TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የበረራ አስተናጋጇ አያንቱ🔝

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን #መከስከስ ሕይወቷን ያጣችው የ24 ዓመቷ የበረራ አስተናጋጅ #አያንቱ_ግርማ አባት አቶ #ግርማ_ሌሊሳ ልጃቸው በአየር መንገዱ መሥራት ከጀመረች ሁለት ዓመታት ማስቆጠሯን ገልጸው፣ አስከሬን አይተው ካልቀበሩ በስተቀረ ማመን እንዳልቻሉ ይናገራሉ፡፡ አደጋው መከሰቱን በሚዲያ የሰሙ ሰዎች በስልክ እንደነገሯቸው የገለጹት አቶ ግርማ፣ ልጃቸው በግንቦት ወር 25ኛ ዓመቷን ትይዝ ነበር ሲሉም #በሀዘን ተናግረዋል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፥ ዛሬ በባሕር ዳር ስታዲየም በነበረ የዒድ ሶላት ስነስርዓት ወቅት ፥ ከቀናት በፊት በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የተፈፀመውን ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

ህዝበ ሙስሊሙ ጉዳዩን እጅግ በሰከነ መንገድ ፣ በአስተውሎት ተመልክቶ ችግሩ እንዳይባባስ ላደረገው ጥረት ምስጋና አቅርቧል።

ግድያው የዒድ አልፈጥር በዓል በሀዘን ስሜት እንዲከበር እንዳደረገውም ገልጿል።

የከተማ አስተዳደሩ  ፤ በአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ የተፈፀመውን ግድያ " አረመኔያዊ ነው " ያለ ሲሆን " ግድያው በዓሉን #በሀዘን ውስጥ ሆነን እንድናከብረው አስገድዶናል " ብሏል።

ግድያውን " የሽብር ድርጊት ነው " ሲልም ጠርቶ " ሁሉም ሰው በአንድ ቃል ማወገዝ አለበት " ሲል ገልጿል።

ህዝበ ሙስሊሙ ከሌላው ወገኖቹ ጋር ግጭት ውስጥ እንዲገባ ፣ አካባቢውን ፣ ከተማውን እንዲሁም ክልሉን የእልቂትና ውድመት ማዕከል ለማድረግ የታሰበ ግድያ ነው ሲልም አስረድቷል።

የሙስሊም ማህበረሰብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ በመመልከት የግድያው ፈጻሚዎች በህግ አግባብ ብቻ እንዲዳኙ እንጂ " እሾህን በእሾህ መንቀል " ተገቢ አይደለም በማለት ላደረገው አስተዋጽኦ ፣ መረጋጋትና ስክነት የከተማው አስተዳደር ምስጋና አቅርቧል።

ከቀናት በፊት በባህር ዳር ቀበሌ 14 የመግሪብ ሰላት ሰግደው ሲመለሱ የነበሩ አባት ከ3 ልጆቹ እንዲሁም 1 ጎረቤታቸውን ጨምሮ አጠቃላይ 5 ሰዎች በጥይት ተመተው መገደላቸው ይታወሳል።

እስካሁን ከግድያው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋለ አካል ስለመኖሩ በይፋ የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
😢451😡140130😱56🕊55😭44🙏34🤔23🥰6👏3