#AddisAbaba
በአዲስ አበባ 1,735 የንግድ ቤቶች ለጨረታ ቀረቡ።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ክ/ከተሞች ተገንብተው በተጠናቀዉ የ40/60 የጋራ ህንጻዎች ላይ የሚገኙ 1,735 የንግድ ቤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።
ኮርፖሬሽኑ ለጨረታ ያቀረባቸውን የ40/60 ንግድ ቤቶች ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 21 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ) ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሽት 11:30 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1000.00 / አንድ ሺህ በመክፈል መግዛት ይችላል ተብሏል።
የጨረታ ሰነድ የሚሸጥባቸው ስፍራዎች የት ናቸው ?
- ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (ባምቢስ አካባቢ)
- የካ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (መገናኛ)
- አራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (አራት ኪሎ)
- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት (ቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት)
- አ/አ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅ/ጽ/ቤት (40/60 በሻሌ ሳይት ብሎክ 13)
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

🤔168❤118😭33🙏25😱24😡19👏17🕊14🥰12💔10😢6
#አቢሲንያ_ባንክ
የሁሉም ምርጫ !
ሸሪዓውን መሠረት አድርገውና ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል አካተው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተመሰከረለት የአይማል ኮር ባንኪንግ ሲስተም እየታገዙ ዳጐስ ያሉ ጥቅሞችን ለአስቀማጮች የሚያስገኙትን፤ የሴቶች (ዘህራህ)፣ የወጣቶች (ፊትያህ)፣ የባለውለታዎች (ሙስኒን)፣ የሃጅ እና ዑምራ፣ የዕድር (ጀሚአህ)፣ የዕቁብ (ሱንዱቅ) እና የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ሙዷረባህ ትርፍ አጋሪ ሂሳቦችን በመክፈት፤ ከባንካችን ጋር ኢንቨስት አድርገው በተሻለ ትርፍና በከፍተኛ ጥቅም የወደፊት ህልምዎን እውን ያድርጉ!
አቢሲንያ አሚን
ዕሴትዎን ያከበረ!
#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia #አቢሲኒያአሚን #Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

🥰43❤19😭16🙏4🤔2
#AddisAbaba
ከለሊት 10:00 ጀምሮ በአዲስ አበባ መንገዶች ይዘጋሉ።
116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓል ነገ እሁድ ሚያዚያ 26/2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶች ይከበራል።
በዚህም ምክንያት መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
➡️ ከ22 አደባባይ ወደ ወደ ቅዱስ ዑራኤል -መስቀል አደባባይ (22 አደባባይ በተመሣሣይ ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ ላይ)
➡️ ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ)
➡️ ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
➡️ ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት
➡️ ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ ጋዜቦ አደባባይ (መስቀል ፍላዎር አደባባይ ላይ)
➡️ ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኤግዚብሽን ውስጥ ለውስጥ ወደ ፊላሚንጎ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ)
➡️ ከቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ወደ ለገሃር መብራት ( ቅዱስ ቂርቆስ ወደ ጋዜቦ ላይ)
➡️ ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ
➡️ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር መብራት (ሜክሲኮ አደባባይ ላይ)
➡️ ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ)
➡️ ከጥይት ቤት ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ጥይት ቤት መታጠፊያ ላይ )
➡️ ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ ላይ) ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።
በተጨማሪም፦
- ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም
- ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ጀምሮ ዝግ ተደርጓል።
#AddisAbabaPolice

1😡1.07K❤325👏88😭65🕊48🙏45🤔44😢27💔22🥰15😱13
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ ሚያዚያ 27 ቀን የአርበኞች (የድል) ቀን በዓል ነው። በዓሉ በሀገርአቀፍ ደረጃ ተከብረው ከሚውሉ ብሔራዊ በዓላት አንዱ ሲሆን የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ሆኖነው ይውላሉ። @tikvahethiopia
#AddisAbaba
ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል።
ነገ ሚያዚያ 27/2017 ዓ/ም የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ይከበራል።
በዚህም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ አሳውቋል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ተብሏል።

❤703👏121😡101🙏68🤔28🕊21😢16😭16🥰14
#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጎሮ ገብርኤል በተለምዶ " ጉሊት " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ ሱቆች መውደማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
አደጋው የተከተሰው ከጠዋቱ 4 ሰዓት ገደማ እንደሆነ ምክንያቱን ገና እንዳላወቁት፣ በሰዎች ላይ ጉዳት ባይደርስም በርካታ ሱቆች መውደማቸውን ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በመደዳው የተደረደሩ ሱቆችም በእሳት ቃጠሎው ነደዋል።
የከተማዋ እሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ሠራተኞችና ተሽከርካሪዎች በቦታው እንደተገኙ፣ የእሳት ቃጠሎው በቁጥጥር ስር እንደዋለም በቦታው ያሉ የዓይን እማኞች ነግረውናል።
አንድ ቃላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የሠፈሩ ነዋሪ፣ " በአደጋው ሱቆቹ ሙሉ ለሙሉ አመድ ሆነዋል " ሲሉ አስረድተዋል።
እኚሁ አካል ከቦታው ያጋሩን ቪዲዮና ፎቶ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በተባለው ቦታ ቃጠሎ መከሰቱን የሚያሳይ ሲሆን፣ ሁሉም ከላይ ተያይዟል።
በአደጋው ዙሪያ የእሳትና አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽንን ለማነጋገር ጥረት እያደርግን እንገኛለን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

😭253❤56🤔40🙏22😢16🕊14🥰4😱4👏3😡3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
በጉርሻ 1.6 ሚሊዮን ብዙ ነው? ግን እውነት ነው! ክፍያዎችን በአቢሲንያ ባንክ በመቀበል ብቻ ቢዝነስ የሚደጉም ጉርሻ!!
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ

❤37🤔2😱2
#AddisAbaba
" አሰራሩ ብክነትን ከመከላከል በተጨማሪ አላግባብ የፓርኪንግ ክፍያ የሚጠይቁ ግለሰቦችን ያስቀራል " - ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ከጥር 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ አውቶማቲክ ኢንፎርስመንት እና ፓርኪንግ ማኔጅመንት ሲስተም የተሰኘ አሰራር አበልጽጎ ወደ ስራ አስገብቷል።
የዚህ መተግበሪያ ተግባራዊ መሆን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በየአመቱ ለደረሰኝ ህትመት ያወጣው የነበረውን ከ17 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚያስቀር ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረልኝ ታረቀኝ " የቁጥጥር ስራው በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ በሚል " አሰራሩ ተግባራዊ መደረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አብራርተዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዝርዝር በሰጡን ሃሳብ ምን አሉ ?
" ከዚህ ቀደም ማንዋል የነበረ አሰራር ነበር የነበረው ደረሰኞችን በመስጠት የቅጣት አይነቱ ምንድነው የሚለውን በመጻፍ የሚደረግ ሂደት ነበር።
የአሁኑ አሰራር ግን የደንብ ተላላፊዎችን እንግልት በእጅጉ የሚቀንስ ሆኗል ምክንያቱም የቅጣት አይነቱ ተፈጻሚ የሚሆነው መንጃ ፈቃዳቸውን በመቀበል መረጃቸውን ስካን ተደረጎ በኤስ ኤም ኤስ (SMS) ቴክስት ነው።
ክፍያውን በስልኩ በሚገኙ የመክፈያ አማራጮች ያከናውናል መንጃ ፈቃድ መስጠትም ሆነ ሰሌዳ ማስፈታት አይጠበቅባቸውም።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያወጣው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 አለ እሱ ላይ የተጠቀሱ ህጎችን በሙሉ ወደ ሲስተሙ በመጫን ተግባራዊ እየሆነ ነው።
አንድ ተላላፊ ምን አይነት ጥፋት ነው ያጠፋው ፣በዛሬው ዕለት ስንት ደንብ ተላላፊዎች ተመዝገቡ ፣የትኞቹን እርከን የጥፋት አይነቶች ነው የተላለፉት ፣ማን የሚባል ተቆጣጣሪ የት ቦታ ላይ ምን አይነት ቅጣት ወሰደ የሚለውን የተሟላ መረጃ ቀጥታ ማግኘት የሚቻልበትን አሰራር ነው የዘረጋነው።
አሁን የገጠመን ችግር ሙሉ በሙሉ ከመተግበር አኳያ ሁለት ነገሮች ይፈልጋል የመጀመሪያው የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የመዘገባቸውን 1,124,000 (አንድ ሚሊየን አንድ መቶ ሃያ አራት ሺህ) መንጃ ፈቃዶችን እና 772,000 የተሽከርካሪ መረጃዎችን ነው የወሰድነው።
እዚህ ምዝገባ ውስጥ ያሉ በሙሉ በአዲሱ የአገልግሎት ሲስተም እንዲገለገሉ ለማድረግ እድሉ አለ ነገር ግን የክልሎች መንጃ ፈቃድ እና ሰሌዳዎች በአግባቡ ተመዝግበው ወደ እኛ የመረጃ ቋት ባለመግባታቸው ምክንያት ማንዋሊ አገልግሎቱን ለመስጠት የምንገደድበት ጊዜ አለ።
ሁለተኛው በመረጃ ቋታችን የተመዘገቡትም ቢሆኑ አድራሻቸውን በትክክል ያለገለጹና መደበኛ ስልክ ቁጥሮችን ያስቀመጡ መረጃው ላይደርሳቸው የሚችልበት እድል ስለሚኖር እና ከ10 ቀን በላይ ቅጣታቸውን ያልከፈሉ አሽከርካሪዎች በደንቡ መሰረት የቅጣቱን 5 በመቶ ወለድ እየጨመረ የሚሄድ በመሆኑ እክል ይፈጠራል።
በእኛ በኩል በመረጃ ቋት ውስጥ የሌሉ አሽከርካሪዎች ለአንድ ጊዜ በማንዋል ከተቀጡ በኋላ ለሁለተኛው ምዝገባቸውን አከናውነው በሲስተሙ የሚስተናገዱ ይሆናል።
ጎን ለጎን በክልሎች የሚገኙ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችም አድራሻቸውን በትክክል የሚገልጽ መንጃ ፈቃድ መረጃቸው እንዲሰጠን ጥያቄ አቅርበናል በቅርቡ መረጃዎቹም ልናገኝ እንችላለን።
ይህ በሁሉም ክልሎች ያሉ መረጃዎች እስከሚመጣ ግን በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ የተመዘገቡ መንጃ ፈቃዶች እና የተሽከርካሪ መረጃዎች ላይ ተግባራዊ አድርገን እየሰራን ነው።
የፓርኪንግ አሰራራችንም ለብክነት የሚዳርግ ፣ ሰአታቸው በትክክል የማይገለጽ እና ማንዋሊ በደረሰኞች የሚሰሩበት ሁኔታዎች ያሉበት እንደሆነ ይታወቃል ይህንንም ለማስቀረት የፓርኪንግ ሲስተሙን በ13 ሳይቶች ላይ ተግባራዊ አድርገናል።
ተሽከርካሪው የገባበትንን ፣ የወጣበትን ሰዓት እና አጠቃላይ ክፍያው ባስመዘገበው ስልክ ቁጥር በSMS መልእክት እንዲደርሰው ይደረጋል።
አሰራሩ ብክነትን ከመከላከል በተጨማሪ አላግባብ የፓርኪንግ ክፍያ የሚጠይቁ ግለሰቦችን ያስቀራል።
አሁን በ13 ሳይቶች ቢጀመርም ሙሉ በሙሉ በከተማችን እያሰፋን ተግባራዊ እንዲሆን ይደረጋል " ብለዋል።

❤442😡108👏91🙏45🤔19😭18🥰15😢14💔14🕊9😱2
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ፖሊስ ልዩ ቦታው " ሶማሌ ተራ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ሰዒድ ጀማል እና ብርሀኑ ቢያድግልኝ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።
ግለሰቦቹን የያዘው የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ እንደሚያዘጋጁ ከህብረተሠቡ በደረሠው ጥቆማ ነው።
የፍርድ ቤት የመያዣና የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ባደረገው ብርበራ ተጠርጣሪዎቹን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር እንዳዋለቸው አመልክቷል።
ከተያዙት ሀሰተኛ ሰነዶች መካከል ፦
- የተለያዩ የነዋሪነት መታወቂያዎች፣
- ፓሰፖርቶች፣
- የትምህርት እና የህክምና ማስረጃዎች፣
- መንጃ ፈቃዶች ይገኙበታል።
ሰነዶቹን የሚያዘጋጁበት 1 ኮምፒውተር፣ 1ፕሪንተር እንዲሁም የተለያዩ የፕሪንተር ቀለማት መያዛቸውንም ፖሊስ ገልጿል።
ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተገቢውን ምርመራ የማስፋት ተግባር እያከናወነ እንደሆነ ገልጾ ሲጠናቀቅም በዐቃቤ ህግ በኩል ክስ እንደሚያስመሠርት አሳውቋል።

👏279❤93😭33😱15😡13🥰12🕊10🤔7🙏5😢1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤32🙏27🥰10👏7🕊3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
#የሁሉም_ምርጫ
ጠብሰቅ ያለ ጉርሻ!! ክፍያዎችን በአቢሲንያ ባንክ ለሚቀበሉ የንግድ ባለቤቶች በ3 ወራት እስከ 1.6 ሚሊዮን ብር!!
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#የሁሉም_ምርጫ
ጠብሰቅ ያለ ጉርሻ!! ክፍያዎችን በአቢሲንያ ባንክ ለሚቀበሉ የንግድ ባለቤቶች በ3 ወራት እስከ 1.6 ሚሊዮን ብር!!
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
❤177🙏13🕊12🥰11😢4
TIKVAH-ETHIOPIA
ዒድ ሙባረክ ! 1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ አርብ (በጁምዓ እለት) ተከብሮ ይውላል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆን ከልብ ይመኛል። #TikvahEthiopiaFamily❤️ @tikvahethiopia
#AddisAbaba
ከለሊቱ 10:00 ሠዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።
በነገው ዕለት የሚከበረው 1446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓልን ምክንያት በማድረግ የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ የሚዘጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት፡-
- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ
- ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ
- ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛ ላይ
- ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ላንድ ማርክ ሆስፒታል አካባቢ
- ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት ትራክ መብራቱ መስቀለኛ ላይ
- ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ከፍተኛ ፍ/ቤትአደባባይ አካባቢ
- ከኑር ህንፃ ወደ ባልቻ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ኑር ህንፃ መስቀለኛ ላይ
- ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ የሚወስደው መንገድ ጨፌ ሜዳ ትራፊክ መብራት አጠገብ
- ከበርበሬ በረንዳ ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ አካባቢ
- ከተ/ሃይማኖት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ጎማ ቁጠባ ተ/ሃይማኖት አደባባይ
- ከሰንጋ ተራ 40/60 ኮንደሚኒየም ወደ ሠንጋ ተራ መብራት ሰንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ አካባቢ
- ከጌጃ ሰፈር በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ አካባቢ
- ከተ/ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ተ/ሃይማኖት አደባባይ አካባቢ
- ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ድሮ EBC የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መታጠፊያ
- ከጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ኢምግሬሽን መስቀለኛ አካባቢ
- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ
- ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ፍልውሃ ንግድ ማተሚያ መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ
- ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ ፓርላማ መብራት ላይ
- ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ውጭ ጉዳይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መታጠፊያ አካባቢ
- ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ ላይ ከለሊቱ 10:00 ሠዓት ጀምሮ ይዘጋል።
በተመሳሳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዓለም ባንክ መስቀለኛ አካባቢ ከሚከበረው በዓል ጋር ተያይዞ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይደረጋሉ፡፡
በዚህም መሰረት፡-
° ከዩኒሳ አደባባይ ወደ በላይ አብ መኪና መገጣጠሚያ የሚወስደው መንገድ
° ከቱሉዲምቱ - ወደ ጨፌ ይርጋ አደባባይ እስከ ዓለም ባንክ መስቀለኛ የሚወስደው መንገድ
° ከፌሮ ድልድይ እስከ ዩኒሳ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ከሌሊቱ 10፡00 ሠዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል፡፡
ህብረተሰቡም ከፖሊስ የሚሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

❤1.97K😡190🕊53🥰49😭31🤔24💔23👏22🙏22😱14😢2
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba
እጅግ በርካታ ደጋፊዎች የሚጠብቁት የወላይታ ዲቻ እና ሲዳማ ቡና " የኢትዮጵያ ዋንጫ " ፍፃሜ ጨዋታ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በዝግ ያለ ደጋፊ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን " ደጋፊዎች የፍጻሜ ጨዋታውን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) እና በሌሎች ቻናሎች ስለሚተላለፍ በቀጥታ ይከታተሉ " ብሏል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ " በፌዴሬሽኑ ውሳኔ መሠረት ነው ጨዋታው በዝግ የሚደረገው " ሲሉ መናገራቸውን " AMN ዲጂታል ሚዲያ " ዘግቧል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ደግሞ ፥ " በጸጥታ ስጋት ምክንያት ከበላይ አካል በመጣ ድንገተኛ ትእዛዝ ያለ ደጋፊ እንዲከናወን ይደረጋል " ብለዋል።
" ጨዋታውን በዝግ እንዲደረግ መወሰን የፌደሬሽኑ ፍላጎት ባይሆንም ' የደህንነት ስጋት አለ ' ከተባለ መቀበል የግድ ነው " ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው " መረጃው ዘግይቶ ወደ ፌደሬሽኑ ቢላክም እንደደረሳቸውና ውይይት ከተደረገ በኋላ በአስቸኳይ ለተጋጣሚ ቡድን አመራሮችና ሃላፊዎች የማሳወቅ ስራ ተሰርቷል " ሲሉ ገልጸዋል።
ለዚህ ጨዋታ እጅግ በጣም በርካታ የሲዳማ ቡና እና ወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች ትናንት ቀን እንዲሁም ለሊቱን ተጉዘው አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዛሬም ጥዋት በበርካታ መኪናዎች ጉዞ ላይ የነበሩ ደጋፊች ነበሩ።
ደጋፊዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ ከዘገየ በኃላ ያውም ትላንት ከመሸ በኃላ በሰሙት ውሳኔ እጅግ ቅር እንደተሰኙ ገልጸዋል።
" ቀድሞ መናገር ይገባ ነበር ፤ እዚህ ከመጣን በኃላ ፣ ጉዞ ከተጀመረና ደጋፊው ብዙ ወጪ ካወጣ በኃላ ይህንን መናገር ትክክል አይደለም " ብለዋል
የፌዴሬሽኑ ድንገተኛ ውሳኔ በደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ማስነሳቱን የሁለቱም ክለብ ደጋፊ ማኅብራት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ፎቶ፦ ቲክቫህ ስፖርት (@tikvahethsport)

❤1.28K😡539😭100👏65💔56🕊28🤔16😢16🥰15🙏13😱8
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሰማ ይፍጠን። ክፍያዎችን በአቢሲንያ ባንክ በመቀበል ብቻ ብር ይታፈሳል!
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
❤115😡24👏22🙏10🤔8😱8
#AddisAbaba
የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ !
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ሚገኙ 1,227 የግል ትምህርት ቤቶች በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን እስከ 65 በመቶ ድረስ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ እንዲያደርጉ እንደተፈቀደለቸው ተሰምቷል።
የጭማሪውን ጣሪያ 65 በመቶ መጨመር እንዲችል የተፈቀደለት ግን አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ነው ተብሏል።
የከተማው ካቢኔ ባፀደቀው፣ " የግል ትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሠራር ሥርዓት ረቂቅ ደንብ ቁጥር 194/2017 " መሠረት በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ከ1,585 የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1,227 ያህሉ እስከ 65 በመቶ ብቻ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢዘዲን ሙስባህ ለሪፖርተር ጋዜጣ ተናግረዋል።
በ2018 ዓ.ም. ጭማሪ ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁ 1,227 ትምህርት ቤቶች አስቀድሞ የክፍያ ጭማሪ መነሻ ሐሳባችሁን አቅርቡ ሲባሉ " የዋጋ ግሽበት (Inflation) ጨምሯል " በሚል ያቀረቡት ጭማሪ አስደንጋጭ ነበር ብለዋል።
ከትምህርት ቤቶቹ ውስጥ 10 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እስከ 50 በመቶ የጭማሪ ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን፣ ቀሪ 90 በመቶ ያህሉ ከ75 እስከ 263 በመቶ ጭማሪ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።
ሆኖም ትምህርት ቤቶች ፣ ወላጆች፣ የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ቢሮ፣ የንግድ ቢሮ፣ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የፍትሕ ቢሮና የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በተሳተፉበት ጥናት፣ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችልና በሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚኖር የዋጋ ማሪ ጣሪያ ይፋ መደረጉን አስረድተዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የክፍያ ጭማሪ ጣሪያውን ሲያስቀምጥ አንዱ መሠረት ያደረገበት ነጥብ የትምህርት ቤቶች ጥራት እንደሆነ ጠቁመዋል።
በዚህም ት/ቤቶች ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ አራት ተብለው በመሥፈርት መለየታቸውን ገልጸዋል። ከእነዚህም ውስጥ ጥራቱ የተሻለ የሚባለው ደረጃ አራት ትምህርት ቤት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
" ደረጃ አራት የተሻለ ጥራት ያለው ትምህርት ቤት ነው፤ ጭማሪ ሲደረግም ከደረጃ ሁለት ጋር እኩል መሆን የለበትም፡፡ ስለዚህ ጭማሪውን በፐርሰንት (በመቶኛ) አለያይተነዋል " ብለዋል።
በዚህም ቅድመ መደበኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉት እስከ 45 በመቶ ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል። " 45 በመቶ ጨምሩ ማለት ሳይሆን ከዜሮ ጀምሮ 10 301 45 በመቶ ብቻ መጨመር ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በላይ ማለፍ አይችሉም " ብለዋል።
- አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ 40 በመቶ
- መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ 45 በመቶ፣
- ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ 55 በመቶ ዋጋ መጨመር ይችላሉ ተብሏል።
በጣሪያው መሠረት ፦
° 144 ትምህርት ቤቶች እስከ 40 በመቶ፣
° 591 ትምህርት ቤቶች እስከ 45 በመቶ
° 378 ትምህርት ቤቶች እስከ 50 በመቶ፣
° 47 ትምህርት ቤቶች እስከ 55 በመቶ፣
° 66 ትምህርቶች እስከ 60 በመቶ ሊጨምሩ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ የመጨረሻውን ጣሪያ ማለትም እስከ 65 በመቶ ክፍያ መጨመር እንደሚችል አቶ ኢዘዲን አመላከተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ 1,585 ትምህርት ቤቶች መካከል 358 ያህሉ በ2016 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የጨመሩ ስለሆኑ በቀጣዩ ዓመት እንደማይጨምሩ ገልጸዋል። እነዚህ ትምህርት ቤቶች ክፍያ መጨመር የሚችሉት በ2019 ዓ.ም. እንደሚሆንም አክለዋል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

❤1.09K😡1.05K😭69🙏58🤔32👏17😢15😱14🕊13💔12
#AddisAbaba #እንድታውቁት
ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ሴንተር ወይም በሜክሲኮ ማከፋፈያ ትራንስፎርመር ላይ አስቸኳይ የጥገና ሥራ እንደሚከናወን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።
በዚህም ምክንያት ፦
- በሜክሲኮ፣
- በአፍሪካ ህብረት፣
- በቄራ፣
- በገነት ሆቴል፣
- በደንበል፣
- በመስቀል ፍላወር፣
- በወሎ ስፈር፣
- በመስቀል አደባባይ በባምቢስ እና አካባቢው ኤሌክትሪክ ተቋርጦ እንደሚቆይ አሳውቋል።
የጥገና ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ነዋሪዎች ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
#EEP

❤782😭175😡86🙏73👏47😢17🕊15😱11🥰9🤔9
#AddisAbaba
" በዘንድሮ የግብር ማሳወቂያ እና መክፈያ ወቅት በገቢዎች ቢሮ 256 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል " - ገቢዎች ቢሮ
ከሐምሌ 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30/2018 ዓ/ም ድረስ የ2017 ዓ/ም የግብር ማሳወቂያ ወቅት ነው።
በዛሬው ዕለት የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋይ ደንበኞች ግብራቸውን ማሳወቅ የጀመሩ ሲሆን እስከ ሐምሌ 30/2017 ዓም ድረስ ግብር ግብራቸውን እያሳወቁ ይቆያሉ።
ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር ለየት ባለ መልኩ በየደረጃው ያሉ ግብር ከፋዮች በወጣላቸው መርሃ ግብር መሰረት ግብራቸውን እንዲከፍሉ እንደሚደረግ የቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አቶ ሰውነት " ከዚህ ቀደም የደረጃ 'ለ' ግብር ከፋዮች ከሃምሌ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ነበር የሚከፍሉት ዘንድሮ ይህ አሰራር ተቀይሮ ሃምሌን ለዝግጅት እንዲጠቀሙት እና ግብራቸውን ከ ነሐሴ 1 እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ እንዲከፍሉ ተወስኗል አከፋፈላቸውም በስም ቅደም ተከተል ይሆናል " ብለዋል።
ዳይሬክተሩ በስም ቅደም ተከተል እንዲከፍሉ መደረጉ ግብር ከፋዩ ላይ መጨናነቆች እንዳይኖሩ እና ለብልሹ አሰራሮች እንዳይዳረጉ ያግዛል ነው ያሉት።
አቶ ሰውነት አየለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር በሰጡት ሃሳብ ምን አሉ ?
" የደረጃ 'ለ' ግብር ከፋይ ደንበኞች በነሐሴ ወር የመጀመሪያው ሳምንት ላይ የስም ዝርዝራቸው ከ A-D ያሉ ግብር ከፋዮች የሚስተናገዱበት ፕሮግራም ወጥቷል፣ በዚህም መሰረት ግብር ከፋዩን በአራት ሳምንት በመከፋፈል አመታዊ ግብራቸውን እንዲያሳውቁ እና እንዲከፍሉ ይደረጋል።
የደረጃ 'ሀ' ግብር ከፋዮችን በሚመለከትም ከዚህ ቀደም ከሐምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30 የአመታዊ ግብራቸውን የመክፈያ እና የማሳወቂያ ጊዜያቸው ነበር።
እነዚህ ግብር ከፋዮችም ሐምሌ እና ነሃሴን ለዝግጅት ተጠቅመው መስከረም እና ጥቅምትን ግብራቸውን የሚከፍሉበት ፕሮግራም ወጥቷል።
ቢሮው በተለያዩ ጊዜያት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጋቸው ውይይቶች ወቅት የተነሱ የተለያዩ ችግሮች ነበሩ እነዚህን የተጠቀሱ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ በጥናት የተለዩ 24 አይነት አዳዲስ አሰራሮችን ዘርግተናል ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።
ለምሳሌ የኦዲት ጥራት ጋር ላይ ከአሰራር ጋር በተያያዘ ባሉ ክፍተቶች ምክንያት ሁለት ኦዲተሮች አንድ አይነት ፋይል ተመልክተው ውሳኔ ሲወስኑ ግን ሁለት አይነት ውሳኔ የሚወስኑበት አሰራር ነበር ይህንን ለማስቀረት የሚያስችል የአሰራር ስርአት ተዘርግቷል።
ከሂሳብ መዝገብ ጋር በተገናኘም የሂሳም መዝገብ መያዝ ያለባቸው ግብር ከፋዮች መዝገቡን ባለመያዛቸው በቁርጥ ግብር ሲስተናገዱ ነበር።
አፈጻጸም ላይ በነበረ ክፍተት ምክንያት በተለይም የደረጃ 'ሀ' እና 'ለ' ግብር ከፋዮች ያለ ሂሳብ መዝገብ ሲስተናገዱ የቆዩ ቢሆንም ከአሁኑ የ2017 ዓ/ም የግብር ማሳወቂያ ወቅት ጀምሮ ያለ ሂሳብ መዝገብ አይሰራም።
ሂሳብ መዝገብ ሳይዙ የሚመጡ ከሆነ ግን የሚወሰነው ውሳኔ አስተማሪ የሚሆን ይሆናል።
የግብር አሰባሰብ ስርአቱም ከእጅ ንክኪ በጸዳ መንገድ እንዲሆን በማሰብ የደረጃ 'ሐ' ግብር ከፋዮች በET-TAX በተሰኘ በተቋሙ በለማ መተግበሪያ እቤታቸው ተቀምጠው ግብራቸውን የሚያውቁበት እና የሚከፍሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
በSMS በሚደርሳቸው መረጃም በTelebirr እና CBE Birr ግብራቸውን መክፈል ይችላሉ።
የደረጃ 'ሀ' እና የደረጃ 'ለ' ግብር ከፋዮችም በተመሳሳይ E-TAX በተሰኘ መተግበሪያ እንዲከፍሉ እያደረግን ያለንበት ሁኔታ አለ ነገር ግን ሁሉም ወደዚህ አሰራር ስርአት ገና አልገቡም።
ከፍተኛ ግብር ከፋዮች 100 ፕርሰንት ወደዚህ አሰራር ስርአት ገብተዋል ቀሪዎቹ በየቅርንጫፉ እቅድ ተይዞ አብዛኛው ግብር ከፋይ ወደዚህ አሰራር እንዲገባ እየተሰራ ነው።
የኦዲት ጥራትን የሚያረጋግጥ የስራ ክፍል ተደራጅቷል ኦዲተሩ የወሰነው ውሳኔ ምን ያህል ጥራት አለው የሚለውን ያረጋግጣል ከፍተኛ ልዩነት ከተፈጠረም ግብር ከፋዩ እንዲከፈል ይደረጋል፣ ይህንን የወሰነው አካልም ተጠያቂ ይሆናል።
የግብር ከፋዩን ሂሳብ መዝግብ የሚያዘጋጁ ባለሞያዎች በሚመለከት ከዚህ ቀደም ከግብር ከፋዩ ጋር በመደራደር ከፍተኛ የሆነ ግብር የመሰወር ስራ የሚሰሩበት እና የተሳሳቱ ሰነዶችን የሚያቀርቡበት ሁኔታ ነበር።
በዚህ ጊዜ ግብር ከፋዩን ኦዲት አድርገን ገንዘቡን ብናስከፍልም የሂሳብ ባለሞያዎቹ ተጠያቂ የምናደርግበት አሰራር አልነበረም አሁን የሂሳብ ባለሞያዎቹም ተጠያቂ የሚሆኑበትን አሰራር ዘርግተናል።
ኦንላይን ግብይትንም ለመቆጣጠር እና ግብር እንዲከፍሉ ለማድረግ የሚቻልበት የአሰራር ስረዓት ለመዘርጋት እየተሰራ ነው።
ከማዕከል ሁሉንም ቅርንጫፎች ለመቆጣጠር የሚያስችል ካሜራ አስገጥመናል።
በዘንድሮ የግብር ማሳወቂያ እና መክፈያ ወቅት በገቢዎች ቢሮ 256 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

❤968😡476😭89😱44🤔22🙏22🕊20😢10👏8💔7🥰6
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2017 ዓ/ም የግብር ዘመን ግብር አወሳሰንና አሰባሰብ አሰራር ይፋ አድርጓል።
አዲሱ መመሪያ የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ፣ የመክፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታ ተፈጻሚ የማይደረግባቸው ግብር ከፋዮችን በሚመለከት።
እንዲሁም የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ፣ የመከፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታን ያልተወጡ ግብር ከፋዮችን በተመለከተ መደረግ ስላለበት ዝርዝር ሃሳብ የያዘ ደብዳቤ በቢሮው የታክስ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ወርቅነሽ ሰቦቃ ተፈርሞ ለሁሉም ለግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተልኳል።
ደብዳቤው "የተወሰኑ ግብር ከፋዬች በህጉ የተጣለባቸውን ግዴታ ለመወጣት የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ ባለው የተለየ ባህሪ ምክንያት መቸገራቸውን በተለያየ ጊዜ በመጥቀስ አቤቱታ ያቀረቡ" መሆኑን ገልጿል።
ይሁን እንጂ የግብር ሕጉ ለየትኛውም የንግድ ዘርፍ በተለየ መልኩ የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ የመከፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታን ቀሪ አለማድረጉንም አሳውቋል።
ይህንኑ ግዴታ አለመወጣትም አስተዳደራዊ ቅጣት የሚያስከትል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የተለየ ባህሪ ያላቸው የተወሰኑ የሥራ ዘርፎች የግብር ህጉን ድንጋጌዎች በአስከበረ አግባብ የገቢ አሰበሰቡን እና የአገልግሎት አሰጣቱን ፍታሀዊነት ማዕከል ያደረገ የአሰራር ሥርዓት ለ2017 የግብር ማሳወቂያ ጊዜ ሂሳብ መዝገብ የማቅረብ ግዴታን ተፈጻሚነት በቅጣት ብቻ በማለፍ ማዘግየት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበታል ብሏል።
ስለሆነም የደረጃ "ሀ" እና የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዬች የሂሳብ መዝገብና የሂሳብ መግለጫ መሰረት በማድረግ የማሳወቅ፣ የመከፈል እና ሰነዶችን የመያዝ ግዴታን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ግብር ከፋዬች በማይወጡበት ጊዜ ለደረጃ «ሐ» ግብር ከፋዬች የወጣውን ገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 የትርፍ ሕዳግ እና በግምት ግብር አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 138/2010 በቁርጥ የወጪ ሰንጠረዥ መጠቀም ዘርፉ ግዴታውን በገቢ ግብር ሕጉ መሰረት እንዳይወጣ ከተማውም ማግኘት የሚገባውን ገቢ እንዳይሰበስብ ምክንያት ስለሚሆን ይህንኑ ክፍተት ለመዝጋት በገቢ ግብር አዋጁ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 80 መሰረት ግብር በግምት በሚሰላበት ጊዜ፦
ከግብር ከፋዮች ግንዛቤ የተለየ ድጋፍ የሚፈልጉ እና ሥራቸውም ከመንግስት ጋር በተገባ ውል ብቻ የሚያከናውኑ በማህበር የተደራጁ :-
- የትምህርት ቤቶችና የምገባ ማዕከላት መጋቢ እናቶች
- በከተማ ጽዳትና ውበት ደረቅ ቆሻሻ እና ገጸ-ምድር ማስዋብ ላይ የተሰማሩ
- ከንግድ ቢሮ ትስስር የተፈጠረላቸው የሸገር ዳቦን የሚሸጡ ማህበራት
ከመንግስት ተቋማት ጋር ያላቸውን ውልና በበጀት ዓመቱ ከአሰራቸው የመንግስት ተቋም ዓመቱን ሙሉ የተከፈላቸውን ክፍያ የሚገልጽ መረጃ ሲያመጡ መረጃን መሰረት አድርጎ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ገቢው ተወስኖ እንዲሰበሰብ።
በተጨማሪም የሸገር ዳቦን የሚሸጡ በተጓዳኝ የሚከናውኑ የንግድ ስራዎች መኖራቸው በመስክ ምልከታ ተረጋግጦ በየዘርፉ የቀን ገቢ ግምት እንዲገመትላቸው ተደርጎ ግብሩ ተወስኖ እንዲሰበሰብ።
የንግድ ሥራ ፍቃድ ሳይኖራቸው በሞያ ፍቃድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ጠበቆች ፣የኢንሹራንስ ወኪሎች ፣ኢንሹራንስ ጉዳት ገማች ግለሰቦች በሚመለከት:-
➡️ ከግብር አመቱ አጠቃላይ እንደ ገቢ 35 በመቶ እንደ ወጪ 65 በመቶ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ።
➡️ የንግድ ሥራ ያልሆነ ገቢ ያላቸው የመኖሪያ ቤት አከራዮች ከግብር አመቱ አጠቃላይ ገቢ 35 በመቶ እንደ ወጪ 65 በመቶ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ።
➡️ በግል ኮድ 02 እና በንግድ ኮድ 03 ተሸከርካሪ የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ አጠቃላይ የኪራይ ገቢ ላይ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት በመረጃ የሚወሰን በመሆኑ ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ።
➡️ በህግ ደረሰኝ የመጠቀም ግዴታ ተፈጻሚ የማይደረግባቸው የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች /በቴክኖሎጂ ስምሪት የሚሰጣቸውን የሜትር ታከሲዎች ጨምሮ/ የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 ሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ተወስኖ ገቢው እንዲሰበሰብ መወሰኑን ይገልጻል።
(ተጨማሪውን ከተያያዘው ደብዳቤ ይመልከቱ)

1❤1.33K😡175🤔35🙏35🥰26😭24😢23🕊23😱18👏16
TIKVAH-ETHIOPIA
" ትምህርት ቤቶች ባቀረቡት የዋጋ ጭማሪ ፕሮፖዛል ላይከወላጆች ጋር መግባባት ላይ መድረስ ካልተቻለ ባለሥልጣኑ ውሳኔ የሚሰጥ ይሆናል " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ 1,227 የግል ትምህርት ቤቶች በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን እስከ 65 በመቶ ድረስ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ እንዲያደርጉ እንደተፈቀደለቸው መዘገቡ ይታወሳል። ጭማሪውን ተከትሎ የአዲስ…
#AddisAbaba
የትምህርት ቤት ክፍያ !
20 በመቶ ትምህርት ቤቶች በ2018 የትምህርት ዘመን አገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ላይ ከወላጆች ጋር አለመስማማታቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በቅርቡ ባጸደቀው የግል ትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርአት ደንብ ቁጥር 194/2017 መሰረት በ2018 የትምህርት ዘመን አገልግሎት ክፍያ ላይ ከ ተማሪ ወላጅና አሳዳጊዎች ጋር ካልተስማሙ መንግስታዊ ካልሆኑ የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት መካሄዱን የከተማው ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።
በውይይት መርሃ ግብሩ ፦
- የትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ፣
- የትምህርት እና ሥልጠና ባለሥልጣን ከፍተኛ አመራሮች
- የግል ትምህርት ቤቶች አሰሪዎች ማህበር ፣
- የግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች እና የተማሪ ወላጅ ኮሚቴ ተወካዮች እንደ ተሳተፉ ቢሮው በማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል።
ውይይቱ የተካሄደው በጭማሪው ላይ መስማማት ላይ ያልደረሱ ትምህርት ቤቶች ደንቡ በሚያስቀምጠው መሰረት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ውሳኔ ያሳለፈ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የጋራ አስተሳሰብ ለመያዝ እንዲቻል መሆኑን ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ "በደንቡ መሰረት 80 ፐርሰንት ያህል ትምህርት ቤቶች ከወላጆችና አሳዳጊዎች ጋር በመስማማት የአገልግሎት ክፍያ መጨመራቸው የሚበረታታ ተግባር ነው" ብለዋል።
እንደ ትምህርት ቢሮ ሃላፊው ገለጻ 20 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ከክፍያ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ከወላጆች እና አሳዳጊዎች መስማማት ላይ አለመድረሳቸውን አመላክቷል።
የትምህርትና ስልጠናና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢዘዲን ሙስባህ "በደንቡ ላይ በመግባባት ወደ ስራ መገባቱን በዚህም መሰረት በርካታ ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር በመስማማት መጨመራቸውን ፣ መመሪያውን መሰረት በማድረግም ባለስልጣኑ በተቀሩትና መስማማት ባልቻሉት ላይ ውሳኔ መስጠቱን" አሳውቀዋል ።
ባለሥልጣኑ ምን ውሳኔ እንዳሳለፈ በዝርዝር ባይገለጽም የወላጆችን የመክፈል አቅም እና የትምህርት ተቋማቱን የግብአት አቅርቦት ታሳቢ አድርጎ ተግባራዊ የሆነ መሆኑን ስለመናገራቸው ትምህርት ቢሮው አሳውቋል።
#AddisAbabaEducationBureau

❤397😭57😡40🕊10😢8🤔7😱3
#AddisAbaba
ሽንኩርት ፣ ድንችና ሌሎች የአትክልት ምርቶች #ከቫት ነጻ እንደሆኑ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አሳውቋል።
ቢሮው " ማህበረሰቡ ዕለት በዕለት የሚሸምታቸው ያልተዘጋጁ የአትክልት ምርቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ ተደርገዋል " ሲል ገልጿል።
ከሰሞኑን ለቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በወረደው ሰርኩላር ያልተዘጋጁ እንደ ሽንኩርት፣ ድንችና ሌሎች የአትክልት ምርቶች ከቫት ውጭ መደረጋቸውን አመላክቷል።
በሰርኩላሩ ላይ " የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ 1341/2016 አንቀፅ 10 እና አዋጅን ለማስፈፀም በወጣው ደንብ ቁጥር 570/2017 ዓ.ም መሰረት ያልተዘጋጁ እንደ ሽንኩርት፣ ድንችና ሌሎች አትክልቶች ያሉ ምርቶች ወደሀገር ውስጥ ሲገቡም ሆነ በሀገር ውስጥ ተመርተው ለግብይት ሲቀርቡ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መደረጋቸውን ተደንግጓል " በሚል ተቀምጧል።
በዚህም መሰረት ያልተዘጋጁ የአትክልት ምርቶች የሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች ብቻ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የተደረጉ መሆናቸው ታውቆ ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ተገቢው ክትትል በማድረግ እንዲፈፀም አዟል።
ይሁንና በአዋጁ ከታክስ ነፃ ከተደረጉ ውጪ የፍራፍሬ ምርቶች በሚያቀርቡ ግብር ከፋዮች የቫት አሰራሩ የሚቀጥል መሆኑን በመግለፅ ተገቢው ክትትል እንዲደረግ ቢሮው አሳስቧል፡፡

❤1.93K🙏224👏109🤔74😡54🕊24😱20😢18🥰17😭17
#AddisAbaba
በመዲናዋ የተመረጡ የመንግሥት ተቋማት እስከ እሁድ ግማሽ ቀን ድረስ አገልግሎት ሊሰጡ ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ላይ መደበኛ የሥራ ቀናት መራዘሙን የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው እንዳሳወቀው፥ አገልግሎት ፈላጊዎች በተመረጡ ተቋማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 እና እሁድ እስከ ቀኑ 6፡30 ድረስ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የገለጸው።
አገልግሎቱም ከማዕከል መስሪያ ቤቶች ጀምሮ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች ድረስ የሚዘልቅ መሆኑን አስታውቋል።
በተጠቀሱት ቀናት አገልግሎት የሚሰጡ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ተቋማት የትኞቹ ናቸው ?
- ንግድ ቢሮ፣
- ገቢዎች ቢሮ፣
- መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ፣
- መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ፣
- ግንባታ ፍቃድ ቁጥጥር ባለስልጣን፣
- ህብረት ስራ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ላይ በተጠቀሰው መሰረት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።
@TikvahethMagazine @tikvahethiopia

😡1.38K❤1.23K👏283😭124🤔43💔31🙏28🕊27😱23🥰14😢1