ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሶስት
“የተወለደበት ቀን”
ኢየሱስ ተወለደ የሚባለው በሃገራችን ታህሳስ 29 ሲሆን በግሪጎሪያን አቆጣጠር ደግሞ ታህሳስ 25 ነው፣ ነገር ግን ይህ ልደት ሚጥራ የሚባል የኢራናውያን ጣኦት የተወለደበት ቀን ነው፣ ኢትዮጵያን ሆነ ግሪጎርያን ኢየሱስ የተወለደበት ቀን ቢብሊካል መሰረት የለውም፣ ባይሆን የኢትዮጵያን የሚገርመኝ ገና በ 4 አራት አመት አንዴ ታህሳስ 29 የነበረው ታህሳስ 28 ይሆናል፣ ምክንያቱ ሲባሉ በ 4 አራት አመት አንዴ ጳጉሜ 5 የነበረው 6 ስለሚሆን ነው ይላሉ፣ ስነ-አመክንዮው ያስኬዳል ታዲያ ጥምቀት በአሉ በ 11 የነበረው ለምን በ 10 አልሆነም ከተራ በ 10 የነበረው ለምን በ 9 አልሆነም? ለዚህ መልስ እንፈልጋለን። መደምደሚያችን ምንድን ነው ኢየሱስ የተወለደበት አመት፣ ወር፣ ቀን ቢብሊካል መሰረት ሆነ መረጃ የሌለው ብቻ ሳይሆን ከታሪክ ጋር እጅጉን ይጣረሳል፣ ከዛም ባሻገር ጣኦት የተወለደበትን ቀን እንጂ ኢየሱስ የተወለደበትን ቀን እያከበራችሁ አይደለምና ሞት ሳይቀድማችሁ ያላችሁበትን መንገድ መርምራችሁ ወደ ኢስላም ኑ፦
5:77 *እላንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ”*! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የሆነን ማለፍ ወሰንን አትለፉ፤ በፊትም በእርግጥ *”የተሳሳቱትን እና ብዙዎችን ያሳሳቱትን ከቀጥተኛው መንገድም የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ”*፣ በላቸው قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ غَيْرَ ٱلْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوٓا۟ أَهْوَآءَ قَوْمٍۢ قَدْ ضَلُّوا۟ مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا۟ كَثِيرًۭا وَضَلُّوا۟ عَن سَوَآءِ ٱلسَّبِيلِ ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢየሱስ የት ተወለደ?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11:120 ከመልክተኞቹም “ወሬዎች” ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ኃያሲ የሆኑ ምሁራን ኂስ መኃየስ ልምዳቸው ነው፤ እኛም ማንኛውም ተግዳሮት በቁርአን ላይ የሚነሳ ኂስ እንማርበታለን እንጂ አናፍርበትም፤ ታዲያ ጠይቆ መረዳት እና ማፍረስ መገርሰስ አስቦ መጠየቅ ይለያያል፤ ከኃያሲያን በተቃራኒው ሚሽነሪዎች የቁርአንን ምጥቀትና ጥልቀት ከመረዳት ይልቅ በምን ጥላሸት እናጠልሸው ብለው ተነስተዋል፤ እኛም ለዚህ መደዴ አካሄድ በቂ መልስ አለን የሚል መጀገኛ ይዘናል።

ወደ ጥላሸቱ ስገባ፦ “የቁርአን ዒሳ እና የባይብሉ ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ማንነቶች ናቸው፤ ከስማቸው ጀምሮ የት እንደተወለዱ ባይብል ሆነ ቁርአን ለየቅል የትየለሌ አድርገው ነው ያስቀመጡት” የሚል እሳቤ አላቸው፤ እኛ ደግሞ የምንለው ከመነሻው ሚዛኑ ትክክል አይደለም የሚል ሙግት አለን፤ ምክንያቱም የቁርአን ተናጋሪ እና ተራኪ የዓለማቱ ጌታ አላህ ነው፤ ከነብያችን”ﷺ” በፊት ያለው የዒሳ ታሪክ “አል-ገይቡል ማዲ” الغيبه المادي ሲሆን ያለፈ ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ ከዚህ በፊት አላፊ የሆነ ነገር ነው፤ ከፍጡራን በፊት ያሉትን የሩቅ ወሬዎች አላህ ብቻ ነው በትክክል የሚያውቃቸው፤ አላህ ይህንን የሩቅ ወሬ “ነቁስሱ አለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ “እንተርክልሃለን” በማለት ለነብያችን”ﷺ” ይናገራል፦
11:120 ከመልክተኞቹም “ወሬዎች” ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

አላህ ለነብያችን”ﷺ” የሚተርክበት ምክንያት ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው እንጂ እከሌ እከሌን ወለደ ብሎ የሚናገር የቀበሌ አሊያም የእድር መዝገብ አይደለም፤ የባይብል ታሪክ ግን የታሪክ ሰዎች ቃላቸው ከልብ የፈለቀ ነው፦
ኢዮብ 8፥8-10 ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነውና፤ እኛ የትናንት ብቻ ነን፤ ምንም አናውቅም፤ ስለዚህ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፥ አባቶቻቸውም ለመረመሩት ነገር ትጋ፤ እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥ *ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?* እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥

“ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?” የሚለው ይሰመርበት፤ የባይብል ታሪክ ታራኪው አምላክ ሳይሆን ታሪካዊያን የቀደመውን ትውልድ ጠይቀው የዘገቡት ነው፤ የቀደመው ትውልድ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ ደግሞ ቃልንም ከልባቸው አውጥተው እንጂ ከአምላክ ሰምተው አይደለም፤ ሉቃስም ለቴዎፍሎስ የጻፈለት ትረካ ከአምላክ የሰማው ሳይሆን ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እርሱ ደግሞ ለቴዎፍሎስ ሊጽፍለት መልካም ሆኖ ስለታየው የቀደመው ትውልድ ያስተላለፉለትን ነው፦
ሉቃስ 1፥1-4፤ *የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ*።

ስለዚህ የአምላክ ንግግር ከታሪካውያን ትውፊት ቅሪት ጋር ማወዳደር ከመነሻው ስህተት ነው፤ ሲቀጥል ባይብል ላይ እና ቁርኣን ላይ ስለ ኢየሱስ የተገለጸው መረጃ ተለያየ ማለት ኢየሱስ ሁለት ኢየሱስ አያረገውም። እስቲ ይህንን ገለባ ክስ ነጥብ በነጥብ ድባቅ እናስገባው፦
ነጥብ አንድ
“የኢየሱስ ስም”
“ኢየሱስ” የሚለው ስም ፦ በግሪክ “ኤሱስ” Ἰησοῦ በቀዳማይ ዕብራይስጥ “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁעַ ፣ በደሃራይ ዕብራይስጥ “ያሱአ” יֵשׁוּעַ ፣ በአረማይክ “ዔሳዩ” ܝܫܘܥ ፣ በቀዳማይ ዐረቢኛ “ዒሳ” عيسى ፣ በደሃራይ ዐረቢኛ “የሱዐ” يسوع ሲሆን ትርጉሙ “ያህ መድሃኒት ነው” የሚል ፍቺ አለው፤ በተለይ ኢየሱስ ሰዎች ሲጠሩበት የነበረ የሰው ስም መሆኑን ለማሳየት በዕብራይስጥ “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁ֣עַ በግሪክ “ኤሱስ” Ἰησοῦ ተብሎ ለሌሎች ሰዎች አገልግልግሎት ላይ ውሏል፤ ይህንን ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ ኪዳን ማየት ይቻላል።
የግሪክ ሰፕቱጀንት ብሉይ ኪዳን ኢየሱስ የሚለውን ስም “ኤሱስ” Ἰησοῦ ብሎ አቀምጦታል፤ የዕብራይስጡ እደ-ክታባት ደግሞ ያህሹአ יְהוֹשֻׁ֣עַ በሚል አስቀምጦታል፤ የግዕዙ ባይብልም በተመሳሳይ “ኢያሱ” ሳይሆን “ኢየሱስ” እያለ አስቀምጦታል፤ ኢየሱስ የሚለው ስም የፍጡራን ስም መሆኑን የነዌ ልጅ ኢየሱስ፣ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢየሱስ እና የግሪክ አዲስ ኪዳን እደ-ክታባት ኢየሱስ የሚለውን ስም “ኤሱስ” Ἰησοῦ ብሎ አቀምጦታል፤ ይህም የማርያም ልጅ ኢየሱስ፣ የነዌ ልጅ ኢየሱስ፣ ኢዮስጦስ ኢየሱስ ወዘተ።

ስለዚህ የኢየሱስ ስም ስረ-መሰረቱ “ያህሹአ” እንጂ “ኢየሱስ” አሊያም “ዒሳ” አይደለም፤ ለምሳሌ በዕብራይስጥ “ሺን” ש‎ በግሪክ ስለሌለ “ሲግማ” σ ሆኖ “ሸ” የነበረው “ሰ” ተብሎ ሲነበብ በዕብራይስጥ “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁעַ የነበረው በግሪክ ኮይኔ “ኤሱስ” Ἰησοῦ ይሆናል፤ አንድ ስም ወደ ሌላ ቋንቋ ሲመጣ የአነባነብ ስልቱ ተቀየረ ማለት ስሙ ተቀየረ ማለት እንዳልሆነ ከቋንቋ ሙግት መረዳት ይቻላል፤ ቀዳማይ ዐረቢኛ የቁርአን ዐረቢኛ ሲሆን ደኃራይ ዐረቢኛ ደግሞ ባይብል የተጻፈበት ዐረቢኛ ነው፤ ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን ሆነ አዲስ ኪዳን ወደ ዐረቢኛ የተተረጎመው ከቁርኣን መውረድ በኃላ በ 867 AD ኮዴክስ ዐረቢከስ ነው። ስለዚህ በቁርአን በቀዳማይ ዐረቢኛ “ዒሳ” عيسى በባይብል በደሃራይ ዐረቢኛ “የሱዐ” يسوع መባሉ አንዳች የትርጉም ልዩነት የለውም። “የሱ” ישו የሚለው የዕብራይስጥ ቃል በዐይን ከመጣ “ዐ” ተብሎ አሊያም በያ ከመጣ “የ” ተብሎ ሊነበብ ይችላል፤ የዕብራይስጡ “ዐይን” ע‎ በዐረቢኛ “ዐ” ተብሎ አሊያም “የ” ተብሎ መነበብ ይችላል።
ነጥብ ሁለት
“የተወለደበት ቦታ”
ሉቃስ ኢየሱስ የተኛበትን ስፍራ በግርግም እንደሆነ ይናገራል፦
ሉቃስ 2፥7-8 የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው *በግርግም* አስተኛችው። በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ *በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ*።

“ግርግም” ማለት የከብት መኖ መመገቢያ አሸንዳ ነው። ይህ በበጋ ወቅት እረኞች በሜዳ መንጋዎችን ለመጠበቅ ውጪ ነበሩ። እዚህ አንቀጽ ላይ “በበረት ተወለደ” የሚል የት አለ? ሲቀጥል በግርግም አስተኛችው እንጂ ወለደችው መቼ ይላል? ኢየሱስ በክረምት አልተወለደም፤ ተወለደ ካሉ እረኞች እንዴት በክረምት ሜዳ ላይ አደሩ? በረት ደግሞ በክረምት መንጋዎች የሚያድሩበት ነው። ግርግም በበጋ መንጋዎች የሚመገቡበት መኖ መመገቢያ አሸንዳ ነው። ከመነሻው ቁርኣን ላይ መርየም ያማጠሽበት ቦታ እንጂ የወለደችበትን ቦታ አይናገርም፦
19፥23 ምጡም ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት፡፡ «ዋ ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ» አለች፡፡ فَأَجَآءَهَا ٱلْمَخَاضُ إِلَىٰ جِذْعِ ٱلنَّخْلَةِ قَالَتْ يَٰلَيْتَنِى مِتُّ قَبْلَ هَٰذَا وَكُنتُ نَسْيًۭا مَّنسِيًّۭا

ስለዚህ የሌለ ነገር እንዳለ አድርጎ እና አስመስሎ ማጋጨት የሥነ-አፈታት ጥናት”Hermeneutics” ያማከለ ሙግት አይደለም፤ የዘንባባ ግንድ አጠገብ ወለደችው እንበል፤ በረት ውስጥ አሊያም በሜዳ ላይ ባለው ግርግም የዘንባባ ግንድ ሊኖር አይችልምን? ዘንባባ ዐረብ አገር ብቻ ሳይሆን እስራኤልም አለ፦
ዘዳግም 34፥3 እስከ ዞዓር ድረስ ያለውንም *የዘንባባ ዛፎች* ያሉባትን ከተማ የኢያሪኮን ሸለቆ ሜዳ አሳየው።
1ኛ ነገሥት 6፥35 የኪሩቤልንና *የዘንባባ ዛፍ* የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸባቸው፤ በተቀረጸውም ሥራ ላይ በወርቅ ለበጣቸው።
ሕዝቅኤል 41፥26 በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ የዓይነ ርግብ መስኮቶችና የተቀረጹ *የዘንባባ ዛፎች* ነበሩበት፤ የመቅደሱም ጓዳዎችና የእንጨቱ መድረክ እንዲሁ ነበሩ።
ዮሐንስ 12፥13 *የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ* ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ ጮኹ።

“ሳያውቁ መናገር ኃላ ለማፈር” ይሉ የለ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
በዚያ በተወለደበት ቀን ሰላም በእርሱ እንደሆነ ሁሉ በሚሞትበት በዚህ ጊዜ ሰላም በእርሱ ላይ ይሆናል፤ ሕያው ኾኖ በሚቀሰቀስበትም በትንሳኤ ቀን ሰላም በእርሱ ላይ ይሆናል፤ በዚያ ቀን ከመምጣቱ በፊት በነበሩት ደረጃውን ዝቅ ባደረኩት አይሁዳውያን እና ደረጃውን ከፍ ባደጉት ክርስቲያኖች ላይ መስካሪ ይኾናል፦ 19፥33 «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ *በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም…
ዒሣ ሞቷልን?

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ *"ያለፉ"* የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَة

ዒሣ በእርግጥ የወረደለትን መልእክት አድርሷል፤ እርሱ ካለፉት መልእክተኞች አንዱ ነው፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ *"ያለፉ"* የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَة

"ያለፉ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ኸለት" خَلَتْ የብዙ ቁጥር ሲሆን ያለፉትን መልእክተኞች ያመለክታል እንጂ የሞቱትን የሚለውን አይዝም፦
3፥144 ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُل

"ያለፉ" የሚለውን ለዒሣ ሞት ይሰራል ካልን "ያለፉ" የሚለው በተመሳሳይ "ለነቢያችን"ﷺ" አገልግሎት ላይ ውሏል፤ ይህ አንቀጽ ሲወርድ ነቢያችን"ﷺ" መቼ ሞቱ? አይ ወደ ፊት ሟት መሆናቸውን ያሳያል ከተባለ ለዒሣም ወደፊት ሟች መሆኑን ያሳያል ብሎ መረዳት ከጉንጭ አልፋ ንትርክ ግልግል ነው። ሙግቱን አስፍተን "ያለፉ" የሆነ ማለት "የሞቱ ነው ካሉ ይህንን አንቀጽ እንዴት ይወጡታል? "አስጠንቃቂ "ያላለፈባት" የለችም" ስለሚል፦
35፥24 እኛ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእውነቱ መምሪያ ላክንህ፡፡ ማንኛይቱም ሕዝብ በውስጧ አስጠንቃቂ *"ያላለፈባት"* የለችም፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ بِالْحَقِّ بَشِيرًا وَنَذِيرًا ۚ وَإِن مِّنْ أُمَّةٍ إِلَّا خَلَا فِيهَا نَذِيرٌ

"ያላለፈባት" የሚለው ቃል ላይ "ኢላ ሐላ" إِلَّا خَلَا ሲሆን "ሐላ" خَلَا የሚለው ቃል "ኸለት" خَلَتْ ለሚለው ቃል ሥርወ-ቃል ነው። "ማንኛይቱም ሕዝብ በውስጧ አስጠንቃቂ *"ያልሞተባት"* የለችም" ትርጉም ይሰጣልን? በፍጹም አይሰጥም። ቅሉ ግን ዘመነ መግቦታቸው"dispensation" ያለቀ ማለት ነው። በተጨማሪም "ያለፉ" የሚለው በብዙ ቁጥር መልእክተኞችን ለማሳየት ስለገባ "ያለፉ የኾነ መልክተኛ" ማለት "ከመልክተኞቹ አንዱ፥ ከባለሟሎችም አንዱ" ነው ማለት ነው፦
3፥45 መላእክት ያሉትን አስታውስ፡- «መርየም ሆይ! አላህ ከርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ *"ከ"ባለሟሎችም በኾነ ያበስርሻል"*፡፡ إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ
36፥3 *"አንተ በእርግጥ "ከ"መልክተኞቹ ነህ"*፡፡ إِنَّكَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ

ከላይ በተዘረዘሩት አናቅጽ ላይ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ "ከአለፉት ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም" የሚል ፍቺ ይኖረዋል።

አሕመዲያህ ቃዲያኒህ ሌላው ዒሣ እንደሞተ ለማሳየት የሚጠቀሙበት አንቀጽ ይህ ነው፦
21፥34 *"ከአንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም"*፡፡ ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን? وَمَا جَعَلْنَا لِبَشَرٍ مِّن قَبْلِكَ الْخُلْدَ ۖ أَفَإِن مِّتَّ فَهُمُ الْخَالِدُونَ

ትክክል! አላህ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት ለነበሩት ለማንም ሰው "ዘላለማዊነትን" ቃል አልገባም፤ ሁሉ ነገር ከአላህ በቀር ሟችና ጠፊ ነው። የመርየምን ልጅ አልመሲሕን እናቱንም በምድር ያለንም ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማንም የለም። በምድር ላይ ያለው ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው፦
5፥17 እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ *የመርየምን ልጅ አልመሲሕን እናቱንም በምድር ያለንም ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማነው?* በላቸው፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ مِنَ اللَّهِ شَيْئًا إِنْ أَرَادَ أَن يُهْلِكَ الْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا
55፥26 *በእርሷ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው*፡፡ كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ
28፥88 *ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው*፡፡ وَلَا تَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ ۘ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَيْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُ ۚ لَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
25፥58 በዚያም *በማይሞተው ሕያው አምላክ* ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا
"የማይሞት" አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው። ዒሣም ቢሆን በክፍል አንድ እንዳየነው አልሞተም አልን እንጂ አይሞትም ዘላለማዊ ነው አላልንም፥ ይሞታል። ጅማሬ ያለው ቅዋሜ ማንነት ሞትም ቀማሽ ነው። አላህ ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረገም። "ከአንተ በፊት" ማለት ከአንተ በኃላም አንተም ሁላችሁም ሟች ናችሁ ማለት ነው፤ ሥረ-መሠረቱ ዐፈር የሆነ ፍጡር ወደ ዐፈር ይመለስና ከእርሷም በትንሳኤ ቀን ይቀሰቀሳል፦
3፥185 *ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት*፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ
39፥30 *"አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው"*፡፡ إِنَّكَ مَيِّتٌ وَإِنَّهُم مَّيِّتُونَ
20፥55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን*፡፡ مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ
71፥17 አላህም *ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ*፡፡ وَاللَّهُ أَنبَتَكُم مِّنَ الْأَرْضِ نَبَاتًا
71፥18 ከዚያም *በውስጧ ይመልሳችኋል። ማውጣትንም ያወጣችኋል*፡፡ ثُمَّ يُعِيدُكُمْ فِيهَا وَيُخْرِجُكُمْ إِخْرَاجًا

በዚህ የተፈጥሮ ሂደት ዒሣም መጥቶ ይሞታል በትንሳኤ ቀን ይቀሰቀሳል፦
19፥33 «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ *"በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን"*፡፡» وَالسَّلَامُ عَلَيَّ يَوْمَ وُلِدتُّ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሰላም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥86 *በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ “ሰላምታ” አክብሩ፤ ወይም እርሷኑ መልሷት*። وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا

በፊቅህ ነጥብ ውስጥ “ዓዳህ” የሚባል እሳቤ አለ፤ “ዓዳህ” عادَة ማለት “ወግ” “ባህል” “ልማድ”custom” ማለት ነው፤ ለምሳሌ በአገራችን “ጤና ይስጥልኝ” ወይም “ሰላም” እየተባባልን ሰላምታ እንለዋወጣለን፤ ይህ በኢሥላም ይፈቀዳል። ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒው በባይብል ከእምነት ለሚወጣ ሁሉ እና በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው “በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና” የሚል ትእዛዝ አለ፦
2 ዮሐንስ 1፥9-11 *”ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም*፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት። *ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና*።

ይህ የክርስትና ትእዛዝ ቢሆንም በክርስቲያኖች ላይተገበር ይችላል። እዚህ ድረስ ሰላም በክርስትና በግርድፉ ካየ ዘንዳ ሰላም በኢሥላም ያለው እሳቤ ማየት እንችላለን።
በቁርአን ከተገለጹት የአላህ ስሞች አንዱ “አሥ-ሠላም” السَّلَام ሲሆን ትርጉሙ የሰላም ባለቤት”the source of peace” ማለት ነው፤ ሰላም ከአላህ ዘንድ ነው፦
59፥23 እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ *የሰላም ባለቤቱ*፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኀያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 977
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በሚያሰላምቱ ጊዜ፦ *”አላህ ሆይ! አንተ የሰላም ባለቤት ነህ፤ ሰላም ከአንተ ዘንድ ነው፤ የግርማ እና የክብር ባለቤት ሆይ! ብሩክ ነህ” በማለት እንጂ አይቀመጡ ነበር*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ إِذَا سَلَّمَ لَمْ يَقْعُدْ إِلاَّ مِقْدَارَ مَا يَقُولُ ‏ “‏ اللَّهُمَّ أَنْتَ السَّلاَمُ وَمِنْكَ السَّلاَمُ تَبَارَكْتَ يَا ذَا الْجَلاَلِ وَالإِكْرَامِ

“ሠላም” سَلَٰم የሚለው ቃል “ሠለመ” سَلَّمَ ማለትም “ሰላምታ ሰጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ሰላም” ማለት ነው፤ “አሥ-ሠላም ዐለይኩም” የጀነት ሰላምታ ነው፦
13፥24 «ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ ይህ ምንዳ በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» ይሏቸዋል፡፡ سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ
“ሰላም ለእናንተ ይኹን” ለሚለው ቃል የገባው “ሠላም ዐለይኩም” سَلَامٌ عَلَيْكُم ነው። የአላህን ሰላም አንዱ አማኝ በሌላው አማኝ ላይ እንዲሆን መመኘት የሙስሊም ሰላምታ ነው፤ “ተሥሊም” تَسْلِيم ማለት “ሰላምታ” ማለት ነው፦
4፥61 *ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ፤ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ*፡፡ فَإِذَا دَخَلْتُم بُيُوتًا فَسَلِّمُوا عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ تَحِيَّةً مِّنْ عِندِ اللَّهِ مُبَارَكَةً طَيِّبَة

ሠሊሙ” سَلِّمُوا ማለት “ሰላም በሉ” ማለት ሲሆን ትእዛዛዊ ግስ ነው፤ ይህም ሰላምታ “አሠላሙ አለይኩም” السَّلَامُ عَلَيْكُم ነው፤ ትርጉሙ “የአላህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን” ማለት ነው።
አንድ ሙስሊም መጥቶ “አሠላሙ አለይኩም” ቢለን፥ እርሱ ካለን ይበልጥ ባማረ መልኩ “ወአለይኩም አሥ-ሠላም፣ ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ” السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ  ማለትም “የአላህ ሰላም፣ ምህረት፣ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን” ብለን እንመልሳለን፤ ወይንም እራሷኑ “ወአለይኩም አሥ-ሠላም” وَعَلَيْكُم السَّلَام ብለን እንመልሳለን፦
4፥86 *በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ “ሰላምታ” አክብሩ፤ ወይም እርሷኑ መልሷት*። وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا

“በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ አንድ ሙሥሊም ሙሥሊም ያልሆነን ሰው አሠላሙ አለይኩም አይልም፤ ምክንያቱም ይህ የሙስሊም ሰላምታ ነውና፤ ከዛ ይልቅ እንደ አገሩ ባህል “ጤና ይስጥልኝ” “ሰላም” “እንደምን ዋልክ” ወዘተ.. ማለት ይችላል፤ ነገር ግን ሙስሊም ያልሆነ ሰው አሠላሙ አለይኩም ካለን አላህ፦ “እርሷኑ መልሷት” ስላለ “ወአለይኩም” وَعَلَيْكُمْ ብለን እንመልሳለን፦
አል-አደበል ሙፍረድ መጽሐፍ 44, ሐዲስ 2
አቢ በስረል ጊፋሪይ እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ነገ ወደ አንድ አይሁድ እጓዛለው፤ በመጀመሪያ ሰላም(አሠላሙ አለይኩም) አትበሏቸው፤ አሠላም አለይኩም ቢሏችሁ ግን ወአለይኩም በሉ*። عَنْ أَبِي بَصْرَةَ الْغِفَارِيِّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ إِنِّي رَاكِبٌ غَدًا إِلَى يَهُودَ، فَلاَ تَبْدَأُوهُمْ بِالسَّلاَمِ، فَإِذَا سَلَّمُوا عَلَيْكُمْ فَقُولُوا‏:‏ وَعَلَيْكُمْ‏.‏
አል-አደበል ሙፍረድ መጽሐፍ 44, ሐዲስ 3
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”የመጽሐፉ ሰዎችን ቅድሚያ ሰላም(አሠላሙ አለይኩም) አትበሏቸው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ أَهْلُ الْكِتَابِ لاَ تَبْدَأُوهُمْ بِالسَّلاَمِ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 41
ዐነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም ከመጽሐፉ ሰዎች ሠላም(አሠላሙ አለይኩም) ብሎ ሰላምታ ከሳጣችሁ፥ “ወአለይኩም” በሉ*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِذَا سَلَّمَ عَلَيْكُمْ أَحَدٌ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ فَقُولُوا وَعَلَيْكُمْ‌‏.‏
የአላህ ሰላም የሚገኘው አላህን በኢኽላስ በመታዘዝ ብቻ ነው፤ “ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መታዘዝ” ማለት ነው። “ሠለም” سَلَم ማለት ደግሞ “ታዛዥነት” ማለት ነው።
“ሙሥሊም” مُسْلِم ማለት “ታዛዥ” ማለት ነው፤ አንድ ሙስሊም አላህን በፍጹም ሲታዘዝ የአላህ ሰላም ከእርሱ ጋር ይሆናል፤ ያኔ ውስጡ “ሠሊም” سَلِيم ማለትም “ንፁህ” ይሆናል፤ እርሱም “ሠሊሙን” سَٰلِمُون ማለትም “ሰላማዊ” ይሆናል፤:ፍርሃት እና ሃዘን ይወገዳል፦
2፥112 አይደለም እርሱ በጎ ሠሪ ኾኖ *ፊቱን ለአላህ የሰጠ* ሰው ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳ አለው፡፡ በእነሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡ بَلَىٰ مَنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَلَهُ أَجْرُهُ عِندَ رَبِّهِ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

“ፊት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ወጅህ” وَجْه ሲሆን “ሁለንተና” ማለት ነው፤ “የሰጠ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለመ” أَسْلَمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አምላካችን አላህ እርሱን በመታዘዝ የውስጥ ሰላም ከሚያገኙት ሰላማውያን ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አላህ ያተመው ልብና ጆሮ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥7 *አላህ በልቦቻቸው ላይ እና በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አለ፤ ለእነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው*፡፡ خَتَمَ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَعَلَىٰ سَمْعِهِمْ ۖ وَعَلَىٰ أَبْصَارِهِمْ غِشَاوَةٌ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

ክርስቲያን ፕሪንስ የሚባለው የኢሥላም ቀንደኛ ጠላት በፓልቶክ፦ "እኔን አላህ በልቤ ላይ እና በመስሚያዬ ላይ አትሞብኛል፤ ስለዚህ አላምንም" እያለ ዲስኩሩን ይዶሶክራል። የኢሥላም መልእክት ሰምተክ ሆን ብለክ ካስተባበልክ አዎ አላህ በልብህ ላይ እና በመስሚያህ ላይ ያትምብሃል። እውነትን ከመስማትህና ከማወቅህ በፊት በፍጹም በማንም ላይ አያትምም። ከእውነት በተዘነበልክ ጊዜ አላህ ልብህን አዘነበለብህ፤ አላህም እውነት ከመቀበል ይልቅ ያመጸን አመጸኛ አያቀናም፤ አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ኹኔታ በራሳቸው እስከሚለውጡ ድረስ ሂዳያን በመንሳት አይለውጥም፦
61፥5 *"ከእውነት በተዘነበሉም ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው፡፡ አላህም አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም"*፡፡ فَلَمَّا زَاغُوا أَزَاغَ اللَّهُ قُلُوبَهُمْ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ
13፥11 *አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ኹኔታ እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም*፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለውም፡፡ ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸውም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنفُسِهِمْ ۗ وَإِذَا أَرَادَ اللَّهُ بِقَوْمٍ سُوءًا فَلَا مَرَدَّ لَهُ ۚ وَمَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَالٍ

"እመኑ" ተብሎ ጥሪ ቀርቦላቸው፣ ስለ እምነት ተነግሯቸው፣ መልክተኛውም እውነት መኾኑን ተመስክሮላቸው፣ የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም፦
4፥170 እናንተ ሰዎች ሆይ! *መልክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ፡፡ "እመኑም" ለእናንተ የተሻለ ይኾናል፡፡ ብትክዱም አትጐዱትም*"፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الرَّسُولُ بِالْحَقِّ مِن رَّبِّكُمْ فَآمِنُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ وَإِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا
3፥86 *ከእምነታቸው እና መልክተኛውም እውነት መኾኑን ከመሰከሩ የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም*፡፡ كَيْفَ يَهْدِي اللَّهُ قَوْمًا كَفَرُوا بَعْدَ إِيمَانِهِمْ وَشَهِدُوا أَنَّ الرَّسُولَ حَقٌّ وَجَاءَهُمُ الْبَيِّنَاتُ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

እነዚህን ከካዱ በኃላ ብታስጠነቅቃቸውም ባታስጠነቅቃቸውም በእነርሱ ላይ እኩል ነው፤ አያምኑም፦
2፥6 እነዚያ *"የካዱትን" ሰዎች ብታስጠነቅቃቸውም ባታስጠነቅቃቸውም በእነርሱ ላይ እኩል ነው፤ አያምኑም*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا سَوَاءٌ عَلَيْهِمْ أَأَنذَرْتَهُمْ أَمْ لَمْ تُنذِرْهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ በብዜት "ከፈሩ" كَفَرُوا ማለት "ካዱ" ማለት ሲሆን በነጠላ “ከፈረ” كَفَرَ ማለት ደግሞ “ካደ” ማለት ነው፤ “ፋ” ف በሸዳ ተሽዲድ ስናረጋት ደግሞ “ከፈረ” كَفَّرَ ሲሆን “ሸፈነ” ማለት ነው፤ “ካፉር” كَافُور ማለት “የተሸፈነ” ማለት ነው፤ ለምሳሌ በጀነት ለበጎ አድራጊዎች መበረዣዋ “ካፉር” ተብላለች። “ካፊር” كَافِر ማለት “ከሃዲ” ማለት ሲሆን "ኩፍር" كُفْر ደግሞ "ክህደት" ማለት ነው፤ አንድ ሰው እውነቱ ተነግሮት ሆን ብሎ ሲያስተባብል ማስተበያው "ኩፍር" ይባላል፤ እርሱም "ካፊር" ይሰኛል፦
2፥7 *አላህ በልቦቻቸው ላይ እና በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አለ፤ ለእነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው*፡፡ خَتَمَ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَعَلَىٰ سَمْعِهِمْ ۖ وَعَلَىٰ أَبْصَارِهِمْ غِشَاوَةٌ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ ልብ፣ መስሚያ፣ ዓይን ውሳጣዊ ተፈጥሮን ያመለክታል፤ በካፊሮች "በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አለ" ይህም መሸፈኛ ኩፍር ነው፤ እነርሱም እውነቱ ተነግሯቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ከዚያም በልብ የካዱ በመኾናቸው አላህ በልቦቻቸው ላይ እና በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፦
63፥3 ይህ *እነርሱ በምላስ ያመኑ ከዚያም በልብ የካዱ በመኾናቸው* ነው፡፡ *በልቦቻቸውም ላይ ታተመባቸው*፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ ءَامَنُوا۟ ثُمَّ كَفَرُوا۟ فَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَفْقَهُونَ
47፥16 *እነዚህ እነዚያ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተመባቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ናቸው*፡፡ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَٱتَّبَعُوٓا۟ أَهْوَآءَهُمْ
ያተመባቸው ስለ ካዱ እንጂ እንዲክዱ አይደለም። በአላህ አንቀጾች ከተገሰጸና ከእርሷ ከዞረ እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር የረሳ ሰው ይበልጥ በዳይ ነው፤ እንዲህ የሚያደርጉትን አላህ በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሺፋኖችን፥ በጆሮዎቻቸውም ውስጥ ድንቁርናን አደረገባቸው፤ ከእነርሱ አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ልቡን ለኢሥላም ይከፍትለታል። ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት አንደሚታገል ያደርገዋል፦
18፥57 *በጌታውም አንቀጾች ከተገሰጸና ከእርሷ ከዞረ እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር ከረሳ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው እኛ በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሺፋኖችን በጆሮዎቻቸውም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን፡፡ ወደ መመራትም ብትጠራቸው ያን ጊዜ ፈጽሞ አይመሩም*፡፡ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِآيَاتِ رَبِّهِ فَأَعْرَضَ عَنْهَا وَنَسِيَ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ ۚ إِنَّا جَعَلْنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ أَكِنَّةً أَن يَفْقَهُوهُ وَفِي آذَانِهِمْ وَقْرًا ۖ وَإِن تَدْعُهُمْ إِلَى الْهُدَىٰ فَلَن يَهْتَدُوا إِذًا أَبَدًا
3፥125 *"አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ልቡን ለኢሥላም ይከፍትለታል፡፡ ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት አንደሚታገል ያደርገዋል"*፡፡ እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያምኑት ላይ ርክሰትን ያደርጋል፡፡ فَمَن يُرِدِ اللَّهُ أَن يَهْدِيَهُ يَشْرَحْ صَدْرَهُ لِلْإِسْلَامِ ۖ وَمَن يُرِدْ أَن يُضِلَّهُ يَجْعَلْ صَدْرَهُ ضَيِّقًا حَرَجًا كَأَنَّمَا يَصَّعَّدُ فِي السَّمَاءِ ۚ كَذَٰلِكَ يَجْعَلُ اللَّهُ الرِّجْسَ عَلَى الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ

እዚህ ድረስ ከተግባባን ባይብል ላይ ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ኃይሉ ይገልጥበት ዘንድ እና ስሙ በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ነው፦
ዘጸአት 9፥16 ነገር ግን *ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ*።
ሮሜ 9፥17 መጽሐፍ ፈርዖንን፦ *ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና*።

“ቃሻህ” קָשָׁה ማለት “ማደንደን” ማለት ሲሆን እግዚአብሔር ፈርዖን የእስራኤል ልጆችን እንዳይለቅ እና ሙሴን እንዳይሰማ የፈርዖንን ልብ አደንድኖታል፦
ዘጸአት 7፥3 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ אַקְשֶׁ֖ה * ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ።
ዘጸአት 14፥4 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ וְחִזַּקְתִּ֣י * ፥ እርሱም ያባርራቸዋል፤
ዘጸአት 9፥12 እግዚአብሔርም *የፈርዖንን ልብ አደነደነ וַיְחַזֵּ֤ק *፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም።
ዘጸአት 14፥8 እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ *የፈርዖንን ልብ አደነደነ* וַיְחַזֵּ֣ק ፥

እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ልብን ስላደነደነው የፈርዖን ልብ ደነደነ፦
ዘጸአት 7፥3 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ אַקְשֶׁ֖ה ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ*።
ዘጸአት 14፥4 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ וְחִזַּקְתִּ֣י ፥ እርሱም ያባርራቸዋል*፤
ዘጸአት 9፥12 እግዚአብሔርም *የፈርዖንን ልብ አደነደነ וַיְחַזֵּ֤ק ፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም*።
ዘጸአት 14፥8 እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ *የፈርዖንን ልብ አደነደነ* וַיְחַזֵּ֣ק ፥

እውን ፈርዖን ተጠያቂ ነውን? ልቡንስ እግዚአብሔር ካደነደነው ህዝቤን ልቀቅ ብሎ ሙሴና አሮንን መላክ ለምን አስፈለገ? ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ ብሎ ፈርዖንን መውቀስ ለምንስ አስፈለገ? በዚህ አላበቃም፤ እግዚአብሔር የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን መንፈሱን አደንድኖታል፤ ሰዎች እንዳያምኑ ማለትም በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም እግዚአብሔር ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ፦
ዘዳግም 2፥30 የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ *እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና*፥ ልቡንም አጽንቶታልና።
ዮሐንስ 12፥39 ኢሳይያስ ደግሞ፦ *"በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ፡ ብሎአልና ስለዚህ ማመን አቃታቸው"*።

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦
ሮሜ 11፥8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው* ተብሎ ተጽፎአል።
ኢሳይያስ 29፥10 *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል*።

እግዚአብሔር ሰዎችን የጠማምነትን መንፈስ በውስጣቸው በመደባለቅ ያጠማቸዋል፤ እርሱ ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው ይችላል?
ኢሳይያስ 19፥14 *እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል*፤
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ *ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው* ይችላል?

እግዚአብሔር ለጳውሎስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳይታበይ የሥጋው መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመው የሰይጣን መልእክተኛ ሰቶታል፦
2 ቆሮንቶስ 12፥7 ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ *የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ*፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።

ለነገሩ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር የሆነውን ክፉን መንፈስ ይልካል፤ ይህም ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር እተመካከረ ለእግዚአብሔር ያሳስትለታል፤ የሚሳሳተው ሰው እና የሚያሳስተው ክፉ መንፈስ ለእግዚአብሔር ናቸው፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
1ኛ ነገሥት 22 20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ *አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?* አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። *መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ *ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ *ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ*። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ *በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል*፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።
ኢዮብ 12፥16 ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ *የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው*።
እግዚአብሔር፦ "ነቢዩም ቢታለል ያንን ነቢይ ያታለልኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ይለናል፤ ሕዝቅኤልን፣ ኤርሚያስን እና ኢሳይያስን ያታለላቸው እርሱ እንደሆነ እራሳቸው ይናገራሉ፦
ሕዝቅኤል 14፥9 *ነቢዩም ቢታለል ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ ያታለልሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ*፥
ኤርሚያስ 20፥7 አቤቱ፥ *አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ*፥
ኢሳይያስ 63፥17 *አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን "አሳትኸን”?* እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።

ይህንን ጉድ ይዞ ከላይ የቁርኣንን አናቅጽ መተቸት ማለት የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ እንደማለት ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ረሕማህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ። እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

40፥7 እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ *«ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነት እና በዕውቀት ከበሃል*"፡፡ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፡፡» እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَيْءٍ رَّحْمَةً وَعِلْمًا فَاغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا وَاتَّبَعُوا سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ الْجَحِيم

“አር-ረሕማን” ٱلرَّحْمَٰنِ ማለትም “እጅግ በጣም ሩኅሩኅ” ማለት ሲሆን “አር-ረሒም” ٱلرَّحِيمِ ማለት ደግሞ “እጅግ በጣም አዛኝ” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ ነው። በቁርአን ውስጥ፦ “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ተሥሚያህ ወይም በሥመላህ 114 ጊዜ ሰፍሯል፤ በእያንዳንዱ ምዕራፍ መግቢያ 113 ጊዜ እና በሱረቱል ነምል መሃል ላይ ደግሞ 1 ጊዜ ይገኛል፦
27፥30 እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም *በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በኾነው*፡፡ إِنَّهُۥ مِن سُلَيْمَٰنَ وَإِنَّهُۥ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የአር-ረሕማን ባሕርይ ደግሞ "ረሕማህ" ነው፤ "ረሕማህ" رَّحْمَةً ማለት "እዝነት" ማለት ሲሆን ነገርን ሁሉ ያካበበት የአላህ ባሕርይ ነው፦
40፥7 እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ *«ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነት እና በዕውቀት ከበሃል*"፡፡ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፡፡» እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَيْءٍ رَّحْمَةً وَعِلْمًا فَاغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا وَاتَّبَعُوا سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ الْجَحِيم

እዚህ አንቀፅ ላይ የምንመለከተው "ረሕማህ" ማለትም "እዝነት" እና “ሸይእ” شَىْء ማለትም “ነገር’thing” ሁለት ጉዳዮች መናንቸውን ናቸው፤ “እዝነት” ምንም ነገር ሳይኖር የአላህ ባህርይ ሲሆን “ነገር” ደግሞ “ፍጡር” ነው፤ “ነገር” ጊዜና ቦታ ሁሉ ነው፤ አላህ ሁሉንም ነገር በባሕርያቱ ያካበበ ነው። ታዲያ አላህ የራሱን እዝነት እንዴት ፈጠረው? አላህ የራሱን ባሕርይ ይፈጥራልን? ይህ የሚሽነሪዎች ጥያቄ ነው። ሚሽነሪዎች ሆይ! ጮቤ ረግጣችሁ አንባጒሮ አትፍጠሩ። ተረጋጉ! የጅብ ችኩል አትሁኑ! በሰላና በሰከነ መንፈስ ሐዲሱን ቅድሚያ እንመልከት፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 50, ሐዲስ 21
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ መቶ የእዝነት ክፍሎችን ፈጠረ፤ ከእነርሱም አንዷን ለፍጥረቱ አሰራጨ፤ ከእርሷ የተቀሩትን እራሱ ጋር አደረገ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَلَقَ اللَّهُ مِائَةَ رَحْمَةٍ فَوَضَعَ وَاحِدَةً بَيْنَ خَلْقِهِ وَخَبَأَ عِنْدَهُ مِائَةً إِلاَّ وَاحِدَةً
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 50, ሐዲስ 23
ሠልማን አል-ፋርሢይ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ለአላህ መቶ የእዝነት ክፍሎችን አሉ፤ ከእነርሱም አንዷ በፍጥረቱ መካከል ያለው መተዛዘን ነው፤ የተቀሩትን ዘጠና ዘጠኝ ለትንሳኤ ቀን አዘጋጀ"*። عَنْ سَلْمَانَ الْفَارِسِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ لِلَّهِ مِائَةَ رَحْمَةٍ فَمِنْهَا رَحْمَةٌ بِهَا يَتَرَاحَمُ الْخَلْقُ بَيْنَهُمْ وَتِسْعَةٌ وَتِسْعُونَ لِيَوْمِ الْقِيَامَة

ምን ትፈልጋለህ? ይህ እዝነት ባሕርይ ሳይሆን አላህ ለፍጡራን የለገሳቸው ነገሮች ናቸው። ለምሳሌ ከመቶ አንዲቷ መካከል የሆኑት ነቢያት እራሳቸው እዝነት ናቸው፤ ለምሳሌ ነቢያችን"ﷺ" እና ዒሣ እዝነት ናቸው፦
21፥107 *"ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም"*፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا رَحْمَةً لِّلْعَالَمِينَ
19፥21 አላት «ነገሩ እንደዚህሽ ነው፡፡» ጌታሽ «እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፡፡ ለሰዎችም ታምር ከእኛም *"እዝነት"* ልናደርገው ይህንን ሠራን የተፈረደም ነገር ነው» አለ። قَالَ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٌ ۖ وَلِنَجْعَلَهُ آيَةً لِّلنَّاسِ وَرَحْمَةً مِّنَّا ۚ وَكَانَ أَمْرًا مَّقْضِيًّا

ነቢያችን"ﷺ" እና ዒሣ እዝነት ስለተባሉ ነገርን ሁሉ ያካበበው የአላህ ባሕርይ እዝነት ናቸውን? እረ በፍጹም! የአላህ ባሕርይ የሆነው እዝነት በተባለበት መልክና ልክ እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው። በባል እና በሚስት መካከል ያለው እዝነት፥ ልጆች ለወላጆች ያላቸው እዝነት ከአላህ ዘንድ የሆኑ እዝነቶች ናቸው፦
30፥21 ለእናንተም ከራሳችችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ *"በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው"*፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አሉ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُون
17፥24 *ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው*፡፡ «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ በርኅራኄ እንዳሳደጉኝ እዘንልላቸውም» በል፡፡ وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ وَقُل رَّبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا
18፥10 ጎበዞቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና «ጌታችን ሆይ! *"ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን"*፤ ለእኛም ከነገራችን ቅንን አዘጋጅልን» ባሉ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ أَوَى الْفِتْيَةُ إِلَى الْكَهْفِ فَقَالُوا رَبَّنَا آتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً وَهَيِّئْ لَنَا مِنْ أَمْرِنَا رَشَدًا
ይህ ከላይ የተዘረዘሩት እዝነት አላህ ለእኛ የፈጠረልን ከመቶ አንዲቷ ስትሆን የተቀረው ዘጠና ዘጠኙ በትንሳኤ ቀን በጀነት ውስጥ የሚኖሩት የማያቋርጥ መጠቀሚ ናቸው። ለአማንያን በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ በጀነት አላቸው፤ ይህ ታላቅ ፈድል ነው፦
9፥21 *ጌታቸው ከእርሱ በኾነው እዝነት እና ውዴታ በገነቶችም ለእነርሱ በውስጥዋ የማያቋርጥ መጠቀሚያ ያለባት ስትኾን ያበስራቸዋል"*፡፡ يُبَشِّرُهُمْ رَبُّهُم بِرَحْمَةٍ مِّنْهُ وَرِضْوَانٍ وَجَنَّاتٍ لَّهُمْ فِيهَا نَعِيمٌ مُّقِيمٌ
42፥22 በደለኞችን ከሠሩት ሥራ ዋጋ በትንሣኤ ቀን ፈሪዎች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ እርሱም በእነርሱ ላይ ወዳቂ ነው፡፡ *እነዚያም ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት በገነቶች ጨፌዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ የሚሹት ሁሉ አላቸው፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ ችሮታ ነው*"፡፡ تَرَى الظَّالِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا كَسَبُوا وَهُوَ وَاقِعٌ بِهِمْ ۗ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فِي رَوْضَاتِ الْجَنَّاتِ ۖ لَهُم مَّا يَشَاءُونَ عِندَ رَبِّهِمْ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَضْلُ الْكَبِيرُ

ተግባባን መሰለኝ? ስለዚህ አላህ ነገሮችን ያካበበት ባሕርይ እና ለፍጡራን የሚለግሰው ፈድል ሁለት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው። አትቀላቅሉ። እንዲገባችሁ አንድ ናሙና ላቅርብ፥ ለምሳሌ “ሙልክ” مُلْك የሚለው ቃል “መሊክ” مَلِك ማለትም “ንጉሥ” ከሚል የስም መደብ የመጣ ሲሆን “ንግሥና” ማለት ነው፤ ይህ የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ባሕርይ ሲሆን የአላህ ብቻ ገንዘብ ነው፦
3፥189 *የሰማያትና የምድር ንግሥና ለአላህ ብቻ ነው*፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
5፥120 *የሰማያትና የምድር በውስጣቸውም ያለው ሁሉ ንግሥና የአላህ ብቻ ነው*፡፡ እሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ لِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا فِيهِنَّ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ይህንን ንግሥና አላህ ለማንም አይሰጥም፥ ለማንም አያጋራም። በዚህ ንግሥናውም ለአላህ ተጋሪ የለውም፦
25፥2 *እርሱ ያ የሰማያትና የምድር ንግሥና የእርሱ ብቻ የኾነ፣ ልጅንም ያልያዘ፣ በንግሥናውም ተጋሪ የሌለው*፣ ነገሩንም ሁሉ የፈጠረና በትክክልም ያዘጋጀው ነው፡፡ الَّذِي لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُن لَّهُ شَرِيكٌ فِي الْمُلْكِ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ فَقَدَّرَهُ تَقْدِيرًا

ይህ የራሱ ባሕርይ የሆነው ንግሥና እና ለሰዎች የሚሰጠው ንግሥና ሁለት የተለያዩ ባሕርያት ናቸው፤ ለሰው የሚሰጠው ንግሥና የፍጡር ባሕርይ ያላቸው የፍጡራን ሥልጣን ነው፤ ይህንንም የሚሰጠው አላህ ነው፦
2፥251 በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፡፡ ዳውድም ጃሉትን ገደለ፡፡ *"ንግሥናን እና ጥበብንም አላህ ሰጠው"*፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ وَآتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ وَالْحِكْمَةَ
3፥26 በል፡- *«የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ*፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡» قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَاءُ ۖ بِيَدِكَ الْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير

አላህ ለሚሻው ሰው የሚሰጠው ንግሥና ተጋሪ ከሌለው ከራሱ ንግሥና ጋር እንደሚለያይ ሁሉ የራሱ ባሕርይ የሆነው እዝነት እና ለፍጡራን ካዘጋጀው እዝነት ይለያያል። ሌላ ናሙና እንመልከት፥ “አል-ሐከም” الحَكَم ከአላህ ስሞች አንዱ ሲሆን ትርጉሙ “ፈራጅ ወይም ዳኛ” ማለት ሲሆን “ሁክም” حُكْم ማለትም “ፍርድ” ደግሞ የእርሱ ባህርይ ነው፤ አምላካችን አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ በትክክል ፈራጅ ነው፤ በፍርዱ ቀን ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው፤ እርሱ የፍርዱ ቀን ባለቤት ነው፤ በዚያ ቀን በፍርዱ ማንንም አያጋራም፦
95፥8 *አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? ነው*፡፡ أَلَيْسَ اللَّهُ بِأَحْكَمِ الْحَاكِمِين
10፥109 ወደ አንተም የሚወረደውን ተከተል፡፡ *አላህም በእነርሱ ላይ እስከሚፈርድ ድረስ ታገስ፡፡ እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነው*፡፡ وَاتَّبِعْ مَا يُوحَىٰ إِلَيْكَ وَاصْبِرْ حَتَّىٰ يَحْكُمَ اللَّهُ ۚ وَهُوَ خَيْرُ الْحَاكِمِينَ
34፥26 «ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ *እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው» በላቸው*፡፡ قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ
1፥4 *የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው*፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
6፥62 *ከዚያም እውነተኛ ወደ ኾነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡ ንቁ! ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው*፡፡ እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው፡፡ ثُمَّ رُدُّوا إِلَى اللَّهِ مَوْلَاهُمُ الْحَقِّ ۚ أَلَا لَهُ الْحُكْمُ وَهُوَ أَسْرَعُ الْحَاسِبِينَ
18፥26 ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ *በፍርዱም አንድንም አያጋራም*፡፡ مَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِي حُكْمِهِ أَحَدًا

አምላካችን አላህ የፈራጆች ሁሉ ፈራጅ ሲሆን በዱኒያህ ግን ለሁሉም ነብያት ማለትም ለሉጥ፣ ለዩሱፍ፣ ለሙሳ፣ ለዳውድ፣ ለሱለይማን ወዘተ የሚፈርዱበት ፍርድ ሰቷቸዋል፦
21፥74 *ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا
12፥22 *ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ፍርድን እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንደዚሁም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
28፥14 ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ *ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንዲሁም መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ وَاسْتَوَىٰ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
21፥79 *ለሱለይማንም ትክክለኛይቱን ፍርድ አሳወቅነው፡፡ ለሁሉም ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠን*፡፡ فَفَهَّمْنَاهَا سُلَيْمَانَ ۚ وَكُلًّا آتَيْنَا حُكْمًا وَعِلْمًا
አይ አላህ የሚፈርድበት ፍርድ እና ፍጡራን የሚፈርዱበት ፍርድ ይለያያል ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም ሙግት በዚህ ስሌትና ቀመር መረዳት ይቻላል።

እዚህ ድረስ ከተግባባን ከዚህ የባሰ ነገር በባይብል እግዚአብሔር የራሱን ባሕርይ መፍጠሩ ነው፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)
ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)
ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

ይህንን አንቀጽ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የይሖዋ ምስክሮች ለኢየሱስ ነው ሲሉ ፕሮቴስታትን፣ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን እና የኦርቶዶክስ ተሃዶሶያውያን ስለ ጥበብ ነው ይላሉ። ጥሩ! ስለ ጥበብ ነው በሚል እንሟገት፤ እግዚአብሔር የራሱን ጥበብ ምንም ነገር ሳይፈጥር ፈጥሯል? በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ሔዋን “አገኘሁ” ብላ ለተጠቀመችበት የዋለው ቃል “ቃኒቲ” קָנִ֥יתִי ሲሆን ዳዊት ደግሞ ኲላሊቴን “ፈጥረሃል” ለሚለው የተጠቀመው “ቃኒታ” קָנִ֣יתָ ብሎ ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር *አገኘሁ* קָנִ֥יתִי አለች።
መዝሙር 139፥13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን *ፈጥረሃልና* קָנִ֣יתָ ፥
ዘዳግም 32፥6፤ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? *የፈጠረህ* קָּנֶ֔ךָ እና ያጸናህ እርሱ ነው።

የመጨረሻው ጥቅስ ላይ “የፈጠረክ” ለሚለው የገባው “ቃነካ” קָּנֶ֔ךָ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እግዚአብሔር ምድርንና ዓለምን የፈጠረው በጥበቡ ነው፦
ምሳሌ 3፥19 *"እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ"*፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና። በእውቀቱ” ቀላያት ተቀደዱ፥ ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።
ኤርምያስ 10፥12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ *"ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ"* ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።

ታዲያ የራሱ ባሕርይ የሆነውን ምድርንና ዓለምን የመሰረተበትን ጥበብ እንዴት ከሁሉ አስቀድሞ ፈጠረው? አይ ምን ችግር አለው ከተባለ "እግዚአብሔር ኢየሱስን ፈጥሮ በኢየሱስ ሌላውን ፍጥረት ፈጠረ" የሚሉትን የይሆዋ ምስክሮችንስ እንዴት መኮነን ይቻላል? አሳ ጎርጒሪ ዘንዶ ያውጣል ይባላል የለ? ሐዲስ ላይ ስለ እዝነት የሚናገረውን ቀላሉን አሳ ስትጎረጉሩ የሥነ-መለኮት አስተምሮታችሁን የሚያናጋ ዘንዶ የሆነ ጥያቄ ወጥቶባችኃልና ተጋፈጡት። የራሱ እያረረበት የሰውን የሚያማስል ተሟጋች ዕውር ድንብር የሆነ ጸለምተኛ ተሟጋች ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ፈላሕ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

40፥41 *«ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳት የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ?!* وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

በየመንገዱ፣ በየትምህርት ቤት፣ በሥራ ቦታ ከክርስቲያኖች ወገኖች በተለይ ከፕሮቴስታንት አንጃ፦ “ድነሃልን? የሚል ዋስትና የሌለው ጥያቄ ተደጋግሞ ሲመጣ ይጤናል፤ ታዲያ በኢሥላም ስለ መዳን ያለውን እሳቤ ምንድን ነው? የሚለውን ጉዳይ በአፅንዖትና በአንክሮት መዳሰስ ያስፈልጋል። በቅድሚያ ክርስትና መዳን የሚለው ሰው ባልነበረበት በአዳም ወንጀል የሚጠየቅበትና የሚቀጣበት ከዚያ በክርስቶስ ስቅላት የሚዳንበት ጉዳይ ሲሆን በኢሥላም ግን ሰው እራሱ በራሱ ለሚያደርገው ወንጀል የሚጠየቅበትና የሚቀጣበትን ከዚያም አላህ ባስቀመጠው መስፈርት የሚዳንበት ጉዳይ ነው።
በኢሥላም ነገረ-ደህንነት”Soteriology” እራሱን የቻለ ትልቅ ነጥብ ሲሆን “ፈላሕ” فلاح ይባላል። እኛ ሙሥሊሞች ሰውን የምንጠራው ወደ መዳን ሲሆን ካፊሮች የሚጠሩን ደግሞ ወደ እሳት ነው፦
40፥41 *«ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳት የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ?!* وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

አምላካችን አላህ፦ "ትድኑ ዘንድ ንስሃ ግቡ፣ ትድኑ ዘንድ በጎንም ነገር ሥሩ፣ ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ" እያለ ብዙ አናቅጽ ላይ ለመዳን የሚሆነውን እሳቤ ነግሮናል፤ ሰው የሚድነው ከጀሃነም ቅጣት ሲሆን ከዚህ አሳማሚ ቅጣት ምህረትን የሚያደርግ መሓሪው አዛኙ እርሱ አላህ ነው፦
15፥49 *ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መኾኔን ንገራቸው*፡፡ نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيمُ
15፥50 *"ቅጣቴም እርሱ አሳማሚ ቅጣት መኾኑን ንገራቸው"*፡፡ وَأَنَّ عَذَابِي هُوَ الْعَذَابُ الْأَلِيمُ
46፥31 ወገኖቻችን ሆይ! የአላህን ጠሪ ተቀበሉ፡፡ በእርሱም እመኑ፡፡ *"አላህ ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና፡፡ ከአሳማሚ ቅጣትም ያድናችኋልና"*፡፡ يَا قَوْمَنَا أَجِيبُوا دَاعِيَ اللَّهِ وَآمِنُوا بِهِ يَغْفِرْ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُجِرْكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ

"ንገራቸው" ለሚለው ቃል የመጣው "ነቢ" نَبِّئْ ሲሆን "ነቢይ” نَّبِىّ የሚለው ቃል ለረባበት ሥርወ-ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ለሚለው ትእዛዛዊ ግስ ነው። ከጀሃነም ቅጣት ለመዳን እና የጀነት ለመሆን ይህ "ነበእ" نَبَأ ማለትም ከአላህ ወደ ነቢዩ"ﷺ" የሚወርደው ግህደተ-መለኮት"Revelation" ወሳኝ ነጥብ ነው።
አምላካችን አላህ ምህረት አድርጎ ከአሳማሚ ቅጣትም የሚያድንበት ነገር እንዲህ ይናገራል፦
20፥82 *እኔም ለተጸጸተ፣ ላመነም፣ መልካምንም ለሠራ፣ ከዚያም ለተመራ ሰው፣ በእርግጥ መሐሪ ነኝ*። وَإِنِّي لَغَفَّارٌ لِّمَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا ثُمَّ اهْتَدَىٰ

"ለተጸጸተ" ሲል ተውባን፣ "ላመነ" ሲል ኢማንን፣ "መልካምንም ለሠራ" ሲል ዐሚሉስ ሷሊሐትን፣ "ከዚያም ለተመራ ሰው" ሲል ኢሥቲቃምን ያመለክታል፤ ስለዚህ ለመዳን ንስሃ፣ እምነት፣ መልካም ሥራ እና ፅናት ወሳኝ ነጥቦች ናቸው፤ እነዚህ እስቲ አንድ በአንድ እንያቸው፦

ነጥብ አንድ
“ተውባህ”
“ተውባህ” تَوْبَة ማለት " ከነበሩበት ስህተት በንስሃ ወደ አላህ መመለስ" ማለት ነው፤ አላህ ወደ እርሱ የሚመለሱት ንስሃን የሚቀበል ስለሆነ ስሙ “አት-ተዋብ” التَّوَّاب ሲባል በንስሃ የሚመለሱት ሰዎች ደግሞ “አት-ተዋቢን” التَّوَّابِينَ ይባላሉ፤ አላህም፦ "እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ" ይላል፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *"እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ"*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

እንግዲያውስ ከጀሃነም ለመዳን አንድ ሰው በንስሃ ወደ አላህ መመለስ አለበት፦
24፥31 *"ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተጸጸቱ"* وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

ይህ የንስሃ ጸጸት ተቀባይነት የሚያገኘው ሞት በመጣበት በጣዕረ-ሞት ጊዜ ላይ አሊያም በትንሳኤ ቀን ስንቀሰቀስ ሳይሆን ከዚያም ከቅርብ ጊዜ ለሚጸጸቱት ብቻ ነው፦
4፥17 *"ጸጸትን መቀበል በአላህ ላይ የሚገባው ለእነዚያ ኀጢአትን በስህተት ለሚሠሩና ከዚያም ከቅርብ ጊዜ ለሚጸጸቱት ብቻ ነው፡፡ እነዚያንም አላህ በእነርሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል"*፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ إِنَّمَا التَّوْبَةُ عَلَى اللَّهِ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِن قَرِيبٍ فَأُولَـٰئِكَ يَتُوبُ اللَّهُ عَلَيْهِمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا
4፥18 "*ጸጸትንም መቀበል ለእነዚያ ኀጢአቶችን ለሚሠሩ አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ «እኔ አሁን ተጸጸትኩ» ለሚልና ለእነዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ኾነው ለሚሞቱ አይደለችም፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል*፡፡ وَلَيْسَتِ التَّوْبَةُ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السَّيِّئَاتِ حَتَّىٰ إِذَا حَضَرَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ إِنِّي تُبْتُ الْآنَ وَلَا الَّذِينَ يَمُوتُونَ وَهُمْ كُفَّارٌ ۚ أُولَـٰئِكَ أَعْتَدْنَا لَهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا
25፥27 *በዳይም «ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!» እያለ በጸጸት ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን አስታውስ*፡፡ وَيَوْمَ يَعَضُّ الظَّالِمُ عَلَىٰ يَدَيْهِ يَقُولُ يَا لَيْتَنِي اتَّخَذْتُ مَعَ الرَّسُولِ سَبِيلًا
33፥66 ፊቶቻቸው በእሳት ውሰጥ በሚገለባበጡ ቀን *«ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ*፡፡ يَوْمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ يَقُولُونَ يَا لَيْتَنَا أَطَعْنَا اللَّهَ وَأَطَعْنَا الرَّسُولَا
ነጥብ ሁለት
“ኢማን”
“ኢማን” إِيمَٰن በሩቅ ሚስጥር ላይ ያለን “እምነት” ሲሆን “ሙዑሚን” مُؤْمِن ደግሞ በሩቅ ሚስጥር ላይ የሚያምነው "ምእመን" ወይም “አማኝ” ማለት ነው፤ ምእምናን አላህ በንስሃን ተመልሰው ስላመኑ ምህረትን ያደርግላቸዋል ፦
7፥153 *"እነዚያም ኃጢአቶችን የሠሩ ከዚያም ከእርሷ በኋላ የተጸጸቱ ያመኑም ጌታህ ከእርሷ በኋላ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው"*፡፡ وَالَّذِينَ عَمِلُوا السَّيِّئَاتِ ثُمَّ تَابُوا مِن بَعْدِهَا وَآمَنُوا إِنَّ رَبَّكَ مِن بَعْدِهَا لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ

“መልካም ሥራ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው።
“ኢማን” إِيمَٰن ማለት “እምነት” ሲሆን ያለ ኢማን ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።
“ኢኽላስ” إخلاص ማለት ደግሞ ከእዩልይና ስሙልኝ እና ከሙገሳና ወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚነየት መተናነስ፣ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ እና ማጥራት ሲሆን ያለ ኢኽላስ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።
ሦስተኛው “ኢቲባዕ” إتباع ነው፤ “ኢቲባዕ” የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ “ተከተለ” ከሚለው የመጣ ሲሆን “መከተል” ማለት ሲሆን ቁርኣንና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ሑክም ማምለክ ነው፤ ያለ ኢቲባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም።
ይህንን ካየን ዘንዳ መልካም ሥራ ያለ ኢማን ከተሠራ በትንሣኤ ቀን ምንም አያድንም። ያ በጎ ሥራ የሠራው ሰው በጎ ሥራ ብልሹ ነው፤ አይጠቅመውም፤ የእነርሱ መልካም ሥራ ያለ እምነት ስለሆነ በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው ውኃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ እንደማያገኘው ነው፤ አላህ የተበተነ ትቢያም ያደርገዋል፤ በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም፦
11፥16 *እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሠሩትም ሥራ በእርሷ ውስጥ ተበላሸ፤ ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው*፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ إِلَّا النَّارُ ۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا فِيهَا وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ
24፥39 *እነዚያም የካዱት ሰዎች መልካም ሥራዎቻቸው በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ የጠማው ሰው ውኃ ነው ብሎ እንደሚያስበው በመጣውም ጊዜ ምንም ነገር ኾኖ እንደማያገኘው ነው*፡፡ وَالَّذِينَ كَفَرُوا أَعْمَالُهُمْ كَسَرَابٍ بِقِيعَةٍ يَحْسَبُهُ الظَّمْآنُ مَاءً حَتَّىٰ إِذَا جَاءَهُ لَمْ يَجِدْهُ شَيْئًا وَوَجَدَ اللَّهَ عِندَهُ فَوَفَّاهُ حِسَابَهُ ۗ وَاللَّهُ سَرِيعُ الْحِسَابِ
25፥23 *ከሥራም ወደ ሠሩት እናስባለን፡፡ የተበተነ ትቢያም እናደርገዋለን*፡፡ وَقَدِمْنَا إِلَىٰ مَا عَمِلُوا مِنْ عَمَلٍ فَجَعَلْنَاهُ هَبَاءً مَّنثُورًا
14፥18 *የእነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች ምሳሌ መልካም ሥራዎቻቸው በነፋሻ ቀን ነፋስ በእርሱ እንደ በረታችበት አመድ ነው፡፡ በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡ ይህ እርሱ ሩቅ ጥፋት ነው*፡፡ مَّثَلُ الَّذِينَ كَفَرُوا بِرَبِّهِمْ ۖ أَعْمَالُهُمْ كَرَمَادٍ اشْتَدَّتْ بِهِ الرِّيحُ فِي يَوْمٍ عَاصِفٍ ۖ لَّا يَقْدِرُونَ مِمَّا كَسَبُوا عَلَىٰ شَيْءٍ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الضَّلَالُ الْبَعِيدُ

እንግዲያውስ ለመዳን አንድ ሰው ኢማን ያስፈልገዋል፦
23:1 *"ምእምናን በእርግጥም “ዳኑ”*። قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ

ኢንሻላህ በክፍል ሁለት የተቀሩትን ነጥቦች እና ድምዳሜውን እናያለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ፈላሕ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥5 እነዚያ ከጌታቸው *"በመመራት ላይ ናቸው"*፤ እነዚያም *"እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው"*፡፡ أُولَـٰئِكَ عَلَىٰ هُدًى مِّن رَّبِّهِمْ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

በክፍል አንድ መዳን የሚገኝበት ስለ ተውባህ እና ኢማን ስንመለከት ነበር፥ ዛሬ ደግሞ የቀሩትን ነጥቦች እና ድምዳሜውን እንመለከታለን፦

ነጥብ ሥስት
“ዐሚሉስ ሷሊሓት”
“ዐሚሉስ ሷሊሓት” عَمِلُوا الصَّالِحَات በኢማን የሚሠራ “መልካም ሥራ” ማለት ነው፤ አላህ መልካም ሥራ ከኢማን ተከትሎ የሚመጣ መሆኑን ለማመልከት፦ “እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ” በማለት ይናገራል፤ አምኖ መልካም የሠራ ሰው የጀነት ነው፦
18:107 *“እነዚያ ያመኑ እና መልካም ሥራዎችን የሠሩ”፥ የፊርደውስ ገነቶች ለእነርሱ መስፈሪያ ናቸው*። إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَانَتْ لَهُمْ جَنَّاتُ الْفِرْدَوْسِ نُزُلًا
4፥124 *ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ"*፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا
19፥60 ግን *የተጸጸተና ያመነም በጎንም ሥራ የሠራ ሰው እነዚህ ገነትን ይገባሉ"*፡፡ አንዳችንም አይበደሉም፡፡ إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ شَيْئًا

እንግዲያውስ ለመዳን አንድ ሰው በኢማን መልካም ሥራ መሥራት አለበት፦
22፥77 እያመናችሁናንተ ሰዎች ሆይ! በስግደታችሁ አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም አምልኩ፣ *ትድኑ ዘንድ በጎንም ነገር ሥሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

“ለዐለኩም” لَعَلَّكُمْ በሚለው መነሻ ቃል ላይ ቅጥያ ሆኖ የመጣው ቃል “ለዐል” لَعَل ነው፣ “ለዐል” ማለት “ዘንድ”so that” ማለት ሲሆን ይህም ምክንያታዊ መስተዋድድ አመክንዮን ያመለክታል። ምንኛ መታደል ነው? ወደ አላህ ተጸጽቶ፥ አምኖ መልካም ሥራ የሠራ ከሚድኑት ነው፦
28፥67 *የተጸጸተ፣ ያመነ እና ሰውማ መልካምንም የሠራ ከሚድኑት ሊኾን ይከጀላል"*። فَأَمَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صَالِحًا فَعَسَىٰ أَن يَكُونَ مِنَ الْمُفْلِحِينَ

ነጥብ አራት
“ኢስቲቃማህ”
“ኢስቲቃማህ” استقامة ሰው በንስሃ በተጸጸተበት፣ ባመነበት ኢማን እና በሚሣራው መልካም ሥራ “መፅናት” ነው፤ "ፅናት" በያዝነው ነገር ቀጥ ብሎ መቆም ነው፦
42፥15 ለዚህም ድንጋጌ ሰዎችን ጥራ፡፡ *"እንደታዘዝከውም ቀጥ በል"*፡፡ فَلِذَٰلِكَ فَادْعُ ۖ وَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُم
11፥112 *"እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ"*፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

"ቀጥ በል" ለሚለው ቃል የገባው “ኢሥተቂም” اسْتَقِمْ ሲሆን “ፅና” ማለት ነው፤ በቀጥተኛው መንገድ ላይ መፅናት ፍርሃትና ሃዘን ሳይኖር የጀነት ለመሆን መበሰር ነው፦
46፥13 እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ፣ *"ከዚያም ቀጥ ያሉ በነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም። እነርሱም አያዝኑም"*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ
41፥30 እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም *"ቀጥ ያሉ" «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ»* በማለት በእነርሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُون

በዚህ አንቀጽ ላይ "ቀጥ ያሉ" ለሚለው ቃል የገባው “ኢሥተቃሙ” اسْتَقَامُوا ሲሆን “የጸኑ” ማለት ነው፤ "ትእግስት" "ጥረት" "ተስፋ" የፅናት ክፍሎች ናቸው። አላህን በትንሳኤ ቀን አገኘዋለው፣ ሳላካብበው አየዋለው፣ ሲናገር እሰማዋለን ብሎ የሚጓጓ በትግስት፣ በጥረት እና በተስፋ” ፅናት ይኖረዋል። እንግዲያውስ ለመዳን በአላህ መንገድ እየታገሉ መፅናት ይፈልጋል፦
5:35 *"ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ”*። وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

መደምደሚያ
ቁርኣን አላህን ለሚፈሩት፣ ለእነዚያ በሩቁ ነገር የሚያምኑ ለኾኑት፣ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀው የሚሰግዱ ለኾኑት፣ አላህ ከሰጠቸውም ሲሳይ የሚቸሩ ለኾኑት፣ ለእነዚያም ወደ ነቢያችን"ﷺ" በተወረደው እና ከእሳቸው በፊትም በተወረደው የሚያምኑ ለኾኑት፤ በመጨረሻይቱም ዓለም እነርሱ የሚያረጋግጡ ለኾኑት መሪ ነው። አላህን መፍራት፣ በሩቅ ነገር ማመን፣ ሶላትን ደንቡን ጠብቆ መስገድ፣ ዘካ መስጠት፣ በተወረዱት ወሕይ ማመን፣ የመጨረሻይቱም ዓለም በዒልሙል የቂን ማረጋገጥ በቀጥተኛው መንገድ ላይ መመራት ነው። ከላይ የተዘረዘሩት አማኞች በመነሻ እና በመዳረሻ ላይ ባለው በቀጥተኛው መንገድ ላይ በመመራት ላይ ናቸው፦
2፥5 እነዚያ ከጌታቸው *"በመመራት ላይ ናቸው"*፤ እነዚያም *"እነርሱ ፍላጎታቸውን ያገኙ ናቸው"*፡፡ أُولَـٰئِكَ عَلَىٰ هُدًى مِّن رَّبِّهِمْ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

"ፍላጎታቸውን ያገኙ" ለሚለው ቃል የገባው "ሙፍሊሑን" مُفْلِحُون ሲሆን "የሚድኑት" ማለት ነው። ከላይ የተዘረዘሩት ኢማን እና መልካም ሥራዎች በትንሳኤ ቀን ሚዛኖች እንዲከብዱ ያደርጉታል፤ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎችም እነዚያ "ሙፍሊሑን" ናቸው፦
7፥8 *ትክክለኛውም ሚዛን የዚያን ቀን ነው፡፡ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ "የሚድኑት" ናቸው*፡፡ وَالْوَزْنُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ ۚ فَمَن ثَقُلَتْ مَوَازِينُهُ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ
በአላህ መንገድ ጅሃድ የሚያደርጉ በጀነት ውስጥ መልካሞች ሁሉ ለእነርሱ ናቸው፤ እነዚያም እነርሱ "ሙፍሊሑን" ናቸው፦
9፥88 ግን መልክተኛው እነዚያም ከእርሱ ጋር ያመኑት *በገንዘቦቻቸውም በነፍሶቻቸውም ታገሉ፡፡ እነዚያም መልካሞች ሁሉ ለእነርሱ ናቸው፡፡ እነዚያም እነርሱ "የሚድኑት" ናቸው*፡፡ لَـٰكِنِ الرَّسُولُ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ جَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ ۚ وَأُولَـٰئِكَ لَهُمُ الْخَيْرَاتُ ۖ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُون

አማኞች አላህን እና መልእክተኛውን የሚያንቋሽሹ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ከሆኑት ጋር በዲን አይወዳጁም። እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ንቁ! የአላህ ሕዝቦቸ እነርሱ "ሙፍሊሑን" ናቸው፦
58፥22 *በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፡፡ ከእርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል፡፡ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፡፡ አላህ ከእነርሱ ወዷል፡፡ እነርሱም ወደዋል፡፡ እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ንቁ! የአላህ ሕዝቦቸ እነርሱ "የሚድኑት" ናቸው*፡፡ لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ أُولَـٰئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ الْإِيمَانَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٍ مِّنْهُ ۖ وَيُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ ۚ أُولَـٰئِكَ حِزْبُ اللَّهِ ۚ أَلَا إِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

አምላካችን አላህ ስለ ፈላሕ ተረድተው ሙፍሊሑን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ተሕሪፍ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥71 *የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! “እዉነቱን በዉሸት” ለምን *ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ?* يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

አምላካችን አላህ ወደ ነቢያችን"ﷺ" ወሕይ እንዳወረደ ሁሉ ከእርሳቸውም በፊት ወደነበሩትም ነቢያት አውርዷል፤ “ወሕይ” وَحْى የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ “ገለጠ” ወይም “አወረደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት”Revelation” ማለት ነው፦
2፥4 ለእነዚያም *ወደ አንተ በተወረደው እና ከአንተ በፊትም በተወረደው የሚያምኑ"* በመጨረሻይቱም ዓለም እነርሱ የሚያረጋግጡ ለኾኑት መሪ ነው፡፡ وَالَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْكَ وَمَا أُنزِلَ مِن قَبْلِكَ وَبِالْآخِرَةِ هُمْ يُوقِنُونَ
42፥3 እንደዚሁ *"አሸናፊው ጥበበኛው አላህ ወደ አንተ ያወርዳል፡፡ ወደ እነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት አውርዷል*"፡፡ كَذَٰلِكَ يُوحِي إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

ቁርኣን ወደ ነቢያችን"ﷺ" ቢወርድም አምላካችን አላህ ወደ እኛ በማስጠጋት፦ "ወደ እናንተ በተወረደው" ይለናል፤ ከእርሳቸው በፊት ወደ ነቢያት ቢወርድም ወደ ሕዝቦቻቸው በማስጠጋት፦ "ወደ እነርሱ በተወረደው" ይለናል፤ ለእነርሰም፦ "በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን" በሉ! ይለናል፦
3፥199 ከመጽሐፉም ባለቤቶች ለአላህ ፈሪዎች በአላህ አንቀጾችም ጥቂትን ዋጋ የማይለወጡ ሲኾኑ በአላህ እና *"በዚያ ወደ እናንተ በተወረደው በዚያም ወደ እነርሱ በተወረደው የሚያምኑ ሰዎች አሉ"*፡፡ እነዚያ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ አላህ ምርመራው ፈጣን ነው፡፡ وَإِنَّ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ لَمَن يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْهِمْ خَاشِعِينَ لِلَّهِ لَا يَشْتَرُونَ بِآيَاتِ اللَّهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۗ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ *በሉም፦ «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን"*፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» وَلَا تُجَادِلُوا أَهْلَ الْكِتَابِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِلَّا الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

አላህ እነዚህን የመጽሐፉ ሰዎች፦ "አላህም ባወረደው ቁርኣን «እመኑ» በተባሉ ጊዜ፦ እነርሱም፦ «በእኛ ላይ በተወረደው እናምናለን» ይላሉ፤ ከእነርሱ በኋላ የወረደው ቁርኣን ወደ እነርሱ የተወረደውን አረጋጋጭ እና እውተኛ ሲኾን ይክዳሉ፦
2፥91 *ለእነርሱ፦ "አላህም ባወረደው «እመኑ» በተባሉ ጊዜ፦ «በእኛ ላይ በተወረደው እናምናለን» ይላሉ፡፡ ከእነርሱ በኋላ ባለው እርሱ ከእነርሱ ጋር ላለው አረጋጋጭ እና እውተኛ ሲኾን ይክዳሉ*፡፡ «አማኞች ከኾናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነቢያት ለምን ገደላችሁ?» በላቸው፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ آمِنُوا بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ قَالُوا نُؤْمِنُ بِمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَيَكْفُرُونَ بِمَا وَرَاءَهُ وَهُوَ الْحَقُّ مُصَدِّقًا لِّمَا مَعَهُمْ ۗ قُلْ فَلِمَ تَقْتُلُونَ أَنبِيَاءَ اللَّهِ مِن قَبْلُ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

እንግዲህ ከቁርኣን በፊት ወደ እነርሱ የተወረደው ተውራት እና ኢንጂል ናቸው፤ አምላካችን አላህ ተውራት እና ኢንጂል ከቁርኣን በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው፦
5፥68 *"«እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! "ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደ እናንተ የተወረደውን" እስከምታቆሙ ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም» በላቸው"*፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَسْتُمْ عَلَىٰ شَيْءٍ حَتَّىٰ تُقِيمُوا التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُم
3፥3 *”ከእርሱ በፊት ያሉትን የሚያረጋግጥ”* ሲኾን መጽሐፉን በአንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ *”ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል”*፡፡ نَزَّلَ عَلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ
3፥4 *”ከእርሱ በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ አወረዳቸው”*፡፡ مِن قَبْلُ هُدًۭى لِّلنَّاسِ

"ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ አምላካችን አላህ፦ "እመኑ" ያለን ከቁርኣን በፊት ባወረደው ወሕይ ነው፦
4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው፤ በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ፤ በዚያም *”ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ ءَامِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِى نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَٱلْكِتَٰبِ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ مِن قَبْلُ