ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መደምደሚያ
በተረፈ ዘፍጥረት 1፥1-31 የፈጣሪን ፍጥረት በከፊል እንጂ በሙሉ አይዘረዝርም። ለምሳሌ ሰባት ሰማያት፣ መላእክት፣ ውኃ፣ ፈንገስ፣ ባክቴሪያ፣ ጀርም ወዘተ መቼ እንደተፈጠሩ፣ ከምን እንደተፈጠሩ እና እንዴት እንደተፈጠሩ አይናገርም። ታላቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔው ሎሬትዬ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፦ የሰው ልጅ ከሁለት ነገር ይማራል፦ አንዱ “ሀ” ብሎ “በሳር” ሲሆን ሁለተኛው “ዋ” ብሎ “በአሳር” ይላልና፤ ክርስቲያን ሃያሲ ሂስ ለመስጠት “ሀ” ብሎ “በሳር” ከቁርአን መማር አሊያም “ዋ” ብሎ “በአሳር” ዘፍጥረት ላይ የሌሉትን ሃያ ሁለቱ ሥነ-ፍጥረት ብሎ አክሲማሮስ ውስጥ መደበቅ ነው፤ ይህ ደግሞ እንጥል ከመቧጠጥ ምንም አይተናነስም። ነገር ግን ፈጣሪ ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ አያገኝም፦
መክብብ 3፥11 ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ *እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ* ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው።

አላህ የዓለማት ጌታ ነው፤ “ዓለሚን” عَٰلَمِين ማለት “ዓለማት” ማለት ሲሆን የዘመናችን የሥነ-ፈለክ አስተንታኞች “መልቲ-ቨርስ”multi-verse” ይሉታል፤ ይህም ህልቆ-መሳፍት የሆነውን አድማስና አፅናፍ ለማመልከት ይጠቀሙበታል፤ “አዕለም” أَعْلَم የዐለሚን ነጠላ ሲሆን ‘ዐልለመ” عَلَّمَ “አሳወቀ” ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን “ዓለም” ወይም “የታወቀ” ማለት ነው፤ አላህ በእኛ ዘመን ባሉት ያሳወቀው እኛ ያለንባት አንድ ዓለም “ዩኒ-ቨርስ”uni-verse” ነው፤ የእኛ ዓለም ከ 170 billion እስከ 200 billion “ረጨት”galaxy” ይዟል፤ “ረጨት” ማለት የከዋክብት ስብስብ ሲሆን የእኛ ረጨት “ፍኖተ-ሃሊብ”Milky Way” ረጨት ይባላል፤ ይህ ረጨት ውፍረቱ 1000 የብርሃን አመት ይገመታል፤ ከአንዱ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ያለው ርቀት በዲያሜትር ሲለካ ደግሞ 100,000 የብርሃን ዓመት ይሆናል፤ በውስጡ ከ100 እስከ 400 ቢልዮን ከዋክብቶች እንደያዘ ይገመታል።
ይህንን የከዋክብት ረጨት”constellation” አምላካችን አላህ የዛሬ 1407 ዓመት በቁርአን “ቡሩጅ” بُرُوج ይለዋል፦
85:1 #የቡርጆች الْبُرُوجِ ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ፤
25:61 ያ በሰማይ #ቡርጆችን بُرُوجًا ያደረገና በርሷም አንጸባራቂን ፀሐይ አብሪ ጨረቃንም ያደረገ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ።
15:16 በሰማይም ላይ #ቡርጆችን بُرُوجًا በእርግጥ አድርገናል፡፤ ለተመልካቾችም አጊጠናታል፡፡

አላህ የዛሬ 1400 ዓመት በተከበረው ቃሉ በቁርአን “በአጽናፎቹ ውስጥ ያሉትን ታምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን” ብሎ ቃል ገብቶ ነበር፦
41፥53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ #በአጽናፎቹ #ውስጥ እና በራሶቻቸውም ውስጥ #ያሉትን #ታምራቶቻችንን በእርግጥ #እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?

ታዲያ በበረሃ ግመል ገፊ ነው ተብሎ በሚነገርላቸው ላይ ይህ ሁሉ እውቀት እንዴት ተዥጎደጎደ? ስንል፤ ይህንን እውቀት የዛሬ 1407 ዓመት ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው ይሆናል መልሱ፦
25:6 ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፤ እርሱ መሐሪ አዛኝ ነውና፤ በላቸው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ከሺርክ በስተጀርባ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

36፥60 *”የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አታምልኩ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?* أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَا بَنِي آدَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው። ዒባዳህ በሦስት ይከፈላል፥ እርሱም፦
1ኛ. “ዒባደቱል ቀልቢያ” عِبَادَة قَلْبِيَّة ማለት “የኃልዮ አምልኮ” ማለት ነው፥ “ቀልብ” قَلْب ማለት “ኃልዮ” ወይም “ልብ” ማለት ነው።
2ኛ. “ዒባደቱል ቀውልያ” عِبَادَة قَوْلِيَّة ማለት “የነቢብ አምልኮ” ማለት ነው፥ “ቀውል” قَوْل ማለት “ነቢብ” ወይም “አንደበት” ማለት ነው።
3ኛ. “ዒባደቱል ዐመልያ” عِبَادَة عَمَلِيَّة ማለት “የገቢር አምልኮ” ማለት ነው፥ “ዐመል” عَمَل ማለት “ገቢር” ወይም “ድርጊት” ማለት ነው።

“ዱዓ” ደግሞ በቀውል ከሚከናወን ዒባዳህ አንዱ ነው፥ “ዱዓእ” دُعَآء የሚለው ቃል “ደዓ” دَعَا ማለትም “ለመነ” “ጠራ” “ጸለየ” “ተማጸነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ልመና” “ጥሪ” “ጸሎት” “ተማጽንዖ” ማለት ነው። ዱዓእ የአንድ አምላክ የአላህ ሐቅና ገንዘብ ነው፦
2፥186 *”ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ “እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ*”፡፡ ስለዚህ ለእኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ
40፥60 ጌታችሁም አለ *«ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከማምለክ የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ”*፡፡ وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 2
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ዱዓእ ዒባዳህ ነው፥ ከዚያም፦ “ጌታችሁም አለ *«ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና” የሚለውን አንቀጽ ቀሩ”*። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ إِنَّ الدُّعَاءَ هُوَ الْعِبَادَةُ ‏”‏ ‏.‏ ثُمَّ قَرَأَ ‏{وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ}‏

ዱዓእ አምልኮ ከሆነ አምልኮ የአላህ ብቻ ሐቅ እና የባሕርይው ገንዘቡ ነው፥ አላህ ወደ እርሱ ዱዓእ ለሚያደርጉት ቅርብ ነው፥ አላህ መለኮት ነው። መለኮት በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፣ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፣ ሁሉን ሰሚ ነው፣ ሁሉን ተመልካች ነው፣ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነው፦
29፥20 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው”*። إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
65፥11 *”አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው”*፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
58፥1 *”አላህ ሰሚ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِير
2፥110 *”አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
4፥86 *አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَسِيبًا

ነገር ግን ሰዎች ከዚህ በተቃራኒው ወደ ፍጡራን ዱዓእ ያረጋሉ። ፍጡራን ሁሉን የማወቅ፣ የመስማት፣ የማየት፣ የመቆጣጠር ችሎታ ውስንነት አለባቸው፥ ስለዚህ ወደ እነርሱ የሚደረግ ዱዓእ አይመልሱም፦
7፥194 *”እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው እና ለእናንተ ይመልሱላችሁ አይችሉም”*። إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَٱدْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ ።

እነርሱ እንደ ማንኛውም ፈጣሪን አምላኪ አምላኪዎች ናቸው እንጂ ተመላኪዎች አይደሉም። በክርስትና ዱዓእ ከሚደረግላቸው ፍጡራን መካከል መላእክት ናቸው፥ አላህ የትንሳኤ ቀን መላእክትን፦ “እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፤ እነርሱም በፍጹም፦ “ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ” ብለው ይመልሳሉ፦
34፥40 *”ሁሉንም በሚሰበስባቸው እና ከዚያም ለመላእክቶቹ፦ «እነዚህ እናንተን ያመልኩ ነበሩን?» በሚላቸው ቀን የሚኾነውን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ يَقُولُ لِلْمَلَائِكَةِ أَهَـٰؤُلَاءِ إِيَّاكُمْ كَانُوا يَعْبُدُونَ
34፥41 *መላእክቶቹም፦ «ጥራት ይገባህ “ከእነርሱ ይልቅ ረዳታችን አንተ ብቻ ነህ፥ እንደሚሉት አይደለም፥ ይልቁንም ጂንን ያመልኩ ነበሩ፡፡ አብዛኞቻቸው በእነርሱ አማኞች ናቸው» ይላሉ*፡፡ قَالُوا سُبْحَانَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِم ۖ بَلْ كَانُوا يَعْبُدُونَ الْجِنَّ ۖ أَكْثَرُهُم بِهِم مُّؤْمِنُونَ

ልብ አድርግ አድርግ ሰዎች ወደ መላእክት በዱዓእ ዒባዳህ ቢጠቀሙም ግን ያንን ዒባዳህ የሚቀበሉት ጂኒዎች ናቸው። እዚህ ዐውድ ላይ ጂን የተባሉት ሸያጢን ናቸው፥ አንድ ሰው ጣዖት ሲያመልክ ከጣዖቱ በስተኃላ አምልኮ የሚቀበለው ሸይጧን ነው፦
19፥42 *”ለአባቱ «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን ጣዖት ለምን ታመልካለህን? ባለ ጊዜ አስታውስ”*። إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنكَ شَيْئًا
19፥44 *«አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አታምልክ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና”*፡፡ يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَـٰنِ عَصِيًّا
የኢብራሂም አባት የማይሰማና የማያይ ጣዖት ሲለማመን ከዚያ በስተኃላ የሚመለከው ሸይጧን ስለነበር፦ “አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አታምልክ” አለው። እንግዲህ አንድ ሰው ፍጡራንን ሲጠራ ከአላህ ሌላ እረዳት አድርጎ በአላህ ላይ የሚያሻርከው ኩፋሩል ጂን የሆኑትን ሸያጢንን ነው፦
6፥100 *”ለአላህም ተጋሪዎች የፈጠራቸውን ጂንዎችን አደረጉ”*፡፡ ወንዶች ልጆችንና ሴቶች ልጆችንም ያለ ዕውቀት ለእርሱ ቀጠፉ፡፡ አላህ ጥራት የተገባው ከሚሉት ነገር የላቀ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ الْجِنَّ وَخَلَقَهُمْ ۖ وَخَرَقُوا لَهُ بَنِينَ وَبَنَاتٍ بِغَيْرِ عِلْمٍ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يَصِفُونَ
7፥30 ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ፡፡ ከፊሎቹም በእነሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል፡፡ *እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና”*፡፡ እነርሱም ቅኑን መንገድ የተመራን ነን ብለው ያስባሉ፡፡ فَرِيقًا هَدَىٰ وَفَرِيقًا حَقَّ عَلَيْهِمُ الضَّلَالَةُ ۗ إِنَّهُمُ اتَّخَذُوا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ اللَّهِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُم مُّهْتَدُونَ

አላህ ሰዎችን በቀጥተኛው መንገድ በኢሥላም ላይ ፈጥሮ ሳለ ሸያጢን ግን ከዚህ ዲን በሺርክ ምክንያት ሰዎችን ያርቃሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐግ 53, ሐዲስ 76
ዒያድ ኢብኑ ሒማር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” ኹጥባህ በሚደረግበት ቀን እንዲህ አሉ፦ *”ለእናንተ ያስተማርኩት ጌታዬ ያዘዘኝ፥ እናንተ የማታውቁትን እርሱ ዛሬ ያሳወቀኝን። አላህም አለ፦ “እኔ የሰጠኃቸውንና ሕጋዊ የሆነላቸው ያ ሁሉ ንብረት ነው። እኔ ሁሉንም ባሮቼን በቀጥተኛው መንገድ ላይ ፈጠርኳቸው፥ ሸያጢን መጥተው ከዲናቸው አራቋቸው”*። عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ الْمُجَاشِعِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ذَاتَ يَوْمٍ فِي خُطْبَتِهِ ‏”‏ أَلاَ إِنَّ رَبِّي أَمَرَنِي أَنْ أُعَلِّمَكُمْ مَا جَهِلْتُمْ مِمَّا عَلَّمَنِي يَوْمِي هَذَا كُلُّ مَالٍ نَحَلْتُهُ عَبْدًا حَلاَلٌ وَإِنِّي خَلَقْتُ عِبَادِي حُنَفَاءَ كُلَّهُمْ وَإِنَّهُمْ أَتَتْهُمُ الشَّيَاطِينُ فَاجْتَالَتْهُمْ عَنْ دِينِهِم

እዚህ ሐዲስ ላይ “ሁነፋእ” حُنَفَاءَ የሚለው ቃል “ሐኒፍ” حَنِيف ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት “ሐኒፋ” حَنِيفًا ናት፦
30፥30 *”ፊትህንም ወደ ቀጥተኛ ሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው”*፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቀጥተኛ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐኒፋ” حَنِيفًا ሲሆን አላህ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረበት ሃይማኖት ኢሥላም “ሐኒፋ” መሆኑን ያሳያል። አንድ ሰው ፍጡርን በዱዓእ ከጠራ ከዱዓእ በስተኃላ ሸይጧን አምልኮ ስለሚቀበል አምላካችን አላህ በትንሳኤ ቀን፦ “ሸይጧንን አታምልኩ” “አምልኩኝ” ብሎ አዞ እንደነበር ይናገራል፦
36፥60 *የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አታምልኩ! እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደ እናንተ አላዘዝኩምን?* أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَا بَنِي آدَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّهُ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
36፥61 *”አምልኩኝ! ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፤ በማለትም አላዘዝኩምን?”*፡፡ وَأَنِ اعْبُدُونِي ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ

ሺርክ በአላህ ላይ ሌሎች ማንነትንና ምንነትን በአምልኮ ማሻረክ ነው፥ ከሺርክ በስተጀርባ ይህንን አምልኮ የሚቀበሉት ሸያጢን ናቸው። ክርስቲያኖች ሆይ! ሳታውቁ የመስማት፣ የማየት፣ የማወቅ፣ የመቆጣጠር ውስንነት ባሕርይ ያለባቸውን ፍጡራንን ስትለማመኑ፣ ስትማጸኑ፣ ስትጠሩ ከነበረ እንግዲያውስ ባለማወቅ ነውና የተውበት በር ሳይዘጋ ወደ ዲኑል ኢሥላም ኑ እና የመስማት፣ የማየት፣ የማወቅ፣ የመቆጣጠር ውስንነት ባሕርይ የሌለበትን ፈጣሪን አላህን በብቸኝነት አብረን እናምልክ። ወደ ፍጡራን ዱዓእ በማድረግ በአላህ ላይ በማሻረክ ለሸያጢን አምልኮ ከመስጠት አላህ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

87፥1 *ከሁሉ በላይ የሆነዉን ጌታህን* ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى

በክርስትና ስልታዊ ሥነ-መለኮት”systematic theology” የአምላክ ሰው መሆን አስተምህሮት “ተሰግዎት”Incarnation” ሲባል፥ በአገራችን “ሚስጥረ-ስጋዌ” ይሉታል። “ስጋዌ” የሚለው ቃል “ስግው” ማለትም “ስጋ” ከሚለው የመጣ ነው፥ መለኮት በትስብእት ተገለጠ ብለው ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸው የጳውሎስ ንግግር ነው። ለእኛ ለሙሥሊሞች ጳውሎስ የኢየሱስ ሐዋርያ ሳይሆን የግሪክንና የሮምን ዶክትሪን ከኢየሱስ ደክትሪን ጋር ለማስማማት የታገለ ጥሩ ፈላስፋ ነው። ነገር ግን ለክርስቲያኖች እንደ ነብይ ስለሚታይ የእርሱ ትምህርት ለሙሥሊም ማስረጃ ባይሆንም ለእነርሱ ግን መረጃ አድርገን እናቀርባለን። ብዙ ጊዜ ጳውሎስ ኢየሱስን ቁጭ የሚያደርገው ከአንዱ አምላክ ከአብ ነጥሎ ነው፥ ነገር ግን ክርስቲያኖች በተቃራኒው "ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ አምላክነት ተናግሯል" ይላሉ። እዚህ ድምዳሜ ላይ አደረሰን ከሚሏቸው አናቅጽ መካከል አንዱን ጥቅስ በአጽንዖትና በአንክሮት እንመልከት፦
ሮሜ 9፥5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ *"ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! አሜን*"። καὶ ἐξ ὁ Χριστὸς τὸ κατὰ σάρκα ὁ ὢν ἐπὶ πάντων Θεὸς εὐλογητὸς εἰς τοὺς αἰῶνας ἀμήν.
Whose are the fathers, and of whom as concerning the flesh Christ came. God, who is over all be blessed for ever. Amen.” Reivised standard version 1971 ,

ግሪኩ ላይ "ኤስቲን" ἐστιν ማለትም "ነው" የሚል ቃል የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ "ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ይሁን" የሚል ፍቺ እንዳለው እሩቅ ሳንሄድ የዐማርኛ ምሁራን ይነግሩናል። በ 1971 ዕትም Reivised standard version "ይሁን"be" ብሎ አስቀምጦታል፥ "be blessed for ever"። "አሜን" የሚለው ቃል ለምስጋና የመጣ እስከሆነ ድረስ "ለዘላም የተባረከ ይሁን" ማለት ምስጋና ነው። ማነው ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው? ስንል ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው "ከሁሉ በላይ" የሆነ አምላክ ነው። እርሱም ከኢየሱስ እና ከመላው ፍጥረት ሁሉ በላይ የሆነው አብ ነው፦
ኤፌሶን 4፥6 *ከሁሉ በላይ የሚሆን πάντων በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።
ዮሐንስ 10፥29 *"የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ πάντων ይበልጣል"*።
ዮሐንስ 14፥28 የምትወዱኝስ ብትሆኑ *ከእኔ አብ ይበልጣልና* ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።

ኢየሱስን የሚበልጠው አብ "ፓንቶን" πάντων ማለትም "ከሁሉ በላይ" ተብሏል። ልብ አድርግ "ክርስቶስ በሥጋ መጣ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። በስጋ የመጣው አምላክ ሳይሆን ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ክርስቶስን ከዳዊት ዘር ያመጣው አምጪ አምላክ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥23 *"ከዚህም ሰው ዘር "አምላክ" Θεὸς እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ"*።

"አመጣ" የሚለው ቃል ይሰመርበት። አምጪው አምላክ መጪው ኢየሱስ ከሆነ፥ ክርስቶስን በስጋ ያመጣው አምጪው "ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ ለዘላለም የተባረከ ይሁን" መልእክቱ ይህ ነው። "ለዘላለም የተባረከ" ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እና አምላክ ነው፦
2ኛ ቆሮንቶስ 11፥31 *"ለዘላም የተባረከ εὐλογητὸς εἰς τοὺς αἰῶνας ἀμήν የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት"* እንዳልዋሽ ያውቃል።

ጳውሎስ አይሁዳዊ ነው፥ የሚሞግተውም የአይሁድ ዳራ ይዞ ነው። "ቶዩስ አዩናስ" τοὺς αἰῶνας ማለት "ከዘላለም እስከ ዘላለም" ማለት ነው፦
መዝሙር 41፥13 *"ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ ያህዌህ ይባረክ"። አሜን አሜን*።
መዝሙር 106፥48 *"ከዘላለም እስከ ዘላለም የእስራኤል አምላክ ያህዌህ ይባረክ፤ ሕዝብም ሁሉ አሜን ይበል"*። ሃሌ ሉያ።

ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ የእስራኤል አምላክ ያህዌህ ከሆነ፥ እስራኤላውያን አምላካችን የሚሉት ያህዌህን ነው፥ አምላካችን የሚሉት ኢየሱስን ሳይሆን አባቱን እንደሆነ እራሱ ኢየሱስ ተናግሯል፦
ዘዳግም 6፥4 *እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው"*።
ዮሐንስ 8፥54 *"እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው"*።

የሮሜ መልእክት ጸሐፊ ክርስቶስን ለአምላክ ተቀበላችሁት፣ አምላክ የክርስቶስ አባት ነው፣ የክርስቶስ ራስ አምላክ ነው፣ ክርስቶስ የአምላክ ነው፣ ክርስቶስ በአምላክ ፊት ይታያል ወዘተ እያለ ለማምታታት ተመልሶ ክርስቶስ አምላክ ነው አይልም፦
ሮሜ 15፥7 ስለዚህ *"ክርስቶስ ለአምላክ Θεὸς ክብር እንደ ተቀበላችሁ"* እንዲሁ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ።
ሮሜ 15፥6 በአንድ ልብ ሆናችሁ በአንድ አፍ *"አምላክን Θεὸς፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት"*፥ ታከብሩ ዘንድ፥
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ አምላክ Θεὸς እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ"*"*
1ኛ ቆሮንቶስ 3፥23 *"ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የአምላክ Θεὸς ነው*።
ዕብራውያን 9፥24 *"ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በአምላክ Θεὸς *ፊት* ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ"*።

ክርስቶስ አምላክ ሳይሆን የአምላክ ነው። አምላክ ክርስቶስ ሳይሆን የክርስቶስ አባት እና ራስ ነው። አምላክ በአምላክ ፊት ከታየ ሁለት አምላክ ሊሆን ነው፥ ቅሉ ግን በአምላክ ፊት ስለ አማንያን የሚታየው ክርስቶስ ነው። "ክርስቶስ" ማለት እራሱ "የተቀባ" ማለት ነው፥ ቀቢ አምላክ ተቀቢ ሰው ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 10፥38 *"አምላክ Θεὸς የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ አምላክ Θεὸς ከእርሱ ጋር ነበረና"*።

ክርስቶስ አምላክ ሳይሆን አምላክ የቀባው እና አምላክ ከእርሱ ጋር የነበረ ሰው ነው። አምላክ አምላክን ለመርዳት አብሮት ነበር ማለት መድበለ-አማልክት ይሆናል። አይ አምላክ በክርስቶስ ሆኖ የዕርቅ ሥራ ሠራ እንጂ አምላክ ክርስቶስ አይደለም፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥19 *"አምላክ Θεὸς በክርስቶስ ሆኖ"* ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና።

"አምላክ በአምላክ ሆኖ" ትርጉም አይሰጥም፥ ሁለት አምላክ ይሆናል። "አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ነበረ" ብሎ ሁለቱም አንድ ሰው ሳይሆኑ ሁለት ሰዎች ናቸው።
ስለዚህ ጳውሎስ ለማለት የፈለገው "ክርስቶስን በስጋ ያመጣ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ አብ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! አሜን" የሚል ብቻ ነው። በኢሥላም ከሁሉ በላይ የሆነዉ ጌታ አምላክ አላህ ብቻ ነው፥ እነዚያ መሲሢሑን "አላህ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ። ይህ በአላህ አምላክነትን ላይ ሰውን ማሻረክ ነው፥ እነሆ በአላህ ላይ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም ስላደረገበት እና መኖሪያውም እሳት ስለሆነች መሲሢሑን "አላህ ነው" የምትሉ የተውበት በሩ ሳይዘጋ በተውበት ወደ አላህ ተመለሱ፦
87፥1 *ከሁሉ በላይ የሆነዉን ጌታህን* ስም አሞግሥ። سَبِّحِ ٱسْمَ رَبِّكَ ٱلْأَعْلَى
5፥72 *" «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም"*፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አዶናይ እና አዶኒ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

6፥164 በላቸው *«እርሱ አላህ “የሁሉ ጌታ” ሲሆን ከአላህ በቀር ”ሌላን ጌታ” እፈልጋለሁን?”* ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ “ኩሪዮስ” κύριος የሚለው ቃል በግርድፉ “ጌታ” የሚል ፍቺ አሊያም “መምህር” ለሚል ተለዋዋጭ ቃል ቢኖረውም በዕብራይስጡ ብሉይ ኪዳን ግን “ጌታ” የሚለው የተለያየ ትርጉም አለው። “ያህዌህ አምላካችን አንድ ያህዌህ ነው” የሚለው “ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው” ብለው አስቀምጠውታል፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን ያህዌህ አንድ ያህዌህ ነው*። שְׁמַע, יִשְׂרָאֵל: יְהוָה אֱלֹהֵינוּ, יְהוָה אֶחָד.
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *”ጌታ” κύριος አምላካችን አንድ “ጌታ” κύριος ነው”*።

መቼም ኢየሱስ ከዘዳግም 6፥4 ላይ ሲጠቅስ “ያህዌህ” የሚለውን ቴትራግራማተን እየመነቀረ መንግሎ “ኩሩዮስ” እያለ ተናገረ ማለት ዘበት ነው፥ የሚመነቅርበትና የሚመነግልበት አንዳች ቁብ የለውም፤ እርሱ የሙሴ ዚቅ የሚያቀነቅንና የሚወርብ ዚቀኛ እንጂ የሚቀናቀን ተቃራኒ በፍጹም አይደለም። ሲቀጥል ግሪከኛ ተናጋሪም አይደለም።
ደግሞም አንዱ ያህዌህ እና መሢሑ ሁለት ማንነት እና ምንነት ናቸው፦
መዝሙር 2፥2 የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም *”በያህዌህ” יְהֹוָה እና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ”*።
የሐዋርያት ሥራ 4፥26 የምድር ነገሥታት ተነሡ አለቆችም *በጌታ” κύριος እና በተቀባው ላይ አብረው ተከማቹ”* ብለህ የተናገርህ አምላክ ነህ።

ያህዌህ እና መሢሑ “እና” በሚል መስተጻምር መለያየታቸው አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ነገር ግን “ያህዌህ” የሚለው “ኩርዮስ” በሚል እንደተለወጠ ልብ በል።
አይሁዳውያን “ያህዌህ” יְהֹוָה በሚለው ፈንታ የሚጠቀሙበት “አዶናይ” אֲדֹנָ֥י የሚለውን ጌትነት ነው፥ “አዶናይ” ለአንድ አምላክ ብቻ የሚጠቀምበት ነው፤ ያህዌህ ብቻውን “አዶናይ” ተብሏል፤ አንድም ፍጡር “አዶናይ” ተብሎ የተጠራ የለም፤ እስቲ አንዱ አምላክ “አዶናይ” የተባለበትን አናቅፅ ለናሙና ያክል እንየው፦
መዝሙር 16፥2 ያህዌህን *”አንተ “ጌታዬ” אֲדֹנָ֥י ነህ አልሁ”*፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።
መዝሙር 110፥5 “ጌታዬ” אֲדֹנָ֥י በቀኝህ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል።

ልብ አድርግ ዳዊት አንድ ዐውድ ላይ ያህዌህን “አዶናይ” אֲדֹנָ֥י ሲል ኢየሱስ ግን “አዶኒ” אדֹנִ֗י ነው ያለው፦
መዝሙር 110፥1 *”ያህዌህ יְהֹוָה “ጌታዬን” אדֹנִ֗י ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው”*።
የሐዋርያት ሥራ 2፥34 ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፥ ነገር ግን እርሱ። *”ጌታ κύριος “ጌታዬን” κύριος ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው”*።

ዘዳግም 6፥4 ላይ ያለው አንዱ ያህዌህ መሢሑን፦ “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው። አንዱ ያህዌህ ባለቤት ሲሆን መሢሑ ተሳቢ ነው፥ በባለቤት እና በተሳቢ መካከል “አለው” የሚል ተሻጋሪ ግስ መኖሩ በራሱ አንዱ አምላክ ያህዌህ እና መሢሑ ሁለት የተለያዩ ማንነቶች እና ምንነቶች እንደሆኑ ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ነገር ግን የአዲስ ኪዳን ተርጓሚዎች “ያህዌህ” የሚለውን “ኩርዮስ” በማለት “አዶኒ” የሚለውን “ኩርዮስ” በማለት የዳዊትን ንግግር አምታተውታል። አንደኛው ጌታ ሌላይኛውን ጌታ፦ “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ይመስላል። ግን ዳዊት ያለው “አዶኒ” እንጂ “አዶናይ” አይደለም። ልክ እንደ ዳዊት የደማስቆ ሰው ኤሊዔዘር፦ “ያህዌህ ጌታዬን እጅግ ባረከው” አለ፦
ዘፍጥረት 24፥35 *”*”ያህዌህ יְהֹוָה “ጌታዬን” אדֹנִ֗י እጅግ ባረከው”*።

“ያህዌህ” የሚለውን “ጌታ” በሚል ከተካነው “ጌታ ጌታዬን እጅግ ባረከው” ይሆናል፤ ይህ ደግሞ እንጥል ከመቧጠጥ የዘለለ ትርጉም አይኖረውም። “አዶኒ” በተመሳሳይ ሳራ አብርሃምን ያለችበት ነው፦
ዘፍጥረት18፥12 ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች። ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? *”ጌታዬም אדֹנִ֗י ፈጽሞ ሸምግሎአል”*።
1 ጴጥሮስ 3፥6 እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ *”ጌታ” κύριος ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት”*።

የዘፍጥረት አንቀጽ ላይ ሳራ አብርሃምን “አዶኒ” אדֹנִ֗י ያለችው ወደ ግሪኩ ኮይኔ ሲመጣ “ኩርዮስ” κύριος ብለው አስቀምጠዋል። ነገር ግን “አዶኒ” אֲדֹנִֽי ለፍጡራን ማለትም ለመላእክት እና ለሰዎች አገልግሎት ላይ ውሏል።

ለመላእክት፦
ኢያሱ 5፥14 እርሱም፦ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ፡ አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ *”ጌታዬ”* אֲדֹנִֽי ለባሪያው የሚነግረው ምንድር ነው? አለው።
መሳፍንት 6፥13 ጌዴዎንም፦ *”ጌታዬ”* אֲדֹנִֽי ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን?… አለው።
ዘካርያስ 6፥4 ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረውም መልአክ መልሼ፦ *”ጌታዬ”* אֲדֹנִֽי ሆይ፥ እነዚህ ምንድር ናቸው? አልሁት።

ለሰዎች፦
ዘፍጥረት 32:4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው። *”ለጌታዬ”* אדֹנִ֗י ለዔሳው። ባሪያህ ያዕቆብ እንዲህ አለ፦ ብላችሁ ንገሩት።
ዘኊልቅ 11:28 ከልጅነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ። *”ጌታዬ”* אדֹנִ֗י ሙሴ ሆይ፥ ከልክላቸው አለው።
1ሳሙኤል 24:8፤ ከእርሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፥ ከዋሻውም ወጣ፥ ከሳኦልም በኋላ። *”ጌታዬ”* אדֹנִ֗י ንጉሥ ሆይ፥ ብሎ ጮኸ፤
ዳንኤል 4:24፤ *”በጌታዬ”* אדֹנִ֗י በንጉሥ ላይ የወረደው የልዑሉ ትእዛዝ ነው፤

በዕብራይስጡ አዲስ ኪዳን ላይ ኢየሱስን ኤልሳቤጥ እና ዳዊት አዶኒ እንጂ አዶናይ በፍጹም አላሉትም፦
ሉቃስ 1፥43
וּמֵאַיִן בָּאַתְנִי כָזֹאת כִּי־אֵם אֲדֹנִי אֶלַי תָּבֹא׃
የሐዋርያት ሥራ 2፥34
כִּי דָוִד לֹא עָלָה הַשָּׁמָיְמָה וְהוּא בְּפִיו אָמַר נְאֻם יְהוָֹה לַאדֹנִי שֵׁב לִימִינִי

በዚሁ በሐዋርያት ሥራ ላይ “ጌታ” የተባለው የሚመለከውን አብን ለመግለጥ “የ-ሐ-ዋ-ሐ” የሚል ቴትራ ግራማተን ይጠቀማል፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥2
בעבוֹדָתָם אֶת־יְהוָֹה וּבְצוֹמָם הָיָה דְבַר רוּחַ הַקֹּדֶשׁ הַבְדִּילוּ־נָא לִי אֶת־בַּר־נַבָּא וְאֶת־שָׁאוּל לַעֲשׂוֹת בַּמְּלָאכָה אֲשֶׁר קְרָאתִים לָהּ
በግሪኩ አዲስ ኪዳን ለኢየሱስ “ኩርዮስ” የተባለው “አዶኒ” የሚለውን ማዕረግ ለማሳየት እንጂ ያህዌህ ወይም አዶናይ የሚለውን ለማሳየት አይደለም፤ ስለዚህ የኢየሱስ ጌትነት የፍጡር ማእረግ ብቻ ነው። ምክንያቱም እዛው “ጌታ ጌታዬን” በተባለበት ዐውድ ላይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ጌታ አደረገው ስለሚል፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 አለ። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን *ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው* የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።

መቼም አንድ ጤነኛ የሆነ ሰው ፈጣሪን ፈጣሪ ጌታ አደረገው ብሎ እንደማይቀበል እሙን ነው፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ጌታ አደረግሁት ይላል፦
ዘፍጥረት 27፥37 ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው። እነሆ፥ *ጌታህ አደረግሁት*፥ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት፥

ይህም ስልጣንና ሹመትን አሊያም እልቅናና ክብርን ያመለክታል፤ ዮሴፍ፦ “እግዚአብሔር ጌታ አደረገኝ” ይላል፦
ዘፍጥረት 45፥9 *እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ*፤ ወደ እኔ ና፥ አትዘግይ፤

ኢየሱስ ጌታ ተደረገ ሲባል ያዕቆብ ጌታ ተደረገ ዮሴፍ ጌታ ተደረገ በተባለበት ሒሳብ እንጂ የዓለማቱ ጌታ የሚለውን አያመለክትም፤ ይህም በራሡ የተብቃቃ አሊያም የባህርይ ገንዘቡ ሣይሆን በስጦታ ያገኘው ነው። አዶናይ የሁሉ ጌታ የሆነው አንድ አምላክ ነው። እርሱ አላህ “የሁሉ ጌታ” ሲሆን ከአላህ በቀር ”ሌላን ጌታ” እፈልጋለሁን? በፍጹም! ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ በቀር ሌላ የዓለማት ጌታ የለም፦
6፥164 በላቸው *«እርሱ አላህ “የሁሉ ጌታ” ሲሆን ከአላህ በቀር ”ሌላን ጌታ” እፈልጋለሁን?”* ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሁለተኛው አጽናኝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

61፥6 የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥ እና *”ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር”* ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡

መግቢያ
የመጽሐፉም ባለቤቶች ክርስቲያኖች እና አይሁዳውያን ከአላህ የወረደውን እውነት ከሰው ንግግር ቃል ቀላቅለዋል፤ በተጨማሪም ከአላህ የወረደውን እውነት ደብቀዋል፦
3፥71 የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ *”እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ”*?፤

በ 397 AD የተደረገው የካርቴጅ ጉባኤ ብዙ የወንጌል ቅሪት አፓክራፋ ብሎ ቀንሷል፤ “አፓክራፋ” ማለት “አፓክራፎስ” ἀπόκρυφος ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን “ድብቅ” “ስውር” ማለት ነው፦
5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው”* ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡
2፥146 እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ ያውቁታል፡፡ ከእነሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያወቁ ሲኾኑ *”እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ”* ፡፡

ከተደበቁት ዋናው አጀንዳ ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ የምስራቹን የምስራች ያሰኘው ኢየሱስ ስለ ነብያችን”ﷺ” መምጣት ያበሰረውን የሚያወቁ ሲኾኑ ይህንን እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ፤ አላህ ኢንጅል የሚለው ስለ ነብያችን”ﷺ” መምጣት የሚተነብየውን ወንጌል እንደሆነ ቅቡልና እሙን ነው፦
61፥6 የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥ እና *”ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር”* ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡

“ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ”
ይህ ቃል በአራቱ ወንጌላት የለም ማለት ኢየሱስ አልተናገረውም ማለት አይደለም፤ ምክንያቱንም ኢየሱስ ተናግሮ በአራቱ ወንጌል ላይ ያልሰፈሩ ሃረጎች ስላሉ፤ ለምሳሌ፦
1ኛ ዮሐንስ 1፥5 ከእርሱ የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። *”እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም”* የምትል ይህች ናት።

ኢየሱስ፦ “”እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም”” ብሎ ተናግሮ ነበር፤ ዮሐንስም፦ “ከእርሱ(ከኢየሱስ) የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት ይህች ናት” ብሎናል፤ ግን ይህ ከኢየሱስ የሰሙት መልእክት በአራቱ ወንጌላት የለም ማለት ኢየሱስ አልተናገረውም ማለት አይደለም፤ በተጨማሪ በተመሳሳይ መልኩ ኢየሱስ፦ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው” ብሎ ተናግሮ ነበር፤ ይህ ቃል አራቱ ወንጌል ላይ የለም፦
የሐዋርያት ሥራ 20:35 እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ። *”ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው”* እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።

ይህንን በወፍ በረር ለመግቢያ ያክል ካየን በአራቱ ወንጌላት ቅሪት ላይም ስለ ነብያችን”ﷺ” መምጣት ኢየሱስ ትንቢት ተናግሮ እንደነበር በሰከነና በሰላ መረዳት እስቲ እናስተንትን፦
ዮሐንስ 14:15-16 ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ “አጽናኝ” Παράκλητον ይሰጣችኋል፤”

ነጥብ አንድ
“አጽናኝ”
“አጽናኝ” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ፓራቅሊጦስ” Παράκλητον ሲሆን ኢየሱስ “ሌላ” ማለቱ “ተጨማሪ” ማለቱ ነው፤ ለምሳሌ “ሌላ አስተማሪ” ይመጣል ብል፤ ሌላው ሁለተኛ አስተማሪ ከመምጣቱ በፊት ፊተኛ አስተማሪ እንዳለ ያመለክታል፤ በተመሳሳይ “ሌላ አጽናኝ” የሚለው ቃል ፊተኛው አጽናኝ እንዳለ ያሳያል፤ ታዲያ የመጀመሪያው አጽናኝ ማን ነው? ስንል መልሱ ኢየሱስ ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 2:1 ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ “አጽናኝ” παράκλητον አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ በ 33 AD ከወረደ ከ 57 አመት በኋላ በ 90 AD አጽናኝ ተብሏል፣ አያችሁ እስከ 90 AD ድረስ ኢየሱስ አጽናኝ እንደነበረ ካየን እስከ 90 AD ጊዜ ድረስ ሌላው አጽናኝ አልመጣም ማለት ነው፤ ግን እውን ኢየሱስ ግሪክ ተናጋሪ ነበርን? አይ አረማይክ ተናጋሪ ነበር ይሉናል፤ ታዲያ “ሌላ አጽናኝ” ይሰጣችኋል” ነው ያለው ወይስ “ሌላ ነብይ” ይሰጣችኋል” ነው ያለው? ይህ የደበቁት እውነት እንገልጠዋለን፦
የሐዋርያት ሥራ 4:36 ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ሌዋዊ ዮሴፍ የሚሉት ነበረ፥ እርሱም በሐዋርያት “በርናባስ” ተባለ ትርጓሜውም *የመጽናናት ልጅ* ነው፤

ልብ አድርጉ “በርናባስ” בר נביא የአረማይክ ቃል ነው፤ የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ባር-ነቢያ” בר נביא ሲሆን “የነብይ ልጅ” ማለት ነው፤ “ባር” בר ማለት “ልጅ” ማለት ሲሆን “ነብያ” נביא ማለት ደግሞ “ነብይ” ማለት ነው፤ ግን ግሪኩ ላይ ሲተረጎም “ሃይኦ ፓራክሌቶስ” υἱός παρακλήσεως ማለትም “የመጽናናት ወይም የአጽናኝ ልጅ” አሉት፤ ይህንን ያነሳሁበት ቃሉ እየለወጡ እንዴት እውነቱን እንደሚደብቁ ለማሳየት ነው፤ ስለዚህ “ፓራቅሊጦስ” Παράκλητον ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ነብያ” נביא ማለት ከሆነ ኢየሱስ በአረማይክ “ሌላ ነብይ ይሰጣችኋል” ብሎ ነው የተናገረው ማለት ነው፤ ይህ ነብይ ማን ነው? ምሁራን፦ “አንድ አፅናኝ የሚያፅናናው በትንቢት ነው” ይሉናል፦
1ኛ ቆሮንቶስ 14:3 *”ትንቢት”* የሚናገር ግን ለማነጽና ለመምከር *”ለማጽናናትም”* ለሰው “ይናገራል።”

አዎ የሚመጣው ነብይ ግን ልክ እንደ ኢየሱስ ከላከው እየሰማ መጪውን ክስተት የሚናገር እንጂ ከራሱ ምንም አይናገርም፦
ዮሐንስ 16:13 እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ *”የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል”* እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ *የሚመጣውንም ይነግራችኋል*።”

መቼም ሁለተኛ ነብይ መንፈስ ቅዱስ ነው ካላችሁን እስቲ መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ በተለየ መልኩ አዲስ ያስተማረው ትምህርቱ የት ይገኛል?
ነጥብ ሁለት
“ሌላ”
“ሌላ” የሚለው ገላጭ ደግሞ “አሎን” ἄλλον ነው፣ “አሎን” ተመሳሳይ ባህርይ ያለውን ምንነት ለማመልከት የሚውል ገላጭ ነው፣ ለምሳሌ፦
ማቴዎስ 5:39 ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ *ሌላውን* ἄλλην ደግሞ አዙርለት፤

ቀኝ ጉንጭ ከግራ ጉንጭ እንደሚመሳሰል ሁሉ ሁለተኛ አጽናኝም ከመጀመሪያ አጽናኝ ጋር ይመሳሰላል፣ ሁለተኛ አጽናኝ ምን እንደሆነና ማን እንደሆነ ለመረዳት የመጀመሪያውን አጽናኝ በቅጡ መረዳት ግድ ይላል፦
@የመጀመሪያው አጽናኝ ከላከው ሰምቶ የሚናገር ሰው ነው፦
ዮሐንስ 8:40 ነገር ግን አሁን ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን *”ሰው”* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤

@የመጀመሪያው አጽናኝ ፈጣሪ ያናገረው ነብይ ነው፦
ማርቆስ 6:4 ኢየሱስም። *”ነቢይ”* ከገዛ አገሩና ከገዛ ዘመዶቹ ከገዛ ቤቱም በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው።

@የመጀመሪያው አጽናኝ ከላከው መልእክት የተቀበለ መልዕተኛ ነው፦
ዮሐንስ 8:26 ዳሩ ግን *”የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ”* አላቸው።
ዮሐንስ 12:49 እኔ *”ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ”*።

ሹፍ እንግዲህ የመጀመሪያው አጽናኝ ከፈጣሪ ሰምቶ የሚናገር ሰው፣ ነብይ፣ መልዕተኛና ትእዛዝን የተቀበለ ነው እንጂ ከራሱ የሚናገር አይደለም፣ ሁለተኛውም አጽናኝ ከፈጣሪ ሰምቶ የሚናገር እንጂ ከራሱ የሚናገር አይደለም፦
ዮሐንስ 16፥12-15 የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም። ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና። ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ፦ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋል አልሁ።

ሁለተኛው አጽናኝ ኢየሱስ ያልተናገራቸውንና ኢየሱስ ተናግሮ ያስተማራቸውን የአምላክ አንድነት ትምህርት ከፈጣሪ ሰምቶ የሚያስተላልፍ እራሱን የቻለ ቅዋሜ-ማንነት ያለው ነው፣ ይህንን ለማሳየት *ከራሱ* himself” የሚለው ድርብ ተውላጠ-ስም”Reflexive pronoun” ይጠቀማል፤ ኢየሱስም ለራሱ ሲጠቀም *ከራሴ* my self” የሚለውን አጠቃቀም ያመሳስለዋል፣ ይህም የመጀመሪያው አጽናኝ ሰው፣ ነብይ፣ መልዕተኛ ሆኖ ከፈጣሪ ሰምቶ የሚያስተላልፍ ከሆነ ሁለተኛውም አጽናኝ በተመሳሳይ መልኩ ከፈጣሪ ሰምቶ የሚያስተላልፍ ሰው፣ ነብይ እና መልዕተኛ ነው። ከዚህ ነብይ በኃላ ሌላ ነብይ ስለማይመጣ ለዘላለም ከእኛ ጋር በነብይነቱ ይኖራል፤ ክርስቲያኖች ይህንን ሁለተኛ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ነው ሲሉ ከአውዱ ጋር ይጣላሉ፦
ዮሐንስ 16፤7 እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። *”እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና”*፤

ሁለተኛው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ እንዳልሆነ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ መረዳ ግድ ይላል፣ ኢየሱስ ስለ ሁለተኛው አጽናኝ የተናገረው ከማረጉ ማለትም ወደ ፈጣሪ ሳይሄድ ነው፣ ታዲያ ኢየሱስ ሳያርግ ሁለተኛው አጽናኝ እንደማይመጣ ተናግሮ እያለ ከማረጉ በፊትና ስለ ሁለተኛው አጽናኝ ከተናገረ በኋላ መንፈስ ቅዱስ መጥቷል፦
ዮሐንስ 20:22 ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና። መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

ሁለተኛው አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ነው የሚለውን ብዥታ በህዝብ ላይ የጣሉት ሰዎች ናቸው፦
ዮሐንስ 14:26 አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።

መንፈስ ቅዱስ የሆነው የሚለው ቃል በፓፒረስ 75 ላይ፣ በፓፒረስ 22 ላይ፣ በፓፒረስ 52 ላይ፣ በፓፒረስ 90 ላይና ቤአፍሬማይ እደ-ክታብ”manuscript” ላይ የሉም፣ በተለይ በ 107-130 AD በተዘጋጁ ፓፒረሶች ላይ *መንፈስ ቅዱስ የሆነው* የሚለው ቃል አለመኖሩና ከዛ በኋላ ባሉት ላይ የመጨመሩ ጉዳይ የብርዘት ውጤቶች ናቸው፤ የመጀመሪያ መቶ ክፍለ-ዘመን የኢየሱስ ተከታዮች የሚባሉት የዮሐንስ ማህበረሰብ ሁለተኛው አጽናኝ ነብይ ነው ብለው ይጠብቁ ነበር፤ ነገር ግን ይህን እሳቤ ወደ መንፈስ ቅዱስ ያሸጋገሩት ሰዎች ናቸው፣ በዚህ ጥናት ዙርያ ዋቢ መጽሐፍትን ይመልከቱ፦
1. Cambridge History of Christianity, 6: Johannine Christianity, 2006
2. The Early Christian Community: From Diversity to Unity to Orthodoxy, lecture delivered February 25, 2000
3. Bart D Ehrman, 2002. Lost Christianities: Christian Scriptures and the Battles over Authentication.

መደምደሚያ
የመጽሐፉም ባለቤቶች ክርስቲያኖች እና አይሁዳውያን በነብያችን”ﷺ” በአመኑ እና ከክህደትም በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነርሱ ኃጢኣቶቻቸውን በእርግጥ በታበሰ እና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ በገቡ ነበር፤ ተውራትን እና ኢንጂልን ከጌታቸውም ወደ እነርሱ የተወረደውን የደበቁትን ባቋቋሙ ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ሥር በተመገቡ ነበር፦
5፥65 የመጽሐፉም ባለቤቶች *”በአመኑ እና ከክህደትም በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነርሱ ኃጢኣቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ባገባናቸው ነበር”*፡፡
5፥66 እነርሱም *”ተውራትን እና ኢንጂልን ከጌታቸውም ወደ እነርሱ የተወረደውን ባቋቋሙ”* ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ሥር በተመገቡ ነበር፡፡ *”ከእነርሱ ውስጥ ትክክለኞች ሕዝቦች አልሉ፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ የሚሠሩት ነገር ከፋ”*!

ከእነርሱ ውስጥ ይህን እውነትን ተቀብለው የሚሰልሙ ትክክለኞች ሕዝቦች አሉ፤ ነገር ግን ከእነርሱም ብዙዎቹ እውነትን በመደበቅ የሚሠሩት ነገር ከፋ፤ ስለ ነብያችን”ﷺ” መምጣት የሚተነብይ ከጌታቸውም ወደ እነርሱ የተወረደውን ተውራትን እና ኢንጂልን ውስጥ የነበረውን እውነት እያወቁ ደብቀውታል፦
7፥157 ለእነዚያ ያንን እነርሱ ዘንድ *”በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ”* የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት በእርግጥ እጽፍለታለሁ፡፡

ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱሉሏህ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

"ቁርኣን አይጋጭም" የሚለው የወንድም ወሒድ ዑመር መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል።
በአት-ተውባህ የመጽሐፍት መደብር፣
በአን-ነጃሺይ የመጽሐፍት መደብር፤
በአቅሷ የመጽሐፍት መደብር ያገኙታል።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት ዐብዱ አር-ራሕማን 0920781016 ብለው ይደውሉ!
ከቁርኣን አይጋጭ መቅድም የተወሰደ!

ኢሥላምን የሕይወቴ መርሕ አርጌ ከመያዜ በፊት በክርስትና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ጥናት በጀመርኩበት ጊዜ ወደ ሃይማኖት ንጽጽር ውስጥ ገባሁኝ። ሙሥሊሞች ባይብል ላይ ከሚያነሱት ጥያቄ የተነሳ እከክልኝ ልከክልህ በሚል መርሕ ቁርኣንን ማጥናት ጀመርኩኝ፥ ያ አልበቃ ብሎኝ ሐዲስን፣ ሲራን፣ ተፍሢሪን ማንበብ ጀመርኩኝ። አላማዬና ኢላማዬ ግን ለመሥለም ሳይሆን ቁርኣንን ለማብጠልጠል፣ ለማነወር፣ ለመተቸት ነበር። ነገር ግን ቁርኣንን በማጠናበት ጊዜ የቁርኣን ተናጋሪ እንደ ባይብሉ ሰዎች ሳይሆን የዓለማቱ ጌታ አላህ መሆኑ አስደነገጠኝ፥ ቁርኣንን የማስበው የአንድ ግመል ገፊ ሰው ድርሰት እንጂ የዓለማቱ ጌታ በመልአኩ ለነቢዩ ያወረደው ወሕይ ነው" ብዬ በእውኔ ሆነ በሕልሜ አስቤው ዐላውቅም።

በመቀጠል ክርስትና ከእሥልምና ጋር ያለውን ሥነ-መለኮታዊ ልዩነት ማጥናት ጀመርኩኝ፥ አምላካችን አላህ በአንድ ምንነቱ ላይ ሁሉት ወይም ሦስት ማንነት የሌለበት፣ በአምላክነቱ ላይ ሰውነት የሌለበት፣ በጌትነቱ ላይ ባርነት የሌለበት፣ በሕያውነቱ ላይ ሞት የሌለበት፣ በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሌለበት፣ በኀያልነቱ ላይ ድካም የሌለበት፣ በፈጣሪነቱ ፍጡርነት የሌለበት መሆኑን እና መከፋፈል፣ ሰው መሆን፣ ባሪያ መሆን፣ መሞት፣ ማንቀላፋት፣ መድከም፣ መፈጠር የፍጡር ባሕርይ መሆኑን ደረስኩበት።
ክርስትና የሚጣራው ሦስት ማንነቶችን ማለትም ሥላሴን እንድናመልክ ነው። ግን መመለክ ያለበት አንድ ማንነት ብቻ ነው።
ክርስትና የሚጣራው ሰው እንድናመልክ፣ ኢየሱስ ሰውነቱ ይመለካል፣ በሰውነቱ ፍጡር ነው ይላሉና።ግን መመለክ ያለበት አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው።
ክርስትና የሚጣራው ፍጡራንን በሌሉበት ወደ እነርሱ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ፣ መለማመን፣ መጸለይ፣ ስለት መሳል፣ መስዋዕት ማቅረብ፣ ስማቸውን መጥራት ነው። ሁሉን የሚሰማ፣ የሚያይ፣ የሚያውቅ አንድ መለኮት ብቻ ሆኖ ሳለ ወደ መላእክትና ቅዱሳን ይህንን ማድረግ ሺርክ ነው።
ክርስትና የሚጣራው ለተቀረጸ ምስል እንድንሰግድ ነው። ለተቀረጸ ምስል አትስገድ ተብሎ ነገር ግን በተቃራኒው ከእንጨት፣ ከብር፣ ከወርቅ፣ ከብረት፣ ከድንጋይ ለተቀረጹ መስቀል፣ ስዕል እና ሃውልት ይሰግዳሉ። ይህም ሺክር ነው።
ይህንን የኢሥላም ሥነ-መለኮት ልዋጋ መጥቼ በቁርኣን ተማርኬ ከቀረሁኝ አሁን ሰባት ዓመት ሞላኝ። ወደ ዲኑል ኢሥላም ከመጣሁኝ በኃላ በኢሥላም ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ላይ እገኛለሁኝ። ከዚህ ጎን ለጎን ኢሥልምና ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች ደግሞ፦ "ቁርኣን እርስ በእርሱ ይጋጫል" በማለት ስሑት ሙግት አላቸው። እኔ ደግሞ ቁርኣን ምንም አይጋጭም ብዬ ስሙር ሙግት አቅሬቤአለሁኝ፥ መልካም ንባብ ይሁንልዎ!

ወሒድ ዑመር
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

በአገር ውስጥ ያለው የዘር ፓለቲካ ይዞ የመጣ ፈሣድ እየተቀጣጠለ ስለሆነ ከስሜታዊነት ወጥተን ለሊሏሂ ብለን ፍትኃዊ እንሁን! በዘር ፓለቲካ እርስ በእርስ መሰዳድብ፣ መነቋቆር እና መዘራረጥ ዲናዊ አይደለም። ጥቂት የዘር ፓለቲካ አንቀንቃኞች ብዙኃኑ ላይ ፕሮፓጋንዳ በመቅረፅ እና በማስረፅ እያፋጁት ይገኛሉ። አሏህ በዟሊሚን ላይ ቁጣውን ያውርድባቸው! አሚን።
ጥቁር አዝሙድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ኢሥላም ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች፦ “ነቢያችሁ"ﷺ"፦ *"በጥቁር አዝሙር ውስጥ ከሞት በስተቀር ከሁሉም በሽታ መድኃኒት ነው” ብለዋል፥ ስለዚህ ጥቁር አዝሙር ለኤች አይቪ ኤድስ፣ ለኮሮና ቫይረስ እና ለመሳሰሉት መድኃኒት እንዴት አልሆነም? እያሉ ይጠይቃሉ። እኛም ደግሞ ጥሬውን ከብስል ምርቱን ከእንክርዳር የሚለዩ ሊሒቃን፦ “ ነገርን ከሥሩ ውኃን ከጡሩ” እንደሚሉት ኢንሻሏህ ከሥሩ ጥናት በማድረግ መልስ እንሰጣለን፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 76, ሐዲስ 11
አቢ ሁራይራህ ሰምቶ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በጥቁር አዝሙር ውስጥ ከሞት በስተቀር ከሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው"*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ، أَخْبَرَهُمَا أَنَّهُ، سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ فِي الْحَبَّةِ السَّوْدَاءِ شِفَاءٌ مِنْ كُلِّ دَاءٍ إِلاَّ السَّامَ ‏"‌‏

፨ አንደኛ እዚህ ሐዲስ ላይ “ኩል” كُلٌّ ማለትም “ሁሉ” የሚለው ቃል ተቀምጧል። “ኩል” كُلٌّ በዐረቢኛ ሰዋስው ውስጥ ፍጹማዊ “Absolute” ሆኖ ሲመጣ “ኩሉል ሙጥለቅ” كُلٌّ ٱلْمُطْلَق ሲባል፥ በአንጻራዊ “Relative” ሆኖ ሲመጣ ደግሞ “ኩሉል ቀሪብ” كُلٌّ ٱلْقَرِيب‎ ይባላል። እዚህ ሐዲስ ላይ "ኩል" የሚለው ቃል ኩሉል ቀሪብ መሆኑን የምናውቀው "ኩል" በሚል ቃል መነሻ ላይ "ሚን" مِنْ ማለትም "ከ"from" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ ነው፥ እስቲ ተመሳሳይ ሰዋስው እንመልከት፦
14፥34 "ከ"ለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው፡፡ وَآتَاكُم مِّن كُلِّ مَا سَأَلْتُمُوهُ
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም “ከ”ፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው*፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ

"የለመናችሁትን ሁሉ የሰጣችሁ ነው" ሳይሆን "ከ"ለመናችሁት ሁሉ" ማለት ከፊልን ያሳያል፥ በተመሳሳይ "ፍሬዎች ሁሉ" ሳይሆን "ከ"ፍሬዎች ሁሉ " ማለት ከፊልን ያሳያል። በተመሳሳይም "ለሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው" ሳይሆን "ከ-ሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው" ማለት ከፊልን ያሳያል።

፨ ሁለተኛ ሐዲሱ ላይ "ኢላ" إِلَّا ማለትም "በቀር" የሚል ሐርፉል ሐስድ ይጠቀማል። "ሐርፉል ሐስድ" حَرْف الحَصْرْ ማለት "ግድባዊ መስተዋድድ"restriction particle" ማለት ሲሆን ይህም ሐስድ በሁለት ዋና ዋና ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፥ እርሱም አንደኛው “ሐስዱል ሙጥለቅ” حَصْرْ ٱلْمُطْلَق ማለትም “ፍጹማዊ ግድብ“Absolute restriction” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “ሐስዱል ቀሪብ” حَصْرْ ٱلْقَرِيب‎ ማለትም “አንጻራዊ ግድብ“Relative restriction” ነው። ይህንን ናሙና እንይ፦
26፥77 *”«እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር እርሱ ወዳጄ ነው”*፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ
46፥25 *"በጌታዋ ትዕዛዝ አንዳቹን ሁሉ ታጠፋለች፥ ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር ምንም የማይታዩ ኾኑ፡፡ تُدَمِّرُ كُلَّ شَيْءٍ بِأَمْرِ رَبِّهَا فَأَصْبَحُوا لَا يُرَىٰ إِلَّا مَسَاكِنُهُمْ

ኢብራሂም፦ "የዓለማት ጌታ ሲቀር" ሲል ከአሏህ ውጪ ያሉ መላእክት፣ ነቢያት እና ምእመናን ጠላቶቼ ናቸው ማለት እንዳልሆነ ሁሉ፣ እንዲሁ ነፋስ ከመኖሪያዎቻቸው በቀር ሁሉን ታጠፋለች ሲባል መላእክት፣ ነቢያት እና ምእመናን ታጠፋለች ማለት እንዳልሆነ ሁሉ በተመሳሳይ "ከሞት በስተቀር ከሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው" ማለት "ሁሉ" የሚለው ቃል አንጻራዊ "በቀር" የሚለው ግድባዊ አነጋገር ነው። ስለዚህ ጥቁር አዝሙድ ለካንሰር እባጭ፣ ለስኳር በሽታ፣ ለተቅማጥ፣ ለደረቅ ሳል፣ ለጆሮ ህመም፣ ለዓይን ህመም፣ ለእይታ ችግር፣ ለፊት ፓራሊሲስ፣ ለጉንፋን፣ ለፍሉ፣ ለሐሞት ጠጠር፣ ለጉበት ጠጠር፣ ለሆድ ትላትል፣ ለሆድ ህመም፣ ለሪህ፣ ለጀርባ ህመም፣ ለአፍ ኢንፌክሽን ቫይረስ፣ ለጡንቻ ህመም፣ ለራስ ህመም፣ ለማይግሬን፣ ለማስታወስ ችሎታ ለፀጉር መሳሳት እረ ስንቱ ተዘርዝሮ ይለቅ? ለዚህ ሁሉ መድኃኒት ነው፥ ቅሉ ግን "ሁሉ" እና "በቀር" የሚለው "ኢሥቲስናእ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለትም "ግድባዊ"exceptional" ሆኖ የመጣ ነው።

፨ ሦስተኛ "በጥቁር አዝሙር ውስጥ ከሞት በስተቀር ከሁሉም በሽታ መድኃኒት ነው" ስለተባለ ጥቁር አዝሙድን ዝም ብሎ መውሰድ ያድናል ማለት ሳይሆን እንዴት መቀመም እንዳለበት ጥናት እና ከአሏህ ዘንድ ጥበቡ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የፋርማሲይ ምልክቱ የእባብ መርዝ ነው፥ የእባብ መርዝ ፕሮቲን ሲሆን ከእኛ ፕሮቲን ጋር በቀጥታ ስለማይመጣጠን ለእኛ መርዝ ነው። ቅሉ ግን የእባብ ፕሮቱኑ ለምሳሌ ለደም ግፊት አሁን ሥራ ላይ እየዋለ ካሉ መድኃኒቶች ዉስጥ "Angiotensin-converting enzyme (ACE) inhibitors" ከሚባሉት ዉስጥ የዚህ ACE I ግሩፕ አካል የሆነ እና "Prodrug" በመባል የሚታወቀው ''Captopril'' ምንጩ የእባብ መርዝ ነው፥ ታዲያ የእባብ መርዝ "ለደም ግፊት መድኃኒት ነው" ስለተባለ ያለ ጥናት እና ያለ ጥበብ እስቲ ምክረውና ምን እንደሚፈጠር መገመት አያዳግትም። በተመሳሳይም የጥቁር አዝሙር መድኃኒትነትን የሰው ልጅ ሙሉ ለሙሉ አልደረሰበት ማለት ለሁሉ ነገር መድኃኒት አይደለም ማለት አይደለም፥ የእባብ መርዝ አጠቃቀሙ የተነገረበት "ሢያቅ" سِيَاق ማለትም "ዐውድ"context" እንደሚወስነው ሁሉ የጥቁር አዝሙድ አጠቃቀም ዐውዱ ይወስነዋል። ለአንድ በሽታ መድኃኒት ለማግኘት አምላካችን አሏህ ዕውቀቱን እና ጥበቡ እንዲያገኙ ሲፈቅድ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 39, ሐዲስ 95
ጃቢር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ለሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው፥ መድኃኒቱ በሽታውን ካገኘው በአሏህ አዘ ወጀል ፈቃድ ይፈውሳል"*። عَنْ جَابِرٍ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ "‏ لِكُلِّ دَاءٍ دَوَاءٌ فَإِذَا أُصِيبَ دَوَاءُ الدَّاءِ بَرَأَ بِإِذْنِ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ

የጥቁር አዝሙር መድኃኒትነትን ከላይ በተዘረዘረው የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ ሙግት መረዳት በቀላሉ ይቻላል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አትግደሉ!

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥33 *”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

“ዘንብ” ذَنب ማለት “ኃጢአት” ማለት ነው፥ በሥነ-ኃጢአት ጥናት”hamartiology” ውስጥ "ኃጢአት” ማለት "አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር አለማድረግ፥ የከለከለውን ክፉ ነገር ማድረግ" ማለት ነው። ኃጢአት “ከባኢሩ አዝ-ዘንብ” كَبَائِر الْذَنب እና “ሶጋኢሩ አዝ-ዘንብ” صَغَائِر الْذَنب ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ፥ “ከባኢር” كَبَائِر ማለት “ዐብይ” “ታላቅ” ማለት ሲሆን “ሶጋኢር” صَغَائِر ማለት ደግሞ “ንዑስ” “ትንሽ” ማለት ነው። ከዐበይት ኃጢአቶች መካከል አንዱ ነፍስን ያለ ሕግ መግደል ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْكَبَائِرُ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ ‏”‌‏.‏

"ቀትሉ አን-ነፍሥ" قَتْلُ النَّفْس የሚለው ቃል ይሰመርበት! አምላካችን አሏህ ነፍስን መግደል ሐራም አርጓል፦
17፥33 *”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

“እርም ያረጋት” ለሚለው የገባው ቃል “ሐረመ” حَرَّمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ሐረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የተከለከለ” ማለት ነው። እንደውም ያለጥፋት አንድን ሰው መግደል ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነው፦
5፥32 *”በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፥ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው”* ማለትን ጻፍን፡፡ مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا

አንድን ነፍስ ያለ ሕግ መግደል እርሱ አግብቶ ቤተሰብ፣ ነገድ፣ ጎሳ፣ አገር እያለ ሕዝብ የሚሆንበትን የተፈጥሮ ዐላማና ዒላማ መቅጨት ስለሆነ ነፍስ ያለ ሕግ የገደለ ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው። የአር-ረሕማንም ባሮች ያችንም አሏህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ቂሷስ ሕግ የማይገድሉ ናቸው፥ ነገር ግን ያችንም አሏህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ቂሷስ ሕግ በመግደል ይህንንም የሚሠራ ሰው ከዱንያ ፍርድ ቢያመልጥ በአኺራ ከአሏህ ቅጣትን ያገኛል፦
25፥68 *”እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል”*፡፡ وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

ቅሉ ግን ወሰን አልፈው የሚገሉትን ሰዎች መግደል ቂሷስ ነው፥ “ቂሷስ” قِصَاص የሚለው ቃል “ቋሶ” قَاصَّ ማለትም “አመሳሰለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመሳሰል” ማለት ነው። ሰው ጤናማ ሕይወት ይኖር ዘንድ አምላካችን አሏህ ቂሷስን ደንግጓል፦
2፥179 *”ባለ አእምሮዎች ሆይ! ለእናንተም በማመሳሰል ሕግ ውስጥ ሕይወት አለላችሁ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ”*፡፡ وَلَكُمْ فِي الْقِصَاصِ حَيَاةٌ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

"ገዳይን መግደል" ሐላል ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ “ማመሳሰል” ለሚለው ቃል የገባው “ቂሷስ” قِصَاص መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቂሷስ ወሰን በታለፈበት ላይ ወሰን ያለፈውን ብጤውን ወሰን ማለፍ ነው፦
2፥194 *”የተከበረው ወር በተከበረው ወር አንጻር ነው፡፡ ሑሩማት ሁሉ ቂሷስ ናቸው፥ በእናንተም ላይ ወሰን ያለፈባችሁን ሰው በእናንተ ላይ ወሰን ባለፈው ብጤ በእርሱ ላይ ወሰን እለፉበት፡፡ አላህንም ፍሩ አላህ ከሚፈሩት ጋር መኾኑንም ዕወቁ”*፡፡ الشَّهْرُ الْحَرَامُ بِالشَّهْرِ الْحَرَامِ وَالْحُرُمَاتُ قِصَاصٌ ۚ فَمَنِ اعْتَدَىٰ عَلَيْكُمْ فَاعْتَدُوا عَلَيْهِ بِمِثْلِ مَا اعْتَدَىٰ عَلَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ مَعَ الْمُتَّقِينَ

"በእናንተ ላይ ወሰን ባለፈው ብጤ በእርሱ ላይ ወሰን እለፉበት" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! እነዚህን የሚጋደሉ ሰዎች መጋደል ፍትሓዊ ነው፦
2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ
2፥193 *ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሉዋቸው፡፡ ቢከለክሉም ወሰንን ማለፍ በበዳዮች ላይ እንጂ የለም ወሰን አትለፉባቸው*፡፡ وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ ۖ فَإِنِ انتَهَوْا فَلَا عُدْوَانَ إِلَّا عَلَى الظَّالِمِينَ

አሏህ ወሰን አላፊዎን አይወድም፥ ወሰን የሚያልፉት በዳዮች ናቸው። ከመጋደል የሚከለከሉትን ወሰን አይታለፍም፥ ከዚህ ውጪ ወሰን ታልፎባቸው ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፦
22፥39 *”ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፡፡ አላህም እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው”*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

"በሕግ ቢሆን እንጂ" ማለት እንደዚህ ነው፥ ወሰን አልፎ የሚመጣውን በዳይ ሁሉ ጂሃዱል ዐመሊያህ በመጠቀም መጋደል ሐላል ነው። ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አትግደሉ!

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥191 *"ባገኛችኋቸውም ስፍራ ሁሉ ግደሉዋቸው! ከአወጧችሁም ስፍራ አውጧቸው!* وَاقْتُلُوهُمْ حَيْثُ ثَقِفْتُمُوهُمْ وَأَخْرِجُوهُم مِّنْ حَيْثُ أَخْرَجُوكُمْ

ነቢያችን"ﷺ" እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 610 ድኅረ-ልደት የተውሒድ አንኳር የሆነውን “ላ ኢላሀ ኢልለሏህ” لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ካወጁ በኃላ የመካ ሙሽሪኮች እሳቸውን ሊያስሩ ወይም ሊገድሉ አሊያም ከመካህ ሊያስወጡ ተማከሩባቸው፦
8፥30 *"እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም ከመካ ሊያወጡህ በአንተ ላይ ”በመከሩብህ” ጊዜ አስታውስ"*፡፡ وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ

ከዚያም የመካ ሙሽሪኮች እርሳቸውን እና ባልደረቦቻቸው ከመካህ ወደ መዲናህ በ 622 ድኅረ-ልደት አሳደዷቸው፥ የመካ ሙሽሪኮች በደል በዚህ አላበቃ ብሎ መዲናህ ድረስ መጥተው መግደል ጀመሩ። አምላካችን አሏህም ለምእመናን መጋደልን ፈቀደላቸው፦
22፥39 *”ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፡፡ አላህም እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው”*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ
22፥40 *"ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት ተፈቀደ"*፡፡ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَن يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ

ያለ አግባብ ከአገራቸው ለተባረሩት ምእመናን መጋደል ከተፈቀደ በኃላ በ 624 ድኅረ-ልደት በበድር ዘመቻ አምላካችን አሏህ፦ "እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ" የሚል አንቀጽ አወረደ፦
2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

"እነዚያ" የሚል አመልካች ተውላጠ-ስም የሚያመለክተው ወሰን አልፈው የሚጋደሉትን የመካህ ሙሽሪኮች ነው፥ አንድ ምእመን መጋደል ያለበት ለክብሩ፣ ለዘሩ፣ ለብሔሩ፣ ለፓለቲካ አቋሙ ሳይሆን ለአሏህ ብሎ መሆን ስላለበት "በአላህ መንገድ" የሚል መርሕ በአጽንዖትና በአንክሮት ያስቀምጣል። ዐውደ-ንባቡ ላይ "ባገኛችኋቸውም ስፍራ ሁሉ ግደሉዋቸው" የሚለው ከመካ ያወጧቸውን የመካ ሙሽሪኮች ስለሆነ "ከአወጧችሁም ስፍራ አውጧቸው" የሚል ኃይለ-ቃል አለ፦
2፥191 *"ባገኛችኋቸውም ስፍራ ሁሉ ግደሉዋቸው! ከአወጧችሁም ስፍራ አውጧቸው!* وَاقْتُلُوهُمْ حَيْثُ ثَقِفْتُمُوهُمْ وَأَخْرِجُوهُم مِّنْ حَيْثُ أَخْرَجُوكُمْ

የአንድን አንቀጽ ዐረፍተ-ነገሩን ከዐውዱ አያይዞ መረዳት "ፈቲሆት”exegesis” ሲሆን ብዙ ጊዜ የሚሽነሪዎች ችግር የአንድን አንቀጽ ዐረፍተ-ነገሩን ከዐውዱ አፋቶ በመረዳት “ሰጊጎት”Eisegesis” ማድረግ ነው። ሐረጉ ይቀጥልና፦ "መከራም ከመግደል ይበልጥ የበረታች ናት፡፡ በተከበረው መስጊድም ዘንድ በእርሱ ውስጥ እስከሚጋደሉዋችሁ ድረስ አትጋደሉዋቸው፡፡ ቢጋደሉዋችሁም ግደሉዋቸው! የከሓዲዎች ቅጣት እንደዚህ ነው" ይላል፦
2፥191 *"መከራም ከመግደል ይበልጥ የበረታች ናት፡፡ በተከበረው መስጊድም ዘንድ በእርሱ ውስጥ እስከሚጋደሉዋችሁ ድረስ አትጋደሉዋቸው፡፡ ቢጋደሉዋችሁም ግደሉዋቸው! የከሓዲዎች ቅጣት እንደዚህ ነው"*፡፡ وَالْفِتْنَةُ أَشَدُّ مِنَ الْقَتْلِ ۚ وَلَا تُقَاتِلُوهُمْ عِندَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ حَتَّىٰ يُقَاتِلُوكُمْ فِيهِ ۖ فَإِن قَاتَلُوكُمْ فَاقْتُلُوهُمْ ۗ كَذَٰلِكَ جَزَاءُ الْكَافِرِينَ

“አል-መሥጂዱል ሐረም” الْمَسْجِدِ الْحَرَام መካህ ውስጥ የሚገኘው ከዕባህ ሲሆን እዛ ቦታ "እስከሚጋደሉዋችሁ ድረስ አትጋደሉዋቸው! ቢጋደሉዋችሁም ግደሉዋቸው" ተብሏል። ከመበደል እና ከመጋደል ቢከለከሉ አሏህ መሓሪ ነውና ወሰን አትለፉባቸው፦
2፥192 *"ቢከለከሉም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው"*፡፡ فَإِنِ انتَهَوْا فَإِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
2፥193 *"ቢከለክሉም ወሰንን ማለፍ በበዳዮች ላይ እንጂ የለም ወሰን አትለፉባቸው*፡፡ فَإِنِ انتَهَوْا فَلَا عُدْوَانَ إِلَّا عَلَى الظَّالِمِينَ

ቅሉ ግን ወሰን አልፈው እነዚያ በሃይማኖት ከሚጋደሉት፣ ከቤት ከሚያስወጡት፣ በማስወጣትም በሚረዱት በዳዮች ላይ ወሰን ማለፍ ሐላል ነው፦
60፥9 አላህ የሚከለክላችሁ ከእነዚያ በሃይማኖት ከተጋደሉዋችሁ፣ ከቤቶቻችሁም ካወጡዋችሁ፣ እናንተም በማውጣት ላይ ከረዱት ከሓዲዎች እንዳትወዳጁዋቸው ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ قَاتَلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَأَخْرَجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ وَظَاهَرُوا عَلَىٰ إِخْرَاجِكُمْ أَن تَوَلَّوْهُمْ

በተቃራኒው ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሉት እና ከአገሮች ካላወጡት ከሓዲዎች መልካም መዋዋል እና ወደ እነርሱ ማስተካከል አሏህ አይከለክልም፥ አምላካችን አሏህ አስተካካዮችን ይወዳል፦
60፥8 *"ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸው እና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና"*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አትግደሉ!

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

9፥5 *"የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው"*፡፡ فَإِذَا انسَلَخَ الْأَشْهُرُ الْحُرُمُ فَاقْتُلُوا الْمُشْرِكِينَ حَيْثُ

ሑሩማት ሁሉ ቂሷስ ናቸው፥ በእናንተም ላይ ወሰን ያለፈባችሁን ሰው በእርሱ ላይ ወሰን እለፉበት፡፡ አሏህንም ፍሩ! አሏህ ከሚፈሩት ጋር መኾኑንም ዕወቁ፦
2፥194 *”የተከበረው ወር በተከበረው ወር አንጻር ነው፡፡ ሑሩማት ሁሉ ቂሷስ ናቸው፥ በእናንተም ላይ ወሰን ያለፈባችሁን ሰው በእናንተ ላይ ወሰን ባለፈው ብጤ በእርሱ ላይ ወሰን እለፉበት፡፡ አላህንም ፍሩ! አላህ ከሚፈሩት ጋር መኾኑንም ዕወቁ”*፡፡ الشَّهْرُ الْحَرَامُ بِالشَّهْرِ الْحَرَامِ وَالْحُرُمَاتُ قِصَاصٌ ۚ فَمَنِ اعْتَدَىٰ عَلَيْكُمْ فَاعْتَدُوا عَلَيْهِ بِمِثْلِ مَا اعْتَدَىٰ عَلَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ مَعَ الْمُتَّقِينَ

“ሙተቂን” مُتَّقِين ማለት “አሏህን የሚፈሩ” ማለት ነው፥ አሏህ የሚፈራ ሰው የሰውን ሐቅ በመንካት ወሰን አያልፍም፥ ወሰን ባለፈው ብጤ በእርሱ ላይ ወሰን ማለት ግን ሐላል ነው። የተከበረው ወር በተከበረው ወር አንጻር ነው፥ የወሮች ቁጥር አሏህ ዘንድ ዐሥራ ሁለት ወር ናቸው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ወሮች ዙል-ቀዒዳህ፣ ዙል-ሒጃህ፣ ሙሐረም እና ረጀብ ናቸው፦
9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 4662
አቡበከር”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ዘመን አላህ ሰማያትን እና ምድር በፈጠረበት ቀን የቀድሞ ሁኔታ ይመለሳል። አንድ ዓመት ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ ከእነርሱም አራቱ የተከበሩ ናቸው። ሦስቱ ተከታታይ ዙል-ቀዒዳህ፣ ዙል-ሒጃህ፣ ሙሐረም ናቸው፥ አራተኛው በጀማዱ-ሣኒ እና በሻዕባን መካከል ያለው ረጀብ ነው*። عَنْ أَبِي بَكْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ إِنَّ الزَّمَانَ قَدِ اسْتَدَارَ كَهَيْئَتِهِ يَوْمَ خَلَقَ اللَّهُ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ، السَّنَةُ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا مِنْهَا، أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ، ثَلاَثٌ مُتَوَالِيَاتٌ، ذُو الْقَعْدَةِ وَذُو الْحِجَّةِ وَالْمُحَرَّمُ وَرَجَبُ مُضَرَ الَّذِي بَيْنَ جُمَادَى وَشَعْبَانَ

የመካ አጋሪዎችን የመታገሻ ጊዜ የተከበሩ ወሮች ዙል-ቀዒዳህ፣ ዙል-ሒጃህ፣ ሙሐረም እና ረጀብ ተሰቷቸዋል፥ በዚህ የጊዜ ገደብ ካልተከለከሉ እነዚህ የተከበሩ ወሮች ባለቁ ጊዜ "በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው" ተባለ፦
9፥5 *"የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው"*፡፡ فَإِذَا انسَلَخَ الْأَشْهُرُ الْحُرُمُ فَاقْتُلُوا الْمُشْرِكِينَ حَيْثُ

የመካ አጋሪዎች ከሙሐጅሮች ጋር አንዳቸው ለአንዳቸድ ላይ ጦር በድጋሚ እንዳይከፍት በሚል የስምምነት ኪዳን ነበራቸው፦
9፥1 *"ይህች ከአላህ እና ከመልክተኛው ወደ እነዚያ ቃል ኪዳን ወደ ተጋባችኋቸው አጋሪዎች የምትደርስ ንጽሕና ናት"*፡፡ بَرَاءَةٌ مِّنَ اللَّهِ وَرَسُولِهِ إِلَى الَّذِينَ عَاهَدتُّم مِّنَ الْمُشْرِكِينَ

ይህንን ውል አፍርሰው ወደ ጦርነት ሲገቡ ውሉን የሚያድሱበት አራት የተከበሩ ወሮች ተሰጣቸው፥ ከቃል ኪዳንን በኃላ መሓላን በማፍረስ፣ ሃይማኖትን በማነወር እና ትንኮሳውን በመጀመራቸው በተገኙበት እንዲገደሉ ታዘዘ፦
9፥12 *"ከቃል ኪዳናቸው በኋላ መሓላዎቻቸውን ቢያፈርሱ፣ ሃይማኖታችሁንም ቢያነውሩ፣ የክህደት መሪዎችን ከክህደት ይከለከሉ ዘንድ ተዋጉዋቸው፡፡ እነርሱ ቃል ኪዳን የላቸውምና"*፡፡ وَإِن نَّكَثُوا أَيْمَانَهُم مِّن بَعْدِ عَهْدِهِمْ وَطَعَنُوا فِي دِينِكُمْ فَقَاتِلُوا أَئِمَّةَ الْكُفْرِ ۙ إِنَّهُمْ لَا أَيْمَانَ لَهُمْ لَعَلَّهُمْ يَنتَهُونَ
9፥13 *"መሓላዎቻቸውን ያፈረሱትን መልክተኛውንም ለማውጣት ያሰቡትን ሕዝቦች እነርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩዋችሁ ሲኾኑ ለምን አትዋጉዋቸውም? ትፈሩዋቸዋላችሁን? ምእምናን እንደ ኾናችሁም አላህ ይበልጥ ልትፈሩት የተገባው ነው"*፡፡ أَلَا تُقَاتِلُونَ قَوْمًا نَّكَثُوا أَيْمَانَهُمْ وَهَمُّوا بِإِخْرَاجِ الرَّسُولِ وَهُم بَدَءُوكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ ۚ أَتَخْشَوْنَهُمْ ۚ فَاللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَوْهُ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

ከአጋሪዎቹ እነዚያ ቃል ኪዳን ምንም ያላጎደሉት እና አንድንም ያልረዱትን ግን እስከ ህልፈተ ሕይወታቸው ሳይነኩ ይኖራሉ፦
9፥4 *"ከአጋሪዎቹ እነዚያ ቃል ኪዳን የተጋባችኋቸው እና ከዚያም ምንም ያላጎደሉባችሁ በእናንተ ላይም አንድንም ያልረዱባችሁ ሲቀሩ፤ እነዚህን ቃል ኪዳናቸውን እስከ ጊዜያቸው መጨረሻ ሙሉላቸው፡፡ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና"*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ عَاهَدتُّم مِّنَ الْمُشْرِكِينَ ثُمَّ لَمْ يَنقُصُوكُمْ شَيْئًا وَلَمْ يُظَاهِرُوا عَلَيْكُمْ أَحَدًا فَأَتِمُّوا إِلَيْهِمْ عَهْدَهُمْ إِلَىٰ مُدَّتِهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَّقِينَ

"አሏህ የምሠራውን ያየኛል፣ የምናገረውን ይሰማኛል፣ የማስበውን ያውቅብኛል" ብለው የሚፈሩትን ሙተቂን ባሮቹን ይወዳል፥ እነዚያ በአል-መሥጂዱል ሐረም ዘንድ ቃል ኪዳን የተጋቡት ሙሽሪኮች በውሉ መሠረት ቀጥ እስካሉ ድረስ ሳይነኩ ቀጥ ተብሎላቸዋል፦
9፥7 *"ለአጋሪዎቹ አላህ ዘንድ እና እመልክተኛው ዘንድ ቃል ኪዳን እንዴት ይኖራቸዋል? እነዚያ በተከበረው መስጊድ ዘንድ ቃል ኪዳን የተጋባችኋቸው ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነዚህ በቃል ኪዳናቸው ለእናንተ ቀጥ እስካሉላችሁ ድረስ ለእነርሱም ቀጥ በሉላቸው፡፡ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና"*፡፡ كَيْفَ يَكُونُ لِلْمُشْرِكِينَ عَهْدٌ عِندَ اللَّهِ وَعِندَ رَسُولِهِ إِلَّا الَّذِينَ عَاهَدتُّمْ عِندَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ فَمَا اسْتَقَامُوا لَكُمْ فَاسْتَقِيمُوا لَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَّقِينَ
በአናቅጽ ማብቂያ ላይ፦ "አላህንም ፍሩ! አላህ ከሚፈሩት ጋር መኾኑንም ዕወቁ" "ምእምናን እንደ ኾናችሁም አላህ ይበልጥ ልትፈሩት የተገባው ነው" "አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና" መባሉ በራሱ ጂሃዱል ዐመሊያህ ከነፍሢያህ ባሻገር ለሊሏሂ ተብሎ የሚደረግ ጅሁድ መሆኑን አመላካች ነው። በጦርነቱ የተማረኩ እና የተከበቡ መጠባበቅ በየመንገዱ ይደረግላቸዋል፥ ይህም ወደ አሏህ በተውባህ መጥተው ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገድ ይለቀቅላቸዋል። ያንን ካደረጉ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፦
9፥5 *"ያዙዋቸውም፣ ክበቡዋቸውም፣ ለእነርሱም መጠባበቅ በየመንገዱ ተቀመጡ፡፡ ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምጽዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና"*፡፡ وَجَدتُّمُوهُمْ وَخُذُوهُمْ وَاحْصُرُوهُمْ وَاقْعُدُوا لَهُمْ كُلَّ مَرْصَدٍ ۚ فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَخَلُّوا سَبِيلَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
9፥11 *"ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦችም አንቀጾችን እናብራራለን"*፡፡ فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ ۗ وَنُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

አንድ ምርኮኛ በፍልሚያው ወቅት ሳይሠልም ተማርኮ ጥገኝነት"Asylum" ቢጠይቅ ምንም ሳይነካ የአሏህን ንግግር እስኪሰማ ዘንድ ጥገኝነት ይሰጠዋል፥ ጥበቃ እንዲደረግለት ወደ መጠበቂያው ስፍራ ይወሰዳል፦
9፥6 *"ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ንግግር እስኪሰማ ዘንድ አስጠጋው! ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው፡፡ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው"*፡፡ وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ

ምርኮኛው የአሏህን ንግግር ከቃሪው ሲሰማ ልቡ የመማረክ አጋጣሚ ስላለው ማሰማቱ ጥሩ የሂዳያህ ሰበብ ነው። ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አትግደሉ!

ገቢር አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥193 *"ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሉዋቸው"*። وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ

ዓለም እስኪሰማና እስኪስማማ ድረስ ጂሃድ በሐቅ እና በባጢል መካከል ያለ ትግል ነው፥ እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ እውነት ለማንገሥ ሐሠትን ለማርከሥ መጋደል “ፈርዱል ኪፋያህ” فَرْض الكِفَايَة ማለትም “የጥቅል ግዴታ” ነው፦
2፥193 *"ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሉዋቸው"*። وَقَاتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ الدِّينُ لِلَّهِ

አንቀጹን ልብ ብለነው ከሆነ "ተጋደሉ" እንጂ "ግደሉ" አይልም። ልዩነቱን እስቲ እንመልከት፦
4፥84 *"በአላህም መንገድ ተጋደል"*፡፡ فَقَاتِلْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ
2፥244 *"በአላህም መንገድ ተጋደሉ"*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ተጋደል" ለሚለው የገባው ቃል "ቃቲል" قَاتِلْ ሲሆን "ተጋደሉ" ለሚለው ደግሞ "ቃቲሉ" قَاتِلُوا ነው። "ግደል" ለማለት ቢሆን ኖሮ "ኡቅቱል" اقْتُلْ ሲሆን "ግደሉ" ለማለት ደግሞ "ኡቅቱሉ" اقْتُلُوا ይሆን ነበር፥ ተጨማሪ አንድ አንቀጽ እንመልከት፦
9፥111 *"በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ፣ ይገድላሉ፣ ይገደላሉ"*፡፡ يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَيَقْتُلُونَ وَيُقْتَلُونَ

አያችሁ? "ይጋደላሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ዩቃቲሉነ" يُقَاتِلُونَ ሲሆን "ይገድላሉ" ለሚለው ግን "የቅቱሉነ" يَقْتُلُونَ ነው። "ቀትል" قَتْل ማለትም "መግደል" እና "ቂታል" قِتَال ማለትም "ገድል" ሁለት ለየቅል ቃላት እና ትርጉም አላቸው፥ ስለዚህ "መጋደል" ወይም "ገድል" ማለት ጂሃዱል ቀልቢያህ፣ ጂሃዱል ቀውሊያህ እና ጂሃዱል ዐመሊያህ ተጠቅሞ የአሏህን ንግግር የበላይ ማድረግ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 65
አቡ ሙሣ እንደተረከው፦ "አንድ ሰው ወደ ነቢዩ"ﷺ" መጥቶ፦ *"የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! የትኛው መጋደል ነው በአሏህ መንገድ መጋደል? ከእኛ መካከል በቁጣውና በንዴት ምክንያት የሚጋደል አለ፥ አንዳንዱ ለኩራትና ለንዴት የሚጋደል አለ" ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም ወደ እርሱ ከፍ ብለው፦ "የአሏህ ንግግር የበላይ ለማድረግ የሚጋደል እርሱ ነው በአሏህ መንገድ የሚጋደል" ብለው መለሱለት"*። عَنْ أَبِي مُوسَى، قَالَ جَاءَ رَجُلٌ إِلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَا الْقِتَالُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ فَإِنَّ أَحَدَنَا يُقَاتِلُ غَضَبًا، وَيُقَاتِلُ حَمِيَّةً‏.‏ فَرَفَعَ إِلَيْهِ رَأْسَهُ ـ قَالَ وَمَا رَفَعَ إِلَيْهِ رَأْسَهُ إِلاَّ أَنَّهُ كَانَ قَائِمًا ـ فَقَالَ "‏ مَنْ قَاتَلَ لِتَكُونَ كَلِمَةُ اللَّهِ هِيَ الْعُلْيَا فَهُوَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ

ሁከት እስከማይገኝ እና ሃይማኖት ለአሏህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ከኩፋሮች ጋር እንጋደላለን፥ ዓለም በአሏህ ሸሪዓህ እስክትደዳደር ድረስ መጋደሉ ይቀጥላል። ተወዳጁ ነቢያች"ﷺ" የታዘዙበት መርሕ ይህ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3 ሐዲስ 18
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ሰዎችን "ከአሏህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድም የአሏህ መልእክተኛ ነው" ብለው እስኪመሰክሩ፣ ሶላትን እስኪቆሙ እና ዘካህን እስኪያወጡ ድረስ እንድጋደላቸው ታዝዣለሁ"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ أُمِرْتُ أَنْ أُقَاتِلَ النَّاسَ حَتَّى يَشْهَدُوا أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ، وَيُقِيمُوا الصَّلاَةَ، وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ

እዚህም ሐዲስ ላይ "አን ኡቃቲለ" أَنْ أُقَاتِلَ ማለትም "እንድጋደል" የሚል ቃል እንጂ "አን አቅቱለ" أَنْ أَقْتُلَ ማለትም "እንድገድል" የሚል ቃል የለም። ገድል አጠቃላይ ሦስቱንም የጂሃድ ክፍል የሚይዝ ቃል ነው፦
ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ *“ከእናንተ ውስጥ እኩይ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው፣ ካልቻለ በምላሱ ያውግዝ፣ ይህንንም ካልቻለ በልቡ ይጥላው። በልብ መጥላት ደካማው ኢማን ነው”*። عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال‏:‏ سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏ “‏من رأى الخد منكرًا فليغيره بيده ، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان

በእጅ፣ በምላስ እና በልቡ ያልታገለ የጎመንዘር ያህል ኢማን የለውም። ምእምናን ማለት በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአሏህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፥ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው። አሏህ እኛን ውርደት ያከናነበን ከጂሃድ በመራቃችን ነው፦
49፥15 *ምእምናን እነዚያ በአላህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት “በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው”፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 47
ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በሪባ በተገበያያቹህ ጊዜ፣ ከብቶችን በተከትላችሁ ጊዜ፣ እርሻኝ በወዳዳቹህ ጊዜ እና ጂሃድን በተዋቹህ ጊዜ አሏህ ውርደት ያከናንባችኃል፥ ይህንንም ውርደት ወደ ዲናቹህ እስካልተመለሳቹህ ድረስ ከእናንተ አያነሳም”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ إِذَا تَبَايَعْتُمْ بِالْعِينَةِ وَأَخَذْتُمْ أَذْنَابَ الْبَقَرِ وَرَضِيتُمْ بِالزَّرْعِ وَتَرَكْتُمُ الْجِهَادَ سَلَّطَ اللَّهُ عَلَيْكُمْ ذُلاًّ لاَ يَنْزِعُهُ حَتَّى تَرْجِعُوا إِلَى دِينِكُمْ

ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም