ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
“ለ”ተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ እየተባለ ለምንድን ነው ለግዑዝ ነገር የፀጋ ስግደት የሚሰገድለት? የሚሰማበት ዐቅል የት አለውና ነው ምስጋናስ የሚቅብለት? ይህንን ስንላቸው ለመስቀል ስግደት እንደሚገባው ይህ ጥቅስ ያሳያል ይላሉ፦
መዝሙር 132፥7 ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን፤ *እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን*።

እዚህ አንቀጽ ላይ "መስቀል" የሚለው ቃል ይቅርና ስለ መስቀል እሳቤው እንኳን የለም። "እግሮቹ የቆሙበት በመስቀል ላይ ነው" የሚል ተልካሻ ምክንያት በማቅረብ ይዳዳሉ። ቅሉ ግን "እግሮቹ "በ"ሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን" አለ እንጂ "እግሮቹ "ለ"ሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን" አላለም፤ "ለ" እና "በ" የሚሉ በይዘትና በአይነት ሁለት መስተዋድዶች ናቸው። ሲቀጥል "በ"ሚቆሙበት "ስፍራ" አለ እንጂ "በ"ሚቆሙበት "መስቀል" መቼ አለ? አውዱ ላይ "ስፍራ" የሚለው ቦታን እንደሆነ ይናገራል፦
መዝሙር 132፥5 *ለእግዚአብሔር "ስፍራ"፥ ለያዕቆብ አምላክ "ማደሪያ" እስካገኝ ድረስ ብሎ*።

ምን ትፈልጋለህ? "ስፍራ" የተባለው መስቀል ሳይሆን "የቅድስናው ስፍራ" ነው፤ "በ"ዚህ ስፍራ "ለ"እግዚአብሔር ይሰገዳል ይላል፦
መዝሙር 96፥9 *"በ"ቅድስናው ስፍራ "ለ"እግዚአብሔር ስገዱ"*፤

አሁንም "ለ" እና "በ" የሚሉ ሁለት መስተዋድዶች ለዩ፤ "በ" ቦታን "ለ" ምነነትን ያመለክታል፤ በቅድስና ስፍራ ለእግዚአብሔር ይሰገዳል እንጂ ለስፍራ አይሰገድም። የእግሮቹ መቆሚያ ማለትም የእግሮቹ መረገጫ የቅድስናው ስፍራ እንጂ መስቀሉ አይደለም፦
ሕዝቅኤል 43፥7 እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምቀመጥበት *የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ይህ ነው*።

ይህንን ጉድ እያየ ወደ ክርስትና የሚገባ ሰው ቂል ካልሆነ ወይም በጥቅማ ጥቅም አሊያም በተቃራኒ ጾታ ፍቅር መነደፍ ካልሆነ በስተቀር አይሞክረውም። መስቀል በሃውልት ድንጋይ፣ እንጨት፣ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ ነሐስ ወዘተ ነው፤ ለዚህ ግዑዝ ነገር የምትሰግዱ ካላችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ። ከአላህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና፦
7፥197 *እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም*። وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኦርቶዶክስ እና ኦሮሞ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአዋልድ መጽሐፍ አንዱ "ራዕየ ማርያም" ነው፤ እዚህ መጽሐፍ ላይ በሲዖል ስላሉት ሰዎች እንዲህ ይላል፦
ራዕየ ማርያም ገጽ 36-37 "ከዚህም በኃላ ከሥር እስከ ጫፍ፥ ከጫፍ እስከ ሥር ድረስ በአምስት ሺህ ዓመት የማይደረስ ገደል አሳየኝ። ያንዱ ነፍስ ባንዱ ነፍስ ላይ ሲወድቅ አየሁ። እኔም ምንድን ናቸው? ብዬ ልጄን ጠየኩት፤ እርሱም፦ "በአባታቸው፣ በወንድማቸው፣ በልጃቸው፣ በባልንጀራቸው ሚስት የሚሴስኑ ናቸው" አለኝ።
1. አራስ መርገም
2. ደንቆሮን
3. እስላም
3. ጋላ
4. ሻንቅላ
5. ፈላሻ
6. የተኙ ፈረስ፥ አህያ የሚያደርጉ
7. ምድርን ሰንጥቀው የሚያደርጉ
8. ወንዱን ግብረ ሰዶም ወገሞራ የሚያደርጉ
9. ካህን ሆኖ ከሌላ ሴት የካህኑ ሚስት ከሌላ ወንድ ቢሄዱ።
እነዚህ ሁሉ ኲነኔያቸው ይህ ነው" አለኝ።

ልብ አድርግ አራስ መርገም ማለት ሴት በወሊድ ጊዜ የሚኖራት ደም ነው፤ ይህ ደም እንዴት ለሲዖል ይዳርጋታል? ፈልጋ የምታመጣው ነገር አይደለም? ሲቀጥ ከዚህ የአራስ መርገም ነጻ የምትሆን ሴት የት አለች?
ሻንቅላ የተባሉት ጥቁር ሰዎች ናቸው። ጥቁርነት በተፈጥሮ የሚታደሉት ከሆነ እንዴት ለሲዖል ይዳርጋቸዋል?
ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ጋላ ማለትም ኦሮሞ መሆን እንዴትስ ለሲዖት ይዳርጋል? ኦሮሞ ሆኖ ይህንን እምነት የሚከተል አማኝ ካለ ለምን በኦሮሞነቱ ሲዖል እንደሚገባ መጠየቅ አለበት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዋቄፈና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አላህ መለኮት ነው፤ “መለኮት” ማለት ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ ማለት ነው፤ እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢና ሕያው መለኮት ነው፤ ብዙ አንቀጾች ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

እኛ ሙስሊም አላህ ስናመልከው እርሱን እንዴት ማምለክ እንዳለብን በቅዱስ ቃሉ በቁርኣን ውስጥ እና በእርሱ ነቢይ ሐዲስ ውስጥ በተቀመጠልን መስፈርት ብቻ ነው። ይህንን ካወቅን ስለ ዋቄፈና ደግሞ በግርድፉና በሌጣው እንይ።

"ዋቄፈና" የሚለው ቃል "ዋቃ" ማለትም "አምላክ" ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን የእምነቱ ስም ነው፤ ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ "ዋቄፈታ" ይባላል፤ “ኢሬቻ” ማለት "ምስጋና" ወይም "አምልኮ" ማለት ሲሆን "ገልማ" ማለትም "ቤተ-አምልኮ" ውስጥ በጭፈራዎቹና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው፤ ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም "መዝሙር" መዘመሩን ነው። ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ "ቃሉ" ይባላሉ፤ ፓለቲካውን "ሲርነ ገዳ" ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ "አባ ገዳ" ይባላሉ።

ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው፤ "ቱሉ" ማለት "ተራራ" ማለት ሲሆን "ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) "ቱሉ ፊሪ" "ቱሉ ኤረር" እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል። "ሆረ" ማለት "ሃይቅ" ማለት ሲሆን "ሆረ አርሰዴ" "ሆረ ፊንፊኔ" "ሆረ ኪሎሌ" እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፤ ይህ በዓል በአመት ሁለት ጊዜ ይከበራል።

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ-ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል። እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ-ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር፤ በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፤ አንዳንዶች ደግሞ፦ "አብዛኛው ዋቄፈናን ከእስልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው" ይላሉ፤ ይህ ስህተት ነው። ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም፥ ደግሞም "አይናገርምም" ይላሉ፤ እነርሱም ባወጡት ሰው ሰራሽ አምልኮ ያመልኩታል፤ ይህ ደግሞ ቢድዓ ነው፤ እዚህ አምልኮ ውስጥ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሃይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት"Pantheism" እሳቤ ሺርክ ነው፤ በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፤ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ነው? እንደውም "ቃሊቻ" የሚለው ቃል የተገኘው "ቃሉ" ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፤ "ቃሉ" የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *“አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ከእነዚህ ሁለት በዓል ውጪ ሌሎች በዓላት ተቀባይነት የላቸውም፤ ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም"* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ያገኛል፤
*ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል*። حَدَّثَنِي كَثِيرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ جَدِّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ أَحْيَا سُنَّةً مِنْ سُنَّتِي قَدْ أُمِيتَتْ بَعْدِي فَإِنَّ لَهُ مِنَ الأَجْرِ مِثْلَ أَجْرِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِ النَّاسِ شَيْئًا وَمَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لاَ يَرْضَاهَا اللَّهُ وَرَسُولُهُ فَإِنَّ عَلَيْهِ مِثْلَ إِثْمِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ آثَامِ النَّاسِ شَيْئًا ‏”‏ ‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። *ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አላህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው፤ ሙስሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩምና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሃ ወደ አላህ ተመለሱ። አላህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ስለ ዋቄፈና ዋቢ መጽሐፍት፦
1. Mulugeta Jaleta Gobenooromo; Indiginious Religion: Anthroplogical Understanding of Waaqeffanna-Nature Link, With Highlight on Livelihood in Guji Zone, Adola Redde and Girja Districts, A thesis submitted to the department of Social Anthropology, College of Social Science Addis Ababa University, June 2017,
2. Census (PDF), Ethiopia, 2007,
3. Workinesh Kelbessa, Traditional Oromo Attitudes towards the Environment, Social Science Research Report Series.

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የወር አበባ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥222 ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ “የተበከለ” ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ “ራቋቸው”፡፡ ንጹሕ እስከሚኾኑም ድረስ “አትቅረቡዋቸው”፡፡ ንጹሕ በኾኑም ጊዜ አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ “ተገናኙዋቸው”፡፡ አላህ ከኃጢኣት ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْمَحِيضِ ۖ قُلْ هُوَ أَذًۭى فَٱعْتَزِلُوا۟ ٱلنِّسَآءَ فِى ٱلْمَحِيضِ ۖ وَلَا تَقْرَبُوهُنَّ حَتَّىٰ يَطْهُرْنَ ۖ فَإِذَا تَطَهَّرْنَ فَأْتُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ أَمَرَكُمُ ٱللَّهُ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلتَّوَّٰبِينَ وَيُحِبُّ ٱلْمُتَطَهِّرِينَ ፡፡

የሚሽነዎች ጉዳይ መላ ቅጡ፣ ውጥን ቅጡ እና ቅጥ አንባሩ የጠፋበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፤ እስልምና በፍጥነት ማደጉ ከሚያብከነክናቸውና ከሚከነክናቸው የኢስላም ጠላቶች አንዱ ሚሽነሪዎች ናቸው፤ እስልምናን ለማጠልሸት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም፤ ጭራሽ ነብያችንን ለማነወር ሲቃጡ፦ “ነብያችሁ በወር አበባ ጊዜ ተራክቦ ያደርጉ ነበር” ወሊ-አዑዝቢሏህ ብለው እርፍ። ሆነም ቀረ ይህ ትችት የሚያሳየው ሴትን ዝቅ ለማድረግ የተቃጣ ትችት ነው። ወደዱም ጠሉም ሴት ልጅ በኢስላም ክቡድና ክቡር ናት፤ ይህንን ከእኔ ከተባእቱ ሳይሆን ወደ ኢስላም ከሚጎርፉት እንስታት ማረጋገጥ ይቻላል፤ በኢስላም አንድ ተባእት ከተራክቦ በስተቀር ተቃራኒ ከሆነች እንስት ጋር በወር አበባዋ ጊዜ መሳሳም፣ መተቃቀፍ፣ መተሻሸት እና መተኛት ሃላል ነው፤ አምላካችን አላህ “የተበከለ” ወይም “ቆሻሻ” የሚለው ሴቷን ሳይሆን ከሴቷ የሚወጠውን የወር አበባ ነው፤ በዚህ ጊዜ ተራክቦ ማድረግ ሃራም ነው፤ “ራቋቸው” እና “አትቅረቡዋቸው” የሚለው ቃል የ”ተገናኙዋቸው” ተቃራኒ ሆኖ ስለመጣ ራቁ ማለትና አትቅረቡ ማለት ተራክቦ አታድርጉ ማለት ነው፤ ለምሳሌ ዝሙት ማለት ከጋብቻ ውጪና በፊት የሚደረግ ተራክቦ ነው፤ ይህንን ተራክቦ “አትቅረቡ” ይላል፤ ያ ማለት “አትገናኙ” ማለት እንጂ ከሰው ጋር ጤናማ ግኑኝነት አይኑራችሁ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ሴት ራቁ ማለትና አትቅረቡ ማለት ተራክቦ አታድርጉ ማለት እንጂ አትቀፏቸው፣ አትሳሟቸው፣ አብራችሁ አትተኙ ማለት አይደለም፦
2፥222 ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ “የተበከለ” ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ “ራቋቸው”፡፡ ንጹሕ እስከሚኾኑም ድረስ “አትቅረቡዋቸው”፡፡ ንጹሕ በኾኑም ጊዜ አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ “ተገናኙዋቸው”፡፡ አላህ ከኃጢኣት ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْمَحِيضِ ۖ قُلْ هُوَ أَذًۭى فَٱعْتَزِلُوا۟ ٱلنِّسَآءَ فِى ٱلْمَحِيضِ ۖ وَلَا تَقْرَبُوهُنَّ حَتَّىٰ يَطْهُرْنَ ۖ فَإِذَا تَطَهَّرْنَ فَأْتُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ أَمَرَكُمُ ٱللَّهُ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلتَّوَّٰبِينَ وَيُحِبُّ ٱلْمُتَطَهِّرِينَ ፡፡
17፥32 ዝሙትንም “አትቅረቡ”፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ وَلَا تَقْرَبُوا۟ ٱلزِّنَىٰٓ ۖ إِنَّهُۥ كَانَ فَٰحِشَةًۭ وَسَآءَ سَبِيلًۭا !

በተለይ ሱረቱል በቀራህ 2፥222 የወረደበት ምክንያት አይሁዳውያን ሴት በወር አበባ ጊዜ ስትሆን ምግብ አብረው አይበሉም በቤታቸውም አይኖሩም ስለነበርና ሰሃባዎችም ይህንን ጉዳይ ወደ ነብያችን”ﷺ” ጥያቄውን በማምራታቸው ነው፤ ነብያችንም”ﷺ” የመለሱት በወር አበባ ጊዜ ከተራክቦ በስተቀር ሁሉንም ማድረግ እንደሚቻል ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 3 , ሐዲስ 16:
አነሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦
አይሁዳውያን ሴት በወር አበባ ጊዜ ስትሆን ምግብ አብረው አይበሉም በቤታቸውም አይኖሩም፤ የነብዩም”ﷺ” ባልደረቦች ነብዩን”ﷺ” ስለ ጉዳዩ ጠየቁ፤ ከሁሉ የላቀው አላህም ይህንን አንቀፅ አወረደ፦
2፥222 ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ “የተበከለ” ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ “ራቋቸው”፡፡
የአላህም መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ሁሉን ነገር አድርጉ ከተራክቦ በስተቀር”። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ ال يَهُودَ، كَانُوا إِذَا حَاضَتِ الْمَرْأَةُ فِيهِمْ لَمْ يُؤَاكِلُوهَا وَلَمْ يُجَامِعُوهُنَّ فِي الْبُيُوتِ فَسَأَلَ أَصْحَابُ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الْمَحِيضِ قُلْ هُوَ أَذًى فَاعْتَزِلُوا النِّسَاءَ فِي الْمَحِيضِ‏}‏ إِلَى آخِرِ الآيَةِ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ اصْنَعُوا كُلَّ شَىْءٍ إِلاَّ النِّكَاحَ

በሥነ-ቃላት ጥናት”Morphology “የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ለምሳሌ፦ በኢንግሊሽ  “Volume” ማለት፦ ስለ ሥነ-አካል የምናወራበት የዐውድ ፍሰት ላይ “ይዘት” ማለት ሲሆን፣ ስለ ድምጽ አጨማመር እና አቀናነስ የምናወራበት የዐውድ ፍሰት ላይ “መጠን” ማለት ሲሆን፣ ስለ ሥነ-ጽሑፍ የምናወራበት የዐውድ ፍሰት ላይ ደግሞ “ቅጽ” ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ለምሳሌ በዐረቢኛ፦ “መሥ” مَسّ ማለትም “መንትካ” የሚለው ቃል “ተራክቦን” “መዳሰስን” መፈለግን” ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል፦

1ኛ “ተራክቦ”፦
3፥46 ፡-ጌታዬ ሆይ! “ሰው ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ” ይኖረኛል?” አለች قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ ۖ ፡፡
19፥20 « ሰው “ያልነካኝ” ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች قَالَتْ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى غُلَٰمٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ وَلَمْ أَكُ بَغِيًّۭا ፡፡
2፥236 ሴቶችን “ሳትነኳቸው” ወይም ለእነሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም لَّا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ مَا لَمْ تَمَسُّوهُنَّ أَوْ تَفْرِضُوا۟ لَهُنَّ فَرِيضَةًۭ ۚ ፡፡

“ሰው ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ” ይኖረኛል?” ማለቷ መቼም ሰው በእጁ ሳይዳስሰኝ እንዴት ልጅ” ይኖረኛል እያለች እንዳልሆነ ቅቡል ነው፤ መቼን በእጅ በመነካት ልጅ የሚኖራት እንስት የለችምና፤ በተጨማሪ ሴቶችን ሳትነኳቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም ሲባል በእጅ ሳትዳስሷቸው ማለት እንዳልሆን እሙን ነው።
2ኛ “መዳሰስ”፦
6፥7 በአንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድንና *በእጆቻቸው በነኩት* ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር፡፡ وَلَوْ نَزَّلْنَا عَلَيْكَ كِتَٰبًۭا فِى قِرْطَاسٍۢ فَلَمَسُوهُ بِأَيْدِيهِمْ لَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌۭ مُّبِينٌۭ

“በነኩት” ተብሎ የመጣበት ቃል እና መርየም “ያልነካኝ” ብላ የተናረችበት ቃል አንድ ነው፤ ያ ማለት አንድ ትርጉም ይኖረዋል ማለት አይደለም።

3ኛ “መፈለግ”፦
72፥8 ‹እኛም ሰማይን ለመድረስ *ፈለግን*፡፡ ብርቱ ጠባቂዎችንና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት፡፡ وَأَنَّا لَمَسْنَا ٱلسَّمَآءَ فَوَجَدْنَٰهَا مُلِئَتْ حَرَسًۭا شَدِيدًۭا وَشُهُبًۭا
57፥13 መናፍቃንና መናፍቃት ለእነዚያ ለአመኑት «ተመልከቱን፤ ከብርሃናችሁ እናበራለንና» የሚሉበትን ቀን አስታውስ፡፡ «ወደ ኋላችሁ ተመለሱ፡፡ ብርሃንንም *ፈልጉ*» ይባላሉ፡፡ ግቢው በውስጡ ችሮታ ያለበት ውጭውም ከበኩሉ ስቃይያለበት የኾነ፡፡ يَوْمَ يَقُولُ ٱلْمُنَٰفِقُونَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتُ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱنظُرُونَا نَقْتَبِسْ مِن نُّورِكُمْ قِيلَ ٱرْجِعُوا۟ وَرَآءَكُمْ فَٱلْتَمِسُوا۟ نُورًۭا فَضُرِبَ بَيْنَهُم بِسُورٍۢ لَّهُۥ بَابٌۢ بَاطِنُهُۥ فِيهِ ٱلرَّحْمَةُ وَظَٰهِرُهُۥ مِن قِبَلِهِ ٱلْعَذَابُ

ይህን የሥነ-ቃል እሳቤ ይዘን ሂስ የተሰጠበትን ሐዲስ እንልመከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 6:
ዓኢሻ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦
ነብዩም”ﷺ” እና እኔ ጁኑብ በሆንን ጊዜ በአንድ መታጠቢያ እንታብጠ ነበር፤ እንዲሁ በወር አበባ ጊዜ ከወገብ በታች እንድለብስ ያዙኝና ይዳብሱኝ ነበር፤ በተመሳሳይ በኢዕቲካፍ በወር አበባዬ ጊዜዬ ራሳቸውን ወደ እኔ ያቀርቡና እራሳቸውን አጥባቸው ነበር። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ، كِلاَنَا جُنُبٌ‏.‏ وَكَانَ يَأْمُرُنِي فَأَتَّزِرُ، فَيُبَاشِرُنِي وَأَنَا حَائِضٌ‏.‏ وَكَانَ يُخْرِجُ رَأْسَهُ إِلَىَّ وَهُوَ مُعْتَكِفٌ، فَأَغْسِلُهُ وَأَنَا حَائِضٌ‏.‏
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 7:
የምእመናን እናት ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንዲህ አለች፦ “ከእኛ ውስጥ አንዳችን በሐይድ ላይ ከሆነች እና የአላህ መልክተኛም”ﷺ” እሷን ለመንካት ከፈለጉ ከሐይድ ወቅት ጀምሮ ልብስን እንድታሸርጥ ያዟት ነበር፤ ከዛም ገላዋን ይዳብሷት ነበር፤ የአላህ ነቢይ”ﷺ” ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ እንደነበረው ማንኛችሁ ነው ስሜቱን መቆጣጠር የሚችለው? አለች፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كَانَتْ إِحْدَانَا إِذَا كَانَتْ حَائِضًا، فَأَرَادَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنْ يُبَاشِرَهَا، أَمَرَهَا أَنْ تَتَّزِرَ فِي فَوْرِ حَيْضَتِهَا ثُمَّ يُبَاشِرُهَا‏.‏ قَالَتْ وَأَيُّكُمْ يَمْلِكُ إِرْبَهُ كَمَا كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَمْلِكُ إِرْبَهُ‏.‏ تَابَعَهُ خَالِدٌ وَجَرِيرٌ عَنِ الشَّيْبَانِيِّ‏.‏

“ፈዩባሺሩኒ” فَيُبَاشِرُنِي ማለት “ይዳብሱኝ ነበር” He used to fondle me” ነበር ማለት ነው፤ “ዩባሺሩሃ” يُبَاشِرَهَا ማለት “ይዳብሷት ነበር” He used to fondle her” ነበር ማለት ነው፤ የቋንቋ ምሁራንም በኢንግሊዚኛው ትርጉም ላይ በዚህ መልኩ ነው ያስቀመጡት እንጂ “ተራክቦ”Intercourse” በሚል አላስቀመጡትም። ምክንያቱም ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ ላይ እያለች ተራክቦ ማድረግ ክልክል ብቻ ሳይሆን ክህደትም ነው፦
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 135
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ “ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ ማንም በሓይድ ላይ ካለች ሴት ወይም በመቀመጫዋ በኩል ተራክቦ ቢያደርግ በሙሐመድ”ﷺ” ላይ በተወረደው ክዷል። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ مَنْ أَتَى حَائِضًا أَوِ امْرَأَةً فِي دُبُرِهَا أَوْ كَاهِنًا فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم ‏”‏

ሲቀጥል ተራክቦን እንደማያመለክት ለመግለጽ፦ “ሽርጥን እንድታሸርጥ ያዟት ነበር” የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ ይህ የሚያሳየው ተራክቦን አለመሆኑን ያሳያል፤ በተራክቦ ጊዜ ልብስን እንድትለብስ ማዘዝ ትርጉም የለውም።
ሢሰልስ በሐዲሱ ማብቂያ ላይ እናታችን ዓኢሻ”ረ.ዐ.” ስለ ነብዩም”ﷺ” ስትደመድም፦ “ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ እንደነበረው ማንኛችሁ ነው ስሜቱን መቆጣጠር የሚችለው?” በማለቷ ተራክቦን ጭራሽ አያሳይም፤ ምክንያቱም ተራክቦ በራሱ ስሜት ማርኪያ እንጂ መቆጣጠሪያ ስላልሆነ።
ሲያረብብ፦ በኢዕቲካፍ በወር አበባዬ ጊዜዬ ራሳቸውን ወደ እኔ ያቀርቡና እራሳቸውን አጥባቸው ነበር” ብላለች፤ “ኢዕቲካፍ” اعتكاف‌‎ ማለት “ማዘውተር” ማለት ሲሆን በስብስብ ሶላት ላይ በመስጂድ ውስጥ ለመዘውተር በመነየት የተወሰነ ጊዜ ቆይታ ማድረግ ነው፤ በተለይ የረመዷንን የመጨረሻዎቹን አሥርት ቀናት ላይ የሚረግደ ቆይታ ነው። በዚህ ወቅት ተራክቦ ማድረግ ሃራም ነው፦
2፥187 እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ “አትገናኙዋቸው”፡፡ وَلَا تُبَٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَٰكِفُونَ فِى ٱلْمَسَٰجِد

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቱባሺሩሁነ” تُبَٰشِرُوهُنَّ ማለት “ተራክቦ አታድርጓቸው” ማለት ነው፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ እሙንና ቅቡል ነው፤ ይህ ሙግት የሥነ-ቋንቋ ሙግት እና የዐውድ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አል-በላጋህ

12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*። إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

"አል በላጋህ" البلاغة ማለት "የንግግር ስልት"rhetoric" ማለት ነው፤ይህም በስም፣ በተውላጠ-ስም፣ በግስ፣ በገላጭ ላይ የሚታየው የነጠላና የብዜት፣ የተባእታይና የአንስታይ የአነጋገር ስልት ነው፤ በግሪክ "ሬቶሪኮስ" ῥητορικός ይሉታል። አምላካችም አላህ ቁርኣን ዐረቢኛ በላጋህ በማድረግ በዐረቢኛ በላጋህ አውርዶታል፦
43፥3 *እኛ ታውቁ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን አደረግነው*፡፡ إِنَّا جَعَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
12፥2 *እኛ ትገነዘቡ ዘንድ ዘንድ ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን በእርግጥ አወረድነው*። إِنَّا أَنزَلْنَاهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لَّعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

ለናሙና ያክል የተወሰኑ ጥቅሶችን ማየት ይቻላል፦
36፥78 ለእኛም ምሳሌን አደረገልን፡፡ መፈጠሩንም ረሳ፡፡ *«አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲኾኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው?»* አለ፡፡ وَضَرَبَ لَنَا مَثَلًا وَنَسِيَ خَلْقَهُ ۖ قَالَ مَن يُحْيِي الْعِظَامَ وَهِيَ رَمِيمٌ

"ዐዝም" عَظْم በነጠላ “አጥንት”bone” ማለት ነው፤ “ዒዛም” عِظَام ደግሞ የዐዝም ብዜት ሲሆን "አጥንቶች" ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ አጥንቶች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም በነጠላ "ሂየ" هِيَ እንጂ በብዜት “ሁነ” هُنَ አይደለም። በተጨማሪ፦
27፥88 *"ጋራዎችንም እርሷ" እንደ ደመና አስተላለፍ የምታልፍ ስትኾን የቆመች ናት ብለህ የምታስባት ሆና ታያታለህ*፡፡ የዚያን ነገሩን ሁሉ ያጠነከረውን የአላህን ጥበብ ተመልከት፡፡ እርሱ በምትሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ وَتَرَى الْجِبَالَ تَحْسَبُهَا جَامِدَةً وَهِيَ تَمُرُّ مَرَّ السَّحَابِ ۚ صُنْعَ اللَّهِ الَّذِي أَتْقَنَ كُلَّ شَيْءٍ ۚ إِنَّهُ خَبِيرٌ بِمَا تَفْعَلُونَ

"ጀበል" جَبَلْ በነጠላ "ጋራ" ማለት ነው፤ “ጂባል” جِبَالْ ደግሞ የጀበል ብዜት ሲሆን "ጋራዎች" ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ ጋራዎች ለሚለው ስም ተክቶ የገባው ነጠላ አንስታይ ተውላጠ ስም በነጠላ "ሂየ" هِيَ እንጂ በብዜት “ሁነ” هُنَ አይደለም። እስቲ ሌላ አንቀጽ እንመልከት፦
3፥173 *እነዚያ ሰዎቹ ለእነርሱ፡- «ሰዎች ለእናንተ ጦርን አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» "ይሉዋቸውና"* ይህም እምነትን የጨመረላቸው «በቂያችንም አላህ ነው ምን ያምርም መጠጊያ!» ያሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ

“አለዚ” ٱلَّذِىٓ በነጠላ "ያ" ማለት ነው፤ “አለዚነ” الَّذِينَ  ደግሞ የአለዚ ብዜት ሲሆን "እነዚያ" ማለት ነው፤ እዚህ አንቀጽ ላይ እነዚያ ለሚለው አመልካች ተውላጠ ስም ተከትሎ የገባው ግስ "ቃለ" قَالَ በነጠላ እንጂ በብዜት "ቃሉ" قَالُوا አይደለም።
ሌላው "ቃሉ" قَالُوا የሚለውን የተባታይ ብዜት በነጠላ አንስታይ "ቃለት" قَالَت በሚል ይመጣል፦
14፥10 *"መልክተኞቻቸው"*፦ «ከኀጢአቶቻችሁ እንዲምራችሁ ወደ ተወሰነ ጊዜም ያለ ቅጣት እንዲያቆያችሁ የሚጠራችሁ ሲኾን ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ በኾነው አላህ በመኖሩ ጥርጣሬ አለን?» *"አሏቸው"*፡፡ قَالَتْ رُسُلُهُمْ أَفِي اللَّهِ شَكٌّ فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ يَدْعُوكُمْ لِيَغْفِرَ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُؤَخِّرَكُمْ إِلَىٰ أَجَلٍ مُّسَمًّى
3፥42 *"መላእክትም ያሉትን"* አስታውስ፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነጻሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡» وَإِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاكِ وَطَهَّرَكِ وَاصْطَفَاكِ عَلَىٰ نِسَاءِ الْعَالَمِينَ

በእነዚህ አናቅጽ ላይ መልእክተኞች ነቢያት እና መላእክት "አሉ" ለሚለው ቃል የገባው "ቃለት" قَالَت መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ሙዘከር አንድ ማንነት ሲያመልከት ሙአነስ ብዜትን ያመለክታል፤ ለዛ ነው መልእክተኞች ነቢያት እና መላእክት "አሉ" ለሚለው ቃል ሌላ አናቅጽ ላይ "ቃሉ" قَالُوا የሚለው ያለው፦
5፥109 አላህ መልክተኞቹን የሚሰበስብበትን እና፦ «ምን መልስ ተሰጣችሁ» የሚልበትን ቀን አስታውስ፡፡ *"እነርሱም"፦ «ለእኛ ምንም ዕውቀት የለንም አንተ ሩቆችን በጣም ዐዋቂ አንተ ብቻ ነህ» *"ይላሉ"*፡፡ يَوْمَ يَجْمَعُ اللَّهُ الرُّسُلَ فَيَقُولُ مَاذَا أُجِبْتُمْ ۖ قَالُوا لَا عِلْمَ لَنَا ۖ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّامُ الْغُيُوبِ
2፥30 ጌታህ ለመላእክት፡- «እኔ በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ፤» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ፤ *"እነርሱም"*፦ «እኛ ከማመስገን ጋር የምናጠራህ ላንተም የምንቀድስ ስንኾን በርሷ ውስጥ የሚያጠፋንና ደሞችንም የሚያፈስን ታደርጋለህን?» *"አሉ"*፡፡ አላህ «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡ وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً ۖ قَالُوا أَتَجْعَلُ فِيهَا مَن يُفْسِدُ فِيهَا وَيَسْفِكُ الدِّمَاءَ وَنَحْنُ نُسَبِّحُ بِحَمْدِكَ وَنُقَدِّسُ لَكَ ۖ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ مَا لَا تَعْلَمُون

ይህ የበላጋህ እሳቤ ከኡስታዚ Eliyah Mahmoud"አላህ ይጠብቀው" ያገኘሁት ሙግት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ስለ ሼህ አሕመድ"ራህመቱላሂ ዐለይሂ" ዲዳት ከክርስቲያን ምሁራን አንደበት
የሚሽነሪዎችን ደባ እና ሴራ የሚያጋልጥ ቻናል ይፈልጋሉ? እግዲያውስ ወደዚህ ቻናል ይቀላቀሉ፦
join us @answering
ሥነ-ፍጥረት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

“ሥነ-ፍጥረት”creatinology” ማለት ስለ ፍጥረት የሚያጠና የዕውቀት ዘርፍ ነው፤ አምላካችን አላህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፤ “ሸይዕ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ማለት ሲሆን ሁሉንም ነገራት ሁሉ ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
6፥102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው*፤ ስለዚህ ተገዙት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
13፥16 *አላህ ሁሉንም ነገር ፈጣሪ ነው*፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው፤ በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
40፥62 ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ *የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُون

ነጥብ አንድ
“ፍጥረት”
አላህ የፈጠራቸው ፍጥረታት ህልቆ-መሳፍርት ናቸው፤ ከአጽናፍ እስከ አድማስ ያሉትን ትልቅ እና ደቂቅ ፍጥረታት ቢዘረዘሩ አያልቁም፤ እነዚህን ፍጥረታት አላህ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው፦
50፥38 ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ
25፥59 ያ ሰማያትና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዐርሹ ላይ የተደላደለ አልረሕማን ነው፡፡ ከእርሱም ዐዋቂን ጠይቅ፡፡ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۚ الرَّحْمَـٰنُ فَاسْأَلْ بِهِ خَبِيرًا

ይህ ጥቅላዊ ገለጻ ሲሆን በተናጥል አስፈላጊ የሆነው አፈጠጠሩ እንዲህ ይገልጻል፦
41፥9 በላቸው «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀኖች ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው፡፡ قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَرْضَ فِى يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادًۭا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ

ከመጀመሪያው ቀን እስከ አራተኛው ቀናት ባሉት በአራት ቀናት ውስጥ በምድር ላይ የረጉ ጋራዎችን፣ በውስጧም ምግቦችዋን ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፦
42፥10 በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፡፡ በእርሷም በረከትን አደረገ፡፡ በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፡፡ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ مِن فَوْقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقْوَٰتَهَا فِىٓ أَرْبَعَةِ أَيَّامٍۢ سَوَآءًۭ لِّلسَّآئِلِينَ

“ጭስ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዱኻን” دُخَانٌۭ ሲሆን “ጋዝ” ማለት ነው፤ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አላህ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፦
42፥11 ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ

“ሱመ” ثُمَّ ማለት አያያዥ መስተጻምር ሲሆን “ከዚያም” ወይም “እንዲሁ” ማለት ነው፤ አያያዥነቱ “ተርቲቢያህ” ማለትም “ቅድመ-ተከተል” ነው፤ ይህም ቅድመ-ተከተል በሁለት ይከፈላል፦ አንዱ “ተርቲበቱል ከላም” ማለት “የንግግር ቅድመ-ተከተል” ሲሆን ሁለተኛው “ተርቲበቱል ዘመን” ማለት የጊዜ ቅድመ-ተከተል ናቸው፣ እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ዓውዱ የንግግር ቅድመ-ተከተል ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ አላህ ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፤ ጭስ የነበረችውን ሰማይ በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፡፡ فَقَضَىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَاتٍۢ فِى يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ *ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ
ነጥብ ሁለት
“ማስተንተን”
በሰማያትና በምድር ያሉትን ከአጽናፍ እስከ አድማስ ያሉትን ትልቅ እና ደቂቅ ህልቆ-መሳፍርት ፍጥረታት እኛ ቀስ በቀስ በማስተንተን ማወቅ እንችላለን፤ በአላህ አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም፤ ዓይንህንም ወደ ፍጥረታት እይ ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን? በፍጹም አታይም፦
3፥191 እነርሱም እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ *በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ*፡- «ጌታችን ሆይ! *ይህን በከንቱ አልፈጠርከውም*፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَـٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ
67፥3 ያ ሰባትን ሰማያት የተነባበሩ ኾነው የፈጠረ ነው፡፡ *በአልረሕማን አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም*፡፡ ዓይንህንም መልስ፡፡ «ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?» الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ طِبَاقًا ۖ مَّا تَرَىٰ فِي خَلْقِ الرَّحْمَـٰنِ مِن تَفَاوُتٍ ۖ فَارْجِعِ الْبَصَرَ هَلْ تَرَىٰ مِن فُطُورٍ

ለእኛም በሰማያት ያለውን እና በምድርም ያለውን ሁሉ በሙሉ ከአላህ ሲኾን የገራልን ነው፤ በዚህ አፈጣጥር ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ተዓምራት አልለበት፦
45፥13 ለእናንተም በሰማያት ያለውን እና በምድርም ያለውን ሁሉ በሙሉ ከእርሱ ሲኾን የገራላችሁ ነው፡፡ በዚህ *ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች* ተዓምራት አልለበት፡፡ وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ በዚህም ውስጥ *ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች* ምልክቶች አሉ፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

ሰማያትና ምድር ከጌታችንም ጸጋዎች ናቸው፦
55፥7 *ሰማይንም አጓናት*፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡ وَٱلسَّمَآءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ ٱلْمِيزَانَ
55፥10 *ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት*፡፡ وَٱلْأَرْضَ وَضَعَهَا لِلْأَنَامِ
55፥13 *ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?* فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ

በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለእኛ ያገራልን ግልጽም ድብቅም ሲኾኑ የሞላላልን ጸጋዎቹንም ናቸው፦
31፥20 አላህ *በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ ጸጋዎቹንም ግልጽም ድብቅም ሲኾኑ የሞላላችሁ መኾኑን አታዩምን?* أَلَمْ تَرَوْا أَنَّ اللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَأَسْبَغَ عَلَيْكُمْ نِعَمَهُ ظَاهِرَةً وَبَاطِنَةً ۗ

ሰማያትና ምድር፣ በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ እኛ የደረስንበት ግልጽም ያልደረስንበት ድብቅም ለእኛ ያገራልን የአላህንም ጸጋ ናቸው፤ የአላህንም ጸጋ ብትቆጥረው አንዘልቀውም፦
16፥18 *የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም*፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
መደምደሚያ
በተረፈ ዘፍጥረት 1፥1-31 የፈጣሪን ፍጥረት በከፊል እንጂ በሙሉ አይዘረዝርም። ለምሳሌ ሰባት ሰማያት፣ መላእክት፣ ውኃ፣ ፈንገስ፣ ባክቴሪያ፣ ጀርም ወዘተ መቼ እንደተፈጠሩ፣ ከምን እንደተፈጠሩ እና እንዴት እንደተፈጠሩ አይናገርም። ታላቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔው ሎሬትዬ ጸጋዬ ገብረ መድኅን፦ የሰው ልጅ ከሁለት ነገር ይማራል፦ አንዱ “ሀ” ብሎ “በሳር” ሲሆን ሁለተኛው “ዋ” ብሎ “በአሳር” ይላልና፤ ክርስቲያን ሃያሲ ሂስ ለመስጠት “ሀ” ብሎ “በሳር” ከቁርአን መማር አሊያም “ዋ” ብሎ “በአሳር” ዘፍጥረት ላይ የሌሉትን ሃያ ሁለቱ ሥነ-ፍጥረት ብሎ አክሲማሮስ ውስጥ መደበቅ ነው፤ ይህ ደግሞ እንጥል ከመቧጠጥ ምንም አይተናነስም። ነገር ግን ፈጣሪ ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ አያገኝም፦
መክብብ 3፥11 ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ *እግዚአብሔርም ከጥንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠራውን ሥራ ሰው መርምሮ እንዳያገኝ* ዘላለምነትን በልቡ ሰጠው።

አላህ የዓለማት ጌታ ነው፤ “ዓለሚን” عَٰلَمِين ማለት “ዓለማት” ማለት ሲሆን የዘመናችን የሥነ-ፈለክ አስተንታኞች “መልቲ-ቨርስ”multi-verse” ይሉታል፤ ይህም ህልቆ-መሳፍት የሆነውን አድማስና አፅናፍ ለማመልከት ይጠቀሙበታል፤ “አዕለም” أَعْلَم የዐለሚን ነጠላ ሲሆን ‘ዐልለመ” عَلَّمَ “አሳወቀ” ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን “ዓለም” ወይም “የታወቀ” ማለት ነው፤ አላህ በእኛ ዘመን ባሉት ያሳወቀው እኛ ያለንባት አንድ ዓለም “ዩኒ-ቨርስ”uni-verse” ነው፤ የእኛ ዓለም ከ 170 billion እስከ 200 billion “ረጨት”galaxy” ይዟል፤ “ረጨት” ማለት የከዋክብት ስብስብ ሲሆን የእኛ ረጨት “ፍኖተ-ሃሊብ”Milky Way” ረጨት ይባላል፤ ይህ ረጨት ውፍረቱ 1000 የብርሃን አመት ይገመታል፤ ከአንዱ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ያለው ርቀት በዲያሜትር ሲለካ ደግሞ 100,000 የብርሃን ዓመት ይሆናል፤ በውስጡ ከ100 እስከ 400 ቢልዮን ከዋክብቶች እንደያዘ ይገመታል።
ይህንን የከዋክብት ረጨት”constellation” አምላካችን አላህ የዛሬ 1407 ዓመት በቁርአን “ቡሩጅ” بُرُوج ይለዋል፦
85:1 #የቡርጆች الْبُرُوجِ ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ፤
25:61 ያ በሰማይ #ቡርጆችን بُرُوجًا ያደረገና በርሷም አንጸባራቂን ፀሐይ አብሪ ጨረቃንም ያደረገ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ።
15:16 በሰማይም ላይ #ቡርጆችን بُرُوجًا በእርግጥ አድርገናል፡፤ ለተመልካቾችም አጊጠናታል፡፡

አላህ የዛሬ 1400 ዓመት በተከበረው ቃሉ በቁርአን “በአጽናፎቹ ውስጥ ያሉትን ታምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን” ብሎ ቃል ገብቶ ነበር፦
41፥53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ #በአጽናፎቹ #ውስጥ እና በራሶቻቸውም ውስጥ #ያሉትን #ታምራቶቻችንን በእርግጥ #እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?

ታዲያ በበረሃ ግመል ገፊ ነው ተብሎ በሚነገርላቸው ላይ ይህ ሁሉ እውቀት እንዴት ተዥጎደጎደ? ስንል፤ ይህንን እውቀት የዛሬ 1407 ዓመት ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው ይሆናል መልሱ፦
25:6 ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፤ እርሱ መሐሪ አዛኝ ነውና፤ በላቸው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአላህ ባህርይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 53, ሐዲስ 32
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ አላህ አዝዘ ወጀል አደምን ስልሳ ኩብ ቁመት አድርጎ በራሱ "መልክ" ፈጠረው። خَلَقَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا.
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 79, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ አላህ አደምን ስልሳ ኩብ ቁመት አድርጎ በራሱ "መልክ" ፈጠረው። خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ، طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا،

የቋንቋው ሊሂቃን "ሱራ" صورة ማለት "መልክ" image" ብለው ያስቀመጡት ሲሆን ይህም "መልክ" ባህርይ ለማመልከት እንደሚመጣ ይናገራሉ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60 ሐዲስ 2
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ የመጀመሪያው ግሩፕ በሌሊት ሙሉ እንደሆነች በጨረቃ "#መልክ" صُورَةِ ሆኖ ወደ ጀነት ይገባሉ። إِنَّ أَوَّلَ زُمْرَةٍ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ عَلَى صُورَةِ الْقَمَرِ لَيْلَةَ الْبَدْرِ،

በዚህ ሐዲስ ላይ መቼም የጨረቃ መልክ የጨረቃን ቅርፅና ክብደት ለማመልከት ነው ከተባለ የጨረቃ ቅርጷ 1958×1010 km3 እንዲሁ ክብደቷ 7.342×1022 kg ነው፤ ያ ማለት ሰው ጀነት የሚገባው በጨረቃ ቅርፅና ክብደት ነው ማለት ሳይሆን የጨረቃ ባህርይ የሆኑን ንፅህናዋን፣ ድምቀቷ እና ውበቷን ማለቱ ነው፤ እንግዲህ "ሱራ" صورة "መልክ" የአንድን ህላዌ ባህርይ ለማመልከት ከመጣ ይህም "መልክ" ማየት፣ መስማት፣ ማወቅ የሚባሉትን ባህርያት ያቅፋል፤ አላህ ሁሉን ነገር ተመልካች፣ ሁሉን ነገር ሰሚ እና ሁሉን ነገር አዋቂ ነው፤ አላህ አደምን ሲፈጥረው በባህርያቱ የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ እና የሚያውቅበት ልብ"አንጎል" ሰቶታል ማለት ነው፦
67:23 እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም "#መስሚያ" እና "#ማያዎችን" "#ልቦችንም" ያደረገላችሁ ነው፤ ጥቂትንም አታመሰግኑም በላቸው።
23፥78 እርሱም ያ "#መስሚያዎችንና" "#ማያዎችን" "#ልቦችንም" ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፤ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡

አላህ "የሚመስለው ምንም ነገር የለም" አላህ ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው፦
42:11"የሚመስለው" ምንም ነገር የለም፤ እርሱም "ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው።

አላህ ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው እንደተባለ ሁሉ ሰውም ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው ተብሏል፦
76:2 እኛ ሰዉን፥ በሕግ ግዳጅ የምንሞክረዉ ስንሆን፥ ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፤ "ሰሚ" "ተመልካችም" አደረግነዉ።

ነገር ግን አላህ ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው የተባለው ሰው ሰሚ" እና "ተመልካች" በተባለበት ሂሳብ አይደለም፤ ምክንያቱም አላህ ሁሉን ነገር ይሰማል ያያል፤ ይህ ባህርይ ጊዜና ቦታ አይገድበውም፤ ሰው ግን ያለ ብርሃን ማየት እና ያለ ድምፅ መስማት አይችልም፤ በተመሳሳይ አላህ ሁሉን አዋቂን ነው እውቀቱ በጊዜና በቦታ አይገደብም፤ ሰው ግን እውቀቱ ጊዜ እና ቦታ ይገድበዋል፦
58:6 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነው።
67:19 እርሱ በነገር ሁሉ ተመልካች ነው።
4:86 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና።
39:62 እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው።
33:27 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

የሰው መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም ከአላህ የሆኑ ፀጋ ሲሆኑ ከእንስሳ በተለየ መልኩ ይሰሩት በነበሩት ሁሉ ተጠያቂ ናቸው፦
17:36 ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፤ #መስሚያ#ማያም#ልብም፣ እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ #ተጠያቂ ነውና إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ።
102:8 ከዚያም #ከጸጋዎቻችሁ النَّعِيمِ ሁሉ በዚያ ቀን #ትጠየቃላችሁ ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ ።
16:93 ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ #ትጠየቃላችሁ" وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ ።

የአላህ ዛት የራሱ ሲፋ አለው ማየት፣ መስማት፣ መናገር፣ ማወቅ እና እጅ ግን ከፍጡራን ማየት፣ መስማት፣ ማወቅ፣ መናገር እና እጅ ጋር አይመሳሰልም። ለምሳሌ የሰው እጅ ቀኝና ግራ ነው የአላህ እጆች ግን ቀኝ ናቸው፦
ኢማም ሙስሊም 33, ሐዲስ 21 ፍትኸኞች አላህ ዘንድ በብርሃን መንበሮች ላይ ከአር-ረህማን በስ-ተቀኝ በኩል ይሆናሉ፤ ሁለቱም እጆቹ #ቀኝ ናቸው። " ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﻤُﻘْﺴِﻄِﻴﻦَ ﻋِﻨْﺪَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻋَﻠَﻰ ﻣَﻨَﺎﺑِﺮَ ﻣِﻦْ ﻧُﻮﺭٍ ﻋَﻦْ ﻳَﻤِﻴﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﻋَﺰَّ ﻭَﺟَﻞَّ ﻭَﻛِﻠْﺘَﺎ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻳَﻤِﻴﻦٌ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﺪِﻟُﻮﻥَ ﻓِﻲ ﺣُﻜْﻤِﻬِﻢْ ﻭَﺃَﻫْﻠِﻴﻬِﻢْ ﻭَﻣَﺎ ﻭَﻟُﻮﺍ "

አላህ በራሱ ባህርይ ፈጠረው ማለት ለምሳሌ አላህ አደምን በእጁ ፈጥሮታል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *"በሁለት እጆቼ"* "ለፈጠርኩት" ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ
36፥71 እኛ *"እጆቻችን ከሠሩት"* ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَآ أَنْعَٰمًۭا فَهُمْ لَهَا مَٰلِكُونَ

እጅ የአላህ ባህርይ ነው፤ ኹን የሚለው ንግግሩ የራሱ ባህርይ ነው፤ በባህርይው አደምን ፈጥሮታል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሐዲስና ዳራው

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
“ሐዲስ” حَدِيث ማለት የቀጥታ ትርጉሙ *ንግግር* ሲሆን የነቢያችንን ንግግር ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ቃል ነው፣ “ሱና” سنة ደግሞ *መንገድ* አሊያም *ፈለግ* ማለት ሲሆን የነቢያችንን ንግግርና የነቢያችንን ተግባር ያሳያል፣ ሱና በሁለት ረድፍ ይከፈላል፣ እነርሱም፦ ሱነል ቀውሊያህ እና ሱነል ፊኢሊያህ ናቸው፣ ሱነል ቀውሊያህ የነቢያችንን ንግግር ሲሆን ሱነል ፊኢሊያህ የነቢያችንን ተግባር ነው።
Lisan al-Arab, by Ibn Manthour, vol. 2, p. 350; Dar al-Hadith edition.

ነጥብ አንድ
አወራረዱ
ነቢያችን በአቂዳና በፊቅ ጉዳይ ላይ የሚናገሩት ሁሉ ከአላህ የወረዱ ወህይ وحي ማለትም ግልጠተ-መለኮት*Revelation* እንጂ ከራሳቸው የተናገሩት ምንም ጉዳይ የለም፣ የነቢያችን ማስጠንቀቂያ በተወረደላቸው ወህይ ብቻ ነው፦
21:45 ፦ የማስጠነቅቃችሁ *በተወረደልኝ* بِالْوَحْيِ ብቻ ነው፣ ግን ደንቆሮዎች በሚስፈራሩበት ጊዜ ጥሪን አይሰሙም በላቸው።
53:3-4 ከልብ ወለድም አይናገርም። እርሱ ንግግሩ *የሚወረድ*يُوحَىٰ ራዕይ እንጂ ሌላ አይደለም።

*ታዲያ የወረደው ቁርአን ነው* ብሎ አንድ ሰው ሊሞግት ይችላል፣ አዎ ቁርአን ብቻ ሳይሆን ሃዲሰል ነበውይና ቁድስይ የያዙት የነቢያችን ንግግርም የተወረደ ነው፦
4:113 አላህም በአንተ ላይ *መጽሐፍን* الْكِتَابَ እና *ጥበብን* وَالْحِكْمَةِ *አወረደ* أَنْزَلَ፤ የማታውቀዉንም ሁሉ አስተማረህ። የአላህም ችሮታ በአንተ ላይ ታላቅ ነው።
2:231 የአላህንም ጸጋ በናንተ ላይ ያደረገውን ከ*መጽሐፍ* الْكِتَابِ እና ከ*ጥበብም* وَالْحِكْمَةِ በርሱ የሚገስጻችሁ ሲኾን በናንተ ላይ *ያወረደውን* وَأَنْزَلَ አስታውሱ፡፡

ኪታብ كِتَٰب *መጽሐፍን* የተባለው ቁርአን ሲሆን ሂክማት حِكْمَة *ጥበብ*የተባለው ደግሞ ሐዲስ ነው፣ ኪታብና ሂክማት በተባሉት ቃላት መካከል ወوَ ‘’እና‘’የሚል ሃርፉል ዓጥፍ ማለትም አያያዥ መስተጻምር“copulative conjunction‘’ ይጠቀማል፣ ያ ማለት ኪታብ የተባለው እና ሂክማት የተባለው ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን ያሳያል፣ በተጨማሪም አንዘለ አወረደ የሚል ቃላት መጠቀሙ ሁለቱም ተንዚል መሆናቸውን ያረጋግጥልናል፣ ነቢያችንም ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ፦
ሱነን አቢ ዳዉድ መጽሃፍ 42 ሐዲስ 9
عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ” أَلاَ إِنِّي أُوتِيتُ الْكِتَابَ وَمِثْلَهُ مَعَهُ
የአላህ መልእተኛም አሉ፦ መጽሃፍና መሰሉን ለእኔ ተሰጥቶኛል።

መጽሃፍ የተባለው ቁርአን ሲሆን የእርሱ መገለጫ መሰሉ ደግሞ ሃዲስ ነው፣ ታዲያ ልዩነቱ ምንድን ነው? ስንል ቁርአን ለፍዙ لفظ*ቃሉም* ሆነ መኣናው معنى *መልእክቱ* የአላህ ሲሆን ሐዲስ ግን ቃሉ የነቢያችን ሲሆን መልእክቱ ግን የአላህ ነው፦
33:22 አማኞቹም አሕዛብን ባዩ ጊዜ፥ ይህ አላህና መልክተኛው *የቀጠሩን*وَعَدَنَا ነው፤ አላህና መልክተኛዉም እውነትን *ተናገሩ* وَصَدَقَ አሉ።

አላህ ቃል የገባውና የተናገረው በቁርአን ሲሆን ነብያችን ደግሞ ቃል የገቡትና የተናገሩት በሐዲስ ነው፣ ሐዲስ ተንዚልና መልእክቱ የአላህ ባይሆን ኖሮ *መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ* አሊያም *መልክተኛው የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት። ከርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ* ይለን ነበር እንዴ?
4:80 መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፤ ከትዕዛዝም የሸሸ ሰው፣ አያሳስብህ በነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና።
59:7 መልክተኛው የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት። ከርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ።

አላህ እርሱንና መልእክተኛውን ታዘዙ ሲል ቁርአንና ሐዲስን ያሳያል: ከዚያም ባሻገር ምእመናን እርስ በእርሳቸው እንዳይጨቃጨቁ አዟል፣ ምክንያቱም በተጨቃጨቁ ጊዜ ፈሪዎችና ሃይላቸው የተገፈፉ ይሆናሉና፣ የሚያጨቃጭቅ ነገር ካለ ወደ አላህ ቁርአንና ወደ መልክተኛው ሃዲስ ማስረጃ ይዞ መነጋገር ነው፣ የአላህን ትእዛዝ ቁርአንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ ሃዲስን የጣሰ ሰው ግልጥ የሆነን መሳሳትን በእርግጥ ተሳሳተ፣ ሸሪያውም የተመሰረተው ወደ አላህቁርአንና ወደ መልክተኛው ሃዲስ ለመፍረድ ነው፦
8:46 *አላህንና መልክተኛውንም* ታዘዙ፤ አትጨቃጨቁም፤ ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትኼዳለችና፤
4:59 በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትሆኑ የተከራከራችሁበትን ነገር *ወደ አላህና ወደ መልክተኛው* መልሱት ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው።
33:36 *የአላህና የመልክተኛውንም ትእዛዝ* የጣሰ ሰው ግልጥ የሆነን መሳሳትን በእርግጥ ተሳሳተ።
24:48 *ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም* በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ፣ ከነሱ ከፊሉ ወዲያውኑ ይሸሻሉ።

ኢንሻላህ ይቀጥላል…….

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የሐዲስ እውቀት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
ከዚህ በፊት “ሐዲስ” حَدِيث ማለት የነብያችን”ﷺ” ቅዱስ *ንግግር* ማለት እደሆነ እና ወህይ እንደሆነ አይተን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለ “ዒልመል ሐዲስ” علم الحديث‌‎ ማለትም “ሥነ-ሐዲስ ጥናት” እናያለን፤ መቼም የኢስላም ጥናት ዘርፈ-ብዙ ነው፤ ተጅዊድ፣ ዒልመል ቁርአን፣ ዒልመል ሐዲስ፣ አቂዳ፣ ፊቂህ፣ ሲራ፣ ተፍሲር እያለ ይቀጥላል፤ “ሥነ-ሐዲስ ጥናት መሰረታዊ ጭብጦች ለማስጨበጥ ጸሐፊው በዒልመል ሐዲስ አንባቢ ብቻና ብቻ ነው እንጂ የሐዲስ ተማሪም ሆነ አስተማሪ አይደለም፤ ይህንን ጥናት ቅድሚያ ከሙስጠለሑል ሐዲስ እንጀምር “ሙስጠለሑል ሐዲስ” مُصْطَلَحُ الحَدِيْث‌‎ ማለት የሐዲስ ስያሜ”Hadith terminology” ናቸው፤ እነርሱም፦ ሰሒሕ፣ ሐሠን፣ ደኢፍ እና መውዱዕ ናቸው፤ እነዚህ ነጥብ በነጥብ ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
“ሰሒሕ”
“ሰሒሕ” صَحِيْح ማለት “ተአማኒ”authentic” ማለት ሲሆን ከነብያችን”ﷺ” በትክክል የተላለፈ ዘገባ ነው።
“ኢስናድ” اسند ማለት “ትረካ”narration” ሲሆን ትረካው የሚተላለፍበት ሰንሰለት”chain of narration” ደግሞ “ሠነድ” سند ይባላል።
የሚያስተላልፈው “ተራኪ”narrator” በተጨማሪ “ሙስኒድ” مسند ይባላል፤ በጣም ስመ-ጥርና ዝነኛ ተራኪዎች አቢ ሁረይራህ፣ አብደላህ ኢብኑ ኡመር፣ አይሻ፣ ጃቢር ኢብኑ አብደላህ፣ ኢብኑ ዓባስ እና አነስ ኢብኑ ማሊክ ናቸው፤ አንድ ኢስናድ ሰሒሕ ለመባል አምስት ሸርጦች ተቀምጠዋል፦
1ኛ. “አድል”
በትረካው ሰንሰለት ያለው ተራኪ ታማኝ ሰው መሆን፣
2ኛ. “ደብጥ”
ተራኪው የማስታወስ ችሎታው ከጽሑፍ ጋር ማስቀመጡ፤ ይህ ጽሑፍ “መትን” متن ይባላል፣
3ኛ. “ሙተሲል”
የትረካው ሰንሰለት የተቀበለበት “አያያዥ ማንነት”connected predecessor” ያስፈልጋል፤ ይህ አያያዥ ማንነት “ሙተሲል” مُتَّصِل ይባላል፣
4ኛ. “ሰነድ”
የሐዲሱ ሰንሰለት የተሰበረ መሆን የለበትም፤ ያ ማለት ኢስናድ መኖሩ አንዱ ሸርጥ ነው፣
5ኛ. “ሻዝህ”
የሚቀጥለው ዘገባ እነዚህን አራት መስፈርት አልፎ ከቀደመው ዘገባ ጋር ምንም አይነት የሃሳብና የትጉም ተቃርኖ ወይም ግጭት አሊያም መጣረስ የለበትም።
እነዚህ አምስቱ የሰሒሕ ሐዲስ ሸርጦች ናቸው።

ነጥብ ሁለት
“ሐሠን”
የአንድ ተራኪ “የህይወት ዳራ”Biographical evaluation” ከላይ በተቀመጡበት አምስት ሸርጦች የሚጠናበት ጥናት “ኢልሙ ሪጃል” عِلْمُ الرِّجال‎ ይባላል፤ ከአነዚህ ሸርጦች አራቱን ማለትም፦ አድል፣ ሙተሲል፣ ሰነድ እና ሻዝህ አሟልቶ ነገር ግን አንዱን ደብጥ የተባለውን ሸርጥ ካላሟላ ሐዲሱ “ሐሠን” ይሰኛል።

ነጥብ ሶስት
“ደኢፍ”
“ደኢፍ” ضَعِيْف ማለት “ደካማ”weak” ማለት ሲሆን አንድን ዘገባ ደካማ የሚያሰኘው ወደ ሙሐዲስ የሚመጣበት አካሔድ ደካማ መሆኑ ነው፤ “ሙሐዲስ”محديث‎ ማለት “ዘጋቢ”collector” ማለት ሲሆን እነዚህም ሙሐዲሲን ኢማም ቡኻሪ፣ ኢማም ሙስሊም፣ ቲርሚዚ፣ ኢብን ማጃ፣ አቡ ዳውድ፣ ነሳኢ ወዘተ ናቸው፤ አንድ ዘገባ ደካማ ነው የሚያሰኘው አምስት ሸርጦች አሉት፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ሙአለቅ”
“ሙአለቅ” مُعَلَّق ማለት በሙሐዲስ እና በነብያችን”ﷺ” መካከል ምንም አይነት ተራኪና ትረካ ሳይኖር ሲቀር “ሙአለቅ” ይባላል።
2ኛ. “ሙርሰል”
“ሙርሠል”مُرْسَل ማለት በነብያችን”ﷺ” እና በዘጋቢው መካከል ተራኪ ከሌለው ግን ትረካ ካለው “ሙርሰል” ይባላል።
3ኛ. “ሙንቀጢዕ”
“ሙንቀጢዕ” مُنْقَطِع ማለት በነብያችን”ﷺ” እና በተራኪው መካከል ትረካ ከሌለው “ሙንቀጢዕ” ይባላል።
4ኛ. “ሙንከር”
“ሙንከር” مُنْكَر በደካማ ተራኪ ተተርኮ ትረካው ከሰሒሕ ዘገባ ጋር ከተጋጨ “ሙንከር” ይባላል።
5ኛ. “ሙጠሪብ”
“ሙጠሪብ” مُضْطَرِب ማለት አንድ ሐዲስ የተቃረኑ የዘገባ ሰነዶች ሲኖሩት ወይንም ዘገባው የተቃረኑ መትኖች ሲኖሩት “ሙጠሪብ” ይባላል።

ነጥብ አራት
“መውዱዕ”
“መውዱዕ” مَوْضُوْع ማለት “ቅጥፈት”fabricated” ማለት ሲሆን ነብያችን”ﷺ” ሳይሉ እንዳሉ ተደርጎ በሙናፊቂን፣ በሙርተዲን እና በሙብተዲዒን ወዘተ የተቀጠፈ ኢስናድ ነው፤ አነዚህ ሰዎች በዲኑ ላይ አዲስ ነገር እንደሚቀጥፉ ነብያችን”ﷺ” ተናግረዋል፦
ኢማም ቡሃሪ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 170
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ ከባልደረቦቼ ጥቂት ወደ ሐውድ ፏፏቴዬ ይመጣሉ፤ ከዚያም እኔ አውቃቸዋለው፤ ከዚያም ከእኔ ይወገዳሉ፤ እኔም እንዲህ እላለው፦ “ባልደረቦቼ”፤ እርሱም እንዲህ ይላል፦ ከአንተ በኃላ በሃይማኖቱ አዲስ ነገር እንደሚጨምሩ አታውቅም” عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لَيَرِدَنَّ عَلَىَّ نَاسٌ مِنْ أَصْحَابِي الْحَوْضَ، حَتَّى عَرَفْتُهُمُ اخْتُلِجُوا دُونِي، فَأَقُولُ أَصْحَابِي. فَيَقُولُ لاَ تَدْرِي مَا أَحْدَثُوا بَعْدَكَ

ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 514
ኢብን ዑመር”ረ.አ.” የአሏህ መልክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “በእናንተ ላይ የሚሾሙ የማይተገብሩትን እንድትተገብሩ የሚያዝዟችሁ ባለስልጣናት ይመጣሉ ፤ ውሸታቸውን እውነት ነው ብሎ ያጸደቀላቸው፣ በሚሰሩትም ግፍ ላይ ተባባሪ ሆኑ ያገዛቸው እኔ ከእርሱ አይደለሁም እርሱም ከእኔ አይደለም ከሐውዴም መጥቶ አይጣድም”

ኢማም ቡሃሪ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 128
ነብዩም “ﷺ” አሉ፦…በእኔ ላይ ውሸትን የቀጠፈብኝ ግለሠብ መቀመጫውን በጀሃነም እሳት ውስጥ ያደላድል። ومن كذب علي متعمداً، فليتبوأ مقعده من النار”.
ማጠቃለያ
አንድ የነብያችን”ﷺ” ንግግር በትክክል ተተርኳል ለማለት እንዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ሚዛኖች ወሳኝ ነጥቦች ናቸው፤ አንድ ንግግር ሲመጣ ያ የመጣውን ወሬ ማረጋገጥ የሙስሊም ተቀዳሚ እርምጃ ነው፦
49፥6 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! #ነገረኛ” فَاسِقٌۢ #ወሬን” ቢያመጣላችሁ #በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን #እንዳትጎዱ እና በሠራችሁት ነገር ላይ #ተጸጸቾች እንዳትኾኑ #አረጋግጡ፡፡

ይህንን ካደረግም በኃላ ትረካዎችን በአግድም”horizontal” እና በተፋሰስ”vertical” መረዳት ይቻላል፤ ትረካዎቹ በአግድም ሲተረኩ በሁለት እረድፍ ይተረካሉ፤ እነርሱም፦
1ኛ. “አሐድ” آحاد አንድ ትረካ በአንድ ሙስኒድ ከተተረከ ተራኪው “አሐድ” ይባላል፤ ለምሳሌ በኡመር”ረ.አ.” የተተረከው ትረካ ልብ ይለዋል፤
2ኛ. “ሙተዋቲር” مُتَواتِر ደግሞ አንድ ትረካ ከአንድ በላይ ሙስኒድ በጀመዓ የሚደረግ ትረካ ነው።

ትረካዎቹ በተፋሰስ ሲተረኩ በሁለት እረድፍ ይተረካሉ፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ገሪብ” غَرِيْب ማለት የትረካው ሰንሰለት ላይ አንድ ተራኪ ሲሆን ያ ትረካ “ገሪብ” ይባላል።
2ኛ.”አዚይዝ” عَزِيْز የትረካው ሰንሰለት ሁለትና ከሁለት ተራኪዎች በላይ ሲተርኩት ያ ትረካ “አዚይዝ” ይባላል።

ትረካዎች የሚያነጣጥሩበት ሶስት ባህርያት አሉት፤ እነርሱም፦
1ኛ. “መርፉዕ” مَرْفُوْع ስለ ነብያችን”ﷺ” የንግግር ባህርይ የሚተረክ ትረካ ነው፣
2ኛ. “መውቁፍ” مَوْقُوْف ስለ ሶሐባህ ባህርይ የሚተረክ ትረካ ሲሆን፣
3ኛ. “መቅጡዕ” مَقْطُوْع ደግሞ ስለ ታቢኢይ ባህርይ የሚተረክ ትረካ ነው።

ዋቢ መጽሐፍ፦
1. “Nukhbat al-Fikar” Author: Ibn Hajr al Asqalani
2. “Studies in Hadith Methodology and Literature”, by Muhammad Mustafa Al-A’zami

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነፍስ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

75፥2 *ራሷን ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ*፡፡ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፡፡ وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ

ቁርኣን ላይ ስለ ነፍስ እንደየ ዐውዱ የተለያየ አጠቃቀም ይጠቀማል፤ ይህንን በአጽንዖትና በአንክሮት ማየት ይቻላል፤ "ነፍስ" نَفْس የሚለው ቃል ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun” ሲሆን “ራስነት”own self-hood” ነው፤ በመጀመሪያ መደብ "ነፍሢ" نَفْسِي ማለት "እራሴ" ፤ በሁለተኛ መደብ "ነፍሢከ" نَفْسِكَ ማለት "እራስህ" እና በሦስተኛ መደብ "ነፍሢሂ" نَفْسِهِ "ራሱ" የሚል መደብ ተውላጠ-ስም ነው፦
4፥79 ከደግም የሚያገኝህ ከአላህ ነው፤ ከፉዉም የሚደርስብህ *ከራስህ* ነው፤ مَّا أَصَابَكَ مِنْ حَسَنَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ۖ وَمَا أَصَابَكَ مِن سَيِّئَةٍ فَمِن نَّفْسِكَ ۚ وَأَرْسَلْنَاكَ لِلنَّاسِ رَسُولًا ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا

“ራስህ” የሚለው ቃል “ነፍሲከ” نَفْسِكَ ሲሆን ማንነትን”identity” ያሳያል፤ “ነፍስ” ነባቢ(ተናጋሪ)፣ ዐዋቂ፣ ሕያው ማንነትን ይገልጻል፤ ለምሳሌ አላህ የራሱ ማንት ስላለው ነባቢ መለኮት፣ ዐዋቂ መለኮት፣ ሕያው መለኮት ነው። የአላህ ማንነት በራሱ ተብቃቂ ሲሆን በሕያውነቱ ጅማሬ ስለሌለው ፍጡር አይደለም፤ በሕያውነቱ ፍጻሜ ስለሌለው የማይሞት ነው፤ ለዚህ ነው “ነፍሲ” نَفْسِي ማለትም “እራሴ” የሚለው፦
20፥41 *ለነፍሴም መረጥኩህ*፡፡ وَاصْطَنَعْتُكَ لِنَفْسِي

በዚህ አንቀጽ ላይ “ለነፍሴ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሊነፍሢ” لِنَفْسِي ሲሆን “ለራሴ” ማለት ነው፤ እንግዲህ ነፍስ ማለት እራስነት”own self-hood” ማለት ከሆነ አላህ፦ "ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁ" ሲል ከአንድ ማንነት የፈጠራችሁ ማለት ነው፦
4፥1 *እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً

“ነፍሥ” نَفْس የሚለው ቃል አደምን ያሳያል፤ “መቀናጃዋ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል ”ዘውጀሃ” زَوْجَهَا ሲሆን የአደም ጥንድን ያሳያል፤ ይህቺም ጥንድ ሐዋ ናት፤ "ነፍሥ" በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ "ከ" የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ከአደም መፈጠራችንን ያሳያል፤ “ከእነርሱም” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሁማ” مِنْهُمَا ሲሆን ሙተና ማለትም ሁለትዮሽ”dual” የሚያሳይ ነው፤ "እነርሱም" በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ "ከ" የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ከአደምና ከሐዋ መፈጠራችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች ተፈጠረ፦
49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ

"ወንድ" እና "ሴት" በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ "ከ" የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ሰዎች ከወንድና ከሴት መፈጠራቸውን ያሳያል፤ ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ከወንድና ከሴት ይፈጠር እንጂ የራሱ ነፍስ ማለትም የሚጠየቅበት ማንነት አለው፦
23፥62 *ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም*፡፡ وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا
2፥286 *አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም*፡፡ لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا

ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው የራሱ ማንነት አለው፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ሰውን ሲገድል "ነፍሰ ገዳይ" ነው፦
17፥33 *ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَق
28፥33 ሙሳ አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ከእነርሱ *ነፍስን ገድያለሁ*፡፡ ስለዚህ እንዳይገድሉኝ እፈራለሁ፡፡ قَالَ رَبِّ إِنِّي قَتَلْتُ مِنْهُمْ نَفْسًا فَأَخَافُ أَن يَقْتُلُونِ

"ነፍስን አትግደሉ" የሚለው ነፍስ የሚገደል ማንነት እንደሆነ ያሳያል፤ ይህ ማንነት መዳረሻው ሞትን መቅመስ ነው፦
3፥185 *ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት*፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ
39፥30 *አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው*፡፡ إِنَّكَ مَيِّتٌ وَإِنَّهُم مَّيِّتُونَ

ልብ አድርግ "ነፍስ" የሚለው "እኔ" "እኛ" "አንተ" "አንቺ" "እናንተ" "እርሱ" "እርሷ" "እነርሱ" የሚለውን ተውላጠ-ስም ተክቶ የሚመጣ ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን በሰው ማንነት ውስጥ ውሳጣዊ፣ ረቂቅ፣ ምጡቅ፣ የማይታይ፣ የማይዳሰስ፣ የማይጨበጥ ነገር አለ፤ ይህ ነገር ሩሕ ይባላል፤ “ሩሕ” رُّوح ማለት “መንፈስ” ማለት ሲሆን ይህ የሰው መንፈስ ሥረ-መሰረቱ ከዐፈር ሳይሆን ከጌታችን ነገር ነው፤ ስለ “ሩሕ” የተሰጠን ዕውቀት ጥቂት ብቻ ነው፦
17፥85 *ስለ ሩሕም ይጠይቁሃል፤ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፤ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِ ۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّى وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًۭا

ነፍሥ የሚለው ቃል ሩሕን ለማመልከት ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ ይመጣል፦
39፥42 *አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል*፡፡ ያችንም ያልሞተችውን *በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል”*፡፡ ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلْأَنفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَٱلَّتِى لَمْ تَمُتْ فِى مَنَامِهَا

“በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል” ማለት አንደኛ እንያንዳንዷ ነፍስ ሟች መሆኗን ያሳያል፤ ሁለተኛ አላህ መልአከ ሞትን ልኮ ነፍስን በሞታቸው ጊዜ “ይወስዳታል፤ አሁንም “ይወስዳችኃል” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ነው፦
32፥11 «በእናንተ የተወከለው መልአከ ሞት *”ይወስዳችኃል”*፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَتَوَفَّىٰكُم مَّلَكُ ٱلْمَوْتِ ٱلَّذِى وُكِّلَ بِكُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ
ከዚያ የሞት መላእክት ያናግራሉ፤ የሚያናግሩት ሩሕዎችን ነው፦
7፥37 የሞት መልክተኞቻችንም *”የሚወስዷቸው ኾነው በመጡባቸው ጊዜ”* «ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው የነበራችሁት የት አሉ» ይሏቸዋል፡፡ «ከእኛ ተሰወሩን» ይላሉ፡፡ እነርሱም ከሃዲያን እንደነበሩ በነፍሶቻቸው ላይ ይመሰክራሉ፡፡ حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَتْهُمْ رُسُلُنَا يَتَوَفَّوْنَهُمْ قَالُوٓا۟ أَيْنَ مَا كُنتُمْ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ ۖ قَالُوا۟ ضَلُّوا۟ عَنَّا وَشَهِدُوا۟ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ أَنَّهُمْ كَانُوا۟ كَٰفِرِين
23፥99 አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል፦ *«ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ
23፥100 *«በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» ይህን ከማለት ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት*፡፡ لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا

“ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ በእንቅልፏ ጊዜ ይወስዳታል” በእንቅልፍ ጊዜ ማስተኛትን ያመለክታል፤ “ይወስዳል” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፈ” يَتَوَفَّى ሲሆን በሌላ አንቀፅ ላይ “የሚያስተኛችሁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የተወፍፋኩም” يَتَوَفَّاكُمْ ነው፦
6፥60 እርሱም ያ በሌሊት *”የሚያስተኛችሁ”* በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ በቀን ውስጥ *”የሚቀሰቅሳችሁ”* ነው፡፡ ከዚያም *”መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው”*፡፡ ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡ وَهُوَ ٱلَّذِى يَتَوَفَّىٰكُم بِٱلَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُم بِٱلنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَثُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَىٰٓ أَجَلٌۭ مُّسَمًّۭى ۖ ثُمَّ إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ ثُمَّ يُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

የሰው አካል እረፍት ሲያደርግ ነገር ግን የሰው መንፈስ ያለ ዓይን ታያለች፣ ያለ ጆሮ ትሰማለች፣ ያለ እግር ትሄዳለች፣ ያለ አፍ ትናገራለች፤ ይህ ህልም ይባላል፤ በእንቅልፍ ጊዜ ሩሕ ከአካላችን ጋር እንዴት እንደምትለያይ ልምምድ ላይ ናት። ይህቺ ሩሕ በትንሳኤ ቀን የፈረሰውን አካል ሕያው ይሆንባት እና ሰው ይቀሰቀሳል፦
75፥2 *ራሷን ወቃሽ በኾነች ነፍስም እምላለሁ*፡፡ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፡፡ وَلَا أُقْسِمُ بِالنَّفْسِ اللَّوَّامَةِ

በቁርኣን "ነፍስ" አንዳንዴ “ነፍሢያን” نفسيه ማለትም "የውስጥ ዝንባሌን"inclination" ለማመልከት ይጠቀምበታል፦
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር *”በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥164 በላቸው «እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ስለ ነፍስ በባይብል እናያለን....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም