ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ አንድ
“ሲታመን ይከዳል”
አምላካችን አላህ አማና ሲጣልብን አማናችን መወጣት እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥58 *አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል*፡፡ በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ النَّاسِ أَن تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا
8፥27 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን አትክዱ፡፡ *አደራዎቻችሁንም እናንተ እያወቃችሁ አትክዱ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَخُونُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ وَتَخُونُوا أَمَانَاتِكُمْ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ

ነጥብ ሁለት
“ሲናገር ይዋሻል”
ሙስሊም ከዋሸ ቀኑ ተበላሸ ይላል ያገሬ ሰው፤ አንድ ሙናፊቅ "ተላላ" “አባይ” “ቀላማጅ” “ዋሾ” “በጥራቃ” “ውሸታም” “ሐሰተኛ” “ወሽከታ” ነው፤ አምላካችን አላህ፦ “ሐሰትንም ቃል ራቁ” “ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ” ብሎ ያዘናል፦
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَاجْتَنِبُوا الرِّجْسَ مِنَ الْأَوْثَانِ وَاجْتَنِبُوا قَوْلَ الزُّورِ
33፥70 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ *ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا

ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ይቀጥላል…

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኒፋቅ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا

ነጥብ ሦስት
“ቃል ገብቶ ያፈርሳል”
ቃል ገብቶ ማፍረስ ከመሃላ አይተናነስም፤ አምላካችን አላህ፦ “በቃል ኪዳኖች ሙሉ” ይለናል፦
5፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በቃል ኪዳኖች ሙሉ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَوْفُوا بِالْعُقُودِ ۚ
23፥8 *እነዚያም እነርሱ ለአደራዎቻቸው እና ለቃል ኪዳናቸው ጠባቂዎች*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
70፥32 *እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውን እና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِأَمَانَاتِهِمْ وَعَهْدِهِمْ رَاعُونَ
17፥34 የየቲምንም ገንዘብ የብርታቱን ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በኾነች ኹኔታ እንጂ አትቅረቡ፡፡ *በኪዳናችሁም ሙሉ፤ ኪዳን የሚጠየቁበት ነውና*፡፡ وَلَا تَقْرَبُوا مَالَ الْيَتِيمِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ حَتَّىٰ يَبْلُغَ أَشُدَّهُ ۚ وَأَوْفُوا بِالْعَهْدِ ۖ إِنَّ الْعَهْدَ كَانَ مَسْئُولًا

ነገር ግን ይህ ምልክት የሚታይበት ሁሉ ሙናፊቅ ላይሆን ይችላል፤ ግን መናፍቅ የሚያሰኘው ጉዳይ ነብያችን”ﷺ” እንዲህ ይነግሩናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 116
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐምር”ረ.ዐ.” እንደነገረን የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- *“አራት ነገሮች ያሉበት ሰው ግልጽ መናፍቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ውስጥ አንዱ ያለበት ሰው ደግሞ እስኪተወው ድረስ ከኑፋቄ ከፊሉ ጠባይ አለበት ማለት ነው፤ አራቱ ነገሮች፡- ሲታመን ይከዳል፣ ሲናገር ይዋሻል፣ ቃል ገብቶ ያፈርሳል፣ ሲሟገት ያስተባብላል*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَرْبَعٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ كَانَ مُنَافِقًا خَالِصًا وَمَنْ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْهُنَّ كَانَتْ فِيهِ خَلَّةٌ مِنْ نِفَاقٍ حَتَّى يَدَعَهَا إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ وَإِذَا عَاهَدَ غَدَرَ وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ وَإِذَا خَاصَمَ فَجَرَ ‏”‏ ‏

ነጥብ አራት
“ሲሟገት ያስተባብላል”
መናፍቃን የአላህ አንቀጾች ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ መከራከር ይወዳሉ፦
45፥25 *አንቀጾቻችንም ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ ክርክራቸው* «እውነተኞች እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡ» *ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም*፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمْ إِلَّا أَن قَالُوا ائْتُوا بِآبَائِنَا إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
10፥95 *ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች ከአስተባበሉት አትሁን፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና*፡፡ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ الْخَاسِرِينَ
4፥107 *ከነዚያም እራሳቸውን ከሚበድሉት ላይ አትከራከር*፤ አላህ ከዳተኛ ኀጢአተኛ የሆነን ሰው አይወድምና። وَلَا تُجَادِلْ عَنِ الَّذِينَ يَخْتَانُونَ أَنفُسَهُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ خَوَّانًا أَثِيمًا

ነጥብ አምስት
“በጥቂት አለመብቃቃት”
በጥቂት መብቃቃትን የአማኞች ባህርይ ነው፤ በጥቂት አለመብቃቃት የመናፍቃን ባህርይ ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ: መጽሐፍ 70, ሐዲስ 22
አቢ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል፤ ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ الْمُؤْمِنَ يَأْكُلُ فِي مِعًى وَاحِدٍ، وَإِنَّ الْكَافِرَ ـ أَوِ الْمُنَافِقَ فَلاَ أَدْرِي أَيَّهُمَا قَالَ عُبَيْدُ اللَّهِ ـ يَأْكُلُ فِي سَبْعَةِ أَمْعَاءٍ ‏”‌‏.

ሙዕሚን በአንድ አንጀት ይመገባል ማለት ሲበላ በቢሥሚላህ ስለሚጀምር በረካ አለው፣ ያጣቅመዋል እና ይብቃቃል ማለት እንጅ አንድ ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። በተጨማሪም ካፊር ወይም ሙናፊቅ በሰባት አንጀት ይመገባል ማለት በቢሥሚላህ ስለማይጀምር በረካ የለውም፣ አያጣቅመውም እና አይብቃቃም ማለት እንጅ ሰባት ነው አንጀቱ ማለት አይደለም። ይህ “መዕነዊይ” ማለትም “ፍካሬአዊ” አነጋገር እንጂ “ሒስሲይ” ማለትም “እማሬአዊ” አይደለም።
ነጥብ ስድስት
“ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ”
ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 288,
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *“ቁርአንን የሚቀራ አማኝ ምሳሌው ልክ “እንደ” ትርንጎ ነው፤ ሽታው ጥሩ ነው ጣዕሙም ጥሩ ነው። ቁርአንን የማይቀራ አማኝ ደግሞ ልክ እንደ ተምር ነው፤ ሽታ የለውም ጣዕም ግን አለው። ቁርአንን የሚቀራ ሙናፊቅ አምሳያው ልክ እንደ አሪቲ ነው፤ ሽታው ያውዳል ጣዕሙ ግን ይመራል። ቁርአንን የማይቀራ ሙናፊቅ ደግሞ ልክ እንደ እንቧይ ነው ሽታ የለውም፤ ጣዕሙም መራራ ነው”* عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْمُؤْمِنُ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالأُتْرُجَّةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَرِيحُهَا طَيِّبٌ، وَالْمُؤْمِنُ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ وَيَعْمَلُ بِهِ كَالتَّمْرَةِ، طَعْمُهَا طَيِّبٌ وَلاَ رِيحَ لَهَا، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالرَّيْحَانَةِ، رِيحُهَا طَيِّبٌ وَطَعْمُهَا مُرٌّ، وَمَثَلُ الْمُنَافِقِ الَّذِي لاَ يَقْرَأُ الْقُرْآنَ كَالْحَنْظَلَةِ، طَعْمُهَا مُرٌّ ـ أَوْ خَبِيثٌ ـ وَرِيحُهَا مُرٌّ ‏”

ኒፋቅ በሁለት ይከፈላል፤ አንደኛው ኒፋቁል አስገር ሲሆን ይህ ባህርይ ያለበት ሙናፊቅ ባይሰኝም ግን ከላይ የተዘረዘሩት የታመኑት ጊዜ መካድ፣ ሲናገሩ መዋሸት፣ ቃል ገብቶ ማፍረስ፣ ቀጠሮን ማዛባት፣ ሲከራከር ማስተባበል ናቸው።
ሁለተኛው ኒፋቁል አክበር ሲሆን ይህ ሰው ሙናፊቅ ይባላል፤ የትልቁ ኒፋቅ ምልክቶች የአላህን መልእክተኛ ማስተባበል፣ የተቀበሉትን መልእክት በከፊሉ ማስተባበል፣ እሳቸውን መጥላት፣ መልእክታቸውን መጥላት፣ በኢስላም ዝቅ ማለት መደሰት፣ የኢስላም የበላይነትን መጥላት ናቸው ወዘተ ናቸው። ሙናፊቅ ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ነው። ምክንያቱም ኒፋቅ ልብ ላይ ያለ በሽታ ነው፦
4፥63 *እነዚህ እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቅባቸው ናቸው፤ እነርሱንም ተዋቸው፤ ገሥጻቸውም፤ ለእነርሱም በራሳቸው ውስጥ ስሜት ያለውን ቃል ተናገራቸው*። ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﻠَﻢُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﻣَﺎ ﻓِﻲ ﻗُﻠُﻮﺑِﻬِﻢْ ﻓَﺄَﻋْﺮِﺽْ ﻋَﻨْﻬُﻢْ ﻭَﻋِﻈْﻬُﻢْ ﻭَﻗُﻞْ ﻟَﻬُﻢْ ﻓِﻲ ﺃَﻧْﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻗَﻮْﻟًﺎ ﺑَﻠِﻴﻐًﺎ ” ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺴﺎﺀ
3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፤ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፤ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፥ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸዉ በእርግጥ ተገለጸች። ልቦቻቸዉም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነዉ*። ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራራያዎችን በእርግጥ ገለጽን። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

አላህ የቀልብ በሽታ ከሆነው ከኒፋቅ ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢኽላስ እና ሪያዕ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

76፥9 *«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም*፡፡ إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا

ነጥብ አንድ
“ኢኽላስ”
“ዒባዳህ” عِبَادَة ማለትም “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉ፤ እነርሱም፦ አንደኛ “ኢማን” إِيمَٰن ሁለተኛ “ኢኽላስ” إخلاص ሦስተኛ “ኢቲባዕ” إتباع ናቸው። “ኢኽላስ” إخلاص ማለት ከእዩልይና ስሙልኝ እና ከሙገሳና ወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚነየት መተናነስ፣ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ እና ማጥራት ነው፣ እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ አምልኳቸውን የፈጸሙ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው፦
13፥22 እነዚያም *የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ፣ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ፣ እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ኾነ በግልጽ የመጸወቱ፣ ክፉውንም ነገር በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው*፡፡ እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለቻቸው*፡፡ وَالَّذِينَ صَبَرُوا ابْتِغَاءَ وَجْهِ رَبِّهِمْ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً وَيَدْرَءُونَ بِالْحَسَنَةِ السَّيِّئَةَ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عُقْبَى الدَّارِ

ፊትን የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከአላህ የሚፈራ ሙስሊም ከሰው ዋጋ እና ምስጋና ፈልጎ ሳይሆን የሚያደርገውን ሁሉ ለአላህ ውዴታ ብሎ ያደርጋል፦
76፥9 *«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም*፡፡ إِنَّمَا نُطْعِمُكُمْ لِوَجْهِ اللَّهِ لَا نُرِيدُ مِنكُمْ جَزَاءً وَلَا شُكُورًا
76፥10 *«እኛ ፊትን የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና» ይላሉ*፡፡ إِنَّا نَخَافُ مِن رَّبِّنَا يَوْمًا عَبُوسًا قَمْطَرِيرًا

ኢኽላስ ያለው ሙስሊም ምሳሌ በተስተካከለች ከፍተኛ ስፍራ ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው፦
2፥265 *የእነዚያም የአላህን ውዴታ ለመፈለግና ለነፍሶቻቸው እምነትን ለማረጋገጥ ገንዘቦቻቸውን የሚለግሱ ሰዎች ምሳሌ በተስተካከለች ከፍተኛ ስፍራ ላይ እንዳለች አትክልት፣ ብዙ ዝናብ እንደነካት ፍሬዋንም እጥፍ ኾኖ እንደሰጠች፣ ዝናብም ባይነካት ካፊያ እንደሚበቃት ብጤ ነው*፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ وَمَثَلُ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمُ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ وَتَثْبِيتًا مِّنْ أَنفُسِهِمْ كَمَثَلِ جَنَّةٍ بِرَبْوَةٍ أَصَابَهَا وَابِلٌ فَآتَتْ أُكُلَهَا ضِعْفَيْنِ فَإِن لَّمْ يُصِبْهَا وَابِلٌ فَطَلٌّ ۗ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

በዓለም ላይ ትልቁ ቁጥር መቼም ሴንቲሊዮን ነው፤ እርሱም ባለ ስድስት መቶ ዜሮ የያዘ ነው፤ ይህንን ትልቅ ቁጥር ግን ከፊት ለፊቱ አንድ ቁጥር ብትነሳ እነዚያ ሁሉ ዜሮ ሆነው ይቀራሉ እንጂ ዋጋ የላቸው። እንደዚሁ ልግስና፣ ዕውቀት፣ ሰማዕትነት፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ሃብት፣ ውበት ወዘተ… ቢደረደሩም ከፊታቸው እንደ አንድ ቁጥር “ኢኽላስ” ከሌለ እንዚህ ሁሉ ዜሮ ናቸው። ኢኽላስ ያለው ሙስሊም “ሙኽሊስ” مُخْلِص ማለትም “አጥሪ” “ምርጥ” ይባላል፦
40፥14 *አላህንም ከሓዲዎች ቢጠሉም ሃይማኖትን ለእርሱ “አጥሪዎች” ኾናችሁ ተገዙት*፡፡ فَادْعُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُون
37፥40 *ግን ምርጥ የሆኑት የአላህ ባሮች ቅጣትን አይቀምሱም*፡፡ إِلَّا عِبَادَ اللَّهِ الْمُخْلَصِينَ
38፥82 እርሱም አለ፦ *”በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ”*፡፡ قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ
38፤83 *”ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ”*፡፡ إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ الْمُخْلَصِينَ

“ሙኽሊሲን” مُخْلِصِين የሙኽሊስ ብዙ ቁጥር ነው፤ ሸይጧን ቃል የገባው ከአላህ ባሮች ሙኽሊሲን የሚባሉትን ላለማሳሳት ነው፤ ሙኽለሲን በአላህ መንገድ የሚለግሱ፣ መመጻደቅንና ማስከፋትን የማያስከትሉ ሲሆኑ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፤ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም፦
2፥262 *እነዚያ ገንዘቦቻቸውን “በአላህ መንገድ የሚለግ ከዚያም የሰጡትን ነገር “መመጻደቅንና ማስከፋትን የማያስከትሉ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም*፡፡ الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ثُمَّ لَا يُتْبِعُونَ مَا أَنفَقُوا مَنًّا وَلَا أَذًى ۙ لَّهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُون

ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ሪያዕ እንቀጥላለን…..

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢኽላስ እና ሪያዕ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

107፥4 *ወዮላቸው ለሰጋጆች*፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلْمُصَلِّينَ
107፥6 *ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት*፡፡ ٱلَّذِينَ هُمْ يُرَآءُونَ

ነጥብ ሁለት
“ሪያዕ”
የኢኽላስ ተቃራኒ የሆነው “አር-ሪያዕ” الرياء ሲሆን ትርጉሙ “እዩልኝ ስሙልኝ” ማለት ነው፤ ይህ ትንሹና ድብቁ ሺርክ ነው፤ ትልቁ እና ግልጹ ሺርክ ከኢስላም አጥር የሚያስወጣ ሲሆን ይህንን ድርጊት የሚያደርግ ሙሽሪክ ይሰኛል፤ ነገር ግን ትንሹና ድብቁ ሺርክ አር-ሪያዕ ነው፤ አር-ሪያዕ ያለው ሰው ምሳሌው በላዩ ዐፈር እንዳለበት ለንጣ ድንጋይ ኃይለኛም ዝናብ እንዳገኘውና ምልጥ አድርጎ እንደተወው ብጤ ነው፤ ከሠሩት ነገር በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም፦
2:264 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *እንደዚያ ገንዘቡን ለሰዎች ማሳየት ሲል እንደሚሰጠው እና በአላህና በመጨረሻውም ቀን እንደማያምነው ሰው ምጽዋቶቻችሁን በመመጻደቅና በማስከፋት አታበላሹ፤ ምሳሌውም በላዩ ዐፈር እንዳለበት ለንጣ ድንጋይ ኃይለኛም ዝናብ እንዳገኘውና ምልጥ አድርጎ እንደተወው ብጤ ነው፤ ከሠሩት ነገር በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُبْطِلُوا صَدَقَاتِكُم بِالْمَنِّ وَالْأَذَىٰ كَالَّذِي يُنفِقُ مَالَهُ رِئَاءَ النَّاسِ وَلَا يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۖ فَمَثَلُهُ كَمَثَلِ صَفْوَانٍ عَلَيْهِ تُرَابٌ فَأَصَابَهُ وَابِلٌ فَتَرَكَهُ صَلْدًا ۖ لَّا يَقْدِرُونَ عَلَىٰ شَيْءٍ مِّمَّا كَسَبُوا ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْكَافِرِينَ
107፥4 *ወዮላቸው ለሰጋጆች*፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلْمُصَلِّينَ
107፥6 *ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት*፡፡ ٱلَّذِينَ هُمْ يُرَآءُونَ

ሶላት ላይ የሚቆሙ “ሙሰሊን” مُصَلِّين ይባላሉ፤ ነገር ግን ሶላት ላይ ለይዩልኝ የሚቆሙት ወዮላቸው ተብሏል፤ ለምን ሲባል የእዩልኝ ስለሆነ፤ ይህ “ሺርኩል አስገር” شِّرْكُ الأَصْغَر ማለትም “ትንሹ ሺርክ” ነው፤ ነብያችን”ﷺ” ስለ ትንሹ ሺርክ እንዲህ ያስጠነቅቁናል፦
አማም አሕመድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 428
መሕሙድ ኢብኑ ለቢድ እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ትንሹን ሺርክ እፈራላችኃለው” ሰሃባዎችም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ትንሹን ሺርክ ምንድን ነው? ብለው ጠየቁ፤ እሳቸውም፦ “አር-ሪያዕ ነው፤ በዋጋ በሚከፈልበት ቀን ሰዎች ዋጋቸውን በሚቀበሉበት ጊዜ አላህም፦ “ስታሳይዋቸው የነበሩት ከእነርሱ አጅር የምታገኙ ከሆነ ይክፈሏችሁ” ብሎ ይላቸዋል” ብለው መለሱ*። عَنْ مَحْمُودِ بْنِ لَبِيدٍ ، أَنّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ” إِنَّ أَخْوَفَ مَا أَخَافُ عَلَيْكُمُ الشِّرْكَ الأَصْغَرَ ” ، قَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ ، وَمَا الشِّرْكُ الأَصْغَرُ ؟ قَالَ : ” الرِّيَاءُ ، يَقُولُ اللَّهُ لَهُمْ يَوْمَ يُجَازِي الْعِبَادَ بِأَعْمَالِهِمُ : اذْهَبُوا عَلَى الَّذِينَ كُنْتُم تُرَاءُونَ فِي الدُّنْيَا ، فَانْظُرُوا هَلْ تَجِدُونَ عِنْدَهُمْ جَزَاءً ” .
አር-ሪያዕ ማለት “ሺርኩል ኸፊይ” شِّرْكُ الْخَفِي ማለትም “ድብቁ ሺርክ” እንደሆነ በሌላ ሐዲስ ነብያችን”ﷺ” ተናግረዋል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4344
አቢ ሠዒድ እንደተናገረው፦ *”ስለ መሢሑል ደጃል በተወያየንበት ጊዜ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ወደ እኛ መጥተው፦ “ከመሢሑል ደጃል የባሰ የምፈራላችሁን ነገር ልንገራችሁን? አሉን፤ እኛም አዎ አልን፤ እርሳቸውም፦ “ድብቁ ሺርክ ነው፤ አንድ ሰው ሶላት ሲቆምና በሰው ፊት ጥሩ አድርጎ ለሰው እንዲያይለት ማድረግ ነው*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ، قَالَ خَرَجَ عَلَيْنَا رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ وَنَحْنُ نَتَذَاكَرُ الْمَسِيحَ الدَّجَّالَ فَقَالَ ‏”‏ أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِمَا هُوَ أَخْوَفُ عَلَيْكُمْ عِنْدِي مِنَ الْمَسِيحِ الدَّجَّالِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ قُلْنَا بَلَى ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ الشِّرْكُ الْخَفِيُّ أَنْ يَقُومَ الرَّجُلُ يُصَلِّي فَيُزَيِّنُ صَلاَتَهُ لِمَا يَرَى مِنْ نَظَرِ رَجُلٍ ‏”‏ ‏.‏

ይህ ሺርኩል ኸፊይ አምልኮን ዋጋ የሚያሳጣ የኢኽላስ ተቃራኒ ነው፤ ኢኽላስ የሌላቸውን ሻሂድ፣ ዐሊም እና ሙንፊቅ አላህ የትንሳኤ ቀን እንዲህ ምላሽ ይሰጣቸዋል፦
ሪያዱ አስ-ሳሊሂን መጽሐፍ 18, ሐዲስ 107
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማሁኝ፦ *”የትንሣኤ ቀን ከሰዎች መጀመሪያ ፍርድ የሚሰጠው በሸሂድ የሞተው ሰው ላይ ይሆናል፤ በእርሱ ላይ የተዋለለትን ጸጋ ያስታውሰውና እርሱም ያምናል፤ ታዲያ ምን ሰራህበት? ተብሎ ሲጠየቅ እርሱም፦ “በአንተ መንገድ ሸሂድ ሆንኩኝ” ይላል፤ አላህም፦ ዋሸህ! አንተ የፈለግኸው እገሌ ጀግና እንድትባል ነበር” ፤ እርሱም ተብሎልሀል ይለውና ወደ እሳት ውስጥ እስኪጣል ድረስ በፊቱ ይጎተታል*፡፡
ሁለተኛው *የተቀሰመና የተገበየ ዕውቀት የተማረው እና ቁርኣን የቀራውም ይመጣል፤ በእርሱ ላይ የተዋለለትን ጸጋ ያስታውሰውና እርሱም ያምናል፤ ታዲያ ምን ሰራህበት? ተብሎ ሲጠየቅ እርሱም፦ “ዕውቀትን ተምሬ ቁርኣንን ቀርቼ ሌሎችንም ለአንተ ብዬ አስተማርኩ” ብሎ ይመልሳል፤ አላህም፦ ዋሸህ! አንተ የፈለከው እገሌ ዐሊም ነው፣ እገሌ ቃሪእ ነው እንድትባል ነበር”፤ እርሱም ተብሎልሀል ይለውና እሳት ውስጥ እስኪጣል ድረስ በፊቱ ይጎተታል*፡፡
ለጥቆ *የሀብት ክምችት የተሰጠው ሰው ይመጣል፤ በእርሱ ላይ የተዋለለትን ጸጋ ያስታውሰውና እርሱም ያምናል፤ ታዲያ ምን ሰራህበት? ተብሎ ሲጠየቅ እርሱም፦ “አንተ እንዲለገስ የምትወደው አንድንም ነገር ለአንተ ብዬ ብለግስ እንጂ ትቼ ያለፍኩት ነገር የለም” ብሎ ይመልሳል፤ አላህም፦ ዋሸህ! አንተ የፈለግኸው ለጋስ ነው እንድትባል ነበር”፤ እርሱም ተብሎልሀል ይለውና እሳት ውስጥ እስኪጣል ድረስ በፊቱ ይጎተታል*፡፡ وعنه قال‏:‏ سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏ “‏ إن أول الناس يقضى يوم القيامة عليه رجل اسُتشهد، فأتي به، فعرفه نعمته، فعرفها، قال‏:‏ فما عملت فيها‏؟‏ قال‏:‏ قاتلت فيك حتى اسُتشهدت، قال‏:‏ كذبت، ولكنك قاتلت لأن يقال‏:‏ جريء، فقد قيل، ثم أمر به، فسحب على وجهه حتى ألقي في النار‏.‏ ورجل تعلم العلم وعلمه، وقرأ القرآن، فأتي به، فعرفه نعمه فعرفها‏.‏ قال فما عملت فيها‏؟‏ قال تعلمت العلم وعلمته وقرأت فيك القرآن‏.‏ قال كذبت، ولكنك تعلمت ليقال‏:‏ عالم‏.‏ وقرأت القرآن ليقال‏:‏ هو قارئ، فقد قيل‏:‏ ثم أُمر به، فسُحب على وجهه حتى ألقي في النار، ورجل وسع الله عليه، وأعطاه من أصناف المال، فأتي به فعرفه نعمه، فعرفها‏.‏ قال‏:‏ فما عملت فيها ‏؟‏ قال‏:‏ ما تركت من سبيل تحب أن ينفق فيها إلا أنفقت فيها لك، قال‏:‏ كذبت، ولكنك فعلت ليقال‏:‏ جواد، فقد قيل، ثم أُمر به فسُحب على وجهه ثم ألقي في النار‏”‏ ‏

አላህ ከሪያዕ ይጠብቀን፤ ሙኽለሲን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ገና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

“ገና” γεννα የሚለው የግሪክ ቃል ጠበቅ አድርገን ስናነበው “ልደት”birth” ማለት ሲሆን የኢየሱስ ልደት ነው ተብሎ የሚታመንበት በዓል ነው፤ የልደት በዓል መከበር የተጀመረው እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 336 AD ነው፤ ከዚያ በፊት ይህ በዓል እንደማይታወቅ የተለያዩ መድብለ እውቀቶች”Encyclopedias” ያትታሉ፤ ለናሙና ያክል ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒድያ እንየው፡-
“ጥንታዊ ክርስትያኖች የእየሱስን መወለጃ ቀን በዓል አርገው አያከብሩም፡፡ ይህም የሆነው የማንንም ሰው የልደትን ቀን ማክበር ጣዖታዊ ስርአት በመሆኑ ነው” ወርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒድያ ቅፅ 3, 1966, ገፅ 416.
“The early Christians did not celebrate His [Christ’s] birth because they considered the celebration of anyone’s birth to be a pagan custom.” World Book Encyclopedia, Volume 3. 1966, pp. 416.

የኢየሱስን ልደት አክብሩ የሚል ባይብል ላይም አንድም ጥቅስ የለም ከሃዋርያት ጀምሮ እስከ ሶስተኛው ክፍለ ዘመን ያከበረ አንድም ሰው በታሪክ ላይ የለም፣ ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ኢየሱስ መቼ ተወለደ? ለሚለው ጥያቄ በግርድፉና በሌጣው ለአንባቢያን ይረዳ ዘንድ አንድ ሁለት እላለው፣ በተረፈ የኢየሱስ ልደት ለእኛ ለሙስሊሞች ያ ያህል ቦታ ባይኖረውም ለጠቅላላ እውቀት ማወቅ ለሚሻ ሰው ፈርጅና ደርዝ ባለው መልኩ ሊያጠና ይችላል። ኢየሱስ የተወለደበት ወር፣ አመት፣ ቀን መቼ ነው? ይህን በወፍ በረር እስቲ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“የተወለደበት ወር”
ኢየሱስ የተወለደበትን ወር ባይብል ይነግረናል፣ ይህን ለማወቅ የዕብራውያን አቆጣጥርን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን፣ የዕብራውያን የመጀመሪያ ወር ኒሳን ሲሆን ይህም በግሪጎሪያን አቆጣጠር ሚያዢያ ላይ ነው የሚያርፈው፣ ይህን ከተረዳን ዘካርያስ ካህን ሲሆን የክህነት ምድቡ ከአብያ ክፍል እንደሆነና በተራው ሊያጥን እንደነበር እንረዳለን፦
ሉቃስ 1፣5 በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን *ከአብያ ክፍል* የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።
ሉቃስ 1፣9-11 እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት። በዕጣንም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ቆመው ይጸልዩ ነበር። የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።

ዘካሪያስ መልአኩን ገብርኤልን ያገኘው በተሰጠው የአባያ ዕጣ ክፍል እንደሆነ ቅቡል ነው፣ በዕብራውያን በአመት 24 የክህነት ምድብ አለ፣ በአንድ ወር ውስጥ ሁለት ክፍል ሲኖር በአስራ ሁለት ደግሞ 24 ምድብ አለ፣ ይህን ከተረዳን አባያ ከሃያ አራቱ ምድብ ስምንተኛ ነው፣ በየወሩ ሁለት ሁለት ሆነው ከገቡ አባያ አራተኛው ወር ላይ ነው የሚደርሰው፦
1ኛ ዜና መዋዕል 24፥5-19 ሰባተኛው ለአቆስ፥ *ስምንተኛው ለአብያ*፥
የጠቀስኩትን ቁጥር ሙሉውን ያንብቡ።

የመጀመሪያው ወር ኒሳን ማለትም ሚያዥያ ከሆነ አራተኛው ወር ደግሞ ተሙዝ በግሪጎሪያን ሃምሌ ይሆናል፣መልአኩ ወደ ዘካሪያስ የመጣው በሃምሌ ወር ከሆነ ወደ ማርያም ደግሞ የመጣው ከዘካርያስ ጋር ከመጣበት በስድስተኛው ወር ነው፣ ይህም ስድስተኛ ወር ጥር ነው፦
ሉቃስ 1፣26-27 በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ።

እንግዲህ ገብርኤል በጥር ከመጣ ኢየሱስ ጽንሱ የሚጀምረው በጥር ነው፣ ከጥር ወር የጽንሱ ጊዜ 9 ወር ስንቆጥር ጥቅምት ይሆናል፣ ኢየሱስ የተወለደው በጥቅምት ይሆናል ማለት ነው፣ በታህሳስ ወር ነው የሚለው ተረት ምንጭ ኣልባና ሰነድ አልባ ነው፣ ታህሳስ እኮ ለዕብራውያን ብርድ ነው ከቤት አይወጡም፣ ኢየሱስ ሲወለድ ግን የበልግ ወራት ሆኖ እረኞች በሜዳ ያድሩ ነበር፦
ሉቃስ 2፣8 በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።

ሌላው ኢየሱስ ሲወለድ ከአውግስጦስ ቄሣር ቆጠራ ነበር፣ ይህም ቆጥራ በበልግ እንጂ በክረምት አልነበረም ምክንያቱም ኢየሱስ ተወለደ የተባለው በቆጠራው ጊዜ ማርያምና ዮሴፍ እራሳቸው ሊያስቆጥሩ ከናዝሬት ቤተልሄም ሲሄዱ ነው፦
ሉቃስ 2፣5 ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።

ነጥብ ሁለት
“የተወለደበት አመት”
ኢየሱስ የተወረደበት አመት ባይብል የሚያምታታ ሃሳብ ይዞአል፣ ኢየሱስ ተወለደ የተባለው እንደ ሉቃስ አዘጋገብ ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ በወጣበት ከሆነ ይህ የሆነው ደግሞ በ 6 BC ነው፦
ሉቃስ 2፣1-2 በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች። ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ።

ታዲያ ኢየሱስ የተወለደው ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ 6 አመት ነው? ምን አይነት ሂሳብ ነው? አስቡት ኢየሱስ የተወለደው ኢየሱስ ከተወለደ ከ 6 አመት በኋላ፣ ትርጉም ይሰጣልን? በዚህ ስገረም የሚያስደምመው ነገር ከሉቃስ ጋር የሚጋጨው የማቴዎስ ዘገባ ነው፣ እንደ ማቴዎስ ዘገባ ኢየሱስ የተወለደው በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን ነው፦
ማቴዎስ 2፣1 ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

ታሪክ እንደሚነግረን ሄሮድስ የኖረው ከ 74 BC – 4 BC ነው፣ ታዲያ ኢየሱስ መቼ ነው የተወለደው? ብለን ስንጠይቅ የአገራችንን አላቅም የውጪዎቹ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ አንግሊካና ፕሮቴስታንት ሆነ አበይት የሃይማኖት ምሁራን በ 6 BC እንደሆነ ያሰምሩበታል፣ እኔ የምለው ኢየሱስ የተወለደው ኢየሱስ ከመወለዱ ከ 6 አመት በፊት ነው የሚለው አነጋገር እስቲ በአላህ ትርጉም ይሰጣቹሃል ግን? AD*Anno domini* በጌታ ጊዜና BC*before christ* ከክርስቶስ ልደት በፊት የሚለው የኢየሱስ ልደት መሰረት ያረገ አይደለምን? ኢየሱስ የተወለደበት አመት ካልታወቀ ከኢየሱስ ልደት በፊትና በኋላ የሚሉ አነጋገሮች ከየት መጡ?
ነጥብ ሶስት
“የተወለደበት ቀን”
ኢየሱስ ተወለደ የሚባለው በሃገራችን ታህሳስ 29 ሲሆን በግሪጎሪያን አቆጣጠር ደግሞ ታህሳስ 25 ነው፣ ነገር ግን ይህ ልደት ሚጥራ የሚባል የኢራናውያን ጣኦት የተወለደበት ቀን ነው፣ ኢትዮጵያን ሆነ ግሪጎርያን ኢየሱስ የተወለደበት ቀን ቢብሊካል መሰረት የለውም፣ ባይሆን የኢትዮጵያን የሚገርመኝ ገና በ 4 አራት አመት አንዴ ታህሳስ 29 የነበረው ታህሳስ 28 ይሆናል፣ ምክንያቱ ሲባሉ በ 4 አራት አመት አንዴ ጳጉሜ 5 የነበረው 6 ስለሚሆን ነው ይላሉ፣ ስነ-አመክንዮው ያስኬዳል ታዲያ ጥምቀት በአሉ በ 11 የነበረው ለምን በ 10 አልሆነም ከተራ በ 10 የነበረው ለምን በ 9 አልሆነም? ለዚህ መልስ እንፈልጋለን። መደምደሚያችን ምንድን ነው ኢየሱስ የተወለደበት አመት፣ ወር፣ ቀን ቢብሊካል መሰረት ሆነ መረጃ የሌለው ብቻ ሳይሆን ከታሪክ ጋር እጅጉን ይጣረሳል፣ ከዛም ባሻገር ጣኦት የተወለደበትን ቀን እንጂ ኢየሱስ የተወለደበትን ቀን እያከበራችሁ አይደለምና ሞት ሳይቀድማችሁ ያላችሁበትን መንገድ መርምራችሁ ወደ ኢስላም ኑ፦
5:77 *እላንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ”*! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የሆነን ማለፍ ወሰንን አትለፉ፤ በፊትም በእርግጥ *”የተሳሳቱትን እና ብዙዎችን ያሳሳቱትን ከቀጥተኛው መንገድም የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ”*፣ በላቸው قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ غَيْرَ ٱلْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوٓا۟ أَهْوَآءَ قَوْمٍۢ قَدْ ضَلُّوا۟ مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا۟ كَثِيرًۭا وَضَلُّوا۟ عَن سَوَآءِ ٱلسَّبِيلِ ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢየሱስ የት ተወለደ?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

11:120 ከመልክተኞቹም “ወሬዎች” ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ኃያሲ የሆኑ ምሁራን ኂስ መኃየስ ልምዳቸው ነው፤ እኛም ማንኛውም ተግዳሮት በቁርአን ላይ የሚነሳ ኂስ እንማርበታለን እንጂ አናፍርበትም፤ ታዲያ ጠይቆ መረዳት እና ማፍረስ መገርሰስ አስቦ መጠየቅ ይለያያል፤ ከኃያሲያን በተቃራኒው ሚሽነሪዎች የቁርአንን ምጥቀትና ጥልቀት ከመረዳት ይልቅ በምን ጥላሸት እናጠልሸው ብለው ተነስተዋል፤ እኛም ለዚህ መደዴ አካሄድ በቂ መልስ አለን የሚል መጀገኛ ይዘናል።

ወደ ጥላሸቱ ስገባ፦ “የቁርአን ዒሳ እና የባይብሉ ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ማንነቶች ናቸው፤ ከስማቸው ጀምሮ የት እንደተወለዱ ባይብል ሆነ ቁርአን ለየቅል የትየለሌ አድርገው ነው ያስቀመጡት” የሚል እሳቤ አላቸው፤ እኛ ደግሞ የምንለው ከመነሻው ሚዛኑ ትክክል አይደለም የሚል ሙግት አለን፤ ምክንያቱም የቁርአን ተናጋሪ እና ተራኪ የዓለማቱ ጌታ አላህ ነው፤ ከነብያችን”ﷺ” በፊት ያለው የዒሳ ታሪክ “አል-ገይቡል ማዲ” الغيبه المادي ሲሆን ያለፈ ክስተት ነው፤ ይህም ድርጊቱ ከዚህ በፊት አላፊ የሆነ ነገር ነው፤ ከፍጡራን በፊት ያሉትን የሩቅ ወሬዎች አላህ ብቻ ነው በትክክል የሚያውቃቸው፤ አላህ ይህንን የሩቅ ወሬ “ነቁስሱ አለይከ” نَقُصُّ عَلَيْكَ “እንተርክልሃለን” በማለት ለነብያችን”ﷺ” ይናገራል፦
11:120 ከመልክተኞቹም “ወሬዎች” ተፈላጊውን ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን “*እንተርክልሃለን*፤ በዚህችም እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

አላህ ለነብያችን”ﷺ” የሚተርክበት ምክንያት ለምእምናን ግሳጼ እና ማስታወሻ ነው እንጂ እከሌ እከሌን ወለደ ብሎ የሚናገር የቀበሌ አሊያም የእድር መዝገብ አይደለም፤ የባይብል ታሪክ ግን የታሪክ ሰዎች ቃላቸው ከልብ የፈለቀ ነው፦
ኢዮብ 8፥8-10 ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነውና፤ እኛ የትናንት ብቻ ነን፤ ምንም አናውቅም፤ ስለዚህ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፥ አባቶቻቸውም ለመረመሩት ነገር ትጋ፤ እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥ *ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?* እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥

“ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?” የሚለው ይሰመርበት፤ የባይብል ታሪክ ታራኪው አምላክ ሳይሆን ታሪካዊያን የቀደመውን ትውልድ ጠይቀው የዘገቡት ነው፤ የቀደመው ትውልድ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ ደግሞ ቃልንም ከልባቸው አውጥተው እንጂ ከአምላክ ሰምተው አይደለም፤ ሉቃስም ለቴዎፍሎስ የጻፈለት ትረካ ከአምላክ የሰማው ሳይሆን ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እርሱ ደግሞ ለቴዎፍሎስ ሊጽፍለት መልካም ሆኖ ስለታየው የቀደመው ትውልድ ያስተላለፉለትን ነው፦
ሉቃስ 1፥1-4፤ *የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ*።

ስለዚህ የአምላክ ንግግር ከታሪካውያን ትውፊት ቅሪት ጋር ማወዳደር ከመነሻው ስህተት ነው፤ ሲቀጥል ባይብል ላይ እና ቁርኣን ላይ ስለ ኢየሱስ የተገለጸው መረጃ ተለያየ ማለት ኢየሱስ ሁለት ኢየሱስ አያረገውም። እስቲ ይህንን ገለባ ክስ ነጥብ በነጥብ ድባቅ እናስገባው፦
ነጥብ አንድ
“የኢየሱስ ስም”
“ኢየሱስ” የሚለው ስም ፦ በግሪክ “ኤሱስ” Ἰησοῦ በቀዳማይ ዕብራይስጥ “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁעַ ፣ በደሃራይ ዕብራይስጥ “ያሱአ” יֵשׁוּעַ ፣ በአረማይክ “ዔሳዩ” ܝܫܘܥ ፣ በቀዳማይ ዐረቢኛ “ዒሳ” عيسى ፣ በደሃራይ ዐረቢኛ “የሱዐ” يسوع ሲሆን ትርጉሙ “ያህ መድሃኒት ነው” የሚል ፍቺ አለው፤ በተለይ ኢየሱስ ሰዎች ሲጠሩበት የነበረ የሰው ስም መሆኑን ለማሳየት በዕብራይስጥ “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁ֣עַ በግሪክ “ኤሱስ” Ἰησοῦ ተብሎ ለሌሎች ሰዎች አገልግልግሎት ላይ ውሏል፤ ይህንን ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ ኪዳን ማየት ይቻላል።
የግሪክ ሰፕቱጀንት ብሉይ ኪዳን ኢየሱስ የሚለውን ስም “ኤሱስ” Ἰησοῦ ብሎ አቀምጦታል፤ የዕብራይስጡ እደ-ክታባት ደግሞ ያህሹአ יְהוֹשֻׁ֣עַ በሚል አስቀምጦታል፤ የግዕዙ ባይብልም በተመሳሳይ “ኢያሱ” ሳይሆን “ኢየሱስ” እያለ አስቀምጦታል፤ ኢየሱስ የሚለው ስም የፍጡራን ስም መሆኑን የነዌ ልጅ ኢየሱስ፣ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢየሱስ እና የግሪክ አዲስ ኪዳን እደ-ክታባት ኢየሱስ የሚለውን ስም “ኤሱስ” Ἰησοῦ ብሎ አቀምጦታል፤ ይህም የማርያም ልጅ ኢየሱስ፣ የነዌ ልጅ ኢየሱስ፣ ኢዮስጦስ ኢየሱስ ወዘተ።

ስለዚህ የኢየሱስ ስም ስረ-መሰረቱ “ያህሹአ” እንጂ “ኢየሱስ” አሊያም “ዒሳ” አይደለም፤ ለምሳሌ በዕብራይስጥ “ሺን” ש‎ በግሪክ ስለሌለ “ሲግማ” σ ሆኖ “ሸ” የነበረው “ሰ” ተብሎ ሲነበብ በዕብራይስጥ “ያህሹአ” יְהוֹשֻׁעַ የነበረው በግሪክ ኮይኔ “ኤሱስ” Ἰησοῦ ይሆናል፤ አንድ ስም ወደ ሌላ ቋንቋ ሲመጣ የአነባነብ ስልቱ ተቀየረ ማለት ስሙ ተቀየረ ማለት እንዳልሆነ ከቋንቋ ሙግት መረዳት ይቻላል፤ ቀዳማይ ዐረቢኛ የቁርአን ዐረቢኛ ሲሆን ደኃራይ ዐረቢኛ ደግሞ ባይብል የተጻፈበት ዐረቢኛ ነው፤ ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን ሆነ አዲስ ኪዳን ወደ ዐረቢኛ የተተረጎመው ከቁርኣን መውረድ በኃላ በ 867 AD ኮዴክስ ዐረቢከስ ነው። ስለዚህ በቁርአን በቀዳማይ ዐረቢኛ “ዒሳ” عيسى በባይብል በደሃራይ ዐረቢኛ “የሱዐ” يسوع መባሉ አንዳች የትርጉም ልዩነት የለውም። “የሱ” ישו የሚለው የዕብራይስጥ ቃል በዐይን ከመጣ “ዐ” ተብሎ አሊያም በያ ከመጣ “የ” ተብሎ ሊነበብ ይችላል፤ የዕብራይስጡ “ዐይን” ע‎ በዐረቢኛ “ዐ” ተብሎ አሊያም “የ” ተብሎ መነበብ ይችላል።
ነጥብ ሁለት
“የተወለደበት ቦታ”
ሉቃስ ኢየሱስ የተኛበትን ስፍራ በግርግም እንደሆነ ይናገራል፦
ሉቃስ 2፥7-8 የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው *በግርግም* አስተኛችው። በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ *በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ*።

“ግርግም” ማለት የከብት መኖ መመገቢያ አሸንዳ ነው። ይህ በበጋ ወቅት እረኞች በሜዳ መንጋዎችን ለመጠበቅ ውጪ ነበሩ። እዚህ አንቀጽ ላይ “በበረት ተወለደ” የሚል የት አለ? ሲቀጥል በግርግም አስተኛችው እንጂ ወለደችው መቼ ይላል? ኢየሱስ በክረምት አልተወለደም፤ ተወለደ ካሉ እረኞች እንዴት በክረምት ሜዳ ላይ አደሩ? በረት ደግሞ በክረምት መንጋዎች የሚያድሩበት ነው። ግርግም በበጋ መንጋዎች የሚመገቡበት መኖ መመገቢያ አሸንዳ ነው። ከመነሻው ቁርኣን ላይ መርየም ያማጠሽበት ቦታ እንጂ የወለደችበትን ቦታ አይናገርም፦
19፥23 ምጡም ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት፡፡ «ዋ ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ» አለች፡፡ فَأَجَآءَهَا ٱلْمَخَاضُ إِلَىٰ جِذْعِ ٱلنَّخْلَةِ قَالَتْ يَٰلَيْتَنِى مِتُّ قَبْلَ هَٰذَا وَكُنتُ نَسْيًۭا مَّنسِيًّۭا

ስለዚህ የሌለ ነገር እንዳለ አድርጎ እና አስመስሎ ማጋጨት የሥነ-አፈታት ጥናት”Hermeneutics” ያማከለ ሙግት አይደለም፤ የዘንባባ ግንድ አጠገብ ወለደችው እንበል፤ በረት ውስጥ አሊያም በሜዳ ላይ ባለው ግርግም የዘንባባ ግንድ ሊኖር አይችልምን? ዘንባባ ዐረብ አገር ብቻ ሳይሆን እስራኤልም አለ፦
ዘዳግም 34፥3 እስከ ዞዓር ድረስ ያለውንም *የዘንባባ ዛፎች* ያሉባትን ከተማ የኢያሪኮን ሸለቆ ሜዳ አሳየው።
1ኛ ነገሥት 6፥35 የኪሩቤልንና *የዘንባባ ዛፍ* የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸባቸው፤ በተቀረጸውም ሥራ ላይ በወርቅ ለበጣቸው።
ሕዝቅኤል 41፥26 በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ የዓይነ ርግብ መስኮቶችና የተቀረጹ *የዘንባባ ዛፎች* ነበሩበት፤ የመቅደሱም ጓዳዎችና የእንጨቱ መድረክ እንዲሁ ነበሩ።
ዮሐንስ 12፥13 *የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ* ይዘው ሊቀበሉት ወጡና፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው እያሉ ጮኹ።

“ሳያውቁ መናገር ኃላ ለማፈር” ይሉ የለ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
በዚያ በተወለደበት ቀን ሰላም በእርሱ እንደሆነ ሁሉ በሚሞትበት በዚህ ጊዜ ሰላም በእርሱ ላይ ይሆናል፤ ሕያው ኾኖ በሚቀሰቀስበትም በትንሳኤ ቀን ሰላም በእርሱ ላይ ይሆናል፤ በዚያ ቀን ከመምጣቱ በፊት በነበሩት ደረጃውን ዝቅ ባደረኩት አይሁዳውያን እና ደረጃውን ከፍ ባደጉት ክርስቲያኖች ላይ መስካሪ ይኾናል፦ 19፥33 «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ *በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም…
ዒሣ ሞቷልን?

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ *"ያለፉ"* የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَة

ዒሣ በእርግጥ የወረደለትን መልእክት አድርሷል፤ እርሱ ካለፉት መልእክተኞች አንዱ ነው፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ *"ያለፉ"* የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَة

"ያለፉ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ኸለት" خَلَتْ የብዙ ቁጥር ሲሆን ያለፉትን መልእክተኞች ያመለክታል እንጂ የሞቱትን የሚለውን አይዝም፦
3፥144 ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُل

"ያለፉ" የሚለውን ለዒሣ ሞት ይሰራል ካልን "ያለፉ" የሚለው በተመሳሳይ "ለነቢያችን"ﷺ" አገልግሎት ላይ ውሏል፤ ይህ አንቀጽ ሲወርድ ነቢያችን"ﷺ" መቼ ሞቱ? አይ ወደ ፊት ሟት መሆናቸውን ያሳያል ከተባለ ለዒሣም ወደፊት ሟች መሆኑን ያሳያል ብሎ መረዳት ከጉንጭ አልፋ ንትርክ ግልግል ነው። ሙግቱን አስፍተን "ያለፉ" የሆነ ማለት "የሞቱ ነው ካሉ ይህንን አንቀጽ እንዴት ይወጡታል? "አስጠንቃቂ "ያላለፈባት" የለችም" ስለሚል፦
35፥24 እኛ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእውነቱ መምሪያ ላክንህ፡፡ ማንኛይቱም ሕዝብ በውስጧ አስጠንቃቂ *"ያላለፈባት"* የለችም፡፡ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ بِالْحَقِّ بَشِيرًا وَنَذِيرًا ۚ وَإِن مِّنْ أُمَّةٍ إِلَّا خَلَا فِيهَا نَذِيرٌ

"ያላለፈባት" የሚለው ቃል ላይ "ኢላ ሐላ" إِلَّا خَلَا ሲሆን "ሐላ" خَلَا የሚለው ቃል "ኸለት" خَلَتْ ለሚለው ቃል ሥርወ-ቃል ነው። "ማንኛይቱም ሕዝብ በውስጧ አስጠንቃቂ *"ያልሞተባት"* የለችም" ትርጉም ይሰጣልን? በፍጹም አይሰጥም። ቅሉ ግን ዘመነ መግቦታቸው"dispensation" ያለቀ ማለት ነው። በተጨማሪም "ያለፉ" የሚለው በብዙ ቁጥር መልእክተኞችን ለማሳየት ስለገባ "ያለፉ የኾነ መልክተኛ" ማለት "ከመልክተኞቹ አንዱ፥ ከባለሟሎችም አንዱ" ነው ማለት ነው፦
3፥45 መላእክት ያሉትን አስታውስ፡- «መርየም ሆይ! አላህ ከርሱ በኾነው ቃል ስሙ አልመሲሕ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለምና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ *"ከ"ባለሟሎችም በኾነ ያበስርሻል"*፡፡ إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ
36፥3 *"አንተ በእርግጥ "ከ"መልክተኞቹ ነህ"*፡፡ إِنَّكَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ

ከላይ በተዘረዘሩት አናቅጽ ላይ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ "ከአለፉት ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም" የሚል ፍቺ ይኖረዋል።

አሕመዲያህ ቃዲያኒህ ሌላው ዒሣ እንደሞተ ለማሳየት የሚጠቀሙበት አንቀጽ ይህ ነው፦
21፥34 *"ከአንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም"*፡፡ ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን? وَمَا جَعَلْنَا لِبَشَرٍ مِّن قَبْلِكَ الْخُلْدَ ۖ أَفَإِن مِّتَّ فَهُمُ الْخَالِدُونَ

ትክክል! አላህ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት ለነበሩት ለማንም ሰው "ዘላለማዊነትን" ቃል አልገባም፤ ሁሉ ነገር ከአላህ በቀር ሟችና ጠፊ ነው። የመርየምን ልጅ አልመሲሕን እናቱንም በምድር ያለንም ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማንም የለም። በምድር ላይ ያለው ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው፦
5፥17 እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ *የመርየምን ልጅ አልመሲሕን እናቱንም በምድር ያለንም ሁሉ ለማጥፋት ቢሻ ከአላህ ማዳንን የሚችል ማነው?* በላቸው፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ مِنَ اللَّهِ شَيْئًا إِنْ أَرَادَ أَن يُهْلِكَ الْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَأُمَّهُ وَمَن فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا
55፥26 *በእርሷ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ጠፊ ነው*፡፡ كُلُّ مَنْ عَلَيْهَا فَانٍ
28፥88 *ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው*፡፡ وَلَا تَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ ۘ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَيْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُ ۚ لَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
25፥58 በዚያም *በማይሞተው ሕያው አምላክ* ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا
"የማይሞት" አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው። ዒሣም ቢሆን በክፍል አንድ እንዳየነው አልሞተም አልን እንጂ አይሞትም ዘላለማዊ ነው አላልንም፥ ይሞታል። ጅማሬ ያለው ቅዋሜ ማንነት ሞትም ቀማሽ ነው። አላህ ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረገም። "ከአንተ በፊት" ማለት ከአንተ በኃላም አንተም ሁላችሁም ሟች ናችሁ ማለት ነው፤ ሥረ-መሠረቱ ዐፈር የሆነ ፍጡር ወደ ዐፈር ይመለስና ከእርሷም በትንሳኤ ቀን ይቀሰቀሳል፦
3፥185 *ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት*፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ
39፥30 *"አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው"*፡፡ إِنَّكَ مَيِّتٌ وَإِنَّهُم مَّيِّتُونَ
20፥55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን*፡፡ مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ
71፥17 አላህም *ከምድር ማብቀልን አበቀላችሁ*፡፡ وَاللَّهُ أَنبَتَكُم مِّنَ الْأَرْضِ نَبَاتًا
71፥18 ከዚያም *በውስጧ ይመልሳችኋል። ማውጣትንም ያወጣችኋል*፡፡ ثُمَّ يُعِيدُكُمْ فِيهَا وَيُخْرِجُكُمْ إِخْرَاجًا

በዚህ የተፈጥሮ ሂደት ዒሣም መጥቶ ይሞታል በትንሳኤ ቀን ይቀሰቀሳል፦
19፥33 «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ *"በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን"*፡፡» وَالسَّلَامُ عَلَيَّ يَوْمَ وُلِدتُّ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሰላም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥86 *በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ “ሰላምታ” አክብሩ፤ ወይም እርሷኑ መልሷት*። وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا

በፊቅህ ነጥብ ውስጥ “ዓዳህ” የሚባል እሳቤ አለ፤ “ዓዳህ” عادَة ማለት “ወግ” “ባህል” “ልማድ”custom” ማለት ነው፤ ለምሳሌ በአገራችን “ጤና ይስጥልኝ” ወይም “ሰላም” እየተባባልን ሰላምታ እንለዋወጣለን፤ ይህ በኢሥላም ይፈቀዳል። ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒው በባይብል ከእምነት ለሚወጣ ሁሉ እና በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው “በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና” የሚል ትእዛዝ አለ፦
2 ዮሐንስ 1፥9-11 *”ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም*፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት። *ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና*።

ይህ የክርስትና ትእዛዝ ቢሆንም በክርስቲያኖች ላይተገበር ይችላል። እዚህ ድረስ ሰላም በክርስትና በግርድፉ ካየ ዘንዳ ሰላም በኢሥላም ያለው እሳቤ ማየት እንችላለን።
በቁርአን ከተገለጹት የአላህ ስሞች አንዱ “አሥ-ሠላም” السَّلَام ሲሆን ትርጉሙ የሰላም ባለቤት”the source of peace” ማለት ነው፤ ሰላም ከአላህ ዘንድ ነው፦
59፥23 እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ *የሰላም ባለቤቱ*፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኀያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 977
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በሚያሰላምቱ ጊዜ፦ *”አላህ ሆይ! አንተ የሰላም ባለቤት ነህ፤ ሰላም ከአንተ ዘንድ ነው፤ የግርማ እና የክብር ባለቤት ሆይ! ብሩክ ነህ” በማለት እንጂ አይቀመጡ ነበር*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ إِذَا سَلَّمَ لَمْ يَقْعُدْ إِلاَّ مِقْدَارَ مَا يَقُولُ ‏ “‏ اللَّهُمَّ أَنْتَ السَّلاَمُ وَمِنْكَ السَّلاَمُ تَبَارَكْتَ يَا ذَا الْجَلاَلِ وَالإِكْرَامِ

“ሠላም” سَلَٰم የሚለው ቃል “ሠለመ” سَلَّمَ ማለትም “ሰላምታ ሰጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ሰላም” ማለት ነው፤ “አሥ-ሠላም ዐለይኩም” የጀነት ሰላምታ ነው፦
13፥24 «ሰላም ለእናንተ ይኹን፡፡ ይህ ምንዳ በመታገሳችሁ ነው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር ምን ታምር!» ይሏቸዋል፡፡ سَلَامٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ
“ሰላም ለእናንተ ይኹን” ለሚለው ቃል የገባው “ሠላም ዐለይኩም” سَلَامٌ عَلَيْكُم ነው። የአላህን ሰላም አንዱ አማኝ በሌላው አማኝ ላይ እንዲሆን መመኘት የሙስሊም ሰላምታ ነው፤ “ተሥሊም” تَسْلِيم ማለት “ሰላምታ” ማለት ነው፦
4፥61 *ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ፤ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ*፡፡ فَإِذَا دَخَلْتُم بُيُوتًا فَسَلِّمُوا عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ تَحِيَّةً مِّنْ عِندِ اللَّهِ مُبَارَكَةً طَيِّبَة

ሠሊሙ” سَلِّمُوا ማለት “ሰላም በሉ” ማለት ሲሆን ትእዛዛዊ ግስ ነው፤ ይህም ሰላምታ “አሠላሙ አለይኩም” السَّلَامُ عَلَيْكُم ነው፤ ትርጉሙ “የአላህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን” ማለት ነው።
አንድ ሙስሊም መጥቶ “አሠላሙ አለይኩም” ቢለን፥ እርሱ ካለን ይበልጥ ባማረ መልኩ “ወአለይኩም አሥ-ሠላም፣ ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ” السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ  ማለትም “የአላህ ሰላም፣ ምህረት፣ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን” ብለን እንመልሳለን፤ ወይንም እራሷኑ “ወአለይኩም አሥ-ሠላም” وَعَلَيْكُم السَّلَام ብለን እንመልሳለን፦
4፥86 *በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ “ሰላምታ” አክብሩ፤ ወይም እርሷኑ መልሷት*። وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا

“በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ አንድ ሙሥሊም ሙሥሊም ያልሆነን ሰው አሠላሙ አለይኩም አይልም፤ ምክንያቱም ይህ የሙስሊም ሰላምታ ነውና፤ ከዛ ይልቅ እንደ አገሩ ባህል “ጤና ይስጥልኝ” “ሰላም” “እንደምን ዋልክ” ወዘተ.. ማለት ይችላል፤ ነገር ግን ሙስሊም ያልሆነ ሰው አሠላሙ አለይኩም ካለን አላህ፦ “እርሷኑ መልሷት” ስላለ “ወአለይኩም” وَعَلَيْكُمْ ብለን እንመልሳለን፦
አል-አደበል ሙፍረድ መጽሐፍ 44, ሐዲስ 2
አቢ በስረል ጊፋሪይ እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ነገ ወደ አንድ አይሁድ እጓዛለው፤ በመጀመሪያ ሰላም(አሠላሙ አለይኩም) አትበሏቸው፤ አሠላም አለይኩም ቢሏችሁ ግን ወአለይኩም በሉ*። عَنْ أَبِي بَصْرَةَ الْغِفَارِيِّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ إِنِّي رَاكِبٌ غَدًا إِلَى يَهُودَ، فَلاَ تَبْدَأُوهُمْ بِالسَّلاَمِ، فَإِذَا سَلَّمُوا عَلَيْكُمْ فَقُولُوا‏:‏ وَعَلَيْكُمْ‏.‏
አል-አደበል ሙፍረድ መጽሐፍ 44, ሐዲስ 3
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”የመጽሐፉ ሰዎችን ቅድሚያ ሰላም(አሠላሙ አለይኩም) አትበሏቸው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ أَهْلُ الْكِتَابِ لاَ تَبْدَأُوهُمْ بِالسَّلاَمِ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 41
ዐነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም ከመጽሐፉ ሰዎች ሠላም(አሠላሙ አለይኩም) ብሎ ሰላምታ ከሳጣችሁ፥ “ወአለይኩም” በሉ*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِذَا سَلَّمَ عَلَيْكُمْ أَحَدٌ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ فَقُولُوا وَعَلَيْكُمْ‌‏.‏
የአላህ ሰላም የሚገኘው አላህን በኢኽላስ በመታዘዝ ብቻ ነው፤ “ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መታዘዝ” ማለት ነው። “ሠለም” سَلَم ማለት ደግሞ “ታዛዥነት” ማለት ነው።
“ሙሥሊም” مُسْلِم ማለት “ታዛዥ” ማለት ነው፤ አንድ ሙስሊም አላህን በፍጹም ሲታዘዝ የአላህ ሰላም ከእርሱ ጋር ይሆናል፤ ያኔ ውስጡ “ሠሊም” سَلِيم ማለትም “ንፁህ” ይሆናል፤ እርሱም “ሠሊሙን” سَٰلِمُون ማለትም “ሰላማዊ” ይሆናል፤:ፍርሃት እና ሃዘን ይወገዳል፦
2፥112 አይደለም እርሱ በጎ ሠሪ ኾኖ *ፊቱን ለአላህ የሰጠ* ሰው ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳ አለው፡፡ በእነሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡ بَلَىٰ مَنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَلَهُ أَجْرُهُ عِندَ رَبِّهِ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

“ፊት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ወጅህ” وَجْه ሲሆን “ሁለንተና” ማለት ነው፤ “የሰጠ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለመ” أَسْلَمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አምላካችን አላህ እርሱን በመታዘዝ የውስጥ ሰላም ከሚያገኙት ሰላማውያን ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አላህ ያተመው ልብና ጆሮ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥7 *አላህ በልቦቻቸው ላይ እና በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አለ፤ ለእነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው*፡፡ خَتَمَ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَعَلَىٰ سَمْعِهِمْ ۖ وَعَلَىٰ أَبْصَارِهِمْ غِشَاوَةٌ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

ክርስቲያን ፕሪንስ የሚባለው የኢሥላም ቀንደኛ ጠላት በፓልቶክ፦ "እኔን አላህ በልቤ ላይ እና በመስሚያዬ ላይ አትሞብኛል፤ ስለዚህ አላምንም" እያለ ዲስኩሩን ይዶሶክራል። የኢሥላም መልእክት ሰምተክ ሆን ብለክ ካስተባበልክ አዎ አላህ በልብህ ላይ እና በመስሚያህ ላይ ያትምብሃል። እውነትን ከመስማትህና ከማወቅህ በፊት በፍጹም በማንም ላይ አያትምም። ከእውነት በተዘነበልክ ጊዜ አላህ ልብህን አዘነበለብህ፤ አላህም እውነት ከመቀበል ይልቅ ያመጸን አመጸኛ አያቀናም፤ አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ኹኔታ በራሳቸው እስከሚለውጡ ድረስ ሂዳያን በመንሳት አይለውጥም፦
61፥5 *"ከእውነት በተዘነበሉም ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው፡፡ አላህም አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም"*፡፡ فَلَمَّا زَاغُوا أَزَاغَ اللَّهُ قُلُوبَهُمْ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْفَاسِقِينَ
13፥11 *አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ኹኔታ እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም*፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለውም፡፡ ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸውም፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا مَا بِأَنفُسِهِمْ ۗ وَإِذَا أَرَادَ اللَّهُ بِقَوْمٍ سُوءًا فَلَا مَرَدَّ لَهُ ۚ وَمَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَالٍ

"እመኑ" ተብሎ ጥሪ ቀርቦላቸው፣ ስለ እምነት ተነግሯቸው፣ መልክተኛውም እውነት መኾኑን ተመስክሮላቸው፣ የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም፦
4፥170 እናንተ ሰዎች ሆይ! *መልክተኛው እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ፡፡ "እመኑም" ለእናንተ የተሻለ ይኾናል፡፡ ብትክዱም አትጐዱትም*"፡፡ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الرَّسُولُ بِالْحَقِّ مِن رَّبِّكُمْ فَآمِنُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ وَإِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا
3፥86 *ከእምነታቸው እና መልክተኛውም እውነት መኾኑን ከመሰከሩ የተብራሩ አንቀጾችም ከመጡላቸው በኋላ የካዱን ሕዝቦች አላህ እንዴት ያቀናል! አላህ በዳዮችንም ሕዝቦች አያቀናም*፡፡ كَيْفَ يَهْدِي اللَّهُ قَوْمًا كَفَرُوا بَعْدَ إِيمَانِهِمْ وَشَهِدُوا أَنَّ الرَّسُولَ حَقٌّ وَجَاءَهُمُ الْبَيِّنَاتُ ۚ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

እነዚህን ከካዱ በኃላ ብታስጠነቅቃቸውም ባታስጠነቅቃቸውም በእነርሱ ላይ እኩል ነው፤ አያምኑም፦
2፥6 እነዚያ *"የካዱትን" ሰዎች ብታስጠነቅቃቸውም ባታስጠነቅቃቸውም በእነርሱ ላይ እኩል ነው፤ አያምኑም*፡፡ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا سَوَاءٌ عَلَيْهِمْ أَأَنذَرْتَهُمْ أَمْ لَمْ تُنذِرْهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ በብዜት "ከፈሩ" كَفَرُوا ማለት "ካዱ" ማለት ሲሆን በነጠላ “ከፈረ” كَفَرَ ማለት ደግሞ “ካደ” ማለት ነው፤ “ፋ” ف በሸዳ ተሽዲድ ስናረጋት ደግሞ “ከፈረ” كَفَّرَ ሲሆን “ሸፈነ” ማለት ነው፤ “ካፉር” كَافُور ማለት “የተሸፈነ” ማለት ነው፤ ለምሳሌ በጀነት ለበጎ አድራጊዎች መበረዣዋ “ካፉር” ተብላለች። “ካፊር” كَافِر ማለት “ከሃዲ” ማለት ሲሆን "ኩፍር" كُفْر ደግሞ "ክህደት" ማለት ነው፤ አንድ ሰው እውነቱ ተነግሮት ሆን ብሎ ሲያስተባብል ማስተበያው "ኩፍር" ይባላል፤ እርሱም "ካፊር" ይሰኛል፦
2፥7 *አላህ በልቦቻቸው ላይ እና በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፤ በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አለ፤ ለእነሱም ታላቅ ቅጣት አላቸው*፡፡ خَتَمَ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَعَلَىٰ سَمْعِهِمْ ۖ وَعَلَىٰ أَبْصَارِهِمْ غِشَاوَةٌ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ ልብ፣ መስሚያ፣ ዓይን ውሳጣዊ ተፈጥሮን ያመለክታል፤ በካፊሮች "በዓይኖቻቸውም ላይ መሸፈኛ አለ" ይህም መሸፈኛ ኩፍር ነው፤ እነርሱም እውነቱ ተነግሯቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ከዚያም በልብ የካዱ በመኾናቸው አላህ በልቦቻቸው ላይ እና በመስሚያቸውም ላይ አትሞባቸዋል፦
63፥3 ይህ *እነርሱ በምላስ ያመኑ ከዚያም በልብ የካዱ በመኾናቸው* ነው፡፡ *በልቦቻቸውም ላይ ታተመባቸው*፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ ءَامَنُوا۟ ثُمَّ كَفَرُوا۟ فَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَفْقَهُونَ
47፥16 *እነዚህ እነዚያ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተመባቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ናቸው*፡፡ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَٱتَّبَعُوٓا۟ أَهْوَآءَهُمْ
ያተመባቸው ስለ ካዱ እንጂ እንዲክዱ አይደለም። በአላህ አንቀጾች ከተገሰጸና ከእርሷ ከዞረ እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር የረሳ ሰው ይበልጥ በዳይ ነው፤ እንዲህ የሚያደርጉትን አላህ በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሺፋኖችን፥ በጆሮዎቻቸውም ውስጥ ድንቁርናን አደረገባቸው፤ ከእነርሱ አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ልቡን ለኢሥላም ይከፍትለታል። ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት አንደሚታገል ያደርገዋል፦
18፥57 *በጌታውም አንቀጾች ከተገሰጸና ከእርሷ ከዞረ እጆቹም ያስቀደሙትን ነገር ከረሳ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው እኛ በልቦቻቸው ላይ እንዳያውቁት ሺፋኖችን በጆሮዎቻቸውም ውስጥ ድንቁርናን አደረግን፡፡ ወደ መመራትም ብትጠራቸው ያን ጊዜ ፈጽሞ አይመሩም*፡፡ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّن ذُكِّرَ بِآيَاتِ رَبِّهِ فَأَعْرَضَ عَنْهَا وَنَسِيَ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ ۚ إِنَّا جَعَلْنَا عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ أَكِنَّةً أَن يَفْقَهُوهُ وَفِي آذَانِهِمْ وَقْرًا ۖ وَإِن تَدْعُهُمْ إِلَى الْهُدَىٰ فَلَن يَهْتَدُوا إِذًا أَبَدًا
3፥125 *"አላህም ሊመራው የሚሻውን ሰው ልቡን ለኢሥላም ይከፍትለታል፡፡ ሊያጠመውም የሚሻውን ሰው ደረቱን ጠባብ ቸጋራ ወደ ሰማይ ለመውጣት አንደሚታገል ያደርገዋል"*፡፡ እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያምኑት ላይ ርክሰትን ያደርጋል፡፡ فَمَن يُرِدِ اللَّهُ أَن يَهْدِيَهُ يَشْرَحْ صَدْرَهُ لِلْإِسْلَامِ ۖ وَمَن يُرِدْ أَن يُضِلَّهُ يَجْعَلْ صَدْرَهُ ضَيِّقًا حَرَجًا كَأَنَّمَا يَصَّعَّدُ فِي السَّمَاءِ ۚ كَذَٰلِكَ يَجْعَلُ اللَّهُ الرِّجْسَ عَلَى الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ

እዚህ ድረስ ከተግባባን ባይብል ላይ ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ኃይሉ ይገልጥበት ዘንድ እና ስሙ በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ነው፦
ዘጸአት 9፥16 ነገር ግን *ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ*።
ሮሜ 9፥17 መጽሐፍ ፈርዖንን፦ *ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና*።

“ቃሻህ” קָשָׁה ማለት “ማደንደን” ማለት ሲሆን እግዚአብሔር ፈርዖን የእስራኤል ልጆችን እንዳይለቅ እና ሙሴን እንዳይሰማ የፈርዖንን ልብ አደንድኖታል፦
ዘጸአት 7፥3 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ אַקְשֶׁ֖ה * ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ።
ዘጸአት 14፥4 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ וְחִזַּקְתִּ֣י * ፥ እርሱም ያባርራቸዋል፤
ዘጸአት 9፥12 እግዚአብሔርም *የፈርዖንን ልብ አደነደነ וַיְחַזֵּ֤ק *፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም።
ዘጸአት 14፥8 እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ *የፈርዖንን ልብ አደነደነ* וַיְחַזֵּ֣ק ፥

እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ልብን ስላደነደነው የፈርዖን ልብ ደነደነ፦
ዘጸአት 7፥3 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ אַקְשֶׁ֖ה ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ*።
ዘጸአት 14፥4 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ וְחִזַּקְתִּ֣י ፥ እርሱም ያባርራቸዋል*፤
ዘጸአት 9፥12 እግዚአብሔርም *የፈርዖንን ልብ አደነደነ וַיְחַזֵּ֤ק ፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም*።
ዘጸአት 14፥8 እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ *የፈርዖንን ልብ አደነደነ* וַיְחַזֵּ֣ק ፥

እውን ፈርዖን ተጠያቂ ነውን? ልቡንስ እግዚአብሔር ካደነደነው ህዝቤን ልቀቅ ብሎ ሙሴና አሮንን መላክ ለምን አስፈለገ? ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ ብሎ ፈርዖንን መውቀስ ለምንስ አስፈለገ? በዚህ አላበቃም፤ እግዚአብሔር የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን መንፈሱን አደንድኖታል፤ ሰዎች እንዳያምኑ ማለትም በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም እግዚአብሔር ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ፦
ዘዳግም 2፥30 የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ *እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና*፥ ልቡንም አጽንቶታልና።
ዮሐንስ 12፥39 ኢሳይያስ ደግሞ፦ *"በዓይኖቻቸው እንዳያዩ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ እንዳይመለሱም፥ እኔም እንዳልፈውሳቸው፥ ዓይኖቻቸውን አሳወረ ልባቸውንም አደነደነ፡ ብሎአልና ስለዚህ ማመን አቃታቸው"*።

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦
ሮሜ 11፥8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው* ተብሎ ተጽፎአል።
ኢሳይያስ 29፥10 *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል*።

እግዚአብሔር ሰዎችን የጠማምነትን መንፈስ በውስጣቸው በመደባለቅ ያጠማቸዋል፤ እርሱ ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው ይችላል?
ኢሳይያስ 19፥14 *እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል*፤
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ *ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው* ይችላል?

እግዚአብሔር ለጳውሎስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳይታበይ የሥጋው መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመው የሰይጣን መልእክተኛ ሰቶታል፦
2 ቆሮንቶስ 12፥7 ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ *የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ*፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።

ለነገሩ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር የሆነውን ክፉን መንፈስ ይልካል፤ ይህም ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር እተመካከረ ለእግዚአብሔር ያሳስትለታል፤ የሚሳሳተው ሰው እና የሚያሳስተው ክፉ መንፈስ ለእግዚአብሔር ናቸው፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
1ኛ ነገሥት 22 20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ *አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?* አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። *መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ *ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ *ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ*። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ *በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል*፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።
ኢዮብ 12፥16 ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ *የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው*።
እግዚአብሔር፦ "ነቢዩም ቢታለል ያንን ነቢይ ያታለልኩት እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ይለናል፤ ሕዝቅኤልን፣ ኤርሚያስን እና ኢሳይያስን ያታለላቸው እርሱ እንደሆነ እራሳቸው ይናገራሉ፦
ሕዝቅኤል 14፥9 *ነቢዩም ቢታለል ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ ያታለልሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ*፥
ኤርሚያስ 20፥7 አቤቱ፥ *አታለልኸኝ እኔም ተታለልሁ*፥
ኢሳይያስ 63፥17 *አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን "አሳትኸን”?* እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።

ይህንን ጉድ ይዞ ከላይ የቁርኣንን አናቅጽ መተቸት ማለት የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ እንደማለት ነው። አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ፥ ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ረሕማህ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ። እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

40፥7 እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ *«ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነት እና በዕውቀት ከበሃል*"፡፡ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፡፡» እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَيْءٍ رَّحْمَةً وَعِلْمًا فَاغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا وَاتَّبَعُوا سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ الْجَحِيم

“አር-ረሕማን” ٱلرَّحْمَٰنِ ማለትም “እጅግ በጣም ሩኅሩኅ” ማለት ሲሆን “አር-ረሒም” ٱلرَّحِيمِ ማለት ደግሞ “እጅግ በጣም አዛኝ” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ ነው። በቁርአን ውስጥ፦ “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ተሥሚያህ ወይም በሥመላህ 114 ጊዜ ሰፍሯል፤ በእያንዳንዱ ምዕራፍ መግቢያ 113 ጊዜ እና በሱረቱል ነምል መሃል ላይ ደግሞ 1 ጊዜ ይገኛል፦
27፥30 እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም *በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በኾነው*፡፡ إِنَّهُۥ مِن سُلَيْمَٰنَ وَإِنَّهُۥ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ

የአር-ረሕማን ባሕርይ ደግሞ "ረሕማህ" ነው፤ "ረሕማህ" رَّحْمَةً ማለት "እዝነት" ማለት ሲሆን ነገርን ሁሉ ያካበበት የአላህ ባሕርይ ነው፦
40፥7 እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ *«ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነት እና በዕውቀት ከበሃል*"፡፡ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፡፡» እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡ الَّذِينَ يَحْمِلُونَ الْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَيْءٍ رَّحْمَةً وَعِلْمًا فَاغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا وَاتَّبَعُوا سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ الْجَحِيم

እዚህ አንቀፅ ላይ የምንመለከተው "ረሕማህ" ማለትም "እዝነት" እና “ሸይእ” شَىْء ማለትም “ነገር’thing” ሁለት ጉዳዮች መናንቸውን ናቸው፤ “እዝነት” ምንም ነገር ሳይኖር የአላህ ባህርይ ሲሆን “ነገር” ደግሞ “ፍጡር” ነው፤ “ነገር” ጊዜና ቦታ ሁሉ ነው፤ አላህ ሁሉንም ነገር በባሕርያቱ ያካበበ ነው። ታዲያ አላህ የራሱን እዝነት እንዴት ፈጠረው? አላህ የራሱን ባሕርይ ይፈጥራልን? ይህ የሚሽነሪዎች ጥያቄ ነው። ሚሽነሪዎች ሆይ! ጮቤ ረግጣችሁ አንባጒሮ አትፍጠሩ። ተረጋጉ! የጅብ ችኩል አትሁኑ! በሰላና በሰከነ መንፈስ ሐዲሱን ቅድሚያ እንመልከት፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 50, ሐዲስ 21
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ መቶ የእዝነት ክፍሎችን ፈጠረ፤ ከእነርሱም አንዷን ለፍጥረቱ አሰራጨ፤ ከእርሷ የተቀሩትን እራሱ ጋር አደረገ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَلَقَ اللَّهُ مِائَةَ رَحْمَةٍ فَوَضَعَ وَاحِدَةً بَيْنَ خَلْقِهِ وَخَبَأَ عِنْدَهُ مِائَةً إِلاَّ وَاحِدَةً
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 50, ሐዲስ 23
ሠልማን አል-ፋርሢይ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ለአላህ መቶ የእዝነት ክፍሎችን አሉ፤ ከእነርሱም አንዷ በፍጥረቱ መካከል ያለው መተዛዘን ነው፤ የተቀሩትን ዘጠና ዘጠኝ ለትንሳኤ ቀን አዘጋጀ"*። عَنْ سَلْمَانَ الْفَارِسِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ لِلَّهِ مِائَةَ رَحْمَةٍ فَمِنْهَا رَحْمَةٌ بِهَا يَتَرَاحَمُ الْخَلْقُ بَيْنَهُمْ وَتِسْعَةٌ وَتِسْعُونَ لِيَوْمِ الْقِيَامَة

ምን ትፈልጋለህ? ይህ እዝነት ባሕርይ ሳይሆን አላህ ለፍጡራን የለገሳቸው ነገሮች ናቸው። ለምሳሌ ከመቶ አንዲቷ መካከል የሆኑት ነቢያት እራሳቸው እዝነት ናቸው፤ ለምሳሌ ነቢያችን"ﷺ" እና ዒሣ እዝነት ናቸው፦
21፥107 *"ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም"*፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا رَحْمَةً لِّلْعَالَمِينَ
19፥21 አላት «ነገሩ እንደዚህሽ ነው፡፡» ጌታሽ «እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፡፡ ለሰዎችም ታምር ከእኛም *"እዝነት"* ልናደርገው ይህንን ሠራን የተፈረደም ነገር ነው» አለ። قَالَ كَذَٰلِكِ قَالَ رَبُّكِ هُوَ عَلَيَّ هَيِّنٌ ۖ وَلِنَجْعَلَهُ آيَةً لِّلنَّاسِ وَرَحْمَةً مِّنَّا ۚ وَكَانَ أَمْرًا مَّقْضِيًّا

ነቢያችን"ﷺ" እና ዒሣ እዝነት ስለተባሉ ነገርን ሁሉ ያካበበው የአላህ ባሕርይ እዝነት ናቸውን? እረ በፍጹም! የአላህ ባሕርይ የሆነው እዝነት በተባለበት መልክና ልክ እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው። በባል እና በሚስት መካከል ያለው እዝነት፥ ልጆች ለወላጆች ያላቸው እዝነት ከአላህ ዘንድ የሆኑ እዝነቶች ናቸው፦
30፥21 ለእናንተም ከራሳችችሁ ጥንዶችን ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ *"በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው"*፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አሉ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُون
17፥24 *ለሁለቱም ከእዝነትህ የመዋረድን ክንፍ ዝቅ አድርግላቸው*፡፡ «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ በርኅራኄ እንዳሳደጉኝ እዘንልላቸውም» በል፡፡ وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ وَقُل رَّبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا
18፥10 ጎበዞቹ ወደ ዋሻው በተጠጉና «ጌታችን ሆይ! *"ከአንተ ዘንድ እዝነትን ስጠን"*፤ ለእኛም ከነገራችን ቅንን አዘጋጅልን» ባሉ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ أَوَى الْفِتْيَةُ إِلَى الْكَهْفِ فَقَالُوا رَبَّنَا آتِنَا مِن لَّدُنكَ رَحْمَةً وَهَيِّئْ لَنَا مِنْ أَمْرِنَا رَشَدًا