ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.2K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መለኮታዊ እግር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

68፥42 እግር የሚገለጥበትን ከሓዲዎች ወደ መስገድም የሚጠሩበትን እና የማይችሉበት ቀን አስታውስ፡፡ يَوْمَ يُكْشَفُ عَن سَاقٍۢ وَيُدْعَوْنَ إِلَى ٱلسُّجُودِ فَلَا يَسْتَطِيعُونَ

“ሣቅ” سَاق ማለት “እግር” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ የትንሳኤ ቀን ከሓዲዎችን ወደ መስገድ የሚጠራበት እና የማይችሉበት ቀን ነው፤ በተቃራኒው ጌታችን እግሩን ይገልጣል፤ ሁሉም ምእመናንና ምእመናት ይሰግዱለታል፤ ታላቁ ሙፈሲር ኢብኑ ከሲር”ረሒመሁላህ” የኢማም ቡኻርይን ሐዲስ ይዞ ይህንን አንቀጽ በዚህ መልኩ ፈስሮታል፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4919
አቢ ሠዒድ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፤ ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው፦ “ጌታችን እግሩን ይገልጣል፤ ሁሉም ምእመናንና ምእመናት ይሰግዱለታል፤ عَنْ أَبِي سَعِيدٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ سَمِعْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ يَكْشِفُ رَبُّنَا عَنْ سَاقِهِ فَيَسْجُدُ لَهُ كُلُّ مُؤْمِنٍ وَمُؤْمِنَةٍ،

ሚሽነሪዎች ይህንን እሳቤ ይዘው የአላህ እግር ልክ እንደ ፍጡራን እግር ፍጥረታዊ እግር ለማስመሰል ሲዳዱ ይታያል፤ ይህ ስሁት ሙግት ልከክልህ እከክልኝ በሚል ቁጭት ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ፍጥረታዊ እግር ስላለው የግድ አላህንም እንደዛ ለማድረግ ነው፤ ሲጀመር የኢየሱስ እግር አካላዊና ፍጥረታዊ እግር ማለትም ስጋ፣ አጥንት፣ ነርቭ፣ ጅማት እና ጡንቻ ያለው ነው፦
ሉቃስ 7፥38 በስተ ኋላውም *በእግሩ* አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ *እግሩን* ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው *እግሩንም* ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች።
ሉቃስ 7፥44 ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ *ለእግሬ* አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ *እግሬን* አራሰች በጠጕርዋም አበሰች።

ሲቀጥል ይህ እግር በቁመት የሚያድግ ፍጥረታዊ እግር ነው፦
ሉቃስ 2፥52 ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና *በቁመት* በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት *ያድግ* ነበር።

አስቡት የጫማ ቁጥሩ 30, 35, 40, 41, 42 እያለ የሚተልቀው እግሩ ስለሚያድግ ነው።
ሲሠልስ የኢየሱስ እግር እናቱ ማህጸን ውስጥ ከመፈጠሩ በፊት የኢየሱስ እግርን የፈጠረ ፈጣሪ የእራሱ መለኮታዊ፣ አምላካዊ እና መንፈሳዊ እግር አለው፦
ኢሳይያስ 66፥1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም *የእግሬ* መረገጫ ናት፤
መዝሙር 99፥5 አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ *እግሩ* መረገጫ ስገዱ።
ኢሳይያስ 60፥13 *የእግሬንም* ስፍራ አከብራለሁ።
ናሆም 1፥3 እግዚአብሔር በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፥ ደመናም *የእግሩ* ትቢያ ነው።

ፈጣሪ የሚመስለው ምንም ነገር ከሌለ የእርሱን መለኮታዊ እግር ከፍጥረታዊ እግር ጋር ማመሳሰል ነውር ነው፦
ኢዮብ23፥13 እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ *እርሱንስ የሚመስለው* ማን ነው? 
ኢሳይያስ 40፥18 እንግዲህ *ያህዌህን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?*

የፈጣሪ ባህርይ ከፍጡር ባህርይ ጋር ማመሳል ነውር ከሆነ የአላህንም መለኮታዊና አምላካዊ እግር ከፍጥረታዊና ከአካላዊ እግር ጋር ማመሳሰል ነውር ነው፤ አላህ የሚመስለው ምንም ማንም የለም፤ ለእርሱ አንድም ቢጤ የለውም፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
112፤4 *ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም*፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሐጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥26 *ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩት፣ ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱት እና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» ባልነው ጊዜ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

“ሓጅ” حَآجّ ወይንም “ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት”pilgrimage” ማለት ነው፤ “ሐጅ” መደበኛ ዐብይ ጉብኝት ሲሆን “ዑምራ” عُمْرَة ደግሞ መደበኛ ያልሆነ ንዑስ ጉብኝት ነው፦
2፥196 *ሐጅን እና ዑምራንም ለአላህ ሙሉ*፡፡ وَأَتِمُّوا الْحَجَّ وَالْعُمْرَةَ لِلَّه
3፥97 በውስጡ ግልጽ የኾኑ ተዓምራቶች የኢብራሒምም መቆሚያ አለ፡፡ ወደ ውስጡ የገባ ሰው ጸጥተኛ ይኾናል፡፡ ለአላህም በሰዎች ላይ ወደ እርሱ መኼድን በቻለ ሁሉ ላይ *ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው*፡፡ የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው፡፡ فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَّقَامُ إِبْرَاهِيمَ ۖ وَمَن دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا ۗ وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا ۚ وَمَن كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
2፥158 *ሶፋና መርዋ ከአላህ ምልክቶች ናቸው፤ “ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ” ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም*፡፡ إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِن شَعَائِرِ اللَّهِ ۖ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَا

“የጎበኘ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐጀ” حَجَّ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ሐጅ የራሱ ጊዜ አለው፦
2፥89 *ከለጋ ጨረቃዎች መለዋወጥ ይጠየቁሃል፡፡ እነርሱ ለሰዎች ጥቅም ለሐጅም ማወቂያ ጊዜያቶች ምልክቶች ናቸው በላቸው*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْأَهِلَّةِ ۖ قُلْ هِيَ مَوَاقِيتُ لِلنَّاسِ وَالْحَج
2፥197 *ሐጅ ጊዜያቱ የታወቁ ወሮች ናቸው፡፡ በእነርሱም ውስጥ ሐጅን እንዲሠራ ነፍሱን ያስገደደ ሰው በሐጅ ውስጥ ሴትን መገናኘት ማመጽም ክርክርም የለም*፡፡ الْحَجُّ أَشْهُرٌ مَّعْلُومَاتٌ ۚ فَمَن فَرَضَ فِيهِنَّ الْحَجَّ فَلَا رَفَثَ وَلَا فُسُوقَ وَلَا جِدَالَ فِي الْحَج
22፥28 ለእነርሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ *በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ ይመጡልሃል*፡፡ ከእርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡ لِّيَشْهَدُوا۟ مَنَٰفِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا۟ ٱسْمَ ٱللَّهِ فِىٓ أَيَّامٍۢ مَّعْلُومَٰتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّنۢ بَهِيمَةِ ٱلْأَنْعَٰمِ ۖ فَكُلُوا۟ مِنْهَا وَأَطْعِمُوا۟ ٱلْبَآئِسَ ٱلْفَقِيرَ
89፥2 *በዐሥር ሌሊቶችም እምላለው*፡፡ وَلَيَالٍ عَشْرٍۢ

የታወቁ ቀኖች 12ኛ ወር- ዙል-ሒጃህ ላይ የመጀመሪያዎቹ ዐሥሩ ሌሊቶች ናቸው። አላህ በዚህ ወቅት ቤቱን እንዲጎበኙ ያዘዘው ለኢብራሂም ነው፦
22፥27 *አልነውም፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ*፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና፡፡ وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ
22፥26 *ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩት፣ ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱት እና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» ባልነው ጊዜ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

“ለሚዞሩት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሊጧዒፊነ” لِلطَّائِفِينَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ “ጠዋፍ” طَواف የሚለው ቃል “ጧፈ” طَافَ ማለትም “ዞረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዙረት” ማለት ነው፤ ቤቱን በመጎብኘት ሰባት ጊዜ መዞር አምላካችን አላህ ለኢብራሂም የሰጠው ትእዛዝ ነው፦
22፥29 ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላቸውንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፡፡ ስለቶቻቸውንም ይሙሉ፤ *በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ*፡፡ ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ
“ይዙሩ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የጠወፉ” يَطَّوَّفُوا  መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ቤቱን የሚዞሩት ዘዋሪዎች ደግሞ “ጧዒፍ” طَآئِف ይባላሉ፦
2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻ እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ *ወደ ኢብራሂም እና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ”፣ ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን*፡፡ وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

ለኢብራሂም በመጀመሪያ አገናዛቢ መደብ “ቤቴን” የሚለው የሚለው የዓለማቱ ጌታ አላህ እንደሆነ ልብ አድርግ፤ ቁሬሾች በሶፋ እና በመርዋ መካከል ይጎበኙ ስለነበር የአንሷር ሰዎች በዛ ቦታ ጠዋፍ ማድረግ በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረ ሥርዓት አድርገው ያስቡ ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 25, ሐዲስ 129
ዓሲም እንደተረከው፦ *”እኔ አነሥ ኢብኑ ማሊክን”ረ.ዐ”፦ “በሶፋ እና በመርዋ መካከል መዞርን ትጠላ ነበርን? ብዬ ጠየኩት፤ እርሱም፦ አዎ! አላህ፦ “ሶፋና መርዋ ከአላህ ትዕዛዝ መፈጸሚያ ምልክቶች ናቸው፡፡ ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም” የሚለው አንቀጽ እስከሚያወርድ ድረስ በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረ ሥርዓት አርገን እናስብ ነበር*። أَخْبَرَنَا عَاصِمٌ، قَالَ قُلْتُ لأَنَسِ بْنِ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ أَكُنْتُمْ تَكْرَهُونَ السَّعْىَ بَيْنَ الصَّفَا وَالْمَرْوَةِ قَالَ نَعَمْ‏.‏ لأَنَّهَا كَانَتْ مِنْ شَعَائِرِ الْجَاهِلِيَّةِ، حَتَّى أَنْزَلَ اللَّهُ ‏{‏إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِنْ شَعَائِرِ اللَّهِ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلاَ جُنَاحَ عَلَيْهِ أَنْ يَطَّوَّفَ بِهِمَا‏}‌‏.‏

“ኢሕራም” إحرام ማለት ቋንቋዊ ፍቺው “ክልክል” ማለት ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ በሐጅ እና በዑምራ ያለውን የቅድስና ሁኔታ ያመለክታል፤ በኢሕራም ውስጥ የሚገባው ሰው ሙሕሪም” محرم ይባላል። ሙሽሪኮች ሶፋና መርዋ መካከል መናት የሚባለውን ጣዖት አስገብተው ያመልኩ ነበር፣ ይህን የተረዱት የመዲና ሰዎች ኢሕራም የማናት ስም ይመስላቸው ነበር፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 4861
ዑርዋ እንደተረከው፦ *”እኔም ዓኢሻን”ረ.ዐ.” ስለ ሶፋና መርዋ ጠየኳት፤ እርሷም፦ “መናት የምትባለው ጣዖት በሙሸለል ተቀምጦ ነበር፤ ኢሕራም የእርሱ ስም ስለሚመስላቸው በሶፋ እና በመርዋ መካከል ጠዋፍ የማያረጉ ነበሩ። አላህም፦ “ሶፋና መርዋ ከአላህ ትዕዛዝ መፈጸሚያ ምልክቶች ናቸው” የሚለውን አንቀጽ አወረደ፤ ስለዚህ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እና ሙስሊሞች ጠዋፍ ያረጉ ጀመር*። سَمِعْتُ عُرْوَةَ، قُلْتُ لِعَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ فَقَالَتْ إِنَّمَا كَانَ مَنْ أَهَلَّ بِمَنَاةَ الطَّاغِيَةِ الَّتِي بِالْمُشَلَّلِ لاَ يَطُوفُونَ بَيْنَ الصَّفَا وَالْمَرْوَةِ، فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِنْ شَعَائِرِ اللَّهِ‏}‏ فَطَافَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَالْمُسْلِمُونَ‏.‏

ሚሽነሪዎች፦ “ሐጅን የጀመሩት ፓጋን ዐረቦቹ ናቸው” የሚሉት የቡና ወሬ አላቸው። ሐጅ እና በውስጥ ያሉት ቅድመ-ተከተል አምላካችን አላህ ለነቢዩ ኢብራሂ ያዘዘው ሥርዓት እንደሆነ በአንክሮትና በአጽንዖት ከላይ አይተናል፤ ከዘመነ-ጃህሊያህ ሥርዓት ወስዶ ዐቂደቱል ረባንያ በሆነው በዲነል ኢስላም ላይ መጨመር ቢድዓም ሺርክም እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን፤ አላህ ዘንድ ከተጠሉት ክፉ አድራጊዎች ሁለተኛው ከዘመነ-ጃህሊያህ ሥርዓት ወስዶ ዲነል ኢስላም ላይ መጨመር መሆኑን ሐዲሳች ላይ በግልጽና በማያሻማ ተቀምጧል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 87 ሐዲስ 21
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ “ነብዩም፦ “ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”አላህ ዘንድ የተጠሉ ሦስት ሰዎች አሉ፦ አንደኛው ከትክክለኛው ግብረገብ ወጥቶ ክፉ ነገር አድራጊ፣ ሁለተኛው ከዘመነ-ጃህሊያህ ሥርዓት ኢስላም ውስጥ ለማስቀረት የሚፈልግ፣ ሦስተኛው ያለ ሕግ የአንድ ሰው ደም ማፍሰስ የሚፈልግ*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ أَبْغَضُ النَّاسِ إِلَى اللَّهِ ثَلاَثَةٌ مُلْحِدٌ فِي الْحَرَمِ، وَمُبْتَغٍ فِي الإِسْلاَمِ سُنَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ، وَمُطَّلِبُ دَمِ امْرِئٍ بِغَيْرِ حَقٍّ لِيُهَرِيقَ دَمَهُ ‏

አምላካችን አላህ ቤቱን ከሚጎበኙት ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አደም እና ዝርዮቹ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

7፥11 *በእርግጥም ፈጠርናችሁ፡፡ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክት «ለአዳም ስገዱ» አልን*፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ ዲያብሎስ ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَاكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَاكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ لَمْ يَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ

"ኀጢአት" ማለት አበሳ፣ አመፅ፣ አለመታዘዝ፤ ወንጀል፣ ጥፋት ሲሆን አላህ አድርግ ወይም አታድርግ የሚለውን ትእዛዝ መተላለፍ ነው፤ ኀጢአት አለመታዘዝ ከሆነ አደም የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም፦
20፥121 ከእርሷም በሉ፡፡ ለእነርሱም ኀፍረተ ገላቸው ተገለጸች፡፡ ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር፡፡ *"አደምም የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም"*፡፡ فَأَكَلَا مِنْهَا فَبَدَتْ لَهُمَا سَوْءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ ٱلْجَنَّةِ ۚ وَعَصَىٰٓ ءَادَمُ رَبَّهُۥ فَغَوَىٰ

አደምና ሐዋም በሰሩት ስህተት፦ “ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፡፡ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን” በማለት ንስሃ ገብተዋል፤ አላህም ጸጸትን በመቀበል ተመለሰላቸው፤ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፦
7፥23 *«ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፡፡ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ*፡፡ قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ
2፥37 *አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ፡፡ በእርሱ ላይም ጌታው ጸጸትን በመቀበል ተመለሰለት፤ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና*፡፡ فَتَلَقَّىٰ آدَمُ مِن رَّبِّهِ كَلِمَاتٍ فَتَابَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّهُ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ከአደም ወደ ዝርዮቹ የተላለፈ ምንም አይነት የውርስ ኀጢአት የለም። አደምና ሐዋም ለሰሩት ወንጀል ቶብተው አላህ ይቅር ብሏቸዋል። አደምና ሐዋም ባይጸጸቱ ኖሮ ወደፊት በጀሃነም ይቀጡ ነበር፤ ነገር ግን ስለተጸጸቱ አላህ ለተጻቾች ባዘጋጀው ዘላለሚቱ ጀነት ይገባሉ፦
85፥10 እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ *ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አላቸው*፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ

እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አላህ በነብያችም"ﷺ" ዘመን እኛን በሁለተኛ መደብ፦ "በእርግጥም ፈጠርናችሁ፥ ከዚያም ቀረጽናችሁ" ይለናል፤ ከዚያም ከፈጠረንና ከቀረጸን በኃላ፦ "ለመላእክት «ለአዳም ስገዱ» አለ፦
7፥11 *በእርግጥም ፈጠርናችሁ፥ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክት «ለአዳም ስገዱ» አልን*፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ ዲያብሎስ ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَاكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَاكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ لَمْ يَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ

ለአደም እና ለሐዋ ቢሆን ኖሮ በሙተና "ኸለቅናኩማ" خَلَقْنَاكُما "ሰወርናኩማ" صَوَّرْنَاكُما ይሆን ነበር፤ ነገር ግን ከሁለት በላይ እኛን ለማሳየት በጀመዕ "ኸለቅናኩም" خَلَقْنَاكُمْ "ሰወርናኩም" صَوَّرْنَاكُمْ ነው የሚለው፤ ከዚያም ለመላእክት ለአደም ስገዱ አለ፤ ይህንን ከማለቱ በፊት እኛ ተፈጥረን ነበርን? አዎ እኛ የአደም ዘር ሆነን በአብራክ ውስጥ አለን፦
7፥172 *"ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና፦ «ጌታችሁ አይደለሁምን?» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡ «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ፡፡ «በትንሣኤ ቀን ከዚህ ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ፡፡»* وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِن بَنِي آدَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ ۖ قَالُوا بَلَىٰ ۛ شَهِدْنَا ۛ أَن تَقُولُوا يَوْمَ الْقِيَامَةِ إِنَّا كُنَّا عَنْ هَـٰذَا غَافِلِينَ

"ዘሮቻቸው" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዙረየተሁም" ذُرِّيَّتَهُمْ ሲሆን አላህ አደምን በፈጠረ ጊዜ ጀርባውን አበሰው፤ ከጀርባው ሁሉንም ነፍስ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከዝርያው የሚፈጥረውን አወጣ፤ "ጌታችሁ አይደለሁምን? ሲል በነፍሶቻቸው ላይ አስመሰከረባቸው፤ እነርሱም «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3356
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ አደምን በፈጠረ ጊዜ ጀርባውን አበሰው፤ ከጀርባው ሁሉንም ነፍስ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከዝርያው የሚፈጥረውን አወጣ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ مَسَحَ ظَهْرَهُ فَسَقَطَ مِنْ ظَهْرِهِ كُلُّ نَسَمَةٍ هُوَ خَالِقُهَا مِنْ ذُرِّيَّتِهِ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَة

"ዝርያው" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዙረየቲሂ" ذُرِّيَّتِهِ ሲሆን ከእናት እና አባት ከመፈጠራችን በፊት በአደም አብራክ ውስጥ ነበርን፤ አደም በጀነት እያለ በእርሱ አብራክ ውስጥ ዘሩ ነበረ፤ ሲወጣም አብሮ ከጀነት ወጥቷል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 140
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነብዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አደም እና ሙሳ እርስ በእርሳቸው ተሟገቱ፤ ሙሳም፦ "አንተ አደም ያ ዝርያህን ከጀነት ያስወጣህ ነህ። አደምም አለ፦ "አንተ ሙሳ አላህ በመልእክቱ የመረጠክ እና ያናገረክ ነህ፤ ከመፈጠሬ በፊት በተቀደረው ነገር ትወቅሰኛለህን? ያኔ አደም ሙሳን እረታው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ احْتَجَّ آدَمُ وَمُوسَى، فَقَالَ مُوسَى أَنْتَ آدَمُ الَّذِي أَخْرَجْتَ ذُرِّيَّتَكَ مِنَ الْجَنَّةِ‏.‏ قَالَ آدَمُ أَنْتَ مُوسَى الَّذِي اصْطَفَاكَ اللَّهُ بِرِسَالاَتِهِ وَكَلاَمِهِ، ثُمَّ تَلُومُنِي عَلَى أَمْرٍ قَدْ قُدِّرَ عَلَىَّ قَبْلَ أَنْ أُخْلَقَ‏.‏ فَحَجَّ آدَمُ مُوسَى ‏
አደም ጀነት ውስጥ መኖሩ ጊዚያዊ እንጂ ዘላለማዊ አይደለም፤ ምክንያቱም ለዘላለም እንዲኖር ተፈጠረ የሚል አስተምህሮት በኢስላም የለም። ስለዚህ ከገነት መውጣቱ ውጤቱን አላህ ቀድሞውኑ በዕውቀቱ ቀድሮታል። "ዝርያህ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዙረየተከ" ذُرِّيَّتَكَ ሲሆን በአብራኩ ያለው ዘር በምድር ላይ እንዲኖር የቀደረው አላህ ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 390
ሑደይፋህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ተባረክ ወተዓላ ሰዎችን ይሰበስባል፤ አማንያን ጀነት ወደ እነርሱ እስክትቀርብ ድረስ ይቆማሉ፤ ወደ አደም መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ "አባታችን ሆይ! ጀነትን ለእኛ ክፈትልን፤ እርሱም፦ ማነው ከጀነት ያስወጣችሁ የአባታችሁ የአደም ህፀፅ አይደለምን? ያንን ለማድረግ ደረጃዬ አይደለም። የአላህ ወዳጅ ወደሆነ ወደ ልጄ ኢብራሂም መሄዱ የተሻለ ነው*። عَنْ حُذَيْفَةَ، قَالاَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ يَجْمَعُ اللَّهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى النَّاسَ فَيَقُومُ الْمُؤْمِنُونَ حَتَّى تُزْلَفَ لَهُمُ الْجَنَّةُ فَيَأْتُونَ آدَمَ فَيَقُولُونَ يَا أَبَانَا اسْتَفْتِحْ لَنَا الْجَنَّةَ ‏.‏ فَيَقُولُ وَهَلْ أَخْرَجَكُمْ مِنَ الْجَنَّةِ إِلاَّ خَطِيئَةُ أَبِيكُمْ آدَمَ لَسْتُ بِصَاحِبِ ذَلِكَ اذْهَبُوا إِلَى ابْنِي إِبْرَاهِيمَ خَلِيلِ اللَّهِ

አደም በመሳሳቱ ሲወጣ ሰዎች በህልውና ደረጃ ሳይሆን በዘር ደረጃ በእርሱ አብራክ ይኖሩ ነበር። ይህ አገላለጽ ፍካሬአዊ እንጂ እማሪያዊ አይደለም፦
ዕብራውያን 7፥9-10 ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥ *አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤ መልከ ጼዴቅ በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበረና*።

ልብ አድርግ ሌዊ የአብርሃም የልጅ ልጅ ልጅ ነው፤ አብርሃም ለሌዊ ቅድመ-አያት ነው፤ አብርሃም መልከ ጼዴቅን በተገናኘው ጊዜ አልተወለደም አልተፈጠረም። ነገር ግን በአባቱ ወገብ ነበረ፤ ሌዊ በአባቱ ወገብ ሆኖ አስራት በአብርሃም እጅ ለመልከ ጼዴቅ ሰጥቷል። ግን ያ ዘር ቃል በቃል ነበረ እንዴ? አስራትስ ሰጥቷልን? በፍጹም! ይህ ዘር በአብራክ ይኖራል እንጂ ስብዕና ኖሮት አልኖረም ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ የአደም ዘር በአደም አብራክ ውስጥ ተፈጥሮ፣ አብሮ በጀነት ነበረ፣ ሲወጣም አብሮ ወጥቷል፤ ለመውጣቱ መንስኤ አደም ሲሆን ውጤቱ ግን አላህ አስቀድሞ ቀድሮታል። ሌላውን የሚነሳው ጥያቄ ይህ ሐዲስ ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3356
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦.... *አደም ተሳሳተ ዝርያዎችም ተሳሳቱ፣ አደም ረስቷል ዝርያዎችም ረስተዋል፤ አደም በድሏል፤ ዝርያዎችም በድለዋል*። فَجَحَدَ آدَمُ فَجَحَدَتْ ذُرِّيَّتُهُ وَنَسِيَ آدَمُ فَنَسِيَتْ ذُرِّيَّتُهُ وَخَطِئَ آدَمُ فَخَطِئَتْ ذُرِّيَّتُه

ይህ ሐዲስ ላይ አደም እንደሚሳሳት፣ እንደሚረሳ፣ እንደሚበድል ዝርያዎቹም ይሳሳታሉ፣ ይረሳሉ፣ ይበድላሉ ማለት እንጂ በአደም የተነሳ ይሳሳታሉ፣ ይረሳሉ፣ ይበድላሉ የሚል ሽታው የለም። ከዚያ ይልቅ የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፤ ነገር ግን በተውበት ወደ አላህ ከተመለሱ አላህ ይቅር ይላቸዋል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4392
አነሥ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፡፡ ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው"*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏:‏ ‏ "‏ كُلُّ بَنِي آدَمَ خَطَّاءٌ وَخَيْرُ الْخَطَّائِينَ التَّوَّابُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአላህ ቤት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

106፥3 ስለዚህ *የዚህን ቤት ጌታ ያምልኩ*፡፡ فَلْيَعْبُدُوا رَبَّ هَـٰذَا الْبَيْتِ

አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾች ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

አላህ የሚመለክበት ቦታ ደግሞ የእርሱ ቤት እንደሆነ ለማመልከት ለኢብራሂምም፦ “በይቲይ” بَيْتِىَ ማለትም “ቤቴ” በማለት ይናገራል፦
22:26 ለኢብራሂምም፦ *”የቤቱን” ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በእኔ ምንንም አታጋራ፤ ”ቤቴንም”* ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው፣ ”ባልነው ጊዜ አስታውስ”*። وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًۭٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ

አላህ፦ “በእኔ ምንም አታጋራ” ማለቱ አላህ እኔነት ያለው ነባቢ መለኮት መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ይህም ቤቱ በመካ የሚገኝ የመጀመሪያው እና ጥንታዊ ቤት ነው፦
3:96 ለሰዎች *”መጀመሪያ የተኖረዉ ቤት”* ብሩክና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ ሲኾን ያ በበካህ ያለው ነው። إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍۢ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِى بِبَكَّةَ مُبَارَكًۭا وَهُدًۭى لِّلْعَٰلَمِينَ
22፥29 ከዚያም ትርፍ አካላቸውንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፡፡ ስለቶቻቸውንም ይሙሉ፤ *በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ*፡፡ ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ

ይህ ቤት ታላቁ ቤት ስለሆነ “በይተል ሐረም” ْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ ማለትም “የተከበረው ቤት” ይባላል፤ አላህ የሚመለክበት ቤት ስለሆነ “መስጂደል ሐረም” الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ማለት “የተከበረ መስጊድ” ይባላል፦
5፥2 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የአላህ ክልክል ያደረጋቸውን ምልክቶች የተፈቀዱ አታድርጉ፤ የተከበረውንም ወር በመጋደል አትድፈሩ፡፡ ወደ መካ የሚነዱትን መስዋዕትና የሚታበቱባቸውንም ገመዶች ከጌታቸው ችሮታንና ውዴታን ፈልገው *ወደ ተከበረው ቤት* አሳቢዎችንም ሰዎች አትንኩ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تُحِلُّوا۟ شَعَٰٓئِرَ ٱللَّهِ وَلَا ٱلشَّهْرَ ٱلْحَرَامَ وَلَا ٱلْهَدْىَ وَلَا ٱلْقَلَٰٓئِدَ وَلَآ ءَآمِّينَ ٱلْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ يَبْتَغُونَ فَضْلًۭا مِّن رَّبِّهِمْ وَرِضْوَٰنًۭا
2፥149 ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን *ወደ ተከበረው መስጊድ* አግጣጫ አዙር፡፡ وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ

“መሥጂድ” مَسْجِد የሚለው ቃል “ሠጀደ” ማለትም “ሰገደ” سَجَدَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መስገጃ” ማለት ሲሆን “ሡጁድ” سُّجُود ደግሞ “ስግደት” ማለት ነው፤ በምድር ላይ ያሉት መስጊዶች ሁሉ የአላህ ብቻ ናቸው፤ በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አንገዛም፤ ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ እናወድሰዋለን፤ በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ እናጠራለን፦
72፥18 *እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው። በውስጣቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ”* ማለትም፡፡ وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا
24፥36 *አላህ እንድትከበርና ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ አወድሱት፡፡ በውስጧ በጧትና በማታ ለእርሱ ያጠራሉ*፡፡ فِى بُيُوتٍ أَذِنَ ٱللَّهُ أَن تُرْفَعَ وَيُذْكَرَ فِيهَا ٱسْمُهُۥ يُسَبِّحُ لَهُۥ فِيهَا بِٱلْغُدُوِّ وَٱلْـَٔاصَالِ

“ቤቶች” የሚለው ይሰመርበት፤ መስጊዶች ሁሉ የአላህ ቤቶች ናቸው፤መስዋዕቱንና ታላቁ ቤት ንድፉ “አንኳር” ስለሆነ “ከዕባህ” ተብሏል፤ “ከዕባህ” الكعبة ማለት “አንኳር“Cube” ማለት ነው፤ አንኳር “ምልዓት” ነው፤ ምልአት ባለ ሦስት ቅጥ ነው፤ ይህም ቁመት፣ ርዝምት እና ስፋት ነው፦
5፥97 *ከዕባን የተከበረውን ቤት፤* ክልክል የኾነውንም ወር፣ ባለ ምልክቶቹንም መንጋዎች አላህ ለሰዎች መቋቋሚያ አደረገ፡፡ جَعَلَ ٱللَّهُ ٱلْكَعْبَةَ ٱلْبَيْتَ ٱلْحَرَامَ قِيَٰمًۭا لِّلنَّاسِ وَٱلشَّهْرَ ٱلْحَرَامَ وَٱلْهَدْىَ وَٱلْقَلَٰٓئِدَ

ሁላችንም አላህ ባዘዘን መሰረት ቂብላችን ወደዚህ ቤት ነው፤ “ቂብላህ” قِبْلَة የሚለው ቃል “አቅበለ” أَقْبَلَ ማለትም “ተቀጣጨ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “አቅጣጫ”direction” ማለት ነው፤ የትም ቦታ ሆነን ለአንድነት ለአላህ የምንሰግደው ወደ ከዕባህ ነው፦
2፥149 ከየትም ለጉዞ ከወጣህበት ስፍራ ፊትህን *ወደ ተከበረው መስጊድ* አግጣጫ አዙር፡፡ وَمِنْ حَيْثُ خَرَجْتَ فَوَلِّ وَجْهَكَ شَطْرَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ ۖ

”ወደ” ከዕባህ ”ለ” ከዕባህ መስገድ ይለያያል፤ “ወደ” ምድር መስገድ እና “ለ” ምድር መስገድ አንድ ነው? “ለ” እና “ወደ” የተባሉት መስተዋድዶች ትርጉሙን ሁለት ያረጉታል፤ ስግደታችን ”ለ”አላህ ሲሆን አቅጣጫው ”ወደ” ከዕባህ ነው፤ የምናመልከውም ቤቱን ሳይሆን የቤቱን ጌታ አላህን ብቻ ነው፦
106፥3 ስለዚህ *የዚህን ቤት ጌታ ያምልኩ*፡፡ فَلْيَعْبُدُوا رَبَّ هَـٰذَا الْبَيْتِ
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢብሊሥ መልአክ ነበርን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ! ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

“ኢብሊሥ” إِبْلِيس  የሚለው ቃል "በለሠ" بَلَسَ ማለትም "ተስፋ ቆረጠ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተስፋ የቆረጠ" ማለት ነው፥ "ኢብሊሥ” إِبْلِيس  የሚለው ቃል 11 ጊዜ በ 11 ቦታ ከጂን ለሆነ ፍጡር የተሰጠ የግብር ስም ነው፦
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ! ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር። ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ

"ከጂን ነበር" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት "ጂኒ" جِنِّيّ የሚለው ቃል "ጀነ" جَنَّ ማለትም "ሰወረ" "ደበቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስውር" "ድብቅ" ማለት ነው፥ "ጂን" جِنّ ደግሞ የጂኒ ብዙ ቁጥር ነው። ኢብሊሥ ጥንተ ተፈጥሮው ከጂን ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፣ ጃን ከእሳት ነበልባል ተፈጥሯል፣ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል"፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

"ጃን" جَانّ ልክ እንደ "ሰው" ለጂኒዎች ጥቅላዊ ስም ነው፥ መላእክት እና ጃን "ወ" وَ ማለትም "እና" የሚል መስተጻምር መጠቀሙ በራሱ መላእክት እና ጂን ሁለት የተለያዩ ፍጥረታት እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። እዚህ ድረስ ከተግባባን "ኢብሊሥ መልአክ ነበር" ብለው ሚሽነሪዎች የሚሞግቱት በዚህ ጥቅስ ነው፦
17፥61 ለመላእክትም "ለአደም ስገዱ" ባልናቸው ጊዜ አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ

፨ሲጀመር "ለ" የሚለው መስተዋድድ "መላእክት" በሚል መነሻ ቅጥያ ላይ መግባቱ አሏህ "ስገዱ" ያለው "ለመላእክት ብቻ" እንደሆነ ማስረጃ መሆን በፍጹም አይችልም። ይህንን በአንድ ተመሳሳይ ሙግት እንሞግት፦
7፥79 "ለ"-እነርሱም ልቦች አሏቸው፥ ግን አይገነዘቡበትም፣ "ለ"-እነርሱም ዓይኖች አሉዋቸው፥ ግን ዐያዩበትም፣ "ለ"-እነርሱም ጆሮዎች አሉዋቸው ግን አይሰሙበትም፡፡ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا

ዐውዱ ላይ "እነርሱ" የተባሉት "ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፥ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው" የተባሉትን ነው፥ ቅሉ ግን "ለ" የሚለው መስተዋድድ "እነርሱ" በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ መምጣቱ ልቦች፣ ዓይኖች፣ ጆሮዎች አሉዋቸው የተባሉት ዘንጊዎቹ እና የተሳሳቱት ብቻ ናቸው እንደማንል ሁሉ አሏህ "ስገዱ" ያለው ለመላእክት ብቻ ሳይሆን ለኢብሊሥም ጭምር ነው፦
7፥12 አላህ፦ «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ» አለው፡፡قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ

አሏህ ያለው "ባዘዝኳችሁ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" ሳይሆን "ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" ነው፥ "ባዘዝኩህ" የሚለው ኃይለ-ቃል አሏህ ለአደም "ስገድ" ብሎ አዞት እንደነበር ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። "ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ" ማለቱ በራሱ እንዲሰግድ የታዘዙት መላእክት ብቻ አለመሆናቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል፦
18፥50 ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ፡፡ وَإِذْ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ
፨ሲቀጥል "ለመላእክትም ለአደም ስገዱ! ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ! ወዲያውም ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር" በሚል አንቀጽ ውስጥ "ሲቀር" "በቀር" ለሚለው የገባው ቃል "ኢላ" إِلَّا ሲሆን ኢሥቲስናእ ነው። "ኢሥቲስናእ" اِسْتِثْنَاء‏ የሚለው ቃል "ኢሥተስና" اِسْتَثْنَى ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "በስተቀረት"exception" ማለት ነው፥ ኢሥቲስናእ በሁለት ይከፈላል። አንዱ "ኢሥቲስናኡል ሙተሲል" اِسْتِثْنَاء‏ الْمُتَّصِل ሲሆን "ሙተሲል" مُتَّصِل ማለት "የተያያዘ"attached" ማለት ነው፦
43፥67 ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ "ሲቀሩ"፡፡ الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢላ" إِلَّا የሚለው ኢሥቲስናኡል ሙተሲል ስለሆነ ተመሳሳይ ጥንተ ተፈጥሮን ያሳያል፥ ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት የሚሆነው እና አሏህን ፈሪዎች ጥንተ ተፈጥሯቸው ተመሳሳይ ነው። ተጨማሪ ይህንን ጥቅስ መመልከት ይቻላል፦
103፥2 ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው፡፡ إِنَّ الْإِنسَانَ لَفِي خُسْرٍ
103፥3 እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት፣ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ "ሲቀሩ"፡፡ إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَتَوَاصَوْا بِالْحَقِّ وَتَوَاصَوْا بِالصَّبْرِ

ሁለተኛው ደግሞ "ኢሥቲስናኡል ሙንቀጢዕ" اِسْتِثْنَاء‏ الْمُنقَطِع ሲሆን "ሙንቀጢዕ" مُنقَطِع ማለት "ያልተያያዘ"detached" ማለት ነው፦
26፥77 «እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፥ ግን የዓለማት ጌታ "ሲቀር"»፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ

ኢብራሂም "እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው" ያላቸው እና "ሲቀር" ያለው "የዓለማት ጌታ" ሁለት የተለያዩ ኑባሬዎች እንደሆኑ ሁሉ በተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር "መላእክት" እና "ኢብሊሥ" ሁለት የተለያዩ ኑባሬዎች ናቸው። በተጨማሪ አንድ ጥቅስ እንመልከት፦
17፥67 በባሕሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛችሁ ጊዜ የምትጠሩዋቸው ሁሉ ይጠፋሉ፥ እርሱ(አላህ) "ሲቀር"፡፡ وَإِذَا مَسَّكُمُ الضُّرُّ فِي الْبَحْرِ ضَلَّ مَن تَدْعُونَ إِلَّا إِيَّاهُ

ጣዖታዊያን በባሕሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛቸው ጊዜ የሚጠሩዋቸው ጣዖታታት የሰው እጅ ሥራዎች ሲሆኑ ይጠፋሉ፥ አሏህ ግን ሕያው ፈጣሪ ስለሆነ አይጠፋም። ስለዚህ "በቀር" "በስተቀር" ስለተባለ ዐውዱ እና አጠቃላይ አሳቡ ሳይታይ "አንድ ምድብ ነው" ማለት ስህተት እንዳለው ከተረዳን ዘንዳ "በቀር" ስላለ ኢብሊሥን የመላእክት ጥንተ ተፈጥሮ ውስጥ ማካተት ስህተት ነው።
ኢብሊሥ ከጂን እንጂ ከመላእክት አለመሆኑ ሐሠን አል-በስሪይ እንደተናገረው በኢብኑ ጀሪር ተተርኳል፥ በኢሥናዱም ሶሒሕ ነው። ኢብኑ ከሲር በመቀጠል በተፍሢሩ ላይ አድ-ደሓክ፣ ሠዒድ ኢብኑ ጀቢር፣ ኢብኑ ኢሥሐቅ ወዘተ "ኢብሊሥ መልአክ ነበር" ያሉት ከኢሥራዒልያት ትርክት እንደሆነ ተናግሯል፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 18፥50
"ሐሠን አል-በስሪይ እንደተናገረው፦ "ኢብሊሥ ከመላእክት አይደለም፥ ለአንዲት ቅጽበት እንኳን አልነበረም። ልክ አደም"ዐ.ሠ." ለሰው ሥረ-መሠረት እንደሆነ ሁሉ ኢብሊሥም ለጂን ሥረ-መሠረት ነው"። ይህ በኢብኑ ጀሪር ተተርኳል፥ በኢሥናዱም ሶሒሕ ነው። قال الحسن البصري : ما كان إبليس من الملائكة طرفة عين قط ، وإنه لأصل الجن ، كما أن آدم ، عليه السلام ، أصل البشر . رواه ابن جرير بإسناد صحيح
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 18፥50
"በእርግጥ በዚህ ሪዋያህ ከቀደምቶቹ የተተረከው ዘገባ አብዛኛውን ከኢሥራኢልያት እንደሆነ ይጤናል"። وقد روي في هذا آثار كثيرة عن السلف ، وغالبها من الإسرائيليات التي تنقل لينظر فيها

፨ሢሰልስ መላእክት የተፈጠሩበት ንጥረ ነገር ብቻ ሳይሆን ባሕርያቸውም ይለያል፥ መላእክት ፆታ የላቸውም፦
43፥19 "መላእክትንም እነርሱ የአልረሕማን ባሮች የኾኑትን ሴቶች አደረጉ"፡፡ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትጻፋለች፡፡ ይጠየቃሉም፡፡ وَجَعَلُوا الْمَلَائِكَةَ الَّذِينَ هُمْ عِبَادُ الرَّحْمَـٰنِ إِنَاثًا ۚ أَشَهِدُوا خَلْقَهُمْ ۚ سَتُكْتَبُ شَهَادَتُهُمْ وَيُسْأَلُونَ
37፥150 ወይስ እኛ እነርሱ የተጣዱ ሆነው "መላእክትን ሴቶች አድርገን ፈጠርን? أَمْ خَلَقْنَا الْمَلَائِكَةَ إِنَاثًا وَهُمْ شَاهِدُونَ

ከመላእክት መካከል ሴቶች ቢኖሩ ኖሮ ቁሬሾች፦ "መላእክት ሴቶች ናቸው" ማለታቸውን አይቃወምም ነበር፥ አሏህ መላእክትን ሴቶች አድርጎ አልፈጠረም። ጂኒዎች ግን ጾታ አላቸው፥ ዝርያ ስላላቸው የሚራቡ ወንድ እና ሴት ናቸው፦
18፥50 "እርሱን እና ዘሮቹን እነርሱ ለእናንተ ጠላቶች ሲኾኑ ከእኔ ላይ ረዳቶች አድርጋችሁ ትይዛላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ! أَفَتَتَّخِذُونَهُ وَذُرِّيَّتَهُ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِي وَهُمْ لَكُمْ عَدُوٌّ ۚ بِئْسَ لِلظَّالِمِينَ بَدَلًا
72፥6 እነሆም "ከሰዎች የኾኑ ወንዶች በጂኒ ወንዶች ይጠበቁ ነበሩ"፡፡ ኩራትንም ጨመሩዋቸው፡፡  وَأَنَّهُ كَانَ رِجَالٌ مِّنَ الْإِنسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٍ مِّنَ الْجِنِّ فَزَادُوهُمْ رَهَقًا
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 312
ዘይድ ኢብኑ አርቀም እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ቆሻሻ ቦታዎች በሰይጣናት ይጎበኛሉ፥ ከእናንተም ወደዚያ ሲገባ፦ "አሏህ ሆይ! ከወንድ እና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለው" ይበል። عَنْ زَيْدِ بْنِ أَرْقَمَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ هَذِهِ الْحُشُوشَ مُحْتَضَرَةٌ فَإِذَا دَخَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْخُبُثِ وَالْخَبَائِثِ ‏”‏ ‏.‏
ኢብሊሥ ከጂን ስለሆነ አሏህን የማመጽ እና የመታዘዝ ነጻ ፈቃድ ስላለው በጌታው ላይ አምጾ ኮራ፥ መላእክት ግን የማመጽ እና የመታዘዝ ነጻ ፈቃድ ስለሌላቸው በባሕያቸው ውስጥ ኩራትና አመጽ የለም። አሏህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፥ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፦
38፥74 ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር፡፡ "ኮራ"፤ ከከሓዲዎቹም ሆነ፡፡ إِلَّا إِبْلِيسَ اسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ
16፥49 "እነርሱም አይኮሩም" وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ
21፥19 እርሱ ዘንድ ያሉትም መላእክት እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ አይሰለቹምም፡፡ وَمَنْ عِندَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
66፥6 አላህ ያዘዛቸውን ነገር በመጣስ አያምጹም፤ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡ لَّا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ

፨ሲያረብብ መላእክት በአሏህ ላይ አምጸው የሚገቡበት ጀሀነም ሆነ ታዘው የሚገቡበት ጀነት የለም። ጂኒዎች ግን በምርጫቸው አምነው ጀነት ወይም ክደው ጀሀነም መግባት ይችላሉ፦
11፥119 የጌታህም ቃል፦ "ገሀነምን ከጂኒዎ እና ከሰዎች ሁሉ በእርግጥ እሞላታለሁ" በማለት ተፈጸመች። وَتَمَّتْ كَلِمَةُ رَبِّكَ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ
55፥45 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَان
55፥46 በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሁለት ገነቶች አሉት፡፡ وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ

ሱረቱር ረሕማን ዐውዱ ላይ ያሉት ሰው እና ጃን ናቸው፥ "ጌታችሁ" የሚለው ቃል "ረቢኩማ" رَبِّكُمَا ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙሰና ሰውን እና ጃንን ያመለክታል። “ታስተባብላላችሁ” የሚለው ቃል “ቱከዚባኒ” تُكَذِّبَانِ ሲሆን ሁለተኛ መደብ ሙሰና ሰውን እና ጃንን ያመለክታል፦
55፥14 ሰውን እንደ ሸክላ ከሚቅጨለጨል ደረቅ ጭቃ ፈጠረው፡፡ خَلَقَ الْإِنسَانَ مِن صَلْصَالٍ كَالْفَخَّارِ
55፥15 "ጃንንም ከእሳት ከኾነ ነበልባል ፈጠረው"፡፡ وَخَلَقَ الْجَانَّ مِن مَّارِجٍ مِّن نَّارٍ

የትንሳኤ ቀን ለሁለቱም የተቀጠረ ቀጠሮ ነው፥ የዚያን ቀን የተውበት በር ስለተዘጋ ሰው ሆነ ጂን ከኃጢኣቱ አሏህን ይቅርታ እንዲጠይቅ አይጠየቅም። ከዛ ይልቅ "የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስጠነቅቋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልእክተኞች አልመጧችሁምን" በመባል ፍርድ ያገኛሉ፦
44፥40 የመለያው ቀን ለሁሉም ቀጠሯቸው ነው፡፡ إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ مِيقَاتُهُمْ أَجْمَعِينَ
55፥39 በዚያም ቀን ሰው እና ጃን ከኃጢኣቱ ገና አይጠየቅም፡፡ فَيَوْمَئِذٍ لَّا يُسْأَلُ عَن ذَنبِهِ إِنسٌ وَلَا جَانٌّ
6፥130 የጂኒዎች እና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ! አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስጠነቅቋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልእክተኞች አልመጧችሁምን? ይባላሉ፡፡ يَا مَعْشَرَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ أَلَمْ يَأْتِكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي وَيُنذِرُونَكُمْ لِقَاءَ يَوْمِكُمْ هَـٰذَا

ለጂኒዎች ጀነት እና ጀሃነም እንዲሁ የትንሳኤ ቀን ቀጠሮ እንዳላቸው እና የተፈጠሩበት አላማ ካየን ዘንዳ በነጻ ምርጫቸው አምነው ሙሥሊም አልያም ክደው ኩፋር የመሆን ምርጫ አላቸው፦
72፥14 «እኛም ከእኛ ውስጥ ሙሥሊሞች አሉ፡፡ ከእኛም ውስጥ በዳዮች አሉ፡፡ የሠለሙም ሰዎች እነዚያ ቅንን መንገድ መረጡ፡፡» وَأَنَّا مِنَّا الْمُسْلِمُونَ وَمِنَّا الْقَاسِطُونَ ۖ فَمَنْ أَسْلَمَ فَأُولَـٰئِكَ تَحَرَّوْا رَشَدًا

ስለዚህ "ኢብሊሥ መልአክ ነበር" የሚለው ትርክት ቁርኣን ላይ ሆነ ሐዲስ ላይ የለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቁርአን ኢየሱስን ብቻ ንጹህ ይለዋልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

19:19 ፦ እኔ *ንጹሕን* زَكِيًّا ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ፣ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ አላት።

መግቢያ
ብዙ ሚሽነሪዎች ይህ ጥቅስ ተመርኩዘው የኢየሱስን ልዩ መሆን አሊያም አምላክ መሆን ያሳያል ብለው እንደ በቀቀን ሲደጋግሙት ይሰማል፣ ዘኪይ زَكِيّ የሚለው ቃል *ንጹሕ* ማለት ሲሆን ይህም ቃል ለኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሰዎችም ጥቅም ላይ ውሏል፦

አንደኛ ለየሕያህ፦
19:13 ከኛም የኾነን ርኅራኄ፣ ንጽሕናንም وَزَكَاةً፤ ጥንቁቅም ነበር።

ሁለተኛ ለወጣቱ ልጅ፦
18:74 ወርደው ተጓዙም፤ ወጣትንም ልጅ ባገኙና በገደለው ጊዜ ያለ ነፍስ መግደል ንጹሕን زَكِيَّةً ነፍስ ገደልክን? በእርግጥ መጥፎ ነገር ሠራህ አለው።
18:81 ጌታቸውም በንጹሕነት زَكَاةً ከርሱ በላጭን፣ በእዝነትም ከርሱ በጣም ቀራቢን ልጅ ሊለውጥላቸው ፈለግን።

ሶስተኛ ለአህለል ጀና፦
20:76 ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ አሏቸው፤ ይህም የተጥራራ تَزَكَّىٰ ሰው ምንዳ ነው።
87:14 የተጥራራ تَزَكَّىٰ ሰዉ በእርግጥ ዳነ፤

ዘኪይ زَكِيّ *ንጹሕ* ማለት ልዩ መሆንን አሊያም አምላክ መሆንን ካሰኘ ለምን ከላይ የተዘረዘሩት ሰዎች ልዩና አምላክ አልሆኑም? ከቁርአኑ በተቃራኒው ባይብሉ ከሴት የተወለደ ንጹህ ሊሆን አይችልም ብሎ ይሞግታል፣ እንኳን ከሴት የተወለደ ብስብስ የሆነ ሰውና ትልም የሆነ የሰው ልጅ ይቅርና ሰማያት፣ ከዋክብት፣ መላእክት ንጹሃን እንዳልሆኑ ይነግረናል፦
ኢዮብ 25:4-6 ከሴትስ የተወለደ *ንጹሕ* ይሆን ዘንድ እንዴት ይችላል? እነሆ፥ ጨረቃ እንኳ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ *ንጹሐን* አይደሉም። ይልቁንስ ብስብስ የሆነ ሰው፥ ትልም የሆነ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!
ኢዮብ 14:1 *ከሴት የተወለደ* ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ መከራም ይሞላዋል።
ኢዮብ 14:4 *ከርኩስ ነገር ንጹሕን* ሊያወጣ ማን ይችላል?
ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድር ነው?
ኢዮብ 14:14-15 ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድር ነው? እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም፤ ሰማያትም በፊቱ *ንጹሐን* አይደሉም።
ኢዮብ 4:17-18 በውኑ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን፥ ወይስ ሰው በፈጣሪው ፊት *ሊነጻ* ይችላልን? እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም፤ መላእክቱንም *ስንፍና* ይከስሳቸዋል፤

በባይብሉ መስፈርት መሰረት ታዲያ ከሴት የተወለደ ብስብስ የሆነ ሰውና ትልም የሆነ የሰው ልጅ ንጹህ ካልሆነ ኢየሱስም ንጹህ አይደለም ማለት ነው፣ ምክንያቱም ኢየሱስ ከሴት የተወለደ ሰውና የሰው ልጅ ነው፦

አንደኛ ከሴት የተወለደ ነው፦
ገላትያ 4:4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር *ከሴት የተወለደውን* ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤

ሁለተኛ ሰው ነው፦
ዮሐንስ 8:40 ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን *ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤ አብርሃም እንዲህ አላደረገም።
የሐዋርያት ሥራ 2:22 የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ *ሰው* ነበረ፤
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 25 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም *ሰው* የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤

ሶስተኛ የሰው ልጅ ነው፦
ማቴዎስ 11፥19 *የሰው ልጅ* እየበላና እየጠጣ መጣ፥ እርሱም፦ እነሆ፥ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ ይሉታል።
ዮሐንስ 5፥27 *የሰው ልጅም* ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው።
ዮሐንስ 13፥31 ኢየሱስ እንዲ አለ፦ አሁን *የሰው ልጅ* ከበረ እግዚአብሔርም ስለ እርሱ ከበረ፤

ወሰላሙ አለይኩም
ነቢይነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥79 *ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠው* እና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፡፡ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِّي مِن دُونِ اللَّهِ

“ነቢይ” نَبِيّ የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሩቅ ወሬ አውሪ” ማለት ነው፥ አላህ የሚሰጠው "ነቢይነት" ደግሞ "ኑቡዋህ" نُبُوَّة ይባላል፦
3፥79 *ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠው* እና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፡፡ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِّي مِن دُونِ اللَّهِ

ይህ ለአንድ ነቢይ የሚሰጠው ነቢይነት የተጠናቀቀው በመጨረሻው ነቢይ በነቢያችን”ﷺ” ነው፥ ነብያችን”ﷺ” የነቢያት ሁሉ መደምደሚያ ናቸው፦
33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም፤ ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና *”የነቢያት መደምደሚያ ነው*፥ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

በተለያየ ጊዜ የሚመጡት የአላህ ነብያት ከኣደም ጀምሮ ተከታታይ ግህደተ-መለኮት ይወርድላቸው ነበር፥ እንዲሁ አላህ የወሰነላቸው የራሳቸው ዘመነ-መግቦትም ነበራቸው። ነገር ግን አንድ ዕድገት ጅማሬ እና ድምዳሜ እንዳለው ሁሉ ነብይነትም በኣደም ተጀምሮ በነብያችን”ﷺ” ተጠናቋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 91, ሐዲስ 9
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ከነቢይነት የተቋጨ የለም ከሙበሺራት በስተቀር። እነርሱም፦ "ሙበሺራት ምንድን ናት? አሉ። እርሷቸውም፦ "መልካም ሕልም ናት" አሉ"*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ لَمْ يَبْقَ مِنَ النُّبُوَّةِ إِلاَّ الْمُبَشِّرَاتُ ‏"‌‏.‏ قَالُوا وَمَا الْمُبَشِّرَاتُ قَالَ ‏"‏ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነብይነት ተዘግቷል፥ ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነቢይም የለም። አነሥም፦ "ሰዎችም ስለዚያ ጉዳይ አጢነው ነበር" አለ። እርሳቸውም፦ "ሙበሺራት ትሆናለች" አሉ። እነርሱም፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ሙበሺራት ምንድን ናት? አሉ። እርሳቸውም፦ "የሙሥሊም ሕልም፥ እርሷም ከነቢይነት ክፍል ናት" አሉ"*። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ ‏"‏ ‏.‏ قَالَ فَشَقَّ ذَلِكَ عَلَى النَّاسِ فَقَالَ ‏"‏ لَكِنِ الْمُبَشِّرَاتُ ‏"‏ ‏.‏ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ وَمَا الْمُبَشِّرَاتُ قَالَ ‏"‏ رُؤْيَا الْمُسْلِمِ وَهِيَ جُزْءٌ مِنْ أَجْزَاءِ النُّبُوَّةِ

"ሪሳላህ" رِسَالَة ማለት "መልእክት" ማለት ሲሆን "ረሱል" رَسُول ማለት ደግሞ "መልእክተኛ" ማለት ነው። ለነቢይ የሚሰጠው ነቢይት እንደተዘጋ ሁሉ ለመልእክተኛ የሚሰጥ መልእክትም ተዘግቷል። ከነቢያችን”ﷺ” በኃላ የሚመጣ ነቢይ ሆነ የሚላክ መልእክተኛ እንደሌለ ነቢያችን”ﷺ” እዚህ ሐዲስ ላይ ፍርጥ አርገው እንቅጩን ነግረውናል። ነቢይነት ቢዘጋም ሙበሽራት ግን አለ፥ "ሙበሺራት" مُبَشِّرَات ማለት የሙሥሊም ሕልም ነው። የሷሊሕ ሙሥሊም መልካም ሕልም ከአርባ ስድስቱ የኑቡዋህ ክፍል አንዱ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 91, ሐዲስ 2
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *"የሷሊሕ ሰው መልካም ሕልም ከአርባ ስድስቱ የነቢይነት ክፍል አንዱ ነው"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ الرُّؤْيَا الْحَسَنَةُ مِنَ الرَّجُلِ الصَّالِحِ جُزْءٌ مِنْ سِتَّةٍ وَأَرْبَعِينَ جُزْءًا مِنَ النُّبُوَّةِ
መልአኩ ጂብሪል ወደ ነቢያችን”ﷺ” ከመምጣቱ በፊት ነቢያችን”ﷺ” ወሕይ በሕልም ይመጣላቸው ነበር፥ ይህም የእርሳቸው ሕልም ቆይታ 6 ወር ሲሆን የነቢይነት አንድ ክፍል ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 1 , ሐዲስ 3
የምእመናት እናት ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ *"በእንቅልፍ ውስጥ ለአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ከወሕይ መጀመሪያ ልክ እንደ ጎህ ንጋት ግልጽ ብሎ መልካም ሕልም ቢሆን እንጂ አይመጣላቸው ነበር። ከዚያም በራሳቸው መገለልን ይወዱ ነበር፥ በሒራእ ዋሻ ውስጥ ይገለሉ እና ቀጥ ይሉ ነበር። እርሳቸውም ቤተሰባቸውን ለማየት ከመፈለጋቸው በፊት ለብዙ ቀናት በተከታታይ አላህን ያመልኩ ነበር፥ ለቆይታም የጉዞ ምግብ ይይዙ ነበር። በሒራእ ዋሻ ሐቁ ወደ እሳቸው እስኪመጣላቸው ድረስ ወደ ባለቤታቸው(ኸዲጃህ) በመመለስ እንደዚሁ በድጋሚ ምግባቸውን ይወስዱ ነበር። ከዚያም መልአኩ ወደ እርሳቸው መጥቶ፦ "ኢቅራእ" አላቸው"*። عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ الْمُؤْمِنِينَ، أَنَّهَا قَالَتْ أَوَّلُ مَا بُدِئَ بِهِ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِنَ الْوَحْىِ الرُّؤْيَا الصَّالِحَةُ فِي النَّوْمِ، فَكَانَ لاَ يَرَى رُؤْيَا إِلاَّ جَاءَتْ مِثْلَ فَلَقِ الصُّبْحِ، ثُمَّ حُبِّبَ إِلَيْهِ الْخَلاَءُ، وَكَانَ يَخْلُو بِغَارِ حِرَاءٍ فَيَتَحَنَّثُ فِيهِ ـ وَهُوَ التَّعَبُّدُ ـ اللَّيَالِيَ ذَوَاتِ الْعَدَدِ قَبْلَ أَنْ يَنْزِعَ إِلَى أَهْلِهِ، وَيَتَزَوَّدُ لِذَلِكَ، ثُمَّ يَرْجِعُ إِلَى خَدِيجَةَ، فَيَتَزَوَّدُ لِمِثْلِهَا، حَتَّى جَاءَهُ الْحَقُّ وَهُوَ فِي غَارِ حِرَاءٍ، فَجَاءَهُ الْمَلَكُ فَقَالَ اقْرَأْ‏

በእንቅልፍ ከመልካም ሕልም ጅማሬ እስከ ጂብሪል ቁርኣንን "ኢቅራእ" ማለት ድረስ ስድስት ወር ያክል ነበር፦
የኢብኑ ሐጀሩል አሥቀላኒ ፈተሑል ባሪ ፊ ሸርህ ሰሒሑል ቡኻርይ መጽሐፍ 91, ሐዲስ 1 ኪታቡ አት-ተዕቢር ባብ 2
"አሏህ ወደ ነቢዩ ለስድስት ወራት በሕልም ወሕይ አውርዷል"*። أَنَّ اللَّه أَوْحَى إِلَى نَبِيّه فِي الْمَنَام سِتَّة أَشْهُر

አንድ የእርሳቸው የነቢይነት ክፍል 6 ወር ከሆነ ሁለት ክፍል ደግሞ 6×2= 12 ወር ወይም አንድ ዓመት ነው፥ የእርሳቸው የነቢይነት ክፍል በአንድ ዓመት ሁለት ክፍል ከሆነ በ 23 ዓመት 46 ክፍል ይሆናል ማለት ነው። 23×2=46 ይሆናል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 63, ሐዲስ 128
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በ 40 ዓመታቸው ወሕይ መቀበል ጀመሩ፥ በመካ 13 ዓመት ወሕይ እየተቀበሉ ቆይተው ከዚያ ተሰደው እንደ ስደተኛ 10 ዓመት ቆይተው በ 63 ዓመታቸው በሆነ ጊዜ ሞተዋል*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ بُعِثَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَرْبَعِينَ سَنَةً، فَمَكُثَ بِمَكَّةَ ثَلاَثَ عَشْرَةَ سَنَةً يُوحَى إِلَيْهِ، ثُمَّ أُمِرَ بِالْهِجْرَةِ فَهَاجَرَ عَشْرَ سِنِينَ، وَمَاتَ وَهُوَ ابْنُ ثَلاَثٍ وَسِتِّينَ‏.‏

13+10=23 ይሆናል። 23 ዓመቱ በሁለት ክፍል ሲሆን 46 ከሆነ እንግዲያውስ መልካም ህልም ከአርባ ስድስቱ የነቢይነት ክፍል አንዱ ነው። አምላካችን አላህ ለሷሊሕ ሙሥሊም በሕልማቸው የሚያሳውቃቸው ዕውቀት "ኢልሃም" ነው፥ "ኢልሃም" إِلْهَام የሚለው ቃል "አልሀመ" أَلْهَمَ ማለትም "አነቃቃ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መነቃቃት" ማለት ነው። አላህ በነቢያችን"ﷺ" ነቢይነት ተጠቃሚ ያድርገን! ኢልሃም ከሚሰጣቸው ሷሊሕ ሙሥሊም ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የነብያችን ጉብኝት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
ብዙ ጊዜ ከሓዲዎች በጥላቻ የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህ ግን ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አፈልግም፤ ከዚያም ባሻገር ነብያችንን”ﷺ” በቅን መንገድ እና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርጋቸው ዘንድ የላከቸው ነው፦
9፥32-33 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም يُرِيدُونَ أَن يُطْفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفْوَٰهِهِمْ وَيَأْبَى ٱللَّهُ إِلَّآ أَن يُتِمَّ نُورَهُۥ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَٰفِرُونَ ፡፡
እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُونَ ፡፡

ነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶቻቸውን በመዞር በአንድ ሌሊት ይጎበኙ ነበር፤ ይህንን ጉብኝት ከሓዲያን በመገልበጥ መሳለቂያ አድርገው ብዙ ጊዜ እንደ በቀቀን ሲደጋግሙት ይደመጣል፤ ይህንን ገላባ ጥያቄ እስቲ እንመልከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 5 , ሐዲስ 36:
አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዓ.” እንደተረከው፦ የአላህ ነብይ”ﷺ” በአንድ ሌሊት ሚስቶቻቸውን “ይዞሩ” ነበር፤ ለእርሳቸው በዚያን ጊዜ ዘጠኝ ሚስቶች ነበሩ أَنَّ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ، حَدَّثَهُمْ أَنَّ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَطُوفُ عَلَى نِسَائِهِ فِي اللَّيْلَةِ الْوَاحِدَةِ، وَلَهُ يَوْمَئِذٍ تِسْعُ نِسْوَةٍ‏.‏ ።

ይህ ዘገባ በኢማም ቡኻሪይ ውስጥ በተመሳሳይ አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዓ.” የተረከበት ብዙ ቦታ ሰፍሯል፤ ይህንን ዘገባ ጥልል እና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንየው፦

ነጥብ አንድ
“ጉብኝት”
አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዓ.” የተረከው፦ የአላህ ነብይ”ﷺ” በአንድ ሌሊት ሚስቶቻቸውን “ይዞሩ” ነበር” ብሎ ነው፤ “ይዞሩ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የጡፉ” يَطُوفُ ሲሆን “ጣፈ” طَافَ ማለትም “ዞረ” ከሚለው ኢሽቲቃቀል ከቢር ወይንም “ጠዋፍ” طَواف ማለትም “ዙረት” ከሚለው ኢሽቲቃቅ አሰጊር የመጣ ነው፤ በምን ቀመርና ስሌት ነው “ዙረት” ሲተረጎም “ተራክቦ” የሚሆነው? አላህ በሐጅ ጊዜ ቤቴንም “ለሚዞሩት”፣ ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ”፣ በጥንታዊው ቤት “ይዙሩ” ብሎ የለ እንዴ? ያ ማለት ተራክቦ ያድርጉ ማለት ነው እንዴ? ይህ የሌለ ፉርሽ ኢሥነ-አመክንዮ ነው፦
2:125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻ እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ” እና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን وَإِذْ جَعَلْنَا ٱلْبَيْتَ مَثَابَةًۭ لِّلنَّاسِ وَأَمْنًۭا وَٱتَّخِذُوا۟ مِن مَّقَامِ إِبْرَٰهِـۧمَ مُصَلًّۭى ۖ وَعَهِدْنَآ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْعَٰكِفِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ ፡፡
22:26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም “ለሚዞሩት” እና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው ባልነው ጊዜ አስታውስ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًۭٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ ።
22:29 ከዚያም ትርፍ አካላችቸንን እና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ በጥንታዊው ቤት “ይዙሩ” ثُمَّ لْيَقْضُوا۟ تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا۟ نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا۟ بِٱلْبَيْتِ ٱلْعَتِيقِ ።

ስለዚህ ነብያችን”ﷺ” ይዞሩ የነበሩት ጉብኝት እንጂ ተራክቦ የሚል አልሰፈረም፤ ይጎበኙ ነበር ማለት ተራክቦ ነው ቢባልስ ችግሩ ምንድን ነው? አላህ የሰጣቸው ችሎታና ፀጋ ቢሆንስ? በክርስትናው አስተምህሮት ተራክቦ የኃጢአት ውጤት ነው ተብሎ የሚታመነው ኢስላም ጋር አይሰራም።
ምክንያቱም ተራክቦ ሰው የሚረካበትና አይኑን በአይኑ የሚያይበት የአብራኩ ክፋይ ነው፤ ለማንኛውም የሚቀጥለው ነጥብ “ይዞሩ” ነበር ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ዓኢሻ”ረ.ዓ.” ትነግረናለች፦
ነጥብ ሁሉት
“መነካካት”
በቁርአን አገላለፅ “መነካካት” የሚለው በግልፅና በማያሻማ ተራክቦን ነው፤ ይህንን በቀላሉ ለመረዳት መርየም ለመላኩ የመለሰችው መልስ እና አላህ ስለ ሴቶች የተናገረውን ማየት ይቻላል፦
3፥46 ፡-ጌታዬ ሆይ! “ሰው ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ” ይኖረኛል?” አለች قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ ۖ ፡፡
19፥20 « ሰው “ያልነካኝ” ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች قَالَتْ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى غُلَٰمٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ وَلَمْ أَكُ بَغِيًّۭا ፡፡
2፥236 ሴቶችን “ሳትነኳቸው” ወይም ለእነሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም لَّا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ مَا لَمْ تَمَسُّوهُنَّ أَوْ تَفْرِضُوا۟ لَهُنَّ فَرِيضَةًۭ ۚ ፡፡

“ሰው ያልነካኝ” እና “ሳትነኳቸው” የሚለው ቃል “ተራክቦን” ካመለከተ ይህንን ነጥብ ይዘን ዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደነገረችን እያንዳንዳቸው የነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶቻቸው የየራሳቸው ቀናት እንዳላቸውና ግን በቀን ውስጥ ሁሉንም ሴቶች “ያለ ንክኪ” ማለትም ያለ ተራክቦ “ይዞሩ” እንደነበር ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 12 , ሐዲስ 90:
ዓኢሻ”ረ.ዓ.” አለች፦ የእህቴ ልጅ ሆይ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እኛ ጋር በሚቆይበት ጊዜ አንደኛችን ከሌላኛችን ጋር አያበላልጡም ነበር፤ ትንሽ ወቅት ሁላችንም ጋር “ይዞሩ” يَطُوفُ ነበር፤ ቀኑዋ የደረሰበት ሴት እስከሚደርስ እና እስከሚያድር ድረስ ሁላችንም ሴቶች ጋር “ያለ ንኪክይ” غَيْرِ مَسِيسٍ ይቀርቡን ነበር قَالَتْ عَائِشَةُ يَا ابْنَ أُخْتِي كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لاَ يُفَضِّلُ بَعْضَنَا عَلَى بَعْضٍ فِي الْقَسْمِ مِنْ مُكْثِهِ عِنْدَنَا وَكَانَ قَلَّ يَوْمٌ إِلاَّ وَهُوَ يَطُوفُ عَلَيْنَا جَمِيعًا فَيَدْنُو مِنْ كُلِّ امْرَأَةٍ مِنْ غَيْرِ مَسِيسٍ حَتَّى يَبْلُغَ إِلَى الَّتِي هُوَ يَوْمُهَا فَيَبِيتُ” ።

ምን ትፈልጋለህ? አንዱን አጠማለው ብትል በአንዱ ትያዛለህ፤ ሚሽነሪዎች የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ቢፈልጉም አላህ ብርሃኑን ገላጭ ነው፦
61፥8-9 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፤ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው يُرِيدُونَ لِيُطْفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفْوَٰهِهِمْ وَٱللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَٰفِرُونَ ፡፡
እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በመምሪያ በእውነተኛው ሃይማኖትም ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُونَ ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጽላት እና ታቦት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥145 *ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት*፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ

"ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" "ፊደል" ማለት ነው፤ የጽሌ ብዙ ቁጥር "ጽላት" ሲሆን "ሰሌዳዎች" ወይም "ፊደሎች" ማለት ነው፤ በዕብራይስጥ ደግሞ "ላሁት" לֻחֹ֣ת ሲሆን በዐረቢኛ "ለውሕ" لَوْح ነው፣ አምላካችን አላህ ለሙሳ ቃላትን በፊደል ላይ ጽፎ እንደሰጠው በተከበረ ቃሉ ይናገራል፦
7፥145 *ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት*፡፡ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِن كُلِّ شَيْءٍ
7፥154 *ከሙሳም ቁጣው በበረደ ጊዜ ሰሌዳዎቹን በግልባጫቸው ውስጥ ለእነዚያ እነርሱ ጌታቸውን የሚፈሩ ለኾኑት መምሪያና እዝነት ያለባቸው ሲኾኑ ያዘ*፡፡ وَلَمَّا سَكَتَ عَن مُّوسَى الْغَضَبُ أَخَذَ الْأَلْوَاحَ ۖ وَفِي نُسْخَتِهَا هُدًى وَرَحْمَةٌ لِّلَّذِينَ هُمْ لِرَبِّهِمْ يَرْهَبُونَ

ይህን ድርጊት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተምዝግቧል፦
ዘጸአት 24፥12 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን፤ *እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው*።

"ታቦት" ማለት "ማህደር" "ሰገባ" "ሳጥን" "ማደሪያ" ማለት ነው፣ በዕብራይስጥ ደግሞ "አሮውን" אֲר֖וֹן ሲሆን በዐረቢኛ "አት-ታቡት" التَّابُوتُ ነው፣ አምላካችን አላህ ስለ ታቡት እንዲህ ይለናል፦
2፥248 ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- *«የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሳ ቤተሰብና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ "ሳጥኑ" ሊመጣላችሁ ነው*፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አልለ» አላቸው፡፡ وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ آيَةَ مُلْكِهِ أَن يَأْتِيَكُمُ التَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ آلُ مُوسَىٰ وَآلُ هَارُونَ تَحْمِلُهُ الْمَلَائِكَةُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

"ሳጥኑ" ለሚለው ቃል የገባው "አት-ታቡት" التَّابُوتُ ነው፤ ይህ ቃል የሙሳ እናት ለጣለችው ሳጥን አገልግሎት ላይ ውሏል፦
20፥39 *«ሕፃኑን በሳጥኑ ውስጥ ጣይው*፡፡ እርሱንም ሳጥኑን በባሕር ላይ ጣይው፡፡ ባሕሩም በዳርቻው ይጣለው፡፡ ለእኔ ጠላት ለእርሱም ጠላት የኾነ ሰው ይይዘዋልና በማለት ባሳወቅን ጊዜ ለገስንልህ፡፡ أَنِ اقْذِفِيهِ فِي التَّابُوتِ فَاقْذِفِيهِ فِي الْيَمِّ فَلْيُلْقِهِ الْيَمُّ بِالسَّاحِلِ يَأْخُذْهُ عَدُوٌّ لِّي وَعَدُوٌّ لَّهُ ۚ وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مِّنِّي وَلِتُصْنَعَ عَلَىٰ عَيْنِي

ይህንን እንዲህ በእንዲህ ካየን ዘንዳ ታቦት የጽላቱ ማህደር ወይም ሰገባ ሲሆን ይህን ድርጊት በፔንታተች በተመሳሳይ መልኩ ተምዝግቧል፦
ዘጸአት 25፥10 *ከግራር እንጨትም "ታቦትን" ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን*።
ዘዳግም 10፥5 *ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፥ "ጽላቶችንም በሠራሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው" እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ኖሩ*።

ይህ እንዲህ ከሆነ ይህ ጽላት እና ታቦት የት ገባ? በተለይ የአገራችን ሰዎች እንደሚተርኩልን ይህን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ አቢሲኒያ በዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን በሰለሞን ዘመነ-መንግሥት እንደገባ ይነገራል፣ ነገር ግን በዓለማችን ታሪክ ላይ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደጠፋና ከዚያ በፊት ኢየሩሳሌም ውስጥ እንደነበረ ተዘግቧል፤ በተጨማሪ የእዝራ ሱቱኤል ጽሐፊ ታቦቱ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ እንደተማረከና እንደጠፋ ይዘግባል፦
እዝራ ሱቱኤል 9፥6-7 ቤተ መቅደሳችን እንደፈረሰ አታይም ግናይቱ እንደጠፍች ምስጋና እንደቀረ ዘውዳችን እንደወደቀ ተድላ ደስታችን እንደጠፍ የህጋች ማደሪያ *ታቦተ ፅዮን እንደተማረከች ንዋየ ቅዱሳት አንዳደፉ ምልኮታችን እንደቀረ። ከዚህ ሁሉ የሚበልጥ ታቦተ ፅዮን እንደጠፍች ቀረች*፤ ከእሷም ንዋየ ቅድሳቱ ተማርኮ ሄደ በጠላቶቻችን በባቢሎን እጅ ወደቅን።

የአገራችን ታሪክ የተፋለሰ መሆኑን የምናውቀው ይህ ጥቅስ ታቦተ ጽዮን በባቢሎናውያን እንደጠፋች መናገሩ ነው። ከዚያም ባሻገር ከሰለሞን 400 ዓመት በኋላ በኢዮስያስ ዘመነ-መንግሥት ታቦቱ በኢየሩሳሌም መኖሩን በዜና መዋዕል ላይ ተዘግቧል፦
ዜና መዋዕል ካልዕ 35፥3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት፥ ለእግዚአብሔርም ለተቀደሱት ሌዋውያን እንዲህ አለ፦ *ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በሠራው ቤት ውስጥ *አኑሩት*፤ ከዚህም በኋላ በትከሻችሁ ላይ ሸክም አይሆንባችሁም፤

ታቦተ ጽዮን አክሱም ላይ አለች የሚለው ትረካ ከክብረ ነገሥት ውጪ የታሪክ፣ የባይብል እና የሥነ-ቅርፅ መረጃ ሆነ ማስረጃ የለም። ታቦቱ እና ጽላቱ ቢኖሩም እንኳን በአዲስ ኪዳን ጥቅም የላቸውም። የአዲስ ኪዳን ታላቁ ጸሐፊ ጳውሎስ እንደሚነግረን ከሆነ ሙሴ ንዋየ-ቅዱሳቱን የሚሰራው የሚመጣውን ነገር እያየ እንደነበር ተዘግቧል፦
ዕብራውያን 8፥5 እነርሱም *ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና*።
ዘጸአት 25፥40 በተራራ ላይ *እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ*።
የሐዋርያት ሥራ 7፥44 *እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች*፤

ይህንን ጳውሎስ ታቦትና ጽላት "ጥላ"typology" እንደሆነ ይናገራል፤ ብሉይ ላይ የነበረው ኪዳን በአዲስ ኪዳን ተሽሯል፤ ይህም ኪዳን ጥላነቱ ታቦቱ የሰው አካል ሲሆን የሚጻፍበት ፊደል ደግሞ ለሰው ልብ ምሳሌ ሆኖ አዲሱ ኪዳን በልብ የሚጻፍ መሆኑኑን ይነግረናል፦
ኤርምያስ 31፥31 እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር *አዲስ ቃል ኪዳን* የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር *የምገባው ቃል ኪዳን ይህ* ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ *ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ*፥ *በልባቸውም እጽፈዋለሁ*፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ዕብራውያን 8፥10-13 ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ *ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ*፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል። .. *አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል*።
ብሉይ ማለት አሮጌ ማለት ነው። አሮጌ ያሰኘው አዲሱ ነው፣ አሮጌው ኪዳን ህጉ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈበት ኪዳን ሲሆን አዲሱ ደግሞ በልብ ጽላት ላይ የተጻፈበት ኪዳን ነው፣ በድንጋይ ላይ የተጻፈው ኪዳን አሮጌና ውራጅ እንደተባለ አስተውሉ፣ ከዚያም ባሻገር በአዲሱ ኪዳን አሮጌው ኪዳን ተሽሯል ይላል፦
2ኛ ቆሮ 3፥3 እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፥ *ሥጋ በሆነ በልብ ጽላት* እንጂ *በድንጋይ ጽላት* ያልተጻፈ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ የተገለጠ ነው።
2ኛ ቆሮ 3፥7 ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ *ተሻረው* ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ *ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት* በክብር ከሆነ፥ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም?
2ኛ ቆሮ 3፥13 *የዚያንም ይሻር* የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም።
2ኛ ቆሮ 3፥14 ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ፡፡ ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ *የተሻረ* ነውና።

ምን ትፈልጋለህ? በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸው ጽላት በልብ ጽላት ተሽሯል፣ ቤተመቅደሱም ሰው ሆኗል፦
1ኛ ቆሮ 3፥16-17 *የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ* የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም *የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ*።
1ኛ ቆሮ 6፥19-20 ወይስ *ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?*

አዲሱ ኪዳን ህጉ የተጻፈው በልብ ጽላት ላይ ከሆነ ቤተመቅደሱ የሰው አካል ከሆነ እግዚአብሔር ሰው በሰራው ቤተ መቅደስ አይኖርም ይለናል፦
የሐዋርያት ሥራ 17፥24 ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም
የሐዋርያት ሥራ 7፥50 ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል *የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም*።
ኢሳይያስ 66፥1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ *የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?*
ኤርምያስ 3፥16 በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ *የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም* ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ *ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም*።

የሚገርመው የአገራችን ክርስቲያኖች ከብሉይ ኪዳን ስንጠቅስ "ተሽሯል" ይሉናል፣ የተሻረው ታቦቱትና ጽላቱ እንጂ ሕጉ አይደለም። ሕጉማ በልብ ተጽፏል ተብሏል። የአገራችን ክርስቲያኖች ሕጉ ተሽሯል ይሉና የተጻፈበት ድንጋይ ሆነ የሚቀመጥበት ታቦት አልተሻረም ብለው ድርቅ ይላሉ፣ እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ በግልጽ የድንጋይ ጽላት እንደተሻረና አምላክ ሰው በሰራው ቤተመቅደስ እንደማይኖር ተናግሯል፣ ነገር ግን ዛሬ ያሉት ያገራችን ሰዎች ዛርኒሽ በተቀባ እንጨት ቀርጸው ታቦት ነው ብለው ለታቦቱ ሲሰግዱ፣ ሲለማመኑ፣ ሲማጸኑ፣ ሲሳሉ፣ ዕጣን ሲያጨሱ ይታያል፣ ይህ በትንቢት ስለ እነርሱ የተነገረው እየተፈጸመ ነውና በተውበት ወደ አላህ ተመለሱና አንዱን አምላክ በብቸኝነት አምልኩ፦
ኢሳይያስ 44፥15-19 *ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፥ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፥ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል፥ ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል፤ ይሞቃልና፦ እሰይ ሞቅሁ፥ እሳቱን አይቻለሁ ይላል። የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል። አያውቁም፥ አያስቡም፤ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፥ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን ጨፍነዋል። በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአክሱም ሙስሊሞች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

14፥42 *አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው*፡፡ وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

አክሱም ላይ የአክሱም ሥልጣኔ በነበረበት ሰአት የተተከለው የ24 ሜትር ወይም 78 ጫማ ርዝመት እና 160 ቶን የሚመዝነው የአክሱም ሃውልት ነው። ይህ ሃውልት የወንድ ሃፍረተ-ስጋ ምስል ነው። ከኩሻይቲክ የሜሮይ አገዛዝ የተወሰደ ይህ ምስል ቅድመ-ክርስትና በአክሱም ላይ ይመለክ እንደነበረ ታሪክ በወርቃማ ብዕሩ ያሰፈረው ጉዳይ ነው። ክርስትና አክሱም ሲገባ ይህንን ጣዖት ከማፍረስ ይልቅ አጠገቡ በአራተኛው ክፍለ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስትናን ይዞ በገባው በአቡነ ሰላማ ማለትም በፍሬምናጦስ ከሣቴ ብርሃን ዘመን የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ተገንብቷል፤ አሁን ያለችውን ደግሞ በዓፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ-መንግሥት የተሠራች ናት።

ዛሬ አክሱም ውስጥ ያሉት ሙስሊሞች መስኪድ እንዳይገነቡ የአክሱም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች አግደዋል። ይህም የሆነው በሁለት ተልካሻ ምክንያት ነው። አንደኛው በአምልኮት ቦታቸው ላይ ባዕድ አምልኮ እንዳይገባ ሲሆን ሁለተኛው ሳውዲ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ስላልተገነባ እኛም ጋር አይገነባም የሚል ሁለት ተልካሻ ምክንያቶች ይዘዋል።

ምክንያት አንድ
በአምልኮት ቦታችሁ ላይ ባዕድ አምልኮ እንዳይገባ የሚለው ተልካሻ ምክንያት የሚሆንበት ቅድሚያ እዛው አክሱም ውስጥ ሲመለክ የነበረውን ጣዖት በቅርስነት ከጽዮን ቤተክርስቲያን ጋር ከመደበል ይልቅ አፈራርሶ ማቃጠል ይጠበቅባችሁ ነበር፦
ዘዳግም 7፥5 ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ *ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ*።

ሁለተኛ የሙስሊም አምልኮ ባዕድ አምልኮ ሳይሆን ጥንት የነበሩት ነብያት ሲያመልኩት የነበረው የዓለማቱ ጌታን አላህን ብቻ በብቸኝነት የሚመለክበት ነው። ሦስተኛ ጥንት የነበረው የሙሴ ታቦት ጽዮን ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የለም። ለምን ይዋሻል? አሁን አርስቱ ስላልሆነ "ጽላት እና ታቦት" የሚለውን የእኔን መጣጥፍ አንብቡት።

ሁለተኛው ምክንያት
ሳውዲ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ስላልተገነባ እኛም ጋር አይገነባም የሚለው ተልካሻ ምክንያት የሚሆንበት ከመነሻው እኛ ኢትዮጵያውያን እንጂ ዐረባውያን አይደለንም። ሲቀጥል ሳውዲ ቤተ-ክርስቲያን የማይገነባው ሳውዲ ውስጥ ክርስቲያን ስለሌለ እንጂ አሁን ከተለያዩ አገር ለሥራ የመጡ ዜጎች የአምልኮ ቦታ ያስፈልጋቸው ተብሎ ቤተ-ክርስቲያን ሊሰራላቸው ተፈራርመው ጨርሰዋል። በኢስላምም አህለል ዚማህ ማለትም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በኢስላም አገር ውስጥ ጂዚያህ እስከከፈሉ ድረስ የአምልኮ ነጻነት አለ።
ሢሰልስ ኢትዮጵያ የሁለቱም ሃይማኖት አገር ናት፤ የምትመራበት መርሕ በሕገ መንግሥት እንጂ በፍትሐ-ነገሥት ወይም በሲኖዶስ አሊያም በመጅሊስ አይደለም። ሕገመንግሥቱ አንቀጽ 27 ንዑስ አንቀጽ 2 እንዲህ ይላል፦
"የሃይማኖት ተከታዮች ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት እና ለማደራጀት የሚያስችሏቸውን የሃይማኖት ትምህርት እና ተቋማት ማቋቋም ይችላሉ።"

ምን ትፈልጋለህ? አክሱም ላይ ያሉት ሙስሊሞች መስጊድ መገንባት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ነው። በመነጋገር ከማመን ይልቅ በዱላ እመን የሚለውን የአጼዎቹ ሥርዓት ናፋቂዎቹ፦ "አክሱም ላይ መስኪድ እሰራለው ያለ ደሙ ይፈሳታል" የሚል ቃለ ፉከራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲለፈልፉ ይደመጣል፤ ክርስትና ፍቅር ናት፣ ክርስትና ቀኝህን ሲመታ ግራህን ስጠው ስብከት ላይ ብቻ ነው የሚሰራው። እናንተ እነማን ናችሁ? ምንስ ስለሆናችሁ ነው? የመከልከል ሞራሉም ብቃቱም የላችሁም። በዚህ ነጥብ ላይ ማንም ምንም ናችሁ። ሕገ-መንግሥቱን የማያከብር ግለሰብ ሆነ ተቋም ሕገወጥ ነው። አጼዎቹ አንዴ በግድ ካልተጠመቃችሁ፣ አንዴ የኢስላም ልጅ ትምህርት አያስፈልገውም እየተባለ ከትምህርት ገበታው ሲያባርር አባት ለሰራው ልጅ አይጠየቅም በሚል መርሕ በይቅርታ ስናልፋችሁ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ስትሞሉ ፈለጋችሁ? የአክሱም ሙስሊሞችን በደል የሚካሱበትን ቀን አላህ ያፍጥነው! አሚን። በዓለም ላይ በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰው በደል ታሪክ ይቁጠረው፤ አላህ የፍርዱ ቀን ለበደለኞች ቅጣት አዘጋጅቷል። አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፤ የሚያቆያቸው እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ብቻ ነው፦
14፥42 *አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው*፡፡ وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَارُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የአላህ ባህርይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 53, ሐዲስ 32
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ አላህ አዝዘ ወጀል አደምን ስልሳ ኩብ ቁመት አድርጎ በራሱ "መልክ" ፈጠረው። خَلَقَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا.
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 79, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ አላህ አደምን ስልሳ ኩብ ቁመት አድርጎ በራሱ "መልክ" ፈጠረው። خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ، طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا،

የቋንቋው ሊሂቃን "ሱራ" صورة ማለት "መልክ" image" ብለው ያስቀመጡት ሲሆን ይህም "መልክ" ባህርይ ለማመልከት እንደሚመጣ ይናገራሉ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60 ሐዲስ 2
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ የመጀመሪያው ግሩፕ በሌሊት ሙሉ እንደሆነች በጨረቃ "#መልክ" صُورَةِ ሆኖ ወደ ጀነት ይገባሉ። إِنَّ أَوَّلَ زُمْرَةٍ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ عَلَى صُورَةِ الْقَمَرِ لَيْلَةَ الْبَدْرِ،

በዚህ ሐዲስ ላይ መቼም የጨረቃ መልክ የጨረቃን ቅርፅና ክብደት ለማመልከት ነው ከተባለ የጨረቃ ቅርጷ 1958×1010 km3 እንዲሁ ክብደቷ 7.342×1022 kg ነው፤ ያ ማለት ሰው ጀነት የሚገባው በጨረቃ ቅርፅና ክብደት ነው ማለት ሳይሆን የጨረቃ ባህርይ የሆኑን ንፅህናዋን፣ ድምቀቷ እና ውበቷን ማለቱ ነው፤ እንግዲህ "ሱራ" صورة "መልክ" የአንድን ህላዌ ባህርይ ለማመልከት ከመጣ ይህም "መልክ" ማየት፣ መስማት፣ ማወቅ የሚባሉትን ባህርያት ያቅፋል፤ አላህ ሁሉን ነገር ተመልካች፣ ሁሉን ነገር ሰሚ እና ሁሉን ነገር አዋቂ ነው፤ አላህ አደምን ሲፈጥረው በባህርያቱ የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ እና የሚያውቅበት ልብ"አንጎል" ሰቶታል ማለት ነው፦
67:23 እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም "#መስሚያ" እና "#ማያዎችን" "#ልቦችንም" ያደረገላችሁ ነው፤ ጥቂትንም አታመሰግኑም በላቸው።
23፥78 እርሱም ያ "#መስሚያዎችንና" "#ማያዎችን" "#ልቦችንም" ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፤ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡

አላህ "የሚመስለው ምንም ነገር የለም" አላህ ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው፦
42:11"የሚመስለው" ምንም ነገር የለም፤ እርሱም "ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው።

አላህ ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው እንደተባለ ሁሉ ሰውም ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው ተብሏል፦
76:2 እኛ ሰዉን፥ በሕግ ግዳጅ የምንሞክረዉ ስንሆን፥ ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፤ "ሰሚ" "ተመልካችም" አደረግነዉ።

ነገር ግን አላህ ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው የተባለው ሰው ሰሚ" እና "ተመልካች" በተባለበት ሂሳብ አይደለም፤ ምክንያቱም አላህ ሁሉን ነገር ይሰማል ያያል፤ ይህ ባህርይ ጊዜና ቦታ አይገድበውም፤ ሰው ግን ያለ ብርሃን ማየት እና ያለ ድምፅ መስማት አይችልም፤ በተመሳሳይ አላህ ሁሉን አዋቂን ነው እውቀቱ በጊዜና በቦታ አይገደብም፤ ሰው ግን እውቀቱ ጊዜ እና ቦታ ይገድበዋል፦
58:6 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነው።
67:19 እርሱ በነገር ሁሉ ተመልካች ነው።
4:86 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና።
39:62 እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው።
33:27 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

የሰው መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም ከአላህ የሆኑ ፀጋ ሲሆኑ ከእንስሳ በተለየ መልኩ ይሰሩት በነበሩት ሁሉ ተጠያቂ ናቸው፦
17:36 ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፤ #መስሚያ#ማያም#ልብም፣ እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ #ተጠያቂ ነውና إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ።
102:8 ከዚያም #ከጸጋዎቻችሁ النَّعِيمِ ሁሉ በዚያ ቀን #ትጠየቃላችሁ ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ ።
16:93 ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ #ትጠየቃላችሁ" وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ ።

የአላህ ዛት የራሱ ሲፋ አለው ማየት፣ መስማት፣ መናገር፣ ማወቅ እና እጅ ግን ከፍጡራን ማየት፣ መስማት፣ ማወቅ፣ መናገር እና እጅ ጋር አይመሳሰልም። ለምሳሌ የሰው እጅ ቀኝና ግራ ነው የአላህ እጆች ግን ቀኝ ናቸው፦
ኢማም ሙስሊም 33, ሐዲስ 21 ፍትኸኞች አላህ ዘንድ በብርሃን መንበሮች ላይ ከአር-ረህማን በስ-ተቀኝ በኩል ይሆናሉ፤ ሁለቱም እጆቹ #ቀኝ ናቸው። " ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﻤُﻘْﺴِﻄِﻴﻦَ ﻋِﻨْﺪَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻋَﻠَﻰ ﻣَﻨَﺎﺑِﺮَ ﻣِﻦْ ﻧُﻮﺭٍ ﻋَﻦْ ﻳَﻤِﻴﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﻋَﺰَّ ﻭَﺟَﻞَّ ﻭَﻛِﻠْﺘَﺎ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻳَﻤِﻴﻦٌ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﺪِﻟُﻮﻥَ ﻓِﻲ ﺣُﻜْﻤِﻬِﻢْ ﻭَﺃَﻫْﻠِﻴﻬِﻢْ ﻭَﻣَﺎ ﻭَﻟُﻮﺍ "

አላህ በራሱ ባህርይ ፈጠረው ማለት ለምሳሌ አላህ አደምን በእጁ ፈጥሮታል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *"በሁለት እጆቼ"* "ለፈጠርኩት" ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ
36፥71 እኛ *"እጆቻችን ከሠሩት"* ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَآ أَنْعَٰمًۭا فَهُمْ لَهَا مَٰلِكُونَ

እጅ የአላህ ባህርይ ነው፤ ኹን የሚለው ንግግሩ የራሱ ባህርይ ነው፤ በባህርይው አደምን ፈጥሮታል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አሥራ ሁለቱ ነገዶች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

“ነቢይ” نبي የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ወይም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “አውሪ” ወይም “ነጋሪ” ማለት ነው፤ ይህንን እስቲ ከቁርአን እንመልከት፦
66፡3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ *ይህን ማን “ነገረህ”? አለች፤ ዐዋቂው ውስጠ አዋቂው “ነገረኝ” አላት*። وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِ وَأَظْهَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُ وَأَعْرَضَ عَنْ بَعْضٍ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِ قَالَتْ مَنْ أَنْبَأَكَ هَذَا قَالَ نَبَّأَنِيَ الْعَلِيمُ الْخَبِيرُ ፤

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን “ነገረኝ” ለሚለው ደግሞ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ነው፤ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነበአ” نَبَّأَ የሚለው ቃል ነው፤ ስለዚህ ነቢይ ማለት ሁሉን ዐዋቂውና ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው፤ በዚህ ስሌት አሥራ ሁለቱ ነገዶች በሙሳ ዘመን በኢስራኢል ልጆች የተነሱ ነቢያት ናቸው፦
5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

"በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ ጊዜ" የሚለው ይሰመርበት፤ እነዚህ ነብያት ነገዶቹ ናቸው፤ አላህ ወደ ነገዶቹ ወሕይ አውርዷል፦
4፥163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ *ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
3፥84 «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም፣ በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ *በነገዶችም ላይ በተወረደው*፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው አመንን፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «በአላህና ወደኛ በተወረደው፣ ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብ እና *ወደ ነገዶቹም በተወረደው* በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

አላህ ወሕይ የሚወርድላቸውን እነዚህን ነገዶች አሥራ ሁለት አለቆች አድርጎ አስነሳቸው፤ ለአሥራ ሁለትም ሕዝቦች ከፋፈላቸው፦
5፥12 *አላህም የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው፡፡ ከእነርሱም አሥራ ሁለትን አለቆች አስነሳን*፡፡ وَلَقَدْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَبَعَثْنَا مِنْهُمُ اثْنَيْ عَشَرَ نَقِيبًا
7፥160 *አሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው*፡፡ ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን፡፡ መታውም *ከእርሱ አሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ*፡፡ وَقَطَّعْنَاهُمُ اثْنَتَيْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ إِذِ اسْتَسْقَاهُ قَوْمُهُ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَرَ ۖ فَانبَجَسَتْ مِنْهُ اثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا
ጥንት የአሥራ ሁለቱ አበው የቃልኪዳን መጽሐፍ የነበረ ሲሆን አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ ውሳኔ የአፓክራፋ መጽሐፍ ብለው ቀንሰውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ብዙውን የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛውን በእርግጥ ልኳል፦
5፥15 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

“አፓክራፋ” የሚለው ቃል “አፓክራፈስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፤ ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት አስፈላጊውን አላህ የገለጸ ሲሆን ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት ብዙውን ትቶታል፤ ወደ ነብያት ምን ተወርዶ እንደነበረ መልእክተኛው እንዲገልጹ ቁርኣንን አውርዷል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ *ወደ አንተም ለሰዎች ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን*፡፡ بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

ይህ ቁርኣን ከበፊቱ ከአላህ የተወረዱትን የአላህ ንግግሮች የሚያረጋግጥ እና በእነዚያ ንግግሮች ውስጥ ያለውን ጭብጥ የሚዘረዝር ነው፦
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፤ *ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَمَا كَانَ هَـٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَـٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም