TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🌱 የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀመረ። በአጠቃላይ 7.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል  ዕቅድ ተይዟል። በዛሬው ዕለት በወንዝ ዳርቻ ልማት አንዱ ክፍል በሆነው በእንጦጦ ዙሪያ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ፣ የናይጄሪያ ምክትል ፕረዚዳንት ካቲም ሼቲማን ጨምሮ የክልል አመራሮችና ሚኒስትሮች በተገኙበት የችግኝ ተከላ ተካሂዷል። በዚህ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት…
#Ethiopia 🌱🇪🇹

ነገ ከንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በሀገር ደረጃ 700 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ዘመቻ ይካሄዳል።

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ " ነገ ለንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ጀምሮ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራችን አካል የሆነውን በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል አላማን ለማሳካት እንነሳለን " ብለዋል።

" ከፍ ያለ ግብ ነው። ግን ጥንካሬያችንን፣ አንድነታችንን እና ለሕዝባችን ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ይኽ ችግኝ ከመትከል በላይ ነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ትንሽ ትልቅ፣ የከተማ የገጠር ሳንል ዜጎች ሁሉ አካባቢያችን እንዲያገግም፣ የውሃ ምንጮቻችን እንዲጠበቁ፣ የኑሮ ሁኔታችን እንዲሻሻል እንዲሁም ለመጪው ትውልዶች ዘላቂነት ያለው ነገን ለማረጋገጥ የምንሳተፍበት ተግባር ነው " ብለዋል።

ሁሉም በዚህ ታላቅ ሀገራዊ ሥራ ላይ እንዲሳተፍ እና እንዲያስተባብር አሳስበዋል።

" በጋራ ጠንካራ ዛፎችን ብቻ ሳይሆን ጠንካራ እና የበለጠ አረንጓዴ የሆነች ኢትዮጵያን እናሳድጋለን " ብለዋል።

#Ethiopia 🇪🇹 #GreenLegacy #የአረንጓዴ_ዐሻራ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😡691565👏42🙏25😭18🕊14🤔12😢9🥰5😱2