ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አህሉል ሡናህ ወል ጀማዓህ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥92 *"ይህቺ አንዲት ኡማህ ስትሆን በእርግጥ ኡማችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"*፡፡ إِنَّ هَـٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ

የኢሥላም አስኳሉ “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” ነው፤ “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ ማለትም “ከአሏህ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ማለት ነው። ይህ ተህሊል በቁርኣን “ጠንካራ ዘለበት” ይባላል፦
2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ *በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ*፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
31፥22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ *ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ*፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ ۗ وَإِلَى اللَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ

በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ፊቱ ለአላህ የሚሰጥ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨብጧል፤ “ፊት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ወጅህ” وَجْه ሲሆን “ሁለንተና” ማለት ነው፦
3፥20 ቢከራከሩህም፦ *«ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ» በላቸው*፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَن
6፥79 «እኔ ለዚያ ሰማያትንና ምድርን *ለፈጠረው አምላክ ቀጥተኛ ስኾን ፊቴን አዞርኩ*፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» አለ። إِنِّي وَجَّهْتُ وَجْهِيَ لِلَّذِي فَطَرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ حَنِيفًا ۖ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
4፥125 እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ *ፊቱን ለአላህ ከሰጠ* እና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው፡፡ وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا

“ሰጠሁ” ተብሎ የተቀመጠበት ቃል “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ሲሆን “ታዘዝኩ” ማለት ነው፤ “ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” “ተገዛ” ” አመለከ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “መታዘዝ” “መገዛት” “ማምለክ” ማለት ነው፤ አንድ ሁለንተናውን ለአላህ የሰጠ “ሙሥሊም” مُسْلِم ማለትም “አምላኪ” “ተገዢ” “ታዛዥ” ይባላል። ለዛ ነው አምላካችን አላህ፦ "ሙሥሊሞች* ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ" ያለው፦
3፥102 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት፡፡ *እናንተም ሙሥሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ"*። أَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِۦ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ
3፥103 *የአላህንም ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም*። وَٱعْتَصِمُوا۟ بِحَبْلِ ٱللَّهِ جَمِيعًۭا وَلَا تَفَرَّقُوا۟ ۚ

የአላህ ዘለበት “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” ነው፤ ይህንን ዘለበት "ያዙ" ተብለናል፤ ኡማውን የሚያስተሳስር ይህ ዘለበት ነው፤ "አተለያዩ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ከዚህ ኡማ በፊት እንደነበሩት ሃይማኖታቸውን ከለያዩትና ክፍልፍሎችም ከሆኑት አትሁኑ፦
30፥32 *ከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩትና ክፍልፍሎችም ከሆኑት አትሁኑ*፡፡ ሕዝብ ሁሉ እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ተደሳቾች ናቸው፡፡ مِنَ الَّذِينَ فَرَّقُوا دِينَهُمْ وَكَانُوا شِيَعًا ۖ كُلُّ حِزْبٍ بِمَا لَدَيْهِمْ فَرِحُونَ
3፥105 እንደነዚያም ግልጽ ተዓምራት ከመጣላቸው በኋላ *እንደተለያዩትና እንደ ተጨቃጨቁት አትኹኑ፡፡ እነዚያም ለእነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸው*፡፡ وَلَا تَكُونُوا كَالَّذِينَ تَفَرَّقُوا وَاخْتَلَفُوا مِن بَعْدِ مَا جَاءَهُمُ الْبَيِّنَاتُ ۚ وَأُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

"እንደተለያዩትና እንደ ተጨቃጨቁት አትኹኑ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ሆን ብሎ ኡማውን ለመከፋፈል መጨቃጨቅ ታላቅ ቅጣት አለው፤ "እነዚያም ለእነርሱ ታላቅ ቅጣት አላቸው" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ብዙ ጊዜ በኡማው መካከል መጨቃጨቅ እና መከራከር የሚመጣው አላህ እና መልእክተኛው ካለመታዘን ነው፤ አምላካችን አላህ “አትጨቃጨቁ” ብሎናል፤ እርስ በእርስ መጨቃጨቅ ውጤቱ ደግሞ “ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትኼዳለችና” በማለት የጭቅጭቅ ውጤቱ ፍርሃት እና ኃይላችን እንሚሄድና እንደሚቀንስ ነግሮናል፦
8፥46 *አላህን እና መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ አትጨቃጨቁም፡፡ ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትኼዳለችና*፡፡ ታገሱም፤ አላህ ከትዕግስተኞች ጋር ነውና፡፡ وَأَطِيعُوا اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَا تَنَازَعُوا فَتَفْشَلُوا وَتَذْهَبَ رِيحُكُمْ ۖ وَاصْبِرُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን አማኝ የሚያከራክርና የሚያጨቃጭ ነገር ሲኖር ወደ አላህ ቁርኣን እና ወደ መልእክተኛው ሐዲስ ጉዳዩን ይመልሳል፤ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፦
4፥59 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛው እና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا
“ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” የአላህ ዘለበት የያዘችው ይህቺ ኡማህ አንድ ኡማህ ናት፤ አላህም፦ "ይህቺ አንዲት ኡማህ ስትሆን በእርግጥ ኡማችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ፥ ፍሩኝ" ይላል፦
21፥92 *"ይህቺ አንዲት ኡማህ ስትሆን በእርግጥ ኡማችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"*፡፡ إِنَّ هَـٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ
Dr. Laleh Bakhtiar translation፦ Truly, this, your community, is one community and I am your Lord so worship Me.
23፥52 *"ይህቺ አንዲት ኡማህ ስትሆን በእርግጥ ኡማችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ"*፡፡ وَإِنَّ هَـٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاتَّقُونِ
Dr. Laleh Bakhtiar translation፦ And, truly, this, your community is one community and I am your Lord so fear Me.

አምላካችን አላህ ስለዚህ አንድ ኡማህ ሲናገር፦ "በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያመልኩኛል" በማለት ነው፦
24፥55 *"በእኔ ምንንም የማያጋሩ ኾነው ያመልኩኛል፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው"*፡፡ يَعْبُدُونَنِي لَا يُشْرِكُونَ بِي شَيْئًا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ

አላህን በብቸኝነት ከማምለክ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፤ ይህ አንድ ኡማ አንድ ስም አለው፤ እርሱም "ሙሥሊም" የሚል ስም ብቻ ነው፦
41፥33 *ወደ አላህ ከጠራ እና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙሥሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?* وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِين

ጌታችን አላህ፦ "ሙሥሊም ከሚለው ስም ያማረ ስም የለም" እያለን እኛ ማን ነንና ነው ታፔላ እየለጠፍን ያንን የአላህ ለዘበት የያዘውን ሙሥሊም በማይፈልግበት ስም የምንጠራው? “አልቃብ” أَلْقَٰب ማለት “ቅፅል ስም”nickname” ማለት ነው፤ በዚህ ስም መጠራራት ሆነ እርስ በእርሳችን አንዱ ሌላውን ማነወር፣ መንቀፍ፣ መዝለፍ ሃራም ነው፦
49፥11እላንተ ያመናችሁ ሆይ .. *እራሳችሁንም አታነውሩ፤ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ"*። وَلَا تَلْمِزُوا أَنْفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 121
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አንድ ሰው ወንድሙን ካፊር ያለ ቢያንስ ኩፍሩ ወደ ራሱ ይመለሳል"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا كَفَّرَ الرَّجُلُ أَخَاهُ فَقَدْ بَاءَ بِهَا أَحَدُهُمَا

ሙሥሊም ከሚለው ስም ውጪ በሌላ ስም መጠራራት እራሳችንን ማነወር ነው። የአላህ ዘለበት የሆነውን “ላ ኢላሃ ኢለ ሏህ” የጨበጠ ሙሥሊም ወንድምን በዝንባሌ ማክፈር ኩፍሩ ወደ ራስ ይመለሳል።
ታዲያ የሙሥሊም ስም ይዘው ከቁርኣን እና ከሐዲስ ውጪ ወጥተው ከአንዱ ኡማ ውጪ ያሉትን በምን እንለያቸው? በሐዲስ ላይስ የነቢያችን"ﷺ" ኡማህ ሰባ ሦስት ቦታ ተከፍሎ ሰባ ሁለቱ የእሳት ሆኖ ቁርኣን አንድ ኡማህ ያለው የጀነት እንደሆነ ተነግሮ የለምን? ይህ የጀነት የሚሆነው የቱ ነው? በምን እንለየው? ኢንሻላህ ይህንን ነጥብ በክፍል ሁለት እናያለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አህሉል ሡናህ ወል ጀመዓህ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥59 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛው እና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا


"አህሉል ሡናህ ወል ጀማዓህ" أَهْلُ السُنَّة والجماعة‎ ማለት "የሡናህ እና የጀማዓህ ባለቤት"the people of the sunnah and the community" ማለት ነው።
አምላካችን አላህ በቁርኣን አንዲት ኡማህ ያላት የሱና እና የጀማዓህ ባለቤቶችን ነው። "ሡናህ" سُنَّة ማለት "ፈለግ" "ፍኖት" "መንገድ" "ፋና" ማለት ነው፤ የነቢያችን"ﷺ" ፈለግ የተከተለ በግልጽ ማስረጃ ላይ ነው፤ ከዚህ ቀጥተኛ መንገድ ውጪ ያሉት የጥመት መንገዶች ከቀጥተኛው መንገድ አውጥቶ ወደ እሳት የሚከት ነው፦
12፥108 *«ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»* በል፡፡ قُلْ هَـٰذِهِ سَبِيلِي أَدْعُو إِلَى اللَّهِ ۚ عَلَىٰ بَصِيرَةٍ أَنَا وَمَنِ اتَّبَعَنِي ۖ وَسُبْحَانَ اللَّهِ وَمَا أَنَا مِنَ الْمُشْرِكِينَ
6፥153 *«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ፡፡ ከቀጥተኛው መንገድ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ፡፡»* በላቸው وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُون
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ *“አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

“ቢድዓህ” بِدْعَةٍ ማለት ነቢያችን"ﷺ" እና ቀደምት ሠለፎች ያልተገበሩት "ፈጠራ” ማለት ነው፤ ቢድዓህ ማለት የኢቲባዕ ተቃራኒ ነው፤ “ኢቲባዕ” የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ “ተከተለ” ከሚለው የመጣ ሲሆን ቁርኣን እና ሐዲስን ብቻ “መከተል” ማለት ነው። ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው፤ የሡናህ ባለቤት ያልሆነ በቢድዓ ያለ ግለሰብ የእሳት ነው። የነቢያችን"ﷺ" መንሃጅ ቀደምት ሠለፎች የተከተሉት ሡናህ ነው፤ “መንሃጅ” منہاج ማለት "ፈለግ" "ፍኖት" "መንገድ" "ፋና" ማለት ነው፤ ከዚህች መንሃጅ ውጪ ያለ ማንኛውም ቢድዓ የሆነ የጥመት መንገድ የእሳት ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 36
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ .........*"በኒ ኢሥራኢል ለሰባ ሁለት ተከፈለ፥ የእኔ ኡማህ ሰባ ሦስት ቦታ ትከፋፈላለች፥ ሁሉም የእሳት ናቸው አንዲቷ ስትቀር፤ እነርሱም(ሶሓባዎች)፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ያቺ አንዲቷ የቷ ናት? አሉ፤ እርሳቸውም፦ "እኔ እና ሶሓባዎቼ ያለንባት መንገድ ናት"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"........‏ وَإِنَّ بَنِي إِسْرَائِيلَ تَفَرَّقَتْ عَلَى ثِنْتَيْنِ وَسَبْعِينَ مِلَّةً وَتَفْتَرِقُ أُمَّتِي عَلَى ثَلاَثٍ وَسَبْعِينَ مِلَّةً كُلُّهُمْ فِي النَّارِ إِلاَّ مِلَّةً وَاحِدَةً قَالُوا وَمَنْ هِيَ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ مَا أَنَا عَلَيْهِ وَأَصْحَابِي
እንግዲህ አንዲቷ የተባለችው ነቢያችን"ﷺ" እና ሶሓባዎች የነበሩባት ፈለግ ናት፤ ከእርሷ ውጪ ያለ የጥመድ መንገዶች ለእሳት የሚዳርጉ ናቸው። አንድ ሙሥሊም ቆም ብሎ፦ "ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ"ﷺ" መመሪያ ነው፤ ከዚህ ውጪ ሰው ሰራሽ የሆነ ከዝንባሌ የመነጨ ቢድዓህ እየተከተልኩኝ ነውን? ብሎ መጠየቅ አለበት። "ሶሓባህ" صحابة ማለት የነቢያችን"ﷺ" "ባልደረባ"companion" ማለት ሲሆን እነዚህ ባልደረቦች በሁለት ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦ “ሙሃጂር” እና “ነሲር” ናቸው፤ “ሙሃጂር” مُهَاجِر ማለት ደግሞ “ስደተኛ” ማለት ሲሆን ከመካ ወደ መዲና የተሰደዱትን መካውያን ሶሓባዎችን ያመለክታል፤ መዲና ላይ ከመካ የተሰደዱትን እረድተው የተቀበሉ ሶሓባዎች “ነሲር” نَصِير ማለትም “ረዳት” በብዜት “አንሷር” أَنْصَار ይባላሉ፦
8፥74 *እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉ እና የረዱ እነዚያ እነርሱ በእውነት አማኞች ናቸው፡፡ ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَهَاجَرُوا وَجَاهَدُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ وَالَّذِينَ آوَوا وَّنَصَرُوا أُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ
9፥100 *ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነርሱ ወዷል እነርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው*፡፡ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

"እነርሱ በእውነት አማኞች ናቸው" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ከስደተኞቹ እና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነርሱ ወዷል እነርሱም ወደዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 72
ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"ከእናንተ ምርጡ የእኔ ትውልድ ነው፥ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ነው፥ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ናቸው"*። قَالَ سَمِعْتُ عِمْرَانَ بْنَ حُصَيْنٍ، يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم

አላህ በቂርኣን፦ "በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፤ ይህ ታላቅ ዕድል ነው"ሦስቱ ብሎ የመሰከረላቸው እና ነቢያችን"ﷺ" በሐዲስ የመሰከሩላቸው የሶሓባዎች ሁለተኛው እና ሦስተኛው ተከታዮች ምርጡ ትውልድ ናቸው። እነዚህን ትውልድ ማለትም ሶሓባህ፣ ታቢኢይ እና አትባኡ ታቢኢይ አላህ፦ "ቀዳሚዎች" ማለቱን እናስተውል፤ "ሠለፍ" سلف‎ "ቀዳማይ" ማለት ነው። የቀደምት ሠለፎችን መንሃጅ የያዘው "አብላጫውን"majority" መከተል ከስህተት ይታደጋል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 25
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንዳስተላለፈው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"የእኔ ኡማ ከስህተት ጋር አታብርም፤ በኡማው መካከል ሲከፋፈሉ ካያችሁ አብላጫውን ተከተሉ"*። قَالَ سَمِعْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ، يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ "‏ إِنَّ أُمَّتِي لَنْ تَجْتَمِعَ عَلَى ضَلاَلَةٍ فَإِذَا رَأَيْتُمُ اخْتِلاَفًا فَعَلَيْكُمْ بِالسَّوَادِ الأَعْظَمِ ‌‏.‏
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 2
አቢ ዓሚሩል ሀውዘኒ እንደተረከው፦ "ሙዓዊያህ ኢብኑ አቢ ሡፍያን በመካከላችን ቆሞ፦ "ተጠንቀቁ! አለ፤ የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" በመካከላችን ቆመው እንዲህ አሉ፦ "ተጠንቀቁ! አህለል ኪታብ ሰባ ሁለት ቦታ ተከፋፈሉ፤ ይህ ኡማም ሰባ ሦስት ቦታ ይከፋፈላል፥ ሰባ ሁለቱ የእሳት ናቸው፥ አንዲቷ ግን የጀነት ናት፤ እርሷም ጀማዓት ናት"*። عَنْ أَبِي عَامِرٍ الْهَوْزَنِيِّ، عَنْ مُعَاوِيَةَ بْنِ أَبِي سُفْيَانَ، أَنَّهُ قَامَ فِينَا فَقَالَ أَلاَ إِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَامَ فِينَا فَقَالَ ‏"‏ أَلاَ إِنَّ مَنْ قَبْلَكُمْ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ افْتَرَقُوا عَلَى ثِنْتَيْنِ وَسَبْعِينَ مِلَّةً وَإِنَّ هَذِهِ الْمِلَّةَ سَتَفْتَرِقُ عَلَى ثَلاَثٍ وَسَبْعِينَ ثِنْتَانِ وَسَبْعُونَ فِي النَّارِ وَوَاحِدَةٌ فِي الْجَنَّةِ وَهِيَ الْجَمَاعَةُ

ከአይሁድ ፈሪሳውያን፣ ሰዱቃውያን፣ ኤሳውያን፣ መቃቢያን ወዘተ እያሉ ይከፋፈሉ ነበር። ከክርስትና ሰባሊዮሳውያን፣ አሮሳውያን፣ መቅዶኖሳውያን፣ ንስጥሮሳውያን፤ ኢቦናይት፣ ማርኮናይት፣ ኖስቲስ፣ ዳይናሚክ ሞናርኪዝም(ማደጎአውያን) ወዘተ እየተባሉ ይከፋፈሉ ነበር። እንደዚሁ ይህ ኡማህ በመጨረሻው ዘመን ሲከፋፈል አብላጫው እና የቀደምት ሠለፎችን መንሃጅ የያዘችው አንዲቷ ጀማዓህ የጀነት ናት ሌላው የጥመት መንገዶች የእሳት ናቸው። አህሉል ሡናህ ወል ጀማዓህ ማለት በጎጠኝነት የተደራጀ አንጃ ሳይሆን የነቢያችን"ﷺ" የሕይወት ዘይቤ ፈለግ ነው። ይህ መጣጥፍ ግብና ዓላማው ሙሥሊሙ ዝንባሌን ተከትሎ በጭፍን ከመጨቃጨቅ፣ ከመነታረክ፣ ከመዘላለፍ ይልቅ የሚያወዛግብ ነገር ሲኖር ወደ አላህ ቁርኣን እና ወደ መልእክተኛው ሐዲስ ጉዳዩን እንድንመልሰው ነው፤ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፦
4፥59 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛው እና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا
ያኔ አላህ በቁርኣን፦ "ይህቺ አንዲት ኡማ ናት" ነቢያችን"ﷺ" በሐዲስ፦ "አንዲቷ ግን የጀነት ናት" በተባለችውን አህሉሥ ሡናህ ወል ጀመዓህ ውስጥ እራሳችንን እናገኛለን፤ ቀት ያልያዙትን ልጓም እንዲያበጁ እንረዳቸዋለን። ቀምደት ሠለፎች ብዙኃኑ ሙጃሂዶች ነበሩ፤ እንግዲያውስ እውነተኛ ምእምናን በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው፦
49፥15 *ምእምናን እነዚያ በአላህ እና በመልእከተኛው ያመኑት ከዚያም ያልተጠራጠሩት “በገንዘቦቻቸው እና በነፍሶቻቸውም በአላህ መንገድ የታገሉት ብቻ ናቸው”፡፡ እነዚያ እነርሱ እውነተኞቹ ናቸው*፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ الَّذِينَ آمَنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ ثُمَّ لَمْ يَرْتَابُوا وَجَاهَدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الصَّادِقُونَ
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 28
አነሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" አሉ፦ *"በንብረታችሁ፣ በነፍሶቻችሁ እና በአንደበታችሁ ሙሽሪኮችን ታገሉ"*። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏:‏ ‏ "‏ جَاهِدُوا الْمُشْرِكِينَ بِأَمْوَالِكُمْ وَأَنْفُسِكُمْ وَأَلْسِنَتِكُمْ ‏

አምላካችን አላህ በሠለፎች መንሃጅ ከሚከተሉት ሙሥሊሞች ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ተሳላቂዎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥106 ነገሩ ይህ ነው፡፡ በክህደታቸው አንቀጾቼን እና *መልክተኞቼንም መሳለቂያ አድርገው በመያዛቸው ፍዳቸው ገሀነም ነው*፡፡ ذَٰلِكَ جَزَآؤُهُمْ جَهَنَّمُ بِمَا كَفَرُوا۟ وَٱتَّخَذُوٓا۟ ءَايَٰتِى وَرُسُلِى هُزُوًا

መግቢያ
ስለ ነብያችን”ﷺ” የሚነገሩ ታሪኮች በድልብና በግልብ የምንቀባለቸው ሳይሆን ሰሒህ ከሆኑ ሐዲሳት ሪዋያህ መገኘት አለበት፤ የመካከለኛው ምስራቅ ጥንተ-ነገር አጥኚዎች”Orientalists”፣ ምዕራባዊያን ሆኑ ሚሽነሪዎች ከሊቅ እስከ ደቂቅ መውዱዕ ቂሳዎችን ተገን አድርገው ብዥታው አላንዳች ከልካይ እንደ ተዛማጅ በሽታ በዓለማችም ላይ ያዛምታሉ፤ እነዚህ የኢስላም ጥላሸት ቀቢዎች ነብያችንን”ﷺ” “የልጁን ሚስት ቀምቶ አገባ” ወሊአዑዙቢላህ! ብለው ባልተረጋገጠ እና መሬት ባረገጠ የቡና ወሬ ሲሳለቁ መስማት እጅጉን ያማል፤ ይህንን ስላቅ ዛሬ መሳለቃቸው አይገርም፤ ነብያችም”ﷺ” ነብይ ሆነው በተላኩበት ጊዜም የነበሩ ሰዎች የተያየ ስላቅ ይሳለቁ ነበር፤ ለዚህ ሆነ ለማንኛውም ስላቅ አላህ በበቂ ሁኔታ ስለላከው ነብይ በቂ ምላሽ ሰጥቷል፤ ተሳላቂዎች በክህደታቸው አንቀጾቹን እና መልክተኛውንም መሳለቂያ አድርገው በመያዛቸው ፍዳቸው ገሀነም ነው፦
15፥95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡ إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ
18፥106 ነገሩ ይህ ነው፡፡ በክህደታቸው አንቀጾቼን እና *መልክተኞቼንም መሳለቂያ አድርገው በመያዛቸው ፍዳቸው ገሀነም ነው*፡፡ ذَٰلِكَ جَزَآؤُهُمْ جَهَنَّمُ بِمَا كَفَرُوا۟ وَٱتَّخَذُوٓا۟ ءَايَٰتِى وَرُسُلِى هُزُوًا

ታዲያ መሳለቅ ለምን አስፈለገ? ለመሆኑ ይህ አንቀፅ እውን ነብያችን”ﷺ” የልጃቸውን ሚስት ቀምተው አገቡ ይላልን? እስቲ ይህንን አንቀጽ በሰላና በሰከነ ዐቅል እናስተንትነው፦
33፥37 ለእዚያም አላህ በእርሱ ላይ ለለገሰለት እና አንተም ነጻ በማውጣት በእርሱ ላይ ለለገስክለት ሰው አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ፦ *«ሚስትህን በአንተ ዘንድ ያዝ፤ ከመፍታት አላህንም ፍራ»* በምትል ጊዜ አስታውስ፡፡ ዘይድም *ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው ሰዎች ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ በማግባት ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባንህ*፡፡ የአላህም ትእዛዝ ተፈጻሚ ነው፡፡ وَإِذْ تَقُولُ لِلَّذِىٓ أَنْعَمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ وَأَنْعَمْتَ عَلَيْهِ أَمْسِكْ عَلَيْكَ زَوْجَكَ وَٱتَّقِ ٱللَّهَ وَتُخْفِى فِى نَفْسِكَ مَا ٱللَّهُ مُبْدِيهِ وَتَخْشَى ٱلنَّاسَ وَٱللَّهُ أَحَقُّ أَن تَخْشَىٰهُ ۖ فَلَمَّا قَضَىٰ زَيْدٌۭ مِّنْهَا وَطَرًۭا زَوَّجْنَٰكَهَا لِكَىْ لَا يَكُونَ عَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ حَرَجٌۭ فِىٓ أَزْوَٰجِ أَدْعِيَآئِهِمْ إِذَا قَضَوْا۟ مِنْهُنَّ وَطَرًۭا ۚ وَكَانَ أَمْرُ ٱللَّهِ مَفْعُولًۭا
ነጥብ አንድ
“ዘይድ”
ዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህ”ረ.ዐ” አላህ ሂዳያ በመስጠት የለገሰለት እና በነብዩ”ﷺ” ቀዳማይ ባለቤት በከዲጃህ”ረ.ዐ.” አገልጋይ ሆኖ ሳለ ነብያችን”ﷺ” ነጻ በማውጣት በእርሱ ላይ የለገሱለት ሰው ነው፤ ይህ ሰሃባ ነብያችን”ﷺ” ያሳደጉት ልጅ ነው፤ ይህ ሰሃባ ዘይነብ ቢንት ጀሕሽ”ረ.ዐ” የምትባል ባለቤት ነበረችው፤ በመከላቸው በነበረው አለመግባባት ስለ መፍታት ሲናገር ነብያችን”ﷺ”፦ “ሚስትህን በአንተ ዘንድ ያዝ፤ ከመፍታት አላህንም ፍራ” ብለው አሉት፤ የዚህ አንቀጽ ሰበበል ኑዙል ኢማም ቡኻሪይ እንዲህ ዘግቦታል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 97 ሐዲስ 48
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ ዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህ ወደ ነብዩ”ﷺ” መጥቶ ስለ ባለቤቱ ቅሬታ አቀረበ፤ ነብዩ”ﷺ”፦ “ሚስትህን በአንተ ዘንድ ያዝ፤ ከመፍታት አላህንም ፍራ” አሉት፤ ዓኢሻም አለች፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” የደበቁት ማንኛውም ነገር ካለ የደበቁት ይህንን አንቀጽ ነው፤ ዘይነብ በነቢዩ”ﷺ” ባለቤቶች ፊት በኩራት፦ “እናንተን ቤተሰቦቻችሁ ዳርዋችሁ፤ እኔን ግን ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው አላህ ዳረኝ” እያለች ትናገር ነበር፤ ሳቢትም፦ “አላህ ገላጩ የሆነን ነገር በነፍስህ ውስጥ የምትደብቅና አላህ ልትፈራው ይልቅ የተገባው ሲሆን ሰዎችን የምትፈራ ሆነህ” የሚለውን አንቀጽ አነበበ፤ ይህ አንቀጽ የወረደው በዘይነብ እና በዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህ ጉዳይ ነው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ جَاءَ زَيْدُ بْنُ حَارِثَةَ يَشْكُو فَجَعَلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ اتَّقِ اللَّهَ، وَأَمْسِكْ عَلَيْكَ زَوْجَكَ ‏”‌‏.‏ قَالَتْ عَائِشَةُ لَوْ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَاتِمًا شَيْئًا لَكَتَمَ هَذِهِ‏.‏ قَالَ فَكَانَتْ زَيْنَبُ تَفْخَرُ عَلَى أَزْوَاجِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم تَقُولُ زَوَّجَكُنَّ أَهَالِيكُنَّ، وَزَوَّجَنِي اللَّهُ تَعَالَى مِنْ فَوْقِ سَبْعِ سَمَوَاتٍ‏.‏ وَعَنْ ثَابِتٍ ‏{‏وَتُخْفِي فِي نَفْسِكَ مَا اللَّهُ مُبْدِيهِ وَتَخْشَى النَّاسَ‏}‏ نَزَلَتْ فِي شَأْنِ زَيْنَبَ وَزَيْدِ بْنِ

ዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህ ዘይነብ ቢንት ጀሕሽን ያጋቡትም ነብያችን”ﷺ” ናቸው እንጂ ቤተሰቦቿ አይፈልጉም፤ መልክተኛውም የሰጡንን ማንኛውንም ነገር እንይዛለን፤ ከእርሱም የከለከሉንን ነገር እንከለልላለን፤ መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም፤ “ሚስትህን በአንተ ዘንድ ያዝ፤ ከመፍታት አላህንም ፍራ” ማለታቸው ተገቢ ነው፦
33፥36 *አላህና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም*! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡ وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍۢ وَلَا مُؤْمِنَةٍ إِذَا قَضَى ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥٓ أَمْرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ ٱلْخِيَرَةُ مِنْ أَمْرِهِمْ ۗ وَمَن يَعْصِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَٰلًۭا مُّبِينًۭا
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ነጥብ ሁለት
“ዒዳህ”
“ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ” የሚለው ይሰመርበት፤ ይህ የዒዳህ ጊዜ ነው፤ “ዒዳህ” عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው፤ ይህ የተጻፈውም ዒዳህ ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ሌላ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ ሐሳብ ማድረግ ክልክል ነው፦
2፥235 *የተጻፈውም ዒዳህ ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ ሐሳብ አታድርጉ*፡፡ አላህም በነፍሶቻችሁ ያለውን ነገር የሚያውቅ መኾኑን ዕወቁ፤ ተጠንቀቁትም፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ መኾኑን ዕወቁ፡፡ وَلَا تَعْزِمُوا۟ عُقْدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ ٱلْكِتَٰبُ أَجَلَهُۥ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِىٓ أَنفُسِكُمْ فَٱحْذَرُوهُ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌۭ
65፥1 አንተ ነቢዩ ሆይ! *ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቱዋቸው፡፡ ዒዳንም ቁጠሩ፡፡ አላህንም ጌታችሁን ፍሩ*፡፡ ግልጽ የኾነችን ጠያፍ ካልሠሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጡዋቸው፤ አይውጡም፡፡ ይህችም የአላህ ሕግጋት ናት፡፡ *የአላህንም ሕግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ*፡፡ ከዚህ ፍች በኋላ አላህ የመማለስ ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِذَا طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَطَلِّقُوهُنَّ لِعِدَّتِهِنَّ وَأَحْصُوا۟ ٱلْعِدَّةَ ۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ رَبَّكُمْ ۖ لَا تُخْرِجُوهُنَّ مِنۢ بُيُوتِهِنَّ وَلَا يَخْرُجْنَ إِلَّآ أَن يَأْتِينَ بِفَٰحِشَةٍۢ مُّبَيِّنَةٍۢ ۚ وَتِلْكَ حُدُودُ ٱللَّهِ ۚ وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ ٱللَّهِ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُۥ ۚ لَا تَدْرِى لَعَلَّ ٱللَّهَ يُحْدِثُ بَعْدَ ذَٰلِكَ أَمْرًۭا
65፥4 እነዚያም ከሴቶቻቸው ከአደፍ ያቋረጡት ብትጠራጠሩ *ዒዳቸው ሦስት ወር ነው*፡፡ وَٱلَّٰٓـِٔى يَئِسْنَ مِنَ ٱلْمَحِيضِ مِن نِّسَآئِكُمْ إِنِ ٱرْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَٰثَةُ أَشْهُرٍۢ

ዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህ ከባለቤቱ ከዘይነብ ቢንት ጀሕሽ ይህንን የዒዳህ ጊዜ ሲያልቅ ተፋቷል፤ በዚህ ጊዜ በዐረቦቹ ባህል ያሳደጉትን ልጅ ሚስት ከተፋታ በኃላ ማግባት ነውር ነው ብለው ስለሚያስቡ ነብያችን”ﷺ” እየወደዷት ማህበረሰቡ ምን ይለኛል በሚል ሲፈሩ አላህ በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው ሰዎች ሚስቶች ከእነርሱ የዒዳቸውን ጊዜ በፈጸሙ ጊዜ በማግባት ችግር እንዳይኖርባቸው ነብያችንን”ﷺ” ከዘይነብ ቢንት ጀሕሽ ጋር ወሊይ በመሆን አጋባ፤ ለዛ ነው አላህ፦ “በምእምናኖች ላይ ልጅ አድርገው ባስጠጉዋቸው ሰዎች ሚስቶች ከእነርሱ ጉዳይን በፈጸሙ ጊዜ በማግባት ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባንህ” ያለው፤ እርሷም፦ “እናንተን ቤተሰቦቻችሁ ዳርዋችሁ፤ እኔን ግን ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው አላህ ዳረኝ” ያለችው።
ነጥብ ሶስት
“ማደጎ”
አላህ አንድ ሰው የልጁን ሚስት ማግባት ሃራም እንደሆነ ሲናገር፦ “የእነዚያ ከጀርባዎቻችሁ የኾኑት ወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችም እርም ነው” ብሏል፦
4፥23 *የእነዚያ ከጀርባዎቻችሁ የኾኑት ወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችም*፣ በሁለት እኅትማማቾችም መካከል መሰብሰብ እንደዚሁ *እርም ነው*፡፡ ግን ከዚህ በፊት ያለፈው ሲቀር እርሱንስ ተምራችኋል፤ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ وَحَلَٰٓئِلُ أَبْنَآئِكُمُ ٱلَّذِينَ مِنْ أَصْلَٰبِكُمْ وَأَن تَجْمَعُوا۟ بَيْنَ ٱلْأُخْتَيْنِ إِلَّا مَا قَدْ سَلَفَ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ غَفُورًۭا رَّحِيمًۭا

ነብያችን”ﷺ” ዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህን በእድሜ የሚበልጡት በአራት አመት ብቻ ነው፤ ልጅ ሊሆን አይችልም። አላህ በተከበረ ቃሉ የማደጎ ልጅ ከአብራክ እንደሚገኘው ልጅ አድርጎ አላደረገም፤ በአሳዳጊው ስም አባትነት መጠራትም ክልክል ነው፤ በወለዷቸው አባቶች ስም መጥራት ወይም ወላጆቿቸው ካልታወቁ የሃይማኖት ወንድምና ዘመድ ናቸው፦
33፥4 *ልጅ በማድረግ የምታስጠጓቸውንም ልጆቻችሁ አላደረገም፡፡ ይህ በአፎቻችሁ የምትሉት ነው*፡፡ አላህም እውነቱን ይናገራል፡፡ እርሱም ትክክለኛውን መንገድ ይመራል፡፡ وَمَا جَعَلَ أَدْعِيَآءَكُمْ أَبْنَآءَكُمْ ۚ ذَٰلِكُمْ قَوْلُكُم بِأَفْوَٰهِكُمْ ۖ وَٱللَّهُ يَقُولُ ٱلْحَقَّ وَهُوَ يَهْدِى ٱلسَّبِيلَ
33፥5 *ለአባቶቻቸው በማስጠጋት ጥሯቸው፡፡ እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛ ነው፤ አባቶቻቸውንም ባታውቁ በሃይማኖት ወንድሞቻችሁ እና ዘመዶቻችሁ ናቸው*፡፡ በእርሱ በተሳሳታችሁበት ነገርም በእናንተ ላይ ኀጢአት የለባችሁም፡፡ ግን ልቦቻችሁ ዐውቀው በሠሩት ኀጢአት አለባችሁ፤ አላህም መሃሪ አዛኝ ነው። ٱدْعُوهُمْ لِـَٔابَآئِهِمْ هُوَ أَقْسَطُ عِندَ ٱللَّهِ ۚ فَإِن لَّمْ تَعْلَمُوٓا۟ ءَابَآءَهُمْ فَإِخْوَٰنُكُمْ فِى ٱلدِّينِ وَمَوَٰلِيكُمْ ۚ وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌۭ فِيمَآ أَخْطَأْتُم بِهِۦ وَلَٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًۭا رَّحِيمًا

አላህ “ዘይድም ከእርሷ የዒዳህ ጊዜዋ ባለቀ ጊዜ በምእምናኖች ላይ የሚያሳድጓቸው ልጆች ሚስቶች ከእነርሱ ዒዳችቸውን በፈጸሙ ጊዜ በማግባት ችግር እንዳይኖርባቸው እርሷን አጋባቸው” ነብያችን”ﷺ” ከወንዶች የአንድም ሰው አባት አይደሉም። ነገር ግን የአላህ መልክተኛና የነቢያት መደምደሚያ ናቸው፦
33፥40 *ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢዮች መደምደሚያ ነው*፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَآ أَحَدٍۢ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَٰكِن رَّسُولَ ٱللَّهِ وَخَاتَمَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ ۗ وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمًۭا

መደምደሚያ
ችግሩ ምንድን ነው? የተፈታች ሴት አታግቡ ነው እንዴ? ከመነሻው ዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህ በነብዩ”ﷺ” ቀዳማይ ባለቤት ባርያ ሆኖ ሳለ ነብያችን”ﷺ” ነጻ በማውጣት በእርሱ ላይ የለገሱለት ሰው እንጂ መቼስ ልጃቸው ነውና? ሲቀጥል የዒዳህ ጊዜያቸውን ጨርሰው ተፋተው የለ እንዴ? ወይስ በራሳችሁ ባይብይ እግዚአብሔር ለገዛ ነብዩ የሰው ሚስቶች ስለሰጠው አለማንበባችሁ ነው? እግዚአብሔር ለነብዩ ዳዊት የጌታውን የሳዖልን ሚስቶች በብብቱ ሰጥቶታል፤ በሰፈሩት ቁና መሰፈር”double standard” ይሉሃል እንደዚህ ነው፦
2ኛ ሳሙኤል 12፥8 የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ *የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ*፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።

ነብዩ ዳዊት ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ ገሎ ሚስቱንም ለራሱ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስዷል፦
2ኛ ሳሙኤል 12፥9 አሁንስ በፊቱ ክፉ ትሠራ ዘንድ የእግዚአብሔርን ነገር ለምን አቃለልህ ኬጢያዊውን *ኦርዮን በሰይፍ መትተሃል፥ ሚስቱንም ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃል*፤ እርሱንም በአሞን ልጆች ሰይፍ ገድለሃል።

በጣም የሚያሳዝነው እርሱ ባጠፋው ጥፋት ሚስቶቹ በዓይኑ ፊት ተወስደዋል፤ ከቤርሳቤህ የተወለድ ህጻን ያለ ወንጀሉ እንዲቀሰፍ ተደርጓል፦
2ኛ ሳሙኤል 12፥11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ *ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ*፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።
2ኛ ሳሙኤል 12፥14-15 ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች ታላቅ የስድብ ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ *የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል* አለው። ናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ። እግዚአብሔርም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችውን ሕፃን ቀሠፈ፥ እጅግም ታምሞ ነበር።

ያልተጠረጠረ ተመነጠረ፤ የተጠረጠረ አስመነጠረ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሥነ-ልቦና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

17፥85 ከሩሕም ይጠይቁሃል፡፡ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِ ۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّى وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًۭا

የሥነ-ልቦና ጥናት”Psychology” ጥናቱን ያደረገው በልብ ላይ ነው፤ “ሳይኮ” ψυχή ማለት “መንፈስ” “ነፍስ” “ልብ” “ህሊና” “አእምሮ” ማለት ነው፤ “ሎጂአ” λογία ደግሞ “ጥናት” ማለት ነው፤ የሰው መንፈስ ማዕከሉ “ልብ” ነው፤ እስቲ ስለ “ልብ”፣ ስለ እንቅልፍ ዓለም፣ ስለ የሞት ጊዜ እና በሞትና በትንሳኤ መካከል ስላለው ቆይታ አላህ በሰጠን ጥቂት ዕውቀት እናስተንትን፦

ነጥብ አንድ
“ልብ”
“ልብ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ቀልብ” قَلْب “ፉዓድ” فُؤَاد እና “ሰድር” صَدْر ሲሆን የውስጥን ማንነት ለማሳወቅ የመጣ ቃል ነው፤ ሰዎች ውሳጣዊ ተፈጥሮን “ቆሌ” “ቆሽት” “አንጀት” “ናላ” ብለው በእማራዊ ቃላት ፍካሬአዊ ልብን ይገልጡታል፤ “ሕሊና” የሚለው ቃል “ሐለየ” ማለትም “አሰበ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማሰቢያ” ማለት ነው፤ “ልብ” የሚለው ቃል “ለበወ” ማለትም “አመዛዘነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመዛዘኛ” ማለት ነው፤ “አእምሮ” የሚለው ቃል “አእመረ” ማለትም “ዐወቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማወቂያ” ማለት ነው፤ ልብ የኢማን መቀመጫ፣ በዚክር የሚረጥብ፣ በአላህ ንግግር የሚረጋጋ እና በአምልኮ የሚሰፋ ውስጣዊ ማንነት ነው፤ እነዚህ ከቃሉ መረዳት ይቻላል፦
“ቀልብ”
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ እርሱ ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ *”በልብህ” ላይ አውርዶታልና፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّۭا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُۥ نَزَّلَهُۥ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ ٱللَّهِ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًۭى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
26፥194 ከአስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ *”በልብህ”* ላይ አወረደው፡፡ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ ٱلْمُنذِرِينَ
13፥28 እነርሱም እነዚያ ያመኑ *”ልቦቻቸውም”* አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት *”ልቦች”* ይረካሉ፡፡ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ ٱللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ ٱللَّهِ تَطْمَئِنُّ ٱلْقُلُوبُ

“ፉዓድ”
11፥120 ከመልክተኞቹም ዜናዎች ተፈላጊውን ሁሉንም *”ልብህን”* በእርሱ የምናረካበትን እንተርክልሃለን፡፡ በዚህችም ሱራ እውነቱ ነገር ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሃል፡፡ وَكُلًّۭا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنۢبَآءِ ٱلرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۚ وَجَآءَكَ فِى هَٰذِهِ ٱلْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌۭ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
25፥32 እነዚያ የካዱትም «ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ እንደዚሁ በእርሱ *”ልብህን”* ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፡፡ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው፡፡ وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ ٱلْقُرْءَانُ جُمْلَةًۭ وَٰحِدَةًۭ ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِۦ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَٰهُ تَرْتِيلًۭا

“ሰድር”
94፥1*”ልብህን”* ለአንተ አላሰፋንልህምን? أَلَمْ نَشْرَحْ لَكَ صَدْرَكَ
20፥25 (ሙሳም) አለ «ጌታዬ ሆይ! “ልቤን” አስፋልኝ፡፡ قَالَ رَبِّ ٱشْرَحْ لِى صَدْرِى
39፥22 አላህ *”ደረቱን”* ለእስልምና ያስፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የኾነ ሰው ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን? *”ልቦቻቸውም”* ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወዮላቸው፡፡ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው፡፡ أَفَمَن شَرَحَ ٱللَّهُ صَدْرَهُۥ لِلْإِسْلَٰمِ فَهُوَ عَلَىٰ نُورٍۢ مِّن رَّبِّهِۦ ۚ فَوَيْلٌۭ لِّلْقَٰسِيَةِ قُلُوبُهُم مِّن ذِكْرِ ٱللَّهِ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ فِى ضَلَٰلٍۢ مُّبِينٍ
ነጥብ ሁለት
“የእንቅልፍ ዓለም”
ሰው ውጫዊው ማንነቱ አካሉ ሲሆን ይህ አካል “እረፍት” ያስፈልገዋል፦
25፥47 እርሱም ያ ለእናንተ ሌሊትን ልብስ እንቅልፍንም “ማረፊያ” ያደረገ፤ ቀንንም መበተኛ ያደረገላችሁ ነው፡፡ وَهُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا وَٱلنَّوْمَ سُبَاتًۭا وَجَعَلَ ٱلنَّهَارَ نُشُورًۭا
40፥61 አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ “ልታርፉበት”፤ ቀንንም ልትሠሩበት የሚያሳይ ያደረገላችሁ ነው፡፡ ٱللَّهُ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِتَسْكُنُوا۟ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبْصِرًا
10፥67 እርሱ ያ *”ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት”*፤ ቀንንም ልትሠሩበት ብርሃን ያደረገላችሁ ነው፡፡ *”በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ”*፡፡ هُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِتَسْكُنُوا۟ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَٰتٍۢ لِّقَوْمٍۢ يَسْمَعُونَ

አላህ ሌሊትን በውስጡ እንቅልፍን ማረፊያ ማድረጉ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ታምራቶች አሉ፤ ከታምራቶች አንዱ የሰው አካል እረፍት ሲያደርግ ነገር ግን የሰው መንፈስ ያለ ዓይን ታያለች፣ ያለ ጆሮ ትሰማለች፣ ያለ እግር ትሄዳለች፣ ያለ አፍ ትናገራለች፤ ምክንያቱም አላህ ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፦
39፥42 አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ *”ይወስዳል”*፡፡ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

የእንቅልፍ ዓለም መንፈሳችን ከአካላችን ጋር እንዴት እንደምትለያይ ልምምድ ላይ ናት፤ አላህ መንፈሳችንን በሞታችን ጊዜ ይወስዳታል፤ “ይወስዳል” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፈ” يَتَوَفَّى ሲሆን ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ ደግሞ በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል፤ በሌላ አንቀፅ ላይ “የሚያስተኛችሁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ሲሆን “የተወፍፈ” ሆነ “የተወፍፋኩም” የረባበት ቃል “ተወፍፋ” تَوَفَّىٰ “ወሰደ” “አስተኛ” ነው፤ አላህ ሩሐችንን በሌሊት በእንቅልፍ ጊዜ እንደሚወስድ እና አካላችንን እንደሚያስተኛ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
6፥60 እርሱም ያ በሌሊት *”የሚያስተኛችሁ”* በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ *”የሚቀሰቅሳችሁ”* ነው፡፡ ከዚያም *”መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው”*፡፡ ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ وَهُوَ ٱلَّذِى يَتَوَفَّىٰكُم بِٱلَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِٱلنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰٓ أَجَلٌۭ مُّسَمًّۭى ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

ነጥብ ሶስት
“የሞት ጊዜ”
በሌሎች አናቅፅ ላይ አላህ መልአከ ሞትን ልኮ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ “ይወስዳችኃል” ይላል፤ አሁንም “ይወስዳችኃል” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ነው፦
32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት *”ይወስዳችኃል”*፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ
7፥37 የሞት መልክተኞቻችንም *”የሚወስዷቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ”* «ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው የነበራችሁት የት አሉ» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፡፡ እነርሱም ከሃዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ፡፡ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوٓا۟ أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ ۖ قَالُوا۟ ضَلُّوا۟ عَنَّا وَشَهِدُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰفِرِين
16፥70 አላህም ፈጠራችሁ፤ ከዚያም “ይወስዳችኃል”፡፡ ከእናንተም ከዕወቅት በኋላ ምንንም ነገር እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፡፡ አላህ ዐዋቂ ቻይ ነው፡፡ وَٱللَّهُ خَلَقَكُمْ ثُمَّ يَتَوَفَّىٰكُمْ ۚ وَمِنكُم مَّن يُرَدُّ إِلَىٰٓ أَرْذَلِ ٱلْعُمُرِ لِكَىْ لَا يَعْلَمَ بَعْدَ عِلْمٍۢ شَيْـًٔا ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌۭ قَدِيرٌۭ

ስለዚህ “እንቅፍ” ማለት “ሞት” ማለት ነው፤ በእንቅልፍ ጊዜ ሩሓችንን በመውሰድ የሚያሞተን አላህ ነው፤ በሞትም ጊዜ አላህ መልአከ ሞትን ልኮ ነፍሶችን ያሞታል፤ “ማሞት” ግን የአላህ ስልጣን ብቻ ነው፦
2፥28 ሙታን የነበራችሁ ስትኾኑ ሕያው ያደረጋችሁ ከዚያም *”የሚገድላችሁ”* ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ሲኾን ከዚያም ወደ እርሱ የምትመለሱ ስትኾኑ በአላህ እንዴት ትክዳለችሁ! كَيْفَ تَكْفُرُونَ بِٱللَّهِ وَكُنتُمْ أَمْوَٰتًۭا فَأَحْيَٰكُمْ ۖ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

“የሚገድላችሁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዩሚቱኩም” يُمِيتُكُمْ ሲሆን “የሚያሞት” ማለት ነው፤ የሚያሞትም አንዱ አምላክ ብቻ ነው፦
15፥23 እኛም ሕያው የምናደርግ እና *”የምንገድል”* እኛው *”ብቻ”* ነን፡፡ እኛም ፍጡርን ሁሉ የምንወርስ ቀሪ ነን፡፡ وَإِنَّا لَنَحْنُ نُحْىِۦ وَنُمِيتُ وَنَحْنُ ٱلْوَٰرِثُونَ
9፥116 አላህ የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሕያው ያደርጋል፤ *”ይገድላልም”*፡፡ ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ لَهُۥ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ ۚ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّۢ وَلَا نَصِيرٍۢ
10፥56 እርሱ ሕያው ያደርጋል፤ *”ይገድላልም”* ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ هُوَ يُحْىِۦ وَيُمِيتُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ
ነጥብ አራት
“በርዘኽ”
“በርዘኽ” برزخ ማለት የቃሉ ትርጉም “ጋራጅ” ማለት ሲሆን “መለያ” እና “መቆያ” ነው፤ አላህ ሩሕን በሞት ጊዜ ይወስዳል፣ በእንቅልፍ ጊዜ የምንወሰደው ነገር ማለትም ያለ አይን ማየቱ፣ ያለ ጆሮ መስማቱ፣ ያለ እግር መሄዱ፣ ያለ አፍ መናገሩ ሩህ ከሞት በኋላ ያለውን ሁኔታ በጥቂቱ የምናይበት ነው፣ ምነው እንቅልፍ የሞት ታናሽ ወንድም ይባል የለ አይደል? ሩሕ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ በበርዘክ ይቆያሉ፣ “በርዘኽ” በሞትና በትንሳኤ መካከል ያለ ሁኔታ”Intermediate zone” ነው፦
23:99-100 አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ፡፡ በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» ይህን ከማለት ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት፡፡ *”ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ “ግርዶ” አለ”*፡፡ لَعَلِّىٓ أَعْمَلُ صَٰلِحًۭا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّآ ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَآئِلُهَا ۖ وَمِن وَرَآئِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

የሁሉም ሩሕ ወደ አላህ ቢመለስም ነገር ግን የሙስሉምና የካፊር ሩሕ እንዳይገናኙ በመካከላቸው “በርዘኽ” አለ፤ የበርዘኽ ምሳሌ ምንድን ነው? የበርዘኽ ምሳሌ በባህር ውስጥ በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል ግርዶ መኖሩን ምሳሌ ይጠቀማል፦
55:19-20 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲሆኑ ለቀቃቸው። *”እንዳይዋሐዱ በመካከላቸው “ጋራጅ” አለ፤ አንዱ ባንዱ ላይ ወሰን አያልፍም”*፤ بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌۭ لَّا يَبْغِيَانِ
25:53 እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች፣ አጐራብቶ የለቀቀ ነው፤ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፤ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፤ *”በመካከላቸውም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን “ክልል” ያደረገ ነው”*። وَهُوَ ٱلَّذِى مَرَجَ ٱلْبَحْرَيْنِ هَٰذَا عَذْبٌۭ فُرَاتٌۭ وَهَٰذَا مِلْحٌ أُجَاجٌۭ وَجَعَلَ بَيْنَهُمَا بَرْزَخًۭا وَحِجْرًۭا مَّحْجُورًۭا
27:61 *”በሁለቱ ባሕሮችም በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል ግርዶን ያደረገ”* ይበልጣልን? ወስ የሚያጋሩት? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም። أَمَّن جَعَلَ ٱلْأَرْضَ قَرَارًۭا وَجَعَلَ خِلَٰلَهَآ أَنْهَٰرًۭا وَجَعَلَ لَهَا رَوَٰسِىَ وَجَعَلَ بَيْنَ ٱلْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

ስለ ውስጥ ተፈጥሮ የምናስተነትንበት ትምህርት “አት-ተሰዉፍ” الْتَّصَوُّف‎ ይባላል፤ የሚያስተነትነው ሰው “ሙተሰዉፍ” مُتَصَوُّف‎ ይባላል። “ሩሕ” ከጌታችን ነገር ናት፤ ስለ “ሩሕ” የተሰጠን ዕውቀት ጥቂት ብቻ ነው፦
17፥85 ከሩሕም ይጠይቁሃል፡፡ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِ ۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّى وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በመጽሐፉ እመኑ!

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው በዚያም *በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي أَنزَلَ مِن قَبْلُ ۚ

ከኢማን መሰረቶች አንዱ በአላህ መጽሐፍት ማመን ነው፤ “ኪታብ” كِتَٰب የሚለው ቃል “ከተበ” كَتَبَ ማለትም “ጻፈ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መጽሐፍ” ማለት ነው፤ “ከተበ” كَتَبَ ደግሞ “ቃለ” قَالَ ማለትም “አለ” ወይም “ከለመ” كَلَّمَ ማለትም “ተናገረ” በሚል ይመጣል፦
2፥178 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተገደሉ ሰዎች ማመሳሰል *በእናንተ ላይ ተጻፈ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الْقِصَاصُ فِي الْقَتْلَى
2፥180 አንዳችሁን ሞት በመጣበት ጊዜ ሀብትን ቢተው ለወላጆችና ለቅርብ ዘመዶች በበጎ መናዘዝ *በእናንተ ላይ ተጻፈ*፡፡ كُتِبَ عَلَيْكُمْ إِذَا حَضَرَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ إِن تَرَكَ خَيْرًا الْوَصِيَّةُ لِلْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ بِالْمَعْرُوفِ
2፥216 መጋደል እርሱ ለእናንተ የተጠላ ሲሆን *በእናንተ ላይ ተጻፈ*፡፡ كُتِبَ عَلَيْكُمُ الْقِتَالُ وَهُوَ كُرْهٌ لَّكُمْ
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ *ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ* ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

“በእናንተ ላይ ተጻፈ” ማለት “በእናንተ ላይ ተነገረ ወይም ተባለ አሊያም ተደነገገ” ማለት ነው፤ “ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ” የሚለው ይሰመርበት፤ “ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ” ማለት “ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተነገረ ወይም ተባለ አሊያም ተደነገገ” ማለት ነው፤ አላህ በቀድሞ ንግግሩ፦ “እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው”፣ “ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፤ ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው” እና “ምድንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል” ማለትን ብሏል፦
5፥32 በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ፦ “እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው” ማለትን *ጻፍን*፡፡ مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا
5፥45 በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ “ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፤ ቁስሎችንም ማመሳሰል አለባቸው” ማለትን *ጻፍን*፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌ
21፥105 ምድንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል ማለትን ከመገሰጫው በኋላ በዘቡር በእርግጥ *ጽፈናል*፡፡ وَلَقَدْ كَتَبْنَا فِي الزَّبُورِ مِن بَعْدِ الذِّكْرِ أَنَّ الْأَرْضَ يَرِثُهَا عِبَادِيَ الصَّالِحُونَ

ስለ ኪታብ እሳቤ ይህንን ከተረዳን አምላካችን አላህ ወደ ነብይ መጽሐፍ አወረደ ማለት የራሱን ንግግር ተናገረ ማለት ነው፦
3፥79 *ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍን እና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠው* እና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፡፡ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِّي مِن دُونِ اللَّهِ وَلَـٰكِن كُونُوا رَبَّانِيِّينَ بِمَا كُنتُمْ تُعَلِّمُونَ الْكِتَابَ وَبِمَا كُنتُمْ تَدْرُسُونَ
ነጥብ አንድ
“የቀድሞቹ መጽሐፍት”
“ወሕይ” وَحْى የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ “ገለጠ” ወይም “አወረደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት”Revelation” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ወደ ነብያት ወሕይ አውርዷል፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ *መጽሐፍትን እና ሚዛንን ወደ እነርሱ አወረድን*፤ لَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلَنَا بِالْبَيِّنَاتِ وَأَنزَلْنَا مَعَهُمُ الْكِتَابَ وَالْمِيزَانَ لِيَقُومَ النَّاسُ بِالْقِسْطِ
4፥163 እኛ *ወደ ኑሕና ከእርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا

“አወረድን” ተብሎ የተቀመጠው “አውሐይና” أَوْحَيْنَا ሲሆን የሚያወርደው ወሕይ ኪታብ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ አላህ በቁርአን ውስጥ በስም የጠቀሳቸው ከቀድሞ መጽሐፍት መካከል ተውራት፣ ዘቡር እና ኢንጂል ናቸው፤ ነገር ግን በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ፦ “አላህን አምልኩ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን ልኳል፤ በዚያ መልእክተኛ ለጊዜው ሁሉ መጽሐፍ አድርጓል፦
16፥36 *በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ* «አላህን አምልኩ፤ ጣዖትንም ራቁ» *በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል*፡፡ وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍۢ رَّسُولًا أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ وَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلطَّٰغُوتَ
13፥38 *ለጊዜው ሁሉ መጽሐፍ አለው*፡፡ لِكُلِّ أَجَلٍ كِتَابٌ

አላህ ኪታብ ለነብያት የሚያወርደው በሦስት መንገድ ነው፤ በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን በመላክ” ነው፦
42:51 *ለሰው አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት* ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም፤ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

ከአላህ ዘንድ ወደ ነብያት የሚወርደው መጽሐፍ በውስጡ የነበረውን የትምህርት ጭብጥ በዐቂዳህ ነጥብ፦ “እነሆ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ማለትን ሲሆን በፊቅህ ነጥብ ደግሞ “መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን” ነው፦
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ *”እነሆ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም”* ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡ يُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ أَنْ أَنذِرُوٓا۟ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ
21፥73 *”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

ቁርአን ይህንን ወርዶ የነበረውን የዐቂዳህ እና የፊቅህ ጉዳይ በመዘርዘር ያረጋግጣል፤ የሚዘረዝርበት ምክንያት ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ ነው፦
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፡፡ ግን ያንን *”ከእርሱ በፊት ያለውን”* የሚያረጋግጥ እና *”በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር”* በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ وَمَا كَانَ هَٰذَا ٱلْقُرْءَانُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن تَصْدِيقَ ٱلَّذِى بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
11፥120 *ከመልክተኞቹም ወሬዎች* ሁሉንም ልብህን በእርሱ የምናረካበትን *እንተርክልሃለን*፡፡ *በዚህችም እውነቱ ነገር፣ ለምእምናን ግሳጼና ማስታወሻ መጥቶልሃል*፡፡ وَكُلًّا نَّقُصُّ عَلَيْكَ مِنْ أَنبَاءِ الرُّسُلِ مَا نُثَبِّتُ بِهِ فُؤَادَكَ ۚ وَجَاءَكَ فِي هَـٰذِهِ الْحَقُّ وَمَوْعِظَةٌ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
አላህ እነዚህን የአላህ መጽሐፍት እንዲጠብቁ ሃላፍትና የሰጣቸው ለሰዎች ነው፦
5፥44 እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን፡፡ እነዚያ ትዕዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፡፡ ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም *ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉት* እና በእርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት ይፈርዳሉ፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَا التَّوْرَاةَ فِيهَا هُدًى وَنُورٌ ۚ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا وَالرَّبَّانِيُّونَ وَالْأَحْبَارُ بِمَا اسْتُحْفِظُوا مِن كِتَابِ اللَّهِ وَكَانُوا عَلَيْهِ شُهَدَاءَ ۚ

ነገር ግን ሰዎች ይህንን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ የአላህን መጽሐፍ በመለወጥ እና እላዩ ላይ በእጆቻቸው ጽፈው በመጨመር «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው እውነትን ከሀሰት ቀላቅለዋል፤ ከንግግሩ ላይ በመቀነስ እውነትን ደብቀዋል፦
2፥75 ከእነርሱ የኾኑ ጭፍሮች *የአላህን ንግግር የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት* ሲኾኑ ለእናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን? أَفَتَطْمَعُونَ أَن يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِّنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِن بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُونَ
2:79 *ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው*፡፡ ለእነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለእነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን *ትደብቃላችሁ*? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

ከዚያ በኃላ ቁርአን ከበፊቱ የተወረደውን መጽሐፍ ሊያረጋግጥ እና በእርሱ ላይ የጨመሩትን ሊያርም ወረደ፤ ከበፊቱ የተወረደውን መጽሐፍ ሊያረጋግጥ “ሙሰዲቃን” مُصَدِّقًا ማለትም “አረጋጋጭ” ሲባል፤ የሰዎች ንግግር የገቡበትን በማረሙ ደግሞ “ሙሃይሚን” مُهَيْمِنًا ማለትም “አራሚ” correcter” ወይም “ተቆጣጣሪ”supervisor” የሚል ስም አለው፦
5:48 *ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ “አረጋጋጭ” እና በእርሱ ላይ “ተጠባባቂ” ሲሆን በእውነት አወረድን*፤ وَأَنزَلْنَآ إِلَيْكَ ٱلْكِتَٰبَ بِٱلْحَقِّ مُصَدِّقًۭا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ ٱلْكِتَٰبِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ
4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው በዚያም *በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي أَنزَلَ مِن قَبْلُ ۚ

አምላካችን አላህ፦ “እመኑ” ያለው “ባወረደው መጽሐፍ” እንጂ በእጆቻቸው ጽፈው በመጨመር «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ብለው እውነትን ከሀሰት የቀላቀሉትን ባይብል አይደለም፤ እመኑ ያለው በዐቂዳህ ነጥብ፦ “እነሆ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም” ማለትን ማውረዱ ወይም በፊቅህ ነጥብ ደግሞ “መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን” ማውረዱን ነው፦
42፥15 ለዚህም ጥራ! እንደታዘዝከውም ቀጥ በል፤ ዝንባሌዎቻቸውንም አትከተል። በላቸውም፦ “ከመጽሐፍ *አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ*፡፡ فَلِذَٰلِكَ فَادْعُ ۖ وَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ ۖ وَقُلْ آمَنتُ بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ مِن كِتَابٍ ۖ وَأُمِرْتُ لِأَعْدِلَ بَيْنَكُمُ

“አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ” የሚለው ይሰመርበት፤ አላህ የቀድሞቹን መጽሐፍት ተከተሉ ብሎ አንድ አንቀጽ ላይ አላለም። ታዲያ መመሪያ አድርጋችሁ ተከተሉ ያለው ማንን ነው? ኢንሻላህ ስለ ቁርኣን በገቢር ሁለት እንቀጥላለን…

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በመጽሐፉ እመኑ!

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

4፥136 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ እና በመልክተኛው በዚያም *በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي نَزَّلَ عَلَىٰ رَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي أَنزَلَ مِن قَبْلُ ۚ

“ቁርኣን” قُرْءَان የሚለው ቃል “ቀረአ” قَرَأَ ማለትም “አነበበ” ወይም “አነበነበ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “መነባነብ”recitation” ማለት ነው፤ ቁርኣን ማለት አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነብያችን”ﷺ” የሚያነበው መነባነብ ነው፦
2፥252 *እነዚህ በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ አንቀጾች ናቸው*፤ አንተም በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ፡፡ تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ ۚ وَإِنَّكَ لَمِنَ الْمُرْسَلِينَ
45፥6 *እነዚህ በአንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከአላህና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?* تِلْكَ آيَاتُ اللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِالْحَقِّ ۖ فَبِأَيِّ حَدِيثٍ بَعْدَ اللَّهِ وَآيَاتِهِ يُؤْمِنُونَ
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

“ማንበቡ” ለሚለው ቃል የገባው “ቁርኣነሁ” َقُرْآنَهُ ሲሆን ይህ የሚነበበው አንቀጽ የአላህ የራሱ ንግግር ስለሆነ አላህ በመጀመሪያ መደብ “አያቱና” آيَاتُنَا ማለትም “አንቀጾቻችን” በማለት ይናገራል፦
31፥7 *አንቀጾቻችንም በእርሱ ላይ በሚነበቡ ጊዜ* እንዳልሰማትና በጆሮቹ ድንቁርና እንዳለበት፣ የኮራ ሆኖ ይዞራል፤ በአሳማሚ ቅጣትም አብስረው። وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِ آيَاتُنَا وَلَّىٰ مُسْتَكْبِرًا كَأَن لَّمْ يَسْمَعْهَا كَأَنَّ فِي أُذُنَيْهِ وَقْرًا ۖ فَبَشِّرْهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ
46፥7 *በእነርሱም ላይ አንቀጾቻችን ግልጾች ኾነው በተነበቡ ጊዜ* እነዚያ እውነቱን በመጣላቸው ጊዜ የካዱትን «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ፡፡ وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ آيَاتُنَا بَيِّنَاتٍ قَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لِلْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُمْ هَـٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ

አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነብያችን”ﷺ” “ኢቅራ” اقْرَأْ ማለትም “አንብብ” ወይም “አነብንብ” ብሎ አዟቸዋል፤ “ኢቅራ” የሚለው ቃል ነብያችም”ﷺ” ሲያነቡት የነበረው ግን በቃል ለሚነበበው መነባነብ ነው፤ ምክንያቱ አላህ፦ “ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል” የሚል ሀይለ-ቃል ይጠቀማል፦
96፥1 *አንብብ* በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡ اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ
75:18 *ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል*። فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَه
29፥45 ከመጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ
18፥27 ከጌታህም መጽሐፍ *ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ*፡፡ وَاتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن كِتَابِ رَبِّك

ቁርኣን መጽሐፍ ሆኖ የወረደው ወደ ነብያችን”ﷺ” ልብ ነው፤ ልብ ላይ የተሰበሰበው ንባብ ደግሞ መጽሐፍ ይባላል እንጂ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ አልወረደም፦
2፥97 ለጂብሪልጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ እርሱ ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን *በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِين
26፥194 ከአስስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ *በልብህ ላይ አወረደው*፡፡ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنذِرِينَ
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ
6፥7 *በአንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድንና በእጆቻቸው በነኩት ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር*፡፡ وَلَوْ نَزَّلْنَا عَلَيْكَ كِتَابًا فِي قِرْطَاسٍ فَلَمَسُوهُ بِأَيْدِيهِمْ لَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا إِنْ هَـٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ

“ቂርጧስ” قِرْطَاس ማለት በብራና የተጻፈ “ወረቀት” ነው፤ ቁርኣን በዚህ ቁስ ተጽፎ አልወረደም፤ ስለዚህ አላህ መጽሐፍ የሚለው በብራና፣ በሰሌን፣ በስስ ድንጋይ፣ በሰሌዳ፣ በበግ አጥንት፣ በዘንባባ ቅርፊት ፣ በቴምር ቅጠል፣ በከብት ቆዳ በመሳሰሉት ላይ 40 የሚያክሉ እነ አቡበከር፣ ኡመር፣ ኡስማን፣ አሊ፣ ዙበይር፣ ኡበይ፣ ሙአዊያህ፣ ዘይድ ኢብኑ ጣቢት በተፃፉ ጊዜ ሳይሆን ከዓለማቱ ጌታ ሲወርድ ነው፦
7፥2 *ይህ ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ ነው፡፡ በደረትህም ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር*፡፡ كِتَابٌ أُنزِلَ إِلَيْكَ فَلَا يَكُن فِي صَدْرِكَ حَرَجٌ مِّنْهُ لِتُنذِرَ بِهِ وَذِكْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
38፥29 *ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው*፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ አወረድነው፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ
29፥51 *እኛ መጽሐፉን በእነርሱ ላይ የሚነበብ ኾኖ በአንተ ላይ ማውረዳችን አይበቃቸውምን?* በዚህ ውስጥ ለሚያምኑ ሕዝቦች ችሮታና ግሳጼ አለበት፡፡ أَوَلَمْ يَكْفِهِمْ أَنَّا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْكِتَابَ يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَرَحْمَةً وَذِكْرَىٰ لِقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ
46:2 *የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከሆነው አላህ ነው*። تَنزِيلُ الْكِتَابِ مِنَ اللَّهِ الْعَزِيزِ الْحَكِيمِ
ሚሽነሪዎች የራሳቸው እያረረ የእኛን ያማስላሉ፤ “መጽሐፍ” ማለት “ጥራዝ” ነው ካሰቡት ነብያት ብሉት የተባለው መጽሐፍ ወረቀት ነበር ወይስ ግህደተ-ቃል? እናስተንትን፦
ሕዝቅኤል 3፥1-3 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ *ያገኘኸውን ብላ፤ ይህን መጽሐፍ ብላ፥ ሄደህም ለእስራኤል ቤት ተናገር አለኝ*።  *አፌንም ከፈትሁ መጽሐፉንም አጐረሰኝ*።  እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ *አፍህ ይብላ፥ በምሰጥህም በዚህ መጽሐፍ ሆድህን ሙላ አለኝ። እኔም በላሁት፥ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ*።
ራእይ10፥9-10 ወደ መልአኩም ሄጄ፦ *ታናሺቱን መጽሐፍ ስጠኝ አልሁት። እርሱም፦ ውሰድና ብላት፥ ሆድህንም መራራ ታደርገዋለች በአፍህ ግን እንደ ማር ትጣፍጣለች አለኝ*።ከመልአኩም እጅ *ታናሺቱን መጽሐፍ ወስጄ በላኋት በአፌም እንደ ማር ጣፋጭ ሆነች፤ ከበላኋት በኋላም ሆዴ መራራ ሆነ*።

ለዚያ ነው አንድ ቃሪ በቃሉ የሚቀራውን የአላህ ንግግር የአላህ መጽሐፍ የተባለው፦
84:21 *በእነርሱም ላይ ቁርአን በተነበበ ጊዜ* የማይሰግዱት፤ ምን አላቸው? وَإِذَا قُرِئَ عَلَيْهِمُ الْقُرْآنُ لَا يَسْجُدُونَ ۩
9:6 ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ *የአላህን ንግግር ይሰማ ዘንድ” አስጠጋው*፤ وَإِنْ أَحَدٌ مِّنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّىٰ يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ أَبْلِغْهُ مَأْمَنَهُ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْلَمُونَ
35፥29 *እነዚያ የአላህን መጽሐፍ የሚያነቡ*፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱ፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በምስጢርም ኾነ በግልጽ የለገሱ፣ በፍጹም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ يَتْلُونَ كِتَابَ اللَّهِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَأَنفَقُوا مِمَّا رَزَقْنَاهُمْ سِرًّا وَعَلَانِيَةً يَرْجُونَ تِجَارَةً لَّن تَبُورَ

ቁርኣን 114 ሱራዎች ሲኖሩት የወረዱት ለ 13 ዓመት 86 ሱራዎች በመካ ሲሆን 28 ደግሞ የወረዱት ለ 10 ዓመት በመዲና ነው፣ ቀስ በቀስ በጨረቃ አቆጣጠር ለ 23 ዓመት ወረደ፦
17:106 *ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፤ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው*። وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا
25:32 እነዚያ የካዱትም፦ *ቁርአን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም? አሉ፤ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ፣ ከፋፍለን አወረድነው*፤ ቀስ በቀስ መለያየትም ለየነው። وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَاهُ تَرْتِيلًا

እዚህ ላይ የሚያጅበት ቁርአን 6,236 አናቅጽ አሉት፣ ቁርኣን አንቀጾቹ የተሰካኩ መጽሐፍ ነው፤ አንቀጾቹ ብቻ ሳይ ሳይሆን ሱራዎቹም ከአላህ የወረዱ ናቸው፤ ነብያችን”ﷺ” ይህ በአንቀጽና በሱራ የተሰካካ መጽሐፍ ወደ እርሳቸው መወረዱት ተስፋ የሚያደርጉት አልነበረም፤ ግን ከጌታ ችሎታ ተወረደላቸው፦
11፥1 አሊፍ ላም ራ፤ *ይህ ቁርኣን አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው*፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው፡፡ الر ۚ كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِن لَّدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ
47፥20 እነዚያም ያመኑት ሰዎች፦ *ሱራ አትወርድም ኖሮአልን?* ይላሉ፡፡ *የጠነከረችም ሱራ በተወረደች* እና በውስጧም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ በሺታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የኾነ መከራ በእርሱ ላይ እንደ ወደቀበት ሰው አስተያየት ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ለእነርሱም ወዮላቸው፡፡ وَيَقُولُ الَّذِينَ آمَنُوا لَوْلَا نُزِّلَتْ سُورَةٌ ۖ فَإِذَا أُنزِلَتْ سُورَةٌ مُّحْكَمَةٌ وَذُكِرَ فِيهَا الْقِتَالُ ۙ رَأَيْتَ الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ يَنظُرُونَ إِلَيْكَ نَظَرَ الْمَغْشِيِّ عَلَيْهِ مِنَ الْمَوْتِ ۖ فَأَوْلَىٰ لَهُمْ
28፥86 *መጽሐፉ ወደ አንተ መወረዱን ተስፋ የምታደርግ አልነበርክም፡፡ ግን ከጌታህ ችሮታ ተወረደልህ*፡፡ ለከሓዲዎችም በፍጹም ረዳት አትኹን፡፡ وَمَا كُنتَ تَرْجُو أَن يُلْقَىٰ إِلَيْكَ الْكِتَابُ إِلَّا رَحْمَةً مِّن رَّبِّكَ ۖ فَلَا تَكُونَنَّ ظَهِيرًا لِّلْكَافِرِينَ
ቁርኣን ከአላህ የተወረደ እውነት ነው፤ ከነብያችም”ﷺ” በኃላ የሚመጣ ነብይ፣ የሚላክ መልእክተኛ እና የሚወርድ ተንዚል ስለሌለ አላህ ቁርኣን እራሱ አውርዶ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት እንዳመጣበት እራሱ ይጠብቀዋል፦
15፥9 *እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا ٱلذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُۥ لَحَٰفِظُونَ
41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም*፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ
78፥48 *ጌታዬ እውነትን ያወርዳል*፤ ሩቅ የኾኑትን ምስጢሮች ሁሉ ዐዋቂ ነው» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّ رَبِّي يَقْذِفُ بِالْحَقِّ عَلَّامُ الْغُيُوبِ
3፥60 *ይህ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት ነው*፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትኹን፡፡ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُن مِّنَ الْمُمْتَرِينَ

አላህ ቁርኣንን የሚጠብቀው በሰው ልብ እንዲታወስ በማግራት ነው፤ ቁርአንን በልብ የሚሰበስበው እራሱ ነው፦
54፥17 *ቁርኣንንም ለማስታወስ በእርግጥ አገራነው*፡፡ አስታዋሽም አለን? وَلَقَدْ يَسَّرْنَا ٱلْقُرْءَانَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍۢ
75፥17 *በልብህ ውስጥ መሰብሰቡ እና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና*፡፡ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ

ስለ ቁርኣን ይህንን ያክል ካየን ዘንዳ አምላካችን አላህ መመሪያ አድርጋችሁ ተከተሉ ያለው ከእርሱ ዘንድ የወረደውን መጽሐፍ ቁርኣንን ነው፦
6፥155 *ይህም ያወረድነው የኾነ የተባረከ መጽሐፍ ነው፤ ተከተሉትም*፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ ከክህደት ተጠንቀቁ፡፡ وَهَـٰذَا كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ مُبَارَكٌ فَاتَّبِعُوهُ وَاتَّقُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ
7፥3 *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ*፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡ اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ
39፥55 እናንተ የማታውቁ ስትኾኑም ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት *ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን መልካሙን መጽሐፍ ተከተሉ*፡፡ وَاتَّبِعُوا أَحْسَنَ مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ بَغْتَةً وَأَنتُمْ لَا تَشْعُرُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ለስዕል ይሰገዳልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ *ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ ”ለሌላ አትስገዱ”*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

በግሪክ "ኢኮን" εἰκών በዕብራይስጥ “ኤሊል” אֱלִיל ማለት "ስዕል"image" ማለት ሲሆን በሰሌዳ ላይ በቀለም፣ በጠመኔ፣ በእርሳስ አለዚያም በሌላ ነገር ተስርቶ በዓይን በማየት የሚገነዘቡት የአንድ ማንነት ወይም ምንነት ምስል ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ላይ ሥዕልን እንዲህ ይገልጹታል፦
ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት 673
*"ስዕል ማለት በቁም መልክ፣ የመልክ ጥላ፣ ንድፍ፣ አምሳል፣ ንድፍ በውኃ፣ በመጽሔት፣ በጥልፍ፣ በስፌት ወይም በቀለም በወረቀት ገዝፎ ተጽፎ ከደብር፣ ከእብን፣ ከእጽ፣ ከማዕድን ታንጦ፣ ተቀርጦ፣ ተሸልሞ፣ አጊጦ የሚታይ የሚዳሰስ ነገር ነው*፡፡"

ያህዌህ ሙሴን በተራራው ሰማያዊ ኑባሬዎችን በመገለጥ እያሳየው እነዚያን ኑባሬዎች በምስል አድርጎ እንዲሰራ አዞት ነበር፦
ዘጸአት 25፥40 *በተራራ ላይ እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ።
ዘጸአት 26፥30 *ማደሪያውንም በተራራ እንዳሳየሁህ ምሳሌ አቁም*።
ዕብራውያን 8፥5 እነርሱም *ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና*።
የሐዋርያት ሥራ 7፥44 *እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው*፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች።

"እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው" የሚለው ሃይለ-ቃል ይመሰርበት፤ ይህም ምስል የመላእክትን ምስል ይጨምራል፤ ለምሳሌ የኪሩቤል ምስል እንዲሰራ ታዞ ነበር፦
ዘጸአት 25፥19 ከስርየት መክደኛውም ጋር *አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሠራዋለህ*።

ኪሩብ በነጠላ ሲሆን በብዜት ደግሞ ኪሩቤል ነው። ያህዌህ ሕዝቅኤልን፦ "የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት" ብሎ አዞት ነበር፦
ሕዝቅኤል 4፥1 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጡብን ወስደህ በፊትህ አኑራት *የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት ክበባት*፥

ይህ እንዲህ በእንዲህ እንዳለ ነቢያት ይህንን ሥነ-ጥበብ ሰውን ለማስተማር ይጠቀሙበት ነበር እንጂ አንድም ቀን ሰግደውለት አያውቁም፥ ስገዱለት የሚል መመሪያም አልተቀበሉም አላስተላለፉም። ከዚያ በተቃራኒው የሙሴ አምላክ ለሙሴ፦ "የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም” ብሎ አዞልታ፤ እንደውም መዝሙረኛው፦ "ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ" ይላል፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ *”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ*።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር *”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤
መዝሙር 97፥7 *”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ*”፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።

ነቢያትም የተቀረጸውን ምስል ሠራተኛ እንደሚሰራው፣ የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ከንቱ እንደኾኑ እና ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ ፍርድ በእነርሱ ላይ እንደለ ተናግረዋል፦
ኢሳይያስ 40፥19 *የተቀረጸውንስ ምስል ሠራተኛ ሠርቶታል*፥ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፥ የብሩንም ሰንሰለት አፍስሶለታል።
ኢሳይያስ 44፥9 *የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው*፥
ኤርምያስ 1፥16 ስለ ክፋታቸውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተው ለሌሎችም አማልክት ስላጠኑ *ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ*።

ሰው ለሠራው የእጅ ሥራ እንዴት ይሰገዳል? በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለስዕል የጸጋ ስግደት ይሰገዳል፤ ልብ አድርግ የጸጋ ስግደት ስገዱ የሚል ትእዛዝ የለም። በተቃራኒው ለተቀረጸ ምስል "አትስገድላቸው" የሚል ትእዛዝ ቢኖር እንጂ። ነገር ግን ይህ ግዑዝ ነገር በዐበይት ክርስቲያኖች ይሰገድለታል፥ ምስጋና ይቀርበለታል፤ ይህ በተግባር ሲሆን በጽሑፍ ደግሞ የዘወትር መቅድም ላይ እንዲህ የሚል መመሪያ አለ፦
የዘወትር መቅድም ቁጥር 35-36 ገጽ 7
ግዕዙ፦
*ወቅድመ ስዕላ ስግዱ! ዘኢሰገደ ላቲ ይደምስስ እምቅዋሙ ወኢይትዐወቅ ዝግረ ስሙ። ወይበሉ መላእክተ ሰማይ ኲሎሙ አሜን*።

ትርጉም፦
*በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ! ስም አጠራሩ አይታወቅ። በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ*።

ነቢያት፦ "ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ" ሲሉ፥ ፈጣሪ "ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ" ሲል ይህ በትውፊት የተቀመጠው አዋልድ መጽሐፍ ደግሞ፦ "በሥዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ" የሚል እርግማን ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው? ለምስል መስገድ እኮ 666 ለሆነው ለክርስቶስ ተቃዋሚ መንገድ የሚጠርግ ነው፦
ራእይ 13፥15 *"የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው"*።

አውሬው ወደፊት የሚመጣው የዓለማችን መንግሥት ነው፤ ለእዚያ መንግሥት ምስል 666 የተባለው ሐሰተኛው ነቢይና መሢሕ እንዲሰግዱ ያደርጋል፤ ታስታውሱ እንደሆነ በሮማውያን ጊዜ የቄሳር ምስል እና ጽሕፈት በሳንቲም ላይ ይሳል ነበር፦
ማርቆስ 12፥16 እነርሱም አመጡለት። *ይህች "ምስል" εἰκών እና ጽሕፈቲቱስ የማን ናት? አላቸው፤ እነርሱም፦ የቄሣር ናት አሉት*።
በተመሳይይ ለእዚህ መንግሥት ምስል ስለው እንዲሰገለት ያደርጋሉ። ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ሆነ ለምስሉም የሚሰግዱ በጀሃነም ስቃይ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም፦
ራእይ 19፥20 አውሬውም ተያዘ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን *ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ*።
ራእይ 16፥2 ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ *የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው*።
ራእይ 14፥9-11 ሦስተኛም መልአክ ተከተላቸው፥ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ፦ *ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ* በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥ እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፥ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሳቀያል። የሥቃያቸውም ጢስ ለዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ይወጣል፥ *ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም*።

ይህንን አስፈሪ ወንጀል እያየ ወደ ክርስትና የሚገባ ሰው ቂል ካልሆነ ወይም በጥቅማ ጥቅም አሊያም በተቃራኒ ጾታ ፍቅር መነደፍ ካልሆነ በስተቀር አይሞክረውም። ይህንን ፍርድ እያወቀ ወደ ኢሥላም የማይመጣ በእሳት የሚጫወት ነው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ *ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ ”ለሌላ አትስገዱ”*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

" እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። በኢሥላም ፈጣሪ ከሆነው ከአንዱ አምላክ ከአላህ ውጪ የሚሰገድለት ማንነት ሆነ ምንነት የለም። ስዕል የሰው እጅ ሥራ ነው፤ ለዚህ ግዑዝ ነገር የምትሰግዱ ካላችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ። ከአላህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና፦
7፥197 *እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም*። وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኒፋቅ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا

“ኒፋቅ” نِفَاق የሚለው ቃል “ናፈቀ” نَافَقَ ማለትም “ነፈቀ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ኑፋቄ” ወይም “ምንፍቅና” አሊያም “አስመሳይነት” ”በአፉ አምኖ በልቡ የሚክድ” ማለት ነው፤ “ኑፋቄ” የሚለው የግዕዝ ቃል “ነፈቀ” ማለትም “ከፈለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክፍልፍል” ወይም “አራጥቃ” ማለት ነው፤ ዓመት ለሁለት ስንከፍለው ስድስት ወሩ “መንፈቅ” ይባላል። አለቃ ኪዳነ-ወልድ ክፍሌ ገፅ 645።

ስለዚህ “መናፍቅ” ማለት “በከፊሉ አምኖ በከፊሉ የሚክድ” ሙሉ ያልሆነ ጎደሎ እምነት ያለው ማለት ነው፤ ኒፋቅ በውስጥ ኩፍር በውጪ ኢማን የሆነ ሁለት አይነት ገጽታ ያለው ነገር ነው፤ ኒፋቅ ያለበት ግለሰብ ደግሞ በነጠላ “ሙናፊቅ” مُنَٰفِق ሲባል በብዜት “ሙናፊቁን” مُنَٰفِقُون ወይም “ሙናፊቂን” مُنَٰفِقِين ይባላል፤ በአማርኛችን በነጠላ “መናፍቅ” በብዜት “መናፍቃን” ማለት ነው። አላማቸው ኡማውን መከፋፈልና መበታተን ነው፦
63፥7 *እነርሱ እነዚያ ፡- «አላህ መልክተኛ ዘንድ ላሉት ሰዎች እስከሚበታተኑ ድረስ አትቀልቡ» የሚሉ ናቸው፡፡ የሰማያትና የምድር ድልቦችም የአላህ ናቸው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም*፡፡ هُمُ الَّذِينَ يَقُولُونَ لَا تُنفِقُوا عَلَىٰ مَنْ عِندَ رَسُولِ اللَّهِ حَتَّىٰ يَنفَضُّوا ۗ وَلِلَّهِ خَزَائِنُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَـٰكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَفْقَهُونَ

ውጪአቸው አማኝ ነው ውስጣቸው ግን ክህደት አለ፤ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፤ አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም፤ ወደ ቁርኣንና ወደ ሐዲስ አይመጡም፦
4፥142 *መናፍቃን አላህን ያታልላሉ፡፡ እርሱም አታላያቸው ነው፡፡ ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَهُوَ خَادِعُهُمْ وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا
2፥8 *ከሰዎችም «በአላህና በመጨረሻው ቀን አምነናል» የሚሉ አሉ፤ እነርሱም አማኞች አይደሉም*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَقُولُ آمَنَّا بِاللَّهِ وَبِالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَا هُم بِمُؤْمِنِينَ
2፥9 *አላህን እና እነዚያን ያመኑትን ያታልላሉ፤ የማያውቁ ሲኾኑ እራሳቸውን እንጅ ሌላን አያታልሉም*፡፡ يُخَادِعُونَ اللَّهَ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَمَا يَخْدَعُونَ إِلَّا أَنفُسَهُمْ وَمَا يَشْعُرُونَ
3፥167 *እነዚያንም የነፈቁትን* እና ለእነርሱ «ኑ፤ በአላህ መንገድ ተጋደሉ፤ ወይም ተከላከሉ፤» የተባሉትን ሊገልጽ ነው፡፡ «መዋጋት መኖሩን ብናውቅ ኖሮ በተከተልናችሁ ነበር» አሉ፡፡ *እነርሱ ያን ጊዜ ከእምነት ይልቅ ወደ ክህደት የቀረቡ ናቸው፡፡ በልቦቻቸው የሌለውን በአፎቻቸው ይናገራሉ፡፡ አላህም የሚደብቁትን ዐዋቂ ነው*፡፡ وَلِيَعْلَمَ الَّذِينَ نَافَقُوا ۚ وَقِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا قَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَوِ ادْفَعُوا ۖ قَالُوا لَوْ نَعْلَمُ قِتَالًا لَّاتَّبَعْنَاكُمْ ۗ هُمْ لِلْكُفْرِ يَوْمَئِذٍ أَقْرَبُ مِنْهُمْ لِلْإِيمَانِ ۚ يَقُولُونَ بِأَفْوَاهِهِم مَّا لَيْسَ فِي قُلُوبِهِمْ ۗ وَاللَّهُ أَعْلَمُ بِمَا يَكْتُمُونَ
4፥61 ለእነርሱም፡- *«አላህ ወደ አወረደው ቁርኣን እና ወደ መልክተኛው ኑ» በተባሉ ጊዜ መናፍቃን ከአንተ መሸሽን ሲሸሹ ታያቸዋለህ*፡፡ وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا إِلَىٰ مَا أَنزَلَ اللَّهُ وَإِلَى الرَّسُولِ رَأَيْتَ الْمُنَافِقِينَ يَصُدُّونَ عَنكَ صُدُودًا
2፥14 *እነዚያንም ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ «አምነናል» ይላሉ፡፡ ወደ ሰይጣኖቻቸውም ባገለሉ ጊዜ «እኛ ከእናንተ ጋር ነን፤ እኛ በእነርሱ ተሳላቂዎች ብቻ ነን»* ይላሉ፡፡ وَإِذَا لَقُوا الَّذِينَ آمَنُوا قَالُوا آمَنَّا وَإِذَا خَلَوْا إِلَىٰ شَيَاطِينِهِمْ قَالُوا إِنَّا مَعَكُمْ إِنَّمَا نَحْنُ مُسْتَهْزِئُونَ

የመናፍቃን ቅጣቱ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፦
4፥145 *መናፍቃን በእርግጥ ከእሳት በታችኛው አዘቅት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱም ረዳትን አታገኝላቸውም*፡፡ إِنَّ الْمُنَافِقِينَ فِي الدَّرْكِ الْأَسْفَلِ مِنَ النَّارِ وَلَن تَجِدَ لَهُمْ نَصِيرًا
9፥68 *መናፍቃንንና መናፍቃትን፣ ከሓዲዎችንም አላህ የገሀነምን እሳት በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ እርሷ በቂያቸው ናት፡፡ አላህም ረግሟቸዋል፡፡ ለእነርሱም ዘውታሪ ቅጣት አላቸው*፡፡ وَعَدَ اللَّهُ الْمُنَافِقِينَ وَالْمُنَافِقَاتِ وَالْكُفَّارَ نَارَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ هِيَ حَسْبُهُمْ ۚ وَلَعَنَهُمُ اللَّهُ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ مُّقِيمٌ

የሙናፊቅ ምልክቶች ሦስት ናቸው፦ ሲናገር ይዋሻል፣ ሲያምኑት ይከዳል፣ ቃል የገባውን ያፈርሳል፦
 ኢማም ቡኻሪይ  መጽሐፍ 55, ሐዲስ 12
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው ነብዩ”ﷺ” ሲናገሩ፦ *”የሙናፊቅ ምልክቶች ሦስት ናቸው፦ ሲናገር ይዋሻል፣ ሲያምኑት ይከዳል፣ ቃል የገባውን ያፈርሳል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ آيَةُ الْمُنَافِقِ ثَلاَثٌ، إِذَا حَدَّثَ كَذَبَ، وَإِذَا اؤْتُمِنَ خَانَ، وَإِذَا وَعَدَ أَخْلَفَ ‏.‏