክና ምንም መጠጥ ከሌለ ክልክል የሆነውን መኽር መጠጣት ትችላለክ። ምን አለፋህ ዲኑል ኢሥላም ገር ሃይማኖት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 32
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዲን ገር ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ الدِّينَ يُسْرٌ،

የሚያጅበው ነገር አምላካችን አሏህ ቁርኣንን ለመቅራት በምላስ ላይ እንዲሁ በልብ ውስጥ በቃል ለማስታወስ አግርቶታል፦
19፥97 *"በምላስህም ቁርኣንን ያገራነው በእርሱ ጥንቁቆቹን ልታበስርበት በእርሱም ተከራካሪዎችን ሕዝቦች ልታስጠነቅቅበት ነው"*፡፡ فَإِنَّمَا يَسَّرْنَاهُ بِلِسَانِكَ لِتُبَشِّرَ بِهِ الْمُتَّقِينَ وَتُنذِرَ بِهِ قَوْمًا لُّدًّا
54፥17 *"ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው፡፡ አስታዋሽ አለን?"* وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "አገራን" ለሚለው የገባው ቃል "የሠርና" يَسَّرْنَا መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። በተጨማሪም ነገሮችን ሳያካብዱ ቀለል አርጎ ማየት እና ሳያስደነብሩ ተረጋግቶ ማየት የነቢያችን"ﷺ" ሡናህ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 152
አነሥ ኢብኑ ማሊክ"ረ.ዐ." ሰምቶ እንዳስተላለፈው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ነገሮችን ቀለል አርጉ! አታካብዱ! አረጋጉ! አታስደንብሩ!"*። قَالَ سَمِعْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يَسِّرُوا وَلاَ تُعَسِّرُوا، وَسَكِّنُوا وَلاَ تُنَفِّرُوا ‏"‌‏.‏

አሏህ የነቢያችንን"ﷺ" ሡናህ የምከተል ባሪያዎቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዐብድ እና ረብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥164 *"በላቸው «እርሱ አላህ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለውን?"* قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَبْغِي رَبًّا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَيْءٍ

"ዐብድ" عَبْد የሚለው ቃል "ዐበደ" عَبَدَ ማለትም “አመለከ” "ተገዛ" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን እንደ ዐውዱ እና ይዘቱ "አምላኪ" "ተገዢ" የሚል ትርጉም አለው፥ በቁርኣን "ዐብድ" عَبْد የሚለው ቃል "ፈታ" فَتًى ማለትም "አገልጋይ" እንዲሁ "አመት" أَمَة የሚለው "ፈታህ" فَتَاة ማለትም "አገልጋይት" በሚል ቃል መጥቷል፦
2፥221 *"አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቡዋቸው! ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ ያመነችው ባሪያ በእርግጥ በላጭ ናት። ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው፥ ከአጋሪው ጌታ ምንም ቢደንቃችሁ ምእምኑ ባሪያ በላጭ ነው"*፡፡ وَلَا تَنكِحُوا الْمُشْرِكَاتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ ۚ وَلَأَمَةٌ مُّؤْمِنَةٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكَةٍ وَلَوْ أَعْجَبَتْكُمْ ۗ وَلَا تُنكِحُوا الْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا ۚ وَلَعَبْدٌ مُّؤْمِنٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكٍ وَلَوْ أَعْجَبَكُمْ

"ረብ" رَبّ የሚለው ቃል "ሠዪድ" سَيِّد ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ በዩሡፍ ዘመን ለግብጹ ንጉሥ "ገዢ" በሚል መጥቷል፦
12፥25 *"በሩንም ተሽቀዳደሙ ቀሚሱንም ከበስተኋላው ቀደደችው፡፡ ጌታዋንም እበሩ አጠገብ አገኙት"*፡፡ وَاسْتَبَقَا الْبَابَ وَقَدَّتْ قَمِيصَهُ مِن دُبُرٍ وَأَلْفَيَا سَيِّدَهَا لَدَى الْبَابِ
12፥41 *«የወህኒ ቤት ጓደኞቼ ሆይ! አንደኛችሁማ ጌታውን ጠጅ ያጠጣል፡፡ ሌላውማ ይሰቀላል፡፡ ከራሱም በራሪ ትበላለች፡፡ ያ ፍቹን የምትጠይቁት ነገር ተፈጸመ» አላቸው"*፡፡ يَا صَاحِبَيِ السِّجْنِ أَمَّا أَحَدُكُمَا فَيَسْقِي رَبَّهُ خَمْرًا ۖ وَأَمَّا الْآخَرُ فَيُصْلَبُ فَتَأْكُلُ الطَّيْرُ مِن رَّأْسِهِ ۚ قُضِيَ الْأَمْرُ الَّذِي فِيهِ تَسْتَفْتِيَانِ

ቅሉ ግን "ረብ" رَبّ የሚለው ቃል ከአሏህ እንዲሁ "ዐብድ" عَبْد ከባሮቹ ውጪ ለአሳዳሪ እና ለአዳሪ ከተጠቀምን ወደ ሌላ የአምልኮ ዘርፍ እንዳይሄድ በነቢያችን"ﷺ" ጊዜ ተከልኳል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 203
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከእናንተ ማንም፦ "ዐብዲይ" እና አመቲይ" አይበል! መምሉክም፦ "ረቢ" እና "ረበቲይ" አይበል። ማሊክም፦ "ፈታየ" እና "ፈታቲይ" ይበል! መምሉክም ደግሞ፦ "ሠዪዲይ እና ሠዪደቲይ" ይበል። ሁላችሁም ለአሏህ ባሮች ናችሁ፥ አሏህ ዐዘ ወጀልም ጌታ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ يَقُولَنَّ أَحَدُكُمْ عَبْدِي وَأَمَتِي وَلاَ يَقُولَنَّ الْمَمْلُوكُ رَبِّي وَرَبَّتِي وَلْيَقُلِ الْمَالِكُ فَتَاىَ وَفَتَاتِي وَلْيَقُلِ الْمَمْلُوكُ سَيِّدِي وَسَيِّدَتِي فَإِنَّكُمُ الْمَمْلُوكُونَ وَالرَّبُّ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ ‏"‏ ‏.‏

"ማሊክ" مَالِك ማለት "አሳዳሪ" ማለት ሲሆን "መምሉክ" مَمْلُوك ደግሞ በባለቤት ሥር ያለ "አዳሪ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ የሁሉ ጌታ ሲሆን ከአሏህ በቀር የሁሉ ጌታ ማንም የለም፦
6፥164 *"በላቸው «እርሱ አላህ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለውን?"* قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَبْغِي رَبًّا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَيْءٍ

ከወንድም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኪራመን ካቲቢን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

50፥17 *ሁለቱ ቃል ተቀባዮች መላእክት ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ*፡፡ إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ

“ኪራመን ካቲቢን” كِرَامًا كَاتِبِين ማለት “የተከበሩ ጸሐፊዎች” ማለት ሲሆን እነዚህ ጸሐፊዎች በእያንዳንዱ ሰው ቀኝ እና ግራ ያሉ ሁለት መላእክት ናቸው፦
82፥11 *የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ ተጠባባቂዎች*፡፡ كِرَامًا كَاتِبِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የተከበሩ ጸሐፊዎች" ለሚለው የገባው ቃል “ኪራመን ካቲቢን” كِرَامًا كَاتِبِين እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። በቀኝ ያለው መልአክ ሠናይ ተግባራትን ሲመዘግብ በግራ ያለው መልአክ ደግሞ እኩይ ተግባራትን ይመዘግባል፦
82፥10 *በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ ስትኾኑ*፤ وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِين
82፥12 *የምትሠሩትን ሁሉ የሚያውቁ*፡፡ يَعْلَمُونَ مَا تَفْعَلُونَ

አነዚህ ሁለት መላእክት በቀኝና በግራችን ስላሉ በሚስጥር የምንሠራውን፣ የምንናገረውን፣ የምንመካከረው እና የምንወያየውን ሁሉ ያውቃሉ፥ እነዚህ ሁለት መላእክት ሥራችንን፣ ንግግራችንን፣ ውይይታችንን እና ምክክራችንን ተጠባብቀው ዝግጁ ሆነው ስለሚመዘግቡ የማዕረግ ስማቸው “ረቂብ” رَقِيب ማለትም “ተጠባባቂ” እና “ዐቲድ” عَتِيدٌ ማለትም “ዝግጁ” ነው፦
68፥1 *“ኑን”፤ በብርዕ እምላለሁ፥ በዚያም በሚጽፉት"*። نٓ ۚ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ
50፥17 *ሁለቱ ቃል ተቀባዮች መላእክት ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ አስታውስ*፡፡ إِذْ يَتَلَقَّى الْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ الْيَمِينِ وَعَنِ الشِّمَالِ قَعِيدٌ
50፥18 *ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂ እና ዝግጁ የኾኑ መላእክት ያሉበት ቢኾን እንጅ*፡፡ مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ
10፥21 *አላህ ቅጣተ ፈጣን ነው፡፡ «መልክተኞቻችን የምትመክሩትን ነገር በእርግጥ ይጽፋሉ» በላቸው*፡፡ قُلِ اللَّهُ أَسْرَعُ مَكْرًا ۚ إِنَّ رُسُلَنَا يَكْتُبُونَ مَا تَمْكُرُونَ
43፥80 ወይም እኛ ምስጢራቸውን እና ውይይታቸውን የማንሰማ መኾናችንን ያስባሉን? አይደለም፤ *መልክተኞቻችንም እነርሱ ዘንድ ይጽፋሉ*፡፡ أَمْ يَحْسَبُونَ أَنَّا لَا نَسْمَعُ سِرَّهُمْ وَنَجْوَاهُم ۚ بَلَىٰ وَرُسُلُنَا لَدَيْهِمْ يَكْتُبُونَ
የምእምናን መጽሐፍ በእርግጥ በዒሊዮን ውስጥ ነው፥ “ዒሊዪን” عِلِّيِّين “ማለት “ከፍተኛ” ወይም “አርያም” ማለት ሲሆን “ዐሊያህ” عَالِيَة ማለት ደግሞ “ከፍተኛይቱ” ማለት ነው፦
88፥10 *በከፍተኛ ገነት* ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
69፥22 *በከፍተኛይቱ ገነት* ውስጥ፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፤ “ሢጂን” سِجِّين ማለት ደግሞ “እስር” ወይም “እንጦሮጦስ” ማለት ነው፥ “ሠጅን” سِّجْن ማለት “መታሰር” ማለት ሲሆን “መሥጁኒን” مَسْجُونِين ማለት “እስረኞች” ማለት ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ

የትንሳኤ ቀን ይህ የሥራ መዝገብ ይቀርባል፥ ለሰዎች ያስተማሩት ነቢያት እና ኪራመን ካቲቢን ምስክሮች ሆነው ይመጣሉ። ሰውንም ሁሉ በራሪውን ሥራው ተከትቦ በአንገቱ ላይ ይይዝና በትንሣኤ ቀን የተዘረጋ መጽሐፍ ሆኖ ይወጣለታል፥ ሰው መላእክት የከተቡትን ያንን የሥራውን መዝገብ "አንብብ" ይባላል። ከሥራ ትንሽንም ትልቅንም የተጻፈ ቢኾን እንጂ የማይተው ምን የለም፥ የሠሩትንም ነገር ሁሉ ቀራቢ ኾኖ ያገኙታል፦
39፥69 ምድርም በጌታዋ ብርሃን ታበራለች፡፡ *መጽሐፉም ይቅቀረባል፡፡ ነቢያቱ እና ምስክሮቹም ይመጣሉ፡፡ በመካከላቸውም በእውነት ይፈረዳል፡፡ እነርሱም አይበደሉም*፡፡ وَأَشْرَقَتِ الْأَرْضُ بِنُورِ رَبِّهَا وَوُضِعَ الْكِتَابُ وَجِيءَ بِالنَّبِيِّينَ وَالشُّهَدَاءِ وَقُضِيَ بَيْنَهُم بِالْحَقِّ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ
17፥13 *ሰውንም ሁሉ በራሪውን ሥራውን በአንገቱ አስያዝነው፡፡ ለእርሱም በትንሣኤ ቀን የተዘረጋ ኾኖ የሚያገኘው የኾነን መጽሐፍ እናወጣለታለን*፡፡ وَكُلَّ إِنسَانٍ أَلْزَمْنَاهُ طَائِرَهُ فِي عُنُقِهِ ۖ وَنُخْرِجُ لَهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ كِتَابًا يَلْقَاهُ مَنشُورًا
17፥14 *«መጽሐፍህን አንብብ፤ ዛሬ በአንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ በቃ» ይባላል*፡፡ اقْرَأْ كِتَابَكَ كَفَىٰ بِنَفْسِكَ الْيَوْمَ عَلَيْكَ حَسِيبًا
18፥49 *ለሰው ሁሉ መጽሐፉም ይቀርባል፡፡ ወዲያውም ከሓዲዎችን በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ «ዋ ጥፋታችን! ለዚህ መጽሐፍ ከሥራ ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢኾን እንጂ የማይተወው ምን አለው» ይላሉም፡፡ የሰሩትንም ነገር ሁሉ ቀራቢ ኾኖ ያገኙታል፡፡ ጌታህም አንድንም አይበድልም*፡፡ وَوُضِعَ ٱلْكِتَٰبُ فَتَرَى ٱلْمُجْرِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا فِيهِ وَيَقُولُونَ يَٰوَيْلَتَنَا مَالِ هَٰذَا ٱلْكِتَٰبِ لَا يُغَادِرُ صَغِيرَةًۭ وَلَا كَبِيرَةً إِلَّآ أَحْصَىٰهَا ۚ وَوَجَدُوا۟ مَا عَمِلُوا۟ حَاضِرًۭا ۗ وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًۭا

በዒሊዮን ውስጥ ያለው የምእምናን መጽሐፍ ለአማንያን በቀኙ ይሰጠዋል፥ በተቃራኒው በሲጂን ውስጥ ያለው የከሓዲዎቹ መጽሐፍ ለከሃድያን በግራው ይሰጠዋል፦
69፥19 *መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰውማ ለጓደኞቹ «እንኩ፤ መጽሐፌን አንብቡ» ይላል*፡፡ فَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِيَمِينِهِ فَيَقُولُ هَاؤُمُ اقْرَءُوا كِتَابِيَهْ
69፥25 *መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል*፡፡ وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِشِمَالِهِ فَيَقُولُ يَا لَيْتَنِي لَمْ أُوتَ كِتَابِيَهْ

መጽሐፉን በቀኙ የተሰጠ ሰው ምንኛ የተከበረ የቀኝ ጓድ ነው፥ መጽሐፉን በግራው የተሰጠ ሰው ምንኛ የተዋረደ የግራ ጓድ ነው፦
56፥27 *የቀኝም ጓዶች ምንኛ የከበሩ የቀኝ ጓዶች! ናቸው?*። وَأَصْحَابُ الْيَمِينِ مَا أَصْحَابُ الْيَمِين
56፥41 *የግራ ጓደኞችም ምንኛ የተዋረዱ የግራ ጓዶች! ናቸው?*፡፡ وَأَصْحَابُ الشِّمَالِ مَا أَصْحَابُ الشِّمَالِ

አላህ ዒሊዪን ውስጥ ያለው የምእምናን መጽሐፍ በቀኛችን ሰጥቶ የቀኝ ጓዶች ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተሥቢሕ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥44 *”ሰባቱ ሰማያት እና ምድርም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያጠራሉ፡፡ ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም፡፡ ግን ማጥራታቸውን ዐታውቁትም”*፡፡ እርሱ ታጋሽ መሓሪ ነው፡፡ تُسَبِّحُ لَهُ السَّمَاوَاتُ السَّبْعُ وَالْأَرْضُ وَمَن فِيهِنَّ ۚ وَإِن مِّن شَيْءٍ إِلَّا يُسَبِّحُ بِحَمْدِهِ وَلَـٰكِن لَّا تَفْقَهُونَ تَسْبِيحَهُمْ ۗ إِنَّهُ كَانَ حَلِيمًا غَفُورًا

“ሡብሓን” سُبْحَٰن የሚለው ቃል “ሠበሐ” سَبَّحَ ማለትም “አመሰገነ” ወይም “አከበረ” “አጠራ” “አወደሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማህሌት” “ውዳሴ” “ስብሐት” ማለት ነው፦
30፥17 አላህንም በምታመሹ ጊዜ በምታነጉም ጊዜ አጥሩት”*፡፡ فَسُبْحَانَ اللَّهِ حِينَ تُمْسُونَ وَحِينَ تُصْبِحُونَ

“አጥሩ” ለሚለው ቃል የገባው “ሡብሓነ” سُبْحَانَ ሲሆን “ተሥቢሕ” تَسْبِيح ማለት ደግሞ “ተስብሖት” ማለት ነው፥ ለአላህ የምራቀርበት ስብሐት ከላይ አንቀጹ ላይ እንደተቀመጠው “ሡብሓነ አላህ” سُبْحَانَ اللَّه ነው። ሰባቱ ሰማያት እና ምድርም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ፥ ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም፦
17፥44 *”ሰባቱ ሰማያት እና ምድርም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያጠራሉ፡፡ ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም፡፡ ግን ማጥራታቸውን ዐታውቁትም”*፡፡ እርሱ ታጋሽ መሓሪ ነው፡፡ تُسَبِّحُ لَهُ السَّمَاوَاتُ السَّبْعُ وَالْأَرْضُ وَمَن فِيهِنَّ ۚ وَإِن مِّن شَيْءٍ إِلَّا يُسَبِّحُ بِحَمْدِهِ وَلَـٰكِن لَّا تَفْقَهُونَ تَسْبِيحَهُمْ ۗ إِنَّهُ كَانَ حَلِيمًا غَفُورًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም” ስለሚል ሚሽነሪዎች “ሰማያት፣ ምድር፣ ነገር ሁሉ እንዴት ለአላህ ተሥቢሕ ያደርጋል? የሚል እንኩቶ ጥያቄ ይጠይቃሉ፥ የሚጠይቁት ለማወቅ ሳይሆን ጉልበት ላይ አስተኝቶ ጸጉር ለመላጨት ነው። ሰማያት፣ ምድር፣ ነገር ሁሉ ለአላህ ተሥቢሕ ያደርጋሉ፥ “ግን ማጥራታቸውን ዐታውቁትም” ስለተባለ እንዴት አድርገው ተሥቢሕ እንደሚያደርጉ “ከይፊያህ” كَيْفِيَّة ማለትም “እንዴትነት”howness” ዐይታወቅም። ይህንን ነጥብ ይዘን ወደ ባይብል እንደ ውኃ ፈሳሽ፥ እንደ እንግዳ ደራሽ ዘው ብለን ብንገባ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ብርሃን ሁሉ፣ ሰማየ ሰማያት፣ ውኃ ተሥቢሕ ያደርጋሉ፥ የዐረቢኛው ባይብል “ኢሥበሒሂ” سَبِّحِيهِ በማለት ተሥቢሕ እንዲያደርጉ ይናገራል፦
መዝሙር 148፥3 *”ፀሐይና ጨረቃ አመስግኑት! ከዋክብትና ብርሃን ሁሉ አመስግኑት!*። سَبِّحِيهِ يا شَمسُ، وَأنتَ يا قَمَرُ سَبِّحْهُ يا كُلَّ النُّجُومِ المُتَلألِئَةِ، سَبِّحِيهِ
መዝሙር 148፥4 *”ሰማየ ሰማያት፥ አመስግኑት የሰማያት በላይም ውኃ”*። أيَّتُها السَّماواتُ وَالمِياهُ مِنْ فَوقُ، سَبِّحِيهِ

“አመስግኑት” የሚለው የግዕዙ ትእዛዋዊ ግስ እራሱ “ይሴብሕዎ” ሲሆን “ሠበሐ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው፥ የሚያቀርቡት “ስብሐት” ደግሞ ““ተስብሖት” ይባላል፦
መዝሙር 148፥3 *”ይሴብሕዎ ፀሓይ ወወርኅ! ይሴብሕዎ ኵሉ ከዋክብት ወብርሃን!*።
መዝሙር 148፥4 *”ይሴብሕዎ ሰማያተ ሰማያት ወማይኒ ዘመልዕልተ ሰማያት”*።

ምሁራን፦ “ስህተት ለማረም ብሎ ስህተት መሥራት ትልቅ ስህተት ነው” ይላሉ። የእኛን ጥያቄ ለማስረሳት የሚመጡ አዳዲስ ጥያቄዎች እራሳቸው በማንጸሪያ ሲፈተሹ ጥያቄዎቹ ተከረባብተው እራሳቸው ላይ እንደሚዘፈዘፉ አያጤኗቸውም። በአንድ ራስ ሁለት ምላስ፥ በአንድ ቢላ ሁለት የሚከላ ለያዙት ለእነርሱ ሐቁ እንዲህ ፈጦና ገጦ ሲመጣ ብስል እና ጥሬ ይለያሉ ብለን እናምናለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዛሬው እለት በአሶሳ ከተማ ሦስት ፕሮቴስታንት ወደ ዲኑል ኢሥላም በሸሀደተይን ገብተዋል። አል-ሓምዱሊሏህ!
ተክቢር
አሏሁ አክበር
አሏሁ አክበር
አሏሁ አክበር
አድዋ

ተረታችን አያልቅም! "የአድዋ ጦርነት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተዋግቷል" ይሉናል። የአድዋ ጦርነት የተካሔደው በ 1888 ድኅረ-ልደት ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕት የሆነው በዱዲያኖስ ዘመነ-መንግሥት በ 393 ድኅረ-ልደት ልዳ በሚባለው አገር ነው። የዛሬ 1,627 ዓመት ልዳ ላይ ሰማዕት የሆነው ሰው አድዋ ላይ በ 1888 ኅረ-ልደት ላይ እንዴት ሊዋጋ ቻለ? መረጃችሁስ ምንድን ነው? "አሞኛችሁ ዘንድ አይናችሁን ጨፍኑ!" አትበሉን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
መስካሪ እና ተመስካሪ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

85፥3 *"በመስካሪ እና በተመስካሪ እምላለሁ"*፡፡ وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ

በቁርኣን አናቅጽ ላይ "ሻሂድ" شَاهِد ማለት የሚመሰክር "መስካሪ" ማለት ሲሆን "መሽሁድ" مَشْهُود ማለት ደግሞ የሚመሰከርበት "ተመስካሪ" ማለት ነው። በተቀጠረው ቀን መስካሪ በተመስካሪ ላይ ይመሰክራሉ፦
85፥2 *"በተቀጠረው ቀንም እምላለው"*። وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ
85፥3 *"በመስካሪ እና በተመስካሪ እምላለሁ"*፡፡ وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ

ኢንግሊሹ ከዐረቢኛው ጋር በተመሳሳይ "And by the witness and the witnessed" ይላል። አምላካችን አሏህ በቁርኣን የማለባቸው ነገሮችን ሁሉ ጉዳዩን አጽንዖትና አንክሮት መስጠቱን የሚያመላክት ነው፥ ያ የተቀጠረው ቀን ደግሞ ሙታን የሚቀሰቀሱበት የትንሳኤ ቀን ነው፦
34፥30 *«ለእናንተ ከእርሱ አንዲትንም ሰዓት የማትዘገዩበት የማትቀድሙበትም "የቀጠሮ ቀን" አላችሁ»* በላቸው፡፡ قُل لَّكُم مِّيعَادُ يَوْمٍ لَّا تَسْتَأْخِرُونَ عَنْهُ سَاعَةً وَلَا تَسْتَقْدِمُونَ
36፥52 *«ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? "ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን" እና መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው»* ይላሉ፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ
11፥103 በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ፡፡ *"ይህ የትንሣኤ ቀን ሰዎች በእርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው፡፡ ይህም የሚጣዱት ቀን ነው"*፡፡ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّمَنْ خَافَ عَذَابَ الْآخِرَةِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّجْمُوعٌ لَّهُ النَّاسُ وَذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّشْهُودٌ

የተቀጠረው ቀን የመሽሁድ ቀን ነው። አሏህ፦ "በመስካሪው እና በሚመሰከርባቸው እምላለው" ብሏል፥ "መስካሪ" የተባሉት "ነቢያት" ሲሆኑ "የሚመሰከርባቸው" ደግሞ "ኡማቸው" ናቸው፦
16፥84 *"ከየሕዝቡም ሁሉ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን ቀን አስታውስ"*፡፡ وَيَوْمَ نَبْعَثُ مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا
4፥41 *"ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን ባመጣን ጊዜ አንተንም በእነዚህ ሕዝብ ላይ መስካሪ አድርገን በምናመጣህ ጊዜ የከሓዲዎች ኹኔታ እንዴት ይኾን?"* فَكَيْفَ إِذَا جِئْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ بِشَهِيدٍ وَجِئْنَا بِكَ عَلَىٰ هَـٰؤُلَاءِ شَهِيدًا
16፥89 *"በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ ከራሳቸው በእነርሱ ላይ መስካሪን የምንቀሰቅስበትን አንተንም በእነዚህ ሕዝብ ላይ መስካሪ አድርገን የምናመጣህን ቀን አስታውስ"*፡፡ وَيَوْمَ نَبْعَثُ فِي كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا عَلَيْهِم مِّنْ أَنفُسِهِمْ ۖ وَجِئْنَا بِكَ شَهِيدًا عَلَىٰ هَـٰؤُلَاء
28፥75 *"ከሕዝቦችም ሁሉ መስካሪን እናወጣለን፡፡ ያን ጊዜ እውነተኛውም አምላክነት ለአላህ ብቻ መኾኑን ያውቃሉ፡፡ ይቀጣጥፉት የነበሩትም ከእነርሱ ይጠፋቸዋል"*፡፡ وَنَزَعْنَا مِن كُلِّ أُمَّةٍ شَهِيدًا فَقُلْنَا هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ فَعَلِمُوا أَنَّ الْحَقَّ لِلَّهِ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَرُونَ

“ኡማህ” أُمَّة ማለት “ሕዝብ” ማለት ሲሆን በአንድ ነቢይ ዘመነ-መግቦት"dispensation" የሚቆዩትን "ሰዎች" ያመለክታል። እያንዳንዱ ነቢይ በራሱ ኡማህ ላይ በትንሳኤ ቀን ይመሰክራሉ። ይህ ሙግት “የተዛማች ሙግትን”textual approach” ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ሙግት ነው።

ነገር ግን "ተጣጅ" እና "ሚጣዱት" የሚለው እንደ ኢትዮጵያ ክርስትና አቆጣጠር በ 1961 ዓመተ-ልደት በተዘጋጀው የሐጅ ሣኒ ሐቢብ የዐማርኛ የቁርኣን ትርጉም ላይ ተቀምጧል። አንዳንዶች፦ "የወሎ አማርኛ ነው" ቢሉም ምን ለማስተላለፍ እንደፈለጉ እኔ በቅጡ አልገባኝም፥ አሏሁ አዕለም ሁሉን። ነገር ግን የኢንግሊሹ የቁርኣን ትርጉም እና እራሱ ኦርጅናሉ ቁርኣን "ሻሂድ" شَاهِد "መስካሪ" "the witness" እና "መሽሁድ" مَشْهُود "ተመስካሪ" "the witnessed" ብሎ ጥልልና ጥንፍፍ አርጎ አስቀምጦታል። የአገራችን ሚሽነሪዎች ጭረው ተፍጨርጭረው ስለ ድስት መጣድ ለማስመሰል ቢዳዱም ከላይ ባለው የቋንቋ ሙግት”linguistical approach” ድባቅ ይገባሉ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዐድዋ በዓል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

ዐድዋ የሚባል በዓል በኢሥላም ውስጥ የለም። ሙሥሊም ያሉት ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *”አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው”*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚህ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”በሁለቱ በዓል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና ሐዲስ ብቻ መከተል አለብን፦
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ ማለት ከአላህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው። ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ብቻ ዒድ ያከብራል። ከዚህ ውጪ በዓል እያሉ ማክበር ቢድዓህ ነው፥ “ቢድዓህ” بِدْعَة ደግሞ “በደዐ” بَدَّعَ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው። ቢድዓህ የኢትባዕ ተቃራኒ ነው። “ቢድዓህ” ማለት አላህ ሳያዘን እና ሳይፈቅድልን ዝንባሌአችንን ተከትለን የምናደርገው አዲስ አምልኮ ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ያገኛል፤
ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል። حَدَّثَنِي كَثِيرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ جَدِّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ أَحْيَا سُنَّةً مِنْ سُنَّتِي قَدْ أُمِيتَتْ بَعْدِي فَإِنَّ لَهُ مِنَ الأَجْرِ مِثْلَ أَجْرِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِ النَّاسِ شَيْئًا وَمَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لاَ يَرْضَاهَا اللَّهُ وَرَسُولُهُ فَإِنَّ عَلَيْهِ مِثْلَ إِثْمِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ آثَامِ النَّاسِ شَيْئًا ‏”‏ ‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፤ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ .

ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፤ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ቢድዓህ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው “ሙብተዲዕ” مبتدئ ይባላል። አሏህ ከሙብተዲዕ ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሥነ-ፍጥረት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

“ሥነ-ፍጥረት”creatinology” ማለት ስለ ፍጥረት የሚያጠና የዕውቀት ዘርፍ ነው፤ አምላካችን አላህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፤ “ሸይዕ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ማለት ሲሆን ሁሉንም ነገራት ሁሉ ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
6፥102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው*፤ ስለዚህ ተገዙት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
13፥16 *አላህ ሁሉንም ነገር ፈጣሪ ነው*፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው፤ በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
40፥62 ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ *የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُون

ነጥብ አንድ
“ፍጥረት”
አላህ የፈጠራቸው ፍጥረታት ህልቆ-መሳፍርት ናቸው፤ ከአጽናፍ እስከ አድማስ ያሉትን ትልቅ እና ደቂቅ ፍጥረታት ቢዘረዘሩ አያልቁም፤ እነዚህን ፍጥረታት አላህ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው፦
50፥38 ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ
25፥59 ያ ሰማያትና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዐርሹ ላይ የተደላደለ አልረሕማን ነው፡፡ ከእርሱም ዐዋቂን ጠይቅ፡፡ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۚ الرَّحْمَـٰنُ فَاسْأَلْ بِهِ خَبِيرًا

ይህ ጥቅላዊ ገለጻ ሲሆን በተናጥል አስፈላጊ የሆነው አፈጠጠሩ እንዲህ ይገልጻል፦
41፥9 በላቸው «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀኖች ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው፡፡ قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَرْضَ فِى يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادًۭا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

ከመጀመሪያው ቀን እስከ አራተኛው ቀናት ባሉት በአራት ቀናት ውስጥ በምድር ላይ የረጉ ጋራዎችን፣ በውስጧም ምግቦችዋን ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፦
42፥10 በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፡፡ በእርሷም በረከትን አደረገ፡፡ በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፡፡ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ مِن فَوْقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقْوَٰتَهَا فِىٓ أَرْبَعَةِ أَيَّامٍۢ سَوَآءًۭ لِّلسَّآئِلِينَ

“ጭስ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዱኻን” دُخَانٌۭ ሲሆን “ጋዝ” ማለት ነው፤ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አላህ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፦
42፥11 ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ

“ሱመ” ثُمَّ ማለት አያያዥ መስተጻምር ሲሆን “ከዚያም” ወይም “እንዲሁ” ማለት ነው፤ አያያዥነቱ “ተርቲቢያህ” ማለትም “ቅድመ-ተከተል” ነው፤ ይህም ቅድመ-ተከተል በሁለት ይከፈላል፦ አንዱ “ተርቲበቱል ከላም” ማለት “የንግግር ቅድመ-ተከተል” ሲሆን ሁለተኛው “ተርቲበቱል ዘመን” ማለት የጊዜ ቅድመ-ተከተል ናቸው፣ እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ዓውዱ የንግግር ቅድመ-ተከተል ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ አላህ ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፤ ጭስ የነበረችውን ሰማይ በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፡፡ فَقَضَىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَاتٍۢ فِى يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ *ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ
ነጥብ ሁለት
“ማስተንተን”
በሰማያትና በምድር ያሉትን ከአጽናፍ እስከ አድማስ ያሉትን ትልቅ እና ደቂቅ ህልቆ-መሳፍርት ፍጥረታት እኛ ቀስ በቀስ በማስተንተን ማወቅ እንችላለን፤ በአላህ አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም፤ ዓይንህንም ወደ ፍጥረታት እይ ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን? በፍጹም አታይም፦
3፥191 እነርሱም እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ *በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ*፡- «ጌታችን ሆይ! *ይህን በከንቱ አልፈጠርከውም*፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَـٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ
67፥3 ያ ሰባትን ሰማያት የተነባበሩ ኾነው የፈጠረ ነው፡፡ *በአልረሕማን አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም*፡፡ ዓይንህንም መልስ፡፡ «ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?» الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ طِبَاقًا ۖ مَّا تَرَىٰ فِي خَلْقِ الرَّحْمَـٰنِ مِن تَفَاوُتٍ ۖ فَارْجِعِ الْبَصَرَ هَلْ تَرَىٰ مِن فُطُورٍ

ለእኛም በሰማያት ያለውን እና በምድርም ያለውን ሁሉ በሙሉ ከአላህ ሲኾን የገራልን ነው፤ በዚህ አፈጣጥር ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ተዓምራት አልለበት፦
45፥13 ለእናንተም በሰማያት ያለውን እና በምድርም ያለውን ሁሉ በሙሉ ከእርሱ ሲኾን የገራላችሁ ነው፡፡ በዚህ *ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች* ተዓምራት አልለበት፡፡ وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ በዚህም ውስጥ *ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች* ምልክቶች አሉ፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

ሰማያትና ምድር ከጌታችንም ጸጋዎች ናቸው፦
55፥7 *ሰማይንም አጓናት*፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡ وَٱلسَّمَآءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ ٱلْمِيزَانَ
55፥10 *ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት*፡፡ وَٱلْأَرْضَ وَضَعَهَا لِلْأَنَامِ
55፥13 *ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?* فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለእኛ ያገራልን ግልጽም ድብቅም ሲኾኑ የሞላላልን ጸጋዎቹንም ናቸው፦
31፥20 አላህ *በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ ጸጋዎቹንም ግልጽም ድብቅም ሲኾኑ የሞላላችሁ መኾኑን አታዩምን?* أَلَمْ تَرَوْا أَنَّ اللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَأَسْبَغَ عَلَيْكُمْ نِعَمَهُ ظَاهِرَةً وَبَاطِنَةً ۗ

ሰማያትና ምድር፣ በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ እኛ የደረስንበት ግልጽም ያልደረስንበት ድብቅም ለእኛ ያገራልን የአላህንም ጸጋ ናቸው፤ የአላህንም ጸጋ ብትቆጥረው አንዘልቀውም፦
16፥18 *የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም*፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ