ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መሥጂድ ፈረሰ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፡፡ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፡፡ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፡፡ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች፡፡ ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ ልብ የምታደርጉ እንደኾናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

በምድር ላይ ያሉት መስጊዶች ሁሉ የአላህ ብቻ ናቸው። በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አንገዛም፤ ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ እናወድሰዋለን፥ በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ እናጠራለን። መስጊዶች በውስጣቸው የአላህ ስሙ እንዳይወሳ የሚከለክሉ እና መስጊዶች በማፈራረስ እንዳይገነባ ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፥ ለእነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፦
2፥114 *”የአላህንም መስጊዶች በውስጣቸው ስሙ እንዳይወሳ ከከለከለና እርሷንም በማበላሸት ከሮጠ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው?”* እነዚያ ፈሪዎች ኾነው እንጂ ለእነርሱ በቅርቢቱ ዓለም ውርደት አላቸው፡፡ ለነርሱም በመጨረሻይቱ አገር ታላቅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن مَّنَعَ مَسَاجِدَ اللَّهِ أَن يُذْكَرَ فِيهَا اسْمُهُ وَسَعَىٰ فِي خَرَابِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ مَا كَانَ لَهُمْ أَن يَدْخُلُوهَا إِلَّا خَائِفِينَ ۚ لَهُمْ فِي الدُّنْيَا خِزْيٌ وَلَهُمْ فِي الْآخِرَةِ عَذَابٌ عَظِيمٌ

መሥጂድ ሲያፈራርሱ እጃችሁን አጣምራችሁ እዩ አልተልተባለም። ነገር ግን ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፦
22፥39 *”ለእነዚያ ለሚገደሉት ምእመናን እነርሱ የተበደሉ በመኾናቸው መጋደል ተፈቀደላቸው፡፡ አላህም እነርሱን በመርዳት ላይ በእርግጥ ቻይ ነው”*፡፡ أُذِنَ لِلَّذِينَ يُقَاتَلُونَ بِأَنَّهُمْ ظُلِمُوا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ نَصْرِهِمْ لَقَدِيرٌ

አንቀጹ ይቀጥልና ሲበደሉ ፍትሕ የሚያስተካክሉ አካላት ከሌሉ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም ይፈርሳሉ፥ ይለናል፦
22፥40 ለእነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ከማለታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ከአገራቸው የተባረሩ ለሆኑት ተፈቀደ፡፡ *”አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ ባልነበረ ኖሮ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና በውስጣቸው የአላህ ስም በብዛት የሚወሳባቸው መስጊዶችም በተፈረሱ ነበር*”፡፡ አላህም ሃይማኖቱን የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል፡፡ አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና፡፡ الَّذِينَ أُخْرِجُوا مِن دِيَارِهِم بِغَيْرِ حَقٍّ إِلَّا أَن يَقُولُوا رَبُّنَا اللَّهُ ۗ وَلَوْلَا دَفْعُ اللَّهِ النَّاسَ بَعْضَهُم بِبَعْضٍ لَّهُدِّمَتْ صَوَامِعُ وَبِيَعٌ وَصَلَوَاتٌ وَمَسَاجِدُ يُذْكَرُ فِيهَا اسْمُ اللَّهِ كَثِيرًا ۗ وَلَيَنصُرَنَّ اللَّهُ مَن يَنصُرُهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ

ስለዚህ ገዳማት፣ ቤተክርስቲያኖችም፣ ምኩራቦችም እና መስጊዶች ማፍረስ ወሰን ማለፍ ነው። “አላህ ሰዎችን ከፊላቸውን በከፊሉ መገፍተሩ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። አንደኛው በሌላኛ ፍትሕ ለማስከበር መገፍተሩ ማለትም መጋደል ከሌለ ወሰን አላፊዎች ምድሩቱን ያበላሻሉ። የታከለ ኡማ አስተዳደር የመሥጂድ ማፍረስ መንስኤ ፍትሕ ያለመኖር፥ በነሲብ፣ በስሜት፣ በጭፍን ከማሰብ፣ ከመናገር፣ ከመተግበር የመጣ ነው። ከዛ ይልቅ የሙሥሊሙ ደም በመካከለኛው ምስራቅ እንደ ጎርፍ ሲፈስ እየታየ ነው። ችግሩ ያለው ግን እኛ ጋርም ነው ባይ ነኝ። ምክንያቱም አምላካችን አላህ እውነቱን ቀድሞውኑ ነግሮናል፦
3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፡፡ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፡፡ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፡፡ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች፡፡ ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ ልብ የምታደርጉ እንደኾናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

"ማበላሸትን አይገቱላችሁም" ማለት እኛን ለማጥፋት አያንቀላፉም። "ጉዳታችሁን ይወዳሉ" ማለት ኢሥልምና ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ ሲሉ እያየን ነው። "ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች" ማለት እንደነ ዘመድኩን በቀለ ያሉ በሚድያ ላጫቸውንና ቅርሻታቸውን የሚያዝረከርኩ አሉ። ከእነሱ ይልቅ ሙሥሊሙ እንደሚወዱ አፈ ቅቤ፤ ልበ ጬቤ ሰዎች ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች እሥልምና ዶግ አመድ ቢሆንላቸው የልባቸው ምኞች ነው። የኢሥላም እድገት፥ የሙሥሊሙ ጥንካሬ ያስከፋቸዋል። የሙሥሊሙ ውድቀት ደስታቸው ነው፦
3፥120 ደግ ነገር ብትነካችሁ ታስከፋቸዋለች፡፡ መጥፎም ነገር ብታገኛችሁ በእርሷ ይደሰታሉ፡፡ ብትታገሱና ብትጠነቀቁም ተንኮላቸው ምንም አይጎዳችሁም፡፡ አላህ በሚሠሩት ሁሉ በዕውቀቱ ከባቢ ነውና፡፡ إِن تَمْسَسْكُمْ حَسَنَةٌ تَسُؤْهُمْ وَإِن تُصِبْكُمْ سَيِّئَةٌ يَفْرَحُوا بِهَا ۖ وَإِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا لَا يَضُرُّكُمْ كَيْدُهُمْ شَيْئًا ۗ إِنَّ اللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطٌ

አላህ በሚሠሩት ሁሉ በዕውቀቱ ከባቢ ነውና ብንታገስና ብንጠነቅ ቅቤ አንጓችና አስብቶ አራጅ ተንኮላቸው ምንም አይጎዳንም፡፡ "ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ" ተብለናል። አለመዝረክረክ ነው። አላህ ጥንቁቆች ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሠለፍ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነርሱ ወዷል እነርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

"ሠለፍ" سَلَف የሚለው በሰፊው የሚነገር ቃል "ሠለፈ" سَلَفَ ማለትም "ቀደመ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቀደምት" ማለት ሲሆን "ሠለፊይ" سَلَفِيّ ማለት ደግሞ "ቀዳማይ" ማለት ነው። የሠለፊይ ብዙ ቁጥር "ሠለፊዩን" سَلَفِيُّون‎ ሲሆን "ቀዳማውያን" ማለት ነው። አምላካችን አላህ ስለ ቀዳማውያን እንዲህ ይናገራል፦
9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ "የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች" እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነርሱ ወዷል እነርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

"የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። እነዚህም "ሰሓቢይ" صَحَابِيّ ሲባሉ የነቢያችን”ﷺ” ውድ “ባልደረባ”companion” ናቸው። እነዚህ ባልደረቦች በሁለት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦ “ሙሃጂር” እና “ነሲር” ናቸው። “ሙሃጂር” مُهَاجِر ማለት “ስደተኛ” ማለት ሲሆን የሙሃጂር ብዙ ቁጥር "ሙሃጂሩን" مُهَاجِرُون ነው፥ ሙሃጂሩን ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱትን መካውያን ሰሓባዎችን ያመለክታል። መዲና ላይ ከመካ የተሰደዱትን እረድተው የተቀበሉ ሰሓባዎች “ነሲር” نَصِير ማለትም “ረዳት” በብዜት “አንሷር” أَنْصَار ይባላሉ፦
8፥74 *እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉ እና የረዱ እነዚያ እነርሱ በእውነት አማኞች ናቸው፡፡ ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

"የተሰደዱ" የተባሉት ሙሃጂሩን ሰሓቢይ ሲሆኑ "የረዱ" የተባሉት ደግሞ አንሷር ሰሓቢይ ናቸው፥ እነዚህ የመጀመሪያው ትውልድ ናቸው። "የተከተሏቸው" የተባሉት ሁለተኛው ትውልድ "ታቢዒይ" تَابِعِيّ እና ሦስተኛው ትውልድ "ታቢዑ አት-ታቢዒን" تَابِع التَابِعِين ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ ሠለፍይ ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 72
ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ከእናንተ ምርጡ የእኔ ትውልድ ነው፥ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ነው፥ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ናቸው”*። قَالَ سَمِعْتُ عِمْرَانَ بْنَ حُصَيْنٍ، يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم

የመጀመሪያው ትውልድ ሰሓቢይ ነው፣ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ታቢዒይ ነው፣ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ታቢዑ አት-ታቢዒን ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ "አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን" ٱلسَلَف ٱلصَالِحُون ማለትም "መልካሞቹ ቀደምት" ሲሆኑ የእነርሱ መንሀጅ ጂሃድ ነው። “መንሀጅ” مَنْهَج ማለት "ፍኖት" "ፋና" "መንገድ" ማለት ነው። "በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “ጂሃድ” جِهَاد የሚለው ቃል “ጃሀደ” جَٰهَدَ ማለትም “ታገለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትግል” ማለት ነው። “ጁሁድ” جُهْد ማለት “መታገል” ነው፥ ጂሃድ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ በሐቅ እና በባጢል መካከል የሚደረግ ትግል ነው። እውነትን ለማንገስ ሐሰትን ለማርከስ፥ ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ በአላህ መንገድ የሚታገል፣ የሚጥርና የሚጋደል በነጠላ “ሙጃሂድ” مُجَٰهِد ይባላል፥ በብዜት ደግሞ “ሙጃሂዱን” مُجَاهِدُون ይባላሉ፦
49፥15 *ምእምናን እነዚያ በአላህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት “በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው”፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ

ምእምናን ማለት በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፥ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 28
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በንብረታችሁ፣ በነፍሶቻችሁ እና በአንደበታችሁ ሙሽሪኮችን ታገሉ”*። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏:‏ ‏ “‏ جَاهِدُوا الْمُشْرِكِينَ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنْفُسِكُمْ وَأَلْسِنَتِكُمْ ‏

እኩይ ድርጊት ለመታገል ሦስት ምርጫ አለን፥ እርሱም፦
1. በእጅ መታገል፣
2. በአንደበት መታገል፣
3. በልብ መታገል ነው፦
ሪያዱ አስ-ሳሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ *“ከእናንተ ውስጥ እኩይ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው፣ ካልቻለ በምላሱ ያውግዝ፣ ይህንንም ካልቻለ በልቡ ይጥላው። በልብ መጥላት ደካማው ኢማን ነው”*። عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال‏:‏ سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏ "‏من رأى الخد منكرًا فليغيره بيده ، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان
ስለዚህ ሠለፍይ ማለት ከላይ የተጠቀሱት ሦስቱ ትውልድ ሲሆኑ ሠለፍ ማለት የሦስቱ ትውልድ መንሀጅ ነው፥ የሦስቱ ትውልድ መንሀጅ ደግሞ ጂሃድ ነው። እኛ ደግሞ የእነርሱን ፈለግ መከተል ያለብን ሙዕሚን ነን። ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው በዚህ ዓለም በተሾመበት ጥመት ተሹሞ መጨረሻው እሳት ነው፦
4፥115 ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው በዚህ ዓለም በተሾመበት ጥመት ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا

አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን የተረዱበትን እና የተገበሩበትን መንሀጅ ለመረዳትና ለመተግበር ያብቃን፥ አላህ በአሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን መንሀጅ የምንመራ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም!

ለመላው ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እህቶቼ፦ "እንኳን የዒዱል አድሓ በዓል በሠላም አደረሳችሁ" ብያለው።

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፤ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፤ ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

በዓሉ ዘርፈ ብዙ የአምልኮ መርሃ-ግብር ያዘለ እንደመሆኑ ረገድ አላህ በኢኽላስ ይቀበለን። በዓሉን የደስታ፣ የፍቅር፣ የመከባበር፣ የብልጽግና ያርግልን! አሚን። ተቀበለሏህ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል፥ ዒድ ሙባረክ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዚክር

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥28 *"እነርሱም እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ"*፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ

ኢሥላም አጠቃላይ የሕይወት ዘይቤ አቅፏል፥ ይህም መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ(ሥ-መንግሥት) ይዘት ነው። መንፈሳዊ ማለት "አምልኮታዊ" ይዘት ነው፥ ከአምልኮ መካከል አንዱ ደግሞ ዚክር ነው። "ዚክር" ذِكْر የሚለው ቃል “ዘከረ” ذَكَرَ ማለትም “አስታወሰ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አላህ ማስታወስ” ማለት ነው፥ ዚክር በሌላ ስሙ "ኢሥቲዝካር" اِسْتِذْكَار "ተዝኪር" تَذْكِير "ተዝኪራ" تَذْكِرَة "ተዝካር" تَذْكَار "ቲዝካር" تِذْكَار ይባላል። "አዝካር" أَذْكَار የዚኪር ብዙ ቁጥር ነው።
አምላካችን አላህን በሶላት ማስታወስ በዋነኝነት የአምልኮ ክፍል ነው፦
20፥14 «እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ *"ሶላትንም እኔን ለማውሳት ስገድ"*፡፡ إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
62፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ*፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
29፥45 ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ *ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አላህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው"*፤ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡ اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ ۖ إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَصْنَعُونَ

ሶላት በኢማን፣ በኢኽላስ እና በኢቲባዕ ከተሰገደ ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ይከለክላል፥ አላህን ማውሳት ግን ከሶላት ውጪም ስለሚደረግ ከሁሉ ነገር በላጭ ነው። ጠዋትና ማታ የሚዘከረው የዓለማቱ ጌታ የአሏህ ስም ነው፦
7፥205 ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል *በጧትም በማታም አውሳው*፡፡ ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡ وَاذْكُر رَّبَّكَ فِي نَفْسِكَ تَضَرُّعًا وَخِيفَةً وَدُونَ الْجَهْرِ مِنَ الْقَوْلِ بِالْغُدُوِّ وَالْآصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ الْغَافِلِينَ
76፥25 *"የጌታህንም ስም በጧትና ከቀትር በላይ አውሳ"*፡፡ وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
73፥8 *"የጌታህንም ስም አውሳ፥ ወደ እርሱም መገዛትን ተገዛ"*፡፡ وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ وَتَبَتَّلْ إِلَيْهِ تَبْتِيلًا

"ተበተል" تَبَتَّلْ ማለት "ተገዛ" ማለት ሲሆን ትእዛዝ ነው፥ "ተብቲል" تَبْتِيل ማለት ደግሞ "መገዛት" ማለት ነው። አላህን ብዙ በማውሳት መገዛት ልብ ያረካል፥ ልብም ይረጥባል። ልቦችን ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ግን ወዮልን፦
33፥41 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اذْكُرُوا اللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا
13፥28 *"እነርሱም እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ"*፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ
39፥22 *ልቦቻቸውም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወዮላቸው"*፡፡ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው፡፡ فَوَيْلٌ لِّلْقَاسِيَةِ قُلُوبُهُم مِّن ذِكْرِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ فِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ

ከዚክር የራቀ ሰው ወዮ ያስባለው ጉዳይ ምን ይሆን? አዎ ሸያጢን የሚጸናወጡት ከዚኪር የራቀው ሰው ነው፥ ከዚክር የሚርቀውን ሰው ሸይጧን “ቀሪን” قَرِين ማለት “ጓደኛ” ይሆነዋል። ሸይጧን ደግሞ ብዙ አጀንዳ አለው፥ ከአጀንዳዎቹ መካከል በሚያሰክር መጠጥ፣ በቁማር፣ በመካከላችን ጠብንና ጥላቻን ማድረግ ነው፦
43፥36 *ከአልረሕማን ዚክር የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን፡፡ ስለዚህ እርሱ ለእርሱ ቁራኛ ነው*፡፡ وَمَن يَعْشُ عَن ذِكْرِ الرَّحْمَـٰنِ نُقَيِّضْ لَهُ شَيْطَانًا فَهُوَ لَهُ قَرِين
5፥91 *ሰይጣን የሚፈልገው በሚያሰክር መጠጥና በቁማር በመካከላችሁ ጠብንና ጥላቻን ሊጥል አላህን ከማውሳት እና ከስግደትም ሊያግዳችሁ ብቻ ነው"*፡፡ ታዲያ እናንተ ከእነዚህ ተከልካዮች ናችሁን? ተከልከሉ፡፡ إِنَّمَا يُرِيدُ الشَّيْطَانُ أَن يُوقِعَ بَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ فِي الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ وَيَصُدَّكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ وَعَنِ الصَّلَاةِ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّنتَهُونَ
ቁርኣን "ዚክር" ذِكْر ነው፥ በውስጡ አያቱል ሩቀያህ ይዟል። ከቁርኣን ስንርቅ ዘፈን ማዳመጥ ይጀመራል፣ ዘፈን ከተደመጠ ደግሞ መዝሙር ይደመጣል፣ ከዚያ በኩፍር ውስዋስ "ከፈርኩኝ" ይባላል። ሌላው ሸይጧን አላህን ማስታወስ የሚያስረሳን ባለን ሃብት እና በልጆቻችን መሽጉል በማድረግ ነው፦
58፥19 በእነርሱ ላይ ሰይጣን ተሾመባቸው፡፡ *አላህንም ማስታወስን አስረሳቸው፡፡ እነዚያ የሰይጣን ጭፍሮች ናቸው"*፡፡ ንቁ! የሰይጣን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡ اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُون
63፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ገንዘቦቻችሁ እና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታሉዋችሁ፡፡ ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ عَن ذِكْرِ اللَّهِ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ

"ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ከዚክር መራቅ ኪሳራ ከሆነ እንግዲህ ዚክር ይህንን ያህን አንገብጋቢ ጉዳይ ነው ማለት ነው። የአዝካር አይነቶች ደግሞ ብዙ ናቸው፥ እነርሱም፦ ተሕሊል፣ ተክቢር፣ ተሕሚድ፣ ተሥቢሕ፣ ተምጂድ፣ ኢሥቲግፋር፣ ኢሥቲዓዛህ፣ በስመሏህ፣ ሐስበላህ ናቸው። እነዚህን ጥርስ እና ምላሳቸውን እየነቀስን ጥልልና ጥንፍፍ አርገን በሚቀጥሉት ክፍሎች ኢንሻላህ እናያለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዚክር

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥152 *"አስታውሱኝም፥ አስታውሳችኋለሁና"*። ለእኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡ فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ وَاشْكُرُوا لِي وَلَا تَكْفُرُونِ

ዚክር አንድ
"ተሕሊል"
"ተሕሊል" تَحْلِيل የሚለው ቃል "ሐልለለ" حَلَّلَ ማለትም "አወጀ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "አዋጅ" ማለት ነው። ይህም አዋጅ "ላ ኢላሀ ኢልለሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ነው፥ "ላ ኢላሀ ኢልለሏህ" ማለት "አምላክ የለም፥ ከአሏህ በስተቀር" ማለት ነው። ይህ ተሕሊል ሁለት ማዕዘናት አሉት፥ እነርሱም፦ "ነፍይ" እና "ኢስባት" ናቸው።
1ኛ. "ነፍይ" نَفْي የሚለው ቃል "ነፋ" نَفَى‎ ማለትም "አፈረሰ" ለሚለው ሥርወ-ቃል መስደር ሲሆን "ማፍረስ" ማለት ነው። "ላ ኢላሀ" لَا إِلٰهَ ማለት "አምላክ የለም" በማለት ጣዖታትን የምራፈራርስበት አዋጅ ነው።
2ኛ. "ኢስባት" إِثْبَات የሚለው ቃል "አስበተ" أَثْبَتَ‎ ማለትም "ጸደቀ" ለሚለው ሥርወ-ቃል መስደር ሲሆን "ማፅደቅ" ማለት ነው። إِلَّا اللّٰه "ኢልለሏህ" ማለት "ከአሏህ በስተቀር" በማለት አምላክነቱን የምናጸድቅበት አዋጅ ነው።

የሚያጅበው ነገር ከንፈር እና ከንፈር ሳይነካካ በምላስ የሚዘከር ዚክር ቢኖር "ላ ኢላሀ ኢልለሏህ" ነው። አምላካችን አላህ በሦስተኛ መደብ፦ "ላ ኢላሀ ኢልለሏህን ዕወቅ" ይለናል፥ ነቢያችንም"ﷺ"፦ *"በላጩ ዚክር ላ ኢላሀ ኢልለሏህን ነው" ብለውናል፦
47፥19 *እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ*፡፡ فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 14
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ"ረ.ዐ" ሰምቶ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"በላጩ ዚክር ላ ኢላሀ ኢልለሏህን ነው፥ በላጩ ዱዓእ አልሓምዱ ሊላህ ነው"*። قَالَ سَمِعْتُ جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ، رضى الله عنهما يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ أَفْضَلُ الذِّكْرِ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَفْضَلُ الدُّعَاءِ الْحَمْدُ لِلَّهِ ‏

የኢማን ትልቁ ቅርንጫፍ ከሊመቱል-ዐቂዳህ የሆነው “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፤ ትልቁ ቅርንጫፍ “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” ማለት ነው፥ ትንሹ ደግሞ ከመንገድ ላይ እንቅፋት ማስወገድ ነው። ሐያእ የኢማን ቅርንጫፍ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ وَالْحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ ‏

ዚክር ሁለት
"ተክቢር"
"ተክቢር" تَكْبِير የሚለው ቃል "ከብበረ" كَبَّرَ‎ ማለትም "አተለቀ" ወይም "አከበረ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "ማክበር" ወይም "ማተለቅ" ማለት ነው። ይህም ተክቢራ "አሏሁ አክበር" اللّٰهُ أَكْبَر ነው፥ "አሏሁ አክበር" ማለት "አሏህ ታላቅ ነው" ወይም "አሏህ ክቡር ነው" ማለት ነው፦
23፥10 እነዚያ የካዱት ሰዎች «ወደ እምነት በምትጠሩ እና በምትክዱ ጊዜ *አላህ እናንተን መጥላቱ እራሳችሁን ዛሬ ከመጥላታችሁ የበለጠ ታላቅ ነው*» በማለት ይጠራሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا يُنَادَوْنَ لَمَقْتُ اللَّهِ أَكْبَرُ مِن مَّقْتِكُمْ أَنفُسَكُمْ إِذْ تُدْعَوْنَ إِلَى الْإِيمَانِ فَتَكْفُرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አሏሁ አክበር" اللَّهِ أَكْبَر የሚል ኃይለ-ቃል አለ። አላህን "አሏሁ አክበር" በማለት እናከብረዋለን፥ "ተክቢራ" تَكْبِيرًا ማለት የተክቢር ተለዋዋጭ ቃል ነው፦
17፥111 «ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዘው፣ ለእርሱም በንግሥናው ተጋሪ ለሌለው፣ ለእርሱም ከውርደት ረዳት ለሌለው ይገባው በልም፡፡ *"ማክበርንም አክብረው"*፡፡ وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي لَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُن لَّهُ شَرِيكٌ فِي الْمُلْكِ وَلَمْ يَكُن لَّهُ وَلِيٌّ مِّنَ الذُّلِّ ۖ وَكَبِّرْهُ تَكْبِيرًا

ዚክር ሦስት
"ተሕሚድ"
“ሐምድ” حَمْد ማለት “ሐሚደ” حَمِدَ ማለትም “አመሰገነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምስጋና” ማለት ነው፥ ሐምድ የአምልኮ አይነት ነው፤ በቁርኣን ከተጠቀሱ የአላህ ስሞች መካከል “አል-ሐሚድ” الْحَمِيد ሲሆን “እጅግ በጣም የተመሰገነ” ማለት ነው፦
31፥26 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነው፡፡ *አላህ እርሱ ተብቃቂ ምስጉን ነው*፡፡ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

አላህ አምላኪዎች “ሓሚዱን” حَٰمِدُون ማለትም “አመስጋኞች” ይባላሉ፦
9፥112 እነርሱ ተጸጻቺዎች፣ ተገዢዎች፣ *”አመስጋኞች”*፣ ጿሚዎች፣ አጎንባሾች፣ በግንባር ተደፊዎች፣ በበጎ ሥራ አዛዦች ከክፉም ከልካዮች፣ የአላህንም ሕግጋት ጠባቂዎች ናቸው ምእምናንንም አብስር፡፡ التَّائِبُونَ الْعَابِدُونَ الْحَامِدُونَ السَّائِحُونَ الرَّاكِعُونَ السَّاجِدُونَ الْآمِرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَالنَّاهُونَ عَنِ الْمُنكَرِ وَالْحَافِظُونَ لِحُدُودِ اللَّهِ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِين

"ተሕሚድ" تَحْمِيد የሚለው ቃል "ሐምመደ" حَمَّدَ ማለትም "ተመሰገነ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "ማመስገን" ማለት ነው። ይህም ተዝኪራ "አልሓምዱ ሊላህ" ٱلْحَمْدُ لِلَّه ነው፥ "አልሓምዱ ሊላህ" ማለት "ምስጋና ለአላህ ይገባው" ማለት ነው፦
1፥2 *"ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው"*። ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
ዚክር አራት
"ተሥቢሕ"
"ሡብሓን" سُبْحَٰن የሚለው ቃል "ሠብበሐ" سَبَّحَ ማለትም "አመሰገነ" ወይም "አከበረ" "አጠራ" "አወደሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማህሌት" "ውዳሴ" "ስብሐት" ማለት ነው፦
30፥17 አላህንም በምታመሹ ጊዜ በምታነጉም ጊዜ አጥሩት"*፡፡ فَسُبْحَانَ اللَّهِ حِينَ تُمْسُونَ وَحِينَ تُصْبِحُونَ

"አጥሩ" ለሚለው ቃል የገባው "ሡብሓነ" سُبْحَانَ ሲሆን "ተሥቢሕ" تَسْبِيح ማለት ደግሞ "ተስብሖት" ማለት ነው። ለአላህ የምራቀርበት ስብሐት ከላይ አንቀጹ ላይ እንደተቀመጠው "ሡብሓነ አላህ" سُبْحَانَ اللَّه ነው፦
15፥98 *ጌታህንም "ከማመስገን ጋር "አጥራው" ከሰጋጆቹም ኹን*፡፡ فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ
103፥3 *ጌታህን ከማመስገን ጋር "አጥራው"፡፡ ምሕረትንም ለምነው፡፡ እርሱ ጸጸትን በጣም ተቀባይ ነውና*፡፡ فَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ وَاسْتَغْفِرْهُ ۚ إِنَّهُ كَانَ تَوَّابًا

ዚክር አምስት
"ተምጂድ"
"መጅድ" مَجْد የሚለው ቃል "መጀደ" مَجَدَ ማለትም "አከበረ" "ከፍ አረገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ክብር" "ከፍታ" ማለት ነው። በቁርኣን ከተጠቀሱ የአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አል-መጂድ” الْمَّجِيد ሲሆን “እጅግ በጣም የተከበረ” ማለት ነው፦
11፥73 «ከአላህ ትዕዛዝ ትደነቂያለሽን የአላህ ችሮታና በረከቶቹ በእናንተ በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ ይሁን *እርሱ አላህ ምስጉን ክቡር ነውና*» አሉ፡፡ قَالُوا أَتَعْجَبِينَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ ۖ رَحْمَتُ اللَّهِ وَبَرَكَاتُهُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ ۚ إِنَّهُ حَمِيدٌ مَّجِيدٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 48
አቡ ሑመይድ አሥ-ሣዒዲይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ *”ሰዎች፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በእርሶ ላይ እንዴት ሰለዋት እናውርድ? አሉ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ሆይ! ሰለዋትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ፥ ሰለዋትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ በረካትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ ልክ በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ፤ አንተ የተመሰገንክ እና የተከበርክ ነህ*። أَخْبَرَنِي أَبُو حُمَيْدٍ السَّاعِدِيُّ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُمْ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ قُولُوا اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ‏”‌‏.‏

ይህ አላህ በአምልኮ ከፍ ከፍ ማድረግ "ተምጂድ" تَمْجِيد ወይም "ሐውቀላህ" حَوْقَلَة ይባላል። ይህም ተዝኪራ "ላ ሀውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢልሏህ" لا حَوْلَ وَلا قُوَّةَ إِلا بالله ነው። "ላ ሀውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢልሏህ" ማለት "ከአላህ በስተቀር ብልሃት ሆነ ኃይል የለም" ማለት ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 170
አቢ ዘር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ *"ከጀነት ሃብት አንዱን ሃብት ልጠቁምህን? አሉኝ። እኔም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አዎ" አልኩኝ። እርሳቸውም፦ "ከአላህ በስተቀር ብልሃት ሆነ ኃይል የለም" ነው፥ አሉ"*። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ قَالَ لِي رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏"‏ أَلاَ أَدُلُّكَ عَلَى كَنْزٍ مِنْ كُنُوزِ الْجَنَّةِ ‏"‏ ‏.‏ قُلْتُ بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ ‏.‏ قَالَ ‏"‏ لاَ حَوْلَ وَلاَ قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ ‏

ኢንሻላህ የተቀሩትን ስለ ኢሥቲግፋር፣ ኢሥቲዓዛህ፣ በስመሏህ፣ ሐስበላህ በክፍል ሦስት እናጠቃልላለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዚክር

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥35 *"አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል"*፡፡ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

ዚክር ስድስት
"ኢሥቲግፋር"
በቁርኣን ከተጠቀሱ የአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አል-ገፋር” الغَفَّار ወይም “አል-ገፉር” الغَفُور ሲሆን “ይቅርባዩ” ማለት ነው። “መግፊራህ” مَّغْفِرَة ማለት “ይቅርታ” ማለት ሲሆን የእርሱ ባሕርይ ነው፦
15፥49 *”ባሮቼን እኔ ይቅርባዩ መሓሪው እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው”*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
49፥5 ወደ እነርሱም እስክትወጣ ድረስ እነርሱ በታገሱ ኖሮ ለእነርሱ በላጭ በኾነ ነበር፡፡ *”አላህም እጅግ ይቅርባይ መሓሪ ነው”*፡፡ وَلَوْ أَنَّهُمْ صَبَرُوا۟ حَتَّىٰ تَخْرُجَ إِلَيْهِمْ لَكَانَ خَيْرًۭا لَّهُمْ ۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ

"ኢሥቲግፋር" اِسْتِغْفار የሚለው ቃል "ኢሥተግፈረ" اِسْتَغْفَرَ ማለትም "ይቅርታ ጠየቀ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "ይቅርታ መጠየቅ" ማለት ነው። ይህም ተዚኪራ "አሥተግፊሩሏህ" أَسْتَغْفِرُ اللّٰه‎ ነው። አሥተግፊሩሏህ" ማለት "አላህን ይቅርታ እጠይቃለው" ማለት ነው፦
11፥3 *"ጌታችሁንም ይቅርታን ጠይቁት"*፡፡ وَأَنِ ٱسْتَغْفِرُوا۟ رَبَّكُمْ

"ይቅርታን ጠይቁ" ለሚለው ቃል የገባው "ኢሥተግፊሩ" ٱسْتَغْفِرُوا۟ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። የአላህ የይቅርታው ጥልቀትና ስፋት፥ ምጥቀትና ልቀት የሚያጅብ ነው።

ዚክር ሰባት
"ኢሥቲዓዛህ"
"ኢሥቲዓዛህ" إِسْتِعَاذَة የሚለው ቃል "ኢሥተዓዘ" اِسْتَعَاذَ ማለትም "ተጠበቀ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "መጠበቅ" ማለት ነው። ይህም ተዚኪራ "አዑዙ ቢሏሂ ሚነሽ ሸይጧኒር ረጂም" أَعُوذُ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ ነው። "አዑዙ ቢሏሂ ሚነሽ ሸይጧኒር ረጂም" ማለት "እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ እጠበቃለው" ማለት ነው፦
16፥98 *"ቁርኣንንም ባነበብህ ጊዜ እርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ"*፡፡ فَإِذَا قَرَأْتَ الْقُرْآنَ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተጠበቅ" ለሚለው ቃል የገባው "ኢሥተዒዝ" اسْتَعِذْ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ “ሸይጧን” ልክ እንደ “ሌባ” “ውሸታም” “ባለጌ” የባህርይ ስም እንጂ የተፀውኦ ስም አይደለም፤ ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጂን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ
7፥200 *ከሰይጣንም በኩል ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና*፡፡ وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
ዚክር ስምንት
"በስመሏህ"
አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” “ኢቅራ” اقْرَأْ ማለትም “አንብብ” ብሎ አዟቸዋል፦
96፥1 *”አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም”*፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

ቁርኣን ሲጀምር የሚነበበው “ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም” ነው፥ ከአንድ ሱራህ በስተቀር እያንዳንዱ ሱራህ ሲጀምር “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው” በሚል ነው። አንድ ሱራህ ከሌላው ሱራህ የሚለየው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” በሚል ቃል ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 398
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”ነቢዩ”ﷺ” ሁለት ሱራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ”*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}

"በስመሏህ" بَسْمَلَة የሚለው ቃል "በሥመለ" بَسْمَلَ‎ ማለትም "ጠራ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "የአላህን ስም መጥራት" ማለት ነው። ይህም ተዝኪራ "ቢሥሚል ሏሂር ረሕማኒር ረሒም" بِسْمِ اللهِ الرَّحْمٰنِ الرَّحِيْمِ ነው። "ቢሥሚል ሏሂር ረሕማኒር ረሒም" ማለት "በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው" ማለት ነው፦
1፥1 *"በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው"*፡፡ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيم

ዚክር ዘጠኝ
"ሐስበላህ"
በቁርኣን ከተጠቀሱት የአላህ የተዋቡ ስሞች መካከል “አል-ወኪል” الْوَكِيل ሲሆን “መመኪያ” “መጠጊያ” “መሸሸጊያ” ማለት ነው፦
39፥9 እርሱም የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ *”ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ አድርገህም ያዘው”*፡፡ رَّبُّ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ فَاتَّخِذْهُ وَكِيلًا

በአላህ ላይ መመካት “ተወኩል” تَوَكُّل‎ ይባላል። ሰይጧን በእነዚያ ባመኑት እና በአላህ ላይ በሚመኩት ላይ ስልጣን የለውም፦
16፥99 *”እርሱ በእነዚያ ባመኑት እና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ላይ ለእርሱ ስልጣን የለውምና”*፡፡ إِنَّهُ لَيْسَ لَهُ سُلْطَانٌ عَلَى الَّذِينَ آمَنُوا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

“በሚጠጉት” ለሚለው ቃል የገባው “የተወከሉነ” يَتَوَكَّلُونَ ሲሆን ቁርጥ ሐሳብም ባደረጉ ጊዜ አላህ በቂዬ ነው ብለው በአላህ ላይ ሙሉ ለሙሉ የተወከሉ ባሮቹ ደግሞ “ሙተወከሉን” مُتَوَكِّلُون ይባላል፦
39፥38 *«አላህ በቂዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ»* በል፡፡ قُلْ حَسْبِيَ اللَّهُ ۖ عَلَيْهِ يَتَوَكَّلُ الْمُتَوَكِّلُونَ
6፥159 *”ቁርጥ ሐሳብም ባደረግህ ጊዜ በአላህ ላይ ተመካ፡፡ አላህ በእርሱ ላይ ተመኪዎችን ይወዳልና”*፡፡ فَإِذَا عَزَمْتَ فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَوَكِّلِينَ

ይህ አላህን በቂ ማድረግ "ሐስበላህ" حَسْبَلَة ይባላል። አላህ መጠጊያ ስናደርግ “ሐሥቡነል ሏህ ወኒዕመል ወኪል” حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيل እንላለን፥ "ሐሥቡነል ሏህ ወኒዕመል" ማለት “በቂያችንም አላህ ነው፥ ምን ያምርም መጠጊያ” ማለት ነው፦
3፥173 እነዚያ ሰዎቹ ለእነርሱ፡- «ሰዎች ለእናንተ ጦርን አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» ይሉዋቸውና ይህም እምነትን የጨመረላቸው *«በቂያችንም አላህ ነው፥ ምን ያምርም መጠጊያ!»* ያሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4564
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ኢብራሂም በእሳት ውስጥ እያለ የመጨረሻ ንግግሩ፦ *”በቂያችንም አላህ ነው፥ ምን ያምርም መጠጊያ”* የሚል ነበር”። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ كَانَ آخِرَ قَوْلِ إِبْرَاهِيمَ حِينَ أُلْقِيَ فِي النَّارِ حَسْبِيَ اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ‏

ከላይ የዘረዘርናቸው የዚክር አይነቶች ትሩፋትና ምንዳ፥ ወሮታና አጸፌታ በዱንያህ ቀልብ ማርጠብ ነው። ዚክር የሞተ ቀልብን ሕያው ማድረጊያ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 80, ሐዲስ 102
አቢ ሙሣ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ጌታውን የሚዘክር እና የማይዘክር ምሳሌ፥ ልክ እንደ ሕያው እና እንደ ሙታን ነው"*። عَنْ أَبِي مُوسَى ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَثَلُ الَّذِي يَذْكُرُ رَبَّهُ وَالَّذِي لاَ يَذْكُرُ مَثَلُ الْحَىِّ وَالْمَيِّتِ

አላህ የሚዘክር ደግሞ በአኺራ አላህ ስሙን ይዘክርለታል፦
2፥152 *አስታውሱኝም፥ አስታውሳችኋለሁና"*። ለእኔም አመስግኑ፤ አትካዱኝም፡፡ فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ وَاشْكُرُوا لِي وَلَا تَكْفُرُونِ
ኢማም ሙስሊም, መጽሐፍ 55, ሐዲስ 22
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አላህ እንዲህ ይላል አሉ፦ *“እኔን እንደረሳኸኝ እረሳካለው”* فَيَقُولُ فَإِنِّي أَنْسَاكَ كَمَا نَسِيتَنِي

አላህን የሚያስታውሱ ወንድ ባሮቹ በነጠላ "ዛኪር" ذَاكِر‎ በብዜት "ዛኪሪን" ذَّاكِرِين ሲባሉ፥ አላህን የሚያስታውሱ ሴት ባሮቹ ደግሞ በነጠላ "ዛኪራህ" ذَاكِرَة በብዜት "ዛኪራት" ذَّاكِرَات ይባላሉ። አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፦
33፥35 *"አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል"*፡፡ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

ምንኛ የታደሉ ናቸው? አላህ ዛኪሪን እና ዛኪራት ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ስግደት በኢሥላም

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥15 *"በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ"*። وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا

“ሡጁድ” سُّجُود የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለትም “ታዘዘ” “ተገዛ” ለሚለው መስደር ሲሆን “መታዘዝ” “መገዛት” ማለት ነው። በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም ለአላህ የታዘዙ ናቸው፦
13፥15 *"በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ"*። وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا

“ይሰግዳሉ” ለሚለው ቃል የገባው የግስ መደብ “የሥጁዱ” يَسْجُدُ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይሰግዳሉ" የሚለው "በሰማያትና በምድርም ያሉት ሁሉ በውድም ሆነ በግድ ለአላህ ይታዘዛሉ" በሚል መጥቷል፦
3፥83 *”በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ በውድም በግድም “ለእርሱ የታዘዙ” ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአላህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን?”* أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ “በግዴታ ይሰግዳሉ” ማለት “ሙጅመል” مُجّمَل ማለትም “ጥቅላዊ መታዘዝን”general prostration” ያሳያል። በሰማያት እና በምድር ያሉ ሁሉ “በውዴታ ይሰግዳሉ” ማለት ደግሞ “ሙፈሰል” مُفَصَّل ማለትም “በተናጥል መታዘዝን”particular prostration” ያሳያል። ከዚህ አንቀጽ የምንረዳው ፍጥረት በሁለት መልኩ ለአላህ ይታዘዛል፥ አንዱ በግድ ሲሆን ይህ የግዴታ መታዘዝ “አሥ-ሡጁዱ አት-ተክውኒይ” السُّجُود التَكْو۟نِي ይባላል። ሁለተኛው ደግሞ በውድ ሲሆን ይህ የውዴታ መታዘዝ “አሥ-ሡጁዱ አት-ተሽሪዒይ” السُّجُود التَشْرِعِي ይባላል። ይህንን ነጥብ በነጥብ ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
“አሥ-ሡጁዱ አት-ተክውኒይ”
“ተክውኒይ” تَكْو۟نِي ማለት “ኹነት” ማለት ሲሆን የሚሆን ማንኛውም ፍጥረት ያለ ምርጫው ለአላህ በግዴታ ይሰግዳል። ሰማይና ምድርም፣ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት፣ ተራራዎችም፣ ለአላህ ይሰግዳሉ፦
22፥18 *አላህ በሰማያት ያለው ሁሉ፣ በምድርም ያለው ሁሉ፣ ፀሐይ እና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾችም ከሰዎች ብዙዎችም ለእርሱ የሚሰግዱለት መሆኑን አታውቁምን?"* أَلَمْ تَرَ أَنَّ اللَّهَ يَسْجُدُ لَهُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَمَن فِي الْأَرْضِ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ وَالنُّجُومُ وَالْجِبَالُ وَالشَّجَرُ وَالدَّوَابُّ وَكَثِيرٌ مِّنَ النَّاس

ለአላህ ይሰግዳሉ ማለት በትእዛዙ የተገሩ ናቸው ማለት ነው፦
7፥54 *ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም “በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ” ፈጠራቸው፡፡ ንቁ! “መፍጠር እና ማዘዝ” የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ ክብሩ ላቀ*፡፡ وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ وَالنُّجُومَ مُسَخَّرَاتٍ بِأَمْرِهِ ۗ أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ ۗ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ

ፀሐይ እና ጨረቃም፣ ከዋክብትም፣ ተራራዎችም፣ ዛፎችም፣ ተንቀሳቃሾች ይሰግዳሉ ሲባል "ሡጁድ" ማለት በወገብ "ማጎንበስ" እና በግንባር "መደፋት" ብቻ ነው ብለን ስለተረዳነው ነው።
"ኸር" خَرّ የሚለው ቃል "ኸረ" خَرَّ ማለትም "ተደፋ" ለሚለው መስደር ሲሆን "መደፋት" ማለት ነው።
"ሩኩዕ" رُكُوع የሚለው ቃል "ረከዐ" رَكَعَ ማለትም "አጎነበሰ" ለሚለው መስደር ሲሆን "ማጎንበስ" ማለት ነው።
ዐቅል የሌለው ፍጥረት "ኸር" እና "ሩኩዕ" ላያደርግ ይችላል። ነገር ግን አላህ ላስቀመጠው የተፈጥሮ ሕግ ይታዘዛሉ። እንዴት እንደሚታዘዙ ላናውቅ እንችላለን፥ ተሥቢሕ ሲያረገሩ እንደማናውቀው ሁሉ እንዴት እንደሚታዘዙም ዐናውቅም፦
4፥44 *"ሰባቱ ሰማያት እና ምድርም በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያጠራሉ፡፡ ከነገርም ሁሉ ከማመስገን ጋር የሚያጠራው እንጂ አንድም የለም፡፡ ግን ማጥራታቸውን ዐታውቁትም"*፡፡ እርሱ ታጋሽ መሓሪ ነው፡፡ تُسَبِّحُ لَهُ السَّمَاوَاتُ السَّبْعُ وَالْأَرْضُ وَمَن فِيهِنَّ ۚ وَإِن مِّن شَيْءٍ إِلَّا يُسَبِّحُ بِحَمْدِهِ وَلَـٰكِن لَّا تَفْقَهُونَ تَسْبِيحَهُمْ ۗ إِنَّهُ كَانَ حَلِيمًا غَفُورًا
ነጥብ ሁለት
“አሥ-ሡጁዱ አት-ተሽሪዒይ”
“ተሽሪዒይ” تَشْرِعِي ማለት “ሕግጋት” ማለት ሲሆን ከአላህ ወደ ነቢያቱ የሚወርድ መመሪያ፣ መርሕ፣ ሥርዓት ነው። ወደ ነቢያት የሚወርደው ተሽሪዒይ በውዴታ ላይ የተመሰረተ መገዛት ነው፦
64፥12 *"አላህንም ተገዙ፤ መልክተኛውንም ታዘዙ፤ ብትዞሩም መልክተኛውን አትጎዱም፤ በመልክተኛውም ላይ ያለበት ግልጽ ማድረስ ብቻ ነው"*፡፡ وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ ۚ فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَإِنَّمَا عَلَىٰ رَسُولِنَا الْبَلَاغُ الْمُبِينُ

“አሥ-ሡጁዱ አት-ተሽሪዒይ” ለሁለት ይከፈላል፥ እርሱም “ሡጁዱል ዒባዳህ” سُّجُود العِبَادَة ማለትም "የአምልኮ ስግደት" እና "ሡጁዱ አ-ተሒያህ" سُّجُود التَحِيَّة ማለትም "የአክብሮት ስግደት" ነው።
“ዒባዳህ” عِبَادَة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ ማለትም “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው። ይህም የአምልኮ ስግደት ለአንዱ አምላክ ለአላህ ብቻ የተገባ ነው፦
41፥37 *"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

"ተሒያህ" تَحِيَّة የሚለው ቃል "ሐያ" حَيَّا ማለትም "አከበረ" "እጅ ነሳ" "ሰላምታ ሰጠ" ለሚለው መስደር ሲሆን "አክብሮት" "እጅ መንሳት" "ሰላምታ" ማለት ነው። ለምሳሌ መላእክት ለአደም፥ የዩሱፍ ቤተሰብ ለዩሱፍ የሰገዱት አክብሮትን የሚገልጽ ብቻ ነው፦
18፥50 *"ለመላእክትም ለአደም ስገዱ ባልናቸው ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡ ወዲያውም ሰገዱ"*። وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا
12፥4 *ዩሱፍ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም በሕልሜ አየሁ፡፡ :ለእኔ ሰጋጆች ሆነው" አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ*፡፡ إِذْ قَالَ يُوسُفُ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ إِنِّي رَأَيْتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوْكَبًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ رَأَيْتُهُمْ لِي سَاجِدِينَ
12፥100 *ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው፡፡ "ለእርሱም ሰጋጆች ኾነው" ወረዱለት፡፡ እርሱም፦ «አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፡፡ ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት» አለ*፡፡ وَرَفَعَ أَبَوَيْهِ عَلَى الْعَرْشِ وَخَرُّوا لَهُ سُجَّدًا ۖ وَقَالَ يَا أَبَتِ هَـٰذَا تَأْوِيلُ رُؤْيَايَ مِن قَبْلُ قَدْ جَعَلَهَا رَبِّي حَقًّا

ይህ የአክብሮት ስግደት ከአምልኮ ስግደት የሚለየው በኒያህ ነው፥ "ኒያህ" نِيَّة የሚለው ቃል "ነዋ" نَوَى ማለትም "ወጠነ" ለሚለው ቃል መስደር ሲሆን "ውጥን"intention" ማለት ነው። ነገር ግን ይህ የአክብሮት ስግደት አቅጣጫውን ቀይሮ አምልኮ እየሆነ ስላለ፥ በነቢያችን”ﷺ” ጊዜ ተከልክሏል፦
41፥37 *"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون
ሡነን ኢብኑ ማጀህ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 1926:
ዐብደላህ ኢብኑ አቢ ዐውፋ እንደተረከው፦ *"ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ከሻም ምድር በተመለሰ ጊዜ ለነቢዩ”ﷺ” ሰገደ፥ እሳቸውም፦ “ሙዓዝ ሆይ! ምንድነው ይህ?” አሉት፤ እርሱም፦ “ሻም ምድር ሄጄ ነበር፣ ለኤጲስ ቆጶሳቶቻቸው እና ለጳጳሳቶቻቸው ሲሰግዱ ተመለከትኩኝ፥ ይህንን ለእርሶ ልንሰራው ተመኘሁ” አለ። የአላህ መልክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ይህንን በፍጹም እንዳትሰሩ!"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي أَوْفَى، قَالَ لَمَّا قَدِمَ مُعَاذٌ مِنَ الشَّامِ سَجَدَ لِلنَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ مَا هَذَا يَا مُعَاذُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَتَيْتُ الشَّامَ فَوَافَقْتُهُمْ يَسْجُدُونَ لأَسَاقِفَتِهِمْ وَبَطَارِقَتِهِمْ فَوَدِدْتُ فِي نَفْسِي أَنْ نَفْعَلَ ذَلِكَ بِكَ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ فَلاَ تَفْعَلُوا

ስግደት በኢሥላም በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል። ኢንሻላህ ስግደት በክርስትና ያለውን ምልከታ በክፍል ሁለት ይቀጥላል.......

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ስግደት በክርስትና

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥37 *"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

“ስግደት” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ሻኻህ” שָׁחָה ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ፕሩስኩኔኦ” προσκυνέω ይባላል፥ ይህም ስግደት ለተለያየ ምንነት ሆነ ማንነት በውጥን”intention” የሚቀርብ አምልኮን”Adoration” ለማመልከት ወይም አክብሮትን”prostration” ለማመልከት በባይብል ተጠቅሞበታል። በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ለተቀረጸ ምስል አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም" ተብሏል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን *”ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ”* ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር *የማናቸውንም ምሳሌ፥ "የተቀረጸውንም ምስል" ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም*።
ራዕይ 19፥10 *”ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ”*። እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ *”ለእግዚአብሔር ስገድ”*፤ …አለኝ።

ለማንም ለምን “አትስገድ” ከተባለ ለምንድን ነው ሰዎች ለሰዎች የሰገዱት?፦
ዘፍጥረት 23፥7 አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም፥ *”ለኬጢ ልጆች ሰገደ”* ።
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም *”ይስገዱልህ”*፤ ለወንድሞችህ ጌታ ሁን፥ *”የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ”*፤
ዘፍጥረት 37፥9 ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እንዲህም አለ። እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፤ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ አሥራ አንድ ከዋክብትም *”ሲሰግዱልኝ”* አየሁ።
ዘፍጥረት 42፥6 ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ፥ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ *”በግምባራቸው ሰገዱለት”*።
ዘፍጥረት 43፥26 ዮሴፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእጃቸው ያለውን እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀረቡለት፥ *”ወደ ምድርም ወድቀው ሰገዱለት”*።
ዘፍጥረት 43፥28 እነርሱም አሉት። ባሪያህ አባታችን ደኅና ነው፤ ገና በሕይወት አለ። *”አጐንብሰውም ሰገዱለት”*።
1ኛ ዜና 29፥20 ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ። አምላካችሁን እግዚአብሔርን ባርኩ አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔር እና *”ለንጉሡ ሰገዱ”*።
ቁርኣን መላእክት ለአደም፥ የዩሱፍ ቤተሰብ ለዩሱፍ መስገዳቸው መግለጹን ስትቃወሙ ባብይል ላይ ቅዱሳን ሰዎች ለሰዎች መስገዳቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። ምን ይህ ብቻ ኢየሱስ ሲመጣ ኢአማንያንን መጥተው በአማንያን እግር ፊት ይሰግዱ ዘንድ ማድረጉ ይደንቃል፦
ራእይ 3:9 እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው *”በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ”* προσκυνήσουσιν ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።

ዮሐንስ ሊሰግድለት በእግሩ ፊት ሲደፋ “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ! ባሪያ ነኝ ለእግዚአብሔር ስገድ” ብሎት እያለ ኢየሱስ ኢአማንያንን መጥተው በአማንያን እግር ፊት ይሰግዱ ዘንድ ማድረጉ አግባብ ነው ወይ? ስንል ፦አይ መልአኩ ለዮሐንስ "አትስገድ" ያለው “የአምልኮት ስግደት” ሲሆን ኢየሱስ "የሚያሰግደው ደግሞ “የአክብሮት ስግደት” ነው። የአምልኮት ስግደት በባሕርይ የአንድ አምላክ ሐቅና ገንዘብ ሲሆን የአክብሮት ስግደት ደግሞ በፀጋ ለቅዱሳን ማክበን ያመለክታል” ይሉናል። እንግዲያውስ የቁርኣኑንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉሃል እንደዚህ ነው፥ በተጨማሪም ፍጥረታት ሁሉ ለአዳም እንደሰገዱ በአሁን ጊዜ ጥንት ከሚባሉት እደ-ክታባት አንዱ በሆነው በአሌክሳድሪየስ ኮዴክስ በሚገኘው በሮሙ ክሌመንት ማለትም በቀለሚንጦስ ተገልጿል፦
ክሌመንት 1፥41 አራዊት፣ እንስሳት ወፎች *እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ ወደ አዳም ተሰበሰቡ ከፊቱ ቁመው ራሳቸውን አዘነበሉ፤ ለአዳምም ሰገዱ"*።

በተጨማሪም በመቃብያን ላይ ዲያቢሎስ የወደቀበት ለአደም አልሰግድ በማለቱ እንደሆነ ተገልጿል፦
3ኛ መቃብያን 1፥6 *የሚጠፉ በኔም የሚስቱ ሰዎች ፈጽመው ይበዙ ዘንድ የአዳምም ልጆች ይጠፉ ዘንድ ይህንን በተናገሩ ጊዜ እኔ ደስ ይለኛል። ለሚዋረድልኝ "ለአዳም አልሰግድም በማለቴ" እግዚአብሔር ስለአባታቸው ስለአዳም ከማዕረጌ አዋርዶኛልና*።

የዐበይት ክርስትና ማለትም የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክ እና የአንግሊካን ስግደት ግን ከባይብሉ ይለያል። ሰዎች እና መላእክት በሌሉበት መስገድ ይህ እራሱ የአምልኮ ስግደት ነው፥ ምክንያቱም ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉንም ነገር ማየት፣ መስማት የሚችልና ሁሉንም ነገር ማወቅ የሚችል አንድ አምላክ ብቻ ነው። ሲቀጥል ለተቀረጸ ምስል ለስዕል እና ለመስቀል የጸጋ ስግደት ይሰግዳሉ፦
የዘወትር መቅድም ቁጥር 35-36 ገጽ 7
ግዕዙ፦
*ወቅድመ ስዕላ ስግዱ! ዘኢሰገደ ላቲ ይደምስስ እምቅዋሙ ወኢይትዐወቅ ዝግረ ስሙ። ወይበሉ መላእክተ ሰማይ ኲሎሙ አሜን*።

ትርጉም፦
*በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ! ስም አጠራሩ አይታወቅ። በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ*።

መልክአ ሥዕል ዘበዓለ ሃምሳ አርኬ 20
“ወእሰግድ ካዕበ ለድንግልናኪ ክልኤ፤ *”ወእሰግድ ሠልሰ ለስዕልኪ ቅድመ ጉባዔ፤ ዘኢሰገድ ለስዕልኪ አስሪጾ ምማኤ በሥጋሁ ወበነፍሱ ኢይርከብ ትንሳኤ*”።

ትርጉም፦
:በሁለት በኩል ድንግል ነሽና እሰግድልሻለው፤ *ለስዕልሽም በጉባኤ ፊት ሥስት ጊዜ እሰግዳለሁ፤ ለስዕልሽ ከመስገድ ወደ ኋላ ያለ በነፍሱም በስጋውም ትንሳኤ አያግኝ”*።

የዘወትር ፀሎት ላይ እንዲህ ይነበባል፦
ግዕዙ፦
*“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”*

ትርጉም፦
*“ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው”*

"ለተቀረጸ ምስል አትስገድ" እያለ ለወረቀት ስዕል፣ ለእንጨት መስቀል እና ለድንጋይ ሃውልት ይሰግዳሉ። ይህንን የማይናገርና የማይጋገር፥ የማይሰማና የማይለማ ግዑዝ ነገር ሲሰግዱለት ያሳዝናሉ። ዛሬ ክርስቲያኖች ይህንን መልእክት ከሰሙበት ጀምሮ ውስጣቸውን የሚረብሻቸው እሳቦት ነው፥ ሙሥሊሞች ይህንን እውነታ ለሁሉም አዳርሱ! ምናልባት ለሂዳያህ ሰበብ ይሆናቸዋል። ይህንን መጣጥፍ ለምታነቡ ክርስቲያኖች ጥሪያችን ለፍጡርራን መስገድ ትታችሁ ፍጡራንን የፈጠረውን አላህ በብቸኝነት እያመለካችሁት እንድትሰግዱለት ነው፦
41፥37 *"ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ"*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተዝኪያህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

91፥9 *"ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ"*፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا

"ነፍሥ" نَفْس ማለት "እራስነት"own self" ማለት ነው፥ የነፍሥ ብዙ ቁጥር "ኑፉሥ" نُفُوس‎ ወይም "አንፉሥ" أَنْفُس‎ ነው። "ነፍሢ" نَفْسِي ስል "እራሴ"my self" ማለቴ ነው፣ "ነፍሢከ" نَفْسِكَ ስል "እራስክ"your self" ማለቴ ነው፣ "ነፍሢሂ" نَفْسِهِ ስል "እራሱ"him self" ማለቴ ነው። ነፍሥ በሰዋስው "ደሚሩ አን-ነፍሢያህ" ضَمِير الْنَفْسِيَّة‎ ማለትም "ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun” ነው። በነፍሥ ውስጥ ያለው ዝንባሌ ደግሞ "ነፍሢያህ" نَفْسِيَّة‎ ይባላል፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

“አህዋእ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” ማለት ነው። ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው "ዝንባሌ" ነው። ዝንባሌ ደግሞ ቦታ ከተሰጠው ሊመለክ የሚችል ክፉ አዛዥ ነው፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ሸይጧን ለአላህ አልታዘዝም ብሎ ያመጸው ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ ስለያዘ ነው፥ የሸይጧንን እርምጃ የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ፦
24፥21 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ፡፡ የሰይጣንንም እርምጃዎች የሚከተል ሰው ኀጢአትን ተሸከመ"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّبِعُوا خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ ۚ وَمَن يَتَّبِعْ خُطُوَاتِ الشَّيْطَانِ

በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት። ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ፥ በኀጢኣት የሸፈናትም በእውነት አፈረ፦
79፥40 *በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ* وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 *ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ
91፥9 *"ነፍሱን ያጠራት በእርግጥ ዳነ"*፡፡ قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا
91፥10 *"በኀጢኣት የሸፈናትም በእውነት አፈረ"*፡፡ وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّىٰهَا

"አፍለሐ" أَفْلَحَ የሚለው አላፊ ግስ ሲሆን "ትድኑ ዘንድ" ለሚለው "ቱፍሊሑነ" تُفْلِحُونَ በሚል መጥቷል፦
24፥31 *”ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተጸጸቱ”* وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
5፥35 *”ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ”*። وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

ነፍስን ከዝንባሌዋ ማጥራት "ተዝኪያህ” ይባላል፥ “ተዝኪያህ” تَزكِية የሚለው ቃል “ዘካ” زَكَىٰ ማለትም “ጠራ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መጥራራት" ማለት ነው፦
2፥151 በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን *በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁ እና “የሚያጠራችሁ”፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን ጸጋን ሞላንላችሁ*፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُونَ

“የሚያጠራችሁ” ለሚለው ቃል የገባው “ዩዘኪኩም” يُزَكِّيكُمْ መሆኑ ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያረገ ነው። ተዝኪያህ ሦስት ደረጃዎች አሉት፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ተዕሊም” تَعْلِيم‎ ማለትም “ትምህርት”
2ኛ. “ተርቢያህ” تَرْبِيَة ማለትም “እድገት”
3ኛ. “ተዕዲል” تَعْدِيل‎ ማለትም “ግብረገብ” ነው።
አል-አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 273
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“እኔ የተላኩትን መልካም ሥነ-ምግባርን ላሟላ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ إِنَّمَا بُعِثْتُ لِأُتَمِّمَ صَالِحَ الأَخْلاق

ተዝኪያህ ከራሳችን ዝንባሌ ጋር የሚደረግ ጂሃድ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 22, ሐዲስ 3
ፈዷላህ ኢብኑ ዑበይድ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"ከራሱ ነፍስ ጋር የታገለ ሙጃሂድ ነው"*። فَضَالَةَ بْنَ عُبَيْدٍ، وَسَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ الْمُجَاهِدُ مَنْ جَاهَدَ نَفْسَهُ

እዚህ ሐዲስ ላይ "የታገለ" ለሚለው የገባው ቃል "ጃሀደ" جَاهَدَ መሆኑን ልብ አድርግ። “ጂሃድ” جِهَاد የሚለው ቃል “ጃሀደ” جَاهَدَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ትግል” ማለት ነው፥ እውነትን ለማንገስ ሐሰትን ለማርከስ፥ ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ ሆኖ በአላህ መንገድ በልቡ፣ በምላሱ እና በእጁ የሚታገል ሙጃሂድ” ْمُجَاهِد ይባላል። ነፍስን ለማጥራት ተዝኪያህ ማድረግም “ጁሁድ” جُهْد ነው፥ ሸይኩል ኢሥላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏህ ስለ ጂሃዱ አን-ነፍሥ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦
ረውደቱል ሙሒቢን 1/478
*"ከነፍስ እና ከስሜት ጋር የሚደረግ ጂሃድ ከኩፋር እና ከሙናፊቂ ጋር ለሚደረግ ጂሃድ መሠረት ነው። እርሱ(ሙሥሊም) እነርሱን ከመታገሉ በፊት ቅድሚያ ነፍሱና ስሜቱን መታገል ይቀድማልና"*። جِهَادُ النَّفْسِ وَالْهَوَى أَصْلُ جِهَادِ الْكُفَّارِ وَالْمُنَافِقِينَ فَإِنَّهُ لَا يَقْدِرُ عَلَى جِهَادِهِمْ حَتَّى يُجَاهِدَ نَفْسَهُ وَهَوَاهُ أَوَّلًا حَتَّى يَخْرُجَ إلَيْهِمْ

እንግዲህ ከነፍስ ጋር ጂሃድ ማድረግ ውስጣዊ ትግል ሲሆን ከዲኑ ጠላቶች ጋር ጂሃድ ማድረግ ውጫዊ ትግል ነው። አላህ በእርሱ መንገድ ከራሳችን ጋር የምንታገል ሙጃሂድ ያርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሰው ሰይጣን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ

ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው፤ “ሸያጢን” شَيَاطِين ደግሞ የሽይጧን ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሰይጣናት” ማለት ነው፤ “ሸይጧን” ልክ እንደ “ሌባ” “ውሸታም” “ባለጌ” የግብር ስም እንጂ የተፀውዖ አሊያም የባሕርይ ስም አይደለም። ሸይጧን የሰውም የጂኒም አለ፦
6፥112 እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ *ከሰው እና ከጂን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት* አደረግን፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِن
114፥6 *«ከጂኒዎችም ከሰዎችም ሰይጣናት እጠበቃለሁ»* በል። مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ
23፥97 በልም *«ጌታዬ ሆ! ከሰይጣናት ጉትተጎታዎች በአንተ እጠበቃለሁ»* ፡፡ وَقُل رَّبِّ أَعُوذُ بِكَ مِنْ هَمَزَاتِ الشَّيَاطِينِ
7፥200 *ከሰይጣንም በኩል ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና*፡፡ وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

"የሰው ሰይጣን" አለ ስንል ሚሽነሪዎች ቧልትና ፌዝ ውስጥ መግባታቸው የራሳቸውን መጽሐፍ ጠንቅቀው ካለማወቅ የመጣ ዕውር ድንብር ጸለምተኛ ሙግት ነው። ሰይጣን የሚለው ቃል በዕብራይስጥ "ሳታን" שָּׂטָ֖ן ሲሆን "ጠላት" ማለት ነው፥ ይህ ስም ለሰው ሰይጣን አገልግሎት ላይ ውሏል፦
1ኛ. ነገሥት 11፥14 እግዚአብሔርም ከኤዶምያስ ነገሥታት ዘር የኤዶምያስን ሰው ሃዳድን *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן አድርጎ በሰሎሞን ላይ አስነሣው።
1ኛ. ነገሥት 11፥23 እግዚአብሔርም ደግሞ ከጌታው ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር የኰበለለውን የኤልያዳን ልጅ ሬዞንን *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן አድርጎ አስነሣበት።
1ኛ. ነገሥት 11፥25 ሃዳድም ካደረገው ክፋት ሌላ በሰሎሞን ዘመን ሁሉ የእስራኤል *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן ነበረ።
2ኛ. ሳሙኤል 19፥22 ዳዊትም፦ እናንተ የጽሩያ ልጆች፥ እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ዛሬ ስለ ምን *ሰይጣናት* לְשָׂטָ֑ן ትሆኑብኛላችሁ?
1ኛ. ሳሙኤል 29፥4 የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን ተቆጥተው። ይህ ሰው ባስቀመጥኸው ስፍራ ይቀመጥ ዘንድ ይመለስ በሰልፉ ውስጥ *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן እንዳይሆነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይውረድ ከጌታው ጋር በምን ይታረቃል? የእነዚህን ሰዎች ራስ በመቍረጥ አይደለምን?

በዐማርኛችን ላይ "ጠላት" ተብሎ የተቀመጠው የዕብራይስጥ ቃል "ሰይጣን" ነው የሚለው። አንዳንድ ባይብልን አገላብጠው ያላዩ ሚሽነሪዎች፦ "ሰይጣን" በኢ-አመልካች መስተአምር "ሳታን" שָּׂטָ֖ן ሲሆን ለሰው፥ በአመልካች መስተአምር "ሀ-ሳታን" הַשָּׂטָ֖ן ሲሆን ደግሞ "ለዲያብሎስ ነው" ይላሉ። ይህ እሳቤ ስህተት ነው። ምክንያቱም የሰው ሰይጣንን ለማመልከት "ሀ-ሳታን" הַשָּׂטָ֖ן በሚል አመልካች መስተአምር ገብቷል፦
1ኛ. ሳሙኤል 29፥4 የፍልስጥኤማውያን አለቆች ግን ተቆጥተው። ይህ ሰው ባስቀመጥኸው ስፍራ ይቀመጥ ዘንድ ይመለስ በሰልፉ ውስጥ *ሰይጣን* לְשָׂטָ֖ן እንዳይሆነን ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይውረድ ከጌታው ጋር በምን ይታረቃል? የእነዚህን ሰዎች ራስ በመቍረጥ አይደለምን?

በኢ-አመልካች መስተአምር "ሳታን" שָּׂטָ֖ן ለዲያብሎስ ጥቅም ላይ ውሏል፦
1 ዜና 21፥1 *ሰይጣንም* שָׂטָ֖ן በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን አንቀሳቀሰው።

አመልካች መስተአምር ኖረ አልኖረ አንዳች ለውጥ ከሌለው የሰው ሰይጧን እንዳለ አያችሁልኝን? ምነው ጴጥሮስ ሰይጣን ተብሎ የለምን? አዎ! ተብሏል፦
ማቴዎስ 16፥23 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ *ሰይጣን* የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል፡ አለው።

ስለዚህ ቁርኣን ላይ ሰይጣን የሰውም የጂንም አለ ሲባል እዛ ሰፈር አቧራ አታስነሱ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዋው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ስለ "ዋው" و ተስተምህሮ ለማሳያነት ይህንን አንቀጽ እንመልከት፦
39፥71 እነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ ይከፈታሉ*፡፡ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

የጀሃነም ደጆች “ይከፈታሉ” የሚለው ቃል ላይ “ፉቲሐት” فُتِحَتْ ሲሆን መነሻው ላይ “ወ” و የሚል ቃል የለውም፤ ግን የጀነት ደጆች “የተከፈቱ” የሚለው ቃል ግን “ወፉቲሐት” وَفُتِحَتْ ሲሆን “ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ “ወ” የሚል መነሻ ቅጥያ አለ፦
39፥73 እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገነት ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ “የተከፈቱ”* ሲኾኑ፤ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوْا۟ رَبَّهُمْ إِلَى ٱلْجَنَّةِ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا وَفُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

እስቲ ይህ “ዋው” و የሚለው ቃል”ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ የሌለበትን ምክንያት እናስተንትን፤ ገሃነም ሰባት ደጆች አሏት፦
15፥43-44 «ገሀነምም ለእርሱና ለተከተሉት ለመላውም በእርግጥ ቀጠሯቸው ናት፡፡ وَإِنَّ جَهَنَّمَ لَمَوْعِدُهُمْ أَجْمَعِينَ «ለእርሷ *ሰባት ደጃፎች* አሏት፡፡ ለየደጀፉም ሁሉ ከእነሱ የተከፈለ ፋንታ አለ፡፡ لَهَا سَبْعَةُ أَبْوَٰبٍۢ لِّكُلِّ بَابٍۢ مِّنْهُمْ جُزْءٌۭ مَّقْسُومٌ
39፥71 እነዚያ የካዱትም የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገሀነም ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ *ደጃፎችዋ* ይከፈታሉ፡፡ وَسِيقَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءُوهَا فُتِحَتْ أَبْوَٰبُهَا

ቀጥሎ “ዋው” و የሚለው ቃል”ፉቲሐት” በሚለው ቃል ላይ ያለበትን ምክንያት እናስተንትን፤ ጀነት ስምንት ደጆች አሏት፦
7፥40 እነዚያ አንቀጾቻችንን ያስተባበሉ ከእርሷም የኮሩ ለእነርሱ *የሰማይ ደጃፎች አይከፈቱላቸውም*፡፡ ግመል በመርፌ ቀዳዳ እስከሚገባም ድረስ *ገነትን አይገቡም*፡፡ እንደዚሁም አጋሪዎችን እንቀጣለን፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱسْتَكْبَرُوا۟ عَنْهَا لَا تُفَتَّحُ لَهُمْ أَبْوَٰبُ ٱلسَّمَآءِ وَلَا يَدْخُلُونَ ٱلْجَنَّةَ حَتَّىٰ يَلِجَ ٱلْجَمَلُ فِى سَمِّ ٱلْخِيَاطِ ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُجْرِمِينَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 67:
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ጀነት ስምንት ደጃፎች አሏል*፤ ከእነርሱ አንዷ ስሟ አር-ረይያን ፆመኛ እንጂ ሌላ አይገባባትም። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ فِي الْجَنَّةِ ثَمَانِيَةُ أَبْوَابٍ، فِيهَا باب يُسَمَّى الرَّيَّانَ لاَ يَدْخُلُهُ إِلاَّ الصَّائِمُونَ ‏”‌‏

ነጥቡ ያለው እዚህ ጋር ነው፤ ቁርአን ላይ ሰባት ቁጥር ተነግሮ ስምንት ቁጥር ከመጣ ሰባት ላይ ዋው የለውም ግን ስምንት ላይ ዋው አለ፤ ምሳሌ አንድ፦
18፥22 በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው በጥርጣሬ «ሦስት ናቸው፤ አራተኛቸው ውሻቸው ነው» ይላሉ፡፡ «አምስት ናቸው፤ ስድስተኛቸው ውሻቸው ነውም» ይላሉ፡፡ «ሰባት ናቸው፤ *ስምንተኛቸውም* ውሻቸው ነው» ይላሉም፡፡ سَيَقُولُونَ ثَلَٰثَةٌۭ رَّابِعُهُمْ كَلْبُهُمْ وَيَقُولُونَ خَمْسَةٌۭ سَادِسُهُمْ كَلْبُهُمْ رَجْمًۢا بِٱلْغَيْبِ ۖ وَيَقُولُونَ سَبْعَةٌۭ وَثَامِنُهُمْ كَلْبُهُمْ ۚ

“ወ” የሚል ቃል “ሳሚን” ثَامِن ማለትም “ስምንተኛ” በሚል ቃል ላይ መጥቷል፤ “*ወ*ሳሚኑሁም” وَثَامِنُهُمْ ። ነገር ግን “ሠብዐቱን” سَبْعَةٌ ማለትም “ሰባተኛ” በሚለው ቃል ላይ ግን አልመጣም፤ ምሳሌ ሁለት፦
69፥7 ተከታታይ በኾኑ ሰባት ሌሊቶች *እና ስምንት* መዓልቶች ውስጥ በእነርሱ ላይ ለቀቃት፡፡ سَخَّرَهَا عَلَيْهِمْ سَبْعَ لَيَالٍۢ وَثَمَٰنِيَةَ أَيَّامٍ حُسُومًۭا فَتَرَى ٱلْقَوْمَ فِيهَا صَرْعَىٰ كَأَنَّهُمْ أَعْجَازُ نَخْلٍ خَاوِيَةٍۢ

“ወ” የሚል “ሰማኒን” ثَمَٰنِين ማለትም “ስምንት” በሚል ቃል ላይ መጥቷል፤ “ወሰማኒየታህ” وَثَمَانِيَةَ ። ነገር ግን “ሠብዐ” سَبْعَ ማለትም “ሰባት” በሚለው ቃል ላይ ግን አልመጣም። “ዋው” እዚህ ጋር አርፉል አጥፍ ሳይሆን ዋው ሙተና ነው፤ ዋው ሁልጊዜ መነሻ ቅጥያ ላይ ሆኖ ሲመጣ አያያዥ መስተጻምር ነው ተብሎ አይደመደምም፤ ለምሳሌ “ወላሂ” وَٱللّٰهِ እንላለን፤ እዚህ ጋር “ወ” و የሚለው “ቢ” بِا በሚል ሲመጣ “ቢላህ” بِالله “በአላህ” እንደማለት ነው። አንድ ቃል ሁልጊዜ አንድ ትርጉም ይኖረዋል ማለት አይደለም፤ ለምሳሌ “ለው” َلَوْ ማለት “ቢሆን”if” ሲሆን “ኢን” إِن በሚል ይመጣል። ለናሙና ያክል ሌላ ሰዋስው ከቁርኣን ብንመለከት ለምሳሌ “ላ” َلَا የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም ይኖረዋል፦
1ኛ. “ላ” የሚለው ቃል ለቀድ” َلَقَدْ ማለትም “እርግጥ” የሚል ሆና ትመጣለች፤ ለምሳሌ፦
70፥40 በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ فَلَآ أُقْسِمُ بِرَبِّ ٱلْمَشَٰرِقِ وَٱلْمَغَٰرِبِ إِنَّا لَقَٰدِرُونَ

2ኛ. “ላ” የሚለው ቃል “ማ” مَا ማለትም “አፍራሽ ቃል” ሆና ትመጣለች፤ ለምሳሌ፦
4፥71 «ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ وَلَا تَقُولُوا۟ ثَلَٰثَةٌ

ስለዚህ ዋው መጀመሪያ ስለ ጀሃነም በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ አለመኖሩ እና ሁለተኛው ስለ ጀነት በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ መኖሩ ያለው ጥበብ በአጋጣቢ የሆነ ሳይሆን አላህ የጀሃነም ደጆች ያላቸው ውርደት የሚያመለክ ሲሆን የጀነት ደጆች ደግሞ ያላቸውን ክብር ያሳያል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አላህ ቅርብ ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥186 *"ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ "እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ*"፡፡ ስለዚህ ለእኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

"ዱዓእ" دُعَآء ማለት "ደዓ" دَعَا‎ ማለትም "ለመነ" "ተማጸነ" "ጸለየ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ልመና" "ተማጽንዖ" "ጸሎት" ማለት ነው። አምላካችን አላህ የሚለምኑትን ልመና ይቀበላል፦
2፥186 *"ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ "እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ*"፡፡ ስለዚህ ለእኔ ይታዘዙ፤ በእኔም ይመኑ፤ እነርሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ

"እኔ" ለሚለው ተውላጠ-ስም የገባው "ኢኒ" إِنِّي ሲሆን ማንነትን ያሳያል፥ ወደ አላህ ዱዓእ ስናደርግ በማንነቱ ለእኛ ቅርብ ነው። ዱዓእን በመስማት ቅርብ ነው፥ ይቅርታ ለጠየቁት ይቅርታ በማድረግ ቅርብ ነው፦
34፥50 «ብሳሳት የምሳሳተው በራሴ ላይ ብቻ ነው፡፡ ብመራም ጌታዬ ወደ እኔ በሚያወርደው ነው፡፡ *እርሱ ሰሚ፥ ቅርብ ነውና»* በላቸው፡፡ قُلْ إِن ضَلَلْتُ فَإِنَّمَا أَضِلُّ عَلَىٰ نَفْسِي ۖ وَإِنِ اهْتَدَيْتُ فَبِمَا يُوحِي إِلَيَّ رَبِّي ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ قَرِيبٌ
11፥ 61 ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ፡፡ *"ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደ እርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ፥ ለለመነው ተቀባይ ነውና»* አላቸው፡፡ وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ

በአንድ ጊዜ የሁሉንም ጸሎት የሚሰማው እርሱ ብቻ ነው። እርሱ በተለይ በሶላቱል ለይል ጊዜ የእኛ ዱዓእ ለመስማት ቅርብ ነው፦
ጃሚዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 210
ዐምር ኢብኑ ዐበሣህ እንደተረከው፦ "አቡ ኡማማህ ሰምቶ ለእኔ እንደነገረኝ ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ጌታ ወደ ባሪያው በሌሊቱ መገባደጃ ቀራቢ ነው፥ ስለዚህ በዚያ ሰአት አላህን ከሚዘክሩት ከሆንክ ያኔ ኹን"*። قَالَ سَمِعْتُ أَبَا أُمَامَةَ، رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ يَقُولُ حَدَّثَنِي عَمْرُو بْنُ عَبَسَةَ، أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ أَقْرَبُ مَا يَكُونُ الرَّبُّ مِنَ الْعَبْدِ فِي جَوْفِ اللَّيْلِ الآخِرِ فَإِنِ اسْتَطَعْتَ أَنْ تَكُونَ مِمَّنْ يَذْكُرُ اللَّهَ فِي تِلْكَ السَّاعَةِ فَكُنْ ‏

"አቅረብ" أَقْرَب ማለትም "ቀራቢ" የሚለው በሌላ ሐዲስ "የንዚሉ" يَنْزِلُ ማለትም "ይወርዳል" በሚል መጥቷል። "ዱንያ" دُّنْيَا ማለት "ቅርብ" ማለት ነው፥ እኛን ወዳቀፈው ሰማይ አምላካችን አላህ ይወርድና፦ "ማነው የሚለምነኝ እኔም የምቀበለው? ማነው የሚጠይቀኝ እኔም የምሰጠው? ማነው ይቅርታ የሚለኝ እኔም ይቅር የምለው? ይላል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6 ሐዲስ 201
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህም መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፡- *"ክብሩ ከፍ ያለውና የላቀው ጌታችን የሌሊቱ መገባደጃ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል፡፡ ከዛም፡- "ማነው የሚለምነኝ፥ እኔም የምቀበለው? ማነው የሚጠይቀኝ፥ እኔም የምሰጠው? ማነው ይቅርታ የሚለኝ፥ እኔም ይቅር የምለው? ይላል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ يَنْزِلُ رَبُّنَا تَبَارَكَ وَتَعَالَى كُلَّ لَيْلَةٍ إِلَى السَّمَاءِ الدُّنْيَا حِينَ يَبْقَى ثُلُثُ اللَّيْلِ الآخِرُ فَيَقُولُ مَنْ يَدْعُونِي فَأَسْتَجِيبَ لَهُ وَمَنْ يَسْأَلُنِي فَأُعْطِيَهُ وَمَنْ يَسْتَغْفِرُنِي فَأَغْفِرَ لَهُ
አላህ በምንነቱ ከዐርሽ በላይ ነው። በማንነቱ ደግሞ ወደ እኛ ይቀርብና ዱዓችንን ይቀበላል። አላህ ሁሉን ማድረግ ይችላል፥ በአንድ ጊዜ የሁሉንም ጸሎት መስማት ይችላል። በቀንና ሌሊት ውስንነት ያለብን እኛ ነን፥ እርሱ እንደ እኛ አይደለም፥ እኛ ከፎቅ ላይ ከወረድን ፎቅ ላይ የለንም። ምንነታችን በጊዜና በቦታ ውስን ስለሆነ። እርሱ ግን ለእልቅናው በሚገባው በማንነቱ ይወርዳል፥ ይቀርባል። የእርሱ አወራረድና አቀራረብ "ከይፊያህ" كَيْفِيَّة ማለትም "እንዴትነት"howness" ዐይታወቅም።
እኛ በዱዓእ ወደ አላህ በስንዝር ብንመጣ እርሱ ወደ እኛ በክንድ ይመጣል፥ እኛ በዱዓእ ወደ እርሱ በክንድ ብንመጣ እርሱ ወደ እኛ በሁለት ክንድ ይመጣል። በእርምጃ ወደ እርሱ ብንመጣ እርሱ በሩጫ ወደ እኛ ይመጣል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 34
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፡- *"የላቀው አላህ እንዲህ አለ፦ "ባሪያዬ ለእርሱ እደማደርግለት እንደሚያስበኝ ነኝ። ቢዘክረኝ እኔ ከእርሱ ጋር ነኝ፥ በራሱ ቢዘክረኝ እኔም እንዲሁ በራሴ እንዘክረዋለው። በብዙኃን ቢዘክረኝ እኔም ከእነርሱ በበለጠ በብዙኃን እንዘክረዋለው። እርሱ ወደ እኔ በስንዝር ቢመጣ እኔ ወደ እርሱ በክንድ እመጣለው፥ እርሱ ወደ እኔ በክንድ ቢመጣ እኔ ወደ እርሱ በሁለት ክንድ እመጣለው። በእርምጃ ወደ እኔ ቢመጣ እኔ በሩጫ ወደ እርሱ እመጣለው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ يَقُولُ اللَّهُ تَعَالَى أَنَا عِنْدَ ظَنِّ عَبْدِي بِي، وَأَنَا مَعَهُ إِذَا ذَكَرَنِي، فَإِنْ ذَكَرَنِي فِي نَفْسِهِ ذَكَرْتُهُ فِي نَفْسِي، وَإِنْ ذَكَرَنِي فِي مَلأٍ ذَكَرْتُهُ فِي مَلأٍ خَيْرٍ مِنْهُمْ، وَإِنْ تَقَرَّبَ إِلَىَّ بِشِبْرٍ تَقَرَّبْتُ إِلَيْهِ ذِرَاعًا، وَإِنْ تَقَرَّبَ إِلَىَّ ذِرَاعًا تَقَرَّبْتُ إِلَيْهِ بَاعًا، وَإِنْ أَتَانِي يَمْشِي أَتَيْتُهُ هَرْوَلَةً

መቅረብ፣ መውረድ፣ አብሮ መሆን፣ በእርምጃ መምጣት፣ በሩጫ መምጣት የማንነት ጉዳይ ነው። እኛ ወደ አላህ በስንዝር፣ በክንድ፣ በእርምጃ፣ በሩጫ መቅረባችን ምንነታዊ ሳይሆን ማንነታዊ እውነታ ነው። ይህ ሁሉ ሲገርመን አላህ ከራሳችን ይልቅ ለራሳችን ቅርብ ነው፦
50፥16 ሰውንም ነፍሱ በሐሳቡ የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፥ *እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደ እርሱ ቅርብ ነን*፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ ۖ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ الْوَرِيدِ

ይህ የሚያሳየው የአላህ ሁሉቻይነት፣ ሁሉን ሰሚነት፣ ሁሉን ተመልካችነት፣ ሁሉን ዐዋቂነት ነው። እኛ ወደ እርሱ በዱዓእ፣ በዚክር፣ በሶላት ስንቀርብ ሙቀረብ" مُقَرَّب ማለትም "ባለሟል" ወይም በብዜት "ሙቀረቡን" مُقَرَّبُون ይባላል፦
56፥11 *እነዚያ "ባለሟሎቹ" ናቸው*፡፡ أُولَـٰئِكَ الْمُقَرَّبُونَ
83፥21 *"ባለሟልዎቹ ይጣዱታል"*፡፡ يَشْهَدُهُ الْمُقَرَّبُونَ

ወደ እርሱ መቃረቢያ የምናደርገው አምልኮ "ቁርባን" قُرْبَان ይባላል፦
5፥35 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ *"ወደ እርሱም መቃረቢያን ፈልጉ*፡፡ ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መቃረቢያ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ወሢላህ" وَسِيلَة ሲሆን መልካም ሥራ ሁሉ "ተወሡል" تَوَسُّل ነው። አምላካችን አላህ ሙቀረቡን ከሚላቸው ባሮቹ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጣዖት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

16፥36 *በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን አምልኩ፥ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ

"ጧጉት" طَّٰغُوت የሚለው ቃል "ጠጋ" طَغَىٰ ማለትም "ወሰን አለፈ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "በአላህ ሐቅ ላይ ወሰን ማለፍ" ማለት ነው፦
79፥17 ወደ ፈርዖን ኺድ፡፡ እርሱ ወሰን አልፏልና፡፡ اذْهَبْ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ إِنَّهُ طَغَىٰ
79፥24 አለም፡- *«እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ፡፡»* فَقَالَ أَنَا رَبُّكُمُ الْأَعْلَىٰ

"ወሰን አልፏል" ለሚለው አላፊ ግስ የገባው ቃል "ጠጋ" طَغَىٰ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል፥ ፊርዐውን በአላህ ሐቅ ላይ ወሰን ያለፈው፦ "እኔ ታላቁ ጌታችሁ ነኝ" በማለት ነው። ስለዚህ በአላህ ሐቅ ላይ ያለፈ ማንነት ሆነ ምንነት "ጣዖት" ይባላል።
ሌላው የጣዖት አይነት አውሳን እና አስናም ናቸው፥ “አውሳን” أَوْثَٰن ማለት ከድንጋይ ተቀርፀው አምልኮ የሚቀርብላቸው ምንነት ናቸው፦
29፥25 ኢብራሂም አለም፦ *ከአላህ ሌላ ጣዖታትን አማልክት የያዛችሁት በቅርቢቱ ሕይወት በመካከላችሁ ለመዋደድ ብቻ ነው*። وَقَالَ إِنَّمَا ٱتَّخَذْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ أَوْثَٰنًۭا مَّوَدَّةَ بَيْنِكُمْ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا

“አስናም” أَصْنَام ማለት ደግሞ ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሰርተው አምልኮ የሚቀርብላቸው ምንነት ናቸው፦
26፥70 *ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ታመልካላችሁ?*» ባለ ጊዜ፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا تَعْبُدُونَ
26፥71 *ጣዖታትን እናመልካለን፤ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ نَعْبُدُ أَصْنَامًۭا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ

ሌላው ጣዖት ሊሆን የሚችለው በራሳችን ውስጥ ያለችው "ነፍሢያህ" نَفْسِيَّة‎ ናት፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

“አህዋእ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” ማለት ነው፥ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው "ዝንባሌ" ነው። ታዲያ ስንጋደል በምን መንገድ ይሆን? አላህን ብቻ አምላክ አርገን ይዘን የእርሱን ውዴታ ለመፈለግ ወይስ ዝንባሌ አምላክ አርገን ይዘን ለዘረኝነት፣ ለጎጠኝነት፣ ለጠርዘኝነት፣ ለቡድንተኝነት? ልቡንም አላህ ከማስታወስ የዘነጋውን፣ ፍላጎቱንም የተከተለውን፣ ነገሩም ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው መታዘዝ የለብንም፦
18፥28 *"ልቡንም እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውን፣ ፍላጎቱንም የተከተለውን፣ ነገሩም ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ"*፡፡ وَلَا تُطِعْ مَنْ أَغْفَلْنَا قَلْبَهُ عَن ذِكْرِنَا وَاتَّبَعَ هَوَاهُ وَكَانَ أَمْرُهُ فُرُطًا

እንደዚህ አይነት ሰው የሚጋደለው በልቡ ላለው ጣዖት ለዝንባሌው ነው። እነዚያ ያመኑት ሰዎች በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፥ እነዚያ የካዱትም በጣዖት መንገድ ይጋደላሉ፦
4፥76 *"እነዚያ ያመኑት ሰዎች በአላህ መንገድ ይጋደላሉ፡፡ እነዚያ የካዱትም በጣዖት መንገድ ይጋደላሉ፡፡ የሰይጣንንም ጭፍሮች ተጋደሉ፡፡ የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነውና"*፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ كَفَرُوا يُقَاتِلُونَ فِي سَبِيلِ الطَّاغُوتِ فَقَاتِلُوا أَوْلِيَاءَ الشَّيْطَانِ ۖ إِنَّ كَيْدَ الشَّيْطَانِ كَانَ ضَعِيفًا