ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.2K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ሥነ-ፅንስ

ክፍል ሶስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

ደረጃ ሶስት
“ሙድጋ”
“ሙድጋ” مُضْغَة ማለት “ቁራጭ ስጋ”embryonic lump” ወይም “የታኘከ ስጋ”chewed gum” ማለት ሲሆን ልክ ጥርስ እንዳረፈበት ስጋ የሚመስልበት የፅንስ ደረጃ ነው፤ ይህን ደረጃ ለማመልከት “ሱምሙ” ثُمَّ “ከዚያም” የሚል መስተፃምር ከመጠቀም ይልቅ “ፈ” فَ “ም” የሚል ቅፅበታዊ መስተፃምር ይጠቀማል፤ ምክንያቱም 21-24 ቀናት የረጋ ደም ጊዜ ሲሆን 24ኛ ቀን ላይ በቅፅፈት የታኘከ ስጋ ቅርፅ ይጀምራል፤ በዚህ ጊዜ “”ፍጥረትዋ ሙሉ ካልሆነች”” ጅማት፣ አንጀት፣ ስስ ጡንቻ፣ ስስ የደም ስር ወዘተ ስለሚፈጠሩ ነው፦
22:5 እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ፤ እኛም ከአፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ ከዚያም ከቁራጭ ስጋ مُضْغَةٍ “”ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች”” ችሎታችንን ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውን”ም” ደም “ቁራጭ ሥጋ” مُضْغَةً አድርገን ፈጠርን፤

“ፍጥረትዋ ሙሉ የሆነች” ቁራጭ ሥጋ በአምተኛው ደረጃ ላይ ይመጣል፤ ይህንን ለማመልከት “ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል” ይላል፦
39:6 በእናቶቻችሁ ማህፀኖች ውስጥ፣ በሦስት ጨለማዎች ውስጥ፣ “ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል”፤

ሶስት ጨለማ የተባሉት፦ ሆድ፣ ማህፀንና የእንግዴ ልጅ ናቸው።

ደረጃ አራት
“ዐዝም”
“ዐዝም” عَظْم በነጠላ ሲሆን “ዒዛም” عِظَام ደግሞ በብዜት ነው፤ ትርጉሙም “አፅም”skeleton” ወይም “አጥንት”bone” ማለት ነው፤ ከ 24-35 ቀናት የቁራጭ ስጋ ሂደት ሲሆን ከመቅፅበት 35ኛው ቀን የደም ዝውርውር፣ የነርቭ ሥርዓት፣ አፅም ወዘተ የሚፈጠርበት ሂደት ነው፤ ይህን አጭር ጊዜ ለማመልከት “ፈ” فَ “ም” የሚል ቅፅበታዊ መስተፃምር ይጠቀማል፦
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም “ቁራጭ ሥጋ” አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጯን”ም” ሥጋ “አጥንቶች” عِظَامًا አድርገን ፈጠርን፤
ደረጃ አምስት
“ለህም”
“ለህም” لَحْم ማለት “ስጋ” ማለት ሲሆን ይህ ስጋ ጠንካራ ጡንቻ ያለው ስጋ ነው፤ ከ 35-38 ቀናት የአጥንት ሂደት ሲሆን ከመቅፅበት በ 38ኛው ቀን ልብ፣ አንጎል፣ ቆዳ፣አይን፣ አፍንጫ ወዘተ የሚፈጠርበት ሂደት ነው፦
23:12 አጥንቶቹንም “ሥጋን” لَحْمًا አለበስናቸው፤

በዚህ ጊዜ ሩህ ይነፋል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 1:
ዓብደላህ ኢብን መስዑድ እንዲህ አለ። እውነት ተናጋሪ እና እውነት የተነገራቸው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፦
إِنَّ أَحَدَكُمْ يُجْمَعُ خَلْقُهُ فِي بَطْنِ أُمِّهِ أَرْبَعِينَ يَوْمًا نُطْفَةً، ثُمَّ يَكُونُ عَلَقَةً مِثْلَ ذلِكَ، ثُمَّ يَكُونُ مُضْغَةً مِثْلَ ذلِكَ، ثمَّ يُرْسَلُ إلَيْهِ الْمَلَكُ فَيَنْفُخُ فيهِ الرُّوحَ، وَيُؤمَرُ بأرْبَعِ كَلِمَاتٍ: بِكَتْبِ رِزْقِهِ وَأَجَلِهِ وَعَمَلِهِ وَشَقِيٌّ أوْ سَعِيدٌ.
እያንዳንዳቹህ በእናቱ ሆድ ውስጥ ፍጥረቱ ይሰበሰባል፤ አርባ ቀን የፍትወት ጠብታ ይሆናል፤ ከዛም በተመሳሳይ የረጋ ደምን ይሆናል፤ ከዛም በተመሳሳይ የታኘከን ስጋ ይሆናል፤ ከዛም መልአክ ይላክና ሩሕ ይነፋበታል፤ መልአኩም አራት ነገሮች ላይ ይታዘዛል፦ ሲሳዩን፣ ፍጻሜውን፣ ስራውን፣ የተከፋ ወይንም ደስተኛ መሆኑን እንዲጽፍ ይታዘዛል።

ደረጃ ስድስት
“ነሽአ”
“ነሽአ” نَّشْأَة የሚለው ቃል “አንሸአ” أَنشَأَ “አስገኘ” ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን “ግኝት”production” ማለት ነው፤ አላህም “አንሸናሁ” أَنْشَأْنَاهُ “አስገኘነው” ይለናል፤ ይህም ፅንስ እስከ መወለድ ጊዜ ያለው ሽልን የሚያመለክት ሲሆን “ሌላ ፍጥረትን” ይለዋል፤ በዚህ ጊዜ ከንፈር፣ ጥፍር፣ ፀጉር ወዘተ የሚገኘበት ጊዜ ነው፤ ይህን እረጅም ደረጃ ለማመልከት “ሱምሙ” ثُمَّ “ከዚያም” የሚል መስተፃምር ይጠቀማል፦
23፥12 ከዚያም “ሌላ ፍጥረትን” خَلْقًا آخَرَ አድርገን “አስገኘነው” أَنْشَأْنَاهُ ፤ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡

መደምደሚያ
አላህ ከራሳችን ጥንድ እንድንረካ መፍጠሩ፣ በመካከላችን መተዛዘንና ፍቅር መኖሩ በመርካትም ማህፀን ውስጥ የሚፈሱት የፍትወት ጠብታ ሰው መሆኑ ለሚያስውሉ ሕዝቦች ከአስደናቂ ታምራቶቹ ተጠቃሽ ነው፦
30:21 ለእናንተም ከራሳችሁ “ጥንዶችን” أَزْوَاجًا “mates” ወደ እነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፤ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ “ታምራቶቹ” آيَاتِهِ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስውሉ ሕዝቦች “ታምራቶች” አሉ።

ይህንን ታምር አላህ በሥነ-ፅንስ እውቀት በራሳችን ያሉትን የአላህ ታምራት በዘመናችን አሳይቶናል፤ ከዚህ የሚበልጥ ምን መታደል አለ? ምስጋና ሁሉ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን፦
41፥53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ በአጽናፎቹ ውስጥ እና #በራሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን #ታምራቶቻችንን በእርግጥ #እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?

ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. The Developing Human ( Prof. Keith Moor & Prof. T. Persaud) Edition 6 – 1998
2. Clinical Anatomy . By Richard Snell ( 3ed edition) published in 1986 – Little, Brown
3. A Scientist’s Interpretation of References to Embryology in the Quran (Prof. Keith Moor) Journal of the Islamic Medical Association, 1986: vol.18, Page 15-16

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርአን ሱራህ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
“ሱራህ” سُورَة የሚለው ቃል ትርጉሙ “ምዕራፍ” ወይም “ክፍል” አሊያም “ደረጃ” ማለት ነው፤ ቁርአን ሱራህ እንዳለው አላህ በቁርአን 10 ጊዜ ያነሳዋል፣ ለናሙና ያክል ውስን ጥቅሶችን ብንመለከት፦
24:1 ይህች ያወረድናትና የደነገግናት “ሱራ” سُورَةٌ ናት፣
2:23 በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን “ምዕራፍ” بِسُورَةٍ አምጡ፡፡
10:38 በእውነትም «ቀጣጠፈው » ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን አንዲት “ሱራ” بِسُورَةٍ አምጡ፡፡
11፥13 ይልቁንም «ቀጣጠፈው» ይላሉን፡- «እውነተኞች እንደሆናችሁ ብጤው የሆኑን ዐስር የተቀጣጠፉ “ሱራዎች” سُوَرٍ አምጡ፡፡
9፥64 መናፍቃን በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር የምትነግራቸው “ሱራ” سُورَةٌ በእነርሱ ላይ መውረዷን ይፈራሉ፡፡

ቁርአን 114 ሱራዎች ሲኖሩት ለ 13 ዓመት 86 ሱራዎች የወረዱት በመካ ሲሆን ለ 10 ዓመት ደግሞ 28 ሱራዎች የወረዱት በመዲና ነው፣ አላህ ቁርአንን በሱራህ ከፋፍሎ ያወረደው ልብህ በማርጋት ለማንበብ እንዲመች ነው፦
17:106 ቁርአንንም በሰዎች ላይ ሆነህ ታነበው ዘንድ “ከፋፈልነው” ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው ።
25:32 እነዚያ የካዱትም፦ ቁርአን በርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም? አሉ፤ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ “ከፋፍለን” አወረድነው ፤ ቀስ በቀስ “መለያየትም” ለየነው።
3፥3 መጽሐፉን በአንተ ላይ “ከፋፍሎ” በእውነት አወረደ፡፡

አንድ ሱራህ ከሌላው ሱራህ የሚለየው በተስሚያህ ማለትም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” በሚል ቃል ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ቁጥር 398
ኢብኑ አባስ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ሁለት ሱራዎች አይለያዩ በመካከላቸው “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ።
قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}‏ ‏
96፥1 አንብብ በዚያ ሁሉን “በፈጠረው ጌታህ ስም”፡፡

እያንዳንዱ ሱራህ ሲጀምር በተስሚያህ ነው ከአንድ ሱራህ በስተቀር፤ ይህም ሱራህ ሱረቱ አት-ተውባህ ነው፤ 9ኛው ሱራህ ተስሚያህ ባይኖርም ሱረቱ አን-ነምል 27፥30 ላይ ይደግመዋል፤ ይህም ሱረቱ አት-ተውባህ የቁጣ ሱራህ ሆና ብትዘለልም የዘጠኝ ድምር የሆነችው ሱረቱ አን-ነምል ላይ ይገኛል፤ 2+7=9 ይሆናል፦
27፥30 «እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው”፡፡

ኦሪት፣ መዝሙራት፣ የነቢያት መጽሐፍት ጸሐፊዎቻቸው ባልሆኑ ሰዎች ቢከፋፈሉም ባይብል ግን በምእራፍ የተከፋፈለው ከ 1244 AD እስከ 1248 AD እቴቨን ላንቶን በሚባል ሰው ነው፤ ከዚያም ባሻገር የመጽሐፍቱን ስም የዳቦ ስም አድርገው በሰው ስም የሰየሙት ነብያት ሳይሆኑ ታሪክ ጸሐፊዎች ናቸው፤ የቁርአን ሱራህ ስም ግን ከመለኮት በጂብሪል ወደ ነብያችን የተላለፈ ነው፤ ይህን ከነብያችን ንግግር ለናሙና ማቅረብ ይቻላል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 311
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “”ከሱረቱል ከህፍ”” መጀመሪያ አስር አናቅፅ ያፈዘ ማንኛውም ከደጃል ይጠበቃል።
أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ مَنْ حَفِظَ عَشْرَ آيَاتٍ مِنْ أَوَّلِ سُورَةِ الْكَهْفِ عُصِمَ مِنَ الدَّجَّالِ ‏”‏
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 33
ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “ሱረቱል ያሲንን” በሟቻችሁ ላይ ቅሩ።
قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ اقْرَءُوا ‌‏ يس عَلَى مَوْتَاكُمْ ‏”

የቁርአን ሱራህ እያንዳንዱ ስም በውስጡ ይገኛል ከሶስት ሱራዎች በስተቀር፤ እነርሱም፦ ሱረቱል ኢኽላስ፣ ሱረቱል አንቢያ እና ሱረቱል ፋቲሃ ናቸው፤ እነዚህ ሱራዎች ውስጣቸው ባለው ትርጉም ተሰይመዋል፤ ሌላው 111 ሱራዎች ስማቸው በውስጣቸው ይገኛል፤ ዝርዝሩን ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ይዤ እቀርባለው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርአን ሱራህ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

የቁርአን ሱራህ እያንዳንዱ ስም በውስጡ ይገኛል ከሶስት ሱራዎች በስተቀር፤ እነርሱም፦ ሱረቱል ኢኽላስ፣ ሱረቱል አንቢያ እና ሱረቱል ፋቲሃ ናቸው፤ እነዚህ ሱራዎች ውስጣቸው ባለው ትርጉም ተሰይመዋል፤ ሌላው 111 ሱራዎች ስማቸው በውስጣቸው ይገኛል፤ ይህንን ዝርዝር እንመልከት፦

“በቀራህ”
“በቀራህ” بَقَرَةٌ ማለት “ላም” ወይም “ጊደር” ማለት ሲሆን ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
2፥68 «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች ዕድሜዋን ያብራራልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች *ጊደር* بَقَرَةٌ ናት ይላችኋል፤

“ዒምራን”
“አለ-ዒምራን” َءَالَ عِمْرَٰنَ ማለት “ኢያቄም” ማለት ሲሆን የማርያም አባት ስም ነው፤ *የዒምራንንም ቤተሰብ* ማለት ነው፤ ይህም ሶስተኛው ሱራህ ሲሆን ይህ ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
3፥33 አላህ አደምን፣ ኑሕንም፣ የኢብራሂምንም ቤተሰብ፣ *የዒምራንንም ቤተሰብ* وَءَالَ عِمْرَٰنَ በዓለማት ላይ መረጠ፡፡

“ኒሳእ”
“ኒሳእ” النِّسَاءَ ማለት “ሴቶች” ማለት ሲሆን አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
4፥4 *ሴቶችንም* النِّسَاءَ መህሮቻቸውን በደስታ ስጡ፡፡ ለእናንተም ከእርሱ አንዳችን ነገር ነፍሶቻቸው ቢለግሱ መልካም ምስጉን ሲኾን ብሉት፡፡

“ማኢዳህ”
“ማኢዳህ” مَائِدَةً ማለት “ማእድ” ወይም “ገበታ” ማለት ሲሆን አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
5፣112 ሐዋርያት፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ጌታህ በእኛ ላይ ከሰማይ *ማእድን* مَائِدَةً ሊያወርድልን ይችላልን» ባሉ ጊዜ አስታውስ፡፡ «ምእመናን እንደ ኾናችሁ አላህን ፍሩ» አላቸው፡፡

“አንአም”
“አንአም” أَنْعَٰمٌۭ ማለት *”የቤት እንስሳ”* ማለት ሲሆን ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
6፥138 በሐሳባቸውም ይህች እርም የኾነች *”ለማዳ እንስሳ”* أَنْعَٰمٌۭ እና አዝመራ ናት፡፡ የምንሻው ሰው እንጂ ሌላ አይበላትም፡፡

“አዕራፍ”
“አዕራፍ” الْأَعْرَافِ ማለት *”ኮረብታ”* ማለት ሲሆን ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
7፤46 በመካከላቸውም ግርዶሽ አልለ፡፡ *በአዕራፍም* الْأَعْرَافِ ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አልሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም፡፡

“አንፋል”
“አንፋል” الْأَنفَالِ ማለት *”ምርኮ”* ማለት ሲሆን ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
8:1 *ከምርኮ* الْأَنفَالِ ይጠይቁሃል፡፡ «የዘረፋ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው፡፡» ስለዚህ አላህን ፍሩ፡፡ በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ፡፡ አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ በላቸው፡፡

“ተውባህ”
“ተውባህ” تَوْبَة ማለት *”ፀፀት”* ወይም “ንስሃ” ማለት ሲሆን ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
2፥102 ሌሎችም በኃጢአቶቻቸው የተናዘዙ መልካም ሥራንና ሌላን መጥፎ ሥራ የቀላቀሉ አልሉ፡፡ አላህ “ከእነሱ ጸጸታቸውን” يَتُوبَ عَلَيْهِمْ ሊቀበል ይከጀላል፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
ዩኑስ”
“ዩኑስ” يُونُسَ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስረኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
10:98 ያመነችና እምነትዋ የጠቀማት ከተማ ለምን አልኖረችም ግን *የዩኑስ* يُونُسَ ሕዝቦች ባመኑ ጊዜ በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ከእነሱ ላይ አነሳንላቸው፡፡ እስከ ጊዜም ድረስ አጣቀምናቸው፡፡

“ሁድ”
“ሁድ” هُودُ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
11:53 አሉ፡- «*ሁድ* هُودُ ሆይ! በአስረጅ አልመጣህልንም፡፡ እኛም ላንተ ንግግር ብለን አማልክቶቻችንን የምንተው አይደለንም፡፡ እኛም ለአንተ አማኞች አይደለንም፡፡

“ዩሱፍ” ”
ዩሱፍ” يُوسُفُ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
12:4 *ዩሱፍ* يُوسُفُ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም በሕልሜ አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡

“ረዕድ”
“ረዕድ” الرَّعْدُ ማለት *ነጎድጓድም* ማለት ሲሆን አስራ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
13 ፣13 *ነጎድጓድም* الرَّعْدُ አላህን በማመስገን ያጠራል፡፡ መላእክትም እርሱን ለመፍራት ያጠሩታል፡፡

“ኢብራሂም”
“ኢብራሂም” إِبْرَاهِيمُ ማለት የአላህ ነብይ ሲሆን አስራ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
14፣35 *ኢብራሂምም* إِبْرَاهِيمُ ባለ ጊዜ አስታውስ «ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን፡፡

“ሂጅር”
“ሂጅር” الْحِجْرِ ማለት *የሸለቆ ስም* ሲሆን አስራ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
15: 80 *የሒጅርም* الْحِجْرِ ሰዎች መልክተኞቹን በእርግጥ አስተባበሉ፡፡

“ነሕል”
“ነሕል” النَّحْلِ ማለት *ንብ* ማለት ሲሆን አስራ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
16፣68 ጌታህም ወደ *ንብ* النَّحْلِ እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ፡፡

“ኢስራእ”
“ኢስራእ” أَسْرَىٰ ማለት *ጉዞ* ማለት ሲሆን አስራ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
17፣1 ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ “ያስኼደው” أَسْرَىٰ ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው አስኼድነው፡፡ እነሆ እርሱ አላህ ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡

“ከህፍ”
“ከህፍ” الْكَهْفِ ማለት *ዋሻ* ማለት ሲሆን አስራ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
18:9 *የዋሻው* الْكَهْفِ እና የሰሌዳው ባለቤቶች ከተዓምራቶቻችን ሲሆኑ ግሩም መሆናቸውን አሰብክን?

“መርየም”
“መርየም” مَرْيَمَ ማለት “የኢሳ እናት” ስትሆን አስራ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
19፣16 በመጽሐፉ ውስጥ *መርየምንም* ከቤተሰቧ ወደ ምሥራቃዊ ስፍራ በተለይች ጊዜ አውሳ፡፡

“ጧሃ”
“ጧሃ” طه ማለት ከሃያ ዘጠኙ ሃርፎች አንዱ ሲሆን ሃያኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
20:1 ጠ.ሀ. *ጧሃ* طه

ኢንሻላህ ይቀጥላል….

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርአን ሱራህ

ክፍል ሶስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

“ሐጅ” حَجِّ ማለት “ጉብኝት” ማለት ሲሆን ሃያ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
22፥27 አልነውም፡- በሰዎችም ውስጥ *በሐጅ* بِالْحَجِّ ትዕዛዝ ጥራ፡፡

“ሙዕሚኑን”
“ሙዕሚኑን” الْمُؤْمِنُونَ ማለት “ምዕመናን” ወይም “አማኞች” ማለት ሲሆን ሃያ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
23፣1 *ምእምናን* الْمُؤْمِنُونَ ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡

“ኑር”
“ኑር” نُورُ ማለት “ብርሃን” ማለት ሲሆን ሃያ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
24፣35 አላህ የሰማያትና የምድር *አብሪ* نُورُ ነው፡፡

“ፉርቃን”
“ፉርቃን” الْفُرْقَانَ ማለት “እውነትን ከሃሰት መለያ” ማለት ሲሆን ሃያ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
25.1 ያ *ፉርቃንን* الْفُرْقَانَ በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው፡፡

“ሹዐራህ”
“ሹዐራህ” وَالشُّعَرَاءُ ማለት “ባለ ቅኔዎችንም” ማለት ሲሆን ሃያ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
26፣224 *ባለ ቅኔዎችንም* وَالشُّعَرَاءُ ጠማማዎቹ ይከተሉዋቸዋል፡፡

“ነምል”
“ነምል” النَّمْلِ ማለት “ባለ ቅኔዎችንም” ማለት ሲሆን ሃያ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
27፣18 *በጉንዳንም* النَّمْلِ ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን «እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያዎቻችሁ ግቡ፡፡ ሱለይማንና ሰራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ» አለች፡፡

“ቀሶስ”
“ቀሶስ” الْقَصَصَ ማለት “ባለ ቅኔዎችንም” ማለት ሲሆን ሃያ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
28፣25 ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሐፍረት ጋር የምትኼድ ሆና መጣችው፡፡ «አባቴ ለእኛ ያጠጣህልንን ዋጋ ሊሰጥህ ይጠራሃል» አለችው፡፡ ወደእርሱ በመጣና ወሬውን በእርሱ ላይ *በተረከለትም* الْقَصَصَ ጊዜ «አትፍራ ከበደለኞቹ ሕዝቦች ድነሃል» አለው፡፡

“ዓንከቡት”
“ዓንከቡት” الْعَنكَبُوتِ ማለት “ሸረሪት” ማለት ሲሆን ሃያ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
29፣41የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች *ሸረሪት* الْعَنكَبُوتِ ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡

“ሩም”
“ሩም” الرُّومُ ማለት “የጣሊያን ሀገር ስም” ሲሆን ሰላሳኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
30፣2 *ሩም* الرُّومُ ተሸነፈች፡፡

“ሉቅማን”
“ሉቅማን” لُقْمَانَ ማለት “የጻድቅ ስም” ሲሆን ሰላሳ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
31 :12 ለ*ሉቅማንም* لُقْمَانَ ጥበብን በእርግጥ ሰጠነው፡፡

“ሰድጃህ”
“ሰድጃህ” سُجَّدًا ማለት “ሰጋጆች” ሲሆን ሰላሳ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
32:15 በአንቀጾቻችን የሚያምኑት እነዚያ በእርሷ በተገሰጹ ጊዜ *ሰጋጆች* سُجَّدًا ሆነው የሚወድቁትና እነርሱም የማይኮሩ ሆነው በጌታቸው ምስጋና ተጎናጽፈው የሚያወድሱት ብቻ ናቸው፡፡

“አሕዛብ”
“አሕዛብ” الْأَحْزَابَ ማለት “ህዝብ” ወይም “ክፍፍል” ማለት ሲሆን ሰላሳ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
33፥20 መናፍቆች *አሕዛብን* الْأَحْزَابَ አልኼዱም ብለው ያስባሉ፡፡

“ሰበእ”
“ሰበእ” لِسَبَإٍ ማለት “ሳባ” ማለት ሲሆን “የአገር ስም” ነው፤ ሰበእ ሰላሳ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
34:15 *ለሰበእ* لِسَبَإٍ በመኖሪያቸው በእውነት አስደናቂ ምልክት ነበራቸው፡፡ ከግራና ከቀኝ ሁለት አትክልቶች ነበሯቸው፡፡

“ፋጢር”
“ፋጢር” فَاطِرِ ማለት “ፈጣሪ” ማለት ሲሆን ሰላሳ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
35፣1 ምስጋና ሰማያትንና ምድርን *ፈጣሪ* فَاطِرِ ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ባለ ሶስት ሶስትም፣ ባለ አራት አራትም ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡
“ያሲን”
* ያ ሲን* يس ማለት ከሃያ ዘጠኙ ሃርፎች ውስጥ ሲሆኑ ሰላሳ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
36:1 * ያ ሲን* يس

“ሷፋት”
“ሷፋት” َٱلصَّٰٓفَّٰت ማለት “መሰለፍ” ማለት ሲሆን ሰላሳ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
37፥1 መሰለፍን وَٱلصَّٰٓفَّٰتِ በሚሰለፉት፡፡

“ሷድ”
“ሷድ” ص ማለት ከሃያ ዘጠኙ ሃርፎች ውስጥ ሲሆን ሰላሳ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
38፡1 ሷድ* ص የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ

“ዙመር”
“ዙመር” الَّذِينَ ማለት “ጭፍሮች” ማለት ሲሆን ሰላሳ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
39 :73 እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ *ጭፍሮች* الَّذِينَ ኾነው ወደ ገነት ይንነዳሉ፡፡

“ጋፊር”
“ጋፊር” غَافِرِ ማለት “መሓሪ” ማለት ሲሆን አርባኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
40:3 ኀጢአትን *መሓሪ* غَافِرِ ፣ ጸጸትንም ተቀባይ፣ ቅጣተ ብርቱ፣ የልግስና ባለቤት ከኾነው (አላህ የወረደ ነው)፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ መመለሻው ወደርሱ ብቻ ነው፡፡

“ፉሲለት”
“ፉሲለት” فُصِّلَتْ ማለት “የተብራሩ” ማለት ሲሆን አርባ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
41።3 አንቀጾቹ *የተብራሩ* فُصِّلَتْ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች (የተብራራ) ነው፡፡

“ሹራ”
“ሹራ” شُورَىٰ ማለት “መመካከር” ማለት ሲሆን አርባ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
42:38 ለእነዚያም የጌታቸውን ጥሪ ለተቀበሉት፣ ሶላትንም ላዘወተሩት፣ ነገራቸውም በመካከላቸው *መመካከር* شُورَىٰ ለኾነው ከሰጠናቸውም ሲሳይ ለሚለግሱት፡፡

“ዙኽሩፍ”
“ዙኽሩፍ” َزُخْرُفًا ማለት “የወርቅ ጌጥንም” ማለት ሲሆን አርባ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
43:35 *የወርቅ ጌጥንም* وَزُخْرُفًا ባደረግንላቸው ነበር፡፡ ይህም ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጣቀሚያ እንጅ ሌላ አይደለም፤ ጠፊ ነው፡፡ መጨረሻይቱም አገር በጌታህ ዘንድ ለጥንቁቆቹ ናት፡፡

“ዱኻን”
“ዱኻን” ِدُخَانٍ ማለት “ጭስ” ማለት ሲሆን አርባ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
44:10 ሰማይም በግልጽ *ጭስ* بِدُخَانٍ የምትመጣበትን ቀን ተጠባበቅ፡፡

“ጃሢያህ”
“ጃሢያህ” جَاثِيَةً ማለት “ተንበርካኪ” ማለት ሲሆን አርባ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
45:28 ሕዝብንም ሁሉ *ተንበርካኪ* جَاثِيَةً ኾና ታያታለህ፡፡ ሕዝብ ሁሉ ወደ መጽሐፏ ትጥጠራለች፡፡ «ዛሬ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ» ይባላሉ፡፡

“አሕቃፍ”
“አሕቃፍ” لْأَحْقَافِ ማለት “አሸዋማ የቦታ ስም ነው”፤ አሕቃፍ አርባ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
46: 21 የዓድንም ወንድም ሁድን ሕዝቦቹን *በአሕቃፍ* بِالْأَحْقَافِ ባስጠነቀቀ ጊዜ አውሳለቸው፡፡

“ሙሐመድ”
“ሙሐመድ” مُحَمَّدٍ “ሰላዋቱል ረቢ አለይሂ ወሰላም” የነብያት መደምደሚያ ናቸው፤ “ሙሐመድ” አርባ ሰባተኛው ሱራህ ሲሆን ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
47:2 እነዚያም ያመኑ፣ በጎዎችንም የሠሩ፣ *በሙሐመድ* مُحَمَّدٍ ላይም የወረደው እርሱ ከጌታቸው ሲኾን እውነት ስለ ኾነ ያመኑ ከእነርሱ ላይ ኃጢአቶቻቸውን ያባብሳል፡፡ ኹኔታቸውንም ሁሉ ያበጃል፡፡

“ፈትህ”
“ፈትህ” فَتْحًا ማለት “መክፈት” ማለት ሲሆን አርባ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
48፣1 እኛ ላንተ ግልጽ የኾነን *መክፈት* فَتْحًا ከፈትንልህ፡፡

“ሑጁራት”
“ሑጁራት” الْحُجُرَاتِ ማለት “ክፍሎች” ማለት ሲሆን አርባ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
49:4 እነዚያ *ከክፍሎቹ* الْحُجُرَاتِ ውጭ ኾነው የሚጠሩህ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

“ቃፍ”
“ቃፍ” ማለት ከሃያ ዘጠኙ ሃርፎች ውስጥ ሲሆን ሃምሳኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
50:1 *ቃፍ* ق በተከበረው ቁርአን እምላለሁ፤

ኢንሻላህ ይቀጥላል…

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርአን ሱራህ

ክፍል አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

“ዛሪያት”
“ዛሪያት” َالذَّارِيَات ማለት “በታኞች” ማለት ሲሆን አምሳ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
51፥1 መበተንን *በታኞች* وَالذَّارِيَاتِ በኾኑት ነፋሶች፡፡

“ጡር”
“ጡር” َالطُّورِ ማለት “የተራራ ስም” ሲሆን አምሳ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
52፥1 *በጡር* وَالطُّورِ እምላለሁ፡፡

“ነጅም”
“ነጅም” النَّجْمِ ማለት “ኮከብ” ማለት ሲሆን አምሳ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
53፥1 *በኮከብ* وَالنَّجْمِ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡

“ቀመር”
“ቀመር” الْقَمَرُ ማለት “ጨረቃ” ማለት ሲሆን አምሳ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
54፥1 ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ *ጨረቃም* الْقَمَرُ ተገመሰ፡፡

“ረሕማን”
“ረሕማን” الرَّحْمَٰنُ ማለት “እጅግ በጣም ሩኅሩህ” ማለት ሲሆን አምሳ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
55፥1 *አል-ረሕማን* الرَّحْمَٰنُ ፤

“ዋቂዓህ”
“ዋቂዓህ” الْوَاقِعَةُ ማለት “መከራይት” ማለት ሲሆን አምሳ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
56፥1 *”መከራይቱ”* الْوَاقِعَةُ በወደቀች ጊዜ፡፡

“ሐዲድ”
“ሐዲድ” الْحَدِيدَ ማለት “ብረት” ማለት ሲሆን አምሳ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
57፥25 መልክተኞቻችንን በግልጽ ማስረጃዎች በእርግጥ ላክን፡፡ ሰዎችም በትክክል ቀጥ እንዲሉ መጽሐፎችንና ሚዛንን ወደእነርሱ አወረድን፤ *ብረትንም* الْحَدِيدَ በውስጡ ብርቱ ኀይልና ለሰዎችም መጠቃቀሚያዎች ያልሉበት ሲኾን አወረድን፡፡

“ሙጃደላህ”
“ሙጃደላህ” ወይም “ጂዳል” جِدَال ማለት “ክርክር” ማለት ሲሆን አምሳ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
58፥1 አላህ የዚያችን በባሏ ነገር *የምተከራከርህን* تُجَادِلُكَ እና ወደ አላህ የምታሰማውን ሴት ቃል በእርግጥ ሰማ፡፡ አላህም በንግግር መመላለሳችሁን ይሰማል፡፡ አላህ ሰሚ ተመልካች ነውና፡፡

“ሐሽር”
“ሐሽር” الْحَشْرِ ማለት “ማውጣት” ማለት ሲሆን አምሳ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
59፥2 እርሱ ያ ከመጽሐፉ ሰዎች እነዚያን የካዱትን ከቤቶቻቸው ለመጀመሪያው *ማውጣት* الْحَشْرِ ያወጣቸው ነው፡፡

“ሙምተሒናህ”
“ሙምተሒናህ” مْتَحِنُوهُنَّ ማለት “ፈታኝት” ማለት ሲሆን ስልሳኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
60፥10 እላንተ ያመናችሁ ሆይ! ምእምናት ስደተኞች ኾነው በመጧችሁ ጊዜ ለሃይማኖት መሰደዳቸውን “ፈትኑዋቸው” فَامْتَحِنُوهُنَّ ፡፡

“ሶፍ”
“ሶፍ” ማለት صَفًّا “ሰልፍ” ማለት ሲሆን ስልሳ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
61፥4 አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ *የተሰለፉ* صَفًّا ኾነው በመንገዱ (በሃይማኖቱ) የሚጋደሉትን ይወዳል፡፡

“ጁሙዓህ”
“ጁሙዓህ” الْجُمُعَةِ ማለት “ስብስብ” ማለት ሲሆን ስልሳ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
62፥9 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *”በዐርብ”* الْجُمُعَةِ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡

“ሙናፊቁን”
“ሙናፊቁን” الْمُنَافِقُونَ ማለት “መናፍቃን” ማለት ሲሆን ስልሳ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
63፥1 *መናፍቃን* الْمُنَافِقُونَ በመጡህ ጊዜ «አንተ የአላህ መልክተኛ መኾንህን በእርግጥ ምለን እንመሰክራለን» ይላሉ፡፡
“ተጋቡን”
“ተጋቡን” التَّغَابُنِ ማለት “መጎዳዳት” ማለት ሲሆን ስልሳ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
64፥9 ለመሰብሰቢያ ቀን የሚሰበስብባችሁን ቀን አስታውሱ፤ ይህ *የመጎዳዳት* التَّغَابُنِ ቀን ነው፡፡

“ጦላቅ”
“ጦላቅ” طَلِّقُوهُنَّ ማለት “ፍቺ” ማለት ሲሆን ስልሳ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
65፥1 አንተ ነቢዩ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው *ፍቱዋቸው* فَطَلِّقُوهُنَّ ፡፡ ዒዳንም ቁጠሩ፡፡

“ተሕሪም”
“ተሕሪም” تُحَرِّمُ ማለት “እርም” ማለት ሲሆን ስልሳ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
66፥1 አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትኾን በአንተ ላይ ለምን *እርም* تُحَرِّمُ ታደርጋለህ? አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው፡፡

“ሙልክ”
“ሙልክ” الْمُلْكُ ማለት “ንግሥና” ማለት ሲሆን ስልሳ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
67፥1 ያ ንግሥና الْمُلْكُ በእጁ የኾነው አምላክ ችሮታው በዛ፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

“ቀለም”
“ቀለም” الْقَلَمِ ማለት “ብርእ” ማለት ሲሆን ስልሳ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
68፥1 ኑን “በብርእ” وَالْقَلَمِ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡

“ሓቃህ”
“ሓቃህ” الْحَاقَّةُ ማለት “እውነት” ማለት ሲሆን ስልሳ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
69፥1 *እውነትን* الْحَاقَّةُ አረጋጋጪቱ (ትንሣኤ)፡፡

“መዓሪጅ”
“መዓሪጅ” الْمَعَارِجِ ማለት “መሰላል” ማለት ሲሆን ሰባኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
70፥3 የሰማያት *መሰላሎች* الْمَعَارِجِ ባለቤት ከኾነው አላህ መላሽ የለውም፡፡

“ኑሕ”
“ኑሕ” نُوحًا ማለት “የአላህ መልእክተኝ” ሲሆን ሰባ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
71፥1 እኛ *ኑሕን* نُوحًا «ሕዝቦችህን አሳማሚ ቅጣት ሳይመጣባቸው በፊት አስጠንቅቅ በማለት ወደ ሕዝቦቹ ላክነው፡፡»

“ጂን”
“ጂን” الْجِنِّ ማለት “ስውራን” ማለት ሲሆን ሰባ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
72፥1 በል «እነሆ *ከጂን* الْجِنِّ የኾኑ ጭፈሮች ቁርአንን አዳመጡ፡፡‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርአን ሰማንም› አሉ ማለት ወደ እኔ ተወረደ፡፡

“ሙዘሚል”
“ሙዘሚል” الْمُزَّمِّل ማለት “ተከናናቢ” ማለት ሲሆን ሰባ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
73፥1 አንተ *ተከናናቢው* الْمُزَّمِّلُ ሆይ፡፡

“ሙደሢር”
“ሙደሢር” الْمُدَّثِّرُ ማለት “ደራቢ” ማለት ሲሆን ሰባ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
74፥1 አንተ ልብስህን *ደራቢው* الْمُدَّثِّرُ ሆይ!

“ቂያማህ”
“ቂያማህ” الْقِيَامَةِ ማለት “ትንሣኤ” ማለት ሲሆን ሰባ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
75፥1 (ነገሩ ከሓዲዎች እንደሚሉት) አይደለም፡፡ *በትንሣኤ* الْقِيَامَةِ ቀን እምላለሁ፡፡

“ደህር”
“ደህር” الدَّهْرِ ማለት “ዘመን” ማለት ሲሆን ሰባ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
76፥1 በሰው ላይ የሚታወስ ነገር ሳይኾን *ከዘመናት* الدَّهْرِ የተወሰነ ጊዜ በእርግጥ አልፎበታል፡፡

“ሙርሰላት”
“ሙርሰላት” َالْمُرْسَلَاتِ ማለት “የተላኩ” ማለት ሲሆን ሰባ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
77፥1 ተከታታይ ኾነው በተላኩት وَالْمُرْسَلَاتِ ፣

“ነበእ”
“ነበእ” النَّبَإِ ማለት “ዜና” ማለት ሲሆን ሰባ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
78፥2 ከታላቁ *ዜና* النَّبَإِ ከቁርአን ይጠያየቃሉ፡፡

“ናዚያት”
“ናዚያት” َالنَّازِعَاتِ ማለት “አውጪዎች” ማለት ሲሆን ሰባ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
79፥1 በኃይል *አውጪዎች* وَالنَّازِعَاتِ በኾኑት፤

“ዐበስ”
“ዐበስ” عَبَسَ ማለት “ማጨፍገግ” ማለት ሲሆን ሰማንያኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
80፥1 ፊቱን *አጨፈገገ* عَبَسَ ፤ ዞረም፡፡

ኢንሻላህ ይቀጥላል…

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርአን ሱራህ

የመጨረሻው ክፍል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

“ተክዊር”
“ተክዊር” ማለት “መጠቅለል” ማለት ሲሆን ሰማንያ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
81፥1 ፀሐይ *”በተጠቀለለች”* ጊዜ፤ إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ

“ኢንፊጣር”
“ኢንፊጣር” ማለት “መሰንጠቅ” ማለት ሲሆን ሰማንያ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
82፥1 ሰማይ *”በተሰነጠቀች”* ጊዜ፤ إِذَا السَّمَاءُ انفَطَرَتْ

“ሙጠፈፊን”
“ሙጠፈፊን” ማለት “ሰላቢዎች” ማለት ሲሆን ሰማንያ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
83፥1 *ለሰላቢዎች* ወዮላቸው፡፡ وَيْلٌ لِّلْمُطَفِّفِينَ

“ኢንሺቃት”
“ኢንሺቃት” ማለት “መቀደድ” ማለት ሲሆን ሰማንያ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
84፥1 ሰማይ *በተቀደደች* ጊዜ፤ إِذَا السَّمَاءُ انشَقَّتْ

“ቡሩጅ”
“ቡሩጅ” ማለት “ፈለካት” ማለት ሲሆን ሰማንያ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
85፥1*የቡርጆች* ባለቤት በኾነችው ሰማይ እምላለሁ፡፡ وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْبُرُوجِ

“ጣሪቅ”
“ጣሪቅ” ማለት “መጪ” ማለት ሲሆን ሰማንያ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
86፥1 በሰማዩ በሌሊት *መጪውም* እምላለሁ፡፡ وَالسَّمَاءِ وَالطَّارِق ِ

“አዕላ”
“አዕላ” ማለት “የበላይ” ማለት ሲሆን ሰማንያ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
87፥1 *”ከሁሉ በላይ* የኾነውን ጌታህን ስም አሞግሥ፡፡ سَبِّحِ اسْمَ رَبِّكَ الْأَعْلَى

“ጋሺያህ”
“ጋሺያህ” ማለት “ሸፋኝቱ” ማለት ሲሆን ሰማንያ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
88፥1 *የሸፋኝቱ* (ትንሣኤ) ወሬ መጣህን? هَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ الْغَاشِيَةِ

“ፈጅር”
“ፈጅር” ማለት “ጎህ” ማለት ሲሆን ሰማንያ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
89፥1 *በጎህ* እምላለሁ፡፡ وَالْفَجْرِ

“በለድ”
“በለድ” ማለት “አገር” ማለት ሲሆን ዘጠናኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
90፥1 በዚህ *”አገር* (በመካ) እምላለሁ፡፡ لَا أُقْسِمُ بِهَٰذَا الْبَلَدِ

“ሸምስ”
“ሸምስ” ማለት “ፀሐይ” ማለት ሲሆን ዘጠና አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
91፥1 *በፀሐይ* እና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡ وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا

“ለይል”
“ለይል” ማለት “ሌሊት” ማለት ሲሆን ዘጠና ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
92፥1 *በሌሊቱ* እምላለሁ (በጨለማው) በሚሸፍን ጊዜ፡፡ وَاللَّيْلِ إِذَا يَغْشَىٰ

“ዱሓ”
“ዱሓ” ማለት “ረፋድ” ማለት ሲሆን ዘጠና ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
93፥1 በረፋዱ እምላለሁ፡፡ وَالضُّحَىٰ

“ኢንሻራህ”
“ኢንሻራህ” ማለት “ማስፋት” ማለት ሲሆን ዘጠና አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
94፥1 ልብህን ለአንተ *አላሰፋንልህምን*? (አስፍተንልሃል)፡፡ أَلَمْ نَشْرَحْ لَكَ صَدْرَكَ

“ቲን”
“ቲን” ማለት “በለስ” ማለት ሲሆን ዘጠና አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
95፥1 *በበለስ* እና በዘይት ወይራ እምላለሁ፡፡ وَالتِّينِ وَالزَّيْتُونِ

“ዐለቅ”
“ዐለቅ” ማለት “የረጋ ደም” ማለት ሲሆን ዘጠና ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
96፥2 ሰውን *ከረጋ ደም* በፈጠረው (ጌታህ ስም)፡፡ خَلَقَ الْإِنسَانَ مِنْ عَلَقٍ

“ቀድር”
“ቀድር” ማለት “ውሳኔ” ማለት ሲሆን ዘጠና ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
97፥1 እኛ (ቁርኣኑን) *በመወሰኛይቱ* ሌሊት አወረድነው፡፡ إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ

“በይናህ”
“በይናህ” ማለት “ግልፅ” ማለት ሲሆን ዘጠና ስምተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
98፥1 እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች ከአጋሪዎቹም የካዱት *ግልጹ* አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት ላይ) ተወጋጆች አልነበሩም፡፡ لَمْ يَكُنِ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ مُنفَكِّينَ حَتَّىٰ تَأْتِيَهُمُ الْبَيِّنَةُ

“ዘልዘላህ”
“ዘልዘላህ” ማለት “መንቀጥቀጥ” ማለት ሲሆን ዘጠና ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
99፥1 ምድር (በኀይል) *መንቀጥቀጥዋን* በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤ إِذَا زُلْزِلَتِ الْأَرْضُ زِلْزَالَهَا

“ዓዲያት”
“ዓዲያት” ማለት “ሩዋጮች” ማለት ሲሆን መቶኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
100፥1 እያለከለኩ *ሩዋጮች* በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡ وَالْعَادِيَاتِ ضَبْحًا

“ቃሪዓህ”
“ቃሪዓህ” ማለት “ቆርቋሪይቱ” ማለት ሲሆን መቶ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
101፥1 *ቆርቋሪይቱ* (ጩኸት)፤ الْقَارِعَةُ

“ተካሱር”
“ተካሱር” ማለት “መፎካከር” ማለት ሲሆን መቶ ሁለተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
102፥1 በብዛት *መፎካከር* (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘነጋችሁ፡፡ أَلْهَاكُمُ التَّكَاثُرُ
“ዐስር”
“ዐስር” ማለት “ጊዜ” ማለት ሲሆን መቶ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
103፥1 በጊዜያቱ እምላለሁ፡፡ وَالْعَصْرِ

“ሁመዛህ”
“ሁመዛህ” ማለት “ሃሜተኛ” ማለት ሲሆን መቶ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
104፥1 *ለሃሜተኛ* ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት፡፡ وَيْلٌ لِّكُلِّ هُمَزَةٍ لُّمَزَةٍ

“ፊል”
“ፊል” ማለት “ዝሆን” ማለት ሲሆን መቶ አምስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
105፥1 *በዝሆኑ* ባለቤቶች ጌታህ እንዴት እንደሠራ አላወቅህምን? أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِأَصْحَابِ الْفِيلِ

“ቁረይሽ”
“ቁረይሽ” ማለት “የጎሳ ስም” ሲሆን መቶ ስድስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
106፥1 *ቁረይሽን* ለማላመድ (ባለዝሆኖቹን አጠፋ)፡፡ لِإِيلَافِ قُرَيْشٍ

“ማዑን”
“ማዑን” ማለት “ትውስታ” ማለት ሲሆን መቶ ሰባተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
107፥7 የዕቃ ትውስታንም (ሰዎችን) የሚከለክሉ ለኾኑት (ወዮላቸው)፡፡ وَيَمْنَعُونَ الْمَاعُونَ

“ከውሰር”
“ከውሰር” ማለት “በጎ ነገር” ማለት ሲሆን በጀነት ውስጥ የሚገኝ ፀጋ ነው፤ ከውሰር መቶ ስምንተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
108፥1 እኛ በጣም ብዙ *በጎ ነገሮችን* ሰጠንህ፡፡ إِنَّا أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ

“ካፊሩን”
“ካፊሩን” ማለት “ከሃዲያን” ማለት ሲሆን መቶ ዘጠነኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
109፥1 በላቸው «እናንተ *ከሓዲዎች* ሆይ! قُلْ يَا أَيُّهَا الْكَافِرُونَ

“ነስር”
“ነስር” ማለት “እርዳታ” ማለት ሲሆን መቶ አስረኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
110÷1 የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤ إِذَا جَاءَ نَصْرُ اللَّهِ وَالْفَتْحُ

“መሰድ”
“መሰድ” ማለት “ጭረታዊ ገመድ” ማለት ሲሆን መቶ አስራ አንደኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
111፥5 በአንገትዋ ላይ ከጭረት የኾነ ገመድ ያለባት ስትኾን፡፡ فِي جِيدِهَا حَبْلٌ مِّن مَّسَدٍ

“ፈለቅ”
“ፈለቅ” ማለት “ተፈልቃቂ” ማለት ሲሆን መቶ አስራ ሶስተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
113፥1 በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ፡፡ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ

“ናስ”
“ናስ” ማለት “ሰዎች” ማለት ሲሆን መቶ አስራ አራተኛው ሱራህ ነው፤ ይህም ስም በዚህ አንቀፅ ይገኛል፦
114፥1 በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ፡፡ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ

መደምደሚያ
2:23 በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ *ከብጤው* مِثْلِهِ አንዲትን ሱራ አምጡ፡፡ እውነተኞችም እንደኾናችሁ ከአላህ ሌላ መስካሪዎቻችሁን ጥሩ፡፡

“ሚስል” مِثْل የሚለው ቃል “ብጤ” አሊያም “መሰል” ማለት ሲሆን ብጤነት ከምን አንጻር? ለአላህ ንግግር ብጤ አምጡ የሚለው ተግዳሮት ለመቋቋም ቁርአንን ቅዱ እና ኮፕይ አድርጉ ማለቱ ሳይሆን ከራሳችሁ ተባብራችሁ የቁርአንን ንግግር መሰረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ አምጡ ማለት ነው፣ አላህ ንግግሩን ለነቢያችን ያወረደው በአረቢኛ ነው።
በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ፣ በፈረንሳይኛ ወዘተ የምናነባቸው የቁርአን ትርጉሞች ቁርአን ሳይሆኑ የቁርአን ትርጉም ናቸው፣ ቁርአን መሰረቱና ውቅሩ፣ ጥልቅቱና ስፋቱ አረቢኛ ነው፣ ይህ የቁርአን አንዱ አይነተኛ ባህርይ ነው፤ “ከላም” كَلَٰم ማለት “ቃል” አሊያም “ንግግር” ማለት ሲሆን ቃል ደግሞ የፊደላት ውቅር ነው፣ “ሃርፍ” حَرف በነጠላ “ፊደል” ማለት ሲሆን “ሁሩፍ” حروف ደግሞ በብዜት “ፊደላት” ማለት ነው፣ በቁርአን አሊፍ፣ ላም፣ ሚም፣ ሷድ፣ ራ፣ ካፍ፣ ሃ፣ ያ፣ ዓይን፣ ጧ፣ ሲን፣ ሐ፣ ቃፍ፣ ኑን ወዘተ እነዚህም በጥቅሉ 29 ሃርፎች ከአላህ ዘንድ የወረዱ የአላህ ንግግር ናቸው፤ የአነዚህ ሆሄያት ጥልቅ ትርጉማቸውን የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፣ እነዚህ ሃርፎች ቁርአን በወረደበት ጊዜ ለአረቦች ተግዳሮት ነበር፣ ይህ የቁርአን ዋልታና ማገር ሲሆን ታምር ነው፦
24፤1 ይህች *ያወረድናት* እና የደነገግናት *ሱራህ* سُورَةٌ ናት፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ፓለቲካ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥48 *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ*፡፡ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّه

ኢሥላም አጠቃላይ የሕይወት ዘይቤ ይዟል፤ ይህም ዘይቤ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዘይቤ ነው። "ፓለቲካ" πολιτικά የሚለው የግሪክ ቃል "ፓሊቲኮስ" πολιτικός ማለት "ዜግነት"citizen" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን "ፓሊስ" πόλις ማለትም "ከተማ" እና "ፓሊተስ" πολίτης ማለትም "ፓሊስይ" ያቀፈ የአስተዳደር ጥበብ ነው፤ በጥንቷ ሄለናዊ ግሪክ ከተማ የምትመራበት ፓሊሲይ ፓለቲካ ይባል ነበር።
በጥቅሉ ፓለቲካ ማለት በፓሊስይ ማለትም በመርሕ ዜጎችም የሚመራ ሥነ-መንግሥት ጥናት ነው፤ ሕገ-መንግሥት"constitution" ማለት ደግሞ የመንግሥት መርሕ፣ ሕግ እና መመሪያ ነው፤ "መንግሥት" አገዛዝ" "ኃይል" "ሥልጣን" በግሪክ "ክራቶስ" κράτος ይባላል፤ "ክራሲ" የሚለው ቃል "ክራቶስ" ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን የመንግሥት ቅርፅ መዳረሻ ቅጥያ ሆኖ ሲመጣ የተለያየ የመንግሥት እርከን ይሆናል፤ ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ፕሉቶ-ክራሲ"
"ፕሉቶ-ክራሲ" ማለት "የሃብት አገዛዝ" ማለት ነው፤ "ፕሉቶስ" πλοῦτος ማለት "ሃብት" ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ ሃብት ያላቸው ሃብታሞች ሃብት ስላላቸው በሃብታቸው የሚገዙበት ሥርዓት ነው፤ ይህ እሳቤ በድህረ ዘመነ አብርሆት ውድቅ ሆኗል።

ነጥብ ሁለት
"አርስቶ-ክራሲ"
"አርስቶ-ክራሲ" ማለት "የልዕልና አገዛዝ" ማለት ነው፤ "አርስቶስ" ἄριστος ማለት "ልዕልና" ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ ልዕልና ያላቸው ልዑላን በልዕልናቸው የሚገዙበት ሥርዓት ነው፤ እኛ ምርጥ ዘር ነን የሚል አቋም አላቸው፤ ይህ እሳቤ በድህረ ዘመነ አብርሆት ውድቅ ሆኗል።

ነጥብ ሥስት
"አውቶ-ክራሲ"
"አውቶ-ክራሲ" ማለት "የኃይል አገዛዝ" ማለት ነው፤ "አውቶስ" αὐτός ማለት "ኃይል" ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ ኃይል ያላቸው ኃያላን በኃይላቸው የሚገዙበት ሥርዓት ነው፤ ይህ እሳቤ በተለይ የሞናርኪስም እሳቤ በሳውዲ፣ በዖማን፣ በሲዊዘርላድ፣ በደቡብ ኮርያ ወዘተ ያለ እሳቤ
ነው፤ ይህ እሳቤ እየወደቀ ነው፤ ቅርብ ቀን ኢንሻላህ ሙሉ ለሙሉ ይወድቃል።

ነጥብ አራት
"ዲሞ-ክራሲ"
"ዲሞ-ክራሲ" ማለት "የሕዝብ አገዛዝ" ማለት ነው፤ "ዴሞስ" δημο ማለት "ሕዝብ" ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ በሕዝብ ምርጫ በተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤት ውስጥ የተመረጠው ሰው የሚገዛበት ሥርዓት ነው፤ ሕገ-መንግሥቱን የሚያረቁት ከአእምሮ አፍልቀው ነው።

ነጥብ አምስት
"ቴክኖ-ክራሲ"
"ቴክኖ-ክራሲ" ማለት "የሙያ አገዛዝ" ማለት ነው፤ "ቴክኖስ" τέχνη ማለት "ሙያ"skill" ወይም "እደ-ሙያ"art" ማለት ነው፤ ይህ አገዛዝ በእያንዳንዱ ሚኒስትሪ ሚኒስቴ መሆን ያለበት የሙያው ባለቤት ነው የሚል እሳቤ ነው፤ ለምሳሌ በጤና ሚኒስትሪ ሜዲካል ያጠና ዶክተር፤ በትምህርት ሚኒስቴር ፔዳጎጂ ያጠና ሚኒስተር፣ በግብርና ሚኒስትሪ ግብርና ያጠና ሚኒስቴር ወዘተ የሚመራበት እሳቤ ነው። "ሚንስትሪ" ማለት "አገልግሎት" ማለት ሲሆን "ሚንስተር" ማለት "አገልጋይ" ማለት ነው፤ ይህ እሳቤ በአንጻራዊ ተመራጭ ነው።

ነጥብ ስድስት ኢስላም የያዘውን ፓለቲካዊ ዘይቤ ቴኦ-ክራሲ ሲሆን ኢንሻላህ በክፍል ሁለት ይህንን እሳቤ እንቀጥላለን...

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ፓለቲካ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥189 *የሰማያትና የምድር ንግሥና ለአላህ ብቻ ነው*፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَلِلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۗ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ነጥብ ሥድስት
"ቴኦ-ክራሲ"
"ቴኦ-ክራሲ" ማለት "የአምላክ አገዛዝ" ማለት ነው፤ "ቴኦስ" θεός ማለት "አምላክ" ማለት ነው፤ በክፍል አንድ ያየናቸው የአገዛዝ ቅርጽ ምክር ቤት ውስጥ ያሉትን ሕገ-መንግሥት የሚያረቁት ከሰው አእምሮ ነው፤ ነገር ግን በቴኦክራሲ ቅርጽ መመሪያው መለኮታዊ ብቻ ነው። "መጅሊስ" مجلس‎ የሚለው የዐረቢኛ ቃል "ሲኖዶስ" σῠ́νοδος የሚለው የግሪክ ቃል ትርጉማቸው "ምክር ቤት"council" ማለት ነው፤ እዚህ ምክር ቤት ውስጥ ሕገ-መንግሥቱ ሸሪዓህ ነው፤ “ሸሪዓህ” شَرِيعَة የሚለው ቃል "ሺርዓህ” شِرْعَة ማለትም "ሕግ" ከሚለው የስም መደብ የመጣ ሲሆን "ትክክለኛ ሕግ" ማለት ነው፦
45፥18 *ከዚያም ከነገሩ ከሃይማኖት "በትክክለኛይቱ ሕግ" ላይ አደረግንህ*፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ الْأَمْرِ
5፥48 *ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን*፡፡ لِكُلٍّ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهَاجًا

አላህ ለሁሉም መልእክተኞች "ሕግ" እና "መንገድ" አድርጓል፤ “መንገድ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሃጅ” مِنْهَاج ማለትም "ፋና" ማለት ሲሆን “መንሃጅ” منہاج የሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ይህ ሕግ የሚዋቀረው ውቅር አራት ሲሆኑ፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ቁርኣን” قرآن‌‎ ማለትም የአላህ ቃል፣
2ኛ. “ሡናህ” سنة የነብያችን"ﷺ" ሰሒህ ሐዲስ፣
3ኛ. “ቂያሥ” قياس‌‎ “ማመጣጠን”Analogy”
4ኛ. “ኢጅማዕ” إجماع‌‎ ማለትም የዐሊሞች ስብስብ ናቸው።
ስለዚህ ፍርድ ከአላህ በወረደው ሕግ ይፈረዳል፦
5፥48 *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ*፡፡ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّه

“ፍረድ” ለሚለው ቃል የተጠቀመበት “ፈሕኩም” فَاحْكُمْ ሲሆን "ሑክም" ለሚለው የግስ መደብ ነው፤ “ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው፤ “አሕካም” أحكام ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ነው፤ በኢስላም “ሕጎች” በአምስት ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فرض ማለትም “የታዘዘ”
2ኛ. “ሙስተሐብ” مستحب” ማለትም “የተወደደ”
3ኛ. “ሙባሕ” مباح ማለትም “የተፈቀደ”
4ኛ. “መክሩህ” مكروه” ማለትም “የተጠላ”
5ኛ. “ሐራም” حرام” ማለትም “የተከለከለ” ናቸው።
“ፊቅህ” فقه ማለት “ጥልቅ መረዳት” ማለት ሲሆን የሥነ-ሕግ ጥናት”the study of law” ነው፤ ሕግ አዋቂ ደግሞ “ፈቂህ” فقيه ይባላል፤ “ፊቅህ” ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ “መረዳት” ማለት ነው፦
6፥98 *"ለሚያወቁ" ሕዝቦች አንቀጾችን በእርግጥ ዘረዘርን*፡፡ قَدْ فَصَّلْنَا الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَفْقَهُونَ

“ሚያወቁ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የፍቀሁነ” يَفْقَهُونَ ሲሆን “ሚረዱ” ማለት ነው። ሙስሊሙ የስልጣን ባለቤቶች ለሆኑት ለአሚሮቻችን ይታዘዛል፤ የሚያወዘግብ ነገር ካለ ወደ አላህ ቁርኣን እና ወደ መልእክተኛው ሐዲስ መረጃ እና ማስረጃ ማግኘት ነው፦
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ መልክተኛው እና *ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ*፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ *የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው መልሱት*፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا

ቀደምት ሰለፎች የስልጣን ባለቤቶች የሆኑትን ኸሊፋዎች ይታዘዙ ነበር። "ኸሊፋህ" خَلِيفَة ማለት "ምትክ" ማለት ሲሆን "ኺላፋህ" خِلافَة ማለት ደግሞ "ተተኪ" ማለት ነው።
ከ 632–661 ድህረ-ልደት"AD" የነበሩት "አል-ኺላፈቱ አር-ረሺዳህ" اَلْخِلَافَةُ ٱلرَّاشِدَة ማለትም "ትክክለኛ ተተኪ" አቡበከር ሲዲቅ፣ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ፣ ዑስማን ኢብኑ ዐፋን እና ዐሊይ ኢብኑ አቡ ጧሊብ ናቸው። ስለ እነርሱ ዘመነ-መግቦት ነብያችን"ﷺ" እንዲህ በትንቢት ይናገራሉ፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 51
ሠፊናህ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ "የነብያዊ ኺላፋህነት ሰላሳ ዓመት ነው፤ ከዚያም አላህ መንግሥትን ለሚሻው ይሰጣል፤ ወይም የእርሱን መንግሥት ለሚሻው ያመጣል፤ ሠዒድም ለሠፊናህ እንደተናገረው፦ "የአቡበከር ኸሊፋነት ሁለት ዓመት፣ ዑመር አስር ዓመት፣ ዑስማን አስራ ሁለት ዓመት፣ ዐሊይ እንዲህና እንዲያ(6 ዓመት) አሰላው*። عَنْ سَفِينَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ خِلاَفَةُ النُّبُوَّةِ ثَلاَثُونَ سَنَةً ثُمَّ يُؤْتِي اللَّهُ الْمُلْكَ - أَوْ مُلْكَهُ - مَنْ يَشَاءُ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ سَعِيدٌ قَالَ لِي سَفِينَةُ أَمْسِكْ عَلَيْكَ أَبَا بَكْرٍ سَنَتَيْنِ وَعُمَرَ عَشْرًا وَعُثْمَانَ اثْنَتَىْ عَشْرَةَ وَعَلِيٌّ كَذَا ‏.‏
እንደሚታወቀው የመጨረሻው ዘመን ጥናት"Eschatology" በኢስላም "አል-አኺሩል ዘማን" لَلْآخِر لَلْزَمَان ይባላል፤ የመጨረሻው ዘመን ምልክቶች በሁለት ይከፈላሉ፤ አንዱ ንዑሣን ምልክቶች ሲሆኑ ሁለተኛ ዐበይት ምልክቶች ናቸው፤ የኺላፋህ ሥርዓት ተመልሶ መምጣት ከንዑሳን ምልክቶች አንዱ ሲሆን በነብያችን"ﷺ" ትንቢት ውስጥ እንዲህ ይነበባል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 14, ሐዲስ 163
ሑደይፋህ ኢብኑል-የማን እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ነብይነት አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በነብይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ይጀመርና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም ዘውዳዊ ንግሥና ቦታውን ይይዝና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም የወንጀለኛ ንግሥና ይነሳልና አላህ እስከፈቀደው ጊዜ ይቆያል፤ ከዚያም በስተመጨረሻም በነብይነት ሚንሃጅ ኺላፋህ ከእንደገና ይመጣል*። فَقَالَ حُذَيْفَةُ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ - صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ -: « تَكُونُ النُّبُوَّةُ فِيكُمْ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةٌ عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا عَاضًّا فَيَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ يَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ مُلْكًا جَبْرِيَّةً فَتَكُونُ مَا شَاءَ اللَّهُ أَنْ تَكُونَ ثُمَّ يَرْفَعُهَا إِذَا شَاءَ أَنْ يَرْفَعَهَا، ثُمَّ تَكُونُ خِلَافَةً عَلَى مِنْهَاجِ النُّبُوَّةِ

የነብያችን"ﷺ" ነብይነት ቆይታው እንደ ጎርጎሮሳውን አቆጣጠር ከ 610-632 ድህረ-ልደት ነበር፤ ከዚያም በነብያችን"ﷺ" ፋና አል-ኺላፈቱ አር-ረሺዳህ ከ 632-631 ድህረ-ልደት ነበር፤ ከዚያ የበኑ ኡመያድ ሥርወ-መንግሥት እና የበኑ ዐባሥ ሥርወ-መንግሥት ዘውዳዊ ንግሥና ሆኖ ከ 661-1258 ድህረ-ልደት ነበር፤ ከዚያም ከ 1258 ድህረ-ልደት እስከ ዘመናችን የነገሥታት ጊዜ ውስጥ ነን፤ ከዚያም ኢንሻላህ በነብያችን"ﷺ" ፋና እንደገና የኺላፋህ ሥርዓት ይመለሳል። ኢንሻላህ በክፍል ሦስት ስለ ሥነ-መንግሥት እናጠቃልላለን፤ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ፓለቲካ

ገቢር ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

25፥26 *እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልራሕማን ብቻ ነው*፡፡ በከሓዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡ الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ لِلرَّحْمَـٰنِ ۚ وَكَانَ يَوْمًا عَلَى الْكَافِرِينَ عَسِيرًا

የኢስላም ሊሂቃን የመጨረሻው ዘመን ጥናት ዘርፈ ብዙ እና መጠነ ሰፊ እንደሆነ ያትታሉ፤ ከእነዚህ ጥናት አንዱ ቴኦክራሲ በትክክል የሚያመጣው መሪ ነው፤ ይህ መሪ የተጸውዖ ስሙ ሙሐመድ ሲሆን የአባቱ ስም አብደሏህ ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 38, ሐዲስ 4
ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ *"ነብዩም"ﷺ" አሉ፦ "ከቀን በስተቀር ከዱንያህ ምንም ባይቀር(ዛዒዳህ በሐዲሱ እንደተናገረው) አላህ ያንን ቀን እስከ ከእኔ ወይም ከአህለል በይት እስከሚነሳው ሰው ድረስ ያረዝመዋል፤ እርሱም ስሙ የእኔን ስም የአባቱ ስም የአባቴ ስም ይሆናል። ምድር በበደል እንደተሞላች በፍትሕ እና በእኩልነት ያስተዳድራል*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ لَوْ لَمْ يَبْقَ مِنَ الدُّنْيَا إِلاَّ يَوْمٌ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ زَائِدَةُ فِي حَدِيثِهِ ‏"‏ لَطَوَّلَ اللَّهُ ذَلِكَ الْيَوْمَ ‏"‏ ‏.‏ ثُمَّ اتَّفَقُوا ‏"‏ حَتَّى يَبْعَثَ فِيهِ رَجُلاً مِنِّي ‏"‏ ‏.‏ أَوْ ‏"‏ مِنْ أَهْلِ بَيْتِي يُوَاطِئُ اسْمُهُ اسْمِي وَاسْمُ أَبِيهِ اسْمَ أَبِي ‏ ‏.‏ زَادَ فِي حَدِيثِ فِطْرٍ

ይህ መሪ የማዕረግ ስሙ ደግሞ አል-መህዲ ይባላል፤ "አል-መህዲ" الْمَهْدِيُّ ማለት "መሪው"The Guided one" ማለት ነው፤ ይህ መህዲ የሚመጣው ከአህለል በይት ነው። "አህለል በይት" أَهْلَ الْبَيْت ማለት "የነብያችን"ﷺ" ቤተሰብ" ማለት ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ  መጽሐፍ 36, ሐዲስ 160
ዐሊይ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አል-መህዲ ከአህለል በይት ነው፤ አላህ በአንድ ሌሊት ያስነሳዋል"*። عَنْ عَلِيٍّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ الْمَهْدِيُّ مِنَّا أَهْلَ الْبَيْتِ يُصْلِحُهُ اللَّهُ فِي لَيْلَةٍ ‏"‏
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 38, ሐዲስ 6
ኡሙ ሠለማህ ከአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሰምታ እንደተረከችው፦ እርሳቸው፦ *"አል-መህዲ ከእኔ ቤተሰብ ነው፤ ከፋጢማህ የዘር-ሃረግ ነው" አሉ*። عَنْ أُمِّ سَلَمَةَ، قَالَتْ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ الْمَهْدِيُّ مِنْ عِتْرَتِي مِنْ وَلَدِ فَاطِمَةَ ‏

ይህ መህዲ ከፋጢማህ የዘር-ሃረግ የሚመጣ ሲሆን ጭቆና እና አምናገነንነት አስወግዶ ምድርን በእኩልነት እና በፍትሕ ምድርን በመሙላት ለሰባት ዓመት ይገዛል፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 38, ሐዲስ 7
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ "አል-መህዲ ከእኔ አብራክ ነው፤ ሰፊ ግንባር የታወቀ አፍንጫ ይኖረዋል፤ ጭቆና እና አምናገነንነት ምድርን እንደተሞላች በእኩልነት እና በፍትሕ ይሞላታል፤ ሰባት ዓመት ይገዛል*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الْمَهْدِيُّ مِنِّي أَجْلَى الْجَبْهَةِ أَقْنَى الأَنْفِ يَمْلأُ الأَرْضَ قِسْطًا وَعَدْلاً كَمَا مُلِئَتْ جَوْرًا وَظُلْمًا يَمْلِكُ سَبْعَ سِنِينَ ‏"‏
ይህ መሪ የመርየምን ልጅ ዒሣን እንዲያሰግድ ይጋብዘዋል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 302
ጃቢ ኢብኑ ዐብደላህ እንደዘገበው፦ "ነብዩ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"ከእኔ ኡማ የሆኑ በእውነት ቢሆን እንጂ አይታገሉም፤ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ያሸንፋሉ። ከዚያም ዒሣ የመርየም ልጅ ይወርዳል፤ መሪያቸውም ዒሣን በሶላት እንዲመራ ይጠይቀዋል፤ ዒሣም፦ "አይሆንም! በመካከላችሁ መሪ አለ" ይላል፤ ይህ ከአላህ ለዚህ ኡማህ ክብር ነው*። أَنَّهُ سَمِعَ جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ، يَقُولُ سَمِعْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ‏ "‏ لاَ تَزَالُ طَائِفَةٌ مِنْ أُمَّتِي يُقَاتِلُونَ عَلَى الْحَقِّ ظَاهِرِينَ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ - قَالَ - فَيَنْزِلُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ صلى الله عليه وسلم فَيَقُولُ أَمِيرُهُمْ تَعَالَ صَلِّ لَنَا ‏.‏ فَيَقُولُ لاَ ‏.‏ إِنَّ بَعْضَكُمْ عَلَى بَعْضٍ أُمَرَاءُ ‏.‏ تَكْرِمَةَ اللَّهِ هَذِهِ الأُمَّةَ ‏"‏ ‏

የመርየምን ልጅ ዒሣም ተመልሶ ሲመጣ የሙስሊሙ መሪ ይሆናል፤ መሪ የሚሆነውም በቁርኣን እና በነብያችን"ﷺ" ሱና መመሪያ ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 300
አቢ ሁረይራ"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በመካከላችሁ የመርየም ልጅ በወረደ ጊዜ እና ሲመራችሁ ምን ታደርጋላችሁ? "*። قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ كَيْفَ أَنْتُمْ إِذَا نَزَلَ ابْنُ مَرْيَمَ فِيكُمْ وَأَمَّكُمْ ‏
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 301
አቢ ሁረይራ"ረ.ዐ" እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በመካከላችሁ የመርየም ልጅ በወረደ ጊዜ እና ሲመራችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ኢብኑ አቢ ዚዕብም አቢ ሁረይራ የዘገበው መሰረት አድርጎ፦ "ሲመራችሁ ምን ታደርጋላችሁ?" ምን ማለት ነው? አለ፤ እኔም ለእኔ አብራራልኝ አልኩኝ፤ እርሱም አለ፦ "በጌታችሁ ተባረከ ወተዓላ መጽሐፍ እና በመልእክተኛው በነብያችሁ"ﷺ" ፈለግ ይመራችኃል" አለ*። أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ كَيْفَ أَنْتُمْ إِذَا نَزَلَ فِيكُمُ ابْنُ مَرْيَمَ فَأَمَّكُمْ مِنْكُمْ ‏"‏ ‏.‏ فَقُلْتُ لاِبْنِ أَبِي ذِئْبٍ إِنَّ الأَوْزَاعِيَّ حَدَّثَنَا عَنِ الزُّهْرِيِّ عَنْ نَافِعٍ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ‏"‏ وَإِمَامُكُمْ مِنْكُمْ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ ابْنُ أَبِي ذِئْبٍ تَدْرِي مَا أَمَّكُمْ مِنْكُمْ قُلْتُ تُخْبِرُنِي ‏.‏ قَالَ فَأَمَّكُمْ بِكِتَابِ رَبِّكُمْ تَبَارَكَ وَتَعَالَى وَسُنَّةِ نَبِيِّكُمْ صلى الله عليه وسلم ‏.‏

ማንኛውም ንጉሥ፣ ኸሊፍህ ወይም አሚር ሟች ነው፤ አላህ ግን በምንነቱ የማይሞት እውነተኛ ንጉሥ ነው፦
20፥114 *እውነተኛው ንጉሥ አላህም ከሓዲዎች ከሚሉት ላቀ*፡፡ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፡፡ «ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ» በል፡፡ فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ ۗ وَلَا تَعْجَلْ بِالْقُرْآنِ مِن قَبْلِ أَن يُقْضَىٰ إِلَيْكَ وَحْيُهُ ۖ وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا

እውነተኛ መንግሥት የአላህ መንግሥት ነው፤ ማንኛው ምድራዊ ንጉሥ ንግሥናው ጅማሬ አለው እንዲሁ ፍጻሜ አለው፤ ግን አላህ ንግሥናው መነሻ የሌለው ቀዳማይ መዳረሻ የሌለው ደኃራይ ነው። “ሙልክ” مُلْك የሚለው ቃል “መሊክ” مَلِك ማለትም “ንጉሥ” ከሚል የስም መደብ የመጣ ሲሆን “ንግሥና” “መንግሥት” ማለት ነው፤ የእርሱ ንግሥና ደግሞ የእርሱ ባህርይ ነው፤ የሰማያትና የምድር ንግሥና ሁሉ በትንሳኤ ቀን እውነተኛ ንጉሥ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይሆናል፦
25፥26 *እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልራሕማን ብቻ ነው*፡፡ በከሓዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው፡፡ الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ لِلرَّحْمَـٰنِ ۚ وَكَانَ يَوْمًا عَلَى الْكَافِرِينَ عَسِيرًا

እንግዲያውስ እውነተኛ ፓለቲካ ቴኦክራሲ ብቻ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
👉🏼የዳዒ ወሂድ ዑመር ለክርስትና ምላሽ እንዲሁም ተጨማሪ ዳዕዋዎች ከኢስላማዊ እውነታ ( fb.com/islamictrueth ) ስብስብ ዳዕዋዎችንበኦዲዮ መልክ እንዲያደምጡ ጀባ ብለኖታል።

👉🏼 ከርዕሶቹ ስር ያሉትን ሊንኮች በመንካት ያድምጡ👇🏼

ስለ አክፍሮተ ሃይላት ሴራቸውን
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2k5mVd2

ተውሂድ በዳዒ ወሂድ ዑመር
P1 http://bit.ly/2jJERsy
P2 http://bit.ly/2jilXwY
P3 http://bit.ly/2jE4uh3
P4 http://bit.ly/2kfBYTz
P5 http://bit.ly/2kGE77Q

ጥያቄ ና መልስ በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2jijzWG

ፈጣሪ ማን ነው በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2jru31t

ሙስሊም ሳትሆኑ አትሙቱ በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2kGNgNH

ተውሂድ ወይስ ተስሊስ በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2kfMBWf

ፈጣሪ ስንት ማንነት በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2kAH76d

ኢየሱስ የቱ ጌታ ነው በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2kGvHBd

አላህ 1 ነው በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2jK4XLZ

የባአላትን ቀን ጠብቀን እንኳን አደረሳችሁ ይባላልን? በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2jJOhEF

ወለድ(ሪባ) በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2kfXqbf

እየሱስ አርጓልን? በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2jJSWGr

አንድ አምላክ ወይስ ስላሴ
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2fLP4Tp

ለተክሉ ተመስገን የተሰጠ መልስ
በዳዒ ወሂድ ዑመር
ክ1 http://bit.ly/2h8XWUt
ክ 2 http://bit.ly/2h8wysq

ሀጀሩል አስወድ the black stone
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2hAxVxq

Q1 ለአደም ቃል አልተገባለትም
Q2 የአላህ ስም በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2hxGED3

ከልጅ ልጅህ ተወልጀ አድንሃለው እና የአላህ ስም በተመለከተ በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2ih7gGE .

ቁርአንና ባይብል አፃፃፉ
በዳዒ ቀሂድ ዑመር
http://bit.ly/2hQaSOz

ሱረቱ ተህሪምና የጎግል ተርጓሚዎች
http://bit.ly/2iIe03c

ያመነ የተጠመቀ ይድናል?
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2itAl1e

አይሁድና ክርስቲያኖች ልዩነታቸው ምንድን ነው በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2ib2vAi

ኢየሱስ
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2iHSPdN

በክርስቶስ እየሱስ ተፈጠርን ኤፌሶን_2_10
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2ikCj6Q
.
የኢሳ ስቅለት መመሳሰል በወንድም
በዳዒ ዋሂድ ዑመር
http://bit.ly/2j7hSqz

ከ1 በላይ ማግባት በኢስላም? ና ከሞት ቡሀላ ሂወት አለ?
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2ieaF84

ቢድዓ ምንድን ነው
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2iHcs6H

እየሱስ ጌታ ነው ሲባል ምን ማለት ነው?
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2j85M5e

እየሱስ የአላህ ባሪያ ነው
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2jiR5Y0

እየሱስ የአላህ ባሪያ ነው
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2gFC9rb

ኢትዩጵያ በመፅሀፍ ቅዱስ
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2jdoA2A

ምንኩስና ቢድዓ (ጭማሪ) ነው
በዳዒ ወሂድ ዑመር
http://bit.ly/2hUcExk

ወደፊት የሚለቀቁ የዳዒ ወሂድ ዑመርን ዳዕዋዎች በተከታዩ ሊንክ ያገኙታል

https://goo.gl/LA9Z8v

⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
For more daawa
on facebook
fb.com/islamictrueth

On wordpress
amharicmp3daawa.wordpress.com

On telegram
https://telegram.me/islamictrueth
በወንድም ወሒድ ዑመር የተዘጋጁ በተለያዩ ጊዜያት ሙስልም ባልሆኑ ወገኖች የተጠየቁ ጥያቄዎች መልሶቻቸው እና ኢስላማዊ አስተምህሮዎችን የሚያገኙበት የዩቱብ ሊንክ

አላህ እና እግዚአብሔር ወሒድ ዑመር https://youtu.be/74sPvupjrqc

ቁርአን የማን ንግግር ነው? ወሒድ ዑመር
https://youtu.be/CLN6JNAHlLY

እውን ዘፍጥረት 18 ስላሴን ያሳያል https://youtu.be/Uc-wHo6KeD0

ስላሴ ምንድን ነው? ወሒድ ዑመር https://youtu.be/F2UstBt5_SA

እየሱስ አብም እግዚአብሔርም አይደለም ወሒድ ዑመር https://youtu.be/lgNY2wY05Vk

የማቴዎስ ወንጌል 28 19:20 ስላሴን ያሳያል ወሒድ ዑመር https://youtu.be/bgtzsNKX_Qg

መስጁዶች ላይ ኮከብና ጨረቃ ለምን ይቀመጣል መች ተጀመረ ወሒድ ዑመር
https://youtu.be/1PKfWCHo_PA

ኦርቶዶክሶች ስለማርያም ያላቸው የተሳሳተ ግንዛቤ ወሒድ ዑመር https://youtu.be/Nl6yaSCbRMY

ተዋህዶ ምንታዌ ወይስ ውላጤ ወሒድ ዑመር https://youtu.be/UgiY8Q7s08A

ሁለተኛው አፅናኝ ወሒድ ዑመር https://youtu.be/RkpWQhHqoVU

ወንጌል ክፍል 1 ወሒድ ዑመር https://youtu.be/Ev5aa0lNFr4

ወንጌል ክፍል 2 ወሒድ ዑመር https://youtu.be/ydT59S4fomw

የአምላክ ስም ማን ነው ወይይት ወሒድ ዑመር
https://youtu.be/NJkzRRwlqcU

በእየሱስ ማንነት ዙሪያ ከክርስቲያ ወገናችን ጋር የተደረገ ውይይት ወሒድ ዑመር
https://youtu.be/YqzvsVjZxbc

አምላክ አንድ እንጅ ሶስት አይደለም ባይብል ምን ይላል? ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/rpgTTY8KPZs

እየሱስ አርጓል! ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/hXufXprUTJk

እየሱስ ጌታ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/kLW-bqYM2-s

ዳኢ ኡስታዝ ወሒድ በአክፍሮት ሀይላት ላይ የሰጠው አስ…: http://youtu.be/DneCHrU-9-s

የመስቀል ደመራ እና ማተብ መችና እንዴት ተጀመረ? ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/l9G0WvIrjdc

አንዱ አምላክ ማን ነው ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/5WTkP6MYMAk

አልፍና ኦሜጋ ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/1ztM22Rpu9A

ኢትዮጵያ በመፅሐፍ ቅዱስ ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/yvhjbIGSFrU

ምንኩስና ቢድአ ( ጭማሪ) ነው ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/2SbBsND0LmY

ከአንድ በላይ ማግባት በኢስላምና ከሞት በኃላ ሕይወት ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/58iZOiwncEI

ኢየሱስ? ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/TW6cHzniDtw

አይሁድና ክርስቲያኖች ልዩነታቸው ምንድን ነው ወሒድ ኡመር: http://youtu.be/YwVrCAKgi7I

ያመነ የተጠመቀ ይድናል ዋሂድ ኡመር: http://youtu.be/75oAUYIt7VA

የተገደሉት የአላህ ነብያት እነማን ናቸው? ዋሂድ ኡመር: http://youtu.be/KP_KxTZnci8

ቁርአንና ባይብል አፃፃፉ ዋሂድ ኡመር: http://youtu.be/2jAytbGLKME

ሐጀሩል አስወድ the black stone ወሂድ ኡመር: http://youtu.be/cOxdifxY4ik

ከልጅ ልጅህ ተወልጀ አድንሃለው እና የአላህ ስም በተመለከተ በ ዋሂድ ኡመር: http://youtu.be/iBeDaT1MBfQ

በኢየሱስ ና በአንዱ አምላክ መካከል ያለው የኑባሬ ልዩነት በ ወንድም ወሂድ …: http://youtu.be/qX6mB7HYick

አንድ አምላክ ወይስ ስላሴ? ዋሂድ ኡመር: http://youtu.be/9rv0fNGOfCY

ለተጨማሪ ትምህርቶች

የፌስቡክ አድራሻችን፦ https://www.facebook.com/Hidayatube/

በቴሌግራም ሒዳያ https://telegram.me/hidayaislam

በቴሌግራም ወሒድ የሃይማኖት ንፅፅር መድረክ https://tttttt.me/yahtam
ቀኖና

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

3፥71 *የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?* يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

“አህለል ኪታብ” أَهْلَ الْكِتَاب ማለት “የመጽሐፉ ሰዎች” “የመጽሐፉ ሕዝብ” “የመጸሐፉ ባለቤት”The People of the Book” ማለት ሲሆን እነዚህም ሕዝቦች አይሁዳውያን እና ክርስቲያኖች ናቸው፤ "ኪታብ" كِتَاب የተባለው ከአላህ የወረደው ወሕይ እና በእጆቻቸው ጽፈው ከአላህ ሳይሆን ከአላህ ነው ብለው ከአላህ ንግግር ጋር የቀላቀሉት የሰው ንግግር ነው፦
2፥79 *ለእነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በእርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለእነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለእነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት ኃጢኣት ወዮላቸው*፡፡ فَوَيْلٌۭ لِّلَّذِينَ يَكْتُبُونَ ٱلْكِتَٰبَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَٰذَا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ لِيَشْتَرُوا۟ بِهِۦ ثَمَنًۭا قَلِيلًۭا ۖ فَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌۭ لَّهُم مِّمَّا يَكْسِبُونَ

የመጽሐፉ ባለቤቶች ከአላህ የወረደውን ንግግር ከሰው ንግግር ቃል ቀላቅለውታል፤ ከዚያም ባሻገር ከአላህ የወረደውንን ንግግር ደብቀውታል፦
3፥71 *የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! እውነቱን በውሸት ለምን ትቀላቅላላችሁ እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ትደብቃላችሁ?* يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تَلْبِسُونَ الْحَقَّ بِالْبَاطِلِ وَتَكْتُمُونَ الْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

እስቲ ይህንን ነጥብ በታሪካዊ ዳራ እንቃኝ፤ በዚህ ምህዋር እና ዐውድ ላይ "ቀኖና" ስንል የዶግማ ተቃራኒ የሆነውን የሚለወጠው ሕግ ወይም ሥርዓት ሳይሆን የቅዱሳን መጽሐፍትን "መለኪያ" ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው። "ቀኖና" የሚለው ቃል የአማርኛችን ቃል "ካኑን" κανών ከሚል ግሪክ ቃል የተገኘ ነው፤ ይህም ቃል "ካና" κάννα ማለት "አሰመረ" "ለካ" ከሚል የኮይኔ ግሪክ ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን "ልኬት" ማለት ነው። አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት"AD" በጀሚኒያ ጉባኤ እንዲሁ ክርስቲያኖች በ 387 ድህረ-ልደት"AD" በካርቴጅ ጉባኤ በመጨመርና በመቀነስ ቀኖና እያሉ ሲያስወጡና ሲያስገቡ ነበር፤ በተለይ የካርቴጅ ጉባኤ መጽሐፍቶችን በሁለት ከፍለው ብሉይ እና አዲስ ብለው አስቀምጠውታል፤ እስቲ ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦