TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል🔝

ከላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መካከል በጥገና ላይ የቆየው ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ዛሬ #ተመርቋል፡፡

ከላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት መካከል የመሰንጠቅና የጣሪያ ማፍሰስ ችግር አጋጥሞት የነበረው ቤተ ግልጎታ ሚካኤል ከአሜሪካ አምባሳደር ፈንድ እና ከዓለም ሞኑመንት ፈንድ በተገኘ 700 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ነው ጥገና የተደረገለት፡፡

የጥገና ሥራው ወደፊትም የሚቀጥል ሲሆን በመጠለያ የሚገኙ ቅርሶችን በመጠገን ወደፊት መጠለያዎቹን
ለማንሣት እንደሚሠራ ከቅርስ
ጥበቃ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ሙሉ ጥገና ለማድረግ እስከ 300 ሚለዮን ብር እንደሚያስፈልግ ከዚህ ቀደም በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡

አምባሳደር ማይክል ራይነር ለቅርሱ እድሳት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ቤተክርስትያኗ ካባ አበርክታላቸዋለች፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AU🔝

#በአፍሪካ_ህብረት በሚካሄደው የ32ኛው የመሪዎች ስብሰባ ላይ የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሀውልት ዛሬ የካቲት 03 ቀን 2011.ዓ.ም በይፋ #ተመርቋል፡፡ በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበራቸው ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በህብረቱ ግቢ ውስጥ የቆመላቸው ሀውልት #ከነሃስ የተሰራ ነው፡፡

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia