ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ አራት
"ወሰደ"
"ወፋ" وَفَّىٰٓ ማለት "ወሰደ" የመጣበት አንቀጽ ለምሳሌ ይህ ነው፦
39፥42 *አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ”ይወስዳል”፡፡ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ ”ይወስዳታል”*፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

እዚህ ጋር "ያልሞተችው" ለሚለው ቃል የገባው "ለም ተሙት" لَمْ تَمُتْ ሲሆን "ይወስዳታል" ለሚለው "የተወፈ" يَتَوَفَّى ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ "መሞት" እና "መወሰድ" ሁለት የተለያዩ ግሶች ሆነው እናገኛቸዋለን። ይህንን የቋንቋ ሙግት ነጥብ ካየን ዘንዳ አላህ ዒሣን ወደ ላይ ወስዶታል፦
3፥55 አላህም ባለ ጊዜ አስታውስ፦ “ዒሣ ሆይ! እኔ *”ወሳጂህ”* እና ወደ እኔም *”አንሺህ”* ነኝ”፡፡ إِذْ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَىٰٓ إِنِّى مُتَوَفِّيكَ وَرَافِعُكَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ወሳጂህ” ለሚለው የገባው ቃል “ሙተፈይከ” مُتَوَفِّيكَ ነው፤ ዒሣን አይሁዳውያን በእርግጥም አልገደሉትም፤ ሊገድሉት ሲሉ አላህ ወደ ላይ በማንሳት ወሰደው፤ “ራፊዑከ” َرَافِعُكَ ማለትም “አንሺህ” ማለት ሲሆን ወደ ላይ ማረጉን ያሳያል፦
4፥158 ይልቁኑስ፣ *አላህ ዒሣን ወደ እርሱ አነሳው*፤ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው። بَل رَّفَعَهُ ٱللَّهُ إِلَيْهِ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًۭا

“ረፈዐሁ” رَفَعَهُ ማለትም “አነሳው” የሚለው ቃል “ረፈዐ” رَفَعَ ማለትም “አነሳ” ከሚል ቃል የመጣ ነው። ከዚያስ? ዒሣ ለትንሳኤ ቀን ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው፤ ዒሳ የትንሳኤ ቀን ሲቃረብ በምድር ላይ 40 ዓመት ይቆያል፤ ከዚያም ይሞታል፦
43፥61 *እርሱም ዒሣ ለሰዓቲቱ ማወቂያ በእርግጥ ምልክት ነው*፡፡ «በእርሷም አትጠራጠሩ፡፡ ተከተሉኝም፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» በላቸው፡፡ وَإِنَّهُ لَعِلْمٌ لِّلسَّاعَةِ فَلَا تَمْتَرُنَّ بِهَا وَاتَّبِعُونِ ۚ هَـٰذَا صِرَاطٌ مُّسْتَقِيمٌ
ተፍሢሩል አጥ-ጠበሪ 3፥55
ሐሰን እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ አሉ፦ *"ዒሣ አልሞተም፤ ከትንሳኤ ቀን በፊት ይመጣል”*። قال الحسن: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم لليهود: ” إن عيسَى لم يمتْ، وإنه راجعٌ إليكم قبل يوم القيامة.
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 39, ቁጥር 34
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ “በእኔ እና በዒሣ መካከል ነቢይ የለም። እርሱ ዒሳ ወደፊት ይወርዳል፤ ባያችሁት ጊዜ ታውቁታላችሁ፤ መካከለኛ ቁመት፣ ቀያማ ጸጉር፣ ሁለት ቀለል ያሉ ቢጫ ልብሶችን ይለብሳል፤ እይታል ልክ ነጠብጣብ ከግንባሩ እንደሚወርድ ግን እንደማይረጥብ ነው፤ በኢስላም መንገድ ህዝቦችን ይታገላል፤ መስቀልንም ይሰባብራል፣ አሳማዎችንም ይገድላል፣ ግብርንም ይተዋል፤ አላህም ከኢስላም በስተቀር ሁለንም ሃይማኖቶች ያጠፋል፤ ዒሣ መሲሑል ደጃልን ያስወግዳል፤ *በምድር ላይ 40 ዓመት ይቆያል፤ ከዚያም ይሞታል*፤ ሙስሊሞች ይሰግዱበታል። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لَيْسَ بَيْنِي وَبَيْنَهُ نَبِيٌّ – يَعْنِي عِيسَى – وَإِنَّهُ نَازِلٌ فَإِذَا رَأَيْتُمُوهُ فَاعْرِفُوهُ رَجُلٌ مَرْبُوعٌ إِلَى الْحُمْرَةِ وَالْبَيَاضِ بَيْنَ مُمَصَّرَتَيْنِ كَأَنَّ رَأْسَهُ يَقْطُرُ وَإِنْ لَمْ يُصِبْهُ بَلَلٌ فَيُقَاتِلُ النَّاسَ عَلَى الإِسْلاَمِ فَيَدُقُّ الصَّلِيبَ وَيَقْتُلُ الْخِنْزِيرَ وَيَضَعُ الْجِزْيَةَ وَيُهْلِكُ اللَّهُ فِي زَمَانِهِ الْمِلَلَ كُلَّهَا إِلاَّ الإِسْلاَمَ وَيُهْلِكُ الْمَسِيحَ الدَّجَّالَ فَيَمْكُثُ فِي الأَرْضِ أَرْبَعِينَ سَنَةً ثُمَّ يُتَوَفَّى فَيُصَلِّي عَلَيْهِ الْمُسْلِمُونَ ‏”‏ ‏.‏

መስቀል እንጨት፣ ብር፣ ወርቅ፣ ብረት ነው፤ መስቀሉን ለስግደት ስለሚጠቀሙበት ያኔ መስቀሎችን ይሰባብራቸዋል። ለጤና ጠንቅ የሆኑትን አሳማዎች የምዕራባውያን ምግብ ነው፤ አሳማዎችን እንዳይበሉ በማድረግ ያግዳል። አህለ ዚማህ ማለት በሙስሊም ሸሪዓ ሕገ-መንግሥት የሚኖሩ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች የሚከፍሉትን ጂዝየ ማለትም ግብር ያስቀራል፤ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ሙስሊም ስለሚሆን፤ ከመጽሐፉ ሰዎች አይሁዳውያን ሆኑ ክርስቲያኖች ወለም ዘለም ውልፍጥ ዝልፍጥ ሳይሉ ዒሣ ከመሞቱ በፊት በእርሱ ነብይነት ብቻ የሚያምን እንጅ አንድም አይገኝም፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 118
ከአቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተላለፈው፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ነፍሴ በእጁ በኾነችው ይሁንብኝ! በእናንተ ላይ የመርየም ልጅ እንደ ፍትሐዊ ዳኛ ኾኖ ሊወርድ ይቃረባል፤ መስቀልንም ይሰባብራል፣ አሳማዎችንም ይገድላል፣ ግብርንም ይተዋል፤ ገንዘብንም የሚቀበለው ሰው እስኪጠፋ ድረስ ይበራከታል፤ ለአላህ የሚደረግ አንድ ሱጁድ ዱንያ እና በውስጧ ከያዘችው ኹሉ የበለጠና የተሻለ ይኾናል”
ከዚያም አቡ ሁረይራህ፦ “ከፈለጋችሁ ይህን አንቀጽ አንብቡ” አለ፦
4፥159 *”ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በእርሱ በዒሣ በእርግጥ የሚያምን እንጅ አንድም የለም፤ በትንሣኤም ቀን በእነርሱ ላይ መስካሪ ይኾናል”* سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لَيُوشِكَنَّ أَنْ يَنْزِلَ فِيكُمُ ابْنُ مَرْيَمَ حَكَمًا عَدْلاً، فَيَكْسِرَ الصَّلِيبَ، وَيَقْتُلَ الْخِنْزِيرَ، وَيَضَعَ الْجِزْيَةَ، وَيَفِيضَ الْمَالُ حَتَّى لاَ يَقْبَلَهُ أَحَدٌ، حَتَّى تَكُونَ السَّجْدَةُ الْوَاحِدَةُ خَيْرًا مِنَ الدُّنْيَا وَمَا فِيهَا ‏”‌‏.‏ ثُمَّ يَقُولُ أَبُو هُرَيْرَةَ وَاقْرَءُوا إِنْ شِئْتُمْ ‏{‏وَإِنْ مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ إِلاَّ لَيُؤْمِنَنَّ بِهِ قَبْلَ مَوْتِهِ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يَكُونُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًا‏}‌‏.‏
በዚያ በተወለደበት ቀን ሰላም በእርሱ እንደሆነ ሁሉ በሚሞትበት በዚህ ጊዜ ሰላም በእርሱ ላይ ይሆናል፤ ሕያው ኾኖ በሚቀሰቀስበትም በትንሳኤ ቀን ሰላም በእርሱ ላይ ይሆናል፤ በዚያ ቀን ከመምጣቱ በፊት በነበሩት ደረጃውን ዝቅ ባደረኩት አይሁዳውያን እና ደረጃውን ከፍ ባደጉት ክርስቲያኖች ላይ መስካሪ ይኾናል፦
19፥33 «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ *በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን*፡፡» وَالسَّلَامُ عَلَيَّ يَوْمَ وُلِدتُّ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا
4፥159 *”ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በእርሱ በዒሣ በእርግጥ የሚያምን እንጅ አንድም የለም፤ በትንሣኤም ቀን በእነርሱ ላይ መስካሪ ይኾናል”*። وَإِن مِّنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا لَيُؤْمِنَنَّ بِهِۦ قَبْلَ مَوْتِهِۦ ۖ وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يَكُونُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًۭا

"ከመሞቱ" የሚለው ቃል የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት መሞቱን ያሳያል ካላችሁ ቀጥሎ ያለው ሃይለ-ቃል ያስራችኃል፤ "ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በእርሱ በዒሣ በእርግጥ የሚያምን እንጅ አንድም የለም" ይላል። ከመጽሐፉም ሰዎች ለምሳሌ አይሁዳውያን በመሲሕነቱ አላመኑበትም፤ ክርስቲያኖችም ደረጃውን ከፍ አርገው ነቢይ አይደለም ብለው ክደውታል። ነገር ግን ሲመጣ ከመሞቱ በፊት ከመጽሐፉም ሰዎች ሁሉም በእርሱ ነቢይነትና መሲሕነት ያምናሉ። ሲቀጥል አላፊ ግስ ቢሆን ኖሮ ከመጽሐፉም ሰዎች ከመሞቱ በፊት በእርሱ በዒሣ በእርግጥ "ያመነ" እንጅ አንድም የለም" ይል ነበር። "አመነ" آمَنَ አላፊ ግን ነው፤ ነገር ግን እዚህ አንቀጽ ላይ በወደፊት ግስ "ዩዕሚነንነ" يُؤْمِنَنَّ ማለትም "የሚያምን" በማለት ያስረግጣል። ስለዚህ ሁለቴ መሞት ስለሌለ ከላይ ያለ “ሙተፈይከ” مُتَوَفِّيكَ የሚለው የግስ መደብ የሚያመለክተው ወደ ላይ መወሰዱን ነው። ዒሣ መጥቶ ሲሞት ሩሑን መልአከ ሞት ይወስደዋል፦
32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት *”ይወስዳችኃል”*፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ

አሁንም “ይወስዳችኃል” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ነው፤ አላህ ስለ ዒሣ፦ “ሙተፈይከ” مُتَوَفِّيكَ የሚለው በሞት መወሰድን ነው ብንል እንኳን የነቢያችን"ﷺ" ተወዳጅ ሰሃቢይ ኢብኑ ዐባሥ፣ ኢማም ጀላሉል ዲን አሥ-ሡዩጢ፣ ኢማም ፈኽሩል ዲኑል ራዚ በመጨረሻው ዘመን ዳግም መጥቶ በሞት የሚወሰደውን እንደሆነ እንጂ የዛሬ ሁለት ሺህ ዓመት እንደሞተ አድርገው በአላፊ ግስ አልተጠቀሙም፦
አድ-ዱሩል መንሱር 2/347 አሊ-ዒምራን 3:55
"ኢብኑ ዐባሥ ስለዚህ አንቀጽ ሲናገር፦ *"እኔ ወሳጂህ እና ወደ እኔ አንሺህ ነኝ" ማለት "ወደ እኔ አንሺህ እና የመጨረሻው ዘመን ሲቃረብ እንድትወሰድ አደርግሃለው" ማለት ነው*። عن ابن عباس في قوله { إني متوفيك ورافعك } يعني رافعك ثم متوفيك في آخر الزمان

ኢማም ጀላሉል ዲን አሥ-ሡዩጢ በተመሳሳይ በዚህ መልክ አስቀምጠውታል፦
አል-ኢትቃን ፊ ዑሉሙል ቁርኣን ክፍል 44 አሊ-ዒምራን 3:55
"ቀዳታህ ይህንን አንቀጽ ሲያስረዳ፦ *"እኔ ወሳጂህ እና ወደ እኔ አንሺህ ነኝ" የሚለውን "ወደ እኔ አንሺህ እና እንድትወሰድ አደርግሃለው"* በሚል የግድ እንረዳዋለን። وأخرج عن قتادة في قوله تعالى إني متوفيك ورافعك قال: هذا من المقدم والمؤخر: أي رافعك إلي ومتوفيك

ኢማም ፈኽሩል ዲኑል ራዚ በዚህ ልክ አስቀምጠውታል፦
አት-ተፍሢሩል ከቢር 4/227 አሊ-ዒምራን 3:55
"ትርጓሜው፦ *"እኔ ወሳጂህ ወደ እኔም አንሺህ ነኝ፡፡ ከእነዚያም ከካዱት ሰዎች አጥሪህ ነኝ እና እንትወሰድ አደርግሃለው"* እንደዚህ በቁርኣን ብዙ የአ-ተቅዲም እና የአል-ተኺር ምሳሌዎች አሉ። والمعنى : أني رافعك إليّ ومطهرك من الذين كفروا ومتوفيك بعد إنزالي إياك في الدنيا ، ومثله من التقديم والتأخير كثير في القرآن

"አት-ተቅዲም" التقديم እና አት-ተኺር التأخير ማለት የጊዜ ቅድመ-ተከተል ሳይሆን የንግግር ቅድመ-ተከል ያማከለ ዐረፍተ-ነገር ነው፤ ለምሳሌ ይህንን አንቀጽ ማየት ይቻላል፦
16፥78 አላህም ከእናቶቻችሁ ሆዶች ምንም የማታውቁ ሆናችሁ *"አወጣችሁ"*፡፡ ታመሰግኑም ዘንድ ለእናንተ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም *"አደረገላችሁ"*፡፡ وَاللَّهُ أَخْرَجَكُم مِّن بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ لَا تَعْلَمُونَ شَيْئًا وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۙ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

አላህ መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም ያደረገልን በማህጸን ከመውጣታችሁ በፊት ቢሆንም በንግግር ቅድመ-ተከተል መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም "አደረገላችሁ" ከማለቱ በፊት "አወጣችሁ" የሚለው ተርቲበቱል ከላም ሆኖ መጥቷል። በጊዜ ቅድመ-ተከተል ግን መስሚያን ማያዎችንም ልቦችንም "አደረገላችሁ" ይቀድማል። እንዲሁ ከላይ ያለው የሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፥55 ላይ ያለውን አንቀጽ በዚህ ስሌትና ቀመር መረዳት ይቻላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በሕይወትም እስካለሁ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥31 *በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል*፡፡ وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنتُ وَأَوْصَانِي بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ مَا دُمْتُ حَيًّا

ዒሳ ኢብኑ መርየም፦ “በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል” ማለቱ “አሁን ዘካን ሰለማይሰጥ በሕይወት የለም ሞቷል ወይም በሰማይ በሕይወት ካለ እዛ ዘካ እየሰጠ ነው ወይ?” ብለው ስሁታን ተሟጓቾች ብዙ ጊዜ አድሮ ቃሪያና ከርሞ ጥጃ በመሆን ይጠቅሳሉ፤ ይህንን የሚጠይቁት አለስልሶና አቅለስልሶ ለመንቀፍ እንጂ ለመረዳት አይደለም፤ ይህ ደግሞ እያነቡ እስክስታ ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ! የሚያስብል ስሙር ሙግት እንሞግት እስቲ፦
19፥31 *በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል*፡፡ وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنتُ وَأَوْصَانِي بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ مَا دُمْتُ حَيًّا

“በየትም ስፍራ” ማለት በምድርም በሰማይም አላህ ዒሳን ብሩክ አድርጎታል፤ ቀጥሎ “እስካለው” የሚል ሃይለ-ቃል “ዱምቱ” دُمْتُ ሲሆን ይህም ቃል “በእስራኢል ልጆች መካከል እስካለ ድረስ” መሆኑን ለማመልከት በሌላ አንቀጽ ተጠቅሷል፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ *”በውስጣቸውም እስካለሁ ድረስ” በእነርሱ ላይ ”ምስክር” ነበርኩ*፡፡ *”በወሰድከኝም” ጊዜ አንተ በእነርሱ ላይ *”ተጠባባቂ”* ነበርክ*፡፡ አንተም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነህ፡፡» مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۚ وَكُنتُ عَلَيْهِمْ شَهِيدًۭا مَّا دُمْتُ فِيهِمْ ۖ فَلَمَّا تَوَفَّيْتَنِى كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ شَهِيدٌ

“ዱምቱ” دُمْتُ ማለትም “እስካለው” ድረስ የሚለው ሃይለ-ቃል በምድር ላይ ያለውን ቆይታ ያመለክታል፤ ምክንያቱም ቀጥሎ ያለው “በወሰድከኝ ጊዜ” የሚለው ሃይለ-ቃል ወደ ሰማይ መወሰዱን ስለሚያመለክት “እስካለው” የሚለው ሃይለ-ቃል በምድር ላይ በሕይወት እያለ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ስለዚህ በሕይወት በምድር ላይ እያለ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አሳልፏል፤ አላህ ወደ ሰማይ በወሰደው ጊዜ ግን የዘካ አገልግሎት ይቆማል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የነቢያት መደምደሚያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን *የአላህ መልክተኛ እና የነቢያት መደምደሚያ ነው*፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَـٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

ሰው መነጻጸሪያ ነጥብ ሳይኖረው ፈጽሞና ጨልጦ ወደ ጽርፈት ሲገባ ማየት እጅጉን ያማል፤ ኢስላም እውነትን በመግለጥ ሃሰትን በማጋለጥ እረገድ ፈር ቀዳጅና ፋና ወጊ ነው ብንል ግነት አይሆንብንም፤ ከእውነት በተቃራኒ ደግሞ የሃሰት ትምህርት የሚያራምዱ በዘመናችን የሚንቀሳቀሱ ቃዲያኒይ፣ ባሃኢያህ፣ ቁርአንያ ወዘተ የደጃሎች ተከታዮች ናቸው፤ የእነዚህ አንጃዎች መስራች፦ “ነብይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው የተነሱት ሚርዛ ጉላም አሕመድ የቃዲያኒይ መስራች፣ ሚርዛ ሁሴን አሊ የባሃኢያህን መስራች፣ ዶክተር ራሺድ ኸሊፋ የቁርአንያ መስራች ሲሆኑ፤ እነዚህ ነብያችን”ﷺ” ይመጣሉ ብለው ከተነበዩት ደጃሎች መካከል ናቸው። ይህንን ወደ ዝርዝር ከመግባታችን በፊት ስለ ነብይ እና ረሱል ያለውን እሳቤ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን ቃጣ የምንይዝበት ሚዛን ቁርአን እና ሰሒህ ሐዲስን ይዘን ኢንሻሏህን እናስቀምጣለን፦

ነጥብ አንድ
“ነቢይ”
“ነቢይ” نبي የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ወይም “ተናገረ” ከሚል የግስ መደብ አሊያም “ነበእ” نَبَإِ ማለትም “ወሬ” ወይም “ንግግር” ከሚሉት የስም መደብ የመጣ ቃል ሲሆን “አውሪ” ወይም “ነጋሪ” ማለት ነው፤ ይህንን እስቲ ከቁርአን እንመልከት፦
66፡3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ፤ እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ ከፊሉንም ተወ፤ *በእርሱም ባወራት ጊዜ ይህን ማን “ነገረህ”? አለች፤ ዐዋቂው ውስጠ አዋቂው “ነገረኝ” አላት*፤ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِ وَأَظْهَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُ وَأَعْرَضَ عَنْ بَعْضٍ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِ قَالَتْ مَنْ أَنْبَأَكَ هَذَا قَالَ نَبَّأَنِيَ الْعَلِيمُ الْخَبِيرُ

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን መልሱ “ነበአኒ” نَبَّأَنِيَ ማለትም “ነገረኝ” ማለት ነው፤ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነገረ” ማለት “ነበአ” የሚለው ቃል ነው፤ ስለዚህ ነብይ ማለት ሁሉን አዋቂው ውስጠ አዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው፤ ወይንም አላህ አማንያንን በመልካም የሚያዝበት፤ ከክፉ የሚከለክልበት እና ለራሱ ሶላትን፣ ፆምን፣ ዘካን የሚተገብርበትን የሚያወርድለት ማለት ነው።

አላህ ለፈለገው ሰው “ነቢይነት” ሲሰጠው ያ ሰው ነብይ ይባላል፤ ይህንን የመረጠው ሰው አላህ በሶስት አይነት መንገድ ወህይ በማውረድ ያናግረዋል፤ እነዚህም ሶስት መንገዶች፦
አንደኛ መንገድ በሩዕያ ማናገር ነው፤ “ሩዕያ” رُّءْيَا ማለት “ራዕይ” ማለት ሲሆን ይህም ራዕይ በሪዕይ ውስጥ ሆነው የሚመጣላቸው ንግግር ነው፤ “ሪዕይ” رِءْي ማለት “እይታ” ማለት ሲሆን እውን ላይ ሆኖ ሳይተኛ በሰመመን ወይም በተመስጦ”contemplation” ላይ ሆነው ሲሆን ነው፤ የራዕይ አንዱ ገፅታ “መናም” مَنَام ማለት “ህልም” ሲሆን ይህም በነውም ሆነው የሚመጣላቸው ንግግር ነው፤ “ነውም” نَوْم ማለት “እንቅልፍ” ማለት ነው፤ በዚህ ሁኔታ አላህ ወህይ ካወረደለት ነብይ መካከል የኢማን አባት የሆነው ኢብራሂም ነው።
ሁለተኛ መንገድ በተክሊም ማናገር ነው፤ “ተክሊም” تَكْلِيم ማለት በሁለት ማንነት መካከል የሚደረግ “ምልልስ”conversation” ሲሆን አላህ ያለ ራዕይና ህልም ወይም ያለ መልአክ ሳይታይ ከግርዶ ወዲያ ሆና የሚያናግርበት መንገድ ነው፤ በዚህ መልኩ አላህ ያናገረው ነብይ ለናሙና ያክል ሙሳ ተጠቃሽ ነው።
ሶስተኛ መንገድ በመልአክ ማናገር ነው፤ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” የሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው፤ ይህም የወህይ መልአክ ጂብሪል ነው፤ በዚህ ሁኔታ አላህ ወህይ ካወረደለት ነብይ መካከል ነብያችን”ﷺ” ናቸው፦
3:79 *ለማንም ሰዉ አላህ መጽሐፍንና ጥበብን “ነቢይነትንም” ሊሰጠዉ* እና ከዚያም ለሰዎች ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሆኑ ሊል አይገባዉም፤ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ ٱللَّهُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحُكْمَ وَٱلنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا۟ عِبَادًۭا لِّى مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن كُونُوا۟ رَبَّٰنِيِّـۧنَ بِمَا كُنتُمْ تُعَلِّمُونَ ٱلْكِتَٰبَ وَبِمَا كُنتُمْ تَدْرُسُونَ
42:51 *″ለሰው” አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም*፤ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ
ነጥብ ሁለት
“ረሱል”
“ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል ደግሞ “አርሰለ” أَرْسَلَ “ላከ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን የሚላክ መልእክተኛ ማለት ነው፤ ለረሱል ከአላህ የሚወርድለት “ሪሳላ” رِسَٰلَٰ “መልዕክት” ማለት ነው፦
5:67 *አንተ “መልእክተኛ” ሆይ! ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን አድርስ፤ ባታደሪስ “መልዕክቱን” አላደረስክም*፤ يَا أَيُّهَا الرَّسُولُ بَلِّغْ مَا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ۖ وَإِن لَّمْ تَفْعَلْ فَمَا بَلَّغْتَ رِسَالَتَهُ ۚ وَاللَّهُ يَعْصِمُكَ مِنَ النَّاسِ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْكَافِرِينَ

በነቢይና በረሱል መካከል ልዩነት አለ፤ ነቢይ እና ረሱል በሚሉት የማዕረግ ስሞች መካከል “ወ” و ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር አለ፤ ይህም ነቢይ እና ረሱል ሁለት የተለያየ ደረጃ መሆኑን ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በተጨማሪም “አልላክንም” የሚለው አጽንኦታዊ ቃል “ቢሆን እንጂ” በሚል አፍራሽ ቃል”negative particle” በመምጣቱ ነብይ በመልካም እንዲያዝ በመጥፎ እንዲከለክል ለአማንያን እንደተላከ ሁሉ መልእክተኛ ደግሞ ለአማንያንና ለከሃድያን ለማስጠንቀቅና ለማብሰር ይላካል፦
22:52 *”ከመልእክተኛ እና ከነቢይም”* ከአንተ በፊት አንድንም አልላክንም፣ ባነበበ ና ዝም ባለ ጊዜ፣ ሰይጣን በንባቡ ላይ ማጥመሚያን ቃል የሚጥል ቢሆን እንጂ وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ وَلَا نَبِيٍّ إِلَّا إِذَا تَمَنَّىٰ أَلْقَى الشَّيْطَانُ فِي أُمْنِيَّتِهِ ፤

መልእክተኛ ሁሉ ነቢይ ነው፤ ነገር ግን ነቢይ ሁሉ መልእክተኛ አይደለም፣ ነብይነት ከተደመደመ መልእክተኛነትም ተደምድሟል፤ ምክንያቱም አንድ መልእክተኛ ነብይነትን አሳልፎ ነው መልእክተኛ የሚሆነው፤ ስለዚህ ነብያችን”ﷺ” የነቢያት መደምደሚያ ናቸው፦
33:40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም፤ ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና *”የነቢያት መደምደሚያ”* ነው፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا ።

ነጥብ ሦስት
“መጨረሻ”
“መደምደሚያ” የሚለው ቃል የአሲም ቂርአት ላይ “ኺታም” خِتَٰـم ሲሆን የኪሳእ ቂርአት ላይ ደግሞ “ኻተም” خَاتَم ሲሆን ትርጉሙ “መጨረሻ” “መቋጫ” “ማጠናቀቂያ” ማለት ነው፤ በተለያየ ጊዜ የሚመጡት የአላህ ነብያት ከአደም ጀምሮ “ተከታታይ ግህደተ-መለኮት”progressive revelation” ነበራቸው፤ መልእከተኞችም አላህ የወሰነላቸው የራሳቸው ዘመነ-መግቦት”dispensation” ነበራቸው፤ ነገር ግን አንድ እድገት ጅማሬ እዳለው ሁሉ ድምዳሜም እንዳለው ሁሉ ነብይነትም በአደም ተጀምሮ በነብያችን”ﷺ” ተጠናቋል፤ ነብያችንም”ﷺ” በሰሒህ ሐዲስ የነቢያት ዓቂብ” ْعَاقِبُ ማለትም “መጨረሻ” እንደሆኑና ነብይ ከእርሳቸው በኃላ ፈጽሞና ጨልጦ እንደማይመጣ አስረግጠው ነግራውናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 163
ኢብኑ ጁበይር ከአባቱ አግኝቶ እንደተረከው፤ ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “እኔ ሙሐመድ ነኝ፣ እኔ አሕመድ ነኝ፣ እኔ ማሒ ማለትም ያ ከሃዲ ሲያጠፋ የምቀጣ ነኝ፣ እኔ ሰዎች በሚሰበሰቡት ጊዜ ሐሺር(ሰብሳቢ) ነኝ፣ *ከዚህ በኃላ ነብይ የለም፤ እኔ ዓቂብ(መጨረሻ) ነኝ*። بْنَ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ عَنْ أَبِيهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” أَنَا مُحَمَّدٌ وَأَنَا أَحْمَدُ وَأَنَا الْمَاحِي الَّذِي يُمْحَى بِيَ الْكُفْرُ وَأَنَا الْحَاشِرُ الَّذِي يُحْشَرُ النَّاسُ عَلَى عَقِبِي وَأَنَا الْعَاقِبُ ” . وَالْعَاقِبُ الَّذِي لَيْسَ بَعْدَهُ نَبِيُّ .

እስራኤላውያን በነብይ ይመሩ ነበር፤ አንዱ ነብይ ጊዜው ሲያልቅ ሌላ ነብይ ይነሳ ነበር፤ ከነብያችን”ﷺ” በኃላ ግን የሚመጣ ነብይ የለም፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60 , ሐዲስ 122:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”እስራኤላውያን በነብያት ይመሩ ነበር፤ መቼም ቢሆን አንድ ነብይ ሲሞት በእርሱ ምትክ ሌላ ነብይ ቦታውን ይተካ ነበር፤ ከእኔ በኃላ ነብይ የለም*። ግን በቁጥር የሚጨምሩ ኸሊፋዎች ይሆናሉ። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” كَانَتْ بَنُو إِسْرَائِيلَ تَسُوسُهُمُ الأَنْبِيَاءُ، كُلَّمَا هَلَكَ نَبِيٌّ خَلَفَهُ نَبِيٌّ، وَإِنَّهُ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي، وَسَيَكُونُ خُلَفَاءُ فَيَكْثُرُونَ.
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 64 , ሐዲስ 438:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ከተቡክ ወጥተው ዐሊይን በመዲናህ እንዲከተል ሾሙት፤ ዐሊይ፦ “ከህጻናትና ከሴት ጋር ልተወኝ ትፈልጋለህን? አላቸው፤ ነብዩም ልክ አሮን ለሙሴ እንደሆነው አንተ ለእኔ ብትሆን አትደሰትምን? ነገር ግን *ከእኔ በኃላ ነብይ የለም*። أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم خَرَجَ إِلَى تَبُوكَ، وَاسْتَخْلَفَ عَلِيًّا فَقَالَ أَتُخَلِّفُنِي فِي الصِّبْيَانِ وَالنِّسَاءِ قَالَ ” أَلاَ تَرْضَى أَنْ تَكُونَ مِنِّي بِمَنْزِلَةِ هَارُونَ مِنْ مُوسَى إِلاَّ أَنَّهُ لَيْسَ نَبِيٌّ بَعْدِ
የነብያት ዑደር በአደም ተጀምሮ በነብያችን”ﷺ” ሲጠናቀቅ የተሰጠው ንጽጽር በአንድ ቤት ህንጻ የመጨረሻ ድምዳሜ ሸክላ ነው፤ ነብያችን”ﷺ” ያ የድምዳሜው ሸክላ ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 61 , ሐዲስ 44:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የእኔ ከእኔ በፊት ከነበሩት ነብያት የሚነጻጸረው አንድ ግለሰብ በቆንጆና በተዋበ በሚገነባው ቤት ነው፤ ያ ቤት ድምዳሜው ላይ አንድ ሸክላ ይቀረው ነበር፤ ሰዎች ያ ቤት ጋር ሄደውና አድንቀው ነገር ግን እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሸክላ በድምዳሜ ቦታ ስለሆነ ነው ያማረው” አሉ፤ *ያ ሸክላ እኔ ነኝ፤ እኔ የነብያት መደምደሚያ ነኝ*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” إِنَّ مَثَلِي وَمَثَلَ الأَنْبِيَاءِ مِنْ قَبْلِي كَمَثَلِ رَجُلٍ بَنَى بَيْتًا فَأَحْسَنَهُ وَأَجْمَلَهُ، إِلاَّ مَوْضِعَ لَبِنَةٍ مِنْ زَاوِيَةٍ، فَجَعَلَ النَّاسُ يَطُوفُونَ بِهِ وَيَعْجَبُونَ لَهُ، وَيَقُولُونَ هَلاَّ وُضِعَتْ هَذِهِ اللَّبِنَةُ قَالَ فَأَنَا اللَّبِنَةُ، وَأَنَا خَاتِمُ النَّبِيِّينَ

ምናልባት ከእውነት ለመሸሽ አንድ አውቆ የተኛ ሰው፦ ነብያችን”ﷺ”፦ የነብያት እንጂ የመልእክተኞች መደምደሚያ ነኝ አላሉም” ብሎ ሊሞግት ይችላል፤ ሲጀመር ነብይ ሳይኮን ወደ መልእክተኛ መሻገር የለም፤ ነብይነት ከተዘጋ መልእክተኛነትም ይዘጋል፤ ሲቀጥል ነብያችን”ﷺ” ፍርጥ አርገው እንቅጩን ነብይነት እና መልእክተኝነት እንደተዘጋ እና ከእሳቸው በኃላ ነብይ ብቻ ሳይሆን መልእክተኛም እንደሌለ ተናግረዋል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነብይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነብይም የለም*። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚጠየቀው ጥያቄ ነብያችን”ﷺ” የነብይና የመልእክተኛ መጨረሻ ከሆኑ ዒሳ ከእርሳቸው በኃላ እንዴት ይመጣል? ይህ ቀላል ጥያቄ ነው፤ ዒሳ ካለፉት መልእክተኞች አንዱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሲመጣም ነብይ ሆኖ ነበእ ሊመጣለት ወይም ረሱል ሆኖ ሪሳላ ሊወርድለት ሳይሆን የአደም ልጆችን በአንድ አምልኮ ሊጠቀልል ነው፤ ይህንን ተልእኮ የሚፈጽመው በወረደለትም ወሕይ በኢንጅል ሳይሆን በቁርአን ነው፦
5፥75 *የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 55 , ሐዲስ 658:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የመርየም ልጅ ዒሳ በመካከላችሁ በሚወርድ ጊዜ እንዴት ትሆናላችሁ? እርሱ ሰዎችን በቁርአን ይበይናል እንጂ በኢንጂል አይበይንም*። حَدَّثَنَا ابْنُ بُكَيْرٍ، حَدَّثَنَا اللَّيْثُ، عَنْ يُونُسَ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ نَافِعٍ، مَوْلَى أَبِي قَتَادَةَ الأَنْصَارِيِّ أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ كَيْفَ أَنْتُمْ إِذَا نَزَلَ ابْنُ مَرْيَمَ فِيكُمْ وَإِمَامُكُمْ مِنْكُمْ ‏”‌‏.‏ تَابَعَهُ عُقَيْلٌ وَالأَوْزَاعِيُّ‏.‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 301
አቢ ሁረይራ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በመካከላችሁ የመርየም ልጅ በወረደ ጊዜ እና ሲመራችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ኢብኑ አቢ ዚዕብም አቢ ሁረይራ የዘገበው መሰረት አድርጎ፦ “ሲመራችሁ ምን ታደርጋላችሁ?” ምን ማለት ነው? አለ፤ እኔም ለእኔ አብራራልኝ አልኩኝ፤ እርሱም አለ፦ “በጌታችሁ ተባረከ ወተዓላ መጽሐፍ እና በመልእክተኛው በነብያችሁ”ﷺ” ፈለግ ይመራችኃል” አለ*። أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ كَيْفَ أَنْتُمْ إِذَا نَزَلَ فِيكُمُ ابْنُ مَرْيَمَ فَأَمَّكُمْ مِنْكُمْ ‏”‏ ‏.‏ فَقُلْتُ لاِبْنِ أَبِي ذِئْبٍ إِنَّ الأَوْزَاعِيَّ حَدَّثَنَا عَنِ الزُّهْرِيِّ عَنْ نَافِعٍ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ‏”‏ وَإِمَامُكُمْ مِنْكُمْ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ ابْنُ أَبِي ذِئْبٍ تَدْرِي مَا أَمَّكُمْ مِنْكُمْ قُلْتُ تُخْبِرُنِي ‏.‏ قَالَ فَأَمَّكُمْ بِكِتَابِ رَبِّكُمْ تَبَارَكَ وَتَعَالَى وَسُنَّةِ نَبِيِّكُمْ صلى الله عليه وسلم ‏.‏
ማጠቃለያ
ታዲያ ነብይ እና መልእክተኛ ከነብያችን”ﷺ” በኃላ የለም ከተባለ “ነብይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው የተነሱት ሚርዛ ጉላም አሕመድ የቃዲያኒይ መስራች፣ ሚርዛ ሁሴን አሊ የባሃኢያህን መስራች፣ ዶክተር ራሺድ ኸሊፋ የቁርአንያ መስራች ምንድን ናቸው? ሲባል ኃሳዌ ነብይ እና መልእክተኛ ናቸው።
“አድ-ደጃል” الدجّال‌‎ የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “ቀላቀለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ቀላቃይ” ማለት ነው፤ እውነትን ከሐሰት ጋር የሚቀላቅል ማለት ነው፤ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ “ኀሳዌ” ማለትም “አሳሳች” “ውሸተኛ” “ቀጣፊ” ማለት ነው። ዋናው ደጃል “መሲል ደጃል” ማለትም “ኀሳዌ መሲህ” ሲሆን እርሱ ከመምጣቱ በፊት የሚመጡ ሠላሳ ደጃሎች አሉ፤ “ደጅጃሉን” دَجَّالُونَ የሚለው ቃል “ደጃል” دجّال‌‎ ለሚለው ነጠላ ቃል ብዜት ነው፤ እነዚህ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም *ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”*። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ رَسُولُ اللَّهِ
ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 37, ሐዲስ 13
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ከእኔ ዑማ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች፦ “ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፤ ነገር ግን እኔ የነብያት መደምደሚያ ነኝ፤ ከእኔ በኃላ ነብይ የለም”*። وَحَتَّى تَعْبُدَ قَبَائِلُ مِنْ أُمَّتِي الأَوْثَانَ وَإِنَّهُ سَيَكُونُ فِي أُمَّتِي كَذَّابُونَ ثَلاَثُونَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ نَبِيٌّ وَأَنَا خَاتَمُ النَّبِيِّينَ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي

የጊዜና የቦታ ጥበት እንጂ ህልቆ መሳፍርት መረጃዎችን ማቅረብ ይቻል ነበር፤ “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” ይላል የአገሬ ሰው፤ ከላይ የተዘረዘሩትን የቁርአን እና የሰሒህ ሐዲስ መረጃዎችን በአጽንዖትና በአንክሮት የተገነዘበ ሰው እብሪትና ትእቢት ያለበት አባይና ወላዋይ ካልሆነ በስተቀር ደጃሎች ወደዘረጉት ጽርፈት አይገባም። የዚህ መጣጥፍ አላማ እንደ እኔ ጭላንጭል ዕውቀት ያላቸው ልጆች በዚህ የደጃሎች ጽርፈት ሰለባ እንዳይሆኑ የቀለም ቀንድ ከነከሱ ምሁራኖቻችን ስንክሳር ዕውቀት ይዘው ልጓም እና ለከት እንዲያበጁ እንዲረዳ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢየሱስ ይመለካልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

“ዒባዳ” عبادة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ “አመለከ” ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው፤ አምልኮ የሚገባው አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፤ አላህ ዒሳን በል ብሎ ያዘዘው ቃል፦ “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
«በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ነገር ግን በተቃራኒው ክርስቲያኖች ኢየሱስን በቀጥታ ያመልካሉ፤ “አምልኮ” የሚለው ቃል በእብራይስጥ “አቫድ” עָבַד ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ላትሬኦ” λατρεύω ነው፤ ይህም ለአንዱ አምላክ ብቻ በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት Adoration ነው። ኢየሱስ፦ አምልኩኝ ያለበት፣ ሀዋርያት እና ነብያት፦ ኢየሱስን አምልኩ ያለበት እና ሰዎች ኢየሱስን ያመለኩበት አንድ አንቀጽ የለም። ነገር ግን ኢየሱስ የሚመለክ መሆኑን የሚጠቁሙ ጥቅሶች አሉ ይላሉ፤ እውን ይህ ጥቅስ ኢየሱስ ይመለካል ይላልን? እስቲ ጥቅሱን እንየው፦
ዳንኤል 7፥13-14 በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ “የሰው ልጅ የሚመስል” ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ “ይገዙለት” δουλεύσουσιν ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም “ተሰጠው”፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።

ነጥብ አንድ
“የሰው ልጅ የሚመስል”
ዳንልኤ በራእይ አራትም ታላላቅ አራዊት ከባሕር ሲወጡ አየ፤ እነዚህ አራቱ ታላላቅ አራዊት ከምድር የሚነሡ አራት ነገሥታት ናቸው፤ በራእይ ያየው “የሰው ልጅ የሚመስል” ደግሞ “የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ” ነው፦
ዳንኤል 7፥27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት *”ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ”* ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ “ይገዙለታል* δουλεύσουσι ይታዘዙለትማል።
ዳንኤል 7፥18 ነገር ግን *”የልዑሉ ቅዱሳን”* መንግሥቱን ይወስዳሉ፥ እስከ ዘላለም ዓለምም መንግሥቱን ይወርሳሉ።
ዳንኤል 7፥22 *”በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ”*፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ አሸነፋቸውም።

የአይሁድ ኮሜንቴርይ አንዳቸውም “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ዐውዱ ላይ መሲሁ ነው ብሎ የሰጡበት ማብራሪያ የለም። ዐውዱ ላይ የሰው ልጅ የሚመስል የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ መሆኑን ፍትንው አርጎ ከዘጋ በኃላ ሌላ ትርጉም እንዳንሰጥ “የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው” በማለት ይቋጫል፦
ዳንኤል 7፥28 የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው።

ነጥብ ሁለት
“ተሰጠው”
ሙግቱን ጠበብ አድርገነው ዳንኤል ላይ “የሰው ልጅ የሚመስል” የተባለው ኢየሱስ ነው ቢባል እንኳን አሁንም ፍጡር ከመሆን የዘለለ ማንነት የለውም። ምክንያቱም በሃረጉ ውስጥ “ተሰጠው” የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ ሰጪው ደግሞ “በዘመናት የሸመገለው” አብ ነው፤ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ የአባቱን ዙፋን ሰጥቶታል፦
ማቴዎስ 28፥18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ *ሥልጣን ሁሉ* በሰማይና በምድር *ተሰጠኝ*።
ሉቃስ 10፥22 *ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል*፥
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*፤

ሰው እና የሰው ልጅ የተባለው ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ተለይቶ ፍጡር ነው፤ ታዲያ ይልቁንስ *ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ፊት ምንኛ ያንስ?
ዮሐንስ 13:31 ከወጣም በኋላ ኢየሱስ እንዲ አለ። *አሁን የሰው ልጅ ከበረ እግዚእብሔርም ሰለ እርሱ ከበረ*፤
ኢዮብ 25፥6 ይልቁንስ *ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ*!

የሰው ልጅ የሚመስል የሚባለው ኢየሱስ ነው ብንል እንኳን ኢየሱስ የሚመስለው አለ የሰው ልጅ የሚመስል ተብሏልና፤ ሰውን ይመስላል፤ ነገር ግን ነገር ግን ያ የሚመለከው አንዱ አምላክ የሚመስለው አለን? የለም፦
ኢዮብ 23:13 *እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው?*
ነጥብ ሶስት
“ይገዙለት”
“ይገዙለት” ተብሎ በግሪክ ሰፕቱጀንት”LXX” ላይ የሰፈረው ቃል “ዱልኦስ” δοῦλος ነው፦
ዳንኤል 7፥14 ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ “ይገዙለት” δουλεύσουσιν ዘንድ ግዛትና ክብር መንግሥትም “ተሰጠው”፤ ግዛቱም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቱም የማይጠፋ ነው።

“ይገዙለት” ተብሎ መገዛት የተገባው የሰው ልጅ የሚስመለው የልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ እንደሆነ ዐውዱ ላይ ፍንትውና ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል፦
ዳንኤል 7፥27 መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት “ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ” ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ “ይገዙለታል* δουλεύσουσι ይታዘዙለትማል።

አይ የሰው ልጅ የሚመስል የተባለው ኢየሱስ ነው፤ “ይገዙለት” ማለት “ያመልኩት” ዘንድ ማለት ነው ብላችሁ ከፈሰራችሁት የማትወጡት ገደል ውስጥ ትገባላችሁ፤ እንግዲያውስ የሚመለኩ አበዛዛቸው፦
ኢየሩሳሌም፦
ኢሳይያስ 60:12 ለአንቺም “የማይገዛ” δουλεύσουσί ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።

ያዕቆብ፦
ዘፍጥረት 25፥23 እግዚአብሔርም አላት፦ ሁለት ወገኖች በማኅፀንሽ ናቸው፥ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ “ይገዛል” δουλεύσει ።
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ “ይገዙልህ” δουλευσάτωσάν ሕዝብም ይስገዱልህ፤
ሮሜ 8፥12 ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ “ይገዛል” δουλεύσει ተባለላት።

“እርስ በእርስ”፦
ገላትያ 5፥13 ነገር ግን በፍቅር እርስ በእርሳችሁ “አገልግሉ” δουλεύετε ። KJV

ልብ አድርጉ ሁሉም ጋር መገዛት ተብሎ በግሪኩ ኮይኔ የቀረቡት ቃላት አንድ አይነት ነው።

መደምደሚያ
በተለይ የክርስትና የዐቂህዳህ መጽሐፍ የሆነው ሃይማኖተ-አበው ስጋ ፍጡር ነው ይሉን እና ተመልሰው አምላክ ነው ይላሉ፦
ሃይማኖተ-አበው ዘመጠሊጎን 44፥3
ዘመጠሊጎን አለ፦ “ወለሊሁ ሐነፀ ሥጋሁ ውስጠ ከርሠ ድንግል ወኢተሳተፎ መኑሂ በፈጢረ ሥጋሁ አላ ለሊሁ ባሕቲቱ ፈጠሮ”
ትርጉም፦ ” እርሱ ሥጋውን በድንግል ማሕፀን ፈጠረ፤ ሥጋውን በመፍጠር ማንም አጋዥ አልሆነውም፤ እርሱ እራሱ ፈጠረው እንጂ”
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 78፥31
ቄርሎስም አለ፦ “ወዓዲ ንቤ እስመ ሥጋሁ ለእግዚእነ ክርስቶስ አምላክ ውእቱ”
ትርጉም፦ ” ዳግመኛ የጌታችን የክርስቶስ ስጋ አምላክ እንደሆነ እንናገራለን”

ይህንን ህሊና ይቀበለዋል? ስጋው ምግብ ሲበላ የሚበላው ምግብ ሰውነት ሲሆን ይመለካልን? ሲከሳ ወይም ያ ምግብ ከሰውነት ሲወጣ አይመለክምን? ደሙ ስጋ ውስጥ እያለ የሚመለክ ሲፈስ የማይመለክ ነውን? ይህንን ውስብስብ ትምህርት እንኳን ልታስረዱን ይቅርና ለራሳችሁ አልገባችሁም። ኢየሱስ መመለክ የሚገባው እርሱ ሳይሆን የእርሱ አምላክ እንደሆነ በግልፅ ተናግሯል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።

አንድ ነጠላ ማንነት”person” ብቻ የሚመለክ መሆኑን ለማሳየት “እርሱ” የሚለው ነጠላ ተሳቢ-ተውላጠ ስም እና “ብቻ” በሚል ገላጭ”adjective” የሚመለከው ለኢየሱስ ንግስና የሰጠው ጌታ አምላክ ብቻ መሆኑን ያሳያል፤ ይህ ጌታም አምላክ አንድ ጌታ ነው፤ ይህ አንድ ጌታ ለእስራላልውያን የመረጠውን ኢየሱስን የላከ ነው፦
ሉቃስ 1፥32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ *ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል*፤
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው*፥
ሐዋ ሥራ 3፥20 እንግዲህ *ከጌታ ፊት* የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ *የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ*፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም።

በእርግጥም ኢየሱስ አስተምህሮቱ “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥72 እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ *አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ፡፡»* እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍۢ
19፥36 ዒሳ አለ፦ *«አላህም ጌታዬ ጌታችሁም ነውና አምልኩት፡፡ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡» وَإِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۚ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ
3፥51 *«አላህ ጌታዬ እና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት*፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ
43፥64 *«አላህ ጌታዬ ጌታችሁም ነውና አምልኩት*፡፡ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡» إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۚ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢየሱስ አይመለክም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ዒሳ የትምህርቱ ጭብጥ፦ “አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት” የሚል ነው፤ አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
3፥51 *”አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት”* ፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ
5፥72 እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ፤ እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍۢ
19፥36 ዒሳ አለ፦ *”አላህም ጌታዬ ጌታችሁም ነውና ተገዙት”* ፡፡ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡» وَإِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۚ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ

አምልኮ” የሚለው ቃል በእብራይስጥ “አቫድ” עָבַד ፣ በግሪክ “ላትሬኦ” λατρεύω ፤ በዐረቢኛ “ዒባዳ” عبادة ሲሆን “ስግደት” ደግሞ በዕብራይስጥ “ሻኻህ” שָׁחָה ፣ በግሪክ ደግሞ “ፕሩስኩኔኦ” προσκυνέω ፣ በዐረቢኛ “ሡጁድ” سُّجُود ነው፤ እነዚህ ቃላት በዐረቢኛ ባይብል ላይ በአንድ አንቀጽ ላይ ለየቅል ተቀምጠዋል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፡— ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ *ስገድ* እርሱንም ብቻ *አምልክ*፡ ተብሎ ተጽፎአልና፡ አለው። حِينَئِذٍ قَالَ لَهُ يَسُوعُ: «اذْهَبْ يَا شَيْطَانُ! لأَنَّهُ مَكْتُوبٌ: لِلرَّبِّ إِلَهِكَ تَسْجُدُ وَإِيَّاهُ وَحْدَهُ تَعْبُدُ».

ልብ አድርግ “ስገድ” ለሚለው ቃል የመጣው “ተሥጁዱ” تَسْجُدُ ሲሆን “አምልክ” ለሚለው ቃል ደግሞ “ተዕቡዱ” تَعْبُدُ ነው። “እርሱንም ብቻ አምልክ” የሚለው ሃይለ-ቃል አምልኮ የአንድ አምላክ ብቻ ገንዘብ መሆኑን እንረዳለን። ይህንን እሳቤ ይዘን ለኢየሱስ “ሰገዱለት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሠጀዱሁ ለሁ” سَجَدُوا لَهُ ብቻና ብቻ ነው፦
ማቴዎስ 2፥11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም *ሰገዱለት*፥ فَلَمَّا رَأَوُا النَّجْمَ فَرِحُوا فَرَحاً عَظِيماً جِدّاً وَأَتَوْا إِلَى الْبَيْتِ وَرَأَوُا الصَّبِيَّ مَعَ مَرْيَمَ أُمِّهِ فَخَرُّوا وَسَجَدُوا لَهُ
ማቴዎስ 14፥33 በታንኳይቱም የነበሩት፡— በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፡ ብለው *ሰገዱለት*። وَالَّذِينَ فِي السَّفِينَةِ جَاءُوا وَسَجَدُوا لَهُ قَائِلِينَ: «بِالْحَقِيقَةِ أَنْتَ ابْنُ اللَّهِ!».
ዕብራውያን 1፥6 ያለው ከቶ ለማን ነው? ደግሞም በኵርን ወደ ዓለም ሲያገባ፡— የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ *ይስገዱ*፥ ይላል። وَأَيْضاً مَتَى أَدْخَلَ الْبِكْرَ إِلَى الْعَالَمِ يَقُولُ: «وَلْتَسْجُدْ لَهُ كُلُّ مَلاَئِكَةِ اللهِ».

“ሡጁድ” سُّجُود ፍጡራን ለፍጡራን እጅ መንሳትን ያመለክታል፤ “ይሰግዱ” ለሚለው ቃል ያገለገለው “የሥጁዱነ” َيَسْجُدُونَ ነው፦
ራእይ 3፥9 እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ፡— አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት *ይሰግዱ* ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ። هَئَنَذَا أَجْعَلُ الَّذِينَ مِنْ مَجْمَعِ الشَّيْطَانِ، مِنَ الْقَائِلِينَ إِنَّهُمْ يَهُودٌ وَلَيْسُوا يَهُوداً، بَلْ يَكْذِبُونَ: هَئَنَذَا أُصَيِّرُهُمْ يَأْتُونَ وَيَسْجُدُونَ أَمَامَ رِجْلَيْكَ، وَيَعْرِفُونَ أَنِّي أَنَا أَحْبَبْتُكَ. لأَنَّكَ حَفِظْتَ كَلِمَةَ صَبْرِي،እግዚአብሔር

ፈጣሪ ግን በግልጽ “የዕቡዱነኒ” َيَعْبُدُونَنِي ማለትም “ያመልኩኛል” ብሏል፦
ሐዋ. ሥራ 7፥7 ደግሞም ፡— እንደ ባሪያዎች በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርድባቸዋለሁ፥ ከዚህም በኋላ ይወጣሉ በዚህም ስፍራ *ያመልኩኛል*፤ አለ። وَتَكَلَّمَ اللهُ هَكَذَا: أَنْ يَكُونَ نَسْلُهُ مُتَغَرِّباً فِي أَرْضٍ غَرِيبَةٍ فَيَسْتَعْبِدُوهُ وَيُسِيئُوا إِلَيْهِ أَرْبَعَ مِئَةِ سَنَةٍ وَالْأُمَّةُ الَّتِي يُسْتَعْبَدُونَ لَهَا سَأَدِينُهَا أَنَا يَقُولُ اللهُ. وَبَعْدَ ذَلِكَ يَخْرُجُونَ وَيَعْبُدُونَنِي فِي هَذَا الْمَكَانِ.

ዋቢ መጽሐፍ ዐረቢክ ባይብል ይመልከቱ፦
Arabic/English Online Bible
http://www.copticchurch.net/cgibin/bible/

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቅዱሱ መንፈስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥102 እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር *ቁርኣንን ቅዱሱ መንፈስ እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው* በላቸው፡፡ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ

“ሩሑል ቁዱስ” ِرُوحُ الْقُدُس‎ ማለት “ቅዱሱ መንፈስ” ማለት ሲሆን ቁርኣን ላይ “ሩሑል ቅዱስ” የሚለው ቃል 4 ጊዜ ተጠቅሷል፤ ሚሽነሪዎች፦ “እናንተ ቁርኣናችሁን አትቀበሉትም እንጂ አላህ ታማኝ መንፈስ ወይም ቅዱስ መንፈስ ነው ይላል” ብለው በጥራዝ ነጠቅ መረጃ ከራሳቸው እሳቤ ጋር ለማጣጣም ይሞክራሉ፤ ይህንን ስሁት ሙግት ድባቅ ለማስገባት በኢስላም ስለ ቅዱስ መንፈስ ያለውን እሳቤ ጥልልና ጥንፍፍ አድርገን ኢንሻላህ እናያለን፦

ነጥብ አንድ
“መላእክት እና መንፈሱ”
ሚሽነሪዎች ቅዱሱ መንፈስ ከመላእክት “ወ” وَ ማለትም “እና” በሚል መስተጻምር ተቀምጧል፤ ስለዚህ ከመላእክት የተለየ ደግሞ ፈጣሪ ነው የሚል ስሁት ሙግት ያቀርባሉ፦
97፥4 በእርሷ ውስጥ *መላእክት እና መንፈሱ* በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْر
78፥38 *መንፈሱና መላእክቶቹም* የተሰለፉ ኾነው በሚቆሙ ቀን አል-ረሕማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ሰው ቢኾን እንጅ መነጋገርን አይችሉም፡፡ يَوْمَ يَقُومُ الرُّوحُ وَالْمَلَائِكَةُ صَفًّا ۖ لَّا يَتَكَلَّمُونَ إِلَّا مَنْ أَذِنَ لَهُ الرَّحْمَـٰنُ وَقَالَ صَوَابًا
70፥4 *መላእክቱና መንፈሱም* ልኩ አምሳ ሺሕ ዓመት በኾነ ቀን ውስጥ ወደ እርሱ ያርጋሉ፡፡ تَعْرُجُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ إِلَيْهِ فِي يَوْمٍ كَانَ مِقْدَارُهُ خَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ

ልብ አድርግ መንፈሱ ከመላእክት ጋር በጌታ አላህ ፈቃድ የሚወርድ እና ወደ አላህ የሚያርግ የሚያርግ ከሆነ የሚወርደውና የሚያርገው ቅዱስ መንፈስ እና አላህ ይለያያሉ። በተጨማሪም “ወ” ተብሎ በመስተጻምር መቀመጡ እልቅናና ክብርን ያመለክታል እንጂ ቅዱስ መንፈስ መልአክ አለመሆኑ መረጃ አይሆንም። ለምሳሌ ሱረቱል ፋቲሓህ ከቁርኣን “እና” በሚል መስተጻም ተለይቷል፦
15፥87 *ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትን እና ታላቁንም ቁርኣን በእርግጥ ሰጠንህ*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ

የሚደጋገሙ ሰባት አንቀጾች ሱረቱል ፋቲሓህ ከቁርአን “እና” በሚል መለየቱ ሱረቱል ፋቲሓህ ክብር ያላት ሱራ መሆኗን ለማሳየት እንጂ ቁርኣን አለመሆኗ እንደማያሳይ ሁሉ በተመሳሳይም ቅዱስ መንፈስ ከመላእክት ክብር መኖሩን ያሳያል እንጁ መልአክ አለመሆኑን አያሳይም፤ እሩቅ ሳንሄድ ጂብሪልና ሚካኤል ከመላእክት “ወ” በሚል መስተዋድድ ተነጥለዋል፤ ያ ማለት ጂብሪልና ሚካኤል መላእክት አይደሉም ማለት አይደለም፦
2፥98 ለአላህና ለመላእክቱ ለመልክተኞቹም ለጂብሪልም ለሚካልም ጠላት የኾነ ሰው አላህ ለእነዚህ ከሓዲዎች ጠላት ነው፡፡ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّلَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَرُسُلِهِ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَالَ فَإِنَّ اللَّهَ عَدُوٌّ لِّلْكَافِرِينَ
66፥4 በእርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፡፡ *ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ* ረዳቶቹ ናቸው፡፡ إِن تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ فَقَدْ صَغَتْ قُلُوبُكُمَا ۖ وَإِن تَظَاهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ مَوْلَاهُ وَجِبْرِيلُ وَصَالِحُ الْمُؤْمِنِينَ ۖ وَالْمَلَائِكَةُ بَعْدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ

ለምሳሌ፦ “ሚካኤል እና መላእክቱ” ተብሎ ሚካኤል ከመላእክት “እና” በሚል መነጠሉ ሚካኤል መልአክ አልነበረም ማለት አይደለም፦
ራእይ 12፥7 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ *ሚካኤል እና መላእክቱ* ዘንዶውን ተዋጉ።
ነጥብ ሁለት
“ታማኙ መንፈስ”
ይህ ቅዱስ መንፈስ ከጌታ አላህ ቁርአንን ማውረዱ በራሱ ቅዱስ መንፈስ ከአላህ ተለይቶ ተቀምጧል፦
16፥102 እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር *ቁርኣንን ቅዱሱ መንፈስ እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው* በላቸው፡፡ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ

“ረቢከ” رَّبِّكَ ማለትም “ጌታህ” ከሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ “ሚን” مِن ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህ የሚያሳየው ታማኙ መንፈስ ከነብያችን”ﷺ” ጌታ ከአላህ በታማኝነት ቁርኣንን እንዳወረደው ነው፦
26፥193 እርሱን *ታማኙ መንፈስ* አወረደው፤ نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ

ቅዱስ መንፈስ የዙፋኑ ባለቤት በሆነው በአላህ ዘንድ የእርሱ ባለሟል ነው፤ የአላህ ታማኝ መልእክተኛ ነው፦
81፥20 የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለቤት ዘንድ *ባለሟል* የኾነ፡፡ ذِى قُوَّةٍ عِندَ ذِى ٱلْعَرْشِ مَكِينٍۢ
81፥21 በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ *ታማኝ የኾነ ነው*፡፡ مُّطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ

ቅዱስ መንፈስ “ባለሟል” እና “ታማኝ” መባሉ በራሱ ላኪ እንዳለው ያሳያል፤ ይህም ታማኝ መንፈስ መልእክተኛ ተብሏል፦
19፥17 ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ *መንፈሳችንምም ወደ እርሷ ላክን*፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا
19፥19 «እኔ ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ *የጌታሽ መልክተኛ ነኝ*» አላት፡፡ قَالَ إِنَّمَا أَنَا رَسُولُ رَبِّكِ لِأَهَبَ لَكِ غُلَامًا زَكِيًّا

“መልእክተኛ” ከሆነ ላኪው አላህ ነው፤ ስለዚህ ቅዱስ መንፈስ ፈጣሪ አይደለም፤ አላህ ይህንን ቅዱስ መንፈስ ለእልቅናና ለክብር ወደራሱ በማስጠጋት በአገናዛቢ ቃል “መንፈሳችን” ይለዋል፤ ይህ ቅዱስ መንፈስ ደግሞ መለኮት እንዳልሆነ የምንረዳው የራሱ ጌታ አለው፤ ይህም ጌታው አላህ ነው፤ ነብያችን”ﷺ” ወደ አላህ በሩኩዕና በሡጁድ ጊዜ አላህን “የመላእክትና የመንፈስ ጌታ” ብለው ጠርተውቷል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 4, ሐዲስ 253
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሩኩዕና ሡጁድ ላይ፦ “ጥራት የሚገባህ ቅዱስ የመላእክት እና የሩሕ ጌታ” ይሉ ነበር። أَنَّ عَائِشَةَ، نَبَّأَتْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَقُولُ فِي رُكُوعِهِ وَسُجُودِهِ ‏ “‏ سُبُّوحٌ قُدُّوسٌ رَبُّ الْمَلاَئِكَةِ وَالرُّوحِ ‏”‏ ‏.‏
ነጥብ ሦስት
“ማበረታቻ”
አምላካችን አላህ በዚህ ቅዱስ መንፈስ ሰዎችን ያበረታል፤ ማበረታቻው ቅዱስ መንፈሱ ከሆነ የሚያበረታታው አላህ ከሆነ አላህ እና ቅዱስ መንፈሱ ይለያያሉ፦
2፥87 ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ ከበኋላውም መልክተኞችን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው፡፡ *በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ وَقَفَّيْنَا مِن بَعْدِهِ بِالرُّسُلِ ۖ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ
2፥253 እነዚህን መልክተኞች ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን፡፡ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አልለ፡፡ ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው፡፡ *በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው*፡፡ تِلْكَ الرُّسُلُ فَضَّلْنَا بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۘ مِّنْهُم مَّن كَلَّمَ اللَّهُ ۖ وَرَفَعَ بَعْضَهُمْ دَرَجَاتٍ ۚ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ وَأَيَّدْنَاهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ
5፥110 አላህ በሚል ጊዜ አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! በአንተና በእናትህ ላይ የዋልኩላችሁን ጸጋዬን አስታውስ፡፡ በሕፃንነት እና በከፈኒሳነት ሰዎችን የምትናገር ስትኾን *በቅዱስ መንፈስ ባበረታሁህ ጊዜ*፤ … ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ اذْكُرْ نِعْمَتِي عَلَيْكَ وَعَلَىٰ وَالِدَتِكَ إِذْ أَيَّدتُّكَ بِرُوحِ الْقُدُسِ تُكَلِّمُ النَّاسَ فِي الْمَهْدِ وَكَهْلًا ۖ وَإِذْ عَلَّمْتُكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ ۖ وَإِذْ تَخْلُقُ مِنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ بِإِذْنِي فَتَنفُخُ فِيهَا فَتَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِي ۖ وَتُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ بِإِذْنِي ۖ وَإِذْ تُخْرِجُ الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِي ۖ وَإِذْ كَفَفْتُ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَنكَ إِذْ جِئْتَهُم بِالْبَيِّنَاتِ فَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْهُمْ إِنْ هَـٰذَا إِلَّا سِحْرٌ مُّبِينٌ

“አበረታነው” ለሚለው ቃል የመጣው “አይየድናሁ” أَيَّدْنَاهُ ሲሆን “አበረታሁ” ለሚለው ቃል ደግሞ ‘አይየድቱከ” أَيَّدْتُكَ ነው።
ይህንን ቃላት ሌላ አንቀጽ ላይ “አበርትቷቸዋል” ለሚለው ቃል “አይየደሁም” أَيَّدَهُمْ በሚል መጥቷል፦
58፥22 በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፡፡ *ከእርሱም በኾነ መንፈስ አበርትቷቸዋል*፡፡ لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ ۚ أُولَـٰئِكَ كَتَبَ فِي قُلُوبِهِمُ الْإِيمَانَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٍ مِّنْهُ

ይህ የሚያበረታው ቅዱስ መንፈስ ጂብሪል መሆኑ በዚህ ሐዲስ ላይ መረዳት ይቻላል፤ ይህ ሐዲስ ፍንትውና ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው ሩሑል ቅዱስ ጂብሪል መሆኑን ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 78, ሐዲስ 178-179
አቢ ሰለማህ እንደተረከው፦ ሐሰን ኢብኑ ሳቢት አቢ ሁረይራህን ምስክር እንዲሆነው መጠየቁን እንዲህ ሲል ሰምቻለው፦ አቢ ሁረይራህ ሆይ! በአላህ እለምንሃለው፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ”፦ “ሐሰን ሆይ! ለአላህ መልእክተኛ መልስ ስጥ! አላህ ሆይ! በቅዱስ መንፈስ አበርታው” ሲሉ ሰምተሃልን? አቢ ሁረይራህም አዎ አለ። عَنْ أَبِي سَلَمَةَ بْنِ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ عَوْفٍ، أَنَّهُ سَمِعَ حَسَّانَ بْنَ ثَابِتٍ الأَنْصَارِيَّ، يَسْتَشْهِدُ أَبَا هُرَيْرَةَ فَيَقُولُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ نَشَدْتُكَ بِاللَّهِ هَلْ سَمِعْتَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ يَا حَسَّانُ أَجِبْ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ، اللَّهُمَّ أَيِّدْهُ بِرُوحِ الْقُدُسِ ‏”‌‏.‏ قَالَ أَبُو هُرَيْرَةَ نَعَمْ‏
አልበራዕ”ረ.ዐ” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” ለሐሰን፦ ” በቃላት ይቅርታ አድርግላቸው፤ ጂብሪል ከአንተ ጋር ነው” አሉት። عَنِ الْبَرَاءِ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ لِحَسَّانَ ‏ “‏ اهْجُهُمْ ـ أَوْ قَالَ هَاجِهِمْ ـ وَجِبْرِيلُ مَعَكَ ‏”‌‏.‏
ነጥብ አራት
“መልእክተኛ”
ሌሎች ጥቅሶች ላይ ቁርኣንን ቅዱስ እና ታማኝ መንፈስ በነብያችን”ﷺ” ልብ ላይ አወረደው ሲል ሌላ ቦታ ላይ ጂብሪል በነብያችን”ﷺ” ልብ ላይ አወረደው ይለናል፦
16፥102 እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር *ቁርኣንን ቅዱሱ መንፈስ እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው* በላቸው፡፡ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِالْحَقِّ لِيُثَبِّتَ الَّذِينَ آمَنُوا وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُسْلِمِينَ
26፥193-194 እርሱን *ታማኙ መንፈስ* አወረደው፤ ከአስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ *በልብህ ላይ አወረደው*። نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ عَلَىٰ قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنذِرِينَ
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ *እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ

ይህ ቅዱስ መንፈስ የወሕይ መልአክ ነው፤ አላህ ወደ ነብያት ወሕይ የሚያወርድበት መንገድ ሦስት ናቸው፤ እነርሱም፦ በራዕይ፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ያወርዳል፦
42:51 ለሰው” አላህ *“በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም*፤ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቢኢዝኒሂ” ማለትም “በፈቃዱ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” የሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው፤ ይህም የወህይ መልአክ ጂብሪል”አ.ሰ.” ነው፤ አላህ በሦስተኛው መንገድ ነው ቁርኣን ለነብያችን”ﷺ” ያወረደው፤ “መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን የሚያወርድለት ቢሆን እንጅ” የሚለው ይሰመርበት፤ ጂብሪልም መልአክ እንደመሆኑ መጠን ከአላህ ወደ ነብያችን”ﷺ” ቀልብ ቁርኣንን በአላህ ፈቃድ አውርዶታል፤ “ቢኢዝኒል ሏህ” بِإِذْنِ اللَّهِ ማለትም “በአላህ ፈቃድ” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ መልእክተኛ ደግሞ ከሰው ወይም ከመላእክት ነው የሚመረጠው፦
2፥97 ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት በላቸው፡፡ *እርሱ ቁርኣኑን ከበፊቱ ለነበሩት አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲኾን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና*፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ فَإِنَّهُ نَزَّلَهُ عَلَىٰ قَلْبِكَ بِإِذْنِ اللَّهِ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَهُدًى وَبُشْرَىٰ لِلْمُؤْمِنِينَ
22፥75 *አላህ ከመላእክት ውስጥ መልክተኞችን ይመርጣል፡፡ ከሰዎችም እንደዚሁ*፤ አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ
ማጠቃለያ
ሚሽነሪዎች ጂብሪል ቅዱስ መንፈስ መባሉ እና አላህ፦ “መንፈሳችን” ማለቱ ይገርማቸዋል፤ ለምሳሌ “መንፈስ በነጠላ ሲሆን በብዜት መናፍስት ይሆናል፤ ወደ ባይብሉ ስናጠቃልል መላእክት ቅዱሳን መናፍስት ናቸው፦
ዕብራውያን 1፥14 ከቶ ለማን ብሎአል? ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ *የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት* አይደሉምን?

ቅዱስ መንፈስ በነጠላ ሲሆን በብዜት ቅዱሳን መናፍስት ይባላሉ፤ መላእክት የፈጣሪ መንፈሶች ተብለዋል፦
ራእይ 5፥6 *እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው*።

ስለዚህ በነጠላ ገብርኤል ቅዱስ መንፈስ መባሉ እና አላህ ወደራሱ በማስጠጋት በአገናዛቢ “መንፈሳችን” ማለቱ አያስደንቅም። ምክንያቱም ፈጣሪ መንፈስን እልካለው ብሎ የላከው መልአኩን ነው፦
ኢሳይያስ 37፥7 እነሆ፥ በላዩ *መንፈስን እሰድዳለሁ*፥ ወሬንም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት አላቸው።
ኢሳይያስ 37፥36 *የእግዚአብሔርም መልአክ* ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የነቢያችን"ﷺ" ሥርወ-ግንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥129 «ጌታችን ሆይ! *በውስጣቸውም ከእነርሱ የኾነን መልክተኛ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክ*፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» የሚሉም ሲኾኑ፡፡ رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيم

የሚሽነሪዎች ጉዳይ መላ ቅጡ፣ ውጥን ቅጡ እና ቅጥ አንባሩ የጠፋበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፤ እሥልምና በፍጥነት ማደጉ ሰለሚያብከነክናቸውና ስለሚከነክናቸው ይህንን ብርሃን ለማጥፈት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም። የነቢያችን"ﷺ" ሥርወ-ግንድ"descendant" እንደማይታወቅ ለማስመስል ሲቀጥፉ ይታያል፤ እስቲ ስለ ነቢያችን"ﷺ" ሥርወ-ግንድ እንይ። ኢብራሂም እና ልጁ ኢሥማዒል አላህን፦ "ጌታችን ሆይ! ለአንተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች ሕዝቦችን አድርግ" ብለው ለምነዋል፦
2፥127 *ኢብራሂም እና ኢስማኢልም* «ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡ አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና» የሚሉ ሲኾኑ ከቤቱ መሠረቶቹን ከፍ ባደረጉ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ يَرْفَعُ إِبْرَٰهِـۧمُ ٱلْقَوَاعِدَ مِنَ ٱلْبَيْتِ وَإِسْمَٰعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّآ ۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ
2፥128 «ጌታችን ሆይ! *ለአንተ ታዛዦችም አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች ሕዝቦችን አድርግ*፡፡ ሕግጋታችንንም አሳውቀን፡፡ በእኛም ላይ ተመለስን፤ አንተ ጸጸትን ተቀባዩ ሩኅሩኅ አንተ ብቻ ነህና፡፡» رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ وَأَرِنَا مَنَاسِكَنَا وَتُبْ عَلَيْنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

“ታዛዦችም” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙሥሊመይኒ” مُسْلِمَيْنِ ሲሆን ሙተና”dual” ነው፤ ይህም ሁለቱን አበው ኢብራሂምና ኢሥማዒል ያሳያል፤ በመቀጠል ከዘሮቻቸውም ለአላህ “ሙሥሊሚን” مُسْلِمَيْنِ ማለትም “ታዛዦች” አድርግ ብለው ፀልየዋል፤ "ዙሪየቲና" ذُرِّيَّتِنَا ማለት "ዘሮቻችን" ማለት ሲሆን ይህንን ሥርወ-ግንድ"offspring" የያዙት ቅድሚያ የኢብራሂም እና የልጁ ኢሥማዒል ሥርወ-ግንድ ናቸው፤ ከእነርሱ ውስጥ መልእክተኛ እንዲመጣ ኢብራሂም እና ልጁ ኢሥማዒል አላህን ተማጽነዋል፦
2፥129 «ጌታችን ሆይ! *በውስጣቸውም ከእነርሱ የኾነን መልክተኛ በእነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን ከክህደት የሚያጠራቸውንም ላክ*፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» የሚሉም ሲኾኑ፡፡ رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيم

"ከእነርሱ" የሚለው ሃይለ-ቃል የሚወክለው "ዘሮቻችን" ብለው የተናገሩለትን ነው፤ በእነዚህ ሥርወ-ግንድ አላህ የአንድ አምላክ እሳቤን ቀሪ ቃል አድርጓል፤ ለዚያም ነው አላህ እነርሱን፦ “የአባታችሁን” ሃይማኖት ተከተሉ ያላቸው፦
43፥26 *ኢብራሂምም ለአባቱና ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ «እኔ ከምትግገዙት ሁሉ ንጹሕ ነኝ፡፡»* وَإِذْ قَالَ إِبْرَٰهِيمُ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦٓ إِنَّنِى بَرَآءٌۭ مِّمَّا تَعْبُدُونَ
43፥27 «ከዚያ *ከፈጠረኝ በስተቀር አልግገዛም*፡፡ እርሱ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡» إِلَّا ٱلَّذِى فَطَرَنِى فَإِنَّهُۥ سَيَهْدِينِ
43፥28 *በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ በአንድ አምላክ ማመንን ቀሪ ቃል አደረጋት*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةًۢ بَاقِيَةًۭ فِى عَقِبِهِۦ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
22፥78 በአላህም ሃይማኖት ተገቢውን ትግል ታገሉ፡፡ እርሱ መርጧችኋል፡፡ በእናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፡፡ *”የአባታችሁን ሃይማኖት”* ተከተሉ፡፡ وَجَاهِدُوا فِي اللَّهِ حَقَّ جِهَادِهِ ۚ هُوَ اجْتَبَاكُمْ وَمَا جَعَلَ عَلَيْكُمْ فِي الدِّينِ مِنْ حَرَجٍ ۚ مِّلَّةَ أَبِيكُمْ إِبْرَاهِيم

አምላካችን አላህ ከእነርሱ ሥርወ-ግንድ ነቢያችንን"ﷺ" መልእክተኛ አድርጎ ልኳል፦
2፥151 *"በውስጣችሁ ከእናንተው የኾነን በእናንተ ላይ አንቀጾቻችንን የሚያነብላችሁና የሚያጠራችሁ፣ መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራችሁ፣ ታውቁት ያልነበራችሁትንም ነገር የሚያሳውቃችሁ የኾነን መልክተኛ እንደላክን"* ጸጋን ሞላንላችሁ፡፡ كَمَا أَرْسَلْنَا فِيكُمْ رَسُولًا مِّنكُمْ يَتْلُو عَلَيْكُمْ آيَاتِنَا وَيُزَكِّيكُمْ وَيُعَلِّمُكُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُعَلِّمُكُم مَّا لَمْ تَكُونُوا تَعْلَمُونَ
62፥2 እርሱ ያ በመሃይሞቹ ውስጥ አንቀጾቹን በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፣ ከማጋራት የሚያጠራቸውም፣ *መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸውም የኾነን መልእክተኝም ከእነርሱ ውስጥ የላከ ነው*፡፡ እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስሕተት ውስጥ ነበሩ፡፡ هُوَ الَّذِي بَعَثَ فِي الْأُمِّيِّينَ رَسُولًا مِّنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِهِ وَيُزَكِّيهِمْ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَإِن كَانُوا مِن قَبْلُ لَفِي ضَلَالٍ مُّبِينٍ

ነቢያችንም"ﷺ" በሐዲስ ከኢብራሂም እና ከኢሥማዒል ሥርወ-ግንድ እንደመጡ አበክረውና አዘክረው ተናግረዋል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 49, ሐዲስ 3964
ዋሲላህ ኢብኑል አሥቃዕ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ከኢብራሂም ልጅ ኢሥማዒልን መረጠ፤ ከኢሥማዒል ትውልድ የኪናናን ሥርወ-ግንድ መረጠ፤ ከኪናናህ ሥርወ-ግንድ ቁረይሽን መረጠ፤ ከቁረይሽ የሃሺምን ሥርወ-ግንድ መረጠ፤ ከሃሺም ሥርወ-ግንድ እኔን መረጠ"*። عَنْ وَاثِلَةَ بْنِ الأَسْقَعِ، رضى الله عنه قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَى مِنْ وَلَدِ إِبْرَاهِيمَ إِسْمَاعِيلَ وَاصْطَفَى مِنْ وَلَدِ إِسْمَاعِيلَ بَنِي كِنَانَةَ وَاصْطَفَى مِنْ بَنِي كِنَانَةَ قُرَيْشًا وَاصْطَفَى مِنْ قُرَيْشٍ بَنِي هَاشِمٍ وَاصْطَفَانِي مِنْ بَنِي هَاشِمٍ
ኢብራሂም እና ኢሥማዒል የፊተኛዎቹ አባቶች ናቸው፤ እነርሱ ወሕይ መጥቶላቸው አስጠንቃቂዎች ነበሩ፤ ነቢያችን"ﷺ" ከእነርሱ ሥርወ-ግንድ የሆኑ አስጠንቃቂ ናቸው፦
23፥68 የቁርኣንን ንግግሩንም አያስተነትኑምን ወይስ *“ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው” ያልመጣ ነገር መጣባቸውን?* أَفَلَمْ يَدَّبَّرُوا الْقَوْلَ أَمْ جَاءَهُم مَّا لَمْ يَأْتِ آبَاءَهُمُ الْأَوَّلِينَ
53:56 ይህ *”ከፊተኞቹ አስጠንቃቂዎች” ጎሳ የሆነ አስጠንቃቂ ነው*። هَـٰذَا نَذِيرٌ مِّنَ النُّذُرِ الْأُولَىٰ

ይህ ኂስ የሚሰጥበት ነጥብ አልነበረም። እሩቅ ሳንሄድ ወደ ባይብሉ ስንገባ የኢየሱስ የዘር ሃረጉ አይታወቅም። በማቴዎስ ሆነ በሉቃስ የዘር ሃረግ የዮሴፍ እንጂ የማርያም ሽታው የለም። ዮሴፍ ደግሞ እንደ ባይብሉ የማርያም እጮኛ እንጂ የኢየሱስ ወላጅ አባት አይደለም። ስለ ዮሴፍም አባትና የአባቱ የዘር ሃረግ ቢሆን ማቴዎስ እና ሉቃስ የዘገቡት ይለያያል። የማቴዎስ ጸሐፊ የዮሴፍን አባት ያዕቆብ አድርጎ በሰሎሞን መስመር ይቆጥራል፤ ሉቃስ ደግሞ የዮሴፍን አባት ዔሊ አድርጎ በናታን መስመር ይቆጥራል፦
ማቴዎስ 1፥7 *ሰሎሞንም* ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤
ማቴዎስ 1፥16 *ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ*።
ሉቃስ 3፥23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር እንደመሰላቸው *የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ የኤሊ ልጅ*፥
ሉቃስ 3፥31 የሜልያ ልጅ፥ የማይናን ልጅ፥ የማጣት ልጅ፥ *የናታን ልጅ*፥ የዳዊት ልጅ፥

አንዱ እንጀራ አባቱ ሁለተኛ ወላጅ አባቱ ካላችሁ ከዐውደ-ንባቡ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባችኃል። ከአብርሐም እስከ ዮሴፍ ስንት ትውልድ ነው? 40 ትውልድ ወይስ 57 ትውልድ ? የማቴዎስ ጸሐፊ 40 ትውልድ ሲዘረዝር ሉቃስ ደግሞ 58 ትውልድ ይዘረዝራል፣ የቱ ነው ትክክል? ከ 260–340 ዓመተ-ልደት"AD" ይኖር የነበረው የቂሳሪያው አውሳቢዮስ፦ "ማቴዎስ የዮሴፍን ሲዘግብ ሉቃስ የማርያምን ዘግቧል" ይላል፤ ይህ ግምታዊ እንጂ ውኃ የሚቋጥር ባይብላዊ መረጃ የለውም።
ነጥባችን፦ "የኢየሱስ የዘረግ ሃረግ ባይብል ላይ ሽታው የለም" የሚል ነው። የማርያም አባት እና እናት ስማቸው ሆነ ማንነታቸው በባይብል አይታወቅም። ነገር ግን ባይብል ላይ ሳይሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትውፊት አዋልድ በሚባለው በድርሳነ-ጽዮን መጽሐፍ የማርያም የዘር ሃረግን እንዲህ ይገልጻል፦
📚ድርሳነ-ጽዮን ዘሐሙስ 44 ገጽ 158.
ሜሊኪ ዮሐና
/ \ |
ሴም ሌዊ ኤሊ
| |
ሆናሲን ሜሊኪን
| |
ቀለምዮስን ማቴን
| |
ኢያቄምን ሐና
\ /
ማ ር ያ ም
|
ኢየሱስ
ይህን ይመስላል። ይህ አቆጣጥር ባይብል ላይ ፍንጩ እንኳን የለም። ግን የአንድ ነቢይ ሥርወ-ግንዱ ከየት መምጣት መገለጽ ለአንድ ነቢይ መስፈርት ነውን? አዎ ካላችሁ ይህንን ነቢይ ስሙ ማን ነው? የእናትና የአባቱ ስም ማን ነው? የዘር ሃረጉ ከየት ነው? መቼ ተወለደ? በስንት ዓመቱ ሞተ?
መሣፍንት 6፥8 እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ልጆች *ነቢይ ላከ*፥ እርሱም አለ፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፥ ከባርነትም ቤት አስለቀቅኋችሁ፤

በመሳፍንት መጽሐፍ ዐውደ-ንባብ ላይ የዚህ ነቢይ አይደለም ሥርወ-ግንዱ የራሱ ማንነት አይታወቅም። እና ያ ነቢይ ነቢይ አይደለምን? "አይ ነው፤ ግን አስፈላጊ ቢሆን መረጃው ይቀመጥ ነበር" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን የሙግት ነጥብ በዚህ ሒሳብ ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
መህር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

17፥32 ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!

መግቢያ
“መህር” مَهر‌‎ ማለት ለጋብቻ የሚሰጥ “ጥሎሽ”dowry” ሲሆን በኢስላም ከተጠቀሱት የሚስት ሃቅ አንዱ ነው፤ ህጋዊ ያልሆነ ፃታዊ ግንኙነት “ዚና” زِّنَىٰٓ ማለትም “ዝሙት” ይባላል፤ በቁርአን ዚና ብቻ ሳይሆን የዚና መቃረቢያዎች መዳራትንም ጨምሮ እንድንርቅ ያዘናል፤ ፍፁም ምዕመናን ማለት የማያመነዝሩትም ናቸው፦
17፥32 ዝሙትንም አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!
25:68 አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፤ “የማያመነዝሩትም” ናቸው፤ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል።

“ዝሙት” ሴጋን”masturbation”፣ ተመሳሳይ ፃታ ግንኙነት”homosexual” ወዘተ ያጠቃልላል፤ ይህም ወሰን ማለፍ የሆነ ዝሙት ነው፦
23:6-7 “በሚስቶቻቸው” أَزْوَاجِهِمْ ወይም “እጆቻቸው በያዟቸው ባሪያዎች” مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ ላይ ሲቀር፡፡ “እነርሱ በእነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና”፡፡ “ከዚህም ወዲያ የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ወሰን አላፊዎች” ናቸው፡፡
70:30-31 “በሚስቶቻቸው” أَزْوَاجِهِمْ ወይንም “እጆቻቸው በያዙዋቸው ባሮች” مَلَكَتْ أَيْمَانُهُمْ ላይ ሲቀር። “እነርሱ በእነዚህ የማይወቀሱ ናቸውና”። “ከዚያም ወዲያ የፈለገ ሰው፣ እነዚያ እነርሱ ድንበር አላፊዎች” ናቸው።

ኢስላም ስለ ዝሙት የሚያስተምረውን አስተምሮት መዘርዘር ጊዜም አይበቃም፤ ነገር ግን ሚሽነሪዎች ሆን ብለው በገንዘብ ዝሙት ማድረግ እንደሚቻል እውር ድንብር የሆነ ፀለምተኛ ሙግት ይሟገታሉ፤ እስቲ ለዚያ ድምዳሜ አድርሶናል ያሉትን አንቀፅ በሰላና በሰከነ አዕምሮ እንየው፦
4፥24 ከሴቶችም ጥብቆቹ እጆቻችሁ የያዙዋቸው ሲቀሩ በእናንተ ላይ እርም ናቸው፤ ይህን አላህ በእናንተ ላይ ጻፈ፤ ከዚህችውም ከተከለከሉት ወዲያ ጥብቆች ሆናችሁ ዝሙተኞች ሳትሆኑ “በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ” ለእናንተ ተፈቀደ፤ “”ከእነሱም”” በእርሱ በመገናኘት የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች ” ግዴታ ሲኾን መህሮቻቸው ግዴታ ሲሆን ስጧቸው፤ ከመወሰንም በኋላ በተዋደዳችሁበት ነገር በእናንተ ላይ ኃጢያት የለም። አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ النِّسَاءِ إِلَّا مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ كِتَابَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَأُحِلَّ لَكُمْ مَا وَرَاءَ ذَلِكُمْ أَنْ تَبْتَغُوا بِأَمْوَالِكُمْ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَافِحِينَ فَمَا اسْتَمْتَعْتُمْ بِهِ مِنْهُنَّ فَآتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ فَرِيضَةً وَلَا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ فِيمَا تَرَاضَيْتُمْ بِهِ مِنْ بَعْدِ الْفَرِيضَةِ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا ” سورة النساء ።

1. የአውድ ሙግት
ይህ አንቀፅ ከላዩ አውዱ ማግባት የተከለከሉትን ሴቶች ይዘረዝራል፤ እነሱም፡- የእንጀራ እናትህ፣ ወላጅ እናትህ፣ ሴት ልጅህ፣ እህትህ፣ የአባትህ እህት አክስትህ፣ የእናትህ እህት ሹሜ፣ የወንድምህ ሴት ልጅ፣ የእህትህ ሴት ልጅ፤ ያልወለደችህ የጥቢ እናትህ፣ ከእናትህ እርሷ ወይም ከእናትዋ አንተ በመጥባት በጥቢ የተገናኛችሁ የጥቢ እህትህ፣ የሚስትህን እናት፣ ሚስትህ ከበፊት ባሏ የወለደቻት ሴት ልጇን፣ የወንድ ልጅህን ሚስት፣ ሁለት እህትማማቾችን በአንድ ጊዜ እና የሰው ሚስት ናቸው፦
4:22-23 ከሴቶችም ከአባቶቻችሁ ያገቡዋቸዉን አታግቡ። ትቀጡበታላችሁ ያለፈው ሲቀር፣ እርሱ መጥፎና የተጠላ ሥራ ነውና መንገድነቱም ከፋ! እናቶቻችሁ፣ ሴት ልጆቻችሁም፣ እኅቶቻችሁም፣ አክስቶቻችሁም፣ የሹሜዎቻችሁም፣ የወንድም ሴቶች ልጆችም፣ የእኅት ሴቶች ልጆችም፣ እነዚያም ያጠቡዋችሁ እናቶቻችሁ፣ ከመጥባት የሆኑትም እኅቶቻችሁ፣ የሚስቶቻችሁም እናቶች እነዚያም በጉያዎቻችሁ ያሉት፣ የነዚያ በነርሱ የገባችሁባቸው ሚስቶቻችሁ ሴቶች ልጆች፣ ልታገቧቸው በእናንተ ላይ እርም ተደረጉባችሁ። በእነርሱም በሚስቶቻችሁ ያልገባችሁባቸው ብትሆኑ፣ በፈታችኋቸው ጊዜ ሴቶች ልጆቻቸውን ብታገቡ በእናንተ ላይ ኅጢያት የለባችሁም። የነዚያ ከጀርባዎቻችሁ የሆኑት ወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችም፣ በሁለት እኅትማማቾችም መካከል መሰብሰብ እንደዚሁ እርም ነው፤ ግን ከዚህ በፊት ያለፈው ሲቀር፣ እርሱንስ ተምራችኋል አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።

በመቀጠል አውዱ “በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ ተፈቀደ” የሚለው ቃል “”ዝሙተኞች ሳትሆኑ”” ለሚለው ቃል ተቃራኒ ሆኖ የመጣ ቃል ነው፤ የዝሙት ተቃራኒ ደግሞ ትዳር ነው፤ በመቀጠል አውዱ “”ከእነሱም”” ይለናል፤ “እነሱም” የተባሉት “በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ ተፈቀደ” የተባሉት ለማመልከት የመጣ ተሳቢ ተውላጠ ስም ነው፤ ይህም ገንዘብ መህር መሆኑን ለማሳየት “”መህሮቻቸው”” በማለት ይናገራል፦
4፥24 ከሴቶችም ጥብቆቹ እጆቻችሁ የያዙዋቸው ሲቀሩ በናንተ ላይ እርም ናቸው፤ ይህን አላህ በእናንተ ላይ ጻፈ፤ ከዚህችውም ከተከለከሉት ወዲያ ጥብቆች ሆናችሁ ዝሙተኞች ሳትሆኑ “በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ” ለእናንተ ተፈቀደ፤ “”ከእነሱም”” በእርሱ በመገናኘት የተጠቀማችሁባቸውን ሴቶች ” ግዴታ ሲኾን መህሮቻቸው ግዴታ ሲሆን ስጧቸው፤ ከመወሰንም በኋላ በተዋደዳችሁበት ነገር በእናንተ ላይ ኃጢያት የለም። አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና።
2. የተዛማች ሙግት
ጋብቻን ጋብቻ ከሚያሰኘው አንዱ በህጋዊ እና እውቅና ተሰጦት መህርን ሰጥቶ ማግባት ነው፤ ከዚያ ውጪ እውቅና እና ህጋዊ ያልሆነ የሚስጢር ወዳጅ ወይም የስርቆሽ ወዳጅ ማለትም የከንፈር ወዳጅ ሆነ ዘማዊነት ማለትም አንሶላ መጋፈፍ ሃራም ነው፦
5፥5 ከምእምናት ጥብቆቹም ከነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ክተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም ዘማዊዎች እና የሚስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትሆኑ ጥብቆች ሆናችሁ “”መህሮቻቸውን በሰጠችኋቸው ጊዜ”” ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው፤
4:25 ከእናንተም ውስጥ ጥብቆች ምእምናት የሆኑትን ለማግባት ሀብትን ያልቻለ ሰው እጆቻችሁ ንብረት ካደረጓቸው ከምእመናት፣ ወጣቶቻችሁ ባሪያን ያግባ፤ አላህም እምነታችሁን ዐዋቂ ነው፤ ከፊላችሁ ከከፊሉ የተራባ ነው። ባሮችን በጌቶቻቸውም ፈቃድ አግቡዋቸው። “መህሮቻቸውንም” በመልካም መንገድ ስጧቸው፤ ጥብቆች ሆነው ዝሙተኞች ያልሆኑ የስርቆሽ ወዳጆችንም ያልያዙ ሲኮኑ አግቧቸው፤

“በገንዘቦቻችሁ ልትፈልጉ ተፈቀደ” የተባለው ገንዘብ መህር መሆኑ ሌሎች አንፆች ያስረዳሉ፦
60፥10 ያወጡትንም “ገንዘብ” ስጧቸው፤ “መህራቸውንም” በሰጣችኋቸው ጊዜ ብታገቡዋቸው በእናንተ ላይ ኃጢያት የለባችሁም።
4፥4 ሴቶችንም መህሮቻቸውን በደስታ ስጡ፡፡ ለእናንተም ከእርሱ አንዳችን ነገር ነፍሶቻቸው ቢለግሱ መልካም ምስጉን ሲኾን ብሉት፡፡
4፥19 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱና ግልጽን መጥፎ ሥራ ካልሠሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱ ልታጉላሏቸውም ለእናንተ አይፈቀድም፤ በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፤ ብትጠሉዋቸውም ታገሱ፡፡ አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡

መደምደሚያ
ለመሆኑ ባይብል ስለ ጥሎሽ ምን ይላል? በባይብል ላይ ጥሎሽ የተባለው ቃል “ማጫ” ይባላል፤ ይህም ለትዳት የሚሰጥ ንብረት ነው፤ አንድ ወንድ ከጋብቻ በፊት ሴትን ቢደፍራት ማጫዋን ሰጥቶ ሚስት ያደርጋታል፤ ይህም መህር አምሳ የብር ሰቅል ነው፦
ዘፍጥረት 34፥12 ብዙ “ማጫ” እና እጅ መንሻ አምጣ በሉኝ፥ በነገራችሁኝም መጠን እሰጣለሁ፤ ይህችን ብላቴና ግን “አጋቡኝ”።
ዘጸአት 22፥16 ሰው ያልታጨችውን ድንግል ቢያስታት፥ ከእርስዋም ጋር ቢተኛ፥ “ማጫዋን” ሰጥቶ ሚስት ያድርጋት።
ዘዳግም 22፥29 ያ የደረሰባት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናይቱ አባት ይስጥ፤ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።

ዳዊት ሜልኮልን ለማግባት የሰጠው መህር የመቶ ወንድ ብልት ቆርጦ ነው፦
1ኛ ሳሙኤል 18፥25-27 ሳኦልም ዳዊትን በፍልስጥኤማውያን እጅ ይጥለው ዘንድ አስቦ፦ የንጉሥን ጠላቶች ይበቀል ዘንድ #ከመቶ ፍልስጥኤማውያን #ሸለፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይሻም ብላችሁ ለዳዊት ንገሩት አላቸው። የሳኦልም ባሪያዎች ይህን ቃል ለዳዊት ነገሩት፥ ለንጉሥም አማች ይሆን ዘንድ ዳዊትን ደስ አሰኘው። ዳዊትና ሰዎቹም ተነሥተው ሄዱ፥ ከፍልስጥኤማውያንም #መቶ ሰዎች ገደሉ፤ ዳዊትም ለንጉሥ አማች ይሆን ዘንድ ሰለባቸውን አምጥቶ በቍጥራቸው ልክ ለንጉሡ ሰጠ። ሳኦልም ልጁን ሜልኮልን ዳረለት።

የወንድ ብልት መህር? ይህ ነው እንግዲህ መህር።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአክሱም ሙስሊሞች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም በሆነው።

14፥42 *አላህንም በአዛኝደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው*፡፡ وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

አክሱም ላይ የአክሱም ሥልጣኔ በነበረበት ሰአት የተተከለው የ24 ሜትር ወይም 78 ጫማ ርዝመት እና 160 ቶን የሚመዝነው የአክሱም ሃውልት ነው። ይህ ሃውልት የወንድ ሃፍረተ-ስጋ ምስል ነው። ከኩሻይቲክ የሜሮይ አገዛዝ የተወሰደ ይህ ምስል ቅድመ-ክርስትና በአክሱም ላይ ይመለክ እንደነበረ ታሪክ በወርቃማ ብዕሩ ያሰፈረው ጉዳይ ነው። ክርስትና አክሱም ሲገባ ይህንን ጣዖት ከማፍረስ ይልቅ አጠገቡ በአራተኛው ክፍለ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስትናን ይዞ በገባው በአቡነ ሰላማ ማለትም በፍሬምናጦስ ከሣቴ ብርሃን ዘመን የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ተገንብቷል፤ አሁን ያለችውን ደግሞ በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ-መንግሥት የተሠራች ናት።

ዛሬ አክሱም ውስጥ ያሉት ሙስሊሞች መስኪድ እንዳይገነቡ የአክሱም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች አግደዋል። ይህም የሆነው በሁለት ተልካሻ ምክንያት ነው። አንደኛው በአምልኮት ቦታቸው ላይ ባዕድ አምልኮ እንዳይገባ ሲሆን ሁለተኛው ሳውዲ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ስላልተገነባ እኛም ጋር አይገነባም የሚል ሁለት ተልካሻ ምክንያቶች ይዘዋል።

“ምክንያት አንድ”
በአምልኮት ቦታችሁ ላይ ባዕድ አምልኮ እንዳይገባ የሚለው ተልካሻ ምክንያት የሚሆንበት ቅድሚያ እዛው አክሱም ውስጥ ሲመለክ የነበረውን ጣዖት በቅርስነት ከጽዮን ቤተክርስቲያን ጋር ከመደበል ይልቅ አፈራርሶ ማቃጠል ይጠበቅባችሁ ነበር፦
ዘዳግም 7፥5 ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ *ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ*።

ሁለተኛ የሙስሊም አምልኮ ባዕድ አምልኮ ሳይሆን ጥንት የነበሩት ነብያት ሲያመልኩት የነበረው የዓለማቱ ጌታን አላህን ብቻ በብቸኝነት የሚመለክበት ነው። ባይሆን በአንድ አላህ ላይ ሁለት አካላትን ደብላችሁ ማምለካችሁ፣ ሰው የሆነውን ኢየሱስን ማምለካችሁ፣ ሁሉን ማወቅ፣ መስማት፣ ማየት የማይችሉትን መላእክትና እና ሰዎች መጥራታችሁ፣ መለማመናችሁ፣ ለስእልና ለሃውልት መስገዳችሁ ይህ ነው ባዕድ አምልኮ። ንገሩኝ ባይ አትሁኑ።
ሦስተኛ ጥንት የነበረው የሙሴ ታቦት ጽዮን ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የለም። ለምን ይዋሻል? አሁን አርስቱ ስላልሆነ “ጽላት እና ታቦት” የሚለውን የእኔን መጣጥፍ አንብቡት።
አራተኛ አክሱም ጽዮን የተቀደሰች ናት የሚል የባይብል መረጃ የለም። አይ ታቦቱ ነው ቅዱስ ያረገው ከተባለ ራጉኤል ውስጥም ታቦት አለ፤ አንዋር መስጂድን ምን ልታረጉት ነው? ምነው የቅድስና ጉዳይ ከሆነ አክሱም ዝሙት የሚካሄድበት እና ዘፈንና ዳንስ የሚሞዘቅበት መሸታ ቤት የለምን? ጠጅ ቤትና ጠላ ቤትስ? ለነገሩ ለካስ ጠጅና ጠላ ጽዮን ቤተክርስቲያን ውስጥም አለ አይደል።

“ሁለተኛው ምክንያት”
ሳውዲ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ስላልተገነባ እኛም ጋር አይገነባም የሚለው ተልካሻ ምክንያት የሚሆንበት ከመነሻው እኛ ኢትዮጵያውያን እንጂ ዐረባውያን አይደለንም። ሲቀጥል ሳውዲ ቤተ-ክርስቲያን የማይገነባው ሳውዲ ውስጥ ክርስቲያን ስለሌለ እንጂ አሁን ከተለያዩ አገር ለሥራ የመጡ ዜጎች የአምልኮ ቦታ ያስፈልጋቸው ተብሎ ቤተ-ክርስቲያን ሊሰራላቸው ተፈራርመው ጨርሰዋል። በኢስላምም አህለል ዚማህ ማለትም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በኢስላም አገር ውስጥ ጂዚያህ እስከከፈሉ ድረስ የአምልኮ ነጻነት አለ።
ሢሰልስ 100% ሙስሊም ያለበት ከተማ ውስጥ ቤተ-ክርስቲያን አለ።
ኢትዮጵያ ደግሞ የሁለቱም ሃይማኖት አገር ናት፤ የምትመራበት መርሕ በሕገ መንግሥት እንጂ በፍትሐ-ነገሥት ወይም በሲኖዶስ አሊያም በመጅሊስ አይደለም። ሕገመንግሥቱ አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 2 እንዲህ ይላል፦
“የሃይማኖት ተከታዮች ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት እና ለማደራጀት የሚያስችሏቸውን የሃይማኖት ትምህርት እና ተቋማት ማቋቋም ይችላሉ።”

ምን ትፈልጋለህ? አክሱም ላይ ያሉት ሙስሊሞች መስጊድ መገንባት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ነው። ከዛም አልፈው የሚቀበሩበት መቃብርም ነው የተነፈገት፤ ለቀብር 32 ኪሎ ሜትር ወጥተው ይቀብራሉ፤ የአክሱም ኢአማንያኑ ግን ይቀበራል፤ ዘይገርም። ሙስሊም ሆነው እንዲኖሩ ከተፈቀደ መቃብርና ማምለኪያ ቦታ መከልከል ዳይዳው ምንድን ነው? ሁለተኛ ዜጋ አርጎ ለማኖር ነው? በመነጋገር ከማመን ይልቅ በዱላ እመን የሚለውን የአጼዎቹ ሥርዓት ናፋቂዎቹ፦ “አክሱም ላይ መስኪድ እሰራለው ያለ ደሙ ይፈሳታል” የሚል ቃለ ፉከራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲለፈልፉ ይደመጣል፤ ክርስትና ፍቅር ናት፣ ክርስትና “”ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤ እንዲከስህም እጀ ጠባብህንም እንዲወስድ ለሚወድ መጎናጸፊያህን ደግሞ ተውለት፤ ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ። ለሚለምንህ ስጥ፥ ከአንተም ይበደር ዘንድ ከሚወደው ፈቀቅ አትበል”” የሚለው ንግግር ስብከት ላይ ብቻ ነው የሚሰራው ማለት ነው። ተግባር ላይ ዜሮ።

እናንተ እነማን ናችሁ? ምንስ ስለሆናችሁ ነው? የመከልከል ሞራሉም ብቃቱም የላችሁም። በዚህ ነጥብ ላይ ማንም ምንም ናችሁ። ሕገ-መንግሥቱን የማያከብር ግለሰብ ሆነ ተቋም ሕገወጥ ነው። አጼዎቹ አንዴ በግድ ካልተጠመቃችሁ፣ አንዴ የኢስላም ልጅ ትምህርት አያስፈልገውም እየተባለ ከትምህርት ገበታው ሲያባርር አባት ለሰራው ልጅ አይጠየቅም በሚል መርሕ በይቅርታ ስናልፋችሁ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ስትሞሉ ፈለጋችሁ? የሃይማኖት ነፍጠኞች እንደሆናችሁ ግብአታቹ ያሳብቅባችኃል፤ በመጠበብ ዘመን የእናንተ መጥበብ ያጅባል። የአክሱም ሙስሊሞችን በደል የሚካሱበትን ቀን አላህ ያፍጥነው! አሚን። በዓለም ላይ በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰው በደል ታሪክ ይቁጠረው፤ አላህ የፍርዱ ቀን ለበደለኞች ቅጣት አዘጋጅቷል። አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፤ የሚያቆያቸው እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ብቻ ነው፦
14፥42 *አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው*፡፡ وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም