ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.8K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ቤተክርስቲያን ወይስ ኡማ?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥110 ለሰዎች ከተገለጸች “ኡማ” أُمَّةٍ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ፤ በአላህም ታምናላችሁ፡፡

መግቢያ
ነብያት ሆኑ ሃዋርያት ቤተ-ክርስቲያን ወይም ቸርች”church” የሚለውን ቃል በፍፁም አያውቁትም። ይህንን ስናገር በጨበጣ ሳይሆን በእማኝና በአስረጂነት መረጃ ይዤ ነው፤ “ቤተ-ክርስቲያን” ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ቤት” እና “ክርስቲያን” ትርጉሙም “የክርስቲያን ቤት” ማለት ነው፤ ልብ በል “ክርስቲያን” የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ አገልግሎት ላይ የዋለው ኢየሱስ ካረገ በኃላ በጠላት ስያሜ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 11:26 ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፥ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም #መጀመሪያ በአንጾኪያ #ክርስቲያን ተባሉ።”

ክርስቲያን” ማለት “ክርስቶሳውያን” ወይም “ክርስቶሶች” አሊያም “ቅቡዓን” ማለት ነው፤ ይህንን ስም ነቢያት አያውቁትም፤ “ቸርች””church” የሚለው የኢንግሊሹ ቃልም ቢሆን ከጀርማኒክ ቃል የተገኘ ሲሆን “የጌታ” ማለት እንጂ ስሜት የሚሰጥ ትርጉም የለውም፤ ታዲያ ቤተክርስቲያን ወይም ቸርች የሚለውን ስም ነብያት ሆነ ሃዋርያት ካላወቁት ምን ነበር የሚያውቁት? ብለን ስንጠይቅ መልሱን ነጥብ በነጥብ እናያለን፦

ነጥብ አንድ
“ኤክሌሺያ”
“ኤክሌሺያ” ἐκκλησία ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ “ተጠርተው የወጡ””called out” ማለት ሲሆን ሙያዊ ፍቺው ደግሞ “ጉባኤ””assembly” ወይም “ማህበር”congregation” ማለት ነው፤ ይህንን ቃል አዲስ ኪዳን ኢየሱስ “ጉባኤ” በሚል ተናግሮታል፦
ማቴዎስ 16:18 እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ “ጉባኤዬን” ἐκκλησία እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።”
ማቴዎስ 18:17 እነርሱንም ባይሰማ፥ “ለጉባኤው” ἐκκλησία ንገራት፤ ደግሞም “ጉባኤውን” ἐκκλησία ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።”

በተረፈ በአዲስ ኪዳን ንባባት ሁሉ ላይ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ቤተክርስቲያን ወይም “ቸርች” ሳይሆን “ኤክሌሺያ” ነው፤ በእርግጥ ኢየሱስ ግሪክ ተናጋሪ አልነበረም፤ የአረማይክ ዘዬ ተናጋሪ ነበረ፤ ኢየሱስ የተናገረበት የአረማይኩ ንግግር ምንም ቅሪት ቢጠፋም ኤክሌሺያ ተብሎ በግሪክ እደ-ክታባት ላይ የተቀመጠው ቃል በአማረይክ “ኡማ” የሚል ፍቺ አለው፤ በእብራይስጡ እደ-ክታብ ላይ “ቀሃል” קהל ተብሎ የተቀመጠው ቃል በግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ “ኤክሌሺያ” ἐκκλησία ተብሎ ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 28:3 ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ “ጉባኤ” לִקְהַ֥ל እንድትሆን ይባርክህ፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ፤”
ዘፍጥረት 35፥11 እግዚአብሔርም አለው፦ ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፤ ብዛ፥ ተባዛም፤ ሕዝብና የአሕዛብ “ማኅበር” וּקְהַ֥ל ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ።
ዘፍጥረት 48:4 እንዲህም አለኝ። እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ፥ አበዛሃለሁም፥ ለብዙም ሕዝብ “ጉባኤ” לִקְהַ֣ל አደርግሃለሁ፤ ይህችንም ምድር ከአንተ በኋላ ለዘላለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ።”
ዘኍልቍ 14:5 ሙሴና አሮንም በእስራኤል ልጆች “ጉባኤ” קְהַ֥ל ፊት በግምባራቸው ወደቁ።”
ዘኍልቍ 15:15 ለእናንተ “በጉባኤው” קְהַ֥ל ላላችሁ በእናንተም መካከል ለሚቀመጥ መጻተኛ አንድ ሥርዓት ይሆናል፥ ለልጅ ልጃችሁም የዘላለም ሥርዓት ይሆናል፤ እናንተ እንደ ሆናችሁ እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት መጻተኛ ይሆናል።”

ብዙ ጥቅስ በቁና እየሰፈሩ ጥቅሶችን ማቅረብ ይቻላል፤ ግን ለመረጃ ያክል ከላይ ያየናቸው ናሙናዎች በቂ ናቸው፤ በእብራይስጡ እደ-ክታባት “ቀሃል” קהל ወይም በግሪክ ሰፕቱጀንት “ኤክሌሺያ” ἐκκλησία የሚለው ይህ ቃል 111 ጊዜ ብሉይ ኪዳን ላይ የሰፈውን ቃል ቤተክርስቲያን ወይም ቸርች ብላችሁ ለምን አልተረጎማችሁትም? ምክንያቱም ብሉይ ኪዳን ላይ ያለው ጉባኤ በአዲስ ኪዳን ኤክሌሺያ” ἐκκλησία ስለተባለ፦
የሐዋርያት ሥራ 7:38 ይህ ሰው በሲና ተራራ ከተናገረው መልአክና ከአባቶቻችን ጋር በምድረ በዳ “በማኅበሩ” ἐκκλησίᾳ ውስጥ የነበረው ነው፤ ይሰጠንም ዘንድ ሕይወት ያላቸውን ቃላት ተቀበለ፤”