ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.2K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መኪይ እና መደኒይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

24፥1 *”ይህች ያወረድናት እና የደነገግናት “ሡራህ” ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል”*፡፡ سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا

አምላካችን አላህ ቁርኣንን በሡራህ መከፋፈሉን ለማመልከት ብዙ አናቅጽ ላይ “ሡራህ” እያለ ይናገራል፦
24፥1 *”ይህች ያወረድናት እና የደነገግናት “ሡራህ” ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል”*፡፡ سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
9፥64 መናፍቃን በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር የምትነግራቸው *”ሡራህ” በእነርሱ ላይ መውረዷን ይፈራሉ*፡፡ يَحْذَرُ الْمُنَافِقُونَ أَن تُنَزَّلَ عَلَيْهِمْ سُورَةٌ تُنَبِّئُهُم بِمَا فِي قُلُوبِهِمْ

ስለዚህ የቁርኣን ሡራህ ሡራህ የተባለው ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ ነው። የሡራዎችን ቅድመ-ተከተል እና ስም ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በተናገሩት መሠረት የተቀመጠ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3366
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ለዑስማን ኢብኑ ዐፋን፦ “ሡረቱል አንፋልን ከመቶ በታች የሆነችበት፣ ሡረቱል በራኣህ(ተውባህ) ከመቶ በላይ የሆነችበት፣ በመካከላቸውም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ያልተጻፈበት(ሱረቱል በራኣህ) እና ባለ ሰባት አናቅጽ(ሡረቱል ፋቲሓህ) የሆችበት ምክንያታችሁ ምንድን ነው? አልኩኝ። ዑስማን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አንዳች የቁርኣን ክፍል በሚወርድላቸው ጊዜ ከጸሐፊዎቹ አንዱን በመጥራት፦ “ይህንን አንቀጽ እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት” ይሉ ነበር። አሁንም በድጋሚ የተወሰኑ የቁርኣን አንቀጾች ሲወርድላቸው፦ “እነዚህን አንቀጾች እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሡራህ ውስጥ አስቀምጡት” ይሉ ነበር”*። حَدَّثَنَا ابْنُ عَبَّاسٍ، قَالَ قُلْتُ لِعُثْمَانَ بْنِ عَفَّانَ مَا حَمَلَكُمْ أَنْ عَمَدْتُمْ، إِلَى الأَنْفَالِ وَهِيَ مِنَ الْمَثَانِي وَإِلَى بَرَاءَةَ وَهِيَ مِنَ الْمِئِينَ فَقَرَنْتُمْ بَيْنَهُمَا وَلَمْ تَكْتُبُوا بَيْنَهُمَا سَطْرَ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ وَوَضَعْتُمُوهُمَا فِي السَّبْعِ الطُّوَلِ مَا حَمَلَكُمْ عَلَى ذَلِكَ فَقَالَ عُثْمَانُ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِمَّا يَأْتِي عَلَيْهِ الزَّمَانُ وَهُوَ تَنْزِلُ عَلَيْهِ السُّوَرُ ذَوَاتُ الْعَدَدِ فَكَانَ إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ الشَّىْءُ دَعَا بَعْضَ مَنْ كَانَ يَكْتُبُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَؤُلاَءِ الآيَاتِ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا وَكَذَا وَإِذَا نَزَلَتْ عَلَيْهِ الآيَةُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَذِهِ الآيَةَ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا

ይህ ሐዲስ የሚያሳየው የሡራው ቅድመ-ተከተል እና እከሌ የሚለው ስም በአላህ ነቢይ የታዘዘ መሆኑን ነው። ከሦስት ሡራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሡራህ ስማቸው በውስጣቸው አለ፥ እነዚህም ስማቸው በውስጣቸው ያልተጠቀሱ ሦስት ሡራዎች ሡረቱል ፋቲሓህ፣ ሡረቱል አንቢያህ እና ሡረቱል ኢኽላስ ናቸው። እንደዛም ሆኖ የሡራህ ስያሜ ሶሓባዎች ከነቢያችን"ﷺ" የተማሩት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 45
ሠህል ኢብኑ ሠዒድ እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" ለአንድ ሰው፦ "ከቁርኣን ማንኛውም ነገር አገኘህን? ብለው አሉት። ያም ሰው፦ "አዎ! እንዲህና እንዲያ የሚል ሡራህ፣ እንዲህና እንዲያ የሚል ሡራህ እና የሡራህ ስያሜ" አለ"*። عَنْ سَهْلِ بْنِ سَعْدٍ، قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لِرَجُلٍ ‏ "‏ أَمَعَكَ مِنَ الْقُرْآنِ شَىْءٌ ‏"‌‏.‏ قَالَ نَعَمْ سُورَةُ كَذَا وَسُورَةُ كَذَا‏.‏ لِسُوَرٍ سَمَّاهَا‏.‏

ነቢያችን”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ሡራህ መውረድ ጀምሮ እስከ 63 ዓመታቸው ድረስ ቀስ በቀስ በሒደት 114 ሡራዎች ወርደውላቸዋል፥ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ወሕይ ተቀብለው በ 63 ዓመታቸው ሞተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 63, ሐዲስ 128
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ወሕይ መቀበል ጀመሩ፥ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ቆይተው በ 63 ዓመታቸው በሆነ ጊዜ ሞተዋል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ بُعِثَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَرْبَعِينَ سَنَةً، فَمَكُثَ بِمَكَّةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ سَنَةً يُوحَى إِلَيْهِ، ثُمَّ أُمِرَ بِالْهِجْرَةِ فَهَاجَرَ عَشْرَ سِنِينَ، وَمَاتَ وَهُوَ ابْنُ ثَلاَثٍ وَسِتِّينَ‏.‏
ሡራዎች ወደ ነቢያችን”ﷺ” ልብ በጨረቃ አቆጣጠር ከ 610 ድኅረ-ልደት እስከ 632 ድኅረ-ልደት ለ 23 ዓመት ቀስ በቀስ ወረዱ፥ ለ 13 ዓመት 86 ሡራዎች በመካ የወረዱ ሲሆኑ ለ 10 ዓመት ደግሞ 28 ሡራዎች የወረዱት በመዲና ነው። በዚህም በመካ የወረደች ሡራህ "መኪይ" مَكِّيّ ማለት "መካዊ" ስትባል በመካ የወረዱት 86 ሡራዎች ደግሞ "መኪዩን" مَكِّيُّون‎ ይባላሉ፥ በመዲና የወረደች ሡራህ "መደኒይ" مَدَنِيّ ማለት "መዲዊ" ስትባል በመዲና የወረዱት 28 ሡራዎች ደግሞ "መደኒዩን" مَدَنِيُّون ይባላሉ። ሡራዎች በመካ ይሁን በመዲና የት እንደወረዱ የተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦች ስለሚያውቁ መኪይ እና መደኒይ በማለት ሰይመዋቸዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 24
ዐብደሏህ አብኑ መሥዑድ"ረ.ዐ." እንደተናገረው፦ *"ወሏሂ! ከአሏህ በቀር አምላክ የለም፥ በአሏህ መጽሐፍ ምንም ሡራህ አይወርድ እኔ የት ቦታ እንደወረደች ባውቃት እንጂ"*። قَالَ قَالَ عَبْدُ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ وَاللَّهِ الَّذِي لاَ إِلَهَ غَيْرُهُ مَا أُنْزِلَتْ سُورَةٌ مِنْ كِتَابِ اللَّهِ إِلاَّ أَنَا أَعْلَمُ أَيْنَ أُنْزِلَتْ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4, ሐዲስ 65
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ከቁርኣን ሡራህ እንደሚያስተምሩን አት-ተሸሁድ ያስተምሩን ነበር"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يُعَلِّمُنَا التَّشَهُّدَ كَمَا يُعَلِّمُنَا السُّورَةَ مِنَ الْقُرْآنِ ‏.‏

"አይነ" أَيْنَ ማለትም "የት" የሚለው መጠይቅ ቦታን ያማከለ ነው፥ እንዚህ ቦታዎች መካ እና መዲና ናቸው። አንዲት ሡራህ መኪይ ወይም መደኒይ የሚያሰኛት በውስጧ የያዘችው አናቅጽ አብዛኛው መኪይ ወይም መደኒይ ስለሆነች እንጂ በመኪይ ሡራህ ውስጥ መደኒይ አንቀጽ እንዲሁ በመደኒይ ሡራህ ውስጥ መኪይ አንቀጽ ሊገኝ ይችላል። ለምሳሌ ሡረቱል አንፋል መደኒይ ሲሆን በውስጡ መኪይ አንቀጽ ይዟል፥ እንዲሁ ሡረቱል አንዓም መኪይ ሲሆን በውስጡ መደኒይ አንቀጽ ይህንን ይዟል፦
8፥64 አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ በቂህ ነው፡፡ ለተከተሉህም ምእምናን አላህ በቂያቸው ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ حَسْبُكَ اللَّهُ وَمَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ
6፥153 *"ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ" በል"*፡፡ وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

ስለ ሡረቱል መኪይ እና ስለ ሱረቱል መደኒይ በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል! “አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሸሪዓዊ መንግሥት ይመጣል!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥81 በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና» وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ ۚ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقً

እውነት ሲመጣ ውሸት ተወጋጅ ነው፥ በዓለም ላይ ያለው የኢሉሚናቲ እሳቤ ባጢል ነው። ሸሪዓዊ መንግሥት ሲመጣ ባጢሉ ኢሉሚናቲ እሳቤ ይወገዳል። ሸሪዓዊ መንግሥት በዓለም ላይ እንደሚመጣ ደግሞ በነቢያችን"ﷺ" ተነግሯል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 14, ሐዲስ 163
ሑደይፋህ ኢብኑል-የማን እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ነብይነት አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በነቢይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ይጀመርና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም ዘውዳዊ ንግሥና ቦታውን ይይዝና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም የአንባገነን ንግሥና ይነሳልና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በስተመጨረሻም በነቢይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ከእንደገና ይመጣል*። فَقَالَ حُذَيْفَةُ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ – صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ -: « تَكُونُ النُّبُوَّةُ فِيكُمْ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةٌ عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا عَاضًّا فَيَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا جَبْرِيَّةً فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةً عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ

ምነው ፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች፦ "ርኆቦት እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን" ሲሉ ወይም "በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከካሉ" ሲሉ ወንጀል ካልሆነ፦
ዘፍጥረት 26፥22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድጓድ አስቈፈረ፥ ስለ እርስዋም አልተጣሉም፤ ስምዋንም ርኆቦት ብሎ ጠራት እንዲህ ሲል፦ አሁን እግዚአብሔር አሰፋልን፥ በምድርም እንበዛለን።
ፊልጵስዩስ 2፥10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥

እኛም እንደ እምነታችን "ሸሪዓዊ መንግሥት ይመጣል!" ብለን ማመናችን ወንጀል አይደለም። ሁሌ አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር እሥልምናን የሚነኩት ውስጣቸው ሐቅ ስለሌለ እና በባጢል ስለተበተቡ ነው። በቴኦክራሲ ሥርዓት ውስጥ ሕገ-መንግሥቱ የአምላክ ንግግር ነው። ዲሞክራሲ ማለት ነጻነት ማለት ሳይሆን የኢሉሚናቲ መጫረቻና መጫወቻ ልቅነት ነው፥ ሥልጣኔ በምጣኔ አውንታዊ ነገር ሆኖ ሳለ የኢሉሚናቲ ዲሞክራሲ መሠልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው። ሸሪዓዊ መንግሥት ይመጣል! አትሸማቀቅ!
ደውለቱ አሽ-ሸሪዓህ ባቂያህ!

አላህ በቴኦክራሲ የሚመራውን ሸሪዓዊ መንግሥት በማምጣት ነስሩን ያቅርብልን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነፍስ መግደል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

17፥33 *”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው። “ቂሷስ” قِصَاص የሚለው ቃል “ቋሶ” قَاصَّ ማለትም “አመሳሰለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመሳሰል” ማለት ነው፥ በቂሷስ ነፍስ ያጠፋ ነፍሱ ይጠፋል፣ ዓይን ያጠፋ ዓይኑ ይጠፋል፣ አፍንጫም ያጠፋ አፍንጫው ይጠፋል፣ ጆሮም ያጠፋ ጆሮው ይጠፋል፣ ጥርስ የሰበረ ጥርሱ ይሰበራል። እነዚህ ቁስሎችን በቂሷስ ይፈታሉ፦
5፥45 *”በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ «ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፥ ቁስሎችንም “ማመሳሰል” አለባቸው» ማለትን ጻፍን*፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌ

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ “ማመሳሰል” ለሚለው ቃል የገባው “ቂሷስ” قِصَاص መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። መጥፎ ለሠሩ ሠዎች መጥፎ ቅጣት መቅጣት ቂሷስ ነው፥ የአሏህ መጽሐፍ ጭብጡ ቂሷስ ነው፦
42፥40 *የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም*፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 26
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የአሏህ መጽሐፍ ቂሷስ ነው”*። أَنَّ أَنَسًا، حَدَّثَهُمْ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كِتَابُ اللَّهِ الْقِصَاصُ ‏”‌‏.‏

ከዚህ ሕግ ውጪ ነፍስን መግደል አሏህ እርም አድርጓል፥ ያለ ቂሷስ ነፍስን መግደል ሐራም እና ከዐበይት ኃጢአቶች አንዱ ነው፦
17፥33 *”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْكَبَائِرُ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ ‏”‌‏.‏

“እርም ያረጋት” ለሚለው የገባው ቃል “ሐረመ” حَرَّمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ሐረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የተከለከለ” ማለት ነው፥ እንደውም ያለጥፋት አንድን ሰው መግደል ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነው፦
5፥32 *”በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፥ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው”* ማለትን ጻፍን፡፡ مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا
ከዚህ ውጪ ወሰን ታልፎባቸው ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፦
22፥39 *”ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፡፡ አላህም እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው”*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

አንቀጹ ይቀጥልና ሲበደሉ በቂሷስ ፍትሕ የሚያስተካክሉ አካላት ከሌሉ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም ይፈርሳሉ፦
22፥40 ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት ተፈቀደ፡፡ *”አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም በተፈረሱ ነበር*”፡፡ አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَن يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ ۗ وَلَوْلَا دَفْعُ اللَّهِ النَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّهُدِّمَتْ صَوَامِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَاتٌ وَمَسَاجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا اسْمُ اللَّهِ كَثِيرًا ۗ وَلَيَنصُرَنَّ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

ስለዚህ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና መስጊዶች ማፍረስ ወሰን ማለፍ ነው። “አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። አንደኛው በሌላኛ ፍትሕ ለማስከበር መገፍተሩ ማለትም መጋደል ከሌለ ወሰን አላፊዎች ምድሩቱን ያበላሻሉ። በቂሷስ እነዚያንም ወሰን አላፊዎች በአላህ መንገድ ተጋደሉ! ወሰንንም አትለፉ! አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና፦
2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

የአልረሕማንም ባሮች ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ቂሷስ ሕግ የማይገድሉ ናቸው፥ ነገር ግን ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ቂሷስ ሕግ በመግደል ይህንንም የሚሠራ ሰው ከዱንያ ፍርድ ቢያመልጥ በአኺራ ከአሏህ ቅጣትን ያገኛል፦
25፥68 *”እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል”*፡፡ وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኡሱሉ_ሰላሳ_በኡስታዝ_አቡሀይደር_ያለ_ኔት_ከአማርኛ_ትርጉም_ጋር.apk
57.5 MB
በቃሌ መሰረት #ኡሱሉ_ሱላሳ በኡስታዝ #አቡሀይደር ያለኔት
ከአማርኛ የፅሁፍ ትርጉም ጋር
ከአረብኛ የመትን ፅሁፍ ጋር ይህንን ቀስት ተጭናችሁ አውርዱ

በሁሉም ግሩፕ #ሼርርርርር አድርጉት
🌺🌺🌺
ለምርጥ ምርጥ አፖች
t.me/ISLAMICBOOKSANDAPPS

ወይም

t.me/hussenapp
👆የኡስታዝ አቡ ሐይደር የኡስሉ ሰላሳ ትምህርቶች በአጠቃላይ በኦዲዮ መልኩ አፕልኬሽኑ ላይ ይገኛል። ዳውንሎድ አድርጋችሁ አሰራጩት
ሃሩት እና ማሩት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥102 *”ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩት እና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በእርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ”*፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ

ሰማያውያን ፍጥረታት መላእክት እንደ ጂን እና እንደ ሰው የራሳቸው ሁለት የተለያየ ነጻ ምርጫ የላቸውም። ይህ ክፉን እና ደግ የመምረጥ ነጻ ምርጫ ስለሌላቸው በባሕያቸው ውስጥ ኩራትና አመጽ የለም፦
16፥49 ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሽም በምድር ያለው ሁሉ፣ *”መላእክትም ይሰግዳሉ፡፡ እነርሱም አይኮሩም”*፡፡ وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مِن دَابَّةٍ وَالْمَلَائِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
21፥19 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ *”እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም”*፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَلَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
66፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አሉ፡፡ *”አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ”*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

መላእክት አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ። እዚህ ድረስ ከተግባባን የሚቀጥለውን አንቀጽ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንይ! በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደው የሲሕር ትምህርት ሰዎችን እንዴት እንደሚጎዳ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ነው። ነገር ግን ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት ሰዎችን የሚያስተምሩት ለአሉታዊ ነገር ነበር፦
2፥102 *”ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩት እና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በእርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ”*፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَزَوْجِهِۦ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሃሩትና ማሩት” እንዳመጹ የሚያሳይ ኃይለ-ቃል ወይም ፍንጭ ሽታው የለም። ምናልባት፦ “እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም” የተባለው ስለ ሃሩትና ማሩት መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኃል፦
2፥102 *”እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፥ የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ”*፡፡ وَمَاوَمَا هُم بِضَارِّينَ بِهِ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۚ وَيَتَعَلَّمُونَ مَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُم
ምክንያቱም ሃሩትና ማሩት ሁለት ስለሆኑ ለእነርሱ የምንጠቀምበት ተውላጠ-ስም በሙተና “ሁማ” هُمَا ነው፥ ነገር ግን “በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በእርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም” የተባሉትን ላይ “እነርሱም” ለሚለው የገባው “ሁም” هُم ሲሆን ከሁለት በላይ ጀመዕ መሆኑ “ሸያጢን” شَّيَٰطِين የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው። ሸያጢን ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፥ ሰዎች ከሸያጢን የሚጎዳቸውንና የማይጠቅማቸውንም ይማራሉ።
ሲጀመር እዚህ አንቀጽ ላይ “ወ” وَ የሚለው መስተጻምር ሕዝብን ሲሕር የሚያስተምሩት ሸያጢን እና ሀሩትና ማሩትን የሚያስጠነቅቁበትን ትምህርት ለመለየት የገባ መስተፃምር ነው። ከመነሻው ሸያጢን የሚያስተምሩት ድግምት እና ለሀሩትና ማሩት ተወረደ የተባለው ነገር ሁለት ለየቅል የሆኑ ሀረግ መሆናቸው ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ሃሩትና ማሩት፦ “እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ” እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፥ እነርሱ ላይ የተወረደው ስለ ሲሕር አውንታዊነት ሳይሆን አሉታዊነት የሚያስረዳ ትምህርት ነው።

ሲቀጥል “ማ” مَا የሚለው ቃል ሁለት ፍቺ ይኖረዋል፤ አንዱ “ማ” مَا “መውሱላ” ሲሆን ሁለተኛው “ማ” مَا “መስደሪያ” ነው።
1ኛ. “ማ” مَا የሚለውን “መውሱላ” ማለትም “አንፃራዊ ተውላጠ-ስም” ሆኖ ከተቀራ በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደ ነገር እንዳለ ያመለክታል፥ ያ ነገር ግን ከላይ ባየነው የሰዋስም ሙግት ከሸያጢን ሲሕር ተለይቶ በመስተፃምር ተቀምጧል።
2ኛ. “ማ” مَا የሚለው መስደሪያ ማለት “አፍራሽ-ቃል” በሚለው ከተቀራ ደግሞ በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የሸያጢን ሲሕር አልተወረደም የሚል ፍቺ ይኖረዋል። ምክንያቱም አይሁዳውያን ሚድራሽ በሚባለው መፅሐፋቸው ላይ፦ “ሲሕር በሁለቱ መላእክት በኩል ባቢሎን ላይ ከፈጣሪ የተወረደ ነው” የሚሉትን ቅጥፈት አላህ እያጋለጣቸው ነው። ምክንያቱም አይሁዳውያን አስማት የሰለሞን ጥበብ ነው የሚል እምነት አላቸው፤ ይህንን እሳቤ አንዳንድ ዐበይት ክርስትና በትውፊት ይጋሩታል። ይህንን ነጥብ ኢብኑ ዐባሥ፣ ኢብኑ ጀሪር፣ ቁርጡቢ ያነሱታል።

ሢሰልስ “ሀሩትና ማሩት” ማንና ምን ናቸው? የሚለውን ነጥብ ሁለት አመለካከቶች አሉት፤ ይህንም ጤናማ የተለያየ አመለካከት ያመጣው ጤናማው የቂርኣት ውበት ነው፥ “መለከይኒ” مَلَكَيْنِ የሚለው ቃል ”መለክ” مَلَك ማለትም ”መልአክ” ለሚለው ቃል ሙተና”dual” ሲሆን “ሁለት መላእክት” የሚል ፍቺ የሚኖረው “ላምን”ل ላም ፈትሓ “ለ” لَ ተብሎ ሲቀራ ነው። ሌላው “መሊከይኒ” مَلِكَيْنِ የሚለው ቃል “መሊክ” مَلِك ማለትም “ንጉሥ” ቃል ሙተና ሲሆን “ሁለት ነገሥታት” የሚል ፍቺ “ላምን” ل ላም ከስራ “ሊ” لِ ተብሎ ሲቀራ ነው። ሁለቱም ቂርኣት ከመለኮት የተወረደ እስከሆነ ድረስ በሁለቱም መቅራት ይቻላል። ይህ ነጥብ በጀላለይን፣ በአጥ-ጠበሪ፣ በዛማኽሻሪ፣ በባጋዊ እና በራዚ ተወስቷል። የውይይታችን ዋናውና ተቀዳሚው ሙግት ሀሩትና ማሩት ማንና ምን ናቸው? ሳይሆን "መላእክት በፍጹም አምጸው አያውቁም" የሚል ነው።

ከዐቃቤ እስስልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የንጽጽር ትምህርት ያለ የኢንተርኔት ማንበብ ለምትፈልጉ ይህንን አፕ ያውርዱ፦
https://www.mediafire.com/file/pzlrw8mhc8rcgwc/Ustaz_Wahid.apk/file
የሴት ስብራት

ሴት ከጎንህ የተፈጠረች አጥንት ናት፥ በደግነት ካልያስካት ትሰበራለች፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 17, ሐዲስ 80″
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንም በአሏህ እና በመጨረሻ ቀን የሚያምን በምንም ነገር ሲመሰክር መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል! ሴትን በደግነት ተንከባከቡ! ሴት የተፈጠረችው ከጎን አጥንት ነውና"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَإِذَا شَهِدَ أَمْرًا فَلْيَتَكَلَّمْ بِخَيْرٍ أَوْ لِيَسْكُتْ وَاسْتَوْصُوا بِالنِّسَاءِ فَإِنَّ الْمَرْأَةَ خُلِقَتْ مِنْ ضِلَعٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 138
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"እርስ በእርሳችሁ አትጠላሉ፣ እርስ በእርሳችሁ አትነቃቀፉ፣ የአላህ ባሮች ወንድማማች ሁኑ። ሙሥሊም ወንድሙን ከሦስት ሌሊት በላይ ማኩረፍ አይፈቀድም"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تَبَاغَضُوا وَلاَ تَحَاسَدُوا وَلاَ تَدَابَرُوا وَكُونُوا عِبَادَ اللَّهِ إِخْوَانًا وَلاَ يَحِلُّ لِمُسْلِمٍ أَنْ يَهْجُرَ أَخَاهُ فَوْقَ ثَلاَثِ لَيَال

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 93
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አንድ ባሪያ የሌላውን ባሪያ ነውር በዚህ ዓለም የደበቀለት አላህ የትንሳኤ ቀን ነውሩን ይደብቅለታል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ يَسْتُرُ عَبْدٌ عَبْدًا فِي الدُّنْيَا إِلاَّ سَتَرَهُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَة

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 51
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የአንድ ሰው እሥልምናው ማማሩ ምልክት የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ مِنْ حُسْنِ إِسْلاَمِ الْمَرْءِ تَرْكُهُ مَا لاَ يَعْنِيهِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 46
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَسْكُتْ ‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ነቢዩ ኢስማዒል

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥54 በመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ *መልክተኛ ነቢይም ነበር*፡፡ وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا

“ኢስማኢል” إِسْمَٰعِيْل የሚለው የዐረቢኛው ቃል የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ኢስማ” إِسْم ማለት “ሰማኝ” ማለት ሲሆን “ኢል” َٰعِيْل ማለት “አምላክ” ማለት ነው፤ “አምላክ ጸሎቴን ሰማኝ” ማለት ነው፤ ኢብራሂም ወደ አላህ ልመናው፦ “ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን ልጅ ስጠኝ” የሚል ነበር፤ አላህም ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰረው፤ በዚህ ምክንያት “ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና” አለ፦
37፥100 *ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን ልጅ ስጠኝ*፡፡ رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّٰلِحِينَ
37፥101 *ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው*፡፡ فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢ
14፥39 «ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ *ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ* አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡ *ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና*፡፡ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي وَهَبَ لِي عَلَى الْكِبَرِ إِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ ۚ إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ الدُّعَاءِ

አላህ ወደ ኢስማዒል ወሕይ አውርዷል፤ አላህ ስለ ኢስማኢል ሲናገር “በኢስማዒልም ላይ በተወረደው አመንን በሉ” በማለት ግህደተ-መለኮት ወርዶለት እንደነበር ይናገራል፦
3፥84 «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም፣ በኢብራሂምና *በኢስማዒልም*፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ በነገዶችም ላይ *በተወረደው*፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው *አመንን*፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» *በል*፡፡ قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «በአላህ እና ወደኛ በተወረደው ወደ ኢብራሂምም *ወደ ኢስማዒል* እና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም *በተወረደው* በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከእነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን *አመንን*፤ እኛም ለእርሱ ለአላህ ታዛዦች ነን» *በሉ*፡፡ قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
4፥163 እኛ ወደ ኑሕ እና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ *ወደ ኢስማዒልም*፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም *አወረድን*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا

ኢስማዒልን መልክተኛ ነቢይም ነበር፦
19፥54 በመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ *መልክተኛ ነቢይም ነበር*፡፡ وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا
19፥55 ቤተሰቦቹንም *በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር*፡፡ እጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር፡፡ وَكَانَ يَأْمُرُ أَهْلَهُ بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِ مَرْضِيًّا

“እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና” ይለናል፤ የትኛውን ቀጠሮ አክባሪ ነው? ይህም ቀጠሮ ኢብራሂም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፤ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፤ እርሱም «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፦
37፥102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ *«ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ»* አለ፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

እጌታውም ዘንድ ተወዳጅና ከመልካሞቹ የሆነ ይህ ልጅ አላህ ለኢብራሂም የሰጠው የበኩር ልጅ ነው፦
14፥39 «ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ *ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ* አላህ ምሰጋና ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና፡፡ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي وَهَبَ لِي عَلَى الْكِبَرِ إِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ ۚ إِنَّ رَبِّي لَسَمِيعُ الدُّعَاءِ

እዚህ አንቀጽ ላይ ከኢስሐቅ በፊት ኢስማዒል መጠቀሱ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ አላህ በልጅ ጉዳይ ኢብራሂም ያበሰረው ሁለት ጊዜ ነው፤ የመጀመሪያው፦ “ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው” የሚል ነው፦
37፥101 *ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው*፡፡ فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢا
በመቀጠል ሁለተኛው፦ “በኢስሐቅም አበሰርነው” የሚል ነው፦
37፥103 *በኢስሐቅም አበሰርነው*፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّۭا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

“አበሰርነው” የሚለው ቃል አንድ ዐውድ ላይ ሁለቴ መምጣቱ ኢስሐቅ እና ከላይ የተጠቀሰው በዱዓ የመጣው ልጅ ይለያያሉ፤ በተጨማሪም “ወ” و የሚለው አርፉል አጥፍ ብስራቱ ሁለት ጊዜ መሆኑን ያሳያል፤ አንደኛው ረድፍ “ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅ” ሲሆን ሁለተኛው ረድፍ “በኢስሐቅም አበሰርነው” የሚለው ነው፤ ኢስሐቅ ደግሞ ኢብራሂም አላህን ለምኖ የተሰጠ ልጅ ሳይሆን አንወልድም ብለው ተስፋ በቆረጡበት የተበሰሩት ልጅ ነው፦
15፥53 «አትፍራ፤ እኛ ዐዋቂ በኾነ ወንድ ልጅ *እናበስርሃለን*» አሉት፡፡ قَالُوا۟ لَا تَوْجَلْ إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَٰمٍ عَلِيمٍۢ
15፥54 *«እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ»* አለ፡፡ قَالَ أَبَشَّرْتُمُونِى عَلَىٰٓ أَن مَّسَّنِىَ ٱلْكِبَرُ فَبِمَ تُبَشِّرُونَ
15፥55 «በእውነት *አበሰርንህ፡፡ ከተሰፋ ቆራጮችም አትኹን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ بَشَّرْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ فَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْقَٰنِطِينَ
11፥71 ሚስቱም የቆመች ስትኾን አትፍራ አሉት፤ ሳቀችም፡፡ *በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ በልጁ በያዕቁብ አበሰርናት*፡፡ وَٱمْرَأَتُهُۥ قَآئِمَةٌۭ فَضَحِكَتْ فَبَشَّرْنَٰهَا بِإِسْحَٰقَ وَمِن وَرَآءِ إِسْحَٰقَ يَعْقُوبَ

ኢብራሂም በኢስሀቅ ሲበሰር፦ “እርጅና የደረሰብኝ ከመኾኔ ጋር አበሰራችሁኝን በምን ታበስሩኛላችሁ?” ማለቱ ለምኖ ያገኘው ልጅ ሳይሆን ያላሰበው ልጅ መሆኑ ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል፤ ኢብራሂም የተበሰረው በኢስሀቅ ብቻ ሳይሆን በልጅ ልጁ በያዕቁብም ነው፤ ኢብራሂም ኢስሀቅ ሳይታረድ ተርፎ የልጅ ልጁ ያዕቆብ እንደሚወለድ ካወቀ፤ ኢስሀቅ ያዕቁብ የሚባል ልጅ እንደሚኖረዉ አስቀድሞ ከተበሰረ ልጅህን እረድልኝ ብሎ ማዘዙ ፈተናው ትርጉም አልባ ይሆን ነበር፤ ምክንያቱም ልጅህን እረድልኝ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፤ ፈተና ትርጉም የሚኖረው ተፈታኙ የሚፈተነውን የማያውቅ ሲሆን ብቻ ነው፦
37፥106 ይህ እርሱ በእውነት ግልጽ ፈተና ነው፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ ٱلْبَلَٰٓؤُا۟ ٱلْمُبِينُ
37፥102 ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰ ۚ قَالَ يَٰٓأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُ ۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّٰبِرِينَ

በተጨማሪም አላህ ኢብራሂምንም በቃላት በፈተነው ጊዜ ተያይዞ ኢብራሂምና ኢስማኢል የአላህን ቤት መሠረቶቹን ከፍ በማድረግ እና አላህም፦ “ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ” ብሎ ያዘዘው ኢብራሂምና ኢስማኢል ነው፦
2፥124 *ኢብራሂምንም ጌታው በቃላት በፈተነው* እና በፈጸማቸው ጊዜ አስታውስ፤ «እኔ ለሰዎች መሪ አድራጊህ ነኝ» አለው፡፡ «ከዘሮቼም አድርግ» አለ፡፡ ቃል ኪዳኔ በዳዮቹን አያገኝም አለው፡፡ وَإِذِ ٱبْتَلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ رَبُّهُۥ بِكَلِمَٰتٍۢ فَأَتَمَّهُنَّ ۖ قَالَ إِنِّى جَاعِلُكَ لِلنَّاسِ إِمَامًۭا ۖ قَالَ وَمِن ذُرِّيَّتِى ۖ قَالَ لَا يَنَالُ عَهْدِى ٱلظَّٰلِمِينَ
2፥127 *ኢብራሂምና ኢስማኢልም «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَاهِيمُ الْقَوَاعِدَ مِنَ الْبَيْتِ وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ *ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም* ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ *ስንል* ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

ይህ እርድ የሚካሄድበት ቦታ በመካ እንጂ በሻም አለመሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እንግዲህ ከእነርሱ የትውልድ መስመር በትንቢት ቃል ኪዳን የተገባላቸው የነብያት መደምደሚያ ነብያችን”ﷺ” መጥተዋል፦
2፥129 «ጌታችን ሆይ! *በውስጣቸውም ከእነርሱው የኾነን መልክተኛ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክ*፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» የሚሉም ሲኾኑ፡፡ رَبَّنَا وَٱبْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًۭا مِّنْهُمْ يَتْلُوا۟ عَلَيْهِمْ ءَايَٰتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
2፥151 *በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁና የሚያጠራችሁ፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ*፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُونَ

በቁርአን ላይ ስለ ነቢዩ ኢስማዒል ያለውን ምልከታ ለእይታ ያክል ካየን ዘንዳ ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ነቢዩ ኢስማዒል በባይብል ላይ ያለውን ምልከታ ለእይታ ያክል እንመለከታለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነብዩ ኢስማዒል

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥54 በመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ *መልክተኛ ነቢይም ነበር*፡፡ وَاذْكُرْ فِي الْكِتَابِ إِسْمَاعِيلَ ۚ إِنَّهُ كَانَ صَادِقَ الْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا

ከነብያችን”ﷺ” በፊት የተከሰቱን የሩቅ ወሬዎች ቁርአን ላይ ያሉት ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አንዱ አምላክ አላህ ያወረደው ነው፤ ኢብራሂም እንዲህ ብለን “አበሰርነው” እያለን የሚተርክልን እራሱ ሁሉን ዐዋቂው አላህ ነው፦
25፥6 «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡ قُلْ أَنزَلَهُ ٱلَّذِى يَعْلَمُ ٱلسِّرَّ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ إِنَّهُۥ كَانَ غَفُورًۭا رَّحِيمًۭا
11፥120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን *እንተርክልሃለን*፡፡ وَكُلًّا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ الرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِ فُؤَادَكَ ۚ وَجَاءَكَ فِي هَـٰذِهِ الْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
37፥101 *ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው*፡፡ فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍۢ
37፥103 *በኢስሐቅም አበሰርነው*፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን፡፡ وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّۭا مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

ነገር ግን የዘፍጥረት ትረካ የአምላክ ንግግር ሳይሆን በቶራህ ላይ የተጨመረ ታሪክ ነው፤ ይህንን ታሪክ የሚተርክልን ማን እንደሆነ አይታወቅም። “ቶራህ” תּוֹרָה የሚለው የዕብራይስጥ ቃል “ሕግ” “ትዕዛዝ” “መመሪያ” “መርህ” ማለት ነው፣ ይህ ሕግ ለሙሴ የተሰጠው በ 1312 BC ሲሆን በዚህ ሕግ ላይ መጨመር ሆነ መቀነስ ክልክል ነው፦
ዘዳግም 4፥2 እኔ ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን *ትእዛዝ* ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ *አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም*።

ነገር ግን ከ 600 BC ተጀምሮ በ 400 BC ውስጥ “ፔንታተች” πεντάτευχος ተዘጋጀ፤ “ፔንታ” πεντά ማለት “አምስት” ማለት ሲሆን “ተች” τευχος ማለት ደግሞ “ጥቅል” ማለት ነው፤ አንድ የነበረውን መጽሐፍ ከፋፍለው አምስት አደረጉት፤ እነርሱም ዘፍጥረት፣ ዘጸአት፣ ዘሌዋውያን፣ ዘኁልቅ፣ ዘዳግም ናቸው፣ ዘፍጥረት ላይ ያለው ተራኪ ከ 600 BC ተጀምሮ በ 400 BC ያለ ታሪክ ዘጋቢ እንጂ ሙሴ ወይም ፈጣሪ የተናገረው አይደለም፤ ይህንን ለዘብተኛ ምሁራን ሆነ ጽንፈኛ ምሁራን ይስማማሉ፤ ከዚያም ባሻገር ከ 600 BC ተጀምሮ በ 400 BC የተዘጋጁት የመጀመሪያው “አሲል” أصیل ማለት “ሥረ-መሰረት”origin” የለም። ዛሬ ያለው ቀዳማይ እደ-ክታብ የግሪክ ሰፕቱአጀንት”LXX” ሲሆን ቅጂ ነው፤ የሙት ባህር ጥቅል የሚባሉትም ብጥስጣሽ ቅጂ እንጂ ኦርጅናል የሚባል ቃል የለም።

ያ ማለት ግን ውስጡ እውነታነት ያለው ቁም ነገር የለውም ማለት እንዳልሆነም አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ታሪክ ማስረጃ መሆን ባይችልም መረጃ ግን ይሆናል፤ ይህንን እሳቤ ይዘን ወደ ነብዩ ኢስማዒል ጉዳይ እንግባ፦

ነጥብ አንድ
“ኢሽማኤል”
“ኢሽማኤል” יִשְׁמָעֵאל‎ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ኢሽማ” שָׁמַע ማለት “ሰማኝ” ማለት ሲሆን “ኤል” אֵל ማለት “አምላክ” ማለት ነው፤ “አምላክ ጸሎቴን ሰማኝ” ማለት ነው፤ ይህ ስም የወጣበት ምክንያት አብራምም፦ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? ያለ ልጅ እሄዳለሁ” ብሎ ለለመነው ልመና መልስ ሲሆን “ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል” የሚል ምላሽ ነው፤ ሲወለድም፦ “ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ” በማለት የአብርሃም ልመና መሆኑን ያሳያል፦
ዘፍጥረት 15፥2 አብራምም፦ *አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ ምንን ትሰጠኛለህ? እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ*፤ የቤቴም መጋቢ የደማስቆ ሰው ይህ ኤሊዔዘር ነው፡ አለ። አብራምም፦ *ለእኔ ዘር አልሰጠኸኝም፤ እነሆም፥ በቤቴ የተወለደ ሰው ይወርሰኛል* አለ። እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን *ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል*።
ዘፍጥረት 17፥20 *ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ ባርኬዋለሁ*፥ ፍሬያምም አደርገዋለሁ፥ እጅግም አበዛዋለሁ፤ አሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፥ ታላቅ ሕዝብም እንዲሆን አደርገዋለሁ።

ይህንን ስም ያወጣው ሰው ሳይሆን ፈጣሪ በመልአኩ ያወጣለት ስም ነው፤ ከዚያ አብርሃምም የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው፦
ዘፍጥረት 16፥11 የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ *ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ*፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
ዘፍጥረት16፥15 አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን *የልጁን ስም እስማኤል ብሎ ጠራው*።
ነጥብ ሁለት
“የበኵር ልጅ”
ብዙ ሰዎች እስማኤል የአብርሃም ልጅ አይደለም፤ ጭራሽ አልተባረከም የሚል ሙግት አላቸው፤ ይህ የሚያሳየው ምን ያህል መጽሐፋቸውን እንደማያነቡት ነው፤ እስማኤል የአብርሃም ልጅና ዘር ስለመሆኑና ስለመባረኩ በቁና መረጃ ይኸው፦
ዘፍጥረት 17፥26 በዚያው ቀን አብርሃም ተገረዘ፥ *ልጁ እስማኤልም*።
ዘፍጥረት 16፥15 አጋርም ለአብራም ወንድ ልጅን ወለደችለት፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን *የልጁን ስም እስማኤል* ብሎ ጠራው።
ዘፍጥረት25፥9 *ልጆቹ ይስሐቅና እስማኤልም* በመምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬጢያዊ በሰዓር ልጅ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆነው ዋሻ ውስጥ ቀበሩት።
ገላቲያ 4፥22 አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ *ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት* ተጽፎአልና።
ዘፍጥረት 21፥13 የባሪያይቱን ልጅ ደግሞ ሕዝብ አደርገዋለሁ፥ *ዘርህ ነውና*።
ዘፍጥረት 17፥20 *ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ ባርኬዋለሁ*፥ ፍሬያምም አደርገዋለሁ፥ እጅግም አበዛዋለሁ፤ አሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፥ ታላቅ ሕዝብም እንዲሆን አደርገዋለሁ።

እስማኤል የአብርሃም የበኵር ልጅ ማለትም የመጀመሪያ ልጅ ነው፤ ምክንያቱም አብርሃምም ልጁ እስማኤልን ሲወልድ የሰማንያ ስድስት ዓመት ዕድሜ ነበረ፤ ይስሐቅን ሲወልድ ደግሞ የመቶ ዓመት ዓመት ዕድሜ ነበረ፤ ስለዚህ እስማኤል ይስሐቅን በአስራ አራት ዓመት ይበልጠዋል፦
ዘፍጥረት 16፥16 አጋር እስማኤልን ለአብራም በወለደችለት ጊዜ *አብራም የሰማንያ ስድስት ዓመት ሰው ነበረ*።
ዘፍጥረት 21፥5 አብርሃምም ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ *የመቶ ዓመት ዕድሜ ነበረ*።

አብርሃም አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ነበሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ወልደውለታል፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ሲሆን፥ በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር አላደረገም፤ ነገር ግን ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ አስታውቋል፤ የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው፤ ይህንን ሕግ አብርሃም ጠብቋል፦
ዘፍጥረት 26፥5 አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን *ሕጌንም ጠብቆአልና*።
ዘዳግም 21፥15-17 *ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት*፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ *በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን*፥ ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት *ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው*።

ልጆቹ እስማኤልና ይስሐቅ ሲሆኑ ጽድቅና ፍርድ በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ አዟቸዋል፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ተፈጽሟል፦
ዘፍ 18፡18-19 ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ *የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹን እና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው*።

ነጥብ ሦስት
“የእርዱ ልጅ”
በሙሴ ሕግ አስቀድሞ የተወለደው የበኲር ልጅ ለእግዚአብሔር ይሆናል፤ የበኵር ልጅ በእርሱ ፋንታ እንስሳ ይታረዳል፦
ዘጸአት 13፥2 በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማሕፀንን የሚከፈት *በኵር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ የእኔ ነው*።
ዘጸአት 13፥12 ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ለይ፤ ከሚሆንልህ ከብት ሁሉ ተባት ሆኖ *አስቀድሞ የተወለደው ለእግዚአብሔር ይሆናል*።
ዘጸአት 13፥15 ስለዚህ ወንድ ሆኖ ማሕፀንን የከፈተውን ሁሉ *ለእግዚአብሔር እሠዋለሁ፥ ነገር ግን የልጆቼን በኵር ሁሉ እዋጃለሁ*።

ይህንን የሙሴ ሕግ አብርሃም ፈጽሞታል፦
ዘፍጥረት 26፥5 አብርሃም ቃሌን ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን *ሕጌንም ጠብቆአልና*።
ዘፍጥረት 22፥16 እንዲህም አለው፦ እግዚአብሔር፦ በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ *አንድ ልጅህንም* አልከለከልህምና፤

“አንድ ልጅህን” የሚለው ይሰመርበት፤ አብርሐም አንድ ልጅ ብቻ ነው ያለው? በፍፁም ግን ሁለተኛ ልጅ እስኪመጣ ድረስ የበኲር ልጅ ለወላጅ አንድ ልጅ ነው፦
ዘካርያስ 12፥10 ሰውም *ለአንድያ ልጁ* እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም *ለበኵር ልጁ* እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።
ሉቃስ 7፥12 ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ የሞተ ሰው ተሸክመው አወጡ፤ እርሱም ለእናቱ *አንድ ልጅ* ነበረ፥ እርስዋም መበለት ነበረች፥ ብዙም የከተማ ሕዝብ ከእርስዋ ጋር አብረው ነበሩ።
ሉቃስ 9፥38 እነሆም፥ ከሕዝቡ አንድ ሰው እንዲህ እያለ ጮኸ፦ መምህር ሆይ፥ ለእኔ *አንድ ልጅ* ነውና ልጄን እንድታይልኝ እለምንሃለሁ።

እውን ይስሐቅ ቢሆን የእርዱ ልጅ አንድ ልጅህን የሚለው ትርጉም ይሰጣልን? ይስሐቅ ከመወለዱ በፊት አድጎ ዘር እንደሚኖረው ለአብርሃም ተነግሮታልም፤ ያውቃልም፦
ዘፍጥረት 17፥19 እግዚአብሔርም አለ፦ በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ *ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ* የዘላለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።

ታዲያ አብርሐም ልጁ ይስሐቅ ሳይወለድ ዘሩ እንደሚቀጥል እያወቀ ፈተና ነው ማለት ትርጉም ይኖረዋልን? ምክንያቱም ልጅህን እረድልኝ ፈተና ነው፤ ፈተና ትርጉም የሚኖረው ተፈታኙ የሚፈተነውን የማያውቅ ሲሆን ብቻ ነው፦
ዘፍጥረት 22፥1 ከእነዚህም ነገሮች በኋላ *እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው*፥ እንዲህም አለው፦ አብርሃም ሆይ። አብርሃምም፦ እነሆ፥ አለሁ፡ አለ።
ነጥብ አራት
“የተስፋ ቃል”
እስማኤል በባይብል ነብይ መሆኑ አልተገለጠም፤ እርሱ ብቻ ሳይሆን ይስሐቅም ያዕቆብም ነብይ መሆናቸው አልተገለጠም፤ ስለዚህ ነብይ ነው ወይስ አይደለም ብለን አንሞግትም፤ ነገር ግን እንደ ነብይ አምላክ ከእስማኤል ጋር ነበረ፦
ዘፍጥረት 21፥20 *እግዚአብሔርም ከብላቴናው ጋር ነበረ*፤ አደገም፥ በምድረ በዳም ተቀመጠ፥ ቀስተኛም ሆነ።
ዘፍጥረት 39፥2 *እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ*፥
ዘጸአት 34፥28 በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት *ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ*፤
ኢያሱ 6፥27 *እግዚአብሔርም ከኢያሱ ጋር ነበረ*፤
1ኛ ሳሙኤል 3፥19 ሳሙኤልም አደገ፥ *እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ*፤
1ኛ ሳሙኤል18፥14 ዳዊትም በአካሄዱ ሁሉ አስተውሎ ያደርግ ነበር፤ *እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ*።

አንድ ነብይ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር የሚሆነው ሊያናግረው ነው፤ ነብይ ማለት አምላክ የሚያናግረው ማለት ነው፤ እስማኤል እና እናቱ በፋራን ምድረ-በዳ ተቀመጡ፤ “ዐረብ” ማለት ትርጉሙ “ምድረ-በዳ” ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 21፥20 በ*ፋራን ምድረ በዳም ተቀመጠ*፤ እናቱም ከምድረ ግብፅ ሚስት ወሰደችለት።
ገላትያ 4፥25 ይህችም *አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ-ሲና ናት*፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።

“ደብር” ማለት “ተራራ” ማለት ነው፤ “አድባር” ማለት “ተራሮች” ማለት ነው፤ “ደብረ ሲና” ማለት “የሲና ተራራ” ማለት ነው፤ ሲና ዐረብ አገር እንዳለች ይህ ጥቅስ ያስረዳል፤ ፋራን ማለት መካ፣ መዲና እና ታቡክ እንደሆነ የታሪክ ምሁራን በመድብለ-ዕውቀት ላይ አስፍረዋል፤ ከዚያም ባሻገር የቂሳርያው አውሳቢዮስና የሮሙ ጄሮም ፋራን በዐረቢያ ውስጥ እንደምትገኝ በድርሳናቸው ውስጥ አስፍረዋል፦ “Eusebius of Caesarea, Onomasticon Biblical Dictionary (1971) Translation. pp. 1-75. entry for Pharan No 917“ ከዚህ ከዐረብ ቦታ ካለችው ከፋራን የአምላክ ቅዱስ እንደሚመጣ ትንቢት ነበረ፦
ዕንባቆም 3፥3 እግዚአብሔር ከቴማን፥ *ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል*። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።

“የእርሱ ቅዱስ”his holy one” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “ኤሎሃ” אֱל֙וֹהַ֙ ማለት “አምላክ” ማለት ሲሆን “የእርሱ ቅዱስ” ከአምላክ ለመለየት “ወ” וְ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፤ ይህ የአምላክ ቅዱስ “የቦው” יָב֔וֹא ማለትም “ይመጣል” በሚል በወደፊት ግስ ተተንብዮ ነበር፤ ይህ የአምላክ ቅዱስ ከፋራን የመጡት ነብያችን”ﷺ” ብቻ ናቸው፤ አይ ሌላ የአምላክ ቅዱስ ነው የመጣው አሊያም ወደ ፊት የሚመጣው ነው ከተባለ መረጃና ማስረጃ ማስቀመጥ ነው፤ ምን ይህ ብቻ ነብያችን”ﷺ” ከባልደረቦቻቸው ጋር በ 622 AD ያደረጉትን ስደት ቁልጭ እና ፍትንው ተደርጎ በትንቢት ተቀምጧል፦
ኢሳይያስ 21፥13-15 *ስለ ዓረብ የተነገረ ሸክም*፤ የድዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፥ በዓረብ ዱር ውስጥ ታድራላችሁ። በቴማን የምትኖሩ ሆይ፥ *ወደ ተጠሙት ሰዎች ውኃ አምጡ እንጀራ ይዛችሁ የሸሹትን ሰዎች ተቀበሉአቸው*። *ከሰይፍ፥ ከተመዘዘው ሰይፍ፥ ከተለጠጠውም ቀስት ከጽኑም ሰልፍ ሸሽተዋልና*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም