ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
"ጠንቋይ" ለሚለው የገባው ቃል "መጉን" μάγον መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል።የመጉሥ ብዙ ቁጥር ደግሞ "መጎኢ" μάγοι ሲሆን መጎኢ የተወለደውን ኢየሱስን ለመጎብኘት ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ካለችው ከፋርሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተዋል፦
ማቴዎስ 2፥1 *"ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ"*። Τοῦ δὲ Ἰησοῦ γεννηθέντος ἐν Βηθλέεμ τῆς Ἰουδαίας ἐν ἡμέραις Ἡρῴδου τοῦ βασιλέως, ἰδοὺ μάγοι ἀπὸ ἀνατολῶν παρεγένοντο εἰς Ἱεροσόλυμα

አለቃ ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ሳምኬት ገፅ 661 እና ሳን ገፅ 848 ላይ "ሠገል" ማለት "ጠንቋይ" ማለት እንደሆነ እና "ሠገል" የሚለው ቃል "ሠገለ" አስጠነቆለ" ከሚል የመጣ ሲሆን "ጥንቆላ" ማለት እንደሆነም አስቀምጠዋል።
ጥንቆላ፣ አስማት እና ኮከብ ቆጠራ መላእክት ከሰማይ ይዘውት የመጡት እንደሆነ መጽሐፈ ሆኖክ 2፥11-23 ይናገራል፥ ዘይገርም!
"ሰብእ" ማለት ደግሞ "ሰው" ማለት ሲሆን በጥቅሉ "ሰብአ ሰገል" ማለት "የጥንቆላ ሰው" ወይም "ጠንቋይ ሰው" ማለት ነው። ስንክሳር ዘወርኅ ታኅሣሥ 29 ቁጥር 4-5 ላይ፦
*"ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ እነሆ የፍልስፍና ሰዎች ከምሥራቅ መጥተው ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ፥ "ኮከቡን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና፥ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? እያሉ። እነዚህ ፈላስፎች ከበለዓም ወገን ናቸው፥ እነርሱም በከዋክብት የሚፈላሰፉ ናቸው"*።

ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ጻድቃን ሳይሆኑ በከዋክብት የሚፈላሰፉ ጠንቋዮች ናቸው። የማቴዎስ ወንጌል 2፥2 አንድምታው እንዲህ ይላል፦
*"ስለምን በኮከብ መራቸው ቢሉ በለመዱት ለመሳብ ኮከብ ያመልኩ ነበርና"*።

በግሪኩ "መጎኢ" μάγοι ማለትም "ጠንቋዮች" "አስማተኞች" "ኮከብ ቆጣሪዎች" ማለት ነው፥ በኮከብ እየተመሩ መምጣታቸው ይህ ማሳያ ነው። እጅ መንሻ ይዘው ከሰገዱ በኃላ ወደ አገራቸው ወደ ምስራቅ ሄዱ፦
ማቴዎስ 2፥12 *"ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ"*።

የእነዚህ ሰዎች የቁጥራቸው መጠን "ሦስት ነው" የሚል እና "ሦስት ነገሥታት ጋስፓር፣ ሜልክዮር እና ባልታዛር ናቸው" የሚል ሽታው ባይብል ላይ የለም፥ በተለምዶ ኢየሱስ ሲወለድ እጅ መንሻ ሰተዋል የሚባለው ውሸት ነው፦
ማቴዎስ 2፥11 *"ወደ ቤት ሲገቡም ልጁን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት"*።

የገቡት "ቤት" ውስጥ እንጂ "ግርግም" ጋር አይደለም፥ ግርግም በረት ውስጥ ወይም ሜዳ ላይ ያለ የእንስሳት መመገቢያ አሸንዳ ነው። ሳባ(የመን) ሆነ ኩሽ(ኢትዮጵያ) የሚገኙት ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ሳይሆን በስተ ደቡብ ነው፦
ማቴዎስ 12፥42 *"ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች"*።

"ዓዜብ" ማለት "ደቡብ" ማለት እንደሆነ ባይብልን በሥነ-አፈታት ጥናት ላጠና ሰው እንግዳ አይደለም። ለሰሎሞን የተነገረውን እጅ መንሻ ለኢየሱስ በማድረግ መጁሦችን ኢትዮጵያውያን ናቸው ማለት ስሑት ሥነ-አመክንዮ ነው፦
መዝሙር 72፥9-11 *"በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ። የተርሴስ እና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብ እና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ። ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል"*።

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢትዮጵያ" ብለው ሆን ብለው ለማደናበር ያስቀመጡት ቃል "ሲዪም" צִיִּ֑ים ሲሆን "የምድረበዳ ሕዝቦች" ማለት ነው፥ ኢትዮጵያ ቢባል እንኳን "ይሰግዳሉ" አለ እንጂ "እጅ መንሻን ያቀርባሉ" አይልም። "ኢትዮጵያ እጅ መንሻን ያቀርባሉ" ቢል እንኳን ዐውዱ እየተናገረ ያለው ለንጉሥ ሰሎሞን እንጂ ለኢየሱስ በፍጹም አይደለም፥ የሳባ ንግሥትን እጅ መንሻ ለንጉሥ ሰሎሞን አምጥታለች፦ 1ኛ ነገሥት 10፥1-1-2 ይመልከቱ!

ሲቀጥል ከባቢሎን ምርኮ በኃላ ለመቅደሱ መልሶ ግንባታ ግብፅ፣ ኩሽ እና ሳባ ወርቅንና ዕጣን አምጥተው ለእስራኤል እንደሚሰግዱ የሚያሳይ እንጂ ስለ ኢየሱስ ሽታው የለውም፦
ኢሳይያስ 60፥6 *"የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ"*።
ኢሳይያስ 45፥14 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ የግብፅ ድካም እና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም፡ ብለው ይለምኑሃል"*።

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢትዮጵያ" የሚለው ዕብራይስጡን ብትመለከት የሚለው “ኩሽ” כּ֥וּשׁ ነው። “ኢትዮጵያ” ብለው በዐማርኛ የተረጎሙት በዕብራይስጡ “ኩሽ” כּ֥וּשׁ መሆኑን አስምርበት! ስለዚህ ሰብአ ሰገል ፋርሣውያን እንጂ ኩሻውያን ወይም ሳባውያን በፍጹም አይደሉም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እንቅልፍ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

39፥42 *"አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል"*፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

እንቅልፍ ሰውነታችን በሽታ የመከላከል ዐቅሙን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል፣ የበላነውን ምግብ ከሰውነታችን ጋር በቀላሉ ውሕደት ይፈጥራል፣ አካላችን እረፍት በማግኘት ኃይልን ያሰባስባል፣ የአእምሮ የማስታወስ ብቃትን ያጎለብታል። ቅሉ ግን በኢሥላም እንቅልፍ ከዚህም ባሻገር ዘርፈ-ብዙ እና መጠነ-ሰፊ አንድምታ አለው፥ እረ እንቅልፍ እንደውም ከሕልም፣ ከሩሕ፣ ከሞት ጋር ጥብቅ ተዛምዶ አለው። አምላካችን አሏህ ሰውን ሲያሞት የሞት መልአክ ልኮ ሩሓችንን ይወስዳል፦
32፥11 *"«በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት ”ይወስዳችኃል”፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው"*፡፡ قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ

"ይወስዳችኃል" ለሚለው የገባው ቃል "የተወፋኩም" يَتَوَفَّىٰكُم ነው። "ነፍሥ" نَفْس ማለት እራሱ "ማንነት" ሲሆን የነፍሥ ብዙ ቁጥር "አንፉሥ" أَنْفُس ነው፥ የሰው ማንነት ደግሞ ወደ አፈር የሚሄድ ሟች አካል እና ወደ አሏህ የሚሄድ ሩሕ ነው። አሏህ ሩሕን በሞት ጊዜ ይወስዳል፦
39፥42 *"አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል፥ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል"*፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

"ሞታቸው" ሲል ነፍሥ በአካል ሟች መሆኗን ሲያሳይ "ይወስዳል" ሲል ደግሞ ነፍስን በሩሕዋ ተወሳጅ መሆኗን ነው። "ሩሕ" رُّوح ማለት “መንፈስ” ማለት ሲሆን አሏህ ሩሓችንን በእንቅልፍ ጊዜ ወስዶ በንቃት ጊዜ ይመልሳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 97
አቡ ቀታዳህ እንደተረከው፦ "ከሶላት ሰዎች በተኙ ጊዜ የአሏህ ነቢይም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አሏህ በሚሻው ጊዜ ሩሓችሁን ይወስዳል፥ በሚሻው ጊዜ ይመልሳል"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي قَتَادَةَ، عَنْ أَبِيهِ، حِينَ نَامُوا عَنِ الصَّلاَةِ، قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ قَبَضَ أَرْوَاحَكُمْ حِينَ شَاءَ، وَرَدَّهَا حِينَ شَاءَ ‏"‌‏

"አርዋሕ" أَرْوَاح ማለት "መንፈሶች" ማለት ሲሆን "ሩሕ" رُّوح ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አሏህ ነፍሥን በእንቅልፏ ጊዜ ሲወስዳት ያለ ዓይን ታያለች፣ ያለ ጆሮ ትሰማለች፣ ያለ እግር ትሄዳለች፣ ያለ አፍ ትናገራለች፥ የሕልም ዓለም ሩሕ ከአካል ከተለየች በኃላ ያለውን ሕይወት ማሳያ ናሙና ነው። አምላካችን አሏህ በሌሊት ይወስደናል፥ ከዚያም በቀን ይቀሰቅሰናል፦
6፥60 *"እርሱም ያ በሌሊት የሚወስዷችሁ በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው"*፡፡ وَهُوَ الَّذِي يَتَوَفَّاكُم بِاللَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِالنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰ أَجَلٌ مُّسَمًّى

"የሚወስዷችሁ" ለሚለው የገባው ቃል "የተወፋኩም" يَتَوَفَّاكُم ነው፥ በቁርኣን ውስጥ "እንቅልፍ" ለሚለው የገባው የስም መደብ "ነውም" نَوْم "ኑዓሥ" نُّعَاس "ሩቁድ" رُقُود ነው። አሏህ ሩሕን በሌሊት እንቅልፍ ጊዜ ወስዶ አካላችንን ያሳርፋል፦
78፥9 *"እንቅልፋችሁንም ዕረፍት አደረግን"*፡፡ وَجَعَلْنَا نَوْمَكُمْ سُبَاتًا
10፥67 እርሱ ያ *"ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት፥ ቀንን ልትሠሩበት ብርሃን ያደረገላችሁ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ተአምራት አሉ"*፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ اللَّيْلَ لِتَسْكُنُوا فِيهِ وَالنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَسْمَعُونَ
አምላካችን አሏህ በቀን ደግሞ ይቀሰቅሰናል፥ "በቀን ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው" የሚለው ይሰመርበት። ሰው አካሉ በሌሊት እንቅልፍ እንደሚያርፍ እና በቀን እንደሚቀሰቀስ ሁሉ በሞትን ጊዜ አካሉ በትልቁ እንቅልፍ ያርፍ እና በትንሳኤ ቀን ይቀሰቀሳል፦
36፥51 *"በቀንዱም ይነፋል፥ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ"*፡፡ وَنُفِخَ فِي الصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ الْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ
36፥52 *«ወይ ጥፋታችን! ከእንቅልፋችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ በእርሱ የቀጠረን እና መልክተኞቹ እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ*፡፡ قَالُوا يَا وَيْلَنَا مَن بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ الرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ الْمُرْسَلُونَ

እንቅልፍ ሩሕ እና አካል የሚለያዩበት ስለሆነ የሞት ወንድም ተብሏል፥ እንቅልፍ ትንሹ ሞት ስለሆነ ለዛ ነው የምሽት ዚክር ላይ "አሏህ ሆይ! በስምህ እሞታለው ሕያው እሆናለው" የንጋት ዚክር ላይ ደግሞ፦ "ለአሏህ ምስጋና ይሁን! ለዚያ ከአሞተን በኃላ ሕያው ላደረገን፥ መቀስቀስም ወደ እርሱ ነው" የምንለው፦
አል-ሙጀመል አውሠጥ ሐዲስ 938
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "የአሏህ ነቢይም"ﷺ" እንዲህ ተጠየቁ፦ *"የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! የጀናህ ባለቤቶች ይተኛሉን? የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "እንቅልፍ የሞት ወንድም ነውና የጀናህ ባለቤቶች አይተኙም"*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ سُئِلَ نَبِيُّ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ أَيَنَامُ أَهْلُ الْجَنَّةِ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ النَّوْمُ أَخُو الْمَوْتِ وَأَهْلُ الْجَنَّةِ لا يَنَامُونَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 23
ሑዘይፋህ እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ወደ አልጋቸው በሄዱ ጊዜ፦ "አሏህ ሆይ! በስምህ እሞታለው ሕያው እሆናለው" ይሉ ነበር፥ በነቁ ጊዜ፦ "ለአሏህ ምስጋና ይሁን! ለዚያ ከአሞተን በኃላ ሕያው ላደረገን፥ መቀስቀስም ወደ እርሱ ነው"*። عَنْ حُذَيْفَةَ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِذَا أَوَى إِلَى فِرَاشِهِ قَالَ ‏"‏ اللَّهُمَّ بِاسْمِكَ أَحْيَا وَأَمُوتُ ‏"‌‏.‏ وَإِذَا أَصْبَحَ قَالَ ‏"‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَحْيَانَا بَعْدَ مَا أَمَاتَنَا وَإِلَيْهِ النُّشُورُ ‏"‌‏

እውነት ነው! በእንቅልፍ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ተአምራት አሉበት። አሏህ ከሚሰሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሲና ምሥጢር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

95፥2 *"በሢኒን ተራራም እምላለሁ"*፡፡ وَطُورِ سِينِينَ

"ጀበል" جَبَل ማለት "ተራራ" ማለት ሲሆን የጀበል ተመሳሳይ ቃል ደግሞ "ጡር" طُّور ሲሆን ለየት ያለ የሲና ተራራ ነው፥ በዚህ ተራራ ላይ አምላካችን አሏህ ተውራትን ለበኒ ኢሥራዒል፦ "ያንን የሰጠናችሁን በኀይል ያዙ" በማለት ሰጥቷቸዋል፦
2፥63 *ከበላያችሁም ጡርን ያነሳን ኾነን የጠበቀ ቃልኪዳናችሁን በያዝን ጊዜ የኾነውን አስታውሱ! «ያንን የሰጠናችሁን በኀይል ያዙ! በውስጡ ያለውንም ነገር ትጠነቀቁ ዘንድ አስታውሱ!» አልን*፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِيثَاقَكُمْ وَرَفَعْنَا فَوْقَكُمُ الطُّورَ خُذُوا مَا آتَيْنَاكُم بِقُوَّةٍ وَاذْكُرُوا مَا فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

ሙሣ አሏህን ለማግኘት እና ለማነጋገር የተቀጠረው በዚህ ተራራ ላይ ነው፦
7፥143 *"ሙሣም ለቀጠሯችን በመጣ እና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! እራስህን አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ አላህም፡- «በፍጹም አታየኝም። ግን ወደ ተራራው ተመልከት! በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፥ ሙሳም ጮሆ ወደቀ፡፡ በአንሰራራም ጊዜ፦ «ጥራት ይገባህ! ወደ አንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም በወቅቱ የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ"*፡፡ وَلَمَّا جَاءَ مُوسَىٰ لِمِيقَاتِنَا وَكَلَّمَهُ رَبُّهُ قَالَ رَبِّ أَرِنِي أَنظُرْ إِلَيْكَ ۚ قَالَ لَن تَرَانِي وَلَـٰكِنِ انظُرْ إِلَى الْجَبَلِ فَإِنِ اسْتَقَرَّ مَكَانَهُ فَسَوْفَ تَرَانِي ۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ

"ሠይናእ" سَيْنَآء ማለት "ሲና" ማለት ሲሆን የተራራው ስም ነው፥ የዚህ ተራራ ገላጭ ቅጽል ደግሞ "ሢኒን" سِينِين ነው። አምላካችን አሏህ በዚህ ሲናዊ ተራራ ምሏል፦
95፥2 *"በሢኒን ተራራም እምላለሁ"*፡፡ وَطُورِ سِينِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተራራ" ለሚለው የገባው ቃል "ጡር" طُور መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ከዚህ ከሠናይእ ተራራ ቅባት እና ዘይት ተቀላቅላ የምትበቅል ዛፍ ትወጣለች፦
23፥20 *"ከሲና ተራራም የምትወጣን ዛፍ በቅባት እና ለበይዎችም መባያ በሚኾን ዘይት ተቀላቅላ የምትበቅልን አስገኘንላችሁ"*፡፡ وَشَجَرَةً تَخْرُجُ مِن طُورِ سَيْنَاءَ تَنبُتُ بِالدُّهْنِ وَصِبْغٍ لِّلْآكِلِينَ

ይህቺ ከሲና ተራራ የምትወጣ ዛፍ የተባረከች ዛፍ ስትሆን ዘይቷ ለመብራትነት ይሆናል፥ አሏህ ይህቺን እማራዊ ዛፍ ለፍካሬአዊ ብርሃን ምሳሌ አድርጓታል፦
24፥35 አላህ የሰማያትና የምድር አብሪ ነው፡፡ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጧ መብራት እንዳለባት ዝግ መስኮት፣ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የኾነ፣ ብርጭቆይቱ ፍፁም ሉላዊ ኮከብ የምትመሰል፣ ምሥራቃዊው ምዕራባዊም ካልኾነች *"ከተባረከች የወይራ ዛፍ"* ዘይቷ እሳት ባይነካውም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከኾነች ዘይት የሚቃጠል እንደ ሆነ መብራት ነው፡፡ اللَّهُ نُورُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ مَثَلُ نُورِهِ كَمِشْكَاةٍ فِيهَا مِصْبَاحٌ ۖ الْمِصْبَاحُ فِي زُجَاجَةٍ ۖ الزُّجَاجَةُ كَأَنَّهَا كَوْكَبٌ دُرِّيٌّ يُوقَدُ مِن شَجَرَةٍ مُّبَارَكَةٍ زَيْتُونَةٍ لَّا شَرْقِيَّةٍ وَلَا غَرْبِيَّةٍ يَكَادُ زَيْتُهَا يُضِيءُ وَلَوْ لَمْ تَمْسَسْهُ نَارٌ

ተወዳጁ ነቢያችንም"ﷺ" ከዚህ ከተባረከ ዛፍ የሚወጣውን ዘይት ለመብል እና ለፈውስ አገልግሎት እንድንጠቀምበት ነግረውናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 69
አቢ አሢድ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ዘይትን ብሉ! በእርሱ ተቀቡ! እርሱም ከተባረከ ዛፍ ነው"*። عَنْ أَبِي أَسِيدٍ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ كُلُوا الزَّيْتَ وَادَّهِنُوا بِهِ فَإِنَّهُ مِنْ شَجَرَةٍ مُبَارَكَةٍ ‏"‏ ‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 29, ሐዲስ 69
ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በዘይት ፈውሱ! በእርሱ ተቀቡ! እርሱም ከተባረከ ዛፍ ነው"*። عَنْ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ اِئْتَدِمُوا بِالزَّيْتِ وَادَّهِنُوا بِهِ فَإِنَّهُ مِنْ شَجَرَةٍ مُبَارَكَةٍ ‏"‏

በሥነ-ቁፋሮ ጥናት ይህ የሲና ተራራ የተገኘው የዐረብ አገር ውስጥ ነው፥ ይህንን ሊንክ አስፈንጥረው ይመልከቱ፦ https://youtu.be/-mB5Aw14e4M

በተጨማሪ ባይብል ላይ ይህ የሲና ተራራ በዓረብ ምድር እንደምትገኝ ይናገራል፦
ገላትያ 4፥25 *"ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት"*።

"በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! "ደብር" የግዕዝ ቃል ሲሆን "ተራራ" ማለት ነው፥ "አድባር" የደብር ብዙ ቁጥር ሲሆን "ተራሮች" ማለት ነው። "ደብረ ሲና" ማለት "የሲና ተራራ" ማለት ነው፥ የነቢያት አምላክ የእስራኤል ብቻ ሳይሆን የሲናም አምላክ እንደሆነ ይናገራል፦
መዝሙር 68፥8 ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት ሰማያትም አንጠበጠቡ። the earth quaked, yea, the heavens dropped water at the presence of the God of Sina, at the presence of the God of Israel.

የሙሴ አምላክ ለምን ይሆን ከነዓን ሲገቡ ተውራትን መስጠት ሲችል ዐረብ አገር ውስጥ ባለችው በሲና ተራራ ላይ ተውራትን የሰጠው? ሲቀጥል ከሲና ተጉዘው ከነዓን ከገቡ በኃላ ዳዊት ለምን በሲናህ መቅደስ እንዳለው እና በመቅደሱ በሲናህ በመላእክት መካከል እንዳለ ተናገረ? የአምላክ ሰረገሎት መላእክት ሲሆኑ በሲና ባለው መቅደሱ ውስጥ አሉ፥ አዶይም በመካከላቸው ነው፦
መዝሙር 68፥17 *"የኤሎሂም ሰረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው፥ አዶናይ በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው"*።

"ቁደሽ" קֹדֶשׁ የተባለው ፈጣሪ ሙሴን ያናገረበት ቦታ የሲና ተራራ ነው። ታዲያ ሲና ያለበት አገር ውስጥ አምላካችን አሏህ ነቢያችንን"ﷺ" ነቢይ አድርጎ ማስነሳቱ ዝም ብሎ ይመስላችኃል? ይህንን ሁነኛና ክፉኛ ሙግት ስትሰሙ "ሰርግና ምላሽ፥ ሰኔና ሰኞ ሆነብን" ከማለት ይልቅ የቆላው ሐሩር የደጋው ቁር ሳይበግራችሁ ቆፍጠን ብላችሁ ይህንን የኢሥላምን ብርሃን ለማየት ሞክሩ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ታቦት እና ጽላት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥145 *ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት*፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ

“ጽሌ” ማለት “ሰሌዳ” “ፊደል” ማለት ነው፤ የጽሌ ብዙ ቁጥር “ጽላት” ሲሆን “ሰሌዳዎች” ወይም “ፊደሎች” ማለት ነው፤ በዕብራይስጥ ደግሞ “ላሁት” לֻחֹ֣ת ሲሆን በዐረቢኛ “ለውሕ” لَوْح ነው፣ አምላካችን አላህ ለሙሳ ቃላትን በፊደል ላይ ጽፎ እንደሰጠው በተከበረ ቃሉ ይናገራል፦
7፥145 *ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት*፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ
7፥154 *ከሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን በግልባጫቸው ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚፈሩ ለኾኑት መምሪያና እዝነት ያለባቸው ሲኾኑ ያዘ*፡፡ وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى الْغَضَبُ أَخَذَ الْأَلْوَاحَ ۖ وَفِي نُسْخَتِهَا هُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ هُمْ لِرَبِّهِمْ يَرْهَبُونَ

ይህን ድርጊት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተመዝግቧል፦
ዘጸአት 24፥12 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን፤ *እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው*።

“ታቦት” ማለት “ማህደር” “ሰገባ” “ሳጥን” “ማደሪያ” ማለት ነው፣ በዕብራይስጥ ደግሞ “አሮውን” אֲר֖וֹן ሲሆን በዐረቢኛ “አት-ታቡት” التَّابُوتُ ነው፣ አምላካችን አላህ ስለ ታቡት እንዲህ ይለናል፦
2፥248 ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- *«የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሳ ቤተሰብና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ “ሳጥኑ” ሊመጣላችሁ ነው*፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አልለ» አላቸው፡፡ وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ آيَةَ مُلْكِهِ أَن يَأْتِيَكُمُ التَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ آلُ مُوسَىٰ وَآلُ هَارُونَ تَحْمِلُهُ الْمَلَائِكَةُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

“ሳጥኑ” ለሚለው ቃል የገባው “አት-ታቡት” التَّابُوتُ ነው፤ ይህ ቃል የሙሳ እናት ለጣለችው ሳጥን አገልግሎት ላይ ውሏል፦
20፥39 *«ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ ጣይው*፡፡ እርሱንም ሳጥኑን በባሕር ላይ ጣይው፡፡ ባሕሩም በዳርቻው ይጣለው፡፡ ለእኔ ጠላት ለእርሱም ጠላት የኾነ ሰው ይይዘዋልና በማለት ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ፡፡ أَنِ اقْذِفِيهِ فِي التَّابُوتِ فَاقْذِفِيهِ فِي الْيَمِّ فَلْيُلْقِهِ الْيَمُّ بِالسَّاحِلِ يَأْخُذْهُ عَدُوٌّ لِّي وَعَدُوٌّ لَّهُ ۚ وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مِّنِّي وَلِتُصْنَعَ عَلَىٰ عَيْنِي

ይህንን እንዲህ በእንዲህ ካየን ዘንዳ ታቦት የጽላቱ ማህደር ወይም ሰገባ ሲሆን ይህን ድርጊት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተመዝግቧል፦
ዘጸአት 25፥10 *ከግራር እንጨትም “ታቦትን” ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን*።
ዘዳግም 10፥5 *ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ “ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው” እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ*።

ይህ እንዲህ ከሆነ ይህ ጽላት እና ታቦት የት ገባ? በተለይ የአገራችን ሰዎች እንደሚተርኩልን ይህን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ አቢሲኒያ በዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን በሰለሞን ዘመነ-መንግሥት እንደገባ ይነገራል፣ ነገር ግን በዓለማችን ታሪክ ላይ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደጠፋና ከዚያ በፊት ኢየሩሳሌም ውስጥ እንደነበረ ተዘግቧል፤ በተጨማሪ የእዝራ ሱቱኤል ጸሐፊ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደተማረከና እንደጠፋ ይዘግባል፦
ዕዝራ ሱቱኤል 9፥21-23 *”ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይም? ግናይቱ እንደጠፍች ምስጋና እንደቀረ ዘውዳችን እንደወደቀ ተድላ ደስታችን እንደጠፍ የህጋች ማደሪያ *ታቦተ ፅዮን እንደተማረከች ንዋየ ቅዱሳት አንዳደፉ ምልኮታችን እንደቀረ። ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ፅዮን እንደጠፍች ቀረች*፤ ከእሷም ንዋየ ቅድሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎን እጅ ወደቅን”*።
2ኛ ዕዝራ 1፥54-56 *”እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበት ንዋይ ቅድሳቱን ጥቃቅኑንም እና ታላላቁንም ዕቃ ሁሉ የእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግሥት ዕቃ ቤትም ያለውን ሣጥኑን ሁሉ ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ። የእግዚአብሔር ማደሪያ ቤተ መቅደስንም አቃጠሉ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሯን አፈረሱ ግምቧን በእሣት አቃጠሉ። በውጭ ያለውን ያማረውንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፉ እግዚአብሔር በኤርምያስ አፍ የተናገረው ይደርስ ዘንድ።

እንደውም በተረፈ ኤርሚያስ ላይ የሚያገለግሉበትን ንዋየ-ቅዱሳት ሁሉ ጌታ እንዳዘዛቸው ለምድር ሰጧት ምድርም ያን ጊዜ ተቀብላ ዋጠችው ይለናል፦
ተረፈ ኤርሚያስ 3፥13 *”ባሮክ እና ኤርምያስም ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ የሚያገለግሉበትን ዕቃ ሁሉ ጌታ እንዳዘዛቸው ለምድር ሰጧት ምድርም ያን ጊዜ ተቀብላ ዋጠችው”*።

የአገራችን ታሪክ የተፋለሰ መሆኑን የምናውቀው ይህ ጥቅስ ታቦተ ጽዮን በባቢሎናውያን እንደጠፋች መናገሩ ነው። ከዚያም ባሻገር ከሰለሞን 400 ዓመት በኋላ በኢዮስያስ ዘመነ-መንግሥት ታቦቱ በኢየሩሳሌም መኖሩን በዜና መዋዕል ላይ ተዘግቧል፦
ዜና መዋዕል ካልዕ 35፥3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ *ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ *አኑሩት*፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤

ታቦተ ጽዮን አክሱም ላይ አለች የሚለው ትረካ ከክብረ ነገሥት ውጪ የታሪክ፣ የባይብል እና የሥነ-ቅርፅ መረጃ ሆነ ማስረጃ የለም። ታቦቱ እና ጽላቱ ቢኖሩም እንኳን በአዲስ ኪዳን ጥቅም የላቸውም። የአዲስ ኪዳን ታላቁ ጸሐፊ ጳውሎስ እንደሚነግረን ከሆነ ሙሴ ንዋየ-ቅዱሳቱን የሚሰራው የሚመጣውን ነገር እያየ እንደነበር ተዘግቧል፦
ዕብራውያን 8፥5 እነርሱም *ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና*።
ዘጸአት 25፥40 በተራራ ላይ *እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ*።
የሐዋርያት ሥራ 7፥44 *እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች*፤
ይህንን ጳውሎስ ታቦትና ጽላት “ጥላ”typology” እንደሆነ ይናገራል፤ ብሉይ ላይ የነበረው ኪዳን በአዲስ ኪዳን ተሽሯል፤ ይህም ኪዳን ጥላነቱ ታቦቱ የሰው አካል ሲሆን የሚጻፍበት ፊደል ደግሞ ለሰው ልብ ምሳሌ ሆኖ አዲሱ ኪዳን በልብ የሚጻፍ መሆኑኑን ይነግረናል፦
ኤርምያስ 31፥31 እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር *አዲስ ቃል ኪዳን* የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር *የምገባው ቃል ኪዳን ይህ* ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ *ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ*፥ *በልባቸውም እጽፈዋለሁ*፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ዕብራውያን 8፥10-13 ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ *ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ*፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል። .. *አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል*።

ብሉይ ማለት አሮጌ ማለት ነው። አሮጌ ያሰኘው አዲሱ ነው፣ አሮጌው ኪዳን ህጉ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈበት ኪዳን ሲሆን አዲሱ ደግሞ በልብ ጽላት ላይ የተጻፈበት ኪዳን ነው፣ በድንጋይ ላይ የተጻፈው ኪዳን አሮጌና ውራጅ እንደተባለ አስተውሉ፣ ከዚያም ባሻገር በአዲሱ ኪዳን አሮጌው ኪዳን ተሽሯል ይላል፦
2ኛ ቆሮ 3፥3 እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ *ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት* እንጂ *በድንጋይ ጽላት* ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።
2ኛ ቆሮ 3፥7 ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ *ተሻረው* ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ *ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት* በክብር ከሆነ፥ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም?
2ኛ ቆሮ 3፥13 *የዚያንም ይሻር* የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም።
2ኛ ቆሮ 3፥14 ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ፡፡ ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ *የተሻረ* ነውና።

ምን ትፈልጋለህ? በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸው ጽላት በልብ ጽላት ተሽሯል፣ ቤተመቅደሱም ሰው ሆኗል፦
1ኛ ቆሮ 3፥16-17 *የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ* የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም *የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ*።
1ኛ ቆሮ 6፥19-20 ወይስ *ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?*

አዲሱ ኪዳን ህጉ የተጻፈው በልብ ጽላት ላይ ከሆነ ቤተመቅደሱ የሰው አካል ከሆነ እግዚአብሔር ሰው በሰራው ቤተ መቅደስ አይኖርም ይለናል፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥24 ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም
የሐዋርያት ሥራ 7፥50 ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል *የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም*።
ኢሳይያስ 66፥1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ *የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?*
ኤርምያስ 3፥16 በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ *የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም* ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ *ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም*።

የሚገርመው የአገራችን ክርስቲያኖች ከብሉይ ኪዳን ስንጠቅስ “ተሽሯል” ይሉናል፣ የተሻረው ታቦቱትና ጽላቱ እንጂ ሕጉ አይደለም። ሕጉማ በልብ ተጽፏል ተብሏል። የአገራችን ክርስቲያኖች ሕጉ ተሽሯል ይሉና የተጻፈበት ድንጋይ ሆነ የሚቀመጥበት ታቦት አልተሻረም ብለው ድርቅ ይላሉ፣ እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ በግልጽ የድንጋይ ጽላት እንደተሻረና አምላክ ሰው በሰራው ቤተመቅደስ እንደማይኖር ተናግሯል፣ ነገር ግን ዛሬ ያሉት ያገራችን ሰዎች ዛርኒሽ በተቀባ እንጨት ቀርጸው ታቦት ነው ብለው ለታቦቱ ሲሰግዱ፣ ሲለማመኑ፣ ሲማጸኑ፣ ሲሳሉ፣ ዕጣን ሲያጨሱ ይታያል፣ ይህ በትንቢት ስለ እነርሱ የተነገረው እየተፈጸመ ነውና በተውበት ወደ አላህ ተመለሱና አንዱን አምላክ በብቸኝነት አምልኩ፦
ኢሳይያስ 44፥15-19 *ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፥ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፥ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል፥ ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል፤ ይሞቃልና፦ እሰይ ሞቅሁ፥ እሳቱን አይቻለሁ ይላል። የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል። አያውቁም፥ አያስቡም፤ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፥ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን ጨፍነዋል። በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሸወድ እስከ መቼ?

ኢየሱስ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ወደ እግዚአብሔር፦ "ነፍሴ ታውካለች ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚህ ሰዓት አድነኝ" ብሎ እርዳታ ጠይቆ ጸሎቱ ተሰምቶለታል፦
ዕብራውያን 5፥7 እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤
ዮሐንስ 12፥27 አሁን ነፍሴ ታውካለች ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ነገር ግን ስለዚህ ወደዚህ ሰዓት መጣሁ።

አንድ ማንነት ሆነ ምንነት እራሱን መርዳት ሳይችል ሌላውን ይረዳል ማለት ዘበት ነው፦
26፥93 ከአላህ ሌላ ሲኾኑ ይረዱዋችኋልን? ወይስ ለራሳቸው ይረዳሉን? مِن دُونِ اللَّهِ هَلْ يَنصُرُونَكُمْ أَوْ يَنتَصِرُونَ

እባካችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ወደ አሏህ በንስሓ ተመለሱ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ቀኖና

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

3፥71 *የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?* يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

“አህለል ኪታብ” أَهْلَ الْكِتَاب ማለት “የመጽሐፉ ሰዎች” “የመጽሐፉ ሕዝብ” “የመጽሐፉ ባለቤት”The People of the Book” ማለት ሲሆን እነዚህም ሕዝቦች አይሁዳውያን እና ክርስቲያኖች ናቸው፤ “ኪታብ” كِتَاب የተባለው ከአላህ የወረደው ወሕይ እና በእጆቻቸው ጽፈው ከአላህ ሳይሆን ከአላህ ነው ብለው ከአላህ ንግግር ጋር የቀላቀሉት የሰው ንግግር ነው፦
2፥79 *ለእነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለእነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለእነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው*፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

የመጽሐፉ ባለቤቶች ከአላህ የወረደውን ንግግር ከሰው ንግግር ቃል ቀላቅለውታል፤ ከዚያም ባሻገር ከአላህ የወረደውንን ንግግር ደብቀውታል፦
3፥71 *የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?* يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

እስቲ ይህንን ነጥብ በታሪካዊ ዳራ እንቃኝ፤ በዚህ ምህዋር እና ዐውድ ላይ “ቀኖና” ስንል የዶግማ ተቃራኒ የሆነውን የሚለወጠው ሕግ ወይም ሥርዓት ሳይሆን የቅዱሳን መጽሐፍትን “መለኪያ” ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው። “ቀኖና” የሚለው ቃል የአማርኛችን ቃል “ካኑን” κανών ከሚል ግሪክ ቃል የተገኘ ነው፤ ይህም ቃል “ካና” κάννα ማለት “አሰመረ” “ለካ” ከሚል የኮይኔ ግሪክ ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ልኬት” ማለት ነው። አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ እንዲሁ ክርስቲያኖች በ 397 ድህረ-ልደት”AD” በካርቴጅ ጉባኤ በመጨመርና በመቀነስ ቀኖና እያሉ ሲያስወጡና ሲያስገቡ ነበር፤ በተለይ የካርቴጅ ጉባኤ መጽሐፍቶችን በሁለት ከፍለው ብሉይ እና አዲስ ብለው አስቀምጠውታል፤ እስቲ ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“ብሉይ ኪዳን”
ብሉይ ኪዳን ላይ ስላሉት መጽሐፍት የተለያዩ አንጃዎች አንድ አቋም የላቸውም፤ እነርሱን በተናጥን እስቲ እንይ፦

A. “የፕሮቴስታንት ቀኖና”
ፕሮቴስታንት የሚቀበለው ሁሉም ጋር ተቀባይነት ያለው አቆጣጠር
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት 39 ናቸው፤ እነርሱም፦
1. ኦሪት ዘፍጥረት
2. ኦሪት ዘጸአት
3 ኦሪት ዘኁልቁ
4. ኦሪት ዘሌዋውያን
5. ኦሪት ዘዳግም
6. መጽሐፈ ኢያሱ
7. መጽሐፈ መሳፍንት
8. መጽሐፈ ሩት
9. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
10. መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
11. መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
12. መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
13. ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
14. ዜና መዋዕል ካልዕ
15. መጽሐፈ ዕዝራ
16. መጽሐፈ ነህምያ
17. መጽሐፈ አስቴር
18. መጽሐፈ ኢዮብ
19. መዝሙረ ዳዊት
20. መጽሐፈ ምሳሌ
21. መጽሐፈ መክብብ
22. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
23. ትንቢተ ኢሳይያስ
24. ትንቢተ ኤርምያስ
25. ሰቆቃው ኤርምያስ
26. ትንቢተ ሕዝቅኤል
27. ትንቢተ ዳንኤል
28. ትንቢተ ሆሴዕ
29. ትንቢተ አሞጽ
30. ትንቢተ ሚክያስ
31. ትንቢተ ኢዮኤል
32. ትንቢተ አብድዩ
33. ትንቢተ ዮናስ
34. ትንቢተ ናሆም
35. ትንቢተ ዕንባቆም
36. ትንቢተ ሶፎንያስ
37. ትንቢተ ሐጌ
38. ትንቢተ ዘካርያስ
39. ትንቢተ ሚልክያስ ናቸው።
B. “የአይሁዳውያን ቀኖና”
39 መጽሐፍት አይሁዳውያን እንደጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ 24 የቀኖና መጽሐፍት አርገዋቸዋል፤ አቆጣጠራቸው ግን ይለያል፦
1. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ እና መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ አንድ መጽሐፍ ሻሙኤል ብለው፣
2. መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ እና መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ አንድ መጽሐፍ መላክሂም ብለው፣
3. ዜና መዋዕል ቀዳማዊ እና ዜና መዋዕል ካልዕ አንድ መጽሐፍ ሃያሚን ብለው፣
4. መጽሐፈ ዕዝራ እና መጽሐፈ ነህምያ አንድ መጽሐፍ አዝራ ብለው፣
5. ከሆሴዕ እስከ ሚልኪያስ ያሉት 12 መጽሐፍት አንድ መጽሐፍ ትሬአሳር ብለው ይቆጥሩታል።

ከሆሴዕ እስከ ሚልኪያስ ያሉት በአንድ የተጣፉትን 11 መጽሐፍት እና የተጣፉትን 4 መጽሐፍት ስንደምር 15 ይሆናል፤ 15+24= 39 መጽሐፍት ይሆናሉ። አይሁዳውያን መጽሐፍቶቻቸውን “ታንካህ” תַּנַ”ךְ, ሲሉት የሶስቱ መጽሐፍት መነሻ ላይ ያሉት ቃላት መሰረት አርገው ነው፤ እነዚህም “ታ” תַּ ቶራህ፣ “ና” נַ ነቢኢም፣ “ካ” ךְ ኬቱዊም ናቸው። “ቶራህ” תּוֹרָה ማለት “ኦሪት” “ሕግ” “መርሕ” ማለት ነው፣ ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም ያሉትን ለማመልከት ይጠቀሙብታል።
“ነቢኢም” נְבִיאִים ማለት “ነቢያት” ማለት ሲሆን የኢሳያስ ትንቢት፣ የኤርሚያስ ትንቢት፣ የሕዝቅኤል ትንቢት ወዘተ ለማመልከት ይጠቀሙብታል።
“ኬቱዊም” כְּתוּבִים ማለት “መጻሕፍት” ማለት ሲሆን የኢዮብ መጽሐፍ፣ የመዝሙር መጽሐፍ፣ የምሳሌ መጽሐፍ፣ የመክብብ መጽሐፍ፣ የመኃልየ መኃልይ መጽሐፍ ወዘተ ለማመልከት ይጠቀሙብታል።

C. “የካቶሊክ ቀኖና”
የሮማ ካቶሊክ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 46 ናቸው፤ ካቶሊክ በ 39 ላይ እራሳቸውን የቻሉ 7 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ፦
1. መጽሐፈ ጦቢት፣
2. መጽሐፈ ዮዲት፣
3. መጽሐፈ ጥበብ፣
4. መጽሐፈ ሲራክ፣
5. መጽሐፈ ባሮክ፣
6. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ
7. መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ ናቸው።

D. “የኦርቶዶክስ ቀኖና”
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 46 ናቸው፤ የብሉይ ኪዳን መደበኛ የቀኖና መጽሐፍት 39 ሲሆኑ ተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 18 ናቸው፤ ነገር ግን አቆጣረራቸው ልክ እንደ አይሁድ ይለያል። እራሳቸውን የቻሉ 10 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ አቆጣጠራቸው፦
1. መጽሐፈ ሄኖክ፣
2. መጽሐፈ ኩፋሌ(ጁብሊይ)፣
3. መጽሐፈ ጦቢት፣
4. መጽሐፈ ዮዲት፣
5. መጽሐፈ ተግሣጽ፣
6. መጽሐፈ ጥበብ፣
7. መጽሐፈ ሲራክ
8. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ቀዳማይ እና መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ካልዕ፣
9. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማይ እና መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ፣
10. መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ናቸው።

ነባር መጽሐፍት ላይ በመቀነስ ተጨፍልቀው የሚቆጠሩ 2 መጽሐፍት ናቸው፤ እነርሱም፦
11. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማይ እና መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ናቸው፣
12. መጽሐፈ ዕዝራ ቀዳማይ እና መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ(ነህምያ) ናቸው።

ከነባር መጽሐፍት ጋር ተደምረው የሚቆጠሩ ደግሞ 8 መጽሐፍት ናቸው፤ እነርሱም፦
13. ከትንቢተ ኢሳይያስ ጋር የሚቆጠረው ጸሎተ ምናሴ ነው።
14. ከትንቢተ ኤርምያስ ጋር የሚቆጠሩ፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ፣ ተረፈ ኤርምያስ፣ መጽሐፈ ባሮክ፣ ተረፈ ባሮክ ናቸው።
15. ከትንቢተ ዳንኤል ጋር የሚቆጠሩ መጽሐፈ ሶስና፣ ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ እና ተረፈ ዳንኤል ናቸው።

ከ 39 ላይ 8 መጽሐፍት፦ ሳሙኤል ቀዳማይ፣ ሳሙኤል ካልዕ፣ መጽሐፈ ዕዝራ፣ መጽሐፈ ነህምያ፣ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ትንቢተ ኤርሚያስ፣ ሰቆቃው ኤርሚያስ እና ትንቢተ ዳንኤል ሲቀነሱ 31 መጽሐፍት ይሆናሉ። 31+15= 46 ይሆናል።

F. “የሰፕቱአጀንት ቀኖና”
የሰፕቱአጀንት የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 56 ናቸው፤ የሰፕቱአጀንት”LXX” በ 39 ላይ እራሳቸውን የቻሉ 17 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ፦
1. መጽሐፈ ጦቢት፣
2. መጽሐፈ ዮዲት፣
3. መጽሐፈ ጥበብ፣
4. መጽሐፈ ሲራክ፣
5. መጽሐፈ ባሮክ፣
6. ተረፈ ኤርምያስ፣
7. ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ፣
8. መጽሐፈ ሶስና፣
9. ቤልና ድራጎን፣
10. ጸሎተ ምናሴ፣
11.1ኛ መቃብያን፣
12. 2ኛ መቃብያን፣
13. 3ኛ መቃብያን፣
14. 4ኛ. መቃብያን፣
15. ዕዝራ ሱቱኤል፣
16. የአዛርያ ጸሎት፣
17. መዝሙር 151 ናቸው።

G. “የቩልጌት ቀኖና”
ጄሮም በ 382 ድህረ-ልደት በላቲን ቩልጌት ባዘጋጀው ደግሞ የመጽሐፍት ቀኖና 45 ናቸው፤ የቩልጌት በ 39 ላይ እራሳቸውን የቻሉ 6 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ፦
1. መጽሐፈ ጦቢት፣
2. መጽሐፈ ዮዲት፣
3.1ኛ መቃብያን፣
4. 2ኛ መቃብያን፣
5. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ቀዳማይ፣
6. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ካልዕ

ኢንሻላህ ስለ አዲስ ኪዳን በክፍል ሁለት ይቀጥላል…

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቀኖና

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

5፥15 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

ነጥብ ሁለት
“አዲስ ኪዳን”
የአዲስ ኪዳን መደበኛ መጻሕፍት 27 ናቸው፤ እነርሱም እንደሚከተለው ነው፦
1. የማቴዎስ ወንጌል
2. የማርቆስ ወንጌል
3. የሉቃስ ወንጌል
4. የዮሐንስ ወንጌል
5. የሐዋርያት ሥራ
6. የሮሜ ሰዎች
7. 1ኛ. የቆሮንቶስ ሰዎች
8. 2ኛ. የቆሮንቶስ ሰዎች
9. የገላትያ ሰዎች
10. የኤፌሶን ሰዎች
11. የፊልጵስዩስ ሰዎች
12. የቆላስይስ ሰዎች
13. 1ኛ. የተሰሎንቄ ሰዎች
14. 2ኛ. የተሰሎንቄ ሰዎች
15. 1ኛ. ጢሞቴዎስ
16. 2ኛ. ጢሞቴዎስ
17. ቲቶ
18. ፊልሞና
19. የዕብራዊያን ሰዎች
20. 1ኛ. ጴጥሮስ መልእክት
21. 2ኛ. ጴጥሮስ መልእክት
22. 1ኛ. ዮሐንስ መልእክት
23. 2ኛ. ዮሐንስ መልእክት
24 3ኛ. ዮሐንስ መልእክት
25. የያዕቆብ መልእክት
26. የይሁዳ መልእክት
27. የዮሐንስ ራዕይ

በእነዚህ መጽሐፍት ላይ ሁሉም የጋራ አቆጣጠር ቢኖራቸውም ነገር ግን የጭማሬ እና የቅነሳ ነገር ይታይበታል። ይህንንም በግርድፉ እንይ፦
A. “የኦርቶዶክስ ቀኖና”
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 35 ናቸው፤ የአዲስ ኪዳን መደበኛ የቀኖና መጽሐፍት 27 ሲሆኑ ተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሐፍት ቀኖና 8 ናቸው፤ እነዚህም፦
1. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማይ፣
2. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ
3. መጽሐፈ ሥርዓተ ጽዮን
4. መጽሐፈ አብጥሊስ
5. መጽሐፈ ግጽው፣
6.መጽሐፈ ትእዛዝ፣
7. መጽሐፈ ዲድስቅልያ እና
8. መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ናቸው።

B. “የአርመንያ ቀኖና”
የአርመንያ ቤተክርስቲያን በ 27 ቀኖና ላይ 5 መጽሐፍትን ትጨምራለች፤ እነርሱም፦
1. 3ኛ የቆሮንቶስ ሰዎች መልእክት
2. የሎዶቅያ ሰዎች መልእክት
3. የበርናባስ መልእክት
4. 1ኛ የክሌመንት መልእክት
5. 2ኛ የክሌመንት መልእክት

C. “የሉተር ቀኖና”
የፕሮቴስታንት ተሃድሶ ንቅናቄ መሪ ማርቲን ሉተር ከ 27 ላይ 4 መጽሐፍትን ቀንሶ 23 ብቻ ነው የተቀበለው፤ እነርሱም፦
1. የዕብራዊያን ሰዎች
2. የያዕቆብ መልእክት
3. የይሁዳ መልእክት
4. የዮሐንስ ራዕይ

ማጠቃለያ
አይሁዳውያን ለሙሳ የተሰጠውን መጽሐፍ በመከፋፈል ኦሪት ዘፍጥረት፣ ኦሪት ዘጸአት፣ ኦሪት ዘኁልቁ፣ ኦሪት ዘሌዋውያን፣ ኦሪት ዘዳግም በማለት ከፋፍለውታል፤ እነርሱም የማይመቻቸውን አፓክራፋ ማለት ድብቅ በማለት በመቀነስ ደብቀውታል፤ ከዚያም ባሻገር አባቶቻቸውም የማያውቁት ንግግር በአምላክ ንግግር ላይ ጨምረዋል፦
6፥61 እንዲህ በላቸው፡- «ያንን ብርሃን እና ለሰዎች መሪ ኾኖ *ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው? የወደዳችኋትን ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፤ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ*። قُلْ مَنْ أَنزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَىٰ نُورًا وَهُدًى لِّلنَّاسِ ۖ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيرًا ۖ وَعُلِّمْتُم مَّا لَمْ تَعْلَمُوا أَنتُمْ وَلَا آبَاؤُكُمْ ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ ثُمَّ ذَرْهُمْ فِي خَوْضِهِمْ يَلْعَبُونَ

አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ የአርመንያ ቀኖና ውስጥ የሚገኘውን የአስራ ሁለቱ ነገዶችን መጽሐፍ፣ የአብርሃምን የቃል ኪዳን መጽሐፍ፣ የነቢዩ ሸማያ፣ የነቢዩ አዶ፣ የነቢዩ ናታን፣ የነቢዩ ኦሒያ፣ የነቢዩ ዖዴድ የትንቢት መጽሐፍት፣ መጽሐፈ ሄኖክ፣ መጽሐፈ ኩፋሌ፣ መጽሐፈ ጦቢት፣ መጽሐፈ ዮዲት፣ መጽሐፈ ጥበብ፣ መጽሐፈ ሲራክ፣ መጽሐፈ ባሮክ፣ የመሳሰሉትን “አፓክራፋ” ማለትም “ድብቅ” ብለው ሲቀንሱ በተቃራኒው የሰው ንግግር የሆኑትን መጽሐፈ ኢያሱ፣ መጽሐፈ መሳፍንት፣ መጽሐፈ ሩት፣ መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ፣ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ወዘተ በአምላክ ንግግር ላይ ጨምረዋል። ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. Bruce, Frederick (1988). The Canon of Scripture. Downers Grove, Illinois, U.S.: IVP Academic.
2. The Writings: The Third Division of the Old Testament Canon. George Allen & Unwin Ltd., 1963,
3. Michael Coogan. A Brief Introduction to the Old Testament: The Hebrew Bible in Its Context. Oxford University Press, 2009,
ክርስቲያኖች በ 387 ድህረ-ልደት”AD” በካርቴጅ ጉባኤ ከወንጌላት የቶማስ፣ የይሁዳ፣ የጴጥሮስ፣ የያዕቆብ፣ የበርናባስ፣ የፊሊጶስ፣ የበርተሎሞዎስ፣ የመቅደላዊት ማርያም የተባሉትን ወንጌላትን ቀንሰዋል።
ከሥራም ዘገባ የጴጥሮስ ስራ፣ የእንድሪያስ ስራ፣ የፊሊጶስ ስራ፣ የበርናባስ ስራ፣ የጳውሎስ ስራ፣ የዮሐንስ ስራ፣ የቶማስ ስራ ቀንሰዋል።
ከመልእክታትም 3ኛ የቆሮንቶስ ሰዎች መልእክት፣ የሎዶቅያ ሰዎች መልእክት፣ የበርናባስ መልእክት፣ 1ኛ የክሌመንት መልእክት፣ 2ኛ የክሌመንት መልእክት፣ የሄርሜኑ እረኛ መልእክት ወዘተ ቀንሰዋል።
ከአፓልካሊፕስም(ራዕይ) የጴጥሮስ አፖልካሊፕስ፣ የጳውሎስ አፖልካሊፕስ፣ የቶማስ አፖልካሊፕስ፣ የያዕቆብ አፖልካሊፕስ ቀንሰዋል።
ልብ አድርግ እነዚህ አፓክራፋ በጥንታዊያን እደ-ክታባት ለምሳሌ በክላሮሞንታነስ እደ-ክታብ”Codex Claromontanus” ውስጥ የጳውሎስ ስራ፣ የጴጥሮስ ራዕይ፣ የሄርሜኑ እረኛ መልእክት፣ የበርናባስ መልእክት ይገኛሉ፤ በአሌክሳንድሪየስ እደ-ክታብ”Codex Alexandrinus” ውስጥ 2ኛ የክሌመንት መልእክት ይገኛሉ፤ በሳይናቲከስ እደ-ክታብ”Codex Sinaiticus” ውስጥ የሄርሜኑ እረኛ መልእክት እና የበርናባስ መልእክት ይገኛሉ።
ከዚያም ባሻገር የሰው ንግግር የሆኑትን ታሪክና መልእክት በወንጌል ላይ ቀላቅለዋል። ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. Lost Scriptures: Books that Did Not Make It into the New Testament. Oxford University Press, USA. 2003
2. The New Testament and Other Early Christian Writings: A Reader. Oxford University Press, USA. 2003
3. The Other Gospels: Accounts of Jesus from Outside the New Testament. Oxford University Press, USA. 2013 by Bart D. Ehrman.

ይህ በእንዲህ እንዳለ አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ብዙውን የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛውን በእርግጥ ልኳል፦
5፥15 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

“አፓክራፋ” የሚለው ቃል “አፓክራፈስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፤ ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት አስፈላጊውን አላህ የገለጸ ሲሆን ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት ብዙውን ትቶታል፤ ወደ ነብያት ምን ተወርዶ እንደነበረ መልእክተኛው እንዲገልጹ ቁርኣንን አውርዷል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ *ወደ አንተም ለሰዎች ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን*፡፡ بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

ይህ ቁርኣን ከበፊቱ ከአላህ የተወረዱትን የአላህ ንግግሮች የሚያረጋግጥ እና በእነዚያ ንግግሮች ውስጥ ያለውን ጭብጥ የሚዘረዝር ነው፦
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፤ *ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَمَا كَانَ هَـٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَـٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ

የአዲስ ኪዳን እና የብሉይ ኪዳን ጽንፈኛ ሆነ ለዘብተኛ ምሁራን የባይብል ሥረ-መሰረት”orgin” ማለትም ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ኪታባት የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልዕክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት በዘመናችን እንደሌሉ ይናገራሉ፤ ባይብል ሙሉ ለሙሉ የፈጣሪ ንግግር ነው ብለው አያምኑም፤ “ፈጣሪ ሰዎችን የራሳቸውን ቃላት፣ ቋንቋ፣ ክህሎት እና ንግግር ተጠቅመው እንዲናገሩ ፈቀደላቸው” ይላሉ፤ ይህ ስህተት ነው። ለዛ ነው የፈጣሪ ንግግር ተበርዟል የምንለው፤ እውነትን በውሸት ሲቀላቅሉ እውነት የሆነው የአላህ ንግግር ከሰው ንግግር ጋር ስለተቀላቀለ እውነትን ከሐሰት ለመለየት አምላካችን አላህ ቁርአንን ፉርቃን አድርጎ አውርዷል፤ “ፉርቃን” فُرْقَان ማለት “እውነትን ከሐሰት የሚለይ” ማለት ነው፦
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *“እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
25፥1 ያ *ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው*፡፡ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጠቃሚ ዕውቀት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

በሥነ-ዕውቀት ጥናት "መውሡዓህ" مَوْسُوعَة ማለት "መድብለ-ዕውቀት"encyclopedia" ማለት ሲሆን ፍልስፍናን መሠረት ያደረገ የዕውቀት መድብል ነው፥ "ፈልሠፋህ" فَلْسَفَة የሚለው ቃል "ፈልሠፈ" فَلْسَفَ ማለትም "ተፈላሰፈ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ፍልስፍና" ማለት ነው፥ ፍልስፍና የሚፈላሰፍ "ፈላስፋ" ደግሞ "ፈይለሡፍ" فَيْلَسُوف‎ ይባላል። ፍልስፍና "ኢስሙል ኢሥቲፍሃም" اِسْم الاِسْتِفْهَام ማለት "መጠይቅ ተውላጠ-ስም"interrogative pronoun" ያለበት ሲሆን እነዚህም፦
"ማ" مَاْ ማለት "ምንድን"what" ማለት ሲሆን "ምንነትን" የምጠይቅበት መጠይቅ ተውላጠ-ስም ነው፣
"መን" مَنْ ማለት "ማን"who" ማለት ሲሆን "ማንነትን" የምጠይቅበት መጠይቅ ተውላጠ-ስም ነው፣
"መታ" مَتَى ማለት "መቼ"when" ማለት ሲሆን "ጊዜን" የምጠይቅበት መጠይቅ ተውላጠ-ስም ነው፣
"አይነ" أَيْنَ ማለት "የት"where" ማለት ሲሆን "ቦታን" የምጠይቅበት መጠይቅ ተውላጠ-ስም ነው፣
"ከይፈ" كَيْفَ ማለት "እንዴት"how" ማለት ሲሆን "ሁኔታን" የምጠይቅበት መጠይቅ ተውላጠ-ስም ነው፣
"ሊመ" لِمَ ማለት "ለምን"why" ማለት ሲሆን "ምክንያትን" የምጠይቅበት መጠይቅ ተውላጠ-ስም ነው፣
"ከም" كَمْ ማለት "ምን ያህል"how much" ማለት ሲሆን "መጠንን" የምጠይቅበት መጠይቅ ተውላጠ-ስም ነው።

ፍልስፍና በራሱ ችግር ያለው ነገር ባይሆንም መሬት ላይ የማይተገበር እና በቃላት ተጀምሮ በቃላት የሚያልቅ አየር ላይ የተንሳፈፈ ዕውቀት ሁሉ መዋዕለ ጊዜን እና መዋዕለ ጉልበትን ከማፍሰስ እና ከማባከን ውጪ ለዲንያህ ሆነ ለአኺራ ሕይወት የሚፈይደው አንዳች ነገር እና ቁብ የለም፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 17
ጃቢር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አሏህን ጠቃሚ ዕውቀት ጠይቁት! ከማይጠቅም ዕውቀት በአሏህ ተጠበቁ!"*። عَنْ جَابِرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ سَلُوا اللَّهَ عِلْمًا نَافِعًا وَتَعَوَّذُوا بِاللَّهِ مِنْ عِلْمٍ لاَ يَنْفَعُ ‏"‏

የማይጠቅም ዕውቀት የተቆላ ገብስ ነው፥ ሲበሉት ይጣፍጣል ሲዘሩት ግን አይበቅልም። ጠቃሚ ዕውቀት ለእለት ለእለት ሕይወታችን የሚሆን የነቅል ሆነ የዐቅል ዕውቀት ያካትታል። "ነቅል" نَقْل የሚለው ቃል "ነቀለ"نَقَلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከአሏህ በነቢይ የሚተላለፍ ዕውቀት ነው፥ "ዐቅል" عَقْل የሚለው ቃል ደግሞ "ዐቀለ"عَقَلَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን በቀለም የሚተላለፍ ዕውቀት ነው። አምላካችን አሏህ ሰውን ያላወቀውን ሁሉ በቀለም ያሳወቀው ነው፦
96፥4 *"ያ በብርዕ ያስተማረ"*፡፡ ٱلَّذِى عَلَّمَ بِٱلْقَلَمِ
96፥5 *ሰውን ያላወቀውን ሁሉ ያሳወቀ ሲኾን*፡፡ عَلَّمَ ٱلْإِنسَٰنَ مَا لَمْ يَعْلَمْ

"ቀለም" قَلَم የሚለው ቃል "ቀለመ" قَلَمَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ብዕር" ማለት ነው። ከሞት ጋር ሥራዎች ሲያከትሙ ጠቃሚ ዕውቀት ግን ለአኺራም አጅር የሚያስገኝ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 25, ሐዲስ 20
አቡ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሰው በሞተ ጊዜ ከሦስት ነገር ከሶደቀቱል ጃሪያህ ወይም በእርሱ የሚጠቀሙበት ዕውቀት አሊያም ዱዓእ የሚያደርግለት ሷሊሕ ልጅ በቀር ሥራው ያከትማል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا مَاتَ الإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَنْهُ عَمَلُهُ إِلاَّ مِنْ ثَلاَثَةٍ إِلاَّ مِنْ صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ ‏"‏

መልካም ሥራዎች መሠረታቸው ጠቃሚ ዕውቀት ነው። ያለ ዕውቀት ማመን እና መልካም ነገር መሥራት እምነቱም ጭፍን እምነት ነው፥ ሥራውም እዚሁ ዲንያህ ላይ የሚቀር ነው፦
17፥36 *"ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል! መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና"*፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا

"ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ይህንን የዐቅል ሆነ የነቅል ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 229
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"*" አሉ፦ *"ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ

ይህንን ጠቃሚ ዕውቀት ግዴታ የሆነው ማወቅ ብቻ ሳይሆን ማሳወቅም ጭምር ነው፥ ማንም ስለ ዕውቀት የሚያውቀውን ተጠይቆ የደበቀ በትንሳኤ ቀን ከእሳት ልጓም ይለጎማል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 266
አቡ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም ስለ ዕውቀት የሚያውቀውን ተጠይቆ የደበቀ በትንሳኤ ቀን ከእሳት ልጓም ይለጎማል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ مَنْ سُئِلَ عَنْ عِلْمٍ يَعْلَمُهُ فَكَتَمَهُ أُلْجِمَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ بِلِجَامٍ مِنْ نَارٍ ‏"‏

አምላካችን አሏህ ጠቃሚ ዕውቀት ዐውቀው ከሚያሳውቁ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሚድያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥125 *”ወደ ጌታህ መንገድ በጥበብ እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ

"ሚድያ" ማለት "መገናኛ ብዙኃን" ማለት ነው፥ የሳይበሩ ዓለም ሚድያ "ማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን"social media" ይባላል። ሚድያ አውንታዊ የጎንዮሽ ተጽዕኖ ሆነ አሉታዊ የጎንዮሽ ተጽዕኖ በሕዝብ ላይ ለማሳረፍ ጉልህ ሚና አለው፥ ስለዚህ የኢሥላምን መልእክት ሙሥሊሙን ለማጠናከር እና ከሙሥሊም ውጪ ያሉትን ወደ ኢሥላም ለመጣራት ልንጠቀምበት ይገባል! ሚድያ ላይ ወደ ኢሥላም ለመጣራት ጥሩ መድረክ ነው፥ ሰዎችን ወደ ኢሥላም በሚድያ እንጣራ፦
16፥125 *”ወደ ጌታህ መንገድ በጥበብ እና በመልካም ግሳጼ ጥራ፡፡ ادْعُ إِلَىٰ سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የባቢል አማልክት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥161 *«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የአብርሃምን መንገድ መራኝ፥ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል"*፡፡ قُلْ إِنَّنِي هَدَانِي رَبِّي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ دِينًا قِيَمًا مِّلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

"ባቢል" بَابِل የሚለው ቃል "ባብ" እና "ኢል" የሚባሉ የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ባብ" بَاب ማለት "በር" ማለት ሲሆን "ኢል" إيل ደግሞ "ኢላህ" إِلَـٰه የሚለው ምጻረ-ቃል ሲሆን "አምላክ" ማለት ነው። በጥቅሉ "ባቢል" بَابِل ማለት "የአምላክ በር" ማለት ነው፥ ይህንን ስፍራ "ወደ አምላክ የሚያደርስ በር ነው" በማለት ሕንፃዎችን ገንብተው እነዚያን ሕንፃዎች አሏህ ከመሠረታቸው ደረማመሰባቸው፦
16፥26 *"እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት በእርግጥ መከሩ፡፡ አላህም ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ፥ ጣሪያውም በእነርሱ ላይ ከበላያቸው ወደቀባቸው፡፡ ቅጣቱም ከማያውቁት ሥፍራ መጣባቸው"*፡፡ قَدْ مَكَرَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ فَأَتَى اللَّهُ بُنْيَانَهُم مِّنَ الْقَوَاعِدِ فَخَرَّ عَلَيْهِمُ السَّقْفُ مِن فَوْقِهِمْ وَأَتَاهُمُ الْعَذَابُ مِنْ حَيْثُ لَا يَشْعُرُونَ

ባቢል በሚባል ስፍራ የኢብራሂም አባት እና ሕዝቦቹ አማልክትን ያመልኩ ነበር። "ኢላህ" إِلَـٰه ብዙ ቁጥሩ "አሊሃህ" آلِهَة ሲሆን "አማልክት" ማለት ነው፦
6፥74 *"ኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር «ጣዖታትን አማልክት አድርገህ ትይዛለህን? እኔ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ!"* وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ لِأَبِيهِ آزَرَ أَتَتَّخِذُ أَصْنَامًا آلِهَةً ۖ إِنِّي أَرَاكَ وَقَوْمَكَ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አማልክት" የተባሉት "ጣዖታት" ናቸው፥ "ጣዖታት" ለሚለው የገባው ቃል "አስናም" أَصْنَام ሲሆን ብረት ከሆኑ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሰርተው አምልኮ የሚቀርብላቸው ናቸው። በተለይ በባቢል ሦስት ዐበይት በቀለማዊ ብረት የሚሠሩ አማልክት ያመልኩ ነበር፥ እነዚህም አማልክት "ኢሽታር" በሰማያዊ ናስ፣ "ሲን" በአረንጓዴ ብር፣ "ሻማሽ" በቢጫ ወርቅ የተሠሩ ናቸው። ኢብራሂም እነዚህን አማልክት አባቱ እና ሕዝቦቹ ማምለክ እንዲተዉ አምላካችን አሏህ የሰማያትን እና የምድርን ግዛት አሳየው፦
6፥75 *"እንደዚሁም ኢብራሂምን እንዲያውቅና ከአረጋጋጮቹም ይኾን ዘንድ የሰማያትን እና የምድርን መለኮት አሳየነው"*፡፡ وَكَذَٰلِكَ نُرِي إِبْرَاهِيمَ مَلَكُوتَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلِيَكُونَ مِنَ الْمُوقِنِينَ

“መለኩት” مَلَكُوت ማለት “ግዛት” ማለት ነው፥ “መለኮት” የሚለው የግዕዝ ቃል እራሱ ሁለት ትርጉም አለው፥ አንዱ “አምላክ” ማለት ሲሆን ሁለተኛው “ግዛት” ማለት ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ 594-595 ላይ ይመልከቱ!
አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም "አሳየነው" ይለናል፥ ምንድን ነው ያሳየው? አዎ! ያሳየው የሰማይ ግዛት ነው። ኢብራሂም በሰማይ ግዛት ያለውን ኮከብ ተመለከተ፦
6፥76 *"ሌሊቱም በእርሱ ላይ ባጨለመ ጊዜ ኮከብን አየ፡፡ «ይህ ጌታዬ ነው» አለ፡፡ በጠለቀም ጊዜ፡- «ጠላቂዎችን አልወድም» አለ"*፡፡ فَلَمَّا جَنَّ عَلَيْهِ اللَّيْلُ رَأَىٰ كَوْكَبًا ۖ قَالَ هَـٰذَا رَبِّي ۖ فَلَمَّا أَفَلَ قَالَ لَا أُحِبُّ الْآفِلِينَ

"አየ" የሚለው ይሰመርበት! የሚያሳየው ደግሞ አሏህ ነው፥ አሏህ ለኢብራሂም የሰጠው ሒክማህ የሚደንቅ ነው። ኢብራሂም ኮከቡን በለበጣና በሽሙጥ ንግግር "ጌታዬ ነው" እያለ ግን ያ ኮከብ ሲሰወር ቋሚ ነገር እንዳልሆነ በማሳየት የሚያመልኩትን ኮከብ ያስተባብል ነበር፥ አሏህ ሌሊቱን ሲያጨልም ይህ ኮከብ ይታያል፦
86፥1 *"በሰማዩ በሌሊት መጪውም እምላለሁ"*፡፡ وَالسَّمَاءِ وَالطَّارِقِ
86፥2 *"የሌሊት መጪውም ምን እንደ ኾነ ምን አሳወቀህ?"* وَمَا أَدْرَاكَ مَا الطَّارِقُ
86፥3 *"ጨለማን ቀዳጁ ኮከብ ነው"*፡፡ النَّجْمُ الثَّاقِبُ

በባቢል ከሚመለኩት ከሦስቱ ዐበይት አማልክት አንዱ በሰማያዊ ናስ ምስል "ኢሽታር" ነው፥ "ኢሽታር" በአካድ ቋንቋ፣ በዕብራይስጥ “አሸራ” אֲשֵׁרָה በግሪክ "አስትሮን" ᾰ̓́στρον ሲሆን "ኮከብ" ማለት ነው። "star" የሚለው የእንግሊዚኛ ቃል እራሱ እንኳን "አስትሮን" ᾰ̓́στρον ከሚለው ከግሪኩ ቃል የተወሰደ ነው፥ ይህንን ጣዖት ምንም ማድረግ እንደማይችል ኢብራሂም ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ መመለክ እንደማይችሉ አስረገጠላቸው። በመቀጠል ጨረቃን ሲወጣ አይቶ፦ "ይህ ጌታዬ ነው" ብሎ በተሰወረ ጊዜ ግን "ጌታዬ ቅኑን መንገድ ባይመራኝ በእርግጥ ከተሳሳቱት ሕዝቦች እኾናለሁ" አለ፦
6፥77 ጨረቃንም ወጪ ኾኖ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው» አለ፡፡ በገባም ጊዜ፡- «ጌታዬ ቅኑን መንገድ ባይመራኝ በእርግጥ ከተሳሳቱት ሕዝቦች እኾናለሁ» አለ"*፡፡ فَلَمَّا رَأَى الْقَمَرَ بَازِغًا قَالَ هَـٰذَا رَبِّي ۖ فَلَمَّا أَفَلَ قَالَ لَئِن لَّمْ يَهْدِنِي رَبِّي لَأَكُونَنَّ مِنَ الْقَوْمِ الضَّالِّينَ
በባቢል ከሚመለኩት ከሦስቱ ዐበይት አማልክት አንዱ በአረንጓዴ ብር ምስል "ሲን" ነው፥ "ሲን" ማለት በአካድ ቋንቋ "ጨረቃ" ማለት ነው። ኢብራሂም አሏህን፦ "ጌታዬ" ማለቱ በራሱ ኢሽታርን፣ ሲንን እና ሻማሽን "ጌታዬ" የሚለው ለሕዝቦቹ ለማስተማር የተጠቀመበት ሒክማህ መሆኑ ማሳያ ነው፥ አሏህ "ቅኑን መንገድ ባይመራኝ በእርግጥ ከተሳሳቱት ሕዝቦች እኾናለሁ" ማለቱ በራሱ ኢሽታርን፣ ሲንን እና ሻማሽን በማምለክ ከተሳሳቱት ሕዝቦች አለመሆኑን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። በተጨማሪም አሏህ ኮከብን፣ ጨረቃን እና ፀሐይን ለኢብራሂም ከማሳየቱ በፊት፦ "እኔ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ" በማለት እርሱ በሺርክ ውስጥ እንደሌለበት ማሳያ ነው።
በመቀጠል ፀሐይን ጮራዋን ዘርግታ ባየ ጊዜ፦ "ይህ ጌታዬ ነው" ብሎ በተሰወረ ጊዜ ግን "ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹሕ ነኝ" አለ፦
6፥78 *"ፀሐይንም ጮራዋን ዘርግታ ባየ ጊዜ፡- «ይህ ጌታዬ ነው፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ነው» አለ፡፡ በገባችም ጊዜ፡- «ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹሕ ነኝ» አለ፡፡ فَلَمَّا رَأَى الشَّمْسَ بَازِغَةً قَالَ هَـٰذَا رَبِّي هَـٰذَا أَكْبَرُ ۖ فَلَمَّا أَفَلَتْ قَالَ يَا قَوْمِ إِنِّي بَرِيءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ

በባቢል ከሚመለኩት ከሦስቱ ዐበይት አማልክት አንዱ በቢጫ ወርቅ ምስል "ሻማሽ" ነው፥ "ሻማሽ" ማለት በአካድ ቋንቋ "ፀሐይ" ማለት ነው። ኢብራሂም፦ "ወገኖቼ ሆይ! እኔ ከምታጋሩት ሁሉ ንጹሕ ነኝ" ማለቱ በራሱ በፈጣሪያቸው በአሏህ ላይ ከሚያጋሩት ከኢሽታር፣ ከሲን እና ከሻማሽ ኢብራሂም እንዳልተነካካ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፥ ከዚያ ይልቅ ፊቱን ለዚያ ሰማያትን እና ምድርን ለፈጠረው ለአሏህ የሰጠ ሙሥሊም ነበር። እንደ አባቱ እና እንደ ሕዝቦቹ ከአጋሪዎች አልነበረም፦
6፥79 *«እኔ ለዚያ ሰማያትን እና ምድርን ለፈጠረው አምላክ ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» አለ"*፡፡ إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
3፥95 *«አላህ እውነትን ተናገረ፡፡ የኢብራሂምንም መንገድ ወደ እውነት ያዘነበለ ሲኾን ተከተሉ! ከአጋሪዎቹም አልነበረም» በላቸው"*፡፡ قُلْ صَدَقَ اللَّهُ ۗ فَاتَّبِعُوا مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
6፥161 *«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የአብርሃምን መንገድ መራኝ፥ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል"*፡፡ قُلْ إِنَّنِي هَدَانِي رَبِّي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ دِينًا قِيَمًا مِّلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

በአምልካች መስተአምር "አል-ሙሽሪኪን" الْمُشْرِكِين የተባሉት አስናም አማልክት አድርገው የያዙት አባቱ እና ሕዝቦቹ ናቸው፥ እርሱ ግን "ሐኒፍ" حَنِيف ማለትም "ቀጥተኛ" ሙሥሊም ነበረ። ሕዝቦቹ ኢብራሂም ሲከራከሩት፦ "በአሏህ የምታጋሩትን ነገር አልፈራም" በማለት ምላሽ ሰጠ፦
6፥80 *"ወገኖቹም ተከራከሩት፡፡ «በአላህ አንድነት በእርግጥ የመራኝ ሲኾን ትከራከሩኛላችሁን? በእርሱም የምታጋሩትን ነገር አልፈራም፡፡ ግን ጌታዬ ነገርን ቢሻ ያገኘኛል፡፡ ጌታዬም ነገሩን ሁሉ ዕውቀቱ ሰፋ፡፡ አትገነዘቡምን?» አላቸው"*፡፡ وَحَاجَّهُ قَوْمُهُ ۚ قَالَ أَتُحَاجُّونِّي فِي اللَّهِ وَقَدْ هَدَانِ ۚ وَلَا أَخَافُ مَا تُشْرِكُونَ بِهِ إِلَّا أَن يَشَاءَ رَبِّي شَيْئًا ۗ وَسِعَ رَبِّي كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا ۗ أَفَلَا تَتَذَكَّرُونَ
6፥81 *"«በእናንተ ላይ በእርሱ ማስረጃን ያላወረደበትን እናንተ ማጋራታችሁን የማትፈሩ ስትኾኑ የምታጋሩትን ጣዖታት እንዴት እፈራለሁ? የምታውቁም ብትኾኑ ከሁለቱ ክፍሎች በጸጥታ ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው?» አለ"*፡፡ وَكَيْفَ أَخَافُ مَا أَشْرَكْتُمْ وَلَا تَخَافُونَ أَنَّكُمْ أَشْرَكْتُم بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَانًا ۚ فَأَيُّ الْفَرِيقَيْنِ أَحَقُّ بِالْأَمْنِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

አባቱ እና ሕዝቦቹ አሏህ ማስረጃን ያላወረደበትን ማጋራታቸው ለልብ ጸጥታ የማይሰጥ ነገር ነው፥ በአሏህ ላይ ማጋራት ታላቅ በደል ነው። እነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ ጸጥታ አላቸው፦
6፥82 *"እነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ ጸጥታ አላቸው፡፡ እነርሱም የተመሩ ናቸው"*። الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُم بِظُلْمٍ أُولَـٰئِكَ لَهُمُ الْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ

አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም የሰማያትን ግዛት ኮከብ፣ ጨረቃ እና ፀሐይ በማሳየት ምንም ማድረግ እንደማይችሉ እንዲያስተምራቸው ጥበቡን መጠቀሙ ለኢብራሂም በሕዝቦቹ ላይ ሑጃህ ነው፥ አሏህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነው፦
6፥83 *"ይህችም ማስረጃችን ናት፡፡ ለኢብራሂም በሕዝቦቹ ላይ አስረጅ እንድትኾን ሰጠናት፥ የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና"*፡፡ وَتِلْكَ حُجَّتُنَا آتَيْنَاهَا إِبْرَاهِيمَ عَلَىٰ قَوْمِهِ ۚ نَرْفَعُ دَرَجَاتٍ مَّن نَّشَاءُ ۗ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٌ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አልባሌ ጥያቄ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥101 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለጹ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ! ቁርኣንም በሚወርድበት ጊዜ ከእርሷ ብትጠይቁ ለእናንተ ትገለጻለች፤ ከእርሷ አላህ ይቅርታ አደረገ፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ ነው"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَسْأَلُوا عَنْ أَشْيَاءَ إِن تُبْدَ لَكُمْ تَسُؤْكُمْ وَإِن تَسْأَلُوا عَنْهَا حِينَ يُنَزَّلُ الْقُرْآنُ تُبْدَ لَكُمْ عَفَا اللَّهُ عَنْهَا ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ حَلِيمٌ

"አልባሌ ጥያቄ" ማለት ብናውቀው የማይጠቅም እና ባናውቀው የማይጎዳን ጥያቄ ማለት ነው፥ ከዚያ በተቃራኒው ቢታወቅ የሚጠቅም ጥያቄ ሲጠየቅ አምላካችን አሏህ፦ "የሥአሉነከ" يَسْـَٔلُونَكَ ማለትም "ይጠይቁካል" በማለት እራሱ የዓለማቱ ጌታ በማብራራት መልስ ይሰጣል፦
25፥33 *በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ፣ መልካምን ፍች የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ*። وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ፍች” ለሚለው ቃል የገባው “ተፍሢራ” تَفْسِيرًا መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። “ተፍሢር” تَفْسِير የሚለው ቃል እራሱ “ፈሠረ” فَسَرَ ማለትም “አብራራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማብራሪያ" ማለት ነው። ቁርኣንም በሚወርድበት ጊዜ ሲጠየቅ አሏህ ለጥያቄ መልስ ይገልጻል፦
5፥101 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለጹ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ! ቁርኣንም በሚወርድበት ጊዜ ከእርሷ ብትጠይቁ ለእናንተ ትገለጻለች፤ ከእርሷ አላህ ይቅርታ አደረገ፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ ነው"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَسْأَلُوا عَنْ أَشْيَاءَ إِن تُبْدَ لَكُمْ تَسُؤْكُمْ وَإِن تَسْأَلُوا عَنْهَا حِينَ يُنَزَّلُ الْقُرْآنُ تُبْدَ لَكُمْ عَفَا اللَّهُ عَنْهَا ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ حَلِيمٌ

"ቁርኣንም በሚወርድበት ጊዜ ከእርሷ ብትጠይቁ ለእናንተ ትገለጻለች" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ቅሉ ግን ቢገለጽ የሚያስከፉ፣ የሚያሳዝኑ እና ቅስም የሚያሰብሩ አልባሌ ጥያቄ መጠየቅ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፥ ይህ አንቀጽ የወረደበት ምክንያት እንዲህ ተቀምጧል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 177
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ስለ ሶሓባዎች አንድ ነገር ለአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ተባለ፥ እርሳቸውም በኹጥባ እንዲህ አሉ፦ *"ጀናህ እና እሳት ወደ እኔ ታዩኝ፥ እንደ ዛሬው ስለ ሠናይ እና እኩይ አይቼ ዐላውቅም፡፡ ይህንን ብታውቁ ኖሮ ብዙ ባለቀሳችሁ ጥቂት በሳቃችሁ ነበር! እርሱም(ዘጋቢው) አለ፦ "ለአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" ባልደረቦች ከዚህ የበለጠ ከባድ ቀን አልመጣም፥ እራሳቸውን ሸፍነው የልቅሶው ድምጽ ከእነርሱ ተሰማ። ዑመርም ቆሞ፦ "የእኛ ደስታችን አሏህ ጌታችን ነው፣ ዲናችን ኢሥላም ነው፣ ነቢያችን ሙሐመድ ነው" አለ። አንድ ሰው በዚያን ጊዜ ነበር ቆሞ፦ “አባቴ ማን ነው? አለ። ነቢዩም፦ "አባትህ እንዲህ እና እንዲህ ነው" አሉት፥ ያኔ፦ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለጹ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ!" የምትለዋ አንቀጽ ወረደች"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ بَلَغَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ أَصْحَابِهِ شَىْءٌ فَخَطَبَ فَقَالَ ‏"‏ عُرِضَتْ عَلَىَّ الْجَنَّةُ وَالنَّارُ فَلَمْ أَرَ كَالْيَوْمِ فِي الْخَيْرِ وَالشَّرِّ وَلَوْ تَعْلَمُونَ مَا أَعْلَمُ لَضَحِكْتُمْ قَلِيلاً وَلَبَكَيْتُمْ كَثِيرًا ‏"‏ ‏.‏ قَالَ فَمَا أَتَى عَلَى أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَوْمٌ أَشَدُّ مِنْهُ - قَالَ - غَطَّوْا رُءُوسَهُمْ وَلَهُمْ خَنِينٌ - قَالَ - فَقَامَ عُمَرُ فَقَالَ رَضِينَا بِاللَّهِ رَبًّا وَبِالإِسْلاَمِ دِينًا وَبِمُحَمَّدٍ نَبِيًّا - قَالَ - فَقَامَ ذَاكَ الرَّجُلُ فَقَالَ مَنْ أَبِي قَالَ ‏"‏ أَبُوكَ فُلاَنٌ ‏"‏ ‏.‏ فَنَزَلَتْ ‏{‏ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لاَ تَسْأَلُوا عَنْ أَشْيَاءَ إِنْ تُبْدَ لَكُمْ تَسُؤْكُمْ‏}‏

አንድ ሰው አባቱ ወይም እናቱ አሊያም ቤተሰቡ ከሞተ በኃላ የት እንዳለ ቢገለጽለት የሚያስከፋው ጉዳይ ነው። በተረፈ ቁርኣን ብዙ ቦታ ኢስሙል ኢሥቲፍሃም ይዟል፥ “ኢስሙል ኢሥቲፍሃም” اِسْم الاِسْتِفْهَام ማለት “መጠይቅ ተውላጠ-ስም”interrogative pronoun” ማለት ሲሆን እነዚህም፦ “ማ” مَاْ "መን” مَنْ “መታ” مَتَى “አይነ” أَيْنَ “ከይፈ” كَيْفَ “ሊመ” لِمَ “ከም” كَمْ ናቸው። እነዚህን መሠታዊ ጥያቄዎች መመለስ ከአንድ ለኢሥላም ዘብ እና አበጋዝ ከቆመ አርበኛ ዐቃቤ እሥልምና የሚጠበቅ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 30, ሐዲስ 25
ዘይድ ኢብኑ ኻሊዱል ጁሀኒይ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ስለ የተሻለ ምስክር አልንገራችሁን? ያ እርሱ ከመጠየቋ በፊት ማስረጃውን የሚያመጣ ነው"*። عَنْ زَيْدِ بْنِ خَالِدٍ، الْجُهَنِيِّ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِخَيْرِ الشُّهَدَاءِ الَّذِي يَأْتِي بِشَهَادَتِهِ قَبْلَ أَنْ يُسْأَلَهَا ‏"‏ ‏.‏

ጥያቄ በራሱ ችግር ያለው ነገር ባይሆንም መሬት ላይ የማይተገበር እና በቃላት ተጀምሮ በቃላት የሚያልቅ አየር ላይ የተንሳፈፈ ጥያቄ ሁሉ መዋዕለ ጊዜን እና መዋዕለ ጉልበትን ከማፍሰስ እና ከማባከን ውጪ ለዱንያህ ሆነ ለአኺራ ሕይወት የሚፈይደው አንዳች ነገር እና ቁብ የለም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እግዚአብሔር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

1፥2 *"ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው"* الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

“ዱንያ” دُّنْيَا የሚለው ቃል “አድና” أَدْنَى‎ ማለትም “ቅርብ” ለሚለው ተባዕታይ መደብ አንስታይ መደብ ሲሆን “ቅርቢቱ ዓለም” ማለት ነው፥ “አኺራ” آخِرَةِ የሚለው ቃል ደግሞ “አኺር” آخِر ማለትም “መጨረሻ” ለሚለው ተባዕታይ መደብ አንስታይ መደብ ሲሆን “መጨረሻይቱ ዓለም” ማለት ነው። ሁለቱም ዓለማት የአሏህ ናቸው፦
53፥25 *"መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የአላህ ብቻ ናቸው"*፡፡ فَلِلَّهِ الْآخِرَةُ وَالْأُولَىٰ

“ዓለም” عَالَم የሚለው ቃል "ዐሊመ" عَلِمَ ማለትም "ዐወቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የታወቀ" ወይም "ዓለም" ማለት ሲሆን የዓለም ብዙ ቁጥር ደግሞ “ዐለሚን” عَٰلَمِين ወይም "ዓለሙን" عَالَمُون ሲሆን "ዐለማት" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ የሰባቱ ሰማያት ማለትም የመጨረሻይቱ ዓለም፣ የምድር ማለትም የቅርቢቱ ዓለም እና በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነው። እርሱ የእነዚህ ሁሉ ዓለማት ጌታ ነው፦
19፥65 *"እርሱ የሰማያት እና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና አምልከው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?*። رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا
1፥2 *"ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው"* الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
6፥164 *በላቸው «እርሱ አላህ የሁሉ ነገር ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን?* قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَبْغِي رَبًّا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَيْءٍ

"የሁሉ ነገር ጌታ" የሚለው ይሰመርበት! "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን "ጊዜ" እና "ቦታ" ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ፍጥረት ሁሉ ነው። ቁርኣን አምላካችን አሏህን "የዓለማት ጌታ" ሲል በዚህ መልክ እና ልክ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች፦ "በቁርኣን አሏህ የዓለማት ጌታ፥ በባይብል ደግሞ ሰይጣን የዓለም ጌታ ነው" በማለት ወሊ-አዑዝቢሏህ ይቀጥፋሉ፦
ዮሐንስ 12፥31 *"አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደርሶአል፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዥ ወደ ውጭ ይጣላል"*።
2 ቆሮንቶስ 4፥4 *"የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ"*።

እነዚህ ሁለት አናቅጽ ላይ "ዓለም" ከሚለው ቃል በፊት "የዚህ" የሚለው አመልካች ተውላጠ-ስም ስላለው "ዓለም" ሲል ክፉ አስተሳሰብ የተጸናወተውን ሥርዓት እንጂ ጽንፈ-ዓለሙን እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው፦
ዮሐንስ 15፥18 *"ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ"*።

ኢየሱስን እና ደቀ መዛሙርቱን የጠላው ክፉ አስተሳሰብ የተጸናወተውን ሥርዓት እንጂ ጽንፈ-ዓለሙን እንዳልሆነ እሙር እና ስሙር ነው። ሲቀጥል ጽንፈ-ዓለሙ የፈጣሪ ብቻ ነውና፦
መዝሙር 24፥1 *"ምድር እና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ"*።
መዝሙር 50፥12 *"ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና*"።

ዓለም የእግዚአብሔር ከሆነ ሰይጣን የዓለም ጌታ ከሆነ እግዚአብሔር ሰይጣን ነውን? እግዚአብሔር የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "እግዚእ" ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን "ብሔር" ማለት "አገር" ወይም "ዓለም" ማለት ነው። በጥቅሉ "እግዚአብሔር" ማለት "የብሔር ጌታ" ማለት ነው። የዓለም ጌታ እና የዚህ ዓለም ጌታ አንድ ማንነት ከሆኑ እግዚአብሔር ሰይጣን ነውን?

፨ ሲጀመር "እግዚ"እ" ላይ "እ" የነበረው መድረሻ ፊደል ሳድስ ፊደል ወደ አገናዛቢ "የ" ለማለት ስንፈልግ "እ" የነበረውን ወደ ሀግእዝ "አ" ሲሆን "እግዚ"አ" ይሆንና "የ" ብሔር "ጌታ" ይሆናል፥ ለምሳሌ፦ "ፍትሐ-ብሔር" የሚለው ቃል ላይ "ፍት"ሕ" ላይ "ሕ" የነበረው መድረሻ ፊደል ሳድስ ፊደል ወደ አገናዛቢ "የ" ለማለት ስንፈልግ "ሕ" የነበረውን ወደ ሀግእዝ "ሐ" ሲሆን "ፍት"ሐ" ይሆንና "የ" ብሔር "ሕግ" ይሆናል።

፨ ሲቀጥል "እግዚአብሔር" ማለት "የብሔር ጌታ" ማለት ብቻ ነው እንጂ "እግዚእ" ካልን "አ" ስለሌለ "ብ" ብቻ ይመጣል፥ "አብ" የሚል ቃል የለም፥ "አ" የሚለውን ከ "እ" ከሰረቅን ደግሞ "እግዚ" ይሆንና ትርጉም አልባ ይሆናል። "ሔር" ማለት ደግሞ "ቸር" ማለት እንጂ መንፈስ ቅዱስ ማለት በፍጹም አይደለም፦
መዝሙር 136፥1 እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ *"ቸር"* ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

ግዕዙ፦ "ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ሔር፥ እስመ ለዓለም ምህረቱ እስመ ለዓለም" ይለዋል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ቸር" ለሚለው የገባው ቃል በግዕዙ "ሔር" ነው። "እግዚእ" ማለት እኮ "ጌታ" ማለት እንጂ "ወልድ" ማለት አይደለም።

፨ ሢሠልስ እግዚአብሔር ማለት፦ "አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ" ማለት ከሆነ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ሲባል የአብ፣ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ልጅ ይሆን ነበር።

፨ ሲያረብብ እግዚአብሔር ማለት፦ "አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ" ማለት ከሆነ ወልድ እራሱ የወልድ አባት ሆነ ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሱሪ ባንገት ማስገባት ስለሆነ አያስኬድም።

ወደ ዋናው ነጥባችን ስንመለስ "እግዚአብሔር" ማለት "የብሔር ወይም የዓለም ጌታ" ማለት ከሆነ እና እግዚአብሔር የዓለም ጌታ የተባለው ሰይጣን የዓለም ጌታ በተባለበት ስሌት አይደለም" ካላችሁ በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው። እንግዲያውስ አሏህ የዓለማቱ ጌታ ነው የተባለው የአጽናፉ ዓለማት ጌታ በሚል ሒሳብ እና ቀመር መሆኑን ተረድታችሁ የአስተሳሰብ ቅኝታችሁን ቀይሩ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የዒሣ አፈጣጠር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥59 *”አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም”*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

ሰው የተፈጠረው ከምድር ነው። “ምድር” የሚለው ቃል ተክቶ የመጣ “ሃ” ْهَا ማለትም “እርሷ” የሚል ተውላጠ-ስም አለ፥ “ሃ” በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መጥቷል፦
20፥55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ*፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡ مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ

ይህ የሚያሳየው ሰው የተፈጠረው ከምድር ነው፤ ምድር ለአካል መሰራት ግኡዝ ንጥረ-ነገር ነው። አላህ ምድርን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “አርዲ” أَرْضِي ማለትም “ምድሬ” በማለት በአገናዛቢ ተውላጠ-ስም ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! *ምድሬ* በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ አምልኩኝ፡፡* يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ وَاسِعَةٌ فَإِيَّايَ فَاعْبُدُونِ

ይህንን ከምድር የተፈጠረውን ሰው አላህ ሩሕ በመንፋት ሕያው አደረገው። “ሩሕ” رُوح ማለትም “መንፈስ” ማለት ሲሆን አላህ ግኡዛን ነገሮችን ሕያው የሚያደርግበት ንጥረ-ነገር ነው። አላህ ከምድር በተፈጠረው አካል ከመንፈሱ ሲነፋበት ያ ግኡዝ አካል ሕያው ሆነ፦
38፥72 *ፍጥረቱንም ባስተካከልኩ እና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ* ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» አልኩ፡፡ فَإِذَا سَوَّيْتُهُۥ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِى فَقَعُوا۟ لَهُۥ سَٰجِدِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሩሕ” رُوح በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መነሻ ቅጥያ አለ፥ ይህ የሚያሳየው “ሩሕ” አካል ሕያው የሚሆንበት ንጥረ-ነገር መሆኑን ነው። “ከ”ምድር “ከ”መንፈስ የሚለው ቃላት ይሰመርበት። አላህ ምድርን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “አርዲ” أَرْضِي ማለትም “ምድሬ” በማለት እንደተናገረ ሁሉ በተመሳሳይም ሩሕን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “ሩሒ” رُّوحِى ማለትም “መንፈሴ” በማለት በአገናዛቢ ተውላጠ-ስም” ተናግሯል። ምድርም መንፈስም የሰው ምንነት ነው፥ አላህ ልክ ኣደምን ከዐፈር ሰርቶ ከመንፈሱ አካሉ ላይ ሲነፋበት ሰው እንደሆነ ሁሉ መርየም ውስጥ ያለውን አካል ከመንፈሱ ሲነፋበት ዒሣ ሰው ሆነ፦
21፥91 ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን *”በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን”* እርሷንም ልጅዋንም ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ፡፡ وَالَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ

ኣደም እና ዒሣ አፈጣጠራቸው የሚያመሳስላቸው ለዚህ ነው፦
3፥59 *”አላህ ዘንድ የዒሣ ምሳሌ እንደ ኣደም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለ”እርሱ” «ኹን» አለው፤ ኾነም”*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

“ኸለቀ” خَلَقَ ማለትም “ፈጠረ” በሚለው ግስ መዳረሻ ቅጥያ ላይ “ሁ” هُۥ ማለት “እርሱ” የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም አለ፥ ይህም የስም ምትክ “ኣደም” ءَادَم የሚለውን የተጻውዖ ስም ተክቶ የመጣ ነው። “ከአፈር” ፈጠረው የሚለው ኣደምን እንጂ በፍጹም ዒሣን አይደለም። ይህንን ለመረዳት አንድ የሰዋስው ሙግት እናቅርብ፦
2፥45 *”በመታገስ እና በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷም በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ

“ሃ” َّهَا ማለትም “እርሷ” የሚለው ተውላጠ-ስም ተክቶ የመጣው ምንን ነው? “መታገስ” የሚለው ቃል ወይስ “ሶላት” የሚለው ቃል? ስልን፤ መልሱ የቅርብ ቃል “ሶላት” ስለሆነ “እርሷ” የሚለው ተክቶ የመጣው “ሶላት” የሚለውን ቃል ነው። በተመሳሳይ የቅርብ ቃል “ኣደም” ስለሆነ “እርሱ” የሚለው ተክቶ የመጣው “ኣደም” የሚለውን ቃል ነው።
ኣደም እና ዒሣ የተመሳሰሉበት ነጥብ የተፈጠሩበት ንጥረ-ነገር ሳይሆን የተፈጠሩበት ሁኔታ ነው። ሁለቱም በታምር ኹን በሚለው ቃል መፈጠራቸው ነው። አላህ ኣደምን ከዐፈር ፈጥሮ ኹን እንዳለው እንደሆነ ሁሉ ዒሣን ከመርየም ኹን በማለት ፈጥሮታል፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ዒሣ የተፈጠረው ኣደም ላመጣው ጦስ ገፈትና አበሳ ለመቅመስ ሳይሆን አራተኛውን የሰውን ፍጥረት ሊያሟላ ነው። አምላካችን አላህ ኣደምን ያለ ወንድና ሴት ፈጥሮ በተቃራኒው እኛ ደግሞ ከወንድና ከሴት ፈጥሮናል፥ ሐዋን ከወንድ ያለ ሴት ፈጥሮ ስለነበር የሐዋ አፈጣጠር ተቃራኒ ከሴት ያለ ወንድ ዒሣን በመፍጠር ፍጥረቱ ተሟልቷል። ለምን እኛን ልክ እንደ ኣደም ያለ ወንድና ሴት ከዐፈር አልፈጠረንም? መልሱ፦ “የአላህ ምርጫ ነው” ከሆነ እንግዲያውስ የሐዋም ሆነ የዒሣ አፈጣጠር የአላህ ምርጫ ነው፥ ለፍጡራን ግን በዚህ መልኩ ልፈጠር የማለት ምርጫ የላቸውም፦
28፥68 *ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ለፍጡራን ምርጫ የላቸውም*፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَة

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሪዝቅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

51፥57 *"ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም"፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም"*፡፡ مَا أُرِيدُ مِنْهُم مِّن رِّزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَن يُطْعِمُونِ

"ሪዝቅ" رِزْق የሚለው ቃል "ረዘቀ" رَزَقَ ማለትም "ሲሳይን ሰጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሲሳይ" ወይም "ረድኤት" ማለት ነው፥ ከሰማይና ከምድር ሪዝቅን የሚረዝቀው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብረው አሏህ ነው፦
10፥31 *«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው? ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው?» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን?» በላቸው*፡፡ قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ أَمَّن يَمْلِكُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَمَن يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ الْمَيِّتَ مِنَ الْحَيِّ وَمَن يُدَبِّرُ الْأَمْرَ ۚ فَسَيَقُولُونَ اللَّهُ ۚ فَقُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ

አምላካችን አሏህ ከሰማይ ውኃን በማውረድ በእርሱ ከፍሬዎች ሲሳይን ከምድር በማውጣት የሚረዝቀን ነው፦
2፥22 *ከሰማይም ውኃን ያወረደ በእርሱም ከፍሬዎች "ለእናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው፡፡ እናንተም ፈጣሪነቱን የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ*፡፡ وَأَنزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَخْرَجَ بِهِ مِنَ الثَّمَرَاتِ رِزْقًا لَّكُمْ ۖ فَلَا تَجْعَلُوا لِلَّهِ أَندَادًا وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

"ለእናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! እዚህ አንቀጽ ላይ "ሲሳይ" ለሚለው ቃል የገባው “ሪዝቅ” رِزْق ሲሆን አሏህ የሰጠንን ይህንን ሪዝቅ ስንሰጥ “ሲሳይን ሰጪ” እንባላለን፦
2፥3 *"ቁርኣን ለእነዚያ በሩቁ ነገር የሚያምኑ፣ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ እና "ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚቸሩ ለኾኑት መሪ ነው"* الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِالْغَيْبِ وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

"ሰጠናቸውም" ለሚለው ቃል የገባው "ረዘቅናሁም" رَزَقْنَاهُمْ ሲሆን የግስ መደብ ነው። አምላካችን አሏህ ከሰጠን ሪዝቅ ለሌላው ስንረዝቅ "ራዚቂን" رَّازِقِينَ እንባላለን፦
34፥39 *«ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል፥ ለእርሱም ያጠብባል፡፡ ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል፥ እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው» በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّ رَبِّي يَبْسُطُ الرِّزْقَ لِمَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ وَيَقْدِرُ لَهُ ۚ وَمَا أَنفَقْتُم مِّن شَيْءٍ فَهُوَ يُخْلِفُهُ ۖ وَهُوَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ

"ሲሳይ ሰጪዎች" የሚለው ይሰመርበት! "ራዚቅ" رَّازِق ማለት "ሲሳይን ሰጪ" ማለት ሲሆን የራዚቅ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ራዚቂን" رَّازِقِين ነው፥ አምላካችን አሏህ ደግሞ “አር-ረዛቅ” الرَّزَّاق ማለትም “ሲሳይን ሰጪ” ነው፦
51፥58 *"አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ هُوَ الرَّزَّاقُ ذُو الْقُوَّةِ الْمَتِينُ

በቁርኣን ከአሏህ ውጪ “አር-ረዛቅ” الرَّزَّاق የተባለ ማንም የለም፥ እርሱ "ሲሳይን ሰጪ" የተባለበት እኛ በተባልንበት ስሌትና ቀመር አይደለም። እኛ እርሱ የሰጠንን ስንሰጥ፥ እርሱ ግን ለሁሉም ሰጪ ሲሆን የሰጪዎች ሁሉ ሰጪ ነው። ከማንም ምንም ሲሳይ አይሻም፦
51፥57 *"ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም"፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም"*፡፡ مَا أُرِيدُ مِنْهُم مِّن رِّزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَن يُطْعِمُونِ
ሚሽነሪዎች ያነሱት ነጥብ፦ "እነዚያ ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም" ስለሚል ፍጡራን እንዴት "ሲሳይ ሰጪዎች" እንዴት ተባሉ? የሚል ነው፦
29፥17 *"ከአላህ ሌላ የምታመልኩት ጣዖት ነው፡፡ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፥ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፡፡ ስለዚህ ሲሳይን ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ፣ አምልኩት፣ ለእርሱም አመሰግኑ! ወደእርሱ ትመለሳላችሁ"*፡፡ إِنَّمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ أَوْثَانًا وَتَخْلُقُونَ إِفْكًا ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَا يَمْلِكُونَ لَكُمْ رِزْقًا فَابْتَغُوا عِندَ اللَّهِ الرِّزْقَ وَاعْبُدُوهُ وَاشْكُرُوا لَهُ ۖ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

"ከአላህ ሌላ የምታመልኩት ጣዖት ነው" የሚለው ኃይለ-ቃል አንባቢ ልብ ይለዋል። እዚህ አንቀጽ ላይ "ጣዖት" ለሚለው የገባው ቃል "አውሳን" أَوْثَان ሲሆን ከድንጋይ ተቀርፀው አምልኮ የሚቀርብላቸው ግዑዛን አካላት ናቸው፥ እነዚህ አካላት የማይናገሩና የማይሰሙ ስለሆኑ ሲሳይን ሊሰጡ አይችሉም፦
30፥40 *"አላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም የሚያሞታችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ነው። ከምታጋሯቸው ውስጥ ከዚህ ነገር አንዳችን የሚሠራ አለን? ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ"*፡፡ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَكُمْ ثُمَّ رَزَقَكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ۖ هَلْ مِن شُرَكَائِكُم مَّن يَفْعَلُ مِن ذَٰلِكُم مِّن شَيْءٍ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ግዑዛን ጣዖታት ሲሳይ ሰጪዎች ከተባሉት ሰዎች ጋር በይዘትም ሆነ በዓይነት በመንስኤም ሆነው በውጤት አይገናኙም፥ ከሚያጋሩት አውሳን ውስጥ የፈጠረ፣ የሚያሞትና ሕያው የሚያደርግ፣ ከሰማይ እና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጥ የለም፦
27፥64 *"ወይም ያ መፍጠርን የሚጀምር፣ ከዚያም የሚመልሰው፣ ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አምላክ ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? «እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ!» በላቸው"*፡፡ أَمَّن يَبْدَأُ الْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُ وَمَن يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۗ أَإِلَـٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

ሰዎችም ቢሆኑ ከሰማይ እና ከምድርም ሲሳይን መስጠት ስለማይችሉ ከአሏህ በቀር ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን ሰጪ አምላክ የለም፦
35፥3 *"እናንተ ሰዎች ሆይ! በእናንተ ላይ ያለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ! ከአላህ ሌላ ፈጣሪ አለን? ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አለን? ከእርሱ በስተቀር ሰጪ አምላክ የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ?"*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ ۚ هَلْ مِنْ خَالِقٍ غَيْرُ اللَّهِ يَرْزُقُكُم مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۚ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ

ማንበብና ማስነበብ፣ ማጥናትና ማስጠናት፣ መመርመርና ማስመርመር የኢሥላም ዋናው ጭብጥ ስለሆነ የሚነሱትን ጥያቄ ለማረቅ ረብጣ በሆነ መልስ እና በማያወላዳ መልኩ ማስገር ግድ ይላል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም