#update የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የሚድሮክ #ለገደምቢ_የወርቅ_ማምረቻ ኩባንያን ዕገዳ እንደተነሳ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች #በዝግ ስብሰባ ገልፀዋል ተብሎ የሚነገረው ዘገባ ሐሰት ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#update የእነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የምርመራ ጉዳይ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፖሊስ ምርመራ ቡድን የጠየቁት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ረፋድ ባስቻለው ችሎት የመርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን የተጨማሪ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ አደርጓል፡፡ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም ድረስም ክስ እንዲመሠርት…
#BAHIRDAR
ዛሬም ችሎቱ #በዝግ የታየ ሲሆን፣ የፍርድ ቤቱን ድርጊት የተቃወሙ የባህርዳር ነዋሪዎች ሰልፍ አድርገዋል። ፖሊስ ተቃውሞ በሚያሰማው ህዝብ ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል።
Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬም ችሎቱ #በዝግ የታየ ሲሆን፣ የፍርድ ቤቱን ድርጊት የተቃወሙ የባህርዳር ነዋሪዎች ሰልፍ አድርገዋል። ፖሊስ ተቃውሞ በሚያሰማው ህዝብ ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል።
Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AU2022Summit
ህብረቱ በዝግ እየመከረ ነው።
35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት #በዝግ በተለያዩ ጉዳዮች እየመከረ ይገኛል፡፡
በአህጉሪቱ ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በተከናወኑ ስራዎችና በተገኙ ውጤቶች ዙሪያ ነው በዝግ እየመከረ የሚገኘው።
ዛሬ ምሽት ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ዶ/ር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለአፍርካ ሀገራት መሪዎች የእራት ግብዣ እንደሚያደርጉ ኢብኮ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

👍339👎95👏16😢8❤4
#Ethiopia
- ከደቡብ አፍሪካ ፣ ፕሪቶሪያ የቀጠለው የናይሮቢው የሰላም ውይይት ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ይጠናቀቃል ተብሎ ቢጠበቅም ውይይቱ እስከ ትላንት ሀሙስ ድረስ መቀጠሉን ለጉዳዩ ቅርበትና መረጃው ያላቸው አካላት ተናግረዋል።
እስካሁን ውይይቱ ስልተደረሰበት ደረጃ ምንም ይፋ የሆነ መረጃ የለም።
#በዝግ እየተካሄደ በመሆኑ ሚዲያዎችም ስለጉዳዩ መረጃ ለማግኘትም ሆነ ለመናገር እድል አላገኙም። በውይይቱ ፍፃሜ ላይ ስለተደረሰበት ደረጃ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የፖለቲካ ተደራዳሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እየተካፈሉበት ያለው የናይሮቢው የሰላም ውይይት #አጀንዳዎች ናቸው ከተባሉት መካከል ፦
👉 የሰላም ስምምነቱን ሂደትና አፈፃፀም መከታተል፣
👉 የህወሓት ኃይሎችን ትጥቅ ስለማስፈታት፣
👉 በትግራይ ክልል ለወራት ተቋርጦ የነበረውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ስለማስቀጠል፣
👉 የመሠረታዊ አገልግሎቶች መልሶ ስለማስጀመር ይገኙበታል።
- የሰላም ስምምነቱ ተፈፃሚነት ላይ በኬንያ ፣ ናይሮቢ እየተመከረ ባለበት በአሁን ወቅት የኤርትራ ኃይሎች #በትግራይ ውስጥ መጠነ ሰፊ ዘረፋ ፣ አፈና ፣ ግድያ ፣ ጥቃት እየፈፀሙ ነው ሲሉ ከህወሓት አመራሮች መካከል ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት በትዊተር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።
በሽረ አካባቢ የኤርትራ ኃይሎች ሲቪሎችን / ሴቶችን ጨምሮ በዘረፋ ላይ ተሰማርተው ታይተዋል ያሉ ሲሆን በከተማው ከሰዓት እላፊ በኃላ በጨለማ ሁሉንም ክፉ ነገር እያደረጉ ነው ብለዋል።
ይህንን መልዕክት ካሰራጩ በኃላ በናይሮቢ የሚገኙት የህወሓት ተደራዳሪ እና የሰላም ስምምነቱ ፈራሚ አቶ ጌታቸው ረዳ መልዕክቱን " ክንደያ ትግራይ ናቸው " ሲሉ አጋርተዋል።
አቶ ጌታቸው ይህንን ከማለት በዘለለ ምንም ዝርዝር ነገር አልፃፉም።
- አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ትላንትና ለሊት ባሰራጫችው ፅሁፍ ፤ " አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በናይሮቢ እንደተናገሩት ፤ በፕሪቶሪያ እንደተደረሰው ስምምነት በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ የሰብዓዊ እርዳታ ያለምንም እንቅፋት ይገባል ብለዋል " ብላለች።
አሜሪካ ፤ " በትግራይ፣ አፋርና አማራ የሚገኙ የተቸገሩ ኢትዮጵያውያን አሁኑኑ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል " ስትል ገልፃለች።
#የመሰረታዊ_አገልግሎቶች ወደ ነበረበት መመለስ ፣ የሲቪሎች ጥበቃ እና የሰብአዊ መብቶች ተጠያቂነትን ያነሳችው አሜሪካ ስምምነቱን ለማክበርና ለመተግበር የሚወሰዱ እርምጃዎችን በአስቸኳይ በመጠባበቅ ላይ ነን ብላለች።
- ኬንያ ፤ ናይሮቢ የሚገኙት የጠ/ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪና የኢትዮጵያ መንግስት ተደራዳሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በአሁን ሰዓት ሰባ በመቶ (70%) ትግራይ በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝ ገልፀዋል። እስካሁን በሀገር መከላከያ ባልተያዙ ቦታዎች ሳይቀር እርዳታ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየገባ ነው ብለዋል።
ምግብ የጫኑ 35 ተሽከርካሪዎችና መድሃኒት የጫኑ 3 ተሽከርካሪዎች ሽረ ከተማ መግባታቸውን የገለፁት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ " በረራዎች ተፈቅደዋል፣ አገልግሎቶች እንደገና እየተገናኙ ነው ። " ብለዋል።
የሰላም ስምምነቱ አገልግሎቶችን ለማሻሻል እድሎችን ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል። እርዳታን በተመለከተ ምንም አይነት እንቅፋት የለም ሲሉ አክለዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ፤ " አንዳንድ ጥግ ላይ ያሉ አካላት የአፍሪካውያን እውቀት በፕሪቶሪያ ባመጣው ስኬት #ደስተኛ_አይመስሉም ፤ መንፈሱንም ለማበላሸት እየተሯሯጡ ነው " ብለዋል።

👍1.17K🕊161👎72🙏38❤29😱21😢10
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" ዛሬ ወሬ የለም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ
የሃይማኖት አባቶች ልዑክ በመቐለ !
ከአዲስ አበባ ተነስቶ በጥዋቱ ትግራይ ክልል መቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የደረሰው የሃይማኖት አባቶች ልዑክ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት የተወጣጣ ሲሆን አጠቃላይ ልዑኩ ከ20 በላይ አባላት አሉት።
የሰላም ልኡኩ ከአውሮፕላን ማረፍያ በቀጥታ ወደ መቐለ ፕላኔት ሆቴል አዳራሽ በማመራት በፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከሚመራው የጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ጋር #በዝግ ተወያይቷል።
ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጄነራል) ከሰላም ልኡካኑ ጋር የነበራቸውን ቆይታ አጠቃልለው ሲወጡ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የሚገኙባቸው የጋዜጠኞች ቡድን መረጃ ፍለጋ ተጠግተው ነበር።
ፕሬዝዳንቱ በሳቅ ታጅበው " ዛሬ ወሬ የለም " በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የሰላም ልኡኩ በሆቴሉ ጥቂት ደቂቃዎች እረፍት ወስዶ መልሶ በተመሳሳይ አዳራሽ ከትግራይ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።
በዚሁ ወቅት በቦታው ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ውይይቱን ለመከታተል ጥያቄ ቢያቀርቡም መከታተል ይቅርና አዳራሹ ውስጥ እንዳይዘልቁና ፎቶም እንዳያነሱ ተከልክለዋል።
ከሰዓት በኃላ ከውይይቱ ተሳታፊዎች በተገኘው መረጃ የሰላም ልኡካኑ በመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች ጎብኝተው የማወያየት ፕሮግራም የነበራቸው ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ይሄ ፕሮግራም ሳይካሄድ ቀርቷል።
የሰላም ልኡኩ ቀጥሎ ከህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ነው የተወያየው። ውይይቱ እንደ ጠዋቱ #በዝግ መካሄዱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።
የድርጅቱ / የህወሓት ልሳን የሆነው የወይን ጋዜጣ ጋዜጠኞችም ጭምር ወደ ስብሰባው አዳራሽ እንዳይገቡ ተከልክለው ነው ውይይቱ የተካሄደው።
ከአዲስ አበባ የተጓዘው የሰላም ልኡክ ያካሄዳቸው የውይይቱ ርእሰ ጉዳዮች አልታወቁም። ከግምት ባሻገር የተሰጠ ይፋዊ መረጃ የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ የሰላም ልኡኩ ቀኑን ሙሉ ከተለያዩ አካላት ጋር ያካሄደውን ውይይት በማስመልከት የሚሰጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ይኖር እንደሆነ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ የሚድያ ዴስክ ጠይቆ ያገኘው አመርቂ መልስ የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን

❤875🕊179🤔51😡31😢22🙏17👏14🥰9😭6