ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.8K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሁለት
“መሓላ”
የነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶች መጋፊር በልተው የአፋቸው ሽታ እንደተቀየረ ለማስመሰል ስለነገሯቸው ነብያችን”ﷺ”፦ “በፍፁም ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ ግን አልጠጣም” ብለው ምለው ተገዝተው ነበር፤ ለማሃላቸው ማካካሻ ካደረጉ አላህ እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው፤ “የመሓሎቻችሁን መፍቻ” ማድረጉ እርሱም ዐዋቂው ጥበበኛው ነው፦
66፥2 አላህ ለእናንተ የመሓሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፤ አላህም እረዳታችሁ ነው፤ እርሱም ዐዋቂው ጥበበኛው ነው قَدْ فَرَضَ ٱللَّهُ لَكُمْ تَحِلَّةَ أَيْمَٰنِكُمْ ۚ وَٱللَّهُ مَوْلَىٰكُمْ ۖ وَهُوَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ ፡፡

የማለ ሰው መሃላውን ቢፈታ ዐስርን ምስኪኖች ማብላት፣ ወይም እነርሱን ማልበስ ወይንም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፤ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መጾም ነው፤ ይህ የመሐላዎቻችሁ ማካካሻ ነው፦
5፥89 አላህ በመሐላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፤ ነገር ግን መሐላዎችን ባሰባችሁት ይይዛችኋል፡፡ ማስተሰሪያውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ ዐስርን ምስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ ወይንም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፤ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መጾም ነው፤ ይህ በማላችሁ ጊዜ የመሐላዎቻችሁ ማካካሻ ነው፡፡ መሐላዎቻችሁንም ጠብቁ፡፡ እንደዚሁ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ያብራራል፡፡ እናንተ ልታመሰግኑ ይከጀላልና لَا يُؤَاخِذُكُمُ ٱللَّهُ بِٱللَّغْوِ فِىٓ أَيْمَٰنِكُمْ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ ٱلْأَيْمَٰنَ ۖ فَكَفَّٰرَتُهُۥٓ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَٰكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍۢ ۖ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٍۢ ۚ ذَٰلِكَ كَفَّٰرَةُ أَيْمَٰنِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ ۚ وَٱحْفَظُوٓا۟ أَيْمَٰنَكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ ፡፡

ነጥብ ሶስት
“ሚስጥር”
ነብያችን”ﷺ” ከባለቤታቸው አንዷ ለሆነችው ለሃፍሳ”ረ.ዓ.” “በፍፁም ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ ግን አልጠጣም” ብለው ይህ ወሬ በሚስጥር በመሰጠሯት ጊዜ ሄዳ ለዓኢሻ”ረ.ዓ.” ተናገረች፤ ነብይ ማለት የሩቅ እውቀት የሚገለጥለት ነውና ለዓኢሻ”ረ.ዓ.” በተናገረች ጊዜ የተናገረችውን ከፊሉን አሳውቀዋት ከፊሉን ችላ ብለው ሲተዉት፤ በዚያ በነገሯት ነገር ሃፍሳ”ረ.ዓ.”፦ ይህን ማን ነገረህ? ብላ አለቻቸው፤ ነብያችንም”ﷺ”፦ «ዐዋቂው ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አሏት፤ ይህንን ጉዳይ አምላካችን አላህ እንዲህ ይነግረናል፦
66፥3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ፡፡ እርሱንም በነገረች እና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት وَإِذْ أَسَرَّ ٱلنَّبِىُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَٰجِهِۦ حَدِيثًۭا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِۦ وَأَظْهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُۥ وَأَعْرَضَ عَنۢ بَعْضٍۢ ۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتْ مَنْ أَنۢبَأَكَ هَٰذَا ۖ قَالَ نَبَّأَنِىَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْخَبِيرُ ፤
ነጥብ አራት
“ተውበት”
አላህ በተከበረው ንግግሩ፦ ለነብያችን”ﷺ” ሁለቱ ባለቤቶቻቸው ለዓኢሻ”ረ.ዓ.” እና ለሃፍሳ”ረ.ዓ.”፦ ወደ አላህ በተውበት ብትመለሱ ልቦቻው ተዘንብለዋልና፤ አይ ካላችሁ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፣ ጂብሪልም፣ ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው። ከዚያም ባሻገር ቢፈታችሁ አላህ ከእናንተ የበለጡ ሚስቶችን ሙስሊሞች፣ አማኞች፣ ታዛዦች፣ ተጸጻቾች፣ አምላኪዎች፣ ጾመኞች፣ ፈቶች፣ ደናግልም የኾኑትን ሊያመጣለት ይችላል በማለት መለሰ፦
66፥4-5 ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና ትስማማላችሁ፡፡ በእርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፣ ጂብሪልም፣ ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው إِن تَتُوبَآ إِلَى ٱللَّهِ فَقَدْ صَغَتْ قُلُوبُكُمَا ۖ وَإِن تَظَٰهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ هُوَ مَوْلَىٰهُ وَجِبْرِيلُ وَصَٰلِحُ ٱلْمُؤْمِنِينَ ۖ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ بَعْدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ ። ቢፈታችሁ ከእናንተ የበለጡ ሚስቶችን ሙስሊሞች፣ አማኞች፣ ታዛዦች፣ ተጸጻቾች፣ አምላኪዎች፣ ጾመኞች፣ ፈቶች፣ ደናግልም የኾኑትን ጌታው ሊለውጠው ይከጀላል عَسَىٰ رَبُّهُۥٓ إِن طَلَّقَكُنَّ أَن يُبْدِلَهُۥٓ أَزْوَٰجًا خَيْرًۭا مِّنكُنَّ مُسْلِمَٰتٍۢ مُّؤْمِنَٰتٍۢ قَٰنِتَٰتٍۢ تَٰٓئِبَٰتٍ عَٰبِدَٰتٍۢ سَٰٓئِحَٰتٍۢ ثَيِّبَٰتٍۢ وَأَبْكَارًۭا ፡፡

መደምሚያ
ተፍሲሩል ኢብኑ ከሲር ኢማም ቡኻሪይ መሰረት አድገው እና ተፍሲሩል ቁርጡቢ ኢማም ሙስሊም መሰረት አድርገው ይህን ሱራህ ፈስረውቷል፤ ይህንን ወህይ መውረድ ምክንያት አራት ሙሐዲሲን አስቀምጠውታል፤ እነርሱም ኢማን ቡኻሪይ፣ ኢማም ሙስሊም፣ ኢማም አቢ ዳውድ እና ኢማም ነሳኢ ናቸው፦
1ኛ. ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 68 , ሐዲስ 17:
ዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደተናገረችው፦ ነብዩ”ﷺ” ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ጋር ትንሽ ጊዜ በመቆየት እና ከእርሷ ቤት ማር ይጠጡ ነበር፤ ስለዚህ ሃፍሳ”ረ.ዓ.” እና እኔ ፦”ነብዩ”ﷺ”
ወደ እኛ ከመጡ እርሷ፦ የመጋፊር ሽታ ሸተኸኛል እንድትል ወሰንን፤ መጋፊር በልተሃልን? ከዚያም ነብዩ”ﷺ” ከእነርሱ አንዷን ሲዘይሩ እንዲሁ በተመሳሳይ አለቻቸው፤ ነብዩም”ﷺ” ፦ “በፍፁም ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ ግን አልጠጣም” አሉ፤ ስለዚህ ይህ አንቀፅ ወረደ፦
66:1 አንተ ነቢዩ ሆይ አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን በአንተ ላይ ለምን እርም ታደርጋለህ?
66፥4 “ወደ አላህ ሁለታችሁ ብትመለሱ” ይህ የሚያመለክተው ዓኢሻ”ረ.ዓ.” እና ሃፍሳን”ረ.ዓ.” ነው፤
66፥3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ”
ማለትም “እኔ ግን ጥቂት ማር ጠጥቻለው” አሉ።
يَقُولُ سَمِعْتُ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ ابْنَةِ جَحْشٍ، وَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً، فَتَوَاصَيْتُ أَنَا وَحَفْصَةُ أَنَّ أَيَّتَنَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ، أَكَلْتَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُمَا فَقَالَتْ لَهُ ذَلِكَ، فَقَالَ ‏”‏ لاَ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ ابْنَةِ جَحْشٍ وَلَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‌‏.‏ فَنَزَلَتْ ‏{‏يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ‏}‏ إِلَى ‏{‏إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ ‏{‏وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً ‏”‌‏
2ኛ. ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 18, ሐዲስ 27:
وَحَدَّثَنِي مُحَمَّدُ بْنُ حَاتِمٍ، حَدَّثَنَا حَجَّاجُ بْنُ مُحَمَّدٍ، أَخْبَرَنَا ابْنُ جُرَيْجٍ، أَخْبَرَنِي عَطَاءٌ، أَنَّهُ سَمِعَ عُبَيْدَ بْنَ عُمَيْرٍ، يُخْبِرُ أَنَّهُ سَمِعَ عَائِشَةَ، تُخْبِرُ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ فَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً قَالَتْ فَتَوَاطَأْتُ أَنَا وَحَفْصَةُ أَنَّ أَيَّتَنَا مَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ أَكَلْتَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُمَا فَقَالَتْ ذَلِكَ لَهُ ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ وَلَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‏ ‏.‏ فَنَزَلَ ‏{‏ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ‏}‏ إِلَى قَوْلِهِ ‏{‏ إِنْ تَتُوبَا‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ ‏{‏ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً ‏”‏ ‏.‏
3ኛ. ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 27 , ሐዲስ 33:
أَخْبَرَنَا قُتَيْبَةُ، عَنْ حَجَّاجٍ، عَنِ ابْنِ جُرَيْجٍ، عَنْ عَطَاءٍ، أَنَّهُ سَمِعَ عُبَيْدَ بْنَ عُمَيْرٍ، قَالَ سَمِعْتُ عَائِشَةَ، زَوْجَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ وَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً فَتَوَاصَيْتُ وَحَفْصَةَ أَيَّتُنَا مَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُمَا فَقَالَتْ ذَلِكَ لَهُ فَقَالَ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ – وَقَالَ – لَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‏ ‏.‏ فَنَزَلَ ‏{‏ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ ‏}‏ ‏{‏ إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ ‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ ‏{‏ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا ‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاَ ‏”‏ ‏.‏ كُلُّهُ فِي حَدِيثِ عَطَاءٍ ‏.‏
4ኛ. ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 27 , ሐዲስ 46:
حَدَّثَنَا أَحْمَدُ بْنُ مُحَمَّدِ بْنِ حَنْبَلٍ، حَدَّثَنَا حَجَّاجُ بْنُ مُحَمَّدٍ، قَالَ قَالَ ابْنُ جُرَيْجٍ عَنْ عَطَاءٍ، أَنَّهُ سَمِعَ عُبَيْدَ بْنَ عُمَيْرٍ، قَالَ سَمِعْتُ عَائِشَةَ، – رضى الله عنها – زَوْجَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم تُخْبِرُ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ فَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً فَتَوَاصَيْتُ أَنَا وَحَفْصَةُ أَيَّتُنَا مَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُنَّ فَقَالَتْ لَهُ ذَلِكَ فَقَالَ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ وَلَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‏ ‏.‏ فَنَزَلَتْ ‏{‏ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ تَبْتَغِي ‏}‏ إِلَى ‏{‏ إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ ‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ رضى الله عنهما ‏{‏ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا ‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً ‏”‏ ‏.‏

እንዲህ በሰሒሕ እና በሐሠን ሪዋያህ መረዳት ነው እንጂ ሪዋያህ በሌላቸው ከሼኽ ጎግል በሚለቃቀመው ደኢፍ እና መውዱዕ ጥንቅሮች መፎተት እራስን ማታለል ነው፤ አላህ በእርሱ መንገድ ላይ እርሱን ለማግኘት እሾት ያላቸውን ሰዎች ሂዳያ ይስጣቸው ለእኛም ፅናቱን ይስጠን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዒድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፤ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል፤ ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” በሁለቱ በአል በኢደል አደሐ እና ኢደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

ታዲያ በየዓመቱ የሚከበረው ሥስተኛው በዓል መውሊድ ምንድን ነው? አዎ ይህ ድብን ያለ ቢድዓ ነው፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።
ሲጀመር ነብያችን”ﷺ” የተወለዱበት ሳምንት እንጂ የተወለዱበት ቀን በሐዲስ አልሰፈረም።
ሲቀጥል አላህም እና መልእክተኛው መውሊድ አክብሩ አላሉም።
ሢሰልስ ነቢያችን”ﷺ” የተወለዱበትን ቀን ከቀደምት ሰለፎች ማለትም ሶሐባህ ወይም ታቢኢይ አሊያም አትባኡ ታቢኢይ ያከበረ የለም።
ስለዚህ መውሊድ በቁርኣንና በሐዲስ አሕካሙ ካልተቀመጠ እና አይ የፈለግነውን በዲኑ ላይ እንጨምራለን ከሆነ ቢድዓ ነው፤ ሑክም የአላህ እና የመልክተኛ ብቻና ብቻ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏

“ከትእዛዛችን” የሚለው ይሰመርበት። አንድ ነገር ፈርድ ነው፣ ሙስተሐብ ነው፣ ሙባሕ ነው፣ መክሩህ ነው፣ ሐራም ነው ማለት የሚቻለው ከአላህ እና ከመልእክተኛ ትእዛዝ ሲመጣ ብቻና ብቻ ነው፦
3፥32 *አላህን እና መልክተኛውን ታዘዙ*፡፡ ብትሸሹም አላህ ከሓዲዎችን አይወድም» በላቸው፡፡ قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَالرَّسُولَ ۖ فَإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْكَافِرِينَ
4፥80 *መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ፡፡ ከትእዛዝም የሸሸ ሰው አያሳስብህ*፡፡ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና፡፡ مَّن يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ ۖ وَمَن تَوَلَّىٰ فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا
“ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም” የሚለው የነብያችን”ﷺ” ንግግር ይሰመርበት፤ ማንኛውም መመሪያ ቁርአን እና የነብያችን”ﷺ” ሐዲስ ላይ ይገኛል፤ አላህን የሚወድ መልእክተኛውን ይከተላል፤ አላህም፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፤ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” ብሎናል፦
3፥31 *በላቸው፡- አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ “ተከተሉኝ*፤ አላህ ይወዳችኋልና፤ ኀጢኣቶቻችሁንም ለእናንተ ይምራልና፤ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው” قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ ፡፡
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ ፡፡

ጥሩ ቢድዓ ካለ የሌሎችን ነብያት ልደት ለምን አይከበርም? ለምሳሌ “ገና” የዒሳ ልደት አይከበርም? ነብያችን”ﷺ” ወሕይ የመጣላቸው ቀን፣ ያረፉበት ቀን ወዘተ እየተባለ ልክ እንደ ኦርቶዶክስ ሰላሳውም ቀን ለምን አይከበርም? ይህ ደግሞ ዲኑን ያባሻል። አይ ዝንባሌአችን ደስ ያለውን መልካም ነገር በዒባዳህ ላይ እናካትት ማለት ዲኑ ሙሉ ነው የሚለንን አምላካችን አላህን እየተቃረንን ነው፦
5፥3 *ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ*፡፡ ጸጋዬንም በእናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا

“ነፍስያ” نفسيه ማለትም “የራስ ዝንባሌ” ጌታችን የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ነው፤ ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም፦
12፥53 ነፍሴንም ከስሕተት አላጠራም፡፡ *ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና*፡፡ ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» አለ፡፡ وَمَا أُبَرِّئُ نَفْسِي ۚ إِنَّ النَّفْ

سَ لَأَمَّارَةٌ بِالسُّوءِ إِلَّا مَا رَحِمَ رَبِّي ۚ إِنَّ رَبِّي غَفُورٌ رَّحِيمٌ
6፥164 በላቸው እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا

ቢድዓ፣ ኩርፍ፣ ሽርክ እና ኒፋቅ ምንጫቸው ዝንባሌ ነው፤ ብዙ ጊዜ ሰርጎ-ገብ የሆኑት ቡድንተኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት መነሻቸው ዝንባሌ ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

አላህ ከነፍሲያ ከሚመጣ ዝንባሌ ጠብቆን፤ እርሱንና መልእክተኛው ባስቀመጡልን ሑክም የምንመራ ያድርገን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ከአህለል ኪታብ ሴት ጋር መጋባት ይቻላልን? ያረዱትንስ መብላት ይቻላልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥5 ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ *የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለእነሱ የተፈቀደ ነው*፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም *ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው*፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ ۖ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّۭ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّۭ لَّهُمْ ۖ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍۢ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

አምላካችን አላህ በእርሱ ላይ ሌሎች ማንነትንና ምንነትን የሚያጋሩ ሙሽሪኮችን እንዳናገባ እና ከእርሱ ስም ውጪ በሌላ ፍጡር ስም ተባርኮ የታረደን እርድ እንዳንበላ ከልክሏል፦
2፥221 *አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቡዋቸው*፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ ያመነችው ባሪያ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ *ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው*፡፡ ከአጋሪው ጌታ ምንም ቢደንቃችሁ ምእምኑ ባሪያ በላጭ ነው፡፡ *እነዚያ አጋሪዎች ወደ እሳት ይጣራሉ፡፡ አላህም በፈቃዱ ወደ ገነትና ወደ ምሕረት ይጠራል*፡፡ ሕግጋቱንም ለሰዎች ይገልጻል እነርሱ ሊገሰጹ ይከጀላልና፡፡ وَلَا تَنكِحُوا الْمُشْرِكَاتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ ۚ وَلَأَمَةٌ مُّؤْمِنَةٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكَةٍ وَلَوْ أَعْجَبَتْكُمْ ۗ وَلَا تُنكِحُوا الْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا ۚ وَلَعَبْدٌ مُّؤْمِنٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكٍ وَلَوْ أَعْجَبَكُمْ ۗ أُولَـٰئِكَ يَدْعُونَ إِلَى النَّارِ ۖ وَاللَّهُ يَدْعُو إِلَى الْجَنَّةِ وَالْمَغْفِرَةِ بِإِذْنِهِ ۖ وَيُبَيِّنُ آيَاتِهِ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
6፥121 *በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ*፡፡ እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው፡፡ ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ፡፡ *ብትታዘዙዋቸውም እናንተ በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ*፡፡ وَلَا تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ وَإِنَّهُ لَفِسْقٌ ۗ وَإِنَّ الشَّيَاطِينَ لَيُوحُونَ إِلَىٰ أَوْلِيَائِهِمْ لِيُجَادِلُوكُمْ ۖ وَإِنْ أَطَعْتُمُوهُمْ إِنَّكُمْ لَمُشْرِكُونَ

"ለናሙና ያክል" “ሺርክ” شِرْك የሚለው ቃል “አሽረከ” أَشْرَكَ ማለትም “አጋራ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ማጋራት” ማለት ነው፤ የሚያጋራው ሰው ደግሞ “ሙሽሪክ” مُشْرِك ማለትም “አጋሪ” ይባላል፤ እንዲሁ በአላህ ላይ የሚያጋሩት ማንነትና ምንነት “ሸሪክ” شَرِيك ማለትም “ተጋሪ” ይባላሉ፤ ከአህለል ኪታብ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ከነሳራዎች አበይት የሚባሉት ሙሽሪኪን ናቸው፦
5፤72 *እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» *እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ*፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፤ እነሆ ይህ ንግግራቸው ማጋራት ነውና አላህ በእርሱ ላይ የሚያጋራ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ይህ ጥቅላዊ መልእክት “ሙጅመል” مجمل ወይም “ዓም” عام ይባላል፤ ነገር ግን አላህ ከሙሽሪኪን አህለል ኪታቦችን በተናጥል “ሙፈሰል” مُفَصَّل ወይም “ኻስ” خاص በማድረግ ለያቸው፤ ይህም ሙሽሪኪን እና አህለል ኪታብ በሚሉ ቃላት መካከል “ወ” وَ ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር አስቀምጧል፦
98፥1 *እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች እና ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ ተወጋጆች አልነበሩም፡፡ لَمْ يَكُنِ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ مُنفَكِّينَ حَتَّىٰ تَأْتِيَهُمُ الْبَيِّنَةُ

“በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ” የሚለው “ዓም” عام ሆኖ ከመጣ በኃላ “የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው” “ኻስ” خاص ሆኖ እንደመጣ ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” ተናግሯል፦
ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 16, ሐዲስ 30
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” እንደተናገረው፦ 6፥118 “የአላህ ስም በእርሱ ላይ ከተወሳበት እንስሳ ብሉ” የሚለው አንቀጽ እና 6፥116 “በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ” የሚለው አንቀጽ ኢስቲስናዕ በመሆን “የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው” በሚለው ተነሥኻል” عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ ‏{‏ فَكُلُوا مِمَّا ذُكِرَ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ ‏}‏ ‏{‏ وَلاَ تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ ‏}‏ فَنُسِخَ وَاسْتَثْنَى مِنْ ذَلِكَ فَقَالَ ‏{‏ وَطَعَامُ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حِلٌّ لَكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَهُمْ ‏}‏ ‏.‏
ይህንን ሪዋያህ ሼኹል አልባኒ ሐሠን ነው ብለውቷል፤ “ወኢሥተስና” وَاسْتَثْنَى የሚለው ይሰመርበት፤ “ኢሥቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለት “ግድባዊ ቃል”Exceptional word” ነው፤ ከዚህ ሐዲስ የምረዳው አምላካችን አላህ ከጥቅላዊ መልእክት ተናጥሏዊ መልእክት ይህንን አንቀጽ ማውረዱ ነው፦
5፥5 ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ *የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለእነሱ የተፈቀደ ነው*፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም *ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው*፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ ۖ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّۭ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّۭ لَّهُمْ ۖ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍۢ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

አላህ ለሙስሊም ወንድ ከአህለል ኪታብ ሴትን የፈቀደበት ሂክማ ሴት በቀጥታ ሙስሊም ቤት ስለምትገባ ነው፤ በተቃራኒው ሴት ሙስሊም ወንድ ካፊርን ማግባት ያልፈቀደበት ሴቷ ሙስሊም ሙሽሪክ ቤት ስለምትገባ ነው።
ከላይ የተዘረዘረው ግንዛቤ የዐሊሞቻችን አንዱ እይታ”dimension” ነው፤
ስለ አህለል ኪታብ ሁለተኛው የዐሊሞቻችን እይታ” ደግሞ “ሢያቅ” سیاق ማለትም “አውዳዊ መልእክት”context” ነው። ይህንን እስቲ ነጥብ በነጥብ እንመልከት። ከሙሳ እና ዒሳ ተከታዮች ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፤ ነገር ግን አላህ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጣቸው፤ በእነርሱ ላይ ቁርአን በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፤ እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን» ይላሉ፦
28፥52 እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ *በእርሱ ያምናሉ*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُونَ
28፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ *እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን*» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ

ልብ አድርግ “እኛ ከእርሱ ማለትም ከቁርአን መውረድ በፊት ሙስሊም ነበርን” ማለታቸው ምክንያታዊ ነው፤ ሙስሊም” مُسْلِم ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው። እንደሚታወቀው ከመጽሐፉ ሰዎች ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፤ አይሁዳውያን አላህ የተቆጣባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳቱተት ናቸው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3212
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፤ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ وَالنَّصَارَى ضُلاَّلٌ ‏”‏ ‏.‏

ነገር ግን ከአይሁዳውያን ጥቂት ያልተቆጣቸው፤ እንዲሁ ከክርስቲያኖች ጥቂት ያልተሳሳቱ ነበሩ፤ እኛም ከመንገዱ እንዳንስት የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋለላቸውን መንገድ ምራን ብለን እንቀራለን፦
1፥7 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፣ በእነርሱ ላይ *”ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን”*፤ በሉ። صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ ٱلْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4475
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ኢማሙ፦ “ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” ባለ ጊዜ አሚን በሉ፤ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ إِذَا قَالَ الإِمَامُ ‏{‏غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ فَقُولُوا آمِينَ‏.

ስለዚህ ከመጽሐፉ ሰዎች በተውሒድ ያሉትን የኢስራኢል ልጆች እና ነሳራዎች ያረዱትን መብላትን እና በሃላል ሴቶቻቸውን ማግባት ተፈቅዷል፦
5፥5 ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ *የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለእነሱ የተፈቀደ ነው*፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም *ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው*፡፡ ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ ۖ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّۭ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّۭ لَّهُمْ ۖ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍۢ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

“መጽሐፍን የተሰጡት” በሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ “ሚን” مِنَ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ያ የሚያሳየው ከአህለል ኪታብ መካከል ያሉትን ያላሻረኩ፣ የፍጡር ስም ሳይሆን የአላህን ስም ብቻ የሚጠሩ እና ከዝሙት ብልቶቻቸውን ጥብቆች የሆኑ ሴቶች ማግባት ሙባህ ነው። ይህ ሁለተኛው እይታ ነው። ሁለቱም እይታዎች ቁርኣናዊ ናቸው፤ መርጦ መቀበል የግል ምርጫ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቤተክርስቲያን ወይስ ኡማ?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥110 ለሰዎች ከተገለጸች “ኡማ” أُمَّةٍ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ፤ በአላህም ታምናላችሁ፡፡

መግቢያ
ነብያት ሆኑ ሃዋርያት ቤተ-ክርስቲያን ወይም ቸርች”church” የሚለውን ቃል በፍፁም አያውቁትም። ይህንን ስናገር በጨበጣ ሳይሆን በእማኝና በአስረጂነት መረጃ ይዤ ነው፤ “ቤተ-ክርስቲያን” ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ቤት” እና “ክርስቲያን” ትርጉሙም “የክርስቲያን ቤት” ማለት ነው፤ ልብ በል “ክርስቲያን” የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ አገልግሎት ላይ የዋለው ኢየሱስ ካረገ በኃላ በጠላት ስያሜ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 11:26 ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም #መጀመሪያ በአንጾኪያ #ክርስቲያን ተባሉ።”

“ክርስቲያን” ማለት “ክርስቶሳውያን” ወይም “ክርስቶሶች” አሊያም “ቅቡዓን” ማለት ነው፤ ይህንን ስም ነቢያት አያውቁትም፤ “ቸርች””church” የሚለው የኢንግሊሹ ቃልም ቢሆን ከጀርማኒክ ቃል የተገኘ ሲሆን “የጌታ” ማለት እንጂ ስሜት የሚሰጥ ትርጉም የለውም፤ ታዲያ ቤተክርስቲያን ወይም ቸርች የሚለውን ስም ነብያት ሆነ ሃዋርያት ካላወቁት ምን ነበር የሚያውቁት? ብለን ስንጠይቅ መልሱን ነጥብ በነጥብ እናያለን፦

ነጥብ አንድ
“ኤክሌሺያ”
“ኤክሌሺያ” ἐκκλησία ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ “ተጠርተው የወጡ””called out” ማለት ሲሆን ሙያዊ ፍቺው ደግሞ “ጉባኤ””assembly” ወይም “ማህበር”congregation” ማለት ነው፤ ይህንን ቃል አዲስ ኪዳን ኢየሱስ “ጉባኤ” በሚል ተናግሮታል፦
ማቴዎስ 16:18 እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ “ጉባኤዬን” ἐκκλησία እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።”
ማቴዎስ 18:17 እነርሱንም ባይሰማ፥ “ለጉባኤው” ἐκκλησία ንገራት፤ ደግሞም “ጉባኤውን” ἐκκλησία ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።”

በተረፈ በአዲስ ኪዳን ንባባት ሁሉ ላይ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ቤተክርስቲያን ወይም “ቸርች” ሳይሆን “ኤክሌሺያ” ነው፤ በእርግጥ ኢየሱስ ግሪክ ተናጋሪ አልነበረም፤ የአረማይክ ዘዬ ተናጋሪ ነበረ፤ ኢየሱስ የተናገረበት የአረማይኩ ንግግር ምንም ቅሪት ቢጠፋም ኤክሌሺያ ተብሎ በግሪክ እደ-ክታባት ላይ የተቀመጠው ቃል በአማረይክ “ኡማ” የሚል ፍቺ አለው፤ በእብራይስጡ እደ-ክታብ ላይ “ቀሃል” קהל ተብሎ የተቀመጠው ቃል በግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ “ኤክሌሺያ” ἐκκλησία ተብሎ ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 28:3 ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ “ጉባኤ” לִקְהַ֥ל እንድትሆን ይባርክህ፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ፤”
ዘፍጥረት 35፥11 እግዚአብሔርም አለው፦ ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፤ ብዛ፥ ተባዛም፤ ሕዝብና የአሕዛብ “ማኅበር” וּקְהַ֥ל ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ።
ዘፍጥረት 48:4 እንዲህም አለኝ። እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ፥ አበዛሃለሁም፥ ለብዙም ሕዝብ “ጉባኤ” לִקְהַ֣ל አደርግሃለሁ፤ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለዘላለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ።”
ዘኍልቍ 14:5 ሙሴና አሮንም በእስራኤል ልጆች “ጉባኤ” קְהַ֥ל ፊት በግምባራቸው ወደቁ።”
ዘኍልቍ 15:15 ለእናንተ “በጉባኤው” קְהַ֥ל ላላችሁ በእናንተም መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ አንድ ሥርዓት ይሆናል፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል።”

ብዙ ጥቅስ በቁና እየሰፈሩ ጥቅሶችን ማቅረብ ይቻላል፤ ግን ለመረጃ ያክል ከላይ ያየናቸው ናሙናዎች በቂ ናቸው፤ በእብራይስጡ እደ-ክታባት “ቀሃል” קהל ወይም በግሪክ ሰፕቱጀንት “ኤክሌሺያ” ἐκκλησία የሚለው ይህ ቃል 111 ጊዜ ብሉይ ኪዳን ላይ የሰፈውን ቃል ቤተክርስቲያን ወይም ቸርች ብላችሁ ለምን አልተረጎማችሁትም? ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን ላይ ያለው ጉባኤ በአዲስ ኪዳን ኤክሌሺያ” ἐκκλησία ስለተባለ፦
የሐዋርያት ሥራ 7:38 ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ “በማኅበሩ” ἐκκλησίᾳ ውስጥ የነበረው ነው፤ ይሰጠንም ዘንድ ሕይወት ያላቸውን ቃላት ተቀበለ፤”
ነጥብ ሁለት
“ኡማ”
“ኡማ” أُمَّة የሚለው ቃል “ህዝብ” “ማህበረሰብ” ማህበር” “ሃማኖታዊ ጉባኤ” የሚል ፍቺ አለው፤ ይህንን አሰራር የኢብራሒም አምላክ አላህ በተከበረው ከሊማ እነ ኢብራሒም ስለ ኡማ የፀለዩትን ፀሎት እንዲህ ይነግረናል፦
2፥128 ጌታችን ሆይ! ለአንተ “ታዛዦችም” مُسْلِمَةً አድርገን፡፡ ከዘሮቻችንም ለአንተ “ታዛዦች” مُسْلِمَيْنِ “ኡማዎችን” أُمَّةً አድርግ፡፡

“ታዛዦችም” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙስሊመይኒ” مُسْلِمَيْنِ ሲሆን ሙተና”dual” ነው፤ ይህም የሚያሳየው የኢብራሂምና የኢስማኢል ቤተሰብ የሚመጣ ኡማ ነው፤ ከኢብራሂም ቤተሰብ የይስሐቅና የያዕቁብ ኡማ መስመር ውስጥ የሙሳ ኡማ እና የኢሳ ኡማ ስናገኝ ይህቺ ኡማ ያለፈች ኡማ ናት፦
2፥134 ይህች የተወሳችው በእርግጥ ያለፈች “ኡማ” أُمَّةٌ ናት፤ ለእርሷ የሠራችው ምንዳ አላት፤ ለእናንተም የሠራችሁት ምንዳ አላችሁ፤ ይሠሩትም ከነበሩት አትጠየቁም፡፡
2፥141 ይህቺ በእርግጥ ያለፈች “ኡማ” أُمَّةٌ ናት፤ ለእርሷ የሠራችው አላት፤ ለናንተም የሠራችሁት አላችሁ፤ ይሠሩትም ከነበሩት አትጠየቁም፡፡

የኢስማኢል ቤተሰብ ደግሞ የነብያት መደምደሚያ የሆኑት ነብያችን ሲሆኑ ይህም የተተነበየው የነብያችን ኡማ ነው፤ “ለእናንተም የሠራችሁት ምንዳ አላችሁ” የተባለው የእርሳቸው ኡማ ነው፤ ይህም ኡማ አንድ ኡማ ነው፦
21:92 ይህች አንዲት ኡማ ስትኾን በእርግጥ ኡማችሁ ናት إِنَّ هَٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً ፤ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ።
Dr. Laleh Bakhtiar translation፦ Truly, this, your community, is one community and I am your Lord so worship Me
23:52 ይህችም አንድ ኡማ ስትኾን ኡማችሁ ናት وَإِنَّ هَٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً ፤ እኔም ጌታችሁ ነኝና ፍሩኝ፡፡
Dr. Laleh Bakhtiar translation፦ And, truly, this, your community is one community and I am your Lord so be Godfearing.

ይህ የነብያችን ኡማ ምርጥ እና ሚዛናዊ ኡማ ነው፦
2፥143 እንደዚሁም በሰዎች ላይ መስካሪዎች ልትሆኑና መልክተኛውም በእናንተ ላይ መስካሪ ይሆን ዘንድ “ምርጥ” “ኡማ” أُمَّةً አደረግናችሁ፡፡
3፥110 ለሰዎች ከተገለጸች “ኡማ” أُمَّةٍ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ፤ በአላህም ታምናላችሁ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የጨረቃ መከፈል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

54፥1 *ሰዓቲቱ ተቃረበች፤ ጨረቃም ተከፈለች*፡፡ اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانشَقَّ الْقَمَرُ

"ሰዓቲቱ" ማለት "የትንሳኤ ቀን" መሆኗ እሙንና ቅቡል ነው፤ የሰዓቲቱ መምጣት ዕውቀቷ በአላህ ዘንድ ብቻ ነው፤ በጊዜዋ አላህ እንጂ ሌላ አይገልጣትም፤ ስትመጣም በድንገት ቢኾን እንጂ አትመጣም፦
7፥187 *ከሰዓቲቱ መቼ እንደምትመጣ ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ በጌታዬ ዘንድ ነው፡፡ በጊዜዋ እርሱ እንጂ ሌላ አይገልጣትም፡፡ በሰማያትና በምድርም ከበደች፡፡ በድንገት ቢኾን እንጂ አትመጣችሁም» በላቸው፡፡ ከእርሷ አጥብቀህ እንደ ተረዳህ አድርገው ይጠይቁሃል፡፡ «ዕውቀቷ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው"*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ السَّاعَةِ أَيَّانَ مُرْسَاهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ رَبِّي ۖ لَا يُجَلِّيهَا لِوَقْتِهَا إِلَّا هُوَ ۚ ثَقُلَتْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ لَا تَأْتِيكُمْ إِلَّا بَغْتَةً ۗ يَسْأَلُونَكَ كَأَنَّكَ حَفِيٌّ عَنْهَا ۖ قُلْ إِنَّمَا عِلْمُهَا عِندَ اللَّهِ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُون

የሰዓቲቱንም መምጣት ምልክቶችዋ በሁለት ይከፈላሉ፤ ዐበይት ምልክቶች እና ንዑሳን ምልክቶች ናቸው፤ ከንዑሳን ምልክቶች ውስጥ የተወሰኑት በነብያችን"ﷺ" ዘመን ተፈጽመዋል፦
47፥18 ሰዓቲቱንም ድንገት የምትመጣባቸው መኾንዋን እንጅ ይጠባበቃሉን? *"ምልክቶችዋም በእርግጥ መጥተዋል"፡፡ በመጣቻቸውም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል?* فَهَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا السَّاعَةَ أَن تَأْتِيَهُم بَغْتَةً ۖ فَقَدْ جَاءَ أَشْرَاطُهَا ۚ فَأَنَّىٰ لَهُمْ إِذَا جَاءَتْهُمْ ذِكْرَاهُم

"ምልክቶችዋም በእርግጥ መጥተዋል" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ከንዑሳን ምልክቶች ቀዳማይ ምልክት የነቢያችን"ﷺ" መላክ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4936
ሠህል ኢብኑ ሠዕድ"ረ.ዕ." እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ጠቋሚ ጣታቸውን እና የመሃል ጣታቸውን ሲያመላክቱ አየኃቸው፤ እንዲህ አሉ፦ የእኔ መምጣት እና ሰዓቲቱ ልክ እንደነዚህ ጣቶች ቅርብ ናቸው*። حَدَّثَنَا سَهْلُ بْنُ سَعْدٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ رَأَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ بِإِصْبَعَيْهِ هَكَذَا بِالْوُسْطَى وَالَّتِي تَلِي الإِبْهَامَ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 68, ሐዲስ 50
የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሶሓባ ሠህል ኢብኑ ሠዕድ አሥ-ሣዒዲ እንደተረከው፦ *"የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ጠቋሚ ጣታቸውን እና የመሃል ጣታቸውን እያመላከቱ እንዲህ አሉ፦ የእኔ መምጣት እና ሰዓቲቱ ልክ እንደነዚህ ጣቶች ቅርብ ናቸው*። حَدَّثَنَا عَلِيُّ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، حَدَّثَنَا سُفْيَانُ، قَالَ أَبُو حَازِمٍ سَمِعْتُهُ مِنْ، سَهْلِ بْنِ سَعْدٍ السَّاعِدِيِّ صَاحِبِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ بُعِثْتُ أَنَا وَالسَّاعَةَ كَهَذِهِ مِنْ هَذِهِ أَوْ كَهَاتَيْنِ ‏"‌‏.‏ وَقَرَنَ بَيْنَ السَّبَّابَةِ وَالْوُسْطَى‏.‏
ጠቋሚ ጣት እና ከመሃል ጣት ምን ያህል የተቀራረበ እንደሆነ ሁሉ የነብያችን"ﷺ" መላክ እና ሰዓቲቱ በጣም ቅርብ ናቸው፤ ከሰዓቲቱ መቃረቢያ ንዑሳን ምልክቶች አንዱ የጨረቃ መከፈል ነው፦
54፥1 *ሰዓቲቱ ተቃረበች፤ ጨረቃም ተከፈለች*፡፡ اقْتَرَبَتِ السَّاعَةُ وَانشَقَّ الْقَمَرُ

"ኢንሸቀ" ٱنشَقَّ ማለት "ተከፈለች" "ተሰነጠቀች" "ተገመሰች" ማለት ነው፤ ከሰዓቲቱ መቃረቢያ ንዑሳን ምልክቶች አንዱ የጨረቃ መከፈል ነው፤ ይህ የጨረቃ መከፈል በነብያችን"ﷺ" ዘመን ተፈጽሟል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 61, ሐዲስ 141
አነሥ ኢብኑ ማሊክ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *"የመካ ሰዎች የአላህ መልእክተኛን"ﷺ" ታምር እንዲያሳያቸው ጠየቁት፤ ከዚያም እርሳቸው ጨረቃን በመክፈል አሳያቸው"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُ حَدَّثَهُمْ أَنَّ أَهْلَ مَكَّةَ سَأَلُوا رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنْ يُرِيَهُمْ آيَةً، فَأَرَاهُمُ انْشِقَاقَ الْقَمَرِ‏.‏

አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከን የመካ ሰዎች የአላህ መልእክተኛን"ﷺ" ታምር እንዲያሳያቸው ጠየቁት፤ ከዚያም እርሳቸው ጨረቃን በመክፈል አሳይተዋል፤ ነገር ግን በጊዜው ይህ ታምር ያዩት የመካ ሰዎች፦ "ሙሐመድ"ﷺ" አስደግሞብን ነው" ብለው ታምሩን አስተባብለዋል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3600
ከአባቱ ሙሐመድ ኢብኑ ጁበይር ኢብኑ ሙጥዒም እንደተረከው፦ *"በነቢዩ"ﷺ" ጊዜ ጨረቃ አንዷ በዚህ ተራራ አንዷ በዚያ ተራራ ለሁለት እስክትሆን ድረስ ተከፍላለች፤ ከዚያም ሕዝቦቹ፦ "ሙሐመድ"ﷺ" አስደግሞብን ነው" ሲሉ፤ ከእነርሱ ጥቂቶቹ፦ "በእኛ አስደግሞብን ከሆነ በሁሉም ሕዝቦች ሊያስደግም አይችልም" አሉ*። عَنْ مُحَمَّدِ بْنِ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ انْشَقَّ الْقَمَرُ عَلَى عَهْدِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم حَتَّى صَارَ فِرْقَتَيْنِ عَلَى هَذَا الْجَبَلِ وَعَلَى هَذَا الْجَبَلِ فَقَالُوا سَحَرَنَا مُحَمَّدٌ فَقَالَ بَعْضُهُمْ لَئِنْ كَانَ سَحَرَنَا مَا يَسْتَطِيعُ أَنْ يَسْحَرَ النَّاسَ كُلَّهُمْ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى وَقَدْ رَوَى بَعْضُهُمْ هَذَا الْحَدِيثَ عَنْ حُصَيْنٍ عَنْ جُبَيْرِ بْنِ مُحَمَّدِ بْنِ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ عَنْ أَبِيهِ عَنْ جَدِّهِ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ نَحْوَهُ ‏.‏

ጠያቂዎቹ መካውያን ስለተየቁ ተደገመብን ካሉ፤ ያልጠየቁት መካውያን ግን ሳይጠይቁ ይህንን ታምር አይተዋል፤ ስለዚህ ተደግሞብናል የሚል ማስተባበያ አይሠራም። ለዛ ነው አምላካችን አላህ እዛው ስለ ጨረቃ መከፈል በተናገረበት አንቀጽ ፦ ተዓምርንም ቢያዩ ከእምነት ይዞራሉ፤ ይህ «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ ያለው፤ መካውያን ያንን ታምር አስተባበሉ፤ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፦
54፥2 *ተዓምርንም ቢያዩ ከእምነት ይዞራሉ፡፡ ይህ «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ*፡፡ وَإِن يَرَوْا آيَةً يُعْرِضُوا وَيَقُولُوا سِحْرٌ مُّسْتَمِرٌّ
54፥3 *አስተባበሉም፤ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ*፡፡ ነገርም ሁሉ ረጊ ነው፡፡ وَكَذَّبُوا وَاتَّبَعُوا أَهْوَاءَهُمْ ۚ وَكُلُّ أَمْرٍ مُّسْتَقِرٌّ
ሚሽነሪዎች፦ "ጨረቃ ለሁለት መከፈሉን ማን አየ? ብለው በሞቀበት ጣዱን ይላሉ፤ ጨረቃ ለሁለት ስለ መከፈሉ የነብያችን"ﷺ" ባልደረቦች ምስክርነት በቂ ነው፤ ምክንያቱም እነርሱ ይህንን ታምር በዓይናቸው አይተዋልና፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 52, ሐዲስ 28
ዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ *"በሚና ከአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ጋር ነበርን፤ ጨረቃ ተከፈለች፤ አንዷ ክፍሏ ከተራራ ባሻገር ነበረ፤ ሌላው ክፍሏ ከተራራው ጎን ነበረ። የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ለእኛ፦ "መስክሩ" አሉ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، قَالَ بَيْنَمَا نَحْنُ مَعَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم بِمِنًى إِذَا انْفَلَقَ الْقَمَرُ فِلْقَتَيْنِ فَكَانَتْ فِلْقَةٌ وَرَاءَ الْجَبَلِ وَفِلْقَةٌ دُونَهُ فَقَالَ لَنَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْهَدُوا

እንግዲህ ከላይ የዐብደላህ ኢብኑ መሥዑድ እና የአነሥ ኢብኑ ማሊክ ምስክርነት አይተናል፤ በተጨማሪ የኢብኑ ዑመር እና የኢብኑ ዐባሥ ምስክርነትን ማየት ይቻላል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3599
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ *"በአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ጊዜ ጨረቃ ተከፈለች። የአላህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ "መስክሩ" አሉ"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ انْفَلَقَ الْقَمَرُ عَلَى عَهْدِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْهَدُوا
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 52, ሐዲስ 34
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ *"በአላህ መልእክተኛም"ﷺ" ጊዜ ጨረቃ ተከፈለች*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ إِنَّ الْقَمَرَ انْشَقَّ عَلَى زَمَانِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏

ሚሽነሪዎች ይህ ስሁት ሙግት አላዋጣ ሲላቸው፦ "ነቢያችሁ ታምር እንደማያደርግ በቁርኣን ተነግሯል" ብለው እነዚህ አናቅጽ በመጥቀስ ቅቤ ጥበሱልን ይላሉ፦
13፥7 እነዚያም የካዱት፦ *በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደለትም* ይላሉ፡፡ አንተ አስጠንቃቂ ብቻ ነህ፡፡ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው፡፡ وَيَقُولُ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا أُنزِلَ عَلَيْهِ آيَةٌ مِّن رَّبِّهِ ۗ إِنَّمَا أَنتَ مُنذِرٌ ۖ وَلِكُلِّ قَوْمٍ هَادٍ
29፥50 *«በእርሱ ላይም ከጌታህ ዘንድ ተዓምራቶች ለምን አልተወረዱም» አሉ፡፡ «ተዓምራቶች አላህ ዘንድ ብቻ ናቸው፡፡ እኔም ግልጽ አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ»* በላቸው፡፡ وَقَالُوا لَوْلَا أُنزِلَ عَلَيْهِ آيَاتٌ مِّن رَّبِّهِ ۖ قُلْ إِنَّمَا الْآيَاتُ عِندَ اللَّهِ وَإِنَّمَا أَنَا نَذِيرٌ مُّبِينٌ

"ኢነማ" إِنَّمَا የሚለው ቃል "ብቻ" ማለት ሲሆን ይህ ቃል በፍጹማዊ ገላጭነት አሊያም በአንጻረዊ ገላጭነት ይመጣል፤ እዚህ ዐውድ ላይ በአንጻረዊነት የመጣ ነው፤ ነብያችን"ﷺ" አስጠንቃቂ ብቻ ናቸው ማለት አምላክ ወይም መልአክ አይደሉም ለማለት ተፈልጎ እንጂ አብሳሪ፣ ነቢይ እና መልእክተኛ አይደሉም ማለት አይደለም፤ ቁሬሾች የጠየቁት ታምር ከአላህ የሚወርድ ታምር ነው፤ እንዲወርድ የሚፈልጉት ታምር የገንዘብ ድልብ፣ መልአክ እና በብራና የተጻፈ መጽሐፍ ነው፦
11፥12 *በእርሱ ላይ የገንዘብ ድልብ ለምን አልተወረደም? ወይም ከእርሱ ጋር መልአክ ለምን አልመጣም? ማለታቸውንም* በመፍራት ወደ አንተ ከሚወርደው ከፊሉን ልትተው በእርሱም ልብህ ጠባብ ሊኾን ይፈራልሃል፡፡ አንተ አስጠንቃቂ ብቻ ነህ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ተጠባባቂ ነው፡፡ فَلَعَلَّكَ تَارِكٌ بَعْضَ مَا يُوحَىٰ إِلَيْكَ وَضَائِقٌ بِهِ صَدْرُكَ أَن يَقُولُوا لَوْلَا أُنزِلَ عَلَيْهِ كَنزٌ أَوْ جَاءَ مَعَهُ مَلَكٌ ۚ إِنَّمَا أَنتَ نَذِيرٌ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
43፥53 *«በእርሱም ላይ የወርቅ አንባሮች ለምን አልተጣሉበትም ወይም መላእክት ከእርሱ ጋር ተቆራኝተው ለምን አልመጡም» አሉ*፡፡ فَلَوْلَا أُلْقِيَ عَلَيْهِ أَسْوِرَةٌ مِّن ذَهَبٍ أَوْ جَاءَ مَعَهُ الْمَلَائِكَةُ مُقْتَرِنِينَ
17፥93 «ወይም ከወርቅ የኾነ ቤት ላንተ እስከሚኖርህ፤ ወይም በሰማይ እስከምትወጣ፤ ለመውጣትህም በእኛ ላይ የምናነበው የኾነን *መጽሐፍ እስከምታወርድልን* ድረስ ፈጽሞ አናምንልህም» አሉ፡፡ «ጌታዬ ጥራት ይገባው፤ እኔ ሰው መልክተኛ እንጂ ሌላ አይደለሁም» በላቸው፡፡ أَوْ يَكُونَ لَكَ بَيْتٌ مِّن زُخْرُفٍ أَوْ تَرْقَىٰ فِي السَّمَاءِ وَلَن نُّؤْمِنَ لِرُقِيِّكَ حَتَّىٰ تُنَزِّلَ عَلَيْنَا كِتَابًا نَّقْرَؤُهُ ۗ قُلْ سُبْحَانَ رَبِّي هَلْ كُنتُ إِلَّا بَشَرًا رَّسُولًا
ስለዚህ እነዚህን የሚወርዱ ነገሮች እነርሱ በፈለጉት መንገድ ማውረድ እኔ አልችልም፤ አሉ እንጂ እኔ ታምር አላደርግም አላሉም።
ሚሽነሪዎች ልክ እንደ ኢ-አማንያን፦ "አላህ መኖሩን ከቁርኣን ውጪ አረጋግጥሉን" ማለት ጀምረዋል፤ ተገልብጦ ጥያቄው፦ "እግዚአብሔር መኖሩን ከባይብል ውጪ አረጋግጥሉን" ሲባሉ እንዲህ ይላሉ፦ "ይህ የእምነት ጉዳይ ነው፤ ባይብል ዮናስ በአሳ ነበሪ ሆድ ውስጥ ነበረ ይቅርና አሳ ነባሪው ዮናስ ሆድ ውስጥ ነበረ ቢባል እንቀበላለን፤ ምክንያቱም ይህ እምነት ነውና"፤ ታዲያ ይህንን ካላችሁ እስልምና ላይ ሲሆን ምነው ከእምነት ውጪ ኢ-አማንያን ትሆናላችሁ? በመቀጠል ልክ እንደ ኢ-አማንያን ጨረቃ ስለመከፈሏ የሥነ-ፈለክ መረጃ እንዲቀርብ ይዳዳሉ፤ በዘመናችን ያሉ የሥነ-ፈለክ ተመራማሪዎች አንድን ክስተት አልደረሱበትም ማለት ክስተቱ አልተከናወነም ማለት አይደለም፤ ለምሳሌ፦
ኢያሱ 10፥13  *ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ። ይህስ በያሻር መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ፥ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም*።

ጸሐይ እንደቆመች የሚያሳይ የሥነ-ፈለክ መረጃ የሚያቀርብልኝ አለን? በኢዩኤል ትንቢት ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ የሚል ትንቢት ነበረ፦
ኢዮኤል 2፥31 ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ *ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል*።
የሐዋርያት ሥራ 2፥20 ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ *ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ*።
የሐዋርያት ሥራ  2፥16  *ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለው ነው*።

ይህ ትንቢት በዓለ ኀምሳ ከተፈጸመ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም እንደተለወጡ የሚያሳይ የሥነ-ፈለክ ማስረጃ ይቅረብልን። እስራኤላውያን በኤርትራ ባሕር ሲሻገሩ ባሕሩ እንደግድግዳ ቆመ፥ ግብጻውያንን ግን ምድር ተሰንጥቃ ዋጠቻቸው ይላል፤ ቆሬ፣ ዳታን እና አቤሮን በማመጻቸው ከነቤተሰባቸው ምድር ተሰንጥቃ ዋጠቻቸው ይላል፦
ዘጸአት 14፥22 የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ መካከል በየብስ ገቡ፥ *ውኃውም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆነላቸው*።
ዘጸአት 15፥12 ቀኝህን ዘረጋህ፥ *ምድርም ዋጠቻቸው*።
ዘኍልቍ 16፥31-32  *እንዲህም ሆነ፤ ይህን ቃል ሁሉ መናገር በፈጸመ ጊዜ *ከበታቻቸው ያለው መሬት ተሰነጠቀ፤ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ እነርሱን ቤተ ሰቦቻቸውንም፥ ለቆሬም የነበሩትን ሰዎች ሁሉ፥ ዕቃዎቻቸውንም ሁሉ ዋጠቻቸው*።

ውኃ እንደ ግድግዳ መቆሙ እና ምድር ተሰንጥቃ ቆሬ፣ ዳታን እና አቤሮን በማመጻቸው ከነቤተሰባቸው መዋጧን የሥነ-ምድር ጥናት ማስረጃ ይቅረብልን። የለም። ስለሌለ ክስተቱ አልተከናወነም ብሎ በአራት ነጥብ መዝጋት ይቻላልን? በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉሃል እንደዚህ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የነቢያት መደምደሚያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድም ሰው አባት አይደለም፡፡ ግን የአላህ መልክተኛና የነቢያት መደምደሚያ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ مَّا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِّن رِّجَالِكُمْ وَلَـٰكِن رَّسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

ሰው መነጻጸሪያ ነጥብ ሳይኖረው ፈጽሞና ጨልጦ ወደ ጽርፈት ሲገባ ማየት እጅጉን ያማል፤ ኢስላም እውነትን በመግለጥ ሃሰትን በማጋለጥ እረገድ ፈር ቀዳጅና ፋና ወጊ ነው ብንል ግነት አይሆንብንም፤ ከእውነት በተቃራኒ ደግሞ የሃሰት ትምህርት የሚያራምዱ በዘመናችን የሚንቀሳቀሱ ቃዲያኒይ፣ ባሃኢያህ፣ ቁርአንያ ወዘተ የደጃሎች ተከታዮች ናቸው፤ የእነዚህ አንጃዎች መስራች፦ “ነብይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው የተነሱት ሚርዛ ጉላም አሕመድ የቃዲያኒይ መስራች፣ ሚርዛ ሁሴን አሊ የባሃኢያህን መስራች፣ ዶክተር ራሺድ ኸሊፋ የቁርአንያ መስራች ሲሆኑ፤ እነዚህ ነብያችን”ﷺ” ይመጣሉ ብለው ከተነበዩት ደጃሎች መካከል ናቸው። ይህንን ወደ ዝርዝር ከመግባታችን በፊት ስለ ነብይ እና ረሱል ያለውን እሳቤ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ ጥርስና ምላሱን እየነቀስን ቃጣ የምንይዝበት ሚዛን ቁርአን እና ሰሒህ ሐዲስን ይዘን ኢንሻሏህን እናስቀምጣለን፦

ነጥብ አንድ
“ነቢይ”
“ነቢይ” نبي የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ወይም “ተናገረ” ከሚል የግስ መደብ አሊያም “ነበእ” نَبَإِ ማለትም “ወሬ” ወይም “ንግግር” ከሚሉት የስም መደብ የመጣ ቃል ሲሆን “አውሪ” ወይም “ነጋሪ” ማለት ነው፤ ይህንን እስቲ ከቁርአን እንመልከት፦
66፡3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ ይህን ማን “ነገረህ”? አለች፤ ዐዋቂው ውስጠ አዋቂው “ነገረኝ” አላት፤ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِ وَأَظْهَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُ وَأَعْرَضَ عَنْ بَعْضٍ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِ قَالَتْ مَنْ أَنْبَأَكَ هَذَا قَالَ نَبَّأَنِيَ الْعَلِيمُ الْخَبِيرُ

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን መልሱ “ነበአኒ” نَبَّأَنِيَ ማለትም “ነገረኝ” ማለት ነው፤ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነገረ” ማለት “ነበአ” የሚለው ቃል ነው፤ ስለዚህ ነብይ ማለት ሁሉን አዋቂው ውስጠ አዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው፤ ወይንም አላህ አማንያንን በመልካም የሚያዝበት፤ ከክፉ የሚከለክልበት እና ለራሱ ሶላትን፣ ፆምን፣ ዘካን የሚተገብርበትን የሚያወርድለት ማለት ነው።

አላህ ለፈለገው ሰው “ነቢይነት” ሲሰጠው ያ ሰው ነብይ ይባላል፤ ይህንን የመረጠው ሰው አላህ በሶስት አይነት መንገድ ወህይ በማውረድ ያናግረዋል፤ እነዚህም ሶስት መንገዶች፦
አንደኛ መንገድ በሩዕያ ማናገር ነው፤ “ሩዕያ” رُّءْيَا ማለት “ራዕይ” ማለት ሲሆን ይህም ራዕይ በሪዕይ ውስጥ ሆነው የሚመጣላቸው ንግግር ነው፤ “ሪዕይ” رِءْي ማለት “እይታ” ማለት ሲሆን እውን ላይ ሆኖ ሳይተኛ በሰመመን ወይም በተመስጦ”contemplation” ላይ ሆነው ሲሆን ነው፤ የራዕይ አንዱ ገፅታ “መናም” مَنَام ማለት “ህልም” ሲሆን ይህም በነውም ሆነው የሚመጣላቸው ንግግር ነው፤ “ነውም” نَوْم ማለት “እንቅልፍ” ማለት ነው፤ በዚህ ሁኔታ አላህ ወህይ ካወረደለት ነብይ መካከል የኢማን አባት የሆነው ኢብራሂም”አ.ሰ.” ነው።
ሁለተኛ መንገድ በተክሊም ማናገር ነው፤ “ተክሊም” تَكْلِيم ማለት በሁለት ማንነት መካከል የሚደረግ “ምልልስ”conversation” ሲሆን አላህ ያለ ራዕይና ህልም ወይም ያለ መልአክ ሳይታይ ከግርዶ ወዲያ ሆና የሚያናግርበት መንገድ ነው፤ በዚህ መልኩ አላህ ያናገረው ነብይ ለናሙና ያክል ሙሳ”አ.ሰ.” ተጠቃሽ ነው።
ሶስተኛ መንገድ በመልአክ ማናገር ነው፤ “ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል “ተላላኪ” ማለት ሲሆን “መለክ” مَلَك ማለትም “መልአክ” የሚለው ቃል ተለዋዋጭ”inter-change” ሆኖ የመጣ ነው፤ ይህም የወህይ መልአክ ጂብሪል”አ.ሰ.” ነው፤ በዚህ ሁኔታ አላህ ወህይ ካወረደለት ነብይ መካከል ነብያችን”ﷺ” ናቸው፦
3:79 ለማንም ሰዉ አላህ መጽሐፍንና ጥበብን “ነቢይነትንም” ሊሰጠዉና ከዚያም ለሰዎች ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ሆኑ ሊል አይገባዉም፤ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ ٱللَّهُ ٱلْكِتَٰبَ وَٱلْحُكْمَ وَٱلنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا۟ عِبَادًۭا لِّى مِن دُونِ ٱللَّهِ وَلَٰكِن كُونُوا۟ رَبَّٰنِيِّـۧنَ بِمَا كُنتُمْ تُعَلِّمُونَ ٱلْكِتَٰبَ وَبِمَا كُنتُمْ تَدْرُسُونَ
42:51″ለሰው” አላህ “በራእይ”፣ ወይም “ከግርዶ ወዲያ”፣ ወይም “መልክተኛን መልአክን” የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም፤ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ
ነጥብ ሁለት
“ረሱል”
“ረሱል” رَسُول የሚለው ቃል ደግሞ “አርሰለ” أَرْسَلَ “ላከ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን የሚላክ መልእክተኛ ማለት ነው፤ ለረሱል ከአላህ የሚወርድለት “ሪሳላ” رِسَٰلَٰ “መልዕክት” ማለት ነው፦
5:67 አንተ “መልእክተኛ” ሆይ! ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን አድርስ፤ ባታደሪስ “መልዕክቱን” አላደረስክም፤ يَا أَيُّهَا الرَّسُولُ بَلِّغْ مَا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ۖ وَإِن لَّمْ تَفْعَلْ فَمَا بَلَّغْتَ رِسَالَتَهُ ۚ وَاللَّهُ يَعْصِمُكَ مِنَ النَّاسِ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْكَافِرِينَ

በነቢይና በረሱል መካከል ልዩነት አለ፤ ነቢይ እና ረሱል በሚሉት የማዕረግ ስሞች መካከል “ወ” و ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር አለ፤ ይህም ነቢይ እና ረሱል ሁለት የተለያየ ደረጃ መሆኑን ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በተጨማሪም “አልላክንም” የሚለው አጽንኦታዊ ቃል “ቢሆን እንጂ” በሚል አፍራሽ ቃል”negative particle” በመምጣቱ ነብይ በመልካም እንዲያዝ በመጥፎ እንዲከለክል ለአማንያን እንደተላከ ሁሉ መልእክተኛ ደግሞ ለአማንያንና ለከሃድያን ለማስጠንቀቅና ለማብሰር ይላካል፦
22:52 “”ከመልእክተኛ እና ከነቢይም”” ከአንተ በፊት አንድንም አልላክንም፣ ባነበበ ና ዝም ባለ ጊዜ፣ ሰይጣን በንባቡ ላይ ማጥመሚያን ቃል የሚጥል ቢሆን እንጂ وَمَا أَرْسَلْنَا مِنْ قَبْلِكَ مِنْ رَسُولٍ وَلَا نَبِيٍّ إِلَّا إِذَا تَمَنَّىٰ أَلْقَى الشَّيْطَانُ فِي أُمْنِيَّتِهِ ፤

መልእክተኛ ሁሉ ነቢይ ነው፤ ነገር ግን ነቢይ ሁሉ መልእክተኛ አይደለም፣ ነብይነት ከተደመደመ መልእክተኛነትም ተደምድሟል፤ ምክንያቱም አንድ መልእክተኛ ነብይነትን አሳልፎ ነው መልእክተኛ የሚሆነው፤ ስለዚህ ነብያችን”ﷺ” የነቢያት መደምደሚያ ናቸው፦
33:40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም፤ ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና “”የነቢያት መደምደሚያ”” ነው፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا ።

ነጥብ ሦስት
“መጨረሻ”
“መደምደሚያ” የሚለው ቃል የአሲም ቂርአት ላይ “ኺታም” خِتَٰـم ሲሆን የኪሳእ ቂርአት ላይ ደግሞ “ኻተም” خَاتَم ሲሆን ትርጉሙ “መጨረሻ” “መቋጫ” “ማጠናቀቂያ” ማለት ነው፤ በተለያየ ጊዜ የሚመጡት የአላህ ነብያት ከአደም ጀምሮ “ተከታታይ ግህደተ-መለኮት”progressive revelation” ነበራቸው፤ መልእከተኞችም አላህ የወሰነላቸው የራሳቸው ዘመነ-መግቦት”dispensation” ነበራቸው፤ ነገር ግን አንድ እድገት ጅማሬ እዳለው ሁሉ ድምዳሜም እንዳለው ሁሉ ነብይነትም በአደም ተጀምሮ በነብያችን”ﷺ” ተጠናቋል፤ ነብያችንም”ﷺ” በሰሒህ ሐዲስ የነቢያት ዓቂብ” ْعَاقِبُ ማለትም “መጨረሻ” እንደሆኑና ነብይ ከእርሳቸው በኃላ ፈጽሞና ጨልጦ እንደማይመጣ አስረግጠው ነግራውናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 43, ሐዲስ 163
ኢብኑ ጁበይር ከአባቱ አግኝቶ እንደተረከው፤ ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “እኔ ሙሐመድ ነኝ፣ እኔ አሕመድ ነኝ፣ እኔ ማሒ ማለትም ያ ከሃዲ ሲያጠፋ የምቀጣ ነኝ፣ እኔ ሰዎች በሚሰበሰቡት ጊዜ ሐሺር(ሰብሳቢ) ነኝ፣ ከዚህ በኃላ ነብይ የለም፤ እኔ ዓቂብ(መጨረሻ) ነኝ። بْنَ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ عَنْ أَبِيهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” أَنَا مُحَمَّدٌ وَأَنَا أَحْمَدُ وَأَنَا الْمَاحِي الَّذِي يُمْحَى بِيَ الْكُفْرُ وَأَنَا الْحَاشِرُ الَّذِي يُحْشَرُ النَّاسُ عَلَى عَقِبِي وَأَنَا الْعَاقِبُ ” . وَالْعَاقِبُ الَّذِي لَيْسَ بَعْدَهُ نَبِيُّ .

እስራኤላውያን በነብይ ይመሩ ነበር፤ አንዱ ነብይ ጊዜው ሲያልቅ ሌላ ነብይ ይነሳ ነበር፤ ከነብያችን”ﷺ” በኃላ ግን የሚመጣ ነብይ የለም፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60 , ሐዲስ 122:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “እስራኤላውያን በነብያት ይመሩ ነበር፤ መቼም ቢሆን አንድ ነብይ ሲሞት በእርሱ ምትክ ሌላ ነብይ ቦታውን ይተካ ነበር፤ ከእኔ በኃላ ነብይ የለም። ግን በቁጥር የሚጨምሩ ኸሊፋዎች ይሆናሉ። عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” كَانَتْ بَنُو إِسْرَائِيلَ تَسُوسُهُمُ الأَنْبِيَاءُ، كُلَّمَا هَلَكَ نَبِيٌّ خَلَفَهُ نَبِيٌّ، وَإِنَّهُ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي، وَسَيَكُونُ خُلَفَاءُ فَيَكْثُرُونَ.
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 64 , ሐዲስ 438:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ከተቡክ ወጥተው ዐሊይን በመዲናህ እንዲከተል ሾሙት፤ ዐሊይ፦ “ከህጻናትና ከሴት ጋር ልተወኝ ትፈልጋለህን? አላቸው፤ ነብዩም ልክ አሮን ለሙሴ እንደሆነው አንተ ለእኔ ብትሆን አትደሰትምን? ነገር ግን ከእኔ በኃላ ነብይ የለም። أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم خَرَجَ إِلَى تَبُوكَ، وَاسْتَخْلَفَ عَلِيًّا فَقَالَ أَتُخَلِّفُنِي فِي الصِّبْيَانِ وَالنِّسَاءِ قَالَ ” أَلاَ تَرْضَى أَنْ تَكُونَ مِنِّي بِمَنْزِلَةِ هَارُونَ مِنْ مُوسَى إِلاَّ أَنَّهُ لَيْسَ نَبِيٌّ بَعْدِ

የነብያት ዑደር በአደም ተጀምሮ በነብያችን”ﷺ” ሲጠናቀቅ የተሰጠው ንጽጽር በአንድ ቤት ህንጻ የመጨረሻ ድምዳሜ ሸክላ ነው፤ ነብያችን”ﷺ” ያ የድምዳሜው ሸክላ ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 61 , ሐዲስ 44:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የእኔ ከእኔ በፊት ከነበሩት ነብያት የሚነጻጸረው አንድ ግለሰብ በቆንጆና በተዋበ በሚገነባው ቤት ነው፤ ያ ቤት ድምዳሜው ላይ አንድ ሸክላ ይቀረው ነበር፤ ሰዎች ያ ቤት ጋር ሄደውና አድንቀው ነገር ግን እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሸክላ በድምዳሜ ቦታ ስለሆነ ነው ያማረው” አሉ፤ ያ ሸክላ እኔ ነኝ፤ እኔ የነብያት መደምደሚያ ነኝ። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” إِنَّ مَثَلِي وَمَثَلَ الأَنْبِيَاءِ مِنْ قَبْلِي كَمَثَلِ رَجُلٍ بَنَى بَيْتًا فَأَحْسَنَهُ وَأَجْمَلَهُ، إِلاَّ مَوْضِعَ لَبِنَةٍ مِنْ زَاوِيَةٍ، فَجَعَلَ النَّاسُ يَطُوفُونَ بِهِ وَيَعْجَبُونَ لَهُ، وَيَقُولُونَ هَلاَّ وُضِعَتْ هَذِهِ اللَّبِنَةُ قَالَ فَأَنَا اللَّبِنَةُ، وَأَنَا خَاتِمُ النَّبِيِّينَ
ምናልባት ከእውነት ለመሸሽ አንድ አውቆ የተኛ ሰው፦ ነብያችን”ﷺ”፦ የነብያት እንጂ የመልእክተኞች መደምደሚያ ነኝ አላሉም” ብሎ ሊሞግት ይችላል፤ ሲጀመር ነብይ ሳይኮን ወደ መልእክተኛ መሻገር የለም፤ ነብይነት ከተዘጋ መልእክተኛነትም ይዘጋል፤ ሲቀጥል ነብያችን”ﷺ” ፍርጥ አርገው እንቅጩን ነብይነት እና መልእክተኝነት እንደተዘጋ እና ከእሳቸው በኃላ ነብይ ብቻ ሳይሆን መልእክተኛም እንደሌለ ተናግረዋል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነብይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነብይም የለም። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚጠየቀው ጥያቄ ነብያችን”ﷺ” የነብይና የመልእክተኛ መጨረሻ ከሆኑ ዒሳ ከእርሳቸው በኃላ እንዴት ይመጣል? ይህ ቀላል ጥያቄ ነው፤ ዒሳ ካለፉት መልእክተኞች አንዱ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሲመጣም ነብይ ሆኖ ነበእ ሊመጣለት ወይም ረሱል ሆኖ ሪሳላ ሊወርድለት ሳይሆን የአደም ልጆችን በአንድ አምልኮ ሊጠቀልል ነው፤ ይህንን ተልእኮ የሚፈጽመው በወረደለትም ወሕይ በኢንጅል ሳይሆን በቁርአን ነው፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 55 , ሐዲስ 658:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የመርየም ልጅ ዒሳ በመካከላችሁ በሚወርድ ጊዜ እንዴት ትሆናላችሁ? እርሱ ሰዎችን በቁርአን ይበይናል እንጂ በኢንጂል አይበይንም። حَدَّثَنَا ابْنُ بُكَيْرٍ، حَدَّثَنَا اللَّيْثُ، عَنْ يُونُسَ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ نَافِعٍ، مَوْلَى أَبِي قَتَادَةَ الأَنْصَارِيِّ أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ كَيْفَ أَنْتُمْ إِذَا نَزَلَ ابْنُ مَرْيَمَ فِيكُمْ وَإِمَامُكُمْ مِنْكُمْ ‏”‌‏.‏ تَابَعَهُ عُقَيْلٌ وَالأَوْزَاعِيُّ‏.‏
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 301
አቢ ሁረይራ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በመካከላችሁ የመርየም ልጅ በወረደ ጊዜ እና ሲመራችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ኢብኑ አቢ ዚዕብም አቢ ሁረይራ የዘገበው መሰረት አድርጎ፦ “ሲመራችሁ ምን ታደርጋላችሁ?” ምን ማለት ነው? አለ፤ እኔም ለእኔ አብራራልኝ አልኩኝ፤ እርሱም አለ፦ “በጌታችሁ ተባረከ ወተዓላ መጽሐፍ እና በመልእክተኛው በነብያችሁ”ﷺ” ፈለግ ይመራችኃል” አለ*። أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ كَيْفَ أَنْتُمْ إِذَا نَزَلَ فِيكُمُ ابْنُ مَرْيَمَ فَأَمَّكُمْ مِنْكُمْ ‏”‏ ‏.‏ فَقُلْتُ لاِبْنِ أَبِي ذِئْبٍ إِنَّ الأَوْزَاعِيَّ حَدَّثَنَا عَنِ الزُّهْرِيِّ عَنْ نَافِعٍ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ‏”‏ وَإِمَامُكُمْ مِنْكُمْ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ ابْنُ أَبِي ذِئْبٍ تَدْرِي مَا أَمَّكُمْ مِنْكُمْ قُلْتُ تُخْبِرُنِي ‏.‏ قَالَ فَأَمَّكُمْ بِكِتَابِ رَبِّكُمْ تَبَارَكَ وَتَعَالَى وَسُنَّةِ نَبِيِّكُمْ صلى الله عليه وسلم ‏.‏

ማጠቃለያ
ታዲያ ነብይ እና መልእክተኛ ከነብያችን”ﷺ” በኃላ የለም ከተባለ “ነብይ ነኝ” ወይም “መልእክተኛ ነኝ” ብለው የተነሱት ሚርዛ ጉላም አሕመድ የቃዲያኒይ መስራች፣ ሚርዛ ሁሴን አሊ የባሃኢያህን መስራች፣ ዶክተር ራሺድ ኸሊፋ የቁርአንያ መስራች ምንድን ናቸው? ሲባል ኃሳዌ ነብይ እና መልእክተኛ ናቸው።
“አድ-ደጃል” الدجّال‌‎ የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “ቀላቀለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ቀላቃይ” ማለት ነው፤ እውነትን ከሐሰት ጋር የሚቀላቅል ማለት ነው፤ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ “ኀሳዌ” ማለትም “አሳሳች” “ውሸተኛ” “ቀጣፊ” ማለት ነው። ዋናው ደጃል “መሲል ደጃል” ማለትም “ኀሳዌ መሲህ” ሲሆን እርሱ ከመምጣቱ በፊት የሚመጡ ሠላሳ ደጃሎች አሉ፤ “ደጅጃሉን” دَجَّالُونَ የሚለው ቃል “ደጃል” دجّال‌‎ ለሚለው ነጠላ ቃል ብዜት ነው፤ እነዚህ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ رَسُولُ اللَّهِ
ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 37, ሐዲስ 13
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ከእኔ ዑማ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች፦ “ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፤ ነገር ግን እኔ የነብያት መደምደሚያ ነኝ፤ ከእኔ በኃላ ነብይ የለም”። وَحَتَّى تَعْبُدَ قَبَائِلُ مِنْ أُمَّتِي الأَوْثَانَ وَإِنَّهُ سَيَكُونُ فِي أُمَّتِي كَذَّابُونَ ثَلاَثُونَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ نَبِيٌّ وَأَنَا خَاتَمُ النَّبِيِّينَ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي

የጊዜና የቦታ ጥበት እንጂ ህልቆ መሳፍርት መረጃዎችን ማቅረብ ይቻል ነበር፤ “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ” ይላል የአገሬ ሰው፤ ከላይ የተዘረዘሩትን የቁርአን እና የሰሒህ ሐዲስ መረጃዎችን በአጽንዖትና በአንክሮት የተገነዘበ ሰው እብሪትና ትእቢት ያለበት አባይና ወላዋይ ካልሆነ በስተቀር ደጃሎች ወደዘረጉት ጽርፈት አይገባም። የዚህ መጣጥፍ አላማ እንደ እኔ ጭላንጭል ዕውቀት ያላቸው ልጆች በዚህ የደጃሎች ጽርፈት ሰለባ እንዳይሆኑ የቀለም ቀንድ ከነከሱ ምሁራኖቻችን ስንክሳር ዕውቀት ይዘው ልጓም እና መረን እንዲያበጁ እንዲረዳ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ታቦት እና ጣዖት
እኛ ሙስሊሞች፦ "ታቦት ጣዖት ነው" አላልንም። ምክንያቱም ታቦት የጽላት ማስቀመጫ ሳጥን ነው።
ባይሆን የአገራችን የተዋሕዶ ክርስቲያኖች ናቸው፦ "ጣዖቱን ታቦት ነው" የሚሉን። ምክንያቱም አንድ ድንጋይ፣ ወርቅ፣ ብረት፣ እንጨት የጸጋ ይሁን የአምልኮ ስግደት ከተሰገደለት ያ ነገር ጣዖት ነው። ያንን ቅርጻ ቅርጽ ለምን የጸጋ ስግደት ትሰግዱለታላችሁ? ስንላቸው "ታቦት ነው" ይሉናል። ለታቦት የሰገደ ሰው በባይብል የለም። ለታቦት ስገዱ የሚል የለም። ሙሴ የሰራው ታቦት አንድ ሲሆን ጠፍቷል።
ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ንግሥተ ሳባእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

27፥22 ወፉ ዕሩቅ ያልኾነንም ጊዜ ቆዬ፡፡ አለም «ያላወቅከውን ነገር አወቅኩ፡፡ *ከሰበእም እርግጠኛን ወሬ አመጣሁልህ*፡፡ فَمَكَثَ غَيْرَ بَعِيدٍۢ فَقَالَ أَحَطتُ بِمَا لَمْ تُحِطْ بِهِۦ وَجِئْتُكَ مِن سَبَإٍۭ بِنَبَإٍۢ يَقِينٍ

“ንግሥተ ሳባእ” ማለት በዕብራይስጥ “መለከት ሰባእ” מַלְכַּת־שְׁבָא ትባላለች፤ ትርጉሙም “የሳባ ንግሥት” ማለት ነው፤ ስለ ሳባ ንግሥት ከማየታችን በፊት ስለ ሳባ አገር እንመልከት፤ ሳባ የአብርሃም የልጅ ልጅ ነው፤ አብርሃም ኬጡራ የተባለች ሚስት አገባ፤ ከእርሷም ዮቅሳንን ወለደ፤ ዮቅሳን ሳባን ወለደ፦
ዘፍጥረት 25፥1-3 አብርሃምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተባለች ሚስት አገባ። እርስዋም ዘምራንን፥ ዮቅሳንን፥ ሜዳንን፥ ምድያምን፥ የስቦቅን፥ ስዌሕን ወለደችለት። ዮቅሳንም *ሳባን* እና ድዳንን ወለደ። የድዳንም ልጆች አሦርያውያን፥ ለጡሳውያን፥ ለኡማውያን ናቸው።
1ኛ ዜና መዋዕል 1፥32 የአብርሃምም ገረድ የኬጡራ ልጆች ዘምራን፥ ዮቅሳን፥ ሜዳን፥ ምድያም፥ የስቦቅ፥ ስዌሕ። *የዮቅሳንም ልጆች ሳባ፥ ድዳን*።

ከዛ በኃላ ከሳባ የተወለዱ ዝርያዎች ሳባውያን ይባላሉ፤ አገራቸውም ሳባ ትባላለች፤ የዚህች አገር ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች፤ ንጉሡም ሰሎሞን፥ በገዛ እጁ ከሰጣት ሌላ፥ የወደደችውን ሁሉ ከእርሱም የለመነችውን ሁሉ ለሳባ ንግሥት ሰጣት እርስዋም ተመልሳ ከባሪያዎችዋ ጋር ወደ ምድርዋ ሄደች፦
1ኛ ነገሥት 10፥1 *የሳባም ንግሥት* በእግዚአብሔር ስም የወጣለትን የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች።
2ኛ ዜና መዋዕል 9፥1 *የሳባም ንግሥት የሰሎሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በግመሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ የከበረም ዕንቍ አስጭና ከታላቅ ጓዝ ጋር ሰሎሞንን በኢየሩሳሌም በእንቆቅልሽ ትፈትነው ዘንድ መጣች*፤ ወደ ሰሎሞንም በገባች ጊዜ በልብዋ ያለውን ሁሉ አጫወተችው።
1ኛ ነገሥት 10፥13 ንጉሡም ሰሎሞን፥ በገዛ እጁ ከሰጣት ሌላ፥ የወደደችውን ሁሉ ከእርሱም *የለመነችውን ሁሉ ለሳባ ንግሥት ሰጣት እርስዋም ተመልሳ ከባሪያዎችዋ ጋር ወደ ምድርዋ ሄደች*።

ዳዊትም ስለ ልጁ ስለ ሰለሞን በሚናገርበት አንቀጽ ላይ የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ ብሏል፦
መዝሙር 72፥10 የተርሴስ እና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብ እና *የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ*።

“ሳባ” ስለምትባለው አገር ለማወቅ ቀላል ነው፤ ኢሳይያስ ስለ እስራኤል በተናገረበት የዐውድ ፍሰት ላይ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ እና ሳባን የተለያዩ አገር ናቸው፦
ኢሳይያስ 43፥3 እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ *ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያን እና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ*።
ኢሳይያስ 45፥14 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ *የግብጽ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ*፤

ሳባውያን በነጋዴነታቸው ይታወቃሉ፤ ሽቶ፣ የከበረ ድንጋይ፣ ወርቅ፣ እጣን ወዘተ ይነግዱ ነበር፦
ኢሳይያስ 60፥6 የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ *ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፥ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ* የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ።
ኢዮኤል 3፥8 እግዚአብሔር ተናግሮአልና ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁን በይሁዳ ልጆች እጅ እሸጣለሁ፥ እነርሱም ለሩቆቹ ሕዝብ *ለሳባ ሰዎች* ይሸጡአችኋል።
ሕዝቅኤል 27፥22 *የሳባ እና የራዕማ ነጋዴዎች እነዚህ ነጋዴዎችሽ ነበሩ*፤ በጥሩ ሽቶና በከበረ ድንጋይ ሁሉ በወርቅም ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር።

ይህቺ ሳባ የምትባለው አገር የት ናት የሚለውን ለማወቅ አሁንም ጥናታችንን እንቀጥል፤ ቅድሚያ “አዜብ” ተብሎ የተቀመጠው በዕብራይስጥ “ኔጌብ” נֶ֫גֶב ሲሆን “ደቡብ” ማለት ነው፦
ሉቃስ 12፥55 *በአዜብም* ነፋስ ሲነፍስ፦ ትኩሳት ይሆናል ትላላችሁ፥ ይሆንማል።
1ኛ ነገሥት 7፥39 ኵሬውንም በቤቱ ቀኝ *በአዜብ* በኩል አኖረው።

ሳባ በእስራኤል በስተ ደቡብ የምትገኝ አገር ናት፤ አብርሃም የተጓዘበትና በእንግድነት የሄደበት ቦታ ነው፦
ዘፍጥረት 12፥9 አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ *አዜብ* ሄደ።
ዘፍጥረት 13፥1 አብራምም ከግብፅ ወጣ፤ እርሱና ሚስቱ ለእርሱ የነበረውም ሁሉ ሎጥም ከእርሱ ጋር ወደ *አዜብ* ወጡ።

ይህ አዜብ የተባለው ቦታ በቃዴስና በሱር መካከል ያለ ቦታ ነው፦
ዘፍጥረት 20፥1 አብርሃምም ከዚያ ተነሥቶ *ወደ አዜብ ምድር ሄደ*፥ *በቃዴስ እና በሱር መካከልም ተቀመጠ* በጌራራም በእንግድነት ተቀመጠ።