TIKVAH-ETHIOPIA
" አሁንም በርካታ ሰዎች ፍል ውሃው ከሚገኝበት ስፍራ ወደ ሆስፒታሉ ታመው እየገቡ ነው " - የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በጃዊ ወረዳ " ብሄራዊ " ተብሎ በሚጠራ ፍል ውሃ በተከሰተ በሽታ የሰው ህይወት ማለፉ ተገለጸ። በአማራ ክልል፤ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ ባለፈው ሰኞ መጋቢት 22/2017 " ብሄራዊ " ተብሎ በሚጠራ ፍል ውሃ ፀበል ተከስቷል በተባለ በሽታ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን…
#Update
" ኮሌራ መሆኑን በናሙና ተረጋግጧል " - የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አፈፃፀም ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከመጋቢት 19 / 2017 ዓ.ም ወዲህ በክልሉ በሶስት የፀበል ቦታዎች በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ አራት ሰዎች መሞታቸውንና ከ600 በላይ ሰዎች መያዛቸውን ገልፀዋል።
ሟቾቹ ሁለቱ ከጃዊ ሁለቱ ከአንዳሳ ፀበል መጥተው በባህር ዳር ከተማ ህክምና እየተደረገላቸው እያለ መሞታቸውን ተናግረዋል። ይህ የሆነው በአንድ ሳምንት ውስጥ መሆኑ የበሽታውን ስርጭት አስፈሪ ያደርገዋል ብለዋል።
በሽታው የተከሰተባቸው ቦታዎች ፦
- በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በሚገኘው " በርሜን ጊዮርጊስ "
- በሰሜን ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ "አንዳሳ" ፀበል
- በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ "ብሄራዊ " ተብሎ በሚጠራው ፍል ውሃ ፀበል እንደሆነ ሲስተር ሰፊ ተናግረዋል።
የበሽታው ስርጭት በዚህ ሳምንት ውስጥ እንዲስፋፋ ያደረገውን ምክንያት ሲገልፁ " ህብረተሰቡ በስፋት ወደ ፀበል ስፍራዎች በመጓዙ ነው " ብለዋል።
በእነዚህ የፀበል ስፍራዎች ደግሞ በቂ የሆነ የንፁህ ውሃ አቅርቦትና በቂ የሆነ መፀዳጃ ስፍራ አለመኖሩ የበሽታው ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ አድርሶታል ሲሉ ነው የገለጹት።
በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ " ብሄራዊ " ተብሎ በሚጠራ ፍል ውሃ ፀበል ባለፈው ሰኞ መጋቢት 22/2017 ዓ.ም በተከሰተ በሽታ ሁለት ሰዎች መሞታቸውንና 50 ሰዎች ታመው ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ስለሺ ወለሊ ለቲክቫህ መናገራቸው ይታወሳል።
በወቅቱም የበሽታውን ምንነት ለማወቅ ለክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ናሙና መላኩን አቶ ስለሽ ተናግረው ነበር።
ሲስተር ሰፊ ደርብ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከጃዊ ሆስፒታል የተላከው ናሙና #ኮሌራ መሆኑን #መረጋገጡን ተናግረዋል።
ባለፍት አራት ወራት ውስጥ ማለትም ታህሳስ 24፤ 2017 ዓ.ም በቋራ ወረዳ በርሚል ጊዮርጊስ ከተከስተው የኮሌራ ወረርሽኝ ጀምሮ እስከ ትላንት መጋቢት 25፤ 2017 ዓ.ም ድረስ በወረርሽኙ 11 ሰዎች ሲሞቱ ከ1ሺ 1መቶ 42 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸውን ሲስተር ሰፊ አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ዛሬ በፊስ ቡክ ገፁ ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሌራ በሽታ እንዲጠብቅ የሚያሳብብ ፁሁፍ አሰራጭቷል።
በቢሮው የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት የመጀ/ደረጃ ጤና ክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድሜነህ ልየው እንዳሉት በክልሉ ከሚገኙ 20 ዞኖች ውስጥ 45 ወረዳዎች የኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን ጠቁመዋል።
የ2ኛው ኮሌራ ወረርሽኝ ከተከሰተ ከሚያዚያ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 5ሺ 4መቶ 36 ህሙማን በበሽታው እንደተያዙ እና ከእነዚህ ውስጥ 75 ሰዎችን ለሞት መዳረጉን አክለዋል፡፡
በሽታው በስፋት በተከሰተባቸው የጸበል ቦታዎች የጤና ባለሙያዎች በጊዜያዊነት በመመደብ የህሙማን ልየታ፣ የህክምና አገልግሎት፣ እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል።
ጊዜያዊ የኮሌራ ህክምና ማዕከል ቦታዎችን በቋራ ሆስፒታልና በበርሚል ቅዱስ ጊዮርጊስ ፀበል ቦታ በማዘጋጀት ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ሲሉ አክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባሕር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBahirDar
@tikvahethiopia

😭289❤88🤔50🙏44😢23💔11🥰10🕊10👏5😡2