TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይነበብ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ይጀምራል። በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እና ከፈታኞች ምን እጠበቃል ? [ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ] - ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍላቸው ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ…
#ይነበብ2

የመውጫ ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ከሚኖሩ ዲስፕሊንና እና ፕሮቶኮል መካከል ፦

- ከተፈቀደላቸው የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ለእለቱና ለዛ ፈተና ከተመደቡ አስተባባሪዎች፣ ለፈተናው ከተመደቡ ፈታኞች ውጭ የትኛውም አካል ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

- ፈተናው በኦንላይን ስለሚሰጥ የአይሲቲ ሙያተኞች በመፈተኛ ክፍሎች አቅራቢያ በመሆን ድጋፍ ይሰጣሉ፡፡

- የፀጥታ ሃይል ወደ መፈተኛ ክፍል እንዲገባ አስገዳጅ ሁኔታ ከተፈጠረ በማንኛውም ጊዜ ሊገባ ይችላል፡፡

- የዩኒቨርስቲ የበላይ ኃላፊዎችን ጨምሮ የትኛውም አካል በምንም ሁኔታ ስልክ፣ ስማርት ዋች፣ ታብሌት እና ተመሳሳይ ቁሶችን ይዞ ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት አይችልም፡፡

- የአይሲቲ ሙያተኞች በመፈተኛ ክፍሎች የሚስጡት ድጋፍ ከትምህርት ሚኒስቴር ባልደረቦች ወይም ከዩኒቨርስቲው አመራር ድጋፍና አመራር ማግኘትን ስለሚያካትት በልዩ ሁኔታ በዩኒቨርስቲው ተመዝግቦ የሚያዝና የሚታወቅ ቁጥር ያለው ስልክ ይዘው ወደ መፈተኛ አዳራሽ እንዲገቡ ሊፈቀድ ይችላል፡፡

- በአንዳንድ ፕሮግራሞች #ካልኩሌተር ማምጣት ይፈቀዳል፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ ፕሮግራሞች ለማስልያ የሚረዳ ንፁህ ወረቀት በዩኒቨርሰቲዎች በኩል ሊፈቀድ ይችላል፡፡ ይህም ሆኖ ስልክ፣ ስማርት ዋች፤ ታብሌት እና ተመሳሳይ ቁሶችን እንደ ካልኩሌተር መጠቀም ፈፅሞ አይፈቀደም፡፡ ሥራ ላይ የሚውሉ ካልኩሌተሮች የተራቀቁና ፕሮግራ መብል እንዳይሆነ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡

- በማንኛውም ወቅት ከተፈቀደላቸውና ለድጋፍ ከተመደቡ የአይ.ሲ.ቲ ባለሙያዎች በስተቀር የተፈታኙን መፈተኛ ኮምፒውተር መንካት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

(ተጨማሪ ከላይ ያንብቡ)

በድጋሚ መልካም ፈተና !

@tikvahethiopia
👍1.03K👎329106🕊36🙏23🥰21😱17😢17