"ከበፊቱ "ባወረደው" መጽሐፍ እመኑ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ እንግዲህ አምላካችን አላህ ተውራትና ኢንጅል የሚላቸው ወደ ሙሳ እና ዒሣ የወረዱትን ወሕይ ብቻና ብቻ ነው። ታዲያ ወደ ነቢያት የተወረዱትን “ኑዙል” ለምን ወደ አይሁድ እና ክርስቲያን በማስጠጋት “ወደ እናንተ በተወረደው” በማለት ይናገራል? የሚለውን ሙግት በአንድ ናሙና መረዳት ይቻላል፤ ለምሳሌ አላህ ደመናን ያጠለለውና መናን እና ድርጭትን ያወረደው በሙሳ ዘመን ቢሆንም በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ወደነበሩት አይሁድ ላይ እንደሆነ እና ወይፈንን አምላክ አድርገው የያዙት እነርሱ እንደሆኑ ይናገራል፦
2፥57 *”በእናንተም ላይ”* ደመናን አጠለልን፡፡ *”በእናተም ላይ”* መናን እና ድርጭትን አወረድን፡፡ وَظَلَّلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْمَنَّ وَٱلسَّلْوَىٰ
2፥51 ሙሳንም አርባን ሌሊት በቀጠርነው ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ ከዚያም ከእርሱ መኼድ በኋላ *”እናንተ በዳዮች ስትኾኑ ወይፈንን አምላክ አድርጋችሁ ያዛችሁ”*፡፡ وَإِذْ وَٰعَدْنَا مُوسَىٰٓ أَرْبَعِينَ لَيْلَةًۭ ثُمَّ ٱتَّخَذْتُمُ ٱلْعِجْلَ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَأَنتُمْ ظَٰلِمُونَ
አላህ በሙሳ ጊዜ መናን እና ድርጭትን አውርዶ ግን በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ያሉትን አይሁዳውያንን በሁለተኛ መደብ “በእናተም ላይ” መናን እና ድርጭትን አወረድን ካለ፥ በተመሳሳይ ወደ ነብያት ያወረደው በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ወደነበሩት አይሁድ እና ክርስቲያን “ወደ እናንተ አወረድን” ቢል ምን ያስደንቃል?
የአይሁድ ምሁራን ሆነ የክርስትና ምሁራን በእጃቸው ያሉት አምስቱ ኦሪት እና አራቱ ወንጌሎች ሙሉ ለሙሉ ከአምላክ የወረዱ የአምላክ ንግግር ናቸው ብለው አያምኑም፤ ከዚያ ይልቅ በአምላክ ንግግር ላይ የታሪክ ጸሐፊያን ንግግር እንዳለበት ያምናሉ፤ የአምላክ ንግግር ሙሉ ለሙሉ እንዳልሰፈረ፥ ሆን ተብሎም ይሁን ሳይታወቅ በቀኖና መጽሐፍት ያልተካተቱ የጠፉ ቅነሳዎች እንዳሉ ያትታሉ። እነዚህ መጽሐፍት በጊዜ ሂደት የሰው ንግግር ገብቶባቸዋል፥ ከዚያም ባሻገር ተቀንሰውባቸዋል።
ይህ በኢሥላም ተሕሪፍ ይባላል፤ "ተሕሪፍ" تَحريف ማለት "ብርዘት"corruption" ማለት ሲሆን ይህም ብርዘት በአንድ ተናጋሪ ንግግር ላይ ሌላ ሰው ያንን ንግግር ሲቀንስ አሊያም በዛ ንግግር ላይ ሲጨምር መበረዝ ይባላል፤ የፈጣሪን ንግግር ሰው ከቀነሰ ወይም ከጨመረ "ተሕሪፍ" ይባላል።
ነቢያችን”ﷺ” ከመጽሐፉ ሰዎች የምንሰማውን ሁሉ መቀበልና ማስተባበል እንደሌለብን ነግረውናል፤ ከተቀበልን የጨመሩት ጉዳይ ስላለ ጥሩ አይመጣም፤ ካስተባበልን መለኮታዊ ቅሪት ውስጡ ስላለው ጥሩ አይመጣም፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65 , ሐዲስ 4485
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ የመጽሐፉ ሰዎች ተውራትን በዕብራይስጥ ያነቡ ነበር፤ ለሙሥሊሙ ደግሞ በዐረቢኛ ያብራሩ ነበር፤ የአላህም መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *“የመጽሐፉን ሰዎች አትመኗቸው፤ አታስተባብሏቸውም። ነገር ግን “በአላህ እና ወደ እኛ በተወረደው አመንን” በሉ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ كَانَ أَهْلُ الْكِتَابِ يَقْرَءُونَ التَّوْرَاةَ بِالْعِبْرَانِيَّةِ، وَيُفَسِّرُونَهَا بِالْعَرَبِيَّةِ لأَهْلِ الإِسْلاَمِ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” لاَ تُصَدِّقُوا أَهْلَ الْكِتَابِ وَلاَ تُكَذِّبُوهُمْ، وَقُولُوا {آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنْزِلَ} الآيَةَ”
ይህ ጆሮን ኮርኩሮ በርን ቆርቁሮ የሚገባ የተሕሪፍ እሳቤን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ጭማሬ"
አምላካችን አላህ ከራሱ የሚያወርደው ወሕይ እውነት ነው፦
34፥48 ፦ጌታዬ *“እውነትን ያወርዳል"*፤ ሩቅ የኾኑትን ሚስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው *በላቸው*። قُلْ إِنَّ رَبِّى يَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَّٰمُ ٱلْغُيُوبِ
ይህ ከአላህ የወረደውን እውነት የመጽሐፉ ሰዎች ከውሸት ማለት ከሰው ንግግር ጋር ቀላቅለውታል፦
3፥71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *“እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ*? እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
ይህ የሰው ንግግር "ውሸት" ለምን ተባለ? ምክንያቱም የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የቀጠፉት ጭማሬ ስለሆነ ነው፦
2፥79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
እዚው ዐውድ ላይ ስንመለከት ከመጽሐፉ ሰዎች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው በርዘውታል፦
2፥75 *ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ "የሚለውጡት" ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?"* أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون
"የሚለውጡት" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዩሐረፉነሁ" يُحَرِّفُونَهُ ሲሆን "የሚበርዙት" ማለት ነው፤ "ዩሐረፉ" يُحَرِّفُ የሚለው አላፊ ግስ "ሐረፈ" حَرَفَ ማለትም "በረዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ የሚበርዙት ፊደሉ "ሐርፍ" حَرْف ሲባል፥ በራዡ "ሙተሐሪፍ" مُتَحَرِّف ሲልባ፥ የመበረዙ ድርጊቱ ደግሞ "ተሕሪፍ" تَحريف ይባላል፤ ይህ ሙግት የሥነ-ቋንቋ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።
በተጨማሪም ከቀደምት የነቢያችን”ﷺ” ቅርብ ባልደረባ ኢብኑ ዓባሥ”ረ.ዐ” የሱረቱል በቀራ 2፥79 አንቀጽን በሶሒህ ሐዲስ ሲፈስረው እንዲህ ይላል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 52, ሐዲስ 46:
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ" ሲናገር፦ *ሙስሊሞች ሆይ ለምን የመጽሐፉ ሰዎችን ትጠይቃላችሁ? በተመሳሳይ መጽሐፋችሁ ከአላህ ዘንድ ለነቢዩ"ﷺ" የተወረደው ወቅታቂ መረጃ እና የምትቀሩት እያለ? መጽሐፋ አልተበረዘምን? አላህ ለእናንተ የመጽሐፉ ሰዎች በእጆቻቸው በርዘው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» እንደሚሉ አውርዷል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ يَا مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ، كَيْفَ تَسْأَلُونَ أَهْلَ الْكِتَابِ، وَكِتَابُكُمُ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَى نَبِيِّهِ صلى الله عليه وسلم أَحْدَثُ الأَخْبَارِ بِاللَّهِ، تَقْرَءُونَهُ لَمْ يُشَبْ، وَقَدْ حَدَّثَكُمُ اللَّهُ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ بَدَّلُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ وَغَيَّرُوا بِأَيْدِيهِمُ الْكِتَابَ، فَقَالُوا هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ، لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلاً أَفَلاَ يَنْهَاكُمْ مَا جَاءَكُمْ مِنَ الْعِلْمِ عَنْ مُسَاءَلَتِهِمْ، وَلاَ وَاللَّهِ مَا رَأَيْنَا مِنْهُمْ رَجُلاً قَطُّ يَسْأَلُكُمْ عَنِ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَيْكُمْ
የመጽሐፉ ሰዎች እዉነቱን በዉሸት በመቀላቀል ሲበረዙት አምላካችን አላህ ቁርኣንን ፉርቃን በማድረግ አውርዷል፤ “ፉርቃን” فُرْقَان ማለት “እውነትን ከውሸት የሚለይ” ማለት ነው፦
25፥1 ያ *ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው*፡፡ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا
ተውራትንና ኢንጂልን ከቁርኣን በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ ቢያወርዳቸውም ቁርኣን ግን ከእርሱ በፊት ያሉትን ተውራትንና ኢንጂልን የሚያረጋግጥ እና የተቀላቀለው እውነት ከውሸት የሚለይ ነው፦
3፥3 *”ከእርሱ በፊት ያሉትን የሚያረጋግጥ”* ሲኾን መጽሐፉን በአንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ *”ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል”*፡፡ نَزَّلَ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ
3፥4 *ከቁርኣን በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፡፡ ፉርቃንንም አወረደ*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَأَنزَلَ الْفُرْقَان
5:48 *"ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ “አረጋጋጭ” እና በእርሱ ላይ “ተጠባባቂ” ሲሆን በእውነት አወረድን"*። وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ
የመጽሐፉ ሰዎች ጋር ያለው የተበረዘ መፅሐፍ ነው ማለት ወተት ከቡና ጋር ሲቀላቀል ኦርጂናሉ ወተት ተበርዟል፤ ነገር ግን የወተት ቅሪት በማኪያቶ ላይ አለ፤ በተመሳሳይ የአላህ ንግግር የወረደበት ቋንቋ ስረ-መሰረቱ፣ የቃሉ አንጓ ባይኖርም መልእክቱ እና ሃሳቡ በቅሪት ደረጃ አለ፤ የመጽሐፉ ሰዎች ጋር ያሉት መጽሐፍት ሙሉ ለሙሉ እውነትን ነው ብለን እንደማንቀበል ሁሉ ሙሉ ለሙሉ ሐሰት ነው ብለን አናስተባብልም፤ ቁርኣን ከወረደበት ግብና አላማ፣ ፋይዳና ሚና አንዱ ከአላህ የወረደውን እውነት ለማረጋገጥ እና ቀጥፈው የጨመሩትን ውሸት ደግሞ ሊያርም ነው፤ ከአላህ የወረደውን እውነት ስለሚያረጋግጥ “ሙሰዲቃን” مُصَدِّقًا “አረጋጋጭ” ሲባል የሰዎች ንግግር የገቡበትን በማረሙ ደግሞ “ሙሃይሚን” مُهَيْمِنًا ማለትም “አራሚ” correcter” ወይም “ተቆጣጣሪ”supervisor” ይባላል።

የአይሁድ ሆነ የክርስትና ምሁራን ባይብል የአምላክ ንግግር እና የሰው ንግግር ቅልቅል እንደሆነ ያምናሉ፤ ይህ በግሪክ "ስይነርጎስ" ይባላል፤ "ስይነርጎስ" συνεργός ማለትም "ቅልቅል" ማለት ነው። ለምሳሌ ለሙሴ በተሰጠው ቶራህ ላይ ታሪክ ጸሐፊዎች ከሙሴ በፊት፣ በሙሴ ጊዜ እና ከሙሴ በኃላ ያለውን ታሪክ ጨምረውበታል። በተመሳሳይ ለኢየሱስ በተሰው ወንጌል ላይ ታሪክ ጽሐፊዎች ከኢየሱስ ማስተማር በፊት፣ በሚያስተምርበት ጊዜ እና ካስተማረ በኃላ ያለውን ታሪክ ጨምረውበታል። በተለይ አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ በተውራት ላይ የተጨመሩትን ታሪኮች ቀኖና በማድረግ አጽድቀዋል፥ እንዲሁ ክርስቲያኖች በ 397 ድህረ-ልደት”AD” በካርቴጅ ጉባኤ በኢንጅል ላይ የተጨመሩትን ታሪኮች ቀኖና በማድረግ አጽድቀዋል።
ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ቅነሳ እናያለን......
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ወሰላሙ አለይኩም
ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ቅነሳ እናያለን......
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ወሰላሙ አለይኩም
ተሕሪፍ
ገቢር ሁለት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
3፥71 *የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን *ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ*? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
አላህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት መልክተኞቹን በግልጽ ማስረጃዎች ልኳል፤ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችን ወደ እነርሱ አውርዷል፤ ነቢያችንም”ﷺ” ወደ መልክተኞቹ የተወረደውን ለሰዎች ሊገልጹ ቁርኣን ወርዶላቸዋል፤ ቁርኣን ከእርሱ በፊት ወደ ነቢያት የተወረደውን የሚያረጋግጥ እና በውስጡ ያለውን የሚዘረዝር ሲሆን ከዓለማቱ ጌታ የተወረደ ነው፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *”መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን”*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْمِيزَانَ لِيَقُومَ ٱلنَّاسُ بِٱلْقِسْطِ
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎች እና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ ወደ አንተም ለሰዎች *”ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው”* እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን፡፡ بِٱلْبَيِّنَٰتِ وَٱلزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُون
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን *”ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር”* በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
“ተፍሲል” تَفْصِيل ማለት “ፈሰለ” فَصَّلَ ማለትም “አብራራ” “ተነተነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማብራሪያ” ወይም “መተንተኛ”explanation” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ በበፊቱ በወረደው ወሕይ ላይ ምን ብሎ ተናግሮ እንደነበረ ለመናገር፦ “ከተብና” َكَتَبْنَا ወይም “ቁልና” قُلْنَا አሊያም “አውሐይና” َأَوْحَيْنَا በሚል ለእኛ ይነግረናል፤ ለምሳሌ በተውራት ምን ተናግሮ እንደነበር ያረጋግጣል፦
5፥45 በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ *“ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፤ ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው”* ማለትን *ጻፍን*፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌ
2፥60 ሙሳም ለሕዝቦቹ መጠጥን በፈለገ ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ «ድንጋዩንም በበትርህ ምታ» *አልነው*፡፡ وَإِذِ اسْتَسْقَىٰ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ فَقُلْنَا اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَر
26፥63 ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» *ስንል ላክንበት*፡፡ መታውና ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡ فَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْبَحْرَ ۖ فَانفَلَقَ فَكَانَ كُلُّ فِرْقٍ كَالطَّوْدِ الْعَظِيمِ
ከላይ የዘረዘርናቸው አንቀጾች በአይሁዳውያን የቶራህ ቀኖና ውስጥ መልእክቱና ሃሳቡ በቅሪት ደረጃ ተቀምጠዋል፦
ዘጸአት 21፥24-25 *ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ መቃጠል በመቃጠል፥ ቍስል በቍስል፥ ግርፋት በግርፋት ይከፈል*።
ዘጸአት 20፥7-8 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ *በትርህን ውሰድ፤ አንተና ወንድምህ አሮን ማኅበሩን ሰብስቡ፥ ድንጋዩም ውኃን እንዲሰጥ እነርሱ ሲያዩ ተናገሩት፤ ከድንጋዩም ውኃ ታወጣላቸዋለህ*፤ እንዲሁም ማኅበሩን ከብቶቻቸውንም ታጠጣላቸዋለህ።
ዘጸአት 14፥16 *አንተም በትርህን አንሣ፥ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ*፥ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ።
ነገር ግን አላህ ካወረዳቸው ቅሪት ሁሉም በአህለል ኪታብ ይገኛል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ወደ ኑሕ፣ ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት ወደ ሁድና ሷሊሕ፣ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም የተወረዱት ቅሪት በመጽሐፉ ሰዎች እጅ የሉም፦
4፥163 እኛ *"ወደ ኑሕ እና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን"*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
ወደ ኑሕ የወረደው እናንተ ጋር አለ ወይ? ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት ወደ ሁድና ሷሊሕ የወረዱት እናንተ ጋር አለ ወይ? ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም የተወረደ እናንተ ጋር አለ ወይ? መልሱ የለም ነው።

ነጥብ ሁለት
"ቅነሳ"
አምላካችን አላህ ተውራት እና ኢንጅል የሚላቸው ከራሱ የወረዱት ስለ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት የሚናገሩ ናቸው፤ በተውራትና በኢንጂል ተነግሮ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ በሆነ "እመኑ" ይላል፦
7፥157 *ለእነዚያ ያንን እነርሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ* የሚከተሉ ለኾኑት በእርግጥ እጽፍለታለሁ፡፡ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِندَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ
7፥158 በአላህ በዚያም በአላህና በቃላቶቹ በሚያምነው *"የማይጽፍ የማያነብ ነቢይ በኾነው መልክተኛው እመኑ"*፡፡ ቅንንም መንገድ ትመሩ ዘንድ ተከተሉት፡፡» فَآمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ النَّبِيِّ الْأُمِّيِّ الَّذِي يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَكَلِمَاتِهِ وَاتَّبِعُوهُ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
የመጽሐፉም ሰዎች በተውራትና በኢንጂል ተነግሮ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ በሆነ ባመኑ እና ከክህደትም በተጠነቀቁ ኖሮ አላህ ከእነርሱ ኃጢኣቶቻቸውን ባበሰ እና የመጠቀሚያ ገነቶችንም ባስገባቸው ነበር፤ ስለ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት የሚናገሩትን ከጌታቸው ወደ እነርሱ የተወረደውን ተውራትንና ኢንጂልን ባቋቋሙ ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ሥር በተመገቡ ነበር፦
5፥65 *የመጽሐፉም ሰዎች "ባመኑ" እና ከክህደትም በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነርሱ ኃጢኣቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ባገባናቸው ነበር*፡፡ وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَكَفَّرْنَا عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأَدْخَلْنَاهُمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ
5፥66 *እነርሱም ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታቸውም ወደ እነርሱ የተወረደውን መጽሐፍ ባቋቋሙ ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ሥር በተመገቡ ነበር፡፡ ከእነርሱ ውስጥ ትክክለኞች ሕዝቦች አሉ፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ የሚሠሩት ነገር ከፋ*! وَلَوْ أَنَّهُمْ أَقَامُوا التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْهِم مِّن رَّبِّهِمْ لَأَكَلُوا مِن فَوْقِهِمْ وَمِن تَحْتِ أَرْجُلِهِم ۚ مِّنْهُمْ أُمَّةٌ مُّقْتَصِدَةٌ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ سَاءَ مَا يَعْمَلُونَ
ከመጽሐፉም ሰዎች ውስጥ ትክክለኞች ሕዝቦች አሉ፤ ነገር ግን ከእነርሱም ብዙዎቹ የሚሠሩት ነገር ከፋ፤ ብዙዎች ከእነሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያወቁ ሲኾኑ ስለ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት የሚናገረውን እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ፦
2፥146 *"እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል፡፡ ከእነሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያወቁ ሲኾኑ እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ*"፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ يَعْرِفُونَهُ كَمَا يَعْرِفُونَ أَبْنَاءَهُمْ ۖ وَإِنَّ فَرِيقًا مِّنْهُمْ لَيَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَهُمْ يَعْلَمُونَ
3፥71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ? *እዉነቱንም እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ?* يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
ጥያቄአችን ለአህለል ኪታብ፦ "በእናንተ እጅ በሚገኘው አምስቱ የኦሪት መጽሐፍት እና በአራቱ ወንጌሎች ስለ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት ትንቢት አለን? መልሳችሁ፦ "ኸረ በፍጹም የለም" ከሆነ እንግዲያውስ አላህ ተውራት እና ኢንጅል የሚለው ከእርሱ የተወረዱትንና ስለ ነቢያችን"ﷺ" መምጣት የሚናገሩትን ብቻ ነው። እናንተ ጋር ያለው መለኮታዊ ቅሪት እንጂ ሥረ-መሠረት"orgin" አይደለም። አምላካችን አላህ በተውራት፦ "እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው" ብሎ ተናግሮ ነበር፦
5፥32 በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ፦ “እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው” ማለትን *ጻፍን*፡፡ مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا
ይህ ንግግር በፔንታተች ውስጥ ተቀንሶ ነገር ግን በአፖክራፋ ውስጥ ዛሬ ተገኝቷል፦
ሚሽናህ ሳንድሬህ 4፥4 *በምድር ላይ ያለማጥፋት ነፍስን የገደለ ሰው፣ ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው፣ ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው*። לפיכך נברא אדם יחידי ללמדך שכל המאבד נפש אחת [מישראל] מעלה עליו הכתוב כאילו איבד עולם מלא וכל’המקיים נפש אחת מישראל מעלה עליו הכתוב כאילו קיים עולם

አላህ ለዒሣ፦ "በል" ብሎት በኢንጅል ከተናገረው አንዱ፦ "የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና *ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ" የሚል ነው፦
61፥6 የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና *ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ*፡፡ በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِن بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ ۖ فَلَمَّا جَاءَهُم بِالْبَيِّنَاتِ قَالُوا هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ
ነገር ግን ይህ ንግግር ዛሬ በአራቱ ወንጌሎች የሉም፤ ለዛ ነው አላህ ለነቢያችን"ﷺ"፦ "የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! "ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደ እናንተ የተወረደውን እስከምታቆሙ ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም" በል ያለው፦
5፥68 *"«እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! "ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደ እናንተ የተወረደውን" እስከምታቆሙ ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም» በላቸው"*፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَسْتُمْ عَلَىٰ شَيْءٍ حَتَّىٰ تُقِيمُوا التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُم
አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ ከተውራት የማይፈልጓቸውን በቃል ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የነበረውን የተውራት ክፍሎች ማለትም "ሚሽናህ" የተባሉትን በመቀነስ፥ እንዲሁ ክርስቲያኖች በ 397 ድህረ-ልደት”AD” በካርቴጅ ጉባኤ ከኢንጅል ላይ የማይፈልጓቸው የወንጌል ክፍሎች በመቀነስ “አፓክራፋ” አድርገዋል። “አፓክራፋ” የሚለው ቃል “አፓክራፈስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፤ እውነትን እያወቁ በማደባበስና በማለባበስ ደብቀዋል። እነዚያ አላህ ከመጽሐፍ ያወረደውን የሚደብቁ በእርሱም በመደበቃቸው ጥቂትን ዋጋ የሚገዙ እነዚያ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም፦
2፥174 *እነዚያ አላህ ከመጽሐፍ ያወረደውን የሚደብቁ በእርሱም በመደበቃቸው ጥቂትን ዋጋ የሚገዙ እነዚያ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም"*፡፡ አላህም በትንሣኤ ቀን አያናግራቸውም፤ ከኃጢኣት አያጠራቸውምም፡፡ ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ يَكْتُمُونَ مَا أَنزَلَ اللَّهُ مِنَ الْكِتَابِ وَيَشْتَرُونَ بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۙ أُولَـٰئِكَ مَا يَأْكُلُونَ فِي بُطُونِهِمْ إِلَّا النَّارَ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን በተውራትና በኢንጂል የተነገረለት የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የሆነ መልክተኛው በእርግጥ መጣላችሁ፦
5፥15 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ قَدْ جَآءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًۭا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَيَعْفُوا۟ عَن كَثِيرٍۢ ۚ قَدْ جَآءَكُم مِّنَ ٱللَّهِ نُورٌۭ وَكِتَٰبٌۭ مُّبِينٌۭ

መደምደሚያ
ከመጽሐፉ ሰዎች እውነት ከውሸት ጋር በመቀላቀል የሚጨምሩ እና እውነትን የሚደብቁት ጥቂትን ዋጋን ለመግዛት ነው፦
2፥79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለእነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
2፥174 *እነዚያ አላህ ከመጽሐፍ ያወረደውን የሚደብቁ በርሱም በመደበቃቸው ጥቂትን ዋጋ የሚገዙ እነዚያ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም"*፡፡ አላህም በትንሣኤ ቀን አያናግራቸውም፤ ከኃጢኣት አያጠራቸውምም፡፡ ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ يَكْتُمُونَ مَا أَنزَلَ اللَّهُ مِنَ الْكِتَابِ وَيَشْتَرُونَ بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۙ أُولَـٰئِكَ مَا يَأْكُلُونَ فِي بُطُونِهِمْ إِلَّا النَّارَ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
"ጥቂት ዋጋ መግዛት ወይም መለወጥ" ማለት ለጥቂቱ የዱንያህ ዋጋ ማለትም ጥቅምና ሥልጣን ነው፦
40፥39 «ወገኖቼ ሆይ! *ይህቺ ቅርቢቱ ሕይወት ጥቂት መጣቀሚያ ብቻ ናት፡፡ መጨረሻይቱም ዓለም እርሷ መርጊያ አገር ናት*፡፡» يَا قَوْمِ إِنَّمَا هَـٰذِهِ الْحَيَاةُ الدُّنْيَا مَتَاعٌ وَإِنَّ الْآخِرَةَ هِيَ دَارُ الْقَرَارِ
16፥95 በአላህም ቃል ኪዳን ጥቂትን ዋጋ አትግዙ፡፡ የምታውቁ ብትኾኑ አላህ ዘንድ ያለው ምንዳ እርሱ ለእናንተ በላጭ ነውና፡፡ وَلَا تَشْتَرُوا بِعَهْدِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۚ إِنَّمَا عِندَ اللَّهِ هُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
3፥77 *እነዚህ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሐላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ዕድል የላቸውም*፡፡ በትንሣኤ ቀንም አላህ አያነጋግራቸውም፡፡ ወደ እነርሱም አይመለከትም አያነጻቸውምም፡፡ ለእነሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ يَشْتَرُونَ بِعَهْدِ اللَّهِ وَأَيْمَانِهِمْ ثَمَنًا قَلِيلًا أُولَـٰئِكَ لَا خَلَاقَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ وَلَا يَنظُرُ إِلَيْهِمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ
ከመጽሐፉ ሰዎች ጥቂትን ዋጋን ለመግዛት እውነት ከውሸት ጋር በመቀላቀል የሚጨምሩ እና እውነትን የሚደብቁት "ወይል" وَيْل በሚባል የጀሃነም እቶን ይቀጣሉ፤ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን ይበላሉ፡፡ አምላካችን አላህ ግልጽ ከሆነው ከአህሉል ኪታብ ፈሣድ እና ስውር ከሆነው ከሙብተዲዕ ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን።

ተፍሢር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
38፥29 ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ *የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው*፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَاب
“ተደቡር” تَدَبُر ማለት “ማስተንተን” ማለት ነው፤ “ዱቡር” دُبُر ማለት “ጀርባ” ማለት ሲሆን ከቁርኣን ሑሩፍ በስተ-ጀርባ ያለውን ዕውቀት መረዳት ተደቡር ይባላል፤ አምላካችን አላህ ብሩክ የሆነው መጽሐፍ ቁርኣንን ወደ ነቢያችን"ﷺ" ያወረደው የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ ነው፦

የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን ለማስተንተን በተደቡር ይፈስሩታል፤ "ተፍሢር" تَفْسِير የሚለው ቃል "ፈሠረ" فَسَرَ ማለትም "አብራራ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማብራሪያ"commentary" ማለት ነው፦
25፥33 በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ መልካምን "*"ፍችም"* የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ፡፡ وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا
"ፍች" ለሚለው ቃል የገባው "ተፍሢራ" تَفْسِيرًا ሲሆን የተፍሢር አንስታይ መደብ ነው፤ ቁርኣን በማስተንተን የሚፈሥሩ የአእምሮ ባለቤቶች በነጠላ "ሙፈሢር" مُفسّر ይባላሉ፥ በብዜት ደግሞ "ሙፈሥሩን" مفسّرون ይባላሉ። ይህ የሥነ-አፈታት ጥናት"hermeneutics" በአምስት አይነት አፈታት ይፈታል፤ እነርሱም፦ የዐውድ ሙግት፣ የቋንቋ ሙግት፣ የሰዋስው ሙግት፣ የተዛማች ሙግት እና የታሪክ ሙግት ይባላሉ። እስቲ እናስተንትን፦
ነጥብ አንድ
"የዐውድ ሙግት"
"የዐውድ ሙግት"contextual approach" ማለት አንቀጹ ላይ ያለውን እና ከአንቀጹ በፊትና በኃላ ያሉትን አናቅጽ በማስተንተን የአንቀጹን ምህዋር፣ አውታርና ምህዳር መረዳት ነው፤ ይህ "ሢያቅ" سیاق ማለትም "ዐውድ"context" በምሁራን ዘንድ "ፍተታ"exegesis" ይባላል፤ ለናሙና ያክል አንድ አንቀጽ እንመልከት፦
2፥79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሰው ንግግር በእጆቻቸው ፅፈው «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው የበረዙት እነማን እንደሆኑ ቁጥር 75 ላይ ዐውደ-ንባቡን ተከትለን ማግኘት እንችላለን፦
2፥75 *ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ንግግር የሚሰሙ እና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ “የሚለውጡት” ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?”* أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُون
በግርድፉ ይህ በቂ ነው፤ እስቲ የቋንቋ ሙግት እንመልከት፦
ነጥብ ሁለት
"የቋንቋ ሙግት"
"የቋንቋ ሙግት"linguistical approach" ማለት ቁርኣን በወረደበት ቋንቋ መረዳት ነው፤ አምላካችን አላህ ቁርኣንን ያወረደው በዐረቢኛ ነው፦
43፥3 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
13፥37 *እንደዚሁ በዐረብኛ የተነገረ ፍትሕ ሲኾን አወረድነው*፡፡ وَكَذَٰلِكَ أَنزَلْنَاهُ حُكْمًا عَرَبِيًّا
ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ ሀሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ መታየት ያለበት። ለናሙና ያክል አንዳንድ የቋንቋ ሙግት እንመልከት፦
“ፊ” فِي ማለት “ውስጥ” ማለት ቢሆንም “ቢ” بـِ ማለትም “በ” በሚል ይመጣል፦
2፥195 *”በ”አላህም መንገድ ለግሱ*፡፡ በእጆቻችሁም ነፍሶቻችሁን ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡ በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡ وَأَنفِقُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةِ ۛ وَأَحْسِنُوا ۛ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُحْسِنِينَ
“ላ” َلَا ማለትም “አይደለም” ማለት ቢሆንም “ለቀድ” َلَقَدْ ማለትም “እርግጥ” በሚል ይመጣል፦
70፥40 *በምሥራቆችና በምዕራቦችም ጌታ እምላለሁ፡፡ እኛ “በእርግጥ” ቻዮች ነን*፡፡ فَلَا أُقْسِمُ بِرَبِّ الْمَشَارِقِ وَالْمَغَارِبِ إِنَّا لَقَادِرُونَ
“ማ” مَا ማለት “አይደለም” ማለት ቢሆንም “አለዚ” الَّذِي ማለትም “ያ” በሚል ይመጣል፦
2፥285 *መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም እንደዚሁ አመኑ*፡፡ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُون
“ወ” وَ ማለት “እና” ማለት ቢሆንም “ቢ” بـِ ማለትም “በ” በሚል ይመጣል፦
53፥1 *”በ”ኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ*፡፡ وَالنَّجْمِ إِذَا هَوَىٰ
በሌጣው ይህ በቂ ነው፤ እስቲ የሰዋስው ሙግት እንመልከት፦

ነጥብ ሦስት
"የሰዋስው ሙግት"
"የሰዋስው ሙግት"grammatical approach" ማለት በቁርኣን ላይ ስም፣ ተውላጠ-ስም ለምሳሌ ባለቤት፣ ተሳቢ፣ አገናዛቢ፣ አመልካች፣ አንጻራዊ፣ ድርብ ተውላጠ-አስማት(ስሞች) መረዳት፣ ግሥ፣ ተውሳከ-ግሥ፣ መስተጻምር፣ መስተዋድድ መረዳትን ያጠቃልላል። ይህ እሳቤ “አል በላጋህ” ይባላል፤ “አል በላጋህ” البلاغة ማለት “የንግግር ስልት”rhetoric” ማለት ነው፤ ይህም በስም፣ በተውላጠ-ስም፣ በግስ፣ በገላጭ፣ በመስተዋድድ፣ በመስተጻምር ላይ የሚታየው የነጠላና የብዜት፣ የተባእታይና የአንስታይ፣ የተለዋዋጭ ቃላት የአነጋገር ስልት ነው፤ በግሪክ “ሬቶሪኮስ” ῥητορικός ይሉታል። ለናሙና ያክል የተወሰኑ ጥቅሶችን ማየት ይቻላል፦
36፥78 ለእኛም ምሳሌን አደረገልን፡፡ መፈጠሩንም ረሳ፡፡ *«አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲኾኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው?»* አለ፡፡ وَضَرَبَ لَنَا مَثَلًا وَنَسِيَ خَلْقَهُ ۖ قَالَ مَن يُحْيِي الْعِظَامَ وَهِيَ رَمِيمٌ
እዚህ አንቀጽ ላይ “ዐዝም” عَظْم በነጠላ “አጥንት”bone” ማለት ነው፤ “ዒዛም” عِظَام ደግሞ የዐዝም ብዜት ሲሆን “አጥንቶች” ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ አጥንቶች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም በነጠላ “ሂየ” هِيَ እንጂ በብዜት “ሁነ” هُنَ አይደለም። በተጨማሪ፦
27፥88 *”ጋራዎችንም እርሷ” እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትኾን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያታለህ*፡፡ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ ተመልከት፡፡ እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ وَتَرَى الْجِبَالَ تَحْسَبُهَا جَامِدَةً وَهِيَ تَمُرُّ مَرَّ السَّحَابِ ۚ صُنْعَ اللَّهِ الَّذِي أَتْقَنَ كُلَّ شَيْءٍ ۚ إِنَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَفْعَلُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ “ጀበል” جَبَلْ በነጠላ “ጋራ” ማለት ነው፤ “ጂባል” جِبَالْ ደግሞ የጀበል ብዜት ሲሆን “ጋራዎች” ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ጋራዎች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም በነጠላ “ሂየ” هِيَ እንጂ በብዜት “ሁነ” هُنَ አይደለም። በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል ይህ በቂ ነው፤ እስቲ የተዛማች ሙግት እንመልከት፦
ነጥብ አራት
"የተዛማች ሙግት"
"የተዛማች ሙግት""textual approach" ማለት ቁርኣንን በቁርኣን መፈሰር ነው፤ ቁርኣን አንድ እሳቤ በአንድ ሱራህ ላይ ያንጠለጥል እና በሌላ ሱራህ የተቀሩትን እሳቤ ይጨርሰዋል፤ ይህ የቁርኣን አንዱ ውበት ነው፦
39፥23 *አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ*፡፡ اللَّهُ نَزَّلَ أَحْسَنَ الْحَدِيثِ كِتَابًا مُّتَشَابِهًا مَّثَانِيَ تَقْشَعِرُّ
“ሙተሻቢህ” مُتَشَٰبِه ማለትም “ተመሳሳይ” ማለት ሲሆን አንቀጾችን አንዱ ሱራህ ላይ ተናግሮ ሌላ ሱራህ ላይ ተመሳሳዩን የተቀረውን ይናገራል፤ ይህ አላህ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት የነበረውን ክስተትና መስተጋብር አንዱ ሱራህ ላይ ተናግሮ ያንጠለጥለው እና እንደገና በሌላ ሱራህ የተቀሩትን መሳ ለመሳ ይደግመዋል፤ ይህም “መሳኒይ” مَّثَانِى ማለት “ተደጋጋሚ” ማለት ነው። ይህንን በተለያዩ ሱራዎች የተለያዩ ናሙናዎችን ማየት እንችላለን፤ ኢብራሂም ለመላእክቶቹ ያላቸው ሙሉ ንግግሩ፦ “ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ፤ እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን” ሲሆን አላህ ግን ይህንን የኢብራሂም ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
51፥24 *የተከበሩት የኢብራሂም እንግዶች ወሬ መጥቶሃልን?* هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ الْمُكْرَمِينَ
51፥52 በእርሱ ላይ በገቡ እና ሰላም ባሉት ጊዜ አስታውስ፤ እርሱም፦ *«ሰላም ያልታወቃችሁ ሕዝቦች ናችሁ»* አላቸው፡፡ إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ قَوْمٌ مُّنكَرُونَ
15፥51 *ከኢብራሂም እንግዶችም ወሬ ንገራቸው*፡፡ وَنَبِّئْهُمْ عَن ضَيْفِ إِبْرَاهِيمَ
15፥52 በእርሱ ላይ በገቡ እና ሰላም ባሉት ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤ እርሱም፦ *«እኛ ከእናንተ ፈሪዎች ነን»* አላቸው፡፡ إِذْ دَخَلُوا عَلَيْهِ فَقَالُوا سَلَامًا قَالَ إِنَّا مِنكُمْ وَجِلُونَ
ሌላ ናሙና ሙሳ ለጌታው ያለው ሙሉ ንግግሩ፦ “ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ፣ ለእነርሱም በእኔ ላይ የደም ወንጀል አለ” ሲሆን አላህ ግን ይህንን የሙሳን ንግግር በአንድ ሱራህ ላይ አንጠልጥሎ የተቀረውን በሌላ ሱራህ ላይ ደግሞ ይጨርሰዋል፦
28፥33 ሙሳም አለ፦ *«ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ ነፍስን ገድያለሁ*፤ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ፡፡ قَالَ رَبِّ إِنِّي قَتَلْتُ مِنْهُمْ نَفْسًا فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُون
26፥14 ሙሳም አለ፦ *«ለእነርሱም በእኔ ላይ የደም ወንጀል አለ*፤ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ። وَلَهُمْ عَلَيَّ ذَنبٌ فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُونِ
ይህንን ሙግት ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ማስቀመጥ ይቻል ነበር፤ ነገር ግን ከላይ ያለው በቂ ነው፤ እስቲ የታሪክ ሙግት እንመልከት፦

ነጥብ አምስት
"የታሪክ ሙግት"
"የታሪክ ሙግት"historical approach" ማለት ቁርኣን የወረደበትን ዳራ መረዳት ነው፤ ይህ ሠበቡ አን-ኑዙል ይባላል፤ “ሠበብ” سَبَب ማለት “ምክንያት” ማለት ሲሆን የሰበብ ብዙ ቁጥር ደግሞ “አሥባብ” أسباب ነው፤ “ኑዙል” نُزُل ማለት “አወራረድ” ማለት ነው፥ ቁርኣን የወረደበት ምክንያት “ሠበቡ አን-ኑዙል” سَبَب النزول ወይም “አሥባቡ አን-ኑዙል” أسباب النزول ይባላል፤ ይህ የአወራረድ ምክንያት”circumstance of revelation” ነቢያችን”ﷺ” በተላኩበት ጊዜ ሰዎች በጥያቄ ሲመጡ አላህ “ይጠይቁሃል” “በላቸው” በማለት መልስ ይሰጣል፦
25፥33 *በጥያቄም አይመጡብህም እውነተኛውን መልስ፣ መልካምን ፍች የምናመጣልህ ብንኾን እንጅ*። وَلَا يَأْتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئْنَاكَ بِالْحَقِّ وَأَحْسَنَ تَفْسِيرًا
ለምሳሌ አንድ አንቀጽ መመልከት ይቻላል፤ መዲና ላይ የነበሩ አይሁዳውያን፦ "ማንም የሚስቱን ሃፍረት በጀርባ በኩል ተራክቦ ያደረገ ልጁ ጠንጋራ ይሆናል" የሚል የተንጋደደ መረዳት ሲይዙ አምላካችን አላህ፦ "ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው፡፡ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ" የሚለውን አንቀጽ አወረደ፦
2፥223 *"ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው፡፡ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ"*፡፡ ለራሳችሁም መልካም ሥራን አስቀድሙ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ *"እናንተም ተገናኝዎቹ መኾናችሁን ዕወቁ"*፡፡ ምእመናንንም በገነት አብስር፡፡ نِسَاؤُكُمْ حَرْثٌ لَّكُمْ فَأْتُوا حَرْثَكُمْ أَنَّىٰ شِئْتُمْ ۖ وَقَدِّمُوا لِأَنفُسِكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْلَمُوا أَنَّكُم مُّلَاقُوهُ ۗ وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3245
ከጃቢር ኢብኑ ሙንከዲር ሰምቶ እንደተረከው፦ *"አይሁዳውያን፦ "ማንም የሚስቱን ሃፍረት በጀርባ በኩል ተራክቦ ያደረገ ልጁ ጠንጋራ ይሆናል" አሉ፤ ከዚያም አላህ፦ "ሴቶቻችሁ ለእናንተ እርሻ ናቸው፡፡ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ" የሚለውን አንቀጽ አወረደ"*። عَنِ ابْنِ الْمُنْكَدِرِ، سَمِعَ جَابِرًا، يَقُولُ كَانَتِ الْيَهُودُ تَقُولُ مَنْ أَتَى امْرَأَتَهُ فِي قُبُلِهَا مِنْ دُبُرِهَا كَانَ الْوَلَدُ أَحْوَلَ فَنَزَلَتْ : (نِسَاؤُكُمْ حَرْثٌ لَكُمْ فَأْتُوا حَرْثَكُمْ أَنَّى شِئْتُمْ )
ይህ ሙግት የቁርኣን መቸት"Setting" ማለትም "መቼ? እና የት?" እንደወረደ የምናጠናበትም ጭምር ነው፤ ይህ የሰበቡ አን-ኑዙል አፈሳሰር ነቢያችን"ﷺ" እና ሶሓባዎች በአስተላለፉት መረዳት "አት-ተፍሢር ቢል መእሱር" التفسير بالمأثور ወይም "አት-ተፍሢር ቢ አር-ሪዋያህ" التفسير بالرواية ይባላል። በኢብኑ ጀሪር አጥ-ጠበሪ የተዘጋጀው ተፍሲሩል ጃሚል በያን እና በኢብኑ ከሲር የተዘጋጀው ተፍሲሩል ቁርኣን አል-ዚዙም በዚህ አፈሳሰር ተመራጭ ነው።
ሌላው ከላይ የዐውድ፣ የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ እና የተዛማች ሙግት አፈሳሰር "ተፍሢር ቢ አር-ረእይ" التفسير بالرأي ወይም "አት-ተፍሢር ቢ አድ-ዲራያህ" التفسير بالدراية ይባላል፤ ይህ በፊቅህ “ኢጅቲሀድ” اجتهاد ይወጅብበታል፤ የኢጅቲሀድ ምሁር ደግሞ “ሙጅተሂድ” مجتهد ይባላል። በአል-በይዷዊይ የተዘጋጀው አንዋረል ተንዚል እና በኢማም ፈኽሩል ዲኑል ራዚ የተዘጋጀው መፋቲሑል ገይብ በዚህ አፈሳሰር ተመራጭ ነው።
በተረፈ ከአህለል ኪታብ የሚገኝ ኢሥራዒልያት አፈሳሰር መረጃ መሆን ይችላል እንጂ ማስረጃ አይሆንም። አምላካችን አላህ ቁርኣንን ከሚያስተነትኑ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

የፍጥረት በኵር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
በ 325 ድህረ-ልደት በኒቂያ ጉባኤ በአትናቴዎስ እና በአርዮስ መካከል ውይይት ከተደረገ በኃላ የአርዮስ ተከታዮች ከዐበይት የሥላሴያውያን መሪዎች ግዝት እና ግዞት ደርሶባቸዋል፤ የአርዮስ እሳቤ ባዕዳና እንግዳ ኢያም ያረጀና ያፈጀ እሳቤ ሳይሆን ጳውሎሳዊ እሳቤ ነው፤ በግሪክ ኮይኔ "ፕሮቶኮስ" πρωτότοκος ማለት "በኵር" "ቀዳማይ" "መጀመሪያ" ማለት ነው፦
ቆላስይስ 1፥15 እርሱም የማይታይ አምላክ መልክ እና *"የፍጥረት ሁሉ በኵር ነው"*። who is the image of the invisible God, the firstborn of all creation; (English Revised Version)
ግሪክ፦ πρωτότοκος πάσης κτίσεως
"ፓሰስ" πάσης ማለት "ሁሉ" ማለት ነው፤ "የፍጥረት ሁሉ በኵር" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርት፤ "ክቲሶስ" κτίσεως ማለት "ፍጥረት" ማለት ነው። "ፍጡር" በነጠላ "ፍጥረት" በብዜት ነው፤ የፍጥረት ሁሉ በኵር ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው። ይህንን ናሙና ለመረዳት ተመሳሳይ ሰዋስው እንይ፦
ራእይ 1፥5 ከታመነውም ምስክር *"የሙታንም በኵር"* and from Jesus Christ, who is the faithful witness, the firstborn of the dead, (English Revised Version)
ግሪክ፦ πρωτότοκος τῶν νεκρῶν
"ኔክሮን" νεκρῶν ማለት "ሙታን" ማለት ነው። "ሙት" በነጠላ "ሙታን" በብዜት ነው፤ የሙታን በኵር ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የፍጥረት በኩር ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ካልሆነ ምን ማለት ነው? እንቀጥል፦
1 ቆሮንቶስ 15፥20 አሁን ግን *"ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል"*።
ግሪክ፦ Νυνὶ δὲ Χριστὸς ἐγήγερται ἐκ νεκρῶν, ἀπαρχὴ τῶν κεκοιμημένων.
"በኵር" የሚለው የግሪኩ ቃል "አፕ-አርኬ" ἀπαρχὴ ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ "አፓ" ἀπό ማለትም "ከ" እና "አርኬ" ἀρχή ማለትም "መጀመሪያ" ነው፤ ላንቀላፉት ሙታን "መጀመሪያ" ነው ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው፦
ራእይ 3፥14 አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ *"የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ"* የነበረው እንዲህ ይላል፦ the beginning of the creation of God. (English Revised Version)
ግሪኩ፦ ἡ ἀρχὴ τῆς κτίσεως τοῦ θεοῦ:
"የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ "መጀመሪያ" ለሚለው የገባው ቃል ልክ እንደ የሙታን መጀመሪያ "አርኬ" ἀρχή መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሌላው የእንስሳ በኵር ማለት ከእንስሳ የመጀመሪያው እንስሳ ማለት ነው፦
ዘሌዋውያን 27፥26 ለእግዚአብሔር ግን የሚቀርበውን *"የእንስሳ በኵር"* ማንም ይቀድሰው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው።
የእንስሳ በኵር ማለት ከእንስሳ የመጀመሪያው እንስሳ ማለት ከሆነ የፍጥረት በኵር ማለት ከፍጥረት የመጀመሪያው ፍጡር ማለት ነው፤ ፍጥረት የሚለው አዲስ ፍጥረትን ነው የሚያመለክተው ብንል ኢየሱስ የአዲስ ፍጥረት በኩር ነው፦
ሮሜ 8፥29 *ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ*፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *"አዲስ ፍጥረት ነው"*፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
"ሁሉም አዲስ ሆኗል" የሚለዉ ይሰመርበት፤ "ሁሉ" አንጻራዊ ከሆነ "የፍጥረት "ሁሉ" መጀመሪያ" ማለት የአዲስ ፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ ማለት ነው፤ ግን ፍጥረት የሚለው አጠቃላይ ፍጥረትን ያመለክታል ከተባለ የፍጥረት በኵር ማለት ከሁሉ አስቀድሞ የተፈጠረ ማለት ነው፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)
ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)
ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ
በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው።
በዚህም አለ በዚያ ኢየሱስ ፍጡር መሆኑ አርዮሳዊ ብቻ ሳይሆን ጳውሎሳዊ አልያም ባይብላዊ እሳቤ ነው። አምላካችን አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል፤ ከተፈጠሩት አንዱ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፦

አንድያ ልጅ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
"አንድያ ልጅ" የሚለው የግሪኩ ቃል "ሞኖ-ጌነስ" μονογενὴς ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ "ሞኖስ" μόνος ማለት "ብቸኛ" ማለት ሲሆን "ጌኑስ" γένος ማለት ደግሞ "የተወለደ" ማለት ነው፤ በጥቅሉ "ብቸኛ የተወለደ"the only begotten" ማለት ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 4፥9 እግዚአብሔር *"አንድ ልጁን"* μονογενῆ ወደ ዓለም ልኮታልና።
በግዕዝ "ወልድ ዋሕድ" ይሉታል። ይህንን ውልደት እግዚአብሔር በመዝሙር ኢየሱስን እኔ ዛሬ ወለድሁህ ብሎታል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ *"ዛሬ "ወለድሁህ"* γεγέννηκά ።
"ዛሬ" የሚለው የጊዜ ተውሳከ-ሥስ ጊዜን የሚያሳይ ነው፣ ኢየሱስ መወለዱ ጅማሬ ያለው መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፣ ይህ ጊዜ ከሞት ሲነሳ እንደሆነ ጳውሎስ ይናገራል፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥33 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ *"እኔ ዛሬ ወለድሁህ"* γεγέννηκά ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ *ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና*።
"እኔ ዛሬ ወለድሁህ" ተብሎ በሁለተኛው መዝሙር የተጻፈው ቃል ኢየሱስ ሲነሳ ተፈጽሞአል እያለን ነው፤ ስለዚህ "ዛሬ ወለድሁህ" የተባለን ቅድመ-ዓለም ከአብ ያለ እናት የሚለው ዶግማ ውኃ የሚያስበላና ድባቅ የሚያስገባ ነው። ኢየሱስ ከሙታን በኵር ተብሏል፤ "በኵር” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ፕሮቶ-ቶኮስ” πρωτότοκος ሲሆን የሁለት ቃላት ጥምረት ነው፤ አንዱ “ፕሮቶስ” πρῶτος ማለት “ፊተኛ” ሲሆን ሁለተኛው “ቶኮስ” τοκος ማለትም “መወለድ” ነው፤ በጥቅሉ "መጀመሪያ የተወለደ" ማለት ነው። ኢየሱስ በብዙ ወንድሞች መካከል ፊተኛ በመሆን ከሙታን በአብ እንደተወለደ ይናገራል፦
ሮሜ 8፥29 *“ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል “በኵር” πρωτότοκον ይሆን ዘንድ*፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
"የበኵር ልጅ" ሁለተኛ ልጅ እስኪመጣ ድረስ ለወላጅ "አንድያ ልጅ" ነው፦
ዘካርያስ 12፥10 ሰውም *ለአንድያ ልጁ* እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም *ለበኵር ልጁ* እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።
"አንድያ ልጁ" እና "የበኵር ልጁ" ተለዋዋጭ ሆነው እንደገቡ ልብ በል፤ ታዲያ ቀጣይ ልክ እንደ ኢየሱስ ከአብ የሚወለዱ እነማን ናቸው? ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፦
1ኛ ዮሐንስ 5:1 ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር *ተወልዶአል* γεγέννηται ፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ *የተወለደውን* γεγεννημένον ደግሞ ይወዳል። የሐዋርያት ሥራ 17:28-29 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ። እኛ ደግሞ *ውልደቶቹ* γένος ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንቀሳቀሳለን እንኖርማለን። እንግዲህ የእግዚአብሔር *ውልደቶች* γένος ከሆንን፥
ዮሐንስ 1፥13 እነርሱም ከእግዚአብሔር *"ተወለዱ"* ἐγεννήθησαν እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ *"አልተወለዱም"*።
"ጌኑስ" γένος የሚለው ቃል ልክ ለኢየሱስ እንደተጠቀመበት እዚህ ላይም ተጠቅሟል፤ እንደ ጳውሎስ ትምህርት ኢየሱስ ከሞት ሲነሳ እንደተወለደ ሁሉ አማኞች በትንሳኤ ቀን ሲነሱ ሲጠባበቁት የነበረውን ልጅነት ዳግም ያገኛሉ፦
ሮሜ 8፥23 *"የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን"* ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።
ማቴዎስ 19፥28 *"በዳግመኛ ልደት"* የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥
ዳግም ልደት ማለት አዲስ ልደት ማለት ነው፤ ኢየሱስ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጅ የሚለው እሳቤ ፉርሽ ሆነ ማለት ነው፤ ምክንያቱም ከኢየሱስ በኃላ አማኞች ከእግዚአብሔር እንደሚወለዱ ሁሉ ከኢየሱስ ትንሳኤ በፊት መላእክእት፣ አዳም እና እስራኤል የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል፦
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።
ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *"እስራኤል የበኵር ልጄ ነው"*፤
እስራኤል የመጀመሪያ ልጄ ከሆነ ከእስኤል በፊት አዳም እና መላእክት እንዴት ልጆች ተባሉ? "በኵር” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ፕሮቶ-ቶኮስ” πρωτότοκος ሲሆን ከላይ ለእስራኤል ከዚያ ለኤፍሬም፣ ቀጥሎ ለዳዊት፣ ለጥቆ ለኢየሱስ አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ኤርምያስ 31፥9 እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ *"ኤፍሬምም በኵሬ ነውና"*።
መዝሙር 89፥27 *እኔም ደግሞ በኵሬ አደርሀዋለው* ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል።
ዕብራውያን 1፥6 *"እግዚአብሔር የበኵር ልጁን ልኮ ወደ ዓለም"* ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት፥ ይላል። (1980 አዲስ ትርጉም)

"መውለድ" በእማሬአዊ የአብራክ ክፋይ ማለት ሲሆን ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በፍካሬአዊ ግን "መፍጠርን" ያመለክታል። “ልደት” ማለት “ፍጥረት” ማለት ስለሆነ “አዲስ ፍጥረት” የሚለውን ተክቶ “አዲስ ልደት” ተብሏል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *”አዲስ ፍጥረት”* ነው።
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን *”ለአዲስ ልደት”* γένεσις በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥
መወለድ መፈጠር ባይሆን ኖሮ ሰማይንና ምድር ፍጥረት ሆኖ ሳለ “ልደት” ባልተባለ ነበር፤ ስለ ሰማይንና ምድር አፈጣጠር የሚናገረው መጽሐፍ “ዘፍጥረት” ይባላል፤ “ፍጥረት” በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ “ዘ’ አያያዥ መስተዋድድ “የ” ማለት ነው፤ “የፍጥረት” ማለት ነው፤ በግዕዙ አርስት ላይ “ዘልደት” ይባላል፦
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ *”የሰማይና የምድር ልደት”* ይህ ነው።
ግዕዙ፦
ዝንቱ *”ፍጥረተ ሰማይ ወምድር”* ዘምአመ ኮነት ዕለት አንተ ባቲ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ።
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς, ὅτε ἐγένετο· ᾗ ἡμέρᾳ ἐποίησε Κύριος ὁ Θεὸς τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν
“ጀነሲዋስ” γενέσεως ማለት “ልደት” ማለት ነው፤ “Genesis” የሚለው የኢንግሊዝኛው ስያሜ “ጀነሲስ” γένεσις ከሚለው ከግሪኩ ቃል የመጣ ነው፤ መቼም ሰማይና ምድር ልደት አለው ሲባል ፈጣሪ በእማሬአዊ ወለደው ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ መፍጠሩን የሚያሳይ ስለሆነ ግዕዙ፦ “ፍጥረተ ሰማይ ወምድር” ማለትም “የሰማይና የምድር ፍጥረት” ይለዋል። “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV
“ይሽሩ” የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን “ወለደ” ወይስ “ፈጠረ”? ተራራ እንደተወለደ ይናገራል፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
አሞፅ 4፥13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥
መዝሙር 90፥2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”*፥
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
psalms 90፥2 πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι καὶ πλασθῆναι τὴν γῆν καὶ τὴν οἰκουμένην,
ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ “ጌኒቲና” γενηθηναι ማለትም “ሳይወለዱ” የሚለው በተመሳሳይ “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግሥ የመጣ ነው። ፈጣሪ ኢየሱስን፣ አማኞችን፣ እስራኤላውያንን፣ ተራራን፣ ሰማይና ምድር ሳይቀር ወለደ ማለት ፈጠረ ማለት ካልሆነ ምን ማለት ነው? ሃይማኖተ-አበው ላይ የቂሳሪያው ባስልዮስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው ብሎ እንቅጩን ፍርጥ አድርጎ ነግሮናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦
*”ወለደኒ ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ ፈጠረኒ በእንተ ትስብእቱ”*
ትርጉም፦
*”ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለትም ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል”*
ልጅ ማለት፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል" ማለትም "ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ" ወይም "አምላክ ዘእም-አምላክ" ማለትም "ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦

ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Photo
♨️♨️♨️ የምስራች ♨️♨️♨️
ይህ የኡስታዝ ወሒድ መጽሐፍ የሚሽነሪዎችን ጽርፈት በጥሩ ሁኔታ የሚፈትሽ እና መልስ የሚሰጥ ነው። ሙግቱ የስማ በለው ሳይሆን የቁርኣንን ታሪካዊ ዳራ በመረጃና በማስረጃ በመጥቀስ ተገቢ መልስ ሰቶበታል። ሚሽነሪዎች ዐላዋቂዎችን በመዋዕለ ንዋይ እየበዘበዙ ቢሆንም ይህ መጽሐፍ ግን ዝምታ ፍርሓት የመሰለበትን ሁኔታ የሚያንኮታኩት ሆኖ አግኝተነዋል።
በገበያ ላይ ውሏል፤ እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ ይግዙት በአዲስ አበባ በየትኛውም የመጽሐፍት መደብር በተለይ በነጃሺ የመጽሐፍት መደብር እና በአት-ተውባህ የመጽሐፍት መደብር ላይ ያገኙታል።

በርዘኽ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
23፥100 *ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አለ*፡፡ ۖ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ
ሞት በመጣ ጊዜ “ሙንከር” مُنْكَر እና “ነኪር” نَّكِير የተባሉት ሁለት መላእክት ለሟቹ በሩሑ፦ “ጌታህ ማን ነው? ዲንህ ምንድን ነው? ነቢይህ ማን ነው?” ብለው በቀብር ውስጥ ይጠይቃሉ፤ አማኝም ከሆነ፦ “ጌታዬ አላህ ነው፣ ዲኔ ኢስላም ነው፣ ነብዬም የአላህ መልእክተኛ ነው” ብሎ ይመልሳል፤ ለእርሱ ጀነት እዲገባ ይከፈትለታል። ከሃዲ ከሆነ፦ “ዐላውቅም፣ ዐላውቅም፣ ዐላውቅም” ብሎ ይመልሳል፤ ለእርሱ እሳት እዲገባ ይከፈትለታል። አቢ ዳውድ እና ተርሚዚ ዘግበውታል፤ ሐዲሱ እረጅም ስለሆነ ገብተው ያንብቡ፦
ሱነን አቢ ዳውድ: መጽሐፍ 42, ሐዲስ 158
ጃምዒ አት-ተርሚዚ: መጽሐፍ 10, ሐዲስ 107
“በርዘኽ” برزخ ማለት የቃሉ ትርጉም “ጋራጅ” ወይም “ግርዶ” ማለት ነው፤ ጥቁር ባሕር፣ አትላንቲ ውቂያኖስ፣ ባልቲክ ባሕር፣ ፓስፊክ ውቂያኖስ፣ ሜድትራኒያን ባሕር፣ ኢንዲያን ውቂያኖስ፣ ቀይ ባሕር በውስጣቸው መራራ ውኃ እና ጣፋጭ ውኃ ይዘዋል፤ እነዚህ ሁለቱ ባሕሮች እንዳይገናኙ በመካከላቸው “በርዘኽ” አለ፦
55፥19 *ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው*፡፡ مَرَجَ الْبَحْرَيْنِ يَلْتَقِيَانِ
55፥20 *እንዳይገናኙ በመካከላቸው “ጋራጅ” አለ፡፡ አንዱ ባንዱ ላይ ወሰን አያልፉም*፡፡ بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌ لَّا يَبْغِيَانِ
25፥53 *እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች፣ አጐራብቶ የለቀቀ ነው፤ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፤ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፤ በመካከላቸውም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን “ግርዶ” ያደረገ ነው*። وَهُوَ ٱلَّذِى مَرَجَ ٱلْبَحْرَيْنِ هَٰذَا عَذْبٌۭ فُرَاتٌۭ وَهَٰذَا مِلْحٌ أُجَاجٌۭ وَجَعَلَ بَيْنَهُمَا بَرْزَخًۭا وَحِجْرًۭا مَّحْجُورًۭا
27፥61 *በሁለቱ ባሕሮችም በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል “ግርዶን” ያደረገ ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?* ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም። أَمَّن جَعَلَ ٱلْأَرْضَ قَرَارًۭا وَجَعَلَ خِلَٰلَهَآ أَنْهَٰرًۭا وَجَعَلَ لَهَا رَوَٰسِىَ وَجَعَلَ بَيْنَ ٱلْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
በተመሳሳይ ከሞት በኃላ የገነትም ሰዎች እና የእሳትን ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከላቸውም ግርዶሽ አለ፦
7፥46 *በመካከላቸውም “ግርዶሽ” አለ፤ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለእናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም የአዕራፍ ሰዎች የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም*፡፡ وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ ۚ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ ۚ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ ۚ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُون
“አዕራፍ” أَعْرَاف በጀነት ሰዎች እና በእሳት ሰዎች መካከል ያለ ስፍራ ሲሆን ሚዛናቸው እኩል የሆኑ ሰዎች ደግሞ የአዕራፍ ሰዎች ይባላሉ፤ የገነት ሰዎች የእሳት ሰዎችን እንዲሁ የእሳት ሰዎች የገነት ሰዎችን ያነጋግሯቸዋል፦
7፥44 *የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎች፦ «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፡፡ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን» ሲሉ ይጣራሉ፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል*፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ
7፥50 *የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎች፦ «በእኛ ላይ ከውሃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ጣሉልን» ብለው ጠሩዋቸዋል፡፡ እነርሱም «አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም አድርጓቸዋል» ይሏቸዋል*፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ النَّارِ أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَنْ أَفِيضُوا عَلَيْنَا مِنَ الْمَاءِ أَوْ مِمَّا رَزَقَكُمُ اللَّهُ ۚ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ حَرَّمَهُمَا عَلَى الْكَافِرِينَ
ምን ዋጋ አለው አይደለም ሰውን ይቅርና ጌታን ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ ብሎ ማናገር ለከሃድያን ከንቱ ቃል ናት፤ ነገር ግን ለአማንያን መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚወስዷቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» ይሏቸዋል፦
39፥58 *ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ ወደ ምድረ ዓለም አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝ እና ከበጎ አድራጊዎቹ በኾንኩ» ማለቷን ለመፍራት መልካሙን ተከተሉ*፡፡ أَوْ تَقُولَ حِينَ تَرَى الْعَذَابَ لَوْ أَنَّ لِي كَرَّةً فَأَكُونَ مِنَ الْمُحْسِنِينَ
23፥99 አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል፦ *«ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ
23፥100 *«በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» ይህን ከማለት ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት*፡፡ لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا
16፥32 እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚወስዷቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» ይባላሉ፡፡ الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ طَيِّبِينَ ۙ يَقُولُونَ سَلَامٌ عَلَيْكُمُ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُون
እንግዲህ በርዘኽ የሚባለው የገነት ሰዎች እና የእሳት ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከላቸውም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ መካከል ያለ ሁኔታ”Intermediate zone ነው፦

ይህ በርዘኽ ውስጥ የገነት ሰዎች ሩሕ በዒሊዪን ሲሆን “ዒሊዪን” عِلِّيِّين “ማለት “ከፍተኛ” ወይም “አርያም” ማለት ነው፤ “ዐሊየት” عَالِيَة ማለት ደግሞ “ከፍተኛይቱ” ማለት ነው፦
88፥10 *በከፍተኛ ገነት* ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

የእሳት ሰዎች ሩሕ ደግሞ በሢጂን ነው፤ “ሢጂን” سِجِّين የሚለው ቃል “ዩሥጀነ” يُسْجَنَ ማለትም “ታሰረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እስር” ወይም “እንጦሮጦስ” ማለት ነው፤ “ሠጅን” سِّجْن ማለት “መታሰር” ማለት ሲሆን “መሥጁኒን” مَسْجُونِين ደግሞ “እስረኞች” ማለት ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ
ሩሕ በትንሳኤ ቀን ከአካል ጋር ተዋሕዶ ፍርድ እስከሚሰጠው ድረስ በበርዘኽ ያለው ጊዚያዊ ቆይታ በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል። “ሩሕ” رُّوح ማለት “መንፈስ” ማለት ሲሆን ይህ የሰው መንፈስ ሥረ-መሰረቱ ከዐፈር ሳይሆን ከጌታችን ነገር ነው፤ ስለ “ሩሕ” የተሰጠን ዕውቀት ጥቂት ብቻ ነው፦
17፥85 *ስለ ሩሕም ይጠይቁሃል፤ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፤ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِ ۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّى وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًۭا
አላህ በዒሊዮን ውስጥ ከሚደሰቱ ባሮቹ ያድርገን፤ ከሢጂን ውስጥ ቅጣት ይጠብቀን! አሚን።

የተሳከረ ምልከታ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
10፥68 በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን? ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ
” አሏህ” በዕብራይስ “ላሜድን” ל ተሽዲድ ስናደርገው “አሏህ” אללה ሲሆን ይህንን ቃል በዕብራይስጥ የቁርአን ትርጉም ላይ እናገኘዋለን፤ ነገር ግን ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች ግልብ እና ድልብ ሃሳብ ይዘው ቃላትን በምላሶቻቸው ሲያጣምሙ ይታያሉ፤ “ኣላህ” אלה አንድ “ላሜድ” ל ብቻ ሲሆን ይላላል፤ ይህ ቃል 36 ጊዜ በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰ ሲሆን፦
1ኛ. “መሃላ” ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 24:41የዚያን ጊዜ “ከመሐላዬ” אָלָה ንጹሕ ነህ፤ ወደ ዘመዶቼ ሄደህ እነርሱ ባይሰጡህ ካማልሁህ መሐላ ንጹሕ ትሆናለህ።”
2. “እርግማን” ማለት ነው፦
ዘኍልቍ 5:23 ካህኑም እነዚህን “መርገሞች” אָלָה በሰሌዳ ይጽፈዋል፥ በመራራውም ውኃ ይደመስሰዋል፤”
“አሏህ” የሚለው ቃል ግን ይለያል። አሏህ በዕብራይስ አሁንም “ላሜድን” ל ተሽዲድ ስናደርገው “አሏህ” אללה ሲሆን በውስጡ ሁለት “ላሜድ” ל አለው። ነገር ግን አሏህ የሚለው አንድ “ላሜድ” ל በመቀነስና በማላላት አሏህ ማለት “እርግማን” አስተግፊሩላህ! ማለት ነው እያሉ ይሳለቃሉ፤ ሌላው “አክበር” أكبر ማለት “ታላቅ” ማለት ሲሆን “elative degree” ነው፤ ይህንን ቃል ወደ ዕብራይስጥ “ከ” የነበረውን ወደ “ኸ” ይቀይሩትና ያጣምማሉ፤ “አኽባር” עַכְבָּר ማለት “አይጥ” ማለት ነው፤ “አሏሁ አኽባር” ማለት “አሏህ አይጥ ነው” አስተግፊሩላህ! ብለው ንግግርን ከስፍራው ይቀይራሉ፤ ይህ ዛሬ ያሉት ከሃድያን ንግግሮችን ቢያጣምሙ አይደንቅም፤ ነብያችን”ﷺ” ነብይ ሆነው በተላኩበትም ጊዜ አይሁዳውን ቃላትን ያጣምሙ ነበር፤ “ራዒና” َرَٰعِنَا ማለት “ጠብቀን” ማለት ሲሆን በዕብራይስጥ ግን “ጅል” ማለት ነው፤ ለዛ ነው አላህ “አንዙርና” ٱنظُرْنَا ማለትም “ተመለከትን” በሉ ያለው፦
4፥46 ከነዚያ አይሁዳውያን ከኾኑት ሰዎች ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አልሉ፡፡ «ሰማንም አመጽንም የማትሰማም ስትኾን ስማ» ይላሉ፡፡ በምላሶቻቸውም ለማጣመምና ሃይማኖትንም ለመዝለፍ *”ራዒና”* ይላሉ፡፡ እነሱም «ሰማን ታዘዝንም ስማም ተመልከተንም» ባሉ ኖሮ ለነሱ መልካምና ትክክለኛ በኾነ ነበር፡፡ ግን በክህደታቸው አላህ ረገማቸው፡፡ ጥቂትንም እንጅ አያምኑም፡፡ مِّنَ ٱلَّذِينَ هَادُوا۟ يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِۦ وَيَقُولُونَ سَمِعْنَا وَعَصَيْنَا وَٱسْمَعْ غَيْرَ مُسْمَعٍۢ وَرَٰعِنَا لَيًّۢا بِأَلْسِنَتِهِمْ وَطَعْنًۭا فِى ٱلدِّينِ ۚ وَلَوْ أَنَّهُمْ قَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا وَٱسْمَعْ وَٱنظُرْنَا لَكَانَ خَيْرًۭا لَّهُمْ وَأَقْوَمَ وَلَٰكِن لَّعَنَهُمُ ٱللَّهُ بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًۭا
2፥104 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *”ራዒና”* አትበሉ፡፡ *”ተመለከትን”* በሉም፡፡ ስሙም፤ ለከሓዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَقُولُوا۟ رَٰعِنَا وَقُولُوا۟ ٱنظُرْنَا وَٱسْمَعُوا۟ ۗ وَلِلْكَٰفِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌۭ

አርካኑል ኢሥላም
ገቢር አንድ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
3፥19 አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት *“ኢሥላም”* ብቻ ነው፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ
“ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” “ተገዛ” ” አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው፤ አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፦
3፥19 *አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት “ኢሥላም” ብቻ ነው*፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ
"አርካን" أَرْكان ማለት "ምሰሶ" ማለት ነው፤ የኢሥላም ምሰሶ አምስት ናቸው፤ እነርሱም፦ ሸሃደተይን፣ ሶላት፣ ዘካህ፣ ሰውም እና ሐጅ ናቸው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 4
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ኢሥላም በአምስቱ መሠረቶች ላይ ተገንብቷል፤ እነርሱም፦ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው" በሚል ምስክርነት፣ ሶላትን በመቆም፣ ዘካህን በመስጠት፣ ረመዷንን በመፆም እና የአላህ በይት በመጎብኘት"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامُ الصَّلاَةِ وَإِيتَاءُ الزَّكَاةِ وَصَوْمُ رَمَضَانَ وَحَجُّ الْبَيْتِ
ነጥብ አንድ
"ሸሃደተይን"
“አሽ-ሸሃዳ” الشهادة የሚለው ቃል “ሸሂደ” شَهِدَ ማለትም “መሰከረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምስክርነት” ማለት ነው፤ ሻሂድ شَاهِد አሊያም “ሸሂድ” شَهِيد ደግሞ “ምስክር” ማለት ሲሆን የሻሂድ ብዙ ቁጥር “ሹሀዳ” شُهَدَاء ነው። አንድ ሰው ወደ ዲኑል ኢሥላም የሚገባበት “ከሊመተ-ሸሃዳ” كلمة الشهادة ማለትም “ቃለ-ምስክርነት” ይባላል፤ ይህም ቃለ-ምስክርነት “ላ ኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” لا إله إلا الله محمد رسول الله ትርጉሙ “ከአላህ በስተቀር አምላክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ነው” የሚል ነው፥ በእያንዳንዱ ዘመን የተለያዩ መልእክተኛ ስላሉ በዛ ዘመን ባለው መልእክተኛ ለምሳሌ በዒሣ ከሆነ "ዒሣ ረሱሉሏህ" ብለው ይቀበሉ ነበር። ለምሳሌ አላህ በዒሣ ዘመን "በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ" በማለት ወሕይ አውርዷል፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም *«በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ»* በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ «አመንን፤ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ
ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ሸሃደተይን ከጥንት ጀምሮ አለ፤ አላህም ሲልካቸው “ማ ለኩም ሚን ኢላሂ ገይሩሁ” مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ማለትም “ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም” ብለው እንዲናገሩ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ እነሆ *”ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም”* ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡ يُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ أَنْ أَنذِرُوٓا۟ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ
ነጥብ ሁለት
"ሶላት"
“ሶላት” صَلَوٰة ማለት “ፀሎት” ሲሆን በውስጡ ሦስት አበይት ክፍሎች ያቅፋል፤ እነርሱም፦
1. “ቂያም” قيام “መቆም”
2. “ሩኩዕ” رُكوع “ማጎንበስ”
3. “ሡጁድ” سُّجُود “ስግደት” ናቸው፤
ሶላት የሚፈፅሙ ሰዎች ደግሞ “ሙሰሊን” مُصَلِّين ይባላሉ፤ ሙሰሊን በቂያም “ሙቂሚ” مُّقِيم ” ሲባሉ፣ በሩኩዕ “ራኪዕ” رَاكِع ሲባሉ፣ በሱጁድ ደግሞ "ሣጂድ" سَاجِد ይባላሉ። ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናት፤ በኢማን እና በኩፍር መካከል ያለው ግድግዳ ሶላት ነው፦
4፥103 *"ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና"*፡፡ إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 13
ጃቢር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በኢማን እና በኩፍር መካከል ያለው ሶላት ነው"*። عَنْ جَابِرٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ " بَيْنَ الْكُفْرِ وَالإِيمَانِ تَرْكُ الصَّلاَةِ
ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ነቢያት በቀን አምስት ጊዜ ሶላት ላይቆሙ ይችላሉ፤ ወይ ያንሳል አሊያም ይበዛ ይሆናል፤ ነገር ግን ሶላትን መስገድ ወደ እነርሱ ተወርዷል፦
21፥73 *”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة
ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ሶላት ኢሥላም እስካለ ድረስ ከጥንት ጀምሮ አለ ማለት ነው። ኢንሻላህ የተቀሩትን አርካኑል ኢሥላም በክፍል ሁለት እንዳስሳለን........

3፥85 *”ከእሥልምና ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም”፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው*፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًۭا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
ነጥብ ሦስት
"ዘካህ"
“ዘካህ" زَكَوٰة ማለት "ምጽዋት" ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ከሰጠን ሲሳይ ላይ የምንለግሰው ልግስና ዘካህ ይባላል፦
8፥3 እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ *"ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው"*፡፡ الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُون
“ኢንፋቅ” إِنفَاق ማለት “ልግስና” ማለት ሲሆን “ሙንፊቂን” مُنفِقِين ደግሞ “ለጋሾች” ማለት ነው፤ ልግስና የበረከት ምንጭና ለአላህ ውዴታ ያለን መገለጫ ነው፤ ዘካህ ከትርፍ ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው። ዘካህ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ነቢያት ጊዜ ከመቶ 2.5 % ላይሰጥ ይችላል፤ ወይ ያንሳል አሊያም ይበዛ ይሆናል፤ ምናልባት ከመቶ 10 % አሥራት ሊሆን ይችል ይሆናል፥ አላህ ነው ሁሉን ዐዋቂ። ነገር ግን አላህ ዘካንም ስለ መስጠት ትእዛዝ ወደ ነቢያት አውርዷል፦

ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ዘካህ ኢሥላም እስካለ ድረስ ከጥንት ጀምሮ አለ ማለት ነው።
ነጥብ አራት
"ሰውም"
“ሰውም” صَوْم ማለት "ጾም" ማለት ነው፤ አንድ ሰው ምንም ነገር ሳይቀምስ ሲቀር "ጾሙን ዋለ" ይባላል፤ ያ ማለት ከምግብና ከመጠጥ “ተከለከለ” አሊያም “ተቆጠበ” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ጾምን ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ላይ እንደ እንደደነገገ በእኛም ላይ ደነገገ፦
2፥183 *“እናንተ ያመናችሁ ሆይ “ጾም” በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፤ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
በዚህ አንቀጽ ላይ “ኩቲበ” كُتِبَ ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ከተበ” كَتَبَ ከሚለው የመጣ ሲሆን “ተገለጸ" "ተደነገገ" "ተደነባ"prescribed” ማለት ነው፤ ጾም የምጾምበት ምክንያት ደግሞ “ተቅዋ” تَقْوَى ማለትም “አላህ መፍራት” ለማግኘት ነው፤ "ተተቁን" تَتَّقُون ማለት "አላህን ልትፈሩ" ማለት ነው፤ “ይከጀላልና” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ለዐለኩም” لَعَلَّكُمْ ነው፤ "ለዐለኩም" በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የመጣው “ለዐል” لَعَلَّ ነው፤ "ለዐል" ማለት "ምክንያት" “ዘንድ”so that” ማለት ሲሆን ምክንያታዊ መስተዋድድ ነው፤ "ጾም አላህን ልትፈሩ ዘንድ በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተነደገገ በእናንተም ላይ ተደነገገ" ማለት ነው። “ረመዷን” رمضان ማለት “ድርቀት” “ሞቃታማ” ማለት ሲሆን የጾም ስም ሳይሆን የወር ስም ነው፤ የዘጠነኛው ወር ስም ነው፤ ይህ ወር ቁርኣን የወረደበትና መውረድ የጀመረበት ወር ነው። ጾም ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ነቢያት ጊዜ በዚህ ወር ላይጾሙት ይችላል። ነገር ግን አላህ ጾምን ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ላይ እንደደነገገ ከላይ ያለው አንቀጽ ያስረዳል። ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ሰውም ኢሥላም እስካለ ድረስ ከጥንት ጀምሮ አለ ማለት ነው።