ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ይህ አላዋጣ ያላቸው ሥላሴአውያን ግራንቪል ሻርፕ በራሱ መጣጥፍ ላይ ባላስቀመጠው መስፈርት፦ "የሻርፐስ ሕግ ማንነት ለሌለው፣ ለብዜት ስም፣ ለተጸውዖ ስም አይሠራም" ብለው አረፉት። እሺ በነጠላ ስም እንሞግት፦
ኤፌሶን 5፥5 ጣዖትን የሚያመልክ *በክርስቶስ "እና" በአምላክ መንግሥት* ርስት የለውም።

እዚህ አንቀጽ አንቀጽ ላይ "ክርስቶዩ" Χριστοῦ ማለትም "ክርስቶስ" ከሚል ስም በፊት "ቶዩ" τοῦ የሚል ውስን መስተአምር ይጠቀማል፣ "ቴኦዩ" Θεοῦ ማለትም "አምላክ" በሚለው ስም ግን ውስን መስተአምር አይጠቀምም፣ ሁለቱም ስሞች "እና" በሚል መስተጻምር ተያይዘዋል፣ ሁለት ስሞች ተመሳሳይ አገናዛቢ ሙያ አላቸው። ግን ክርስቶስ የተባለው ወልድ እና አምላክ የተባለው አብ ተመሳሳይ ማንነት አልነበሩም። "የክርስቶስ ራስ አምላክ ነው" "ክርስቶስ ለአምላክ ለአባቱ መንግሥትን አሳልፎ ይሰጣል" "ክርስቶስ ለአምላክ ራሱን አሳልፎ ሰጠ" የሚሉ ሐረጋት መኖራቸውን አትዘንጋ፦ 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥23-24 ኤፌሶን 5፥2 ። ሙግቱን እቀጥል፦
2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥1 *በአምላክ እና በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት"*። τοῦ Θεοῦ καὶ Χριστοῦ Ἰησοῦ,

እዚህ አንቀጽ አንቀጽ ላይ "ቴኦዩ" Θεοῦ ማለትም "አምላክ" ከሚል ስም በፊት "ቶዩ" τοῦ የሚል ውስን መስተአምር ይጠቀማል፣ "ክርስቶዩ" Χριστοῦ ማለትም "ክርስቶስ" በሚለው ስም ግን ውስን መስተአምር አይጠቀምም፣ ሁለቱም ስሞች "እና" በሚል መስተጻምር ተያይዘዋል፣ ሁለት ስሞች ተመሳሳይ አገናዛቢ ሙያ አላቸው። ግን አምላክ የተባለው አብ እና ክርስቶስ የተባለው ወልድ ተመሳሳይ ማንነት አልነበሩም።
በቁና ሰፍረን ብዙ ናሙና ማቅረን ይቻል ነበር፥ ቅሉ ግን አንባቢን ማሰልቸት ነው ብለን ትተነዋል።
እሺ ሙግቱን ጠበብ አርገነው ሻርፐስ ሕግ ትክክል ነው ብለን በግናንቪል ሻርፕ ሕግ ኢየሱስ እራሱ የታላቁ አምላክ ክብር ነው" ቢባል እንኳን አሁንም አያጣላንም፥ ምክንያቱም ወንድ እራሱ የእግዚአብሔር ክብር ተብሏልና፦
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥7 *"ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌ እና ክብር ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም"*።

ወንድ "የእግዚአብሔር ክብር ነው" ማለት እና "እግዚአብሔር ነው" ማለት በይዘትና በአይነት፥ በመንስኤና በውጤት ሁለት የተለያየ ለየቅል ትርጉም እንዳለው ሁሉ ኢየሱስ "የታላቁ አምላክ ክብር ነው" ማለት እና "ታላቁ አምላክ ነው" ማለት በይዘትና በአይነት፥ በመንስኤና በውጤት ሁለት የተለያየ ለየቅል ትርጉም ነው። የቲቶ ጸሐፊ ጳውሎስ እዛው ዐውድ ላይ አብ አምላክ፥ ወልድን መድኃኒት በማለት "እና" በሚል መስተጻምር ለይቶ አስቀምጧቸዋል፦
ቲቶ 1፥4 *ከአምላካችን Θεοῦ ከአብ "እና" καὶ ከመድኃኒታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ* ጸጋ እና ምሕረት ሰላምም ይሁን።

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቴኦዩ" Θεοῦ አገናዛቢ ዘርፍ ሲሆን ልክ እንደ ቲቶ 2፥13 "አምላካች" ተብሎ ሲነበብ አብ አምላክ ወልድ መድኃኒት መሆኑን ያሳያል። ጳውሎስ ገማልያ እግር ስር ተቀምጦ ይማር የነበረ እስራኤላዊ ሰው ነበር፥ እስራኤላውያን ደግሞ አምላካችን የሚሉት የኢየሱስን አባት ታላቁን አምላክ ነው፦
ዮሐንስ 8፥54 *እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው"*።
መዝሙር 77፥13 *እንደ አምላካችን ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው?*
መዝሙር 86፥10 አቤቱ፥ ድንቅ የምታደርግ *አንተ ታላቅ ነህና፥ "አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህና*።

መዝሙረኛው አንድ ነጠላ ማንነት "አንተ" ብሎ በነጠላ ተውላጠ-ስም ከመጠቀሙ ባሻገር ያንን ነጠላ ማንነት "አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህ" ይለዋል። እውነት ነው፥ እስራኤላውያን አምላካችን የሚሉት ያህዌህ ነው፥ ያህዌህ ብቻውን ታላቅ አምላክ ነው፦
ነህምያ 8፥6 ዕዝራም *ታላቁን አምላክ ያህዌህን ባረከ"*።
መዝሙር 95፥3 *ያህዌህ ታላቅ አምላክ ነውና"*።

በቁርኣን አስተምህሮት የበላዩ ታላቁ ጌታ አላህ ብቻ ነው፥ መሢሑን ታላቁ አምላክ ነው ማለት መሢሑን አላህ ነው ማለት ነው። እነዚህ "መሢሑን አላህ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
42፥4 በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ *እርሱም የበላዩ ታላቁ ነው*፡፡ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ
69፥52 *የታላቁን ጌታህንም ስም አወድስ*፡፡ فَسَبِّحْ بِاسْمِ رَبِّكَ الْعَظِيمِ
5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነጻ ፈቃድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر

“ሻእ” شَآء ማለት “ፈቃድ” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ በፍጥረተ-ዓለማት ውስጥ የሚሻውን ይፈጥራል፦
24፥45 *አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير
86፥16 *የሚሻውን ሁሉ ሠሪ ነው*፡፡ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ
5፥17 *የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው*፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
3፥47 *አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

“የሚሻውን” ለሚለው ቃል የገባው “የሻኡ” يَشَاءُ ማለትም “የሚፈቅደውን” ነው። ማንኛውም ነገር ሲከሰት፣ ሲከናወንና ሲሆን አላህ ፈቅዶ ነው፥ ያለ አላህ ፈቃድ ምንም እኩይ ወይም ሰናይ ነገር አይከሰትም፤ አይከናወንም፣ አይሆንም። የአላህ ፈቃድ በሁለት መልክ ለፍጡራን ሆኗል፥ አንዱ ያለፈቃዳቸው ሲሆን ሁለተኛው በተሰጣቸው ነጻ ፈቃድ ላይ ነው።
የመጀመሪያው ፍጥረት ሲፈጠር ያለፈቃዱ በአላህ ፈቃድ ብቻ የሚከናወነው “ተሐዚዝ” تحديد ማለት “የተቆረጠ”determination” ይባላል። ይህም ሰው በመወለድ፣ በሞት፣ በመተኛት፣ በማስነጠስ ምርጫ የለውም። ልጅ እንኳን ሲወልድ ወንድ ወይም ሴት እወልዳለው ብሎ ምርጫ የለውም፤ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ ለሚሻው ሰው ሴቶችን ይሰጣል፤ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል። ለሚሻው መንታ ያደርጋል፤ የሚሻውን መካን ያደርገዋል። ለፍጡራን ግን ይህንን ለማድረግ ምርጫ የላቸውም፦
42፥49 *የሰማያትና የምድር ንግሥና የአላህ ነው፡፡ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ ለሚሻው ሰው ሴቶችን ይሰጣል፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን ይሰጣል*፡፡ لِّلَّهِ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ
42፥50 *ወይም ወንዶችና ሴቶች አድርጎ ያጠናዳቸዋል፡፡ የሚሻውንም ሰው መካን ያደርገዋል፡፡ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና*፡፡ أَوْ يُزَوِّجُهُمْ ذُكْرَانًا وَإِنَاثًا ۖ وَيَجْعَلُ مَن يَشَاءُ عَقِيمًا ۚ إِنَّهُ عَلِيمٌ قَدِيرٌ
28፥68 *ጌታህም የሚሻውን ይፈጥራል፤ ይመርጣልም፡፡ ለእነርሱ ለፍጡራን ምርጫ የላቸውም*፡፡ وَرَبُّكَ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ وَيَخْتَارُ ۗ مَا كَانَ لَهُمُ الْخِيَرَة

ሰው ወንድ ወይም ሴት ለመሆን ለመወለድ ለመሞት ምርጫ የለውም። አላህ የሚሻውን በምርጫው ይህንን ይፈጥራል። በዚህ ምርጫ በሌለው ነገር ሰው አይጠየቅበትም፣ አይቀጣበትም፣ አይሸለምበትም።

ሁለተኛው ፍጥረት በተሰጠው ነጻ ፈቃድና ምርጫ ይጠየቃል፦
21፥23 *ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ ፍጥረቶቹ ግን ይጠየቃሉ*፡፡ لَا يُسْأَلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْأَلُونَ
16፥93 *ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ*፡፡ وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنتُمْ تَعْمَلُون

አላህ በሚሠራው ሥራ አይጠየቅም። እርሱ ፈጣሪ ስለሆነ ፍጡራን ግን በሚሠሩት ሥራ ይጠየቃሉ። አላህ ትዳርን ፈቅዶ ዝሙትን መከልከሉ፥ ንግድን ፈቅዶ አራጣን መከልከሉ፥ መጠጥን ፈቅዶ ኸምርን መከልከሉ፥ ምግብን ፈቅዶ እሪያን መከልከሉ፥ እርሱን እንድናመልክ ፈቅዶ ጣዖትን መከልከሉ ይህ ተጠያቂነትን ያሳያል። መስሚያ የሚሰማውን የመምረጥ ነፃነቱ፣ ማያም የሚያየውን የመምረጥ ነፃነቱ፣ ልብም የሚያስበውን የመምረጥ ነፃነቱ የተሰጠን ጸጋ ነው። የዚህ ጸጋ ባለቤት ሰው በተሰጠው ጸጋ ተጠያቂ ነው፦
23፥78 *እርሱም ያ መስሚያዎችን፣ ማያዎችን እና ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው*፤ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡ وَهُوَ الَّذِي أَنشَأَ لَكُمُ السَّمْعَ وَالْأَبْصَارَ وَالْأَفْئِدَةَ ۚ قَلِيلًا مَّا تَشْكُرُون
17፥36 *ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፤ መስሚያ፣ ማያም እና ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና*። وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَاد3َ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا
102፥8 ከዚያም *ከጸጋችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ*። ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ

“ነዒም” نَّعِيمِ ማለት “ጸጋ” ማለት ነው። ነጻ ፈቃድ አድርግ የተባለውን የመታዘዝዝና ያለመታዘዝ፥ አታድርግ የተባለውን የመከልከልና ያለመከልከል ነጻነት ነው። ይህ አላህ የፈቀደልን ነጻ ፈቃድ “ሚሣን” ميسان ማለትም “ነጻነት”Libration” ይባላል። ይህ ጸጋ ሁሉም ሰው ጋር በተፈጥሮ የተቸረ ጸጋ ነው። በተሰጠን ነጻ ፈቃድና ምርጫ የምንሰራው መልካም ሥራ ሆነ ክፉ ሥራ ያስጠይቀናል። የተሰጠን ጸጋ ነጻ ፈቃድ”free will” ይባላል። ሰው በነጻ ፈቃዱ መብቱና ነጻነቱን መጠቀም ይችላል፥ “መብት” ማለት ማድረግ እና አለማድረግ ተጠያቂነት የሌለው ነገር ሲሆን “ነጻነት” ግን ባለማድረግ እና በማድረግ ተጠያቂነት ያለው ነገር ነው።
ሰዎች የሚፈጽሙና የሚያከናውኑት እውነትና ውሸት፣ ትክክልና ስህተት፣ መልካሙና ክፉ አላህ ፈቅዶ ነው። ያለ አላህ ፈቃድ ምንም የሚሆን ነገር የለም፣ አላህ ፈቀደ ማለት ግን ጉዳዩን ወዶታል አሊያም ተስማምቶበታል ማለት አይደለም፣ አላህ ስለፈቀደ ነው ሰው ነጻ ፈቃድ ያለው፣ አላህ ሳይፈቅድ ሰው ነጻ ፈቃድ አይኖረውም ነበር፦
81፥29 *የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም*፡፡ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ
76፥30 *አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና*፡፡ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا
“ማ የሻኡነ ኢላ አን የሻኣሏህ” وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّه ማለትም “አላህ ካልፈቀደ አትፈቅዱም” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ሰው ይህ ነጻ ፈቃድ ስላለው በፈቃዱ ማመን ወይም መካድ ይችላል፦
18፥29 *«እውነቱም ከጌታችሁ ነው፡፡ የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ»* በላቸው፡፡ وَقُلِ الْحَقُّ مِن رَّبِّكُمْ ۖ فَمَن شَاءَ فَلْيُؤْمِن وَمَن شَاءَ فَلْيَكْفُر

“የሻም ሰው ይመን፥ የሻም ሰው ይካድ” ዛቻ ነው። በኃላ ይጠየቃል፥ ትሩፋትና ቅጣት ይቀበላል። አምላካችን አላህ እርሱ የሚወደው እምነት እና የሚጠላው ክህደት ይህ ነው ብሎ ሁለቱንም የእምነት መንገድ እና የክህደት መንገድ በተከበረ ቃሉ ነግሮናል፦
39፥7 *ብትክዱ አላህ ከእናንተ የተብቃቃ ነው፡፡ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም፡፡ ብታመሰግኑም፤ እርሱን ይወድላችኋል*፡፡ إِن تَكْفُرُوا فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنكُمْ ۖ وَلَا يَرْضَىٰ لِعِبَادِهِ الْكُفْرَ ۖ وَإِن تَشْكُرُوا يَرْضَهُ لَكُمْ
2፥256 በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ *ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ*፡፡ لَا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ ۖ قَد تَّبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ ۚ
90፥10 *ሁለትን መንገዶችም አልመራነውምን?* وَهَدَيْنَاهُ النَّجْدَيْنِ
76፥3 *እኛ ወይ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ ሲኾን መንገዱን ገለጽንለት*፡፡ إِنَّا هَدَيْنَاهُ السَّبِيلَ إِمَّا شَاكِرًا وَإِمَّا كَفُورًا

ቅኑ የእምነት መንገድ ከጠማማው የክህደት መንገድ ተገልጧል፥ አመስጋኝ ወይም ከሓዲ የመሆን ያለመሆን ምርጫው ተገልጿል። ለዚያ ነው ዛሬ በዓለማችን ላይ ሁለት ተቃራኒ የሆኑ አማኝ እና ከሓዲ ያሉት፦
64፥2 እርሱ ያ የፈጠራችሁ ነው፡፡ *ከእናንተም ከሓዲ አለ፡፡ ከእናንተም አማኝ አለ*፡፡ አላህም በምትሠሩት ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَكُمْ فَمِنكُمْ كَافِرٌ وَمِنكُم مُّؤْمِنٌ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
14፥7 ጌታችሁም *«ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም እቀጣችኋለሁ፤ ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ አስታውሱ*፡፡ وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِي لَشَدِيدٌ

“ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ” ማለት ለአማንያን የተዘጋጀ ትሩፋት ጀነት እንዳለ የሚጠቁም ነው፥ “ብትክዱም እቀጣችኋለሁ” ማለት ለከሓድያን የተዘጋጀ ቅጣት ጀሃነም እንዳለ የሚጠቁም ነው። ስለዚህ ቅጣትና ሽልማት፣ የተፈቀና የተከለለ ነገር መኖሩ፥ እኩይና ሰናይ ነገር መኖሩ በራሱ ሰው ነጻ ፈቃድ እንዳለው የሚያሳይ ማስረጃ ነው። አንድ ሰው ነጻ ፈቃድ የለኝም ብሎ ሰው ቢገድል፣ ቢሳደብ፣ ቢማታ ወዘተ አይደለም አላህ በአኺራ ሰዎች በዱንያህ ይጠይቁታል። ኢቭን መብቱን ለማስከበር ግዴታውን መወጣቱ በራሱ ሰው ነጻ ፈቃድ እንዳለው ማስረጃ ነው። 
በኢሥላም ዐቂዳህ ውስጥ ሁለት ጠርዘኛ እሳቦት ነበሩ፥ አንደኛው እሳቤ “አል-ጀብሪያህ” الجبرية ማለትም ሰው በአላህ ዕውቀትና ፈቃድ ብቻ የሚኖር ነጻ ፈቃድ የሌለው ፍጡር”Necessitarian” ነው የሚሉ እና ሁለተኛው እሳቤ “አል-ቀደሪያህ” القدريه‎ ማለትም ሰው ያለ አላህ ዕውቀትና ፈቃድ ብቻውን በራሱ ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር”Libriterian” ነው የሚል ነው። ሁለቱም ጽንፍ ያላቸው እሳቦት በኢሥላም ዐቂዳህ አንዳች ቦታ የላቸውም። ሰው በአላህ ዕውቀትና ፈቃድ ነጻ ፈቃድ ያለው ፍጡር ነው። አምላካችን አላህ ለሰው የሰጠው መልካም እና ክፋ የማሰብ፣ የመናገር፣ የማድረግ ነጻ ምርጫ በችሎታችን ልክ ነው፤ ያለ ችሎታችን ልክ አያስገድደንም፦
23፥62 *ማንኛይቱንም ነፍስ ችሎታዋን እንጂ አናስገድዳትም*፡፡ وَلَا نُكَلِّفُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا
2፥286 *አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም*፡፡ لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا

ኢቭን አላህ ስንፈራው እንኳን የቻልነውን ያክል ነው፥ አላህ የምንፈራው በተረዳነው፣ በገባን፣ በደረስንበትና ባወቅነክ ልክ ነው። ይህ ተገቢ ፍርሃት ነው፦
65፥16 *አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት*፤ ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤ ለግሱም፤ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ይሰጣችኋልና። فَاتَّقُوا اللَّهَ مَا اسْتَطَعْتُمْ وَاسْمَعُوا وَأَطِيعُوا وَأَنفِقُوا خَيْرًا لِّأَنفُسِكُمْ
3፥102 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *አላህን ተገቢውን መፍራት ፍሩት*፡፡ እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሰው ሲጃጃል እና ሲደናቆር አብሮ መጃጃል እና መደናቆር ያሳፍራል። ነቢያችን”ﷺ” ከሰው ልጆች ሁሉ ያላቃቸው አላህ ነው፦
48፥28 እርሱ ያ መልክተኛውን በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት በሃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው የላከ ነው፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ፡፡ هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ شَهِيدًا

ከሰው ልጆች ሁሉ የላቁ መሆናቸው መስካሪም በአላህ በቃ፡፡
ጎግል who is the world best man? ብላችሁ ስትጠይቁት prophet Muhammad የሚላችሁ ሙሥሊሞች ያስገቡትን እንጂ ጎግሉ እራሱ በራሱ ያስቀመጠውን አይደለም። ጎግል ስማቸው ሲጠራ ”ﷺ” ብሎ ሶላዋት አያወርድም። እንኳን እርሳቸው ወሒድ ማን ነው? ብትሉት የእኔን ጽሑፎች ያመጣላችኃል። ያ ማለት ጎግል ወሒድን ወሒድ ነው አለው ብላችሁ ጮቤ ልትረግጡ ነው? ጥንቃቄ እናድርግ! ምክንያቱም ከጎግል የሚገኝ ነገር ሁሉ እውነት አይደለም። ኢሥላም ከሚጠለሽበት አንዱ ፈሳድ ጎግል ነው። አሳቤን በቅነንት ተረድታችሁ ታረሙ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሙሥሊሞች መጀመሪያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

6፥163 *”«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙሥሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል”*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ

"ኢሥላም" إِسْلَام‎ የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" "አመለከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "ማምለክ" ማለት ነው። አላህ ዘንድ ዕውቅና ያለው ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፦
3፥19 *አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት “ኢሥላም” ብቻ ነው*፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ
22፥34 *አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

“አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው” በማለት ከተናገር በኃላ “ለእርሱም ብቻ ታዘዙ” ይላል፥ “ታዘዙ” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “አሥሊሙ” أَسْلِمُوا ነው። ኢሥላም ማለት አንድን አምላክ ብቻ በብቸኝነት ማምለክ ማለት ነው።
ሙሥሊም" مُسْلِم የሚለው ቃል ሠለመ" سَلَّمَ "ማለትም "ታዘዘ" "አመለከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ታዛዥ" "አምላኪ" ማለት ነው፦
21፥108 ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *“አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን*? በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

“አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” በማለት ከተናገር በኃላ “እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን?” ይላል፥ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُّسْلِمُون ሲሆን የሙሥሊም ብዙ ቁጥር ነው። ሙሥሊም ማለት አንድን አምላክ ብቻ በብቸኝነት የሚያመልክ ማለት ነው። ኢሥላም እና ሙሥሊም የሚጀምረው ከነቢያችን"ﷺ" ነውን? በፍጹም አይደለም። ሚሽነሪዎች እንደበቀቀን የሚቀጥፉበትን ጥቅስ እስቲ እንይ፦
6፥163 *”«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙሥሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል”*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ

ቁልፉ ያለው "አወል" የሚለው ቃል ላይ ነው። "አወል" أَوَّل ማለት "መጀመሪያ" ማለት ሲሆን በዐረቢኛ ሰዋስው ውስጥ ሁለት ዓይነት መጀመሪያነት አለ፥ አንደኛው "አወሉል ሙጥለቅ" أَوَّل ٱلْمُطْلَق ማለትም “ፍጹማዊ መጀመሪያ“Absolute first” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "አወሉል ቀሪብ" أَوَّل ٱلْقَرِيب‎ ማለትም "አንጻራዊ መጀመሪያ“Relative first” ነው። ይህንን ነጥብ በነጥብ እንይ፦

ነጥብ አንድ
"አወሉል ሙጥለቅ"
“ሙጥለቅ” مُطْلَق ማለት "ፍጹም" ማለት ነው፥ በምድር ላይ የመጀመሪያው ነቢይ አደም ነው፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1781
አቡ ዘር እንደተረከው፦ *"የአላህ ነቢይ”ﷺ” ሆይ የመጀመሪያው ነቢይ ማን ነው? ብሎ አለ። እርሳቸውም፦ "አደም ነው" አሉ። እርሱም፦ "እርሱ ነቢይ ነበርን? ብሎ አለ። እርሳቸውም፦ "አዎ" አሉ"*። عَن أَبُو ذَرٍّ قُلْتُ : يَا نَبِيَّ اللَّهِ، فَأَيُّ الْأَنْبِيَاءِ كَانَ أَوَّلَ. قَالَ : " آدَمُ ". قَالَ : قُلْتُ : يَا نَبِيَّ اللَّهِ، أَوَنَبِيٌّ كَانَ آدَمُ ؟ قَالَ : " نَعَمْ،

ሸይኹል አልባኒይ ሠነዱን ሶሒሕ ነው ብለውታል። ከአደም በፊት ሰው እና ነቢይ ስለሌለ የአደም ነቢይነት ጅማሮ ነው፥ ይህም ጅማሬ ፍጹማዊ መጀመሪያ ነው። አምላካችን አላህ ወደ አደም ወሕይ አውርዷል፦
20፥115 *"ወደ አደምም ”ከዚህ በፊት” ኪዳንን በእርግጥ አወረድን*፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَآ إِلَىٰٓ ءَادَمَ مِن قَبْلُ

"ከዚህ በፊት" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። "ከዚህ በፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ሚን ቀብሉ” مِنْ قَبْلُ ሲሆን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ ነው፥ "ከዚህ በፊት" አላህ በአደም ጊዜ "ሙሥሊሞች" ብሎ ሰየመ፦
22፥78 *"እርሱ "ከዚህ በፊት" ሙስሊሞች ብሎ ሰይሟችኋል*፡፡ هُوَ سَمَّاكُمُ الْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ

አሁንም "ከዚህ በፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ሚን ቀብሉ” مِنْ قَبْلُ ሲሆን የአደምን ጊዜ ያስታውሰናል። "እርሱ" የተባለው "አላህ" የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ነው፥ አላህ "ሙሥሊሞች" ብሎ ሰየመ። በመቀጠል ኑሕ፦ ”ከሙስሊሞችም እሆን ዘንድ ታዝዣለሁኝ” ብሏል፦
10፥72 “ብትሸሹም አትጎዱኝም ፣ከምንዳም ምንንም አለምናችሁም፡፡ምንዳዬም በአላህ ላይ እንጂ በሌላ አይደለም፣ *”ከሙስሊሞችም እሆን ዘንድ ታዝዣለሁኝ”* فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَمَا سَأَلْتُكُم مِّنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ
አምላካችን አላህ ለኢብራሂም “አሥሊም” أَسْلِمْ ማለትም “ታዘዝ” ሲለው እርሱም “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ማለትም “ታዘዝኩ” አለ፦
2፥131 *ጌታው ለእርሱ ”ታዘዝ” ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ ”ታዘዝኩ” አለ*፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

ለዓለማት ጌታ መታዘዝ ኢሥላም ነው፥ እርሱም፦ "ጌታችን ሆይ! ለአንተ “ታዛዦችም” አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች አድርግ" ብሏል፦
2፥128 «ጌታችን ሆይ! *ለአንተ “ታዛዦችም” አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ ታዛዦች “ሕዝቦችን” አድርግ*» رَبَّنَا وَٱجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَآ أُمَّةًۭ مُّسْلِمَةًۭ لَّكَ

“ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙሥሊመይኒ” مُسْلِمَيْنِ ሲሆን ሙሰና ነው፥ ሁለቱን አበው ኢብራሂምን እና ኢስማኢልን ያሳያል። በመቀጠል ያዕቁብም ልጆቹን፦ "እናንተ “ሙስሊሞች” ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ" አላቸው፥ እነርሱም፦ "እኛ ለእርሱ ፍፁም “ታዛዦች” አሉ፦
2፥132 በእርሷም በሕግጋቲቱ ኢብራሂም ልጆቹን አዘዘ፡፡ ያዕቁብም እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ፡፡ *«ልጆቼ ሆይ! አላህ ለእናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ ”ሙስሊሞች” ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ» አላቸው*፡፡ وَوَصَّىٰ بِهَآ إِبْرَٰهِـۧمُ بَنِيهِ وَيَعْقُوبُ يَٰبَنِىَّ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰ لَكُمُ ٱلدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ
2፥133 ያዕቁብን ሞት በመጣበት ጊዜ ለልጆቹ ከኔ በኋላ ማንን ትገዛላችሁ? ባለ ጊዜ ቀራቢዎች ነበራችሁን? *እነርሱም አምላክህንና የአባቶችህን የኢብራሂምን የኢስማዒልንና የኢስሐቅንም አምላክ አንድ የኾነውን አምላክ እኛ ለእርሱ ፍፁም ”ታዛዦች” ኾነን እናመልካለን አሉ*፡፡ أَمْ كُنتُمْ شُهَدَآءَ إِذْ حَضَرَ يَعْقُوبَ ٱلْمَوْتُ إِذْ قَالَ لِبَنِيهِ مَا تَعْبُدُونَ مِنۢ بَعْدِى قَالُوا۟ نَعْبُدُ إِلَٰهَكَ وَإِلَٰهَ ءَابَآئِكَ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ وَإِسْحَٰقَ إِلَٰهًۭا وَٰحِدًۭا وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ

“ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሙሥሊሙን" مُّسْلِمُون እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሙሣም ለሕዝቦቹ “ታዛዦች” እንደ ሆናችሁ በአላህ ላይ ትመካላችሁ አለ፦
10:84 *ሙሳም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ *”ታዛዦች”* እንደ ሆናችሁ በአላህ ላይ ትመካላችሁ"*፡፡ وَقَالَ مُوسَىٰ يَٰقَوْمِ إِن كُنتُمْ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوٓا۟ إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ

“ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል አሁንም “ሙስሊሚን” مُّسْلِمِين ነው። የዒሣ ሐዋርያትም የጥንቱን አምላክ በብቸኝነት የሚያመልኩ ስለነበሩ፦ "ሙሥሊሙን ነን" ብለዋል፦
5:111 ወደ ሐዋርያትም በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፤ አመንን፣ *እኛም *”ሙስሊሞች”* መሆናችንን መስክር አሉ*።وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى ٱلْحَوَارِيِّـۧنَ أَنْ ءَامِنُوا۟ بِى وَبِرَسُولِى قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا وَٱشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ
3:52 ዒሳ ከእነርሱ ክሕደት በተሰማዉም ጊዜ፦ ወደ አላህ ረዳቶቼ እነማን ናቸዉ? አለ፤ ሐዋሪያት ፡ -እኛ የአላህ ረዳቶች ነን፤ በአላህም አምነናል፤ *እኛም ትክክለኛ *”ታዛዦች”* መሆናችንን፥ መስክር፥ አሉ*። فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ
ነጥብ ሁለት
"አወሉል ቀሪብ"
"ቀሪብ" قَرِيب‎ ማለት "አንጻራዊ" ማለት ነው፥ ከላይ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት የነበሩት ነቢያት ሙሥሊም ከነበሩ የነቢያችን"ﷺ" መጀመሪያነት አንጻራዊ ነው፦
6፥163 *”«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት "ታዘዝኩ"፡፡ እኔም የሙሥሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል”*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ

"ታዘዝኩ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። ምንድን ነው የታዘዙት? ቁርኣን “ትእዛዝ” ሆኖ ወደ እርሳቸው ወርዷል፦
65፥5 *”ይህ “የአላህ ትእዛዝ ነው”። ወደ እናንተም አወረደው”*። ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ

ይህንን ትእዛዝ ተቀብለው የታዘዙ የመጀመሪያው ታዛዥ እርሳቸው ናቸው፦
6፥14 *«እኔ መጀመሪያ ትእዛዝን ከተቀበለ ሰው ልኾን ታዘዝኩ*”፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን ተብያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

“ትእዛዝን ከተቀበለ” የሚለው ይሰመርበት። “ትእዛዝን የተቀበለ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለመ” أَسْلَمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ እንግዲህ ቁርኣንን ተቀብሎ ከሠለሙት ሙሥሊሞች መጀመሪያ ነቢያችን”ﷺ” ናቸው ማለት ነው፦
6፥163 *”«ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም በማጥራት ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙሥሊሞች መጀመሪያ ነኝ» በል”*፡፡ لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ
3፥20 ቢከራከሩህም፡- *”«ፊቴን ለአላህ ሰጠሁ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ»* በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

“ሰጠሁ” ለሚለው ቃል የገባው “አሥለምቱ” أَسْلَمْتُ ሲሆን እርሳቸው ቀጥሎ ተከታዮቻቸው ሁለንተናቸውን ለአላህ ያሠለሙ መሆናቸውን ፍንትው አርጎ ያሳያል። ለአላህ ከሠለሙት ተከታዮቻቸው አንጻር ቅድሚያ የሠለሙ እርሳቸው ናቸው። አምላካችን አላህ ለነቢያችን"ﷺ" እና ለተከታዮቻቸው ኑሕን፣ ኢብራሂምን፣ ሙሳን እና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖን ኢሥላምን እንድንከተል ነው፦
42፥13 *ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ! በእርሱም አትለያዩ። شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ

እዚህ ድረስ ከተግባባን በንጽጽር ወደ ባይብል እንግባ! በባይብል የእግዚአብሔር የመጀመሪያ ልጅ እስራኤል ነው፦
ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *”እስራኤል የበኵር ልጄ ነው”*።

“በኵር” ማለት "መጀመርያ" ማለት ነው። እስራኤል የእግዚአብሔር የመጀመሪያ ልጅ ሆኖ ሳለ ከእስራኤል መፈጠር በፊት መላእክእት እና አደም የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል፦
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥
ዘፍጥረት 6፥2 *”የእግዚአብሔር ልጆችም የሰውን ሴቶች ልጆች መልካሞች እንደ ሆኑ አዩ፤ ከመረጡአቸውም ሁሉ ሚስቶችን ለራሳቸው ወሰዱ”*።
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።

አይ እስራኤል "መጀመርያ" የተባለበት አንጻራዊ እንጂ ፍጹማዊ አይደለም" ካላችሁን፥ በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉሃል እንደዚህ ነው። ከላይ ያለውንም ነጥብ በዚህ መልክ እና ልክ ተረዱት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሥነ-ሰብእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

51፥21 *በራሳችሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ፥ ታዲያ አትመለከቱምን?* وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ سورت الذاريات ?

"ሰብእ" ማለት "ሰው" ማለት ነው፥ "ግለ-ሰብእ" ማለት "ግላዊ ሰው" ማለት ነው፣ "ቤተ-ሰብእ" ማለት "የሰው ቤት" ማለት ነው፣ "ኅብረተ-ሰብእ" ማለት "የሰው ኅብረት" ማለት ነው፣ "ማኅበረ-ሰብእ" ማለት "የሰው ማኅበር" ማለት ነው። ስለ ሰው ጥናት በመስኩ ምሁራን ዘንድ "አንትሮፖሎጂ"anthropology" ይሉታል፥ ይህም ቃል "አንትሮፖስ" ἄνθρωπος ማለትም "ሰው" እና "ሎጂአ" λογία ማለትም "ጥናት" ከሚል ሁለት የግሪክ ቃላት የተዋቀረ ሲሆን "ሥነ-ሰብእ ጥናት" ማለት ነው። በቁርኣን "ኢንሣን" إِنسَٰن ማለት "ሰው" ማለት ሲሆን ይህም ቃል በነጠላ የተጠቀሰው 65 ጊዜ ብቻ ነው፥ ሰው የተፈጠረው ደግሞ ከአፈር፣ ከፍትወት ጠብታ፣ ከረጋ ደም፣ ከቁራጭ ስጋ፣ ከአጥንት እና ከጡንጫ ስጋ ነው፦
23፥12 *በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው*፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن سُلَالَةٍ مِّن طِينٍ
23፥13 *ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ የፍትወት ጠብታ አደረግነው*፡፡ ثُمَّ جَعَلْنَاهُ نُطْفَةً فِي قَرَارٍ مَّكِينٍ
23፥14 *ከዚያም ጠብታዋን የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ مَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ ۚ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

ሰው የአፈር፣ የፍትወት ጠብታ፣ የረጋ ደም፣ የቁራጭ ስጋ፣ የአጥንት እና የጡንጫ ስጋ ሁሉ ድምር ነው፥ ይህንን በዝርዝር ማየት እንችላለን፦
1. "ቱራብ" تُرَاب "አፈር" የሚለው ቃል 17 ጊዜ
2. "ኑጥፋህ" نُّطْفَة "የፍትወት ጠብታ" የሚለው ቃል 12 ጊዜ
3. "ዐለቃህ" عَلَقَة “የረጋ ደም” የሚለው ቃል 6 ጊዜ
4. "ሙድጋህ" مُضْغَة "ቁራጭ ስጋ" የሚለው ቃል 3 ጊዜ
5. "ዐዝም" عَظْم "አጥንት" የሚለው ቃል 15 ጊዜ
6. "ለሕም" لَحْم "ስጋ" የሚለው ቃል 12 ጊዜ ተጠቅስዋል።
---------------
በድምሩ = 65= ይሆናል። ይህም "ኢንሣን" إِنسَٰن "ሰው" የሚለው ቃል 65 ጊዜ መጠቀሱ ያለምክንያት አልነበረም፥ አላህ ነገር ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ስለሆነ ነው፦
72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና *ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን*፥ የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል፡፡ لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዲን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

42፥13 *ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ! በእርሱም አትለያዩ። شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ

“ዲን” دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ፈረደ" "በየነ" "አመነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ሃይማኖት” “ፍትሕ” “ፍርድ” “ሕግ” “መርሕ”Doctrine” ማለት ነው፥ ዲን በግሪክ “ዶግማ” δόγμα ይባላል። ዲን የእምነት እሴት እና የሥነ-ምግባር መርሖ ያቀፈ ሥርወ-እምነት ነው፥ “ሃይማኖት” የሚለው የግዕዝ ቃልም “ሀይመነ” ማለትም “አመነ” ወይም “ታመነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመን” ወይም “መታመን” ማለት ነው። እምነት በዕውቀት እያደገ የሚመጣ ሲሆን ሃይማኖት ግን የእምነት ተቋም ያለው አቋም ነው፥ ዲን ያለው ሰው "ሙተዲን" مُتَدَيِّن ይባላል። ዲኑል ኢሥላም ነቢያትን ወንድማማች ያደረገ ዐቂዳህ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 113
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ለዒሣ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም በመጨረሻይቱ ዓለም ቅርብ ነኝ። ነቢያት ወንድማማቾች ናቸው፤ እናቶቻቸው ይለያያሉ፤ ነገር ግን ሃይማኖታቸው አንድ ነው”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ أَنَا أَوْلَى النَّاسِ بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ، وَالأَنْبِيَاءُ إِخْوَةٌ لِعَلاَّتٍ، أُمَّهَاتُهُمْ شَتَّى، وَدِينُهُمْ وَاحِدٌ ‏

“እናቶቻቸው ይለያያሉ” ማለት በተላኩበት ዘመን ያለውን “ሸሪዓህ” እንደየ ማኅበረሰቡ የእድገት እና የአስተሳሰብ ደረጃ ይለያያል ማለት ነው፥ ዲናቸው ግን አንድ ነው። “ዲን” ደግሞ ሦስት ደረጃ አሉት፥ እነርሱም፦
1. “ኢሥላም” إِسْلَٰم
2. “ኢማን” إِيمَٰن
3. “ኢሕሣን” إِحْسَٰن ናቸው።

ነጥብ አንድ
“ኢሥላም”
“ኢሥላም” إِسْلَام‎ የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” “አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “መታዘዝ” “ማምለክ” ማለት ነው። “አርካን” أَرْكَان ማለት “ምሰሶ” ማለት ነው። አርካኑል ኢሥላም አምስት ናቸው፥ እነርሱም፦ ሸሃደተይን፣ ሶላት፣ ዘካህ፣ ሰውም እና ሐጅ ናቸው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 4
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ኢሥላም በአምስቱ መሠረቶች ላይ ተገንብቷል፥ እነርሱም፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው” በሚል ምስክርነት፣ ሶላትን በመቆም፣ ዘካህን በመስጠት፣ ረመዷንን በመፆም እና የአላህ በይት በመጎብኘት”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامُ الصَّلاَةِ وَإِيتَاءُ الزَّكَاةِ وَصَوْمُ رَمَضَانَ وَحَجُّ الْبَيْتِ

ነጥብ ሁለት
“ኢማን”
“ኢማን” إِيمَٰن የሚለው ቃል “አሚነ” أَمِنَ ማለትም “አመነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እምነት” ነው፥ “እምነት” በግል እና በዕውቀት እንደገባህ እና እንደተረዳከው የሚያድግ አሊያ የሚቀንስ ነው። አርካኑል ኢማን ስድስት ሲሆኑ፥ እነርሱም፦ በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በቀደር ማመን ናቸው። ይህ በሐዲሱል ጂብሪል ተገልጿል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 5
ዑመር ኢብኑ ኽጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፤ ወደ ነብዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ሙሐመድ ሆይ! ኢማን ምንድን ነው? እርሳቸውም፦ “በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሰናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው” አሉ*። ‏ قَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَجَاءَ رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَلْزَقَ رُكْبَتَهُ بِرُكْبَتِهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ مَا الإِيمَانُ قَالَ ‏”‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ
ነጥብ ሦስት
"ኢሕሣን”
“ኢሕሣን” إِحْسَٰن የሚለው ቃል “አሕሠነ” أَحْسَنَ ማለትም “አስዋበ” “አሳመረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማስዋብ” “ማሳመር” ማለት ነው፥ ኢሕሣን የዲን ማሳመሪያና ማስዋቢያ ነው። ኢሕሣን “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ” ማለት ነው፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 47 , ሐዲስ 6
ዑመር ኢብኑ ኸጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፣ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ አይታይም ነበር፥ ወደ ነቢዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት ተቃራኒ አድርጎ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ሙሐመድ ሆይ! ስለ ኢሥላም ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው” የሚል ምስክርነት፣ ሶላትን መቆም፣ ዘካህን መስጠት፣ ረመዷንን መፆም እና ለመጓዝ አቅም ካለህ የአላህን ቤት መጎብኘት ነው” አሉ። እርሱም፦ “እውነት ተናገርክ” አለ፥ እኛም በሚጠይቃቸው ነገር ተገረምን። ከዚያም ስለ ኢማን ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ “በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሰናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው” አሉ። እርሱም፦ “እውነት ተናገርክ” አለ፥ ከዚያም ስለ ኢሕሣን ንገረኝ አለ፥ እርሳቸውም፦ “አላህን እንደምታየው አርገህ ማምለክ፥ አሊያም አላህ እንደሚያይህ አርገህ ማምለክ ነው” አሉ”*። قَالَ حَدَّثَنِي عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ، قَالَ بَيْنَمَا نَحْنُ عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ذَاتَ يَوْمٍ إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى جَلَسَ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إِلَى رُكْبَتَيْهِ وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخِذَيْهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ أَخْبِرْنِي عَنِ الإِسْلاَمِ قَالَ ‏”‏ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَتُقِيمَ الصَّلاَةَ وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ وَتَصُومَ رَمَضَانَ وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلاً ‏”‏ ‏.‏ قَالَ صَدَقْتَ ‏.‏ فَعَجِبْنَا إِلَيْهِ يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ ثُمَّ قَالَ أَخْبِرْنِي عَنِ الإِيمَانِ قَالَ ‏”‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ كُلِّهِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ صَدَقْتَ ‏.‏ قَالَ فَأَخْبِرْنِي عَنِ الإِحْسَانِ قَالَ ‏”‏ أَنْ تَعْبُدَ اللَّهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ

አንድ ሰው በኢስላም “ሙሥሊም” مُسْلِم ሲባል፣ በኢማን “ሙእሚን” مُؤْمِن ሲባል፣ በኢሕሣን ደግሞ “ሙሕሢን” مُحْسِن ይባላል። አምላካችን አላህ ለነቢያችን”ﷺ” እና ለተከታዮቻቸው ያዘዘው ዲን ኑሕን፣ ኢብራሂምን፣ ሙሳን እና ዒሳንም ያዘዘበት ዲን ይህ ነው፦
42፥13 *ለእናንተ ከሃይማኖት ያንን በእርሱ ኑሕን ያዘዘበትን ደነገገላችሁ፡፡ ያንንም ወደ አንተ ያወረድነውን ያንንም በእርሱ ኢብራሂምን ሙሳንና ዒሳንም ያዘዝንበትን ሃይማኖትን በትክክል አቋቁሙ! በእርሱም አትለያዩ። شَرَعَ لَكُم مِّنَ الدِّينِ مَا وَصَّىٰ بِهِ نُوحًا وَالَّذِي أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ وَمَا وَصَّيْنَا بِهِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَىٰ ۖ أَنْ أَقِيمُوا الدِّينَ وَلَا تَتَفَرَّقُوا فِيهِ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የዘካህ ገንዘብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥219 *”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”*፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ

ዘካህ ከካፒታል ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5% ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 5፥2=2.5 ይሆናል፦
2፥219 *”ምንን እንደሚመጸውቱም መጠኑን ይጠይቁሃል፡፡ «ትርፍን መጽውቱ» በላቸው”*፡፡ እንደዚሁ ታስተነትኑ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾችን ይገልጽላችኋል፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ مَاذَا يُنفِقُونَ قُلِ الْعَفْوَ ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُمْ تَتَفَكَّرُونَ
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”*። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

በዚህ ሐዲስ መሠረት የአንድ ሰው ካፒታል 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ዘካህ ይወጅበታል፥ በሸሪዓህ የዘካህ አነስተኛ የክፍያ መጠን “ኒሷብ” نِصاب ይባላል፥ ይህም ኒሷብ የሚለካው 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ነው። “ዲናር” دِينَار‎ ማለት “የወርቅ ሳንቲም”gold coin” ማለት ሲሆን “ዲርሀም” دِرْهَم‎ ማለት ደግሞ “የብር ሳንቲም”silver coin” ማለት ነው። ይህ በጥንት “የኮሞዲቲ ገንዘብ”commodity money” ይባላል።
“ዲናር” እና “ዲርሀም” የሚለኩት በሚስቃል ነው፥ “ሚስቃል” مِثْقَال የሚለው ቃል “ሰቀለ” ثَقَلَ ማለትም “ከበደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክብደት” ማለት ነው።
1 ሚስቃል ወርቅ 4.25 ግራም ነው፥ 20 ሚስቃል ወርቅ ደግሞ 4,25x 20 = 85 ግራም ወርቅ ይሆናል ማለት ነው።
1 ሚስቃል ብር 2.975 ግራም ነው፥ 200 ሚስቃል ብር ደግሞ 2.975x 200= 595 ግራም ብር ይሆናል ማለት ነው።

በዘካህ ላይ የሚወጅበው ኒሷብ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ነው።
አንድ ሙሥሊም ያለው ካፒታል በዓመት ውስጥ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ያክል ከሆነ ዘካህ ማውጣት ግዴታው ነው። ይህ ኒሷብ ወደ ወረቀት ገንዘብ”Fiat money” ለመቀየር ወርቅን ዛሬ ባለው በ 24 ካራት የወቅቱ ግብይት ለናሙና ያክል መሥራት ይቻላል፦
1. በስውዲን አንድ ግራም ወርቅ 396 ክራውን ነው፥ 396×85= 33,660 ክራውን ይሆናል።
2. በኢትዮጵያ አንድ ግራም ወርቅ 1,181 ብር ነው፥ 1,181×85= 100,385 ብር ይሆናል።
3. በአሜሪካ አንድ ግራም ወርቅ 41.30 ዶላር ነው፥ 41.30×85= 3,510.30 ዶላር ይሆናል።

ስለዚህ አንድ ሙሥሊም ያለው ካፒታል በገንዘብ ሲተመን በስውዲን 33,660 ክራውን፣ በኢትዮጵያ 100,385 ብር፣ በአሜሪካ 3,510.30 ዶላር ወዘተ ከሆነ ከዚያ ወዲህ ዘካህ ማውጣቱ ፈርድ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው በኢትዮ 100,385 ሺ ብር ካለው ከ 100,385 ሺ ብር ላይ 2.5% ዘካ ያወጣል፥ ያ ማለት የዘካው ብር 100,385×2.5÷100= ውጤቱ 2,509 ብር ይሆናል ማለት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእግዚአብሔር ወይስ የክርስቶስ ደም?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥17 *እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

በክርስትና ስልታዊ ሥነ-መለኮት ውስጥ “ኢየሱስ አምላክ ነው” ብለው ድምዳሜ ላይ ካደረሳቸው አናቅጽ መካከል ይህ ጥቅስ ይጠቀሳል፦
የሐዋርያት ሥራ 20፥28 *በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን* ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። προσέχετε ἑαυτοῖς καὶ παντὶ τῷ ποιμνίῳ, ἐν ᾧ ὑμᾶς τὸ Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ἔθετο ἐπισκόπους, ποιμαίνειν τὴν ἐκκλησίαν τοῦ Θεοῦ, ἣν περιεποιήσατο διὰ τοῦ αἵματος τοῦ ἰδίου.

ቅድሚያ እንደ ባይብሉ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ መንፈስ ስጋ እና አጥንት የለውም፦
ዮሐንስ 4፥24 *እግዚአብሔር “መንፈስ” ነው*።
ሉቃስ 24፥39 *“መንፈስ ሥጋ እና አጥንት የለውምና”*።

እግዚአብሔር ስጋ ከሌለው የስጋ ደም በስጋ ውስጥ ስላለ እግዚአብሔር ደም የለውም፦
ዘሌዋውያን 17፥11 *"የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና"*።

ይህ የሥነ-አመክንዮ ሙግት ነው። ሲቀጥል እንደ ባይብሉ ደም አለው የተባለው እግዚአብሔር ሳይሆን ልጁ ነው፦
ዕብራውያን 9፥14 ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ *"ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም"*

"ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም" ማለት ደሙ የክርስቶስ እንጂ የእግዚአብሔር አለመሆኑን ያሳያል። የደሙ ባለቤት እራሱ አምላክ አለው። አምላኩ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፦
ራእይ 1፥5-6 ለወደደን ከኃጢአታችንም *በደሙ ላጠበን፥ መንግሥትም ለአምላኩ እና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ*።
ዕብራውያን 13፥12 ስለዚህ *ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ* ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ።
1ኛ ዮሐንስ 1፥7 *የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም* ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።

ልጁ የማን ልጅ? የእግዚአብሔር ልጅ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ ደሙ የልጁ እንጂ የእግዚአብሔር አይደለም፦
1ኛ ዮሐንስ 5፥12 *ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም*።

"ሢሠልስ "ኢድኦስ" ἴδιος ማለት "ገዛ"own" ማለት ሲሆን ገላጭ ቅጽል ነው። "በገዛ" ምን? "የገዛ ልጁ" የሚል ጥሩ የተዛማች ሙግት አለ፦
ሮሜ 8፥32 *ለ-"ገዛ" ἰδίου ልጁ ያልራራለት*።
ሮሜ 8፥3 *እግዚአብሔር የገዛ ልጁን* በኃጢአተኛ *ሥጋ* ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና።

"ስጋ" የሚለው ይሰመርበት። ስጋ ያለው ልጁ ሲሆን አባቱ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፥ "የገዛ" በሚለው ቃል ውስጥ "ልጁ" የሚለው ቃል ተደብቆ የመጣ ነው። ለምሳሌ እነዚህ አናቅጽ ላይ "የገዛ" ብለን ብንተወው ትርጉም አይሰጥም፦
ዮሐንስ 1፥11 የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ *"የገዛ" ἴδιοι ወገኖቹም* አልተቀበሉትም።
ዮሐንስ 13፥1 "የገዛ" ἰδίους "ወገኖቹን" የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።
የሐዋርያት ሥራ 4፥23 ተፈትተውም ወደ *"ገዛ" ἰδίους "ወገኖቻቸው" መጡ።

"ወገን" የሚለው የግሪኩ ቃል "ሰገኒአ" συγγένεια ሲሆን ሦስቱም አናቅጽ ላይ የለም። ታዲያ "የገዛ አልተቀበሉትም" "የገዛ የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው" "ወደ ገዛ መጡ" ትርጉም ይሰጣልን? አይ "የገዛ" በሚለው ቃል ውስጥ "ወገን" የሚለው ቃል ተደብቆ የመጣ ነው። ሌላ ናሙና፦
ዮሐንስ 19፥27 ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ *ወደ "ገዛ" ἴδια "ቤቱ" ወሰዳት*።

"ቤት" የሚለው የግሪኩ ቃል "ኡኪአ" οἰκία ሲሆን እዚህ አንቀጽ ላይ የለም። ታዲያ ወደ "ገዛ" ወሰዳት" ትርጉም ይሰጣልን? አይ "የገዛ" በሚለው ቃል ውስጥ "ቤት" የሚለው ቃል ተደብቆ የመጣ ነው። ታዲያ "ወገን" እና "ቤት" የሚለው ስለሚመጣ ነው ካላችሁ እንግዲያውስ "የገዛ" በሚለው ቃል ውስጥ "ልጁ" የሚለው ቃል ተደብቆ ስለሚመጣ የሥላሴ አማንያን ሳይቀሩ "በገዛ "ልጁ" ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ" ብለው ተርጉመውታል፦
1. "the blood of his own Son."
(NET) New English Translation- 2005
2. "the blood of his own Son."
(NRSV) New Revised Standard Version – 1989
3. "the blood of his own Son."
(RSV) Revised Standard Version - 1946
4. "the death of his own Son."
(CEB) Common English Bible – 2011
5. "the blood of his own."
(DARBY) J.N.Darby – 1890
6. "his own Son’s blood."
(CJB) Complete Jewish Bible – 1998
7. "the blood of his own Son."
(CEV) Contemporary English Version – 1995
8. "the blood of his own (Son); or with his own blood."
(EXB) Expanded Bible – 2011
9. "the blood of his Son."
(GNT) Good News Translation – 1992
10. "the blood of his own Son."
(LEB) Lexham English Bible – 2010
11. "the ho blood haima of ho his own idios Son."
(MOUNCE) Mounce Reverse-Interlinear New Testament – 2011
13. "the death of his own son."
(NCV) New Century Version – 2005
13. "the blood of His own Son."
(VOICE) The Voice Bible Translation – 2011

እነዚህ 13 ስመጥርና ዝነኛ ትርጉማን እንዳልተሳሳቱ የምናውቀው የአዲሱ ዓለም ዓቀፍ ትርጉም"the New International Version(NIV) እራሱ በግርጌ ማስታወሻው፦ "ወይም በገዛ ልጁ ደሙ"Or with the blood of his own Son” መባል እንደሚችል አስፍሯል። "ገዛ"own" ገላጭ ቅጽል ስለሆነ የሚፈታው ሌላ ጥቅስ ላይ ባለው ቃል ነው፥ ለምሳሌ፦
ኤፌሶን 1፥6 *በውድ ልጁም* እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ።

"ልጁ" የሚል ግሪኩ ላይ የለም። ግን "ውድ" የሚለውን ገላጭ ቅጽል ሌላ ቦታ "ውድ ልጄ" በሚለው ይፈታል፦
ማቴዎስ 3፥17 *ውድ ልጄ ይህ ነው"* አለ።

ኤፌሶን 1፥6 ላይ ልጁ የሚለውን ካላስገቡ ደሙ የአብ ሆኖ ያርፋል፦
ኤፌሶን 1፥7 *በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ* የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።
"ልጁ" የሚል ግሪኩ ላይ የለም። ዐውዱ ስለ አብ ስለሚናገር አንደኛችሁን እንደ ቄስ ተክለ-ማርያም ገዛኸኝ ደሙ የአብ ነው ብላችሁ እረፉት። "ውድ" የሚለውን "በውድ ልጁ" በሚል እንደተረዳችሁት፥ "ገዛ" የሚለውን "በገዛ ልጁ" በሚል ተረዱት።
ሲያረብብ የሐዋርያት ሥራ "ሄን" ἣν ማለትም "እርሱ" የሚለው አንጻራዊ ተውላጠ-ስም "ክርስቶስ" የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፦
1 ጴጥሮስ 1፥19 *በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ*።

አየህ "በገዛ ደሙ የዋጃትን" የሚለውን "በክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ" በሚለው ይፈታል፥ በቀላሉ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን በገዛ ደሙ መዋጀቱን ያሳያል። ክርስቶስ ደግሞ እግዚአብሔር ሳይሆን የእግዚአብሔር ነው፥ እግዚአብሔር ለክርስቶስ ራስ ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 3፥23 *ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው*።
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ*።

ጳውሎስ፦ "አንድ እግዚአብሔር አለ፥ በእግዚአብሔር እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" ብሎናል፥ ደሙ የእግዚአብሔር ሳይሆን በመካከለኛ ያለው የሰው ደም ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 2፥5 *አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔር እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው*።
ዕብራውያን 12፥23 *የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት "ደም" ደርሳችኋል*።

የሚገርመው እኮ "ቴኦዩ" Θεοῦ ማለትም "የእግዚአብሔርን" ቤተክርስቲያን የሚል የግሪክ እደ-ክታባት እንዳለ ሁሉ "ኩርዮዩ" Κυρίοῦ ማለትም "የጌታን" ቤተክርስቲያን የሚል አለ። American Standard Version በበኩሉ በገዛ ደሙ የዋጃትን የጌታን ቤተ ክርስቲያን" ብለው ተርጉመውታል፦
Acts 20:28 (ASV) The church of the *Lord* which he purchased with his own blood.

የ 1980 አዲስ ትርጉም፦ "ጌታ በገዛ ደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ" ብለው ተርጉመውታል፦
የሐዋርያት ሥራ 20፥28 *ጌታ በገዛ ደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ*።

አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ ላይም ፦ "ብዙ የጥንት ቅጆች የጌታን" እንዳሉት እና "በገዛ ልጁ ደም ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፥ የገዛ የሚለው ቃል ተወዳጅነትን ለመግለጽ የገባ ቃል ነው። ይህም ልጁን ያመለክታል" ብሎ ተናግሯል። ይህ የትርጉም ሥራ ሢሠራ ከተሳተፉት መካከል ምራቅ የዋጠ ተወያይ የሚባለው ዶክተር ተስፋዬ ሮበሌ ሲሆን፥ ግን እርሱ፦ "በገዛ ደሙ የዋጃትን የጌታን ቤተ ክርስቲያን" እና "በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን የእግዚአብሔ ቤተ ክርስቲያን" የሚል የለም" ሲል ቀጥፏል። ብዙ ጊዜ ይዋሻል፥ ወትሮም አባይ መዋሸት ልምዱ ነው።
በጥቅሉ የጳውሎስ ንግግር ላይ "የልጅ ደም" ወይም "መዋጀት" አሊያም "ልጅ" የእኛ የሙሥሊሞች እሳቤ አይደለም። ዋናው ነጥብ የሐዋርያት ሥራ 20፥28 ላይ ጳውሎስ "እግዚአብሔር ደም አለው" አላለም የሚል ነው። ፈጣሪ የፍጡር ደም ጥገኝነት አይጠይቅም፥ ፍጡሩን ኢየሱስ ፈጣሪ ነው ማለት ክህደት ነው፦
5፥17 *እነዚያ አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሊቃውንት እና መነኮሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

9፥31 *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፥ እንዲሁ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ያዙ። ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው*፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ሚሽነሪዎች፦ "እኛ ሊቃውንቶቻችንን እና መነኮሳቶቻችንን አማልክት አድርገን አልያዝን፥ እነርሱን አምልከንም አናውቅም። ስለዚህ ቁርኣን ያቀረበብን ክስ አግባብ አይደለም" ይላሉ። በኢሥላም ያሉ የመስኩ ሊሒቃን፦ “ውኃን ከጡሩ፥ ነገርን ከሥሩ” ይላሉና እኛም ከሥሩ ይህንን ተጻራሪ ምልከታ እንመልከት።
"ሐብር" حَبْر ወይም "ሒብር" حِبْر ማለት "ምሁር" "ሊቅ" "ዐዋቂ" ማለት ነው፥ የሐብር ወይም የሒብር ብዙ ቁጥር ደግሞ "አሕባር" أَحْبَار ሲሆን "ምሁራን" "ሊቃውንት" "ሊሒቃን" ማለት ነው። እነዚህም ምሁራን የአይሁዳውያን ምሁራን ናቸው፦
26፥197 *የእስራኤል ልጆች ሊቃውንት የሚያውቁት መኾኑ ለእነርሱ(ለመካ ከሓዲዎች) ምልክት አይኾናቸውምን?* أَوَلَمْ يَكُن لَّهُمْ آيَةً أَن يَعْلَمَهُ عُلَمَاءُ بَنِي إِسْرَائِيلَ

"ዐሊም" عَلِيم ማለት "ዐዋቂ" ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ የተቀመጠው የዐሊም ብዙ ቁጥር "ዑለማእ" عُلَمَاء ሲሆን "ሊቃውንት" ማለት ነው።
"ራሂብ" رَاهِب ማለት "መነኩሴ" ማለት ነው፥ የራሂብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሩህባን" رُهْبَان ሲሆን "መነኮሳት" ማለት ነው። እነዚህም መነኮሳት የክርስቲያን መነኮሳት ናቸው፦
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ በእነዚያም በተከተሉት ሰዎች ልቦች ውሰጥ መለዘብንና እዝነትን አደረግን፡፡ *”አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም*”፡፡ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ وَجَعَلْنَا فِي قُلُوبِ الَّذِينَ اتَّبَعُوهُ رَأْفَةً وَرَحْمَةً وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ابْتِغَاءَ رِضْوَانِ اللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا ۖ فَآتَيْنَا الَّذِينَ آمَنُوا مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَاسِقُونَ

ክርስቲያኖች አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና አላህ በእነርሱ ላይ አልደነገገም፥ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት።
እዚህ ድረስ ከተግባባን ድንጋጌ ውስጥ አምስት ሕግጋት አሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ. “ፈርድ” فَرْد‎ ማለትም “የታዘዘ” ግዴታ ነው።
2ኛ. “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ ማለትም “የተወደደ” ሡናህ ነው።
3ኛ. “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ ማለትም “የተፈቀደ” ሐላል ነው።
4ኛ. “መክሩህ” مَكْرُوه‎ ማለትም “የተጠላ” ድርጊት ነው።
5ኛ. “ሐራም” حَرَام ማለትም “የተከለከለ” ድርጊት ነው።
አንድን ነገር ፈድር፣ ሙስተሐብ፣ ሙባሕ፣ መክሩህ፣ እና ሐራም ማለት የሚችለው አላህ ብቻ ሆኖ ሳለ የአይሁዳውያን ሊቃውንት እና የክርስትና መነኮሳት ሐላሉን ሐራም፥ ሐራሙን ሐላል በማድረግ ሕግጋትን ከገዛ ዝንባሌአቸው ደነገጉ፦
9፥31 *ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊያመልኩ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፥ እንዲሁ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ያዙ። ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው*፡፡ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَـٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ታላቁ ሙፈሢር ኢብኑ ከሲር "አማልክት አድርገው ያዙ" ማለት ምን ማለት እንደሆነ በዚህ ሐዲስ ፈሥሮታል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3378
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው፦ *"ወደ ነቢዩም”ﷺ” ስመጣ በአንገቴ ዙሪያ የወርቅ መስቀል ነበረኝ፥ እርሳቸውም፦ "ይህንን ጣዖት ከአንተ አስወግድ" አሉ። ሱረቱል በራኣህ "ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ" የሚለው ሲነበብ ሰማዋቸው። እርሳቸውም፦ ለእነርሱ አያመልኳቸውም፥ ነገር ግን ሐላል ባደረጉላቸው ጊዜ ሐላል አርገው ይቀበሉታል። ሐራም ባደረጉላቸው ጊዜ ሐራም አርገው ይቀበሉታል" አሉ*። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، قَالَ أَتَيْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَفِي عُنُقِي صَلِيبٌ مِنْ ذَهَبٍ ‏.‏ فَقَالَ ‏"‏ يَا عَدِيُّ اطْرَحْ عَنْكَ هَذَا الْوَثَنَ ‏"‏ ‏.‏ وَسَمِعْتُهُ يَقْرَأُ فِي سُورَةِ بَرَاءَةََ ‏:‏ ‏(‏ اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ ‏)‏ قَالَ ‏"‏ أَمَا إِنَّهُمْ لَمْ يَكُونُوا يَعْبُدُونَهُمْ وَلَكِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا أَحَلُّوا لَهُمْ شَيْئًا اسْتَحَلُّوهُ وَإِذَا حَرَّمُوا عَلَيْهِمْ شَيْئًا حَرَّمُوهُ
መስቀል በአንገት ላይ ማድረግ ከመነኮሳት የመጣ ትእዛዝ እንጂ ከአላህ ዘንድ አይደለም። ሲጀመር "ረብ" رَبّ የሚለው ቃል "ረበ" رَبَّ ማለትም "አዘዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጌታ" ወይም "አዛዥ" ማለት ነው፥ የረብ ብዙ ቁጥር ደግሞ "አርባብ" أَرْبَاب ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው። "አላህ ብቻውን ትእዛዝ አውጪ ነው" ብሎ አላህ ከፍጡራን መነጠል "ተውሒደ አር-ሩቡቢያህ" تَوْحِيد الرُبُوبِيّة ነው፥ "ሩቡቢያህ" رُبُوبِيّة ማለት በራሱ "ጌትነት" ማለት ነው። "ያልታዘዙ ሲኾኑ" የሚለው ይህንኑ ነው፥ ነቢያችን"ﷺ" ሆኑ አሚሮቻችን አላህ ባዘዘው ያዛሉ፥ በከለከለው ይከለክላሉ እንጂ የእራሳቸው ድንጋጌ አያወጡም። ነገር ግን አይሁዳውያን ሊቃውንቶቻቸውን ክርስቲያኖች መነኮሳታቸውን ከአላህ ሌላ ድንጋጌ በመቀበል ጌቶች አድርገው ያዙ። "አያመልኳቸውም" የሚለው ይሰመርበት፥ አላህ በአምልኮ ከፍጡራን መነጠል "ተውሒደል ኡሉሂያህ" تَوْحِيد الأُلُوهِيَّة ነው፥ "ኡሉሂያህ" أُلُوهِيَّة ማለት በራሱ "አምላክነት" ማለት ነው። ተውሒድ ትክክለኛ የሆነች ቃል ናት፥ ተውሒደል ኡሉሂያህ "አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ" ነው፣ ተውሒደ አር-ሩቡቢያህ "ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አርባብ አድርጎ ላይዝ" ነው፦
3፥64 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አርባብ አድርጎ ላይዝ ነው"* በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ ۚ

ነገር ግን መደንገግ የሚችለው አላህ ብቻ ሆኖ ሳለ ሌላ ማንነት የደነገገውን ድንጋጌ ማድረግ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ ሕግን የሚደነግግልን አርባብ አድርጎ መያዝ ነው፥ ይህ በአላህ ጌትነት ላይ ማሻረክ ነው፦
42፥21 ከሃይማኖት *አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነርሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን?* أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُم مِّنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَن بِهِ اللَّهُ

"ሸሪክ" شَرِيك ማለት "ተጋሪ" ማለት ነው፥ የሸሪክ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሹረካእ" شُرَكَاء ሲሆን "ተጋሪዎች" ማለት ነው፥ አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ነገር ሐላል ማድረግ ለእነርሱ የደነገጉ በአላህ ሐቅ ላይ ተጋሪዎች አሏቸው። ለዚህ ነው "ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው" ነው ያለው፥ ስለዚህ "ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን በአላህ ላይ በማጋራት ጌቶች አድርገው ያዙ ማለት በዚህ ስሌት እንረዳዋለን።
ሲቀጥል "ጌቶች" የሚለው "አማልክት" ተብሎ ቢቀመጥም "አምላክ አድርጎ መያዝ" ማለት ያንን ማንነት ሆነ ምንነት በቀጥታ ማምለክ ብቻ አይደለም። ምክንያቱም ለአላህ የሚገባውን ሐቅ ለዝንባሌ መስጠት በራሱ አምላክ አድርጎ መያዝ ከሆነ ለአላህ የሚገባውን ሐቅ ለሊቃውንቶቻቸውን እና ለመነኮሳታቸውን መስጠት አምላክ አድርጎ መያዝ ነው፦
25፥43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትኾናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا
12፥53 «ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْسَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ

መቼም ዝንባሌውን በቀጥታ "አምላኬ" እያለ የሚያመልክ ፍጡር የለም። ዝንባሌ ከነፍሢያችን ነው፥ ነፍሢያህ አላህ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በሐራም ነገር በእርግጥ አዛዥ ናት። ነፍሢያህ ሐራሙን በማዘዟ ዝንባሌን አምላክ አድርጎ እንደሚያዝ ሁሉ እነርሱም ሊቃውንቶቻቸውን እና መነኮሳታቸውን በሐራም በመታዘዝ፥ በሐላል በመከልከል አምላክ አድርገው ይዘዋል። ከላይ የቀረበው ተጻራሪ ምልከታ በዚህ የሙግት አግባብ ሐቁን አውጥተናል፥ ባጢል በሐቅ ፊት እሳት የነካው ሰም፣ ፀሐይ ያየው ቅቤ፣ ነፋስ የጎበኘው አቧራ ይሆናል፦
17፥81 በልም *«እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»* وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًۭا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

የዐሊማችን የሼኽ ኢብራሂም ሲራጅ ከዱንያ መለየት የተሰማን ጥንቅ ሀዘን በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ይህ ጥልቅ ሀዘን ሲነካን፦ "ኢና ሊሏሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን" إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُون ብለናል፦
2፥156 እነዚያን መከራ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ ነን፥ እኛም ወደ እርሱ ተመላሾች ነን» የሚሉትን አብስር፡፡ الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُم مُّصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ

አምላካችን አላህ ለቤተሰባቸው፣ ለተማሪዎቻቸው እና ለሚወዷቸው ሁሉ ጽናቱን፣ መጽናናቱን እና ትእግስቱ ይስጠን። ሃዘናችንን አጅር የምናገኝበት ያርግልን። እርሳቸውንም ጀነቱል ፊርደውሥ ይወፍቃቸው! አሚን።
ተስዊር

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

59፥24 *እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ አስገኚው፣ "ቅርፅን አሳማሪው" ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ

አምላካችን አላህ በማኅፀን ውስጥ እንደሚሻ አርጎ የሚቀርፀን እርሱ ነው፥ እርሱ በሚሻው መንገድ ስለሚቀርፀን "አል-ሙሶዊር" الْمُصَوِّرُ የሚል ስም አለው፦
59፥24 *እርሱ አላህ ፈጣሪው፣ አስገኚው፣ "ቅርፅን አሳማሪው" ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
3፥6 *እርሱ ያ በማሕጸኖች ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርፃችሁ ነው*፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ ۚ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
64፥3 ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ፡፡ *ቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም አሳመረ*፡፡ መመለሻችሁም ወደ እርሱ ነው፡፡ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ ۖ وَإِلَيْهِ الْمَصِيرُ
82፥8 *በማንኛውም በሻው ቅርፅ በገጣጠመህ*፡፡ فِي أَيِّ صُورَةٍ مَّا شَاءَ رَكَّبَكَ

"ሙሶዊር" مُصَوِّر የሚለው ቃል "ሶወረ" صَوَّرَ ማለትም "ቀረፀ" "ሳለ" "ሠራ" "ፈጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቀራፅ" "ሰዓሊ" "ሠሪ" "ፈጣሪ" ማለት ነው። አላህ አደምን በሚሻው ቅርፅ ፈጥሮታል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 79, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"አላህ አደምን በቅርጹ ፈጠረ፥ ስፋቱ ስድሳ ይዘት ነበር። በፈጠረው ጊዜ፦ ሒድና እዚያ የተቀመጡትን የመላእክት ቡድን ሰላም በል! ሰላምታህን ምን ብለው እንደሚመልሱ ስማቸው! ሰላምታህም የአንተና የዝርያህ ሰላምታ ትሆናለች" አለው። አደምም፦ "አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም" አለ፥ እነርሱም፦ "አሥ-ሠላሙ ዐለይከ ወራሕመቱሏህ" አሉ፥ እነርሱ፦ "ወራሕመቱሏህ" ጨበሩለት። ነቢዩም"ﷺ"፦ *"ማንም ጀነት የሚገባው በአደም ቅርፅ ነው" አሉ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ، طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا، فَلَمَّا خَلَقَهُ قَالَ اذْهَبْ فَسَلِّمْ عَلَى أُولَئِكَ النَّفَرِ مِنَ الْمَلاَئِكَةِ جُلُوسٌ، فَاسْتَمِعْ مَا يُحَيُّونَكَ، فَإِنَّهَا تَحِيَّتُكَ وَتَحِيَّةُ ذُرِّيَّتِكَ‏.‏ فَقَالَ السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ‏.‏ فَقَالُوا السَّلاَمُ عَلَيْكَ وَرَحْمَةُ اللَّهِ‏.‏ فَزَادُوهُ وَرَحْمَةُ اللَّهِ، فَكُلُّ مَنْ يَدْخُلُ الْجَنَّةَ عَلَى صُورَةِ آدَمَ

"ሱራህ" صُورَة‎ በሚለው ቃል መድረሻ ላይ ያለው "ሂ" هِ የሚለው አገናዛቢ ተውላጠ ስም "አደም" آدَم የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፥ ምክንያቱም "ሱራቲ-አደም" صُورَةِ آدَمَ የሚለው "ሱራቲ-ሂ" صُورَتِهِ ለሚለው ተለዋዋጭ ነው። "ሱራቲ-ሂ" صُورَتِهِ የሚለው ወደ አላህ የሚጠጋ ነው" የሚሉ ምሁራን አሉ። ይህንን ለመረዳት ስለ ኢዷፋህ እሳቤው ሊኖረን ይገባል። "ኢዷፋህ" إِضَافَة የሚለው ቃል "አዷፈ" أَضَافَ‎ ማለትም "አገናዘበ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አገናዛቢ"possessive" ማለት ነው፥ የኢዷፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ኢዷፋት" إِضَافَات‎ ነው። ኢዷፋህ በሁለት ዐብይ ክፍል ይከፈላሉ፥ እነርሱም "ኢዷፈቱ አሽ-ሸሪፋህ" إِضَافَة الشَرِيفَة እና "ኢዷፈቱ አስ-ሲፋህ" إِضَافَة الصِفَة ናቸው።

ነጥብ አንድ
"ኢዷፈቱ አሽ-ሸሪፋህ"
"ሸሪፋህ" شَرِيفَة የሚለው ቃል "ሸሩፈ" شَرُفَ ማለትም "ላቀ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እልቅና" ማለት ነው፥ የሸሪፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሸሪፋት" شَرِيفَات‎ ነው። ነቢያችን"ﷺ" የአደምን ቅርፅ ወደ አላህ በማስጠጋት በአገናዛቢ "ቅርፁ" ማለታቸው እልቅናን ያመለክታል፥ ልክ የአላህ ቤት፣ የአላህ ግመል፣ የአላህ ምድር ተብሎ በቁርኣን እደተቀመጠው ማለት ነው፦
2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም *ቤቴን* ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ
11፥64 ሕዝቦቼም ሆይ! ይህቺ ለእናንተ ተዓምር ስትሆን *የአላህ ግመል ናት*፡፡ ተውዋትም፡፡ *በአላህ ምድር* ውስጥ ትብላ፡፡ በክፉም አትንኳት፡፡ ቅርብ የሆነ ቅጣት ይይዛችኋልና» አላቸው፡፡ وَيَا قَوْمِ هَـٰذِهِ نَاقَةُ اللَّهِ لَكُمْ آيَةً فَذَرُوهَا تَأْكُلْ فِي أَرْضِ اللَّهِ وَلَا تَمَسُّوهَا بِسُوءٍ فَيَأْخُذَكُمْ عَذَابٌ قَرِيبٌ

ቤት፣ ግመል፣ ምድር የአላህ ባሕርይ ሳይሆኑ እልቅና ለመስጠት እንደሆኑ ሁሉ "የአደም ቅርፅ" ወደ አላህ በማስጠጋት እልቅና ሰቶቷል። ይህ አንዱ የምሁራን እይታ ነው።

ነጥብ ሁለት
"ኢዷፈቱ አስ-ሲፋህ"
"ሲፋህ" صِفَة የሚለው ቃል "ወሰፈ" وَصَفَ‎ ማለትም "ገጠለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መገለጫ" ወይም "ባሕርይ" ማለት ነው፥ የሲፋህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሲፋት" صِفَات‎ ነው። "ሱራህ" صُورَة‎ የሚለው ቃል "መልክ" በሚል ከመጣ ባሕርይን ታሳቢ ያደረገ ነው፥ የአላህ ዕውቀት፣ የአላህ ቻይነት፣ የአላህ እይታ፣ የአላህ መስማት፣ የአላህ እጅ ወዘተ የአላህ ባሕርያት ናቸው። አላህ በባሕርይው አደምን ፈጥሮታል፥ ለምሳሌ በእጆቹ ፈጥሮታል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት* ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

ይህ የምሁራን ሁለተኛ እይታ ነው። ኢንሻላህ ስለ ተስዊር በክፍል ሁለት እንዳስሳለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተኩላ እና አህያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

22፥8 *ከሰዎችም ውስጥ ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አለ*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَابٍ مُّنِيرٍ

ከዕለታት አንድ ቀን ተኩላ እና አህያ፦ "የሳር ቀለም እንዲህ ነው እንዲያ ነው" በሚል ክርክር ውስጥ ገቡ። አህያ፦ “የሳር ቀለም ቢጫማ ነው” አለ። ተኩላ፦ "በፍፁም ! አረንጓዴ ነው” አለ።
ክርክራቸው እየጦፈ መጣ፤ ሊያስማማ የሚችል ነጥብ ላይ መድረስ አልቻሉም። በመጫረሻም የጫካ ንጉሥ ከሆነው አንበሳ ዘንድ ቀርበው መሸማገል እንዳለባቸው ወሰኑ። ሽምግልናው ተጀመረ፥ ሁለቱም የመከራከሪያ አሳባቸውን አቀረቡ። አንበሳም የሁለቱን የመከራከያ ነጥብ በጥሞና አዳመጠ፥ የፍርድ ሒደቱን ለመከታተል የታደሙት እንስሳት በሙሉ ውሳኔውን ለመስማት ጆሯቸውን ጣል አደረጉ። አንበሳው ታዳሚውንም ሆነ ተኩላውን ቅር የሚያሰኝ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ፥ ተኩላው በአንድ ወር እስራት እንዲቀጣ ሲወሰንበት፤ አህያው ደግሞ በነፃ ተሰናበተ።

በፍርዱ ውሳኔ ቅር የተሰኘው ተኩላ እንዲህ በሚል ስሞታ አቀረበ፦ "ክቡር አንበሳ ሆይ! የሳር ቀለም አረንጓዴ አይደለምን? አንበሳም፦ "አዎ! በርግጥ አረንጓዴ ነው” በማለት መለሰ። ተኩላውም፦ "ታዲያ በየትኛው ጥፋቴ ነው ለአንድ ወር ያክል ዘብጥያ እንድወርድ የወሰንክብኝ? አንበሳውም፦ “ትክክል ነህ! በአመለካከትህ ቅንጣት ስህተት አላስተዋልኩም። ጥፋትህ በዚህ ጉዳይ ከአህያ ጋር ክርክር ውስጥ መግባትህ ነው። ነገሮችን በጥልቀት መረዳት እና መገንዘብ ከማይችል አካል ጋር መከራከር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዘን አንደሚችል የአንድ ወር እስራት የወሰንኩብህ ትምህርት ትቀስም ዘንድ ብየ ነው” አለው።
ከተኩላ እና ከአህያው የምንማረው ቁምነገር ቢኖር ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም ከሚከራከር ሰው ጋር ጊዜን፣ ጉልበትን፣ ዕውቀትን አለማባከንን ነው፦
22፥8 *ከሰዎችም ውስጥ ያለ ዕውቀት፣ ያለ ማስረጃም፣ ያለ አብራሪ መጽሐፍም በአላህ ነገር የሚከራከር ሰው አለ*፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يُجَادِلُ فِي اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَلَا هُدًى وَلَا كِتَابٍ مُّنِيرٍ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተስዊር

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

"ሙሶዊር" مُصَوِّر ማለት "ቀራፅ" "ሰዓሊ" "ሠሪ" "ፈጣሪ" ማለት እንደሆነ አይተን ነበር፥ የሙሶዊር ብዙ ቁጥር ደግሞ "ሙሶዊሩን" مُصَوِّرُون ወይም "ሙሶዊሪን" مُصَوِّرِين ሲሆን "ቀራፆች" "ሰዓሊዎች" ማለት ነው፦
23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

"ሰዓሊዎች" ለሚለው ቃል የገባው "ኻሊቂን" خَالِقِين ሲሆን "ሙሶዊሪን" مُصَوِّرِين ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 150
ዐብደላህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በትንሳኤ ቀን ከሰዎች በጣም ተቀጪ ሰዓሊዎች ናቸው"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ أَشَدَّ النَّاسِ عَذَابًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ الْمُصَوِّرُونَ ‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 182
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የስዕላት ባለቤት በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ፥ ለእነርሱም፦ "የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ" ይባላሉ"*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ إِنَّ أَصْحَابَ هَذِهِ الصُّوَرِ يُعَذَّبُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَيُقَالُ لَهُمْ أَحْيُوا مَا خَلَقْتُمْ

ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው። ነቢያችን”ﷺ” በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው፥ ይህም “ጀዋሚዓል ከሊም” ነው። “ጀዋሚዓል ከሊም” جَوَامِعَ الْكَلِم ማለት “አንድ ቃል ሆኖ ብዛት ትርጉም ያለው” ማለት ነው። "ሱራህ" صُورَة‎ ማለት ብዙ አውራ ትርጉም ያለው ሲሆን "ስዕል" "ቅርፅ" "መልክ" "ፎቶ" ማለት ነው፥ "ሱወር" صُوَر ደግሞ የሱራህ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ስዕላት" "ቅርፃት" ማለት ነው። "የፈጠራችሁትን" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቅቱም" خَلَقْتُمْ ሲሆን ስዕሉን ስለሳሉት እና ቅርፁን ስለቀረፁት እንጂ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተውት አይደለም፥ ይህ "ኢሕቲራዕ" اِخْتِرَاع ማለትም "ፈጠራ" ነው። በእጃቸው የፈጠሩትን ላይ እንደ አላህ ሩሕ ማድረግ አይችሉም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 77, ሐዲስ 179
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ "ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"በዚህ ዓለም ቅርፅ የቀረፀ በትንሳኤ ቀን በውስጡ ሩሕ እንዲነፋበት ይጠየቃል፥ ግን መንፋት አይችልም"*። فَقَالَ سَمِعْتُ مُحَمَّدًا صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ مَنْ صَوَّرَ صُورَةً فِي الدُّنْيَا كُلِّفَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنْ يَنْفُخَ فِيهَا الرُّوحَ، وَلَيْسَ بِنَافِخٍ

እዚህ ሐዲስ "ሶወረ" صَوَّرَ ማለት "ቀረፀ" "ሳለ" "ሠራ" ማለት ነው። "ኸልቅ" خَلْق የሚለው ቃል "ተስዊር" تَصْوِير ለሚለው ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ እንደገባ አንባቢ ልብ ይለዋል፥ ይህ የቋንቋ ሙግት ታሳቢ ያደረገ ነው። ነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦቻቸውን ወደ ሐበሻህ ሲልኳቸው ከሔዱት መካከል በአክሱም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስዕላትን አይተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 77
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ *"ኡሙ ሐቢባህ እና ኡሙ ሠለማህ በሐበሻህ ስላዩአት በውስጧ ስዕሎች ስለነበሩባት ቤተክርስቲያን ዘክረዋል፥ ስለዚህ ለነቢዩም"ﷺ"ዘክረዋል። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "በእነዚያ ሰዎች መካከል የትኛውም ሷሊሕ ሰው ቢሞት በመቃብሩ ላይ የአምልኮ ስፍራ ቢገነቡ እና እነዚህን ስዕላት ቢያደርጉ፥ በትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው"*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ أُمَّ حَبِيبَةَ، وَأُمَّ سَلَمَةَ ذَكَرَتَا كَنِيسَةً رَأَيْنَهَا بِالْحَبَشَةِ فِيهَا تَصَاوِيرُ، فَذَكَرَتَا لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ ‏ "‏ إِنَّ أُولَئِكَ إِذَا كَانَ فِيهِمُ الرَّجُلُ الصَّالِحُ فَمَاتَ بَنَوْا عَلَى قَبْرِهِ مَسْجِدًا، وَصَوَّرُوا فِيهِ تِلْكَ الصُّوَرَ، فَأُولَئِكَ شِرَارُ الْخَلْقِ عِنْدَ اللَّهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ

"ተስዊራህ" تَصْوِيرَة ማለት "ስዕል" ማለት ነው፥ የተስዊራህ ብዙ ቁጥር "ተሷዊር" تَصَاوِير ማለት ሲሆን "ስዕላት" ማለት ነው። ስዕል በአምልኮ ውስጥ ምንም ሚና መኖር የለበትም፥ የሥላሴ፣ የኢየሱስ፣ የማርያም፣ የመላእክት እና የቅዱሳን ሰዎች ስዕል ስሎ በፊታቸው መለማመን ባዕድ አምልኮ ነው። በተመሳሳይ ቁረይሾች የአላህ ቤት ውስጥ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በእጆቻቸው አዝላም የያዙ አስመስለው ስዕላት ስለው ነበር፥ "አዝላም" أَزْلاَم ማለት "የጥንቆላ ቀስት" ማለት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 32
ኢብኑ ዐባሥ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"ነቢዩ"ﷺ" በአላህ ቤት ስዕላት በተመለከቱ ጊዜ ባልደረቦቻቸው እንዲያጠፉ እንኪያዙ ድረስ ወደ እዚያ አልገቡም። ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል"ሠላም በእነርሱ ላይ ይሁን! በእጆቻቸው አዝላም የያዙ ስዕላት ነበሩ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ "አላህ ይርገማቸው(ቁረይሾችን)! ወሏሂ ኢብራሂምን እና ኢሥማዒል በአዝላም አይለማመዱም"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم لَمَّا رَأَى الصُّوَرَ فِي الْبَيْتِ لَمْ يَدْخُلْ، حَتَّى أَمَرَ بِهَا فَمُحِيَتْ، وَرَأَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ ـ عَلَيْهِمَا السَّلاَمُ ـ بِأَيْدِيهِمَا الأَزْلاَمُ فَقَالَ ‏ "‏ قَاتَلَهُمُ اللَّهُ، وَاللَّهِ إِنِ اسْتَقْسَمَا بِالأَزْلاَمِ قَطُّ
የኢብራሂም አባት እና የኢብራሂም ሕዝቦች ቅርጻ ቅርጽ የሆነ አስናምን ያመልኩ ነበር፥ “አስናም” أَصْنَام ማለት ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሠርተው አምልኮ የሚቀርብላቸው ናቸው፦
26፥70 *ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ምንን ታመልካላችሁ?*» ባለ ጊዜ፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا تَعْبُدُونَ
26፥71 *አስናምን እናመልካለን፥ እርሷንም በመገዛት ላይ እንቆያለን*» አሉ፡፡ قَالُوا۟ نَعْبُدُ أَصْنَامًۭا فَنَظَلُّ لَهَا عَٰكِفِينَ
21፥52 ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ «ይህቺ *"ቅርጻ ቅርጽ"* ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት?» ባለ ጊዜ መራነው፡፡ إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ مَا هَـٰذِهِ التَّمَاثِيلُ الَّتِي أَنتُمْ لَهَا عَاكِفُونَ

"ቲምሳል" تِمْثَال ማለት "ምስል" "ቅርጽ" ማለት ነው፥ የቲምሳል ብዙ ቁጥር ደግሞ "ተማሲል" تَمَاثِيل ሲሆን "ምስሎች" "ቅርጻ ቅርጽ" ማለት ነው። የአምልኮ ይዘት ያላቸው ማንኛውም ምስል ሆነ ስዕል ያለበት ቤት መላእክት አይገቡም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 156
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ምስሎች ወይም ስዕሎች ያለበት ቤት አይገቡም"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ تَدْخُلُ الْمَلاَئِكَةُ بَيْتًا فِيهِ تَمَاثِيلُ أَوْ تَصَاوِيرُ

ስለ ሱራህ በመስኩ ምሁራን ዘንድ ያለው እይታ በአራት ይከፈላሉ፥ እነርሱም፦
1ኛ. ለምንም ነገር ሱራህ መጠቀም ሐራም ነው፣
2ኛ. በእጅ የተሠራ እንጂ ልክ እንደ መስታዎት እራሳችንን የሚያሳዩ በካሜራ እና በፊልም የሚታዩ ነገሮች ችግር የላቸውም፣
3ኛ. ለፓስፓርት፣ ለመታወቂያ እና ለሰርተፍኬት ብቻ መጠቀም ይቻላል፣
4ኛ. ለአምልኮ አንጠቀም እንጂ ስዕል እና ቅርጻ ቅርጽ በራሱ ሥነ-ጥበብ"art" ነው" የሚሉ ናቸው።
አራተኛውን እይታ ለማስደገፍ፦ "ሡለይማን በቤተ-መንግሥቱ ምስሎች አድርጓል፥ እነዚህ ምስሎች ስዕሎች ነበሩ" ይላሉ፦
34፥13 *ከምኩራቦች፣ "ከምስሎችም"፣ እንደ ገንዳ ከኾኑ ገበታዎችም፣ ከተደላደሉ ታላላቅ ድስቶችም የሚሻውን ሁሉ ይሠሩለታል*፡፡ يَعْمَلُونَ لَهُ مَا يَشَاءُ مِن مَّحَارِيبَ وَتَمَاثِيلَ وَجِفَانٍ كَالْجَوَابِ وَقُدُورٍ رَّاسِيَاتٍ ۚ اعْمَلُوا آلَ دَاوُودَ شُكْرًا ۚ وَقَلِيلٌ مِّنْ عِبَادِيَ الشَّكُورُ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 34፥13
ወሱዲይ ከወድሐክን፣ ዐጢይል ዐውፊይ አለ ብሎ እንደተናገረው፦ *"ምስሎች ማለት ስዕሎች ናቸው"*። فقال عطية العوفي ، والضحاك والسدي : التماثيل : الصور

በሱራህ እሳቤ ዙሪያ "አንጡራ መረጃ አላገኘንም" ካላችሁ በአካባቢያችሁ ወደሚገኙት ምሁራን እና ሊሒቃን ጎራ ብላችሁ ጠይቁ! አሏሁ አዕለም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም