TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #እናትፓርቲ

እናት ፓርቲ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር በተያያዘ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው " መንግሥት እየተገበረው ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፍቱን መድኃኒት ሳይሆን በጫናና አጣብቂኝ የመጠ የሥርዓቱን እድሜ ማራዘሚያ ኪኒን ነው " ሲል ገልጾታል።

በዚሁ መግለጫው ላይ ፤ የሚፈራ ማኅበራዊ ቀውስ እንዳለ በማመላከት ይህ ቀውስ ሊታከም ከማይችልበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራውን እንደገና እንዲያጤነው አሳስቧል።

መንግሥት በግል ዘርፉና ማኅበረሰቡ ላይ የጫነውን እንቅፋቶች ሁሉ እየመረመረ በአስቸኳይ እንዲያነሳም ጠይቋል።

የሠራተኛውና ደሞዝተኛው የዛሬ 6 ዓመቱ የኑሮ ደረጃን የሚመልሰውን (የሚያስተካክለውን) የደሞዝ ጭማሪ በአስቸኳይ እንዲያደርግም መንግስትን ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርሶ እንዳይበላና አቅርቦት እንዳይጨምር የምርት ግብዓቶች (factors of production) ሁሉ ከካድሬ እጅ ወጥቶ አምራቹ/ባለቤቱ እንዲይዘውና እንዲያዝበት እንዲደረግም ፓርቲው እናሳስቧል።

እናት ፓርቲ በላከው መግለጫ ፤ " በአጠቃላይ ሲንከባለል የመጣውና አሁን የባሰበት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በካድሬዎች ሳይሆን በባለሞያዎች እንዲመራ በማድረግ ግልጽ የኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ እንዲቀመጥ እንጠይቀለን " ብሏል።

በተጨማሪ ፥ መንግሥት ራሱ ፈቅዶና ፈርሞ ያመጣው ፖሊሲ የፈጠረውን ምስቅልቅል በነጋዴው ማኅበረሰብ ላይ እያመካኙ ሱቅ ማሸግና እጅ መንሻ መቀበል ሥራዬ ብለው የያዙትን ባለስልጣኖቹን አደብ እንዲያስገዛ አሳስቧል።

ፓርቲው ፤ " መንግሥት በኢኮኖሚው ውስጥ " ሁሉንም ድስት እኔ ካልጣድኩ " ማለቱን አቁሞና ከሁለገብ ተጫዋችነቱ ወጥቶ ወደ የመንግሥት ዳኝነቱ ብቻ እንዲገባ፤ " ነጻ ገበያን ተቀብያለሁ " ካለ በነጻነት መሥራትንና ሀብት ማፍራትንም እንዲቀበልና ዜጎች እድሜ ልካቸውን ሠርተው ያፈሩትን ንብረት ያለ ካሳ እያፈረሱ ሕዝብን ማደህየቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም " ሲልም በጥብቅ አሳስቧል።

#እናትፓርቲ

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👏921167😡62🙏50🕊31😭20🤔19😢18😱12🥰10
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC በአረጋዊው መልአከ/መ/ ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌውና አራት ቤተሰባቸው ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግድያን በልዩ  ሁኔታ እንደሚከታተለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አሳውቋል።  በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሉሜ (ሞጆ )  ወረዳ ቤተ ክህነት  በቢቃ ደ/መ/ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ  ለ41 ዓመታት ያህል ከድቁና እስከ…
#እናትፓርቲ

" አንዱን ሰቆቃ ማን ፣ እንዴት ፣ ለምን እንዳደረገው በበቂ ሳይጠናና ጠያቂም፣ ተጠያቂም ሳይኖር ለጥቂት ጊዜያት ዝም ያለና የቆመ ካስመሰለ በኋላ ያለፈውን በሚያስንቅ እልቂቱ ይቀጥላል " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልኳል።

ፓርቲው " በሀገራችን ኢትዮጵያ ሥርዓታዊ የሆነ በእምነት ተቋማት፣ በሃይማኖት አባቶችና ምእመናን ላይ የሚደርስ ጥቃት አቻ በሌለው መልኩ ከዳር ዳር ሲያምሳት ማየትና ምንም እንዳልተፈጠረ በዝምታ ማለፍ የተለመደና በተዘዋዋሪ ይኹንታ የመስጠት የሚመስል ክስተት ከሆነ ዓመታት ተቆጥረዋል " ብሏል።

" የግፉ መጠን ከዕለት ዕለት እየቀነሰ ከመሄድ ይልቅ መልኩንና ቦታውን እየቀያየረ አሰቃቂነቱንም በየወቅቱ የከፋ እያደረገ ቀጥሏል " ሲል ገልጿል።

" አንዱን ሰቆቃ ማን፣ እንዴት፣ ለምን እንዳደረገው በበቂ ሳይጠናና ጠያቂም፣ ተጠያቂም ሳይኖር ለጥቂት ጊዜያት ዝም ያለና የቆመ ካስመሰለ በኋላ ያለፈውን በሚያስንቅ እልቂቱ ይቀጥላል። እንደማኅበረሰብም ጣት መቀሳሰርና አኹን አኹን ደግሞ እልቂትን በጥንቃቄ በመለማመድ ላይ ያለን ይመስላል " ብሏል።

" ባለፈው መስከረም 16/2017 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ሞጆ ወረዳ የቢቃ ደ/መ/ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን የነበሩት ቀሲስ ወልደ ኢየሱስ አያሌው እና 4 ቤተሰባቸው በግፍ በአሰቃቂ ኹኔታ መገደል ተራ ግድያ ሳይሆን በእምነት ተቋማት ላይ ያነጣጠረ፣ ቤተሰብን በሙሉ በአንድ ላይ በመፍጀት ዘር እንዳይተርፍ ጭምር የተወሰደና ቀደም ሲል ከተፈጸሙ መሰል ግድያዎች የጥፋት ደረጃውን ከፍ አድርጎ ያሳየ ጭፍጨፋ ነው " ሲል ፓርቲው ገልጿል።

ፓርቲው " ይኽንና ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት የደረሱ ጥቃቶችና የጅምላ ፍጅቶች በአጋጣሚና በዘፈቀደ እየሆኑ ያሉ ሳይሆን በተጠና መልኩ ሀገርን አጽንተው ባቆሙ ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ላይ ያነጣጠሩና ፈርጀ ብዙ አንድምታ ያላቸው በመጣህብኝ ሰበብ የተጠና ዘር ማጽዳትና ማሳሳት/systemic ethnic cleansing/፣ በቀል/revenge/፣ ማዋረድ/humiliation/፣ የአዲሱን ዓለም አስተሳሰብ/new world order/ ትግበራ አካል እንደሆነ በጽኑ እናምናለን " ብሏል።

" በዓለም ላይ የተፈጸሙ መሰል ድርጊቶች ያለመንግሥት መዋቅር ቀጥተኛም ይኹን ተዘዋዋሪ ተሳትፎ አልተፈጸሙም " የሚለው ፓርቲው " የእኛውም ከዚያ ሊለይበት የሚችል አመክንዮና ዕውናዊ ማሳያ ይኖራል ተብሎ አይታመንም " ሲል ገልጿል።

" እንዲህ ያሉ ድርጊቶች በጥንቃቄና አሻራ በማይተው መልኩ፣ ገፋ አድርጎ ቢሄድም በማዳፈን የሚፈጸሙ ናቸው። እርግጥ ነው የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር የዚኽም ሆነ የቀደሙ ጅምላ ጭፍጨፋዎች ተዋንያን ለፍርድ አደባባይ መቅረባቸው አይቀሬ ነው " ብሏል።

" የእኛን ፓርቲ ጨምሮ መሰል ተቋማትና ግለሰቦች በቀደሙት ጊዜያት በተደጋጋሚ ያሰማነው ዜጎችና ተጋላጭ የሆኑ የሃይማኖት ተቋማት /hotspot areas/ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ያስተላለፍነው ጥሪ ሰሚ በማጣቱ ወይም ሆነ ተብሎ በመታለፉ ዛሬም ጭፍጨፋውና ግድያው በከፋ መልኩ እንደቀጠለ ነው " ብሏል።

" ኢትዮጵያውያን አንዳችን የአንዳችንን ደህንነት እየጠበቅን የእምነት ተቋማቶቻችንን ከሥርዓታዊ ጥቃት ለመታደግ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንቆምና ለተሻለ ጊዜ እንድንተጋ " ሲል እናት ፓርቲ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
669👏139😭77🙏35🤔20😡20🕊14😢7🥰6😱5
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia 🕊 " ሰው በየሄደበት ይገደል ነበር በጣም ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለፍነው አሁን ከሰላም በላይ ምን ጥቅም አለ ? ሰላምን የሚበልጥ ነገር የለም ! " - ነዋሪዎች 🟢 " ክልሉን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለማምጣት እንዲህ ያሉ እምርጃዎች ይበረታታሉ " - አቶ ሽመልስ አብዲሳ " የሰላም ስምምነቱን የተቀበልነው የህዝባችንን ስቃይ ከተመለከትን በኃላ ነው፤... ስምምነቱ ለኦሮሞ ህዝብ ትልቅ እፎይታ…
" በመርሕ ደረጃ መጥፎ ሰላም ጥሩ ጦርነት ባይኖርም የስምምነቶች ግልጽነት ማጣት ውጤቱን የተገላቢጦሽ ሊያደርገው ይችላል ! " - የትብብሩ ፓርቲዎች

መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄና እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግለጫ ልከዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ " አገራችን በሰላም እጦት፣ ሕዝባችን ለዓመታት በዘለቀ ጦርነት ቁምስቅሉን እያየ እንዳለ ምሥክር መቁጠር አይሻም። " ብለዋል።

" በተለይ በብዙ ተስፋና ጉጉት ተጠብቆ የነበረው ' ለውጥ ' የኋልዮሽ መሄድ ከጀመረ ወዲህ ሰላም ማደር ብርቅ፣ ፍጅትና ትርምስ ጌጣችን ከኾነ ሰነበተ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ከዚህ ቀደም ኤርትራ በረሃ ከኦነግ ጋር በክልል አመራሮች ደረጃ ግልጽነት የጎደለው ስምምነት ከተደረገ በኋላ ሕዝብ ደስታውን ሳያጣጥም የሰላም ተፈራራሚው ኃይል " ቃል የተገባልኝ አልተፈጸመም " በሚል ሰበብ ተመልሶ ጫካ ከገባ ወዲኽ እንደ አገር ባጠቃላይ በተለይም ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ያየው ቁምስቅል ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሰሞኑ መንግሥት ' ኦነግ ሸኔ ' እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት የተወሰነ ቡድን ሰላም መፈረሙ በመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን በስፋት መዘገቡን የገለጹት ፓርቲዎቹ " መጥፎ ሰላም የለም በሚል ጥቂቶች እንኳን የሰላም አካል መኾናቸውን በበጎ የምንመለከተው ነው " ብለውታል።

ከዚኹ ጋር ተያይዞ " የታጣቂ ቡድኑ መሪ ናቸው የተባሉ ግለሰብና የተወሰኑ ወጣቶች ከክልል አመራሮች ጋር ስምምነት ሲፈራረሙ ታይተዋል " ብለዋል።

" ከስምምነቱ ማግስትም አዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለሦስት ቀናት በዘለቀ ተኩስ ስትናጥ ከርማለች " ያሉት ፓርቲዎቹ " በተኩሱ እስከ አኹን አንዲት እናት በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን አረጋግጠናል " ብለዋል።

ይኸው ድርጊት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እንደተከሰተ ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሂደቱ ጥርጣሬን እንዳጫረባቸው ጥርጣሬያቸው የሚነሳውም ከስምምነቱ ግልጸኝነት ማጣት ብቻ ሳይሆን ከእንዲህ ዓይነት ክስተቶች ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

" ስምምነቱ መሣሪያ ማውረድን አይጨምርም ወይ ? " ያሉት ፓርቲዎቹ " የከተማ አስተዳደሩ ርችት እንኳን እንዳይተኮስ ሲከለክል እንዳልከረመ እንዴት ሙሉ ትጥቅ ተይዞ መግባትንና ለቀናት ጭምር የድልነሺነት ብሥራት በሚመስያመስል መልኩ ተኩስን ሊፈቅድ ቻለ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ ፦

° ' ከተማ ውስጥ ኹከት ለመፍጠር የመጡ ' በሚል በመታወቂያ ማንነት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው የመጡ ነብሰ ጡሮችና አረጋውያን ጭምር ከአዲስ አበባ መግቢያ ክብረ ነክ በኾነ መንገድ ሲመልስ የነበረ ኃይል አኹን የት ሄዴ ?

° ከዚኹ መሐል ሲገድል ሲቀማ የነበረ በውል ተጣርቶ ተጠያቂነት አይኖርም ወይ ?

° መንግሥት የሰላም ስምምነት ፈጸመ ከተባለው ግለሰብና ቡድን ጋር ከዚኽ ቀደም የነበረው ግንኙነት ምን ነበር ?

° ታንዛኒያ ድረስ ኹለት ጊዜ አድካሚ ሙከራዎች ተደርገው ጫፍ እየደረሱ የተናፈቀው ሰላም ሲጨነግፍ በአቋራጭ አዲስ አበባ እውን የኾነበት ተዓምር ምን ቢኾን ነው ?

° የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ ሥነልቡናዊ ጫና እንዲደርስበት ታስቦ ተሠርቷል ወይ ? የሚሉ ጥያቄዎችን ፓርቲዎቹ አንስተዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ የለአንድም ቀን እንኳን ሰላም መስፈን እጅጉን እንሻለን ብለዋል።

" የአንድም ሰው የሰላምን መንገድ መምረጥ ያስደስተናል " ሲሉ አክበላለዋል።

" በአንጻሩ ደግሞ በሂደቱ ዙሪያ የግልጽነት አለመኖርና የሰላሙ ዘላቂነት እጅግ ስለሚያሳስበን አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲኖሩ ማንሳት በጎ ይመስለናል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ፦

➡️ የሰላም መጥፎ የለውምና የተደረሰውን ስምምነት ከነገዘፉ ችግሮቹ በበጎ እናየዋለን ብለዋል።

➡️ መንግሥት የስምምነቱን ሂደትና ዝርዝር ነጥቦች የመከራው ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ በአጽንኦት አሳስበዋል።

➡️ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ለቀናት የዘለቀው ተኩስ፣ በሰላም ስምምነት የመጣ ሳይኾን ኾን ተብሎ የሕዝብን ሥነ ልቡና ለመስለብና ለማስፈራራት የተደረገ መኾኑን ሕዝባችን እንዲያውቀው እንሻለን ብለዋል።

➡️ በዚኹ የተኩስ እሩምታ ሰበብ መገናኛ አካባቢ ለተገደሉት እናት መንግሥት ሓላፊነት የሚወስድ ኾኖ ቢያንስ ቤተሰባቸውን ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቅና ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን ብለዋል።

➡️ መንግሥት ከሽርፍራፊ ደስታና ማስመሰል ወጥቶ ዘላቂ ሰላምን በሰጥቶ መቀበል መርኅ በገለልተኛ ታዛቢዎች አማካይነት ድርድር ለማድረግ ፈቃደኝነቱን በመግለጽና ለዚህም ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ደም አፋሳሽ ጦርነቶች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኙ፣ በአፋጣኝም ተኩስ አቁም እንዲታወጅ በአጽንዖት አሳስበዋል።

#እናትፓርቲ
#መኢአድ
#ኢሕአፓ
#ዐማራግዮናዊንቅናቄ

@tikvahethiopia
887👏330🕊82😡62😭36🙏32🤔17😢15😱11🥰10
#እናትፓርቲ

እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የጣሪያ ግድግዳ/ ንብረት ግብር መመርያ እንዲቆም የመሠረተው ክስ በፍርድ ቤት ተቀባይነት አግኝቶ መመሪያው "ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም" ሲል ፍርድ ቤት ጥር 9 ቀን ብይን መስጡቱን ፓርቲው አስታውቋቃ።

ፓርቲው የወጣው መመርያ " ሕግን ባልተከተለ መንገድ እና የከተማ አስተዳደሩ ባልተሰጠው ሥልጣን የወጣ በመሆኑ " መመሪያው እንዲሻሻል ሲል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት ክስ መስሮቶ መቆየቱን ገልጿል።

ፍ/ቤቱ የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ያቀረባቸውን ሦስት መቃወምያዎች ውድቅ አድርጎ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ከገባ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ መመሪያው " ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም " የሚል ውሳኔ መስጠቱን፤ የውሳኔውን አፈጻጸም እንደሚከታተልም ፓርቲው አስታውቋል።

(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
2.64K👏1.3K🥰439🙏192🤔41🕊38😢25😭23😡20😱15
#እናትፓርቲ

" አማራ ክልል በተሟላ ጦርነት ውስጥ ነው። በየቀኑ ሰዎች በድሮን ጭምር ይጨፈጨፋሉኮሚሽኑና መንግስት ደግሞ ' የለም እየሞትክም ተመካከር' ' ይላሉ ! " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ባደረገው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ያልተሳተፈበትን ምክንያትና የኮሚሽኑን አካሄድ በተመለከተ የሰላ ትችት ሰንዝሯል።

Q.
በክልሉ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ያልተሳተፋችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? ኮሚሽኑ ‘ይምጡ በራችን ክፍት ነው’ ይላል፤ እናንተ ደግሞ እየተሳተፋችሁ አይደለምና ልዩነቱ ምንድን ነው? መፍትሄውስ?

እናት ፓርቲ ፦

"
ግልጽ ነውኮ! ክልሉ በተሟላ ጦርነት ውስጥ ነው ያለው፡፡ በየቀኑ ሰዎች በድሮን ጭምር ይጨፈጨፋሉ፡፡ በአጠቃላይ ከባድ ውድመት እየደረሰ ነው፡፡

በክልሉ ለሚሊዮን የሚጠጉ ተፈናቃዮች፤ በብዙ ቦታዎች ከፍተኛ ድርቅና ሰው ሰራሽ ረሃብ አለ፡፡ ለሕዝቡ ጥቅም ሊሟገቱ የሚችሉ በርካታ ምሁራንና ፖለቲካኞች በእስር ናቸው ወይም ተሰደዋል።

በየሳምንቱ ዜጎች እየታገቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ይጠየቅባቸዋል፡፡ በክልሉ እንኳን ምክክር ሊያስደርግ የሚችል አውድ ገበያ ወጥቶ ቤት ለመግባት፣ ነብሰጡርን ሀኪም ቤት መውሰድ፣ ህፃናትን ትምህርት ቤት መሄድ፣ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስም ብርቅ ሆኗል፡፡

ማህበረሰቡ 'የህልውና ችግር ገጥሞኛል በቅድሚያ እሱን ፍቱልኝ' (quick fix) እያለ ነው፡፡ ኮሚሽኑና መንግስት ደግሞ 'የለም እየሞትክም ተመካከር” ይላሉ።

በእነዚህ አበሳዎች ውስጥ ያለን ማህበረሰብ ነው ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል 'ናና  አዲስ ማኅበራዊ ውል ለሚፈራረምበት ምክክር አጀንዳ አዋጣ'፣ ተመካከር' የሚባለው?

ኮሚሽኑ ከነችግሩ መጀመሪያ የነበረውን አቋም ወደመያዝ መመለስ አለበት፡፡ ኮሚሽኑ ለመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያነት እየዋለ ነው። እንደዚያ መሆናቸውን ያቁት ይሆን አይሆን እርግጠኞች አይደለንም።

መፍትሄው፥ በአጠቃላይ ከምክክሩ በፊት ድርድር መቅደም፤ ተኩስ መቆም አለበት፡፡ ጦርነቱ ፖለቲካዊ መፍትሄ ያሻዋልል።

የኮሚሽኑ ሰዎች ያ እንዲሆን ባላቸው ተጽዕኖ በጎ አስተዋጽዖ ቢያሳራፉ ውለታም ጭምር ነው፤ ካልሆነ ግን ቢያንስ በሰው ቁስል እንጨት ከመስደድ ቢቆጠቡ እንመክራለን” ብሏል።

Q. በአማራ ክልል አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት እንደማትሳተፉ ገልጻችሁ ለነበረው በተለይም "ቅድሚያ ጦርነት ይቁም" የሚለውን ሀሳባችሁን ኮሚሽኑ ምላሽ ሰጠበት ? 

እናት ፓርቲ ፦

" እንደማንሳተፍ የሚገልጸውን ደብዳቤ ለኮሚሽኑ ከላክንና ለህዝብ ይፋ ካደረግን በኋላ በሚዲያዎች በኩል በተወሰወነ ደረጃ መልስ የሚመስል ነገር ሰጥቷል።

ሀሳቡ የሚጣል እንዳልሆነና በጊዜ ሂደት (እስከዚያው) የተጠቀሱ ችግሮች ይፈታሉ ብለው እንደሚያምኑ የሚያወሱ ነበሩ፡፡ 

ከሦስት ሳምንታት በፊትም ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር በባሕር ዳር ተገኝተው በተወያዩበት ወቅት እኛ ያነሳናቸውን፥ መንግስት በራሱ ተነሳሽነት ተኩስ አቁም እንዲያውጅ፣ እስረኞችን እንዲፈታ የሚሉትን ቅድመ ሁኔታዎች አንስተዋቸዋል።

ግን አጠንክረው አልዘለቁባቸውም፤ አይዘልቁባቸውም፡፡ "

Q. ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ አጀንዳ ማሰባሰብ ሲጀምር ተሳትፋችሁ ነበር፤ ከዚያ በኋላስ በሌሎች ክልሎች (ለምሳሌ በኦሮሚያ) ተሳትፋችሁ ነበር ?

እናት ፓርቲ ፦

"አዎ ተሳትፈናል፡፡ በአጠቃላይ የፓርቲያችን እምነት በዋናው ምክክር ላይ ቅድመ ሁኔታዎች ቢኖሩንም በአንጻራዊነት ለመመካከር የምትሆን ክፍተት ከተገኘች ለዚህ አገር ከምክክር የተሻለ መፍትሄ ይኖራል ብለን አናምንም፤ ያንንም ከማንም በላይ ስናቀነቅን ቆይተናል፡፡ 

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መነሳትን ጨምሮ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው የመነመነም አስቻይ ሁኔታ አለ ብለን ስላመንን አድርገነዋል፡፡"

Q. በአማራ ክልል በነበረው ሂደት ኮሚሽኑ ምን ክፍተቶችን ቢያስተካክል አሁንስ አጀንዳችሁን ታስረክባላችሁ ? ነው ወይስ ከዚህ በኋላ አጀንዳ የማስገባት እቅዱ የላችሁም? ከሌላችሁ ለምን ? 

እናት ፓርቲ

" የእኛ የቅድሚያ ቅድሚያ ጉዳይና ሆድ ቁርጠት የህዝብ ደህንነትና በሰላም ወጥቶ የመግባት ሁኔታ ነው።

የመሳሪያ ድምጽ በቅድሚያ ፀጥ ይበል፣ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ በአንድም በሌላም ከምክክሩ ራሳቸውን ያገለሉ ኃይሎች እንዲመለሱ ይደረግ። በተለይ አሁን አሁን ደግሞ የኮሚሽኑ ለመንግስት ያደላና ፖለቲካዊ ዝንባሌ ያለው አካሄድ ካልተስተካከለ አጀንዳ ማቀበሉንም አናደርገውም ከዋና ምክክሩም ለመግባት ይቸግረናል።

ኳሱ እነርሱ እግር ላይ ነው፡፡ እንዲያውም አሁን አሁን አንድ ሥጋት እየጫረብን የመጣ ጉዳይም አለ፡፡ ምን አልባት እንዲህ እያጓተቱ ምርጫ 2018’ን ለመጋፋት እንዲውል ሊያደርጉት ይሆን? የሚል። " 
 
Q. የምክክር ኮሚሽኑ በተለያዬ ክልሎች ያካሄዳቸውን አጀንዳዎች የማሰባሰብና የመረከብ ሂደቶች እንዴት ገመገማችኋቸው ? ምንስ መስተካከል አለበት? ምንስ ጥሩ ጎን አለው ?

እናት ፓርቲ ፦

" በአጠቃላይ በጣም ጥሩ ባይባልም መጥፎ የሚባል አልነበረም፡፡ እንዲነሱ የያዝናቸው አጀንዳዎች በተለያዩ አካባቢዎችና የማኅበረሰብ ክፍሎች ጉዳይ ሆነው ሲነሱ ታዝበናል፡፡ አብዛኛው ሰው አዲስ ማኅበራዊ ውል ሰርተን የተሻለች ሀገር እንድትኖረን የመናፈቅ ነገሩ ይታያል።

በአንጻሩ በርካታ ለብልጽግና ታማኝ የሆኑ ሰዎች እንዲሳተፉ የማድረግ፣ በአንዳንድ ቦታዎችም ጭሬ ላፍሰው ዓይነት አካሄዶችን ታዝበናል፡፡ ወደ ፊት የመራመድ ጥማት ሳይሆን ወደ ኋላ የመመለስና የብጥበጣ ዓይነት አዝማሚያም አስተውለናል፡፡

ኢትዮጵያን ከስሟ ጀምሮ ክዶ የመነሳትና ፖለቲካ ወለድ ጉምዠታና የኔ፣ የኔ ዓይነት ነገሮች ነበሩት፡፡ ኮሚሽኑን ደጋግመን እንዳሳሰብነው የማይታለፉ ቀይ መስመሮች ይኖሩታል ብለን እናምናለን።

ምክክር ያስፈለገው ከነበረው የተሻለ ለመጨመርና ጥሩ ለማድረግ እንጂ ጭራሽ ያለንንም ለማጣት እንዳልሆነ ማስታወስ አይከፋም" ብሏል።

(ፓርቲው በአማራ ክልል ጉዳይ ስላነሳው ሀሳብ በቀጣይ ይቀርባል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
👏581102😡52😭25🕊23🙏18🤔16😢8😱5🥰4
#እናትፓርቲ #ምርጫቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ " እናት ፓርቲ በአዋጅ እና በመመሪያ ከተደነገገው ውጭ የፋይናንስ አስተዳደሩን እየመራ እና እያስተዳደረ ይገኛል " በማለት በዚህ አመት የሚሰጠውን የመንግስት የፋይናንስ ድጋፍ ሊያገኝ አይገባውም ሲል ውሳኔ አሳልፏል።

ከዚህ በተጨማሪ የፖርቲውን የባንክ ሒሳብ ወጪ ሆኖ ከታለመለት አላማ ውጪ የመንግስት ድጋፍ ገንዘብ እንዲውል አድርገዋል ባላቸው ሒሳቡን በጣምራ የሚያንቀሳቅሱት የፓርቲው አመራሮች ፦
- ዶ/ር ሰይፈሥሰላሴ አያሌው የፓርቲው ፕሬዚደንት፤
- ወ/ሪት ሜሮን ታደለ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ
- ወ/ሪት ኩሪ አሠፋ የፓርቲው የሂሳብ ክፍል ኃላፊ ላይ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ተገቢውን ምርመራ እንዲያደርግ የወሰነ መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።

ቦርዱ ተገኙ ያላቸው የፋይናንስ ግኝቶች ምንድናቸው ?

እናት ፖርቲ ከመንግስት ስለአገኘው የ2016 የበጀት ድጋፍ ሂሳቡን በራሱ የውጭ ኦዲተር አሰርቶ ሪፖርት ለቦርዱ ማቅረቡን አመልክቷል።

በፖርቲው የተሰየመው የውጭ ኦዲተር በኦዲት ሪፖርቱ ላይ ፦

ፓርቲው ከአባላት ለሰበሰበው መዋጮ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ያለመስጠቱን በዚህ ምክንያት በሶስት ባንኮች ላይ የሚገኘውን 65,315ብር ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉን፤

ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወጪ የሆኑ ገንዘቦች ህጋዊ በሆኑ የወጪ ደረሰኞች አለማስደገፉን ፤

ፓርቲው ለዕርዳታ በሚል ወጪ አድርጎ ብር 158,425 መክፈሉን ይገልጻል።

ቦርዱ ከላይ የተገለፁት ግኝቶች ከውጭ ኦዲተሩ ሲቀርብለት እንዲሁም የፓርቲው አባላት ጥቅምት 3/2017 ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ የፓርቲው ፋይናንስ አስተዳደር ችግር ላይመሆኑን ጠቅሰው ተገቢው ማጣራት በቦርዱ እንዲደረግ በመጠየቃቸው ጉዳዩን የፌደራል ዋና አዲተር መ/ቤት እንዲያየው ማድረጉን አስረድቷል።

የፓርቲው አባላት ያቀረቧቸውን ቅሬታዎች እና የፓርቲው የውጭ ኦዲተር የዘረዘሯቸውን ግኝቶች የያዘውን የኦዲት ሪፖርት ለፌደራል ዋና ኦዲተር በመላክ ፓርቲው ከመንግስት ያገኘውን ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ መዋል /አለመዋሉን አጣርቶ እንዲገልጽ መጠየቁን አመልክቷል።

የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤትም የፓርቲውን የመንግስት በጀት ድጋፍ ኦዲት አድርጎ ውጤቱ እንዳሳወቀው ገልጿል።

በዋና ኦዲተር የኦዲት ሪፖርቱ ላይ የታዩት ግኝቶች በዋናነት ምንድናቸው ?

🔴 ፓርቲው በአዋጅ እና በመመሪያ ከመንግስት የተሰጠውን የበጀት ድጋፍ በተለየ የሒሳብ መዝገብ በየወጪ አርእስቱ ዘርዝሮ መያዝ እንዳለበት ቢደነግግም የሒሳብ መዝገብ እንደሌለው፤ የሒሳብ ማመዛዘኛ ሪፖርት እና የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ እንዳላዘጋጀ እንዲሁም ከቦርዱ የተሰጠውን ድጋፍ ወጪ ሲያደርግ በተለየ የሂሳብ መዝገብ በየወጪ አርእስቱ ዘርዝሮ ሳይዝ የተፈፀመ መሆኑን ይገልጻል።

🔴 ለማህበራዊ አገልግሎት በሚል ፖርቲው ከመንግስት ያገኘውን የበጀት ድጋፍን ከታለመለት ተግባር ውጪ አውሎ እንደተገኘ ይኸውም፦
• በጎፋ ዞን ለተከሰተው የመሬት መንሸራተት እርዳታ እንዲውል ሐምሌ 25/2016ዓ/ም በወጪ ማዘዣ 000098 ብር 20ሺ ማውጣቱን፤
• ለአቶ ዳዊት ብርሀኑ መሸኛ የሚውል መስከረም 18/2017ዓ/ም በወጪ ማዘዣ 000121 15 ሺ ወጪ ማድረጉን፤
• ለአቶ ተመስገን ሹመት የሐዘን በሚል ሐምሌ 25/2016ዓ/ም በወጪ ማዘዣ 000044 3,500ብር ወጪ ማድረጉን በድምሩ 38,500 ብር ከታለመለት አላማ እና ተግባር ውጪ ያወጣ መሆኑን ይገልጻል።

🔴 በተለያዩ ጊዜያት ለ13 ቅ/ጽ/ቤቶች በባንክ ቤት በኩል በዝውውር የላከው ብር 438,500ብር ለምን ተግባር እንደዋለ የወጪ ደጋፊ ሰነድ ተያይዞ ያልቀረበ መሆኑን ይህንንም ግኝት በተመለከተ የፖርቲው ፕሬዚደንት ሲጠየቁ የሰጡት መልስ አሳማኝ ያለመሆኑን ገልጿል።

በዚህም ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ከመንግስት የተመደበለትን ድጋፍ ከታለመለት አላማ ውጭ እንዳዋለው መገንዘቡን አሳውቋል።

በዚሀ አመት የሚሰጠውን የመንግስት ድጋፍ ሊያገኝ አይገባውም ሲልም ወስኗል።

የፓርቲውን ባንክ ሒሳብ በጣምራ ሚያንቀሳቅሱት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ላይ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምርመራ እንዲያደርግ የወሰነ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

(የእናት ፓርቲ ምላሽ በቀጣይ ይቀርባል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
😡393110🤔24👏19😭13🙏10🕊7😱6😢6🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#እናትፓርቲ #ምርጫቦርድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ " እናት ፓርቲ በአዋጅ እና በመመሪያ ከተደነገገው ውጭ የፋይናንስ አስተዳደሩን እየመራ እና እያስተዳደረ ይገኛል " በማለት በዚህ አመት የሚሰጠውን የመንግስት የፋይናንስ ድጋፍ ሊያገኝ አይገባውም ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ከዚህ በተጨማሪ የፖርቲውን የባንክ ሒሳብ ወጪ ሆኖ ከታለመለት አላማ ውጪ የመንግስት ድጋፍ ገንዘብ እንዲውል አድርገዋል ባላቸው ሒሳቡን…
#እናትፓርቲ

" በጀት በመከልከልና በማስከልከል የሚደናቀፍ ትግል አይኖርም ! " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፓርቲው ላይ ያሳለፈውን የበጀት ክልከላ " ፖለቲካዊ ውሳኔ " ሲል ጠርቶት አውግዟል።

" በጀት በመከልከልና በማስከልከል የሚደናቀፍ ትግል የለም "ም ብሏል።

እናት ፓርቲ ምን አለ ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር በጻፈው እና ለፓርቲው ግልባጭ በተደረገ ደብዳቤ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ለፓርቲው በ2016 ዓ.ም የተሰጠን ድጋፍ ብር 1,702,561.65 (አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ኹለት ሺህ አምስት መቶ ስድሳ አንድ ከ65/100) ኦዲት ማድረጉን አመልክቷል።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በቀጥታ የኦዲት ሪፖርቱን ለኦዲት ተደራጊ እናት ፓርቲ እንዳላደረሰና ሪፖርቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ፓርቲው ጋር መምጣቱን ገልጿል።

የኦዲት ግኝት ተብሎ በዋነኛነት የቀረበውና ትልቅ ጥያቄ ያስነሳው ፓርቲያው ከተደረገለት ድጋፍ ፦

- በጎፋ ዞን ለተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) መለገሱ ፤
- ለአንድ የፓርቲው ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ስንብት ለማስታወሻ ብር 15,000.00 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) ወጪ ማድረጉ፤
- የፓርቲያው የላዕላይ ምክር ቤት አባል ከዚኽ ዓለም በሞት በተለዩበት ወቅት ለባነር ማሠሪያ የወጣ ብር 3,500.00 (ሦስት ሺህ አምስት መቶ ብር) በድምሩ ፓርቲው ብር 38,500.00 (ሠላሳ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር) " ከታለመለት ዓላማ እና ተግባር ውጭ ያወጣ መኾኑ" መመላከቱን አስረድቷል።

በዚህም ምክንያት ቦርዱ በዚህ ዓመት ፓርቲው የሚሰጠውን የመንግሥት ድጋፍ ሊያገኝ እንደማይገባ መወሰኑን ፤ የፓርቲውን ሂሳብ በጣምራ በሚያንቀሳቅሱት 3 አመራሮች ላይ ፌዴራል ፖሊስ ምርመራ እንዲያደርግ መወሰኑን በደብዳቤ እንደገለጸለት ጠቅሷል።

እናት ፓርቲ የቦርዱ ውሳኔ " አላግባብ ወጣ " ስለሚለው 38,500.00 ብር ሳይሆን ከጀርባው ሌላ ጉዳይ እንዳለው እገምታለሁ ብሏል።

" አላግባብ ወጣ " የተባለው ወጪ ፦

ብር 20,000 የመሬት መንሸራተት ለደረሰባቸው ወገኖች የወጣ እጅግ አነስተኛ ገንዘብ መሆኑና ይህም የነገ መራጮቹን ጎን ለሚጠይቀው የስብዕና ሞራል መቆም ከማስፈለጉ አኳያ ሊደረግ ከሚችል በጣም አነስተኛው ነገር እንደሆነ፤

ምንም ክፍያ ሳይከፈላቸው ለሀገራቸውና ሕዝባቸው ለመታገል ጊዜያቸውንና መላ እነሱነታቸውን ሰጥተው ለአደጋ ጭምር ራሳቸውን አጋልጠው የመጓጓዣ ወጪያቸው እንኳን ሳይሸፈን ለሀገር ከመቆም አኳያ በፓርቲው ከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ ከፓርቲው በሞት እንዲኹም በአካል ሲለዩ ወጣ የተባለው ወጪ እዚህ ግባ የማይባል መሆኑንና ከአግባብ ውጭ የወጣ ነው ብሎ እንደማያምን ገልጿል።

ከፓርቲው አመራር ቀብር ጋር ከተያያዘው ብር 3,500 ውጪ ሌሎቹ የተፈጸሙት ወጪዎች በፓርቲው ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚና መላ መዋቅሩ ውሳኔ መሠረት እንደሆነ ጠቁሟል።

ይህ ሆኖ ሳለ " አመራሮችን በተለየ መልኩ ተጠያቂ ለማድረግ የተኬደበት ርቀት ትናንት የፓርቲ አመራሮችና አባላት እሥርና አፈና ሲገጥማቸው ባሉበት ድረስ በመሄድ ያጽናና እና ለማስፈታት ግብ ግብ ይገጥም የነበረ ቦርድ በቅጽበት እንዲህ የመውጊያ ስለት አቀባይ ወደመሆን ያሽቆለቆለበት ቅጽበት ያስገርማል፣ ያሳዝናልም። የኢትዮጵያ ሕዝብም ይመዘግባል " ብሏል።

የተጠቀሰው ገንዘብ ፓርቲው በድጋፍ ከተሰጠው ገንዘብ ወጪ እንዲደረግ ያስገደደው ምክንያት በወቅቱ ፓርቲው ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚጠቀምበትና ከአባላትና ደጋፊዎች የሚሰበሰብ ገንዘብ ከተቀመጠበት የባንክ ሒሳብ ማንቀሳቀስ ባለመቻሉና ገንዘቡ በወቅቱ ወጪ መደረግ የግድ ስለነበረ እንደሆነ አመልክቷል።

ነገር ግን የማኅበራዊ አገልግሎት የባንክ ሂሣቡን ማንቀሳቀስ በቻለበት በአሁኑ ሰዓት ግን የተጠቀሰውን በውንጀላ የተያዘበትን ገንዘብ ብር 38,500 አዛውሮ ዝግጁ ያደረገና ለመመለስም የሚችል መሆኑን ለፌዴራል ዋና ኦዲተር በፈረመው መተማመኛ ጽሑፍ መስጠቱን ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፓርቲው ጉዳዩን ቀለል አድርጎ ወደሥራው ባተኮረበት ወቅት ከዚህ ቀደም ' ፓርቲውን ከመፍረስ ለመታደግ በሚል ከፓርቲው የተቆረጠ ኃይል " ፓርቲውን በጀት አስከለከልኩ" ፣ " እነ እከሌንና እከሊትን ላሳስር ነው " እያለ ለተለያዩ ግለሰቦችና ሚዲያ አካላት ወሬ እየነዛ መመልከቱን በዚህም " በሬ ከአራጁ " ለማለት መገደዱን ገልጿል።

ይህን አካል ከነዝርዝር ማንነቱ በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ጠቁሟል።

ፓርቲው የመንግሥትን ሥልጣን በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ለመጨበጥ እንደሚሰራ ገልጾ የገንዘብ አጠቃቀምን በተመለከተ እያንዳንዷ ሳንቲም ተጠያቂነት ባለው መልኩ ብቻ መውጣት እንዳለባት እንደሚያምን ለዚህም ተግቶ እንደሚሰራ ፤ ኦዲት መደረጉም እንደሚያስደስተው ገልጿል።

ነገር ግን የኦዲት ግኝት ተብሎ ነቀረበውና ቦርዱ ያሳለፈው ውሳኔ ከአስተዳደራዊ ውሳኔነቱ ይልቅ ፖለቲካዊ ግብ ያዘለ ነው ብሎ እንደሚያምን አመልክቷል።

" በቦርዱ ውሳኔ ላይ ዕለት ከዕለት የሚያስጨንቀንና ዘወትር የምንጮኽለት ወዲኽም ግራ ቀኝ ጥርስ ያስነከሰብን የሕዝባችን ስቃይ ከቀለለና ጊዜ ከተረፈን እንደአስፈላጊነቱ ሕጋዊ መንገድ ተከትለን ይግባኝ እንልበት ይሆናል " ብሏል።

ፓርቲው አለኝ ባለው መረጃ እንዳይሰጠው የታገደው የ2017 የበጀት ድጋፍ ብር 600 ሺህ ገደማ መሆኑን ጠቁሟል።

" በጀት በመከልከልና በማስከልከል የሚደናቀፍ ትግል አይኖርም " ሲልም አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
541😡60👏53🙏31🕊17😭11🤔10😱1😢1