ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
አሚን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

1፥7 *የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፥ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ*፡፡ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ

"አሚን" أَمِين የሚለው ቃል "አሚነ" أَمِنَ‎ ማለትም "አመነ" "ተስማማ" "ተዋዋለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አምኛለው" "ተስማምቻለው" "ተዋውያለው ይሁንልኝ" ማለት ነው። "አሜን" የሚለው የግዕዙም ቃል ተመሳሳይ ትርጉም አለው፦
1፥7 *የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፥ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ*፡፡ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4475
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ኢማሙ፦ “ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” ባለ ጊዜ "አሚን" በሉ። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ إِذَا قَالَ الإِمَامُ ‏{‏غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ فَقُولُوا آمِينَ‏.

አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፥ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው። ነገር ግን ከአይሁዳውያን ጥቂት ያልተቆጣህባቸውን እና ከክርስቲያኖች ጥቂት ያልተሳሳቱትንም ተውሒድን የሚከተሉ ሰዎች ከቁርኣን መውረድ በፊት ስላሉ፥ እነርሱ የሄዱበትት ቀጥተኛው መንገድ ምራን ብለን ዱዓእ እናደርግና ስንጨርስ አሚን እንላለን፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3212
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፥ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው። ‏ عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ وَالنَّصَارَى ضُلاَّلٌ

ይህ ሶላት ላይ ሱረቱል ፋቲሓህ በሚቀራበት ጊዜ ነው። የሰው አሚን ከመላእክት አሚን ጋር ከተስማማ አላህ ለእርሱ የቀደመውን ኀጢአቱን ይቅር ይለዋል፦
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 11, ሐዲስ 50
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *"ቃሪእ "አሚን" ባለ ጊዜ እናንተም እንዲሁ "አሚን" በሉ! መላእክትም ይላሉ። የሰው አሚን ከመላእክት አሚን ጋር ከተስማማ አላህ ለእርሱ የቀደመውን ኀጢአቱን ይቅር ይለዋል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِذَا أَمَّنَ الْقَارِئُ فَأَمِّنُوا فَإِنَّ الْمَلاَئِكَةَ تُؤَمِّنُ فَمَنْ وَافَقَ تَأْمِينُهُ تَأْمِينَ الْمَلاَئِكَةِ غَفَرَ اللَّهُ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ

በተጨማሪም ነቢያችን”ﷺ” ሱረቱል ፋቲሓን ላይ ያለው ዱዓእ የአላህ ባሪያ አላህን የሚያነጋግርበት ዱዓእ እንደሆነ አበክረውና አዘክረው ነግረውናል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 4 ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው *ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ “የቁርኣን እናት ሳያነብ የሰገደ ሰው ሶላቱ ጎዶሎ ነው”* አንድ ሰው ለአቢ ሁረይራህ፦ “ከአሰጋጁ በኋላ ብንሆንም እንኳን? አለው። እርሱም አለ፦ “ለራስህ አንብብ ምክንያቱም ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁና፦ *”ኃያሉና የተከበረው አላህ እንዲህ ብሏል፦ “ሶላትን በእኔ እና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፍየዋለሁ፥ እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል፤ ባሪያው፦ ”ምስጋና ለአላህ ይገባው የዓለማት ጌታ ለኾነው” ሲል አላህ፦ “ባሪያዬ አመሰገነኝ” ይላል። ባሪያው፦ ”እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ” ሲል ደግሞ አላህ፦ “ባሪያዬ አሞገሰኝ’ ይላል። ባሪያው፦ ”የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው” ሲል አላህ፦ ባሪያዬ አላቀኝ” ይላል። ባሪያው፦ ”አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን” በሚል ግዜ አላህ፦ “ይህ በእኔ እና በባሪያዬ መካከል ነው እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል” ይላል። ባሪያው፦ ”ቀጥተኛውን መንገድ ምራን የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” በሚል ግዜ ደግሞ አላህ፦ “ይህ ለባሪያዬ ነው፤ እናም ባሪያዬ የጠየቀውን ያገኛል” ይላል"*፡፡ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ مَنْ صَلَّى صَلاَةً لَمْ يَقْرَأْ فِيهَا بِأُمِّ الْقُرْآنِ فَهْىَ خِدَاجٌ – ثَلاَثًا – غَيْرُ تَمَامٍ ‏”‏ ‏.‏ فَقِيلَ لأَبِي هُرَيْرَةَ إِنَّا نَكُونُ وَرَاءَ الإِمَامِ ‏.‏ فَقَالَ اقْرَأْ بِهَا فِي نَفْسِكَ فَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏”‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى قَسَمْتُ الصَّلاَةَ بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي نِصْفَيْنِ وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ فَإِذَا قَالَ الْعَبْدُ ‏{‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى حَمِدَنِي عَبْدِي وَإِذَا قَالَ ‏{‏ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ اللَّهُ تَعَالَى أَثْنَى عَلَىَّ عَبْدِي ‏.‏ وَإِذَا قَالَ ‏{‏ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ‏}‏ ‏.‏ قَالَ مَجَّدَنِي عَبْدِي – وَقَالَ مَرَّةً فَوَّضَ إِلَىَّ عَبْدِي – فَإِذَا قَالَ ‏{‏ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا بَيْنِي وَبَيْنَ عَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏.‏ فَإِذَا قَالَ ‏{‏ اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ * صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ ‏.‏ قَالَ هَذَا لِعَبْدِي وَلِعَبْدِي مَا سَأَلَ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ سُفْيَانُ حَدَّثَنِي بِهِ الْعَلاَءُ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ يَعْقُوبَ دَخَلْتُ عَلَيْهِ وَهُوَ مَرِيضٌ فِي بَيْتِهِ فَسَأَلْتُهُ أَنَا عَنْهُ ‏.‏

አምላካችን አላህ የሁላችንን አሚንን ታሳቢ ያደረገ ዱዓእ ይቀበለን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አዛን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥58 *"ወደ ሶላትም በጠራችሁ ጊዜ ጥሪይቱን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው ይይዟታል፡፡ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው"*፡፡ وَإِذَا نَادَيْتُمْ إِلَى الصَّلَاةِ اتَّخَذُوهَا هُزُوًا وَلَعِبًا ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْقِلُونَ

"አዛን" أَذَان የሚለው ቃል "አዚነ" أَذِنَ‎ ማለትም "ጠራ" ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥሪ" ማለት ነው። "ሙአዚን" مُؤَذِّن የሚለው ቃል "አዘነ" أَذَّنَ‎ ማለትም "ተጣራ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጠሪ" ማለት ነው። አምላካችን አላህ፦ "በጁሙዓህ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ" ብሎናል፦
62፥9 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በጁሙዓህ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡ ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا نُودِيَ لِلصَّلَاةِ مِن يَوْمِ الْجُمُعَةِ فَاسْعَوْا إِلَىٰ ذِكْرِ اللَّهِ وَذَرُوا الْبَيْعَ ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

"ፈርድ" فَرْض የሚለው ቃል "ፈረደ" فَرَضَ ማለትም "ተገደደ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ግዴታ" ማለት ነው። ፈርድ በሁለት ይከፈላል፥ እርሱም "ፈርዱል ዐይን" فَرْض العَيْن እና "ፈርዱል ኪፋያህ" فَرْض الكِفَايَة ናቸው።
"ዐይን" عَيْن የሚለው ቃል "ዓነ" عَانَ‎ ማለትም "ነጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተናጥል" ማለት ነው። "ፈርዱል ዐይን" فَرْض العَيْن ማለት "የተናጥል ግዴታ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ ሶላት፣ ሓጅ፣ ዘካህ፣ ፆም ወዘተ።
"ኪፋያህ" كِفَايَة የሚለው ቃል "ከፋ" كَفَى ማለትም "ጠቀለለ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጥቅል" ማለት ነው። "ፈርዱል ኪፋያህ" فَرْض الكِفَايَة ማለት "የጥቅል ግዴታ" ማለት ነው፥ ለምሳሌ "ሶላቱል ጀናዛህ" صَّلَات الجَنَازَة እና "ሶላቱል ጁሙዓህ" صَّلَات الْجُمُعَة ናቸው።
አንዳድ ጊዜ ሰዎች በሶላቱል ጁሙዓህ እና በአዘቦቱ ሶላት አዛን ሲሰሙ ጥሪይቱን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው ይይዟታል፦
5፥58 *"ወደ ሶላትም በጠራችሁ ጊዜ ጥሪይቱን መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው ይይዟታል፡፡ ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው"*፡፡ وَإِذَا نَادَيْتُمْ إِلَى الصَّلَاةِ اتَّخَذُوهَا هُزُوًا وَلَعِبًا ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْقِلُونَ

ይህ እነርሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው። እኛም የአዛኑን ትርጉም ሙሥሊም ላልሆኑ ሰዎች እንዲያውቁ ማድረግ አለብን፥ ለናሙና ያክል የጁምዓ አዛን እንይ፦
1. "አሏሁ አክበር" ٱللهُ أَكْبَر ማለት "አሏህ ታላቅ ነው" ማለት ሲሆን የሚባለው 4 ጊዜ ነው።
2. "አሽሀዱ አነ ላ ኢላሀ ኢለሏህ" أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلٰهَ إِلَّا ٱلله ማለት "ከአሏህ በስተቀር አምላክ እንደሌለ እመሰክራለው" ማለት ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
3. "አሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሡሉሏህ" أَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ ٱلله ማለት "ሙሐመድም የአሏህ መልእክተኛ መሆኑን እመሰክራለው" ማለት ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
4. "ሐየ ዐለስ ሶላህ" حَيَّ عَلَى ٱلصَّلَاة ማለት "ወደ ሶላት ኑ" ማለት ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
5. "ሐየ ዐለል ፈላህ" حَيَّ عَلَى ٱلْفَلَاح ማለት "ወደ መዳን ኑ" ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
6. "አሏሁ አክበር" ٱللهُ أَكْبَر ማለት "አሏህ ታላቅ ነው" ማለት ሲሆን የሚባለው 2 ጊዜ ነው።
7. "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا ٱلله ማለት "ከአሏህ በስተቀር አምላክ የለም" ማለት ሲሆን የሚባለው 1 ጊዜ ነው።

ሙአዚኑ ይህንን ጥሪ በተጣራ ጊዜ ሙሥሊሙ በተመሳሳይ ከላይ ያለውን ቃል ይላል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 9
አቢ ሠዒድ አል-ሑድሪይ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ጠሪው የሚለውን በተመሳሳይ በሉ"*። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِذَا سَمِعْتُمُ النِّدَاءَ فَقُولُوا مِثْلَ ما يَقُولُ الْمُؤَذِّنُ

የመጀመሪያው ሙአዚን ሐበሻዊ ቢላል ኢብኑ ረባሕ ወይም ኢብን ሪያሕ"ረ.ዐ." ነው። ይህ ሰሓቢይ ለአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ሙአዚን ነበረ፥ እኛም ሐበሾች በቢላል አዛን መገለጫችን ሆኗል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 700
አሥ-ሣኢብ እንደተረከው፦ *"ለአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ጠሪ አልነበራቸው አንድ ቢላል እንጂ"*። عَنِ السَّائِبِ، قَالَ لَمْ يَكُنْ لِرَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم إِلاَّ مُؤَذِّنٌ وَاحِدٌ بِلاَلٌ
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 46, ሐዲስ 3936
አቢ ሁራይራህ እንደሚተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ንግሥና ከቁራይሽ፣ ፍርድ ከአንሷር፣ አዛን ከሐበሻ፣ አማናህ ከየመን ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الْمُلْكُ فِي قُرَيْشٍ وَالْقَضَاءُ فِي الأَنْصَارِ وَالأَذَانُ فِي الْحَبَشَةِ وَالأَمَانَةُ فِي الأَزْدِ ‏"‏ ‏.‏ يَعْنِي الْيَمَنَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተሸካሚ ነፍስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም*፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ

በቁርአን እስተምህሮት ውስጥ እንደ ክርስትናው “ጥንተ-ተአብሶ”Original sin” ማለትም እንደ ስኳርና ሳይነስ ለትውልድ በዘር የሚተላለፍ ኃጢአት የለም፤ ኃጢአት ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም፤ አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾቹ ላይ፦ “ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም” እያለ ይነግረናል፦
17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም*፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ

ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሚሽነሪዎች፦ “በኢስላም አስተምህሮት ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት ትሸከማለች” በማለት ሐዲሱ ለማለት ያልፈለገውን እጁን ጠምዝዘው ለማስባት ይሞክራሉ፤ ይህ በሥነ-አፈታት ጥናት”hermeneutics” ውስጥ “ስሁት ትርጓሜ”Eisegesis” ይባላል፤ አብዛኛውን ሳይፈሩና ሳያፍሩ ሳይማሩና ሳይመራመሩ ስሁታን የሆኑ ታካቾች ይጠቀሙበታል። በተቃራኒው ተረድቶ ለማስረዳት ዐውቆ ለማሳወቅ አምኖ ለማሳመን የአንድ ዓረፍተ-ነገር ዐውዱ ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ተብሎ እራሱ እንዲናገር ማድረግ ደግሞ “ስሙር ትርጓሜ”Exegesis” ይባላል፤ ይህንን አብዛኛው ጊዜ የሚጠቀሙበት ሊኅቃን የሆኑ ምሁራን ናቸው። እስቲ ሐዲሱን በአጽንኦትና በአንክሮት እንየው፦
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 50, ሐዲስ 60
አቢ ቡርዳ እንዳስተላለፈው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በትንሳኤ ቀን ከሙስሊሞች ሰዎች እንደ ተራራ ከሚመስል ወንጀላቸው ይመጣሉ፤ አላህም ይቅር ይላቸዋል። በእነርሱ ምትክ አይሁዳውያንን እና ክርስቲያኖችን ያስቀምጣል*። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ يَجِيءُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ نَاسٌ مِنَ الْمُسْلِمِينَ بِذُنُوبٍ أَمْثَالِ الْجِبَالِ فَيَغْفِرُهَا اللَّهُ لَهُمْ وَيَضَعُهَا عَلَى الْيَهُودِ وَالنَّصَارَى ‏”
እዚህ ሐዲስ ላይ የሙስሊሞችን ኃጢኣት አይሁድ እና ክርስቲያን ይሸከማሉ የሚል ሽታው እንኳን የለም፤ ከሙስሊሞች እንደ ተራራ ከሚመስል ወንጀላቸው ሲመጡ አላህ ይቅር ይላቸዋል፤ አንደኛ ይቅርታ የሚያገኙት በነብያችን”ﷺ” ምልጃ ሁለተኛ እስካላሻረኩት ድረስ ተቀጥተው ምህረትን ያገኛሉ እንጂ የእነርሱ ኃጢኣት በአይሁድ እና በክርስቲያን ላይ ያደርጋል የሚል ሽታው እንኳን የለም፤ ታዲያ “ምትክ” የሚለው ምንድን ነው? ሐዲሱ እዛው ላይ ይቀጥላል፦
ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 50, ሐዲስ 58
አቢ ቡርዳ እንዳስተላለፈው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ሙስሊም አይሞት የእርሱ ቦታ አላህ አይሁድ ወይም ክርስቲያንን በእሳት ቢያደርግ እንጂ*። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لاَ يَمُوتُ رَجُلٌ مُسْلِمٌ إِلاَّ أَدْخَلَ اللَّهُ مَكَانَهُ النَّارَ يَهُودِيًّا أَوْ نَصْرَانِيًّا ‏
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 50, ሐዲስ 57
አቡ ሙሣ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ የትንሳኤ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ *አላህ ለሁሉም ሙስሊም አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን ያስቀምጣል፤ “ይህ ከእሳት የእናንተ ምትክ ነው” ይባላል*። عَنْ أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِذَا كَانَ يَوْمُ الْقِيَامَةِ دَفَعَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ إِلَى كُلِّ مُسْلِمٍ يَهُودِيًّا أَوْ نَصْرَانِيًّا فَيَقُولُ هَذَا فَكَاكُكَ مِنَ النَّارِ ‏”

አንድ አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን ቢያምን ኖሮ በጀነት የሚያገኘውን ቦታ ስላላመነ ሙስሊሙ በማመኑ የእርሱን ቦታ በገነት ያገኛል። በተቃራኒው አንድ ሙስሊም ቢክድ ኖሮ በገሃነም የሚያገኘውን ቦታ ስላልካደ አንድ አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን በመካዱ የእርሱን ቦታ በገሃነም ያገኛል። ይህ ነው የሐዲሱ እሳቤ እንጂ ስለ ኃጢኣት መሸከም አይናገርም። የሚናገረው ስለ ጀሃነም ቦታ ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ: መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4485
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሁለት ቦታ የሌለው ከእናንተ ማንም የለም፤ አንዱ መኖሪያ በጀነት ሌላው መኖሪያ በጀሃነም፤ የካደ ቢሞትና ጀሃነም ቢገባ የጀነት ባለቤት የእርሱን ቦታ ይወርሳል፤ ይህንን አላህ ሲናገር፦ “እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው” ብሏል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ مَا مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلاَّ لَهُ مَنْزِلاَنِ مَنْزِلٌ فِي الْجَنَّةِ وَمَنْزِلٌ فِي النَّارِ فَإِذَا مَاتَ فَدَخَلَ النَّارَ وَرِثَ أَهْلُ الْجَنَّةِ مَنْزِلَهُ فَذَلِكَ قَوْلُهُ تَعَالَى ‏{أُولَئِكَ هُمُ الْوَارِثُونَ }‏ ‏”‏
23፥10 *እነዚያ ወራሾቹ እነርሱ ናቸው*፡፡ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْوَارِثُون
23፥11 *እነዚያ ፊርደውስን የሚወርሱ ናቸው፡፡ እነርሱ በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው*፡፡ الَّذِينَ يَرِثُونَ الْفِرْدَوْسَ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

ስለዚህ ካፊር በመክፈሩ ጀሃነም ይገባል፤ ባይከፍር በጀነት የሚያገኘውን ቦታ ሙዕሚኑ ይወርሰዋል፤ ሙዕሚን በማመኑ ጀነት ይገባል፤ ባያምን በጀሃነም የሚያገኘውን ቦታ ካፊሩ ይወርሰዋል። ይህ ነው የሐዲሳት ጭብጥ፤ የነብያችንን”ﷺ” መልእክት ሰምቶ ያላመነ አይሁድ ወይም ክርስቲያን ጀሃነም እንደሚገባ እሙንና ቅቡል ነው፦
ኢማም ሙስሊም: መጽሐፍ 1, ሐዲስ 293
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው እምላለው፤ ከዚህ ሕዝብ አይሁዳዊም ሆነ ክርስቲያን የእኔን መላክ ሰምቶ ሳያምን ቢሞት የጀሃነም ጓድ እንጂ ሌላ አይሆንም”*። حَدَّثَهُ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ لاَ يَسْمَعُ بِي أَحَدٌ مِنْ هَذِهِ الأُمَّةِ يَهُودِيٌّ وَلاَ نَصْرَانِيٌّ ثُمَّ يَمُوتُ وَلَمْ يُؤْمِنْ بِالَّذِي أُرْسِلْتُ بِهِ إِلاَّ كَانَ مِنْ أَصْحَابِ النَّارِ ‏”

ቅሉ ግን አይሁዳዊም ሆነ ክርስቲያን የእርሳቸውን መላክ ሰምቶ ሳያምን ከመሞቱ በፊት ካመኑ ሊያገኙት የሚችሉት የጀነት ቦታ ለማግኘት ቶሎ መስለም ነው፤ አይ አስተባብዬ እሞታለው ካላችሁ ብታምኑ የምታገኙትን ቦታ ያመነ ሙስሊም ቦታችሁን ይወርሰዋል። እርሱ ቢክድ የሚያገኘውን የጀሃነም ቦታ በማመኑ የእርሱ ቦታ እናንተ ትወርሳላችሁ። የንስሓ በሩ ሳይዘጋ በጊዜ ሰልሞ ማምለጥ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
መረዳዳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥2 *”በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና”*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

አምላካችን አላህ ከሰው ጋር በሚኖረን ማሕበራዊ ዘይቤ እንዴት መኗኗር እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥36 *አላህንም አምልኩ፤ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆች፣ በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው መልካምን ሥሩ*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا
4፥135 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ይህ ቃል የስም መደቡ “ዐድል” عَدْل ሲሆን “ፍትሕ” ማለት ነው፤ ፍትሕ ለአላህ ፍራቻ ተብሎ እና አላህ በምንሠራው ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ተብሎ የሚደረግ ነው። ይህ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ፍትሕ ለአማንያን ብቻ ሳይሆን ለከሃድያንም ጭምር ነው፦
60፥8 *ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ፣ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸው እና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ዲናችንን አክብረው ካልተጋደሉንና ካላሳደዱን ከሃድያን ጋር በዝምድና፣ በባልደረባ፣ በጉርብትና መልካም መዋዋል እና ማስተካከል ይቻላል። “ብታስተካክሉ” ለሚለው ቃል አሁንም የገባው “ቱቅሢጡ” َتُقْسِطُوا ሲሆን የስም መደቡ “ቂሥጥ” قِسْط ማለትም “ፍትሕ” ነው፤ ለአላህ ብለን ስናስተካክል “ሙቅሢጢን” مُقْسِطِين ማለትም “ፍትኸኞችን” “ትክክለኞች” “አስተካካዮች” እንሰኛለን፤ አላህ ሙቅሢጢንን ይወዳልና። በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም መረዳዳት ተፈቅዷል፦
49፥9 *በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና*፡፡ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ
5፥2 *”በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና”*፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

“በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ” የሚለው ይሰመርበት። ወደ ኩፍርና ሺርክ ሊያስገባ የሚችለውን ሥራ ከሌላ እምነት ጋር መሥራት ከኢሥላም ያስወጣል፥ ይህ ወሰን ማለፍ ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 311
ሰሙራህ ኢብኑ ጁንዱብ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እዲህ አሉ፦ *”ከሙሽሪክ ጋር ያበረ እና የተኗኗረ እርሱን(ሙሽሪኩን) ይመስላል”*። أَمَّا بَعْدُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ جَامَعَ الْمُشْرِكَ وَسَكَنَ مَعَهُ فَإِنَّهُ مِثْلُهُ ‏
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 12, ሐዲስ 34
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም አሉ፦ *”ከማንኛውም ሕዝብ ጋር የሚመሳሰል ከእነርሱ ነው”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ
ስለዚህ የማይመለከተን ነገር ውስጥ ለመመሳሰል ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያን ማጽዳት፣ የመስቀል ደመራ ቦታ ማጽዳት፣ የጥምቀት ቦታ ማጽዳት፥ ታቦት መሸኘት፣ በዓላቸውን ማክበር፣ መዝሙራቸውን መዘመር ከኢሥላም አጥር ያስወጣል። አንዳንድ ቂሎች፦ “ለመረዳዳት ነው” ይሉናል። በጋራ እሴት ማለትም በልማት፣ በጉርብትና፣ በአስኳላ ትምህርት፣ በሰብአዊነት ወዘተ… ልንረዳዳ እንችላለን፥ ነገር ግን በእምነት ጉዳይ እረዳቶች አድርገን ከያዝናቸው ከእነርሱ እንደ አንዱ ነን፦
4፥144 *”እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ*፤ ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን? يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَجْعَلُوا لِلَّهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَانًا مُّبِينًا
5፥51 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከእነርሱ ነው*፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْيَهُودَ وَالنَّصَارَىٰ أَوْلِيَاءَ ۘ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 2939
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የሙሽሪክ እርዳታ አያስፈልገንም”* عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّا لاَ نَسْتَعِينُ بِمُشْرِكٍ ‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጥምቀት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥138 *የአላህን የተፈጥሮ ጥምቀት ያዙ፡፡ በማጥመቅም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? ማንም የለም፤ እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን በሉ*። صِبْغَةَ اللَّـهِ ۖ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّـهِ صِبْغَةً ۖ وَنَحْنُ لَهُ عَابِدُون

"ጥምቀት" የሚለው የግሪኩ ቃል "ፓፕቲዝማ" βαπτισμός ሲሆን "ፓፕቲዞ" βάπτω ማለትም "ጠለቀ" ወይም "ተነከረ" ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ "መነከር" ወይም "መጥለቅ" የሚል ፍቺ አለው። ጥምቀት በባይብል የተለያየ ጥምቀት አለ፦ የውኃ ጥምቀት፣ የንስሐን ጥምቀት፣ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፣ የእሳት ጥምቀት፣ የመከራ ጥምቀት ወዘተ.. እነዚህን ነጥብ በነጥብ እስቲ እንያቸው፦

ነጥብ አንድ
"የውኃ ጥምቀት"
የውኃ ጥምቀት ሙሉ ሰውነትን ወደ ውኃ ውስጥ ማስገባትን ወይም ወደ ውኃ ውስጥ መጥለቅን ወይም ውኃው በሰው ላይ መፍሰሱን አሊያም መረጨቱን የሚያሳይ ነው፤ ለምሳሌ እስራኤላውያን በኤርትራ ባህር ሲሻገሩ እና በደመናው ዓምድ ሲያልፉ ከደመናው እና ከባህር ተጠመቁ ተብሏል፦
1ኛ ቆሮንቶስ 10፥1-2 ወንድሞች ሆይ፥ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ። አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባሕር መካከል ተሻገሩ፤ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ "በደመናና በባሕር ተጠመቁ""፤

የክርስቶስን ጥላነት"typology" ያሳያል የሚባለው ትምህርት ላይ ልዩ ልዩ የመታጠብ ስርዓት በመሴ ህግ ሰፍሮ ይገኛል፤ ይህ መታጠብ ግሪኩ ጥምቀት ይለዋል፤ "መታጠብ" ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል "ፓፕቲዞሞስ" βαπτισμοῖς ሲሆን መጠመቅ ማለት ነው፤ ይህም ልዩ ልዩ መታጠብ "ጥምቀቶች" ተብሏል፦
ዕብራውያን 9:10 እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ""ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም"" βαπτισμοῖς የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም።"
ዕብራውያን 6:1-2 ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ እንሂድ፤ መሠረትን ደግመን አንመሥርት፥ እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐና በእግዚአብሔር እምነት፥ ስለ ""ጥምቀቶች"" እና እጆችንም ስለ መጫን ስለ ሙታንም ትንሣኤ ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው።

ነጥብ ሁለት
"የንስሐን ጥምቀት"
በተመሳሳይ ይህ የውኃ ጥምቀት መጥምቁ ዮሐንስ ለንስሃ የኃጢአት ስርየት ያጠምቅ ነበር፤ ይህ ጥምቀት የንስሐን ጥምቀት ይባላል፦
ማርቆስ 1:4 ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ "የንስሐንም ጥምቀት" ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።

ይህ የንስሐን ጥምቀት በውኃ ሲሆን ለመሲሁ መምጣት መስተንግዶ ነበር፤ ከዚህ ውጪ ኢየሱስ የውኃ ጥምቀት ተጠመቁ ወይም አጥምቁ ብሎ አላስተማረም። ማርቆስ 16፥16 ላይ "ያመነ የተጠመቀም ይድናል" ተብሎ ኢየሱስ እንደተናገረ የሚነገርለት ይህ ጥቅስ ኢየሱስ በሕይወት ዘመኑ የተናገረው ንግግር አይደለም ብለው ምሁራን ያትታሉ፥ ማርቆስ 16.9-20 ያለው የማርቆስ ክፍል አይደለም። በጣም ስመጥርና ገናና የሚባሉ የግሪክ እደ-ክታባት"manuscripts" በሆኑት በሳይናቲከስ፣ በቫቲካነስ፣ በአሌክሳንዲረስ፣ በኤፍሬማይ ላይ የሉም። ይህን ጉዳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ኦርቶዶስ፣ ካቶሊክና ፕሮተስታንት 1980 ባሳተሙት የአዲስ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ ላይ አስፍረውታል፣ ከዚያም ባሻገር ይህ ቃል የኢየሱስ ንግግር እንዳልሆነ በውጪው ዓለም አገር ያወቀው ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው። በተጨማሪ ማቴዎስ 28፥19 ላይ "በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው" ተብሎ ኢየሱስ እንደተናገረ የሚነገርለት ይህ ጥቅስ ኢየሱስ በሕይወት ዘመኑ የተናገረው ንግግር አይደለም ብለው ምሁራን ያትታሉ፣ ማቴዎስ 28፥19 ያለው ክፍል "በስሜ ደቀመዛሙርት አድርጉ" በሚል የተለወጠ ነው ብለው የተለያዩ መድብለ-እውቀቶች"Encyclopedias" ሆነ የባይብል ማብራሪያዎች ያትታሉ። ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1. The Interpreters Dictionary of the Bible, 1962, page 351
2. The Anchor Bible Dictionary, Vol. 1, 1992, page 585:
3. The International Standard Bible Encyclopedia, Vol. 4, page 2637,
4. Word Biblical Commentary, Vol 33B, 1975, page 887-888:

ነጥብ ሶስት
"የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት"
የብዙዎች ክርስቲያኖች ጥምቀት ሲባል ሁልጊዜ በውኃ መጠመቅ ብቻ አርገው ያስባሉ፤ ነገር ግን በአንድ ነገር ውስጥ መጥለቅ ወይም መነከር እራሱ ጥምቀት ነው፤ ይህንን በየመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ማየት ይቻላል፦
ማርቆስ 1:8 እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን "በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል" እያለ ይሰብክ ነበር።"
የሐዋርያት ሥራ 1:5 ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና፥ እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ ""በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ"" አለ።
1ኛ ቆሮንቶስ 12፥13 "በአንድ መንፈስ" አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና።

መቼም በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ ማለት በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር ስር መሆን እንጂ ሌላ በውኃ እንደመጠመቅ አይደለም።
ነጥብ አራት
"የእሳት ጥምቀት"
የእሳት ጥምቀት የሚለውን ቀደምት አብራሪዎች ሮማውያን እስራኤላውያንን በእሳት ማጥፋታቸው ነው የሚል ፍቺ አላቸው፤ ስንዴውን በጎተራ ከቶ በመንፈስ ቅዱስ ካጠመቀ በኃላ ገለባውን በእሳት ያቃጥላል ስለሚል የእሳት ጥምቀት በዚህ ይተረጉሙታል፦
ሉቃስ 3፥16-17 ዮሐንስ መልሶ። እኔስ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን የጫማውን ጠፍር መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ እና "በእሳት ያጠምቃችኋል፤ መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን ""በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል"" አላቸው።

ዘመነኞቹ የካሪዝማ ተንታኞቹ ደግሞ አይ የእሳት ጥምቀት በተደጋጋሚ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ልምምድ ነው፤ ምክንያቱን መንፈስ ቅዱስ የሚቀጣጠል እሳት ተብሏል የሚል ሙግት አላቸው፦
ሐዋርያት ሥራ 18፥25 የዮሐንስንም ጥምቀት ብቻ አውቆ *በመንፈስ ሲቃጠል* ስለ ኢየሱስ ይናገርና በትክክል ያስተምር ነበር።
ሮሜ 12፥11 "በመንፈስ የምትቃጠሉ" ሁኑ፤

አሁንም ልብ አድርጉ በእሳት መጠመቅ ፍካሬአዊ እንደሆነ እንጂ እማሬአዊ እንዳሆነ ቅቡል ነው።

ነጥብ አምስት
"የመከራ ጥምቀት"
ኢየሱስ በውኃ በመጥምቁ ዮሐንስ ከተጠመቀ በኃላ ሌላ የሚጠመቀው ጥምቀት እንደቀረው ይናገራል፦
ሉቃስ 12፥50 ነገር ግን ""የምጠመቃት ጥምቀት"" አለችኝ፥ እስክትፈጸምም ድረስ እንዴት እጨነቃለሁ?

ይህ ጥምቀት በስደት ወይንም በእንግልት ውስጥ ማለፍን ያሳያል፤ ይህንን ጥምቀት ሃዋርያትም ከእርሱ ጋር እንደሚጠመቁ ተናግሯል፦
ማርቆስ 10፥38 ኢየሱስ ግን፦ የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ፥ እኔ ""የምጠመቀውንስ ጥምቀት"" ልትጠመቁ ትችላላችሁን? አላቸው። እነርሱም፦ እንችላለን አሉት። ኢየሱስም፦ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፥ ""እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ""፤

አሁንም ልብ አድርጉ በመከራ መጠመቅ ፍካሬአዊ እንደሆነ እንጂ እማሬአዊ እንዳሆነ እሙን ነው።
ከላይ የደረደርኳቸው የሙግት ነጥቦችpremises" በኢስላም ጥምቀት እንዳለ ለማሳየት ነው፥ ሙሥሊም ሲፈጠር የሚጠመቅበት የሃይማኖት ጥምቀት ኢሥላም ነው። ይህ ጥምቀት በ 40 ቀን ወይም በ 80 ቀን አሊያም ለአቅመ ኣደምና ሐዋ ስንደርስ የምንጠመቀው ሳይሆን በተፈጥሮ የምንጠመቀው ጥምቀት ነው፥ አጥማቂውን ቄስ አሊያም ፓስተር ሳይሆን የዓለማቱ ጌታ አላህ ነው፦
2፥138َ Our religion is the Baptism of Allah: And who can baptize better than Allah? And it is He Whom we worship. Yusuf Ali
*የአላህን የተፈጥሮ ጥምቀት ያዙ፡፡ በማጥመቅም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? ማንም የለም፤ እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን በሉ*። صِبْغَةَ اللَّـهِ ۖ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّـهِ صِبْغَةً ۖ وَنَحْنُ لَهُ عَابِدُون

አምላካችን አላህ ሰዎችን የፈጠረው እርሱን እንዲያመልኩና እንዲታዘዙ ስለሆነ ኢሥላም አላህ ሰዎችን የፈጠረበት ሃይማኖት ነው፦
30፥30 ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን *”አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን ሃይማኖት ያዟት”*፡፡ فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًۭا ۚ فِطْرَتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِى فَطَرَ ٱلنَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ ٱللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ ٱلدِّينُ ٱلْقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

“ሙስሊም” مُسْلِم የሚለው ቃል “አስለመ” أَسْلَمَ “ታዘዘ”፣ “ተገዛ”፣ ” አመለከ” “ሁሉ ነገሩን ሰጠ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው፥ “ኢስላም” إِسْلَٰم ደግሞ ሃይማኖቱ ነው። አላህ ሰውን ሲፈጥር በተፈጥሮ ጥምቀት ሲሆን የህፃኑ ወላጆቹ ግን አይሁዳዊ ወይም ክርስቲያን አሊያም ዞሮስተርያን ያደርጉታል፦
ኢማም ቡኻርይ መፅሐፍ 23, ሐዲስ 138
ከአቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተላለፈው ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- *“ማንም የሚወለድ ሰው “በአል-ፊጥራ በኢሥላም ላይ ሆኖ እንጂ አይወለድም”። ወላጆቹ ግን አይሁዳዊ ያደርጉታል ወይም ክርስቲያን ያደርጉታል አሊያም ዞሮስተርያን ያደርጉታል እንጂ”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ كُلُّ مَوْلُودٍ يُولَدُ عَلَى الْفِطْرَةِ، فَأَبَوَاهُ يُهَوِّدَانِهِ أَوْ يُنَصِّرَانِهِ أَوْ يُمَجِّسَانِهِ

“አል-ፊጥራህ” الْفِطْرَةِ ማለት “ተፈጥሮ” ማለት ነው። አንድ ሰው ከካፊር ቤተሰብ ተወልዶ ወላጆቹ እስከሚያከፍሩት ወይም በአንደበቱ እኔ የዚህ እምነት ተከታይ ነኝ እስከሚል ድረስ በኢሥላም ሥር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 38
አቢ ሙዓዊያህ እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም የሚወለድ ሰው በአል-ፊጥራ በኢሥላም ላይ ሆኖ እንጂ አይወለድም፥ በአንደበቱ እስከሚል ድረስ”*። لَيْسَ مِنْ مَوْلُودٍ يُولَدُ إِلاَّ عَلَى هَذِهِ الْفِطْرَةِ حَتَّى يُعَبِّرَ عَنْهُ لِسَانُهُ

አላህ ሰዎችን በቀጥተኛው መንገድ በኢሥላም ላይ ፈጥሮ ሳለ ሸያጢን ግን ከዚህ ዲን በሺርክ ምክንያት ሰዎችን ያርቃሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐግ 53, ሐዲስ 76
ዒያድ ኢብኑ ሒማር እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” ኹጥባህ በሚደረግበት ቀን እንዲህ አሉ፦ *”ለእናንተ ያስተማርኩት ጌታዬ ያዘዘኝ፥ እናንተ የማታውቁትን እርሱ ዛሬ ያሳወቀኝን። አላህም አለ፦ “እኔ የሰጠኃቸውንና ሕጋዊ የሆነላቸው ያ ሁሉ ንብረት ነው። እኔ ሁሉንም ባሮቼን በቀጥተኛው መንገድ ላይ ፈጠርኳቸው፥ ሸያጢን መጥተው ከዲናቸው አራቋቸው”*። عَنْ عِيَاضِ بْنِ حِمَارٍ الْمُجَاشِعِيِّ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ذَاتَ يَوْمٍ فِي خُطْبَتِهِ ‏”‏ أَلاَ إِنَّ رَبِّي أَمَرَنِي أَنْ أُعَلِّمَكُمْ مَا جَهِلْتُمْ مِمَّا عَلَّمَنِي يَوْمِي هَذَا كُلُّ مَالٍ نَحَلْتُهُ عَبْدًا حَلاَلٌ وَإِنِّي خَلَقْتُ عِبَادِي حُنَفَاءَ كُلَّهُمْ وَإِنَّهُمْ أَتَتْهُمُ الشَّيَاطِينُ فَاجْتَالَتْهُمْ عَنْ دِينِهِم

ስንቋጨው ይህንን የተፈጥሮ ጥምቀት ልክ እንደ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፣ የእሳት ጥምቀት፣ የመከራ ጥምቀት በፍካሬአዊ እንረዳዋለን እንጂ ልክ እንደ የውኃ ጥምቀት በእማሬአዊ አንረዳውም። አላህ በተፈጥሮ ጥምቀት ፀንተው ከሚሞቱ ሙሥሊም ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የውርስ ኀጢአት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም*፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ

በቁርአን እስተምህሮት ውስጥ እንደ ክርስትናው “ጥንተ-ተአብሶ”Original sin” ማለትም እንደ ስኳርና ሳይነስ ለትውልድ በዘር የሚተላለፍ ኃጢአት የለም፤ ኃጢአት ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም፤ አምላካችን አላህ ብዙ አንቀጾቹ ላይ፦ “ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም” እያለ ይነግረናል፦
17፥15 *የተመራ ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው ጉዳቱ በእርሷ ላይ ነው፡፡ ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም*፡፡ مَّنِ اهْتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهْتَدِي لِنَفْسِهِ ۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيْهَا ۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ

እዚህ ድረስ ከተግባባን የሚቀጥለውን አንቀፅ እንዲህ መረዳት ይቻላል፦
16፥25 ይህንንም የሚሉት በትንሣኤ ቀን ኀጢኣቶቻቸውን በሙሉ *”ከእነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኀጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው”*፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ኃጢኣት ምንኛ ከፋ! لِيَحْمِلُوا أَوْزَارَهُمْ كَامِلَةً يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۙ وَمِنْ أَوْزَارِ الَّذِينَ يُضِلُّونَهُم بِغَيْرِ عِلْمٍ ۗ أَلَا سَاءَ مَا يَزِرُونَ

አንድ ሰው ሌላውን ሰው ሲያሳስት አሳሳቹ በማሳሳቱ ምክንያት የተሳሳተው ሰው የሚያገኘውን ቅጣት ከሚሳሳተው ላይ ቅጣቱ ሳይቀነስ ሳይጨመር የተሳሳተውን ሰው ቅጣት አሳሳቹ ይቀበላል፤ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ከመራ መሪው በመምራቱ ምክንያት የተመራው ሰው የሚያገኘውን አጅር ከሚመራው ላይ አጅሩ ሳይቀነስ ሳይጨመር የተመራውን ሰው አጅር መሪው ይቀበላል፤ ከላይ ያለው መልክእት ይህ ነው፤ ኢብኑ ከሲር ይህንን አንቀፅ በሐዲስ እንዲህ ይፈስረዋል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ማንም ጠሪ ሰዎችን ወደ ጥመት የሚጣራ የተከተሉት ሰዎች የሚሸከሙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይጓደል ይሸከማል፤ ማንም ጠሪ ሰዎችን ወደ ምሪት የሚጣራ የተከተሉት ሰዎች የሚያገኙትን ምንዳ ከእነርሱ ላይ ሳይጓደል ያገኛል”*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ أَيُّمَا دَاعٍ دَعَا إِلَى ضَلاَلَةٍ فَاتُّبِعَ فَإِنَّ لَهُ مِثْلَ أَوْزَارِ مَنِ اتَّبَعَهُ وَلاَ يَنْقُصُ مِنْ أَوْزَارِهِمْ شَيْئًا وَأَيُّمَا دَاعٍ دَعَا إِلَى هُدًى فَاتُّبِعَ فَإِنَّ لَهُ مِثْلَ أُجُورِ مَنِ اتَّبَعَهُ وَلاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِهِمْ شَيْئًا ‏”

ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም ማለት ለምሳሌ መቶ ኪሎ ጤፍ ተሸክሜ ከነበረ ሌላ ሰው ለእኔ ጤፉን ከተሸከመልኝ እኔ ላይ መቶ ኪሎ ጤፍ የለም ማለት ነው፤ ግን አጥማሚ የጠመመውን ሰው በእርሱ ምክንያት ነውና ከእርሱ ቅጣት ሳይጓደል ይቀጣል፤ ለምሳሌ ቃየል የአደም ልጆች መግደልን ያስተማረ ነው፤ ሰዎች ሰው በገደሉ ቁጥር ገዳዩ ሊቀጣበት ያለውን ቅጣት ቃየልም ይቀጣል፤ ያ ማለት ገዳዩ ቅጣቱ ይቀልለታል ማለት አይደለም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 28, ሐዲስ 38
ዐብደላህ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“በግፍ ገዳይ አንድም ሰው የለም፥ የእርሱ ወንጀል ድርሻ በመጀመሪያው የአደም ልጅ ላይ ቢሆን እንጂ፤ ምክንያቱም እርሱ ግድያን በማስተዋወቅ የመጀመሪያ ነበር”*። عَنْ عَبْدِ، اللَّهِ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لاَ تُقْتَلُ نَفْسٌ ظُلْمًا إِلاَّ كَانَ عَلَى ابْنِ آدَمَ الأَوَّلِ كِفْلٌ مِنْ دَمِهَا لأَنَّهُ كَانَ أَوَّلَ مَنْ سَنَّ الْقَتْلَ ‏”
ስለዚህ አላህ በሰው ቀኝና ግራ ባሉት መላእክት የሚከትበው ሰዎች የሰሩትን መልካምና ክፉ ስራ ብቻ ሳይሆን “ፈለጎቻቸውንም” ማለትም ያጠመሙትን ወይም የመሩትን ስራ ጭምር ነው፤ አንድ ሰው በመመሳቱ ብቻ ሳይሆን በማሳሳቱም ይጠየቃል፦
36፥12 እኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን፡፡ *”ያስቀደሙትንም ሥራ እና ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን”*፡፡ إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا وَآثَارَهُمْ ۚ وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ فِي إِمَامٍ مُّبِينٍ

ቀጥሎ ያለውን ውዥንብር ተመልከቱ፦ “አላህ በመሐመድ”ﷺ” ዘመን የነበሩትን አይሁድ አባቶቻቸው በሠሯቸው ኃጢኣቶች ሳብያ ሲወቅሳቸው እንመለከታለን፦
2፥51 ሙሳንም አርባን ሌሊት በቀጠርነው ጊዜ የኾነውን አስታውሱ፡፡ ከዚያም ከእርሱ መኼድ በኋላ *”እናንተ በዳዮች ስትኾኑ ወይፈንን አምላክ አድርጋችሁ ያዛችሁ”*፡፡ وَإِذْ وَٰعَدْنَا مُوسَىٰٓ أَرْبَعِينَ لَيْلَةًۭ ثُمَّ ٱتَّخَذْتُمُ ٱلْعِجْلَ مِنۢ بَعْدِهِۦ وَأَنتُمْ ظَٰلِمُونَ

ይህ ከውርስ ኃጢኣት ጋር አንዳች ግንኙነት የውም። ይህ ጥቅላዊ አይሁዳውነትን የሚያሳይ እንጂ በተናጥል የአበውን ወንጀል ወደ ልጆች መሸከምን አያመለክትም። አላህ ደመናን ያጠለለውና መናን እና ድርጭትን ያወረደው በሙሳ ዘመን ቢሆንም በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ወደነበሩት አይሁድ፦ “በእናንተም ላይ ደመናን አጠለልን፡፡ በእናተም ላይ መናን እና ድርጭትን አወረድን” እያለ ይናገራል፦
2፥57 *”በእናንተም ላይ”* ደመናን አጠለልን፡፡ *”በእናተም ላይ”* መናን እና ድርጭትን አወረድን፡፡ وَظَلَّلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْغَمَامَ وَأَنزَلْنَا عَلَيْكُمُ ٱلْمَنَّ وَٱلسَّلْوَىٰ

“እናንተ” የሚለው ጥቅላዊ አነጋገር እንጂ በነቢያችን”ﷺ” ዘመን የነበሩት አይሁድ ደመናም አልጠለለላቸውም፥ እንዲሁ መናን እና ድርጭትን አልወረደላቸውም። አላህ ወደ ነብያት ያወረደው በነቢያችን”ﷺ” ዘመን ወደነበሩት አይሁድ እና ክርስቲያን “ወደ እናንተ አወረድን” ማለቱንም አስተውሉ፦
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ *በሉም፦ «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን”*፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን፡፡» وَلَا تُجَادِلُوا أَهْلَ الْكِتَابِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِلَّا الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

ስለዚህ “እናንተ” የሚለው ኃይለ-ቃል ጥቅላዊ መልእክት እንጂ በተናጥል የአበውን ወንጀል ለልጆች መተላለፉን በፍጹም አያሳይም። አበው ጥጃ በማምለካቸው ልጆችን እየወቀሰ ነው ማለት ነው ብሎ መሞገት ለአበው ደመናን አጠለልን፥ መናን እና ድርጭትን አወረድን የሚለውን ለልጆች ምን አደረገ ብሎ መረዳት ይቻላል? ይህ የቂል እንጉልፏቶ አስተሳሰብ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አምላክ ወይስ ጌታ?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

በግሪክ ኮይኔ የተዘጋጁ የአዲስ ኪዳን እደ-ክታባታት 5800 ገደማ ሲሆኑ፥ ከእነዚህ ዋና ዋናዎቹ ደግሞ ኮዴክስ ሳይናቲከስ፣ ኮዴክስ ቫቲካነስ፣ ኮዴክስ አሌክሳንድሪየስ፣ ኮዴክስ ኤፍሬማይ ናቸው። በ 330 ድኅረ-ልደት በተዘጋጀው በኮዴክስ ሳይናቲከስ እና በ 350 ድኅረ-ልደት በተዘጋጀው በኮዴክስ ቫቲካነስ መካከል የቃላት ሆነ የአሳብ ልዩነት አላቸው፥ ፊተኛው ኮዴክስ ሳይናቲከስ ያዘጋጁት ኢየሱስን "ጌታችን" ሲሉት ኃለኛው ኮዴክስ ቫቲካነስ ያዘጋጁት ደግሞ "አምላካችን" ብለውታል፦
2ኛ ጴጥሮስ 1፥1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ *በጌታችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ* ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ። ϲυμεων πετροϲ δουλοϲ και αποϲτο λοϲ ιυ χυ τοιϲ ϊϲο τιμον ημιν λαχου ϲιν πιϲτιν ειϲ δι καιοϲυνην του κυ ημων και ϲωτη ροϲ ιυ χυ

እዚህ አንቀጽ ላይ በኮዴክስ ሳይናቲከስ "ኮዩ" κυ ብሎታል፥ "ኮዩ" የሚለው ቃል "ኩስ" κος ለሚለው አገናዛቢ ዘርፍ ሲሆን "ጌታችን" ማለት ነው። "ኩስ" κος የሚለው "ኩርዮስ" κύριος ማለትም "ጌታ" ለሚለው ምጻረ ቃል ነው። ቀጣዩን ልዩነት ደግሞ እንመልከት፦
2ኛ ጴጥሮስ 1፥1 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ *በአምላካችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ* ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ። ϲυμεων πετροϲ δουλοϲ και αποϲτο λοϲ ιυ χυ τοιϲ ϊϲο τιμον ημιν λαχου ϲιν πιϲτιν ειϲ δι καιοϲυνην του θυ ημων και ϲωτη ροϲ ιυ χυ

እዚህ አንቀጽ ላይ በኮዴክስ ቫቲካነስ "ቶዩ" θυ ብሎታል፥ "ቶዩ" የሚለው ቃል "ቴስ” Θς ለሚለው አገናዛቢ ዘርፍ ሲሆን "አምላካችን" ማለት ነው። "ቴስ” Θς የሚለው “ቴኦስ” θεός ማለትም "አምላክ" ለሚለው ምጻረ ቃል ነው።
ታዲያ የቱ ነው ትክክል? ስንል ኮዴክስ ሳይናቲከስ በእድሜ ኮዴክስ ቫቲካነስን በ 20 ዓመት ስለሚበልጥ የቀደመው በአንጻራዊ ተአማኒት አለው።
ሲቀጥል የ 2ኛ ጴጥሮስ ደብዳቤ ዐውደ ንባቡን ስንመለከት በኮዴክስ ሳይናቲከስ የተቀመጠው ቃል "ጌታችን እና መድኃኒታችን" τοῦ Κυρίου ἡμῶν καὶ Σωτῆρος Ἰησοῦ Χριστοῦ የሚለው ሦስት ጊዜ ሐቲታዊ ፍሰት"exegetical outline" ሆኖ መምጣቱ በራሱ የ 2ኛ ጴጥሮስ ደራሲ የኮዴክስ ሳይናቲከስ አዘጋጆች አንጻራዊ እውነታ እንዳላቸው አመላካች ነው፦
2ኛ ጴጥሮስ 1፥11 እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ *ጌታችን እና መድኃኒታችን* ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና።
2ኛ ጴጥሮስ 2፥20 *በጌታችን እና በመድኃኒታችን* በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት።
2ኛ ጴጥሮስ 3፥18 ነገር ግን *በጌታችን እና በመድኃኒታችን* በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ።

የሚያጅበው ይህ የጴጥሮስ ድርሰት ኢፕስቴሌ ነው፥ "ኢፕስቴሌ" ἐπιστολή ማለት "ደብዳቤ" ማለት ነው። ይህ ደብዳቤ ለግለሰብ ወይም ለአጥቢያ የሚላክ ምክር እንጂ የፈጣሪ ንግግር ወይም የነቢይ ንግግር በፍጹም አይደለም።
ሲቀጥል የ 2ኛ ጴጥሮስ ደራሲ በተለምዶ "ጴጥሮስ ነው" ይባል እንጂ አብዛኛውን ለዘብተኛ ሆነ ጽንፈኛ ምሁራን በጴጥሮስ ስም የተዋሸ"Pseudepigrapha" እንደሆነ ያትታሉ፥ ጴጥሮስ የሞተው ከ 65–67 ድኅረ-ልደት በሚገመት ጊዜ ሲሆን ይህ ደብዳቤ የተጻፈው ግን ከ 100–150 ድኅረ-ልደት በሚገመት ጊዜ ነው። ዋቢ መጽሐፍ ይመልከቱ፦
Brown, Raymond E., Introduction to the New Testament, Anchor Bible, 1997, p. 767.

ስለዚህ በሥላሴ አማንያን ዘንድ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ተብሎ ከሚጠቀሱት ተወዳጅ አናቅጽ መካከል ይህ አንቀጽ ለኢየሱስ አምላክነት ማስረጃም መረጃም አይሆንም። በሐሰት ሰነድ ቴኦሎጂን ቴኦሎጃይስ ማድረግ እጅጉኑ ሲበዛ ወጨበሬነት ነው። "ጌታ" ማለት ደግሞ "አምላክ" ማለት አይደለም፥ ምክንያቱም "አምላክ ኢየሱስን ጌታ አደረገው" ስለሚል፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 አለ። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን *ኢየሱስን አምላክ θεός ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው* የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።

መቼም አንድ ጤነኛ የሆነ ሰው፦ "ፈጣሪን ፈጣሪ ጌታ አደረገው" ብሎ እንደማይቀበል እሙና ቅቡል ነው። ይስሐቅ ያዕቆብን ጌታ አደረግሁት ይላል፥ ዮሴፍ፦ “እግዚአብሔር ጌታ አደረገኝ” ይላል፦
ዘፍጥረት 27፥37 ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው። እነሆ፥ *ጌታህ አደረግሁት*፥
ዘፍጥረት 45፥9 *እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ*፤ ወደ እኔ ና፥ አትዘግይ!

"እግዚአብሔር ጌታ አደረገኝ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት፥ ይህም ስልጣንና ሹመትን አሊያም እልቅናና ክብርን ያመለክታል። "ኢየሱስ ጌታ ተደረገ" ሲባል "ያዕቆብ ጌታ ተደረገ" አሊያም "ዮሴፍ ጌታ ተደረገ" በተባለበት ሒሳብና ቀመር እንጂ እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ጌታ ማድረግ አያመለክትም። የኢየሱስ ጌትነት ልክ እንደ እግዚአብሔር በራሡ የተብቃቃ አሊያም የባሕርይ ገንዘቡ ሣይሆን እንደ ያዕቆብን እና ዮሴፍ በስጦታ ያገኘው ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአላህ ተመልካችነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥110 *”አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

"በሲር" بَصِير ማለት "ተመልካች" ማለት ሲሆን አላህ የትም ብንሆን ጊዜ እና ቦታ ሳይገድበው የምናደርገውን ሁሉ ተመልካች ነው፥ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነው፦
4፥86 *"አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነው"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ حَسِيبًا

"ሸይእ" شَيْءٍ ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን "ዘመካን" ነው፥ “ዘመካን” زَمَكَان ማለት የዘማንና የመካን ቃላት ውቅር ነው። “ዘማን” زَمَان ማለት “ጊዜ”time” ማለት ነው፥ “መካን” مَكَان ደግሞ “ቦታ”space” ማለት ነው። አላህ ነገርን ሁሉ በእይታው ይቆጣጠራል፦
2፥115 *ምሥራቁም ምዕራቡም የአላህ ነው፥ ፊቶቻችሁን ወደ የትም ብታዞሩ የአላህ ፊት እዚያ ነው፡፡ አላህ ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነውና*፡፡ وَلِلَّهِ الْمَشْرِقُ وَالْمَغْرِبُ ۚ فَأَيْنَمَا تُوَلُّوا فَثَمَّ وَجْهُ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ وَاسِعٌ عَلِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ወጅህ" وَجْه ማለት "ተመልካችነት" በሚል የመጣ ነው። የትም ብንዞር አላህ ይመለከተናል፥ የአላህ ቻይነትና ዐዋቂነት መገለጹ በራሱ የአላህ ፊት ማለት የአላህ ተመልካችነው መሆኑን ያሳያል። አላህ ነገርን ሁሉ በዓይኖቹ ቁጥጥር ውስጥ ነው፥ ከእርሱ የተሰወረ ምንም ነገር የለም፦
52፥48 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ *"አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና"*፡፡ ጌታህንም በምትነሳ ጊዜ ከማመስገን ጋር አወድሰው፡፡ وَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ فَإِنَّكَ بِأَعْيُنِنَا ۖ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ حِينَ تَقُومُ

"ጥበቃችን" ለሚለው የገባው ቃል "አዕዩኒና" أَعْيُنِنَا ነው። "አዕኑን" أَعْيُن የዐይን ብዙ ቁጥ ነው፥ "ዐይን" عَيْن የሚለው ቃል "ዓነ" عَانَ‎ ማለትም "ዓየ" "ተመለከተ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዓይን" "ዕይታ" "መመልከቻ" "ጥበቃ" በሚል ይመጣል፦
20፥39 በአንተ ላይም ከእኔ የኾነን መወደድ ጣልኩብህ፡፡ *በእኔም ጥበቃ ታድግ ዘንድ*፡፡ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مِّنِّي وَلِتُصْنَعَ عَلَىٰ عَيْنِي

"ጥበቃ" ለሚለው የገባው ቃል "ዐይን" عَيْن መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። የአላህ ዓይን ፍጥረታዊ ሳይሆን አምላካዊ፥ አካላዊ ሳይሆን መለኮታዊ ነው። በቋንቋ ደረጃ "ኡዙን" أُذُن ማለት "ጆሮ" ማለት ሲሆን "ሠሚዕ" سَّمِيع ማለትም "ሰሚ" ወይም "ሠምዕ" سَمْع ማለትም "መስሚያ" በሚል እንደሚመጣ ሁሉ "ዐይን" عَيْن የሚለውም "በሲር" بَصِير ማለትም "ተመልካች" ወይም "በሰር" بَصَر ማለትም "መመልከቻ" በሚል ይመጣል፦
32፥9 *ለእናንተም ጆሮዎችን፣ ዓይኖችን እና ልቦችንም አደረገላችሁ*፡፡ በጣም ጥቂትን ብቻ ታመሰግናላችሁ፡፡ وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۚ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ
67፥23 «እርሱ ያ የፈጠራችሁ *ለእናንተም መስሚያ፣ ማያዎችን እና ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው*፡፡ ጥቂትንም አታመስግኑም» በላቸው፡፡ قُلْ هُوَ الَّذِي أَنشَأَكُمْ وَجَعَلَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۖ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُونَ
76፥2 እኛ ሰውን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ *ሰሚ ተመልካችም አደረግነው*፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

ነገር ግን የአላህ መስማት እና ማየት ከማንም ጋር አይመሳሰልም። ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፥ እርሱን የሚመስል ምንም ነገር የለም፦
112፥4 *ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም*፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

አላህ ተመልካች ተብሏል፥ ሰውም ተመልካች ተብሏል። ግን አላህ ተመልካች የተባለበት ሰው በተባለበት ስሌትና ቀመር እንዳልሆነ እሙንና ቅቡል ነው፦
2፥110 *”አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
2፥96 *"አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው"*፡፡ وَاللَّهُ بَصِيرٌ بِمَا يَعْمَلُونَ
አያችሁ? አላህ ፍጡራን የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፥ ሰው ግን ፍጡራን የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች አይደለም። እሩቅ ሳንሔድ የእኛ የውጪ ዓይን ከውስጥ ዓይናችን ጋር አይመሳሰልም፦
22፥46 ለእነርሱም በእነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በእነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮች ይኖሯቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ *ዓይኖች አይታወሩም ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ*፡፡ أَفَلَمْ يَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَتَكُونَ لَهُمْ قُلُوبٌ يَعْقِلُونَ بِهَا أَوْ آذَانٌ يَسْمَعُونَ بِهَا ۖ فَإِنَّهَا لَا تَعْمَى الْأَبْصَارُ وَلَـٰكِن تَعْمَى الْقُلُوبُ الَّتِي فِي الصُّدُورِ
24፥44 አላህ ሌሊትንና ቀንን ያገላብጣል፡፡ በዚህም *ለባለ ውስጥ ዓይኖች* በእርግጥ ማስረጃ አለበት፡፡ يُقَلِّبُ اللَّهُ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبْرَةً لِّأُولِي الْأَبْصَارِ
7፥179 "ለእነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፡፡ ለእነርሱም በሳቸው *"የማያዩባቸው ዓይኖች"* አሉዋቸው፡፡ ለእነርሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا

“ሲፋህ” صِفَة የሚለው ቃል “ወሰፈ” وَصَفَ‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ባሕርይ” ማለት ነው። የአላህ ማየት የእርሱ ሲፋህ ሆኖ በቁርኣን ተወስፏል፥ ይህንን የአላህ ባሕርይ ያለ ተክዪፍ፣ ያለ ተሽቢህ፣ ያለ ተሕሪፍ፣ ያለ ተዕጢል "አላህ ዓይን አለው" ብለን እናምናለን።
1. “ተክዪፍ” تَكْيِيف ማለት “እንዴት ብሎ መፈላሰፍ” ነው፣
2. “ተሽቢህ” تَشبِيه‎ ማለት “ከፍጡር ጋር ማመሳሰል” ነው፣
3. “ተሕሪፍ” تَحْرِيف ማለት “ትርጉሙን ማዛባት” ነው፣
4. “ተዕጢል” تَعْطِيل ማለት “ትርጉም የለሽ ማድረግ” ነው።

ያለ ተክዪፍ፣ ያለ ተሽቢህ፣ ያለ ተሕሪፍ፣ ያለ ተዕጢል “አላህ ዓይን አለው” ብሎ ማመን የሠለፍ መንሃጅ ነው፥ ይህ ቅኑ የሠለፎች መንሃጅ ከተገለጸ በኃላ ከምእመናኑ መንሃጅ ሌላ የኾነን መንሃጅ መከተል በዲንያህ ጥመት ነው፥ በአኺራም የእሳት መሆን ነው፦
4፥115 *ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእመናኑ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው በዚህ ዓለም በተሾመበት ጥመት ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን*፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا

ይህ ያን ያህል ከባድ እሳቤ ሆኖ ጥያቄ የሚያስነሳ አልነበረም። እስቲ በነካ እጃችን ነጥቡን ወደ ንጽጽር እናዙረውና ከባይብል እናነጻጽር፥ በባይብል እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ መንፈስ ስጋና አጥንት የለውም" ይለናል፦
ዮሐንስ 4፥24 *እግዚአብሔር “መንፈስ” ነው*።
ሉቃስ 24፥39 *“መንፈስ ሥጋ እና አጥንት የለውምና”*።

እግዚአብሔር ስጋ ከሌለው እንዴት ዓይን ይኖረዋል? "የእግዚአብሔር ዓይኖች" ይለናል፦
መዝሙር 34፥15 *"የእግዚአብሔር ዓይኖች"* ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።
ኢዮብ 10፥4 *“በውኑ የሥጋ ዓይን” አለህን? ወይስ ሰው እንደሚያይ ታያለህን?*

አይ "እግዚአብሔር የስጋ ዓይን የለውም፥ ሰው እንደሚያይ ዓያይም" ከተባለ እንግዲያውስ የእርሱ ዓይን አካላዊ ሳይሆን መንፈሳዊ፥ ብርሃን የሚቀበል ሌንስ ያለው ተፈጥሮአዊ ሳይሆን መለኮታዊ ነው ማለት ነው። ይህንን በቀላሉ መረዳት ከተቻለ የአላህ ዓይን ብርሃን የሚቀበል ሌንስ ያለው ፍጥረታዊ ሳይሆን አምላካዊ፥ አካላዊ ሳይሆን መለኮታዊ ነው ብሎ መቀበል ምክንያታዊ ነው። ከእግዚአብሔር በተለየ መልኩ ኢየሱስ ብርሃን የሚቀበል ሌንስ ያለው ተፈጥሮአዊ ዓይኖች እናቱ ማኅፀን ውስጥ ተፈጥሮለታል፥ ይህ ዓይን እንባ የሚያፈስ የስጋ ዓይን ነው፦
ዮሐንስ 17፥1 ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ *ዓይኖቹን አነሣና* እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል።
ዮሐንስ 11፥35 *ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አደም እና ዝርዮቹ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

7፥11 *በእርግጥም ፈጠርናችሁ፡፡ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክት «ለአዳም ስገዱ» አልን*፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ ዲያብሎስ ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَاكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَاكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ لَمْ يَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ

“ኀጢአት” ማለት አበሳ፣ አመፅ፣ አለመታዘዝ፤ ወንጀል፣ ጥፋት ሲሆን አላህ አድርግ ወይም አታድርግ የሚለውን ትእዛዝ መተላለፍ ነው፤ ኀጢአት አለመታዘዝ ከሆነ አደም የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም፦
20፥121 ከእርሷም በሉ፡፡ ለእነርሱም ኀፍረተ ገላቸው ተገለጸች፡፡ ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር፡፡ *”አደምም የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም”*፡፡ فَأَكَلَا مِنْهَا فَبَدَتْ لَهُمَا سَوْءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ ٱلْجَنَّةِ ۚ وَعَصَىٰٓ ءَادَمُ رَبَّهُۥ فَغَوَىٰ

አደምና ሐዋም በሰሩት ስህተት፦ “ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፡፡ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን” በማለት ንስሃ ገብተዋል፤ አላህም ጸጸትን በመቀበል ተመለሰላቸው፤ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፦
7፥23 *«ጌታችን ሆይ! እራሳችችንን በደልን፡፡ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ*፡፡ قَالَا رَبَّنَا ظَلَمْنَا أَنفُسَنَا وَإِن لَّمْ تَغْفِرْ لَنَا وَتَرْحَمْنَا لَنَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ
20፥122 *”ከዚያም ጌታው መረጠው ከእርሱም ጸጸቱን ተቀበለው”* መራውም፡፡ ثُمَّ اجْتَبَاهُ رَبُّهُ فَتَابَ عَلَيْهِ وَهَدَىٰ
2፥37 *አደምም ከጌታው ቃላትን ተቀበለ፡፡ በእርሱ ላይም ጌታው ጸጸትን በመቀበል ተመለሰለት፤ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና*፡፡ فَتَلَقَّىٰ آدَمُ مِن رَّبِّهِ كَلِمَاتٍ فَتَابَ عَلَيْهِ ۚ إِنَّهُ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ከአደም ወደ ዝርዮቹ የተላለፈ ምንም አይነት የውርስ ኀጢአት የለም። ሞት በውርስ ኀጢአት በአዳም መጣ ብሎ ያስተማረ ጳውሎስ እንጂ ነብያት ወይም ሐዋርያት አይደሉም። አደምና ሐዋም ለሰሩት ወንጀል ቶብተው አላህ ይቅር ብሏቸዋል፤ አደምና ሐዋም ባይጸጸቱ ኖሮ ወደፊት በጀሃነም ይቀጡ ነበር፤ ነገር ግን ስለተጸጸቱ አላህ ለተጻቾች ባዘጋጀው ዘላለሚቱ ጀነት ይገባሉ፦
3፥133 *ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረት እና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ*፡፡ وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ
85፥10 እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን ያሰቃዩ፣ *ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አላቸው*፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ
8፥33 *እነርሱ ምህረትን የሚለምኑ ሲኾኑ የሚቀጣቸው አይደለም*፡፡ وَمَا كَانَ اللَّهُ مُعَذِّبَهُمْ وَهُمْ يَسْتَغْفِرُونَ

እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አላህ በነብያችም”ﷺ” ዘመን እኛን በሁለተኛ መደብ፦ “በእርግጥም ፈጠርናችሁ፥ ከዚያም ቀረጽናችሁ” ይለናል፤ ከዚያም ከፈጠረንና ከቀረጸን በኃላ፦ “ለመላእክት «ለአዳም ስገዱ» አለ፦
7፥11 *በእርግጥም ፈጠርናችሁ፥ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክት «ለአዳም ስገዱ» አልን*፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ ዲያብሎስ ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَاكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَاكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ لَمْ يَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ

ለአደም እና ለሐዋ ቢሆን ኖሮ በሙተና “ኸለቅናኩማ” خَلَقْنَاكُما “ሰወርናኩማ” صَوَّرْنَاكُما ይሆን ነበር፤ ነገር ግን ከሁለት በላይ እኛን ለማሳየት በጀመዕ “ኸለቅናኩም” خَلَقْنَاكُمْ “ሰወርናኩም” صَوَّرْنَاكُمْ ነው የሚለው፤ ከዚያም ለመላእክት ለአደም ስገዱ አለ፤ ይህንን ከማለቱ በፊት እኛ ተፈጥረን ነበርን? አዎ እኛ የአደም ዘር ሆነን በአብራክ ውስጥ አለን፦
7፥172 *”ጌታህም ከአደም ልጆች ከጀርቦቻቸው ዘሮቻቸውን ባወጣና፦ «ጌታችሁ አይደለሁምን?» ሲል በነፍሶቻቸው ላይ ባስመሰከራቸው ጊዜ የኾነውን አስታውስ፡፡ «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ፡፡ «በትንሣኤ ቀን ከዚህ ኪዳን ዘንጊዎች ነበርን እንዳትሉ፡፡»* وَإِذْ أَخَذَ رَبُّكَ مِن بَنِي آدَمَ مِن ظُهُورِهِمْ ذُرِّيَّتَهُمْ وَأَشْهَدَهُمْ عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ أَلَسْتُ بِرَبِّكُمْ ۖ قَالُوا بَلَىٰ ۛ شَهِدْنَا ۛ أَن تَقُولُوا يَوْمَ الْقِيَامَةِ إِنَّا كُنَّا عَنْ هَـٰذَا غَافِلِينَ
“ዘሮቻቸው” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዙረየተሁም” ذُرِّيَّتَهُمْ ሲሆን አላህ አደምን በፈጠረ ጊዜ ጀርባውን አበሰው፤ ከጀርባው ሁሉንም ነፍስ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከዝርያው የሚፈጥረውን አወጣ፤ “ጌታችሁ አይደለሁምን? ሲል በነፍሶቻቸው ላይ አስመሰከረባቸው፤ እነርሱም «ጌታችን ነህ መሰከርን» አሉ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 9
አነሥ እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”አላህም በትንሹ ቅጣት ለሚቀበል ለእሳት ሰው፦ “በምድር ላይ ሀሉም ነገር ከነበረክ፥ ራስክን ከዚህ ነጻ ለማውጣት ይቻለሃልን? እርሱም፦ አዎ! ይላል። ከዚያም አላህ፦ “ከዚህ ያነሰ ነገር በአደም ጀርባ በነበርክበት ጊዜ በእኔ እንዳታሻርክ ጠይቄህ ነበር፤ ነገር ግን አንተ አሻረክ*። عَنْ أَنَسٍ، يَرْفَعُهُ ‏ “‏ أَنَّ اللَّهَ، يَقُولُ لأَهْوَنِ أَهْلِ النَّارِ عَذَابًا لَوْ أَنَّ لَكَ مَا فِي الأَرْضِ مِنْ شَىْءٍ كُنْتَ تَفْتَدِي بِهِ قَالَ نَعَمْ‏.‏ قَالَ فَقَدْ سَأَلْتُكَ مَا هُوَ أَهْوَنُ مِنْ هَذَا وَأَنْتَ فِي صُلْبِ آدَمَ أَنْ لاَ تُشْرِكَ بِي‏.‏ فَأَبَيْتَ إِلاَّ الشِّرْكَ ‏”‌‏.‏
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3356
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”አላህ አደምን በፈጠረ ጊዜ ጀርባውን አበሰው፤ ከጀርባው ሁሉንም ነፍስ እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ከዝርያው የሚፈጥረውን አወጣ”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَمَّا خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ مَسَحَ ظَهْرَهُ فَسَقَطَ مِنْ ظَهْرِهِ كُلُّ نَسَمَةٍ هُوَ خَالِقُهَا مِنْ ذُرِّيَّتِهِ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَة

“ዝርያው” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዙረየቲሂ” ذُرِّيَّتِهِ ሲሆን ከእናት እና አባት ከመፈጠራችን በፊት በአደም አብራክ ውስጥ ነበርን፤ አደም በጀነት እያለ በእርሱ አብራክ ውስጥ ዘሩ ነበረ፤ ሲወጣም አብሮ ከጀነት ወጥቷል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 140
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”አደም እና ሙሳ እርስ በእርሳቸው ተሟገቱ፤ ሙሳም፦ “አንተ አደም ያ ዝርያህን ከጀነት ያስወጣህ ነህ። አደምም አለ፦ “አንተ ሙሳ አላህ በመልእክቱ የመረጠክ እና ያናገረክ ነህ፤ ከመፈጠሬ በፊት በተቀደረው ነገር ትወቅሰኛለህን? ያኔ አደም ሙሳን እረታው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ احْتَجَّ آدَمُ وَمُوسَى، فَقَالَ مُوسَى أَنْتَ آدَمُ الَّذِي أَخْرَجْتَ ذُرِّيَّتَكَ مِنَ الْجَنَّةِ‏.‏ قَالَ آدَمُ أَنْتَ مُوسَى الَّذِي اصْطَفَاكَ اللَّهُ بِرِسَالاَتِهِ وَكَلاَمِهِ، ثُمَّ تَلُومُنِي عَلَى أَمْرٍ قَدْ قُدِّرَ عَلَىَّ قَبْلَ أَنْ أُخْلَقَ‏.‏ فَحَجَّ آدَمُ مُوسَى ‏

አደም ጀነት ውስጥ መኖሩ ጊዚያዊ እንጂ ዘላለማዊ አይደለም፤ ምክንያቱም ለዘላለም እንዲኖር ተፈጠረ የሚል አስተምህሮት በኢስላም የለም። ስለዚህ ከገነት መውጣቱ ውጤቱን አላህ ቀድሞውኑ በዕውቀቱ ቀድሮታል። “ዝርያህ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዙረየተከ” ذُرِّيَّتَكَ ሲሆን በአብራኩ ያለው ዘር በምድር ላይ እንዲኖር የቀደረው አላህ ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 390
ሑደይፋህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”አላህ ተባረክ ወተዓላ ሰዎችን ይሰበስባል፤ አማንያን ጀነት ወደ እነርሱ እስክትቀርብ ድረስ ይቆማሉ፤ ወደ አደም መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “አባታችን ሆይ! ጀነትን ለእኛ ክፈትልን፤ እርሱም፦ ማነው ከጀነት ያስወጣችሁ የአባታችሁ የአደም ህፀፅ አይደለምን? ያንን ለማድረግ ደረጃዬ አይደለም። የአላህ ወዳጅ ወደሆነ ወደ ልጄ ኢብራሂም መሄዱ የተሻለ ነው*። عَنْ حُذَيْفَةَ، قَالاَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ يَجْمَعُ اللَّهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى النَّاسَ فَيَقُومُ الْمُؤْمِنُونَ حَتَّى تُزْلَفَ لَهُمُ الْجَنَّةُ فَيَأْتُونَ آدَمَ فَيَقُولُونَ يَا أَبَانَا اسْتَفْتِحْ لَنَا الْجَنَّةَ ‏.‏ فَيَقُولُ وَهَلْ أَخْرَجَكُمْ مِنَ الْجَنَّةِ إِلاَّ خَطِيئَةُ أَبِيكُمْ آدَمَ لَسْتُ بِصَاحِبِ ذَلِكَ اذْهَبُوا إِلَى ابْنِي إِبْرَاهِيمَ خَلِيلِ اللَّهِ
ለእኛ አደም የነበረበት ጀነት እንድንገባ ቃል የተገባልን አንድም የተስፋ ቃል በቁርኣንም በባይብልም የለም። አደም ባይሳሳት ገነት ትኖሩ ነበር የሚል ቃል የለም። ቢኖር ኖሮ ትርጉም የሚሰጠው “እንድንወጣ ምክንያት ሆንከን” ሳይሆን “እንዳንገባ አስከለከልከን” ነበር መሆን የነበረበት። ምክንያቱም እንድንወጣ ምክንያት ሆንከን ለገባ ሰው ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው።
አደም በመሳሳቱ ሲወጣ ሰዎች በህልውና ደረጃ ሳይሆን በዘር ደረጃ በእርሱ አብራክ ይኖሩ ነበር። ይህ አገላለጽ ፍካሬአዊ እንጂ እማሪያዊ አይደለም፦
ዕብራውያን 7፥9-10 ይህንም ለማለት ሲፈቀድ፥ *አሥራትን የሚያስወጣ ሌዊ እንኳ በአብርሃም እጅ አሥራትን ሰጥቶአል፤ መልከ ጼዴቅ በተገናኘው ጊዜ ገና በአባቱ ወገብ ነበረና*።

ልብ አድርግ ሌዊ የአብርሃም የልጅ ልጅ ልጅ ነው፤ አብርሃም ለሌዊ ቅድመ-አያት ነው፤ አብርሃም መልከ ጼዴቅን በተገናኘው ጊዜ አልተወለደም አልተፈጠረም። ነገር ግን በአባቱ ወገብ ነበረ፤ ሌዊ በአባቱ ወገብ ሆኖ አስራት በአብርሃም እጅ ለመልከ ጼዴቅ ሰጥቷል። ግን ያ ዘር ቃል በቃል ነበረ እንዴ? አስራትስ ሰጥቷልን? በፍጹም! ይህ ዘር በአብራክ ይኖራል እንጂ ስብዕና ኖሮት አልኖረም ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ የአደም ዘር በአደም አብራክ ውስጥ ተፈጥሮ፣ አብሮ በጀነት ነበረ፣ ሲወጣም አብሮ ወጥቷል፤ ለመውጣቱ መንስኤ አደም ሲሆን ውጤቱ ግን አላህ አስቀድሞ ቀድሮታል። ሌላውን የሚነሳው ጥያቄ ይህ ሐዲስ ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3356
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦…. *አደም ተሳሳተ ዝርያዎችም ተሳሳቱ፣ አደም ረስቷል ዝርያዎችም ረስተዋል፤ አደም በድሏል፤ ዝርያዎችም በድለዋል*። فَجَحَدَ آدَمُ فَجَحَدَتْ ذُرِّيَّتُهُ وَنَسِيَ آدَمُ فَنَسِيَتْ ذُرِّيَّتُهُ وَخَطِئَ آدَمُ فَخَطِئَتْ ذُرِّيَّتُه

ይህ ሐዲስ ላይ አደም እንደሚሳሳት፣ እንደሚረሳ፣ እንደሚበድል ዝርያዎቹም ይሳሳታሉ፣ ይረሳሉ፣ ይበድላሉ ማለት እንጂ በአደም የተነሳ ይሳሳታሉ፣ ይረሳሉ፣ ይበድላሉ የሚል ሽታው የለም። ከዚያ ይልቅ የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፤ ነገር ግን በተውበት ወደ አላህ ከተመለሱ አላህ ይቅር ይላቸዋል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4392
አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የአደም ልጆች ሁሉ ተሳሳች ናቸው፡፡ ከተሳሳቾቹ ሁሉ በላጩ ግን ከስህተታቸው በተውበት ተመላሾቹ ናቸው”*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏:‏ ‏ “‏ كُلُّ بَنِي آدَمَ خَطَّاءٌ وَخَيْرُ الْخَطَّائِينَ التَّوَّابُونَ

አደም የኖረበት ጀነት በቁርኣን ሆነ በባይብል ሰማይ ላይ ነው የሚል የለም። አደም በጀነት ኖረ አልኖረ መሞቱ አይቀርም፤ ለሰው ልጅ ሰማይ ላይ እንደሚኖር ቃል አልተገባለትም። ሲፈጠር በምድር ላይ እንዲኖር ነው ቃል የተገባለት፦
2:30 ጌታህ ለመላእክት፡-«እኔ፦ *በምድር ላይ ምትክን አድራጊ ነኝ*» ባለ ጊዜ የኾነውን አስታውስ። وَإِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَائِكَةِ إِنِّي جَاعِلٌ فِي الْأَرْضِ خَلِيفَةً
መክብብ 1፥4 *”ትውልድ ይሄዳል፥ ትውልድም ይመጣል”*፤ ምድር ግን ለዘላለም ነው።
ዘፍጥረት 1፥28 እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ *”ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት”*፥
መዝሙር 115፥16 የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሔር ነው፤ *”ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት”*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ጠይቅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

10፥94 *”ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፡፡ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን”*፡፡ فَإِن كُنتَ فِي شَكٍّ مِّمَّا أَنزَلْنَا إِلَيْكَ فَاسْأَلِ الَّذِينَ يَقْرَءُونَ الْكِتَابَ مِن قَبْلِكَ ۚ لَقَدْ جَاءَكَ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُمْتَرِينَ

እሥልምና ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች፦ “ነቢያችሁ”ﷺ” ስለተጠራጠሩ እኛ ክርስቲያኖችን እንዲጠይቁ ታዘዋል” ይላሉ፤ እኛ ደግሞ በተቃራኒው እንዲህ አይነት ፍንጭ ሆነ ሽታው እንኳን የለውም ብለን ክፉኛ እንሞግታለን፤ ጥሬውን ከብስል ምርቱን ከእንክርዳር የሚለዩ ሊሂቃን፦ “ነገርን ከሥሩ ውኃን ከጡሩ” እንደሚሉት ኢንሻላህ ቁርኣንን ከሥሩ በማስተንተን አንቀጹን እንየው፦
10፥94 *”ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፡፡ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን”*፡፡ فَإِن كُنتَ فِي شَكٍّ مِّمَّا أَنزَلْنَا إِلَيْكَ فَاسْأَلِ الَّذِينَ يَقْرَءُونَ الْكِتَابَ مِن قَبْلِكَ ۚ لَقَدْ جَاءَكَ الْحَقُّ مِن رَّبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُمْتَرِينَ

ነጥብ አንድ
“ተንዚል”
“ተንዚል” تَنزِيل የሚለው ቃል “አንዘለ” أَنْزَلَ ወይም ማለትም “አወረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የተወረደ”Revelation” ማለት ነው። “ወደ አንተም ካወረድነው” ማለት ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደው ቁርኣን ነው፦
42፥3 እንደዚሁ አሸናፊው ጥበበኛው አላህ *”ወደ አንተ ያወርዳል፡፡ ወደ እነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት አውርዷል”*፡፡ كَذَٰلِكَ يُوحِي إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

“በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን” ማለት ተጠራጥረካል ማለትን አያሲዝም፥ “ኢን” إِن የምትለዋ ሁኔታዊ መስተዋድድ”conditional particle” ናት። ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደው የተውሒድ ትምህርት ነው፦
18፥110 *”እኔ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፥ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ “አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለትን ነው። የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ” በላቸው”*፡፡ قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

“ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙሥሊሚን” مُّسْلِمُون መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ ለዚህ አንድ አምላክ ፍጹም መታዘዝ “ኢሥላም” ይሰኛል።

ነጥብ ሁለት
“የሚያነቡትን”
“እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን” የተባሉት ከእርሳቸው በፊት የነበሩት መልእክተኞች ናቸው፦
7፥35 የአዳም ልጆች ሆይ! *”ከእናንተ ውስጥ በእናንተ ላይ አንቀጾቼን የሚያነቡ መልከተኞች ቢመጧችሁ”* ከእናንተ ክሕደትን የተጠነቀቁና መልካምንም የሠሩ በነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፡፡ እነሱም አያዝኑም፡፡ يَا بَنِي آدَمَ إِمَّا يَأْتِيَنَّكُمْ رُسُلٌ مِّنكُمْ يَقُصُّونَ عَلَيْكُمْ آيَاتِي ۙ فَمَنِ اتَّقَىٰ وَأَصْلَحَ فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

“አንቀጾቼን የሚያነቡ መልከተኞች” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “ከአንተ በፊት” በሚለው ቃል ላይ ብዙ ቦታ መልእክተኞችን ለማመልከት ይመጣል፦
21፥24 ይልቁንም ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን? «ማስረጃችሁን አምጡ፡፡ *ይህ መገሰጫ እኔ ዘንድ ያለው እና ከእኔ በፊትም የነበረ መገሰጫ ነው* በላቸው፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም፡፡ ስለዚህ እነሱ እምቢተኞች ናቸው፡፡ أَمِ اتَّخَذُوا مِن دُونِهِ آلِهَةً ۖ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ ۖ هَـٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِيَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِي ۗ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ الْحَقَّ ۖ فَهُم مُّعْرِضُونَ
21፥25 *”ከአንተ በፊትም እነሆ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” እና አምልኩኝ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም”*፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

ይህ መገሰጫ ማለትም “ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” የሚለው እርሳቸው ዘንድ ያለው እና ከእርሳቸው በፊትም የነበረ መገሰጫ ነው፥ ከእርሳቸው በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው ብጤ እንጅ ለእሳቸው ሌላ አይባልም፦
40፥43 ከአንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች *የተባለው ብጤ* እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፡፡ ጌታህ የምህረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣት ባለቤት ነው፡፡ مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدْ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبْلِكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٍ

“ቢጤ” ማለት ተመሳሳይ ማለት ነው፥ የተባለውም፦ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” የሚለው መገሰጫ ነው፥ “ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን? ማስረጃችሁን አምጡ” በል በማለት ይሞግታል።
ነጥብ ሦስት
“ጠይቅ”
ከአላህ ሌላ አማልክትን የያዙት ቁረይሾች ናቸው፥ አላህ ከእርሱ ሌላ የሚገዙዋቸው የኾኑን አማልክትን አላደረገም። ግን “አድርገን እንደ ኾነ” ከአንተ በፊት የላክናቸውን መልእክተኞች ጠይቃቸው፦
43፥45 *”ከመልእክተኞቻችንም ካንተ በፊት የላክናቸውን ከአልረሕማን ሌላ የሚገዙዋቸው የኾኑን አማልክት አድርገን እንደ ኾነ ጠይቃቸው”*፡፡ وَاسْأَلْ مَنْ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رُّسُلِنَا أَجَعَلْنَا مِن دُونِ الرَّحْمَـٰنِ آلِهَةً يُعْبَدُونَ

ነቢያችን”ﷺ” መልእክተኞችን በለይለቱል ኢስራእ ወል ሚራጅ ላይ አግኝተዋቸው ነበር፦
32፥23 ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ *እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን*፡፡ ለእስራኤል ልጆችም መሪ አደረግነው፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ فَلَا تَكُن فِي مِرْيَةٍ مِّن لِّقَائِهِ ۖ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

የመልእክተኞች የተውሒድ ትምህርት አላህ በቁርኣን ስለዘረዘረ ሁሉን ዐዋቂ አላህን “ጠይቅ” ብሏቸዋል፦
25፥59 ያ ሰማያትና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዐርሹ ላይ የተደላደለ አልረሕማን ነው፡፡ *”ከእርሱም ዐዋቂን ጠይቅ”*፡፡ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۚ الرَّحْمَـٰنُ فَاسْأَلْ بِهِ خَبِيرًا

ግን ነቢያችን”ﷺ” የሚጠይቁት አንደኛ ወደ እርሳቸው ከተወረደው ቁርኣን ከተጠራጠሩ፥ ሁለተኛው አላህ ከእርሱ ሌላ የሚያመልኩት አማልክት አድርጎ ከሆነ ነው። ነቢያችንም”ነቢያችን”ﷺ” አልተጠራጠሩም፥ አላህም ከእርሱ ሌላ የሚያመልኩት አማልክት አላደረገም። ስለዚህ “ጠይቅ” የሚለው ቃል አጽንዖትና አንክሮት ለመስጠት የገባ ነው።

ነጥብ አራት
“አትሁን”
“ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን” ማለት “ከተጠራጣሪዎቹም ነህ” ማለት አይደለም። ይህንን ሃይለ-ቃል ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት የሚቀጥለውን አንቀጽ እንመልከት፦
10፥95 ከእነዚያም የአላህን አንቀጾች *ከአስተባበሉት አትሁን*፡፡ ከከሳሪዎቹ ትሆናለህና፡፡ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الَّذِينَ كَذَّبُوا بِآيَاتِ اللَّهِ فَتَكُونَ مِنَ الْخَاسِرِينَ

“ከአስተባበሉት አትሁን” ማለት አስተባብለካል ማለት ሳይሆን ምክርና ማስጠንቀቂያ ነው፤ አውዱ ይቀጥልና “ከአጋሪዎቹም አትሁን” ይላል፤ ያ ማለት አጋርተሃል ማለት አይደለም፦
10፥105 ፊትህንም ወደ ቀጥታ ያዘነበልክ ስትሆን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ *ከአጋሪዎቹም አትሁን*፡፡ وَأَنْ أَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

በለይለቱል ኢስራእ ወል ሚራጅ ነቢያችን”ﷺ” ሙሳን ከማግኘታቸው በፊት እንደሚያገኙት አምላካችን አላህ ሲናገር፦ “እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን” ብሏል፦
32፥23 ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ *እርሱን ከመገናኘትህም በመጠራጠር ውስጥ አትሁን*፡፡ ለእስራኤል ልጆችም መሪ አደረግነው፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ فَلَا تَكُن فِي مِرْيَةٍ مِّن لِّقَائِهِ ۖ وَجَعَلْنَاهُ هُدًى لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ሙሳን እንደሚያገኙት አውቀው ተጠራጥረው ሳይሆን አትሁን ምክር እና ማስጠንቀቂያ እንጂ እርሱን ከመገናኘት በመጠራጠር ውስጥ ነበሩ የሚለውን እንደማይይዝ ሁሉ በተመሳሳይም “ከአስተባበሉት አትሁን” “ከአጋሪዎቹም አትሁን” “ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን” ማለት ምክርና ማስጠንቀቂያ እንጂ “አስተባባይ” “አጋሪ” “ተጠራጣሪ” ነበርክ የሚል ፍቺ አይኖረውም። አላህ ለከዳተኞችም ተከራካሪ አትኹን ይላል፦
4፥105 እኛ በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን፡፡ *ለከዳተኞችም ተከራካሪ አትኹን*፡፡إِنَّا أَنزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ لِتَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ بِمَا أَرَاكَ اللَّهُ ۚ وَلَا تَكُن لِّلْخَائِنِينَ خَصِيمًا

“ተከራካሪ አትኹን” ማለት “ተከራካሪ ነህ” ማለት እንዳልሆነ ሁሉ “ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን” ማለት “ከተጠራጣሪዎቹም ነህ” ማለት አይደለም። ከላይ የተለያዩ ቅድመ ተከተላዊ የሙግት ነጥብ”premise” አቅርብናል። ይህ ሙግት በሥነ-አፈታት ጥናት”hermeneutics” ቁርኣን በቁርኣን መፈሠር”textual approach” የሚባል ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያረገ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በፍርዱም አንድንም አያጋራም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥26 ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ *በፍርዱም አንድንም አያጋራም*፡፡ مَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِي حُكْمِهِ أَحَدًا

“አል-ሐከም” الحَكَم ከአላህ ስሞች አንዱ ሲሆን ትርጉሙ “ፈራጅ ወይም ዳኛ” ማለት ሲሆን “ሁክም” حُكْم ማለትም “ፍርድ” ደግሞ የእርሱ ባህርይ ነው፤ አምላካችን አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ በትክክል ፈራጅ ነው፤ በፍርዱ ቀን ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው፤ እርሱ የፍርዱ ቀን ባለቤት ነው፤ በዚያ ቀን በፍርዱ ማንንም አያጋራም፦
95፥8 *አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን? ነው*፡፡ أَلَيْسَ اللَّهُ بِأَحْكَمِ الْحَاكِمِين
10፥109 ወደ አንተም የሚወረደውን ተከተል፡፡ *አላህም በእነርሱ ላይ እስከሚፈርድ ድረስ ታገስ፡፡ እርሱም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነው*፡፡ وَاتَّبِعْ مَا يُوحَىٰ إِلَيْكَ وَاصْبِرْ حَتَّىٰ يَحْكُمَ اللَّهُ ۚ وَهُوَ خَيْرُ الْحَاكِمِينَ
34፥26 «ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፡፡ ከዚያም በመካከላችን በእውነት ይፈርዳል፡፡ *እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው» በላቸው*፡፡ قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ
1፥4 *የፍርዱ ቀን ባለቤት ለኾነው*፡፡ مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ
6፥62 *ከዚያም እውነተኛ ወደ ኾነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡ ንቁ! ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው*፡፡ እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው፡፡ ثُمَّ رُدُّوا إِلَى اللَّهِ مَوْلَاهُمُ الْحَقِّ ۚ أَلَا لَهُ الْحُكْمُ وَهُوَ أَسْرَعُ الْحَاسِبِينَ
18፥26 ለእነርሱ ከእርሱ በቀር ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ *በፍርዱም አንድንም አያጋራም*፡፡ مَا لَهُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا يُشْرِكُ فِي حُكْمِهِ أَحَدًا

አምላካችን አላህ የፈራጆች ሁሉ ፈራጅ ሲሆን በዱኒያህ ግን ለሁሉም ነብያት ማለትም ለሉጥ፣ ለዩሱፍ፣ ለሙሳ፣ ለዳውድ፣ ለሱለይማን ወዘተ የሚፈርዱበት ፍርድ ሰቷቸዋል፦
21፥74 *ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا
12፥22 *ጥንካሬውንም በደረሰ ጊዜ ፍርድን እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንደዚሁም መልካም ሠሪዎችን ሁሉ እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
28፥14 ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ ጊዜ *ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠነው*፡፡ እንዲሁም መልካም ሠሪዎችን እንመነዳለን፡፡ وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ وَاسْتَوَىٰ آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِي الْمُحْسِنِينَ
21፥79 *ለሱለይማንም ትክክለኛይቱን ፍርድ አሳወቅነው፡፡ ለሁሉም ፍርድ እና ዕውቀትን ሰጠን*፡፡ فَفَهَّمْنَاهَا سُلَيْمَانَ ۚ وَكُلًّا آتَيْنَا حُكْمًا وَعِلْمًا

አይ አላህ የሚፈርድበት ፍርድ እና ፍጡራን የሚፈርዱበት ፍርድ ይለያያል ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም ሙግት በዚህ ስሌትና ቀመር መረዳት ይቻላል። አላህ ለሁሉም ፍርድ እና ዕውቀትን እንደሰጠ ለነብያችንም”ﷺ” ቁርኣንን እና ሱናው ፍርድ አድርጎ ሰጥቷል፦
5፥49 *በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ*፡፡ وَأَنِ احْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ
5፥42 *ብትፈርድም በመካከላቸው በትክክል ፍረድ፤ አላህ በትክክል ፈራጆችን ይወዳልና*፡፡ وَإِنْ حَكَمْتَ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِالْقِسْطِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

“ፈራጆች” የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ስለዚህ ለነብያችን”ﷺ” በመታዘዝ እና ለአላህ በመገዛት ፍርድን በዱንያህ እንቀበላለን፤ “አላህ እና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ” የሚለው ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ እንጂ በፍርድ ቀን ስለሚፈረደው ፍርድ በፍጹም አይደለም፦
24፥51 *የምእምናን ቃል የነበረው ወደ አላህ እና ወደ መልክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ፦ “ሰማን እና ታዘዝንም” ማለት ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا كَانَ قَوْلَ الْمُؤْمِنِينَ إِذَا دُعُوا إِلَى اللَّهِ وَرَسُولِهِ لِيَحْكُمَ بَيْنَهُمْ أَن يَقُولُوا سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا
33፥36 *አላህ እና መልክተኛውም ነገርን በፈረዱ ጊዜ ለምእምናንና ለምእምናት ከነገራቸው ለእነርሱ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም! የአላህንና የመልክተኛውንም ትእዛዝ የጣሰ ሰው ግልጽ የሆነን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ*፡፡ وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ وَلَا مُؤْمِنَةٍ إِذَا قَضَى اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَمْرًا أَن يَكُونَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ مِنْ أَمْرِهِمْ ۗ وَمَن يَعْصِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا مُّبِينًا

ከፈጣሪ ጋር አብረው የተጠቀሱ አካላት ማሻረክ ከሆነ እኛም በተራችን ከባይብል ጥያቄ እንጠይቃለን። ሳኦል ከእግዚአብሔር ጋር እና በሚል መስተጻምር ተያይዟል፦
1ሳሙ 12፥3 እነሆኝ *በእግዚአብሔር እና “በመሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ፊት መስክሩብኝ* የማንን በሬ ወሰድሁ?
1ሳሙ 12፥5 እርሱም፦ በእጄ ምንም እንዳላገኛችሁ *እግዚአብሔር እና “መሲሑ” מְשִׁיח֗וֹ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክሮች ናቸው* አላቸው፤

“ፊት” በሚል በነጠላ ስም እና በአያያዥ መስተጻምር ሳኦል ከእግዚአብሔር ጋር ስለተቀመጠ ሳኦል ተጋሪ ነውን? የእስራኤል ጉባኤውም ሁሉ ራሳቸውንም አዘንብለው ለእግዚአብሔር እና ለንጉሡ ለዳዊት ሰገዱ፦
1ኛ ዜና መዋዕል 29፥20 ጉባኤውም ሁሉ የአባታቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ባረኩ፥ ራሳቸውንም አዘንብለው *”ለእግዚአብሔር እና ለንጉሡ ሰገዱ”*።

“ሰገዱ” በሚል በነጠላ ግስ እና በአያያዥ መስተጻምር ዳዊት ከእግዚአብሔር ጋር ስለተቀመጠ ዳዊት ተጋሪ ነውን? እግዚአብሔርን እና ንጉሡን ሰለሞንን ፍራ ተብሎ በአንድ መደብ ተቀምጧል፦
ምሳሌ 24፥21-22 ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርን እና ንጉሥን *”ፍራ”*፥ ከዓመፀኞችም ጋር አትደባለቅ። *”መከራቸው”* ድንገት ይነሣልና፤ *”ከሁለቱ የሚመጣውን”* ጥፋት ማን ያውቃል?

“ፍራ” በሚል በነጠላ ግስ እና በአያያዥ መስተጻምር ሰለሞን ከእግዚአብሔር ጋር ስለተቀመጠ ሰለሞን ተጋሪ ነውን? የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር እና በሙሴ አመኑ፦
ዘጸአት 14፥31 ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፥ *በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ*።

“አመኑ” በሚል በነጠላ ግስ እና በአያያዥ መስተጻምር ስለተቀመጠ ሙሴ ተጋሪ ነውን?

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ታላቁ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

42፥4 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ *እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው*፡፡ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ

በክርስትና ስልታዊ ሥነ-መለኮት”systematic theology” ውስጥ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ብለው ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸው የጳውሎስ ንግግር ነው። “ጳውሎስ ስለ ኢየሱስ አምላክነት ተናግሯል” ይላሉ። እዚህ ድምዳሜ ላይ አደረሰን ከሚሏቸው አናቅጽ መካከል አንዱን አንቀጽ ዳሰሳ"servey" እናደርጋለን፥ የማቀርበው ሙግት አዲሱ ዓለም ዐቀፍ ትርጉምን"NIV" ታሳቢ ያደረገ ነው፦
ቲቶ 2፥13 *የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንን ክብር እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ እየጠበቅን"*። while we wait for the blessed hope the appearing of the glory of our great God and Savior, Jesus Christ, (New International Version)
ግሪኩ፦ προσδεχόμενοι τὴν μακαρίαν ἐλπίδα καὶ ἐπιφάνειαν τῆς δόξης τοῦ μεγάλου Θεοῦ καὶ Σωτῆρος ἡμῶν Χριστοῦ Ἰησοῦ,

እዚህ አንቀጽ "ቴስ ዶክስ ቴዩ መጋላዩ ቴኦዩ" τῆς δόξης τοῦ μεγάλου Θεοῦ ማለት "የታላቁን የአምላካችንን ክብር"the glory of our great God" ማለት ነው፥ ጳውሎስ ሊያስተላልፍ የፈለገው መልእክት፦ "የታላቁ አምላክ ክብር እና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የተባረከውን ተስፋችን ነው" የሚል ነው። የታላቁ አምላክ የአብ ክብር በተለያየ ጊዜ ለእስራኤላውያን ይገለጥ ነበር፦
ዘሌዋውያን 9፥6 *የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጥላችኋል"*።
ዘሌዋውያን 9፥23 *"የእግዚአብሔርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ"*።
ዘኍልቍ 14፥10 *"የእግዚአብሔርም ክብር ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ተገለጠ"*።

ኢየሱስ መለኮታዊ ኃይል ተሰጥቶት የሚሠራው ሥራ የእግዚአብሔር ክብር መገለጥ ነው፦
ኢሳይያስ 40፥5 *የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል"*።
ዮሐንስ 11፥40 ኢየሱስ፦ ብታምኚስ *የእግዚአብሔርን ክብር እንድታዪ አልነገርሁሽምን? አላት*።

እዚህ ድረስ ከተግባባን ኢየሱስ የሚመጣው በታላቁ አምላክ በአብ ክብር ነው፦
ማቴዎስ 16፥27 *"የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና"*።

"በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። የእግዚአብሔር ክብር እና ኢየሱስ ደግሞ "ካይ" καὶ ማለትም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል፦
ሐዋርያት ሥራ 7፥55 *የእግዚአብሔርን ክብር "እና" καὶ ኢየሱስን በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየ"*። (New International Version)
ራእይ 21፥23 ለከተማይቱም *የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት "እና" καὶ መብራትዋ በጉ ስለ ሆነ"*። (New International Version)

ጳውሎስ በፍጹም "ታላቁ አምላክ ይገለጣል" አላለም። ባይሆን የታላቁ አምላክ ክብር እና ኢየሱስ እንደሚገለጡ መናገሩ ቢሆን እንጂ። የግሪክ ሰዋስው ግራንቪል ሻርፕ አንደኛው ላይ የተቀመጠው ሕግ ፦ "ሁለት ስሞች ተመሳሳይ ሙያ ካላቸው፣ ሁለቱም ስሞች "እና" በሚል መስተጻምር ከተያያዙ፣ ከመጀመሪያው ስም ላይ ውስን መስተአምር ከተጠቀመ እና ሁለተኛ ስም ላይ ካልተጠቀመ ሁለቱም ስሞች አንድን ማንነትን የሚያሳዩ ነው" If two nouns of the same case and the two nouns are connected by the word “and,” and the first noun has the article while the second does not, both nouns are referring to the same person"
ዋቢ መጽሐፍ ይመልከቱ፦
Wallace, Daniel B. (1996). Greek Grammar Beyond the Basics: An Exegetical Syntax of New Testament Greek. Grand Rapids. Page 270-290.

በዚህ ሕግ ከሔድን ውኃ የማይቋጥር ሙግት ነው፦
ኤፌሶን 2፥20 *"በሐዋርያት "እና" በነቢያት"* መሠረት ላይ ታንጻችኋል። ἐποικοδομηθέντες ἐπὶ τῷ θεμελίῳ τῶν ἀποστόλων καὶ προφητῶν

እዚህ አንቀጽ ላይ "አፓስቶሎን" ἀποστόλων ማለትም "ሐዋርያት" ከሚል ስም በፊት "ቶን" τῶν የሚል ውስን መስተአምር ይጠቀማል፣ "ፕሮፌቶን" προφητῶν ማለትም "ነቢያት" በሚለው ስም ግን ውስን መስተአምር አይጠቀምም፣ ሁለቱም ስሞች "እና" በሚል መስተጻምር ተያይዘዋል፣ ሁለት ስሞች ተመሳሳይ ተሳቢ ሙያ አላቸው። ግን ሐዋርያት እና ነቢያት ተመሳሳይ ማንነት አልነበሩም፦
1 ቆሮንቶስ 12፥28 *እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን፥ ሁለተኛም ነቢያትን.. አድርጎአል*።