ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.2K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ አንድ
"ብሉይ ኪዳን"
ብሉይ ኪዳን ላይ ስላሉት መጽሐፍት የተለያዩ አንጃዎች አንድ አቋም የላቸውም፤ እነርሱን በተናጥን እስቲ እንይ፦

A. "የፕሮቴስታንት ቀኖና"
ፕሮቴስታንት የሚቀበለው ሁሉም ጋር ተቀባይነት ያለው አቆጣጠር
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት 39 ናቸው፤ እነርሱም፦
1. ኦሪት ዘፍጥረት
2. ኦሪት ዘጸአት
3 ኦሪት ዘኁልቁ
4. ኦሪት ዘሌዋውያን
5. ኦሪት ዘዳግም
6. መጽሐፈ ኢያሱ
7. መጽሐፈ መሳፍንት
8. መጽሐፈ ሩት
9. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
10. መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
11. መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
12. መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
13. ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
14. ዜና መዋዕል ካልዕ
15. መጽሐፈ ዕዝራ
16. መጽሐፈ ነህምያ
17. መጽሐፈ አስቴር
18. መጽሐፈ ኢዮብ
19. መዝሙረ ዳዊት
20. መጽሐፈ ምሳሌ
21. መጽሐፈ መክብብ
22. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
23. ትንቢተ ኢሳይያስ
24. ትንቢተ ኤርምያስ
25. ሰቆቃው ኤርምያስ
26. ትንቢተ ሕዝቅኤል
27. ትንቢተ ዳንኤል
28. ትንቢተ ሆሴዕ
29. ትንቢተ አሞጽ
30. ትንቢተ ሚክያስ
31. ትንቢተ ኢዮኤል
32. ትንቢተ አብድዩ
33. ትንቢተ ዮናስ
34. ትንቢተ ናሆም
35. ትንቢተ ዕንባቆም
36. ትንቢተ ሶፎንያስ
37. ትንቢተ ሐጌ
38. ትንቢተ ዘካርያስ
39. ትንቢተ ሚልክያስ ናቸው።

B. "የአይሁዳውያን ቀኖና"
39 መጽሐፍት አይሁዳውያን እንደጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 90 ድህረ-ልደት"AD" በጀሚኒያ 24 የቀኖና መጽሐፍት አርገዋቸዋል፤ አቆጣጠራቸው ግን ይለያል፦
1. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ እና መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ አንድ መጽሐፍ ሻሙኤል ብለው፣
2. መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ እና መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ አንድ መጽሐፍ መላክሂም ብለው፣
3. ዜና መዋዕል ቀዳማዊ እና ዜና መዋዕል ካልዕ አንድ መጽሐፍ ሃያሚን ብለው፣
4. መጽሐፈ ዕዝራ እና መጽሐፈ ነህምያ አንድ መጽሐፍ አዝራ ብለው፣
5. ከሆሴዕ እስከ ሚልኪያስ ያሉት 12 መጽሐፍት አንድ መጽሐፍ ትሬአሳር ብለው ይቆጥሩታል።

ከሆሴዕ እስከ ሚልኪያስ ያሉት በአንድ የተጣፉትን 11 መጽሐፍት እና የተጣፉትን 4 መጽሐፍት ስንደምር 15 ይሆናል፤ 15+24= 39 መጽሐፍት ይሆናሉ። አይሁዳውያን መጽሐፍቶቻቸውን "ታንካህ" תַּנַ”ךְ, ሲሉት የሶስቱ መጽሐፍት መነሻ ላይ ያሉት ቃላት መሰረት አርገው ነው፤ እነዚህም "ታ" תַּ ቶራህ፣ "ና" נַ ነቢኢም፣ "ካ" ךְ ኬቱዊም ናቸው። "ቶራህ" תּוֹרָה ማለት "ኦሪት" "ሕግ" "መርሕ" ማለት ነው፣ ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም ያሉትን ለማመልከት ይጠቀሙብታል።
"ነቢኢም" נְבִיאִים ማለት "ነቢያት" ማለት ሲሆን የኢሳያስ ትንቢት፣ የኤርሚያስ ትንቢት፣ የህዝቅኤል ትንቢት ወዘተ ለማመልከት ይጠቀሙብታል።
"ኬቱዊም" כְּתוּבִים ማለት "መጻሕፍት" ማለት ሲሆን የኢዮብ መጽሐፍ፣ የመዝሙር መጽሐፍ፣ የምሳሌ መጽሐፍ፣ የመክብብ መጽሐፍ፣ የመኃልየ መኃልይ መጽሐፍ ወዘተ ለማመልከት ይጠቀሙብታል።

C. "የካቶሊክ ቀኖና"
የሮማ ካቶሊክ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 46 ናቸው፤ ካቶሊክ በ 39 ላይ እራሳቸውን የቻሉ 7 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ፦
1. መጽሐፈ ጦቢት፣
2. መጽሐፈ ዮዲት፣
3. መጽሐፈ ጥበብ፣
4. መጽሐፈ ሲራክ፣
5. መጽሐፈ ባሮክ፣
6. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ
7. መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ ናቸው።

D. "የኦርቶዶክስ ቀኖና"
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 46 ናቸው፤ የብሉይ ኪዳን መደበኛ የቀኖና መጽሐፍት 39 ሲሆኑ ተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 18 ናቸው፤ ነገር ግን አቆጣረራቸው ልክ እንደ አይሁድ ይለያል። እራሳቸውን የቻሉ 10 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ አቆጣጠራቸው፦
1. መጽሐፈ ሄኖክ፣
2. መጽሐፈ ኩፋሌ(ጁብሊይ)፣
3. መጽሐፈ ጦቢት፣
4. መጽሐፈ ዮዲት፣
5. መጽሐፈ ተግሣጽ፣
6. መጽሐፈ ጥበብ፣
7. መጽሐፈ ሲራክ
8. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ቀዳማይ እና መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ካልዕ፣
9. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማይ እና መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ፣
10. መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ናቸው።

ነባር መጽሐፍት ላይ በመቀነስ ተጨፍልቀው የሚቆጠሩ 2 መጽሐፍት ናቸው፤ እነርሱም፦
11. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማይ እና መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ናቸው፣
12. መጽሐፈ ዕዝራ ቀዳማይ እና መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ(ነህምያ) ናቸው።

ከነባር መጽሐፍት ጋር ተደምረው የሚቆጠሩ ደግሞ 8 መጽሐፍት ናቸው፤ እነርሱም፦
13. ከትንቢተ ኢሳይያስ ጋር የሚቆጠረው ጸሎተ ምናሴ ነው።
14. ከትንቢተ ኤርምያስ ጋር የሚቆጠሩ፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ፣ ተረፈ ኤርምያስ፣ መጽሐፈ ባሮክ፣ ተረፈ ባሮክ ናቸው።
15. ከትንቢተ ዳንኤል ጋር የሚቆጠሩ መጽሐፈ ሶስና፣ ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ እና ተረፈ ዳንኤል ናቸው።

ከ 39 ላይ 8 መጽሐፍት፦ ሳሙኤል ቀዳማይ፣ ሳሙኤል ካልዕ፣ መጽሐፈ ዕዝራ፣ መጽሐፈ ነህምያ፣ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ትንቢተ ኤርሚያ፣ ሰቆቃው ኤርሚያስ እና ትንቢተ ዳንኤል ሲቀነሱ 31 መጽሐፍት ይሆናሉ። 31+15= 46 ይሆናል።

F. "የሰፕቱአጀንት ቀኖና"
የሰፕቱአጀንት ቀኖና የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 56 ናቸው፤ የሰፕቱአጀንት"LXX" በ 39 ላይ እራሳቸውን የቻሉ 17 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ፦
1. መጽሐፈ ጦቢት፣
2. መጽሐፈ ዮዲት፣
3. መጽሐፈ ጥበብ፣
4. መጽሐፈ ሲራክ፣
5. መጽሐፈ ባሮክ፣
6. ተረፈ ኤርምያስ፣
7. ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ፣
8. መጽሐፈ ሶስና፣
9. ቤልና ድራጎን፣
10. ጸሎተ ምናሴ፣
11.1ኛ መቃብያን፣
12. 2ኛ መቃብያን፣
13. 3ኛ መቃብያን፣
14. 4ኛ. መቃብያን፣
15. ዕዝራ ሱቱኤል፣
16. የአዛርያ ጸሎት፣
17. መዝሙር 151 ናቸው።

G. "የቩልጌት ቀኖና"
ጄሮም በ 382 ድህረ-ልደት በላቲን ቩልጌት ባዘጋጀው ደግሞ የመጽሐፍት ቀኖና 45 ናቸው፤ የቩልጌት በ 39 ላይ እራሳቸውን የቻሉ 6 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ፦
1. መጽሐፈ ጦቢት፣
2. መጽሐፈ ዮዲት፣
3.1ኛ መቃብያን፣
4. 2ኛ መቃብያን፣
5. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ቀዳማይ፣
6. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ካልዕ

ኢንሻላህ ስለ አዲስ ኪዳን በክፍል ሁለት ይቀጥላል...

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቀኖና

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

5፥15 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

ነጥብ ሁለት
"አዲስ ኪዳን"
የአዲስ ኪዳን መደበኛ መጻሕፍት 27 ናቸው፤ እነርሱም እንደሚከተለው ነው፦
1. የማቴዎስ ወንጌል
2. የማርቆስ ወንጌል
3. የሉቃስ ወንጌል
4. የዮሐንስ ወንጌል
5. የሐዋርያት ሥራ
6. የሮሜ ሰዎች
7. 1ኛ. የቆሮንቶስ ሰዎች
8. 2ኛ. የቆሮንቶስ ሰዎች
9. የገላትያ ሰዎች
10. የኤፌሶን ሰዎች
11. ያፊልጵስዩስ ሰዎች
12. የቆላስይስ ሰዎች
13. 1ኛ. የተሰሎንቄ ሰዎች
14. 2ኛ. የተሰሎንቄ ሰዎች
15. 1ኛ. ጢሞቴዎስ
16. 2ኛ. ጢሞቴዎስ
17. ቲቶ
18. ፊልሞና
19. የዕብራዊያን ሰዎች
20. 1ኛ. ጴጥሮስ መልእክት
21. 2ኛ. ጴጥሮስ መልእክት
22. 1ኛ. ዮሐንስ መልእክት
23. 2ኛ. ዮሐንስ መልእክት
24 3ኛ. ዮሐንስ መልእክት
25. የያዕቆብ መልእክት
26. የይሁዳ መልእክት
27. የዮሐንስ ራዕይ

በእነዚህ መጽሐፍት ላይ ሁሉም የጋራ አቆጣጠር ቢኖራቸውም ነገር ግን የጭማሬ እና የቅነሳ ነገር ይታይበታል። ይህንንም በግርድፉ እንይ፦
A. "የኦርቶዶክስ ቀኖና"
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 35 ናቸው፤ የአዲስ ኪዳን መደበኛ የቀኖና መጽሐፍት 27 ሲሆኑ ተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሐፍት ቀኖና 8 ናቸው፤ እነዚህም፦
1. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማይ፣
2. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ
3. መጽሐፈ ሥርዓተ ጽዮን
4. መጽሐፈ አብጥሊስ
5. መጽሐፈ ግጽው፣
6.መጽሐፈ ትእዛዝ፣
7. መጽሐፈ ዲድስቅልያ እና
8. መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ናቸው።

B. "የአርመንያ ቀኖና"
የአርመንያ ቤተክርስቲያን በ 27 ቀኖና ላይ 5 መጽሐፍትን ትጨምራለች፤ እነርሱም፦
1. 3ኛ የቆሮንቶስ ሰዎች መልእክት
2. የሎዶቅያ ሰዎች መልእክት
3. የበርናባስ መልእክት
4. 1ኛ የክሌመንት መልእክት
5. 2ኛ የክሌመንት መልእክት

C. "የሉተር ቀኖና"
የፕሮቴስታንት ተሃድሶ ንቅናቄ መሪ ማርቲን ሉተር ከ 27 ላይ 4 መጽሐፍትን ቀንሶ 23 ብቻ ነው የተቀበለው፤ እነርሱም፦
1. የዕብራዊያን ሰዎች
2. የያዕቆብ መልእክት
3. የይሁዳ መልእክት
4. የዮሐንስ ራዕይ
ማጠቃለያ
አይሁዳውያን ለሙሳ የተሰጠውን መጽሐፍ በመከፋፈል ኦሪት ዘፍጥረት፣ ኦሪት ዘጸአት፣ ኦሪት ዘኁልቁ፣ ኦሪት ዘሌዋውያን፣ ኦሪት ዘዳግም በማለት ከፋፍለውታል፤ እነርሱም የማይመቻቸውን አፓክራፋ ማለት ድብቅ በማለት በመቀነስ ደብቀውታል፤ ከዚያም ባሻገር አባቶቻቸውም የማያውቁት ንግግር በአምላክ ንግግር ላይ ጨምረዋል፦
6፥61 እንዲህ በላቸው፡- «ያንን ብርሃን እና ለሰዎች መሪ ኾኖ *ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው? የወደዳችኋትን ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፤ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ*። قُلْ مَنْ أَنزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَىٰ نُورًا وَهُدًى لِّلنَّاسِ ۖ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيرًا ۖ وَعُلِّمْتُم مَّا لَمْ تَعْلَمُوا أَنتُمْ وَلَا آبَاؤُكُمْ ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ ثُمَّ ذَرْهُمْ فِي خَوْضِهِمْ يَلْعَبُونَ

አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ የአርመንያ ቀኖና ውስጥ የሚገኘውን የአስራ ሁለቱ ነገዶችን መጽሐፍ፣ የአብርሃምን የቃል ኪዳን መጽሐፍ፣ የነቢዩ ሸማያ፣ የነቢዩ አዶ፣ የነቢዩ ናታን፣ የነቢዩ ኦሒያ፣ የነቢዩ ዖዴድ የትንቢት መጽሐፍት፣ መጽሐፈ ሄኖክ፣ መጽሐፈ ኩፋሌ፣ መጽሐፈ ጦቢት፣ መጽሐፈ ዮዲት፣ መጽሐፈ ጥበብ፣ መጽሐፈ ሲራክ፣ መጽሐፈ ባሮክ፣ የመሳሰሉትን "አፓክራፋ" ማለትም "ድብቅ" ብለው ሲቀንሱ በተቃራኒው የሰው ንግግር የሆኑትን መጽሐፈ ኢያሱ፣ መጽሐፈ መሳፍንት፣ መጽሐፈ ሩት፣ መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ፣ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ወዘተ በአምላክ ንግግር ላይ ጨምረዋል። ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. Bruce, Frederick (1988). The Canon of Scripture. Downers Grove, Illinois, U.S.: IVP Academic.
2. The Writings: The Third Division of the Old Testament Canon. George Allen & Unwin Ltd., 1963,
3. Michael Coogan. A Brief Introduction to the Old Testament: The Hebrew Bible in Its Context. Oxford University Press, 2009,

ክርስቲያኖች በ 387 ድህረ-ልደት”AD” በካርቴጅ ጉባኤ ከወንጌላት የቶማስ፣ የይሁዳ፣ የጴጥሮስ፣ የያዕቆብ፣ የበርናባስ፣ የፊሊጶስ፣ የበርተሎሞዎስ፣ የመቅደላዊት ማርያም የተባሉትን ወንጌላትን ቀንሰዋል።
ከሥራም ዘገባ የጴጥሮስ ስራ፣ የእንድሪያስ ስራ፣ የፊሊጶስ ስራ፣ የበርናባስ ስራ፣ የጳውሎስ ስራ፣ የዮሐንስ ስራ፣ የቶማስ ስራ ቀንሰዋል።
ከመልእክታትም 3ኛ የቆሮንቶስ ሰዎች መልእክት፣ የሎዶቅያ ሰዎች መልእክት፣ የበርናባስ መልእክት፣ 1ኛ የክሌመንት መልእክት፣ 2ኛ የክሌመንት መልእክት፣ የሄርሜኑ እረኛ መልእክት ወዘተ ቀንሰዋል።
ከአፓልካሊፕስም(ራዕይ) የጴጥሮስ አፖልካሊፕስ፣ የጳውሎስ አፖልካሊፕስ፣ የቶማስ አፖልካሊፕስ፣ የያዕቆብ አፖልካሊፕስ ቀንሰዋል።
ልብ አድርግ እነዚህ አፓክራፋ በጥንታዊያን እደ-ክታባት ለምሳሌ በክላሮሞንታነስ እደ-ክታብ"Codex Claromontanus" ውስጥ የጳውሎስ ስራ፣ የጴጥሮስ ራዕይ፣ የሄርሜኑ እረኛ መልእክት፣ የበርናባስ መልእክት ይገኛሉ፤ በአሌክሳንድሪየስ እደ-ክታብ"Codex Alexandrinus" ውስጥ 2ኛ የክሌመንት መልእክት ይገኛሉ፤ በሳይናቲከስ እደ-ክታብ"Codex Sinaiticus" ውስጥ የሄርሜኑ እረኛ መልእክት እና የበርናባስ መልእክት ይገኛሉ።
ከዚያም ባሻገር የሰው ንግግር የሆኑትን ታሪክና መልእክት በወንጌል ላይ ቀላቅለዋል። ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. Lost Scriptures: Books that Did Not Make It into the New Testament. Oxford University Press, USA. 2003
2. The New Testament and Other Early Christian Writings: A Reader. Oxford University Press, USA. 2003
3. The Other Gospels: Accounts of Jesus from Outside the New Testament. Oxford University Press, USA. 2013 by Bart D. Ehrman.
ይህ በእንዲህ እንዳለ አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ብዙውን የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛውን በእርግጥ ልኳል፦
5፥15 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

“አፓክራፋ” የሚለው ቃል “አፓክራፈስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፤ ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት አስፈላጊውን አላህ የገለጸ ሲሆን ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት ብዙውን ትቶታል፤ ወደ ነብያት ምን ተወርዶ እንደነበረ መልእክተኛው እንዲገልጹ ቁርኣንን አውርዷል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ *ወደ አንተም ለሰዎች ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን*፡፡ بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

ይህ ቁርኣን ከበፊቱ ከአላህ የተወረዱትን የአላህ ንግግሮች የሚያረጋግጥ እና በእነዚያ ንግግሮች ውስጥ ያለውን ጭብጥ የሚዘረዝር ነው፦
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፤ *ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَمَا كَانَ هَـٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَـٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ

የአዲስ ኪዳን እና የብሉይ ኪዳን ጽንፈኛ ሆነ ለዘብተኛ ምሁራን የባይብል ሥረ-መሰረት"orgin" ማለትም ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ኪታባት የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልዕክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት በዘመናችን እንደሌሉ ይናገራሉ፤ ባይብል ሙሉ ለሙሉ የፈጣሪ ንግግር ነው ብለው አያምኑም፤ "ፈጣሪ ሰዎችን የራሳቸውን ቃላት፣ ቋንቋ፣ ክህሎት እና ንግግር ተጠቅመው እንዲናገሩ ፈቀደላቸው" ይላሉ፤ ይህ ስህተት ነው። ለዛ ነው የፈጣሪ ንግግር ተበርዟል የምንለው፤ እውነትን በውሸት ሲቀላቅሉ እውነት የሆነው የአላህ ንግግር ከሰው ንግግር ጋር ስለተቀላቀለ እውነትን ከሐሰት ለመለየት አምላካችን አላህ ቁርአንን ፉርቃን አድርጎ አውርዷል፤ “ፉርቃን” فُرْقَان ማለት “እውነትን ከሐሰት የሚለይ” ማለት ነው፦
3:71 የመጸሐፉ ሰዎች ሆይ! *“እዉነቱን በዉሸት” ለምን ትቀላቅላላችሁ*? “እዉነቱንም” እናንተ የምታወቁ ስትሆኑ ለምን ትደብቃላችሁ? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ
25፥1 ያ *ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው*፡፡ تَبَارَكَ ٱلَّذِى نَزَّلَ ٱلْفُرْقَانَ عَلَىٰ عَبْدِهِۦ لِيَكُونَ لِلْعَٰلَمِينَ نَذِيرًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጽንፈኝነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን ከሓዲዎች በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

ክርስቲያን ሆነው ክርስትና የሚያጠኑ ወይም ሙስሊም ሆነው እስልምናን የሚያጠኑ ምሁራን "ጽንፈኛ ምሁራን"conservative scholar" ሲባሉ በተቃራኒው ክርስትያን ሳይሆኑ ክርስትና የሚያጠኑ ወይም ሙስሊም ሳይሆኑ እስልምናን የሚያጠኑ ምሁራን "ለዘብተኛ ምሁራን"liberal scholar" ይባላሉ። ነገር ግን እዚህ መጣጥፍ ላይ "ጽንፈኛ" የምንለው "ወሰን አላፊ" "ድንበር አላፊ" ጠርዘኛ"Extremist" በሚለው ዐውድና ምህዋር ነው፤ በቁርኣን እነዚህ ሰዎች "ሙዕተዲን" مُعْتَدِين ይባላሉ፤ "ጽንፈኝነት" ወይም "ጠርዘኝነት"Extremism" ደግሞ "ዑድዋን" عُدْوَٰن ይባላል፦
2፥190 *እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን ከሓዲዎች በአላህ መንገድ ተጋደሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና*፡፡ وَقَاتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ الَّذِينَ يُقَاتِلُونَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ

"ወሰን አትለፉ" የሚለውን ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ምክንያቱም አላህ ወሰን አላፊዎን አይወድምና፤ ጅሃድ ስሜትን፣ ዝንባሌን፣ ዘረኝነትን፣ ጎጠኝነትን፣ ጠርዘኝነትን ታሳቢ ያደረገ ሳይሆን “ፊ ሰብሊልላህ” فِي سَبِيلِ ٱللَّه ማለትም “በአላህ መንገድ” ብቻ ነው፤ በአላህ መንገድ ለአላህ ተብሎ ወይም አላህ ባስቀመጠልን መስፈርት ብቻ ማለት ነው፤ የሰውን ሕይወት ይቅርርና ገንዘቡን መብላት እንኳን በቁርኣን ወሰን ማለፍ ነው፦
4፥30 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ፡፡ ግን ከእናንተ በመዋደድ የኾነችውን ንግድ ብሉ፡፡ እራሳችሁንም አትግደሉ*፡፡ አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَأْكُلُوٓا۟ أَمْوَٰلَكُم بَيْنَكُم بِٱلْبَٰطِلِ إِلَّآ أَن تَكُونَ تِجَٰرَةً عَن تَرَاضٍۢ مِّنكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًۭا
4፥30 *ወሰን በማለፍ እና በመበደልም ይህንን የሠራ ሰው እሳትን እናገባዋለን*፡፡ ይኸም በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَانًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا
እራሳችሁን አትግደሉ" የሚለው ይሰመርበት፤ ሀቅ በሦስት ይከፈላል፤ አንደኛው የአላህ ሃቅ ሲሆን በአላህ አምልኮ ላይ ሌላ ማንነትና ምንነት ማሻረክ ትልቁ ዙልም ነው፤ ሁለተኛው የራስ ሃቅ ነው፤ እራስን መበደል ነው፥ ለምሳሌ እራስን መግደል፣ እራስን የሚጎዱ አልኮል መጠጣት፣ የአሳማ ስጋ መብላት ወዘተ፤ ሦስተኛው የሰው ሃቅ ነው፤ የሰውን ገንዘብ፣ ንብረት፣ መብት መንካት፤ ሰው ላይ በመሳደብ፣ በማንቋሸሽ፣ በማማት መድረስ ዙልም ነው፦
5፥87 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ለናንተ የፈቀደላችሁን ጣፋጮች እርም አታድርጉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፡፡ አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُحَرِّمُوا طَيِّبَاتِ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكُمْ وَلَا تَعْتَدُوا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُعْتَدِينَ
11፥112 *እንደ ታዘዝከውም ቀጥ በል፡፡ ከአንተ ጋር ያመኑትም ቀጥ ይበሉ፡፡ ወሰንንም አትለፉ፤ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና*፡፡ فَاسْتَقِمْ كَمَا أُمِرْتَ وَمَن تَابَ مَعَكَ وَلَا تَطْغَوْا ۚ إِنَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

በቁርኣን "ነፍስን አትግደሉ" የሚል ሃይለ ቃል ብዙ ቦታ አለ፦
4፥33 *ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ፡፡ የተበደለም ኾኖ የተገደለ ሰው ለዘመዱ በገዳዩ ላይ በእርግጥ ስልጣንን አድርገናል፡፡ በመግደልም ወሰንን አይለፍ*፤ እርሱ የተረዳ ነውና፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ ۗ وَمَن قُتِلَ مَظْلُومًا فَقَدْ جَعَلْنَا لِوَلِيِّهِ سُلْطَانًا فَلَا يُسْرِف فِّي الْقَتْلِ ۖ إِنَّهُ كَانَ مَنصُورًا

"በሕግ ቢሆን እንጂ" የሚለው ይሰመርበት፤ የተገደለበት ሰው "በመግደልም ወሰንን አይለፍ" የሚለው ይሰመርበት፤ ታዲያ ሁለት ሰዎች ወይም ሁለት ቡድኖች ቢጋደሉ ውሳኔው ምንድን ነው? የመጀመሪያው እርምጃ በመካከላቸው ማስታረቅ ነው፤ ነገር ግን ከሁለቱ አንደኛይቱም በሌላይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ ትዕዛዝ እስከምትመለስ ድረስ መጋደል ነው፤ በነገር ሁሉ ዘርን፣ ሃይማኖትን፣ ፓለቲካን ዝንባሌ ሳናደርግ ፍትኸኛ መሆን ነው፤ አላህ ፍትኸኞችን ይወዳል፦
49፥9 *ከምዕምናንም የኾኑ ሁለት ጭፍሮች ቢጋደሉ በመካከላቸው አስታርቁ፡፡ ከሁለቱ አንደኛይቱም በሌላይቱ ላይ ወሰን ብታልፍ ያችን ወሰን የምታልፈውን ወደ አላህ ትዕዛዝ እስከምትመለስ ድረስ ተጋደሉ፡፡ ብትመለስም በመካከላቸው በትክክል አስታርቁ፡፡ በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና*፡፡ وَإِن طَائِفَتَانِ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ اقْتَتَلُوا فَأَصْلِحُوا بَيْنَهُمَا ۖ فَإِن بَغَتْ إِحْدَاهُمَا عَلَى الْأُخْرَىٰ فَقَاتِلُوا الَّتِي تَبْغِي حَتَّىٰ تَفِيءَ إِلَىٰ أَمْرِ اللَّهِ ۚ فَإِن فَاءَتْ فَأَصْلِحُوا بَيْنَهُمَا بِالْعَدْلِ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ዝንባሉን ሳንከተል፣ ደሃ ሃብታም ሳንል እራስ፣ ወላጅ እና ቅርብ ዘመድን ሳንወግን ለአላህ ስልን በትክክል መስካሪዎች መሆን አለብን፤ ከንቱ እና ጭፍን ፍቅር አሊያም ከንቱ እና ጭፍን ጥላቻ ለአላህ ቀጥተኞች ወይም በትክክል መስካሪዎች እንዳንሆን ያደርገናል፦
4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا
5፥8 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

በምድር ላይ የሰው ንብረት፣ ሕይወት፣ መብት የሚያጠፉ አጥፊዎችን እና አባካኞችን አላህ አይወዳቸውም፦
27፥77 *አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ ለሰዎች መልካምን አድርግ፡፡ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና*፡፡ وَابْتَغِ فِيمَا آتَاكَ اللَّهُ الدَّارَ الْآخِرَةَ ۖ وَلَا تَنسَ نَصِيبَكَ مِنَ الدُّنْيَا ۖ وَأَحْسِن كَمَا أَحْسَنَ اللَّهُ إِلَيْكَ ۖ وَلَا تَبْغِ الْفَسَادَ فِي الْأَرْضِ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ
6፥141 *አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና*፡፡ وَلَا تُسْرِفُوا ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُسْرِفِينَ

በምድር ላይ የሰው ንብረት፣ ሕይወት፣ መብት የሚያጠፉ አጥፊዎችን እና አባካኞችን ወሰን አላፊዎች ናቸው፤ የሰውን ሰላም የሚነሱ፣ ሕይወቱን፣ ንብረቱን፣ መብቱን እና ነጻነቱን የሚያውኩ እንደነዚህ አይነት ወሰን አላፊዎች የሚያወጡትን ትእዛዝ አትከተል፦
26፥151 *የወሰን አላፊዎችንም ትዕዛዝ አትከተሉ*፡፡ وَلَا تُطِيعُوا أَمْرَ الْمُسْرِفِينَ

አላህ ድንበር ከሚያልፉ ጠርዘኞች ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም አላውቅም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ፡፡ *አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና*፡፡ فَٱسْتَمْسِكْ بِٱلَّذِىٓ أُوحِىَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ

መግቢያ
መቼም ሚሽነሪዎች ቆዳዬ ጠበበኝ ብለው የሚያላዝኑት ነገር ቢገርምም የአገራችን ሰዎች ደግሞ እነርሱን በቁርአን ላይ የሚያነሷቸውን ሂሶች እንደ ገደል ማሚቱ ሲያስተጋቡ ማየት ያስደምማል፤ ሚሽነሪዎ እራሳቸው መጽሐፍት ላይ ያሉትን አበሳና አሳር እንደማይወጡት ስለሚያውቁት በጊዜ ቁርአን ላይ መደበቁን መርጠዋል፤ የእኛ ጥያቄ ግን ተከድኖ ይብሰል ከተባለ ይኸው ጊዜ አስቆጠረ፤ እኛም ጠቃሚውን ነገር ከማይጠቅም ነገር ጋር ሳይሆን ጠቃሚውን ነገር ከሚጐዳ ነገር ጋር እያነጻጸርነው እንገኛለን፤ መቼም ስላቅና ፈሊጥ በአሉታዊ ሳይሆን በአውንታዊ ተመልክተን እዳው ገብስ ስለሆነ ሰው እንዲማርበት መልስ እንሰጣለን፤ ወደ ጉዳዩ ስንገባ ነብያችን”ﷺ” ወሕይ ከመጣላቸው በኃላ በቀጥተኛው መንገድ ላይ እንደሆኑ አምላካችን አላህ ተናግሯል፦
43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ፡፡ *አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና*፡፡ فَٱسْتَمْسِكْ بِٱلَّذِىٓ أُوحِىَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ

አላህ ነብያችን”ﷺ” በቀጥተኛ መንገድ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ጀነት ገብተውም በጀነት ያለው ፀጋ እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸዋል፦
108፥1 *እኛ በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን ሰጠንህ*፡፡ إِنَّآ أَعْطَيْنَٰكَ ٱلْكَوْثَرَ

“በጎ ነገር” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ከውሰር” كَوْثَر ሲሆን በጀነት ውስጥ ያለ ከወተት የነጻና ከማር የጣፈጠ ወንዝ ነው፤ ይህ ከውሰር ለነብያችን”ﷺ” የተሰጠ ዋስትና ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3684
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “እኛ ከውሰርን ሰጠንህ” ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ በጀነት ወንዝ ነው፤ በጀነት ወንዝ ድንኳኖቹ ከድንጋይ የተሠሩ አየው፤ ጂብሪል ሆይ! ምንድን ነው? አልኩት፤ እርሱም ከውሰር ነው፤ አላህ ለአንተ የሰጠህ” አለኝ። عَنْ أَنَسٍ ‏:‏ ‏(‏ إناَّ، أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ ‏)‏ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ هُوَ نَهْرٌ فِي الْجَنَّةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ رَأَيْتُ نَهْرًا فِي الْجَنَّةِ حَافَتَاهُ قِبَابُ اللُّؤْلُؤِ قُلْتُ مَا هَذَا يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَذَا الْكَوْثَرُ الَّذِي قَدْ أَعْطَاكَهُ اللَّهُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ

ነብያችን”ﷺ” ጀነት አይደለም መግባት በተጨማሪ የጀነት ጀረጃቸውንም አላህ እንደነገረን ከላይ ያለው አንቀጽ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል በቂ ነው፤ ታዲያ ይህ ዋስትና እያለ አላህ ነብያችንን”ﷺ” “በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም አላውቅም” በል ሲላቸው እውን ሚሽነሪዎች እንደሚሉት ወደ ፊት የት እንደምንገባ አናውቅም በል ማለታቸውን ያሳያልን? ይህንን የተንሸዋረረና የተወላገደ መረዳት ጥንልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንየው፦
46:9 *ከመልክተኞች ብጤ የሌለኝ አይደለሁም፤ በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም አላውቅም፤ ወደ እኔ የሚወረደውን እጅግ ሌላን አልከተልም፤ እኔም ግልጽ አስጠንቃቂ እንጅ ሌላ አይደለሁም* በላቸው። قُلْ مَا كُنتُ بِدْعًۭا مِّنَ ٱلرُّسُلِ وَمَآ أَدْرِى مَا يُفْعَلُ بِى وَلَا بِكُمْ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ وَمَآ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌۭ مُّبِينٌۭ

ነጥብ አንድ
“ብጤ የሌለኝ አይደለሁም”
ከነቢያችን”ﷺ” በፊት የመጡት በእርግጥ ምግብን የሚበሉ፣ በገበያዎችም የሚሄዱ ሰዎች ነበሩ፣ በተመሳሳይም ነቢያችን”ﷺ” ሰው ናቸው፣ በደረጃ እንጂ በሃልዎት ከሰው የተለዩ አልነበሩም፣ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆኑ መልክተኛ ነበሩ፦
36:3 አንተ በእርግጥ *ከመልክተኞቹ ነህ*። إِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
2:252 አንተም *በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ*፡፡ وَإِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
3:144 ሙሐመድም *ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም*፤ وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌۭ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ

ነጥብ ሁለት
“አላውቅም”
ነቢያችን”ﷺ” በራሳቸውና በሰዎች ምን እንደሚከናወን የወደፊቱን አያውቁም፣ ያ ማለት ሰዎች የሚያስጠነቅቁበት ቅርብ ይሁን እሩቅ አያውቁም፣ ከሚወርድላቸው ግህደተ-መለኮት ውጪ ምንም አያውቁም፦
6:50 «ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ *ሩቅንም አላውቅም*፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ *ወደእኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም*» በላቸው፡፡ قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ
7:188 አላህ የሻውን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም፣ ጉዳትንም፣ ማምጣት አልችልም፣ *ሩቅንም የማውቅ በነበርኩ ኖሮ* ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፤ እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስጠንቃቂና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም” በላቸው። قُل لَّآ أَمْلِكُ لِنَفْسِى نَفْعًۭا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ لَٱسْتَكْثَرْتُ مِنَ ٱلْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِىَ ٱلسُّوٓءُ ۚ إِنْ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌۭ وَبَشِيرٌۭ لِّقَوْمٍۢ يُؤْمِنُونَ
21:109 እምቢም ቢሉ በማወቅ በእኩልነት ላይ ሆነን የታዘዝኩትን አስታወቅኋችሁ፤ *የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ፣ ወይም ሩቅ፣ መሆኑን አላውቅም*፤ በላቸው። فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُلْ ءَاذَنتُكُمْ عَلَىٰ سَوَآءٍۢ ۖ وَإِنْ أَدْرِىٓ أَقَرِيبٌ أَم بَعِيدٌۭ مَّا تُوعَدُونَ
21:111 እርሱም *ቅጣትን ማቆየት ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጣቀሚያ እንደኾነም “አላውቅም”*፤ በላቸው። وَإِنْ أَدْرِى لَعَلَّهُۥ فِتْنَةٌۭ لَّكُمْ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٍۢ
ነጥብ ሶስት
“ሚወረደው”
ወደ ነቢያችን”ﷺ” የሚወርደው ለቀደሙት መልክተኞች የሚወርደው የነበረው የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፣ ከነቢያችን በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው ይህ የተውሒድ ተስተምህሮት ነው ነቢያችን”ﷺ” የሚከተሉት፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ
18፥110 እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው”*፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”*፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا
21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ *ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ፣ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም*። وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
41:43 ከአንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች *የተባለው ቢጤ* እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፤ مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدْ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبْلِكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍۢ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٍۢ

ነጥብ አራት
“አስጠንቃቂ”
አላህ የነቢያችን”ﷺ” ቢጤዎች መልክተኞችን አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርጎ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት ልኳል፦
18:56 መልክተኞችንም *አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች* ሆነው እንጂ አንልክም፤ وَمَا نُرْسِلُ ٱلْمُرْسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِين
4:165 ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር *አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች* የሆኑን መልክተኞች ላክን፤ رُّسُلًۭا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى ٱللَّهِ حُجَّةٌۢ بَعْدَ ٱلرُّسُلِ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًۭا
2:213 አላህም ነቢያትን *አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች* አድርጎ ላከ፡፡ وَٰحِدَةًۭ فَبَعَثَ ٱللَّهُ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ

በተመሳሳይ መልኩ በጀነት አብሳሪ በጀሃነም አስጠንቃቂ ይሆኑ ዘንድ ነብያችንን”ﷺ” አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርጎ ልኳል፦
2:119 እኛ *አብሳሪና አስጠንቃቂ* ኾነህ በእውነት ላክንህ፡፡ ከእሳትም ጓዶች አትጠየቅም፡፡ إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ بَشِيرًۭا وَنَذِيرًۭا ۖ وَلَا تُسْـَٔلُ عَنْ أَصْحَٰبِ ٱلْجَحِيمِ
34:28 አንተንም ለሰዎች ሁሉ በሙሉ *አብሳሪና አስጠንቃቂ* አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፤ وَمَآ أَرْسَلْنَٰكَ إِلَّا كَآفَّةًۭ لِّلنَّاسِ بَشِيرًۭا وَنَذِيرًۭا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
33:45 አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ *አብሳሪና አስጠንቃቂ* አድርገን ላክንህ። يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ شَٰهِدًۭا وَمُبَشِّرًۭا وَنَذِيرًۭا

አላህም፦ ”አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ አንድ ከኾነው አላህ በቀር ምንም አምላክ የለም፤ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ ነኝ” በል በማለት አስጠንቃቂ መሆናቸውን አውርዷል፦
11:2 እንዲህ በላቸው ፦ አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ *እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ ነኝ*። أَلَّا تَعْبُدُوٓا۟ إِلَّا ٱللَّهَ ۚ إِنَّنِى لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌۭ وَبَشِيرٌۭ
22:49 ፦ እላንተ ስዎች ሆይ እኔ ለእናንተ *ግልጽ አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ*፣ በላቸው። قُلْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَآ أَنَا۠ لَكُمْ نَذِيرٌۭ مُّبِينٌۭ

ስለዚህ ከላይ ያለውን አንቀጽ የወረደበትም አውድ ስንመለከተው ነብያችን”ﷺ” ጀነት ስለ አለመግባታቸው ምንም የሚያወራው ነገር የለም፣ አውዱ ለማስተላለፍ የፈለገውን በግድ ጠምዝዞ ይህን ለማለት ነው የፈለገው ብሎ ማጣመም ከሥነ-አፈታት ጥናት “hermeneutics” ጋር መላተም እና የደፈረሰ የተሳከረ መረዳት ነው፣ ይህ ሙግት የአውድ ሙግት”contextual approach” ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ቤት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥33 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡

መግቢያ
መቼም ሚሽነሪዎች የኢስላም ብርሃን በምን እናጠልሸው ብለው ከተነሱ ጊዜያት አለፉ፤ የኢስላምን መሰረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ ያልተረዱ ስለሆኑ መደበኛ በሆነ መርሃ-ግብርና መዋቅር ከመማር ይልቅ ጎግል ላይ በሰፈረው የተለቃቀመ ጥራዝ-ነጠቅ መረጃ ድምዳሜ ላይ ሲደርሱ ማየት እጅጉን ያማል፣ አንዱ ሚሽነሪ፦ ነብያችንን”ﷺ” የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ ሲለብሱ እና ከእርሷ ጋር ተራክቦ ሲያደርጉ ብቻ ነው ወህይ የሚወርድላቸው ብሎ በትክክል እንኳን ማንበብ የማይችለውን ጩቤ ጥቅስ ጠቅሶ የጨባራ ለቅሶ እና ተስካር የሆነው ውሃ የማይቋጥ ሙግት ሲሟገተኝ ነበር፤ ይህ ስሁት የሆነ ሙግት ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በእጥቡ ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው ከመነሻው አከርካሪውን መመታት አለበት፤ እስቲ ሐዲሱን እንመልከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 51 , ሐዲስ 16:
ሂሻም ኢብኑ ኡርዋህ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደተረከው….*የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ለኡሙ ሰላማ”ረ.ዓ.” በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም “ከአይሻ ልብስ በስተቀር አሏት”*፤ فَقَالَ لَهَا ‏”‏ لاَ تُؤْذِينِي فِي عَائِشَةَ، فَإِنَّ الْوَحْىَ لَمْ يَأْتِنِي، وَأَنَا فِي ثَوْبِ امْرَأَةٍ إِلاَّ عَائِشَةَ ‏”‌‏ ።

ምን ያህል ቅጥፈት እንዳለ ተመልከቱ፤ እዚህ ሐዲስ ላይ የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ ለበሱ የሚል የት አለ? ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ጋር ተራክቦ ሳደርግ የሚል የት አለ? ወህይ የሚመጣልኝ ከአይሻ ልብስ ውስጥ ብቻ ነው የሚል የት አለ? ይህ ሁሉ ገለባ ሂስ ነው፤ ነብያችን ወህይ የሚመጣላቸው በተለያየ ሁኔታ ቢሆንም ከሌሎች ባለቤቶታቸው ይልቅ የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ቤት እያሉ ብቻ ነው ወህይ የሚመጣላቸው ማለት “ይልቅ” የሚለው ማነፃፀሪያ ከሴቶቹ ጋር እንጂ አጠቃላይ አይደለም፤ “ሠውብ” ثَوْب የሚለው ቃል በብዙ ይመጣል፦
“ሂጃብ” حِجَاب “መጋረጃ”፣
“ፊራሽ” فِرَٰش ምንጣፍ”፣
“ሊሃፍ” لِحَاف “ፍራሽ”
“በይት” بَيْت “ቤት”
“ሊባሥ” لِبَاس “ልብስ” በሚል ይመጣል፤ ይህንን በተለያዩ ነጥቦች ማየት ይቻላል፦

ነጥብ አንድ
“ሊሃፍ”
“ሊሃፍ” لِحَاف የሚለው ቃል “ፍራሽ” ማለት ሲሆን “ከአይሻ ልብስ በስተቀር” የሚለው “ከአይሻ ፍራሽ በስተቀር” በሚለው መጥቷል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 62 , ሐዲስ 122:
*ኡሙ ሰላማ ሆይ በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ፍራሽ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም “ከአይሻ ፍራሽ በስተቀር”* ‏ يَا أُمَّ سَلَمَةَ لاَ تُؤْذِينِي فِي عَائِشَةَ، فَإِنَّهُ وَاللَّهِ مَا نَزَلَ عَلَىَّ الْوَحْىُ وَأَنَا فِي لِحَافِ امْرَأَةٍ مِنْكُنَّ غَيْرِهَا ‏”‌‏.‏ ፤
ነጥብ ሁለት
“በይት”
“በይት” بَيْت ማለት “ቤት” ሲሆን “ከአይሻ ልብስ በስተቀር” የሚለው “ከአይሻ ቤት” በሚለው መጥቷል፤ ቤት የሚከፋፈለው በመጋረኛ ስለሆነ “ሠውብ” የሚለው በሌላ ሪዋያ ላይ “በይት” بَيْت “ቤት” በሚል መጥቷል፦
ኢማሙ አህመድ መጽሐፍ 6 ሐዲስ 293
የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *ኡሙ ሰላማ ሆይ በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ቤት ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከአይሻ ቤት በስተቀር*፤ رسول الله صلى الله عليه و سلم ثم قال يا أم سلمة لا تؤذيني في عائشة فإنه والله ما نزل على الوحي وأنا في بيت امرأة من نسائي غير عائشة ።

ነጥብ ሶስት
“ሊባሥ”
“ሊባሥ” لِبَاس ማለት ትርጉሙ “ልብስ” ማለት ሲሆን “ሠውብ” ማለት “ሊባሥ” ነው ብንል እንኳን “ልብስ” የሚለው ቃል ሁልጊዜ ሱሪን፣ ቀሚስን፣ ጃኬትን ብቻ ሳይሆን የሚያመለክተው መጠለያን፣ መከለያ፣ መሸሸጊያ ለማመልከት ይመጣል፤ አምላካችም አላህ ለምሳሌ ሴት የወንድ ልብስ ናት ወንድ የሴት ልብስ ነው ይለናል፦
2፥187 በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለእናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ *እነርሱ ለእናንተ “ልብሶች” ናቸው፤ እናንተም ለእነርሱ “ልብሶች” ናችሁ*። أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ ٱلصِّيَامِ ٱلرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَآئِكُمْ ۚ هُنَّ لِبَاسٌۭ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌۭ لَّهُن

መቼም ልብስ የሚለውን አንዱ የአንዱ መሸሸጊያ ማለት እንጂ አንዱ የአንዱ ጃኬት ወይም ቀሚስ አሊያም ሱሪ ማለት ነው የሚል ቂል የለም፤ አላህ ሌሊትን ልብስ አደረገ፤ ያ ማለት “መጠለያ” ማለት ነው፦
25:47 እርሱም ያ ለእናንተ *”ሌሊትን” ልብስ፣ እንቅልፍንም ማረፊያ ያደረገ፤ ቀንንም መበተኛ ያደረገላችሁ ነው*። وَهُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا وَٱلنَّوْمَ سُبَاتًۭا وَجَعَلَ ٱلنَّهَارَ نُشُورًۭا
78:10 *ሌሊቱንም ልብስ አደረግን*። وَجَعَلْنَا ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا

ይህንን ካየን ነብያችን”ﷺ”፦ “ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ በስተቀር” ሲሉ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ፍራሽ ወይም ቤት ማለታቸው እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው እንጂ ቃላትን ማንሸዋረር እና ማውረግረግ አይቻልም። እንዴት የአንድ ሴት ልብስ ውስጥ አንድ ወንድ ቃል በቃል ሊገባስ ይችላል? ይህ ሆን ተብሎ ድርቅና አላህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትወዛገቡበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፦
18፥68-69 *ቢከራከሩህም «አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ አላህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትወዛገቡበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡*

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ነብዩ የሕያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥7 «ዘከሪያ ሆይ! እኛ በወንድ ልጅ *ስሙ የሕያ በኾነ ከዚህ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት እናበስርሃለን*» አለው፡፡ يَا زَكَرِيَّا إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَامٍ اسْمُهُ يَحْيَىٰ لَمْ نَجْعَل لَّهُ مِن قَبْلُ سَمِيًّا

ነጥብ አንድ
"ሞክሼ"
"ሞክሼ" የሚለው ቃል "ሠሚይ" سَمِيّ ሲሆን በቁርኣን ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል፤ የአላህን ባህርይ ለማመልከት መጥቷል፦
19፥65 እርሱ የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው፡፡ እርሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ *ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?* رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا فَاعْبُدْهُ وَاصْطَبِرْ لِعِبَادَتِهِ ۚ هَلْ تَعْلَمُ لَهُ سَمِيًّا

የአላህ ባህርያት ሞክሼ የለውም፤ የአላህ ስሞች ባህርያቱ የተሰየሙበት ናቸው፤ አላህ ከፍጡራን ጋር በባህርይ የማይመሳሰሉ በቁርኣን የተገለጹ 99 መልካም ስሞች አሉት፦
7፥180 *ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፡፡ ስትጸልዩ በእርሷም ጥሩት*፡፡ وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا
17፥110 «አላህን ጥሩ ወይም አልረሕማንን ጥሩ፤ ከሁለቱ ማንኛውንም ብትጠሩ መልካም ነው፡፡ *ለእርሱ መልካም ስሞች አሉትና*» በላቸው፡፡ قُلِ ادْعُوا اللَّهَ أَوِ ادْعُوا الرَّحْمَـٰنَ ۖ أَيًّا مَّا تَدْعُوا فَلَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
20፥8 *አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ *ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አሉት*፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
59፥24 እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ *ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى

ለምሳሌ ከአላህ ስሞች መካከል አሥ-ሠሚዕ" السَّمِيعُ እና "አል-በሲር" الْبَصِيرُ ነው፤ ሰውም ሰሚ እና ተመልካች ነው፤ ነገር ግን ሰው ሰው ሰሚና ተመልካች የተባለው አላህ ሰሚ እና ተመልካች በተባለበት ስሌትና ቀመር አይደለም፦
76፥2 እኛ ሰውን በሕግ ግዳጅ የምንሞከረው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ *ሰሚ ተመልካችም* አደረግነው፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም "ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው*፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

"የሚመስለው ምንም ነገር የለም" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ የአላህ መስማት እና ማየት ጊዜና ቦታ ሳይወስነው በጨለማ እና በሹክሹክታ ያሉትን ያያል ይሰማል፤ የፍጡራን መስማት እና ማየት ግን በጊዜና በቦታ ተወስኖ በጨለማ እና በሹክሹክታ ያሉትን አያይም አይሰማም። ስለዚህ የአላህ ስም የወከለውን ባህርይ ሞክሼ የለውም። በተመሳሳይም የየሕያ ስም ሞክሼ የለውም ሲባል ለየት ያለ የስም ትርጉም አለው፤ በተጨማሪም "የሕያ" በሚል ስም የተጠራ ሰው ከእርሱ በፊት የለም ማለት ነው፦
19፥7 «ዘከሪያ ሆይ! እኛ በወንድ ልጅ *ስሙ የሕያ በኾነ ከዚህ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት እናበስርሃለን*» አለው፡፡ يَا زَكَرِيَّا إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَامٍ اسْمُهُ يَحْيَىٰ لَمْ نَجْعَل لَّهُ مِن قَبْلُ سَمِيًّا

ነጥብ ሁለት
"የሕያ"
"የሕያ" يَحْيَىٰ ማለት "ሕያው" ማለት ነው፦
20፥74 እነሆ ከሓዲ ኾኖ ወደ ጌታው የሚመጣ ሰው ለእርሱ ገሀነም አለችው፡፡ *በውስጧም አይሞትም "ሕያውም" አይኾን*፡፡ إِنَّهُۥ مَن يَأْتِ رَبَّهُۥ مُجْرِمًۭا فَإِنَّ لَهُۥ جَهَنَّمَ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ
87፥13 *ከዚያም በእርሷ ውስጥ አይሞትም "ሕያውም" አይኾንም*፡፡ ثُمَّ لَا يَمُوتُ فِيهَا وَلَا يَحْيَىٰ

"ሕያው" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል "የሕያ" يَحْيَىٰ ነው፤ አምላካችን አላህ ስለ የሕያ ለነብያችን"ﷺ" በሚናገርበት አንቀጽ ላይ፦
19፥15 *በተወለደበት ቀን፣ በሚሞትበትም ቀን እና ሕያው ሆኖ በሚነሳበትም ቀን ሰላም በእሱ ላይ ይሁን*፡፡ وَسَلَامٌ عَلَيْهِ يَوْمَ وُلِدَ وَيَوْمَ يَمُوتُ وَيَوْمَ يُبْعَثُ حَيًّا

"ዉሊደ" وُلِدَ ማለት "ተወለደ" ማለት ሲሆን አላፊ ጊዜ ነው፤ "የሙቱ" يَمُوتُ ማለት ግን "የሚሞት" ማለት ሲሆን የወደፊት ጊዜ ነው፤ ይህንን አንቀጽ እና የስሙን ትርጉም የሕያ አልሞተም፤ ወደፊት ይሞትና በትንሳኤ ቀን ይቀሰቀሳል የሚል እሳቤ ይይዛል፤ ይህ አንደኛው እይታ ነው። ሁለተኛው እይታ የሕያ በአላህ መንገድ የተገደለ ሸሂድ ነው፤ ሸሂድ ደግሞ ሕያው ነው፤ ስለዚህ የሕያ ሕያው የተባለበት ይህንን ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ ይህ ሌላው እይታ ነው፦
2፥154 *በአላህ መንገድ የሚገደሉትን ሰዎችም «ሙታን ናቸው» አትበሉ፡፡ በእውነቱ "ሕያዋን ናቸው"፤ ግን አታውቁም*፡፡ وَلَا تَقُولُوا لِمَن يُقْتَلُ فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَمْوَاتٌ ۚ بَلْ أَحْيَاءٌ وَلَـٰكِن لَّا تَشْعُرُونَ
ነጥብ ሦስት
"ስሙ"
"የሕያ" يَحْيَىٰ በሚል ስም የተጠራ ከእርሱ በፊት አንድም የለም፦
19፥7 «ዘከሪያ ሆይ! እኛ በወንድ ልጅ *ስሙ የሕያ በኾነ ከዚህ በፊት ሞክሼን ባላደረግንለት እናበስርሃለን*» አለው፡፡ يَا زَكَرِيَّا إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَامٍ اسْمُهُ يَحْيَىٰ لَمْ نَجْعَل لَّهُ مِن قَبْلُ سَمِيًّا

ሚሽነሪዎች "የሕያ" የሚለው ስም ከእርሱ በፊት ነበረ በማለት የአላህን ንግግር ለማስዋሸት ሲዳክሩ ይታያል፤ ግን እውን "የሕያ" የሚል ስም ነበረን? እስቲ እንይ! "ዮሐና" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዩሓናን" يُوحانان ሲሆን 27 ጊዜ በብሉይ ኪዳን ተጠቀሷል፤ ይህ ስም ለየሃቃጣን ልጅ ዮሐናን እና ለቃሬያም ልጅ ዮሐናን አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ዕዝራ 8፥12 ከዓዝጋድ ልጆች *የሃቃጣን ልጅ ዮሐናን*፥ ከእርሱም ጋር መቶ አሥር ወንዶች። وَمِن بَنِي عَزْجَدَ يُوحَنانُ بْنُ هِقّاطانَ وَمَعَهُ مِئَةٌ وَعَشْرَةُ رِجالٍ. 
ኤርምያስ 40፥8 *የቃሬያም ልጅ ዮሐናን* እና ዮናታን፥ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፥ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ ከሰዎቻቸው ጋር ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ። وَأتَى الرِّجالُ التّالِيَةُ أسماؤُهُمْ إلَى جَدَلْيا فِي المِصفاةِ: إسْماعِيلُ بْنُ نَثَنْيا وَيُوحانانُ وَيُوناثانُ ابنا قارِيحَ، وَسَرايا بْنُ تَنحُومَثَ، وَأبناءُ عُوفايَ النَّطُوفاتِيِّ، وَيَزَنْيا بْنُ المَعكِيِّ. أتَى هَؤُلاءِ مَعَ رِجالِهِمْ إلَى جَدَلْيا فِي المِصفاةِ.

"ዮሐና" እና "ዮሐንስ" ሁለት የተለያዩ ስሞች ናቸው፤ "ዮሐንስ" በዓረቢኛው "ዩሐና" يُوحَنّا እንጂ "ዩሓናን" يُوحانان አይደለም፤ "ዩሐና" ሐ ፈትሃ "ሐ" እና ኑን ሸዳ አሊፍ ስኩን "ንና" ሲሆን "ዩሐናን" ግን ሐ ፈትሃ አሊፍ ስኩን "ሓ"፣ ኑን አሊፍ ስኩን "ና" እና በኑን ስኩን "ን" ተብሎ የሚሰክን ነው፦
ሉቃስ 1፥13 መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ *ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ*። فَقالَ لَهُ المَلاكُ: «لا تَخَفْ يا زَكَرِيّا. لَقَدْ سَمِعَ اللهُ صَلاتَكَ. وَسَتَلِدُ لَكَ زَوجَتُكَ ألِيصاباتُ ابناً، فَسَمِّهِ يُوحَنّا

በዐረቢኛው ባይብል እንኳን ብንሄድ ሁለት የተለያዩ ቃላት ናቸው። እኛ የፈለግነው "የሕያ" በሚል ስም የተጠራ ሰው ካለ መረጃ ይቅረብልን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአሕዛብ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

50፥38 *ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም*፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

"አሕዛብ" أَحْزَاب የሚለው ቃል "ሒዝብ" حِزْب "ማለትም "ሕዝብ" ለሚለው ቃል ብዜት ሲሆን "ሕዝቦች" ማለት ነው፦
33፥22 *አማኞቹም "አሕዛብን" ባዩ ጊዜ «ይህ አላህና መልክተኛው የቀጠሩን ነው፡፡ አላህና መልክተኛውም እውነትን ተናገሩ» አሉ*፡፡ وَلَمَّا رَأَى الْمُؤْمِنُونَ الْأَحْزَابَ قَالُوا هَـٰذَا مَا وَعَدَنَا اللَّهُ وَرَسُولُهُ وَصَدَقَ اللَّهُ وَرَسُولُهُ

ይህ ቃል በብሉይ ኪዳን ግሪክ ሰፕቱአጀንት እና በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ ላይ "ኤትኖስ" ἔθνος ሲሆን በዕብራይስጡ ደሃራይ እደ-ክታባት ላይ ደግሞ "ጎይ" גוי ተብሎ ተቀምጧል፤ ይህ ቃል እንደየ ዐውዱ ለተለያየ ትርጉም አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን "ህዝብ" "ብሔር" "አረማዊ" "ይሁዲ ያልሆነ" የሚል ፍቺ እንዳለው የግሪክና የዕብራይስጥ ሙዳየ-ቃላት ያትታሉ።
ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እዚህ አርስት ላይ "አሕዛብ" ብለን የምንመለከተው "አረማዊ"pagan" የሚለው እሳቤ ነው፦
1ኛ ዜና መዋዕል 16፥26 *የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው*፤

እውን የአሕዛብ አምላክ ሁሉ ጣዖታት ናቸውን? ምክንያቱም እግዚአብሔር የአሕዛብ አምላክ ነው ይላል፦
ሮሜ 3፥29 ወይስ *እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን?*
ራእይ 15፥3 ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ *የአሕዛብ ንጉሥ* ሆይ፥ መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው፤

አይ እግዚአብሔር የአሕዛብ አምላክ ነው ሲባል በመፍጠር ደረጃ ነው፤ የአሕዛብ አምላክ ሁሉ ጣዖታት ናቸው የተባለው ከማምለክ አንጻር ነው ከተባለ እንግዲያውስ አሕዛብ የሚያመልኳቸው አማልክት የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው፤ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ ናቸው፦
መዝሙር 115፥4 *የአሕዛብ ጣዖታቶች የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው*።
ኤርሚያስ 10፥11 እናንተም፦ *ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት* ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ ትሉአቸዋላችሁ።

"ጣዖት" ማለት እንኳን ሊፈጥር የማይሰማ፣ የማይናገር፣ የማያይ፣ የማያውቅ ግዑዝ ነው። እንግዲያውስ አሕዛብ የሚለው ስሙ እኛን ሙስሊሞችን አይመለከትም። ምክንያቱም የእኛ አምላክ አላህ ሁሉን የሚሰማ፣ በቃሉ የሚናገር፣ ሁሉን የሚያይ፣ ሁሉን የሚያውቅ ሕያው ነው፤ እርሱ ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ ነው፦
50፥38 *ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም*፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ

ከዛም አልፎ ከእርሱ ከፈጣሪ ሌላ ጣዖታውያን የሚገዟቸው ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ በል በማለት ጥያቄ ያቀርባል፦
35፥40 በላቸው *«እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን ተጋሪዎቻችሁን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ፤ ወይስ ለእነርሱ በሰማያት ውስጥ ሽርክና አላቸውን?»* ፡፡ قُلْ أَرَأَيْتُمْ شُرَكَاءَكُمُ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُوا مِنَ الْأَرْضِ أَمْ لَهُمْ شِرْكٌ فِي السَّمَاوَات
46፥4 በል፦ *«ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ፡፡ ወይም በሰማያት ለእነርሱ መጋራት አላቸውን?»* ፡፡ قُلْ أَرَأَيْتُم مَّا تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ أَرُونِي مَاذَا خَلَقُوا مِنَ الْأَرْضِ أَمْ لَهُمْ شِرْكٌ فِي السَّمَاوَات

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ፈውስ እና ታምራት በኡስታዞች የተዘጋጀ ደርስ፦
https://youtu.be/D08TaGGVOns
የማይመገብ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥14 *«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?»* በላቸው፡፡ قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَم

አምላካችን አላህ የሚመገቡ አካላትን በመፍጠር እርሱ የሁሉም መጋቢ ነው፤ ነገር ግን በተቃራኒው እርሱ ሲሳይን ሰጪ ስለሆነ የማይመገብ አምላክ ነው፦
6፥14 *«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?»* በላቸው፡፡ قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَم
51፥57 *ከእነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም*፡፡ مَا أُرِيدُ مِنْهُم مِّن رِّزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَن يُطْعِمُونِ

በባይብልም አንዱ አምላክ እንደማይመገብ ተገልጿል፦
መዝሙር 50፥12 *ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና። የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?*

ፈጣሪ፦ እበላለሁን? እጠጣለሁን? ሲል በምጸታዊ አነጋገር አልበላም አልጠጣም እያለ ነው፤ ከዚያ ይልቅ ሁሉን የሚመግብ ነው፦
መዝሙር 136፥25 *ለሥጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ*፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

አምላካችን አላህ መርየምን እና ልጇን ለዓለማት ታምር አድርጓል፤ ነገር ግን እርሱ መልእክተኛ እናቱ ደግሞ እውነተኛ ናቸው እንጂ ከዚያ ያለፈ ደረጃ የላቸውም፤ ሁለቱም እንደማንኛውን ፍጡር ምግብን የሚበሉ ነበሩ፤ መመለክ የሚገባው የሚመግብ የማይመገብ ከማንም ምንም ሲሳይ የማይፈልግ አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
5፥75 *የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ ሁለቱም ምግብን የሚበሉ ነበሩ*፤ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ ۖ كَانَا يَأْكُلَانِ الطَّعَامَ ۗ انظُرْ كَيْفَ نُبَيِّنُ لَهُمُ الْآيَاتِ ثُمَّ انظُرْ أَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ

ኢየሱስ ለሥድስቱ የተፈጥሮ ሕግጋት ይገዛል፤ እነዚህም ሕግጋት፦ መራብ፣ መጠማት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መጸዳዳት እና መሽናት ናቸው። ኢየሱስ እየበላ እና እየጠጣ መጣ፦
ማቴዎስ 11፥19 *የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ*፥
ሉቃስ 24፥42 እነርሱም *ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤ ተቀብሎም በፊታቸው በላ*።

ኢየሱስ ይራብ፣ ይጠማ፣ ይበላ እና ይጠጣ ከነበረ፤ ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ መጸዳዳት ግድ ይለዋል፦
ማቴዎስ 15፥17 *ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?*

ፈጣሪ ሰው ሆኖ ይራባል፣ ይጠማል፤ ይበላል፣ ይጠጣል፣ ይጸዳዳል፣ ይሸናል ማለት ለእርሱ የነውርና የጎደሎ ባህርይ ነው፤ የሰማያትና ምድር ጌታ፣ የዙፋኑ ጌታ፣ የማሸነፍ ጌታ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ፤ “ከሚሉት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የሲፉነ” يَصِفُونَ ማለት “ባህርይ ካደረጉለት”they attribute” ነገር ሁሉ የጠራ ነው፦
43፥82 *የሰማያትና ምድር ጌታ የዙፋኑ ጌታ ከሚሉት ነገር ሁሉ ጠራ*። سُبْحَانَ رَبِّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
21፥22 *የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ*። فَسُبْحَانَ اللَّهِ رَبِّ الْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
6:100 *ጥራት የተገባው ከሚሉት ነገር የላቀ ነው*። سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يَصِفُونَ
23:91 *አላህ ከሚመጥኑት ሁሉ ጠራ*። سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يَصِفُونَ
37፥180 *የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ*። سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ማህበራዊ ዘይቤ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

17፥53 ለባሮቼም በላቸው፦ ያችን እርሷ *“መልካም የሆነችውን ቃል ይናገሩ”፤ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና*፤ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና። وَقُل لِّعِبَادِى يَقُولُوا۟ ٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ كَانَ لِلْإِنسَٰنِ عَدُوًّۭا مُّبِينًۭا

ኢሥላም አጠቃላይ የሕይወት ዘይቤ ይዟል፤ ይህም ዘይቤ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዘይቤ ነው፤ በማህበራዊ ዘይቤ ውስጥ ከሰዎች ጋር በሚኖረን ጤናማ ግንኑኝነት እና መስተጋብር ሥነ-ምግባር እና ግብረገብ ወሳኝ ሚና ናቸው፤ “አኽላቅ” أخلاق ማለት ሥነ-ምግባር”ethics” ማለት ሲሆን “አደብ” أدب ማለት ደግሞ ግብረገብ”manners” ማለት ነው።
አምላካችን አላህ በወላጆች፣ በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ ለሰራተኞች መልካምን እንድንሰራ አዞናል፦
4፥36 *አላህንም አምልኩ፤ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆች፣ በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው መልካምን ሥሩ*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

ኩራት እና ጉራ የሥነ-ምግባ እና የግብረገብ እጦት ነው፤ ከላይ ያለው ግብረገብ ሙስሊም ካልሆኑም ጋር በሚኖረን መስተጋብር ያጠቃልላል፤ ሙስሊም ያልሆኑ ሰላማውያን ጋር መልካምን መዋዋልና በፍትሕ ማስተካከል አላህ አልከለከለንም። አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና፦
60፥8 *ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸውና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

አንድ ሙስሊም ከሰዎች ጋር በሚኖረው ማህበራዊ ዘይቤ ምን ምን የሥነ-ምግባር እና የግብረገብ እሴቶችን ከቁርኣን ነጥብ በነጥብ እናያለን፦

ነጥብ አንድ
“መልካም ጠባይ”
ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ መልካም ባህርይ ነው፤ መልካም ባህርይ በመጥፎ ባህርይ ላይ ተጽእኖ ማድረግ ይችላል፤ አውንታዊ ጠባይ ጠበኛን ሰው አዛኝ ዘመድ ያደርጋል፦
31፥34 *መልካሚቱ እና ክፉይቱም ጸባይ አይተካከሉም፡፡ በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ጸባይ መጥፎይቱን ገፍትር፡፡ ያን ጊዜ ያ በአንተ እና በእርሱ ጠብ ያለው ሰው መካከል እርሱ ልክ እንደ አዛኝ ዘመድ ይኾናል*፡፡ وَلَا تَسْتَوِي الْحَسَنَةُ وَلَا السَّيِّئَةُ ۚ ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ فَإِذَا الَّذِي بَيْنَكَ وَبَيْنَهُ عَدَاوَةٌ كَأَنَّهُ وَلِيٌّ حَمِيمٌ

ይህንን ገር ጠባይ ይዞ በመልካም ማዘዝ ነው፤ የአልረሕማንም ባሮች የተረጋጉ ናቸው፤ ውድቅን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ይርቃሉ፤ ባለጌዎች በክፉ ባነጋገሩዋቸው ጊዜ “ሰላም” የሚሉት ናቸው፦
7፥199 *ገርን ጠባይ ያዝ”፤ በመልካምም እዘዝ “መሃይማንን” ተዋቸው*። خُذِ ٱلْعَفْوَ وَأْمُرْ بِٱلْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ ٱلْجَٰهِلِينَ
25፥63 *የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት”፣ ባለጌዎች በክፉ ባነጋገሩዋቸው ጊዜ፣ “ሰላም” የሚሉት ናቸው*። وَعِبَادُ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى ٱلْأَرْضِ هَوْنًۭا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ ٱلْجَٰهِلُونَ قَالُوا۟ سَلَٰمًۭا
28፥55 *ውድቅንም ቃል በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ይርቃሉ*፡፡ «ለእኛ ሥራዎቻችን አሉን፡፡ ለናንተም ሥራዎቻችሁ አሏችሁ፡፡ *ሰላም በእናንተ ላይ ይኹን መሃይማንን አንፈልግም» ይላሉ*፡፡وَإِذَا سَمِعُوا۟ ٱللَّغْوَ أَعْرَضُوا۟ عَنْهُ وَقَالُوا۟ لَنَآ أَعْمَٰلُنَا وَلَكُمْ أَعْمَٰلُكُمْ سَلَٰمٌ عَلَيْكُمْ لَا نَبْتَغِى ٱلْجَٰهِلِينَ
ነጥብ ሁለት
“መልካም ቃል”
ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ መልካም ቃልን መናገር ነው፤ ሰይጣን መልካም ቃል በማይናገሩት በመካከላቸው ያበላሻል፤ አላህ መልካምን ቃልን ፍሬ በምትሰጥ መልካም ዛፍ ሲመስላት ክፉ ቃልን ደግሞ ፍሬ በማይሰጥ ክፉ ዛፍ ይመስለዋል፦
17፥53 ለባሮቼም በላቸው፦ ያችን እርሷ *“መልካም የሆነችውን ቃል ይናገሩ”፤ ሰይጣን በመካከላቸው ያበላሻልና*፤ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና። وَقُل لِّعِبَادِى يَقُولُوا۟ ٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ يَنزَغُ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّ ٱلشَّيْطَٰنَ كَانَ لِلْإِنسَٰنِ عَدُوًّۭا مُّبِينًۭا
14፥24 *አላህ መልካምን ቃል ሥርዋ በምድር ውስጥ የተደላደለች ቅርንጫፍዋም ወደ ሰማይ የረዘመች እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየኽምን?* أَلَمْ تَرَ كَيْفَ ضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا كَلِمَةً طَيِّبَةً كَشَجَرَةٍ طَيِّبَةٍ أَصْلُهَا ثَابِتٌ وَفَرْعُهَا فِي السَّمَاءِ
14፥25 *ፍሬዋን በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች፡፡ አላህም ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል*፡፡ تُؤْتِي أُكُلَهَا كُلَّ حِينٍ بِإِذْنِ رَبِّهَا ۗ وَيَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
14፥26 *የመጥፎም ቃል ምሳሌ ከምድር በላይ የተጎለሰሰች ለእርሷ ምንም መደላደል የሌላት እንደኾነች መጥፎ ዛፍ ነው*፡፡ وَمَثَلُ كَلِمَةٍ خَبِيثَةٍ كَشَجَرَةٍ خَبِيثَةٍ اجْتُثَّتْ مِن فَوْقِ الْأَرْضِ مَا لَهَا مِن قَرَارٍ

ነብያችንም”ﷺ” በቅዱስ ንግግራቸው፦ “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል” ብለዋል፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 46
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَسْكُتْ ‏”

ነጥብ ሥስት
“ትክክለኛ ንግግር”
ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ ትክክለኛ ንግግር መናገር ነው፤ አንድ አማኝ ትክክለኛውንም ንግግር መናገር እና የሐሰትንም ቃል መራቅ አለበት፦
33:70 እላንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ *ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ *ሐሰትንም ቃል ራቁ*፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

እውነተኛ ሰው በማስረኛ ይናገራል፤ ከእውነተኞችም ጎን ይቆማል፦
2፥111 *እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ* በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ *ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

እውነተኛ ሰው በዕውቀት ትክክለኛውን ንግግር ይናገራል፤ ያለ ዕውቀት ምንም አይከተልም፦
6፥143 *እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ* በላቸው፡፡ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
17፥36 *ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል*፡፡ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌ ۚ إِنَّ ٱلسَّمْعَ وَٱلْبَصَرَ وَٱلْفُؤَادَ كُلُّ أُو۟لَٰٓئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْـُٔولًۭا

ያለ ማስረጃ እና ያለ ዕውቀት በግምት እርገጠኛ ሆኖ መናገር እርግማን ያመጣል፤ አንድ ነገረኛ ሰው ወሬን ቢያመጣልን በስሕተት ላይ ሆነን ሕዝቦችን እንዳንጎዳ እና በሠራነው ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳንሆን በዕውቀት እና በማስረጃ ማረጋገጥ አለብን፦
51፥10 *በግምት የሚናገሩ ውሸታሞች ተረገሙ*፡፡ قُتِلَ الْخَرَّاصُونَ
49፥6 እላንተ ያመናችሁ ሆይ *ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ” በስሕተት ላይ ሆናችሁ “ሕዝቦችን እንዳትጎዱ” እና በሠራችሁት ነገር ላይ “ተጸጻቾች” እንዳትሆኑ ”አረጋግጡ”*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن جَآءَكُمْ فَاسِقٌۢ بِنَبَإٍۢ فَتَبَيَّنُوٓا۟ أَن تُصِيبُوا۟ قَوْمًۢا بِجَهَٰلَةٍۢ فَتُصْبِحُوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَٰدِمِينَ
ነጥብ አራት
“ምክክር”
ከማህበራዊ እሴት መካከል አንዱ ሹራ ነው፤ “ሹራ” شُورَىٰ ማለት “መመካከር” ሲሆን “ተሻዉር” تَشَاوُر ደግሞ “ምክክር”consultation” ማለት ነው፤ “ሹራ” የአንድ ሱራ ስም ሆኖ ወርዷል፤ ይህም ሱራ “ሱረቱ አሽ-ሹራ” ይባላል፦
42፥38 *ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፣ ሶላትንም ላዘወተሩት፣ ”ነገራቸውም በመካከላቸው መመካከር ለኾነው” ከሰጠናቸውም ሲሳይ ለሚለግሱት*፡፡ وَٱلَّذِينَ ٱسْتَجَابُوا۟ لِرَبِّهِمْ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَمْرُهُمْ شُورَىٰ بَيْنَهُمْ وَمِمَّا رَزَقْنَٰهُمْ يُنفِقُونَ

“ነሲሓ” نَّصِيحَة ማለት “ነሰሑ” نَصَحُ ማለትም “መከረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምክር” “ንጹሕ” “ቅንነት” “ፍጹምነት” “ታዛዥነት” የሚል ፍቺ አለው፤ “ናሲሕ” نَاصِح ማለት “መካሪ” ማለት ነው፤ “ኑስሕ” نُصْح ማለት ደግሞ “ምክር” ማለት ነው፦
ሱነን ነሣኢ መጽሐፍ 39 , ሐዲስ 49
ተሚም አድ-ዳሪይ እንደተረከው *የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ዲን ነሲሓ ነው፤ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ነሲሓ ለማን ነው? ብለው አሉ፤ እርሳቸው፦ “ለአላህ፣ ለመጽሐፍቱ፣ ለመልእክተኞቹ፣ ለሙስሊሞች ኢማም እና ለጋራ ህዝቦቻቸው” አሉ*። عَنْ تَمِيمٍ الدَّارِيِّ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّمَا الدِّينُ النَّصِيحَةُ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا لِمَنْ يَا رَسُولَ اللَّهِ قَالَ ‏”‏ لِلَّهِ وَلِكِتَابِهِ وَلِرَسُولِهِ وَلأَئِمَّةِ الْمُسْلِمِينَ وَعَامَّتِهِمْ ‌‏.‏

ችግሮችን በመመነጋገር መፍታት ሹራ ነው፤ የውይይታችን አጀንዳ የአላህ ውዴታ ለመፈለግ ተብሎ ስለ ምጽዋት፣ በሰዎች መካከል ማስታረቅ ሆነ በበጎ ሥራ ሁሉ ከሆነ አጅር አለው፤ ከዚያ ውጪ ደግ ነገር የለበትም፦
4፥114 *ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም፡፡ ይኸንንም የተባለውን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን*፡፡ لَّا خَيْرَ فِى كَثِيرٍۢ مِّن نَّجْوَىٰهُمْ إِلَّا مَنْ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوْ مَعْرُوفٍ أَوْ إِصْلَٰحٍۭ بَيْنَ ٱلنَّاسِ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ ٱبْتِغَآءَ مَرْضَاتِ ٱللَّهِ فَسَوْفَ نُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًۭا
58፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተንሾካሾካችሁ ጊዜ በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ፣ መልክተኛውንም በመቃወም አትንሾካሾኩ፡፡ ግን *”በበጎ ሥራና አላህን በመፍራት ተወያዩ”*፡፡ ያንንም ወደ እርሱ የምትሰበሰቡበትን አላህን ፍሩ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا تَنَٰجَيْتُمْ فَلَا تَتَنَٰجَوْا۟ بِٱلْإِثْمِ وَٱلْعُدْوَٰنِ وَمَعْصِيَتِ ٱلرَّسُولِ وَتَنَٰجَوْا۟ بِٱلْبِرِّ وَٱلتَّقْوَىٰ ۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ٱلَّذِىٓ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ

ነጥብ አምስት
“ትክክለኛ ፍትሕ”
ማህበራዊ ቀውስ የሚያስከትለው ዋናው ዝንባሌ ነው፤ “አህዋ” أَهْوَآء ማለት “ዝንባሌ”inclination” ማለት ሲሆን ብዙ ጊዜ ሰርጎ-ገብ የሆኑት ዘረኝነት፣ ቡድንተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ማዳላት መነሻቸው ዝንባሌ ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

ዝንባሌ ከተከተሉት ሊመለክ የሚችል አደገኛ ጣዖት ነው፦
25:43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ዝንባሉን ሳንከተል፣ ደሃ ሃብታም ሳንል እራስ፣ ወላጅ እና ቅርብ ዘመድን ሳንወግን ለአላህ ስልን ሳናዳላ በትክክል መስካሪዎች መሆን አለብን፤ ከንቱ እና ጭፍን ፍቅር አሊያም ከንቱ እና ጭፍን ጥላቻ ለአላህ ቀጥተኞች ወይም በትክክል መስካሪዎች እንዳንሆን ያደርገናል፦
4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا
5፥8 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፤ አላህ የሚፈራ ሰው ፍትኸኛ ይሆናል፤ አላህ በምሰራው ሁሉ ይመለከተኛል ብሎ ያስባል። አምላካችን አላህ አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፦
16፥90 *አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ውሸትን አትቅጠፉ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥21 *በአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? እነሆ በደለኞች አይድኑም*፡፡ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِآيَاتِهِ ۗ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُونَ

ሚሽነሪዎች እኛ ሙስሊሞች ክርስትና ላይ ላስነሳነው ስሙር ሙግት እልህ ይዟቸው የልብ ፍልጠት፣ የራስ ምታት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጎን ውጋት እና የእግር ቁርጥማት ይዟቸው እንደሆነ እልሃቸው ያሳብቅባቸዋል፤ ቧጠውና ሟጠው በጥላቻ ጥላሸት ለማጠልሸት በአላህ ላይ በውሸት ይቀጥፋሉ፤ በአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? እነሆ በደለኞች አይድኑም፦
6፥21 *በአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? እነሆ በደለኞች አይድኑም*፡፡ وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِآيَاتِهِ ۗ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُونَ

እነዚህ ኃሳውያን እስልምናን ከመዋቅሩ እና ከትምህርት መርሃ-ግብሩ ቁጭ ብለው የተማሩት ትምህርት አይደለም፤ ስለዚህ እኛ ሙስሊሞች የታሪክ ምፀት ከዐሊሞቻችን ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይለናል፤ ይህን ለማድረግ አስረግጦ እና ረግጦ መረዳትና ማስረዳት ይጠበቅብናል፤ እነዚህ ነውጠኞች፦ “ሐዲስ ላይ አላህን እራቁቱን ባዶ እግሩን ሳይገረዝ ታገኙታላችሁ” ወሊአዑዙቢላህ ይላል ይሉናል፤ ይህም የሚሉበት ምክንያት ሰው የሆነ ኢየሱስ መገረዙን ስንነግራቸው እና አምላክ አይገረዝም ለሚል ሙግታችን ምላሽ መሆኑ ነው፣ እስቲ የተቀጠፈበትን ይህንን ሐዲስ እንመልከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 81 , ሐዲስ 113:
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ባዶ እግራችሁን፤እራቁታችሁን እየተራመዳችሁ እና ሳትገረዙ አላህን ታገኙታላችሁ”*። سَمِعْتُ ابْنَ عَبَّاسٍ، سَمِعْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ إِنَّكُمْ مُلاَقُو اللَّهِ حُفَاةً عُرَاةً مُشَاةً غُرْلاً ‏”‌‏.‏ قَالَ سُفْيَانُ هَذَا مِمَّا نَعُدُّ أَنَّ ابْنَ عَبَّاسٍ سَمِعَهُ مِنَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم‏.‏

እዚህ ሐዲስ ላይ በግልጽና በማያሻማ መልኩ “ኢነኩም” إِنَّكُمْ ማለትም “እናንተ” የሚል የብዜት ተውላጠ ስም እኛን ሰዎችን ያመለክታል፤ “ሙላቁል-ሏህ” مُلاَقُو اللَّهِ ማለትም “አላህን ታገኙታላችሁ” ስለሚል ባዳ እግር፣ እራቁት እና አለመገረዝ ሆኖ አግኚው እኛ ስንሆን የምናገኘው አላህን ነው። ይህንን ቅጥፈት እንደበቀቀን ሲደጋግሙት ይታያል፤ ለህሊናው ኖሮ ሃይ እና አንድ የሚል ይጥፋ እንዴ? ሐዲሱን ወረድ ብለን ስንመለከተው ይበልጥ ግልጽ ይሆናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 81 , ሐዲስ 116:
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሰዎች ባዶ እግራቸውን፤ እራቁታቸውን እና ሳይገረዙ ይሰበሰባሉ” እኔም አልኩኝ፦ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ወንዱም ሴቱም እራቁታቸዉን ሲሆኑ አይተፋፈሩምን? እርሳቸውም፦ “ያን ሁኔታ ከባድ ስለሆነ ለእንዲህ አይነቱ ነገር ለማጤን አያስችላቸውም” አሉ*። أَنَّ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ تُحْشَرُونَ حُفَاةً عُرَاةً غُرْلاً ‏”‏ قَالَتْ عَائِشَةُ فَقُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ الرِّجَالُ وَالنِّسَاءُ يَنْظُرُ بَعْضُهُمْ إِلَى بَعْضٍ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ الأَمْرُ أَشَدُّ مِنْ أَنْ يُهِمَّهُمْ ذَاكِ ‏”‌‏.‏

ሰዎች ባዶ እግራቸውን፤ እራቁታቸውን እና ሳይገረዙ ሲሰበሰቡ ሁሉም ስለራሱ እንጂ ተቃራኒ ወገኑ እራቁቱን መሆኑን የሚያስብበት ጊዜም ሆነ አቅም የለውም፤ እዚህ ሐዲስ ላይ ደግሞ ቁልጭ እና ፍንትው ብሎ “ቱሕሸሩነ” تُحْشَرُونَ ማለትም “ይሰበሰባሉ” የሚል ቃላት አለ፤ ቀጥሎ ያሉት ቃላት፦ ባዶ እግራቸውን፤ እራቁታቸውን እና ሳይገረዙ” የሚለው ሰውን እንጂ ፈጣሪን በፍጹም አያመለክትም።

አምላካችን አላህም በተከበረው ቃሉ ሰው አላህን በትንሳኤ ቀን ሲቀሰቀስ ተገኛኝ እንደሆነ እና ወደ እርሱ ሲቀርቡ፦ “በመጀመሪያ ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ ራቁታችሁን በእርግጥ መጣችሁን?” እንደሚላቸው ተናግሯል፦
84፥6 አንተ ሰው ሆይ! *አንተ ጌታህን እስከምትገናኝ ድረስ ልፋትን ለፊ ነህ፤ ተገናኚውም ነህ*፡፡ يَا أَيُّهَا الْإِنسَانُ إِنَّكَ كَادِحٌ إِلَىٰ رَبِّكَ كَدْحًا فَمُلَاقِيهِ
18፥48 የተሰለፉም ኾነው በጌታህ ላይ ይቀረባሉ፡፡ ይባላሉም፦ *”በመጀመሪያ ጊዜ እንደ ፈጠርናችሁ ራቁታችሁን በእርግጥ መጣችሁን? በእውነቱ ለእናንተ ለመቀስቀሻ ጊዜን አናደርግም መስሏችሁ ነበር?”*፡፡ وَعُرِضُوا عَلَىٰ رَبِّكَ صَفًّا لَّقَدْ جِئْتُمُونَا كَمَا خَلَقْنَاكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ ۚ بَلْ زَعَمْتُمْ أَلَّن نَّجْعَلَ لَكُم مَّوْعِدًا

እውነቱ ይህ ነው፤ እውነቱ በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ እና በአላህ ላይም ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ይበልጥ በዳይ ማነው? በገሀነም ውስጥ ለከሓዲዎች መኖሪያ መኖሩን አትርሱ፦
29፥68 *በአላህ ላይም ውሸትን ከቀጣጠፈ ሰው ወይም እውነቱ በመጣለት ጊዜ ከአስዋሸ ይበልጥ በዳይ ማነው? በገሀነም ውስጥ ለከሓዲዎች መኖሪያ የለምን?* وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِالْحَقِّ لَمَّا جَاءَهُ ۚ أَلَيْسَ فِي جَهَنَّمَ مَثْوًى لِّلْكَافِرِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ይቅባይነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

3፥134 ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች *ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት ተደግሳለች*፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِى ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلْكَٰظِمِينَ ٱلْغَيْظَ وَٱلْعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِ ۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ

በቁርኣን ከተገለጹ የአላህ ስሞች መካከል "አል-ዐፉው" العَفُوّ ሲሆን "ዐፋ" عَفَا ማለት "ይቅር አለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ይቅር ባዩ" ማለት ነው፤ አላህ እጅግ በጣም "ይቅርባይ" ነው፦
42፥25 *እርሱም ያ ከባሮቹ ንስሓን የሚቀበል፣ ከኃጢአቶችም ይቅር የሚል፣ የምትሠሩትንም ሁሉ የሚያውቅ ነው*፡፡ وَهُوَ الَّذِي يَقْبَلُ التَّوْبَةَ عَنْ عِبَادِهِ وَيَعْفُو عَنِ السَّيِّئَاتِ وَيَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ
4፥99 እነዚያም አላህ ከእነርሱ ይቅርታ ሊያደርግ ይሻል፡፡ *አላህም ይቅር ባይ መሓሪ ነው*፡፡ فَأُولَـٰئِكَ عَسَى اللَّهُ أَن يَعْفُوَ عَنْهُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ عَفُوًّا غَفُورًا
4፥43 *አላህ ይቅር ባይ መሓሪ ነውና*፡፡ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَفُوًّا غَفُورًا

የአል-ዐፉው" ተለዋዋጭ ቃል "አል-ገፋር" الغَفَّار ወይም "አል-ገፉር" الغَفُور ሲሆን "ገፈረ" غَفَرَ ማለትም "ማረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መሐሪው" ማለት ነው።
"ዐፍዉ" عَفْو ወይም "መግፊራህ" مَّغْفِرَة ማለት "ይቅርባይነት" "ምህረት" ማለት ነው። ተበድለው ለአላህ ብለው ይቅር የሚሉ ይቅርታ አድራጊዎች "ዐፊን" عَافِين ወይም "ሙሥተግፊር" مُسْتَغْفِر ይባላሉ፦
3፥134 ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች *ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት ተደግሳለች*፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡ ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِى ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلْكَٰظِمِينَ ٱلْغَيْظَ وَٱلْعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِ ۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلْمُحْسِنِينَ

አንድ ሰው ተበድሎ የተበደለበትን ሃቅ ማስመለስ ወቀሳ የለበትም፤ ፍትሕ ነውና። የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ነው። ነገር ግን ለአላህ ብሎ ይቅርባይ የሆነ አላህ ዘንድ የሚያገኘው ወሮታ፣ አጸፌታ፣ ምንዳና ትሩፋት ያለ ግምት ነው፦
42፥41 ከተበደሉም በኋላ *በመሰሉ የተበቀሉ እነዚያ በነርሱ ላይ ምንም የወቀሳ መንገድ የለባቸውም*፡፡ وَلَمَنِ ٱنتَصَرَ بَعْدَ ظُلْمِهِۦ فَأُو۟لَٰٓئِكَ مَا عَلَيْهِم مِّن سَبِيلٍ
42፥40 የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ *ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው*፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም፡፡ وَجَزَٰٓؤُا۟ سَيِّئَةٍۢ سَيِّئَةٌۭ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُۥ عَلَى ٱللَّهِ ۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ

አላህ ይቅርባዮችም ኀጢኣታቸውን ይቅር ይላቸዋል፦
42፥37 ለእነዚያም የኀጢኣትን ታላላቆችና ጠያፎችን የሚርቁ *”በተቆጡም ጊዜ እነርሱ የሚምሩት ለኾኑት”*፡፡ وَٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا۟ هُمْ يَغْفِرُونَ
4፥149 ደግ ነገርን ብትገልጹ ወይም ብትደብቁት ወይም ከመጥፎ ነገር *ከበደል ይቅርታ ብታደርጉ አላህ ይቅር ባይ ኃያል ነው*፡፡ إِن تُبْدُوا۟ خَيْرًا أَوْ تُخْفُوهُ أَوْ تَعْفُوا۟ عَن سُوٓءٍۢ فَإِنَّ ٱللَّهَ كَانَ عَفُوًّۭا قَدِيرًا

የይቅርባይነት ተቃራኒ ቁርሾ ነው፤ ቁርሾ ከጥላቻ የሚመጣ ሲሆን ቁርሾ ወደ ይቅርባይነት የሚቀየረው በፍቅር ብቻ ነው፤ ፍቅር የሻከረን ግንኙነት ያለሰልሳል፤ ጥላቻ ኪሳራም ጉዳትም ያመጣል፤ ፍቅር ግን ትርፍም ጥቅምም ያመጣል። ይቅርታ ማድረግ እና የሰዎችን ጥፋት በይቅታ ማለፍ ከአላህ ዘንድ ይቅርባይነት ያሰጣል፤ በተቃራኒው ቂምን መዶለት ቅጣት አለው፦
24፥22 ከእናንተም የችሮታና የክብረት ባለቤቶች የኾኑት ለቅርብ ዘመዶችና ለድኾች በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ላይሰጡ አይማሉ፡፡ *ይቅርታም ያድርጉ፡፡ ጥፋተኞቹን ይለፉም፡፡ አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን? አላህም መሓሪ አዛኝ ነው*፡፡ وَلَا يَأْتَلِ أُولُو الْفَضْلِ مِنكُمْ وَالسَّعَةِ أَن يُؤْتُوا أُولِي الْقُرْبَىٰ وَالْمَسَاكِينَ وَالْمُهَاجِرِينَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ ۖ وَلْيَعْفُوا وَلْيَصْفَحُوا ۗ أَلَا تُحِبُّونَ أَن يَغْفِرَ اللَّهُ لَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ
35፥10 ማሸነፍን የሚፈልግ የኾነ ሰው አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው፤ እርሱን በመገዛት ማሸነፍን ይፈልግ፡፡ መልካም ንግግር ወደ እርሱ ይወጣል፡፡ በጎ ሥራም ከፍ ያደርገዋል፡፡ *እነዚያም መጥፎ ሥራዎችን የሚዶልቱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፡፡ የእነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል*፡፡ مَن كَانَ يُرِيدُ ٱلْعِزَّةَ فَلِلَّهِ ٱلْعِزَّةُ جَمِيعًا ۚ إِلَيْهِ يَصْعَدُ ٱلْكَلِمُ ٱلطَّيِّبُ وَٱلْعَمَلُ ٱلصَّٰلِحُ يَرْفَعُهُۥ ۚ وَٱلَّذِينَ يَمْكُرُونَ ٱلسَّيِّـَٔاتِ لَهُمْ عَذَابٌۭ شَدِيدٌۭ ۖ وَمَكْرُ أُو۟لَٰٓئِكَ هُوَ يَبُورُ

አላህ የተብቃቃ ነው፤ ሰደቃ ስንሰጥ ለእርሱ ታዛዥነትና ፍቅር መገለጫ ብቻ ነው፤ ይቅርባይነት ግን ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው። አምላካችን አላህ ይቅርባዮች ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን፦
2፥263 *መልካም ንግግር እና ምሕረት ማድረግ ማስከፋት ከሚከተላት ምጽዋት በላጭ ነው፡፡ አላህም ተብቃቂ ታጋሽ ነው*፡፡ قَوْلٌۭ مَّعْرُوفٌۭ وَمَغْفِرَةٌ خَيْرٌۭ مِّن صَدَقَةٍۢ يَتْبَعُهَآ أَذًۭى ۗ وَٱللَّهُ غَنِىٌّ حَلِيمٌۭ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም