TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የርብ ግድብ ተመረቀ‼️

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ በዛሬው ዕለት ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ጋር በመሆን የርብ ግድብ #መርቀው ከፍተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጎንደር ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ተመረቀ። ፀሐይ ሁለገብ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን በጎንደር ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባውን ዘመናዊ የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ አስመርቋል። ፋብሪካውን ዛሬ #መርቀው የከፈቱት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ መላኩ አለበልና የፌደራል ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ #ኡስማን_ሱሩር ናቸው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ👆

"ዛሬ በወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት በበጎ አድራጎት ዘርፉ አማካኝንት በወልቂጤና በጉብርየ አካባቢ የሚገኙ አረጋዊያንና ወላጅ አልባ ህፃናትን በመሰብሰብ በአሉን በጋራ አክብሮአል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የግቢያችን የአስ/ል/ኮ/ም/ፕሬዝዳንት ወ/ሮ #ገነት_ወልዴ እና የም/ማ/አ/(የምርመርና ማህበረሰብ አገልግሎት) ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ሲሳይ_ሸዋአማረ የተገኙ ሲሆን ባስተላለፉትም መልዕክት መስዋትነት ከፈለው ሀገራችንን እስከ ክብሯ ላቆዩልን አባቶችና አናቶች ክብርና ፍቅር ልንሰጣቸው ይገባል ያሉ ሲሆን ለእናት ሀገራቸው ሰላም ተግተው እንዲፀልዩ ጠይቀዋል። በፕሮግራሙም ተማሪዎች የአረጋዊያኑን #እግር_ያጠቡ ሲሆን አባቶችም ተማሪዎችን እና በፕሮራሙ ላይ የተገኙትን እንግዶች #መርቀው ለሀገራችን #ሰላም ፀሎት አድረገዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የእስልምና እምነት ተከታይ እናትና አባቶች ለተማሪዎቹ የመቻቻል ባህላችንን በተግባር ያሳዩ ሲሆን እንሱም የታላቁ የረመዳን ወር ፆም መቃረቡን አስታውሰው ሁላችንም እንደየእምነታችን ለሀገራችን ሰላም በጋራ ዱአ (ፀሎት) እንድናደርግ ጠይቀዋል፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia